israel commited on
Commit
360cfa9
·
verified ·
1 Parent(s): 00564c0

Upload gez-native-description.csv

Browse files
Files changed (1) hide show
  1. geez/gez-native-description.csv +435 -0
geez/gez-native-description.csv ADDED
@@ -0,0 +1,435 @@
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
1
+ proverb,Description
2
+ ለለአሐዱ በከመ ምግባሩ።,ለእያንዳንዱ እንደሥራው፡፡
3
+ ለሰብእ ጸሩ ሰብአ ቤቱ፡፡,የሰው ጠላቱ፣ ቤተሰቡ
4
+ ለዘቦ ይሁብዎ፤ ወይዌስክዎ፤ ወለዘለ አልቦ አለሂ ቦ የህይድዎ፡፡,ላለው ይለጡታል፣ ይጨምሩለታልም፡፡ የሌለውን ግን ያለውንም እንኳን ይነጥቁታል፡፡
5
+ አኮ በሲበት አላ በአእምሮ,በሽበት አይደለም፤ በማስተዋል ነው እንጅ።
6
+ መጥወኒ እመጥወ,ስጠኝ እስጥህለሁ
7
+ ምዉት የሀውር ሀበ ምዉት,ሙት ወደ ሙት ይሄዳል
8
+ ወእመ ሖርከ ብሔረ ባዕድ ኩን ከማሆሙ,ሌላ አገር ብትሔድ፤ እንደነሱው ሁን
9
+ ዘበልዐ በአቅም የሀድር በሰላም,በልኩ የበላ ስላማዊ ዕንቅልፍ ይተኛል
10
+ ሀቡ ዘነጋሚ ለነጋሚ፤ ወዘእግዚአብሔር ለእግዜአብሔር,የቂሳርን ለቁሳር፤ የእግኢአብሔርን ለአግዚአብሔር ስጡ
11
+ ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለክ,ለለመነህ ሁሉ ስጥ
12
+ ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር,መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥ
13
+ ሃይማኖት እንተ አልባቲ ምግባረ ሠናይ ምውት ይእቲ,በጎ ሥራ ያልተሠራባት ፃይማኖት የሞተች ናት
14
+ ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ,በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተተኩልሽ
15
+ ለልላነ አጓለእመሕያውሰ አልቦ ዘይክል አግርሮታ,ምላስ ይተባል፤ ጥርስ ይወጋል
16
+ ለሰሚዕ እጹብ,ለሰሚው አስደናቂ
17
+ ለስሒት መኑ ይሴብዋ,ስህተትን ማን ያስተውላታል
18
+ ለእመ ረክብከ ሰብአ በፍኖት ኢትጻባሕ፤ ወለእመ ተጻብሐክ ኢታውስኦ,በመንገድ ካገኘኸው ጋራ አትጣላ እሱ ነገር ቢፈልግህም አትመልስለት
19
+ ለአመ ብከ ህብ ወለእመ አልብከ ኀሊ,ካለህ ስጥ ከሌለህ እዘን
20
+ ለእመ ብከ ጥበብ ጸሐፍ,ዕውቀት ካለህ ጻፍ
21
+ ለወሀቤ ዝናም ማየ ከልእዎም,ለዝናብ ጌታ ውሃ ነሱት
22
+ ለውሂብ ኢትጉጔእ ወውሂበከ ኢትናፍቅ,ለመስጠት አትቸኩል፤ ሰጥተህም አትጸጸት
23
+ ለዘመጽአ በለላም በዝ አባርኮ ወለዘመጽአ በኀኬት በዝ እዘተርኮ,በለላም የመጣውን በዚህ እባርከዋለሁ፤ በክፋት የመጣውን በዚህ እዘተርከዋለሁ
24
+ ዘመጽአ ኀቤየ ኢይሰድዶ፤ ወኢያወጽኦ አፍአ,ወደኔ የመጣውን ወደ ውጭ አላወጣውም
25
+ ዘቦ ይሁብዎ፤ ወይዌስክዎ፤ ወለዘለ አልቦ አለሂ ቦ የህይድዎ፡,ላለው ይለጡታል፣ ይጨምሩለታልም፡፡ የሌለውን ግን ያለውንም እንኳን ይነጥቁታል
26
+ ለዘኢይሰቲ ወይነ ምንት ውእቱ ሕይወቱ,ወይን የማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አሰው?
27
+ ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል,ለሚያምን ሁሉ ይቻላል
28
+ ለጠቢብሰ አሃቲ ቃል ትበቁእ,ላሰተዋይ ሰው አንድ ቃል ይበቃዋል
29
+ ልሳነ እጓለ እመህያው ሐጽ ወኩናት,የሰው አፍ እንደ ተሳለ ጦር ነው
30
+ ልደትሰ በኩሉ ልደት ጸውኡኒ በካልእ ዕለት,የልደት ድግስ በሁሉም ነው፤ ሌላ ቀን ጥሩኝ
31
+ ሎቱ ስብሐት,ምስጋና ለርሱ ይሁን
32
+ ሐለሙ ሕልመ ወአልቦ ዘረከቡ,ሕልም አለሙ፣ ያገኙት ነገር ግን የለም
33
+ ሐንካስ በአግረ ዕውር ሖረ! ዕውርኒ በዐይነ ሐነካስ ነጸረ ወበክልዔሆሙ ወይንየ ተመዝበረ,አንካሳ በዕውሩ አግር ሄደ፤ ዕውሩም በአንካሳው ዐይን አየ፤ በሁለቱም አታከልቴ ተመዘበረ
34
+ ሕሙማን ይፈቅድዎ ለዐቃቤ ሥራይ ወአኮ ጥዑያን,ባለመድኃኒቱን በሽተኞች ይፈልጉታል ጤነኞች አይሹትም፡
35
+ ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ,ያይን በሽታዋ፣ ጠላትን ማየቷ
36
+ ሕንጻ ወውሉድ ያዐብዩ ስመ,ግንብና (ሕንጻ) ልጅ፤ ስምን ያስጠራሉ
37
+ ሕያዋን ይስእሉ ለሙታን፤ ሙታን ይስአሉ ለሕያዋን,ያሉት ለሞቱት ይጸልያሉ፤ የሞቱት ያሉትን ያስባሉ፡፡
38
+ ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን,ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ
39
+ መምህራነ ኮኑ በበደወሉ፤ ፊደላተ በሆለቆ ኩሉ,ፊደል የቆጠሩ ሁሉ፤ በያካባቢው አስተማሪዎች ሆኑ
40
+ መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ,ፊት አይቶ የማያዳላ መምርና መካሪ
41
+ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ,የሕይወት መሠረትና የድኅነት መገ�� ማርያም ናት
42
+ መስዋዕቱ ለእግቢአቢሔር መንፈስ የዋህ,የእግዚአብሔር መስዋዕቱ ቅን መንፈስ ነው
43
+ መስገርትስ ተቀጥቀጠት ወንህነስ ድኅነ,ወጥመድ ተሠበረች፤ እኛ ግን አመለጥን
44
+ መኑ ከመ አምላከነ?,እንደ እግዚአብሕር ያላ ማን አለ?
45
+ መኑ ዘደመሮ ለብርሃን ምስለ ጽልመት?,ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
46
+ መኑ የአቁር እሳተ ውስተ ኅጽኑ?,እሳትን በጭኑ ማን ይሸከማል?
47
+ መንግሥት እንተ ትትናፈቅ በበይናቲሃ ኢተጸንእ,እርስ በርሷ የምትለያይ መንግሥት አትጸናም
48
+ መዐር ኢይጥዕሞ ለአድግ,ለአህያ ማር አይጥማትም
49
+ መዓተ ንጉሥ ከመ መልአክ ሞት,የንጉሥ ቁጣ፣፤ የመልአከ ሞት ያህል ያሰፈራል
50
+ መጋቢ እንበለ ሊሳይ፤ ጸባቲ እንበለ ማይ,ያለ ምግብ መጋቢ የለ ውሃ ዋናተኛ
51
+ መጠኑ ለረድእ በከመ ሊቁ፡፡,የተማሪ ደረጃው (ከብሩ) እንደ መምሩ ነው፡፡
52
+ መጥወኒ አመጥወከ፡፡,ስጠኝ አለጥህለሁ
53
+ ማኅቶቱ ለሥጋክ ዐይንክ ውእቱ,የሥጋህ መብራት ዐይንህ ነው።
54
+ ማዕረሩ ብዙኅ ወገባሩ ህዳጥ,መኸሩ ብዙ ሠራተኛው ጥቂት፡፡
55
+ ማይ ብዙኅ ኢይክል አጥፍአታ ለፊቅር፡፡,ብዙ ውሃ ፍቅርን አያጠፋትም
56
+ ምሉዕ በኩለሄ,በሁሉ የተሟላ
57
+ ምሕረተ እፈቅድ ወአኮ መስዋዕተ,ምሕረትን እወዳለሁ፤ መስዋዕትን አይደለም።
58
+ ምንት ብክ ዘኢነሳእከ እም ካልዕከ?,ከስው ያልወስድከው ምን አለህ?
59
+ ምንዳቤያትሰ ኢኮና ርሁቃተ እምኔከ፤ አላ ይነቅአ እምታህተ እገሪከ፡,ችግሮችህ ሩቆች አይደሉም፤ ከአንተው ከራስህ ይመነጫሉ አእንጅ።፡
60
+ ምክር ሠናይት ለኩሉ ዘይገብራ።,ለሚተገብራት፤ ምከር መልካም ናት
61
+ ሞቱ ሰኃጥኣ ጸዋግ,የኃጢአተኛ አሟሟት የከፋ ነው
62
+ ሞታ ለነፍስ ርቅ እም አግዚብሔር፡፡,የነፍስ ሞቷ፤ ከእግዚአብሔር መራቋ
63
+ ምውት የሐውር ኀበ ምውት፡,ሙት፣ ወደ ሙት ይሄዳል፡፡
64
+ ምኩራብ አነመት ፀምረ፤ ወቤተ ክርሰቲያን ተአጽፈቶ፡፡,ምኩራብ ግምጃ ፈተለች፤ ቤተክርስቲያን ለበሰችው፡፡
65
+ ሠናይ ለብእሲ መቅበርቱ ለእመ ኮነ በውስተ ርስቱ፡፡,የሰው መቃብሩ፣፤ በአገሩ ቢሆን መልካም ነው፡
66
+ ሠናይ ብእሲ ያወጽኣ ለሠናይት፣ እም ሠናይት መዝገበ ልቡ፡፡,በጎ ሰው ከበጎ ልቡ በጎ ነገርን ያወጣል፡
67
+ ሠናይ እገሪሆሙ ለአለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡,መልካም ዚና የሚነግሩ አብሣሪዎች፣ እግሮቻቸው ያማሩ ናቸው፡፡
68
+ ሣህል ወርትዕ ተራከባ፤ ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ።,ቅንነትና ይቅርታ ተገናኙ እውነትና ሰላም ተሰማሙ
69
+ ሥርዉ ለኩሉ እኩይ፣፤ አፍቅሮ ንዋይ፡,የክፉ ተግባር ሁሉ ሥሩ የገንዘብ ፍቅር ነው፡፡
70
+ ሥጋ ትሄይላ ለነፍስ፤ በከዊነ ማኅደር፡፡,ማደሪያ በመሆኗ፤ ሥጋ ነፍስን ትጨቁናታለች
71
+ ርቱዕ አበው ይዝግቡ ለውሉዶሙ፤ ወአኮ ውሉድ ለአዝማዲሆሙ,ወላጆች ለልጆች እንጅ፤ ልጆች ለወላጆች ሀብት ሊያከማቹ አይችሉም
72
+ ርኅቀተ ሀገር፤ ኢይከልኣ ለፍቅር፡፡,የሀገር ርቀት፣ ፍቅርን አያስቀራት
73
+ ሰላም ለላም ለሰራቄ ቅኔ ናሁዳ፤ ዳር ዳሩን ኮርኩሞ፣ መሀሉን ሳይጎዳ፡,ቀነጣጥቦ ለሚሰርቅ የቅኔ ሌባ ሰላም ይሁን
74
+ ሰብአ ቤቱ ይጻረሮ ለለብእ,ሰውን የገንዛ ቤተሰቡ ይቃወመዋል፡፡
75
+ ሰብአሰ ገጸ ይሬኢ፤ ወእግዚአብሔርሰ ልበ ይሬኢ፡፡,ሰው ፊትን እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፡፡
76
+ ሰብእ አልብየ,ለው የለኝም፡፡
77
+ ሰብእ ወጣኒ፤ እግዚአብሔር ፈጻሚ,ሰው ይጀምራል፣ እግዚአብሔር ይፈጽማል፡
78
+ ሰብእ ይሠምር በዘይጌይሶ ለሥጋሁ።,ሰው ሰሥጋው የሚጠቅመውን ይወዳል፡፡
79
+ ሰብእ ይቄድሶ ሰመካን፤ መካን ይቄድሶ ለሰብእ፡፡,ሰው ቦታን ያሰከብረዋል፤ ቦታም ሰውን ያሰከብረዋል፡፡
80
+ ሰብእ ይከብር በእንተ ልብሱ፡፡,ሰው በልብሉ ይከበራል፡፡
81
+ ሰንበት ተዐቢ እምኩሉ ዕለት፤ ወሰብእ ይከብር እም ዙሉ ፍጥረት፡፡,ሰንበት ከዕሰታት፣ ሰው ከፍጥረታት፣ ሁሉ ይ���ልጣሉ፡
82
+ ሰአሉ ወይትወህበክሙ፤ ኅሥሠ ወትረክቡ፤ ጐድኮጐዱ ወያርህዉ ለክሙ፡፡,ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ እንኳኩ ይከፈትላችቷል፡፡
83
+ ሰይፍ ዘክልዔ አፉሁ፡,ሁሰት አፍ፤ ያለው ሠይፍ፡፡
84
+ ሲሲታ ስነፍስ ቃሰ እግዚአብሔር፡፡,የነፍስ ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
85
+ ስማዕ ወልድየ ሕገ አቡከ,ልጄ ሆይ! ያባትህን ትእዛዝ ስማ፡
86
+ ስብሐት ለእግዚአብሔር!,እግዚአብሔር ይመስገን!
87
+ ስብዓ ይወድቅ ጻድቅ ወይትነሣአእ፡,ጻድቅ ሰባት ጌዜ ቢወድቅ ሰባት ጌዜ ይነሣል፡፡
88
+ ሰታይ ወአንስት ያስሕታሆሙ ለመምህራን፡፡,መጠጥና ሴቶች መምህራንን ያስቷቸዋል፡፡
89
+ ሶበ ተሐውር ምስስ ፅድውከ ኅበ መልአክ ተዐረቅ በፍኖት,ወደ ዳኛ በምትሄድበት ገዜ፣ በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ታረቅ
90
+ ሶበ ትረክቦ ኃጢአቱ ይጸልኣ፡,ጥፋቱን ሲያውቃት ይሰቀቃታል፡፡
91
+ ሶበ ኢያሥራሕክምዋ ሰእጐልትየ እም ኢረከብክምዋ ሰአምሳልየ፡፡,በጥጃዬ ባላረሳችሁ፤ የእንቁቅልሼን ፍች ባላወቃችሁ፡
92
+ ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ አግዚአብሔር,የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡
93
+ ቀዳሜ ሕይወቱ ሰሰብእ እክል ወማይ፣፤ ወይን ወሥርናይ,እህልና ውሃ ወይንና ስንዴ ለሰው ሕይወት፣ መሠረት ናቸው፡፡
94
+ ቀጥቅጥ መዝራዕቶ ሰኃጥእ ወሰእኩይ፡፡,ክፉና ተንኮለኛን ሰው ድቅቅ ስብርብር ማድረግ ነው፡፡
95
+ ቃለ መዋቲ ጽንዕት ይኣቲ፡፡,የሙት ቃል አይሻርም፡፡
96
+ ቅኑተ ይኩን ሃቁየክሙ ወኅትወ መኀትዊክሙ።፡,ትጥቃችሁ የጠበቀ መብራታችሁ የበራ ይሁን።
97
+ ቅድመ አውጽእ ሠርዌ እም ዐይንክ,በመጀመሪያ ባንተ ዐይን ያለውን ግንድ አውጣ፡፡
98
+ ቅድመ ይባኡ ውስተ ኅርየት ይምሃርዎሙ ቃለ ሃይማኖት፡,ከመሾማቸው በፊት የሃይማኖትን ቃል ያስተምሯቸው
99
+ በስሐቅ ወበስላቅ ይበውእ ጸላኤ ሠናያት፡፡,ክፉ መንፈስ በሳቅ በስላቅ ይገባል
100
+ በሳምናዊት ዘመን ትሴኮስ ፍቅር፡፡,በስምንተኛው ሽህ ፍቅር ትቀዘቅዛለች፡፡
101
+ በስምዐ ክልዔቱ ወሠለስቱ ይቀውም ኩሉ ነገር፡፡,ነገር ሁሉ በሁለትና በሦስት ምሥክሮች ይጸናል።፡
102
+ በቀዳሚ ጉየይ፤ ወበካልዕ ጉየይ፤ ወበሳልስ ተንሥእ ወተቃተል፡፡,በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሽሽ፣ በሶስተኛው ግን ተነስተህ ተፋለም
103
+ በብዙኅ ጻማ ሀሰወነ ንባእ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር፡፡,ወደ እግዚአብሔር መንግሥት፣ በብዙ ድካም እንገባለን
104
+ በትዕግስትክሙ ታጠርይዋ ለነፍስክሙ፡፡,በመታገሳችሁ ነፍሳችሁን ታድናላችሁ፡፡
105
+ በአርምሞ ይመስል ጠቢብ፡፡,ዝም በማለቱ ብልህ ይመስላል፡፡
106
+ በአይቴ ኀሊፈኪ ድጓ ተምሂረኪ?,በየት አልፈሽ ድጓ ተማርሽ?
107
+ በከንቱ ዘነሳእክሙ ሀቡ በከንቱ፡፡,ያለ ዋጋ የተቀበላችሁትን ያስ ዋጋ ስጡ፡
108
+ በዘሠፈርክሙ ሎሙ ይሠፍሩ ለክሙ፡፡,በሰጣችኋቸው ልክ ይስጧችኋል።
109
+ በዝ ግብርኪ፣ ተገደፍኪ፡፡,በዚህ ሥራሽ፤ ወጥተሽ ወደቅሽ፡፡
110
+ በጽባሕ ዘተናገረ ኢይደግም በሠርክ፡፡,ጧት የተናገረውን ማታ አያስታውሰውም፡
111
+ በሞተ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ፡፡,በርሱ ሞት እኛ ተፈወስን፡፡
112
+ ቢጽ ለቢጹ ይትራድዖ፡,ጓደኛ ጓደኛውን ይረዳዋል
113
+ ቢጽ ምስለ ቢጹ።,ጓደኛ ከጓደኛው፡፡
114
+ ባኡ እንተ ጸባብ አንቀጽ፡፡,በጠበበው በር ግቡ፡፡
115
+ ቤዛ ነፍሉ ለሰብእ ጥሪተ ብዕሉ,ሃብት ለሰው ቤዛው ነው
116
+ ብላዕ በሐፈ ገጽከ,ጥረህ ግረህ ብላ
117
+ ብእሲ ማእምር ኀዘን ለነፍሱ,አስተዋይ ሰው ያዝንበት እያጣም
118
+ ብአሲት አዛል (አዚዝ) አክሊል ለምታ,መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት
119
+ ብእሲ እኩይ የኃብል አእርክተ,ክፉ.ሰው በነገር ሥራ ወዳጆችን ይለያያል
120
+ ብእሲ ወብእሲት እሐዱ አካል እሙንቱ,ባልና ሚስት አንድ ከካል ናቸው
121
+ ብእሲ ጠዋይ ይልዕክ እከየ,ጠማማ ለው ክፋትን ከሁሉ ያደርሳል
122
+ ብዙኃን መኳንንት እለ ወድቁ ውስተ ምድር ወቦ ባሕታዊ ዘተቄጸለ አክሊለ,በዚህ ዓለም በመከራ የወደቁ ባለሥልጣኖች ብዙ ናቸው! ዘውድ የተቀዳጀ ባሕታዊም አለ
123
+ ብዙኃን አለ ወድቁ በሐጺን ወአኮ ከመ እለ ወድቁ በልሳን,በጦር ተደብድበው የወደቁ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን በነገረ ሠሪ አንደበት እንደጠፉት አይሆኑም
124
+ ብዙኃን ይመውኡ,ብዙዎች ያሸንፋሉ
125
+ ብዙኃን ጽዉኣን፤ ወኅዳጣን ኅሩያን,የተጠሩ ብዙዎች፤ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው።፡
126
+ ብየ ሥልጣን ላዕለ ኩሉ ዘኮነ ወአኮ ዙሉ ዘይበቁዓኒ,ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም
127
+ ብፁዓት መካናት ዘኢወለዳ,ያልወለዱ ብፁዓት ናቸው
128
+ ብፁዓን ገባርያነ ሰሳም,የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው
129
+ ብፁፅ ዘይሁብ አም ዘይነስእ,ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ በፁዕ ነው
130
+ ብፁዕ ዘይደበድባ ለከርሱ,ሰውነቱን የሚንከባከባት ብፁዕ ነው
131
+ ቦ እለ ተሐርዩ እምከርሠ እሞሙ፡,ከናታቸው ማህጸን ጀምሮ የተመረጡ አሉ
132
+ ቦ ጊዜ ለዙሉ,ለሁሉም ጊዜ አለው
133
+ ተልዒልየ ተትህትኩ፤ ወተመነንኩ፡,ተከብሬ ሳበቃ ተዋረድኩ
134
+ ተሰአሎ ለአቡከ ይነግረከ፤ ወለሊቃውንቲከ ይዜንዉከ,አባትህን ጠይቀው ይነግርሃል
135
+ ተበአስ በአንተ ጽድቅ እስክ ለሞት,ለአውነት እስከ ሞት ድረስ ተጋደል
136
+ ተንተንኩ ለወዲቅ፤ ወእግዚአብሔር አንሥአኒ,ልወድቅ ተንገዳገድኩ፤ እግዚአብሔር ግን አነሣኝ
137
+ ተአምሑ በበይናቲከሙ በአምሐ ቅድሳት,በተቀደሰ ስላምታ እጅ ተነሳሱ
138
+ ተዓቀብ አምጸላእትከ አሐደ ጊዜ ወተኣቀብ እም ፍቁርክ ፲፻ ጊዜያተ,ከጠላትህ አንድ ጊዜ፣ ከወዳጅህ ሽህ ጊዜ ተጠንቀቅ
139
+ ተዘከሩ መኳንንቲክሙ፣ ዘነገሩከሙ ቃለ እግዚአብሔር,የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን፤ አስተማሪዎቻችሁን አስታውሱ
140
+ ተገሃሥ እም እኩይ፤ ወግበር ሠናየ,ከክፋት ራቅ፤ መልካምንም አድርግ
141
+ ተፋቀሩ በበይናቲከሙ,እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ
142
+ ተፋቅሮሰ ፍጹም ሕግ,ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው
143
+ ትበልዒ ወኢትጸግቢ,ትበያለሽ ግን አትጠግቢም
144
+ ትንቢት ይቀድሞ ለነገር,ድርጊትን ትንቢት ይቀድመዋል
145
+ ትእቢትሰ ጸሩ ስሰክርስቶስ,ትቢተኛ የክርስቶሰ ጠሳት ነው
146
+ ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ,የደጋግ ሰዎች ልጆች ይባረካሉ
147
+ ኅላፊ ንብረት፣ ክመ ጽላሎት,ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው
148
+ ኀበ ሀሎ መዝገብክሙ ሀየ ይሄሉ ልብክሙ,ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛል
149
+ ኀበ ሀሎ ገደላ ሀየ ይትጋብኡ አንሰርት,ጥንብ ባስበት አሞሮች ይሰበሰባሉ
150
+ ሃዘን ለአብዳን፤ ወፍስሐ ለጠቢባን,ሀዘን ለሰነፎች፣ ደስታ ለብልሆች
151
+ ኀጺን ለነጺን ይትባልሁ,ብረት ብረትን ይስስዋል
152
+ ኃይሉ ስስብእ በአምጣነ ቆሙ,የስው ኃይሉ በቁመቱ ልክ
153
+ ኅዳጣን ይትጌበሩ፤ ወብዙኃን የዐርሩ,ጥቂቶች ይሠራሉ፤ ብዙዎች ይስበስባሉ
154
+ ኅድጉ አበሳ ቢጽክሙ,የወንድማችሁን በደል ተዉለት
155
+ ኅድጋ ለመዓት ወግድፋ ለቁጥዓ,ብስጭትን ተዋት፤ ቁጣንም ጣላት
156
+ ኅድግዎሙ ለሕጻናት ይምጽኡ ኀቤየ,ሕጻናትን ተዉአቸው ወደኔ ይምጡ
157
+ ኀድግዎሙጮ ለምጢዉታን፤ ይቅብሩ ምዉታኒሆሙ,ሙታንን ተዉአቸው፤ ሙታኖቻቸውን ይቅበሩ
158
+ ነባህነ ነባህነ ከመ ዘኢነባህነ ኮነ,ጮህን ጮህን አንዳልጮህን ሆን
159
+ ነገሥት ያፈቅሩ ጽልሕዋነ ወመደልዋነ,ገዥዎች ግብዞችንና ሸንጋዮችን ይወዳሉ።
160
+ ነገረ አማጽያን ኃየለነ,የነገረኞች ወሬ በጠበጠን
161
+ ነገረ ዘርቅ,ተራ ወሬ አሉባልታ
162
+ ነፍስ ርኅብት መሪርኒ ጥዑመ ያስተርእያ,የተራበች ነፍስ መራራው ሁሉ ጣፋጭ ይመሰላታል።
163
+ ነፍስየ ትጻእ ምስለ ኢሎፍላውያን፡,ከኢሎፍኣውያን ጋር ነፍሴ ትውጣ
164
+ ነፍስ ጽግብት ጸቃውዓ መዓር ትሜንን,የጠገበች ነፍስ የማር ወለሳ ትረግጣስች
165
+ ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይፄልዉ አኃው ኅቡረ,እነሆ ወንድሞች ተባብረው ሲኖሩ መልካም ነው
166
+ ንሕነ ነአምር ግብሮን ለቆራብት,የቆራቢዎችን ተግባር እ��� እናውቃለን
167
+ ንሥኣ ወብልዓ ለአእንታከቲ መጽሐፍ,አንካ ይችን መጽሐፍ ብላት
168
+ ንቃህ መዋቲ,የተኛህ ንቃ
169
+ ንባብ ይቀትል፤ ወትርጓሜ ያሐዩ፡,ንባብ ይገላል፤ ትርጓሜ ያድናል
170
+ ንነግርሂ ወኢንዘብጥ,እንናገራለን እንጅ እንማታም።
171
+ ንዋይ ከመ እግዜኡ,ገንዘብ እንደጌታው ነው
172
+ ንዋይከ በቅድሜከ፡፡,ገንዘብህን ከፊትህ አትለይ፡፡
173
+ ንግባአኬ ኀበ ጥንተ ነገር፡፡,ወደ ቀደመው ነገር አንመለሰ፡፡
174
+ አልቦ በቁዔት በከሲተ ኅሊናየ,የልቤን ብናገር ጥቅም የለውም፡፡
175
+ አልቦ ክዱን ዞኢይትከለት፤ ወአልቦ ኅቡእዕ ዘኢያስተርኢ,የማይገለጥ ሽሸግ የማይታይ ሥውር የለም፡፡
176
+ አልቦ ዘያበርህ ማኅቶተ ከመ ያንብራ ታህተ ከፈር፡፡,መብራት አብርቶ እንቅብ የሚደፋባት የለም፡፡
177
+ አልቦ ዘይእህዝ እርፈ ወየሐርስ ድኅሪተ፡፡,እርፍ ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም:
178
+ አልቦ ገብር ዘየዐቢ እም እግዚኡ፤ ወአልቦ ረድእ ዘየዐቢ እም ሊቁ፡,ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ፤ ከመምሩ የሚበልጥ ተማሪ የለም፡፡
179
+ አልቦ ገብር ዘይክል ተቀንዮ ለከልዔ አጋአእዝት፡፡,ለሁለት ጌቶች ሊገዛ የሚችል አገልጋይ የለም፡፡
180
+ አሐቲ ይእቲ ለእማ ።,ለእናቷ አንዲት ናት።
181
+ አሐደ ቀለመ ዘነገረከ ይኩን ከመ አቡከ፤ ክልዔተ ቀለመ ዘነገረከ ይኩን ከመ ፈጣሪከ፡፡,አንድ ቀለም የነገረህ እንደ አባትህ፣ ሁለት ቀለም የነገረህ እንደ ፈጣሪህ ይሁንልህ፡፡
182
+ አሐደ ይኩን ቃልክሙ፤ እመኒ እወ አወ ወእመኒ አልቦ አልቦ፡፡,ቃላችሁ አንድ ይሁን፤ አዎ ከሆነ አዎ አይደለም ከሆነም አይደለም በሉ፡፡
183
+ አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ፣ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ,እሳትና ውፃ አቀረብኩልህ፤ እጅህን ወደምትሻው ስደድ፡፡.
184
+ አቅድሙ ስንቀከሙ፡፡,ስንቃችሁን አስቀድሙ።
185
+ አበውኒ ኢታስተቆጥዑ ውሉደክሙ፡፡,አባቶች ልጆቻችሁን አታስቆጡ
186
+ አብዝኖ መጻሕፍት ያዘነግእ ልበ,መጻሕፍትን በብዛት ማንበብ ዝንጉነትን ያመጣል፡፡
187
+ አብድ ይነውም በጊዜ ማአኣረር፡,ሰነፍ በአዝመራ (በሥራ) ጊዜ ይተኛል፡፡
188
+ አነ አዐብዮ ሰአቡየ ዕዝን፣ ደኃራዊ ዘበቁልኩ ቀርን።,በኋላ የበቀልኩ ቀንድ አባቴን ጆሮን እበልጠዋለሁ፡፡
189
+ አነ ዘጳውሎሰ፣ ወአነ ዘአጵሎስ፣ ወአነ ዘኬፋ፡፡,ኦኔ የጳውሎስ፣ አኔ የአጵሎሰ፣ አኔ የኬፋ።
190
+ አንብብዋ ለመልእክት፤ አም ጥንታ እስከ ተፍጻሜታ፡፡,መልአክቲቱን ከመጀመሪያዋ እሰከ መጨረሻዋ አንብቧት፡፡
191
+ አንተ ኮኩህ!,አንተ መሠረት ነህ!
192
+ አንትሙስ ኅሱ እንተ አፍኣ ወእንተ ውሰጡስ የአምር አግዚአብሔር፡፡,እናንተ የላዩን መርምሩ፤ የውስጡን እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡
193
+ አንትሙ ተሐውሩ ግድመ ግድመ፤ አነኒ አሐውር ግድመ ግድመ፡፡፥,እናንተ ግራ ግራውን ትሄደሳችሁ፤ እኔም ግራ ግራውን እሄዳለሁ፡፡
194
+ አንፄዋ ለኅልፈታ አንፈ ፄሴሜት ታጹኑ።,አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች፡፡
195
+ አክብር አባክ ወአመክከ፡,አባትና እናትህን አክብር፡፡
196
+ አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ፡፡,በሮጠ አይደለም በቀደመ እንጅ፡፡
197
+ አኮ በሲበት አላ በአአምሮ።,በሽበት አይደለም፤ በማስተዋል እንጅ፡፡
198
+ አኩቴቶሙ ዕረፍቶሙ፤ ዕረፍቶሙ አኩቴቶሙ።፡,እረፍታችው ማመስገናቸው፤ ማመስገናቸው አረፍታቸው ነው፡፡
199
+ አድኅን ርእስከ፡፡,ራስህን አድን።፡
200
+ አጽንእ ዘብከ ከመ አልቦ ዘይነሥእ አክሊሰከ፡፡,ጸጋህን ማንም እንዳይወስድብህ፣ ያለህን አጥብቀህ ያዝ፡፡
201
+ አፉሁ ለጻድቅ ይትሜህር ጥበብ፡፡,የደግ ሰው አፍ ጥበብን ይማራል፡፡
202
+ አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስክ፡፡,ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡
203
+ አፍትን ርእሰከ ለካህን፡፡,ራስህን ለካህን አሳይ፡
204
+ አፍኒ ወልብኒ ኅቡረ ይእመኑ።,አፍም ልብም በአንድነት ይመኑ፡፡
205
+ አፍ ይጸውአ ለሞት፡፡,አፍ ሞትን ይጠራል፡፡
206
+ ኢተህቡ ፍኖተ ለሠይጣን፡,ለሠይጣን በር አትስጡት፡፡
207
+ ኢታልምድዎ ወኢትክልእዎ፡፡,አታስለምዱት፤ አትከልክሉት፡፡
208
+ ኢታትህት ርአስክ ለብእሲ አብድ,ለሰነፍ ለው ራስከን ዝቅ አታድርግ፡፡
209
+ ኢታንሥእ ዘኢያንበርከ፡፡,ያላስቀመጥከውን አታንሣ፡፡
210
+ ኢታንክር ዘንተ ዘይብእስ ሀሎ፡፡,የባስ አለና ይህን አታድንቅ፡
211
+ ኢታድልዉ ለገጸ ሰብአ፡፡,የሰው ፊት አይታችሁ አታዳሉ፡፡
212
+ ኢታፍቅሩ ወርቀ ወኢብሩረ፡፡,ብርና ወርቅን አትውደዱ፡፡
213
+ ኢትህሚ ሰብአ ውስተ ቤትከ፤ አስመ ዖፈ ሰማይ ያወጽኦ ለነገርከ፡፡,ቤትህ ውስጥ እንኳ ቢሆን ሰውን አትማ፤ ነገርህን የሰማይ ወፍ ያወጣብህልና፡፡
214
+ ኢትልበሱ ልብሰ ሐራ።,የማይገባችሁን ልብስ አትልበሱ።
215
+ ኢትማዖ ሰአኩይ በእኩይ፤ አላ በገቢረ ሠናይ፡፡,ክፉን በክፉ አታሸንፈው መልካም በመሥራት እንጅ፡፡
216
+ ኢትርአይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ፡፡,የኢያልያብን ግርማ ሞገስ አትይ፡፡
217
+ ኢትርፍቅ ውስተ ርእስ ምርፋቅ፡፡,ከላይኛው መቀመጫ አትቀመጥ።
218
+ ኢትስርቁ ትብል ወለሊከ ትሰርቅ፡፡,አትስረቁ ትላለህ፤ አንተ ግን ትዘርፋሰህ፡፡
219
+ ኢትስተይ ማይ እራቆ፤ አላ ቶስህ ወይን በአንተ ህማመ ከብድከ፡፡,ውሃ ብቻ አትጠጣ፤ ስለሆድህ ህመም ትንሽ ወይን ጨምር እንጅ
220
+ ኢትቁም አራቀክ ቅድመ ነቢየ አግዚአብሔር፤,በእግዚአብሔር ሰው ፊት ባዶ እጅህን አትቅረብ፡፡
221
+ ኢትቅናዕ ላዕለ አኩያን፡፡,በክፉዎች አትቅና፡፡
222
+ ኢትኅድግ ዐርከክ ዘትካት፤ እስመ ኢይከውነክ ከማሁ ዐርከ ግብት፡፡,ድንገተኛ ወዳጅ እንደሱ አይሆንልህምና የቀድሞ ወዳጅህን አትተው
223
+ ኢትንአዶ ሰለብእ ዘእንበሰ ትርዐይ ተፍጻሜቶ፡።፡,ሰውን መጨረሻውን ሳታይ አታመስግነው፡
224
+ ኢትኩኑ ከመ መደልዋን፡፡,እንደግብዞች አትሁኑ፡፡
225
+ ኢትኩን ጻድቀ ፈድፋደ፤ ወኢትጠበብ ፈድፋደ፡፡,እጅግ ጻድቅ እጅግም ጠቢብ አትሁን፡፡
226
+ ኢትክሉ ተቀንዮ ለአግዚአብሔር ወለንዋይ፡፡,ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም፡፡
227
+ ኢትክሉ ተቀንዮ ለክልዔ አጋእዝት፡,ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም፡፡
228
+ ኢትክል ተከብቶ ሀገር፤ እንተ ተሐንጸት መልእልተ ደብር,በተራራ ላይ የተሠራች ህገር መሠወር አትችልም፡፡
229
+ ኢትዛለፍ በማእከለ ሊቃውንት፡፡,በሊቃውንቱ መካከል አትጥቀስ፡፡
230
+ ኢትግሥሠ መሲሃንየ ወኢታህስሙ ዲበ ነቢያትየ፡፡,መልእክተኞቼን አታስጨንቁ፤ በነቢያቶቼም ላይ ከፉ አታድርጉ
231
+ ኢትፍርህዎ ለሞት ፍርህዋ ለኃጢአት,ሞትን አትፍሩት፤ ኃጢአትን እንጀ፡፡
232
+ ኢትፍጽሞ ለብዕራይክከ ሶበ ታከይድ እክለክ፡፡,እህልክን ስትወቃ የሚያበራየውን በሬ አፍ አትለጉመው፡፡
233
+ ኢየኃድጋ ለሀገር ዘእንበለ አሐዱ ሔር፡፡,ሀገርን ያለ አንድ ቸር ለው አይተዋትም፡፡
234
+ ኢየአርሩ በለለ እም አስዋክ፤ ወኢይቀስሙ አስካለ እም አሜከላ፡፡,ከአሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንደርም ወይንን አይቆርጠም፡፡
235
+ ኢያስህትከ ላህያ ለብእሲት፡፡,የሴት ውበቷ አያታልህ፡፡
236
+ ኢይመውያ ሰሚዕ ለርእይ፡፤,መስማት ማየትን አያሸንፍም፡፡
237
+ ኢይትፈቀድ ምክንያት ለኢአሚን፤ ዳዕሙ ይትፈቀድ ለአሚን,ለማመን እንጅ ላለማመን ምክንያት አያሻም፡፡
238
+ ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ፡፡,ነቢይ በሀገሩ አይከበርም፡፡
239
+ ኢይድህን ንጉሥ በዝኀ ሠራዊቱ፡፡,ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፡፡
240
+ ኢይጥዕሞ መዓር ለአድግ ዘእንበለ እጉስታር፡፡,ላህያ ገለባ እንጅ ማር እይጥማትም፡፡
241
+ ኢይፈቅድ ይንግርዎ ግኦእዞ ለሰብእ,የሰውን ማንነቱን አንዲነግሩት አይሻም፡፡
242
+ ኤፍሬም ይበልዖ ለምናሴ፤ ወምናሴ ይበልዖ ለኤፍሬም፡,ወንድም ወንድሙን ያጠፋዋል፡፡
243
+ እለ መጥባሕተ ያነሥኡ በመጥባሕት ይመውቱ፡፡,በሾተል የገደሉ፣ በሾተል ይሞታሉ፡፡
244
+ እለ ትነብሩ ተንሥኡ፡፡,��ተቀመጣቸችሁ ተነው፡፡
245
+ እለ ከርሦሙ አምላኮሙ።፡,ሆድ አምላኩዎች፡፡
246
+ እለ ጻጹተ ትነጥፋ ወእለ ገመለ ትውህጡ።,ግመልን የምትውጡ፣ ትንኝን የምታጠሩ፡፡
247
+ እመሰ ይትከሃለክሙ ምስለ ዙሉ ሰብእ ተእኅዉ፡፡,ቢቻላችሁስ ከሰዉ ሁሉ ጋር ተወዳጁ፡፡
248
+ እመሰ ጼው ለስሐ በምንት እንከ ይቄስምዎ?,ጨው አልጫ ቢሆን በምን ያጣፍጡታል?
249
+ አመ ተናገርኩ ጽድቀ ሰብእ ዛቲ ዓለም ይጸልኡኒ፤ ወከመ ኢይንብብ ሀሰተ ኩነኔ ዚእከ ያፈርሃኒ፤ ወእም ኩሉሰ አርምሞ ይቴይስ ወይሜኒ፡፡,እውነት እንዳልናገር የዚህ ዓለም ሰዎች ይጠሉኛል፤ ሀሰትም እንዳልናገር ፍርድህ ያስፈራኛል፡፡ ከሁሉም ዝምታ ይሻለኛል፡፡
250
+ እመ ወሀበ ብእሲ ኩሎ ንብረቶ ለፍቅር መንኖ አይሜንንዎ፡፡,ስው ስለፍቅር ንብረቱን ሁሉ ቢሰጥ ፈጽሞ አይንቁትም፡፡
251
+ እመ ይሰድዱክሙ እም አሐቲ ሀገር ጉዩ ኀበ ካልዕታ፡,ካንዱ አገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌካው ሽሹ
252
+ እም ተናግሮ ይሄይስ አርምሞ፡,ከመናገር ዝም ማለት ይሻሳል፡፡
253
+ እምነ መንግሥት የዐቢ ክህነት,ከቤተ መንግሥት ቤተ ክህነት ይበልጣል፡
254
+ እምነ ረፃብ የሄይስ ኩይናት፡፡,ከረሀብ ጦርነት ይሻሳል፡፡
255
+ እም ንጉሥ እቡድ ይቴይስ ገብር ጠቢብ፡፡,ከሰነፍ ንጉሥ ብልሀ አገልጋይ ይሻካል።፡
256
+ እም አሐዱ አፍ ይወጽኡ ቡራኬ ወመርገም፡,እርግማንና ምርቃት ከእንድ አፍ ይወጣሉ፡፡
257
+ እም እፈ በላዒ ወጽአ መብልዕ፤ ወእም አፈ ኃያል ተረክበ ጥዑም፡፡,ከበላተኛ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ፡፡
258
+ እም ከመ ተፈስሐ ልብ ይበርሀ ገጽ፡፡,ልብ ሲደስት ፊት ይበራል፡፡
259
+ እም ከመ ኀዘነ ልብ ይዴምን ገጽ፡,ልብ ሲያዝን ፊት ይጠቁራል።፡
260
+ እም ድኅረ ሞቱ ለስብእ አልቦቱ ንስሐ፡፡,ስው ከሞተ ንስሐ የሰውም፡
261
+ እም ዙሉ ምግባረ ጽድቅ የዓጽብ ጽሙና፣ ወእም ኩሉ መዓርግ ይትሌዓል ብሕትውና።,ከጽድቅ ሥራ ሁሉ ጭምተኝነት፣ ከማዕረግም ሁሉ ምንኩስና ይበልጣሉ፡፡
262
+ እስመ ሰውዳሴኒ ክንቱ ይልዕካ ዝሙት፡፡,ውዳሴ ከንቱን ዝሙት ይልካታል፡፡
263
+ እስመ ልብሱ ለሥጋ ሞገሱ,ልብስ ለሰውነት ክብሩ ነው፡፡
264
+ እስመ መብልዕ ወመስቴ ያስተፋቅር፡፡,ምግብና መጠጥ ያዋድዳል፡፡
265
+ እስመ ስሙ ይመረሖ ኅበ ግብሩ፡፡,ስሙ ወደ ሥራው ይመራዋል፡፡
266
+ እስመ በብዝኃ ጥበብ ብዙኅ ኀዘን፡፡,በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛል፡፡
267
+ እስመ በትህትና ረከበ ልዕልና፡፡,በትህትና ክብርን አገኘ፡
268
+ እስመ በአሐዱ ፍቁር ይስሀብ ካልኡ፡፡,በአንዱ ፍቅር ሌላው ይሳባል፡
269
+ እስመ ተፋቅሮ ይደፍኖን ለኩሎን ኃጣውአ፡፡,ፍቅር በደልን ሁሉ ይፍቃል፡፡
270
+ እስመ ነፍስ ተሐድር በደም፡፡,ነፍስ በደም ታድራለች፡፡
271
+ እስመ ነፍስ ተዓጽብ እምሲሲት፤ ወሥጋ የዓጽብ እም ዓራዝ፡፡,ሥጋ (ስውነት) ከልብስ ነፍስም ከምግብ ይበልጣሉ፡፡
272
+ እስመ አልቦ ነገር ዘይስአኖ ሰእግዚአብሔር፡፡,ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የሰም፡፡
273
+ እስመ እም ቃልከ ትጸድቅ ወእም ቃልከ ትትኳነን፡፡,በአነጋገርሀ ይፈረድብሀል፤ ወይም ይፈረድልሀል፡፡
274
+ እስመ እምተረፈ ልብ ይነበብ አፍ።፡,ከልብ ሞልቶ የተረፈውን እፍ ይናገራል፡፡
275
+ እስመ ዘአፍቀረ ይጌሥጽ እግዚአብሔር፡፡,እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻል።፡
276
+ እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት ።,ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት፡፡
277
+ እስመ ኩሉ ለቤቱ ይሄሊ።,ሁሉም ለቤቱ ያስባል፡፡
278
+ እስመ ኩሉ ጾሮ ይጸውር፡፡,ሁሉም እዳውን ይሸከማል፡፡
279
+ እስመ ቁር ወረሃብ ያረስዕ ጸሎተ፡,ብርድና ረሃብ ጸሎትን ያስረሳል፡፡
280
+ እስከ ማዕዜኑ ተሐነከሱ በክልዔሆን ጌጋያቲክሙ?,በሁለት ሃሳብ እለከ መቸ ታነከሳሳችሁ?
281
+ አቀትሎ ለኖላዊ ወይዘረዉ አባግዒሁ።፡,እረኛውን እገድለዋለሁ፤ በጎቹም ይበተናሉ፡፡
282
+ እንበለ መከራ፤ ኢይትረከብ ጸጋ፡፡,ያሰመከራ ጸጋ፤ ያለ ድካም ዋጋ አይገኝም፡፡
283
+ እንበለ ዝናም ደመና፤ እንበለ ንጽህ ምንኩስና:,ያለዝናብ ደመና፤ ያሰንጽህና መንኩስና፡፡
284
+ እንተ ኢትልህቅ ጣዕዋ ትመርሕ እማ፡፡,የማታድግ ጥጃ እናቷን ትመራለች፡፡
285
+ እንዘ ቦ ልሂቅ ኢይትናገር ደቂቅ፡፡,አዋቂ ሽማግሌ እያለ ልጅ አይናገርም፡፡
286
+ እንዘ ቦ ርሁብ ውስተ ቤትከ አታውጽእ አፍእ፡፡,ከቤትህ ራብተኛ እያለ ውጭ አውጥተህ አትስጥ።
287
+ እኩይ ብእሲ ያወጽኣ ለእኪት እም እኪት መዝገበ ልቡ።,ክፉ ስው ከክፉ ልቡ ክፋቱን ያወጣታል
288
+ እክል ያጸንእ ኃይለ ሰብእ።,እህል (ምግብ) የለውን ኃይል ያጠነክራል፡፡
289
+ እድ ጽኑእ ብእሴ ያብዕል፡፡,የትጉህ እጅ ታበለጽገዋለች፡፡
290
+ እግዚአብሔር ወኀበ ወአግዚአእብሔር ነሥአ፡፡,እግዚአብሔር ለጠ፤ እግዚአብሔር ነሳ፡፡
291
+ እጽብሰ እጹብ ውእቱ፤ እሰመ ለእጹብ ትርጓሜ እልቦቱ፡፡,እጹብ እጹብ ነው ለእጹብ ትርጉም የለውም፡፡
292
+ ኦሆ በሀሊ፡፡,አሽ ባይ።
293
+ ከመዝ ንግሩ፤ ወከመ ዝ ግበሩ፡፡,እንዲህ ንገሩ፤ እንዲህ ሥሩ።
294
+ ከንቱ ውዳሴ፡፡,የማይገባ ምስጋና
295
+ ኩኑ ቅዱሳነ፤ እሰመ አነሂ ቅዱስ አነ።,እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሶች ሁኑ፡፡
296
+ ኩኑ ከመ ይእዜ እለ ተወልዱ ሕጻናት,ዛሬ እንደ ተወለዱ ሕጻናት ሁኑ።
297
+ ኩኑ ጠቢባነ ከመ እርእዌ ምድር፤ ወየዋሃነ ከመ ርግብ፡፡,እንደ እባብ ብልህ፤ እንደ ርግብ የዋህ ሁኑ።
298
+ ኩን መሃይምነ እስከ ለሞት፡።,እለከሞት ድረስ የታመንከ ሁን፡፡
299
+ ኩን ጠቢበ ለእድውከ,ለባለንጋራህ ብልህ ሁንበት፡።
300
+ ካህናቲከ ይለብሉ ጽድቀ።፡,ካህናቶችህ ጽድቅን የጎናጸፋሉ።
301
+ ካህን ይነብር በየማነ ንጉሥ፡፡,ካሀን በንጉሥ ቀኝ ይቀመጣል፡፡
302
+ ከቡር ሞቱ ለጻድቅ፡፡,የደግ ሰው ሞት የከበረ ነው፡፡
303
+ ከቡር እውስቦ በኩለሄ ወለምስካቡኒ አልቦቱ ስእበት፡፡,መጋባት በሁሉም ዘንድ ከቡር፤ መኝታውም ቅፃዱስ ነው፡፡
304
+ ኮከብ እም ኮከብ ይሄይስ ክብሩ,በክብሩ ኮከብ ከኮከብ ይበልጣል፡፡
305
+ ወለሊሁ ሠይጣን ይትሜሰል ከመ መልአከ ብርሃን፡፡,ሳይጣን ራሱ የብርፃን መልእከን እስኪመሰል ይለወጣል፡፡
306
+ ወለእመ ሖርከ ብሔረ ባዕድ ኩን ከማሆሙ።፡,ሌላ አገር ብትሄድ እንደ እነሱው ሁን
307
+ ወለእመ ይለድድዱክሙ እም አሐቲ ሀገር ጉዩ ኅበ ካልዕታ፡፡,ካንዱ ሀገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌላው ሽሹ።፡
308
+ ወለደቂቀ መንግሥትሰ ያወጽእዎሙ አፍኣ፡፡,የመንግሥትንም ልጆች ወደ ውጭ ይጥሏቸዋል፡፡
309
+ አግዚእ አእምሮ በጠጅ፣ እነወለቡ በደጅ፡፡,ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፡፡
310
+ ወሙጻኡ ለቅስት የሃልቅ በመሐላ፡፡,ከርክር በመሐላ ይዘጋል፡፡
311
+ ወቀላለ ኮነት ዘመንየ ከመ ነገረ ከየአንም፡፡,ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይቸኩላል፡፡
312
+ ወቀደምትኒ ይከውኑ ድኅረ፡፡,ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ፡፡
313
+ ወትወርድ አመጻሁ ዲበ ድማሁ፡፡,ክፋቱ በራሉ ላይ ትደርሳለች፡፡
314
+ ወነገረ ቢጽ ኢይጥዕሞ ስሰቢጹ፡፡,የባልንጀራው ሃሰብ ለባልንጀራው አይጥመውም፡፡
315
+ ወነገርከ ያዔውቀከ፡፡,አነጋገርህ ማንነትህን ይገልጽብሃል፡፡
316
+ ወኢይጻእ ዐቢይ ነገር እም አፉክሙ፡፡,ክፉ ነገር ካፋችሁ አይውጣ፡፡
317
+ ወእምኩሉ የዐቢ ተፋቅሮ፡፡,ከሁሉም ፍቅር ይበልጣል
318
+ ወክልዔቴ ይስድድዎሙ ለእልፍ፡፡,ሁሰቱ ሺህዎቹን ያሳድዷቸዋል፡፡
319
+ ወዘአዝለፊ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን፡፡,ትዕግሥትን ያዘወተረ እርሱ ይድናል፡፡
320
+ ወያገብእ እሁ እኅዋሁ ለሞት፡,ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል
321
+ ወይን ወማኅሌት ያስተፌስሁ አልባበ፡፡,ወይንና ማኅሌት ልብን ያስደስታሉ፡፡
322
+ ወይን ያስተፌስሕ ልበ ለብእ፡፡,ወይን ጠጅ የሰውን ልብ ያስደስታል፡፡
323
+ ወድሶ ለለብእ በዘይደሉ፡፡,ስውን በሚገባው አመስግነው፡፡
324
+ ወኩሉ ዘተጽሕፈ ሰተግሣጸ ዚእነ ተጽሕፈ፡፡,የተጻፈው ሁሉ እኛ አድንመከርበት ተጻፈ።
325
+ ውሂብሰ እም ልማድ ውእቱ፡፡,መስጠት ከመልመድ ይመጣል፡፡
326
+ ውሂብሰ እም ረኪብ ውእቱ፡፡,መስጠት ከማግኘት ይመጣል፡፡
327
+ ውሂብ እም ድኅረ ስኢል እስረተ እድ ውእቱ፤ ወውሂብስ ቅድመ ስኢል ፈቲሐ እድ ውእቱ።,ከተለመኑ በኋሳ መስጠት እጅ መታሠር፤ ሳይለመኑ መስጠት ልግስና ነው፡፡
328
+ ዐቃቤ ሥራይ ፈውስ ርእሰከ፡፡,ባለ መድኃኒት ሆይ! ራስህን ፈውስ፡፡
329
+ ዓስምስ ያፈቅር እሊእሁ፡፡,ዓለም የራሱ የሆኑትን ይወዳል፡፡
330
+ ዕብን ዘመነንዋ ነደቅት፤ ወይእቲ ኮነት ውስተ ርእስ ማዕዘንት፡፡,አናጢዎች የናቋት ድንጋይ እርሷ የማዕዘን ራስ ሆነች፡፡
331
+ ዕውር ለዕውር ይትማርሑ ወይወድቁ ውስተ ግብ፡፡,ዕውር ዕውርን ቢመራ ተያይዞ ገደል፡፡
332
+ ዕውር ኢይባእ ውለተ ዝማሜ ወመሳጣ አይሠራዕ ጋሜ፡፡,ዕውር አይዘም፣ መላጣ ጋሜ አይሠራ፡፡
333
+ ዘላዕለ ነፍሱ ይኤብስ ለመኑ ኄረ ይከውን?,ራሉን የሚነፍግ ለማን ቸር ይሆናል?
334
+ ዘልህቀ በውስቴታ፤ የአምር ሥርዓታ፡፡,በውስጧ ያደገ ሥርዓቷን ያውቃል፡፡
335
+ በመሀሩክሙ ዕቀቡ ወዘከመ ምግባሮሙሰ ኢትግበሩ።,ያስተማሯችሁን ተግብሩ፤ የሚሠሩትን ግን አትሥሩ፡፡
336
+ ዘምር በመጠንከ,በልክ ዘምር!
337
+ ዘምስለ ጠዋይ ተጠዊ፤ ወምስለ ኅሩይ ኅሩየ ትከውን፡,ከጠማማ ጋር ጠማማ ከቀና ጋር ቀና ትሆናለህ፡፡
338
+ ዘረከበ ብአሲተ ሄርተ ረከበ ሞገስ፡፡,ቸር ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፡፡
339
+ ዘሰ በዐቅሙ ይበልዕ ጥዑይ ነፍሱ፡፡,መጥኖ የሚበላ፣ ጤውነቱ ጤና፡፡
340
+ ዘበውሁድ ምዕመን በብዙኅኒ ምዕመን፡፡,በትንሹ የታመነ በብዙዉም ይታመናል።
341
+ ዘቦ ብዙኅ ኢያትረፈ፤ ወዘቦ ውጉድ ኢያኅጸጸ።,ብዙ ያለው አልተረፈውም፤ ትንሽ ያለውም አልጎደለበትም፡፡
342
+ ዘተወክፈ ጻድቀ በስመ ጻድቅ፣ ዐስበ ጻድቅ ወእሴተ ጻድቅ ይረክብ፡፡,ጻድቁን በጻድቁ ስም የተቀበለ የጻድቁን ዋጋ ያገኛል፡፡
343
+ ዘኀሠሠ ክልዔ ኢይረክብ አሐደ፡፡,ሁለት የሻ አንድም አያገኝ
344
+ ዘኒ ትፈቅዱ ይግበሩ ለክሙ ሰብእ አንትሙኒ ግበሩ ሎሙ፤ ወዘኒ ኢትፈቅዱ ይግበሩ ብክሙ ኢትግበሩ ቦሙ,ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትሹትን አድርጉላቸው፤ ቢያደርጉባችሁ የምትጠሱትንም አታድርጉባቸው፡፡
345
+ ዘንስቲት ባቲ፤ ዕረፍት አልባቲ,ትንሽ ያላት፣፤ ዕንቅልፍ የላት፡፡
346
+ ዘአሀዙ ወርቀ ወዘኢአህዙ፣ ክልዓሆሙ ኅቡረ ተከዙ።፡,ወርቅ የያዙትም ሆኑ ያልያዙት በአንድነት አዘኑ።፡
347
+ ዘአልቦ ብእሲት ምንዱብ ውእቱ፡፡,ሚስት የሌለው የተበደለ ነው፡፡
348
+ ዘአልቦ ኃጢአት ለይገራ፡፡,ኃጢአት የሌለበት ይውገራት፡፡
349
+ ዘአልቦ ጽልቱጉት፡፡,ማስመስል የሌለበት፡፡
350
+ ዘአልዐለ ርእሶ የኃስር፤ ወዘአትሀተ ርአሶ ይከብር,ራሱን ከፍ ከፍ ያደረገ ይዋረዳል፤
351
+ ከኢተሰምዐ ተሰምዐ፤ ዘኢተገብረ ተገብረ፡፡,ያልተለማ ተለማ፤ ያልተደረገ ተደረገ፡፡
352
+ ዘኢተገብረ ለመላአክት ተገብረ ለካህናት፡፡,ለመላእክት ያልተደረገው ለካህናት ተደረገ
353
+ ዘኢኮነ ዕድውክሙ ቢጽክሙ ውአቱ፡፡,የማይቃወመን እርሱ ከኛ ጋር ነው፡፡
354
+ ዘኢይክል ሠሪዐ ቤቱ እፎ ያስተሐምም ቤተ አግዚአብሔር?,የራሱን ቤት በሥርዓት ያላደራጀ ቤተ አግዚአብሔርን እንዴት ያስተዳድራል?
355
+ ዘኢይፈቅድ ይትጌበር ኢይሴሰይ፡፡,ሊሠራ የማይወድ አይብላ፡፡
356
+ ዘእም ተረፈ ልብ ይነብብ አፍ፡፡,ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል፡፡
357
+ ዘአግዚአብሔር አስተጻመረ ኢይፍልጥ ሰብእ፡፡,አግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው አይለየው፡፡
358
+ ዘከዐወ ደመ ሰብኣ ይትከዐው ደሙ፡፡,የሰው ደም ያፈሰሰ ደሙ ይፈሳል።፡
359
+ ዘክልዔ ልቡ ህዉክ ውአቱ።፡,መንታ ልብ ያሰው የታወከ ነው፡፡
360
+ ዘወጠነ ይፌጽም፡።,የጀመረ ይፈጽም፡፡
361
+ ዘዐቀበ አስኪቶ የዐቅብ ህይወቶ፡፡,ህፍረተ ሥጋውን የጠበ���፣ ህይወቱን ጠበቀ፡፡
362
+ ዘዘገኑ ወርቀ ወዘኢዘገኑ፤ ክሌዔሆሙ ኅቡረ ኀዘኑ።፡,ወርቅ ያገኙም አዘኑ፤ ያላገኙም አዘኑ፡
363
+ ዘየሐውር መርድአ የኀሥሥ ምክንያተ፡፡,የሚሄድ ተማሪ ምክንያት ይሻል
364
+ ዘየዓቅብ አፋሁ ይትመሐፀን ነፍሶ፡፡,አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፡፡
365
+ ዘያፈቅር ቢጾ ውስተ ብርሃን ይነብር ።,ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል።
366
+ ዘይትናገር ዘኢይደልዎ ይሰምዕ ዘይጸልኦ።፡,የማይገባውን የሚናገር የማይወደውን ይሰማል፡፡
367
+ ዘይከሪ ግበ ለቢጹ ይወድቅ ውስቴቱ፡፡,ለጓደኛው ጉድጓድ የሚቆፍር ራሉ ይወድቅበታል፡፡
368
+ ዘይወጽእ እም አፉሁ ለሰብእ ውእቱ ያረኩሶ።፡,ካፉ የሚወጣው ስውን ያረክሰዋል፡፡
369
+ በድኅረ መጽአ ዐይነ አውጽአ፡፡,ከኋላ የመጣ ዐይን አወጣ፡፡
370
+ ዘጸንአ ዴዴሃ ይበልዕ ፍሬሃ,ደጅ የጠና ፍሬውን ይበላል፡፡
371
+ ዘጻመወ በዓለም የሐዩ ለዝሉፉ፡,በዚህ ዓለም የደከመ ለዘላለም ህያው ይሆናል፡፡
372
+ ዚአከ ለዚአየ፤ ዚአየ ለዚአከ፡፡,አንተ ለኔ እኔ ላንተ፡፡
373
+ ዛቲ ተግሣጽ ትኩነኒ እምዮም፡፡,ከዛሬ ጀምሮ ይች ተግሣጽ ትዝ ትበለኝ፡፡
374
+ ዝልፎ ለጠቢብ ከመ ይዌስክ ጥበበ፤ ኢትዝልፎ ለአብድ ከመ ኢይጽላእከ፡፡,ብልህን ገሥጸው ጥበብን ይጨምራል፤ ሞኝን አትገሥጸው አንተኑ ይጠላሃል፡
375
+ ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ።,የደግ ሰው ሥራ ለዘላስም ይኖራል
376
+ ዝ ኩሉ ሥርጋዌ በአንተ አሐዱ ነገር፡፡,ይህ ሁሉ መሽሞንሞን ለላንድ ጉዳይ ነው፡፡
377
+ የሀጉል ርአሶ ዘኀልያነ ይነሥአ፡፡,መማለጃን የሚጠላ በሕይወት ይኖራል፡፡
378
+ የአምነከ ሰብአ ሶበ ታሴኒ ሎቱ፡።,ሰው ስትውልለት እምነት ይጥልብሃል፡፡
379
+ ያኃሥረከ በአኅደርኮ፤ ወይዘረክየከ ዘለቃሕኮ፡፡,ያሳደርከው ያዋርድሀል፤ ያበደርከው ይሰድብሀል፡፡
380
+ ያዕቆብሃ አፍቀርኩ፤ ወኤሳውዛ ጸላእኩ,ያዕቆብን ወደድኩ፤ ኤሳውን ግን ጠላሁ፡፡
381
+ ይቤ አጋግ «ከመ ዝኑ ሞት መሪር»,«በውነት ሞት አንዲህ መራር ነውን» አጋግ፡፡
382
+ ይብሉ «ሰላም ሰሳም!» ወአልቦ ስላም፡፡,«ሰላም ስላም!» ይሳሱ ሰላም ግን የላቸውም፡፡
383
+ ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር,ሰነፍ በልቡ አምላከ የለም ይላል፡፡
384
+ ይብእስከ ረጊጽ ውስተ ቀኖት በሊህ።፡,የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተው ይብስብሃል፡
385
+ ይትወለወል ሰብእ እም ገዜ ልደቱ እስከ ጊዜ ሞቱ፡፡,ሰው አሰኪሞት ድረሰ ሲያመነታ ይኖራል፡፡
386
+ ይሄይስ ህዳጥ ዘበጽድቅ አምብዙኅ ብዕለ ኃጥአን,በዓመፅ ከተሰበሰበው ከብዙው፤ በሥራ የተገኘው ትንሹ ይበቃል፡
387
+ ይሄይስ ብሂም እምነቢበ ሀሰት፡።,ውሸት ከመናገር ዲዳነት ይሻላል።፡
388
+ ይሄይስ ብእሲ ዕጉስ እም ኃያል,ከኃይለኛ፤ ይሻላል ትዕግሥተኛ፡፡
389
+ ይሄይስ ነዳይ ጥዑይ ሥጋሁ ወፍቱሕ ነፍሱ፤ እምነ ባዕል ዘድውይ ሥጋሁ ወእሱር ነፍሱ፡,ሰውነቱ ከታመመና ሆዱ ከታሰረ ባለጸጋ ሰውነቱ ጤነኛ የሆነና ሆዱ የተከፈተ ደሀ ይሻላል
390
+ ይሄይሰ አሐዱ እም ፲ ፻፤ ወይሄይስ መዊት ዘእንበሰ ውሉድ እም ወሊድ ወልደ እኩየ፡፡,ከሺዎች ይልቅ እንድ አዋቂ ልጅ ይሻላል፤ ከፉ ከመውለድም ሳይወልዱ መሞት ይሻላል፡፡
391
+ ይሄይስ አርክ ቅሩብ እም እሁ ዘርቀ የኀድር።,ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት፡፡
392
+ ይሄይስ ፍተ ሐምል ፍቅር ዘቦቱ አመግዝዕ ዘአልህምት፡፡,የጎመን ወጥ በፍቅር መብላት ጥል ባበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል፡፡
393
+ ይኩን ኩሉ ብእሲ ፍጡነ ለሰሚዕ፤ ወጉንዱየ ለነቢብ ወለመዓት፡፡,ለው ሁሉ ለማዳመጥ ፈጣን፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየ ይሁን፡
394
+ ይወድስከ አፈ ነኪር ወአኮ አፈ ዚአከ,ራስክን አታወድስ! ሌላው ያመስግንህ እንጂ
395
+ ይደልዎ ለዘያነብብ ይዝክር ስሞ ለበዓሰ መጽሐፍ,አንባቢ የባለ መጸሐፉን ስም ሊያስታውስ ይገባዋል፡፡
396
+ ይደልዎ አስቡ ለዘይትቀነይ።፡,ለ��ራተኛ ደመወዙ የገባዋል፡፡
397
+ ይጹም ዐይን፤ ይጹም ልሳን፤ ዕዚንኒ ይጹም።፡,ዐይን ይጹም፤ አፍ ይጹም፤ ጆሮም ይጹም፡፡
398
+ ድልዋኒክሙ ንበሩ!,ተዘጋጅታችሁ ኑሩ!
399
+ ድክምት ቃል ትሰብር አጽመ,የተለሳለስች ቃል እጥንት ትለብራለች፡፡
400
+ ገብአተኒ ወርቅየ፡፡,ገንዘቤን አገኘኋት፡፡
401
+ ጊዜሁ ለመብልዕ ረሃብ ወለስትይ ጽምእ፡,የመመገቢያ ጊዜው መራብ፣ የመጠጫም ጊዜው መጠማት ነው፡፡
402
+ ጊዜ ሰአልኩከ ጸግወኒ ፍታ፤ እስመ ኢየአምር ስብእ ዘትወልድ ሳኒታ፡፡,የስው ልጅ ነገ የሚሆነውን አያውቅምና በለመንኩህ ጊዜ የዕለት እንጀራየን ስጠኘኝ፡
403
+ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡፡,እግዚአብሔር የሥራ ጌዜ አለው፡፡
404
+ ጌሰምሰ ትሄሊ ለርእላ፡፡,ነገ ሰለ ራሷ ታስባለች፡
405
+ ግብር ዘአልቦ ምጣኔ ገዐር ውዕቱ፡፡,ልክ የሌለው ሥራ ብክነት ነው፡
406
+ ጠቢብ ገብር ይሜብል እግዚኡ፡,ጥበበኛ ባሪያ ጌታውን ይገዛል፡፡
407
+ ጥበብ ትትበደር እምወርቅ፡፡,ከገንዘብ ጥበብ ትመረጣለች፡፡
408
+ ጥበብ ትሄይስ እመኩሉ መዛግብት፡፡,ከሀብት ሁሉ ጥበብ ትበልጣለች፡፡
409
+ ጸላእተከሙ አፍቅሩ።,ጠላቶቻችሁን ውደዱ።፡
410
+ ጸሎቱ ለመስተቀይም ኢውክፍት ቅድመ እግዚአብሔር፡,የቂመኛ ጸሎት በአግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የለውም
411
+ ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመ ዘርዕ ዘወድቀ ማዕከስ አስዋክ፡፡,የቂመኛ ጸሎት ከእሾህ ላይ እነደ ወደቀው ዘር ነወ
412
+ ጸጋ በዲበ ጸጋ፡፡,በጸጋ ላይ ጸጋ፡፡
413
+ ጻማ ከናፍር፡፡ ,ጉንጭ አልፋ፡፡
414
+ ጻድቅስ ይምሕር ወይሁብ፡,ደግ ይራራል፤ ይሰጣልም፡፡
415
+ ጽጋብ ያመጽእ ግብረ ቅንጻዌ! ወቅንጻዌ ያፈደፍድ ደዌ,ጥጋብ ያዘልላል፤ ዝላይም ለከፋ ሕመም ያጋልጣል፡፡
416
+ ፀሩ ለከርሥ አፍ፡፡,የሆድ ጠላቱ አፍ ነው፡
417
+ ፈታሒ በጽድቅ ኩናኒ በርትዕ፡፡,እውነት ፈራጅ ቅን ገዥ፡፡
418
+ ፍሬ ከናፍር።,የንግግር ፍሬ ቃል፡፡
419
+ ፍዳ ለኃጥአን ዕሴት ለጻድቃን፡፡,ለኃጥእን ቅጣት፤ ለጻድቃን ሽልማት፡፡
420
+ ፓፓ ዘኢይስሕት፡፡,ፓፓዉ አይሳቱም፡፡
421
+ ኩሉ ማእምር፣ ይገብር በምክር፡፡,ዐዋቂዎች ሁሉ ተማክረው ይሠራሉ፡፡
422
+ ኩሉ ቡሩክ፡፡,ሁሉ መልካም፡፡
423
+ ዙሉ ነፍስ ይሴብሖ ለእግዚአብሔር።,ነፍስ ሁሉ እግዚእብሔርን ያመሰግናል፡፡
424
+ ኩሉ ንጹሕ ለንጹሓን፡፡,ለንጹሖች ሁሉም ንጹሕ ነው፡
425
+ ኩሉ ከንቱ፡፡,ሁሉም ከንቱ ነው፡፡
426
+ ኩሉ ዐረየ ወኅቡረ አለወ,ሁሉም ተባበሮ ከፋ፡፡
427
+ ዙሉ ዕፅ ዘኢይፈሪ ፍሬ ሠናየ ይትገዘም፤ ወውስተ እላት ይትወደይ፡፡,መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል፡
428
+ ኩሉ ዘነፍስ፤ ይበሊ ከመ ልብስ፡፡,ሰው ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃል፡፡
429
+ ኩሉ ዘገብራ ለሠናይት ይረከብ ሠናየ፡,መልካም የሠራ መልካም ነገር ያገኛል፡፡
430
+ ኩሉ ይሴኒ ሰአመ ንሴኒ ንህነ,እኛ ጥሩ ከሆን ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል፡፡
431
+ ኩሉ ይሄሊ ትካዘ ርእሱ፡፡,ሁሉም የራሱን ጭንቅ ያሰባል፡፡
432
+ ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱፅ፡፡,መልካም ጊዜ ሁሉም ደግ ይሆናል፡፡
433
+ ኩሎ አመክሩ ወዘሠናየ አጽንኡ,ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ።
434
+ ጐንዱየ እብጽሕ እገሪከ ኀበ እርከከ፤ ከመ ኢይጽገብከ፤ ወኢይጽላእክ፡፡,እንዳይሰለችህ፣ እንዳይጠላህም የባልንጀራህን ቤት አታዘውትር፡፡
435
+ ጉየያ ለፍትወተ ውርዙትከ፡፡,የወጣትነት ፍላጎትህን ሽሻት፡፡