sentences
list
labels
list
[ "የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ተቆልፎባቸው እንዲሰሩ የተገደዱ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገለፀ የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ውስጥ ተቆልፎባቸው የነበሩ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገልጿል። ሰራተኞቹ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ ከፋብሪካው እንዳይወጡ እግድ ተጥሎባቸውና ተቆልፎባቸው ይሰሩ ነበር ተብሏል። በሰሜናዊ ናይጄሪያ ግዛት በምትገኘው ካኖ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት ሰራተኞች የኮሮናቫይረስ አስገዳጅ የቤት መቀመጥ አዋጅን ተከትሎ ወደቤታቸው እንዳይሄዱና በየወሩም ከሚያገኙት 2 ሺህ 600 ብር ደመወዝ በተጨማሪ 500 ብር እንደሚጨመርላቸው የፋብሪካው አስተዳዳሪዎች ቃል ገብተውላቸው ነበር። ወደቤታችን እንሄዳለን የሚሉት ደግሞ ከስራ እንደሚባረሩ ማስፈራራሪያም ደርሷቸዋል። በፋብሪካው ለመስራት የተስማሙ ሰራተኞች ከፋብሪካው ወጥተው መሄድ እንደማይችሉም ተነግራቸዋል። ይህንንም ተከትሎ አምስት አስተዳደር ላይ ያሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የህንዶች የሆነው ፖፑላር ፋርምስ የተሰኘው ፋብሪካ ከቢቢሲ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠየቅም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። የፖሊስ ቃለ አቀባይ አብዱላሂ ሃሩና ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፋብሪካው እንደተዘጋና ባለቤቶቹም ሰራተኞቹን ያለፍቃዳቸው በመቆለፋቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል። አንዳንድ ሰራተኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የነበሩበት ሁኔታ ከእስር ያልተናነሰ እንደሆነና ትንሽ ምግብም ብቻ ይሰጣቸው እንደነበር ገልፀዋል። \"በጣም ለአጭር ጊዜ ብቻ እንድናርፍ ነበር የሚፈቀደልን። ፀሎት ማድረግ እንዲሁም ቤተሰብ እንዲጠይቀን አይፈቀድልንም ነበር\" በማለት የ28 አመቱ ሃምዛ ኢብራሂም ለቢቢሲ ተናግሯል። ፖሊስ ጉዳዩን የተረዳው አንደኛው ሰራተኛ ለሰብዓዊ መብት ድርጅት እንዲያድኗቸው በመማፀን ከላከው ደብዳቤ ነበር። \"ያየሁት ሁኔታ በጣም ልብ የሚሰብር ነው። ሰራተኞቹ ለእንስሳ እንኳን በማይመጥን ሁኔታ ነው እንዲቆዩ የተደረጉት\" በማለት የግሎባል ሂውማን ራይትስ ኔትወርክ ሰራተኛ ካሪቡ ያሃያ ካባራ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አክለውም \"የሚሰጣቸው ምግብ በጣም አነስተኛ ነበር። ታመው ለነበሩትም ሕክምና ተከልክለዋል፤ የመድኃኒት አቅርቦት አልነበራቸውም\" ያሉት ካሪቡ ለሰራተኞቹ ፍትህንም እንደሚሹ ጠይቀዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንዲቻል ናይጄሪያ ሁሉም ፋብሪካዎችም ሆነ የንግድ ቦታዎች እንዲዘጉ ያዘዘችው መጋቢት አጋማሽ ላይ ነበር። በናይጄሪያ እስካሁን 20 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን መዲናዋ ሌጎስም የስርጭቱ ማዕከል ሆናለች። ከሌጎስ በመቀጠልም የናይጄሪያ ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ካኖም በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ትከተላለች። ወረርሽኙን ለመግታት የተላለፉ መመሪያዎች በሌሎች ቦታዎች ቢላሉም በካኖ ግን የቤት መቀመጥ አዋጁ እንዳለ ነው። ዜጎች ሰኞ፣ ረቡዕና አርብ መንግሥት በወሰነው ሰዓት ብቻ ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመሸመት ይወጣሉ።", "ኢትዮጵያ፡ በደረሰው የጎርፍ አደጋ 130 ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል በኢትዮጵያ እስከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የተነሳ 170 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 130 ሺህ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር ለቢቢሲ ገለፁ። ኮሚሽነሩ አቶ ዳመነ ዳሮታ ከዚህ በፊት የነበረውን ልምድ ከግንዛቤ በማስገባት በዚህ ዓመት ክረምት ወቅት በጎርፍ ምክንያት ወደ 2 ሚሊየን ያህል ሰዎች ሊጎዱ እንዲሁም 434 ሺህ ያህሉ ደግሞ ሊፈናቀሉ ይችላሉ ተብሎ ግምት መያዙን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በአፋር ክልል የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 67 ሺህ 885 አካባቢ ሲሆን፣ 40 ሺህ 130 አካባቢ ደግሞ መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኮሚሽነር ዳመነ አክለውም ደቡብ ኦሞ ዳሰነች አካባቢ በኦሞ ወንዝ ሙላትና የግቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃ በተወሰነ መልኩ መልቀቁን ተከትሎ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በኦሞ በሚገኙ ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች እንዳይጎዱ ከሚኖሩበት አካባቢ የማውጣት ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ መደረጉን ገለፀው ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑት የተለያዩ ድጋፎች ደርሷል ብለዋል። ለቀሪዎቹ 5ሺ ሰዎች ደግሞ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል። ዘንድሮ በጎርፍ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ለቢቢሲ የገለፁት ኮሚሽነሩ፣ ነገር ግን ኮሚሽኑም ሆነ መንግሥት ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ዝግጅት ያደረጉበት ዓመት እንደነበር ለቢቢሲ አብራርተዋል። በዚህ ዓመት በልግ ወቅት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 470 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ከ300 ሺህ በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን ኮሚሽነሩ ጨምረው አስረድተዋል። ኮሚሽኑ ይህን የበልግ ወቅት አደጋን በመቋቋም ላይ ባለበት ወቅት የክረምቱ ዝናብ ከበልጉ ዝናብ ጋር ተያይዞ በመምጣቱ ወንዞችና ግድቦች በመሙላታቸው በርካቶች ለአደጋ መጋለጣቸውን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ በተለየ ሶስት ጊዜ የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን ገልፀው ሁለቱ ማስጠንቀቂያዎች የወጡት በዚህ ክረምት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል። እስከ መስከረም መጨረሻ ተከታታይ ዝናብ ስለሚኖር ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት እንደሚችል የገለፁት ኮሚሽነሩ ነሐሴ መጨረሻዎቹ ላይ የተንዳሆ ግድብ ሊሞላ ስለሚችል ቀጣይም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ፣ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስም የከሰምና፣ የቆቃ ግድቦች እየሞሉ እንደሚሄዱ በመግለጽ ሁሉም አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በመከላከኛውና፣ የታችኛው አዋሽ ላይ ከፍተኛ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው በመግለፅ በዚህም የተነሳ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በዚህ የክረምት ወቅት የደረሰው ጉዳት መቀነሱን ተናግረዋል።", "አየር መንገዶች ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን እንዳያበሩ ዳግም ታገዱ ከሁለት የመከስከስ አደጋ በኋላ ዳግም እንዲበር ፍቃድ አግኝቶ የነበረው የቦይንድ 737 ማክስ አውሮፕላን ዳግም አጣብቂኝ ውስጥ ገባ። የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዢያው ላየን አየር መንገድ ንብረት የሆኑት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የመከስከስ አደጋ ካጋጠማቸው በኋላ በመላው ዓለም አውሮፕላኑ እንዳይበር እግድ ተጥሎበት እንደነበረ ይታወሳል። ከስድስት ወራት በፊት ግን የአሜሪካ የበረራ ደህንነት ተቋማት አውሮፕላኑ ዳግም እንዲበር ፈቃድ ሰጥተው ነበር። ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ ሌላ የኤሌክትሪክ ችግር እንዳለበት በመታወቁ ዳግም ሌላ አጣበቂኝ ውስጥ መግባቱ ተነግሯል። አውሮፕላኑ ዳግም ለማብረር የወሰኑ በመላው ዓለም የሚገኙ 24 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን እንዳያበሩ ተነግሯቸዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ቦይንግ ያመረታቸውን አውሮፕላኖች ከማከፋፈል ተቆጥቧል። ቦይንግ እና የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራን ነው ብለዋል። በአውሮፕላኑ ላይ የኤሌክትሪክ ችግር መገኘቱ ቀድሞውኑ አውሮፕላኑ ጥብቅ የደህንነት ፍተሻ ሳይካሄድበት ለበረራ ብቁ ነው መባሉ ሲተቹ ለነበሩ ሌላ የመከራከሪያ ነጥብ ሆኖላቸዋል። ቦይንግን አጥቦቆ በመተቸት የሚታወቁት የቀድሞ የቦይንግ አስተዳዳሪ ኤድ ፒርሰን፤ በቦይንግ ፋብሪካ ያለው ደካማ የምርት ጥራት የኤሌክትሪክ ችግር እንደምክንያት በማንሳት የበርካቶችን ህይወት ለቀጠፉት አደጋዎች ምክንያቱ ይህ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ቦይንግ እና ኤፍኤኤ አውሮፕላኑ ላይ የተገኘው ችግር የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያመነጨው ስርዓት ላይ ነው ብለዋል። ለዚህ መንስዔው የኤሌክትሪ ግነኙነቶች ሥራ ጥራት ደካማ መሆኑ ነው ይላሉ። ኤፍኤኤ እንደሚለው የአሌክትሪክ ችግር፤ “መሠረታዊ የሆኑ የአውሮፕላኑ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።” ኤፍኤኤ ይህ የአውሮፕላኑ የኤሌክትሪክ ችግር ሳይቀረፍ አውሮፕላኑ አገልግሎት መስጠት የለበትም በማለት ከሁለት ሳምንት በፊት \"አውሮፕላኑ ለመበረር የደህንነት ስጋት አለበት\" የሚል መመሪያ አውጥቶ እንደነበረም ተጠቅሷል። ቦይንግን 737 ማክስ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ሲበር ተከስክሶ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው ይታወሳል። ተመሳሳይ የኢንዶኔዥያ ላየን ኤር ንብረት የሆነ አውሮፕላን ከኢንዶኔዢያ ተነስቶ ባህር ውስጥ መከስከሱ ይታወሳል። በሁለቱ አደጋዎች በአጠቃላይ 346 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።", "ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ500 ቢሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት አዘጋጀች የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀትን ለመጀመሪያ ጊዜ ከ500 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያደርግ ረቂቅ በጀት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ። የመጪው ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት በጀት ከዘንድሮው በ85 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያዘጋጀው ረቂቅ በጀት አመልክቷል። ምክር ቤቱ የቀጣዩ ዓመት የፌደራል መንግሥቱ በጀት 561 ቢሊዮን ብር በላይ በላይ እንዲሆን የወሰነ ሲሆን በ2013 ካለው የ476 ቢሊዮን ብር በጀት በ18 በመቶ ከፍ ብሏል። ይህም የየ85 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ታይቶበታል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2014 ዓ.ምን በጀት ከማጽደቁ በፊት በቀዳሚነት ለዚህ ዓመት ባስፈለገው ተጨማሪ በጀትና የመንግሥት ወጪን ለመሸፈን ያስፈለገው ማስተካከያ ተግባራዊ እንዲሆን በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ መክሯል። በዚህም መሠረት ለ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት ያስፈለገው በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ጦርነት ጋር ተያይዞ ላጋጠሙ ወጪዎች፣ በድርቅ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ እና ለተመላሾች የእለት እርዳታ አቅርቦት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ለማዳበሪያ አቅርቦት ድጎማ፣ ለጎርፍ መከላከል እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም ለማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የአቅም ግንባታ ፕሮጀክትና \"የመጠባባቂያ በጀት በማለቁ በቀጣይ ወራቶች ለሚያስፈልጉ የተለያዩ ወጪዎች የመጠባበቂያ በጀት መመደብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው\" ሲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ አመልክቷል። የተጠየቀው 26.4 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ከተለያዩ ምንጮች የሚገኝ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም ይህንኑ ተቀብሎ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶታል። ከዓመት ዓመት ጭማሪ እያሳየ የመጣው የፌደራል መንግሥቱ ዓመታዊ በጀት በቀጣዩ 2014 ዓ.ም 561.67 ቢሊዮን ብር እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወስኗል። ይህም አስካሁን አገሪቱ ከያዘችው ዓመታዊ በጀት ሁሉ የላቀው ነው። ለቀጣይ ዓመት የተያዘው በጀት ለመደበኛ ወጪዎች 162 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 183.5 ቢሊዮን ብር፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 203.95 ቢሊዮን ብር፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 12 ቢሊዮን ብር መያዙ ተገልጿል። ቅዳሜ ዕለት ግንቦት 28/2013 ዓ.ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ላይ የተወሰነው ተጨማሪ በጀትና ረቂቅ በጀት ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ይኖርበታል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበራትን ዓመታዊ በጀት ስንመለከት በ2012፣ 386 ቢሊዮን 954 ሚሊዮን 965 ሺህ 289 የነበረ ሲሆን በ2011 ደግሞ 346 ቢሊዮን 915 ሚሊዮን 451 ሺ 948 ተመድቦ ነበር። በ2010 የነበረው በጀት 320.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ ከ60 በመቶ የሚበልጠው ለትምህርት፣ ለግብርናና ለመሰረተ ልማትና ለጤና ማስፋፊያ እንዲሆን ተብሎ የተበጀተ ገንዘብ ነበር። ከ300 ቢሊዮን ብር በታች የነበረው የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት በ2009 ዓ.ም ላይ 274.3 ቢሊዮን በጀት መሆኑ የሚታወስ ነው።", "ዓለም አቀፉ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ስዊፍት ምንድን ነው? ስዊፍት የአገራት ድንበሮች ሳይገድቡት በተመቸ እና በፈጣን ሁኔታ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማስተላላፊያ ሥርዓት ነው። ስዊፍት [Swift] ሶሳይቲ ፎር ኢነትረባንክ ፋይናንሻል ቴሌኮምዩኒኬሽን [Society for Worldwide Interbank Financial Telecommunication] የሚለው ስያሜ አህጽሮተ ቃል ነው። በሥርዓቱ የተካተቱ በዓለም ዙሪያ ያሉ ባንኮች ያለምንም ተጨማሪ ውጣ ውረድ ገንዘብ ይላላኩበታል። ስዊፍት እንደ አውሮፓውያኑ በ1973 የተጀመረ ሲሆን መሰረቱ ቤልጂየም ነው። የስዊፍት ሥርዓት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ200 በላይ አገራት ውስጥ የሚገኙ 11 ሺህ ባንኮችን እና የፋይናንስ ተቋማትን አስተሳስሯል። ስዊፍት ከመደበኛው የባንክ ሥርዓት ጋር የሚመሳሰል አይደለም። ይህ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ክፍያዎች ሲደርሱና ሲፈጸሙ ለተጠቃሚዎች የሚያሳውቅ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ሥርዓት ነው። በስዊፍት ትሪሊየን ዶላሮች በኩባንያዎች እና በመንግሥታት ስለሚዘዋወር በቀን ከ40 ሚሊዮን በላይ መልዕክቶችን ይልካል። ከእነዚህ መልዕክቶች ውስጥ ሩሲያ ከአንድ በመቶ በላይ ክፍያዎችን ታስተናግዳለች ተብሎ ይታሰባል። ይህ ግን በገንዘብ ሲሰላ ቀላል የሚባል አይደለም። ሩሲያ ከስዊፍት እንድትታገድ ጥሪ የሚቀርበው ለምንድን ነው? በሺዎች የሚቆጠሩ ባንኮች ከሚጠቀሙበት ከዚህ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ሥርዓት ሩሲያን ማገድ የአገሪቱን የባንክ ኔትዎርክ እና የገንዘብ አቅርቦትን ይጎዳል። ነገር ግን ተጎጂዋ ሩሲያ ብቻ አይደለችም። ይህ ማዕቀብ የራሳቸውን ኢኮኖሚ እና ኩባንያ መልሶ እንዳይጎዳ በርካታ መንግሥታት ይሰጋሉ። ለአብነት ከሩሲያ ነዳጅ የሚቀርብላቸው አገራት በዕገዳው ምክንያት ነዳጅ ሊስተጓጎልባቸው ይችላል። ዩናይትድ ኪንግደም ሩሲያ ከስዊፍት እንድትታገድ በአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ቤን ዋላስ በኩል ጥሪ ብታቀርብም ብቻዋን ልታሳካው እንደማትችል ገልጻለች። \"እንዳለመታደል ሆኖ የስዊፍት ሥርዓት በእኛ ቁጥጥር ውስጥ አይደለም። በአንድ ወገን ውሳኔ የሚሳካ አይደለም\" ብለዋል። ጀርመን ሩሲያ ከስዊፍት እንዳትታገድ የማትፈልግ አገር እንደሆነች ይታማናል። በተመሳሳይ የፈረንሳይ የገንዘብ ሚኒስትር ብሩኖ ለሜሬ እና የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ውሳኔው የመጨረሻ አማራጭ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባው ጠቁመዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያን አሁን ላይ ከስዊፍ ማገድ አማራጭ ሆኖ እንዳልቀረበ ገልጸዋል። ምንም እንኳን \"የተቀረው የአውሮፓ ክፍል አሁን ለመውሰድ የሚፈልገው እርምጃ ይህ ባይሆንም\" አማራጭ ሆኖ እንደሚቆይ ግን ተናግረዋል። የስዊፍትን ባለቤትና ተቆጣጣሪ ማነው? ስዊፍት የተጀመረው አንድ ተቋም ሥርዓቱን ዘርግቶ የባንኮች የገንዘብ ዝውውር ሥርዓትን በብቸኝነት ጠቅልሎ እንዳይዝ ባቀዱ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ባንኮች አማካይነት ነው። ሥርዓቱን ከ2,000 የሚልቁ ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በጋራ ባለቤትነት ይዘውታል። ይህ የስዊፍት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት በቤልጂየም ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር የሚደረግበት ሲሆን የአሜሪካ ፌዴራል ግምጃ ቤትን እና የእንግሊዝ ባንክን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ ዋና ዋና ማዕከላዊ ባንኮችም በቁጥጥሩ ይሳተፋሉ። ስዊፍት በአባል አገራት መካከል ደኅንነቱ የተጠበቀ ዓለም አቀፍ ንግድ እንዲኖር የሚረዳ ሲሆን ግጭቶች ሲኖሩ ለማንም እንዳይወግን ይጠበቃል። ሆኖም ከዚህ መርኅ በተቃራኒ ኢራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት እንደ አውሮፓውያኑ በ2012 ከስዊፍት ታገደች። በዚህም ምክንያት ወደ ውጭ ከምትልከው የነዳጅ ሽያጭ ገቢዋ ግማሹን ያጣች ሲሆን 30 በመቶ የውጭ ንግዷንም አጥታለች። ስዊፍት ግን ማዕቀቡ እንዲጣል ምንም አይነት ተጽእኖ እንዳላደረገ እና ውሳኔው በመንግሥታቱ ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል። ሩሲያን ከስዊፍት ማገድ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል? ሩሲያ ከስዊፍት ሥስርዓት ከታገደች የአገሪቱ ኩባንያዎች በስዊፍት በኩል የሚያገኙት መደበኛ፣ የተመቸ እና ፈጣን የገንዘብ ልውውጥን ያጣሉ። በተጨማሪም ለኃይል አቅርቦት እና ለእርሻ ምርቶች ክፍያዎች የሚፈጸምበት መንገድ ክፉኛ ይስተጓጎላል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ሩሲያ ክሪሚያን መውረሯን ተከትሎ ከስዊፍት ልትታገድ እንደምትችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷት ነበር። ሩሲያ እርምጃውን ጦርነት ከማወጅ አሳንሳ እንደማትመለከተው አሳውቃ ነበር። በወቅቱም ምዕራባውያኑ በውሳኔው ባይገፉበትም ሩሲያ ግን የራሷን ተመሳሳት ሥርዓት እንድትፈጥር አጋጣሚ የፈጠረላት ነበር። እንዲህ ያለውን ማዕቀብ ለመቋቋም የሩሲያ መንግሥት ለካርድ ክፍያዎች የሚሆን 'ሚር' የተሰኘ ብሔራዊ የክፍያ ካርድ ሥርዓት ዘርግቷል። ነገር ግን ጥቅም ላይ የዋለው በጥቂት አገራት ውስጥ ብቻ ነው። ምዕራቡ በስዊፍት ላይ ለምን ተከፋፈለ? ሩሲያን በስዊፍት እንዳትጠቀም ማገድ ከአገሪቱ ጋር የንግድ ልውውጥ ያላቸውን ወይም ምርት የሚያቀርቡ እና የሚገዙ ኩባንያዎችን ይጎዳል። በተለይም ጀርመን የመጀመሪያዋ ተጎጂ ትሆናለች። ሩሲያ የአውሮፓ ሕብረት የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ዋነኛ አቅራቢ ስትሆን፣ ለሕበረቱ አማራጭ አቅርቦቶችን ማግኘት ቀላል አይሆንም። የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በዚህ ሳቢያ መሰል ችግር እንዲፈጠር መንግሥታቱ አይፈልጉም። እንዲሁም በሩሲያ ዕዳ ያለባቸው ኩባንያዎች ክፍያ የሚያገኙበት አማራጭ መንገዶችን መፈለግ ግድ ይላቸዋል። የሩሲያ ከስዊፍት መውጣት የዓለም አቀፍ የባንክ ሥርዓት ላይ የሚፈጥረው ቀውስ ቀላል እንዳሆነ ይታመናል። የሩሲያ የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር አሌክሲ ኩድሪን የአገሪቱ ስዊፍት መታገድ ምጣኔ ሀብቷን በ5 በመቶ እንዲያሽቆለቁል ሊያደርገው ይችላል ብለዋል። ይሁን እንጂ ውሳኔው በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ስለማምጣቱ አጠራጣሪ ነው። ምክንያቱም የሩሲያ ባንኮች የራሷ የክፍያ ሥርዓት ያላት ቻይናን ጨምሮ በሌሎች ማዕቀብ ባልጣሉ አገሮች በኩል የመጠቀም እድል ስላላቸው ነው። ሩሲያ ስዊፍት እንድትታገድ የአሜሪካ የሕግ አውጪዎች ግፊት እያደረጉ ነው። ሆኖም ፕሬዝዳንት ባይደን ምርጫቸው ይህ ሳይሆን ሌሎች ማዕቀቦች ናቸው። ምክንያቱም ውሳኔው ሌሎች አገራትን እና ምጣኔ ሀብታቸውን ስለሚጎዳ ነው። እናም ሩሲያ ከዚህ ሥርዓት እንድትታገድ የአውሮፓ አገራትን ድጋፋ ይፈልጋል። አገራቱ ደግሞ ውሳኔው ራሳቸውን መልሶ የሚጎዳ በመሆኑ ብዙም ሊደፍሩት የሚፈልጉ አይመስሉም።", "የሳምሰንግ ትርፍ ከ50 በመቶ በላይ አሽቆለቆለ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አምራቹ ሳምሰንግ በሁለተኛው ሩብ ዓመት የምርቱ ትርፋማነት እንዳሽቆለቆለበትና ይህም ወደፊት ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አስታወቀ። • የአዲሱ ሳምሰንግ ጋላክሲ S9 በካሜራ ብቃት ላይ አተኩሯል •ሳምሰንግ እንደ መጽሐፍ የሚገለጥ ስልክ አመረተ የዓለማችን ትልቁ ዘመናዊ ስልኮችንና የኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን አምራቹ ኩባንያ- ሳምሰንግ እንዳለው ትርፋማነቱ ከዚህ ዓመት ቀድሞ ባለው የበጀት ዓመት በ56 በመቶ ቀንሷል። ለዚህም በአሜሪካና በቻይና መካከል እየተካሄደ ያለው የንግድ ጦርነት ምክንያት ነው ተብሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን አምራች ድርጅቱ በሶልና ቶክዮ ባለው የንግድ ወረፋ ምክንያት ችግር እያጋጠመው እንደሆነ ገልጿል። በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ድርጅቱ እስከ ሰኔ ወር ባሉት ሦስት ወራት የሥራ ማስኬጃን በመቀነስ ከሚገኝ ትርፍ 6.6 የኮሪያ ዋን (5.6 ቢሊየን ዶላር)፤ ባለፈው ዓመት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ትርፉ 14.87 የኮሪያ ዋን (12.6 ቢሊየን ዶላር) ጋር ሲነፃፀር፤ 56 በመቶ መቀነሱን አስታውቋል። ሳምሰንግ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በፍላጎት ደረጃ ትንሽ መሻሻሎች ቢታይም በምርቶቹ ላይ የገበያ ማጣትና የዋጋ ቅናሽ ግን ታይቷል። \"ኩባንያው እያጋጠመው ያለው ተግዳሮት በንግዱ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚክ ሁኔታ መለዋወጥም ተፈታትኖታል\" ብሏል በመግለጫው። ጃፓን በቅርቡ ወደ ውጭ የሚላኩ የኢንዱስትሪ ቁሳቁሶች፤ 'ሴሚ ኮንዳክተርስ' እና 'ስክሪኖች' ለመስራት የሚውሉ ምርቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ጀምራለች። ይህ እንቅስቃሴም ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጅ እቃዎች አቅርቦት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል በሚል አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል። በመሆኑም የሳምሰንግን የወደፊት የምርት አቅርቦት ሊፈታተነው እንደሚችል ተጠቁሟል። ኩባንያው በቅርቡ እንዳስተዋወቀው ተጣጣፊ ስልኩ፤ አዳዲስ ምርቶች ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ እና በሦስተኛው ሩብ ዓመት ላይ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። • ታጣፊው የሳምሰንግ ስልክ የ'ስክሪን' መሰበር ወቀሳ ቀረበበት ሳምሰንግ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አዲሱን ተጣጣፊ ስልኩ የስክሪን መሰበር ወቀሳ ካጋጠመው በኋላ ለገበያ ለማቅረብ እንደዘገየም አስታውሰዋል። በአዲሱ ስልኩ ላይ ያጋጠመው ችግር በድርጅቱ ላይ አመኔታን ያሳጣ ሲሆን ይህም የዘመናዊ ስልኮች ሽያጭ ለመቀነሱና ከቻይናው ሁዋዌ ጋር ካለው የንግድ ውድድር ላይ መጥፎ አሻራ እንዳሳረፈ ተገልጿል። ሳምሰንግ ተጣጣፊው ጋላክሲ ስልኩ ተሻሽሎ በመጭው መስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ ያስታወቀው ባለፈው ሳምንት ነበር።", "የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስካሁን አንድ ቢሊየን ዶላር ያህል ገቢ አጥቷል ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ላይ በተፈጠረው መስተጓጎል ሳቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳጣ ተገለጸ። የኮሮናቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ በአየር መንገዶች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ማምጣቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ይናገራሉ። ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራዎች መቆማቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ያንን ተከትሎ ደግሞ ከየካቲት እስከ ሰኔ መጨረሻ ድርጅቱ መንገደኛ በማጓጓዝ ሊያገኘው ይገባ የነበረው ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ሳያገኝ መቅረቱን ገልፀዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የዓለም አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ከቤቱ እንዳይወጣ ከተደረገ ወራት አልፈዋል። ይህ ማለት በአየር የሚደረግ ጉዞ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። ይህም በአየር መንገዶች ዓይን በሚታይበት ወቅት በአሁን ሰዓት ብዙ አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸውን አቁመዋል ይላሉ ይላሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው። \"የመንገደኛ በረራ ቆሟል። በኢትዮጵያ አየር መንገድም ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኞች አውሮፕላኖቻችን ቆመዋል።\" \"ይኼ ለአንድ አየር መንገድ እጅግ በጣም ትልቅ የፋይናንስ ቀውስ ነው የሚያመጣው። ይህም ምንም የሚካድ አይደለም እጅግ ተጎድተናል\" በማለትም የዚያን ያህል ደግሞ አየር መንገዱ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ የሚያኮራ ሥራ ሰርቷል ሲሉ ድርጅቱ የሰራቸውን ሥራዎች ዘርዝረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢበርም ባይበርም በወር አምስት ቢሊየን ብር ያወጣል ያሉት አቶ ተወልደ ከመጋቢት ወር ጀምሮ የመንገደኞች ጉዞ በሚቆምበት ጊዜ የድርጅቱን ቋሚ ወጪዎች ለመሸፈን፣ አውሮፕላን ለመግዛት የተበደርውን ብድር ከነወለዱ መመለስ ይተበቅበታል። በተጨማሪም አውሮፕላኖችን የተከራየንበት ወርሃዊ የኪራይ ወጪ ለመክፈል፣ እንዲሁም የሠራተኛ ደሞዝ፣ ጥቅማጥቅም፣ አበል፣ ለመሸፈን የሚያስችለውን \"በየወሩ አምስት ቢሊየን ብር በየወሩ እንዴት ነው የምናገኘው? ይህ ወረርሽኝ ከቀጠለስ ምን እናደርጋለን?\" በማለት መወያየታቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ ወቅት \"መጀመሪያ እድገት የነበረውን ስትራጂያችንን ወደ ሕልውና ማረጋገጥ ለወጥን\" በማለትም ከመንገደኛ ማጓጓዝ ባሻገር ያለውን እድል በመፈተሽ የጭነት አገልግሎት መስጠትን በወቅቱ ያገኙት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል። አየር መንገዱ በዚህ ረገድ አስር 777 በጭነት ትራንስፖርት ምርጥ የሚባሉ አውሮፕላኖች፣ በተጨማሪም ሁለት 737 አውሮፕላኖች ስላሉት፤ እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ቶን ማስተናገድ የሚችልና ከነሲንጋፖር ከነሆንክ ኮንግ ከነአምስተርዳም ጋር ሊወዳደር የሚችል በጣም ዘመናዊ የካርጎ ተርሚናል ስላለው ይህንን እንደ ዕድል መጠቀማቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዚያ ወቅት የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁሶች በጣም የሚፈለጉበት ጊዜ ነበር ያሉት አቶ ተወልደ ያለውን የገበያ ፍላጎት በመመልከት ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አፍሪካ በርካታ ጭነቶችን ማጓጓዛቸውን ያስረዳሉ። የድርጅቱ ገበያ እየጨመረ ሲመጣም ቁሳቁሶቹን በጭነት አውሮፕላኖች ብቻ ማንሳት ስላልተቻለ በፍጥነት የ25 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወንበራቸውን በማውጣት ወደ ወደ ካርጎ ማዞራቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን በማድረጋቸው የተገኙ ጥቅሞችን ሲገልጹም ሠራተኛ ከሥራ አለማሰናበታቸውን፣ የሠራተኛ ደሞዝ አለመቀነሱን እና ነጥቅማጥቅሙ መከፈሉን፣ ሶስተኛ ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ ከማንም አለመጠየቃቸውን ያነሳሉ። አክለውም ለጊዜው ሥራ ማስኬጃ የሚሆን ብድር አልወሰድንም፤ ብድራችንም እንዲራዘምልን አልጠየቅንም በማለት በኮቪድ-19 ወቅት በወሰዷቸው እርምጃዎች ያገኟቸውን ስኬቶች ይዘረዝራሉ። አየር መንገዱ ይህንን ሲያደርግ በዚህ በወረርሽኝ ጊዜ ህይወት የማትረፍ ሥራ መስራቱን ያነሳሉ። \"የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ስፔንን ረድቷል። የኮቪድ-19 መከላከያ እቃዎችን በማቅረብ። ያ ማለት ሕይወት አትርፈናል ማለት ነው።\" ፖርቹጋል፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ብራዚል እና አፍሪካ ሊደርስ ይችል የነበረውን ቀውስ መከላከል የሚያስችሉ የመከላከያ እቃዎችን ሕክምና መሳሪያዎችን በወቅቱ በማድረሳቸው ምክንያት አገሮችና ሕዝቦች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ክብርና ውለታ እንዳላቸውም ጠቅሰዋል። \"የጃክማ ፋውንዴሽን እርዳታን ከቻይና አምጥተን በስድስት ቀን ውስጥ አፍሪካ ውስጥ አከፋፍለናል\" ያሉት አቶ ተወልደ \"ፍጥነታችን በጣም ተደንቋል።\" ሲሉ የአፍሪካ አገሮችም የአሊባባ ፋውንዴሽንም በሥራው መደነቃቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን ተከትሎም የዓለም የምግብ ድርጅት አዲስ አበባን የተባበሩት መንግሥታት በሙሉ የሰብዓዊ እርዳታ ማከፋፈያ አድርጓታል ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ራሳችንን ጠቅመን፣ አየር መንገዱን አድነን፣ ሠራተኞቻችንን ሳንበትን፣ የሠራተኞቻችንን ደሞዝ ሳንቀንስ እና ሕይወት ማትረፍ በመቻላችን እንደ አንድ ዜጋ ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ለቫይረሱ ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስፈላጊውን የግንዛቤ መስጫ ትምህርቶችን በማድረግና ጥንቃቁዎችን በመውሰድ ወደ 17 ሺህ የሚጠጉ የድርጅቱ ሠራተኞች በጤና እንደሚገኙ ገልፀዋል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም አምስት ሠራተኞቹ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማስታወስ ሁሉም ማገገማቸውንና አሁን ደግሞ ባለፈው ሳምንት ሁለት ሠራተኞች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው በድርጅቱ ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ውስጥ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ሥራዎችን በአግባቡ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የገለፁት አቶ ተወልደ \"በረራ ባለማቋረጣችን ለዚህ ልምድ አግኝተናል\" ብለዋል።", "ዚምባብዌ የዋጋ ንረትን ለመግታት የወርቅ ሳንቲሞችን አስተዋወቀች የዚምባብዌ ማዕከላዊ ባንክ ከአገሪቱ ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ጋር ተደምሮ እየናረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመግታት የወርቅ ሳንቲሞችን በመገበያያነት ለመጠቀም ይፋ አድርጓል። የአገሪቱ ዓመታዊው የዋጋ ግሽበት ከ190 በመቶ በላይ ማደጉን ተከትሎ የማዕከላዊ ባንቡ በያዝነው ወር የወለድ ተመኑን ከእጥፍ በላይ በማሳደግ 200 በመቶ አድርሷል። እያንዳንዱ ሳንቲም በዓለም አቀፍ ገበያ አንድ አውንስ ወርቅ የሚኖረውን ዋጋ ብሎም 5 በመቶ ሳንቲሙን ለማምረት የወጣውን ተጨምሮ ያወጣል። ባሳለፍነው አርብ አንድ አውንስ ወርቅ 1,724 ዶላር ያወጣ ነበር። የዚምባብዌ ሪዘርቭ ባንክ ገዥ ጆን ማንጉዲያ እንዳሉት ሳንቲሞቹ የሚጠበቀውን ለውጥ ካመጡ በቀጣይ በሱቆች ውስጥ መጠቀም ሊጀመር ይችላል። ሳንቲሙ \"ሞሲ-ኦአ-ቱኒያ\" የሚል ጽሑፍ ያረፈበት ሲሆን ትርጉሙም \"የነጎድጓድ ጭስ\" ማለት ነው። ይህም በዚምባብዌ እና ዛምቢያ ድንበር ላይ የምትገኘውን ቪክቶሪያ ፏፏቴ የሚያመነጨውን ጭስ ያመለክታል። ለዓመታት ሲያሽቆለቁል የቆየው የዚምባብዌ ዶላር በዚህ ዓመት ከዋና ዋና ምንዛሬዎች አንጻር ዋጋው የበለጠ ወድቋል። አገሪቱ ለአራት አሥርት ዓመታት ያህል በሥልጣን ላይ በነበሩት ሟቹ ሮበርት ሙጋቤ የሥልጣን ዘመን መፈጠር የጀመረውን የኢኮኖሚ ቀውስ አሁንም ድረስ እያስተናገደች ትገኛለች። በዚሁ የዋጋ ግሽበት ምክንያት እአአ በ2009 የዚምባብዌ ዶላርን ለመገበያያነት ላለመጠቀም ተገዳለች። በምትኩ የውጭ ምንዛሬዎችን በተለይም የአሜሪካን ዶላር በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል። የአገር ውስጥ ምንዛሪ ከአሥር ዓመታት በኋላ እንደገና ወደ ሥራ ገብቷል። ነገር ግን በፍጥነት ዋጋውን እንደገና አጥቷል።", "ቢትኮይንን ለሁሉም አገልግሎትና ግብይት የምትጠቀመው አገር የቢትኮይን ዋጋ ከሌላው ጊዜ በተለየ በእዚህ ሳምንት በጣም ቀንሷል። የኤል ሳቫዶር መንግሥት ግን ቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል። ይህንን ለማበረታታትም በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ነው። ይህ ውሳኔ ከተወሰነ ከ9 ወር ወዲህ መንግሥት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለቢትኮይን ፈሰስ አድርጓል። አሁን ደግሞ የውሻ ባለቤቶች በቢትኮይን የሚከፍሉ ከሆነ በጣም በርካሽ እንዲታከሙ አንድ ሆስፒታል አመቻችቷል።", "የአርሶ አደሮችን ሕይወት ለማቅለል ዘመናዊ ጎተራ የሠራችው ወጣት ደራርቱ ደረጀ በጅማ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ የባዮ ሜዲካል ትምህርት ክፍል መምህርት ናት። እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪዋን ባዮ ሜዲካል ኢሜጂንግ በሚባል የትምህርት ዘርፍ እየተማረች ሲሆን፣ ከትምህርቷ ጎን ለጎን ፈጠራዎች ላይ ተሰማርታለች። ከሥራዎቿ መካከል አንዱ የሆነው ደግሞ አርሶ አደሮችን መሠረት በማድረግ የሠራችው ዘመናዊ ጎተራ ነው። \"ገበሬዎቻችን የሚጠቀሙበት ጎተራ ከጭቃ አልያም ከአፈር ስለሚሠራ የታፈነ ነው። በዚህም ምክንያት እህሉ በነቀዝ እንዲበላ ይሆናል\" ትላለች ደራርቱ። ደራርቱ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበት ባሕላዊው ጎተራ ምርታቸውን እንዲባክን ያደርጋል በማለት፣ ይህ ችግርም የከፋ እና ገበሬዎቹን ለምግብ ዋስትና እጥረት የሚያጋልጥ ነው ትላለች። የዓለም የምግብ ድርጅት፣ እያደጉ ባሉ አገራት ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከየሚያመርቱት ምርት፣ 40 እጅ ያህሉ ከማጠራቀሚያ ቦታ እጥረት የተነሳ እንደሚባክን ይገልጻል። አስተማማኝ የእህል ማጠራቀሚያ አለመኖር ደግሞ አርሶ አደሮች ጉልበት እና ጊዜያቸውን የፈጁበት ምርት በተባይ እንዲበላ እና በእርጥበት ምክንያት ለብልሽት እንዲጋለጥ ያደርጋል። ይህ የእህል ብክነትም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን ለምግብ ዋስትና ችግር እንዲጋለጡ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ቀዳሚው ነው። ብዙ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበት ጎተራ ከእንጨት እና ከጭቃ የተሰራ መሆኑን የምትናገረው ደራርቱ \"ብዙ አርሶ አደሮች ይቸገራሉ። እህላቸውን ነቀዝ ይበላዋል\" ትላለች ደራርቱ። የምርት ማከማቻው አሰራር ነፍሳት ወደ ጎተራው በቀላሉ በመግባት እህል ውስጥ እንዲራቡ እንደሚያደርገቸውም ታስረዳለች። በተጨማሪም ይህ በባህላዊ መንገድ የሚሠራ ጎተራ፣ እንደ ልብ አየር ስለማይዘዋወርበት በውስጡ ያለው ሙቀት እንደ ነቀዝ ላሉ ነፍሳት መራቢያነት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። \"የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሁን እየተጠቀሙበት ያለው ጎተራ፣ ነፍሳት ውስጥ ገብተው በቀላሉ እህሉን እንዲያበላሹት ያስችላቸዋል። ስለዚህም ገበሬዎቹ ከሚያመርቱት 44.7 በመቶ ያህሉ በዚህ ሁኔታ ይባክናል\" ስትል ታስረዳለች። ዘመናዊው ጎተራ ደራርቱ ይህንን የአርሶ አደሮች ችግር መሠረት በማድረግ አልሙኒየም በመጠቀም ዘመናዊ ጎተራ መስራቷን ትናገራለች። ይህ ከአልሙኒየም የተሰራው ጎተራ ነፍሳት ወደ ጎተራው በቀላሉ እንዳይገቡ የሚከላከል መሆኑንም ታስረዳለች። ይህ ጎተራ \"አየር እንዲያስገባ ሆኖ ነው የተሰራው። ይህም ጎተራ ውስጥ ሙቀት እነዳይፈጠር ይረዳል። ነፍሳት ወደ ጎተራው ቢገቡ እንኳ ቶሎ እንዲሞቱ ያደርጋቸዋል\" በማለት ታስረዳለች። አየር ወደ ጎተራው እንዲገባ የሚያደርገው መላ የባትሪ ኃይልን በመጠቀም የተሰራ ነው። \"ለወደፊቱ ግን የፀሐይ ብርሃንን በመጠቀም እንዲሰራ ለማድረግ እያሰብን ነው\" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ደራርቱ የሠራችው ይህ ዘመናዊ ጎተራ አነስተኛ የሚባለው እስከ 50 ኪሎ መያዝ የሚችል ሲሆን፣ በሰዎች ፍላጎት ላይ በመመስረት ትልልቅ ጎተራዎችን መስራት ይቻላል። ደራርቱ ይህንን ጎተራ ለመስራት ወጪውን ራሷ መሸፈኗን ገልጻ፣ በሥራው ላይ ግን የሚያማክራት ሰው እንዳለ ትናገራለች። በሌላ በኩል ይህ ፕሮጀክት በተፈለገበት መልኩ ሥራ ላይ እንዳይውል እንቅፋት የሆነባት የገንዘብ ችግር መሆኑን በማንሳትም፣ ይህንን ለመቅረፍ የተለያዩ ውድድሮች ላይ እየተሳተፈች ነው። በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት 'ቶታል ኢነርጂስ ስታርት አፐር' የሚባል ውድድር ላይ የመጀመሪያውን ዙር ማለፏን ትገልጻለች። \"አሁን ማነቆ የሆነብን የገንዘብ እጥረት ነው። ይህንን ውድድር ካለፍን በቀላሉ ገበሬዎቻችን ጋር መድረስ እንችላለን\" ብላለች ደራርቱ።", "ቤይሩት ውስጥ በመሳሪያ አስገድዶ ገንዘቡን ከባንክ የወሰደው ጀግና ተባለ መሳሪያ ታጥቆ ከቁጠባ ሂሳቡ ገንዘቡ እንዲሰጠው ያስገደደው የሊባኖስ ዜጋ በሕዝቡ ጀግና ተብሎ ተወደሰ። ሊባኖስ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ባንኮች ደንበኞቻቸው ወጪ በሚያደርጉት ገንዘብ ላይ ገደብ ጥላለች። ይህ ግለሰብ ግን መሳሪያ ታጥቆና ባንክ ውስጥ ነዳጅ አርከፍክፎ ለሆስፒታል ክፍያ ለመፈጸም የሚያስፈልገው ገንዘቡ እንዲሰጠው በኃይል መጠየቁን ኤኤፍፒ ዘግቧል። በግለሰቡ እና በባንኩ መካከል ለስድስት ሰዓታት ከቆየ ፍጥጫ በኋላ ግለሰቡ የጠየቀውን ገንዘብ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ማግኘት ችሏል። ይህ በስም ያልተጠቀው ግለሰብ ተግባርም በሕዝቡ ዘንድ አድናቆትን አስገኝቶለታል። ከባንኩ ውጪ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች “ጀግና ነህ” እያሉ ጠርተውታል። የግለሰቡ ወንድም ለጋዜጠኞች ሲናገር፤ “ወንድሜ በባንክ ሂሳቡ 210ሺህ ዶላር አለው። የሆስፒታል ወጪውን ለመሸፈን 5ሺህ 500 ዶላር ፈልጎ ነበር” ብሏል። ከባንኩ ውጪ የነበሩት የግለሰቡ ወንድም እና ባለቤት፤ “ሁሉም ሰው ሊያደርገው የሚገባው ይሄን ነው። የራሳቸው የሆነውን ማግኘት አለባቸው\" ብለዋል። ኤልቢሲ የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ የግለሰቡ ቤተሰብ አባላት በሆስፒታል እንደሚገኙ እና ገንዘብ እጅጉን ያስፈልጋቸው እንደነበር ዘግቧል። የቴሌቪዥን ጣቢያው ጨምሮ እንደዘገበው ወደ ባንኩ በኃይል ከገባው ግለሰብ ጋር ድርድር ከተደረገ በኋላ ከቁጠባ ሂሳቡ 35ሺህ ዶላር ተሰጥቶታል። ፖሊስ ግለሰቡን እና በእገታ ስር የቆዩ የባንክ ሠራተኞችን ከአካባቢው ይዞ የወጣ ሲሆን በግለሰቡ ላይ ክስ ይመሰረት እንደሆነ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። እአአ 2019 ላይ ሊባኖስ የገጠማትን ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ለመቋቋም ያስችለኛል ብላ ተግባራዊ ካደረገቻቸው ውሳኔዎች መካከል ሰዎች ከቁጠባ ሂሳባቸው ወጪ በሚያደርጉት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ መጣል ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከአገር ውጪ በሚላክ የገንዘብ መጠን ላይም ገደብ ተጥሏል። ይሁን እንጂ እነዚህ ክልከላዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። በሊባኖስ የተከሰተው ምጣሄ ሃብታዊ ቀውስ የአገሪቱ ገንዘብ ዋጋውን ከ90 በመቶ በላይ እንዲያጣ አድርጎታል። የዋጋ ግሽበት ጣሪያ ነክቷል፤ እንደ መድሃኒት እና ስንዴ ባሉ ምርቶች ላይ እጥረት አጋጥሟል። የተባበሩት መንግሥታት ከአምስት ሊባኖሳዊያን አራቱ በድኅነት ውስጥ ይኖራሉ ይላል።", "ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳሳወቀው ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከ95% በላይ የሚሆነው የአንድ ሺ ሺልንግ ተመልሶ በአዲሱ ተተክቷል። በዚህ መካከል ግን መሃል ላይ ተንሳፎ የቀረ ገንዘብ እንዳለም ተገልጿል። \"ይህ ማለት 7.3 ቢሊዮን ሺልንግ ጥቅም አልባ ሆኗል፤ እንደ ወረቀት ነው የሚቆጠረው\" በማለት የባንኩ አስተዳዳሪ ፓትሪክ እንጆሮጌ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። •የኢትዮጵያ ሙዚቃ- ከመስከረም እስከ መስከረም •ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ባንኩ እንዳሳወቀው አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን ከዚያ ዕለትም ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረ 217 ሚሊዮን ሽልንግም ተገኝቷል። ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በዚህ ወቅትም ከሶስት ሺ የሚበልጡ አጠራጣሪ ልውውጦች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን በሚመለከተው የመንግሥት አካልም ምርምራ እንደሚደረግም ኢንጆሮጌ አክለው ገልፀዋል። የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል ነው። •ኬንያ ሳንቲሞቿ ላይ የነበሩ መሪዎችን በእንስሳት ቀየረች አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው።", "\"ለ15 ዓመታት ኮንዶሚኒየም እየጠበቅኩ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ\" የአዲስ አበባ ነዋሪ \"ለ15 ዓመታት ኮንዶሚኒየም እየጠበቅኩ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ\" ይህ የተሰማው ስሜ አይጠቀስ ካሉ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው። ቤት የመኖር ተስፋቸውን ሰንቀው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ይደርሰኛል ብለው የተመዘገቡት በ1997 ዓ.ም ነበር። የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሰጣቸው በማህበር ተደራጅተው ከተመዘገቡት የመጀመሪያው ዙር ተመዝጋቢም መካከል ናቸው። ለአስራ አምስት ዓመታትም ያህል ቤት ይደርሰኛል ብለው ጠብቀዋል። በእርሳቸው ማህበር ውስጥ ከሚገኙት ከሃያ አባላቱ በላይ በሙሉ የቤት ባለቤት ቢሆኑም እርሳቸው ግን አልደረሳቸውም። ከእርሳቸው የሚጠበቅባቸውን በየወሩ ምንም ሳያዛንፉ ከመቆጠባቸውም አንፃር ለምን አልደረሰኝም ብለው ሲያስቡም የሚሰጡት ምክንያት \"ዕጣው ፍትሃዊ ስላልሆነ ነው\" የሚል ነው። \"በመተዋወቅና በመጠቃቀም ቢሆን ነው እንጂ ይህንን ያህል ዓመት ጠብቄ የማይደርሰኝ ምክንያት የለውም\" ይላሉ። ከዚያም በተጨማሪ ያልተመዘገቡ ሰዎች ቤት እየተሰጣቸው እንደሆነም ሲሰሙ ይህንኑ ጥርጣሬያቸውን አረጋገጠላቸው። ሆኖም ለዓመታትም ቤት ይኖረኛል በሚል ተስፋም የቆጠቡትን ብር ሊነኩም አልፈለጉም \"ለሌላ ነገር እንዳላደርገው ሁሉ ይዞኛል\" ይላሉ። ሲመዘገቡ ገና ወንደላጤ ነበሩ አሁን ሁሉ ተቀይሮ ትዳር ይዘዋል። የሁለት ልጆች አባት ሆነዋል፤ ሆኖም የተመዘገቡት ኮንዶሚኒየም የውሃ ሽታ በመሆኑ \"ላም አለኝ በሰማይ...\" ሆኖባቸዋል። ለአመታትም የኮንዶሚኒየም ዕጣ ሲወጣ በጉጉት ይጠብቃሉ። ይከታተላሉ ግን አልሆነም። የሚያውቋቸው ሰዎች ቤት አግኝተው ሳይኖሩበት ወይ ሲሸጡት ሲያዩ እርሳቸው በኪራይ ቤት መንከራተት ያሳዝናቸዋል። በተከታታይም ቤቶች ልማት ሄደው ሲጠይቁም የተመዝጋቢዎች ዝርዝር ውስጥ እንዳሉ ይነግሯቸዋል። \"ሌሎች ሰዎች እየደረሳቸው ነው እንዴት ነው ነገሩ ብለን ስንጠይቅም 'ያው ስምህ አለ'\" ከማለት ውጭ ሌላ ምላሽ ለዓመታት አልተሰጣቸውም። \"ጠብቅ\" የሚለውም ምላሽ ተስፋ እያስቆረጣቸው እንደመጣ የሚናገሩት እኚህ ግለሰብ፤ ከሰሞኑ ደግሞ ከህገወጥ መሬት ወረራና ኢ-ፍትሃዊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ ጋር ተያይዞ በሚሰሙ መረጃዎች የነበረቻቸውም ትንሽ ተስፋ ተሟጠጠች። \"በጣም ያሳዝናል፤ ያሳፍራል፤ ከዚህ በኋላ ተስፋ አላደርግም\" ይላሉ። ቤት (መጠለያ) መሰረታዊ ጥያቄና መብት ቢሆንም በኢትዮጵያ ባሉ ትልልቅ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ሰዎች የግል ቤት መኖር ማለት እንደ ቅንጦት የሚታይበት ነው። በርካቶች በማይቀመስ ኪራይ ብራቸውን እየገፈገፉ ለመኖርም ተገደዋል። ገዝቶ የቤት ባለቤት መሆን የሚታሰብ ባይሆንም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የጥራትና ሌሎች ጉድለቶች ቢኖርባቸውም፤ ለብዙዎች የቤት ባለቤት የመሆን ተስፋቸው ሆኖ ቆይተዋል። ሆኖም ለዓመታት ጠብቀው ቤት ሳያገኙ የቀሩ እንዲሁም ቤቱ ደርሷቸው ያልተቀበሉ በርካቶች አሉ። ሌላኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ በ40/60 የቁጠባ ፕሮጀክት ተመዝግበው በሁለተኛው ዙር የቤት እጣ እድለኛ እንደሆኑ ተነገሯቸው። ከስድስት ዓመታት በፊት ተመዝግበው ዕጣው ወጥቶ ቤቱ ከደረሳቸው በኋላ፤ በድልድሉ መሰረት ውል ቢዋዋሉም ቤቱን ሳይረከቡ አንድ ዓመት አለፋቸው። ሙሉውን መክፈል የሚችሉ መቶ በመቶ እንዲከፍሉ ካለበለዚያ ደግሞ በወጣው እቅድ መሰረት አርባ በመቶ ከፍለው ቀሪውን ደግሞ ከባንክ ጋር ውል ተፈፅሞ ቤታቸውን እንዲረከቡ ነበር። የዛሬ ዓመትም የሚጠበቅባቸውን አርባ በመቶ ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ቁልፍ ለመረከብና ከቤቶች ልማትም ቤታቸውን ሊረከቡ የደረሳቸው ነገርም የለም። በቅርቡ እንዲሁ እጣ የደረሳቸው ሰዎች በማህበር ሲደራጁ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲነገሩም ቤቱ አልቋልና ተረከቡ ተብለው ወደደረሳቸው አካባቢ ሄዱ። በሁለተኛው ዙር 18 ሺህ ያህል እድለኞች መኖራቸውን የሚናገሩት እኚሁ ግለሰብ \"ልንረከብ ሄደን ቤቱ አላለቀም፤ ቁልፍ ልንረከብ ሄደን ጭራሽ ቤቱ በር የለውም፤ ይሄ እንዴት ይሆናል? የማይሆን ሥራ ነው እየሰሩብን ያሉት\" ብለዋል። የአያት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት እኚሁ ግለሰብ በሚኖሩበት አካባቢ የሚገኙ መሬቶች በአስደናቂ ፍጥነት መታጠራቸው ጥያቄያቸውን አጭሮታል። በሳምንቱ መጀመሪያ፣ ሰኞ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተባባሰ የመጣ፣ የመንግሥታዊ መዋቅሮች ድጋፍ ያለው ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ እንዳለ ባካሄድኩት ጥናት ደርሼበታለሁ ሲል ማስታወቁ ይታወሳል። የጋራ ቤቶችን በተመለከተም የከተማው አስተዳደር ባወጣው ደንብ መሰረት \"በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤትና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል\" ሲል በጋራ የመኖሪያ ቤቶች በኩል አሉ ያላቸውን የአሰራር ችግሮች ጠቅሷል። ጥናቱ እንዳለው በከተማዋ የተለያየ አይነት ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ ተግባራት እንደተከናወኑ አመልክቶ፤ እነዚህም በጅምር ቤት ስም ከባለ ይዞታዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በመግዛት ግንባታ የማካሔድ፣ ባዶ መሬቶችን በቡድንና በግለሰብ ደረጃ በማጠር የመያዝ እንዲሁም ለሌላ ወገን የማስተላለፍ በተጨማሪም \"በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተዘረጋው ሰንሰለት በጥቅም ተጋሪነትና በዝምድና\" ሠፋፊና ቁልፍ ቦታዎችን መያዝ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን ገልጿል። የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የአሁኑ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በበኩላቸው፤ በቀጥታ የኢዜማን ጥናት ባይጠቅሱም ማክሰኞ ዕለት በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በሰጡት ምላሽ የቀረበውን ሪፖርት \" ሐሰተኛ\" ብለውታል። አቶ ታከለ እንዳሰፈሩት \"የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው\" ብለዋል።", "ፈረንሳዊው ቢሊየነር በፓሪስ ተደብድበው ተዘረፉ የፈረንሳዩ ቢሊየነር በርናንድ ታፒ በፓሪስ ኩምላቪል መኖርያ ቤታቸው ውስጥ ሳሉ ነው ዘራፊዎች ገብተው የደበደቧቸው፡፡ ባለቤታቸውም ክፉኛ ተጎድተዋል፡፡ ቢሊየነሩ በርናንድ ታፒ የዝነኛው የአዲዳስ የስፖርት ትጥቅ አምራች የቀድሞ ባለቤት ናቸው፡፡ የቢሊየነሩን ቤት የደፈሩት ዘራፊዎች ቁጥርና ማንነት እስከአሁን አልታወቀም፡፡ ዘራፊዎቹ ቢሊየነሩን በርናንድ ታፒ እና ባለቤታቸው ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ቀስቅሰው በኤሌክትሪክ ገመድ ካሰሯቸው በኋላ ነበር ጠቀም ያለ ገንዘብ ለመዝረፍ የሞከሩት፡፡ ሆኖም በቢሊየነሩ ቤት እምብዛምም የፈለጉትን አላገኙም፡፡ የታፒንና ባለቤታቸውን የወርቅ ጌጣጌጦች ግን ሰብስበው ወስደዋል፡፡ የ78 ዓመቱ በርናንድ ታፒ በፈረንሳይ አወዛጋቢ ባለሀብትና ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ ሽቅርቅርና ሁሌም የሚዲያ መነጋገርያ መሆን የሚወዱት ታፒ ከዚህ ቀደም ሚኒስትር ነበሩ፡፡ በተለይ ዝነኛውን የአዲዳስ ኩባንያን ከመሸጣቸው ጋር ተያይዞ ስማቸው በሙስና ተደጋግሞ ይነሳል፡፡ የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ዶሚኒክ እና ቢሊየነሩ በርናንድ ታፒ ሌሊት 6 ሰዓት ተኩል ግድም በተኙበት ነው ቢያንስ ከ4 በላይ የሆኑ ዘራፊዎች የቤታቸውን አጥርና የጥበቃ ሰንሰለቱን አልፈው በመግባት በቁጥጥር ያዋሏቸው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ሌሊት ነው፡፡ ዘራፊዎቹ ቢሊየነሩን በርናንድን ጸጉራቸውን ይዘው መሬት ለመሬት እየጎተቱ ከወሰዷቸው በኋላ ውድ ጌጣጌጦችንና የሚያስቀምጡበትን ቦታ እንዲጠቁሟቸው ሞክረዋል፡፡ ሆኖም ቤት ያስቀመጡት እዚህ ግባ የሚባል ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ ንብረት ባለመኖሩ ዘራፊዎቹ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸው ተነግሯል፡፡ በዚህ ብስጭትም ቢሊየነሩን በዱላ ነርተዋቸዋል፡፡ በዚህ መሀል የ70 ዓመት ባለቤታቸው ወ/ሮ ዶሞኒክ ዘራፊዎቹን አምልጠው ለጎረቤት ቤታቸው እየተዘረፈ መሆኑን በማሳወቃቸው ፖሊስ ደርሶ አድኗቸዋል፡፡ ባለቤታቸው በዘራፊዎቹ ክፉኛ በመደብደባቸው አሁን ሆስፒታል ነው የሚገኙት፡፡ ሌቦቹ እስከ አሁን ወሰዱ የተባለው 2 ውድ ሮሌክስ የእጅ ሰዓቶችን፣ የጆሮ ጌጦችን፣ የእጅ አምባሮችን እና ቀለበቶችን ብቻ ነው፡፡ ቢሊየነሩ በርናንድ ታፒ ከ1992 እስከ 93 የፈረንሳይ የከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ነበሩ፡፡ የታዋቂው የስፖርት ቁሳቁስ አምራች አዲዳስ ከፍተኛ የአክስዮን ባለቤት ነበሩ፡፡ በኋላ ደግሞ የዝነኛው የኦሎምፒክ ዴ ማርሴይ የእግር ኳስ ቡድን ባለቤት ሆነዋል፡፡ ላ ፕሮቬንሴና ሌሎች በርካታ ሚዲያዎችንን በባለቤትነት አስተዳድረዋል፡፡ እሳቸውም ቢሆን በመተወን፣ በመዝፈን እና የራዲዮና የቴሌቪዥን ትዕይነት በማሰናዳት ዝነኛ ነበሩ፡፡ በ1990ዎቹ ኩባንያቸው ኪሳራ በማወጁ ከሒሳብ ማጭበርበር፣ ከግብር ስወራና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተከሰው 5 ወራት እስር አሳልፈዋል፡፡ በርናንድ ላለፉት 20 ዓመታት በፍርድ ቤት ከአዲዳስ ኩባንያ ሽያጭ ጋር በተያያዘ እየተካሰሱ ይገኛሉ፡፡ ኩባንያውን በወቅቱ የሸጡት በግማሽ ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡", "የሲዳማ ቡና በኪሎ ለምን እስከ አርባ ሁለት ሺህ ብር ተሸጠ? ያለፉት ሦስት ዓመታት ለሲዳማ ቡና ‘ቡናማ’ ዓመታት ናቸው። ወርቃማ እንዳይባሉ ቡና ከወርቅም በላይ ነኝ ያለባቸው ዓመታት ናቸው። ከዚህ ጀርባ ደግሞ ሦስት ስሞች ቀድመው ወደ አዕምሮ ይመጣሉ። ንጉሤ ገመዳ፣ ታምሩ ታደሠ እና ለገሠ በጦሳ ናቸው። ሦስቱም የሲዳማ ቡናን ይዘው ለውድድር ቀርበው አላፈሩም። ይህ የቡና ውድድር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ይባላል። ውድድሩ ቡናን በጥራት ይለያል። ቀጥሎ በዓለም አቀፍ ጨረታ ለገበያ ያቀርባል። ንጉሴ አንድ ኪሎ ቡናውን በ407 ዶላር ሸጠዋል። የታምሩ ቡና ደግሞ 330 ዶላር ይገባዋል ተብሎ ዋጋ ተቆርጦለታል። የለገሠ ቡና ግን ከሁለቱም የላቀ ነው። አንዱ ኪሎ ቡና 884.10 ዶላር ተሽጧል። በዚህ ዋጋ የተሸጠ የኢትዮጵያ ቡና የለም። አንድ ኪሎ ቡና 47 ሺህ 236 ብር ተሽጧል። ስኬቱን ምስጋና “በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ዙሪያ ለተሠራው ሪፎርም” የሚሉት አቶ ምንዳዬ ምትኩ የሲዳማ ክልል ቡና ፍራፍሬ እና ቅመማ ቅመም ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው። ለአቶ ምንዳዬ ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ከውድድርም በላይ ነው። ‘አርሶ አደሮችንም ክልሉንም እየጠቀመ ያለ ውድድር ነው።’ መነቃቃት እና የሥራ ዕድልም ፈጥሯል። “አርሶ አደሮቹና አቅራቢዎች በቀጥታ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሠራር ተዘርግቷል። በዚህም የሲዳማ ክልል በጣም ተጠቃሚ ነው። ከሦስት ዓመት ወዲህ በቡና ላይ ለውጡ ትልቅ ነው” ይላሉ። እውነትም ለውጥማ አለ። በመጀመሪያው ዓመት ያሸነፈው አርሶ አደር አሁን ሌላ ህይወት እየመራ ነው። አርሶ አደር ከሚባለው ማዕረግ በተጨማሪ ላኪነትንም ደርቧል። “ቀደም ሲል አነስተኛ ካፒታል ነበረው። (ከውድድሩ) በኋላ ግን የላኪነት ፈቃድ አውጥቶ ወደ ላኪነት አድጎ ሸላሚም ሆኗል።” ይህ የአንድ ግለሰብ ብቻ ታሪክ ነው። ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸው ሰዎች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። “ይህ የክልሉ ሃብት ነው። ክልሉ ከእነዚህ ትልቅ ጥቅም ያገኛል፤ ገቢው ያድጋል። አርሶ አደሮቹ ህይወት ሲለወጥ ገበያውም ይነቃቃል። የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያለውን ትልቅ ችግር ይፈታል” የአቶ ምንዳዬ ሃሳብ ነው። ይህንን የሰሙ ‘እኛስ?’ ያሉበት ነው። በዚህ ዓመት ውድድርም በርካቶች ተሳትፈዋል። በዚህ ዓመት ደግሞ አርሶ አደሮች ብቻ እንዲያቀርቡ ተደርጓል። ባላቸው መሬት እና የመሬት ይዞታ አቅርበው እንዲወዳደሩ ነው የተደረገው። በዘንድሮው ውድድር አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡት የሲዳማ ቡናዎች ናቸው። “አንደኛ የወጣው ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ያገኘበት እጅግ በጣም አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የነበረ ሰው ነው።” ጥራታቸውም ቢሆን ምርጥ ነበር። የአቶ ምንዳዬ “ዘንድሮ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና ነው ያቀረብነው። አርሶ አደሩም የጥራቱን ሁኔታ ያሻሻለበት እና ፊቱን ወደ ቡና ልማት ያዞረበት ነው” ብለዋል። ዘንድሮ ለፍጻሜ የደረሱ 40 ተወዳዳሪዎች ነበሩ። 14ቱ ደግሞ ከሲዳማ ክልል ናቸው። የሲዳማን ቡና ምን እንዲህ ተፈላጊ፣ ተመራጭ እና ውድ አደረገው? ትልቁ ነገር አየሩ ነው። “በጣም ውጤታማ እየሆኑ ያሉት ደጋማ አካባቢ ያሉ ቡናዎች ናቸው” ይላሉ አቶ ምንዳዬ። ሌላው ደግሞ ‘ኦርጋኒክ’ (ተፈጥሯዊ) ቡና መሆኑ ነው። ምንም ዓይነት ኬሚካል አይዞርበትም። “የጥላ ዛፍም አላቸው። የቡና ፓኬጅ መጠቀማቸውም ሌላው [ምክንያት] ነው። የአየሩ ሁኔታም የረዳን ይመስላኛል” ይላሉ አቶ ምንዳዬ ምክንያቱ ብዙ መሆኑን በመጥቀስ። በተለይ የደጋ አካባቢ ቡናዎች ተመራጭ ሆነዋል። አሁን ቡና ወደ ደጋማው ሲዳማ አካባቢ እየሰፋ ነው። እነ አርቤጎና፣ ቡራ፣ ደንሳ፣ አሮሬሳ አካባቢዎች ቡና ማለትስ የእናንተ ተብለዋል። “በሌሎችም አካባቢ ይስፋፋል የሚል እምነት አለን። እነ ቦና አካባቢም ይጠቀማሉ ብለን እናስባለን” ይላሉ አቶ ምንዳዬ። አስገራሚው ነገር እነዚህ ቦታዎች ከቡና ጋር አይተዋወቁም ነበር። ለምሳሌ የዘንድሮው አሸናፊ ለገሠ በጦሳ ነዋሪነቱ አርቤጎና ወረዳ ቡርሳ ቀበሌ ነው። አርቤጎና አካባቢ በጣም ደጋማ አካባቢ ነው። አልቲቲዩዱም በጣም ከፍተኛ ነው። “አሁን ግን [በእነዚህ ቦታዎች] ከፍተኛ መነቃቃት ነው ያለው።” ቀደም ሲል እንሰት፣ ስንዴ እና ገብስ ያመርቱ ነበር። ጊዜ ሲቀየር እነሱም ተቀየሩ። ጊዜው ሲቀየር የሚያመርቱትም ተቀይሯል። “የኤክስቴንሽን ድጋፍ ይደረጋል። የቡና ፓኬጅ እንዲጠቀሙ ይደረጋል። ያረጁ ቡናዎች የመተከታት ሥራ ይከናወናል። ለባለሙያዎችም የስልጠና ድጋፍ እንሰጣለን። በተራው ባለሙያው እስከ ታች ወርዶ ይደግፋል። የተሻሻሉ ቡናዎች እንዲያመርቱ የበሽታ መከላከል ስራዎችን በተመለከተ ስልጠና፣ ክትትል እና ድጋፍ ይደረጋል” የአቶ ምንዳዬ ሃሳብ ነው። ቢቢሲ፡ እርስዎ ቡና ይጠጣሉ? አቶ ምንዳዬ፡ እኔ በጣም ቡና የምወድ ሰው ነኝ ቢቢሲ፡ ሌላ ቦታም ሄደው ቡና ይጠጣሉ? አቶ ምንዳዬ፡ [ሳቅ] ሌላ ቦታም ቡና እጠጣለሁ ቢቢሲ፡ እና የሲዳማ ቡና ከሌሎች በምን ይለያል? አቶ ምንዳዬ፡ ስለለመድኩት መሰለኝ የሲዳማ ቡና ይለያል። የቅመም ጣዕም አለው። በዚህ በኩል የራሱ ባህሪ አለው። የሲዳማ ቡና መጠጣት ከለመድክ ከፍተኛ ሱስ ነው የሚያሲዝህ። በቀን ቢያንስ 3 ስኒ ቡና ሳልጠጣ አልውልም። ሌላም ቦታ ስሄድ እጠጣለሁ። ብዙ ምርጥ ምርጥ ቡናዎች አሉን። የይረጋጨፌ ቡናም በጣም እወዳለሁ። በአጠቃላይ ቡና እጠጣለሁ። የሲዳማ ቡና ጥሩ ስሙ የገነነ ነው። ዕውቅናው እንዲጎለበት ከክልል እስከ ፌደራል ድረስ እየተሠራ መሆኑ ተነግሮናል። በአንድ ወቅት የቡና ዋጋ ወረደ። አርሶ አደሮች ቁጭ ብለው እንዲያስቡ ያደረገ የዋጋ መውረድ ነበር። በምን ልተካው ሲሉ ወደ አዕምሯቸው ሽው ያለላቸው ጫት ነበር። ጫት ቡናን እግር በእግር ተካ። ግን አልዘለቀበትም። አሁን ደግሞ ቀኝ ኋላ ነው ጉዞው። ቡና ግዛቴን አላስደፍርም አለ። “ጫት እና ባህር ዛፍ እየነቀሉ ወደ ቡና እየቀየሩ ያሉ በርካታ አርሶ አደሮች አሉ” ይላሉ አቶ ምንዳዬ። ከአንድ ኪሎ ቡና በአርባ ሺህዎች ከታፈሰ ጫት ለምኔ ነው ነገሩ። “ከዋጋውጋር ተያይዞ የመጣ [ለውጥ] ነው።” “ቀደም ሲል የልፋታቸውን አያገኙም ነበር። ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ሰንሰለቱ ብዙ እና አስቸጋሪ ዘርፍ ነበር። [አርሶ አደሩ] ካመረተው የጉልበቱን ዋጋ እያገኘ ባለመሆኑ ወደ ሌሎች ሰብሎች እየገባ ነበር። አሁን ከተሻሻለ በኋላ ነው ወደ ቡና የገባው።“ “[አሁንም] ዓለም ላይ ካለው ዋጋ አንጻርም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሚ ነው ማለት አይቻልም” የአቶ ምንዳ ሃሳብ ነው። እንደካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ያሉት ለገበያው መሻሻል ትልቅ ጥቅም እየሰጡ ነው። ለዚህ ለውጥ ደግሞ ከቡናና ሻይ ባለስልጣን ጀምሮ የተዘረጋውን አሠራር በምክንያትነት ያቀርባሉ። ሁለት እና ከዚያ በላይ ሄክታር ያላቸው አርሶ አደሮች ቡናቸውን በተገቢው አዘጋጅተው ወደ ውጭ መላክ ይችላሉ። “የምርት እና ምርታማነት ማሻሻል ላይ ይሠራል። ከግብይት ስርዓቱ ህገወጦችን የመከላከል ስራዎችም ይሠራል። ይህን የሚከላከል ግብረ ሃይልም አለ። ሌላው ደግሞ የግብዓት አቅርቦት ነው። በዚህ በኩልም ማሻሻል አለ።” “የሲዳማ ቡና አልን እንጂ የኢትዮጵያ ቡና ማለት ነው። ቀደም ሲል መዳረሻ ያልነበሩ አካባቢዎችም የኢትዮጵያን ቡና ይፈልጋሉ። እንደ ክልል ስንጠቀም እንደሃገርም እንጠቀማለን። በክልል ደረጃም ቢሆን ከፕሬዝዳንቱ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ በዚህ ልክ ይሠራል።“ ቡና ተተክሎ ምርት ለመስጠት ሦስት ዓመት ይጠይቃል። ቡና እየሰጠ 15 እስከ 18 ዓመት ይቆያል። ከዓመታት በኋላል እርጅና ሲጫነው መታደስ ይፈልጋል። ካልሆነ ምርት ይቀንሳል። ቡና ይህን ሁሉ አልፎ ነው ለገበያ የሚቀርበው። የካፕ ኦፍ ኤክሰለን ‘አውራ ፓርቲ’ ሆነናል የሚሉት አቶ ምንዳዬ ሦስቱንም ዓመት “የፕሬዚዳንሺያል ሽልማት” ማግኘታቸውን አንስተው በቀጣይም ማንም አይነቀንቀንም ይላሉ። “ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ መመልከት የለም። የክልሉም ፕሬዝዳንተ የሚመሩት ስለሆነ ከላይ እስከታች በትኩረት ስለሚሰራ ከዚህ በላይ መስራት እችላለን” ነው መልሳቸው እንዴት ተብለው ሲጠየቁ።", "\"በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ፈርተው ዛሬ መደብር አልከፈቱም\" የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ በአገሪቱ ሰላማዊ ሰልፎችና ነውጥ መቀስቀሱን ተከትሎ በጆሀንስበርግ የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ መደብራቸውን ዘግተው እንደዋሉ በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ለቢቢሲ ተናገሩ። በንግድ ሥራ የተሰማራው ዳዊት ተወልደመድኅን፤ በጆሀንስበርግ በተለይም ጂፒ ጎዳና እና ብሪ ጎዳና በሚባሉት አካባቢዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ፈርተው ዛሬ ሐምሌ 5/2013 ዓ.ም. መደብራቸውን ዘግተው ለመዋል መገደዳቸውን ተናግሯል። ትላንት ሐምሌ 4/2013 ዓ.ም. በዚያው አካባቢ በተነሳው ነውጥ የኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ስደተኞች መደብሮች ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ፖሊስ እንደተከላከለ ዳዊት ይናገራል። በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት ኢትዮጵያ ማኅበሰረብ ማኅበር ዋና አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆነው ንጉሥ ተመስገን እንደሚናገረው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን፣ ፓኪስታናውያን እንዲሁም ሌሎችም የሚነግዱበት አካባቢ ዛሬ ተዘግቶ ውሏል። \"ኒውካስል አካባቢ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከባድ ግን አይደለም። ዛሬ ሶዌቶ አካባቢ አመጽ ስላለ በንግድ የተሰማራው የሀበሻው ማኅበረሰብ ሱቁን ዘግቷል። ደርባን ትላንት ሌሊት ሲዘረፍ፣ መኪና ሲቀጠል ነበር\" ይላል። ከኢትዮጵያውን ማኅበረሰብ እና ከፖሊስ በተገኘው መረጃ መሠረት ከባድ የሚባል ጉዳት እስካሁን እንዳልደረሰ ያክላል። \"ትላንት የስደተኞች መደብሮች ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ እንደሆነ ኢትዮጵያውን ሲሰሙ ተሰብስበው ወደ ጂፒ ስትሪት ሄደው ሱቆቻቸውን ተከላከሉ። ፖሊሶችም ሀበሾችን ሲረዱ ነበር። ኢትዮጵያውያኑ ተሰብስበው ባይሄዱ ኖሮ የከፋ ነገር ይፈጠር ነበር\" ይላል ነጋዴው ዳዊት። በተለይም ጆሀንስበርግ ውስጥ ረብሻ ሲነሳ ጥቃት የሚሰነዘረው ስደተኞች እንዲሁም የንግድ ተቋሞቻቸው ላይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ታይቷል። የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ጃኮብ ዙማ በሥልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል የተባሉ የሙስና ጉዳዮች እየተመለከተ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተጠይቀው ሳይገኙ በመቅረታቸው ፍርድ ቤትን በመድፈር ጥፋተኛ ተብለው የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል። የጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ የሆኑ ደቡብ አፍሪካውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት አደባባይ መውጣት የጀመሩት ጃኮብ ዙማ እጃቸውን ለፖሊስ ከሰጡ በኋላ ነው። ከዚህ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በተነሳው ነውጥ ሕንጻዎች እና ተሽከርካሪዎች ወድመዋል። መደብሮችም ተቃጥለዋል። ግርግር፣ ዝርፊያና ንብረት ማቃጠል ጆሃንስበርግ ውስጥ በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት ወ/ሮ መዓዛ ተስፋዬ እንደተናገሩት ረብሻው መቀስቀሱን ተከትሎ በጣም አሳሳቢ እና አስፈሪ ሁኔታ ተከስቷል። ግርግር፣ ዝርፊያና ንብረት የማቃጠል ድርጊት በየቦታው እንደነበርና መንገዶችም በተቃዋሚዎቹ በሚቃጠሉ ጎማዎች ተዘግተው እንደነበር ገልጸዋል። ተቃውሞው በጃኮብ ዙማ መታሰር የተቀሰቀሰ ይሁን እንጂ ቢቢሲ ያናጋራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት፤ ከተቃውሞው ባሻገር በተለያዩ ስፍራዎች ዝርፊያዎችና የንብረት ውድመት ተፈጽሟል። በተለይ የንግድ ሱቆች የተቃዋሚዎቹ የጥቃት ኢላማ በመሆናቸው በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ሱቆቻቸውን ዘግተው ቤታቸው ተቀምጠዋል። ረብሻው እሳቸው በሚኖሩበት ጆሃንስበርግና ደርባን ከተሞች ውስጥ የበረታ መሆኑን የሚናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፤ ፖሊስ አመጸኞቹን ለመቆጣጠርና የንብረት ውድመት ለማስቆም እየጣረ ነው ብለዋል። ለሁለት ቀናት ከዘለቀ ተቃውሞና የንብርት ውድመት በኋላ ከትናንት ዕሁድ በተሻለ ሰኞ ዕለት መረጋጋት በጆሃንስበርግ መመለሱን የተናገሩት ወ/ሮ መዓዛ \"ከተማው ጸጥ ብሏል\" ብለዋል። የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በረብሻው የወደሙ ንብረቶችናና የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን እያቀረቡ ሲሆን ወ/ሮ መዓዛና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ለሁለት ቀናት ከሥራ ውጪ ሆነው መቆየታቸውን ገልጸዋል። ሌሎች ኢትዮጵያውያንና የመገኛኛ ብዙኃን እንደሚሉት ረብሻው ከተከሰተ በኋላ ከጆሃንስበርግ ይልቅ በደርባን ከባድ ጉዳት መድረሱን እንደተረዱ ጠቅሰዋል። \"ረብሻ ሲነሳ ጥቃት የሚደርሰው ስደተኞች ላይ ነው\" ንጉሥ እንደሚለው፤ ማንኛውም አይነት ነውጥ ሲነሳ ያንን ሰበብ በማድረግ የንግዱ ማኅበረሰብ ላይ ጥቃት ይሰነዘራል። አሁን የተነሳው አይነት አለመረጋጋት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ባለፉት ጥቂት ቀናት ሲነገር እንደነበር እና ሸቀጣቸውን ከመደብር ያወጡ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች እንዳሉ ገልጿል። \"ዛሬ ጥቃት እንደሚደርስ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ስለተነገረ መላው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ከቤቱ አልወጣም\" ብሏል። ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጣው የእንቅስቃሴ ገደብ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ላይ ያሳደረው ጫና ላይ አሁን የተነሳው ነውጥ ሲጨመር ማኅበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ቀውስ እንደሚያስከትልም ንጉሥ ይናገራል። ዳዊት እንደሚለው፤ ከዚህ ቀደምም እንደታየው አንዳች ነውጥ ሲነሳ ስደተኞች ላይ ጥቃት ይሰነዘራል። ይህንን የሚያውቁት ኢትዮጵያውያን ስጋት ስለገባቸው ዛሬ መደብራቸውን አልከፈቱም። \"ትላንት ኢትዮጵያውኑ ተሰብስበው ሳይሄዱ በፊት ጉዳት የደረሰባቸው ሱቆች ነበሩ። ዛሬም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለማይታወቅ ኢትዮጵያውያን ሱቃቸውን ዘግተው ውለዋል\" ይላል። ትላንት የናይጄርያውያን መኪና መሸጫ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብርና ሌሎችም የንግድ ተቋማት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ይናገራል። \"ትላንት ሀበሾች በቁጣ ሱቃቸውን ለመጠበቅ ወጡ። ፖሊስም አገዛቸው። ከዚህ በፊት ፖሊሶችም ጭምር ችግር ይፈጥሩብን ነበር\" ይላል። ኢትዮጵያውያኑ ስጋት ውስጥ እንደሆኑና የጃኮብ ዙማ የፍርድ ቤት ጉዳይ እልባት እስኪያገኝ ወይም እስኪረግብ ድረስ ወደ ሥራ መመለስ እንደሚያስቸግር ዳዊት ለቢቢሲ ገልጿል። ሁሌም ረብሻ ሲነሳ ስደተኞች ጥቃት እንደሚደርስባቸው የሚጠቅሰው ነጋዴው፤ \"ድንገት መጥተው ሊዘርፉን ወይም ሊያጠቁን ስለሚችሉ ዘግቶ መጠበቅ ይሻላል\" ሲል ያስረዳል። ጆሃንስበርግ ውስጥ የሚነግዱ ኢትዮጵያውያን በማንኛውም ጊዜ ነውጥ ሊነሳ እንደሚችል እንደሚሰጉ ገልጾ \"የለመድነው ችግር ስለሆነ ሁሌም በተጠንቀቅ ነው የምንጠብቀው። ረብሻ ሲነሳ ጥቃት የሚደርሰው ስደተኞች ላይ ነው\" ብሎም አክሏል። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም ስደተኞች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ብዙ ጊዜ ተፈጽመዋል። ዳዊት \"ስደተኞች ሲጠቁ ዓለም የደቡብ አፍሪካ መንግሥትን ስለሚጠይቅ ስደተኞችን ለማጥቃት ምክንያት ይፈለጋል\" ሲል ሁኔታውን ያስረዳል። በደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሠራዊቱ ስለመሰማራቱ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት፤ በጃኮብ ዙማ የትውልድ ቦታ ክዋዙሉ-ናታለ ተቀስቅሶ በመላው አገሪቱ እየተንሰራፋ የመጣውን አለመረጋገት ለማርገብ የአገሪቱን መከላከያ ሠራዊት እንዳሰማራ ተገልጿል። ዘረፋ ተፈጽሞባቸዋል በተባሉ ስፍራዎች ፖሊስ ምላሽ እየሰጠ ሲሆን እስካሁን ድረስ 60 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉንም ይፋ አድርጓል። ትናንት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች ዱላ እና ፍልጥ ይዘው በጆሃንስበርግ ከተማ መሃል ታይተዋል። ቅዳሜ ዕለት ደግሞ ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች የጆሃንስበርግን ዋና ጎዳናን ዘግተው ነበር። ከትናንት በስቲያ በነበረው ተቃውሞ ሕንጻዎች እና መኪኖች በእሳት ወድመዋል። አሌክሳንድራ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ወደ 800 የሚጠጉ ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለው አመጽ አንድ የፖሊስ አባል በጥይት መመታቱ ተዘግቧል። ፕሬዝደንት ሲርል ራማፎሳ ትናንት ምሽት ግጭት እያስከተሉ ያሉ ተቃውሞዎች እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ \"ለዚህ አመጽ እና የንብረት ውድመት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም\" ብለዋል። ፍርድ ቤትን በመድፈር ጥፋተኛ ተብለው የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው ጃኮብ ዙማ በሥልጣን ዘመናቸው ምንም ዓይነት ሙስና አለመፈጸማቸውን ይከራከራሉ። የጃኮብ ዙማ ጠበቆች ዛሬ ለአገሪቱ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት የፍርድ ጊዜውን ለማሳጠር ይሞክራሉ ተብሏል።", "ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ በወረርሽኙ ሳቢያ ከተጎዳው ምጣኔ ሐብት ለማገገም 1.2 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካጋጣት የኢኮኖሚ ውድቀት ለማገገም እንዲሁም የጤና ወጪ 1.2 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም [አይኤምኤፍ] አስታወቀ። ገንዘቡ ያስፈልጋታል የተባለው ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት መሆኑ ተገልጿል። የተቋሙ ዳሬክተር ክርስታሊና ጆርጂቫ እንዳሉት ዓለም አፍሪካ ከገባችበት ቀውስ እንድታገግም ለመደገፍ ዓለም ብዙ መስራት አለበት ብለዋል። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌሎች አህጉራት ያነሰ ነው፤ ነገር ግን የዓለም ባንክ በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካዊያን ለከፋ ድህነት የመጋለጥ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል። በወረርሽኙ ሳቢያ የሥራ እድሎች በመታጠፋቸው እና የቤተሰብ ገቢ በ12 በመቶ በመቀነሱ የደረሰው የኢኮኖሚ ተፅእኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ እየታየ የነበረውን ጠንካራ እድገት እየቀለበሰው መሆኑን የገንዘብ ተቋሙ ዳሬክተር በበይነ መረብ በነበራቸው የተቋሙ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ችግሩንም ለማቃለል በርካታ አፍሪካ አገራት መንግሥታት ከልማት እቅዳቸው 2.5 በመቶ ያስወጣቸውን ፖሊሲዎች አስተዋውቀዋል። አይኤም ኤፍ የአፍሪካ አገራት ከደረሰባቸው ተፅዕኖ እንዲያገግሙ 26 ቢሊዮን ዶላር የለገሰ ቢሆንም፤ የግል አበዳሪዎች እና በሌሎች አገራት ድጋፍ ቢኖርም፤ አሁንም ግን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለ ብለዋል። \"አንዳንድ አገራት ከብድር አግልግሎትና ተጨማሪ የማህበራዊና ጤና ወጪዎች መካከል እንዲመርጡ የሚያስገድዳቸውን የዕዳ ጫናዎች እየተጋፈጡ ነው\" ብለዋል ኃላፊዋ። ይህንን ችግር ለመፍታትም ተበዳሪዎች ብድራቸውን የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ለብድር የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ማቅረብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። በአፍሪካ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ወደ 37 ሺህ የሚጠጉት ሕይወታቸውን አልፏል።", "የወቅቱ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ተግዳሮቶች የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) ባለፉት 10 ዓመታት በየዓመቱ በአማካኝ 9.4 በመቶ እያደገ መሆኑን ይናገራል። ኢትዮጵያ ከጥቅምት 24/2013 ጀምሮ በትግራይ ክልል የቀሰቀሰው ጦርነት፣ በቅርቡ የተከሰተው ከፍተኛ ሆነ የምንዛሬ እጥረት እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ኢኮኖሚውን እየተፈታተነው ይገኛል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው ከ64 እስከ 68 ብር ድረስ በመመንዘር ላይ እንደሚገኝ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ይህ ዋጋ እስከ 72 ብር ድረስ ከፍ እንደሚል ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በመደበኛው የምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር በ45 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። የአገሪቱ የዋጋ ግሽበትም ቢሆን ከእለት ወደ እለት እየጨመረ እንደሚሄድ ያሳያል። ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በኮቪድ-19 ምክንያት ተጽዕኖ እንደደረሰበት እና 2 በመቶ ገደማ ዕድገት እንደሚያስመዘገብ ጠቅሰው ነበር። ወርቅነሽ ሲማ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። ከምታገኘው ገቢ በላይ ወጪዋ ሰማይ መንካቱን በመግለጽ የኑሮ ውድነት እንዳማረራት ትናገራለች። \"የቤት ኪራይ፣ በርበሬ፣ ዘይት እና ጤፍ ዋጋቸው ሰማይ የነካ ነው\" የምትለው ወርቅነሽ በአሁኑ ጊዜ ገቢያችን እና ወጪያችን የተመጣጠነ አይደለም ስትል ለቢቢሲ አስረድታለች። ወርቅነሽ መንግሥት ለኑሮ ውድነቱ መፍትሄ ያበጅለታል ብላ ተስፋ ብትጥልም \"ለእኛ ግን በጣም ፈታኝ ነው\" ስትል ኑሮ እንደከበዳት ትገልጻለች። በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራው ለማ አበበ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ስላለው የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ሲናገር \"እያደገ ነው\" በማለት ነው። አክሎም \"የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነቱም በዚያው መጠን እያደገ ነው። ይህ ደግሞ ገበሬውን ሳይሆን ኑሮውን በየወሩ በሚያገኘው ደሞዝ ላይ ያደረገውን መካከለኛ ገቢ የሚያገኝ ነዋሪ እየጎዳው ነው። ገበሬው ግን ያመረተውን በገበያው ዋጋ ስለሚሸጥ አትራፊ ነው\" ሲል ያስረዳል። አቶ ለማ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር የአገር ውስጥ ምርትን መጠቀምን ማበረታታ እና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን መቀነስ መፍትሄ ይሆናል ብሎ ያምናል። የተለያዩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ባለፉት አሥር ዓመታት መንግሥት በከፍተኛ መጠን ከተፈተነባቸው ችግሮች መካከል አንዱ የዋጋ ንረት ነው። መንግሥት የዋጋ ንረትን መቆጣጠር አቅቶታል ብለው የሚተቹ ወገኖች በርካታ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥታቸው የዋጋ ንረት ለመከላከል እንደ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ያሉ ተቋማትን እያቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ኢኮኖሚውን ነፃ ለማድረግ በሚል በመንግሥት ይዞታ ስር የሆኑትን ቴሌኮምዩኒኬሽንን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በከፊል ወደግል ለማዘዋወር ተወስኖ ነበር። ከእነዚህ ድርጅቶች በተጨማሪም የኢንደስትሪ መንደሮችን፣ የስኳር ፋብሪካዎችን፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች አምራች ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የተወሰነው የአገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱንና የዋጋ ግሽበቱን ለመቋቋም፣ የገቢ ማመንጨት አቅምን ለማጠናከርና የወጪ ንግዱን ለማቀላጠፍ በሚል ነው። ለዚህ ውሳኔ ሌላኛው ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የብድር መጠን ከፍ ማለቱ እንደሆነም ይነገራል። ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ተቋማት ክፍት እንደምታደርግ ያስታወቀችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ይፋ በተደረጉ የለውጥ እርምጃዎች ነው። በቅርቡም ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፍ ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ ለተሰኘው ጥምረት ፍቃድ መስጠቷ ይታወሳል። በዚህም የተነሳ ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ነዋይ ወደ አገሪቱ እንዲገባ እና በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተነግሯል። እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በሰኔ ወር ብቻ 24.5 በመቶ ደርሷል። ኢትዮጵያ ከተለያዩ የውጭ አገራት የተበደረችው 42.8 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ይነገራል። ኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብቷን ለማሳደግ ከወሰደቻቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ የተለያዩ ኢንደስትሪ ፓርኮችን ለውጭ ገበያ የሚሆኑ ምርቶችን እንዲያመርቱና እንዲልኩ ማበረታታት ነው። ማርታ ገላነው በአገሪቱ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል በአንዱ ተቀጥራ ትሰራለች። የአውቶሜሽን ኢንጂነር ባለሙያ የሆነችው ማርታ በአገሪቱ እየተስፋፉ ያሉ የኢንደስትሪ መንደሮች የወደፊት ተስፋዋን ብሩህ ማድረጋቸውን ትናገራለች። በአሁኑ ጊዜ ገና በመቋቋም ባለ ፋብሪካ ውስጥ እየሰራች ቢሆንም ለወደፊት ግን \"እንደ አውቶሜሽን ኢንጂነርነቴ በየትኛውም ትልልቅ ፋብሪካዎች ውስጥ ያሉ ማሽኖችን ማንቀሳቀስ እችላለሁ\" ስትል ታስረዳለች። በደብረብርሃን የኢንደስትሪ ፓርክ የእንስሳት መኖ ለማምረት በማሰብ ግንባታ እያካሄዱ መሆኑን የሚናገሩት የባጃኢ ኢትዮ ኢንደስትሪያል ሶሉሽን ባለቤት ባጃኢ ናይከር ናቸው። በደብረብርሃን ኢንደስትሪያል ፓርክ ውስጥ እያስገነቡት ባለው የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ድብልቅ የእንስሳት መኖ ለኢትዮጵያውያን እንስሳት አርቢዎች ለማምረት እየሰሩ ነው። ፋብሪካው ከዚህ ቀደም ከውጭ እየመጣ የነበረውን የእንስሳት ቫይታሚንና ሚነራሎችን ለማስቀረት የሚያስችል እቅድ አለው። ፋብሪካው የአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያም የማቅረብ ሃሳብ እንዳለው ባለቤቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደ ሚስተር ባጃኢ ከሆነ መንግሥት በዚህ የኢንደስትሪ መንደር ፋብሪካቸውን እንዲገነቡ የተለያዩ ማበረታቻዎችን አድርጎላቸዋል። በኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ ሲሰሩ ለተወሰነ ዓመታት ከታክስ ነጻ እንደሚሆኑ፣ ከውጭ የተወሰኑ እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ የማስገባት እድል እንደተመቻቸላቸው፣ መሬት በርካሽ ማግኘታቸውን እንዲሁም በዚህ ኢንደስትሪ መንደር ለእንስሳት አምራቾች የተለየ ትኩረት መሰጠቱ እርሳቸውን ከሳቧቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በመላ አገሪቱ 15 የኢንደስትሪ ፓርኮች እንዳሉና ተጨማሪ 20 ደግሞ የመገንባት እቅድ እንዳለው ያስረዳል። የትግራይ ጦርነት እና የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት እያሳየ ቢሆንም በትግራይ፣ በአፋር እና በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ጦርነት ግን የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት ፈተና ላይ ጥሎታል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት እና የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ የበላይ ኃላፊ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ባለሀብቶች የረዥም ዓመት እቅድ ይዘው መሆኑን ይናገራሉ። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ያለው ግጭት የአጭር ጊዜ መሆኑን እና አገሪቱም እንደምትወጣው ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። ለኢትዮጵያውን ዋነኛ የምጣኔ ሀብት ስጋት የዋጋ ግሽበት መሆኑን የሚያብራሩት አቶ ዘመዴነህ፣ ባለፉት 10 ዓመታት የግሽበት መጠኑ በእጥፍ መጨመሩን በመግለጽ ይህም መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ተግዳሮት ሆኖ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ለዋጋ ግሽበቱ መናር ምክንያት ነው ብለው ከጠቀሷቸው መካከል ከፍተኛ የሆነ የፍላጎት መጨመር ሲኖር የአቅርቦት መጠን በዚያው ልክ ማደግ አለመቻሉን ነው። በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለ ከፍተኛ አለመመጣጠን በተለይ ደግሞ የአገር ውስጥ ምርቶች ከፍላጎት ጋር በተመጣጠነ መልኩ አለማደጋቸውን ያነሳሉ። ሌላው የጅምላ፣ የችርቻሮ እና የማከፋፈል ስርዓት በአገሪቱ ውስጥ አሁንም ኋላ ቀርነት እንዳለው አንስተዋል። ለዚህም መዋቅራዊ ለውጥ መካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ። ኢትዮጵያ ከ126 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቴሌኮምዩኒኬሽኑን ዘርፍ ለግል ባለሀብቶች መስጠቷን የሳፋሪኮም ስምምነትን በመጥቀስ የገለፁት አቶ ዘመዴነህ፤ \"ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ ለተለያዩ ቢዝነሶች በሯን መክፈቷን ያሳያል\" ሲሉ ተናግረዋል። በቴሌኮም ዘርፉ የውጭ ባለሀብቶች መምጣታቸው የአገልግሎት ጥራት፣ የዋጋ ውድድር በመፍጠር ለቴሌኮሙም ሆነ ለፋይናንስ ዘርፉ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ያብራራሉ። አቶ ዘመዴነህ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በአምራች እንዲሁም በቱሪዝምና ሌሎች ዘርፎች በቀጣዩቹ ሦስትና አምስት ዓመታት እድገት እንደምታሳይ ያላቸውን ተስፋም ገልፀዋል።", "እሷ ማናት? #4፡ ከሒሳብ ጋር በአጋጣሚ ነው የተዋደድነው በሒሳብ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪዋን (ፒኤች ዲ) ለማግኘት እየሰራች ነው። ሰዎች እምብዛም ገፍተው በማይሄዱበት የትምህርት ዓይነት እንዴት ውጤታማ ልትሆን እንደቻለች አጫውታናለች። ስሜ ኤቢሴ አዱኛ ይባላል። ተወልጄ ያደኩት በነቀምት ከተማ ነው። የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቴን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተምርያለሁ። በአሁን ሰዓት ደግሞ የሦስትኛ ዲግሪ ትምህርቴን በዴንማርክና በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች እየተከታተልኩ ነው። • የኮምፒዩተር ትምህርት ለኬኒያ ሴት እስረኞች ሁለተኛ እድል ይሰጣቸው ይሆን? • አንድም ሴት የፓርላማ አባል የሌላት ሃገር ሒሳብ መረጠሽ ወይንስ መረጥሽው ? የሙያ ሕይወቴ ከሒሳብ ጋር የተቆራኘ ይሆናል ብዬ አልገመትኩም ነበር። ለመጀመሪያ ዲግሪ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተመደብኩበት ወቅት የሒሳብ ትምህርት ሳልመርጥ በአጋጣሚ ደረሰኝ። ከዚያ በኋላ ግን እኔና ሒሳብ በጣም ተዋደድን። እኔ ልምረጠው ሒሳብ ይምረጠኝ የሚታወቅ ነገር የለም። የሒሳብ ትምህርትን ከድሮም ፈርቼው አላውቅም። ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ትምህርቱ ሲደረሰኝ ጥሩ ነጥብ ማስመስገብ ጀመርኩኝ፤ እየወደድኩትም መጣሁ። በዚያ ላይ ይህ ትምህርት ለሴት ይከብዳል ለወንድ ደግሞ ይመቻል የሚል አመለካከት የለኝም። ማንም ሰው ፍላጎት ካለው፣ ከጣረና በሥራ ካስደገፈው ይሳካል ብዬ ስለማስብ የሒሳብ ትምህርትን አጥብቄ ይዤ ቀጠልኩበት፤ እዚህም ደረስኩኝ። አሁንም ቢሆን ከምወዳቸው ትምህርቶች መካከል ትልቁን ቦታ የያዘው ሒሳብ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እያለሁ 'ጊዜ ቤት' ላይ ሌሎች ልጆች ሸምድደው በፍጥነት እንደሚሉት አልነበርኩም፤ ነገር ግን በልጅነቴ በተወሰነ ደረጃ ይህንን 'የጊዜ ቤት' እሠራ ነበር። በዚያ ወቅት ተማሪ እያለሁ አባቴ የሒሳብ መምህር ስለነበረ በሒሳብ ጥሩ መረዳት እንዲኖረኝ አድርጓል። በጭንቅላቴ ሸምድጄ ከመያዝ ይልቅ ተረድቼ ማስላት ይቀለኝ ነበር። የሒሳብ ጥቅም የተለያየ ነው። ለምሳሌ ሒሳብ በሁለት ይከፈላል፤ 'ፕዩር ማቴማቲክስና አፕላይድ ማቴማቲክስ' ተብለው ይለያሉ። • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? • ሚሼል ኦባማ በአሜሪካ እጅግ ተወዳጇ ሴት ተባሉ እኔ የምማረው 'አፕላይድ ማቴማቲክስ' በተጨባጭ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚጠቅም ነው። ለምሳሌ የምመረምራቸው ስሌቶች ኤች ሲቪ ለተባለው የጉበት ቫይረስ መፍትሔ ለማግኘት የሚረዳ ነው። ስለዚህ ሒሳብ በሕይወታችን ያሉን ተጨባጭ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የሚረዳ የትምህርት ዓይነት ነው። ነገ የሚሆንን ነገር ለመተንበይ ሒሳብ ችግሮቻችንን በቁጥር አስልተን ለማስቀመጥ ይረዳናል። የሒሳብ ምሁሮች ከስሌቱ በኋላ ቀመሩን ከነመፍትሔው ያስቀምጡልናል። የምህድስና ሙያ ያላቸው ሰዎች ደግሞ እንዲህ ዓይነት ቀመሮችን በሥራ ላይ ያውላሉ። ስለዚህ ከሒሳብ ሙያተኞች ይልቅ በምህንድስና ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች በይበልጥ ማስረዳት ይችላሉ። ውጣ ውረዶችን ለማለፍ በሥራም ሆነ በኑሮ እንደማንኛውም ሰው የተለያየ መሰናክል ይገጥመኛል። ነገር ግን የችግሩን ያህል ሳይሆን ነገሮችን ከአቅሜ አንፃር ነው የምገመግማቸው። ችግር እንደሚያበረታኝና እንደሚያጠነክረኝ ስለማውቅ ሁሌም መውጫ ቀዳዳ ነው የምፈልገው። አንዳንዴ ሰዎች ፊቴንና ዕድሜዬን አይተው ይገምቱኛል። አንዳንዴ ጊዜ እንዲያውም በሴትነቴ ጭምር ለመመዘን ይሞክራሉ። እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲገጥሙኝ ደግሞ እራሴን በደንብ አስተዋውቃለሁ። ምን ማድረግ እንደምችል፣ ማን እንደሆንኩ እና ፍላጎቴ ምን እንደሆነ አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ እናገራለሁ። ይህ ደግሞ በሕይወቴ የምፈልገውን ነገር በሙሉ እንዳገኝ አድርጎኛል በዚያ ላይ ተግባቢ ሰው ነኝ። ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ መማር ጊዜን ስለሚፈልግ የጊዜ እጥረት ያጋጥማል። የፒኤች ዲ ትምህርት ምግብ የምበላበት ጊዜ እንኳን አይሰጥም፣ ያስጨንቃል ደግሞም ድብርት ያስከትላል። ቢሆንም ግን ያለኝን ጊዜ አብቃቅቼ ከጓደኞቼም ሆነ ከቤተሰቦቼ ጋር ጊዜ አሳልፋለሁ። ከዚህ ሁሉ ግን ያለንን ጊዜ በደንብ ከተጠቀምንበት የምንፈልገውን ማሳካት ይቻላል ብዬ አስባለሁ። • ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል? • ከመጀመሪያው 'የብላክ ሆል' ምስል ጀርባ ያለችው ሴት እንደሚታወቀው በአገራችን ሴት ልጅ ስትበልጥ ወንዶች ብዙ ደስተኛ አይደሉም፤ ሁሉም እንዲዚህ ናቸው ማለቴም አይደልም ነገር ግን እንዲህ ዓይነት አስተሳብ አለ። በሁሉም መንገድ ወንድ የበላይ ሆኖ አንዲታይ የሚፈልጉ አሉ። እንደእኔ አመለካለከት የትምህርት ደረጃ እና ፍቅር የተለያዩ ናቸው። ስኬቴ ችግር የሚሆንበት ካለ ለማስተናገድ አልችልም። የቤተሰቤ አባላት በማደርገው ጥረት ላይ በጣም የደግፉኛል። ጓደኛና የምወደው ሰው የምለውም ሰው ልክ እነደዚህ የሚደግፈኝ መሆን አለበት። ለምን ትበልጠኛለች ካለ ግን ይህ ፍቅር ነው ወይንስ ቅናት? ብዙ ሴቶች ያለንን አቅም የተረዳነው አይመስለኝም። እንችላለን ብለን ካመንን ማድረግ አያቅተንም። ይህን ከተረዳን ደግሞ በውበት፣ በጋብቻ እና በገንዘብ መወሰን የለብንም። እራሳችን ያለምነው ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ እንደምንችል ማሰብና መጣር ነው ያለብን። ስለዚህም የሚያጋጥሙንን መሰናክሎች በእራሳችን ማለፍ መቻል አለብን። እንደዚህ ወደፊት ከተራመድን አገራችንን ወደፊት ለመምራት አያቅተንም። ያለንን አቅማችንንና መላ የማበጀት ጥበባችንን እንጠቀምበት ብዬ ለሴቶች ምክሬን እሰጣለሁ።", "ሲም ካርድ ያለው ሁሉ ገንዘብ መበደር የሚችልበትን ዕድል የፈጠረው ቴሌብር ከአስራ አራት ወራት በፊት ወደ አገልግሎት የገባው ቴሌብር የተሰኘው የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ባለፈው ሳምንት አርብ ከቁጠባ እና ብድር ጋር የተያያዙ አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት ጀምሯል። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አዳዲሶቹ አገልግሎቶች በፋይናንስ ሥርዓት ያልተሸፈነውን 60 በመቶ የሚሆን የኅብተረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል። የነዳጅ ድጎማ እና የግብር ክፍያን ጨምሮ ባለፉት 14 ወራት ገንዘብ ለመላላክ፣ የግብይትና የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸም እንዲሁም ከውጭ አገራት ገንዘብ ለመቀበል ሲውል የነበረው ቴሌብር አሁን ደግሞ  ‘መላ’፣ ‘እንደኪሴ’ እና ‘ሰንዱቅ’ የተሰኙ አገልግሎቶችን ይፋ አድርጓል። ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር ደንበኞች ገንዘብ እንዲቆጥቡ፣ ሲያስፈልጋቸው እንዲበደሩ የሚረዱት አዳዲሶቹን አገልግሎቶች ለማስጀመር አስራ አራት ወራት በላይ ዘግይቷል። ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም እነዚህን አገልግሎቶች ለማስጀመር ከአንድ ዓመት በላይ የዘገየበትን ምክንያት ሲያስረዱ “የተሰጠን ፍቃድ እሱን አልፈቀደልንም ነበር። ስለዚህ በቴሌ ብር ሌሎቹን አገልግሎቶች እየሰጠን ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ለማግኘት ሥራዎችን ስንሰራ ቆይተናል” ብለዋል። ለመሆኑ አገልግሎቶቹ ምንድን ናቸው? በቴሌብር አማካኝነት በቅርቡ የተጀመሩት ሦስት አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ያለዋስትና/ማስያዣ እንዲበደሩ ወይም እንዲቆጥቡ የሚያስችሉ መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህ የቴሌብር አገልግሎት ደንበኞች ገንዘብ የሚቆጥቡበት ሲሆን፣ ለተቀማጭ ገንዘብ ወለድ የሚከፈልበትን እና ከወለድ ነጻ የሆነ አመራጮችን አካቷል። እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ፣ ወለድ የሚከፈልበት ቁጠባ በየቀኑ የሚሰላ እና ደንበኞች በቀን ያገኙትን መጠን የሚያመላክት ነው። የቴሌብር ደንበኞች ግብይት እየፈጸሙ ገንዘብ በሚያንሳቸው ጊዜ ቀሪውን ገንዘብ የሚያገኙት ሥርዓት ደግሞ እንደኪሴ ይሰኛል። እንደኪሴ ደንበኞች ለግብይት ከሚያጥራቸው ገንዘብ በተጨማሪ እንደ የኤሌክትሪክ እና ውሃ ያሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመፈጸምም ያስችላል። ይህ አሰራር ደንበኞች ለክፍያ የጎደላቸውን እስከ 2 ሺህ ብር የሚሸፍንም ነው። ቴሌብር መላ፣ ደንበኞች የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት መንገድ ሲሆን ግለሰቦችን እና የንግድ ተቋማትን የሚያካትት ነው። በቴሌብር መላ ግለሰቦች በወር እስከ 10 ሺህ ብር፣ የንግድ ተቋማት ደግሞ እስከ 100 ሺህ መበደር እንደሚችሉ የሚያስረዱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ግለሰቦች የተበደሩትን በቀን፣ በሳምንት እና በወር መመለስ የሚችሉበትን አሰራር ማቀፉን ጠቅሰዋል። ለንግድ ተቋማት ደግሞ ለግለሰቦች ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በተጨማሪ የ3፣ የ6 እና የ9 ወር የሚመልሱበትን አሰራር አካትቷል። ቴሌብር መላ “ለሥራ ማስኬጃ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳብ ኖሯቸው ወደ ንግድ መግባት ለሚፈልጉ ሰዎችን ታሳቢ አድርጎ የቀረበ ነው። ለዚያ ነው በፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ያልሆነውን ማኅበረሰብ፣ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናል ብለን ያሰብነው” ሲሉም አክለዋል። መላ፣ እንደ ኪሴ እና ሰንዱቅ በተሰኙት የቴሌብር አገልግሎቶች በመጀመሪያ ዓመት ውስጥ በየወሩ በአማካኝ ከ3 እስከ 4 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገል እና ከ19.5 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለማንቀሳቀስ ማቀዱን ኃላፊዋ ጠቅሰዋል። ከዚህም ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው የብድር አገልግሎቱ ወይም ቴሌብር መላ ሲሆን 9.8 ቢሊዮን ብር ይሸፍናል። 6.4 ቢሊዮን ብር ክፍያን ለማጠናቀቅ ወይም እንደ ኪሴ ለተባለው አገልግሎት እንዲሁም 3.3 ቢሊዮን ብር ደግሞ በቁጠባ ወይም ሳንዱቅ በተሰኘው አገልግሎት የሚጠቃለል ነው። ደጋግመው ብድር የሚወስዱ ደንበኞችን ጨምሮ በዓመት 108 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገል ማታቀዱንም አስረድተዋል። አገልግሎቶቹ በተጀመሩ በቀናት ውስጥ የዕለት ብድር ወስደው የሚመልሱ እንዲሁም የሚቆጥቡ ደንበኞች መኖራቸውን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተስፋ ሰጪ እና “አስገራሚ” ሁኔታዎች መኖራቸው ገልጸዋል። በቴሌብር መላ የሚሰጠው ብድር በሙሉ ዋስትና ወይም ማስያዣ እንደማይጠየቅበትም ጨምረው አስረድተዋል። የፋይናንስ ተቋማት ለሚያበድሩት ገንዘብ ዋስትና ወይም ማስያዣን መጠየቅ የተለመደ አሰራራቸው ነው። ከዚህ አሰራር በተቃራኒ በቴሌብር የሚቀርቡ ብድሮች ዋስትና አይጠየቅባቸውም። ሆኖም ሥርዓቱን በሚንቀሳቀስበት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የደንበኞችን የወጪ ገቢ ዝውውር በመመልከት የብድሩን መጠን ይፈቀዳል። ሥርዓቱ ደንበኛውን በገንዘብ ዝውውሩ በመመልከት በተለያዩ ደረጃዎች የሚገለጽ ነጥብ የሚሰጥ ሲሆን፣ ብድር ለሚመልሱ ደንበኞች ደግሞ የተሻለ ቡድር ማግኘት የሚቻልበትን ነጥብ ይሰጣል። አገልግሎቱ በቴሌብር ሞባይል መተግብሪያ  ወይም #127# አጭር ቁጥር አማካኝነት የሚቀርብ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሲምካርድ ላላቸው ደንበኞች በሙሉ በቴሌብር ያላቸውን የገንዘብ ዝውውር መሰረት አድርጎ ብድርን የሚያቀርብ ነው። እነዚህ አገልግሎቶችን ለማስጀመር የአዋጪነት ጥናት መካሄዱን የሚያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ እንደ ማንኛውም የፋይናንስ አገልግሎት ስጋት ሊኖር እንደሚችል ታሳቢ መደረጉን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ይህ አገልግሎት የኢትዮጵያን ባህል ከግምት ውስጥ ማስገባቱን በማንሳት “ሁሉም ደንበኛ አይመለስም ብለን ልንወስድ አንችልም። . . . ተበድሮ አልመለሰም መባልን የማይፈልግው የማኅበረሰባችን ክፍል ሰፊ ነው። እርሱን እንደ ጥንካሬ ወስደነዋል።” አክለውም “ . . . አንዴ ብድሩን አልመለሰም ማለት በሚቀጥለው ብድር አያገኝም። ስለዚህ አንዴ ሁለት ሺህ ብር ተበድሮ ቢጠፋ ነው የሚሻለው ወይስ በዓመት ሁለቴም ሦስቴም ሁለት ሺህ፣ አራት ሺህ ቢበደር ነው የሚሻለው? ለማኅበረሰቡ የምናስረዳው ይህንን ነው። ይህ ይሆናል ብለን አንጠብቅም። ባለማወቅ ሊፈጠር ይችላል። ለዚያ ግን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እንሰራለን። ምንም ችግር አያጋጥመንም ግን አንልም። በፋይናንስ ሴክተር ያሉ እንደሚያውቁት በዋስትና የሚሰጠው ብድርም ላይመለስም ይችላል። ግን ከቁጥጥር ውጪ አይሆንብንም። እሱን አጥንተን ነው የገባነው” ብለዋል። ሥርዓቱ ላይ ይህ ችግር ሊያጋጥም ይችላል በሚል ይህንን ከመተግበር ወደ ኋላ አንልም የሚሉት ፍሬህይወት “60 በመቶ የኅበረተሰብ ክፍል የፋይናንስ አገልግሎት የማያገኝበት አገር ላይ ሆነን ሪስክ [ስጋት] አለ ብለን የገንዘብ ችግር ከመፍታት አንጻር ትልቅ አቅም የሆነውን አለመጀመር ደግሞ ተገቢ ነው ብለን አናስብም. . .” ስለዚህም ይህንን በአግባቡ ተጠቅመው ኑሯቸውን፣ ሕይወታቸውን፣ ቤተሰባቸውን ሊቀይሩ የሚችሉ ሚሊዮኖች ስላሉ የእነርሱን ዕድል ለማስፋት የተጀመረ ሥራ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ “ሙሉ በሙሉ ስጋት (ሪስክ) የለውም ብለን ሳይሆን መልካም ጎኑን ይዘን ነው የተነሳነው” ሲሉም አክለዋል። ወደ አገልግሎት ከገባ 1 ዓመት ያለፈው ቴሌብር 22.2 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ያስረዳሉ። በእነዚህ ጊዜያትም 34.1 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር ተከናውኖበታል። ከዝውውሩ 18 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ ማውጣት እና ማስገባት ሲሆን 40 በመቶ ደግሞ የአየር ሰዓት መሙላትን ነው። ገንዘብ መላላክ፣ የአገልግሎት ክፍያ እና ግብይት መፈጸም ደግሞ የተቀረውን ድርሻ ይይዛል። የግብር፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና መሰል አግልግሎቶችን ከሚሰጡ በርካታ የመንግሥት ተቋማት፣ ከ13 ባንኮች እንዲሁም ከ22 ሺህ የንግድ ተቋማት ጋር የተሳሰረው ቴሌብር  በመላው አገሪቱ ከ79 ሺህ በላይ ወኪሎች እንዳሉትም ኃላፊዋ ጠቅሰዋል። “ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳካታችንን እንደ ትልቅ ስኬት እንወስደዋለን” የሚሉት ኃላፊዋ ቴሌብር የገንዘብ ዝውውር እና ክፍያን ምቹ እና ቀልጣፋ ማድረግ፣ የክፍያ ሥርዓትን ማዘመን እና የዲጂታል ኢኮኖሚን በማስተዋወቅ በፋይናንስ አገልገሎት ያልተካተተውም ሕዝብ ተደራሽ ማድረግ ዋነኛ አላማው እንደሆነ አንስተዋል። እስካሁን ቴሌብር “የክፍያ ሥርዓቱን ሲያሳልጥ የቆየ” ሲሆን በፋይናንስ ሥርዓት ተደራሽ ያልሆኑ ሰዎችን ተደራሽ የማድረግ ቀዳሚ ዓላማውን ለማሰካት በቅርቡ ይፋ የሆኑት ዓላማዎች ወሳኙን ሚና እንደሚጫወቱ ጠቅሰዋል።", "ቻይና ዝናብ ለማዝነብና የተፈጥሮ ሂደትን ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት እንደ ቻይናዋ ቤይጂንግ የአየር ብክለት የሚፈትነው ከተማ የለም። የቤይጂንግ ሰማይ በመጠኑም ቢሆን ጠርቶ ፀሐይ የምትታየው በከተማዋ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ ውይይት ሲኖር ነው። ይህ የሚሆነው በተፈጥሯዊ ሂደት ሳይሆን መንግሥት በቀየሰው ስልት አማካይነት ነው። የቻይና መንግሥት የአገሪቱን የአየር ሁኔታ ለመለዋወጥ ሰው ሠራሽ መንገድ መጠቀም ጀምሯል። ይህ ሰው ሠራሽ ሂደት በጥቂት የቻይና ከተሞች ብቻ ይተገበር ነበር። ከጥቅምት ወዲህ ግን አገር አቀፍ እንደሚሆን ተነግሯል። ሂደቱ በሰው ሠራሽ መንገድ ዝናብ እንዲጥል ማድረግ፣ በረዶ ማዝነብ ወዘተ. . . ያካትታል። እአአ በ2015 ይህን ሂደት በቻይና 5.5 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትር ማለትም የአገሪቱን 60 በመቶውን ለማዳረስ ታቅዷል። እቅዱ እንደ ሕንድ ላሉ ጎረቤት አገሮች አልተዋጠላቸውም። ቻይና እና ሕንድ ከድሮውም ውጥረት ውስጥ ናቸው። ቻይና የአየር ሁኔታን የምትለውጠው እንዴት ነው? በእንግሊዘኛው ክልውድ ሲዲንግ (cloud seeding) በሰው ሰራሽ መንገድ ዝናብ እንዲጥል የሚደረግበት ቴክኖሎጂ ነው። ለዚህም ሲልቨር አዮዳይድ የተባለ ንጥረ ነገር ወደ ደመና በመላክ የአየር ሁኔታ የሚለወጥበት ሂደት ነው። በሕንድ የአየር ሁኔታ ባለሙያው ዳናስሪ ጃይራም \"ይህንን ቴክኖሎጂ ብዙ አገሮች ይጠቀሙበታል። ቻይናና ሕንድም ይጠቀሳሉ\" ይላሉ። ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራትም ይህ ሂደት ይተገበራል። እንደ አውስትራሊያ ያሉ አገሮች ድርቅን ለመከላከል ይጠቀሙታል። ሂደቱ በተለይም በአሜሪካ ከ1940ዎቹ ወዲህ ነው እየታወቀ የመጣው። ውጤቱ ላይ ጥያቄ ያላቸው ባለሙያዎች ግን አሉ። በቤይጂንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ጆን ሲ ሙር \"ውጤታማነቱን የሚጠቁሙ ጥቂት ሳይንሳዊ ጽሑፎች ብቻ ናቸው ያሉት። ያለ ሳይንሳዊ ማረጋገጫ የተተገበረ ሂደት ነው\" ይላሉ። ሳይንቲስቱ እንደሚሉት፤ 50 ሺህ የቻይና ከተሞችና ወረዳዎች ይህንን መንገድ ተጠቅመው የእርሻ መሬታቸውን ለማዳን ይሞክራሉ። ዝናብን በማስቆም ማዕበል ሰብላቸውን እንዳያጠፋው ለመከላከል ይጥራሉ። ሆኖም ግን ተመራማሪዎች እንደሚሉት ይህ ሂደት ቻይና ውስጥ የሚሠራው ለአንድ ወይም ለሁለት ወራት ነው። ዝናብ የማነው? ቻይና የአየር ሁኔታን በመቆጣጠር ተፈጥሯዊ አደጋ እንዳይከሰት የመከላከል እቅድ እንዳላት አስታውቃለች። ሰብል እንዳይበላሽ፣ ሰደድ እሳት እንዳይስፋፋ፣ ከፍተኛ ሙቀትን ለመቆጣጠር፣ ድርቅን ለመግታት ወዘተ. . . ይውላል። ቤይጂንግ ውስጥ የምትሠራው ጋዜጠኛ ይትሲንግ ዋንግ እንደምትለው ቻይና የአየር ሁኔታን ለመቆጣጠር ያወጣችው መርሃ ግብር ሲተገበር ከግዛት ግዛት ይለያያል። ሂደቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ቻይናን አላሳሰቧትም። የቻይና ውሳኔ ከጎረቤት አገሮቿ ጋር ያላትን የፖለቲካ ፍጥጫ ሊያባብሰው ይችላል። \"የቻይና የአየር ሁኔታ የመለወጥ ሂደትደ የሕንድ የክረምት ዝናብ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት አለ\" ሲሉ የሕንዱ ተመራማሪ ያስረዳሉ። በቻይና እና ሕንድ የድንበር ግጭት ሳቢያ ሕንድ ውስጥ ለቻይና ያለው አመለካከለት እየጠለሸ ነው። የአየር ሁኔታ ለውጡም ከዚሁ ጋር ተያይዞ ይታያል። በታይዋን ዩኒቨርስቲ በ2017 የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ የአየር ሁኔታ ለውጥ ሲደረግ ከጎረቤት አገራት ጋር ውይይት ካልተደረገ ግጭት ሊነሳ ይችላል። የአንድ አገር የዝናብ መጠን ሲቀንስ ሌላውን አገር ተጠያቂ የማድረግ ሁኔታ ይፈጠራል። \"ይህ ስጋት ሳይንሳዊ አይደለም። ሆኖም ግን የቲቤት ተራራ የአየር ሁኔታ የተለያየ መሆኑ ከግምት መግባት አለበት። ስለዚህ አንድ አካባቢ የአየር ንብረት ለውጥ ሲከሰት ሌላው ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም\" ሲሉ ሳይንቲስቱ ጆን ሲ ሙር ያስረዳሉ። ቻይና የተለጠጠ እቅድ በማንገብ ሌሎችም ዘርፎች ላይ ለውጥ ልታካሂድ እንደምትችል ባለሙያዎች ይሰጋሉ። ይህም በሰው ሠራሽ መንገድ የፀሐይ ጨረራን ለመቆጣጠር መሞከርን ያካትታል። እነዚህ ውሳኔዎች የሚተላለፉት ከጎረቤት አገሮች ጋር ባለው ውጥረት ሳቢያ ሊሆን ይችላል የሚል መላ ምትም አለ። ሳይንቲስቱ በበኩላቸው \"ቴክኖሎጂው ችግር አለው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን በቴክኖሎጂው አንዳች ችግር ቢከሰት በምን መንገድ ይፈታል? ኃላፊነቱንስ የሚወስደው ማን ነው? ለሚለው መልስ ሊኖር ይገባል\" ይላሉ። በተጨማሪም የአየር ሁኔታን መለወጥን የመሰሉ ሂደቶች ዓለም አቀፍ ውይይት እና ስምምነት እንደሚፈልጉ ባለሙያው ያስረዳሉ። ሂደቱ የሚተገበርበት ወጥ አሠራር እንዲሁም ሂደቱን ተከትሎ ግጭት ቢነሳ በምን መንገድ መፈታት እንደሚችል አስቀድሞ መታሰብ አለበት ሲሉም ያክላሉ።", "ፓኪስታን ፡ በካርቱን ስዕል ምክንያት የፈረንሣይ ምርቶችን መጠቀም ልታቆም ነው አንድ የፓኪስታን እስላማዊ ቡድን የጠራውን የፀረ-ፈረንሳይ ተቃውሞን የፓኪስታን መንግሥት የፈረንሳይ ምርቶችን ላለመጠቀም በመወሰኑ ማቋረጡን አሳወቀ። ሰልፎቹ የተጠሩት ፈረንሳይ የነቢዩ ሙሐመድን ካርቱን የማሳየት መብትን በመደገፏ ነበር። አንድ መምህር በክፍል ውስጥ በነበረ ውይይት ወቅት የነቢዩ መሐመድን ካርቱን ካሳዩ በኋላ መገደላቸውን ተከትሎ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን አገራቸው በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አትገባም ሲሉ በጥብቅ ተከላክለዋል። ይህም በሙስሊሙ ዓለም ቁጣን ቀስቅሷል። የአክራሪው ተህሪክ ኢ-ላባይክ ፓኪስታን (ቲ.ኤል.ፒ) የተሰኘው ቡድን አባላት የፈረንሳይን ምርት ላለመግዛት የቀረበውን ውሳኔ የደገፉ ቢያንስ የሁለት ሚኒስትሮችን ፊርማ ያካተተ የስምምነት ቅጅዎችን አሳይተዋል። የፓኪስታን መንግስት በጉዳዩላይ በይፋ መግለጫ ካለመስጠቱም በላይ የፈረንሳይ ምርቶችን ያለመጠቀም አድማው እንዴት እንደሚተገበር አላሳወቀም። በፈረንሣይ እስልምናን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ማክሮንን ከተቹ የፖለቲካ መሪዎች መካከል የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን አንዱ ናቸው። ተቀዋሚዎቹ አሁንም ተጨማሪ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። ደጋፊዎች ከእሁድ ጀምሮ ወደ መዲናዋ ኢስላማባድ የሚወስደውን ቁልፍ መንገድ በመዝጋታቸው ከፍተኛ የእንቅስቃሴ መስተጓጎል አስከትሏል። የቲ.ኤል.ፒ አመራሮች መንግሥት ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ መስጠቱን ከተናገሩ በኋላ ተቃውሞው እንዲቋረጥ ተጠይቋል። የቡድኑ ቃል አቀባይ የሆኑት ኢጃዝ አሽራፊ ለሮይተርስ እንደተናገሩት \"የፈረንሳይ ምርቶችን እንደማይጠቀም መንግሥት በይፋ እንደሚደግፍ ስምምነት ከፈረመ በኋላ የተቃውሞ ሰልፎቻችንን እያቆምንው ነው\" ብለዋል። ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ የተደረገው የስምምነት ሰነድ የሐይማኖታዊ ጉዳዮች ሚኒስትሩን እና የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ፊርማ ይዟል። የፈረንሣይ አምባሳደር ከአገር እንዲወጡ በማድረግ ዙሪያ ላይ ፓርላማው እንዲወስን መንግሥት ሐሳብ እንደሚያቀርብም ገልጿል። የፓኪስታን መንግሥት በስምምነቱ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም። ቲ.ኤል.ፒ ቀደም ሲል ሐይማኖታዊ ስድብን ምክንያት በማድረግ ተቃውሞ ለማሰማት እጅግ ብዙ ሰዎችን በመሰብሰብ ይታወቃል። በፓኪስታን ሕግ መሠረት ነቢዩ ሙሐመድን በመሳደብ ጥፋተኛ የተባሉ ሰዎች የሞት ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። በፈረንሳይ የመንግሥት በሐይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ ያለመግባት የአገሪቱ ዋነኛ መገለጫ ነው። በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ሕዝባዊ ቦታዎች ሀሳብን በነፃነት መግለጽም የዚህ አካል ሲሆን የአንድን የተወሰነ ሐይማኖት ስሜት ለመጠበቅ የሃሳብ ነጻነቱን መግታት ብሔራዊ መገለጫውን እንደሚያደፈርስ ተደርጎ ይወሰዳል። 'ቻርሊ ሄብዶ' የተሰኘው መጽሔት የነቢዩ ሙሐመድ ካርቱን ይዞ መውጣቱን ተከትሎ እ.አ.አ በ2015 በፓሪስ ውስጥ የጥቃት ዒላማ ቢሆንም የካቶሊክን እና የአይሁድን እምነት ጨምሮ ሌሎች ሐይማኖቶችም የሚያመለክቱ ስዕሎችን ይዞ ወጥቷል። የፈረንሣይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቀደም ሲል በበርካታ ሙስሊሞች በብዛት በሚገኙባቸው አገሮች ውስጥ የፈረንሳይ ሸቀጦችን ላለመጠቀም የሚደረጉ ጥሪዎችን \"መሠረተ ቢስ\" ብለው \"በአፋጣኝ መቆም\" እንዳለባቸውም ገልጸው ነበር። ባለፈው ወር ለተገደሉት መምህር ክብር የሰጡት ፕሬዝዳንት ማክሮን ፈረንሳይ \"ካርቱኑን አታቆምም\" ብለዋል።", "እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት ባለፉት ጥቂት ወራት የሸቀጦች የዋጋ ንረት እና አጠቃላይ የኑሮ ዋጋ መወደድ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ የብዙሃን መገናኛዎች ተደጋግመው የሚወሱ ጉዳዮች ሆነዋል። የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችም የችግሩን አሳሳቢነት ከመቀበል በዘለለ እየተወሰዱ ናቸው የሚሏቸውን እርምጃዎች ሲናገሩ ተስተውለዋል። በወርሃ ግንቦት 2011 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ በመዲናዋ በግንባታ ዕቃዎች፣ በእህል፣ በጥራጥሬ እና በአትክልት ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎች መከሰታቸውን ጠቅሰዋል። እንደመፍትሄም ችግሩን አባብሰዋል ያሏቸው ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር ማምጣት፣ ፈቃደኛ ያልሆኑት ላይ ደግሞ ይህንን የሚከታተል ግብረ ኃይል በማቋቋም እርምጃ መውሰድ፣ እንዲሁም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የአቀርቦት ሥርዓቱን ማሰተካከል የከተማዋ አስተዳደር የሚያከናውናቸው ተግባራት መሆናቸውን ገልፀው ነበር። • \"ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም\" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) • \"መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ያስገባል\"ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ይሁንና ክረምቱ ሲገባ የዋጋ ንረቱ ከመርገብ ይልቅ ከፍ ብሎ ታይቶ የዋጋ ግሽበቱ ባለሁለት አሀዝ ሆኗል። በወርሃ ነሐሴ እንዲያውም ባለፉት ስድስት ዓመታት ከታየው የዋጋ ግሽበት መጠን ከፍተኛው ተመዝግቧል። የሸቀጦች የዋጋ ንረት ህይወታቸው ላይ ቀጥተኛ ጫና ካሳረፈባቸው የአዲስ አበባ ኗሪዎች መካከል ደግሞ የአርባ ዓመቱ ጎልማሳ ጋሹ መርከቡ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚኖረው ጋሹ ላለፉት ከአስራ ለሚልቁ ዓመታት በሚኒባስ ታክሲ ሾፌርነት ቤተሰቡን ሲያስተዳድር ኖሯል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን \"የኑሮ መወደድ ከአቅሜ በላይ ሆኖ እያንገዳደገደኝ ነው\" ይላል። \"በዋጋ ላይ ያለውን ለውጥ ከቀን ወደ ቀን እያየሁት የመጣሁት ጉዳይ ነው፤ በእኔ [ህይወት] እንኳ ታክሲ ሠርቼ ብሩን ይዤ ብገባም ምንም የሚገዛው ነገር የለም\" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። \"የልጆች ትምህርት ቤት፣ የእህሉ ውድነት፣ እንዲያውም ተስፋ ወደማስቆረጥ ደረጃ እየደረሰ ያለ ይመስለኛል\" ይላል። መጪውን ፍራቻ ጋሹ የአራት ልጆች አባት ሲሆን ትልቋ የአስራ ሁለት ዓመት ልጁ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ናት። ሌሎቹ ሦስት ልጆቹም በመዋዕለ ሕፃናት እና በአንደኛ ደረጃ ትምርት ቤቶች ውስጥ ይማራሉ። ባለፉት ዓመታት ሁሉንም ልጆቹን በግል ትምህርት ቤቶች ያስተምር የነበረ ሲሆን አሁን ግን በኑሮ ውድነት ላይ በየጊዜው የሚጨምረውን የትምህርት ቤት ክፍያን መቋቋም ባለመቻሉ አንደኛውን ልጁን የመንግሥት ትምህርት ቤት፣ ሁለቱን ደግሞ በለጋሽ ድርጅቶች በሚደጎም እና በዚህም ምክንያት በአንፃራዊነት አነስተኛ ከፍያ ወደሚጠይቅ ትምህርት ቤት አስገብቷል። ለእያንዳንዳቸው በየወሩ ሦስት መቶ ብር በመደበኛነት ይከፍላል። • ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቶች አሉ አንደኛዋን ልጁን ብቻ በግል ትምህርት ቤት መማሯን እንድትቀጥል አድርጓል። ለብቸኛዋ የግል ትምህርት ቤት ተማሪ ልጁ መደበኛ ክፍያ ብቻ በዓመት ከአስር ሺህ ብር በላይ ያወጣል። ይህም የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ፣ የአልባሳት፣ የምግብ ወጪዎች ሲደመሩበት \"ናላን የሚያዞር\" ሆኗል ይላል ጋሹ። በዚህ ላይ የቤት ኪራይ ወጪ ይታከልበታል። \"ህይወታችንን ለማቆየት እየሰራን ነው እንጅ እየኖርን ነው ብዬ አላወራውም።\" አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ መጪውን ጊዜ ይበልጥ እንዲፈራው እንዳደረገው ይናገራል ጋሹ፤ \"ወደፊት እንዴት እንደማስተምራቸው ራሱ ግራ ግብት እያለኝ ነው\" በማለት። ተስፋው ከዕለት ወደ ዕለት እንዲሟጠጥ አንድ ምክንያት የሆነው እርሱን ለመሰሉ ከኑሮ ጋር እልህ አስጨራሽ ግብግብ ለገጠሙ ሰዎች በፖለቲካ ልሂቃን ዘንድ ብዙም ትኩረት እየተሰጠ አይደለም ብሎ ማመኑ ነው። • ‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ? የፖለቲካ ልሂቃኑ \"በብሔርም ጉዳይ፣ በምንም ጉዳይ የራሳቸውን ለማመቻቸት እንጂ የድሃውን [ጉዳይ] አንስቶ ልብህን [የሚነካ] ነገር ሲናገሩ እኔ እስካሁን ሰምቼም አላውቅም። የራሳቸውን ጉዳይ ከማስፈፀም በስተቀር ውስጥህን የሚነካ ነገር፣ ስለኑሮህ፣ ስለሽንኩርት የሚያወራ የለም\" ይላል። ከጋሹ አስተያየት ጋር በሚስማማ መልኩ አጠቃላይ ምርጫ በሚከናወንበት ዓመት በፖለቲካዊ መድረኮች ላይ የዋጋ ንረት የሚገባውን ያህል ስፍራ ይዞ ያለመታየቱ እንደሚገርማቸው የሚያስረዱት የምጣኔ ሃብት የፖሊሲ ተንታኝ የሆኑት አሚን አብደላ ናቸው። \"ምርጫ ኖረም አልኖረም፤ የማንኛውም አገር መንግሥት ፈተና የሚሆኑ ሁለት የማክሮኤኮኖሚ አመላካቾች አሉ፤ የሥራ አጥነት እና የዋጋ ንረት።\"

በፖለቲካው መልክዐ ምድር ገኖ ያለው መንግሥታዊው ሥርዓት \"የፌዴራል ይሁን አይሁን የሚል ዓይነት እንጅ የሥራ አጥነት እና የዋጋ ንረት ላይ ብዙም የፖለቲካ ልሂቃን ሲጨቃጨቁ አይቼ አላውቅም\" ባይ ናቸው ተንታኙ። ለአንድ አገር መረጋጋት እና የምጣኔ ሃብት ዕድገት ወሳኝ ናቸው የሚሏቸው እነዚህ ጉዳዮች ብዙም ያለመነሳታቸው \"ዋናው ነገር የተዘነጋ ይመስለኛል\" አስብሏቸዋል። የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ተንታኙ አሚን አብደላ እንደሚሉት አጠቃላይ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ ይላሉ። በተሰናበተው 2011 ዓ.ም የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበቱ ከ15 በመቶ በላይ ደርሶ እንደነበረ የሚያስታውሱት አሚን በወርሃ ነሐሴ ደግሞ ይህ ቁጥር ወደ 18 በመቶ ከፍ ብሎ እንደነበርም ይጠቅሳሉ። ይህም ቁጥር በስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የታየው ትልቁ አሃዝ ነው። ለቁጥሩ ከፍ ማለት የምግብ ዋጋ፣ በተለይም የእህል ሰብል ዋጋ ንረት ምክንያት መሆኑን የስታትስቲክስ መረጃዎች ያመላክታሉ። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ በዚህ ረገድ በአንዳንድ ትርፍ አምራች በሆኑ አካባቢዎች የነበረው የፀጥታ ሁኔታ፣ የመጓጓዣ አገልግሎት እንደልብ ያለመገኘት እና ከዚህም ጋር በተያያዘ ምርትን በተፈለገው ደረጃ ማቅረብ ያለመቻል ለችግሩ ምክንያት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ተንታኙ አሚን ያነሳሉ። እየናረ ያለውን የዋጋ ንረት ለማቃለል ሁለት የመፍትሄ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ የሚሉት ባለሙያው፤ \"አንደኛው በአቅርቦት በኩል ሌላኛው ደግሞ በፍላጎት በኩል ያሉ ናቸው\" እንደአሚን ገለፃ። \"ከፍላጎት አንፃር የመንግሥት ወጪ የቀነሰበት ሁኔታ አለ። ያለፉትን ዓመታት ዓይነት እድገት ስለሌለ፤ ምጣኔ ሃብቱ ውስጥ የሚለቀቀው የገንዘብ መጠን ቀነስ ያለ ይመስላል። ይሁንና በአቅርቦት በኩል እምብዛም ለውጥ ያለ አይመስልም\" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል አቶ አሚን። የምርቶች በተገቢው መጠን አለመገኘት ለዋጋ መወደድ በአንዳንድ ሰዎች እንደምክንያት ተደጋግሞ የሚነሳ ሲሆን፤ ባለሙያውም በምርት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ሰንሰለት ችግር እንደሚስተዋልበት ይናገራሉ። \"ገበሬው አምርቶ ለምርቱ የሚያገኘው ዋጋ እና ከተማ ላይ መጥቶ የሚሸጥበት ዋጋ በጣም ከፍተኛ ልዩነት አለው። ገበሬው ከአንድ ኪሎ ሙዝ እያገኘ ያለው ገቢ እና አንድ ኪሎ ሙዝ ከተማ ውስጥ እየተሽጠበት ያለው ዋጋ ልዩነት አለው። \"በዚህ መካከል ያለው የአገልግሎት፣ የደላላ፣ የመጓጓዣ፣ የቦታ ኪራይ እና የመሳሰሉት ወጪዎች ከፍተኛውን ድርሻ የሚወሰዱ ናቸው። ይህ የገበያ ሰንሰለት ሥርዓት እሰካልያዘ ድረስ፤ የምርቶች ዋጋ ከፍ እንዲል ማድረጉ አይቀሬ ነው\" ለአሚን። • ሸማቹ በውጭ ምንዛሪ ለውጡ ማግስት • ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ? ከውጭ የሚመጣ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የንግድ ውድድርን ማሳለጥ እንዲሁም የሸማቾችን ጥበቃ ማጠናከር ይገባል የሚሉት ባለሞያው፤ ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን የሚያስመጡ ተቋማት እና ግለሰቦች በየተሰማሩበት ዘርፍ ጥቂት መሆናቸው ዋጋው ላይ ከሚገባው በላይ ጫና እንዲፈጠር መንገዱን ይጠርጋል ባይ ናቸው አቶ አሚን። ከውጭ የሚመጣ የዋጋ ንረት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምከንያትም ሊከሰት ቢችልም በእኛ አገር እየተስተዋለ ያለው እውነታ ግን በውጭ ምንዛሬው እጥረት መጠን ያህል መኖር ከሚገባው በላይ ጭማሪ ነው፤ ሲሉ የዋጋው ጭማሪ አሳሳቢ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ባለሞያው አቶ አሚን አብደላ ለፖለቲካዊ ጉዳዮች እየተሰጠ ካለው ጋር የሚመጣጠን አትኩሮት የዋጋ ንረትን ለመሳሰሉ ምጣኔ ሃብታዊ ተግዳሮቶች መቸር አለበት ባይ ናቸው። በዚህ አስተያየታቸው ጋሹም የሚስማማ ይመስላል፤ \"ይሄ ሁሉ እየታየ ቸል የሚባለው እስከመቼ እንደሆነ አይገባኝም።\"", "የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 2.4 ሚሊዮን ብር ገባ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ60 ሺህ ዶላር ወይም 2.4 ሚሊዮን ብር በላይ በመግባት ክብረ ወሰን ሰብሯል። ቢትኮይን መመንደግ የጀመረው በተለይ ደግሞ ከባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ አንስቶ ነው። ይህንን የማይጨበጥ የማይዳሰስ መገበያያ ገንዘብ በርካታ ግዙፍ ድርጅቶች እንቀበለዋለን ማለታቸው ለዋጋው መናር ምክንያት ሆኗል ተብሏል። በዘርፉ ጥርስ የነቀሉ ግን የቦትኮይን ዋጋ እንዲህ ያሻቀበው የአሜሪካ መንግሥት በኮሮናቫይረስ ኪሳቸው ለተጎዳ ዜጎች የሰጠውን ድጎማ ተከትሎ ነው ይላሉ። የቢትኮይን ጠቅላላ የገበያ ዋጋ አሁን ከ1 ትሪሊየን በላይ ሆኗል። ቢሆንም ቢትኮይን ከተፈጠረበት የፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ ዋጋው አንድ ጊዜ ሲያሻቅብ አንዴ ደግሞ ሲያሽቆለቁል ነው የከረመው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የቢትኮይን ማሻቀብ ከግዙፍ ኩባንያዎች ጋር ይያያዛል። ባለፈው ወር በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መኪናዎች የሚያመርተው ተስላ የተሰኘው ድርጅት ባለቤት የሆነው ኢላን መስክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን መግዛቱን ይፋ አድርጎ ነበር። አልፎም ድርጅቱ ተስላ ወደፊት ልክ እንደ ወረቀት ገንዘብ ለመገበያያነት እንደሚያውለው አስታውቆ ነበር። ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል ገንዘብ ወይም መገበያያ ነው ማለት ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል። ለሚያቀርቡት ምርት እና አገልግሎት ቢትኮይንን በክፍያ መልክ የሚቀበሉ በርካቶች ድርጅቶች አሉ። ማይክሮሶፍት፣ የፈጣን ምግብ አቅራቢዎቹ ኬኤፍሲ እና ሰብዌይ፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። ቢትኮይንን በመጠቀም የገዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ በየትኛውም ሰዓት እና በየትኛውም ስፍራ የቢትኮይን ዝውውር ማድረግ ይቻላል። ሕገ-ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ በርካቶች ናቸው።", "ከኮሮናቫይረስ በኋላ ኢኮኖሚያቸው በቶሎ ሊያገግም የሚችል አምስት አገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አገራት ከበሽታ ጋር በሚያደርጉት ትግል በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ከዚህ አንጻር ከወረርሽኙ በኋላ የትኞቹ አገራት በተሻለ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንደሚመለሱ ባለሙያዎች ለመገምገም ሞክረዋል። ይህንን በተሻለ ለመረዳት የኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነው ኤፍ ኤም ግሎባል የ2019 ዓለም አገራት የምጣኔ ሃብት ፈተናን የመቋቋም አቅም አመላካች ደረጃን ተመለከትን። በዚህም አገራት ለቫይረሱ የሰጡትን የመጀመሪያ ምላሽ ከግምት በማስገባት ቀውሱን በተረጋጋ መንገድ የሚወጡበትን ሁኔታና የመቋቋም ዕድላቸው ተቃኝቷል። በደረጃ ጠቋሚው በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ዴንማርክ ከቫይረሱ ስርጭት አንፃር ማኅበራዊ ርቀት እንዲተገበር በፍጥነት እርምጃ ወስዳለች። ጥቂት በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንደተገኙ ነው ትምህርት ቤቶችን፣ አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችንና ድንበሯን በፍጥነት በመዝጋት ውሳኔዋ ውጤታማ መሆኑን ያረጋገጠችው። የዴንማርካዊያን ባህል የሆነው በመንግሥት ላይ እምነት ማሳደርና ለጋራ ዓላማ አብሮ የመቆም ፍላጎት በእርምጃዎቹ ውጤታማነት ላይ አውንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። እናም ብዙ ሰዎች ለሕዝብ ጤና ሲሉ መስዋዕት የማድረግ የሞራል ግዴታ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በዚህ ወቅት ዴንማርክ የሠራተኞችን ደመወዝ እስከ 90 በመቶ ድረስ ለመክፈል መወሰኗ እንደ ምሳሌ እንድትታይ አድርጓታል። ይህን ግን ቀላል አይደለም። እርምጃው ከጠቅላላው የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 13 በመቶውን ያህሉን ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ሲንጋፖር በጠንካራ ኢኮኖሚዋ፣ በአነስተኛ የፖለቲካ አደጋ፣ ጠንካራ መሠረተ ልማት እና ዝቅተኛ ሙስና በደረጃ ጠቋሚው 21ኛ እንድትሆን አድርጓታል። አገሪቱ ቫይረሱን ለመቆጣጠር በፍጥነት ከመንቀሳቀስ ባለፈ ስርጭቱም የተረጋጋ ነው። ቫይረሱን በመዋጋት ረገድ በግልጽነት በሚሰራው መንግሥት ላይ ሕዝቡ ከፍተኛ እምነት አለን። መንግሥት አንድ ውሳኔ ካስተላለፈ ሁሉም ተገዢ ሆኖ ተግባራዊ ያደርጋል። እንደ ትንሽ አገርነቷ የሲንጋፖር በጣም ስኬታማ መልሶ የማንሰራራት ውጤት ለማስመዝገብ በተቀረው ዓለም የማገገም ሂደት ላይ የተመሠረተ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ሰፊ ጂኦግራፊያዊ ቦታ መያዟ በደረጃ ጠቋሚው ላይ በሦስት የተከፈለች ሲሆን በአጠቃላይ ጥሩ ደረጃ ይዛለች። ቫይረሱ እንደ ኒው ዮርክ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ፈታኝ ሲሆን፤ የሥራ አጥነት መጠኑም ታሪካዊ በሚባል ደረጃ ከፍ ብሏል። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የተወሰደው አስገዳጅ የእንቅስቃሴ ገደብና ሌሎችም ለዚህ በምክንያትነት ተቀምጠዋል። ነገር ግን የአሜሪካ መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የማነቃቂያ እርምጃዎችን በፍጥነት መውሰዱና ማኅበራዊ ርቀት መጠበቅ መተግበሩ ውጤት በማምጣት የቫይረሱ አጠቃላይ ተፅእኖን ሊቀንስና ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ማገገም ሊያስገኝ ያስችላል። 21 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማበረታቻ ይፋ ያደረገችው አሜሪካ፤ ሩብ ያህሉን የዓለም አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርትን በመያዟ ወሳኝ የሚያደርጋት ሲሆን የዓለም ምጣኔ ሃብት ማገገም በአሜሪካ ውጤታማነት ላይ ጥገኛ እንደሆነ ይነገራል። በቅርብ በተደረጉት በኮርፖሬት አስተዳደር ማሻሻያዎች ምክንያት ሩዋንዳ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በደረጃ ጠቋሚዎች ውስጥ ትልቁን መሻሻል በማድረግ በዓለም ላይ የ77ኛ ደረጃን፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአራተኛ ደረጃን ይዛለች። ከሁሉም በላይ ደግሞ በአውሮፓዊያኑ 2019 በጎረቤትዋ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ድንበር ላይ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር ከቻለች በኋላ እንደዚህ ዓይነቱን ቀውስ ለመከላከል በጥሩ ሁኔታ የተቀመጠች ይመስላል። ሁለን አቀፍ የጤና አጠባበቅ፣ የህክምና ቁሳቁስን በሚያደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) እገዛ እና በድንበር ላይ የሙቀት ልየታ በማድረግ ሩዋንዳ በዚህ ቀውስ ወቅት ከሌሎች የአካባቢው አገራት አንጻር ጥንካሬዋን ጠብቃ ትቆያለች። ሩዋንዳ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ቤት ለቤት ነፃ ምግብ እያሰራጨች የምትገኝ ሲሆን ይህም ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት የመጀመሪያዋ ያደርጋታል። የቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚገጥመው ይጠበቃል። ሩዋንዳም ለብዙ የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖች ተወዳጅ መድረሻ ናት። አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሚሆኑ እና በፍጥነት ለማገገም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳላት ይታመናል። ኒውዚላንድ በደረጃ ጠቋሚው የ12ኛ ቦታን ይዛለች። አገሪቱ ድንበሮችን ለዓለም አቀፍ ተጓዦች በመዝጋትና አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችን በፍጥነት በመዝጋት የቫይረሱ ስርጭትን ለመቆጣጠር መንቀሳቀስ ችላለች። ቱሪዝምና የወጪ ንግድ የምጣኔ ሃብቷ ዋና አካል ሲሆኑ ኒውዚላንድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያጋጥማታል ተብሎ ተሰግቷል። ነገር ግን ይህ የግድ መጥፎ ውጤት ላይኖረው ይችላል። ወረርሽኙ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳርፈው ጉዳት ቀላል የሚሆን ባይሆንም ኒወ ዚላንድ ግን ይህንን ተቋቁማ ለማገገም ብዙም እንደማትቸገር የምጣኔ ሃብት ሙያተኞች ያምናሉ።", "ላይቤሪያ 4 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ አሮጌ የገንዘብ ኖቶችን አቃጠለች የላይቤሪያ ማዕከላዊ ባንክ ያረጁ እና የተበላሹ የገንዘብ ኖቶችን በአዲስ ለመተካት በሚል አራት ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ አሮጌ የገንዘብ ኖቶችን አቃጥሏል። በአገሬውም የመገበያያ ገንዘብም የተቃጠለው 600 ሚሊዮን የላይቤሪያ ዶላር ነው። የገንዘብ ኖቶቹ እንዲወገዱ የተደረጉትም መንግሥት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አዳዲስ ኖቶችን ቢያትምም አሮጌዎቹ በስርጭት ላይ ይገኛሉ የሚለውን ስጋት ተከትሎ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአውሮፓውያኑ 2018 ከፍተኛ መጠን ያለው የመንግሥት ገንዘብ ጠፍቷል የተባለ ሲሆን እንዲሁም ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ አዲስ የታተሙ የላይቤሪያ የገንዘብ ኖቶች ጠፍተዋል የሚል ክስም እየቀረበ ይገኛል። ማዕከላዊ ባንኩ ይህንን አይቀበለውም የተባለው ገንዘብ በባንክ ካዝና ውስጥ መቀመጡን ገልጿል። የፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ መንግሥት አሮጌውን የላይቤሪያ ዶላር ለመተካት እና የሀገር ውስጥ ምንዛሬን ለማጠናከር በዚያው አመት ከሀገሪቱ የመጠባበቂያ ሂሳቦች ያወጣውን 25 ሚሊዮን ዶላር እስካሁን አልተካም። ይህንን ሊቀበሉ ያልቻሉ የተሟጋች ቡድኖች ማብራሪያ እና ተጠያቂነት እንዲኖር እየጠየቁ ነው። የላይቤሪያ ምጣኔ ኃብት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መንገዳገድ ቢያሳይም ነገር ግን ፕሬዚደንት ዊሃ በዚህ አይስማሙም በቅርቡ ለፓርላማ ባደረጉት አመታዊ ንግግር ኢኮኖሚው የተረጋጋና እያደገ ነው ብለዋል።", "ምጣኔ ሐብት ፡ ከብር ለውጡ በኋላ የወርቅ ዋጋ ለምን ጨመረ? ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ መደብሮች የወርቅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ነጋዴዎችና ገዢዎች ለቢቢሲ ገለጹ። ቢቢሲ በመሐል አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ የወርቅ መሸጫ መደብሮች ተዘዋውሮ እንደተረዳው የወርቅ መግዣ እና የመሸጫ ዋጋዎች ላይ ጭማሪዎች ታይተዋል። በተለይ ኢትዮጵያ የብር ኖቶቿን መቀየሯን ይፋ ካደረገችበት ከመስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ ጭማሪው በተለይ ከፍ ማለቱን በአዲስ አበባ ከተማ በወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እና ሠራተኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ አዲስ አበባ ውስጥ ዋነኛ የወርቅ መሸጫ መደብሮች በሚገኙበት በፒያሳ አካባቢ ቅኝት ባደረገበት በባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ 21 ካራት ወርቅ በግራም ከሦስት ሺህ ሰባት መቶ ብር እስከ አራት ሺህ ብር ይሸጣል መባሉን ከነጋዴዎቹ ለማረጋገጥ ችሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስከረም አስራ ሰባት ቀን ያስቀመጠው የወርቅ የመግዣ ዋጋ ለሃያ አንድ ካራት 2012 ብር ከስድሳ አራት ሳንቲም ሲሆን፤ የጥራት ደረጃው ላቅ ላለው የሃያ አራት ካራት ወርቅ ደግሞ 2300 ብር ከአስራ ስድስት ሳንቲም ዋጋ ሆኖ ተቀምጦለታል። ባለፉት ጥቂት ወራት የወርቅ ዋጋ ጭማሪ ሲያሳይ መቆየቱን ቢቢሲ አግኝቶ ካናገራቸው የወርቅ መሸጫ መደብሮቹ ባለቤቶች እና ሠራተኞች ተረድቷል። ይሁንና የወርቅ ዋጋ ጭማሪው በተለይ የብር ኖቶች መቀየር ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የበለጠ ከፍ ማለቱን በወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩት ነጋዴዎች ጨምረው ተናግረዋል። \"ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በግራም እስከ አምስት መቶ ብር ድረስ ጨምሯል\" ስትል በአንድ የጌጣጌጥ መሸጫ መደብር ውስጥ የምትሰራ እንስት ለቢቢሲ ተናግራለች። ከግለሰቦች ቀለበት፣ ሃብል፣ የጆሮ ጉትቻና የመሳሰሉ የወርቅ ጌጣጌጦችን በመግዛት አትርፎ በመሸጥ የሚተዳደርና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ አንድ ወጣት ደግሞ ጭማሪው ከሽያጭ በተጨማሪም በግዢም ላይ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ተናግሯል።

\"ከአንድ ወር በፊት አንድ ግራም የሃያ አንድ ካራት ወርቅ አንድ ሺህ ብር፤ ከፍ ሲል ደግሞ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ከሰው ላይ እገዛ ነበር\" የሚለው ወጣት \"ባለፈው አስራ አምስት ቀን ውስጥ ግን ብዙ ጭማሪ አሳይቷል\" በማለት ባለፈው አርብ አንድ ግራም ወርቅ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ብር መግዛቱን ተናግሯል። ከሌላው ጊዜ በተለየ ወርቅ የሚገዙ ሰዎች ፍላጎት መጨመር ዋጋውን ማናሩን የሚናገረው ይህ ወጣት፤ ከብር ኖቶች ቅያሪው ጋር ተያይዞ የተከማቸ ገንዘብን ወደአስተማማኝ ውድ ዕቃ መቀየር የሚፈልጉ ሰዎች ሳይኖሩ እንደማይቀሩ ግምቱን አስቀምጧል። \"የገንዘብ ኖቶች ለውጡ ሳይጠበቅ ዱብ ያለ በመሆኑ ውዥንብር እና እርግጠኛ ያለመሆን ስሜቶች ፈጥሯል\" የሚሉት የምጣኔ ሐብት ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልመናን መሃመድ ናቸው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ገንዘብ በእጃቸው ላይ ያላቸው ሰዎች ደኅንነታቸው አስተማማኝ በሆኑ ንብረቶች ላይ ብራቸውን ለማዋል መፈለጋቸውን በወርቅ ግብይቱ ላይ የታየውን የዋጋ ለውጥ እንደምሳሌ በማንሳት ይገልፃሉ፤ \"ይህም በእነዚህ ንብረቶች ዋጋ ላይ የመናር ምክንያት ሊሆን ይችላል\" ባይ ናቸው። \"መኪና እና ቤትን የመሳሰሉ ቋሚ ንብረቶችን እንዲሁም ወርቅን የመሳሰሉ ሌሎች ንብረቶች ላይ ገንዘብን ማዋል እንደአማራጭ ስለሚወሰድ ተፈላጊነታቸው መጨመሩ የሚጠበቅ ነው\" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት አብዱልመናን፤ በሕገ ወጥ መልኩ የተገኘ ገንዘብን ለመሸሸግም ወርቅ ቀላል መንገድ ነው ይላሉ። 

\"ስለዚህም የወርቅ የዋጋ ጭማሪን የፈጠረው የገንዘብ ኖት ለውጡ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም\" ሲሉ እምነታቸውን ይገልጻሉ። ባለፈው ዓመት ወርሃ ግንቦት ላይ ብሔራዊ ባንክ ከ63 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ወርቅ ወደ ገበያ መቅረቡን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የባንኩ ገዥ የሆኑት ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ይህ የተጠቀሰው የወርቅ መጠን ከፍተኛ እንደነበርና ለመንፈቅ ዓመት ያህል የቁልቁል ይጓዝ የነበረው የወርቅ አቅርቦትን መጠን የቀየረ መሆኑን ተናግረው ነበር። ለወትሮውም ብሔራዊ ባንክ ወርቅን በሚገዛበት እና በነጋዴዎች ገበያ ላይ በሚሸጥበት ዋጋ መካከል ልዩነት መኖሩን የጠቀሱት ባለሞያው፤ ይህም ጌጣጌጥ ቤቶች ለንድፍ ሥራዎች፣ ለአገልግሎት ወጪዎች እና ለትርፍ በሚጨምሩት ገንዘብ ምክንያት ይመጣ እንደነበር ያስረዳሉ። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ወደ ውጭ በሚላክ ወርቅ መጠን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ነበረው የሚሉት አብዱልመናን ይህንን ከግምንት ውስጥ በማስገባት በወርሃ ሐምሌ በብሔራዊ ባንክ የዋጋ ሽግሽግ ተደርጓል ብለዋል።", "የነዳጅ ድጎማ መነሳትና ሊያስከትል የሚችለው ጫና የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አሳውቋል። በዚህም አስካሁን ከታዩት የዋጋ ጭማሪዎች ሁሉ ከፍተኛው እንደሆነ ተነግሯል። መንግሥት እንደሚለው የነዳጅ ምርቶችን ለመደጎም በወር በአማካይ 10 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ በመግለጽ፣ በአሁኑ ወቅት 146 ቢሊየን 624 ሚሊየን 248 ሺህ 889 ብር የነዳጅ ድጎማ ዕዳ አለበት ተብሏል። ቀደም ሲል መንግሥት በየወሩ በሚያደርገው የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ላይ ጭማሪው ከ10 በመቶ የሚበልጥ አልነበረም። አሁን ግን ይህንን የመንግሥት ድጎማውን ደረጃ በደረጃ ለማንሳት ባወጣ ዕቅድ መሠረት በቤንዚን ላይ ከ25 በመቶ በላይ፣ እንዲሁም በናፍጣ ላይ ከ35 በመቶ በላይ ጭማሪ ተደርጓል። መንግሥት እንደሚለው በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዋጋ ቢሰላ የ1 ሊትር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ ብር 91 ከ23 ሳንቲም እና የቤንዚን ደግሞ በሊትር 82 ብር ከ07 ሳንቲም መሆን ነበረበት። በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ደግሞ ዋጋው ከዚህ ከፍ ይላል። ነገር ግን አሁንም መንግሥት 75 በመቶውን ጭማሪ እራሱ በመሸፈን 25 በመቶውን ብቻ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ ማድረጉ ተገልጿል። የትኛውም የምርትና የአገለግሎት አቅርቦት በአንድም ሆነ በሌላ በኩል ከነዳጅ ዋጋ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ፣ ሕዝቡን ባስጨነቀው የኑሮ ውድነት ላይ ሌላ ጫናን ሊፈጥር ይችላል እየተባለ ነው። የአሁኑ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ክለሳ እንዲሁም በቀጣይ የሚደረገው የዋጋ ማስተካከያ የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ ከጥቂት ሳምንት በፊት ያዘጋጀነው ጥንቅር በዝርዝር ይዳስሳል። እነሆ . . . መንግሥት የውጭ ምንዛሬን በስስት ነው የሚያየው። እንደ ስእለት ልጅ። የዶላር ጥሪት እንደዋዛ አይቋጠርማ። በብዙ አበሳ፣ በብዙ የወጭ ንግድ፣ በብዙ ተጋድሎ ነው የሚመጣው። እንዲያም ኾኖ ጥሎበት ከአራት ቢሊዮን ዶላር አይዘልም። እሱም ቢኾን መጥቶ አይበረክትም፤ አብዛኛውን ነዳጅ ይጠጣዋል። ይሁን እንጂ፣ እስከዛሬ ድረስ ለነዳጅ የሚከፈለው ዶላር በወጭ ንግድ ከሚገኘው ዶላር በልጦ አያውቅም ነበር። አሁን ግን ታሪክ ተቀየረ፤ ነገሩ ከፋ። ይህ በይፋ የታወቀው ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነው። ለ2015 ነዳጅ መግዣ የሚያስፈልግህ ስንት ነው ሲባል 5.6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ። እንዲህ ያለ አሃዝ ተሰምቶ አይታወቅም ነበር፤ ይህም የመርከብና የነዳጅ ዋጋ መናር ያመጣው ነው ይባላል። ታዲያ ይህ ገንዘብ ከየት ይመጣል? አንደኛ ከውጭ ንግድ እንዲህ ዓይነት ገቢ በጭራሽ ኖሮን አያውቅም። ቡናው፣ ሌጦው፣ ሰሊጡ ተረባርበው ከአገር ወጥተው እንኳ እንዲህ ዓይነት ገቢን አያመጡም። አሳሳቢው ይህ ብቻ በሆነ መልካም። ነዳጁ ከዚህም ከዚያም ዶላር ተፈልጎ ሊገዛ ይችላል። ከተገዛ በኋላም ግን መደጎም አለበት። ከተገዛበት ዋጋ በግማሽ ቀንሶ እንዲሸጥ መደጎም አለበት። ለዚህ ድጎማ ደግሞ አገሪቱ በወር በአማካይ 10 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋታል። አንድ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ከሰሞኑ ለኢዜአ እንደተናገሩት ድጎማው መንግሥትን በጠቅላላው 132 ቢሊዮን ብር ለሚደርስ የዕዳ ክምችት ዳርጎታል። መንግሥት ይህን ህመሙን ለዓመታት ቻል አርጎት ቆየ። በኮቪድ ዘመን የዓለም የነዳጅ ዋጋ መሬት ሲነካ ህመሙን ለጊዜውም ቢኾን አስታግሶለት ይሆናል። ከኮቪድ በኋላ ግን የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ተቀጣጠለ። በእንቅርት ላይ. . . እንዲሉ የዩክሬን ጦርነት ተቀሰቀሰ። በዚህ ጊዜ በዓለም ነዳጅ ዋጋ ላይ ‘ሰደድ እሳት’ ተነሳ። ነዳጅ በዩክሬን ጦርነት ማግስት በበርሜል 140 ዶላር የደረሰበት ጊዜ ነበር። ይህ ዋጋ ሃብታም አገራትን ሳይቀር ሚዛናቸውን አስቷቸዋል። እዚህ ግባ የሚባል የተፈጥሮ ሃብት ለሌላት፣ የባሕር በር ለሌላትና ሰላም ለራቃት አገር ይህ ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል ማብራሪያ አይሻውም። “የማይካደው ነገር በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከአንዳንድ የነዳጅ አምራች አገራት ጋር ሲነጻጸር እንኳ ርካሹ ነው” ይላሉ ተቀማጭነታቸውን በኩዌት ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ተመራማሪው አየለ ገላን። “ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጋር ቢነጻጸር እንኳ የኢትዮጵያ ነዳጅ ዋጋ በትንሹ አነስ ሳይል አይቀርም።” ይህን የሚሉት ድጎማው ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ለማስረዳት ነው። እኚህ ተመራማሪ ድጎማው ከፍተኛ መሆኑን ይግለጹ እንጂ መንግሥት ድጎማውን፣ በተለይ አሁን ላይ፣ ለማንሳት መወሰኑን በፍጹም አይስማሙም። “የነዳጅ ድጎማውን ማንሳት እየነደደ ያለ ቤት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው” ሲሉ የመንግሥትን ዕቅድ ይተቹታል። የነዳጅ ድጎማ በሂደት የተወለደ ሐሳብ ነው። የሕዝብ የመግዛት አቅም ሲያሽቆለቁል፣ የነዳጅ ዋጋ ሲያሻቅብ ድጎማ ተወለደ። ፖሊሲ ሳይሆን ሒደት ወለደው ማለቱ ይቀላል። “በመሠረቱ ይህ ድጎማ ሲጀመርም በፖሊሲ ተደግፎ አያውቅም” ይላሉ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ። “ነዳጅ እንዲሁ በቁጥጥር ሥርዓትና በዋጋ ማረጋጊያ ሰነድ የሚመራ እንጂ በፖሊሲ የተደገፈ የድጎማ ሥርዓት ኖሮት አያውቅም።” ለነዳጅ ሁነኛ መመሪያ የወጣለት ከሦስት ዐሥርታት በፊት ነው። በ1993 ዓ.ም. የነዳጅ ፈንድ ተመሠረተ። የነዳጅ ፈንድ ዋጋን የማረጋጋት ሚናን እንዲጫወት ነበር የታሰበው። ይህም ማለት መንግሥት ከዓለም ገበያ ነዳጅ ይገዛል። ከዚያ አገር ውስጥ ሲሸጥ ሽርፍራፊ ሳንቲሞችን ወደዚህ የነዳጅ ፈንድ እያስገባ ያጠራቅማል። ለምሳሌ ነዳጅ ተገዝቶ ተተምኖ ወደ ገበያ ሲወጣ 21 ብር ከ80 ሳንቲም ቢሆን መንግሥት 22 ብር ይሸጠውና 20 ሳንቲሟ ተጠራቅማ ለሚቀጥለው ድጎማ ትውላለች። በዚህ አሠራር የተወሰኑ ቢሊዮን ብሮች በዚህ የነዳጅ ፈንድ እየተጠራቀሙ ቆዩ። ኾኖም ነዳጅ የሚጨምርበት ፍጥነትና ይህ ፈንድ የሚለቃቅማቸው ሳንቲሞች ሊገናኙ አልቻሉም። የእርምጃና የ100 ሜትር ሩጫ ተወዳዳሪዎችን በአንድ መም የማሮጥ ነገር መሰለ። ይህ ሁኔታ በተለይ ከ2003 ዓ.ም. ወዲህ ጭራሽ ሊገናኝ አልቻለም። ከዚህ ወዲያ ነበር ከመንግሥት ካዝና ቢሊዮን ብሮች እየወጡ ነዳጅን በቀጥታ መደጎም የተያዘው። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነዳጅ ድጎማው በየወሩ እየተከለሰ ዋጋው ከዓለም ዋጋ ከፍና ዝቅ ጋር እየተነጻጸረ እንዲስተካከል ይደረግ ነበር። “ይሁንና ከ2009 ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ የተከለሰው ለ5 ጊዜ ብቻ ነው’’ ይላሉ በቀለች ጫናውን ምን ያህል መንግሥት ተሸክሞት እንደቆየ ለቢቢሲ ሲያስረዱ። ይህ ግን አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ሁኔታ አንጻር የሚያስቀጥል አልሆነም። በዚህ የተነሳ አገሪቱ ከነዳጅ ጋር በተያያዘ በቀጣይ አካሄዷን ለማስተካከል ተገዳለች። የዓለም ዋጋን ያንጸባረቀ ዋጋን ከሕዝብ ጋር ለመጋራት ቆርጣለች። ሕመሜን አስታሙልኝ ነው ነገሩ። በዚህ ጊዜ ለምን እዚህ ውሳኔ ላይ ተደረሰ? ስንል የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስትር መሥሪያ ቤትን ጠይቀናል። “በዚህ ኑሮ እሳት በሆነበት ጊዜ መሆኑ አደጋ የለውም ወይ?’’ ስንል የምጣኔ ሃብት አዋቂዎችን አወያይተናል። በቀለች ኩማ ድጎማውን በዚህ ወቅት ማንሳቱን የሚመለከቱት በተለየ መነጽር ነው። ነገሩን መንግሥት ላይ እያሳደረ ካለው የዕዳ ጫና ብርቱነት፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ መቀጣጠል እና ከሕገ ወጥ ንግድ መበራከት አንጻር መመልከትን ይመርጣሉ። “ድጎማው ከጥቅሙ ጉዳቱ በዛ” የሚሉት በቀለች በዋቢነት የሚያነሱት ሕገ ወጥ የኮንትሮባንድ ነዳጅ ንግድ መበራከትን ነው። ይህ አየር በአየር ሽያጭ አገሪቱን ለከፍተኛ ዕዳ ዳረጋት። በውድ የውጭ ምንዛሬ የሚደጎመው ነዳጅ እያከበረ ያለው ኮንትሮባንዲስቶችን ነው፤ ባለጸጎችን ነው፤ ሲሉ ያስረዳሉ። እርግጥ ሕዝብ ይደጉማል የተባለ ውድ ነዳጅ ማደያ ሳይደርስ ጎረቤት አገር ይቸበቸብ እንደነበር አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ቢሆንም ግን በዚህ ወቅት ቁጥጥርን ማጥበቅ እንጂ ድጎማን ማንሳት ያስኬዳል? ይህ ብቻ ግን አይደለም ድጎማ የማንሳቱ መንስኤ ይላሉ በቀለች፣ “ድጎማው በፖሊሲም ያልተደገፈ ከመሆኑ የተነሳ ጥቅል ድጎማ ነው የነበረው።’’ እርግጥ ድጎማው የጅምላ ድጎማ መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይም አጥብቀው የሚኮንኑት ጉዳይ ነው። ጥቅል ድጎማ ሲባል ምን ማለት ነው? ሃብታምና ድሃን፣ ቤንትሌና ሃይገርን፣ ሊሞዚን፣ መርሴዲስን እና ‘ቅጥቅጥ አይሱዙን’ በእኩል መደጎም ማለት ነው። ኢኮኖሚስቱ አቶ ዋሲሁን፣ “መንግሥት የኤምባሲ መኪናንም የከተማ አውቶቡስንም በአንድ ሲደጉም ነው የኖረው” የሚሉት ለዚሁ ነው። የእስከዛሬው የነዳጅ ድጎማ ከመሠረታዊ የድጎማ (subsidy) ጽንሰ ሐሳብ ጋር የሚጻረር እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች የሚስማሙበት ነጥብ ነው። ድጎማ በባህሪው የአጭር ጊዜ መፍትሄ ነው። የአጭር ጊዜ መሆን ብቻም ሳይሆን ማሳካት የፈለገው ግብ በውል ተለይቶ መቀመጥ አለበት። መቀመጥ ብቻም ሳይሆን ዓላማውን አሳክቷል ወይ ተብሎ መፈተሽ አለበት። ሁሉም ባለሙያዎች የሚሉት ይህንን ነው። በዚህ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ድጎማው ውሉን የሳተ ነበር ብለው ያምናሉ አቶ ዋሲሁን። እሳቸው መደጎም ያለበት የሚሉት በዋናነት ምርትን ማሳደግ የሚችለውን ዘርፍ ነው። ነዳጅ በኢትዮጵያ ሁለት ሚና አለው፤ አንዱ ለፋብሪካዎች የኃይል ምንጭ መሆን ነው፤ ሌላው ትራንስፖርት ነው። በኢትዮጵያ ብዙ አምራች ተቋማት የማምረት አቅማቸው 40 ከመቶ አይሞላም። አንዱ ምክንያታቸው ታዲያ በቂ ኃይል ስለማያገኙ ነው። ስለዚህ መብራት በጠፋ ጊዜ ጄኔሬተር ይለኩሳሉ። ጄኔሬተር ነዳጅ ይጠጣል። ለእነዚህ አምራቾች ቢቻል አስተማማኝ ኃይል ማቅረብ ወይም መደጎም ምርታማነትን ይጨምራል። የኤምባሲ መኪናን ነዳጅ መደጎም ግን ምርታማነት አይጨምርም። ነዳጅን የምትደጉመው ኢትዮጵያ ብቻ ናት? ጥቂት የማይባሉ አገራት ነዳጅን ይደጉማሉ። ካልደጎሙም የኅብረተሰቡ የመግዛት አቅማቸው ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ድጎማ ግቡ ምንድነው? “ማክሮ ኢኮኖሚ እንዳይዛባ፣ ምርትና ምርታማነት እንዳይጎዳ፣ ባለመደጎም የሚመጣ ውስብስብ ኢኮኖሚያዊ መዘዝ ሲኖር ድጎማ አግባብ ሆኖ ሊታይ ይችላል’’ ይላሉ አቶ ዋሲሁን። “ይሄ መንግሥት ግን ከአቅሙ በላይ ብዙ ነገር የሚደጉም መንግሥት ነው፤ ክፋቱ ደግሞ መደጎም የሌለበትንም ይደጉም ነበር።” ለነዳጅ ድጎማ የሚወጣው ከፍተኛ ገንዘብ የኢትዮጵያ መንግሥትን ጀርባው መጉበጡን የምጣኔ ሃብት አዋቂው አቶ አየለ ገላን ያምናሉ። ነዳጅ በኢትዮጰያ የሚሸጥበት ዋጋ አገሪቱን ነዳጅ አምራች እንዳስመሰላትም አልሸሸጉም። የእርሳቸው ልዩነት የሚነሳው ድጎማን በማንሳት ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ነው። “የኢትዮጵያ ሸማች የመግዛት አቅም ደቃቃ ነው። ከሕዝብ አንጻር ስናየው እንዲያውም ድጎማው በቂ አልነበረም ልንል እንችላለን’’ ካሉ በኋላ መንግሥት ከድጎማ በፊት መሥራት የነበረበትን የቤት ሥራ አልሠራም ሲሉ ሂደቱን ክፉኛ ይተቻሉ። እነዚህ የቤት ሥራዎች ምን ነበሩ? “አንደኛ ኢኮኖሚው ተመሰቃቅሏል። ምርት አላደገም፣ የሕዝብ የመግዛት አቅም አልጨመረም። ጥቃቅን ኢንዱስትሪዎች በእግራቸው እንዲቆሙ አልተደረገም። የሕዝብ ደኅንነት አልተጠበቀም።...” መንግሥት እነዚህን መልከ ብዙ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ምስቅሎሽን ሳያስተካክል፤ ኢኮኖሚውን ጠንካራ መሠረት ላይ ሳያስቀምጥ ድጎማ ማንሳት (የእርሳቸው ቃል ለመጠቀም) “ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው።’’ አቶ ዋሲሁን ከድጎማው መነሳት ማግስት ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ትንቢታዊ ጥያቄ በቀጥታ መጋፈጥን የመረጡ አይመስልም። ነገር ግን የመንግሥት ድጎማን የማንሳት ውሳኔን ከጥንቃቄ ጋር በአውንታዊ መልኩ ይረዱታል። “የድጎማ ሥርዓቱ (በአንድ ጥናት ላይ እንደታየው) 70 ከመቶ የሚሆነውን ድሃና 30 ከመቶ የሚሆነውን ሃብታም ነው ሲደጉም የኖረው። ስለዚህ ጤናማ ድጎማ አልበረም። ለድሃ የታሰበው ድጎማ ሃብታም ሲደጉም ነው የኖረው።’’ ስለዚህ በእሳቸው ዕይታ ከዚህ ወዲህ ድጎማው ለታሰበለት ሕዝብ ብቻ ስለመድረሱ እርግጠኛ መሆን ያሻል። “ድጎማ ዘዴኛና መለኛ (ታክቲካል) ካልሆነ ውሉን ሳተ ማለት ነው። ድሃው ነው የሚደጎመው ከተባለ ድጎማው ድሃው ጋር መድረሱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል’’ የሚሉት አቶ ዋሲሁን ነዳጅ በሞያሌ እየወጣ ሲሸጥ፣ አውቶቡስና የኤምባሲ መኪና አብሮ ተሰልፎ በአንድ የዋጋ ተመን ነዳጅ ሲቀዳ ድጎማ ግብ እንደተሳተ ምልክቶች ሆነው ይታያሉ። በዚህ ሐሳብ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስትርም ባልደረባም ይስማማሉ። “የሚደጎምና የማይደጎምን በጥናት መለየት ያስፈለገውም ለዚሁ ነው ይላሉ” በቀለች ኩማ። ከድጎማ የተረፈው ገንዘብ ምን ላይ ይውል ይሆን? አቶ ዋሲሁን ከድጎማ መነሳቱ ይልቅ ከድጎማ የዳነው ገንዘብ የት እንደሚውል በእጅጉ ያሳስባቸዋል። “አሁን ያለው ኢኮኖሚ በግጭትና በጦርነት የቆሰለ ኢኮኖሚ ነው። ከፍተኛ ወጪዎች ይጠብቁታል። በወጪና ገቢ ልዩነት ማጥበብ ላይ ካልተሠራ የከፋ ሀኔታ ሊመጣ ይችላል” ይላሉ። ከፍተኛ የበጀት ጉድለት ደግሞ ወደ ገንዘብ ማተም ስለሚወስድ ለበለጠ የበጀት ቅርቃርና ኑሮ ውድነት ሊወስድ ይችላል የሚል ፍርሃት አላቸው። ስለዚህ መንግሥት ከድጎማ ወጪ ያዳነውን ገንዘብ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሊያውለው ይገባል። “መንግሥት ማኅበረሰቡ ወጪውን እንዲጋራው መሞከሩ መጥፎ ነው ወይ? ብትለኝ እኔ መጥፎ ነው ብዬ አላስብም። ነገር ግን ገንዘቡ ለአበልና ለድግስ ከዋለ ነው ችግሩ።” አሁን በዓለም ገበያ ሰማይ የነካውን ነዳጅ መንግሥት በግማሽ ቀንሶ ነው ለሕዝብ የሚያደርሰው። ቀድም ባሉ ዓመታት በሊትር 5 እና 6 ብር ነበር የሚደጉመው። አሁን ያን ለማድረግ የሚያስችል አቅምን አጥቷል። በውስጣዊና ውጫዊ ዝርዝር ምክንያቶች። ምክንያቶቹን አቆይተን ነገር ግን መንግሥት በዚህ ድጎማ አሠራር ከሐምሌ ወዲያ መሻገር ይችል ነበር ወይ ብለን እንጠይቅ። በሌላ አነጋገር መንግሥት ደግ ሆኖ ልደጉም ቢልስ ይችላል ወይ? የብዙ ኢኮኖሚስቶች ምላሽ በአጭሩ ሲቀመጥ “አይችልም” የሚል ነው። ምክንያቱም፣ “...ሚያዝያ ወር ላይ ብቻ ዕዳው 124 ቢሊዮን ደርሰ” ይላሉ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባልደረባ በቀለች ኩማ። ምክንያቱም፣ “...561 ቢሊዮን ብር ይዞ የተነሳ ኢኮኖሚ ነው ያለው። በዚህ ዓመት በዘጠኝ ወር የተሰበሰበው 290 ቢሊዮን ብር ነው። ልዩነቱ ሰፊ ነው። ይህን የበጀት ጉድለት ይዞ ብዙ መጓዝ አይቻልም” ይላሉ አቶ ዋሲሁን። ይሁንና ነዳጅ ድጎማው የኑሮ ውድነቱን እንዳያባብስ ምን ማድረግ ይቻላል? አቶ ዋሲሁን የነዳጅ ድጎማው በኑሮ መወደድ ላይ የሚያስከትለውን ጣጣ ማንም አያጣውም ይላሉ። ነገር ግን ያን ማስቀረት በምጣኔ ሃብት ሳይንስ የሚቻልበትን ዕድል አይታያቸውም። “የትኛውም ፖሊሲ ሁሉን አስታርቆ መሄድ አይችልም። ሁሉንም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አስደስቶ የሚያቆይ የኢኮኖሚ ውሳኔ በምድር ላይ የለም።’’ ይልቅ በቀጥታ በድጎማ መነሳት ብቻ የሚፈጠር ዋጋ ንረት ሳይሆን ድጎማ የመነሳቱ ወሬ በራሱ የሚፈጥረው የገበያ ትኩሳት ይበልጥ ያሳስባቸዋል። “እኛ አገር ነጋዴው በአጋጣሚው እንዴት በአቋራጭ ልክበር ነው የሚለው፤ የድጎማውን ጭማሪ ብቻ ደምሮ ይሸጣል ብዬ አልገምትም” ይላሉ አቶ አየለ ገላን። ከሐምሌ ወዲህ የሕዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪ ማደያ ገብቶ ነዳጅ ሲቀዳ ጂፒኤስ ተገጥሞለት ነው። ነዳጅ አቅራቢዎች ለማደያዎች ደረሰኝ ይሰጣሉ። ባለታክሲው በታሪፍ የተቀመጠውን ዋጋ ከፍሎ ይሄዳል። ማደያው በደረሰኝ ቀሪውን ያወራርዳል። ይህ አሠራር በመተግበሪያ የሚሠሩት ታክሲዎችን አይጨምርም። የመንግሥት ሰርቪሶችንም አይጨምርም። “ከዚህ በኋላ በየትኛውም ማደያ ነዳጅ ሲራገፍ የኛ ተቆጣጣሪዎች በያንዳንዱ ማደያ ተገኝተው ነው” ይላሉ የነዳጅና ኢንርጂ ሚኒስቴር ባልደረባ በቀለች ኩማ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሕዝብን ለማረጋጋት ይመስላል መንግሥት ድጎማ ማንሳቱ በኑሮ ላይ አንዳችም ጫናን አይፈጥርም የሚሉ ድምጾች እየተስተጋቡ ነው። ይህ ለምጣኔ ሃብት አዋቂዎችም ሆነ ለሰፊው ሕዝብ እምብዛምም ስሜት የሚሰጥ አይደለም። በቀለች ኩማ ግን “ድጎማ መነሳቱ በቀጥታ የሚባለውን ያህል የዋጋ ንረት አያስከትልም፤ ይህ በጥናት የተረጋገጠ ነው” ሲሉ የነገሩን ሀቅነት ይሞግታሉ። እሳቸው ጥናቱን ለቢቢሲ ለማጋራት ባይፈቅዱም የነዳጅ ድጎማ መነሳት በቀጥታ የሚያስከትለው የዋጋ ንረት እዚህ ግባ የሚባል እንዳይደለ ይጠቅሳሉ። “...ድጎማው ሲነሳ በእያንዳንዱ ሸቀጥ ላይ የሚያመጣው ጫና በሳንቲም ቤት እንደሆነ ተደርሶበታል” ይላሉ። ይሁንና ምጣኔ ሃብት ሙያተኞቹ አቶ ዋሲሁን እና አቶ አየለ ግን በዚህ ብዙም አይስማሙም። አንዱ ምክንያታቸው በኢትዮጵያ የንግድ ዘይቤ እንደታየው ዋጋ የሚወሰነው በቀጥታ በሚመጣ ጭማሪ ሳይሆን ገና በሥነ ልቦና በሚፈጠር ፍርሃትም ጭምር ስለሆነ ነው። ለብዙዎች አዲስ ዜና የሆነው ደግሞ የታለመላቸው የሚባሉት ተደጓሚዎችም ቢሆኑ ድጎማቸው ጊዜያዊ መሆኑ ነው። በቀለች ሁሉም ታክሲዎችና የሕዝብ አውቶቡሶች ሳይቀሩ በሂደት ከድጎማ ሥርዓት እንደሚወጡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በአምስት ዓመት ውስጥ ከድጎማው ሙሉ በሙሉ ይወጣሉ። በየሦስት ወሩም ዋጋ ክለሳ ይደረግባቸዋል።” የሰዉ ስሜቱ የተዘበራረቀ ነው። ኑሮ መንደድ ያለበትን ያህል በመንደዱ ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ? የሚል ስሜት ያላቸው አሉ። ነገን በፍርሃትና በሰቀቀን የሚጠብቁም አሉ። ድጎማው ሐምሌ ላይ ሲነሳ የዋጋ ጭማሪው እንደ ሐምሌ ዝናብ ዶፍ ሆኖ ሊወርድ የተሰናዳ ይመስላል። ሐምሌ አሳሳቢ ሆኖ የሚታየው ታዲያ ለተርታው ሕዝብ ብቻ አይደለም። ለጎምቱ ኢኮኖሚስቶችም ጭምር እንጂ። መቀመጫቸውን ኩዌት ያደረጉት አቶ አየለ ገላን፤ “በዚህ ጊዜ ድጎማን ማንሳት ለእኔ ስሜት የሚሰጥ አይደለም፤ ዚምባብዌ ወደ ገጠማት ኢኮኖሚ ሁኔታ የመንደርደር ያህል አድርጌ ነው የምመለከተው” ይላሉ። ምርትና ምርታማነት ፈቅ ሳይል፣ መሠረታዊ የኑሮ ደረጃ ኢምንት ሳይጨምር የገጠሩ የግብርና ኢኮኖሚ ሳያድግ አሁን ባለው ኢኮኖሚ ላይ የነዳጅ ድጎማን ማንሳት ከድጡ ወደ ማጡ ነው፤ ለእርሳቸው። በቀለች ኩማ ግን የተቀናጀ ቁጥጥርና በቂ ግንዛቤ ለኅብረተሰቡ ከደረሰ የከፋ ሁኔታ አይመጣም ባይ ናቸው። አቶ አየለ በፍጹም በዚህ አይስማሙም፤ በዚህ እሳት በሆነ ኑሮ ይህን መሠረታዊ  የነዳጅ ድጎማን ማንሳት “እየነደደ ባለ እሳት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው” ይሉታል።", "ሱዊዝ ቦይ በመዘጋቱ በየቀኑ የ9.6 ቢሊዮን ዶላር ምርት መተላለፍ አልቻለም የግብጹ ሱዊዝ የባሕር ላይ ማቋረጫ ቦይ በመዘጋቱ በየቀኑ 9.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መተላለፍ እንዳልቻሉ ተገለጸ። በሱዊዝ መተላለፊያ ላይ አንድ ግዙፍ የጭነት መርከብ ባሕሩን ዘግቶ ከማክሰኞ ዕለት ጀምሮ በመቆሙ ምክንያት እንቅስቃሴ መገታቱ ይታወሳል። ሎይድስ ሊስት የተባለው የመርከብ ጉዞ ድርጅት እንደሚለው፤ በቀን ውስጥ ከምዕራብ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩ 5.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መጓጓዝ አልቻሉም። ከምሥራቅ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩና የተስተጓጎሉ ምርቶች ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው። የባሕሩን መተላለፊያ የዘጋው መርከብ እንቅስቃሴ እንዲጀምር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች ተናግረዋል። በታይዋኑ ኤቨርግሪን ማሪን ሥር ያለው ኤቨር ጊቭን መርከብ በዓለም ትልቁ ኮንቴነር ጫኝ ሲሆን፤ 200,000 ቶን የሚመዝን እንዲሁም 20,000 ኮንቴነር ማጓጓዝ የሚችል ነው። መርከቡ በመቆሙ ሳቢያ ሌሎች መርከቦች ለቀናት መተላለፍ አልቻሉም። የባሕር ላይ ጉዞ አማካሪ ድርጅት ባለቤት ጆን ሞንሮይ ብዙ ወደቦች ላይ የሚገኙና መጓጓዝ ያልቻሉ ኮንቴነሮች እንዳሉ ይናገራል። መተላለፊያው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ምርቶች የሚተላለፉበት ሲሆን፤ የጦፈ ንግድ የሚካሄድበት መስመር ነው። ከመላው ዓለም የባሕር ንግድም 12 በመቶው የሚያልፈውም በዚሁ የግብጽ የባሕር ላይ ማቋረጫ መስመር በኩል ነው። ሎይድስ ሊስት ባወጣው አሃዝ መሠረት፤ በአሁኑ ጊዜ 160 መርከቦች በሱዊዝ ቦይ በኩል ለማለፍ እየጠበቁ ነው። ከእነዚህ መካከል 41 የሚሆኑት የተለያዩ ምርቶች ሲይዙ 24 ደግሞ ነዳጅ ጫኝ ናቸው። ቢአይኤምሲኦ የተባለው ዓለም አቀፍ የመርከበኞች ማኅበር እንደሚለው መተላለፊያው ተዘግቶ ከቆየ የምርት አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። የሎጂስቲክስ ተቋሙ ኦኤል ዩኤስኤ ፕሬዘዳንት አለን ባይር \"በእያንዳንዱ ቀን ያልተጓጓዙ ምርቶችን ለማሳለፍ ተጨማሪ ሁለት ቀናት ይጠይቃል\" ብለዋል። እስካሁን ለሦስት ቀናት መተላለፍ ያልቻሉትን ምርቶች ለማጓጓዝ ስድስት ቀናት ገደማ ሊያስፈልግ እንደሚችልም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። መተላለፊያው እስኪከፈት ድረስ ቀናት ወይም ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ በመላው ዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ጫና ያሳድራል። የዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ይህ የግብጽ የባሕር ላይ መተላለፊያ ከመዘጋቱ በፊት በኮቪድ-19 ምክንያት መቀዛቀዝ አጋትሞት ነበር። አለን እንደሚሉት፤ መርከቦች ሌላ አማራጭ የጉዞ መስምር ከፈለጉ በምዕራብ አፍሪካ በኩል በመዞር ጉዟቸውን ሊቀጥሉ ብችሉም ይህ ጉዞ ግን ከሰባት እስከ ዘጠኝ ቀናት ሊፈጅ ይችላል። አንዳንድ ተቋሞች መተላለፍ ባልቻሉ ምርቶቻቸው ምትክ ሌሎች ምርቶችን በአውሮፕላን ወይም በባቡር መላክን እንደ አማራጭ ሊወስዱ ይችላሉ። እስካሁን ድረስ ሜርስክ እና ሀፓግ ሎይድ የተባሉ ተቋሞች ከሱዩዝ መተላለፊያ መስመር ውጪ ያሉ አማራጮችን እንደሚጠቀሙ አስታውቀዋል። የግብጹ የሱዊዝ መተላለፊያ ባለሥልጣን ባሕሩን የዘጋውን መርከብ ለማስነሳት የቻለውን ሁሉ እየሞከረ እንደሆነ አስታውቋል።", "ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ባለሐብቶች ክፍት ለማድረግ ወሰነች የኢትዮጵያ መንግሥት ካቢኔ ለአስርታት ለውጭ ባለሐብቶች ዝግ ሆኖ የቆየውን የባንክ ሥራ ዘርፍ ክፍት ለማድረግ የቀረበለትን ረቂቅ ፖሊሲ አጸደቀ። በአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አማካይነት ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ ለዘመናት ለኢትዮጵያውያን ብቻ ተትቶ የነበረውን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ባንኮችም ክፍት እንዲሆን የሚፈቅድ ነው። ይህም በዘርፉ ታዋቂ የሆኑ ዓለም አቀፍ ባንኮች በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ እንዳይሰማሩ አድርጎ የቆየውን የአገሪቱን የፋይናንስ ፖሊሲ የቀየረው ውሳኔ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ይፋ ሆኗል። በዚህም ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ ለአገር ውስጥ ባለሐብቶች ብቻ ክፍት አድርጋው በቆየችው ዘርፍ ለመሳተፍ እድል ይፈጥርላቸዋል። የፋይናንስ ዘርፉ ዝግ ሆኖ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥ የአገሪቱን ምጣኔ ሐብት በተለያዩ መስኮች ሲደግፉ የቆዩት ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አገራት ዘርፉን እንድትከፍት ሲወተውቱ ቆይተዋል። ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ የቀረበውን ረቂቅ ፖሊሲ አጽድቆ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔውን ይፋ ባደረገበት መግለጫው እንዳለው የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ “አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገሪቱን ምጣኔ ሐብት ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር የበለጠ እንዲተሳሰር ለማድረግ ያስችላል።” ብሏል። በተጨማሪም ይህ እርምጃ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን በማቀላጠፍ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን በማጎልበት ለምጣኔ ሐብት ዕድገት አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል። ለረጅም ዘመናት በመንግሥት እና በአገር ውስጥ ባለሐብቶች ተሳትፎ ብቻ ተይዘው የቆዩ ዘርፎችን የመክፈት ፍላጎት እንዳለው ሲገልጽ የቆየው መንግሥት አሁን የባንኩን ዘርፍ ክፍት አድርጎታል። ይህ ዘርፍ ለውጭ ባለሐብቶች ክፍት ሊሆን እንደሚችል እና ዝግጅትም እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተለያዩ አጋጣሚዎች ፍንጭ ሲሰጡ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በተለይ በመንግሥት ተይዘው የሚገኙ ዘርፎችን ከፍት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለ የተነገረ ሲሆን ተግባራዊነቱ ግን አዝጋሚ ሆኖ ነበር። ከ120 ዓመት በላይ በመንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ተይዞ የነበረው የቴሌኮም ዘርፍ ለውድድር ክፍት ሆኖ፣ ከአንድ ዓመት በፊት በተካሄደ ጨረታ ሳፋሪኮም ተመራጭ ሆኖ በዚህ ወር በተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።", "የኬንያው ፕሬዝዳንት በአገራቸው ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እንዳይሸጡ አገዱ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በአገሪቱ ከግንባታዎች ላይ የተነሱ፣ ያገለገሉ እንዲሁም የተጣሉ ብረታ ብረቶች ሽያጭ እንዳይካሄድ አስቸኳይ እገዳ ጣሉ። ይህ የፕሬዝዳንቱ ድንገተኛ እገዳ ይፋ የተደረገው መንግሥት እየጨመረ ነው ያለውን በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ ንብረቶች ላይ የሚፈጸም ዝርፊያና ውድመትን ለመከላከል ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው። ይህ የወዳደቁና አሮጌ ብረቶች ሽያጭ እገዳ ተግባራዊ የሚሆነው የኬንያ መንግሥት የእነዚህን ብረታ ብረቶች ምንጭ፣ ንግድና ወደ ውጭ የሚላኩበትን ሁኔታ በተመለከተ ለመቆጣጠር የሚያስችል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ነው። ባለፈው ሳምንት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በሚገኝ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ተፈጸመ በተባለ ዘረፋ ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ መቋረጥ አጋጥሞ ነበር። በመላዋ ኬንያ በተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሰበብ ዘጠኝ የኬንያ መብራት ኃይል አቅራቢ ተቋም ከፍተኛ ሥራ አስኪያጆች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የባቡር ሃዲዶችን፣ የኮምዩኒኬሽን ማማዎችን እንዲሁም የኤሌክትሪክ ማስተላላፊያ መስመሮችን ጨምሮ ኬንያ ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ መሠረተ ልማቶች ላይ ተደጋጋሚ የሆነ ዘረፋና ውድመት ማጋጠሙ ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የወዳደቁ አሮጌ ብረቶችን ባገዱበት ወቅት እንዳሉት በሕዝብ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸመው ዘረፋና ጥፋት ከምጣኔ ሀብት አሻጥር ጋር የሚስተካከል በመሆኑ የአገር ክህደት ተግባር ነው ብለዋል። በመሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ዘረፋዎችን በበተመለከተ የኬንያው ፕሬዝዳንት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም። ከሦስት ዓመት በፊት የአገሪቱን ግዙፍ የባቡር መስመር ግንባታ ባስጀመሩበት ጊዜ ከቻይና በተገኘ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ብድር በሚሰራው መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሰው በሞት እንዲቀጣ እንደሚያጸድቁ አስጠንቅቀው ነበር። የተለያዩ ግዙፍ ሕዝባዊ መሠረተ ልማቶች የተገነቡባቸውን የተለያዩ የብረት አካላት ዘራፊዎች ነቅለው ወይም ቆርጠው በመውሰድ ለሽያጭና የተለያዩ ነገሮችን ለመስራት ያውሉታል። ይህ የኬንያ ችግር ብቻ ያልሆነው የብረታብረቶች ዝርፊያና ውድመት ከተለያዩ መሠረተ ልማቶች የተዘረፉት ቁርጥራጭ የብረት አይነቶን ከአገር ውጪ በመውሰድ ለሌሎች ወገኖች እንደሚሸጡ ይነገራል።", "ቦይንግ 20 በመቶ ሰራተኞቹን ለመቀነስ ማቀዱን አስታወቀ ቦይንግ በቅርቡ 7 ሺህ የሚሆኑ ሰራተኞቹን እንደሚቀንስ ይፋ አድርጓል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተጎዳው የአሜሪካኑ አውሮፕላን አምራች ቦይንግ በከፍተኛ ሁኔታ የሰራተኞቹን ቁጥር ለመቀነስ እንዳሰበ ያሳወቀ ሲሆን በመጪው አውሮፓውያኑ አመት መጨረሻም 20 በመቶ የሚሆኑትን ወደ 30 ሺህ ሰራተኞቹን እንደሚቀንስ አስታውቋል። ከቀውሱ በፊት ኩባንያው የነበሩት የሰራተኞች ቁጥር 160 ሺህ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተጨማሪ ከ337 ማክስ የደህንነት ስጋቶች ጋር ተደራርቦ ኩባንያውን ለኪሳራ ዳርገውታል። እስከ መስከረም አጋማሽ ባለውም ሶስት ወራት ውስጥ 466 ሚሊዮን ዶላር ከስሬያለሁ ብሏል። ይህም ሁኔታ ለአመት ያህልም ቀጥሏል። ከበረራ ውጭ ሆነው የነበሩት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ በረራ ሊጀምሩ ይችላሉ መባሉም ጋር ተያይዞም ኩባንያው በእነዚህ አውሮፕላኖች ሽያጭ እንደሚያገግም ተስፋ አድርጓል። 737 ማክስ ሁለት አውሮፕላኖች ተከስክሰው የ346 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ከበረራ ከታገደ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል። አውሮፕላኑ ሙሉ ሙሉ ከበረራ የታገደው በጎርጎሳውያኑ መጋቢት ወር 2019 ዓ.ም ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአየር ጉዞ ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ቀውስን ያስከተለ ሲሆን በርካታ አየር መንገዶችንም ኪሳራ ውስጥ ጥሏል። በዚህም ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ሰራተኞቻቸውን አባረዋል እንዲሁም አዳዲስ ሊገዟቸው ያሰቧቸውን አውሮፕላኖች በይዋል ይደር ትተውታል። ቦይንግም ሰራተኞችን ከመቀነስ በተጨማሪ ምርቱንም ዝቅ ለማድረግ ተገዷል። ከዚህ ቀደም 10 በመቶ ሰራተኞቹን የቀነሰው ቦይንግ እስከ 2023 ባለው ወቅትም ካለበት ቀውስ እንደማይወጣ ግምቱን አስቀምጧል። ገቢውም በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ የተነገረለት ቦይንግ በዘጠኝ ወራትም 30 በመቶ ዝቅ ብሏል። የቦይንግ ፕሬዚዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴብ ካልሁን እንዳሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ኢንዲስትሪው ላይ ጉዳት ማድረሱን ነው።", "በቀጣዩ ስምንት ዓመት ቻይና በምጣኔ ሃብት አሜሪካን ትበልጣለች ተባለ ቻይና በፈረንጆቹ 2028 በዓለም ትልቁ የምጣኔ ሃብት ባለቤት በመሆን አሜሪካን ልትቀድማት እንደምትችል ተገምቷል። ከዚህ ቀደም ቻይና አሜሪካን በ2033 ነበር ትቀድማታለች ተብሎ የተገመተው። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የምጣኔ ሃብት እና ቢዝነስ ጥናት ማዕከል ነው ይህን የገመተው። ማዕከሉ እንደሚለው ቻይና ኮቪድ-19ኝን የተቋመመችበት መንገድ ዕድገቷን ሊያፋጥን ይችላል። በተቃራኒው አሜሪካና አውሮፓ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ መደቆሳቸው ጉዳት አለው ተብሏል። በሌላ በኩል ሕንድ በ2030 ከዓለም ሦስተኛዋ ታላቅ ምጣኔ ሃብት ያላት አገር ትሆናለች ተብሎ ተገምቷል። ማዕከሉ በየዓመቱ ታኅሣሥ ወር ላይ የምጣኔ ሃብት ግምትና ትንታኔ ያወጣል። ምንም እንኳ ቻይና በኮቪድ-19 የተመታች የመጀመሪያዋ አገር ብትሆንም በሽታውን በተሳካ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ማዋል ችላለች። ነገር ግን የአውሮፓ አገራት ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ እግድ ጥለዋል። ይህ ደግሞ ምጣኔ ሃብታቸው ላእ ከፍ ያለ ጉዳትን ያስከትላል ይላል ትንታኔው። ቻይና ሌሎች አገራት እንዳጋጠማቸው የምጣኔ ሃብት ድቀት ውስጥ አልገባችም። እንዲያውም ዘንድሮ 2 በመቶ ዕድገት ታመጣለች ተብሎ ይጠበቃል። የዩናይትድ ስቴትስ ምጣኔ ሃብት ደግሞ በተቃራኒው በወረርሽኙ እጅጉን ተመቷል፤ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎችም በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። አሜሪካ ወረርሽኙ ያመጣባትን ድቀት በገንዘብ ፖሊሲና ለዜጎቿ ድጎማ በማድረግ ብትሸፍነው ብታስብም ለሁለተኛ ጊዜ ሊደረግ በታሰበው ድጎማ ላይ ፖለቲከኞች አለመስማማታቸው ጉዳቱ የከፋ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አስከትሏል። ይህ ጉዳይ ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 14 ሚሊዮን ሥራ አጥ አሜሪካዊያንን ያለ ድጎማ ሊያስቀራቸው ይችላል። ማዕከሉ ያወጣው ዘገባ እንደሚለው ቻይና እና አሜሪካ ለዓመታት የምጣኔ ሃብት የበላይነቱን ለመቆጣጠር ሲፎካከሩ ከርመዋል። ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የመጡ ለውጦች እንደሚያሳዩት ቻይና የመጪው ጊዜ የዓለማችን ቁንጮ ናት። ዘገባው እንደሚተነብየው ከሆነ ድኅረ-ኮቪድ-19 ባለው ጊዜ ውስጥ የአሜሪካ ምጣኔ ሃብት ከ2022 አስከ 2024 ድረስ ባለው ጊዜ 1.9 በመቶ ያድጋል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ወደ 1.6 በመቶ ይወርዳል። በተቃራኒው የቻይና ምጣኔ ሃብት እስከ 2025 ድረስ በ5.7 በመቶ ያድግና ከ2026 ወዲያ ባለው ጊዜ 4.5 በመቶ ያድጋል ይላል። ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የምጣኔ ሃብት ድርሻ በፈረንጆቹ 2000 ዓመት ላይ 3.6 ነበር። ዘንድሮ ግን ወደ 17.8 አድጓል። ቻይና በ2023 ከፍተኛ ገቢ ያላት አገር እንደምትሆን ነው የማዕከሉ ምክትል ሊቀመንበር ዳግላስ ማክዊሊያምስ የሚናገሩት። ምንም እንኳ የቻይና ምጣኔ ሃብት ከአሜሪካ ሊበልጥ እንደሚችል ይገመት እንጂ፤ የአንድ ቻይናዊ አማካይ ገቢ ግን ከአንድ አሜሪካዊ ጋር ሲነፃፀር ዕድገት ላያሳይ ይችላል ተብሏል።", "ከጂቡቲ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ሲከፈት የባቡር መስመሩ እንደተዘጋ ነው ተባለ ከቀናት በፊት በተቃዋሚዎች ተዘግቶ የነበረው ከጂቡቲ ወደ መሃል አገር የሚወስደው መንገድ መከፈቱ ተገለጸ። ጂቡቲን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው የባቡር መስመር ግን አሁንም ዝግ ሆኖ እንደሚገኝ የሶማሌ ክልል ኮምዩኒኬሽን ምክትል ኃላፊ መሐመድ ሮብሌ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ካሳለፍነው እሁድ ጀምሮ መንገዱና የባቡር መስመሩ በሶማሌ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት በሚቃወሙ የአካባቢው ወጣቶች ተዘግቶ ነበር። መንገዱ ከጂቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ የተለያዩ ሸቀጦች ዋነኛ መተላለፊያ መስመር ነው። ባለፈው ቅዳሜ በአፋር እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ በሆነና የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት ቦታ በተፈፀመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአፋር ታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌ ክልል ኮምዩኒኬሽን ምክትል ኃላፊው ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። በዚህ ጥቃት የተበሳጩ የሶማሌ ክልል ተወላጆች መንገዱን እና የባቡር መስመሩን መዝጋታቸውን ተከትሎ፤ የተዘጉትን የመንገድ እና የባቡር መስመር ለማስከፈት \"ከወጣቶቹና ከሕዝቡ ጋር እየተወያየን ነው። መንገዱና የባቡር መስመሩ እንዲከፈት እየሠራን ነው\" ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ለሮይተርስ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ምላሽ ሰጥተው ነበር። ትናንት ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡት የክልሉ ኮሚኒኬሽን ምክትል ኃላፊ፤ ከአገር ሽማግሌዎች እና ከወጣቶች ጋር በተደረገው ንግግር መንገዱ ከሐሙስ ጠዋት ጀምሮ የተከፈተ ሲሆን፤ በባቡር መስመሩ ላይ ግን ጉዳት በመድረሱ እስካሁን አገልግሎት አልጀመረም ብለዋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቁ ፎቶዎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተቃዋሚዎች የባቡር መስመሩን እና ዋና አውራ ጎዳናውን በድንጋይ እና በአፈር ዘግተው አሳይተው ነበር። የባቡር ሃዲዱ ብሎኖችም ተፈተው ታይቷል። መንገዱ እና የባቡሩ መስመሩ ስለመዘጋቱም ይሁን ስለመከፈቱ እስካሁን ድረስ የፌደራሉ መንግሥት ያለው ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በሶማሌ እና በአፋር ክልል መካከል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው ቦታዎች በተደጋጋሚ ግጭቶች መነሳታቸው አይዘነጋም። ቅዳሜ ዕለት ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ከአፋር ክልል በኩል መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ወደተለያዩ የክልሉ ባለሥልጣናት ስልክ በተደጋጋሚ ቢደውልም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።", "ንግድ፡ በኢትዮጵያ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያ እንዲያቋቁም ተፈቀደ፤ አዲሱ የንግድ ሕግ ምን ይዟል? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 16/2013 ዓ.ም ላለፉት 62 ዓመታት ሲያገለግል የቆየውን የአገሪቱን የንግድ ሕግ በመሻር በአዲስ እንዲተካ በሙሉ ድመጽ ወስኗል። ይህን አዲሱ የንግድ ሕግ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር በርካታ ለውጦች የተደረጉበት እንደሆነ ይነገራል። ለማዘጋጀትም ረጅም ጊዜ የወሰደና በርካታ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነበር። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸውና አዋጁን በማርቀቅ ሂደት የተሳተፉት ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ታደሰ ሌንጮ (ዶ/ር) የሕጉ መውጣት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን በአወንታዊ መንገድ ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ይናገራሉ። ባለሙያው የሕጉን መውጣት አስፈላጊነት ሲያስረዱ የሚጠቅሱት ላለፉት 62 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው ሕጉ ከወቅታዊው የዓለም ሁኔታ ጋር አለመሄዱን ነው። \"የንግድ ሕጉ በወጣበት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የኢንቨስትመንት፣ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድ የ1952ቷ እና የ2013ቷ ኢትዮጵያ በጣም የተለያዩ ናቸው\" የሚሉት ታደሰ (ዶ/ር) ይህ መሆኑ ደግሞ ኢትዮጵያ ለንግድ ከሚመቹ አገራት ዝርዝር ውስጥ በዝቅተኛ ደርጃ ላይ እንድትቀመጥ እንድርጓታል ሲሉ ገልጸዋል። የዚህ ውጤት ደግሞ አገሪቱን በተለያየ መልክ ዋጋ አስከፍሏታል። \"ኢንቨስተሮች ይሄ አገር እንዴት ቀላል ነው? እንዴት ለንግድ አመቺ ነው? የሚሉትን ነገር ሰለሚያዩ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ኢንቨስመንት ይቀንሳል ማለት ነው። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያለውን ካፒታል የመሳብ አቅሟንም በጣም አሳንሶታል\" በማለት የሚያስርዱት ባለሙያው፤ ይህም የሥራ ፈጠራንና የውጭ ንግድን እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ዕድገቷን የሚገታ ነው ሲሉ አብራርተዋል። በ1952 ዓ.ም የወጣውን ይህን ሕግ ለመቀየር ከ30 ዓመት በፊት ጀምሮ ጥረት ሲደረግ እንደቆየ ተገልጻል። 825 አንቀጾች ያሉት አዲሱ አዋጅ በርካታ ማሻሻያዎችን የያዘ ነው። ከእነዚህ ጥቂቶቹን እንመልከት። አንድ ግለሰብ ለብቻው ኩባንያ መክፈት እንዲችል ተፈቅዷል በቀድሞው የንግድ ሕግ መሠረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ለማቋቋም ቢያንስ ሁለት ሰዎች ያስፈልጋሉ። \"ለምሳሌ የውጭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ሲያደርጉ አንድ ሌላ ሰው ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ይህ ብዙ ወጪ ነው የሚያስወጣቸው። ከፍተኛ ጥርጣሬም ይፈጥራል\" ይላሉ የሕግ ባለሙያው። ከዚህም በላይ አብሮ ኩባንያውን የመሰረተውን ሰው ባለመስማማት ወይም በሞት ምክንያት ለመቀየር ሲፈለግ ያለውን ሒደት \"አበሳ ነው\" ሲሉ ከባድነቱን ይገልጹታል። ይህም የኩባንያውን ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባና አላስፈላጊ ለሆኑ ወጪዎች የሚዳርግ ነው ሲሉም አክለዋል። እንደ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጻ፣ በአገር ውስጥ ያሉ በርካታ ኃላፊነታቸው የተወሰኑ የግል ኩባንያዎች በተግባር የአንድ ሰው ሆነው ሳለ፤ ለሕጉ ሲባል ግን ተጨማሪ ሰው በባለቤትነት ይመዘግባሉ። አዲሱ የንግድ ሕግ ይህን ግዴታ አንስቶ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያን እንዲከፍት ፈቅዷል። ይህም ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡና ባለቤትነትን በተመለከተ ስጋት እንዳይኖራቸው ያግዛቸዋል ብለዋል። የንግድ ትርጓሜን መቀየር በተሻረው ሕግ የተዘረዘሩት የንግድ አይነቶች 21 ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውጪ ያሉት ንግድ አይደሉም ተብለው እንደሚገመቱ ባለሙያው ያስረዳሉ። አሁን ግን ሕጉ የንግድ አይነቶችን ወደ 38 አሳደጓቸዋል። \"ያም ብቻ ሳይሆን በአዲሱ ሕግ የንግድ ትርጉም ክፍት ነው። በግልፅ ካልተከለከለ በስተቀር ማንኛውም ሰው ከፀሐይ በታች ባለን ሥራ ንግድ ነው፤ ያተርፋል ብሎ እንደሙያ የያዘውን ሥራ አስመዝገቦ መቀጠል ይችላል\" ሲሉ አስረድተዋል። ይህ መሆኑ ደግሞ አዳዲስ የንግድ አይነቶችንና የፈጠራ ሐሳቦችን እንደሚያበርታታ አክለዋል። ኃላፊነታቸው የተወሰኑ የሙያ ሽርክና ማኅበራት መፈቀድ ከቀደመው ሕግ በተቃራኒው አዲስ የጸደቀው አዋጅ ግለሰቦች በሙያቸው ተደራጅተው እንዲሠሩ በግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። አዋጁን በማርቀቅ ሒደት የተሳተፉት ከፍተኛ የሕግ አማካሪው፤ እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ይዘው ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱ የሽርክና የሙያ ማኅበራት እንዲስፋፉ ያስችላል ብለዋል። በሌላው ዓለም በስፋት የሚሠራበት ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሕግ በግልጽ ባለመፍቀዱ ዘርፉን አዳክሞታል። በሌላ በኩል የቀድሞው ሕግ የአክስዮን ማኅበራት የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሁሉም የአክሲዮን ባለድርሻ እንዲሆኑ ግዴታ የጣለ ነበር። ነገር ግን በአዲሱ ሕግ ባለድርሻ መሆን ሳይጠበቅባቸው፤ ባለ ድርሻ ያልሆኑ ሰዎች በሙያቸው እስከ አንድ ሦስተኛ ድረስ የሚሆነውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታን እንዲይዙ ይፈቃዳል። በተጨማሪም ከተሻረው ሕግ በተቃራኒ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚከስሩ የንግድ ሰዎች ነጻ የሚሆኑበትን መንገድ እንዳመቻቸም ገልጸዋል። የሕግ ባለሙያው ታደሰ (ዶ/ር) እነዚህን ጨምሮ ለንግድ እንቅስቃሴው የማይመቹ ሕጎችን ያሻሻለው የአዲሱ አዋጅ መውጣት \"በአገር ውስጥ ያለውን እንቅሰቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል\" ብለዋል። በአዲሱ አዋጅ ያልተካተቱት የባንክ፣ የኢንሹራንስና፣ የማጓጓዣ ዘርፎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በቀድሞው አሠራር መሠረት የሚቀጥሉ ሲሆን፤ በቀጣይ ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል። አዲሱ የንግድ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ወጥቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ገብቶ የቀድሞውን ሕግ ይተካል ተብሎ ይጠበቃል።", "በኢትዮጵያ ይጀመራል የተባለው ክሬዲት ካርድ ምንድነው? አገልግሎቱን ለማግኘት ከእርስዎ ምን ይጠበቃል? አዋሽ ባንክ በኢትዮጵያ የክሬዲት ካርድ አገልግሎት በመስጠት የመጀመሪያው ባንክ ለመሆን መቃረቡን አሳውቋል። ባንኩ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው ‘ዴቢት ካርድ’ ከተሰኘው አገልግሎት በተጨማሪ፣ የክሬዲት ካርድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። በዚህም ሁለት ዓይነት የክሬዲት ካርድ አገልግሎት እንደሚጀምር በገለጸበት ወቅት አንደኛው ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ የሚመለስ፣ ሌላኛው ደግሞ ተከፋፍሎ የሚመለስ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ ባንኮች ከዴቢት ካርድ አገልግሎት በቀር ሌሎች የካርድ አገልግሎቶች ለደንበኞቻቸው አይሰጡም። ከዚህ ቀደም ዳሸን ባንክ ኢንተርናሽናል ዴቢት ካርድ የተሰኘ የውጭ ምንዛሪ ለሚጠቀሙ ደንበኞች የሚሆን ካርድ ይፋ አድርጎ ነበር። ይህ የተለያየ ዓይነት የገንዘብ ዝውውር የካርድ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ ያሉ ታላላቅ ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡት አገልግሎት ነው። በርካታ አገር በቀል ባንኮች ያሏት ኢትዮጵያ በቅርቡ የውጭ አገር ባንኮች ወደ ገበያው እንዲገቡ እንደሚፈቅድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሳወቁ ይታወሳል። አብዛኞቹ ዓለም አቀፍ ባንኮች የዴቢት ካርድን ጨምሮ የክሬዲት ካርድ እንዲሁም ሌሎች የካርድ አገልግሎቶች ለደንበኞቻቸው ይሰጣሉ። ለመሆኑ ክሬዲት ካርድ ምንድነው? እርስዎስ የክሬዲት ካርድ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ? ጥቅም እና ጉዳቱስ? የዩናይትድ ኪንግደም የተመሰከረላቸው የሒሳብ አዋቂዎች ማኅበር አባል ጥላሁን ግርማ ባንኮች በተለምዶ ሁለት ዓይነት የካርድ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ያስረዳሉ። የማማከር እና ኦዲቲንግ ባለሙያው እንደሚሉት ዴቢት፤ ደንበኛው ባለው ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከኤቲኤም ወጪ ማድረግ የሚያስችለው፤ እንዲሁም በክፍያ ማሽን መጠቀም የሚያችለው ካርድ ነው። “ነገር ግን ክሬዲት ካርድ ማለት ባንኩ ‘ካለህ ተቀማጭ ገንዘብ በላይ ይህን መጠቀም ትችላለህ’ ብሎ የሚፈቅድልህ ጊዜያዊ ብድር ነው።” ባንኮች ለደንበኞቻቸው ይህን የካርድ አገልግሎት የሚፈቅዱት የቀደመ የሒሳብ አጠቃቀም እንዲሁም የገቢ ምንጭ እና መጠናቸውን ከግምት አስገብተው ነው። አቅም ላላቸው ደንበኞች ካላቸው ተቀማጭ ገንዘብ በላይ ወጪ ማድረግ እንዲችሉ ሊፈቀድላቸው እንደሚችልም ያስረዳሉ። ባለሙያው የክሬዲትና ዴቢት ካርድ ልዩነት ሰርፆ እንዲገባን በምሳሌ ያስረዱናል። ለምሳሌ ይላሉ. . . “ለምሳሌ 20 ሺህ ብር ካለህ፤ ከኤቲኤምም አውጣ፣ ግብይትም ፈጽመበት፣ ካለህ በላይ ማውጣት አትችልም።” ክሬዲት ካርድ ግን ባንኮች የደንበኛው መልሶ የመክፈል አቅም ከግምት በማስገባት ለአጭር ጊዜ የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው። በበርካታ የዓለም አገራት የክሬዲት ካርድ ብድር ወለድ የሚከፈልበት ነው። ነገር ግን በአንዳንድ አገራት ደንበኞች በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ካልከፈሉ ነው ወለድ የሚጣልባቸው። “ለምሳሌ በ15 ቀናት ውስጥ እከፈላለሁ ብለህ ሳትከፍል ቀኑ ካለፈብህ ወለድ ይኖረዋል። የአዋሽ ባንክ ፖሊሲ ምን ሊሆን እንደሚችል የምናየው ነው የሚሆነው።” ደንበኞች የክሬዲት ካርድ አገልግሎት ለማግኘት ለባንኩ ይህን ያህል ብድር ይፈቀድልኝ ብለው ማመልከቻ ማስገባት አለባቸው። ባንኩ ባስቀመጠው መሥፈርት መሠረት የደንበኞችን አቅም እንዲሁም ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ተመልክቶ ፈቃድ ይሰጣል። “የደመወዝ መጠንህ ሊሆን ይችላል፤ ከባንኩ ጋር ያለህ ግንኙነት ሊሆን ይችላል፤ ነጋዴ ከሆንክ የንግድ ሁኔታህ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ባንኩ ኪሳራውን እያወቀ ሊፍቀድ ይችላል።” ባለሙያው ደጋግመው የባንክ ተጠቃሚዎች የክሬዲት ካርድን ዓላማ በግልፅ ማወቅ እንዳለባቸው ይመክራሉ። “ክሬዲት ካርድ የሚሰጥህ ለአጭር ጊዜ የብድር ፍላጎትህ ነው። እንጂ ቋሚ ንብረት [መኪና፣ ቤት] እንድትገዛበት አይደለም።” የክሬዲት ካርድ ዋነኛው ዓላማው ድንገተኛ ለሆነ የገንዘብ ችግር መውጫ ነው። ለዚህ ነው የሚመለስበት የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት ይላሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው። “አዋሽ ባንክም የተጠቀምከውን ገንዘብ የምትመልሰው በምን ያህል ጊዜ ነው የሚለውን በተመለከተ የራሱን ፖሊሲ ያወጣል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ይህ የሚወሰነው በደንበኛው የገቢ ምንጭ ነው።” ለምሳሌ እርስዎ ተቀጣሪ ከሆኑ በወሩ መጨረሻ ደመወዝ ሲቀበሉ ለመክፈል ሊስማሙ ይችሉ ይሆናል፤ በንግድ ከተሠማሩ ደግሞ ምናልባት በወር ሁለት ጊዜ ለመክፈል ይፈርማሉ። አዋሽ ባንክ ይህንን አገልግሎት ለባንኩ ተጠቃሚዎች በሙሉ ለመስጠት ቃል ገብቷል። የ44 ዓመቱ እንግሊዛዊ ዳረን የ32 ሺህ ዩሮ ዕዳ ውስጥ ከገባ በኋላ የሚያደርገው ጠፍቶት ነበር። ዳረን ከባንክ የወሰደውን ክሬዲት ካርድ እየመዠረጠ ለሚያስፈልገው ጉዳይ ጥቅም ላይ ቢያውለውም ዕዳውን በጊዜ መክፈል የሚያስችል አቅም አልነበረውም። “እንኳን ልቀንስ ይቀርና በዕዳ ላይ ዕዳ ስጨምር ነው የከረምኩት። ከወር ወር ሲያድግ፤ ከዓመት ዓመት እዳዬ ሲያሻቅብ ነው የከረመው። በጣም ጭንቀት ውስጥ ነበርኩ።” ምንም እንኳ ዳረን አሁን ዕዳውን ከፍሎ ቢገላገልም በርካታ እንግሊዛዊያን አሁንም የክሬዲት ካርድ ዕዳ ውስጥ ናቸው። ጥላሁን እንደሚሉት ክሬዲት ካርድ በአግባቡ ጥቅም ላይ ካልዋለ ተጠቃሚውንና ባንኮች ለኪሳራ ሊዳርግ ይችላል። ለዚህ ነው የክሬዲት ካርድ ዋነኛ ዓላማው መሆን ያለበት አንድን ችግር ወዲያው ለመፍታት መሆን አለበት የሚሉት። “ለምሳሌ ቤተሰብ ቢታመምብህ አሊያም በሚቀጥለው ወር ዕቁብ የሚወጣልህ ቢሆንና አሁን አንድ ዕቃ መግዛት ብትፈልግ ክሬዲት ካርድ መጠቀም ትችላለህ።” ባለሙያው ክሬዲት ካርድ ማለት “ልክ እንደ ቴሌ ብር ነው” ይላሉ። “ቴሌ ገንዘብ ሳይኖርህ ሲቀር የብድር አገልግሎት ይሰጥሃል። በሚቀጥለው ስትሞላ ከሒሳብህ ላይ ይወስዳል።” በውጭው ዓለም ‘ክሬዲት ስኮር’ የሚባል ሐሳብ አለ። የክሬዲት ስኮር ማለት አንድ ሰው ብድር ወስዶ የመመለስ ታሪኩ እንዴት ያለ ነው የሚለውን የሚያሳይ ነው። ብድር ወስደው በጊዜ የሚመልሱ ሰዎች መልካም ‘ክሬዲት ስኮር’ ያላቸው ተብለው ይጠራሉ። የክሬዲት ታሪካቸው ጥሩ የሆኑ ሰዎች በባንኮች ዘንድ ይከበራሉ፤ የሚፈልጉት ጉዳዩ በቶሎ ይሳልጥላቸዋል። በአብዛኛዎቹ አገራት የክሬዲት ካርድ ወለድ፣ የባንኮች ለደንበኞቻቸው ከሚሰጧቸው ሌሎች ካርዶች ወለድ ከፍ ያለ ነው። “ብድር ስለሆነ ወልድ አለው። አደጋ ስላለው ነው ወለዱ ከፍ የሚለው። ንብረት አስይዞ የሚወስድ ሰው እና ንብረት ሳያስዝ ብድር የወሰደ ሰው እኩል ስላልሆነ የወለድ መጠኑን ከፍ በማድረግ ነው ስጋቱን የሚያጣጡት።” ዴቢት ካርድ ሲጠቀሙ ቀረጥ የሚጥል የግል ማሽን [ኤቲኤም፣ የግብይት ማሽን] ካልሆነ በቀር ተጨማሪ ክፍያ አይከፍሉም። አልፎም ለተጠቀሙበት ክፍያ ካለው ቀድሞ ያሳወቆታል። ወደ ክዴዲት ካርድ ስንመጣ ግን ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ሲያወጡ ክፍያ ይከፍላሉ። አንዳንድ ጊዜ ካርዱን የሰጠዎት ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል። በበይነ መረብ ዕቃና አገልግሎት የሚሸጡ ድርጅቶች ከዴቢት ካርድ ይልቅ ክሬዲት ካርድ ይመርጣሉ። ለዚህ ምክንያቱ ክሬዲት ካርድ ሲሆን ገንዘቡን ከባንክ ቀጥታ ማግኘት ስለሚችሉ ነው። ባለሙያዎች ክሬዲት ካርድ ተጠቅሞ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣትን አይመክሩም። ከዚያ ይልቅ በሚገበያዩበት ወቅት ክሬዲት ካርድዎን ይጠቀሙ ይላሉ። ቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ አሜሪካን ኤክስፕረስ እና ዲስከቨር የክሬዲት ካርድ ኔትዎርኮች ናቸው። ባንኮች እኒህን ኔትዎርኮች ተጠቅመው ነው ለደንበኞቻቸው ክሬዲት ካርድ የሚያውጁት። አብዛኞቹ ዓለም አቀፍ ባንኮች የክሬዲት ካርድ ለሚጠቀሙ ደንኞቻቸው ማበረታቻ ሽልማት ይሰጣሉ። ለምሳሌ የአውሮፕላን ቲኬት ለመቁረጥ፣ ለሆቴል ክፍያ፣ ለበይነ-መረብ ግብይት ክሬዲት ካርድ ከሚጠቀሙ ደንበኞቻቸው ማበረታቻ ይሰጣሉ። ማበረታቻው በአየር መንገድ ማይል፣ በተጨማሪ የሆቴል ክፍያ እንዲሁም በስጦታ ካርድ መልክ ሊሰጥ ይችላል። ባንኮች ለደንበኞቻቸው በየወሩ ‘ስቴትመንት’ [የባንክ ሒሳብ መረጃ] ይልካሉ። ይህ ስቴትመንት ደንኞች ክሬዲት ካርዳቸውን ተጠቅመው ምን ያህል ክፍያ እንደፈፀሙ፣ የወለድ መጠኑን እና ተጨማሪ ክፍያውን የሚያካትት ነው። አክሎም፤ ክሬዲት ካርዳቸው ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ እንደቀረ፤ መልሰው ሊከፍሉ የሚገባቸው ዝቅተኛ መጠን ስንት እንደሆነ እና እንዴት መክፈል እንደሚችሉ ይካተትበታል። የሒሳብ አዋቂው ጥላሁን ከአዋሽ ባንክ እርምጃ በኋላ “ሌሎች ባንኮች ተኝጠው አያድሩም” ይላሉ። “ይህ አገልግኮት እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይጀመር መቆየቱ በጣም የሚገርም ነው። ሌሎችም ባንኮች ለመጀመር ዝግጅት ላይ ናቸው አሊያም ከአዋሽ ባንክ በኋላ መጀመራቸው አይቀርም።”", "ኮቪድ-19፡ ቤት የመቀመጥ ገደብ ጉግልን ትርፋማ አድርጓል ተባለ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው ቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደብ ለጉግል ትርፋማነት አስተዋጽኦ አድርጓል ተባለ። የጉግል ባለቤት ድርጅት የሆነው አልፋቤት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ 17 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም የ162 በመቶ ጭማሪ መሆኑ ተገልጿል። ለትርፋማነቱም ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ እንቅስቃሴያቸው ሲገደብ የጉግልን አገልግሎቶች መጠቀማቸው በምክንያትነት ተቀምጧል። ያለፉት ሦስት ወራትም በድርጅቱ ታሪክ ከፍተኛ ትርፍ የተመዘገበበት ነው ተብሏል። ጉግል ይህን የትርፍ መጨመር \"ደንበኞቼ ኢንተርኔት በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ተግባራቶች መጨመር ያመጣው ነው\" ሲል ገልጾታል። \"ባለፈው ዓመት ሰዎች የጉግል መፈለጊያን ተጠቅመው ራሳቸውን ከመረጃ ላለማራቅ፣ ለመዝናናት እና ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማስቀጠል ሲጠቀሙት ቆይተዋል\" ሲሉ የአልፋቤት እና ጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱንዳር ፒቻዪ ገልጸዋል። የዘርፉ ተንታኞችም የተዘጉ ኢኮኖሚዎች ሲከፈቱ እና የኢንተርኔት ላይ ማስታወቂያዎችም እየተበራከቱ ሲሄዱ ጉግል ከፍተኛ ትርፍ መሰብሰቡን ይቀጥላል ብለዋል። ጉግል ባለፈው ሦስት ወራት በአጠቃላይ ከመፈለጊያ ንግዱ [Search business] የሰበሰበውን ገቢ በ30 በመቶ በመጨመር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል። ዩትዩብ ደግሞ በስድስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ የ49 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በሃርግሬቭስ ላንሱንግ የፍትሐዊነት ተንታኝ የሆኑት ሶፊ ሉንድ-ያትስ በበኩላቸው አልፋቤት \"ጉግል በወረርሽኙ ሳቢያ በተገኘው ገቢ ልክ በክሬም ላይ እደተወረወረች ትልቅ ድመት ሆኗል\" ሲሉ ትርፉን ገልጸውታል። የቴክኖሎጂ ግዙፉ ኩባንያ ጉግል፤ ባልተለመደ መልኩ የማስታወቂያ ንግድ ድርጅት ወደመሆን ማዘንበሉንም ተንታኙ ተናግረዋል። \"የኮሮናቫይረስ ሲከሰት በተለይም የኢንተርኔት ላይ ግብይት በመጧጧፉ ምክንያት የአልፋቤት የንግድ ተቋማት ለእነዚህ ሸቀጦች ማስታወቂያ ማስነገራቸው ገቢያቸው እንዲተኮስ ምክንያት ሆኗል\" ሲሉም ለከፍተኛ ትርፍ ያበቃውን ምክንያት አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ጉግል ከተለያዩ ተቆጣጣሪ ተቋማት በተለይም ፍትሐዊ የንግድ ውድድርን እና የግል ምስጢር መጠበቅን በተመለከተ እያጋጠመው ያሉት ጥያቄዎች ዋና ተግዳሮቶቹ ሆነው ቀጥለዋል።", "\"የዓለም አስር ባለ ጸጎች ሀብት ቢደመር ለሁላችንም ክትባት ይገዛል\" ኦክስፋም ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ በወረርሽኙ ወቅት ሀብታቸው የናረ አስር ወንዶች ሀብት ንብረት ሲደመር 540 በሊዮን ዶላር ይጠጋል። ይህ ሀብት የዓለም ሕዝቦችን ከድህነት የሚያወጣ እንዲሁም ለሁሉም ሰው ክትበት መግዛት የሚያስችል እንደሆነ የተራድኦ ድርጅቱ ኦክስፋም ጠቁሟል። በዓለም ላይ ያሉ ቢሊየነሮች ጠቅላላ ሀብት፤ የጂ-20 አገራት ወረርሽኙ ካሳደረው ጫና ለመላቀቅ ከሚያወጡት ወጪ እኩል መሆኑ በኦክፋም ሪፖርት ተመልክቷል። ኦክስፋም ይህንን ሪፖርት ተመርኩዞ መንግሥታት ባለ ጸጎች ላይ ከፍተኛ ግብር እንዲጥሉ ያሳስባል። 'ኢንኢኳሊቲ ቫይረስ' የተሰኘው ሪፖርት የወጣው መንግሥታት ለዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ጉባኤ በተሰበሰቡበት ወቅት ነው። መንግሥታት ለምጣኔ ሀብታቸው ያደረጉት ድጋፍ የአክስዮን ገበያ እንዲያንሰራራና የቢልየነሮች ገቢ እንዲጨምር አድርጓል። የእነዚህ ግለሰቦች ሀብት ሲጨምር የአገራት ጠቅላላ ምጣኔ ሀብት ግን አሽቆልቁሏል። ከሚያዝያ 2020 እስከ ጥቅምት 2020 የመላው ዓለም የቢልየነሮች ሀብት በ3.9 ትሪሊዮን ጨምሯል። የጂ-20 አገራት ወረርሽኙን ለመከላከል ያወጡት ወጪ ሲደመርም ከባለ ጸጎቹ ሀብት ጋር እኩል ነው። በወረርሽኙ ወቅት ሀብታቸው ከናረ መካከል የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ፣ የተስላ መስራች ኤለን መስክ እና የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ ይገኙበታል። ጄፍ ቤዞስ ካለው ሀብት ለእያንዳንዱ 876,000 የአማዞን ተቀጣሪ 105,000 ዶላር ጉርሻ ቢሰጥ እንኳን ከወረርሽኙ በፊት የነበረው ሀብቱ እንደማይቀንስ ሪፖርቱ ያሳያል። በተቃራኒው በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ወረርሽኙ ከሳደረባቸው ተጽዕኖ ለማገገም አስርት ዓመታት ያስፈልጋቸዋል። በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ሰዎች ወደ ድህንት አረንቋ እንደገቡ ኦክስፋም ገልጿል። የኦክስፋም እንግሊዝ ዋና ኃላፊ ዳኒ ስሪስካንዳርጃህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ \"ሀብታሞች ላይ ግብር በመጣል፣ ለእያንዳንዱ ዜጋ መሠረታዊ የገቢ መነሻ በማበጀትና በሌሎችም መንገዶች ፍትሐዊ ክፍፍልን ማረጋገጥ አለብን።\" በወረርሽኙ ወቅት አንዳንድ ሀብታም ሰዎች የገንዘብ ድጎማ እየሰጡ ነው። የጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት መከንዚ ስኮት ያደረገችው የአራት ቢሊዮን ዶላር ድጎማ ይጠቀሳል።ጄ ፍ ቤዞስ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚደረገውን ትግል ለመደገፍ 125 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቷል። የትዊተር አጋር መስራች ጃክ ዶርሲ ከሀብቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲውል ሰጥቷል። ቢል ጌትስ እና ባለቤታቸው መሊንዳ ለክትባት ምርትና ግዢ 305 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል።", "በከተማ ግብርና የተለወጡት የአዲስ አበባ ዙሪያ አርሶ አደሮች በከተሞች ውስጥና በዙሪያቸው የሚኖሩ አርሶ አደሮች የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለነዋሪዎች ያቀርባሉ። ይም በተወሰነ ደረጃ የከተማ ነዋሪዎችን ፍላጎት ሲያሟላ ለእነሱም የገቢ ምንጭ ይሆናል።", "የምንፈልገውን ሥራ እና እድገት ለማግኘት ራሳችንን እንዴት እንግለጽ? ስለራስ መናገር ምቾት አይሰጥም፤ አይደለም ለአለቃ ለወዳጅ እንኳ ቢሆን 'ምን ጉራህን ትቸረችራለህ' ሊያስብል ያስችላል። የሰው ጀማ ተሰብስቦ ስለራስ 'ጥሩንባ መንፋት' የተለመደ አይደለም፤ ይህ ግን የኢትዮጵያውያን ችግር ብቻ ሳይሆን ፈረንጆቹም እዚህ ላይ ትንሽ ቆንጠጥ ያደርጋቸዋል። ስለራሳቸው ለመናገር ጀምረው ድምጻቸው የሰለለባቸው፣ እጃቸውን ያላባቸው፣ አፋቸውን የፈቱበት ቋንቋ የጠፋቸውን የየመሥሪያ ቤቱ ደጃፍ ይቁጠራቸው። ለስቴፋኒ ስዎርድ ዊሊያምስ ግን \"ይህ ክህሎት ሁለቴ ማሰብ የማያስፈልገው ሁሉም ሊኖረን የሚገባ ነው\" ትላለች። ስቴፋኒ ራስን በብቃት መግለጽ መቻል ላይ በበርካቶች የተነበበ መጽሐፍ አዘጋጅታለች። በሠሯቸው ሥራዎች፣ ባገኟቸው ውጤቶች መኩራራት፣ ደረትን መንፋት ልክ እንደ በጎ ምግባር ሊቆጠር ይገባል ስትል ታስረዳለች። ነውር አለመሆኑንም አጽንኦት ሰጥታ ነው የምትናገረው። በዚህ ፉክክር በበዛበት ዓለም ያለዎትን ክህሎት ማጉላት በሥራ ቦታ ለውጤትዎ ላቅ ያለ ድርሻ ይኖረዋል። በሥራዎ እድገት ለማግኘት፣ አዲስ ሥራ ለመቀየር፣ በአለቃዎ ዕይታ ውስጥ ለመግባት እና የድርጅትዎን የእድገት መሰላል በቀላሉ ለመውጣት ስለራስዎ ያለመሸማቀቅ መናገር ያስፈልግዎታል፤ ይጠበቅብዎታልም። ለአንድ ሥራ በርካቶች የማመልከቻ ዶሴ ተሸክመው በየቀጣሪዎች ደጅ በሚንከራተቱበት በዚህ ወቅት፣ ሁሉም ዲግሪ እና ማስተርስ ኖሮት ያለችው ጥቂት እድገት ላይ ዓይኑን ጥሎ በሚጠብቅበት የሥራ ቦታ \"ራስን መሸጥ\" ተገቢ ክህሎት ሆኖ ይገኛል። ይህ ደግሞ ዓይን አፋር ለሆኑ እና ራሳቸውን መግለጽ ለሚቸገሩ ሴቶች አስፈላጊ ክህሎት ነው። የራሳቸውን ሥራ ከቤታቸው ሆነው ለሚሰሩ፣ በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የገበያ ዕድሎችን ሳስተው፣ ከብዙኃኑ ጋር ተቀላቅሎ ለመወዳደር ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅት ያለው አማራጭ ስለራስ ስኬት፣ ስለ አገልግሎትዎ እና ስለ ክህሎትዎ ደረትን ነፍቶ ማስረዳት መቻል ነው። \"የራሳችንን እሴቶች ለማሳየት ጊዜ የማንወስድ ከሆነ፤ እንደ ተፈላጊ የመቆጠር ዕድላችን ላይ በር እንዘጋለን\" ስትል ስዎርድ ዊሊያምስ ታስረዳለች። \"ስለ ራሳችን የምንታወቅበትን ነጥቦች ይፋ በማድረግ፣ ማንንነታችንን በማሳየት ታሪካችንን ራሳችን መንገር ያስፈልገናል\" ባይ ናት። ስለ እኛ ሌሎች እንዲመሰክሩልን መጠበቅ የዋህነት ነው ስትልም ታክላለች። ራስን ማስተዋወቅ በቀላል ብያኔ ሥራዎና ስኬትዎ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ ማለት ነው። ስለዚህ ስለራስዎ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የሚያስቀምጡት መግለጫ፣ ወይንም በኢሜል መልዕክት ላይ የሚያስገቡት ማብራሪያ ካልሆነ ደግሞ ከአለቃዎ ወይንም ከቁልፍ ሰዎች ጋር በሚኖርዎት ውይይት ወቅት የሚያነሷቸው ነጥቦች ራስዎን በሰዎች ፊት ሞገስ በማሰጠት ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው። በተሰማሩበት መስክ ለማደግ እንዲሁም ማንነትዎን እና ብቃትዎን [ብራንድ] በሚገባ ለማስተዋወቅ ጠቃሚ ነው። በተሰማራበት መስክ እስከ መሰላሉ የላይኛው ጫፍ ለመውጣት የሚፈልግ ሰው ደግሞ ይህንን ቢያደርግ መንገዱን የውሃ ያደርገዋል። ይህ ዓለም የወንዶች ነው በሥራው ዓለም የተደረጉ ጥናቶች እንደሚመሰክሩት ከሆነ ስለራስ በመናገር ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ይደፍራሉ። እኤአ በ2019 መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ አንድ አካዳሚ፣ ይፋ ባደረገው ጥናት ራስን በመግለጽ ረገድ \"ትልቅ የሥርዓተ ጾታ ክፍተት ይታያል።\" ተመራማሪዎቹ ለጥናቱ ተሳታፊዎች የሒሳብ እና የሳይንስ ፈተና እንዲወስዱ፣ ከዚያም ብቃታቸውን ራሳቸው እንዲመዝኑ አድርገዋል። የጥናቱ ተሳታፊዎች ለራሳቸው የሰጡት ውጤት ለአለቆቻቸው ማንን ለመቅጠር እና ምን ያህል መክፈል እንደሚገባቸው መወሰን እንዲችሉ እንዲያውቁት እንደሚደረግ ተነግሯቸዋል። ምንም እንኳ በጥናቱ ወንዶቹም ሴቶቹም እኩል ውጤት ያመጡ ቢሆንም፣ ወንዶች ግን ለራሳቸው በአማካኝ 61 ከመቶ ሲሰጡ ሴቶች ግን 46 ከመቶ ሰጥተዋል። ሴቶች ስለምን ከወንዶች የበለጠ ድሃ ሆኑ (Why Women Are Poorer Than Men) የሚል መጽሐፍ ደራሲዋ አናቤላ ዊሊያምስ \"ሌሎች በርካታ ጥናቶች እንዳሳዩት ከሆነ ወንዶች ስለስኬታቸው ሲጠየቁ 'እራሳቸውን በመሸጥ' ላይ የተዋጣላቸው ናቸው። በተቃራኒው ሴቶች ደግሞ ችሎታቸውን እና ውጤታቸውን ዝቅ አድርገው ሲያቀርቡ ተስተውሏል\" ትላለች። ሴቶች ከልጅነታቸው ጀምሮ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ሲያደርጉ እየተገሰፁ ነው የሚያድጉት። ራሷን ከፍ ከፍ ለምታደርግ ሴትም የሚሰጡ የተለያዩ ቅጽል ስሞች መኖራቸውን ትገልጻለች። \"ነገር ግን ተመሳሳይ ባህሪ የሚያሳይ ወንድ በራስ የመተማመን ብቃት እና የአመራር ችሎታ እንዳለው ይቆጠርለታል\" ስትል ታብራራለች። ስዎርድ ዊሊያምስ በበኩሏ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ እና አርዓያ የሚሆኑ ሴቶች ስለራሳቸው መናገር እና ስኬታቸውን ማንቆለጳጰስ ተገቢ መሆኑን ሲናገሩ አይደመጡም ትላለች። በውጤቱም ሴቶች ለአንድ የሥራ እድል ከወንዱ የበለጠ እንዲታገሉ ያደርጋቸዋል። በእርግጥ አንዳንድ ወንዶች አይናፋር፣ ሴቶች ደግሞ በተፈጥሯቸው ራሳቸውን መግለጽ እና ሰለ ሥራቸው በድፍረት ለመናገር ችግር ላይኖርባቸው ይችላል። በቅርቡ በተደረገ ጥናትም ወጣት ሴቶች በእድሜ ከገፉ ሴቶች ይልቅ ስለራሳቸው ደፈር ብለው መናገር እንደሚችሉ ይፋ አድርጓል። ስለራስ በድፍረት እና በልበ ሙሉነት መናገር ቦታ ካልተመረጠለት ባዶ ጩኸት እና ቀረርቶ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ። ቀጣሪን እና አለቃን ከመማረክ ይልቅ ሊያበሳጭ የሚችልባቸውም ዕድሎች አሉ። በዚህ ወቅትም ስለራስ በልበ ሙሉነት ለመናገር ግቡን መምታት አቅቶት ሲከሽፍ ይስተዋላል። ስለራስዎ በልበ ሙሉነት ለመናገር ምን ያድርጉ? ስለራስ በልበ ሙሉነት መናገር ግን እንዲሁ የሚገኝ ስጦታ አይደለም፤ ልምምድ ይጠይቃል። በተለይ በቢሮዎ ውስጥ፣ በወንበርዎ ላይ በወረቀት ክምር መካከል አልያም ከኮምፒውተር ጀርባ ተቀምጠው የዕለት ሥራዎትን ብቻ የሚከውኑ ከሆነ ከዕይታም ከአእምሮም ውጪ የመሆን ዕድልዎ የሰፋ ነው። እርስዎ ልምዱና ችሎታው እያለዎት ሌሎች አልፈዎት ይሾማሉ፤ ይሸለማሉ። እርስዎ በነበሩበት የደሞዝ እርከን ላይ ተቀምጠው ሲያለቃቅሱ ሌሎች የጥቅማ ጥቅም እና ደረጃ እድገት በረከት ተቋዳሽ ይሆናሉ። ስለዚህ ስለራስዎ በሚገባ መግለጽ፣ ስኬቶችዎን በደማቅ ቀለም በአለቃ አእምሮ ውስጥ ለመጻፍ እንዲችሉ ያለማመንታት ልምምድ ያድርጉ። አለቆች የሰሯቸውን ሥራዎች የሚያስታውሳቸው፣ ስኬቶችዎን እና አስተዋጽኦዎን የሚነግራቸው ይፈልጋሉ። በተቋሙ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ተቀጥረው ቢሰሩ እንኳ ስለራስዎ እስካልተናገሩ ድረስ የመረሳት ዕድልዎ ሰፊ ነው። ስለዚህ ልክ እንደ አዲስ ክህሎት ራስን በልበ ሙሉነት መግለጽንም ሊማሩት እና ሊለማመዱት የሚገባ ክህሎት ነው። \"የረዥም ጊዜ የሥራ ላይ ህልምዎን እና ፍላጎትዎን ለአለቃዎ ይንገሩ\" የምትለው ሃሪት ሚንተር ነች። ሃሪት ሚንተር በዚህ ዘርፍ ጥሩ የተነበበ መጽሐፍ ደራሲ ስትሆን \"አሁን ጊዜው አይደልም አትበሉ። ከዚያ ይልቅ ለኩባንያው ያመጧቸውን ዕሴቶች በመመልከት በዚያ መሰረት ጥያቄያችሁን ሰንዝሩ\" ስትል ትመክራለች። ሚለር ስለስኬትዎ ለሥራ አጋርዎ እና አለቃዎ ለማሳወቅ ኢሜል አንዱ መንገድ ነው ትላለች። በዚህ ኢሜል ውስጥ ማካተት የሚፈልጓቸውን መረጃዎች ማካተትዎን፣ በሚገባ መግለጽዎን እና ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ የመላክ ልምድዎን ያዳብሩ፤ አንዴ መላክ ከጀመሩ በቀጣዮቹ ሳምንታት እየቀለለዎ ይመጣል ስትል ሚለር ትመክራለች። ከዚህ ደግሞ ባለፈ ልምድዎን እና ችሎታዎን ለማሳየት አዲስ ተቀጣሪዎች ሲመጡ ለማማከር፣ ለማለማመድ እና ልምድን ለማጋራት ከፊት ይሁኑ። ለጀማሪዎች ልምድን በድፍረት ማካፈል ያለዎትን ልምድ እና ክህሎት ለሌሎች ለማሳየት ጥሩ ዕድል ነው። በዚህ የዲጂታል ዘመን በፌስቡክ፣ በትዊተር እንዲሁም በሊንክዲን ላይ ስለራስዎ የሚያሰፍሯቸውን መረጃዎችም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በየጊዜው የሚስተለካከሉ እና ያለዎትን ልምድ እና ክህሎት በሚገባ የሚገልጹ መሆናቸውን ያስተውሉ። ከዚህ በኋላ ስራስዎ መናገር ልክ ታሪክ የመንገር ያህል ቀላል ይሆናል። እንዴት አድርጌ ብነግረው የበለጠ ይስብልኛል ቀልብም ልብም ይስብልኛል የሚለው ያስጨንቅዎት ይሆናል እንጂ፤ አፍዎ አይተሳሰርም፣ እጅዎን አያልብዎትም፣ ድምጽዎም አይሰልም።", "በአሜሪካ ማዕቀብ ምክንያት ፊቱን ወደ አሳማ እርባታ ያዞረው ሁዋዌ ሁዋዌ በአሜሪካ ዘመናዊ ስልኮቹ ላይ ከባድ ማዕቀቦችን በመጣሉ ምክንያት ፊቱን ለአሳማ ገበሬዎች ቴክኖሎጂ ወደ ማቅረብ አዙሯል። ግዙፉ የቻይናው የቴሌኮም ኩባንያ የትራምፕ አስተዳደር ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አስጊ ነው ተብሎ በመፈረጁ አስፈላጊ ዕቃዎችን እንዳያገኝ ተደርጓል፡፡ ሁዋዌ የገጠመውን የስማርት ስልክ ሽያጭ ሊያካክስ በመፈለጉ ለቴክኖሎጂው ሌሎች የገቢ ምንጮችን እየተመለከተ ነው፡፡ ለአሳማ ገበሬዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጅ ከመሥራት በተጨማሪ ሁዋዌ የከሰል ማዕድን ኢንዱስትሪ ጋርም ይሠራል፡፡ ሁዋዌ የደንበኞችን መረጃ ለቻይና መንግስት ሊያጋራው ይችላል ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክስ ቢያቀርቡትም ድርጅቱ በተደጋጋሚ አስተባብሏል፡፡ በዓለም ትልቁ የቴሌኮም መሣሪያዎች አምራቹ በዚህ ምክንያት የ 5ጂ ሞዴሎችን አካላት ለማስመጣት የአሜሪካ መንግሥት ፈቃድ ስለላልሰጠው የ 4ጂ ሞዴሎችን በመሥራት ተገድቧል፡፡ በብሔራዊ ደህንነት ላይ ስጋት ፈጥሮብናል ያሉ እንደ እንግሊዝ ያሉ ሌሎች ሃገራትም ሁዋዌ የሚያደርገውን የ 5ጂ ዝርጋታ አስቁመዋል፡፡ በዚህ ዓመት የስማርት ስልኮችን ምርቱን እስከ 60% ድረስ እንደሚቀንሰው ሪፖርቶች ጠቁመዋል፡፡ ይህን ግን ማረጋገጥ አልተቻለም። \"ይህ የሚያሳየው የሁዋዌ ምርቶች ጥራትና ልምዳችን ምንም አይነት ችግር እንደሌለበት ነው፡፡ ሁዋዌ በጂኦፖለቲካዊ ውዝግብ መካከል የተያዘ በመሆኑ ለሁዋዌ የመጫወቻ ሜዳው አይደለም\" ሲሉ የኩባንያው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስለዚህ ሁዋዌ ፊቱን ወደ ሌሎች የገቢ ምንጮችን ያዞረ ይመስላል። እንደክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ስማርት ተሽከርካሪዎች እና ተለባሽ መሣሪያዎች እንዲሁም ስማርት መኪና የማምረትም ዕቅዶች አሉት። በጥቂት ተጨማሪ ባህላዊ ኢንዱስትሪዎች ላይ ዓይኑን ጥሏል፡፡ ቻይና በዓለም ትልቁ የአሳማ እርሻ ኢንዱስትሪ ባለቤት ስትሆን፣ የአለማችን አሳማዎች ግማሽ ያህሉ መኖሪያ ናት፡፡ በሽታዎችን ለመለየት እና አሳማዎችን እንቅስቃሴ ለመከታተል በሚያስችለው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የአሳማ እርሻዎችን ለማዘመን ቴክኖሎጂው እየረዳ ነው፡፡ የፊት መለያ ቴክኖሎጂ እያንዳንዱን አሳማዎች መለየት ሲያስችል ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ክብደታቸውን፣ አመጋገባቸውን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎቻቸውን ይቆጣጠራሉ፡፡ ሁዋዌ የፊት ለይቶ የማወቅ ቴክኖሎጂ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን ባለፈው ወር ግን ትችት ገጥሞታል። ምክንያቱ ደግሞ ከእግረኞች ምስል መካከል የኡሂጉር ተወላጅ የሆኑ የሚመስሉትን ሰዎችን ለይቶ በሚያሳውቀው ስርዓቱ ነው። እንደ ጄዲዳትኮም፣ አሊባባን ጨምሮ ሌሎች የቻይና ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከአሳማ ከሚያረቡ አርሶ አደሮች ጋር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ እየሠሩ ነው፡፡ የሁዋዌ ቃል አቀባይ አክለውም \"በ 5ጂ ዘመን ለኢንዱስትሪዎች የበለጠ እሴት ለመፍጠር አንዳንድ ባህላዊ ኢንዱስትሪዎችን በኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እንደገና ለማነቃቃት የምንሞክርበት ሌላ ምሳሌ ነው\" ብለዋል፡፡ የሁዋዌ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሬን ዤንግፈይ በዚህ ወር መጀመሪያ በሰሜን ቻይና ሻንሺ ግዛት የማዕድን ፈጠራ ቤተ-ሙከራ በይፋ አስጀምረዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለድንጋይ ከሰል ማዕድን አውጪዎች \"አነስተኛ ሠራተኞችን፣ ከፍተኛ ደህንነትን እና ከፍተኛ ብቃትን የሚያመጣ እና ማዕድን አውጪዎቹ በሥራ ቦታቸው ሱፍ እና ከረቫት እንዲለብሱ\" የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂን ለማዳበር ይፈልጋሉ፡፡ በዝግጅቱ ላይ በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ በተደረገ ስብሰባ ላይ ሬን ኩባንያው ከሰል ማዕድን እና ከብረት እንደ ቴሌቪዥኖች፣ ኮምፒውተሮች እና ታብሌቶች ያሉ ምርቶች ላይ ትኩረት እያደረገ ይገኛል፡፡ \"በስልክ ሽያጮች ላይ ሳንመሠረት እንኳን በመቀጠል እንችላለን\" ያሉት ሬን የአሜሪካ ኩባንያዎች ያለፍቃድ ከሁዋዌ ጋር እንዳይሠሩ የሚያግደውን የጥቁር መዝገብ ያነሳል የሚል እምነት እንደሌላቸው ጨምረው ጠቅሰዋል፡፡", "ዩናይትድ አየር መንገድ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ 24 ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ። አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን ከበረራ ያገደው ባሳለፍነው ቅዳሜ ከአውሮፕላኖቹ አንዱ ሞተሩ ላይ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ነው። አውሮፕላኑ 231 መንገደኞችንና አስር የበረራ አስተናጋጆችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን በዴንቨር አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል። እስካሁን በአደጋው የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። የአውሮፕላኑ ስብርባሪዎችም በአቅራቢያው ባሉ የመኖሪያ ቦታዎች ወዳድቀው ተገኝተዋል። ይህንንም ተከትሎ ጃፓን ተመሳሳይ ፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸውን ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን የሚጠቀሙ ሁሉም አየር መንገዶች አየር ክልሏ እንዳይገቡ ጠይቃለች። ወደ ሃዋይ ሆኖሉሉ ከተማ ለመብረር የተነሳው ዩናይትድ 328 አውሮፕላን በቀኝ በኩል ባለው ሞተሩ ላይ አደጋ እንደገጠመው የፌደራል አቪየሽን አስተዳደር ገልጿል። አደጋውን ተከትሎም አስተዳደሩ የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸው ቦይንግ 777 አውሮፕኣኖች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ አዟል። \"አደጋው ካጋጠመ በኋላ ሁሉንም የደህንነት መረጃዎች ተመልክተናል\" ሲሉ የፌደራል አቪየሽን አስተዳዳሪ ስቴቭ ዲክሰን በመግለጫቸው ተናግረዋል። በመጀመሪያ ደረጃ በተገኘው መረጃ መሠረትም፤ ምርመራው በቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ላይ ብቻ ለሚገጠመው ለዚህ የሞተር ሞድል የተለየ የሆነው ወደ ሞተሩ ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ድምዳሜ ላይ ደርሰናል ብለዋል። የፌደራል አቪየሽን አስተዳደርም ከሞተር አምራቹ ድርጅት እና ከቦይንግ ተወካዮች ጋር እየተነጋገረ ነው። የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ እንደሚያመላክተው አውሮፕላኑ አደጋ ያጋጠመው በቀኝ ሞተሩ ላይ ሲሆን፤ በሌሎች ሁለት ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ተሰነጣጥቀዋል። ሌሎቹም እንዲሁ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ የአውሮፕላኑ ዋነኛ አካል ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል መሆኑን ቦርዱ ገልጿል። ይህ አደጋ ባጋጠመው አውሮፕላን ላይ ተሳፍራው የነበሩት መንገደኞች ለበረራ እንደተነሱ ወዲያውኑ ከፍተኛ ፍንዳታ እንደሰሙ ተናግረዋል። ከመንገደኞቹ አንዱ የሆኑት ዴቪድ ዴሉሲያ \"አውሮፕላኑ በኃይል ሲነቃነቅ ነበር። ከዚያም ከፍ ብሎ መብረር ስላልቻለ ወደ ታች መውረድ ጀመረ\" ብለዋል። አክለውም እርሳቸውና ባለቤታቸው ምንአልባት አደጋ ካጋጠመን በሚል የኪስ ቦርሳቸውን ኪሳቸው ውስጥ እንደከተቱት ተናግረዋል። የብሩምፊልድ ከተማ ፖሊስ የአውሮፕላኑ የሞተሩ ሽፋን ስባሪ በአንድ መኖሪያ ቤት አትክልት ቦታ ላይ መውደቁን የሚያሳይ ምስል አጋርቷል። ሌሎቹ ስብርባሪዎችም በከተማዋ አንድ የእግር ኳስ ሜዳ ላይ ወድቀው ታይተዋል። ከአውሮፕላኑ ላይ በወደቀው ስብርባሪ ግን የተጎዳ አለመኖሩ ተገልጿል። በጃፓን የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞደል ሞተር የተገጠመላቸው ሁሉም 777 አውሮፕላኖች ተጨማሪ ማስታወቂያ እስኪነገር ድረስ አየር ክልሏ መግባት ያቆማሉ። ይህም ለበረራ መነሳትን፣ ማረፍን እና በአገሪቷ የአየር ክልል ላይ መብረርን ያካትታል። ባለፈው ታህሳስ ወር የጃፓን አየር መንገድ አውሮፕላን በግራ በኩል ያለው ሞተሩ መስራት ባለመቻሉ ወደ ናሃ አየርማረፊያ እንዲመለስ ተገዶ ነበር። አውሮፕላኑ ባለፈው ቅዳሜ አደጋ ካጋጠመው የዩኒይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር በተመሳሳይ የ26 ዓመት እድሜ ያለው ነው። በ2018፤ አንድ የዩናይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን በሆኖሉሉ ከማረፉ በፊት የቀኝ ሞተሩ ተሰብሮ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በተካሄደው ምርመራ የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ አደጋው የአውሮፕላኑ ሙሉው የንፋስ ማስገቢያ [ፋን] በመሰንጠቁ ምክንያት ያጋጠመ እንደሆነ አስታውቆ ነበር።", "ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ የተወሰኑ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላልተወሰነ ጊዜ ከቀረጥና ታክስ ሙሉ ሙሉ ለሙሉ ነጻ መደረጋቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ እንዳሳወቁት የመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያው ከነሐሴ 28/2013 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተግባራዊ ይሆናል። በዚህም መሠረት የምግብ ዘይት፣ ስኳርና ሩዝ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምባቸው ከቀረጥና ታክስ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሲሆኑ ስንዴ ከውጭ ሲገባ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆን ተወስኗል። ፓስታ እና ማኮሮኒ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የዶሮ እንቁላል ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆን መወሰኑን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ሚኒስትር ዲኤታው ጨምረውም መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠርና የኅብረተሰቡን የመግዛት አቅም ለማሳደግ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን እንዲሁም አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱን ተናግረዋል። ይህ እርምጃ ተግባራዊ ሲደረግ መንግሥት በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ገቢ እንደሚያጣ አመልክተው የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በታክስ ብቻ የሚፈለገውን ውጤት ስለማያመጣ አቅርቦትን ለመጨመር መንግሥት በከፍተኛ ወጪ ሸቀጦችን በመግዛት በዝቅተኛ ዋጋ ለኅብረተሰቡ እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች በሌሎች አካላት የሚገባውን አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ ይጨምር ዘንድ ለስድስት ወር ተፈቅዶ የነበረው ያለውጭ ምንዛሬ ሸቀጦችን የማስገባት አስራር ለሌላ ተጨማሪ ስድስት ወራት እንዲራዘም መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል። እነዚህ ማሻሻያዎች የዋጋ ንረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ፣ በምግብ ዋጋ ላይ የሚከሰተውን ጭማሬ መንግሥት ለመቆጣጠር እንዲረዳውና ከውጭ እቃ ለሚያስገቡ ነጋዴዎችንም ለማበረታት ያለመ እንደሆነም ተገልጿል። በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ያለው የምግብ ዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር 32 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህም በአሥር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል።", "ካፒታሊዝም፡ የአፕል ኩባንያ ሀብት ዋጋ ግምት ሁለት ትሪሊዮን ዶላር ደረሰ የቴክኖሎጂው ኩባንያ አፕል በስቶክ ገበያ የሀብት ምጣኔ ግምት ከቢሊዮን ዶላሮች አልፎ በትሪሊዮን ዶላር የተገመተ ሁለተኛው የዓለም ኩባንያ ሆኗል፡፡ በአሜሪካ በ2 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት ያለው ኩባንያ የለም፡፡ አፕል የመጀመርያው ሆኗል፡፡ ከዚህ ቀደምም አንድ ትሪሊዮን ዶላር ለመድረስ የመጀመርያው ሆኗል፤ በ2018 ዓ.ም መጀመርያ፡፡ አሁን የአፕል የአንድ ሼር ዋጋ ግምቱ $467.77 ዶላር ደርሷል፡፡ ትናንትና ረቡዕ በነበረው የስቶክ ገበያ የኩባንያው ጥቅል ሀብት 2ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተበስሯል፡፡ በዓለም ላይ 2 ትሪሊዮን ዶላር ጣሪያ ለመድረስ ብቸኛና የመጀመርያ የነበረው ኩባንያ የሳኡዲ አረቢያው የነዳጅ ድርጅት አራምኮ ነው፡፡ ሆኖም አራምኮ በስቶክ ገበያ የነበረው ዋጋ ባለፈው ታኅሣሥ ወር የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆልን ተከትሎ የሼር ምጣኔውም በዚያው ወርዷል፡፡ ከዚያ ወዲያ የስቶክ ዋጋ ግምቱ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር ላይ ተቀምጧል፡፡ በሐምሌ ወር አፕል አራምኮን በመብለጥ የዓለም እጅግ ሀብታሙ ድርጅት ሆኗል፡፡.በስቶክ ገበያም በጣም ተፈላጊ የግብይይት ኩባንያ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡ የማያባራ ገበያ የአይፎን ስልኮችን ፈብራኪው አፕል በዚህ ዓመት የሼር ድርሻው በ 50% ነው የተመነደገው፡፡ ይህ የሆነው ታዲያ ዓለም በኮሮና ተህዋሲ በሚታመስበት ወቅት ነው፡፡ የኮቪድ መከሰት አፕል በኢሲያ በተለይም በቻይና ያሉ መደብሮቹን እንዲዘጋ አስገድዶታል፡፡ ቻይና በድርጅቱ ላይ ፖለቲካዊ ጫና ስታደርስ ነው የቆየችው፡፡ እንዲያም ሆኖ ነው የድርጅቱ የስቶክ ድርሻ ገበያው እየደመቀለት የሄደው፡፡ ብዙዎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከሌሎች ዘርፎች በተሻለ አስቸጋሪውን ጊዜ ለማለፍ የሚችሉበት አጋጣሚ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የስቶክ ድርሻቸው እየተመነደጉ ያሉት ከቴክኖሎጂ ጋር የተሳሰሩት ኩባንያዎች ናቸው፡፡ አፕል በዚህ የዓመቱ ሦስተኛው ምዕራፍ ላይ ማለትም ሐምሌ መጨረሻ ላይ ትርፉ ወደ 60 ቢሊዮን ዶላር መጠጋቱን አብስሯል፡፡ በአሜሪካ ከአፕል ቀጥሎ ከፍተኛ የስቶክ ግምት ዋጋ ያለው ኩባንያ አማዞን ሲሆን ምጣኔውም 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ነው፡፡.", "ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት ከምታደርገው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ምን ያህል ተጠቃሚ ናት? በያዝነው ወር ግንቦት 2003 ዓ.ም ነበር ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገር ጂቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የጀመረችው። በአፍሪካ የልማት ባንክ በ95 ሚሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ በተገነባው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር የመጀመሪያው ዓመታዊ 22 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለጅቡቲ በመሸጥም የኃይል ወጪ ንግድ ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት ተበሰረ። የግልገል ጊቤ ሁለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ባጋጠመው የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በመዘጋቱ ከታቀደው አንድ አመት ዘግይቶ ነበር የተጀመረው። በወቅቱ የነበረው የኃይል ሽያጭም ለአገሪቱ በአማካኝ በዓመቱ 10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝላት የአገራትን ምጣኔ ኃብት ትንበያዎችን እንዲሁም ጥልቅ ዳሰሳዎችን የሚያዘጋጀው ኢኮኖሚክ ኢንተለጀንስ ዩኒት በወቅቱ ባወጣው ሪፖርት አስነብቧል። በሪፖርቱ መሰረት ከጂቡቲ ከሚገኘው ገቢም የተወሰነውን በገጠር ያሉ ህዝቦቿ መብራት እንዲያገኙ፣ በተጨማሪም በአገር ውስጥ ያለውንም የኃይል ተደራሽነት ለማሳደግ እቅድ ተይዞ ነበር። ከአስር ዓመት በኋላ በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 90 ሚሊዮን ዶላር ማስገባት ችላለች። ለጂቡቲ በ22 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የጀመረችው ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኃይል ማዕከል ለመሆን የአስር አመት ፍኖተ ካርታን አዘጋጅታለች። በዚህ የቀጣይ አስር ዓመታት ይተገበራል በተባለው የኢነርጂ ልማት መሰረት አገሪቷ በ2022 የምታመነጨውን የኃይል መጠን ወደ 20 ሺህ ማሳደግ እንዲሁም ለጎረቤት አገራት የምትሸጠውን የኃይል መጠንም ወደ 7 ሺህ 184 ጊዋስ (GWH) ለማድረስ ታቅዷል። በአሁኑ ወቅት ለጎረቤት አገራቱ ሱዳንና ጂቡቲ አመታዊ የኃይል ሽያጭ የምታቀርብ ሲሆን ለኬንያም የኃይል ሽያጭ ለመጀመር የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታን ግንባታን ካጠናቀቀች አንድ አመት ሆኗታል፤ ፍተሻውም የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ እንደሚጀመርም ይጠበቃል። የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የወጪ ንግድ ከውሃ ሃይል፣ ነፋስ፣ እንፋሎት፣ የጸሃይ ብርሃንንን በመጠቀም የንጹህ ኃይል አምራች ለመሆን እቅድ ይዛ ያለችው ኢትዮጵያ በዚህም ማሳካት የምትፈልገው ከምስራቅ አፍሪካ ባሻገር የአፍሪካ የኃይል ምንጭ ማዕከል መሆንን ነው። ከጎረቤት አገራት ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠርም ለጂቡቲና ለሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ በአማካኝ በየአመቱ 70 ሚሊዮን ዶላር ገቢን ለማግኘት እየሰራች ትገኛለች። ለሁለቱ አገራት የምትልከው የኃይል መጠን ባለው ስምምነት መሰረት በ100 ሜጋ ዋት የሽያጭ ማዕቀፍ ሲሆን የተወሰነ ከፍና ዝቅ ማለት እንዳለም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ያስረዳሉ። ከ100 ሜጋ ዋት በላይም ይሁን በታች እንደቆጠረው ሁኔታ አገራቱ ክፍያቸውን ይፈጽማሉ። በባለፉት ዘጠኝ ወራት ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ መረጃ በምናይበት ወቅት ለሱዳን የኤሌክትሪክ ኩባንያ ወደ 746.9 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት የመሸጥ እቅድ ተይዞ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከእቅዱ በ4 በመቶ ብልጫ ያለው 774.2 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ወጪ ንግድ ተካሂዷል። በተጨማሪ ወደ ጂቡቲ 385 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም 427.1 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ሽያጭ በመደረጉ ከእቅዱም 11 በመቶ ብልጫ አሳይቷል። በዚህም ለሱዳን ከተሸጠው ኃይል 38.7 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለጂቡቲ ከተሸጠው ደግሞ 27.8 ሚሊዮን ዶላር በአጠቃላይም በዘጠኝ ወራት ከኃይል ሽያጭ 67 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተገኝቷል። ገቢው ከእቅዱ አንፃር ሲታይ የሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ የተጠቀመው 4 በመቶ ጭማሪ፣ የጅቡቲ ደግሞ 15 በመቶ ገደማ ጭማሪ ማሳየቱን አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። በየዓመቱ ለጎረቤት አገራት በጅምላ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 70 ሚሊዮን ዶላር ቢታቀድም በአመታት ውስጥ ጭማሬ እያሳየ መምጣቱንም የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ ሞገስ መረጃዎችን በማጣቀስ ያስረዳሉ። እስካሁን ድረስ ባለው ከፍተኛ የተመዘገበው በባለፈው ዓመት ሲሆን በ2013 ዓ.ም ሲሆን ከነበረው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ወደ 90 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተገኝቷል። በአመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የምትሸጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም እንዲሁም ገቢውም ጨምሯል። ሆኖም ከሁለት አመታት በፊት የአገሪቱ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውሃ ባለመያዛቸው ምክንያት በተፈጠረው ዕጥረት ለወራት ያህል ለሱዳን አቅርቦት ከማቋረጥ በተጨማሪ ኤሌክትሪክ በፈረቃ መከፋፈል ተጀምሮ ነበር። በዝናብ እጥረት ምክንያት በተፈጠረው ችግር በደቡብ እና በምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙት ሦስት ግድቦች ቆቃ፣ መልካ ዋከናና ጊቤ ሶስት በቂ ውሃ እንዳይዙ አድርጓቸዋል። በወቅቱ ሱዳን ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ፍላጎት እንደነበራት የሚያወሱት አቶ ሞገስ፣ የአገር ውስጥ ፍላጎት ባለመሟላቱና ወደ ፈረቃ በመገባቱም ወጪ ንግድ ለአምስት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በዚህም ዓመታዊ ገቢውን ከ60 ሚሊዮን ዶላር በታች አድርጎታል። በተያያዘ ዜና በዘንድሮው ዓመት ሱዳን ያልከፈለችው ውዝፍ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሱዳን ኤሌክትሪክ ኃይል ይከፈለኝ የሚል ደብዳቤ ጽፏል። ተቋሙም በጻፈው ምላሽ አገሪቱ ያለችበትን ፈታኝ ሁኔታ ጠቅሶ ታገሱኝ፣ አገልግሎቱም አይቋረጥ የሚል ጥያቄ መቅረቡንም አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። ከዚህ ቀደም ለሁለት ወይም ሶስት ወራት ሳይከፈል የሚዘልበት ጊዜ ቢኖርም በአሁኑ ወቅት ግን ከተለመደው ውጭ ስድስት ወራት በላይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሞገስ መጠኑን ግን መጥቀስ አልፈለጉም። የኬንያ ኃይል ሽያጭ ለምን ዘገየ? የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭን ከጂቡቲ በመቀጠል ለሱዳን ከዓመታት በፊት ማቅረብ የጀመረችው ኢትዮጵያ ለሌላኛዋ ጎረቤት አገር ኬንያም ኃይል ለማቅረብ የወጠነችው ከአመታት በፊት ነበር። ኢትዮጵያና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመገበያየት የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት ከአስር ዓመት በፊት ነበር። በወቅቱም የነበሩ የአገሪቱ ሚዲያዎችን ስናገላብጥ እንዳገኘነው በወቅቱ የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑና በኬንያው የኢነርጂ ሚኒስትር የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት ከአራት አመት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ እንዲጀመር ነበር። ለምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ከፍተኛ ስፍራ ያለውና 1.3 ቢሊዮን ዶላር የፈጀው የዚህ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን ኢትዮጵያ በባለፈው ዓመት ገንብታ ጨርሳለች። አገራቱን የሚያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር 500 ኪሎ ቮልትና ከኢትዮጵያ በኩል 412 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ በአጠቃላይ ከ1 ሺህ ሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው እንደሆነ አቶ ሞገስ ይናገራሉ። ወጪውም ከዓለም ባንክ ከተገኘው ብድር 684 ሚሊዮን ዶላር፣ ለኢትዮጵያ 441 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 27.4 ቢሊዮን ዶላር የሚሸፈን ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክም ይህንኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የግልገል ጊቤ ሶስት ግድብ ጋር የሚያገናኘውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ድጋፍ ለኢትዮጵያ 232 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 116 ሚሊዮን ዶላር አጽድቋል። ለኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታና ለሌሎች ስራዎች ከለጋሽ ተቋማት በብድር ከተገኘው በተጨማሪ አገራቱም ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ለመስራት የራሳቸውን ወጪ አድርገዋል። በባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ በኩል የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ግንባታና የፍተሻ እንዲሁም የሙከራ ስራዎች ቢጠናቀቅም ከኬንያ በኩል ቀሪ የዝርጋታና የፓወር ተከላ ስራዎች እንዳሉ እየተነገረ መጀመር ከነበረበት ወቅት እየተጓተተ ረዘም ያሉ ወራት ተቆጥረዋል። በያዝነው አመት መስከረም ላይ በኬንያ ኢነርጂ ሚኒስትር የተመራ ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረ ሲሆን በቀሪ ጉዳዮች ላይ ስምምነቱን ለማጠናቀቅና ቀሪው የፕሮጀክቱ አካልም እንዲጠናቀቅ ስምምነት ላይ መደረሱንም አቶ ሞገስ ያወሳሉ ። ከወራት በኋላ እንዲሁ ጥር ወር መጨረሻ ላይ የዘገየውን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር 400 ሜጋ ዋት የሃይል ሽያጭ ለማፋጠን ኢትዮጵያና ኬንያ አዲስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሚዲያዎች ዘግበዋል። በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር እዮብ ተካልኝ የተመራ የልዑካን ቡድን ናይሮቢ ጥር መጨረሻ ላይ መጥቶ ከኬንያ ኤነርጂ ሚኒስትር ሞኒካ ጁማ ጋር ተገናኝተው ነበር። አገራቱ ቀደም ሲል በተፈረሙ የኃይል ስምምነቶች፣ የማጠናቀቂያ ስራዎች፣ የአሰራር መመሪያዎችንም በተመለከተ ተወያይተው መከለሳቸውም ተዘግቧል። የኬንያ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ለኬንያ ከኢትዮጵያ 400 ሜጋ ዋት የምትገዛው ኃይል ርካሽ መሆኑን ነው። ከኬንያ በኩል ከመስመር ዝርጋታ ግንባታ መጓተት በተጨማሪ ስምምነት የተደረሰበት የ400 ሜጋ ዋት ኃይልን በተመለከተ እንዲሁም ከተወሰነው ታሪፍ ጋር ተያይዞ ጥያቄ መነሳቱንም ሚዲያዎች ዘግበዋል። ሆኖም አገራቱ ያላቸውን ልዩነት በመፍታት የያዝነው አመት ከመጠናቀቁ በፊት ኃይል የማስተላለፍ ስራው ይጀመራል የሚል እቅድ ተይዞም እየተጠበቀ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በምስራቅ አፍሪካ ያሉ አገራት መካከል ድንበር ዘለል የሃይል ንግድ እንዲሁም ትስስርን ለማስተባበር በአውሮፓውያኑ 2005 የተቋቋመው ቀጠናዊ ተቋም የሆነው ኢስተርን አፍሪካ ፓወር ፑል አካል ነው። በአጠቃላይ የኃይል ልማት እና ተግባር የማስተባበር ስልጣን የተሰጠው የተቋሙ ዋና ፅህፈት በአዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን አስራ አንድ አባል አገራት አሉት። አገራቱም ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ እና ሊብያ። ኮንጎ (ዲአርሲ)፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ናቸው። ፕሮጀክቱ እነዚህንም ሃገራት በኃይል የማስተሳሰርና የማዋሃድ አቅም እንዳለው ይነገራል። በሁለቱ አገራት የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርም እስከ 2000 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ያለው ነው። እንደ አቶ ሞገስ ይህ የኤሌክትሪክ መስመር ኢትዮጵያና ኬንያን ከማገናኘት በተጨማሪ የመካከለኛው ምስራቅ፣ የምስራቅ አፍሪካና ሌሎች የደቡባዊ አፍሪካ ሃገራትንም ተደራሽ ያደርጋል በሚል እሳቤ የማስተላለፍ አቅሙ ከፍ ተብሎ የተሰራ ነው። ለሌሎቹም አገራት ኤክስፖርት የሚደረግበት የኤሌክትሪክ መስመር በአብዛኛው ጤናማ የሆነ መስመር ያለው ሲሆን እንደ የአገር ውስጥ ማስተላለፊያ መስመሮች አሮጌ አለመሆኑንና ኤሌክትሪክ በመሸከም በኩል ችግር እንደማይጠቀስም አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። ለደቡብ ሱዳን ኃይል ለመሸጥ የተደረሰው ስምምነት ከሰሞኑ ደግሞ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በደቡብ ሱዳን የኢነርጂና ግድብ ሚኒስትር ፒተር ማርሴሎ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ ኢትዮጵያ መጥቶ የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን እና የኮተቤ የኃይል ማከፋፋያ ጣቢያን ከጎበኙ በኋላም ከሶስት ዓመት በኋላ የኃይል ሽያጭ እንዲጀመር የሚያስችል ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስምምነቱ ከሶስት ዓመት በኋላ ሽያጭ እንደሚጀመር የጊዜ ገደብ የተቀመመጠለት ሲሆን ይህም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከመጀመሩ በፊት መሰራት ያለባቸው ተግባራት ስላሉ እንደሆነ አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። በዚህም መስረት በመጀመሪያው ዓመት ሁለቱም አገራት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር መዘርጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በተመለከተና ከአቅርቦቱ ጋር የተያያዘ የአዋጭነት ጥናቶችን የሚያካሂድ ቴክኒካል ቡድን ያቋቁማሉ። ይሄንን የአዋጭነት ጥናትም ተከትሎም ባሉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ የሚከናወነው። ግንባታው ሁለት ዓመት ሊፈጅ እንደሚችልም ታሳቢ ተደርጓል። የሁለቱ አገራት የመግባቢያ ስምምነት በሁለት ምዕራፎች የተከፈለ ነው። የመጀመሪያው 357 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ከጋምቤላ 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳኗ ማላካል ግዛት የሚዘልቀው ነው። ሁለተኛውና ረዘም ባለ ጊዜ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው ደግሞ ከ700 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ባለ 400 ወይም 500 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከቴፒ ወደ ቦር ጁባ የሚዘረጋው ነው። ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ በመጀመሪያው ዓመት ላይ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሽያጭ እንዲኖር ስምምነት ላይ ተደርሷል። ሆኖም በ100 ሜጋ ዋት ብቻ እንደማይወሰን የሚናገሩት አቶ ሞገስ የደቡብ ሱዳንን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎችን እንዲሁም የአገሪቱን መሰረተ ልማት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በየጊዜው ሊያድግ የሚችል የኃይል ፍላጎት አቅርቦት ይደረጋል። በዚህም መሰረት ከፍተኛውና ከ400 ሜጋ ዋት የማይበልጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ ነው የመግባቢያ ስምምነቱ የተደረሰው። የኤሌክትሪክ ኃይል ወጪ ንግድ የሚታዩ ችግሮች ረዘም ባለ ጊዜ ዕቅድ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ብሩንዲ የመሸጥ እቅድ አላት። ነገር ግን ድርድሮች ተካሂደው፣ የመሰረተ ልማቶች ዝርጋታ እንዲሁም ግንባታው እስኪከናወን ዓመታት እንደሚጠይቅ አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። \"በፍላጎት ደረጃ እውነት ነው በተለይ ጎረቤቶቻችን ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀዋል።\" የሚሉት አቶ ሞገስ ለምሳሌ ሶማሌላንድ የኃይል አቅርቦት ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች። በተጨማሪም የኃይል አቅርቦት በየዓመቱ የሚሸጥላቸው እንደ ሱዳን ያሉ አገራትም ጭማሬ እየጠየቁ ይገኛሉ። ሱዳን አሁን ከሚደረገው የኃይል አቅርቦት (ከፍተኛው ወደ ሁለት መቶ ሜጋ ዋት) በተጨማሪ በ1 ሺህ 200 ሜጋ ዋት ጭማሬ ፍላጎት እንዳላት አሳውቃለች። \"ይህንን 1 ሺህ 200 ሜጋ ዋት ወደ ሱዳን ለመላክ የሚያስችል አሁን ባለው ሁኔታ እንደ አገር አቅም የለንም ። ያንን ማስተናገድ አንችልም። አሁን ባለው መሰረተ ልማት ደግሞ ሊሆን የሚችል አይደለም። ስለዚህ እሱ ለወደፊት ምላሽ ማግኘት የሚችል ጉዳይ ነው\" ይላሉ። አገሪቷ አሁን ባላት ሃይል የማመንጨት አቅም ለሱዳን የሚላከው መጠን እስከ 300 ሜጋ ዋት ድረስ ቢሆን ብዙ ችግር ባይኖረውም የሱዳን ፍላጎት ግን በጣም ከፍተኛና ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ማሟላት የማትችለው ነው ይላሉ። ከኤሌክትሪክ ወጪ ንግድ ጋር ተያይዞ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ኤክስፖርት ወደሚደረግባቸው ሃገራት የሚጠይቁትን ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉ እንደሆነ አቶ ሞገስ ይጠቅሳሉ። በዋነኝነት ተቋሙ ትኩረት የሚሰጠው የአገር ውስጥ ፍላጎት ስለሆነ፣ ስምምነቶቹ ላይ የአገር ውስጥ ፍላጎት ማሟላት ካልተቻለ ሙሉ በሙሉ የማቆም እርምጃ እንደሚወሰድ የሚጠቅስ አለ። ለምሳሌም የሚጠቅሱት በ2011 የተከሰተውን የኃይል እጥረት ነው፤ በዚህም ወቅት ኢትዮጵያ ለሱዳን የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ከማቋረጥ በተጨማሪ ለጂቡቲ የቀረበው ኃይልም በግማሽ ገደማ ቀንሶ ነበር። ይህ አሰራር ለኃይል ጠያቂዎቹ አገራት ብዙም እንደማይስማማቸው አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። የአገር ውስጥ የኃይል መቆራረጥ ባለበት ወጪ ንግድ እንዴት ይጣጣማል? የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣የተዛባ የንግድ ስርዓት በተለይም የወጪና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን ለአገሪቷ ለአመታት ከፍተኛ ማነቆ የሆነባት ጉዳይ ነው። በገቢና በወጪ ንግድ ሚዛን መጓደልም ጋር ተያይዞ ባለፈው ዓመት አገሪቱ ከወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ በገቢ ንግድ ደግሞ 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንዳደረገች መረጃዎች ያሳያሉ። ይህንንም ከፍተኛ ልዩነት ለማመጣጠን አገሪቱ የወጪ ንግዷን ማሻሻል የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች እንደ መፍትሄ የሚሰነዝሩት ነው። የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ አገሪቱ ገንዘብ ከምታገኝበት ወጪ ንግድ አንዱ ቢሆንም አገሪቱ ካላት ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ሽፋን እንዲሁም ህዝቧ በኃይል መቆራረጥ በሚሰቃይበት ወቅት ኢትዮጵያ ለውጭ አገራት ኃይል መሸጧ ጥያቄን ማጫሩ አልቀረም። ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ ከግብፅ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውን የቅኝ ግዛት ስምምነት ታሪካዊ ተጠቃሚነት በምታነሳበት ወቅት የምትሰጠው ምላሽ ይህ ታሪካዊ ስህተት መስተካከል እንዳለበት በመጥቀስ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ያለ መብራት እና በድህነት በሚማቅቁበት ሁኔታ ግድቡ ያለውን ጠቀሜታ ስታሳውቅ ቆይታለች። አገሪቷ ያላት የኤሌክትሪክ ሽፋን ዝቅተኛ እንዲሁም በርካታ መቆራረጥ የሚታይበት ነው። የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን በምናይበት ወቅት በ2012 ዓ.ም 5.8 ሚሊዮን ደንበኞች እንዲሁም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎች 44 በመቶ የደረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 33 በመቶ ከብሔራዊ ግሪድ የሚያገኙ እንዲሁም ከግሪድ ውጭ ተጠቃሚ የሆኑ 11 በመቶ መሆኑን ከአስር ዓመቱ የልማት እቅድ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። የአገር ውስጥ ሽፋን እንዲህ ዝቅተኛ በሆነበት መጠንና በአገሪቱ የኃይል አቅርቦት እየተቆራረጠ ባለበት ሁኔታ ለጎረቤት ሃገራት ወጪ ንግድ ማድረግስ እንዴት ይጣጣማል? ቅድሚያ የሚሰጠው የአገር ውስጥ ፍላጎት ማሟላት ላይ እንደሆነ አፅንኦት በመስጠት የሚናገሩት አቶ ሞገስ በአገር ውስጥ እያንዳንዱ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ፋብሪካዎችን ጨምሮ ፍላጎታቸው ሳይሟላ የወጪ ንግድ የሚደረግበት አሰራር እንደሌለ ያስረዳሉ። ለዚህም የኃይል ወጪ ንግድ አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የምትሸጠው ከምታመርተው እስከ 10 በመቶውን መሆኑም አቶ ሞገስ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ 6 ሺህ ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚችል ህዳሴ ግድብን እያጠናቀቀች ከመሆኑ አንፃር የሚመረተውን ኃይል ከፍ የሚያደርገው ሲሆን የአገሪቱንም 10 በመቶ ወጪ ንግድ ድርሻ ከፍ እንደሚያደርግም ያስረዳሉ። \"ከፍተኛ ኃይል አመንጭተናል ብለን ያመነጨነውን ኃይል ኤክስፖርት አናደርግም። አገራችን የኃይል ጥያቄ በየቦታው ነው ያለው። ኤሌክትሪክ የሚፈልገው ህዝብ ብዙ ነው። የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማስፋፋት ይጠይቃል\" እነዚህ ባሉበት ሁኔታ የመነጨውን ሁሉ ኤክስፖርት አይደረግም\" ይላሉ። አቶ ሞገስ እንደሚያስረዱት በተጨማሪም ሽያጩ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ የኃይል አጠቃቀምን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ይህ ማለት አገሪቱ ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት (ፒክ ሃወር) ውጭ ያለውን ነው ለሽያጭ የምታቀርበው። በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ወቅትን አቶ ሞገስ ሲያብራሩ ጠዋት ሰራተኛው ወደ ስራ ከመሄዱ በፊት ምግብ ለማብሰል፣ ሌሎችንም ተግባራት ለማከናወን ከፍ ያለ ነው። ሆኖም ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት በኋላ የተጠቃሚው ቁጥር እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን ወደ ስድስት ሰዓት አካባቢም እንደገና የተወሰነ ጭማሬ እንደሚያሳይም አቶ ሞገስ ይጠቅሳሉ። በመቀጠልም ምሽት ላይ ከ12 ሰዓት በኋላ አጠቃቀሙ ይጨምርና ወደ 4 ሰዓት ማታ የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል። እንደ አቶ ሞገስ ከፍተኛ ፍላጎት ካላበት ሰዓት (ፒክ ሃወርን) ውጭ ያለው አጠቃቀም ዝቅተኛ ሲሆን በተለይም የምሽቱ ሰዓት ላይ ደግሞ የወጪ ንግድ ወደሚደረግባቸው ሱዳንና ጂቡቲ ከፍተኛ ሙቀት ያለበትና ኤይር ኮንዲሽነር ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አስገዳጅ የሚሆንበት ነው። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አጠቃቀም ዝቅ በሚልበት የምሽት ሰዓት የአገራቱ ፍላጎት ከፍ ስለሚል ኢትዮጵያ ይህንን አሰራር በመጠቀም የኃይል ወጪ ንግድ እንደምታደርግ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያን የአፍሪካ ኢነርጂ ማዕከል የማድረግ ዕቅድ ኢትዮጵያ ፍላጎት ላሳዩና ለሌሎች ሃገራት በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት በማድረግ ለአገሪቱ የውጪ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ዘርፎች ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነች እንምትገኝ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ይሰማል። ለዚህም የአስር ዓመቱ ፍኖተ ካርታ ተጠቃሽ ነው። በፕላንና ልማት ኮሚሽን የተዘጋጀው የ2013- 2022 የአስር ዓመት የኢነርጂ ልማት ዕቅድ በአገር ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርቶችን የሚያሟላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማቅረብን በዋነኝነት አቅዷል። በዚህም የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በ2012 ዓ.ም 4478 ሜጋ ዋት ከነበረው በ2022 ወደ 19 ሺህ 900 ሜጋ ዋት ማሳደግ እንዲሁም ለጎረቤት አገራት የምትሸጠውን መጠንም ከ2ሺህ 802 ጊዋስ (GWH) ወደ 7 ሺህ 184 ጊዋስ (GWH) ለማድረስ ታቅዷል። አገሪቷ ከውሃ፣ ንፋስ፣ ጂኦተርማል፣ ጸሃይ፣ ባዮማስ ከፍተኛ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት የሚጠቀስ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በቅርቡ ማመንጨት የጀመረውን የህዳሴ ግድብ አንደኛ ዩኒት 375 ሜጋ ዋትን ጨምሮ 4890 ሜጋ ዋት ኃይል ታመርታለች። በ5ሺህ 150 ሜጋ ዋት ማመንጨት አቅሙ በአፍሪካ ትልቁ እንዲሁም በዓለም ስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጠውን የህዳሴ ግድብ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት እየተቃረበች ሲሆን ይህም የአገሪቱን የኃይል አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድግም የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኢነርጂ ማዕከል ለመሆን በያዘችው እቅድ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 71 የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የ40 ቢሊዮን ዶላር ፍኖተ ካርታ ይፋ ማድረጓን ዘ አፍሪካ ሪፖርት ባለፈው ዓመት ጳጉሜ መጨረሻ ላይ ባወጣው ሪፖርት ይዟል። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ 16ቱ የውሃ ኃይል፣ 24 በነፋስ፣ 17 በእንፋሎት እና 14 የጸሃይ ብርሃንን በመጠቀም ሲሆን ይህም ይላል የዘ አፍሪካ ሪፖርት ንጹህ ኢነርጂን በመጠቀም ረገድ በዓለም ላይ ትልቅ የፖሊሲ ለውጥን የሚያሳይ እንዲሁም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ንጹህ ኢነርጂን በመጠቀም ቀዳሚ እንድትሆን ያስችላታል ይላል። በዚሁ ዘገባ ላይ በአውሮፓውያኑ 2037፣ 35 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጫት አቅም ለመገንባት እቅድም እንደያዘች አስነብቧል። አገሪቷ ከአስር ዓመት ፍኖተ ካርታ በተጨማሪ በዘንድሮው ዓመት ይጠናቀቃል የተባለ በኤሌክትሪክ ዘርፍ የ25 ዓመት መሪ እቅድ እያዘጋጀች መሆኑንም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያሳያል። ለዚህም አገሪቱ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያደረገችው ላለው ጥረት የኤሌክትሪክ ኃይል ቀዳሚ ስራ በመሆኑ ዕቅዱን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ ያሰረዳል። ዕቅዱ ከአሜሪካ መንግሥት በተገኘ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እርዳታ ደብሊው ኤስ ፒ ከተሰኘ የእንግሊዝ አማካሪ ኩባንያ ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።", "የኮሮናቫይረስ ተጽዕኖ በቻይናና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ቻይና በኮሮናቫይረስ በርካታ ዜጎቿን በሞት ከመነጠቋም በተጨማሪ፤ በምጣኔ ሃብቱ ረገድም በዋናነት እየተጎዳች ያለችው ቻይና ስትሆን ሌሎች አገራትም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል። የመጣኔ ሃበቱ ጉዳት በቀጥታ ቫይረሱ በቀጥታ ያስከተው ብቻ ሳይሆን ቫይረሱን ለመከላከልም ከፍተኛ ወጭ ጠይቋል። 11 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የዉሃን ከተማ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የከተማዋ መግቢያ መውጫ በሮች ተዘግተዋል። በሁቤይ ግዛት በሚገኙ ሌሎች ከተሞችም የሰዎችና የሸቀጦች ዝውውውር እንዲገደብ እየተደረገ ነው። ይህም ለከተሞቹ ትልቅ ኪሳራ ከፍተኛ ይዞ መጥቷል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎችም ወደ ሥራ ስንሰማራ ቫይረሱ ሊይዘን ይችላል በማለት ሥራ መስራትና ከሰዎች ጋር መገናኘትን አቁመዋል። ምግብ ቤቶች፣ ሲኒማዎች፣ የትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች፣ ሆቴሎችና ሱቆች የመጀመሪያዎቹ የምጣኔ ኃብት ቀውሱ ተጠቂዎች ናቸው። አምራቾችም ከቻይና ውጭም ገበያ ለማፈላለግ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ዓለም አቀፍ አከፋፋዮችም ለጊዜው በቻይና ያላቸውን መደብር እየዘጉ እየወጡ ነው። አይኪያ የተባለው የቤት እቃ አምራች ኩባንያ እና ስታርባክስ አገልግሎታቸውን በቻይና ካቋረጡት ተጠቃሽ ናቸው። ቻይና በግዥው ሂደት በብዛት የምትሳተፍባቸው የኢንዱስትሪ ነክ ምርቶች በከፍተኛ ደረጃ በዓለም አቀፉ ገበያ ዋጋቸው ቀንሷል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ቢያንስ በ15 በመቶ ቀንሷል። ይህ ደግሞ የሆነው የቻይናው ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ 'ሲኖፔክ' የማጣራት አቅሙን በመቀነሱ ነው ተብሏል። በርካታ የነዳጅ አምራች አገራት ዋጋውን እንደገና ለመጨመር የምርት መጠናቸውን ለመቀነስ እየተነጋገሩ ይገኛሉ። መዳብም በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በ13 በመቶ ከነበረበት ዋጋ አሽቆልቁሏል። አንድ የኦክስፎርድ ምሁር በቫይረሱ ምክንያት የቻይና ምጣኔ ሃብት በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ4 በመቶ ባነሰ ያድጋል በማለት ትንበያቸውን አስቀምጠዋል።", "የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ የእርዳታ ሥራዎቹ ሊገቱ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ነዳጅና ምግብ መተላለፍ ባለመቻሉ የነፍስ አድን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ሥራው ሊቆም መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስጠነቀቀ። ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው ጦርነት ምክንያት ከታህሣሥ ጀምሮ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የእርዳታ ጭነት መኪኖች መቀለ ሊደርሱ እንዳልቻሉ ድርጅቱ ዛሬ ጥር 6/2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። በተጨማሪም ምግብ፣ ነዳጅና የገንዘብ ድጋፍ ዕጥረት እንዳጋጠመው የገለጸው ድርጅቱ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ላለባቸው ህጻናት እና ሴቶችን ለመንከባከብ የሚውለው አልሚ ምግብ ተመናምኗል ብሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የመጨረሻ ክምችት የሆነው እህል፣ ጥራጥሬ እና ዘይት በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚሰራጭም ጨምሮ ገልጿል። \"በአሁኑ ወቅት የትኞቹን መመገብ እንዳለብን የትኞቹን ደግሞ እንዲራቡ ለመተው መምረጥ አለብን\" በማለት የድርጅቱ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ማይክል ደንፎርድ ገልጸዋል። አክለውም \"በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ለሰብዓዊ እርዳታ መተለላፊያ የሚሆኑ መንገዶች ደኅንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ዋስትና እንዲሰጡን እንፈልጋለን\" በማለት አስረድተዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶች በቀላሉ በሚፈለገው ፍጥነትና መጠን መድረስ እንዳልተቻለ የገለጹት ዳይሬክተሩ በትግራይ ባለው የምግብና የነዳጅ እጥረት ምክንያት ከሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን መደረስ የተቻለው 20 በመቶ ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም በትግራይ ያለውን ሁኔታ ሲገልጹት \"በሰብዓዊ ጥፋት አፋፍ ላይ ነን\" ብለዋል። በዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ መሰረት በሰሜን ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ጦርነት ወደ 9.4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህም አሃዝ ከአራት ወራት በፊት ከነበረው የ2.7 ሚሊዮን ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም እስካሁን ከታየው ከፍተኛው መሆኑንም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል። በተጨማሪም ውጊያው ከመፋፋሙም ጋር ተያይዞ የምግብ ስርጭቱም በጣም ዝቅተኛ መሆኑንም ጠቁሟል። ድርጅቱ በትግራይ ለ2.1 ሚሊዮን፣ በአማራ ለ650 ሺህ እና በአፋር ለ534 ሺህ ሕዝብ የምግብ ዕርዳታ ለመስጠት አቅዷል። ሆኖም ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ባጋጠመው የገንዘብ ድጋፍ ዕጥረት ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰጠው የምግብ እና ሌሎች እርዳታዎች አቅርቦት በሚቀጥለው ወር እንደሚያልቅም አስጠንቅቋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ምግብ እርዳታ ለማድረስ 337 ሚሊዮን ዶላር እና ባበለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሶማሌ ክልል በከፋ ድርቅ ለተጎዱ ነዋሪዎች እርዳታ ለማድረስ 170 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት መሰረት እርዳታ የጫኑ መኪኖች ከታኅሣሥ ጀምሮ ወደ ትግራይ አልገቡም። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ ያለውን ከአምስት ሚሊዮን በላይ እርዳታ ፈላጊ ሕዝብ ለመድረስ ከታሰበ በየሳምንቱ 100 እርዳታ የጫኑ መኪኖች ወደ ክልሉ ሊገቡ ይገባል ቢልም፣ እንደ ኦቻ ሪፖርት ወደ ክልሉ መግባት የቻለው ከሚያስፈልገው አቅርቦት ውስጥ 12 በመቶ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዳይደርስ ምንም አይነት ክልከላ እንዳልጣለ ገልጾ፣ ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ ደግሞ ወደ ክልሉ የእርዳታ አቅርቦት እንዳይገባ በማድረግ ህወሓትን ከሷል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል።", "ለከብቶቻችን የምንሰጠውን ያደረ ዳቦ ለራሳችንም አጥተናል፡ አፍጋኒስታናውያን አፍጋኒስታናውያን ናን የሚሉት ዳቦ አላቸው። ናን አምባሻ የሚመስል በእስያ ተወዳጅ ምግብ ነው። አፍጋኒስታናውያን ‘የዕለት እንጀራዬን አትንፈገኝ’ የሚሉት ይህን ዳቦ እያሰቡ ነው። መሃል ካቡል ሰማያዊ መስጂድ ይገኛል። በአቅራቢያው አነስተኛ ጉልት አለች። በዚህች ገበያ ትልልቅ ብርቱካናማ ከረጢቶች በደረቁ የናን ዳቦዎች ተሞልተዋል። ከዚህ ቀደም በየቦታው የሚተራርፉ ዳቦዎች ለእንስሳት ምግብነት ይውሉ ነበር። አሁን ግን ነገሮች ተቀይረዋል። ብዙ አፍጋኒስታናውያን ረሃባቸውን ለማስታገስ ወደ እነዚህ ዳቦዎች ፊታቸውን እያዞሩ ነው። ሻፊ መሐመድ የካቡል ፑል ኬሽቲ ገበያ ነጋዴ ነው። ላለፉት 30 ዓመታት ትኩስ ያልሆነ ዳቦ ይሸጣል። ስለገበያው ሁኔታ ሲገልጽም \"በፊት በፊት በቀን አምስት ያህል ሰዎች ብቻ ነበሩ የሚገዙን።አሁን ከ20 ሰው በላይ ይገዛናል\" ይላል። ያደረ ዳቦ ገበያው ደርቷል። ሁሉም ሰው በአገሪቱ ምጣኔ ሐብት መቆርቆዝ ቅሬታውን ይገልጻል። ታሊባን ባለፈው ነሐሴ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ወዲህ የዜጎች ገቢ በአንድ ሦስተኛ ቀንሷል። የምግብ ዋጋም ጣሪያ ነክቷል። ሻፊ፣ ሻል የሚሉ ዳቦዎችን ከላስቲክ ከረጢቱ ውስጥ እያወጣ ያሳያል። አልሻገቱም እንጂ የቆዩ ዳቦዎች ናቸው። ቢሆንም ለምግብነት የሚገዟቸው ብዙዎች ናቸው። \"የአሁኑ የአፍጋኒስታናውያን ሕይወት ምንም ዓይነት ምግብና ውሃ እንደማታገኝ የታሰረች ወፍ ነው። ይህን መከራና ድህነት ከአገሬ እንዲወገድ እጸልያሁ\" ይላል ሻፊ። የረሃብ ስጋት በመኖሩ ሰብዓዊ ድጋፍ ይሰጣል።ግን በቂ አይደለም። አፍጋኒስታን በልመና ዕርዳታ ላይ የተንጠለጠለች ናት። ታሊባን መንበረ ሥልጣኑን ሲቆጣጠር ምዕራባዊያን ይህንን ዕርዳታ አቋረጡ። የአገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ ሐብትን ማገዳቸው ሲጨመርበት ደግሞ ቀውሱን አባባሰው። እርምጃው የተወሰደው ከሴቶች አያያዝ ጋር በተያያዘ በተነሳ ስጋት ነው። ታሊባን አዲስ ይፋ ባደረገው ጥብቅ ገደብ ከሴቶች አለባበስ ጀምሮ የተለያዩ ሕጎችን አሳልፏል። ይህም ውሳኔውን አስቸጋሪ አድርጎታል። ቀውሱ የሦስት ልጆች አባት እንደሆነው ሃሽማቱላህ ያሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ላይ ክንዱን አበርትቷል። የዕለት ጉርሱን የገበያተኞችን ዕቃ በመሸከም ያገኛል። ገቢው በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ካለፈው ዓመት አንድ አምስተኛውን ነው እያገኘ ያለው። የተረፈ ዳቦ የገዛበትን ፌስታል እያሳየ “ከነጋ በሠራሁት መግዛት የቻልኩት ይህንን ነው” ብሏል። የተረፈ ዳቦ ከሚሸጡት ሰዎች ጀርባ አንድ አነስተኛ ኢንዱስትሪ አለ። ቆሻሻ ሰብሳቢዎች ከምግብ ቤቶች፣ ከሆስፒታሎች እና ከግለሰብ ቤቶች ዳቦዎቹን ይሰበስባሉ። ከዚያም ለነጋዴዎች ይሸጣሉ።ገዢዎች ከእነዚህ ነው የሚገዙት። ግማሽ ያህሉ ሕዝብ ወደ ረሃብ አረንቋ እየተገፋ ነው። ይህ ደግሞ የተረፈ ዳቦ የማግኘት ዕድልን ያጠበዋል። ከአንድ ሳምንት በላይ የተሰበሰበውን አንድ ጆንያ የተረፈ ዳቦ እያሳየ  \"ሰዎች እየተራቡ ነው\" ይላል አንድ የተጣሉ ዕቃዎች ነጋዴ። ቀደም ሲል ግን በቀን አንድ ጆንያ ይሰበስብ እንደነበር ይናገራል። ሌላ ነጋዴ ደግሞ \"ንጹህ ዳቦ ካገኘን ብዙውን ጊዜ ራሳችን እንበላዋለን\" ብሏል። ሃሽማቱላህ የድሃዎች መናኸሪያ በሆነችው የካቡል ሰፈር በሚገኝው ቤቱ ለቤተሰቡ ምግብ ያዘጋጃል። ሦስቱ ልጆቹ እንዲማሩለት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ብዙ ወላጆች እንደሚያደርጉት ልጆቹን ወደ ሥራ ከመላክም ተቆጥቧል። ሕይወታቸው በበሰበሰ ቲማቲም እና ሽንኩርት እና በከረመ ዳቦ ላይ ተንጠልጥሏል። \"በጣም ድሃ በመሆኔ እና ጥሩ ምግብ የማቅረብ አቅም ስለሌለኝ ቤተሰቦቼ ፊት አፍራለሁ\" ይላል። \"ምንም ማድረግ አልችልም። ልበደር ብልስ ማን ያበድረኛል . . . ልጆቼ ጥሩ ምግብ ስለማያገኙ በጣም ቀጫጭን ናቸው።\" ብሏል ሃሽማቱላህ በተሰበረ ስሜት። ካቡል በሚገኙ ዳቦ መጋገሪዎች በር ላይ ህጻናት እና ሴቶች ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነው። ምሽት ላይ ያልተሸጠ ትኩስ ናን ካገኘን በሚል ነው የሚሰበሰቡት። አንዳንዶች እዛው ቁጭ ብለው ልብስ ይሰፋሉ። ቤት ሆነው ሲሰፉ ዳቦ ከተሰጠ ዕድሉ እንዳያመልጣቸው ነው ይህን የሚያደርጉት። በአንድ ወቅት በቢሊዮን ዶላሮች ወደ አፍጋኒስታን ይፈስ ነበር።በዚያ ወቅትም ሙስና እና ጦርነት የዜጎችን ሕይወት ትግል አድርጎት ነበር። አሁን ጦርነቱ አብቅቷል። ከሕይወት ጋር ያለው ግብግብ ግን እየከበደ መጥቷል።", "አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገትን መተንበይ እንዳልቻለ አመለከተ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በአውሮፓውያኑ 2022 አስከ 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራትን አጠቃላይ አገራዊ ምርት እድገትን (ጂዲፒ) መተንበይ እንዳልቻለ ገለጸ። ድርጅቱ ለዚህ እንደምክንያት ያስቀመጠው በምጣኔ ሀብቱ ውስጥ \"ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ እርግጠኛ ያለመሆን\" በመኖሩ እንደሆነ ገልጿል። ይህ የድርጅቱ አስተያየት የተገለጸው በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ አስራ አንድ ወራትን ያስቆጠረው ግጭትን ተከትሎ ነው። አይኤምኤፍ የዓለም ምጣኔ ሀብት ገጽታ ባሳየበት ሪፖርቱ ላይ በያዝነው የአውሮፓውያን ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ አገራዊ ምርት 2 በመቶ እድገት ያሳያል፣ ይህም ባለፈው ዓመት ከነበረው በአራት በመቶ ዝቅ ያለ ነው ብሏል። በንጽጽርም በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆነችው ጎረቤት ኤርትራ በመጪዎቹ 2022 - 2026 ባሉት ዓመታት የ4.8 በመቶ እድገት እንደሚኖራት ተተንብይዋል። በሌላ በኩል በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ትልቅ የሚባለው ምጣኔ ሀብት ያላት ኬንያ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የስድስት በመቶ እድገት ያሳያል ተብሏል። በተጨማሪም ጂቡቲ 5 በመቶ፣ ሶማሊያ 3.9 በመቶ፣ ደቡብ ሱዳን 6.5 በመቶ እንዲሁም ሱዳን 3.5 በመቶ እድገት ሊኖራቸው እንደሚችል ተተንብይዋል። ባለፉት አስር ዓመታት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አስከ ሁለት አሃዝ የሚደርስ ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ከሚጠቀሱ የአፍሪካ አገራት መካከል ውስጥ ቆይቷል። በወቅቱ ምጣኔ ሀብቷ ድርቅና የብሔር ግጭቶችን የመሳሰሉ ጫናዎች ያጋጠሙት ሲሆን፣ አገሪቱ ለግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ የምታውለው እየናረ የሚሄድ የውጭ እዳ ችግር ሊያስከትል ይችላል በማለት ባለሙያዎች ሲያሳስቡ ነበር። አይኤምኤፍ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ትንበያ ያላስቀመጠላቸው ሌሎቹ አገራት ግጭቶች ያሉባቸው አፍጋኒስታን፣ ሊቢያ እና ሶሪያ ናቸው። የድርጅቱ ሪፖርት የዓለም ምጣኔ ሀብት እድገትን በተመለከተ በሰጠው ትንበያ ባለንበት የአውሮፓውያን ዓመት 2021 5.9 በመቶ ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ግን 4.9 በመሆን ቅናሽ እንደሚያሳይ አመልክቷል። አይኤምኤፍ ለእድገቱ መቀነስ የአቅርቦት መናጋት እና እየተባባሰ ያለው የወረርሽኝ ሁኔታ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ምጣኔ ሀብት ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ገልጿል።", "የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ ሠራተኞቹን ከኢትዮጵያ አስወጣ የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ በአገሪቱ ለሚያካሂደው ኢንቨስትመንቶች አደጋ መደቀኑንና የሚፈጠሩት ክስተቶች የወደፊት የንግድ ውሳኔዎች ላይ ተዛማጅነት እንዳለው ለቢቢሲ ገለጸ። ኩባንያው በቅርቡ የተቀጠሩ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሠራተኞቹንና ተቋራጮችን ከአገሪቱ ማስወጣቱን አስታውቆ፤ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞቹ ደግሞ ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እንደሚደረግ ገልጿል። በምሥራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ ትልቁ እና ትርፋማ የሆነው የቴሌኮም ኩባንያ፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ ጎረቤት ክልሎች እየተዛመተ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀች ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው። የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር ንደጓ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ከወራት በኋላ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ ያሸነፈው ሳፋሪኮም በአውሮፓውያኑ 2022 አጋማሽ ላይ ሁሉም መሰረተ ልማቶች ከተዘረጉ በኋላ ሥራውን እንደሚጀምር ብሩህ ተስፋ አሳድረዋል። ቢቢሲ በዛሬ ረቡዕ ጠዋት አዲስ አበባ በሚገኘው የኩባንያው ጽህፈት ቤት በመገኘት ባደረገው ቅኝት አነስተኛ እንቅስቃሴ የተመለከተ ሲሆን ይህም በቅርብ ጊዜ የሚኖረው ሁኔታ ለኩባንያው እርግጠኛ አለመሆኑን ጠቋሚ ነው። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘውና በሳፋሪኮም የሚመራው የኩባንያዎች ጥምረት በመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 2 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ እና ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ለመቅጠር አቅዷል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ ጥምረት በዘርፉ አሉ የሚባሉ ስመ ጥር የቴሌኮም ኩባንያዎችንና ተቋማትን በቅንጅት የያዘ ሲሆን እነዚህም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕና ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕ ናቸው። ሳፋሪኮም የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ለመደገፍ ከአሜሪካ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ይገኛል የተባለው የ500 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሁኔታ ላይ እርግጠኛ አይደለም። የአሜሪካ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሏል። ከዚህም መካከል አጎዋ የተሰኘው የአሜሪካ ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል መታገድ ይገኝበታል። እንደ አውሮውያኑ በ2020 በአግዋ ሥርዓት አማካኝነት ኢትዮጵያ 237 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ወደ አሜሪካ አስገብታለች።", "ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት የሚያስችል የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆኑ ተገለፀ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የሚደረገውን ጥረት በበለጠ ለመደገፍና ለማሳካት የሚያስችል የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የግብርናና የአምራች ዘርፉን በመደገፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት የሚያስችል የሸቀጦች አመዳደብ ስርዓትን ያለመ ነው የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያው። የቀረጥና ታክስ ማሻሻያው እስከ 8 ሺ የሚሆኑ የታሪፍ መስመሮች የሚያካትት ሲሆን ማሻሻያው ትኩረት ያደረገው በጥሬ እቃዎች፣ በከፊል የተመረቱ ግብአቶች፣ ካፒታል እቃዎች እንዲሁም መሰረታዊ የሚባል የፍጆታ እቃዎችን የሚያካትት ነው፡፡ የግብርናና የአምራች ዘርፉን በመደገፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት የሚያስችል የቀረጥና የታክስ ማሻሻያው ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት እንዲቻል ሁለት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። ይህም የአገር ውስጥ አምራቾች ከታሪፍ አንፃር ከውጭ ከሚገቡ ተመሳሳይ ምርቶች አኳያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው። የመጀመሪያው አቅጣጫ የምርቱ ዓይነት በአገር ውስጥ በሚፈለገው መጠንና ጥራት የሚመረት ከሆነ ከውጭ በሚገባው ተመሳሳይ ምርት ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ምጣኔ ይጣላል። በዚህም የአገር ውስጥ ምርት ይበልጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን ማድረግ ያለመ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ምርቱ በአገር ውስጥ በብቃት የማይመረት ከሆነ በአገር ውስጥ ለሚያመርቱ አምራቾች እነዚህን ምርቶች ለማምረት የሚጠቀሙባቸው በአገር ውስጥ የማይገኙ ግብአቶች በዝቅተኛ የታሪፍ ምጣኔ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ ማድረግ ነው፡፡ በአገር ውስጥ በብቃት የማይመረቱ ምርቶች ላይ ከውጭ በሚገቡበት ወቅት ከፍተኛ የታሪፍ ምጣኔ አይጣልም ተብሏል ለዚህም እንደ ምክንያትነት የተጠቀሰው የዋጋ ንረት የሚያስከትል በመሆኑ ነው። ማሻሻያውን ተግባራዊ ለማድረግ እስከ 8 ሺህ የታሪፍ መስመሮች የሸቀጥ አመዳደብ ስርአትን የያዘ የታሪፍ መለያ ዝርዝር ኮዶችን የያዘ የታሪፍ ጥራዝ (Tariff Book) ተዘጅቷል። የቀረጥና ታክስ ማሻሻያው በሁሉም ዘርፎች በቀጣይ 10 ዓመታት በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትና ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለውም ተብሏል። ከዚህም በተጫማሪ ማሻሻያው ኢትዮጵያ በንግድ ዘርፍ ለምታደርጋቸው ስምምነቶች መሰረት የሚጥል እንደሆነም ተገልጿል። ማሻሻያው ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም ከጉምሩክ ኮሚሽን በተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በተቋቋመ የታሪፍ ኮሚቴ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።", "ኮሮናቫይረስ፡''አፍሪካ ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ ይከብዳታል'' የዓለም ጤና ድርጅት የዓለም ጤና ድርጅት ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለአፍሪካ በእጅጉ አስጊና ከባድ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል። ድርጅቱ አክሎም ወረርሽኙ በተለይ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ አስጊ እንደሆነ አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን ያለው በርካታ አገራት የእንቅስቀሴ ገደቦችንና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማላላት መጀመራቸውን ተከትሎ የቫይረሱ ስርጭት እንደገና ማንሰራራት በመጀመሩ እንደሆነ ተጠቁሟል። የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማነቃቃት በማሰብ ወደቀደመው እንቅስቃሴያቸው መመለስ መጀመራቸው ቫይረሱ ከቁጥጥር ውጪ እንዲሆን እድል እንደሚፈጥር ድርጅቱ አስጠንቅቋል። በርካታ አገራትም በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ እንቅስቃሴዎችን እንደገና እያስጀመሩ መሆኑ እንዳሳሰብው ጠቁሟል። ድርጅቱ አክሎም ነገሮች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ እንደአዲስ ተንሰራፍቶ አገራት ተመልሰው ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ማገድ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ አስታውቋል። አፍሪካ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካጋጣት የኢኮኖሚ ውድቀት ለማገገም እንዲሁም የጤና ወጪ 1.2 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም [አይኤምኤፍ] ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ገንዘቡ ያስፈልጋታል የተባለው ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ነው። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌሎች አህጉራት ያነሰ ነው፤ ነገር ግን የዓለም ባንክ በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካዊያን ለከፋ ድህነት የመጋለጥ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል። በወረርሽኙ ሳቢያ የሥራ እድሎች በመታጠፋቸው እና የቤተሰብ ገቢ በ12 በመቶ በመቀነሱ የደረሰው የኢኮኖሚ ተፅእኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ እየታየ የነበረውን ጠንካራ እድገት እየቀለበሰው መሆኑም ተጠቁሟል። አይኤም ኤፍ የአፍሪካ አገራት ከደረሰባቸው ተፅዕኖ እንዲያገግሙ 26 ቢሊዮን ዶላር የለገሰ ቢሆንም፤ የግል አበዳሪዎች እና በሌሎች አገራት ድጋፍ ቢኖርም፤ አሁንም ግን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለ። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ማሺዲሶ ሞዌቲ እንዳሉት አህጉሪቱ የሚገባትን የክትባት ድርሻ እንድታገኝም ከአሁኑ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። በአፍሪካ እስካሁን 1.6 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ወረርሽኙ አህጉሪቱ ውስጥ መግባቱ ከተሰማባት ዕለት አንስቶ ደግሞ ከ39 ሺ በላይ ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።", "ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ምርት አቋርጦ የነበረው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ወደ ሥራ ተመለሰ በአካባቢው ባለው ጸጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት በመስተጓጎሉ የስኳር ምርቱን አቋርጦ የነበረው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ዳግም ወደ ሥራ መመለሱን የስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ሥራ አስፈፃሚ ለቢቢሲ ገለጹ። ፋብሪካው ለሰባት ቀናት ያህል ከየካቲት 02፣ 2014 ዓ.ም ሥራ አቁሞ የነበረ ሲሆን የካቲት 8 ዳግም ወደ ሥራ መግባቱን የኮርፖሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረታ ደመቀ ተናግረዋል። በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ ጫኝ አሸከርካሪዎች ስጋት አድሮባቸው ወደ ቦታው ሊሄዱ ባለመቻላቸው ነበር የነዳጅ እጥረት ያጋጠመው። \"በአሁኑ ወቅት በያዝነው ሳምንት ሰኞ የነዳጅ አቅርቦት በመድረሱ ማክሰኞ ዕለት ፋብሪካው ዳግም ወደ ሥራ ተመልሷል\" ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው። ብሉምበርግ ፋብሪካው ሥራውን ለማቆም የተገደደው የኦሮሞ ነፃነት ጦር ወይም መንግሥት \"ሸኔ\" የሚለው ታጣቂ ቡድን በፋብሪካው ላይ ባደረሰው ጥቃት ምክንያት ነው በሚል አስነብቧል። አቶ ረታ በበኩላቸው ፋብሪካው ሥራ አቋርጦ የነበረው በአካባቢው አልፎ አልፎ በሚፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት በመስተጓጎሉና እጥረት በመፈጠሩ ነው ብለዋል። ከሳምንታት በፊት አራት ያህል ትራክተሮች ተቃጥለው የነበረ ቢሆንም ይህ ግን ፋብሪካው ሥራ እንዲያቆም አላደረገውም ይላሉ። \"ፋብሪካው ብዙ ሺህ ሄክታር የአገዳ መሬት ያለው ሲሆን በዚያ ውስጥ ትራክተሮች ይንቀሳቀሳሉ። ትራክተሮቹ የተቃጠሉትም እዚያ መሃል ላይ ነው።\" የሚሉት አቶ ረታ ማን እንዳቃጠላቸው የጸጥታ አካላት ምላሽ ሊሰጡበት እንደሚገባ ተናግረዋል። እንደ አቶ ረታ ከሆነ ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የአሁኑን ሳይጨምር ፋብሪካው ከዚህ ቀደም ሥራ ያቆመበት ጊዜ የለም። በዚያ አካባቢ አልፎ አልፎ የጸጥታ ችግር የሚያጋጥም ቢሆንም ፋብሪካው ላይ የተከሰተ ችግር አለመኖሩን አስረድተዋል። \"መስመሩ ላይ የጸጥታ ችግር አጋጠመ ማለት ፋብሪካው ላይ ሊያጋጥም ይችላል ማለት አይደለም። ፋብሪካው ከዋናው መስመር ወደ አምሳ ሜትር ተገንጥሎ ነው የሚገኘው። ለብቻው ወደ ውስጥ ገብቶ ነው ያለው።\"ይላሉ። በተጨማሪም ፋብሪካው የማኅበረሰቡ የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ረታ \"የአካባቢው ኅብረተሰብ እስከ ልጆቹ የሚተዳደረው በፋብሪካው ነው።\" ብለዋል። አቶ ረታ አክለውም ፋብሪካው የቴክኒክ ችግር ሲያጋጥመው ለሰዓታት ሊያቆም እንደሚችልና አስፈላጊው ጥገና ተደርጎለት እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ይህ ግን ማቆም የሚባል ሳይሆን ውስብስብ ማሽኖች ባሉት ፋብሪካ ውስጥ የተለመደ ሁኔታ እንደሆነ ያስረዳሉ። በሰባት ቀናት ውስጥ ፋብሪካው ምን ያህል ገንዘብ ወይም ምርት አጣ? የሚል ጥያቄ ቢቢሲ ለአቶ ረታ ያቀረበላቸው ሲሆን ፋብሪካው በአማካኝ በጥሩ የማምረቻው ወቅት በቀን 10 ሺህ ኩንታል እንደሚያመርት ጠቅሰው ሆኖም ፋብሪካው ምን ያህል እንዳጣ የተገመገመ ጉዳይ አለመኖሩን ተናግረዋል። በስኳር አቅርቦትስ ላይ መጉላላት ፈጥሮ ይሆን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም \"አገሪቱ መተሃራ፣ ወንጂና ጥገናውን በቅርቡ ጨርሶ ወደ ሥራ የገባው በአካባቢው የሚገኘው አርጆ ዴዴሳ ፋብሪካን ጨምሮ ሌሎች ፋብሪካዎች በመኖራቸው የአንድ ፋብሪካ ሰባት ቀን ማቆም በስኳር ሥርጭት ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ አይኖረውም \" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል። ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ፋብሪካው በዓመት 270 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም አለው። ፋብሪካው ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ኢታኖል በማምረት ከቤንዚል ጋር ተደባልቆ ለተሸከርካሪዎች በነዳጅነት እንዲውል ያደርጋል።", "የአሜሪካን የአቪዬሽን ንግድ ሚስጥርን ሰርቋል የተባለው ቻይናዊ ተቀጣ ቻይናዊው የስለላ ሠራተኛ የአቪዬሽን ኩባንያዎችን ምስጢር ለመስረቅ አሲሯል በሚል በአሜሪካ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባሉን የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት አስታወቀ። ዡ ያንጁን የተባለው ይህ ግለሰብ ከኢኮኖሚ ስለላ እና ከንግድ ምስጢር ስርቆቶች ጋር በያያዘ በቀረቡበት አምስት ክሶች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን የ60 ዓመት እስራት እና ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቅጣት ይጠብቀዋል። ዡ ለመጀመሪያ ጊዜ በቁጥጥር ስር የዋለው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ቤልጂየም ውስጥ ሲሆን ምናልባትም ለአሜሪካ ተላልፎ የተሰጠ የመጀመሪያው ቻይናዊ ነው ተብሏል። የቻይና ባለስልጣናት ትናንት [አርብ] ስለተላለፈው ውሳኔ የሰጡት አስተያየት ባይኖርም ቻይና ቀደም ብላ ክሱን መሰረተ ቢስ ስትል ውድቅ አድርጋው ነበር። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ መሰረት ዡ በቻይና ደኅንነት ሚኒስቴር ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚሰራ የስለላ ባለሙያ ነው። ቻይናዊው ሰላይ ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ በአሜሪካ እንዲሁም በሌላ አገራት ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኩባንያዎች ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችን ኢላማ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ነበር ተብሏል። ቻይናዊው እንደ አውሮፓውያኑ በ2017 የአንድ አቪዬሽን ሠራተኛን የጉዞ ወጪ በመሸፈን እና አበል በመክፈል፣ ወደ ቻይና ተጉዞ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገለጻ እንዲደረግ እስከመጋበዝ ደርሶ ነበር። ይህ በሆነ በዓመቱ ባለሙያውን የአንድ ንድፍ ሂደትን የተመለከተ መረጃን እንዲሰጠው ዡ ጠይቋል ተብሏል። ታዲያ ከኤፍ ቢ አይ ጋር ሲሰራ የነበረው ባለሙያው ምስጢራዊ የሆነ መረጃ የሚል ባለ ሁለት ገጽ ሰነድ ለዡ በኢሜይል ልኳል። በመቀጠል ዡ ለባለሙያው ሥራ በሚጠቀምበት ኮምፒውተሩ ላይ የፋይል ቅጂ እንዲልክለት ጥያቄ ያቀርባል። በተጨማሪም በቤልጂየም ውስጥ ባለሙያውን ለማግኘት ሞክሯል። ሆኖም በዚህ ሙከራው ቻይናዊው በቁጥጥር ስር ውሏል። የኤፍ ቢ አይ ረዳት ዳይሬክተር አለን ኮህለር \"የቻይናን እውነተኛ ፍላጎት ለሚጠራጠሩ ይህ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይገባል\" ብለዋል። \"የአሜሪካን ቴክኖሎጂ እየዘረፉ ኢኮኖሚያቸውን እና ወታደራዊ ኃይላቸውን ለማጠናከር እየተጠቀሙበት ነው\" ሲሉም አክለዋል። ይህ ክስ የተሰማው በሁለቱ አገራት መካከል ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው። ቻይና በቅርቡ አዲስ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን ስትሞክር የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ታይዋንን ከማንኛውም የቻይና ወታደራዊ ወረራ ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል። እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ የሲአይኤ ዳይሬክተር ቢል በርንስ ቻይናን ለአሜሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ስጋት መሆኗን ገልጿል። ባለፈው ወር የስለላ ድርጅቱ ቻይና ላይ የሚያደርገውን የስለላ ጥረት እንደሚያሳድግ ገልጿል።", "የናይጄሪያ አየር መንገዶች በአውሮፕላን ነዳጅ ጭማሪ ምክንያት የሀገር ውስጥ በረራዎችን ሊያቆሙ ነው የናይጄሪያ አየር መንገዶች የአውሮፕላን ነዳጅ ጭማሮን በመቃወም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የሃገር ውስጥ በረራዎችን ሊያቆሙ ነው። በተያዘው አመት ብቻ አራት እጥፍ ገደማ መጨመሩን ያስታወቀው የናይጄሪያ አየር መንገድ ኦፕሬተሮች (ኤኦኤን) ይህንም ሁኔታ መቋቋም አልተቻለም ብሏል። \"በአለም ላይ ያለ የትኛውም አየር መንገድ ቢሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ አይነት አስደንጋጭ አጨማመርን ሊቋቋም አይችልም። ከዚህ ማገገም አይቻልም\" ብሏል። ለጭማሬው ዋነኛ ምክንያት የሆነው ሩሲያ በየካቲት ወር ዩክሬንን መውረሯ ነው። የናይጄሪያን ዘጠኝ የሃገር ውስጥ አየር መንገዶችን የሚወክለው የናይጄሪያ አየር መንገድ ኦፕሬተሮች (ኤኦኤን) አየር መንገዶቹ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ አገልግሎታቸውን እየሰጡ የነበሩት በድጎማ ነበር ብሏል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ በርካታ የበረራዎች መሰረዝ እንዲሁም መዘግየቶች የነበሩ ሲሆን ይህም አብዛኛውን ጊዜ ከአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ እንደሆነ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል። የአውሮፕላን ቲኬቶች ዋጋም በአንዳንድ አየር መንገዶች በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በሶስት እጥፍ ጨምሯል። በናይጄሪያ ያሉ መንገደኞች በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመጣው የሃገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ናይራ ነው ቲኬት የሚገዙት። ነገር ግን ነዳጅ አቅራቢዎች የሚከፈሉት በአሜሪካን ዶላር ነው። ናይጄሪያ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ የነዳጅ አምራች ብትሆንም ከሞላ ጎደል ሁሉንም የአውሮፕላን ነዳጇን ከውጭ ታስገባለች። አኦኤን ለመንግስት፣ ለፓርላማ አባላት፣ ለመንግሥታዊው የነዳጅ ኩባንያ እና ነዳጅ ሻጮችን ለሚወክለው ማኅበር የነዳጁን ዋጋ ዝቅ ለማድረግ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አስረድቻለሁ ብሏል። የዋጋ ጭማሮው በመንገደኞች ላይ ጫና መፍጠር የለበትም ሲል የሚከራከረው ተቋሙ \"ቀድሞውንም ብዙ ችግሮች እያጋጠሟቸው በመሆኑ\" የዋጋው ጫና እነሱ ጫንቃ ላይ ማረፍ የለበትም ብሏል። ስለታቀደው የስራ ማቆም አድማ መንግሥት እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም።", "የዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ በዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ። ከተሞቹ ምርጥ የተባሉት ለኑሮ ባላቸው ምቹነት መሠረት ነው። አውሮፓዊቷ አገር የኦስትሪያ ዋና ከተማ ቪዬና ቀዳሚዋ የዓለማችን ምቹ ከተማ ተብላለች። በተከታይነት ደግሞ የዴንማርክ ኮፐን ሃገን እና የስዊትዘርላንድ ዙሪክ ከተሞች ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የካናዳ ከተማ የሆኑት ካልጋሪ እና ቫንኩቨር ደግሞ በአራተኝነት በቀጣይ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን፤ የስዊትዘላንዷ ጄኔቫ፣ የጀርመኗ ፍራንክፈርት፣ የካናዳዋ ቶሮንቶ፣ የኔዘርላንድስ አምስተርዳም፣ የጃፓን ኦሳካ እና የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ቀዳሚዎቹን አስር ደረጃዎች ለመያዝ በቅተዋል። ይህንን ደረጃ ይፋ ያደረገው ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት እንደሚለው ከሆነ ከተሞች ለኑሮ ያላቸው ምቹነት ቢጨምርም ዓለም አቀፉ አማካይ ግን አሁንም ዝቅተኛ ነው ብሏል። ለኑሮ ምቹነት ከታዩት ጉዳዮች አንዱ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ተጽዕኖ መሆኑን ተጠቁሟል። የዩክሬን ጦርነት ደግሞ ኪዬቭ ከጥናቱ ውጪ እንድትሆን ሲያስገድዳት፣ በሩሲያዎቹ ሞስኮ እና ሴንት ፒተርስበርግ ውጤት ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል። በዚሁ ጦርነት ምክንያት የምሥራቅ አውሮፓ ከተሞች ደረጃም ዝቅ ብሏል። የምዕራብ አውሮፓ እና የካናዳ ከተሞች ደረጃውን በመምራት ቀዳሚ ሆነዋል። ደማስቆ፣ ትሪፖሊ እና ሌጎስ ደግሞ ከማኅበራዊ አለመረጋጋት፣ ሽብር እና ግጭት ጋር ተተያይዞ በደረጃው መጨረሻ ላይ ለመገኘት ተገደዋል። በዘንድሮው ጥናት 33 አዳዲስ ከተሞች ተካተዋል። በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ከተሞች ብዙ መሻሻል አላሳዩም ተብሏል። የሶሪያዋ ደማስቆ በደረጃው የመጨረሻው ስፍራን ይዛለች። ቴህራን፣ ዱዋላ፣ ሃራሬ፣ ዳካ፣ ፖርት ሞርስባይ፣ ካራቺ፣ አልጀርስ፣ ትሪፖሊ፣ ሌጎስ እና ደማስቆ ናቸው የመጨረሻዎቹን አስር ደረጃዎች የያዙት። ለኑሮ ባላቸው ምቹነት መሻሻል ያሳዩ ከተሞችም ታይተተዋል። እነዚህ ከተሞች በአብዛኛው በምዕራብ አውሮፓ የሚገኙ የጀርመን፣ የዩናይትድ ኪንግደም እና የፈረንሳይ ከተሞች ናቸው። ፍራንክፈርት ካለፈው ዓመት 32 ደረጃዎችን በማሻሻል ሰባተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ በቅታለች። ሃምቡርግ ደግሞ ከ31ኛ ወደ 16ኛ ተመንድጋለች። የኒውዚላንድ እና የአውስታራሊያ ከተሞች ደግሞ ደረጃው ላይ ማሽቆልቆል አስመዝግበዋል። በዚህም ዌሊንግተን እና ኦክላንድ 46 እና 33 ደረጃዎችን ለመውረድ ተገደዋል። ድርጅቱ ይህን ደረጃ ለማውጣት የከተሞቹን መረጋጋት፣ የጤና ዘርፍ፣ ባህል እና አካባቢ፣ ትምህርት እና መሠረተ ልማት ከግምት ያስገባል። ይህንን ደረጃ ይፋ ያደረገው ተቋም የዩክሬን ጦርነት እና ኮቪድ በሚቀጥለው ዓመት በሚኖረው የከተሞች ለኑሮ ምቹነት  ደረጃ ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ብለዋል። ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ላለፉት 70 ዓመታት ኢኮኖሚያዊ ትንታኔዎች በመስጠት የሚታወቀው ሲሆን የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ እህት ኩባንያ ነው።", "የትኞቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያላቸውን ስራ አቋረጡ? ሰላሳ ዓመት ወደኋላ! ከሰላሳ ዓመታት በፊት በሶቭየት ኅብረት ኮምዩኒዝም ሲንኮታኮትና የሩሲያ በሮች ለኢንቨስትመንት እና ንግድ ሲከፈቱ ይህንን ዕድል ለመጠቀም የምዕራባውያን ኩባንያዎችን የቀደመ አልነበረም። ያኔ እንደ ኮካ ኮላ እና ማክዶናልድስ ያሉ ታዋቂ ኩባንያዎች በሩሲያ ስራ ሲጀምሮ የሩሲያ አዲሱ ጊዜ መጣ እስከመባል ደርሶ ነበር። የተለያዩ ምርት አቅራቢዎች፣ ማዕድን አውጪዎች፣ የህግ አማካሪዎችና በርካታ ድርጅቶች ቀስ በቀስ በሩሲያ ተስፋፉ። ሩሲያውያንም በሌዊ ጂንስ መዘነጥ እና የምዕራብያውያኑ ቅንጡ ምርቶችን መጠቀም ጀመሩ። ያ በር ከተከፈተ ሰላሳ ዓመታት ተቆጠረ። ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ አዲስ ነገር ተፈጠረ። ሩሲያ ዩክሬንን ወረረች። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የምዕራባውያኑ ክባንያዎች በሩሲያ ያለውን ስራቸውን እያቆረጡ ነው። አፕል፣ ላንድ ሮቨር፣ ኤች ኤንድ ኤም እና ቡርቤሪን ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎች በሩሲያ ያላቸውን የንግድ እንቅስቃሴ ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል። ለመሆኑ የትኞቹ ኩብንያዎች ስራቸውን እያቆሙ ነው? ሌሎቹስ ለምን ዝምታን መረጡ? የነዳጅ ኩባንያዎች ቢፒ የተባለው በነዳጅ ዘርፍ የሚሰራ ኩባንያ በዩክሬን ግጭት እንደተቀቀሰ ነበር በሩሲያ ያለውን ስራ እንዲያቆም ጫና የተደረገበት።ኩባንያው በሩሲያው ግዙፉ የነዳጅ አምራችና አቅራቢ ኩባንያ ሮስኔፍት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ቢኖረውም በቀናት ውስጥ ስራው እንደሚቋረጥ አስታውቋል። ሼል፣ኤክሶንሞቢል እና ኢኩዊኖር የተሰኙት በነዳጅ ዘርፍ የሚሰሩ ኩባንያዎችም ከባለአክሲዮኖች፣ ከመንግሥታት እና ከዜጎች በደረሰባቸው ግፊት በሩስያ ያላቸውን ኢንቨስትመንቶችን እናቆማለን ብለዋል። እነዚያ የነዳጅ አምራች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ቀላል ዋጋ የሚሰጣቸው አይደሉም። የቢፒ የቅርብ ጊዜ ትርፉ በዘርፉ በአምስተኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አድርጎታል። ሼል ከሩሲያው ግዝዙፍ የነዳጅ ተቋም ጋዝፕሮም ጋር ያለውን ግንኙነት ለማቋረጥ እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ሊከስር እንደሚችል ተገምቷል። በሌላ በኩል ቶታል ኢነርጂ በሩሲያ ውስጥ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ እንደማይደግፍ ተናግሯል። ነገር ግን ከተወዳዳሪዎቹ በተጻራሪ ከነባር ኢንቨስትመንቶቹ የመውጣት እቅድ የለውም። የመዝናኛ ዘርፍ የዋርነር ብሮስን አዲሱ 'ብሎክበስተር ዘ ባትማን' በሩሲያ እንደማይታይ ተረጋግጧል። ይህ በሀገሪቱ ለሚገኙ የፊልም አፍቃሪዎች መልካም ዜና አይመስልም። ፊልም አምራች ኩባንያው በዚሁ በሰሞነኛ ጉዳይ ምክንያት በሀገሪቱ ውስጥ አዳዲስ ፊልሞችን ላለመልቀቅ ወስኗል። ኔትፍሊክስ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም \"ቀጣይ ፕሮጀክቶችን\" ማገዱን ያስታወቀ ሲሆን \" ወቅታዊ ሁኔታዎችን ተፅእኖ\" እየገመገመገምኩ ነው ብሏል። ሁሉም ኩባንያዎች ከውሳኔ ላይ የደረሱት ሩሲያ ላይ በተጣሉ ማዕቀቦች ምክንያት አላደረጉም። ይልቅስ ለውሳኔያቸው መነሻ ያደረጉት በዩክሬን ባለው \"ሰብአዊ ቀውስ\" ነው። ነገር ግን ውሳኔው ለሩሲያ የሚያስተላልፈው ሌላ መልእክት ነው። ይህ መሆኑ የሩሲያውያንን የመገለል እንደሚጨምር ተገምቷል። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አፕል በሩሲያ ውስጥ ሁሉንም የምርት ሽያጭ ያቆመ ሲሆን እንደ ፔይ እና አፕል ማፕ ካርታ ያሉ ሌሎች አገልግሎቶችን ላይ ገደብ አድርጓል። በተጨማሪም በሀገሪቱ የሚገኙ የሽያጭ ሱቆቹን ተዘግተዋል። በሞስኮ ላለፉት 24 ዓመታት ለሰራው አፕል ውሳኔው ራሱንም የሚጎዳው እንደሆነ ይታመናል። በሌላ በኩል አንዳንድ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከሃሰት መረጃ ጋር በተያያዘ በሩሲያ የሚገኙ አገልግሎቶች እየተገደበባቸው ነው። ለምሳሌ ፌስቡክ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ የዜና ድርጅቶችን ይዘት ማረጋገጥ እና ላማጋራት ፈቃደኛ አልሆነም ማለቱን ተከትሎ ሩሲያ ፌስቡክን ገድባለች። ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ግዙፉ የስዊድን ፋሽን ኩባንያ ኤች ኤንድ ኤም በሩሲያ ስራውን ያቆመ ግዙፍ ምርት አቅራቢ ድርጅት ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ኩባንያዎች ይህንን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚችል ተዘግቧል። ኤች ኤንድ ኤም በዩክሬን ውስጥ \" አሳዛኝ ሁኔታዎችን\" ጠቅሶ ስራውን ሲያቆም ናይኪን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ብራንዶች በአሁኑ በሩሲያ ላሉ ደንበኞች ምርት ለማቅረብ ዋስትና እንደማይሰጡ ተናግረዋል። በሞስኮ ታዋቂው አደባባይ አቅራቢያ ግዙፍ መሸጫ ያለው 'ቡርቤሪ' የተሰኘው ብራንድ \"በሩሲያ ውስጥ ትዕዛዞችን ላማድረስ አስቸጋሪ ስለሆነ\" ሁሉንም ጭነት አቁሜያለሁ ብሏል። ሩሲያ በ2021 አምስተኛዋ ትልቅ የአውሮፓ የችርቻሮ ምርቶች ገበያ የነበረች ሲሆን 337 ቢሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ነው። አንዳንድ ብራንዶች ደግሞ ከተወሰነ ወደ ንግዱ የመመለስ እድል ካለ በሚል ሁሉንም መንገድ ዝግ አላደረጉም። ለዚያም ይመስላል በርካታ ድርጅቶች ሽያጫቸውን ሙሉ በሙሉ ከማቆም ይልቅ ጉዳዩን \"እያጤንን ነው\" ወይም \"ስራ በማቆም ላይ ነን\" እያሉ የሚኙት የሚል አስተያየትም የቀረበው። ተሽከርካሪ አምራቾች በሩሲያ ወረራ ምክንያት ወደ ሀገሪቱ ተሽከርካሪዎች ካቆሙት አምራቾች መካከል 'ጃጓር ላንድሮቨር'፣ 'ጄኔራል ሞተርስ'፣ 'አስቶን ማርቲን' እና 'ሮልስ ሮይስ' የተባሉት እውቅ ኩባንያዎች ይገኝበታል። በተጫማሪም የግንባታ መሣሪያዎች አምራቹ 'ጄሲቢ' በሩሲያሁሉንም ሥራዎች አቁሟል። አሁን መኪኖችን ወደ ሩሲያ ማጓጓዝ ከባድ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም የዓለም ሁለቱ ትላልቅ የባህር ማጓጓዣ ባለቤት ኩባንያዎች 'ኤም ኤስ ሲ' እና 'ሜሪስክ ' ከምግብ፣ ህክምና ቁሳቁሶች እና የሰብአዊ አቅርቦት በስተቀር ሌላ ምርት ለሩሲያ አንጭንም ብለዋል። እንደ ቮልስዋገን እና ቢኤምደብሊው ያሉ አንዳንድ የመኪና አምራቾች በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ ፋብሪካዎች ላይ ከዩክሬን የሚቀረቡ የመኪና ክፍሎች ባለመኖራቸው ምርታቸውን ለተወሰ ጊዜ ለማቆም ተገደው ነበር። የህግ አማካሪ ድርጅቶች ከኮሚኒዝም መውደም በኋላ በሩሲያ ስራ ከጀመሩ ቀዳሚ ዘርፎች መካከል ትላልቅ አማካሪዎች እና የሕግ ኩባንያዎች ይገኙበታል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ ተከትሎ አብዛኞቹ ዝምታን መርጠው የቆዩ ቢሆንም መሰረቱ ዩኬ የሆነው 'ኬፒኤምጂ' የተሰኘው አማካሪ ኩባንያ ሃላፊ ጆናታን ሆልት ከማዕቀቡ ጋር በሚናበብ መልኩ ከደንበኞቻቸውን ጋር ያለንን ግንኙነት እየገመገምን ነው ብለዋል። ይህ ማለት በዩናይትድ ኪንግደም እና በመላው አለም ያሉ አንዳንድ ግንኙነቶችን ማቋረጥ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል። ሌላው 'ኢዋይ' የተሰኘው አማካሪ ድርጅት ማዕቀቡን እንደሚያከብር የገለጸ ቢሆንም በሩሲያ ከሚገኙ ከማንኛቸውም ደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጣለው ወይም አላቋርጥም ብሎ እርግጡን አልተናገረም። ሌሎች የህግ እና አማካሪ ድርጅቶች የደንበኞቻቸውን ከሩስያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እናጤናለን ብለዋል። የ'ማክኪንሴ' አማካሪ ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ኩባንያው \"ከእንግዲህ በሩሲያ ውስጥ ማንኛውንም የመንግስት አካል እንደማያገለግል\" በማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ ላይ አጋርቷል። ማን ቀረ? ሩሲያ በማዕቀብ ጎርፍ በምትጥለቀለቅበት በዚህ ሰዓት ተጨማሪ እውቅ ብራንዶች በሩሲያ ስራ እንዲቆሙ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው። ሆኖም ለአንዳንድ ኩባንያዎች ይህንን ማድረግ በጣም ከባድ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ጫናው እየበረታ ቢሄድም በሩሲያ ስራ ማቆም ለነዚህ ድርጅቶች አስቸጋሪ ይሆናል። የምዕራባውያን ማዕቀቦች ለመቋቋም የሩስያ መንግሥት የሩስያ ንብረቶችን ሽያጭ አግዷል። ይህ በመሆኑ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በሩሲያ ውስጥ ስራ የጀመሩ ክባንያዎች ንብረት ሽጦ ሀገር ጥሎ የመውጣት መንገዱ ተዝግቶባቸዋል።", "ሕይወት ከመሠረታዊ አቅርቦቶች ውጪ በሆነችው ትግራይ ኑሮውን ሱዳን ካርቱም ያደረገው እና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ግለሰብ በቅርቡ መቀለ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ የዕለታዊ ፍጆታ መግዣ ገንዘብ መላኩን ይናገራል። የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት ወደ ተቆጠረባት መቀለ 40 ሺህ ብር መላክ ማሰቡን ያወቁ እና ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ ግለሰቦች፣ ገንዘቡን ለቤተሰቦቹ ለማድረስ 20 ሺህ 800 ብር እንዲከፍላቸው እንደጠየቁት ለቢቢሲ ገልጿል። ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ውስጥ በሕጋዊነት የሚሰራ አንድም የፋይናንስ ተቋም ባይኖርም፣ መቀለ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ ገንዘቡን እናደርሳለን ላሉት ግለሰቦች የተጠየቀውን ክፍያ በባንክ ሂሳባቸው ገቢ ማድረጉን ገልጿል። ይህ ግለሰብ አክሎም ይህንን እድል ያገኙ ሌሎች ሰዎችም በተመሳሳይ መንገድ መላክ ያሰቡትን ገንዘብ ግማሽ ያህል ክፍያ ለአቀባባዮች እየከፈሉ አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ያስረዳል። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የትግራይ አማፂያን የመቀለ ከተማን እና አብዛኛውን የትግራይ አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ ትግራይ ለአስር ወራት ያህል እቀባ ላይ ትገኛለች። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በጀመረው በዚህ ጦርነት ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶች ለተወሰኑ ወራቶች አገልግሎት መስጠት ጀምረው የነበሩ ቢሆንም፣ የፌደራል መንግሥቱ መቀለን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ ዳግም ሙሉ በሙሉ ቆመዋዋል። 'የተራበች ከተማ' የመቀለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ገብራይ ገዛኸኝ ከመስከረም ወር ጀምሮ 'ራሳችን ለራሳችን' [ባዕልና ንባዕልና]' በተሰኘ ፕሮጀክት ዘወትር ማለዳ ዳቦ እና ሻይ ይቀርብላቸዋል። እኚህ የዕለት እንጀራቸውን ከበጎ አድራጎት ድርጅት የሚያገኙ አዛውንት ቢቢሲ ቃለመጠይቅ ሲያደርግላቸው ችግራቸውን እና ብስጭታቸውን የገለፁት በዘፈን ነበር። \" ድሮ ኪሮስ አለማየሁ . . . ወላጅ ከልጁ ተለያየ፤ በከፋ ረሃብ ሬሳ መሰለ. . . በአፈሙዝ ሰላሙን አጣ. . . ብሎ ነበር። ዛሬም ይህ ተደገመ\" ካሉ በኋላ \"የሚላስ የሚቀመስ አጥተን የልጆቻችን ድምጽ ርቆብን እየኖርን ነው\" ሲሉ በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና ሕይወት እየከፋ መሄዱን ይናገራሉ። ከጦርነቱ በፊት የመቀለ ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ነዋሪ የነበራት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን ከተለያዩ የክልሉ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች በመጡ ተፈናቃዮች ተጨናንቃለች። በክልሉ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በመቶ ሺህ ዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየትምህርት ቤቱ፣ የስብሰባ አዳራሾች፣ በአብያተ ክርስትያናት ውስጥ ተጠልለው በገንዘብ እና በየፍጆታ እቃዎች አቅርቦት እጥረት ለከፋ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ። አቶ ገብራይ \"ረሃቡ ሁሉም ላይ ደርሷል፤ ትልቁም ሆነ ትንሹ ተርቦ ግራ ገብቶት ይገኛል። ገንዘብ፣ መጓጓዣ የለም። በቀን አንዴ በልተን 'ያልፋል' እያልን እንውላለን\" ሲሉ የሚገኙበትን ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዓለም ሰላም ፋውንዴሽን ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ሙሉጌታ ገብረ ሕይወት፣ በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ በሦስት ክፍል ባሳተሙት ጥናት ውስጥ \"ያለውን ተጽዕኖ አልፋችሁ መግባት የምትችሉ ከሆነ ወደ መቀለ እንድትመጡ እንጋብዛችኋለን፤ እንደገባችሁ መጀመሪያ የምታይዋት የተራበች ከተማን ነው\" በማለት ያለውን ችግር ገልፀውታል። ከአምስት ዓመት በፊት ጧሪ እና ተንከባካቢ የሌላቸው አረጋውያን ለማገዝ የተቋቋመው ከራዲዮን የአረጋውያን እርዳታ ድርጅት በአሁኑ ወቅት መቀለ ከተማ ውስጥ ለስደተኛ ሕጻናት እና እናቶች ምግብ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል። በከተማዋ ውስጥ ከቀን ወደ ቀን ለምጽዋት እጃቸውን የሚዘረጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንዳለ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አማኑዔል ገብረ ጻድቃን ይገልጻል። በጦርነቱ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ከተማዋ የመጡ እና በርከት ያሉ ተንከባካቢ ወይንም ደጋፊ የሌላቸው ሕጻናት ጎዳና ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ተናግሯል። \"ሁሉም ነገር ተዘግቶ ምግብ እና መድኃኒት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። ገጠር እና ሌሎች አካባቢዎችን ይቅር እና መቀለን ብቻ ብንመለከት የከፋ ችግር ውስጥ ናት። ሐብታም የምትለው ደሃ ሆኗል፤ ደሃ የነበረው ደግሞ ከድህነት በታች ወርዶ ከባድ ችግር ውስጥ ይገኛል\" ይላል። ከመስከረም 07/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቁርስ ድጋፍ እየሰጠ የሚገኘው ይህ ማኅበር በአሁኑ ጊዜ ከ300 በላይ ተረጂዎች እንዳሉት አማኑኤል ይገልጻል። መጀመሪያ አካባቢ ሕዝቡ እርስ በእርሱ ይተጋገዝ የነበረ ቢሆንም እጁ ላይ የነበረውን እየጨረሰ በመምጣቱ ይህ መደጋገፍ መቀነሱን አክሎ ተናግሯል። \"ከተማዋ ውስጥ ከእንባው ጋር የሚታገል፣ በጎዳናዎች ላይ ብቻውን እያወራ የሚሄድ፣ እጆቹን ዘርግቶ የሚለምን፣ በርካታ ሰው ማየት እየተለመደ ነው\" ሲል አሁን በከተማዋ ያለውን ሕይወት ለቢቢሲ ገልጿል። \"እስካሁን ሕዝቡ ተስፋ አልቆረጠም\" የሚለው አማኑዔል፣ የመቀለ ነዋሪ ካለው ላይ እየሰጣቸው ለከፋ ችግር የተጋለጡትን እንደሚደግፉ ይናገራል። ትግራይ ውስጥ ከተለያዩ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚሰሩና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈሉ ግለሰብ ለቢቢሲ በሰጡት አስተያየት ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም በኋላ ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ \"በጣም የሚሰቀጥጥ\" እንደሆነ በተለይ ደግሞ ከባድ ውጊያ በተደረገባቸው እና \"የኤርትራ ሠራዊት በነበረባቸው ቆላ ተንቤን እምባሰነይቲ፣ ማይ ቅነጣል እና ዕዳጋ ዓርቢን ውስጥ የከፋ ረሃብ አለ\" ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ የተነሳ በርከት ያሉ ሰዎች የቤት እቃ፣ ጌጣጌጥ እና አልባሳትን እንዲሁም ቤታቸውን እስከ መሸጥ የደረሱ መኖራቸውን፣ በተጨማሪም ላለፉት ወራት ደመወዝ ያላገኙ መምህራን፣ ሐኪሞች እና ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች መለመን እንደጀመሩ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። በተለያየ ወቅት ይፋ የሆኑ የዓለም ምግብ ድርጅት ሪፖርቶች ሰሜን ምዕራብ፣ ምሥራቅ እና ማዕከላዊ የትግራይ ዞኖች ከፍ ያለ የምግብ እጥረት የታየባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ ያሳያሉ። ደመወዝ አልባ የመንግሥት ሠራተኞች የትግራይ ክልል እርሻ እና ገጠር ልማት ቢሮ በክልሉ ውስጥ ከዘጠኝ ወራት በላይ ደመወዝ ያልተከፈላቸው \"220ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች ከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ\" ሲል ገልጾ ነበር። ከጥቂት ወራት በፊት ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የመቀለ ዩኒቨርስቲ ሕክምና ፋኩሊቲ መምህር በበኩሉ ከ7000 በላይ የዩኒቨርስቲው ሠራተኞች ላለፈው አንድ ዓመት ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግሮ ነበር። \"ምንም ምንኳ የፌደራል አካል ብንሆንም የፌደራል መንግሥት ግን በጀት ሊልክልን አልቻለም\" ሲልም ቅሬታውን አቅርቦ ነበር። የትግራይ ቴሌቪዝን የክልሉ ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደባልቀውን ጠቅሶ ባሰራጨው ዘገባ \"በቅርብ ጊዜ እርዳታ ካልገባ ከግማሽ በላይ የትግራይ ሕዝብ ያልቃል\" ሲል አስጠንቅቀዋ። \"እቀባው እየበረታ በመሄዱ በመጥፋት አፋፍ ላይ እንገኛለን፤ እቀባው እስከ ሚያዚያ 09/2014 ድረስ ከቀጠለ ግማሽ የትግራይ ሕዝብ ያልቃል፤ ብዙዎች በመድኃኒት እጥረት እየሞቱ ነው። ለቤተሰቦቻቸው መሰረታዊ አቅርቦት ማቅረብ ባለመቻላቸው ደግሞ በርካቶች ራሳቸውን እያጠፉ እንዳሉ ሪፖርቶች እደረሱን ነው\" ሲሉ ተናግረዋል። አንድ ሻማ 30 ብር የፌደራል መንግሥቱ ለስድስት ወራት ክልሉን ባስተዳደረበት ወቅት ትልልቅ ከተሞች ባንክ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት እና መጓጓዣ ተጀምሮ የነበረው አገልግሎት ዳግም የትግራይ አማፂያን መቀለን ሲቆጣጠሩ ሙሉ በሙሉ ተቋጧል። ከዚህ ወዲህ በክልሉ የሚገኙ የፋይናንስ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው የገንዘብ እጥረት አጋጥሟል። የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋም ከእጥፍ በላይ ጭማሪ እንዳሳየም ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሰዎች ይገልጻሉ። ክልሉ ከዋናው የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት መስመር ጋር ስለተቆራረጠ መደበኛ እና ያልተቆራረጠ የመብራት አገልግሎት ማግኘት አለመቻሉንም ጨምረው ተናግረዋል። በርከት ያለ ሰው ሻማ እንደሚጠቀም የሚናገሩት እነዚህ ነዋሪዎች፣ በፊት ሦስት ብር ይገዙት የነበረውን ሻማ አሁን 30 ብር እንደሚከፍሉበት ያስረዳሉ። በክልሉ በርከት ያለ ገንዘብ በጥቂት ባለሃብቶች እና ነጋዴዎች ካዝና እንደሚገኝ፣ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ክልሉ የሚገቡ ሸቀጦች እና የሚደረጉ የገንዘብ ልውውጦች ከእጥፍ በላይ እንደጨመሩ አማኑዔል ይናገራል። ባለፉት ሳምንታት ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በክልሉ ውስጥ የባንክ፣ ነዳጅ እና የመድኃኒት ችግሮች እንዳሉ በማስታወስ አቅርቦቶች ላይ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች አሉ በሚል ወቅሰዋል። አክለውም \"በዚህ ጭንቀት ውስጥ እበለጽጋለሁ ብሎ ማሰብ ወንጀል ነው\" ሲሉ ተናግረዋል። ከክልሉ ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚያመሩ ነዋሪዎች የህወሓት ሊቀመንበር ባለፈው ወር ላይ በሰጡት መግለጫ \"እቀባው ከባድ ነው፤ ችግር ውስጥ ነው ያለነው፤ ከባድ ማኅበራዊ ቀውስ ነው ያለው\" ሲሉ ተናግረው ነበር። \"በየወቅቱ ከአፋር፣ ከአማራ፣ ከምዕራብ ትግራይ የሚመጡ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ነው። . . .\" በማለት በክልሉ ያለው እቀባ እና ግጭቱ ያስከተለውን ጫና ዘርዝረው ነበር። እቀባው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚፈናቀሉ ሰዎችን ቁጥር እንዳይጨምረው ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ትግራይ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሰሩት ግለሰብ ናቸው። ይህ ግለሰብ አሁንም ወጣቶች ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ ከክልሉ እየወጡ ናቸው ብሏል። \". . . በተለይ በደቡብ ትግራይ፣ በራያ ቆቦ እና አፋር አድርገው ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ የሚሄዱ አሉ። በራያ አላማጣ መስመር ብዙ ሰው ከትግራይ እየወጣ ነው። ገንዘብ ከፍለው በደላላ ነው የሚወጡት\" ይላል። የዓለም አቀፍ ተቋማት ምን ይላሉ? በአሁኑ ወቅት ወደ ክልሉ የሚገባው የሰብኣዊ እርዳታ አነስተኛ በመሆኑ እና በቀጠለው ጦርነት ምክንያት ስለሚደናቀፍ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ እንደተፈጠረ የዓለም አገፍ ድርጅቶች ይገልጻሉ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትግራይ ውስጥ ብቻ 4.6 ሚሊዮን ሰዎች፣ ማለትም ከአምስት ሰዎች መካከል አራቱ የምግብ እህል እርዳታ ጠባቂዎች መሆናቸውን ይናገራል። ድርጅቱ አክሎም ከግማሽ በላይ ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉም አስታውቋል። በተጨማሪም የፌደራል መንግሥት እና የህወሓት አማፂያን ወደ ክልሉ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ የሚደርስበትን መንገድ እንዲያመቻቹ ሲጠይቅ ቆይተዋል። ወደ ክልሉ ሰብዓዊ እርዳታ ላለመግባቱ ግን ህወሓት አመራሮች እና የፌደራል መንግሥቱ እርስ በእርስ ይወነጃጀላሉ። ባለፈው ሳምነት መጨረሻ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት እስከ 454ሺህ የሚደርሱ ህጻናት በምግብ እጥረት እንደተጎዱ፣ ከ115 ሺህ ህጻናት ደግሞ በከባድ የምግብ እጥረት እንደተጠቁ አመልክቷል። አክሎም እስከ 120ሺህ የሚደርሱ ነፍሰጡር እና እንዲሁም ከ25 ሺህ በላይ ከእድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በምግብ እጥረት መጎዳታቸውን ገልጿል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጥር ወር መጨረሻ ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ 40 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ \"ለከባድ የምግብ እትረት\" ተጋልጧል ብሏል። ይህ ሪፖርት 83 በመቶ የሚሆኑት የክልሉ ነዋሪዎች ምግብ እንደጨሰና ልመና ላይ ተሰማርተው በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እየተመገቡ እንዳሉ ያመለክታል። በተጨማሪም አሁን በአፋር ክልል በኩል በቀጠው ግጭት የተነሳ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ሚያልፍበት ብቸኛው የሰመራ-አብዓላ መንገድ እንደዘጋው በተደጋጋሚ ተገልጿል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በክልሉ ውስጥ ያላቸው የእርዳታ አቅርቦት እና ነዳጅ ክምችት እንደተሟጠጠ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በመጓጓዣ እና ነዳጅ እጥረት ምክንያት እርዳታቸውን ለመቀነስ እንደተገደዱ አስታውቀዋል። እስከ መጋቢት 08/2022 (እኤአ) ባለው ጊዜ ውስጥም በአጠቃላይ 600 ሊትር ነዳጅ ብቻ እንደቀራቸው ገልፀዋል። የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ በትግራይ ክልል ያለው እቀባ መቀጠሉ እንደሚያሳስባቸው ገልፀው ነበር። አክለውም \". . .የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጨምሮ ሁሉም ወገኖች ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቀርባለሁ\" ብለው ነበር። የዓለም ማኅበረሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ጦርነት በአፋጣኝ እንዲቆም እንዲሁም በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ እና ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲፈቅዱ ቢጠይቁም እስካሁን ድረስ ግን የታየ ተጨባጭ ለውጥ የለም። ክልሉን የሚያስተዳድረው ህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን (ዶ/ር) ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በተዘዋዋሪ ንግግር እየተደረገ ነው ቢሉም ውይይቱ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቶ አልታየም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባዔ ያካሄደው ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት ማንኛውንም የሰላም አማራጭ እንደሚጠቀም ገልጿል። ይህ ግን ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ መገመት እጅጉን ከባድ ነው።", "የእስራኤሏ ቴልአቪቭ በዓለም ላይ በጣም ውድ ከተማ ተብላ ተሰየመች የእስራኤሏ ከተማ ቴልአቪቭ በዓለም ካሉ ውድ ከተሞች የአንደኛነቱን ሰፍራ ያዘች። እየጨመረ ያለው ግሽበትና የአቅርቦት ሰንሰለት ችግር በዓለም አቀፍ ደረጃ ንረትን ከፍ ባደረገው ወቅትም ነው ቴልአቪቭ ለሰው ልጅ መኖሪያነት ውድ ከሆኑ ከተሞች የቁንጮነቱን ስፍራ የያዘችው። የእስራኤሏ ከተማ በአንደኛነት ስፍራ ስትቀመጥ የመጀመሪያ ሲሆን ፓሪስና ሲንጋፖር ተከታታዩን ስፍራ እንደያዙ ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ያደረገው ጥናት ይፋ አድርጓል ። በዚሁ ተቋም መረጃ መሰረት ቴልአቪቭ ባለፈው አመት አምስተኛ ስፍራ ላይ ነበረች። በጦርነት የምትታመሰው የሶሪያ መዲና ደማስቆ በዓለም ላይ በጣም ርካሹን ስፍራ በመያዝ ደረጃዋን አስጠብቃለች። የዳሰሳ ጥናቱ በ173 ከተሞች ለሸቀጦች እና አገልግሎቶች የሚውለውን ወጪ በአሜሪካ መገበያያ ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ አወዳድሯል። ተቋሙ በአውሮፓውያኑ ነሐሴና መስከረም ባሉ ወራት የሰበሰበው መረጃ እንደሚያሳየው በአገራቱ ውስጥ የምንዛሬ ዋጋ በአማካይ በ 3.5 በመቶ የጨመረ ሲሆን ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የተመዘገበ ፈጣን የዋጋ ግሽበት አድርጎታል። የትራንስፖርት አገልግሎት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ የታየበት ዘርፍ ሲሆን ጥናት በተካሄደባቸው ከተሞች የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ በአማካይ 21 በመቶ ጨምሯል። በተቋሙ የዓለም የኑሮ ውድነት ደረጃ ላይ አንደኛ የሆነችው ቴል አቪቭ በዋነኛነት የእስራኤል መገበያያ ገንዘብ ሸከል ከዶላር ጋር ሲነፃፃር ማሽቆልቆል አሳይቷል። የአገር ውስጥ 10 በመቶ የሚሆነው የሸቀጦች ዋጋም በከፍተኛ ሁኔታ መናር ያሳየ ሲሆን ይህም በተለይ በምግቦች ላይ ታይቷል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ቴል አቪቭ በአልኮል እና ትራንስፖርት ዋጋ ከአለም ሁለተኛ ውድ፣ ለግል እንክብካቤ እቃዎች አምስተኛ እናም በመዝናኛ ዘርፉ ስድስተኛ ውድ ከተማ ሆና ተቀምጣለች። የቴል አቪቭ ከንቲባ ሮን ሁልዳይ ከሃሬትዝ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በተቋሙ ስሌት ውስጥ ያልካተተው የቤቶች ዋጋ መናር ከተማዋ ወደማትቋቋመው ደረጃ ላይ እያደረሳት እንደሆነም አስጠንቅቀዋል። \"አገሪቱ በሙሉ በጣም ውድ እየሆነች እንደመጣች ሁሉ ቴል አቪቭ በጣም ውድ ሆናለች\" ብለዋል። \"በእስራኤል ውስጥ መሰረታዊው ችግር ሌላ አማራጭ ሁሉን ያሟላና ማእከል የሆነ ከተማ የለም። በአሜሪካ ኒውዮርክ፣ ቺካጎ፣ ማያሚ እና የመሳሰሉት አሉ። በብሪታንያ ውስጥ ታላቋ ለንደን፣ ማንቸስተር እና ሊቨርፑል አሉ። የኑሮ ውድነቱ በጣም ከባድ ከሆነ አማራጭ ወደሆኑት ሌሎች ከተሞች መሄድ ይችላሉ\" ብለዋል። የዓለም ውድ ከተሞች በደረጃ የዓለም ርካሽ ከተሞች 169 አልማቲ 170 ቱኒስ 171 ታሽከንት 172 ትሪፖሊ 173 ደማስቆ", "ዛምቢያ፡ ድሮኖች ቀረጥ ያልከፈሉ ተሽከርካሪዎችን እያደኑ ነው የዛምቢያ የግብር ባለሥልጣናት ቀረጥ ሳይከፍሉ እቃዎችን የሚያዘዋውሩ ከባድ መኪናዎችን ለመቆጣጠር ድሮኖችን መጠቀም ጀመሩ። ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የዛምቢያ ገቢዎች ባለሥልጣን በድሮኖች በመታገዝ ከዋናው መንገድ በመውጣት ተደብቀው የነበሩ ሰባት ተሽከርካሪዎች መያዛቸውን አስታውቀዋል። • ያለአብራሪ በሚበረው የሰማይ ታክሲ ይጠቀማሉ? • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት \" ድሮኖቹ የፍተሻ ሠራተኞች በማይደርሱባቸው እንዲሁም አደጋ ባለባቸውና ጥንቃቄን በሚጠይቁ ቦታዎች ድረስ በመግባት አሰሳ ያደርጋሉ\" ሲሉ የዛምቢያ ገቢዎች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ቶፕሲይ ሲካሊንዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ሰባት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ፍተሻ ድሮኖቹ 'ካፒሪ ስርነጅ' በተባለ መንገድ በመግባት ማሰስ የጀመሩ ሲሆን ዋናው የተሽከርካሪ መንገድ ባዶ ሆኖ አግኝተውታል፤ ከዚያም ከዋናው መስመር 14 ኪሎሜትር በሚርቅ ጥሻ ውስጥ አመላክተዋል። በዛምቢያ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በአብዛኛው ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ማላዊ፣ ወይም ታንዛኒያ የሚመጡ ናቸው። ኃላፊው ሲካሊንዳ እንዳስታወቁት አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች በጣም በርካታ እቃዎችን ይጭኑና ወደ ፍተሻ ጣቢያው ሲቃረቡ በትንንሽ መኪና ቀንሰው ይጭናሉ ይህም ባለሙያዎቹ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገቡ ምክንያት ሆኗል። የዛምቢያ የገቢዎች መሥሪያ ቤት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገቢውን ለማሳደግ ተስፋ እንዳለው የቀረጥ ባለሥልጣናት ጨምረው ተናግረዋል።", "በኢትዮጵያ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት መመዝገቡ ተገለጸ በኢትዮጵያ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት እየተመዘገበ መሆኑን የአገሪቱ ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ገለጸ። ምክር ቤቱ የዘጠኝ ወራት የምጣኔ ሀብት አፈጻጸምን ገምግሞ ባወጣው በዛሬው ግንቦት 2፣ 2014 ዓ.ም መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብት ከፍተኛ ፈተና እየገጠመው ያለው ከዋጋ ግሽበት አንጻር መሆኑን ጠቁሟል። በዚህም የዋጋ ግሽበቱ በዋናነት በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መመዝገቡን ጠቅሶ፤ ይህም ካለፈው ዓመት የሚያዝያ ወር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ግሽበቱ 36.6 በመቶ መመዝገቡን አስፍሯል። ምክር ቤቱ ጨምሮም ባለፉት ሦስት ዓመታት የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሐዝ ለማውረድ በርካታ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቅሶ ነገር ግን በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት የሚፈለገው ውጤት አልመጣም ብሏል። ለዚህም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጥሬ ዕቃዎች ዋጋ መናር፣ በአገር ውስጥ ያጋጠሙ ግጭቶች እና የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት የፈጠረው ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት እንዲያሻቅብ ምክንያት መሆኑን አመልክቷል። መንግሥት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ የጠቀሰው መግለጫው፤ ከእነዚህም ውስጥ የመንግሥት ወጪን ከአገር ውስጥ ገቢ መሸፈን፣ የግብር ሥርዓቱን ማዘመን እና የተለያዩ ግብርን የተመለከቱ ማሻሻያዎች ማድረግ በቀጣይ ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሏል። ምግብ ነክ የሆኑና መሠረታዊነታቸው የታመነባቸው የፍጆታ ዕቃዎች በፍራንኮ ቫሉታ አሠራር ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱን እንዲሁም፣ የመድኃኒት፣ ነዳጅ፣ ማዳበርያ፣ ዘይት እና ሌሎችም መሠረታዊ ሸቀጦች ግዢ አቅርቦት አቅርቦት እንዲቀላጠፍ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል። ነዳጅን በተመለከተ ደግሞ ሁሉን አካታች ከሆነ የመንግሥት የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ በመውጣት ድጎማ ለሚያስፈልጋቸው አካላት ብቻ እንዲሆን እየተሠራ ነው ተብሏል። ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት በተፈጥሯዊና በሰው ሰራሽ አደጋዎች በተፈጠሩ ጫናዎች በእጅጉ መፈተኑን ገልጾ፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና ድርቅን በዋናነት አንስቷል። ቢሆንም ግን በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት ላይ የተመዘገበው ዕድገትን መሠረት በማድረግ የዓመቱ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ በ6.6 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል። ጨምሮም በአገሪቱ የብድርና ቁጠባ መጠን ላይ ጭማሪ መታየቱን በመጥቀስ፣ የባንኮች አጠቃላይ የቁጠባ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ25 በመቶ ከፍ ብሎ ወደ 1.6 ትሪልዮን ብር መድረሱ ተገልጿል። በዘጠኝ ወራቱ ውስጥ ከውጭ ንግድ 2.95 ቢሊየን ዶላር እንደተገኘና ከዚህ ውስጥ ደግሞ 2.05 ቢሊየን ዶላር የሚሆነው ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ የተገኘ ነው። በተከታይነት ደግሞ የማዕድን ዘርፉ 453 ሚልዮን ዶላር እና አምራች ኢንዱስትሪው 378.5 ሚልዮን ዶላር ገቢ ተገኝቶባቸዋል ተብሏል።", "\"የቱሪስት ማግኔት\" የሆነችው ቬኒስ ከተማን ጎርፍ እያስጨነቃት ነው በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪስት ማግኔት አላት የምትባለው የጣልያኗ ቬኒስ ከተማ በጎርፍ እየተፈተነች ነው። ጎርፉ ቬኒስን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል ተብሏል። በጎርፉ ምክንያት የውሃ መተላለፊያ የሆነው የከተማዋ ዋና አደባባይ ሴንት ማርክ ፣ትምህርት ቤቶችና ንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። የጣልያን መንግስሥትም በዩኔስኮ ድረ ገፅ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል። • ከባድ ዝናብና የጎርፍ አደጋ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት አስከተለ • ጎርፍ ባጠቃቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል ይችላል ተባለ ለውሃ እና ለስነ ህንፃዎቿ ጥበብ ቱሪስቶች የሚተሙላት ቬኒስን እያስጨነቀ ያለው ጎርፍ እርዝመት ማክሰኞ እለት 187 ሴ.ሜ ደርሶ ነበር ተብሏል። ቤታቸው በጎርፍ የተጎዳባቸው የቬኒስ ኗሪዎች እስከ አምስት ሺህ ዩሮ ሲያገኙ ንግድ ቤቶች ደግሞ 20 ሺህ ዩሮ ድረስ ካሳ ይሰጣቸዋል ተብሏል። ከመቶ በላይ ከሚሆኑ ደሴቶች የተሰራችው ቬኒስ በየአመቱ በጎርፍ የምትጠቃ ሲሆን የአሁን እንደ አውሮፓውያኑ በ1923 ተከስቶ ከነበረውና አስከፊ ከተባለው ጎርፍም የባሰ ነው ተብሏል። የጣልያን መንግሥት ለቬኒስ 20 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ያለታካሚዎች ፈቃድ ቀዶ ህክምና ያደረገው የማህጸን ሀኪም ተከሰሰ", "ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የሚወስነውን ቦርድ ልታቋቁም ነው በኢትዮጵያ የዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ ሊቋቋም መሆኑን ቢቢሲ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል። በአሁኑ ወቅት የዝቅተኛ ደመወዝ ወለልን የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ የተረቀቀ ሲሆን በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የበላይ ኃላፊዎች ምክክር ሲደረግበት ቆይቶ ደንቡ ወደሚፀድቅበት ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል። ይህ ቦርድ በኢትዯጵያ እስካሁን ድረስ ሲሰራበት የነበረው በአሰሪና ሠራተኞች ስምምነት የሚወስኑትን የአከፋፈል ሁኔታ በመቀየር የደመወዝ መጠን ላይ የሚወስን መሆኑን አቶ ፍቃዱ ገብሩ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ዳይሬክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሠራተኞች ደመወዛቸው በህግ ከተደነነገገው በታች እንዳይሆን የሚያደርግ ሲሆን፤ የቅጥር ግንኙነት ባለበት ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናል። ደንቡ በአሁኑ ሰዓት በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ከዚያ በኋላም የቦርዱ መቋቋም የሚቀጥል ይሆናል። የዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ምን አይነት ሁኔታዎችን ማካተት ይገባዋል? በምንስ ይወሰን? የሚሉትን ሁኔታዎች የሚወስነው ይህ ቦርድ በአራት አካላት የሚዋቀር ነው። አባላቱም በዋነኝነት ሠራተኞችና አሰሪዎች፣ መንግሥት፣ እንዲሁም የሲቪክ ማኅበራት የሚካተቱበት ይሆናል። የሲቪክ ማኅበራት የሚባሉት የባለሙያዎች ማኅበራት ሲሆኑ ለምሳሌም እንደ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበርና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የመሳሰሉት በዚህ ቦርድ ውስጥ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አቶ ፍቃዱ ይናገራሉ። የደመወዝ ቦርዱ ዝቅተኛውን ወለልን የሚወስነው የባለሙያዎቹ ማኅበራት የሚያቀርቧቸውን መረጃዎችና የተለያዩ ጥናቶችን ግብአት በማድረግ፤ በተለይም በአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅእኖ በጥልቀት በማየት እንዲሁም የአሰሪዎችና ሠራተኞቸን ጥቅሞች ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ አቶ ፍቃዱ ያስረዳሉ። አቶ ፍቃዱ እንደሚሉት ምንም እንኳን የአገሪቱን ሁኔታ በጥልቀት በማየት ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ቢወሰንም በመርህ ደረጃ ግን ዓለም የሚከተላቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች የሚያካትት ይሆናል። እነዚህ መሰረታዊ የሚባሉትም ሠራተኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመኖር የሚያስፈልጋቸው መጠን እንዲሁም በሌላ በኩል ኩባንያዎች፣ ተቋማትና አሰሪዎች የመክፈል አቅም ምን ይመስላል የሚለውን ያጤናል ይላሉ። የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው ደንቡ ወደ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከመላኩ በፊት ከመንግሥት፣ ከሠራተኞችና ከአሰሪዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማካተት የሦስትዮሽ ምክክርና ውይይት ተደርጎበታል ይላሉ። እንደ ሠራተኛ ማኅበር የራሳቸውን ጥናት እያካሄዱ ቢሆንም ሠራተኞችን በመወከል በዋነኝነት አንድ ሠራተኛ በደመወዙ መኖር መቻል አለበት የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ የያዘ ነው ይላሉ። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የአንድን ሠራተኛ የኑሮ ደረጃ የቤት ኪራይ፣ መብራት፣ ውሃ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች ተደምረው ለአንድ ሰው ኑሮ በአማካይ ምን ያህል ይበቃል የሚለው ከግምት ውስጥ መግባት አለበት ይላሉ። በዚህም አንድ ሠራተኛ ራሱን አስተዳድሮ በአማካኝ ሦስት ወይም አራት ልጅ ማሳደግ የሚችልበት መጠን ሊሆን ይገባል ይላሉ። እንደ ምሳሌም የሚያነሱት በኢትዮጵያ ባሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው የሚገኙትን ሠራተኞችን ነው። አብዛኞቹ ከ750 አስከ 1000 ብር በወር ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞችን ጉዳይ \"አሳዛኝና ሊሻሻል የሚገባው\" ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። \"አብዛኛው ሠራተኛ ምሳ በልቶ እራት መድገም የማይችል ነው። አንድ ሺህ ብር በኢትዮጵያ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ገበያ ተወጥቶ ምንም አይገዛም። አንድ ሳምንትም የሚያቆየው አይደለም። ከዚህ አንፃር እነዚህ ነገሮች ይሻሻላሉ ብለን እንጠብቃለን። ቢያንስ ሌላ ነገር ማድረግ ባይችል በልቶ ማደር ይችላል\" ይላሉ። እነዚህንም ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት የሚሉት አቶ ካሳሁን ይህም ሁኔታ በባለሙያዎች ተጠንቶ ግብዓት ይሆናል ይላሉ። \"ሆኖም ጉንጭ አልፋ ክርክር ሳይሆን መሬት ላይ ያለው ሳይንሳዊ ነገርን የተከተለ ነገር መኖር እንዳለበት በኛ በኩል ስንከራከርም፣ ስንወያይም፣ ስንመካከርም እሱን መሰረት አድርጎ ስለሚሆን ይሄንን ጥናት እያካሄድን ነው ያለነው\" ይላሉ። አቶ ፍቃዱም በበኩላቸው የደመወዝ ቦርዱ ሠራተኞች ማግኘት የሚገባቸውን ብቻ ሳይሆን ኩባንያዎች መክፈል የሚችሉበትን ሚዛናዊነቱን በጠበቀ መልኩ የሚደራደሩበት መድረክ እንደሚሆን ያሰረዳሉ። መንግሥትም በነዚህ አካላት ላይ የማደራደር ሚና የሚኖረው ሲሆን በመጨረሻም ሠራተኞችና አሰሪዎች የተስማሙበት እንዲሁም ባለሙያዎች ጥናት ያደረጉበት ሆኖ በሕግነት ይፀድቃል ይላሉ። በተለይም እነዚህ ባለሙያዎች በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ ይህ ቢወሰን ምን ያመጣል የሚለውን ነፃ አስተያየት እንዲሰጡ የማድረጉ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይጠቁማሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ የማይቀጠረው ሰው 80 በመቶ ሲሆን የእርሻ ዘርፉ በአብዛኛው ከኢ-መደበኛ የሚመደብ ሲሆን በቤተሰብ ደረጃ የሚከናወን ነው። ገበያው ላይ የኢ-መደበኛውና መደበኛ ቅጥሩ ላይ ገበያ ያላቸው ተፅእኖና መመጣጠን ሊታይ ይገባዋል ይላሉ። እንደ ምክንያትነትም የሚያቀርቡት \"ደመወዝ ተከፋዮችና ደመወዝ የሌላቸው ግለሰቦች በገበያው ላይ እኩል ተሳትፎ ስላላቸው ነው\" ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ባለሙያዎች በአገሪቷ የወቅቱ ሁኔታ ለምሳሌ ግሽበት፣ የገበያ መዋዠቅ፣ ወረርሽኞችንና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ክለሳ የማድረግ ሥራ ወቅቱን የሚቋቋምበት ሁኔታ ሊሰራ እንደሚገባ የሚጠቁሙት አቶ ፈቃዱ፤ በተለይም አገሪቱ እያለፈችበት ካለችው የዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን መወሰን አስፈላጊ ነው ይላሉ። \"ሠራተኛው የመግዛት አቅሙ ወርዷል። ሠራተኛው አሁን በሚያገኘው ደመወዝ መግዛት አልቻለም። በልቶ ማደር አይችልም\" ብለዋል። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚመለከተው በአገሪቱ አሰሪና ሠራተኛ አዋጅ የሚተዳደሩትን ወይም በቀጣሪና በቅጥር ግንኙነት ያሉትን ነው። በአጠቃላይ መደበኛ የሆነውን የሥራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የግል ዘርፉ ኩባንያዎች፣ ተቋማት እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ይመለከታል። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለሉ የመንግሥት ሠራተኞች (ሲቪል ሠራተኞችን) አያካትትም እንዲሁም ኢ-መደበኛ የሆነውን የሥራ ዘርፍንም እንደማያካትት አቶ ካሳሁን ያስረዳሉ። የመንግሥት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ቦርዱ ለምን እንደማይወስን የሚናገሩት አቶ ፍቃዱ መንግሥት ቀጣሪ ስለሆነ ያው መንግሥት አትራፊ ስላልሆነ መሰረታዊ የሚባሉ ነገሮችን ወስዶ ነው የሚከፍለው ይላሉ።", "ከወለድ ነጻ ባንክ ሥርዓት ለሚሰጠው 'ብድር' እንዴት ትርፍ ያገኛል? የሼሪያ ሕግን መሰረት አድርጎ ሥራውን የሚያከናውነው እስላማዊ ወይም ከወለድ ነጻ የባንክ ሥርዓት ገንዘብ ሰጥቶ፣ አትርፎ መቀበልን ያወግዛል። ይህም በባንኩ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቁርዓንም የተከለከለ በመሆኑ በቀዳሚነት የእስልምና እምነት ተከታዮችን ያገለግላል። ሆኖም የእምነቱ ተከታዮች ላልሆኑ ደንበኞችም ክፍት ነው። በተቃራኒው መደበኛው የባንክ ሥርዓት፣ የቁጠባ ሂሳብ ለሚከፍቱ ወለድ እየከፈለ ገንዘባቸውን ሲያስቀምጥ፣ ለሚያበድረው ገንዘብ ደግሞ ወለድ ይቀበላል። ይህም የመደበኛ ባንኮች ዋነኛ የትርፍ ምንጭ እና መንቀሳቀሻ ነው። ታዲያ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች ለሚያቀርቡት ገንዘብ እንዴት ትርፋማ ይሆናሉ? ከሦስት ወራት በፊት በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረው ሂጅራ ከወለድ ነጻ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሙባረክ ሸሞሎ እንዲሁም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ የሆነው የዘምዘም ባንክ የቢዝነስ ስትራቴጂ እና ኢኖቬሽን ዳይሬክተር ከድር አባስ ከወለድ ነጻ ባንክን ትርፋማ የሚያደርጉት በርካታ አስራሮች እንዳሉ ይጠቅሳሉ። ከወለድ ነጻ ባንክ ምንም እንኳን በእስልምና አስተምህሮት መሰረት ቢንቀሳቀስም የማትረፍ ዓላማ ያለው ነው። የዚህ የባንክ ሥርዓት ሥራዎች በሙሉ በባንኩ እና በደንበኛው መካከል ትርፍ እና ኪሳራን መጋራትን መሰረት የሚያደርግ ነው። \"ደንበኞች ወደ እኛ ሲመጡ ትርፍንም ኪሳራንም ለመጋራት ወስነው ይመጣሉ ማለት ነው\" ሲል የሚያስረዳው ሙባረክ \"ደንበኞች የሚያስቀምጡት ገንዘብ ባንኩ የተፈቀዱ ቢዝነሶች ላይ ፋይናንስ አድርጎ ያ ፋይናንስ ትርፍ ካመጣ ከደንበኛው ጋር ትርፍ ይጋራል፤ ኪሳራ ይዞ ከመጣም ኪሳራን ነው የሚጋራው\" በማለት ያብራራል። ይህም በተለያየ የባንኩ ሥርዓቶች የሚተገበር ሲሆን ደንበኞች ትርፍም ኪሳራም የማይጋሩበት እና ገንዘባቸውን በአደራ የሚያስቀምጡበትም አሰራር አለ። የባንክ ሥርዓቱ አሰራር ደንበኞች የሚፈልጉትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ገዝቶ ከማቅረብ፣ ከባለሀብቶች ጋር በጋራ ኢንቨስት እስከማድረግ የሚዘልቅ ነው። የሽያጭ ውል ፋይናንሲንግ ከወለድ ነጻ ባንክ 'የሽይጭ ውል ፋይናንሲንግ' በተሰኘው የብድር ሥርዓቱ፣ ባንኩ ደንበኛው ወይም 'ተበዳሪ' የሚፈልጋቸውን ንብረቶች ገዝቶ ያቀርባል። የባንኮቹ አመራሮች በሸሪአ ሕግ ወለድ የተከለከለ ቢሆንም ነግዶ ማትረፍ የተፈቀደ ስለመሆኑ ጠቅሰው፣ ባንኩ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ወይም ቀደም ብሎ ከገዛቸው ንብረቶች ደንበኞች በዱቤ የሚወስዱበት አሰራር መሆኑን ጠቅሰዋል። የተገዛውን ንብረት ባንኩ ለደንበኛው ሲያቀርብ ከተገዛበት ዋጋ ጨምሮ እንደማንኛውም ንግድ የሚያተርፍ ይሆናል። ይህም በተለያየ መንገድ ይቀርባል፤ ለአብነት 'ሙራብሃ' የተሰኘው አገልግሎት ደንበኛው የሚፈልገውን አገልግሎት ወይም ምርት ባንኩ የገዛበትን ዋጋ እና የሚያተርፈውን በግልጽ አስታውቆ የሚያቀርብበት ሥርዓት ነው። የተገዛው ንብረት ወይም አገልግሎት በባንኩ ስም ሆኖ፣ ትርፉም ምርቱ ወይም አገልግሎቱ በጊዜ ውስጥ ሊኖረው በሚችል ዋጋ የሚሰላ ይሆናል። ይህ አገልግሎት በእስላማዊ ባንክ ከ50 እስከ 60 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ይህም እንደ ተሽከርካሪ እና ቤት ያሉ ንብረቶች የሚጠቃለሉበት ነው። ታዲያ እንደ ሙባረክ ገለጻ \"ባንኮች እንደ ነጋዴ ገበያ ወጥተው በሽያጭ ያስተላልፋሉ ማለት ነው።\" በሌላ በኩል 'ባይሰለም' የሚባለው አገልግሎት ደግሞ ለግብርና ሥራዎች የሚቀርብ ሲሆን ከወለድ ነጻ ባንኩ ለአርሶ አደሮች ገንዘብ በማቅረብ ትርፍ ወይም ኪሳራ የሚጋራበት ነው። በሌሎች አገራት ለማኑፋክቸሪንግ ሥራዎች ፋይናንስ የሚቀርበው ከዚሁ የባንክ አገልግሎት ነው። 'ኢስቲስና' የተሰኘው አገልግሎት ደግሞ በጊዜ ሂደት ለሚሻሻል ቢዝነስ የሚቀርብ ፋይናንስ ሲሆን፣ እንደ ህንጻ ግንባታ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። ለአብነት ህንጻ መገንባት የሚፈልግ ሰው ከወለድ ነጻ ባንክ ገንዘብ ወይም 'ብድር' በሚፈልግበት ወቅት የህንጻውን ሙሉ እቅድ ያቀርብና ባንኩ ካመነበት ጨረታ አውጥቶ ያስገነባለታል። ከግንባታው በኋላም ባንኩ አትርፎ መልሶ ለደንበኛው የሚሸጥበት ነው። የሽርክና ፋይናንስ ይህ ሥርዓት ባንኩ ደንበኞች ላሏቸው የቢዝነስ ሃሳቦች ገንዘብ በማቅረብ ወደ ተግባር የሚቀይርበት ሲሆን፣ ባንኩ በድርሻ ወይም በውል ትርፍ ወይም ኪሳራ የሚጋራበት ነው። በዚህ አሰራር ኢንቨስትመንቶቹ ላይ የጋራ አመራር ሊሰጡም ይችላሉ። በዚህ ውስጥም 'ሙዳራባህ' ተጠቃሽ ነው። ይህ አገልግሎት ባንኩ ለደንበኛው ፋይናንስ የሚያቀርብበት ሲሆን ትርፍ ካለ በስምምነታቸው መሰረት በጋራ ይካፈላሉ። ኪሳራ ካለ ግን የባንኩ ብቻ ይሆናል። 'ሙሻራካህ' ደግሞ ከወለድ ነጻ የባንክ ፋይናንስ ዓይነት ሲሆን ደንበኛው ያለውን ካፒታል በማወጣት ከባንኩ ጋር ኢንቨስት የሚያደርጉበት ሲሆን፤ በጊዜ ሂደት ባንኩ ከንግድ ሥራው የሚያገኘው የትርፍ ድርሻ ሊቀር የሚችልበት ነው። በተጨማሪም እስላማዊ የባንክ ሥርዓት የተለያዩ አግልግሎቶች ወይም ምርቶችን በማከራየት፣ ዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በመሰማራት ወይም በሌሎች መንገዶች ትርፍ ሊያሰባስብም የሚችልበት መንገድ አለ። በእነዚህ ሂደቶች ሁሉ በዚህ ሥርዓት ስር ያሉ ባንኮች ገንዘብ ተቀበለው ያለምንም አገልግሎት ወይም ሽያጭ 'ገንዘብ ላይ ገንዘብ ጨምረው' እንዲሁም ከቅዱስ ቁርአን ጋር በማይጻረር መልኩ አለመስራታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። ከወለድ ነጻ ባንክ 'ብድር' መመለስ ያልቻሉ ሰዎችን አይቀጣም። ፋይናንስ የቀረበለት ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ከባንኮቹ የወሰደውን ገንዘብ መመለስ ባይችል ወይም በሚጠበቅበት ጊዜ ባይመልስ \"ቅጣት የሚባል መርህ የሼሪአ ሕጉ አያውቅም\" በማለት ሙባረክ ይገልጻል። \"መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው። ሰዎች ላበደሯቸው ብድር አታስጨንቁ የሚል ነገር አለ። ሳታስጨንቋቸው በተጨማሪ ደግሞ ከቻላችሁ ተዉላቸው የሚል አለ። ስለዚህ ያንን [ቅጣቱን] አያውቅም\" ብሏል። ሆኖም 'ለፍትሃዊነት' በሚል ዓለም አቀፍ የእስልምና ተቋማት የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ድርጅት ገንዘቡን በወሰደው ሰው ፍላጎት የሚፈጸም ወይም ደንበኛው ራሱን የሚቀጣበት የ3 በመቶ ቅጣት ደንግጓል። የተገኘው የቅጣት ገንዘብ ደግሞ የባንኩ ገቢ ሳይሆን ለእርዳታ ተቋማት የሚበረከት መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ከወለድ ነጻ ባንክ በኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዚህ መልኩ የሚተገበረው ከወለድ ነጻ የባንክ ሥርዓት በመደበኛ ባንኮች ውስጥ በመስኮት፤ በመደበኛ ባንኮች በቅርንጫፍ ደረጃ፤ የመደበኛ ባንኮች እህት ኩባንያ በመሆን ወይም እንደ ዘምዘም እና ሂጅራ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ሆኖ ሊቋቋም የሚችልበት አማራጮች አሉት። በኢትዮጵያ ይህ አገልግሎት በመስኮት ደረጃ የተጀመረው ከስምንት ዓመታት በፊት ሲሆን፣ ሙሉ በመሉ ከወለድ ነጻ የሆነ ባንክ ሥራ የጀመረው ግን ከወራት በፊት ነው። በኢትዮጵያ መሰል አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሳይኖር መቆየቱ ከ13 ዓመታት በፊት የተጠነሰሰው እና በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከወለድ ነጻ ባንክ የሆነው ዘምዘም፣ በብዙ ውጣ ውረድ እንዲያልፍ አስገድዷል። ይህም የፋይናንስ አካታችነት ላይ ጥያቄ ያስነሳ ነበር። ይሁን እንጂ በ2011 ዓ. ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ የተለያዩ ከወለድ ነጻ ባንኮች አክሲዮን መሸጥ የጀመሩ ሲሆን ሁለቱ ባንኮች ደግሞ ከወራት በፊት ሥራ ጀምረዋል። ዘምዝዘም ባንክ ሥራ በጀመረባቸው አራት ወራት 30 ሺህ ደንበኞች እና 15 ቅርንጫፎች እንዳፈራ ከድር ገልጿል። ሂጀራ ባንክ ደግሞ በሦስት ወራት 14 ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን ከ22 ሺህ በላይ ደንበኞች እንዳገኘ ሙባረክ ይናገራል። ነገር ግን ከወለድ ነጻ ባንኮች፣ አገልግሎቶችን በተመቻቸ ሁኔታ ለመተግበር የማያስችሏቸው ሁኔታዎች አሁንም መኖራቸውን የሚጠቅሰው ከድር፣ \"ያለው የሕግ ማዕቀፍ ከመደበኛው ጋር የተቆራኘ ነው።...ከመንግሥት እሱን ከማስተካከል አኳያ ቀና ነገሮች አሉ\" ብሏል። ሙባረክ በበኩሉ በብሔራዊ ባንክ ደረጃ ከወለድ ነጻ ባንኮችን የሚከታተል እና ሸሪአን መሰረት ያደረገ ተቆጣጣሪ አካል ሊኖር ይገባል ብሏል።", "የሊባኖስ ባንኮች ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቆሙ የሊባኖስ ባንኮች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ጥበቃ አላደረጉልንም በሚል ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የአገሪቱ ባንኮች ማኅበር ገለጸ። ደንበኞች ባለፈው ሳምንት እንዳይንቀሳቀስ የተደረገውን የቁጠባ ሂሳባቸውን ለማግኘት በኃይል ታግዘው ገንዘባቸውን የመውሰድ ድርጊቶች መበራከታቸውን ተከትሎ ነው የሊባኖስ ባንኮች ማኅበር አገልግሎት መቆሙን ያስታወቀው። በአገሪቱ የሚገኙ ባንኮች ውስጥ የሚያገለግሉ ሠራተኞች መፍትሄ ማግኘት ያልቻሉ የደኅንነት ስጋት ገጥሟቸዋል ሲልም ማኅበሩ ገልጿል። ባሳለፍነው ሳምንት አንዲት ግለሰብ የልጆች መጫወቻ ሽጉጥ በመያዝ ለቤተሰቧ መድኃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ከባንኩ ለመውሰድ በባኩ ውስጥ ሰዎችን በማገቷ መነጋገሪያ ሆና ነበር። በሳምንቱ መጨረሻ አርብ ቀን ብቻ ቢያንስ አምስት ሰዎች ገንዘባቸውን በኃይል ከባንክ ለመውሰድ ጥረት ያደረጉበት ተመሳሳይ ክስተቶች ሪፖርት ተደርገው ነበር። በአሁኑ ጊዜ ሊባኖስ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝቧ የምግብ እና የመድኃኒት አቅርቦት ለማግኘት የሚያስችለው ገቢ የለውም። ደንበኞች በባንኮች ውስጥ ያላቸውን ገንዘብ በኃይል በመጠቀም የመውሰድ እምጃ በሕበረተሰቡ ዘንድ ድጋፍ አግኝቷል። ከዚህ በፊት ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ የሌላቸው ሰዎች የባንክ ሂሳባቸውን በጉልበት ለማንቀሳቀስ መጣራቸው በሕብረተሰቡ ዘንድ በተስፋ መቁረጥ ተገፋፍቶ የሚፈጸም ተደርጎ ይታያል። የሊባኖስ የመገበያያ ገንዘብ እኤአ ከ2019 ጀምሮ ዋጋው እያሽቆቆለ፣ ብሎም በአገሪቱ ያለው የዋጋ ንረት ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን ተከትሎ ባንኮች ደንበኞቻቸው የሚያወጡትን ገንዘብ ገድበዋል።", "በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለው ገደብ ለምን አስፈለገ? በኢትዮጵያ ከባንኮችና ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በሚወጣ የጥሬ ገንዘብ ላይ የተጣለው እገዳ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። ብሔራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ ተቋማትና ግለሰቦች ከባንኮች በቀንና በወር ውስጥ በሚያወጡት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥሏል። በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር እንዲሁም በወር እስከ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ከባንኮች ማውጣት የሚችል ሲሆን፤ ተቋማት ደግሞ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር እና በወር እስከ 2.5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶክተር) ይህንን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው \"የገንዘብ ዝውውርን ሥርዓት በማስያዝ ወንጀልንና የግብር ስወራን ለመከላከል ይረዳል\" በሚል ነው ብለዋል። ይህን የብሔራዊ ባንክ እርምጃን በተመለከተ የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች አሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይ አንድ አገር ላይ የኢኮኖሚ ፖሊስ ሲወጣ፣ ምጣኔ ሃብቱ እንዲረጋጋ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚው ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ሲፈለግ ሁለት ዓይነት ኃይለ ፖሊሲዎችን እንደሚከተሉ ያስረዳሉ። በጀት ምን መምሰል አለበት፣ ሰዎችና የንግድ ተቋማቶች መክፈል ያለባቸው ግብር ምን ይመስላል ተብሎ የሚወሰንበትን እና የገቢዎች ሚኒስቴርና የገንዘብ ሚኒስቴር የሚቆጣጠሩት ፊሲካል ፖሊሲ አንዱ ሲሆን፣ ሞኒተሪ ፖሊሲ ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የሚቆጠጣረው መሆኑን ያስረዳሉ። ብሔራዊ ባንክ ሲቋቋም ጀምሮ የአገሪቱ የገንዘብ አቅርቦት ምን መምሰል አለበት? ምን ያህል ገንዘብ ታትሞ በገበያ ውስጥ መሰራጨት አለባቸው? የሚለውን የመቆጣጠር የሥራ ድርሻው እንዳለው ያብራራሉ። በተጨማሪ ደግሞ በባንኮች በኩል ያለውን የወለድ መጠን፣ የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዋሲሁን፣ ብሔራዊ ባንክ በትናንትናው ዕለት ካሉት ሁለት ትልልቅ ስልጣኖች መካከል በመጠቀም የገንዘብ አቅርቦት በገበያው ምን መምሰል እንዳለበት ወስኗል ሲሉ ያስረዳሉ። እንደ ምጣኔ ሃብቱ ባለሙያ አስተያየት ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የገንዘብ መጠን ላለፉት ብዙ ዓመታት በእርግጠኝነት ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። \"በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከ700 እስከ 800 ቢሊየን ብር ድረስ በገበያው መሰራጨቱ ይታወቃል የሚሉት የምጣኔ ሃብቱ ባለሙያ እርሱንም ቢሆን በእርግጠኝነት ለማወቅ አስቸጋሪ ነው\" ሲሉ ያለውን ፈተና ያብራራሉ። ስለዚህ እዚህ ገበያ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ማወቅ እንደሚያስፈልግ በማንሳት \"የገንዘብ መጠኑ የማይታወቅ ከሆነ የተለያዩ ሕጋዊ ያልሆኑ የንግድ ሥርዓቶች ሊበራከቱ ስለሚችሉ ብሔራዊ ባንክ ያንን ለማወቅ አስቦ እንደወሰነው እገምታለሁ\" ይላሉ። ሌላው መንግሥት ባይጠቅሰውም የገንዘብ እጥረት የአገሪቱ አንዱ ችግር መሆኑን ይጠቅሳሉ። \"ጥሬ ገንዘብ አቅርቦት በጣም እያነሰ ነው። የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎና በሌሎችም ምክንያቶች ሰዎች ያላቸውን ገንዘብ በእጃቸው መያዝ ይፈልጋሉ\" የሚሉት ባለሙያው ለመንግሥት የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል ብሎ መናገር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ከባድ መሆኑን ይናገራሉ። \"ወረርሽኙን ተከትሎ ሰዎች ለመድኃኒት፣ ለሕክምናና ለምግብ የሚሆኑ ወጪዎችን ብቻ ነው እያወጡ የሚገኙት\" የሚሉት ባለሙያው በተጨማሪም ነገ በሚሆነው ነገር ላይ ተስፈኛ መሆን አለመቻል ገንዘብን በባንክ ለማስቀመጥ ፍላጎት እንደሚያሳጣ ይጠቅሳሉ። \"አሁን በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ ከባንክ ቤቶች እየወጣ መሆኑ ግልጽ ነው\" በማለትም ከበሽታው በፊትም ቢሆን የልማት ባንክ ያልተመለሱ የተበላሹ ብድሮች እንዳሉት ሲናገር በርካታ ባለሃብቶች ብድር ወስደው መክፈል አልቻሉም ማለት እንደሆነም ያስረዳሉ። ኢንቨስትመንት ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ብድራቸውን መክፈል እንዲችሉ ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ሰዎች ያስቀመጡት ገንዘብ ባንክ ቤት ውስጥ የለም ማለት መሆኑን በማስረዳት ለገንዘብ እጥረቱ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ያብራራሉ። \"መንግሥት ግን ይህንን ውሳኔ የወሰንኩት እጥረት ስለገጠመኝ ነው ብሎ ሊል አይችልም\" በማለትም የገንዘብ እጥረቱ እየገጠመ ነው ወደፊት ደግሞ በፍጥነት ሊገጥም መቻሉ ገሃድ መሆኑን ያስረዳሉ። \"ምክንያቱም ወደ በሽታው [ኮሮናቫይረስ] ገና እየገባንበት ነው ይላሉ። ወረርሽኙ እየተስፋፋ ሲመጣ፣ የሰዎች እንቅስቃሴ ሲገደብ፣ አሁን ገበያ ላይ ያሉት ነጋዴዎች አቅማቸው ሲዳከም፣ ገንዘባቸውን በእጃቸው ይዘው መጠቀም ሲመርጡና ለአስፈላጊ ነገሮች ብቻ ሲያወጡ፣ የባንክ ቤት ሰልፍ ጠልተው እያወጡ ሲያስቀምጡ ወደፊትም ቢሆን እጥረት መፈጠሩ አይቀርም ይላሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይ። \"ዜጎች በመጪው ጊዜ ላይ እርግጠኛ መሆን የማይችሉ ከሆነ ብራቸውን ስለሚይዙ የመቆጠብ አቅማቸው ደካማ ስለሚሆን የገንዘብ አቅርቦት እያነሰ ስለመጣ እርሱንም አስታኮ የወሰነው ይመስለኛል።\" በተጨማሪነት ግን ኢንቨስትመንት እንዲያድግ ቁጠባን ለማበረታታት አስቦ መንግሥት የወሰነው እንደሚመስላቸው ባሙያው ጠቅሰው \"ገንዘብ ከባንክና ከፋይናንስ ሥርዓት ውጪ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ አይፈቀድም።\" ብዙ አገራቶች ይህንን ነገር እያስቀሩ መምጣታቸውን ገልጸው \"ስለዚህ ብሔራዊ ባንክም የሆነ ቦታ ላይ ለጥሬ ገንዘብ ዝውውሮች ሥርዓት ማበጀት ነበረበት\" ብለዋል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ሲሉ እርምጃውን አጥብቀው ይተቻሉ። \"ይሄ ይዞት የሚመጣው ነገር በጣም አደገኛ ነው። ከዚህ በኋላ ባለሃብቱ የሚከፈለውን ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ይቀበልና ወስዶ ቤቱ ያስቀምጣል። ይህ ደግሞ ገንዘብ ወደ ባንክ ገብቶ እንቅስቃሴ እንዳይፈጠር ያደርጋል። ይሄ እርምጃ ከሚያመጣው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል\" ይላሉ። ግብር ስወራን በተመለከተ ጉቱ (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ የሚጠበቅባቸውን ግብር ላለመክፈል 'ኪሳራ ደርሶብኛል' እያሉ ሪፖርት በማድረግ ግብር የሚያሸሹ በርካታ ነጋዴዎች መኖራቸው አይካድም ይላሉ። \"ነገር ግን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ሰዎችን አሳደን የሚጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ማድረግ እንችላለን ወይ? ይህ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል ወይ?\" ሲሉ ይጠይቃሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ ይህ ዓይነት የመንግሥት ውሳኔ፤ \"ከባንክ ውጪ ሊደረግ ወደ የሚችለው ልውውጥ ስለሚወስድ ምጣኔ ሃብቱን በአፍጢሙ ሊደፋ ይችላል\" ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ጉቱ (ዶ/ር) ይህ የመንግሥት ውሳኔ አገሪቱ ኮሮናቫይረስ ከሚያስከትለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ በኋላ ለማንሰራራት በምታደርገው ጥርት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ያነሳሉ። \"ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በፊት የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የሚያበድሩት በቂ ገንዘብ አልነበራቸውም። ብሔራዊ ባንክ ራሱ ከተቀማጭ ገንዘቡ ማሻሻያ እያደረገ ለባንኮች ገንዘብ የሚለቅበት አጋጣሚዎች ነበሩ\" ይላሉ ባለሙያው። አክለውም ከወረርሽኙ በኋላ ደግሞ እንደሚስተዋለው የዓለም ምጣኔ ሃብት እጅጉን ተጎድቷል፤ በኢትዮጵያም የፋይናንስ ተቋማት ለመደገፍ መንግሥት በብሔራዊ ባንክ በኩል 15 ቢሊዮን ብር እንዲቀርብ ማድረጉን አስታውሰዋል። \"መንግሥት ይህን ያደረገው አበዳሪዎች ለተበዳሪዎች ጊዜ እንዲያራዝሙ፣ የወለድ መጠን እንዲቀንስ፣ ተጨማሪ ብድር የሚፈልጉ ብድር እንዲያገኙ፣ አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስፋፉ ነው። \"ለዚህ ደግሞ ጥሩ የገንዘብ አቅርቦ ወደ ኢኮኖሚው መፍሰስ አለበት እያልን አያሰብን ባለንበት ሰዓት ላይ የገንዘብ ዝውውር ላይ ገደብ መጣል ከተባለው ነገር ጋር የሚቃረን የምጣኔ ሃብት እርምጃ ነው የሚሆነው\" ይላሉ። መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከተገደደብ ምክንያት አንዱ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት በማሰብ ነው። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱም (ዶ/ር) አሁን ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ወጪ በሚደረግ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ መጣል የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ጠቀሜታ አለው በማለት ይስማማሉ። ይህንንም ሲያስረዱ \"ከወረርሽኙ በፊት የሰው እንቅስቃሴ እንደልብ ነበር። ሰዎች ገንዘብ በማዳበሪያ ጭነው ሃርጌሳ ይወስዳሉ፤ ወደ መተማ ይሄዳሉ። አሁን ግን በቫይረሱ ምክንያት ሰዎች እንደፈለጉት መንቀሳቀስ አይችሉም። ስለዚህ ባንክ ለመጠቀም ይገደዳሉ\" ይላሉ። ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ \"አንድ ሰው ወደ ባንክ ገቢ የተደረገውን ገንዘብ ላውጣ ቢል፤ ወጪ የተጠየቀው ቅርንጫፋ ብዙ ገንዘብ ስለተጠየቀ ሥራ መስራት አቆመ ማለት። ግለሰቡም ይህን ያክል ገንዘብ ከየት አመጣህ ተብሎ ይጠየቃል። በዚህ መልኩ መቆጣጠር ይችላል\" በማለት እርምጃው ሊኖረው የሚችለውን ጠቀሜታ ያስረዳሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይበበኩላቸው የመንግሥት ውሳኔ መጥፎ አለመሆኑን ያስረዳሉ። \"የገንዘብ አቅርቦቱን በጣም በጣም መቆጣጠር አለበት። ምክንያቱም የዋጋ ንረት ከሚቀጣጠልባቸው ነገሮች አንዱ ከፍተኛ ብር በገበያው ሲሰራጭ ነው። ሐሰተኛውን በር ከትክክለኛው መለየትም በጣም አስቸጋሪ ነው\" በማለት መንግሥት እነዚህን ለመቆጣጠር አስቦ እንደሆነ ያምናሉ። \"ውሳኔው ጥሬ ገንዘብ የመያዝ እንጂ ሰዎች ገንዘብ ማንቀሳቀስ የለባቸውም\" የሚል አይደለም የሚሉት ባለሙያው፣ ከጥሬ ገንዘብ ውጪ ዲጂታላይዝ በሆነ ገንዘብ ግብይት ማከናወን የሚቻልበት ሥርዓት ካለ በሞባይል መገበያየት፣ በኤቲኤም፣ በቼክ፣ በፖስ ማሽን መገበያየት የሚችሉ ከሆነ ግብይቶች እንዲቆሙ አልተደረገም ይላሉ። ስለዚህም የመሸመት መጠኑን የሚገደብ ምክንያት አለ ብለው እንደማያስቡ የሚናገሩት አቶ ዋሲሁን፤ ከፍተኛ ገንዘብ ገበያ ላይ ተረጭቶ ገንዘቦቹ ምርትና ምርታማነት ላይ የማያርፉ፣ ፍላጎትን የሚያሳድጉ ከሆነ የዋጋ ግሽበትን የማቀጣጠላቸው እድል በጣም ከፍተኛ መሆኑን ያሰምሩበታል።", "ኢትዮጵያ ግሽበትን ለመግታት የባንኮች የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን በእጥፍ እንዲያድግ ወሰነች በከፍተኛ ሁኔታ እያንሰራራ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመግታት ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ እንዲያስቀምጡት የሚጠበቅባቸውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ወደ አስር በመቶ ከፍ እንዲያደርጉት ተወስኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው ከዚህ ቀደም 5 በመቶ የነበረውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል የወሰነው በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን ለመቀነስ ቁጥብ የገንዘብ ፖሊስ ለማድረግ ከመወሰኑ ጋር ተያይዞ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ የወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑም ተገልጿል። ይህ የባንኮች መጠባበቂያና የብሔራዊ ባንክ የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ያለው ግሸበት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን በሐምሌ ወር የነበረው መጠን 26.4 መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አስነብቧል። በዓመቱ ውስጥ የነበረው 20 በመቶ የሆነው የግሽበት መጠን በቅርቡ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን መንግሥት ይህንን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶችን፣ ማሻሻያዎችንና ፖሊሲዎችን እያወጣ ይገኛል። በቅርቡም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ህንፃዎች ያሉ ንብረቶችን እንደ መያዣነት የሚጠቀሙ ባንኮች ሁሉንም ብድሮች ለጊዜው እንዲታገድ የሚወስን አዲስ መመሪያ ወጥቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪንም በተመለከተ ባንኮች ሲጠቀሙበት የነበረው አሰራር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል። በዚህም ማሻሻያ መሰረት ባንኮች ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሃዋላና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ውስጥ 50 በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ አለባቸው ተብሏል። ከዚህ ቀደም ባንኮች ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ ከዲያስፖራ ሂሳብና ከሌሎች ምንጮች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ ሰላሳ በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ የሚያዘውን መመሪያም ተሻሽሏል። ይህ አሰራርም ከዚህ ቀደም በባንኮች በተደጋጋሚ ከሚቀርበው ወቀሳ መካከል ከውጭ ኢንቨስትመንት፣ ከዲያስፖራ ሂሳብና ከውጭ ብድር የሚገኝ የውጭ ምንዛሪ ተቀንሶ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረግ የለበትም ለሚለውም ጥያቄ መልስ እንደሆነም ተገልጿል። ከባንኮች በተጨማሪ ደንበኞችን በተመለከተ መያዝ የሚችሉትን የውጭ ምንዛሪ መጠንም ማሻሻያ ተደርጓል። በባንኮች የውጭ ምንዛሬ ያስገኙ ደንበኞች በውጭ ምንዛሪ ሂሳባቸው ያለ ጊዜ ገደብ መያዝ የሚችሉት የውጭ ምንዛሬ መጠን ከ31.5 በመቶ ወደ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። የገንዘብ ተቋማትና ደንበኞቻቸው ሊኖራቸው ስለሚገባው ግንኙነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። አገሪቱ እየሰራች ያለችው ወጥ ብሔራዊ መታወቂያ እስኪሰጥ ድረስ የገንዘብ ተቋማት ለደንበኞቻቸው የተለየ የደንበኛ መለያ ቁጥር መስጠት አለባቸው ተብሏል። ደንበኞች ወይም ድርጅቶች ከአንድ በላይ አካውንት ቢኖራቸውም ይህ የመለያ ቁጥር ተግባራዊ ይሆናል። ደንበኞች ማንኛውንም የባንክ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ወቅት ገንዘብ ማውጣት፣ ማስቀመጥም ሆነ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ማዘዋወርና ሌሎች ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶችን በተመለከተ የገንዘብ ተቋማት (ባንኮች) ተመሳሳይ ቅፅ (ፎርም) መጠቀም አለባቸው። በዚህም አሰራር መሰረት በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ማንኛውም ባንኮችም ሆነ የገንዘብ ተቋማት ለየትኛውም የባንክ አገልግሎቶች የሚጠቀሟቸው ወጥና ተመሳሳይ የሆኑ ቅፆችን እንደሆነ መመሪያው አስቀምጧል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ደንበኞች ትክክለኛ ያልሆነ ወይም አጠራጣሪ መረጃ የሚሰጡ ወይንም መመሪያዎችን የማያከብሩ ከሆነ የገንዘብ ተቋማቱ አገልግሎትን የመከልከል ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ ባንኮቹ የእነዚህን ደንበኞች መረጃ ለብሔራዊ ባንክና ለፋይናንስ መረጃ ደኅንነት ማዕከል ማስተላለፍ እንዳለባቸው ተጠቅሷል። የገንዘብ ተቋማቱ (ባንኮች) እነዚህን መመሪያዎች በተገቢው መልክ እንዲሰሩም የደንበኞቻቸውን ታሪክ የሚከታተል አዲስ አደረጃጀት ሊያዋቅሩ ይገባል እንዲሁም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሰር መዘርጋት አለባቸው ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለባንኮች ለመድንና ለጡረታ ዋስትና ድርጅቶች ቦንድ መሸጥ እንዲችልም ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት ባንኮች ከዓመታዊ ጠቅላላ የብድር ክምችት አንድ በመቶ የልማት ባንክ ቦንድ፤ የመድን ድርጅቶች ደግሞ ከተጣራ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ15 በመቶ ያላነሰ የልማት ባንክ ቦንድ እንዲገዙ ተወስኗል። ይህ የልማት ባንክ ቦንድ መንግሥት ዋስትና የሚሰጠውና በተነፃፃሪ የተሻለ ወለድ የሚከፈልበት እንደሚሆንም ተገልጿል።", "የቢትኮይን ዋጋ በ50 በመቶ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆለቆለ ዋጋው እያሽቆለቆለ ያለው ቢትኮይን፣ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ቅናሽ በማሳየት አንድ ቢትኮይን 34ሺህ የአሜሪካ ዶላር እየተሸጠ ነው። የክሪፕቶከረንሲ አሻሻጩ ኮይንቤዝ ከስድስት 6 ወራት በፊት ጣራ ነክቶ የነበረው ቢትኮይን በአሁኑ ወቅት ዋጋው 50 በመቶ ቀንሷል ብሏል። በክሪፕቶከረንሲዎች የገበያ ድርሻ ቀዳሚ የሆነው ቢትኮይን ዋጋው መቀነሱ የተሰማው በመላው ዓለም የድርሻ ገበያዎች [ስቶክ ገበያ] መቀነሳቸውን ተከትሎ ነው። የክሪፕቶካረንሲዎች ዋጋ ከዓለም የስቶክ ገበያ ጋር ተያይዞ ዋጋቸው ከፍ እና ዝቅ ሲል ይስተዋላል። በ650 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ዋጋ ቢትኮይን የዓለማችንን አንድ ሦስተኛ የክሪፕቶከረንሲ ጠቅላላ ድርሻ ይይዛል። በአሁኑ ወቅት ቢትኮይን በአንዳንድ አገራት ጨምር ይፋዊ መገበያያ እየሆነ ነው። በቅርቡ መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ ያደረገች ሲሆን ቢትኮይንን አገር አቀፍ መገበያያ በማድረግ ኤል ሳልቫዶር የመጀመሪያዋ ናት። ኤል ሳልቫዶር ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ ስታደርግ አይኤምኤፍን ጨምሮ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ውሳኔውን ተችተው ነበር። ግብይት ለመፈጸም ክሪፕቶከረንሲዎች ለግለሰቦች የሚሰጡት ነጻነት እንዳለው ሁሉ፤ ክሪፕቶከረንሲዎች በሕገ-ወጥ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርጎ ማቅረብ ያስችላሉ። በተጨማሪም ክሪፕቶከረንሲን በመጠቀም አፍራሽ ተልዕኮዎችን በገንዘብ ለመደገፍ ይቻላል እንዲሁም የፋይናንስ ሥርዓት አለመረጋጋትን ይፈጥራል በሚሉ ምክንያቶች ሥርዓቱ ይተቻል። ከቢትኮይን ቀጥሎ ትልቁን የገበያ ድርሻ የሚይዘው ኢቲሪየም በተመሳሳይ ባለፉት ቀናት ዋጋው ከ10 በመቶ በላይ ቀንሷል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አውስትራሊያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ባንኮች የዋጋ ግሽበተን ለመቆጣጠር በሚል የወለድ መጠንን ከፍ አድርገው ነበር። ይህም ተበዳሪዎች ብድር የሚወስዱበትን የወለድ መጠን ከፍ አድርጓል። በርካታ ኢንቨስተሮች የዋጋ ግሽበት እና የብድር ወለድ መጠን ከፍ ማለት በዓለም ምጣኔ ሀብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል።", "ኤሎን መስክ የግል ጀቱን የሚከታተለውን የትዊተር ገጽ ባለቤት ሊከስ ነው ኤሎን መስክ በግል ጀቱ የት እንደተጓዘ የሚከታተለውን የትዊተር ገጽ ባለቤት ሊከስ ነው። የግል ጀቱ እንቅስቃሴ @ElonJet account በሚባለው ገጽ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ የልጁን ደኅንነት አደጋ ላይ እንደሚጥለው መስክ ተናግሯል። ይህ የትዊተር ገጽ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከታዮች አሉት። በዚህ ሳምንት ገጹን ትዊተር አግዶታል። የገጹ ባለቤት የ20 ዓመቱ ጃክ ስዊኒ ነው። በረራ የሚከታተሉ መተግበሪያዎችን ተጠቅሞ ነው የመስክን የግል ጀት የሚከታተለው። የመስክለ ጀት ሲነሳና ሲያርፍ ትዊተር ገጹ ላይ ይጽፋል። መስክ እንዳለው ስዊኒ እና ሌሎችም የፍርድ ቤት ክስ ይጠብቃቸዋል። “ትላንት ማታ አንድ መኪና ልጄ ሊል ኤክስ ያለበትን መኪና ሲከታተል ነበር። እኔ መኪናው ውስጥ ያለው መስያቸው ነው” ብሏል መስክ። የሰዎችን እንቅስቃሴ በቀጥታ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አደጋ ውስጥ ሊከት እንደሚችል ገልጿል። የመስክን ጀት የሚከታተለው ወጣት ፍሎሪዳ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው። ትዊተር ገጹን መርምሮ መርሕ ጥሶ በማግኘቱ እንዲዘጋ መወሰኑን ለሲኤንኤን ገልጿል። ወጣቱ ቢል ጌትስ፣ ጄፍ ቤዞስ እና ማርክ ዙከርበርግን ጨምሮ የሌሎችም ሀብታም አሜሪካውያን የግል ጀት እየተከታተለ የሚጽፋበቸው የትዊተር ገጾች አሉት። በተጨማሪም ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች ጋር የሚገናኙ ገጾችም አሉ። ሁሉንም ገጾች ትዊተር አስወግዷቸዋል። መስክ እንዳለው፣ ወጣቱ ገጾቹን እንዲያጠፋ 5ሺህ ዶላር ለመክፈል ጠይቀውት ነበር። ወጣቱ የክፍያ ጥያቄው ከቀረበለት በኋላ፣ ከፍያውን መፈጸም እንደማያስፈልግ በትዊተር በኩል እንደተገለጸ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ተናግሯል። መስክ ከወር በፊት ገጹን ላለመሰረዝ ቢወስንም አሁን ግን “ሰዎች ያሉበትን ቦታ የሚያጋልጡ ገጾች የደኅንነት ስጋት ናቸው” ብሏል። የትዊተር የደኅንነት ክፍል ባወጣው የተሻሻለ መመሪያ “የሌሎች ሰዎችን የግል መረጃ ያለ ፈቃዳቸው መለጠፍ ክልክል ነው” ብሏል። መስክ ትዊተርን ከገዛው በኋላ የተለያዩ ለውጦችን እያደረገ ይገኛል። ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹን ከማባረሩ ባሻገር በሳን ፍራንሲስኮ ዋና ቅርንጫፍ ለሚገኙ ሠራተኞች የቤት ኪራይ መክፈል ማቆሙም ተዘግቧል። ትዊተርን ከገዛ በኋላ ለኤሌክትሪክ መኪና አምራች ድርጅቱ ተስላ የሚሰጠው ትኩርት በመቀነሱ ኢንቨስተሮች ስጋት ገብቷቸዋል። በዚህ ሳምንት በሦስት ተከታታይ ቀናት 22 ሚሊዮን ድርሻ የሸጠ ሲሆን፣ ይህም 3.58 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል። መስክ በተስላ ያለው ድርሻ 40 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።", "ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከነጮች ባነሰ ሁኔታ የሚኖሩባት ደቡብ አፍሪካ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከነጭ አቻዎቻቸው በሦስት እጥፍ ያነሰ ገቢ እንደሚያገኙ አንድ ጥናት ይፋ አደረገ። ጥናቱ በደቡብ አፍሪካውያን መካከል ያለውን ያልተመጣጠነ ገቢን የተመለከተ ሲሆን፤ ከአገሪቱ 80 በመቶ የሚሆኑት ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የወር ገቢያቸው በአማካኝ 13000 ብር ገደማ ሲሆን፤ የነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ግን 38 ሺህ ብር አካባቢ እንደሆነ ተቀምጧል። • “ከብሔርም ከሐይማኖትም በላይ ሰውነት ከሰሃራ በረሃ ስቃይ አውጥቶኛል\" • ፓርቲዎች በክልላቸው ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚታየው ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ • ከንቲባ ታከለ ኡማ በስህተት ለወጣው የኤርትራ ካርታ ይቅርታ ጠየቁ ጥናቱ አክሎም እንዴት የተለያዩ ብሔሮች በማኅበራዊ መደብ ውስጥ እንደተቀመጡ አሳይቷል። ጥናቱ በአገሪቱ የስታስቲክስ መሥሪያ ቤት እኤአ ከ2002 እስከ 2017 ድረስ የተሰበሰበን መረጃ የተጠቀመ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን በሥራ ማጣት ክፉኛ እንደሚቸገሩ ያሳያል። እነዚህ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የግል የሕክምና ተቋማትን መጎብኘት፣ መጠለያና መብራት የማግኘት ጉዳይም ቅንጦት እንደሆነባቸው ጥናቱ ያመለክታል። ጥናቱ፤ የደቡብ አፍሪካ ከተሞችን ከዓለማችን አገራት መካከል ከፍተኛ ያልተመጣጠነ ገቢ ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባት አገር አድርጓታል። ጥናቱ ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ አከራካሪ ለነበረው ጉዳይ ጠቅለል ያለ ምልከታን በማስቀመጥ መረጃን የሰጠ መሆኑ ተነግሮለታል። በብሔሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የሀብት ልዩነት እንዲኖር ካደረኩጉ ምክንያቶች አንዱ የአፓርታይድ ውጤት ነው የተባለ ሲሆን፣ አፓርታይድ በቁጥር አነስተኛ የሆኑት ነጮች አገሪቱ ያላትን ውስን ሀብት ያለስስት እንዲጠቀሙና ሀብት እንዲያካብቱ አድርጓል ተብሏል።", "በኢንተርኔት መቋረጥ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ቀጥሎ በአፍሪካ ከፍተኛ ገንዘብ አጥታለች - ሪፖርት ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በኢንተርኔት መቋረጥ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ በመቀጠል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዳጣች አንድ ሪፖርት አመለከተ። ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ሆን ተብለው የተፈጸሙ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጦች በአገራት ላይ ያስከተሉትን ኪሳራ በተመለከተ ቶፕ ቴን ቪፒኤን ባወጣው ሪፖርት ላይ በአፍሪካ ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በቀዳሚነት ተቀምጠዋል። በመላው ዓለም መንግሥታት በአገራቸው ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በማቋረጣቸው በአጠቃላዩ የምድራችን ምጣኔ ሀብት ላይ የ5.5 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን ማስከተላቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት ከሁለት ሳምንታት በፊት በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የኢንትርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ በመደረጉና የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች በመዘጋታቸው ኢትዮጵያ 164.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳጣች ተገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በቀጠለው የትግራይ ጦርነት ምክንያት በክልሉ የኢንተርኔት አገለግሎት መቋረጡን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ባለፈው ግንቦት ወር የተሰጠው ብሔራዊ ፈተና በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሾልኮ ወጥቷል በሚል በመላው አገሪቱ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም ከአገልግሎት ውጪ እንደነበሩ ጠቅሷል። እንደ ሪፖርቱ በአንድ ዓመት ውስጥ በአገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ሆነው የቆዩት ለ8,760 ሰዓት ሲሆን የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረኮች ደግሞ ለ104 ሰዓት ተዘግተው ቆይተው ነበር። በዚህም ሳቢያ በኢትዮጵያ ከ21 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኢንተርኔትና በማኅበራዊ ሚዲያ መስተጓጎል መቸገራቸውንና 165 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት መድረሱን አመለክቷል። ዓመታዊው ሪፖርቱ በዓለም ዙሪያ ያጋጠሙ ዋነኛ የሆኑና ሆን ተብለው የተቋረጡ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመመዝገብ የተነተነ ሲሆን፣ በዚህም የደረሱ ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራዎችና አገልግሎት የተነፈጉ ሰዎችን ብዛት አቅርቧል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንተርኔት መቋረጥ ከፍተኛ ኪሳራ የገጠማት አገር ምሥራቅ እስያዊቷ አገር ምያንማር ስትሆን፣ ይህም በአገሪቱ የጦር ጄነራሎች የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥትን ተከትሎ ነው። ባለፈው ዓመት በምያንማር ኢንተርኔት ለ12,238 ሰዓታት የተቋረጠ ሲሆን ይህም የ2.8 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን አስከትሎባታል። ሁለተኛዋ ደግሞ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ስትሆን ሆን ተብሎ ኢንተርኔት በመቋረጡ ምክንያት 104.4 ሚሊዮን ሕዝብ ከአገለግሎት ውጪ ሆኖ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እንድታጣ አድርጓታል ተብሏል። ከኢንተርኔት መቋረጥ በተጨማሪ አገራት የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮችንም ለይተው አገልግሎት እንዳይሰጡ ያደርጋሉ። በዚህም ባለፈው ዓመት ከሁሉም በበለጠ ዕቀባ ተጥሎበት የነበረው ትዊተር ሲሆን፣ በተከታይነት ፌስቡክና ዋትስአፕ በአንዳንድ አገራት ውስጥ አገልግሎታቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል። በአጠቃላይ ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 21 አገራት ውስጥ 50 የሚሆኑ ዋነኛ የሚባሉ የኢንተርኔት መቋረጦች በተለያዩ ምክንያቶች እንዳጋጠሙ ተመዝግቧል። ይህም በአጠቃላዩ የዓለም ምጣኔ ሀብት ላይ የ5.45 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን በማስከተል ከቀደመው ዓመት በ36 በመቶ ከፍ ማለቱን የቶፕ ቴን ቪፒኤን ሪፖርት ዓመልክቷል። ኢንተርኔት በተቋረጠባቸው አገራት ውስጥ 486.2 ሚሊዮን ሰዎች ከአገልግሎት ውጪ ለመሆን የተገደዱ ሲሆን፣ ኢንተርኔት በመንግሥታት ሲቋረጥ ከተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር እንደሚያያዙም አመልክቷል። በዚህም ሳቢያ በምርጫ፣ በመሰብሰብና በመናገር ነጻነቶች ላይ ጥሰቶች ያጋጥማሉ። በዘመናዊው ዓለም የኢንተርኔት አገልግሎት ከመሠረታዊ የሰዎች ፍላጎቶች ውስጥ እየታየ ያለ ሲሆን፣ ኢንተርኔት ለበርካታ ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛው መሳሪያ በመሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ የሚያስከትለው ኪሳራ ቀላል የሚባል አይደለም።", "የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፍለጋና የዋጋ መናር በአዲስ አበባ አዲስ አበባ ውስጥ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በከፍተኛ ገንዘብ ሲሸጥ እንደነበረና በመደብሮች ውስጥ ማግኘት እንዳልቻሉ ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ። አርብ ዕለት አዲስ አበባ ላይ የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት የመጀመሪያው የተረጋገጠ የኮሮናቫይረስ ታማሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ስጋት የገባቸው ሰዎች የፊት ጭንብልና ፈሳሽ የእጅ ማጽጃ ውህዶችን በመግዛት ላይ ናቸው። የቢቢሲ ያናገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳሉት በሽታው አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ ሊከላከለው ይችላል የተባሉ ነገሮችን እየገዙ መሆናቸውን ነገር ግን የጭንብሎቹና ፈሳሽ የንጽህና መጠበቂያዎች [ሳኒታይዘር] እንደልብ እንደማይገኙ ከተገኙም ዋጋቸው በሚያስደነግጥ ሁኔታ መናሩን ገልጸዋል። አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ የመድሃኒት መደብሮችም የፊት ጭንብልና ሳኒታይዘር እንደሌላቸው በሚለጥፉት ማስታወቂያም ሆነ በተጠየቁ ጊዜ የሚሰጡት ምላሽ እንደሆነ ቅዳሜ ዕለት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ ፋርማሲዎችን የተመለከተው የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይም በርካቶች የፊት ጭንብል ስለመጥፋቱና ስለመወደዱ ገጠማቸውን በጽሁፍና በምስል እያሰፈሩ ነው። ጭንብሉ ያለባቸው ፋርማሲዎች ረዘም ያሉ ሰልፎች የታዩ ሲሆን ውስን ቁጥር ያላቸውን መሸፈኛዎችን በመደበኛው ዋጋ ሲሸጡ እንደነበር ተገልጿል። ቢቢሲ በስልክ ያናገራቸው በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለት የመድሃኒት መደብሮች የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንደጨረሱና ሲሸጡ የነበረውም ቀደም ሲል በነበረው ዋጋ እንደሆነ ገልጸዋል። የከተማዋ ባለስልጣናትም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ተፈላጊ በሆኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሚሸጡ የንገድ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አመልክተው፤ ኅብረተሰቡም ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በርካታ ሰዎች በሽታውን ሊከላከል ይችላል በማለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ለመግዛት ወደ መድሃኒት መደብሮች ቢሄዱም ለማግኘት እንደተቸገሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። \"ሰው ሁሉ እየገዛ በመሆኑ ለልጆቼም ሆነ ለእራሴ የሚሆን ማስክ ለመግዛት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በየደረስኩበት ቦታ ያሉ ፋርማሲዎችን ብጠይቅም ላገኝ አልቻልኩም\" ያሉት የሁለት ልጆች እናትና አዲስ አበባ ውስጥ አብነት የሚባለው አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መብራት አስቻለ ናቸው። ወይዘሮ መብራት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጎረቤቶቻቸው ጭንብሉን እስከ 200 ብር በሚደርስ ዋጋ ከሰዎች ላይ መግዛታቸውን እንደሰሙ ነገር ግን ይህን ያህል ገንዘብ በማውጣት ለቤተሰባቸው መግዛት ከባድ ስለሆነባቸው እንደተዉት ገልጸዋል። የጭንብሉን አስፈላጊነት በተመለከተ የሰሙት በዙሪያቸው ካሉ ሰዎች መሆኑን እንጂ ከባለሙያዎች የተነገራቸው ነገር እንደሌለ የሚጠቅሱት ወ/ሮ መብራት \"በሸታው አሳሳቢ በመሆኑ የምችለውን ላድርግ በማለት ነው ከአንዱ ፋርማሲ ወደ ሌላው በመሄድ ስጠይቅ የነበረው\" ይላሉ። ተለያዩ ሰዎች በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ የሚሰጡት አስተያየቶችም ከዚሁ ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብል ከ150 እስከ 500 ብር በሚደርስ ዋጋ እየተሸጡ መሆናቸውን የሚያመለክቱ ናቸው። ከፊት መሸፈኛ ጭምብሎች በተጨማሪ የእጅ ማጽጃ ፋሳሾችም ዋጋቸው የጨመረ ሲሆን ተህዋሲያንን ያጠፋሉ ተብለው የሚነገርላቸው ሳሙናዎችም ተፈላጊነታቸው ጨምሯል። ዋጋቸውም በዚያው ልክ መጨመሩን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የከተማው መስተዳደርም \"የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ተጠቂ ተገኝቷል\" የሚለው መረጃ ከወጣ በኋላ በተለያዩ ሸቀጦች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል አቋቁሞ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አሳወቋል። ከኮሮናቫይረስ መከሰት ጋር በተያያዘ አፍን አፍንጫን የሚሸፍኑ ጭምብሎች በስፋት በዓለም ዙሪያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። በዚህም ሳቢያ በበርካታ አገራት ውስጥ የጭንብሎቹ እጥረት እየተከሰተ በመሆኑ አምራቾች የጭንብል ምርታቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በዓለም የጤና ድርጅት ተጠይቀዋል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚገምተው በየወሩ 89 ሚሊዮን የሚደርስ የፊት ጭምብሎች ያስፈልጋሉ። በኮሮናቫይረስ ስጋትና በተሳሳተ አመለካከት ሳቢያ እነዚህ ጭንብሎች ያላግባብ ጥቅም ላይ ስለሚውሉ የሚየስፈልገው ቁጥር ከዚህም በላይ እንደሚሆን ይገመታል። ድርጅቱ እንዳለውም የፊት ጭንብሎች በስፋት ጥቅም ላይ በመዋላቸውና ሰዎች በብዛት እየገዙ በማስቀመጣቸው የተነሳ የህክምና ባለሙያዎች በየዕለቱ በሚጠቀሙት አቅርቦት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አመልክቶ፤ ይህም በዚህ የወረርሽን ጊዜ ህሙማንን በመርዳት ሥራ ላይ የተጠመዱ የህክምና ባለሙያዎች ለኮሮናቫይረስና ለሌሎች በሽታዎች ተጋላጭ ሊያደርጋቸው ይችላል ሲል ስጋቱን ገልጿል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው የኮሮናቫይረስን ለመካላከል በሚል ሁሉም ሰው የአፍና የአፍናጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ አያስፈልገውም። ጭንብሉን ማድረግ ያለባቸው የሚያስነጥሱና የሚያስሉ ከሆነ እንዲሁም በበሽታው የተጠረጠረ ወይም የተያዘን ሰው የሚቀርቡና የሚንከባከቡ ሰዎች ብቻ ነው። ለእነዚህ ሰዎች ጭንብሉን ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም፤ በውጤታማ ሁኔታ በሽታውን ለመከላከልም በመደበኛነት እጃቸውን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ወይም አልኮል ነክ በሆኑ ፈሳሾች እጃቸውን ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም ጭንብሉን መጠቀም ያለባቸው ሰዎች እንዴት መጠቀምና በተገቢው ሁኔታ እንዴት መወገድ እንዳለበትም ማወቅ ይገባቸዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ይመክራል። ስለዚህም በአዲስ አበባና በሌሎች ስፍራዎች የተጠቀሱት አይነት የበሽታው ስጋቶች ሳይኖሩ ጭምብልን ከሚገባው በላይ ከፍተኛ ገንዘብ እያወጡ መግዛት በሽታውን ለመከላከል የሚኖረው ጠቀሜታ ዝቅተኛ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር መክሯል። እነዚህ ለአጭር ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉት የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች ጥብቅ ብለው አፍንጫና አፍን የሚሸፍኑ ካለመሆናቸው ባሻገር ረጅም ጊዜን አያገለግሉም። የማስነጠስና የማሳል ምልክት የሚታይባቸውን ወይም በኮሮናቫይረስ ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር የግድ መቅረብ ያለባቸው ሰዎች የሚጠቀሙባቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች በቀላሉ በላብ ስለሚባላሹ ወዲያው ወዲያው መቀየር አለባቸው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚመክሩት የተጠቀሱት ምልክቶች እስካልታዩ ድረስ ሁሉም ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ አያስፈልጋቸውም። ከዚያ ይልቅ ግን የበሽታው ስጋት ለማስወገድ ከሚያስሉ፣ ከሚያስነጥሱ ወይም ትኩሳት ካለባቸው ሰዎች ጋር የሚኖርን ንክኪ ማስወገድ፣ እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ካልሆንም ተህዋሲያንን በሚያስወዱ ማጽጃዎች እጅን ማጽዳት ከሁሉ በበለጠ ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም እጅን ሳይታጠቡ ዓይንን፣ አፍንጫንና አፍን አለመንካት እንዲሁም መጨባበጥን ማስወገድ የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታት መወሰድ ካለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል ይጠቀሳሉ።", "ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካ ታችኛው ምክር ቤት ጆ ባይደን ያቀረቡትን የ1.9 ትሪሊየን ዶላር ድጎማ አፀደቀ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት አሜሪካዊያንን ለመርዳት ያቀረቡት የ1.9 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ማዕቀፍ በተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ። የድምፅ አሰጣጥ ሁኔታው ከፓርቲ ወገንተኝነት ጋር የተያያዘ ነበር። ሁሉም ሪፐብሊካኖች ተቃውመውታል። ሁለት ዲሞክራቶችም ገንዘቡ በጣም ብዙ ነው ሲሉ በመቃወም ሪፐብሊካኖችን ተቀላቅለዋል። ማዕቀፉ በሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ ሰብሳቢ በሆኑበት የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ይቀርባል። ይህ ምክር ቤት ከየግዛቱ እኩል 2 እንደራሴዎች የሚሞሉት የመቶ ወኪሎች ሸንጎ ነው። ባለ ትልቅ ሥልጣንም ነው። ምክር ቤቱ ዝቅተኛ የክፍያ መጠንን በእጥፍ ማሳደግ የሚለውን ሃሳብ ውድቅ አድርጓል። ይህ ረቂቅ ሕግ ግን አሁንም የአሜሪካ ዝቅተኛ ክፍያ ጭማሬን አካቷል። ይህ እንዴት እንደሚፈታ ግልፅ የሆነ ነገር የለም። ምንም እንኳን በምክር ቤቱ ይህ ነጥብ እንዳይካተት ቢደረግም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ፤ ሁሉም የቀረቡት እቅዶች እንደሚያልፉ ተናግረዋል። ዝቅተኛ ክፍያን ማሳደግ የዲሞክራቶች ዋነኛ ግብ ነው። አንዳንድ የዲሞክራት መሪዎች በሰዓት ከ15 ዶላር በታች የሚከፍሉ ቀጣሪዎችን ለመቅጣት እያሰቡ ነው። ይህ የገንዘብ ማዕቀፍ የኮሮናቫይረስ ክትባት ስርጭትን እና ምርመራን ለማሳደግ እንዲሁም ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ያለመ ነው። ማዕቀፉ ለሁሉም አሜሪካዊያን ከሚሰጠው 1 ሺህ 400 ዶላር የገንዘብ ድጎማ ጋር ተደማምሮ ለቤተሰብ የሚሰጠውን ድጎማ 1 ትሪሊየን ዶላር ገንዘብን ያካትታል። ከዚህም ባሻገር ወረርሽኙን ለመዋጋት የሚውል 70 ቢሊዮን ዶላር እና ለአነስተኛ ንግዶች ማነቃቂያ 110 ቢሊየን ዶላርንም ይጨምራል ። ለቤተሰብ፣ ለአነስተኛ የንግድ ተቋማትንና የግዛት መንግሥታት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ይሆናልም ተብሏል። ዲሞክራቶች ቅዳሜ ጠዋት በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በቂ ድምፅ አግኝተዋል። በዚህም ፕሬዚደንት ባይደን በኮቪድ -19 እየተፈተኑ ያሉትን አሜሪካዊያን ለመርዳት ባሰቡት 'የአሜሪካ መታዳጊያ እቅድ' አሸናፊ ሆነዋል። ይሁን እንጂ ሪፐብሊካን እቅዱ አላስፈላጊ በሆነ መጠን ብዙ እና ከወረርሽኙ ጋር ተያያዥነት በሌላቸው ዲሞክራሲያዊ ጉዳዮች የተሞላ ነው ብለዋል። ዲሞክራቶች በላዕላይ ምክር ቤቱ ጥብቅ ክርክር ይጠብቃቸዋል ተብሏል። ዲሞክራቱ ጆ ባይደን በአሜሪካ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለውን ወረርሽኝ ለመዋጋት ቃል መግባታቸው ይታወሳል።", "የተሰናባቹ 2013 ዓመት ዓበይት ምጣኔ ኃብታዊ ክስተቶች ኢትዮጵያ 2013ን ተሰናብታ አዲሱን ዓመት ልትቀበል የቀራት ጥቂት ቀናት ናቸው። ተሰናባቹን ዓመት ዘወር ብለን በምናይበት ወቅት አገሪቷ በጦርነት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ የተቀጠፉበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤት አልባ ሆነው በችግር ውስጥ የሚገኙበት፣ ከፍተኛ የዋጋ ንረት የብዙዎችን ናላ እያዞረ ባለበት ነው ያሳለፉት። ፈታኝ በሚባል የታሪክ ሂደት ውስጥ ያለችው አገሪቷ በምትሸኘውም ዓመት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጸጥታ ምክር ቤት ዋነኛ ርዕሰ ጉዳይ፣ የኃያላኑ መንግሥታት መነጋገሪያ፣ በባለስልጣናቷ ላይ የጉዞ ዕቀባ የተጣለባትና ከጫፍ ጫፍ ያሉ የዓለም ሚዲያዎች ዋና ርዕስም ሆናለች። አገሪቷ ከትግራይ ጦርነት ጋር ተያይዞም በረሃብና በመብት ጥሰቶች ስሟ በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ሆኗል። ከጦርነት በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አገሪቷ ላይ ጫና ያሳደረ ከመሆኑ አንፃር በርካታ ጋሬጣዎች የተደቀኑበት ዓመት ሆኖ ማለፉ አሌ አይባልም። ተሰናባቹ ዓመት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የታየበት፣ ከምጣኔ ሀብት ቀውሰ ጋር በተያያዘ ኤምባሲዎች የተዘጉበት፣ አገሪቷ የመገበያያ ገንዘብ ኖት የቀየረችበት፣ አዲስ የቴሌኮም ፈቃድ የተሰጠበት ወቅት ነው። ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱ መመሪያዎች የወጡበት እንዲሁም ኢትዮጵያ ለአስርት ዓመታት ሲጠበቅ የነበረው የንግድ ሕጓን ያሻሻለችው በተሰናባቹ ዓመት ነው። ለመሆኑ የተሰናባቹ ዓመት ዓበይት የምጣኔ ሀብት ክስተቶች ምን ነበሩ? እንዲህ ቃኝተናቸዋል። የብር ኖቶች ቅያሪ ኢትዮጵያ የ2012 ዓ.ምን የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዋን የጀመረችው ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶችን በመቀየርና አዲስ ብር ኖቶችን ይፋ በማድረግ ነው። በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶች ለመቀየር ሌላ ወጪ ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊዮን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ አስታውቀዋል። አገሪቱ በዋነኝነት ወደ ቅያሪ የገባችው ባንኮች የገጠማቸውን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍና ቁጠባቸውን እንዲያሳድግ፣ ሕጋዊ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውርን ከኢኮኖሚው እንቅስቃሴ እንዲወገድ፣ የዋጋ መረጋጋት እንዲኖር፣ የመንግሥት ገቢ እንዲያድግ ያስችላል በሚል ነው። በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከባንክ ውጪ በመኖሩ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኩዊዲቲ) ከማጋጠሙ ጋር ከመሆኑ ተያይዞም ቅያሪው ይህንንም እንደሚቀርፍ ታምኗል። ከቅያሪው ጋር ተያይዞ ከወጡ መመመሪያዎች ጋር በተያያዘ አንዳንድ ለውጦችም ታይተዋል። በአንድ ሰው እጅ ሊቀመጥ የሚችለው የገንዘብ መጠን በ1.5 ሚሊዮን ብር መወሰኑ፣ ግለሰቦች ከባንክ በቀን ማውጣት የሚችሉት ከፍተኛ የገንዘብ መጠን 200 ሺህ ብር፣ እንዲሁም ኩባንያዎች በጥሬ ገንዘብ ማውጣት የሚችሉት 300 ሺህ ብር ገደብ መመሪያዎች ጥያቄ ያጫሩ ሆነው አልፈዋል። ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ እንዳስታወቀው የታተመው ብር በኢኮኖሚው ውስጥ ከሚዘዋወረው በበለጠ እንዲሆንና ለመጠባበቂያም እንዲሆን 262 ቢሊዮን ብር ታትሟል። በ1983 ዓ.ም የታተመው የብር መጠን ስምንት ሚሊዮን ብር ብቻ የነበረ ሲሆን የዘንድሮው በአገሪቱ የብር ቅያሪ ታሪክ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቧል። የትግራይ ጦርነት ያስከተለው ቀውስ በጥቅምት መጨረሻ አካባቢ በትግራይ ክልል የተከሰተው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከመግደሉ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና የምጣኔ ሀብት ቀውስ አስከትሏል። ጦርነቱ እስካሁን ድረስ አገሪቷን ምን ያህል እንዳስወጣት ይፋዊ መረጃ ባይኖርም፣ በትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ትንበያ መሰረት ወታደራዊ ወጪዋ በመጪው ታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ ወደ 502 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ተብሏል። ባለፈው ዓመት ወጪዋ 460 ሚሊዮን ዶላር ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ጦርነቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ከአገሪቱ ግምጃ ቤት አስወጥቷል ብለዋል። አገሪቱ ለጦርነቱ መዋዕለ ንዋይዋን ከማፍሰሷ በተጨማሪ ከትግራይ ክልል ታገኝ የነበረውን ገቢም አጥታለች። ጦርነቱ በተጀመረ በወራት ውስጥ ከትግራይ ክልል በሦስት ወራት ውስጥ መሰብሰብ የነበረበት ሁለት ቢሊዮን ብር አለመገኘቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥር ወር መጨረሻ ላይ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃጸሙን ለሐዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው መረጃ መሰረት በበጀት ዓመቱ ለመሰብብሰብ ከታቀደው 290 ቢሊዮን ብር ውስጥ በትግራይ ክልል ለማግኘት የታሰበው 7.8 ቢሊዮን ብር እንደነበር አስረድቷል። ከጦርነቱ በፊት በነበሩት ሦስት ወራት 1.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል። የትግራይ ክልል ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ውስጥ የምትጠቀስ ስትሆን ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በየዓመቱ ወጪ ንግድ ከምታደርጋቸው ምርቶች ውስጥ ዘጠኝ በመቶ የክልሉ ድርሻ ነው። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የአይኤምኤፍ መረጃ ያሳያል። ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ከተሜን ህይወት እየፈተነና የማይወጡት ተራራ ሆኖባቸዋል። የኑሮ ውድነት አመላካች የሆነው የዋጋ ግሽበት በነሐሴ ወር ወደ 30.4 በመቶ አሻቅቧል። የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው በነሐሴ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ከ32 በመቶ አገሪቷ በአስርት ዓመታት አይታው ወደማታውቀው 37.6 በመቶ ደርሷል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦችን የዋጋ ግሸበት በምናይበት ወቅት ከ19 በመቶ ወደ 20.8 በመቶ አሻቅቧል። የዋጋ ግሽበቱ ጦርነት በሚካሄድባቸውና ምንም ዓይነት የመሠረታዊ አገልግልቶች በሌለባቸው እያሻቀበ ሲሆን የመሠረታዊ ሸቀጦች መመናመኑን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ለምሳሌ ያህል ጥር መጨረሻ ላይ በነበረው መረጃ መሰረት የምግብ ዋጋ ግሽበቱ በትግራይ ከ36 በመቶ በላይ ነበር። የአገሪቷ የዋጋ ግሽበት ከሦስት አስርት አሃዝ በላይ መሆኑ መሠረታዊ በሚባሉ ሸቀጦችም ዋጋ እያናረው ሲሆን በዜጎች ላይም ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳደረ ነው። ኢትዮጵያ ለዓመታት የነበራት የተዛባ የንግድ ሥርዓት በተለይም የወጪና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን፣ ጦርነትና አለመረጋጋት፣ የብር መዳከም የፈጠረው ግሽበት፣ የወጪ ንግድ መቀዛቀዝ፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ተደራርበው ለዋጋ ንረቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በመላው ዓለም የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በምጣኔ ሀብቱ ቀውስ ላይ ጫና እያሳደረ ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ ነጠላ አሀዝ አውርዶ የዋጋ መረጋጋት ለማምጣት እየጣረ የሚገኝ ሲሆን ከሰሞኑም የተወሰኑ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ላልተወሰነ ጊዜ ከቀረጥና ታክስ ነጻ ማድረጉን አስታውቋል። ከነሐሴ መጨረሻም ጀምሮ የምግብ ዘይት፣ ስኳርና ሩዝ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምባቸው ከቀረጥና ታክስ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሲሆኑ ስንዴ ከውጭ ሲገባ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆን ተወስኗል። ፓስታ እና ማኮሮኒ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የዶሮ እንቁላል ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆን ተወስኗል። የውጭ ምንዛሪ ዋጋ መናር ለዓመታት የአገሪቱ አንገብጋቢ ችግር ሆኖ የዘለቀው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በዘንድሮው ዓመትም በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሷል። በዓመታት ከፍተኛ በሚባል ሁኔታ ጭማሪ እያሳየ የመጣው የምንዛሪ ተመን ንሮ ይፋዊ በሆነው የባንክ ግብይት መሰረት አንድ ዶላር በ45.6 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። በትይዩ ወይም በተለምዶ ጥቁር ገበያ በሚባለው ገበያ የምንዛሪ ተመን ደግሞ አንድ ዶላር በ70 ብር አካባቢ እየተመነዘረ ሲሆን ከመደበኛው ገበያ ጋር ያለው ልዩነት ከ20 ብር በላይ መሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን ስጋት ላይ የጣለ ክስተት ሆኗል። በተለይም አገሪቷ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ ፍላጎት የሚመራ ሥርዓት እንዲዘረጋ ከመወሰኗና ከገበያው ጋር ለማቀረራረብ እየሰራች ባለበት ወቅት ይህንን ያህል ልዩነት መፈጠሩ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ጥያቄ ሆኗል። የብር የንምዛሪ ተመን ማሽቆልቆል በትግራይ ክልል ከተነሳውና በአማራና አፋር ክልል ከተዛመተው ጦርነት ጋር ተያይዞ አገሪቷ ካጋጠማት አለመረጋጋት በተጨማሪ የብር ተገቢውን ዋጋ መያዝ (ዲቫሉዌት) የማድረግ ጥረትና የንግድ ሚዛን ጉድለት እንደሆነም ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተለይም የአገሪቷ የተዛባ የንግድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው የወጪና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን በተጨማሪ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለዓመታት መንግሥት ብር ከዶላር ጋር ያለው ምንዛሪ ተመን መዳከም እንዳለበት ከመጎትጎታቸው ጋር ተያይዞ ይህ ተግባራዊ መሆኑ ብሩን አዳክሞታል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጣ ምርቶችን ወደ ውጪ ትልካለች። ምንም እንኳን ይህ አሀዝ ጉድለት ቢታይበትም የአገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ሲሻገር የመጀመሪያው ነው። አዲስ የቴሌኮም ፈቃድ ኢትዮጵያ ለ126 ዓመታት ያህል በመንግሥት ልማት ስር የነበረውን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ክፍት በማድረግ የቴሌኮም ፈቃድ የሰጠችው በዘንድሮው ዓመት ነው። በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለመሰማራት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጨረታ በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት በ850 ሚሊዮን ዶላር አሸንፏል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ ጥምረት በዘርፉ አሉ የሚባሉ ስመ ጥር የቴሌኮም ኩባንያዎችንና ተቋማትን በቅንጅት የያዘ ሲሆን እነዚህም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕና ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕ የተካተቱበት ነው። ጥምረቱ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የቴሌኮም አገልግሎት ከመጪው ጥር 2014 ዓ.ም በኋላ ይጀምራል ተብሏል። ዋነኛው የአገሪቱ አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻውን ለውጪ ባለሀብቶች፣ 5 በመቶውን ለኢትዮጵያውያን እና 55 በመቶውን በመንግሥት ይዞታ ይቀጥላል ተብሏል። ኢትዮጵያ ኢትዮቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥ የወሰነችው በዋነኝነት ያላትን ከፍተኛ ዕዳ ለመክፈል ሲሆን፤ በተጨማሪነት የቴሌኮምን ተደራሽነት ለመጨመርና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እንደሆነም ይጠቀሳል። ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድን ለመስጠት ወደ ገበያው መግባት የሚሹ ፍላጎታቸውን እንዲገልጹ ሲጠየቅ 12 የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ለመሳተፍ ፍለጎት እንዳላቸው ገልጸው ነበር። ከእነዚህ ውስጥም የፈረንሳዩን ኦሬንጅ ጨምሮ ሳዑዲ ቴሌኮም ኩባንያ፣ ሊኩዊድ ቴሌኮም፣ እንዲሁም የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ኢቲሳላትን ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች አፈግፍገዋል። ለዚህም አንደኛው ምክንያት ሆኖ የተጠሰው የአገሪቱ ሕግ ለውጭ ተቋማት በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ለመሰማራት አለመፍቀዱ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታም እንደምታወጣ በገለፀችበት ወቅት የአገልግሎት ፈቃድ የሞባይል ገንዘብ መገበያያን እንዲጨምር ተደርጓል። በተያያዘም ኢትዮ ቴሌኮም በድምፅ፣ በመልዕክት፣ በኢንተርኔት ተወስኖ የነበረውን አገልግሎት በማስፋት የቴሌ ብር የሞባይል አገልግሎት አስጀምሯል። ተቋሙ ከቻይናው ሑዋዌ ኩባንያ ጋር በመተባበር ተግባራዊ ያደረገው ቴሌ ብር ለአስር ሚሊዮኖች ደንበኞቹ በስልካቸው ገንዘብ ለማስተላለፍና እና ለግብይት አገልግሎትም ይውላል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም በአምስት ዓመት 33 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገልና 3.5 ትሪሊየን ብር ለማንቀሳቀስ ማቀዱም ተዘግቧል። የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር መልቀቅ ማቅማትና የናረው ዕዳ ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የገንዘብ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያንገራገሩ ነው ተብሏል። በዋነኝነትም የነዚህ ተቋማት ስጋት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የበለጠ ጫና ውስጥ ይከታታል እንዲሁም መክፈል አቋሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ጋር የተያያዘ ነው። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጰያ ለመስጠት ቃል የገባውን 339 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑ ተነግሯል። ከዚህም በተጨማሪ የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) 3.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) 2.7 ቢሊዮን ዶላር፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላርና ሌሎችም አበዳሪዎች በያዝነው አመት እስከ መጋቢት ድረስ ይሰጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን አልተለቀቀም የተባለውም በዚህ አመት ነው። ከዚህም ጋር በተያያዘ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ሊያስተጓጉል እንደሚችል ተሰግቷል። ከሰሞኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ከአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ እዳው እስከ አውሮፓውያኑ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ 2.4 ትሪሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡን ሪፖርተር ጋዜጣ የገንዘብ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በዘገባው መሰረት ብሔራዊ ባንክ ባለፈው አንድ ዓመት ባደረገው የብር ምንዛሬ ተመን ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅምም በከፍተኛ ደረጃ በመውረዱ አጠቃላይ የአገሪቱ እዳ በ221. 5 ቢሊዮን ብር እንዳሻቀበም ዘገባው አስነብቧል። የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ተብሏል። ብሔራዊ ባንክና አዳዲስ መመሪያዎቹ ብሔራዊ ባንክ በዘንድሮው ዓመት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ከሒሳብ ወደ ሒሳብ ማዘዋወር የሚከለክለው ሰርኩላርን ጨምሮ፣ የባንኮች መመስረቻ ካፒታል አምስት ቢሊዮን ብር እንዲሆን የሚሉና ሌሎች ተጨማሪ አዳዲስ መመሪያዎችን አውጥቷል። ባንኩ በነሐሴ ወር ከዚህ ቀደም ባንኮች ይሰሩበት የነበረውን ቤት፣ ሕንፃ፣ መሬትና ሌሎችም ንብረቶችን በመያዣነት ተጠቅመው ብድር የሚሰጡበትን አሰራር አግዷል። ባንኩ ይህንን እርምጃ የወሰደው በኮኖሚው ውስጥ አሻጥር ታይቷል በሚል ሲሆን በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መያዣነት የሚሰጠው ብድር እግድ እስከ መቼ እንደሆነ አልተጠቀሰም። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ በከፍተኛ ሁኔታ እያንሰራራ ያለውን የዋጋ ግሽበትን ለመግታት ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ እንዲያስቀምጡት የሚጠበቅባቸውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ወደ አስር በመቶ ከፍ እንዲያደርጉት ተወስኗል። ከዚህ ቀደም 5 በመቶ የነበረውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል የተደረገው በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን ለመቀነስ ቁጥብ የገንዘብ ፖሊስ ለማድረግ ከመወሰኑ ጋር ተያይዞ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ የወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ የውጭ ምንዛሬንም በተመለከተ አዲስ መመሪያ የተላለፈ ሲሆን ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሃዋላና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ውስጥ 50 በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ አለባቸው ተብሏል። እነዚህ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ላይ ከታዩት ጉልህ ክስተቶች መካከል የተወሰኑት ናቸው።", "በኬንያ ከኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የሚሰረቅ መርዛማ ዘይት ለምግብ ማብሰያነት እየተሸጠ ነው ተባለ የኬንያ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ድርጅት ከሃይል ማስተላላፊያ ወይም ትራንስፎረመር ላይ እየተሰረቀ እንደ ማብሰያ ዘይት የሚሸጠው ፈሳሽ መሰረተ ልማቶቹ ላይ ጉዳት በማድረስ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሳራ እያስከተለ እንደሆነ ገለጸ። የኬንያ ኤሌክትሪክ ሃይል ወንጀለኞች ፈሳሹን ከትራንስፎርመሮቹ ውስጥ በማውጣት ለሬስቶራንቶች እና በመንገድ ዳር ምግብ ለሚያዘጋጁ በሽያጭ ቀርቦ ምግብ ለማብሰል እና ለመጥበስ እንደሚሸጥ አስታውቋል። ከምግብ ዘይት ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ የመጣው ይህ ድርጊት አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችን እነዚህ የሚዘረፉ ዘይቶችን መግዛትን ጨምሮ ወዳልተለመዱ የምግብ ማብሳያ አማራጮች እንዲሄዱ አድርጓቸዋል። የምግብ ዘይት የሚመስለው እና በትራንስፎርመር ውስጥ የሚገኘው ፈሳሸ ለሰው ልጅ ጤና አደጋ የሆነ እና ከፍተኛ የጤና ጠንቅ የሚያስከትል መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ። ሌሎች ወንጀለኞች ደግሞ የግለሰቦች ወይም የንግዶች ተቋማትን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በማቋረጥ መልሶ ለመቀጠል ገንዘብ ይጠይቃሉ። በኬንያ 20 የሚጠጉ ትራንስፎርመሮች እንደወደሙ ወይም ጉዳት እንደደረሰባቸው እና በማዕከላዊ ኬንያ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ መምጣቱን የኬንያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል። በኬንያ ቢያንስ 22 ሰዎች ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። እየተፈጸሙ ባሉ ስርቆቶች ምክንያት ከፍተኛ የሃይል መቆራረጥ የገጠመው የኬንያ ኤሌክትሪክ ሃይል አሁኑ ላይ የሃይል መሰረተ ልማቶችን ማውደም ስለሚያስከትለው አደጋ በአገር አቀፍ ደረጃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ጀምሯል። ከወራት በፊት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የተፈጸሙ ዝርፊያዎች በሃገሪቱ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የሃይል መቆራረጥ አስከትሏል።", "‘እጅ የበዛበት’ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከሰሞኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር ተያይዘው በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት ዕጣው ውድቅ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል። በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነውና ውዝግብ ባስከተለው ዕጣ ውስጥ መሳተፍ የነበረባቸው 79 ሺህ የሚሆኑ ተመዝጋቢዎች ቢሆኑም፣ በድብቅ የተዘጋጁ 172 ሺህ ያህል ሰዎች በዕጣው ውድድር ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርገዋል ተብሏል። በዚህም 93 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ተገቢ ባልሆነ መንገድ የጋራ መኖሪያ ቤት ለማግኘት በተዘጋጀው ዕጣ ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል። ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ይህ የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ ቤቶች ግንባታ እና ቤቶቹን የማስተላለፍ ሂደት በተለይም ዕጣ አወጣጡ ጋር ተያይዞ ከቅሬታዎች፣ ወቀሳዎችና ሐሜቶች ነጻ ሆኖ አያውቅም። የቤቶቹ ግንባታ ጥቃት፣ ግንባታቸው እና መሠረተ ልማቶቻቸው ያለመሟላት በየጊዜው የሚነሳ ጉዳይ ቢሆንም፣ በቤት ችግር እየተንገላታ ዕድሉ ይደርሰኛል ብሎ የሚጠብቀው ነዋሪ ዋነኛው ቅሬታ ግን ቤቶቹን የማስተላፍ ሂደቱ ወይም ዕጣው ሆኖ ቆይቷል። ከዚህ በፊት በነበሩት ሂደቶች ምዝገባው ውስጥ ያልተካተቱ ሰዎች በባለሥልጣንት ትዕዛዝ ቤቶቹ እንዲሰጣቸው ሲደረግ መቆየቱን ዘወትር የሚነሳ ጉዳይ ነው። በግንባታ ዕቃዎች መወደድ ምክንያት እና ግንባታዎችን ለማከናወን ባጋጠመ የገንዘብ ችግር ምክንያት በሚፈለገው መጠንና ፍጥነት መከናወን ያልቻለው የጋራ ቤቶች ግንባታ በርካቶች ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓል። በዚህ መካከል የከተማው አስተዳደር ተጠናቀዋል ያላቸውን ከ25 ሺህ በላይ ቤቶችን ይፋዊ በመሆነ ሂደት ለተመዝጋቢዎች ሊያስተላልፍ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አሳውቆ ነበር። ይህም በቤት ችግር በእጅጉ እየተፈተነ ላለው የከተማው ነዋሪ አንዳች ተስፋን አጭሮ በጉጉት እንዲጠብቅ አድርጎታል። አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም. ለ20/80 እና ለ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ዕጣው በወጣበት ወቅት፣ ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት የከተማው አስተዳደር ዕጣው የሚወጣበት ሂደት ከአድልዎ ነጻ እንዲሆን የሚያደርግ የቴክኖሎጂ ሥርዓት መዘርጋቱን ተናግረው ነበር። ነገር ግን ከንቲባዋ እዳሉት ሳይሆን የዕጣ ማውጣቱ ሂደት ችግር እንደነበረበት ቅሬታ መቅረብ የጀመረው ብዙም ሳይቆይ ነበር። አስተዳደሩም ጥቆማዎች መድረሳቸውን ተከትሎ በአስቸኳይ የማጣራት ሥራ እንዲካሄድ ተደርጎ፣ የዕጣ ማውጣት ሂደቱ ተዓማኒነት የሌለው ስለነበረ ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንዲሆን ተወስኗል። የአዲስ አበባ ከንቲባዋ ከ14ኛው ዙር የዕጣ ማውጣት ሂደት ጋር በተገነናኘ የተከሰተውን ችግር “የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፣ ድርጊቱም አመራር የመራው ወንበዴ ነው” በማለት ሁኔታው የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት  ጭምር የተስተዋለበት እንደነበር ተናግረዋል። የዚህ ስራ ሌላው አላማ መንግሥት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው በማለት ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡ በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን ህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፡፡ ህዝቡን መታደግ ችለናል፡፡ ለከተማው አስተዳደሩ የዕጣ ማውጣት ሂደቱን በተመለከተ የቀረበው ሪፖርት ሥርዓቱ አስተማማኝ እንደሆነ ነው። በተጨማሪም የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ማረጋገጫ እንደሰጠው ቢነገርም፣ ተቋሙ ሕጋዊ በሆነ ደብዳቤ ማረጋገጫ እንዳልሰጠ በምርመራው ተደርሶበታል። ከንቲባዋ እንዳሉት ለዕጣው ሂደት ግብአት የሚሆኑ መረጃዎች (ዳታ) ለቀናት በሰዎች አጅ መቆየታቸውና ይህም የሆነው በኃላፊዎች ትዕዛዝ መሆኑን አመልክተዋል። ይህ በግለሰቦች እጅ የገባው ወሳኝ መረጃ ቤት ለማግኘት የሚጠበቀውን ቁጠባ ያቋረጡ እና በዚህ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ጭምር እንዲካተቱ ዕድልን ፈጥሯል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው እንዳሉት፣ ይህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተመዝጋቢዎች በዕጣ ለማስተላለፍ በከተማው አስተዳደር ሥራ ላይ የዋለው ሥርዓት በርካታ ችግሮች አሉበት። በዚህም ሥርዓቱ ተመሳሳይ ሶፍትዌሮችን ለማልማት የሚያስፈልጉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያልጠበቀ መሆኑን አመልክተው፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን “ሦስቱን አካላት፤ አልሚውን፣ ተጠቃሚውን እና አረጋጋጩን አካላት የቀላቀለ እንዲሁም ለምዝበራ ያጋለጠ ነው” ብለዋል ዶ/ር ሸመቴ። ጨምረውም ለዚህ የዕታ ማውጣት ሂደት ግብአት የመሆነው መረጃ (ዳታ)፣ ከእጅ ንክኪ ነጻ መሆን የሚጠበቅበት ቢሆንም፣ ነገር ግን እጅ በዝቶበት እንደነበረ ተገልጿል። ባለሙያዎችም እንዳሉት ዕጣውን ለማውጣት ጥቅም ላይ የዋለው ሥርዓት ሲዘጋጅ ተገቢውን መንገድ ያልተከተለና ሁሉም ሂደት በአንድ ሰው የተሰራ እንደሆነ አመልክተዋል። በሂደቱም ቤት ለማግኘት ተመዝግበው የሚጠበቅባቸውን ገንዘብ እየቆጠቡ ለዕጣ ብቁ የሆኑ ነዋሪዎችን የሚመለከተው ከባንክ እና ከቤቶች ልማት የተገኘው መረጃ የአያያዝ ችግር የነበረበትና ለውጥ ለማድረግ የተጋለጠ እንደነበር ተገልጿል። የመረጃ መዛባት በተፈጸመበት ኮምፒውተር ላይ በተደረገው ምርመራ የተፈጸሙ ሕገወጥ ድርጊቶች እንዳይታወቁ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥንቃቄዎች መደረጋቸው የተደረሰበት ሲሆን፣ በተጨማሪም መረጃን ማጥፋት፣ መጨመር እና ማዘዋር ድርጊት መፈጸሙ ተረጋግጧል። በዚህ ተፈጸመ በተባለው “የቴክኖሎጂ ውንብድና” በአጠቃላይ ለውድድር ብቁ ናቸው ተብለው የተገለጹት 79 ሺህ የሚሆኑ ተመዝጋቢዎች የነበሩ ሲሆን፣ በድብቅ የተዘጋጁ 172 ሺህ ያህል ሰዎች ለዕጣው ዝግጁ ሆነው ነበር። በዚህም 93 ሺህ ተገቢ ያልሆኑ ሰዎች በዕጣው መካተታቸው ተገልጿል። በሕገወጥ መንገድ መረጃወቸው በዕጣው ውስጥ ተካተው ከተገኙት ውስጥ ደግሞ በባንክ የቆጠቡትን ገንዘብ ቀድመው አውጥተው የተዘጉ ተመዝጋቢዎች፣ የአመዘጋገብ ችግር ያለባቸውና ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ጭምር ተካተው መገኘታቸውን በምርመራው የተሳተፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል። በሕገወጥ መንገድ በዕጣው ውስጥ እንዲካተቱ በተለያዩ መንገዶች የተዘጋጁ ሰዎች መረጃ ውስጥ እንዲካተት ብቻ ሳይሆን፣ ዕጣ ለማውጣት ጥቅም ላይ የዋለው ሥርዓት የሚፈለገውን ሰው ዕጣ እንዲያወጣ ተደርጎም  የተዘጋጀ መሆኑም ተመልክቷል። በዚህም የሚጠበቅባቸውን የቤት ቁጠባ በባንክ ሲያከናውኑ ከቆዩት ተመዝጋቢዎች መረጃ ውስጥ ያልተካተቱ ሰዎች በዕጣው አሸናፊ ሆነው መገኘታቸውም በምርመራ ተደርሶበታል።" ]
[ 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0, 0 ]
[ "የዋነኛው ክሪፕቶከረንሲ ዋጋ እያሽቆለቆለ ያለው ለምንድን ነው? ያለፉት ጥቂት ቀናት ለቢትኮይንም ሆነ ለክሪፕቶከረንሲ አስከፊ ጊዜ ነው። አሁን ላይ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 21 ሺህ 974 ዶላር ነው። ቢትኮይን ቀድሞ ከነበረው ዋጋ ጋር ሲነጻጸር ባለፉት አምስት ቀናት ብቻ 25 በመቶ አሽቆልቁሏል። ይህም ባለፉት 18 ወራት የተመዘገበው ዝቅተኛው ዋጋው ነው። ቢትኮይን በዘመኑ ያወጣው ከፍተኛ ዋጋ ባለፈው ኅዳር ወር ላይ የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም ዋጋው 70 ሺህ ዶላር የሚጠጋ ነበር። ባለሙያዎች እንደሚሉት ለዚህ ምክንያቱ በዓለም ላይ ያለው ሁኔታ ነው። በእርግጥ በዓለማችን ነገሮች ጥሩ መስለው የማይታዩት በክሪፕቶከረንሲው በኩል ብቻ አይደለም። በዓለም ዙርያ የምጣኔ ሃብት ቀውስ እያንዣበበ፣ የዋጋ ንረት እያሻቀበ፣ ወለድ እየጨመረ እና የኑሮ ውድነቱ እየናረ ነው። የአክሲዮን ገበያዎችም ብርክ ይዟቸዋል። የአሜሪካው ስታንዳርድ ኤንድ ፑርስ 500 የድርሻ ገበያ (ስቶክ ማርኬት) በቅርብ ጊዜ ከፍተኛ ከነበረው 20 በመቶ ቀንሷል። የድርሻ ገበያ ማለት ኩባንያዎች የኩባንያው የባለቤትነት ድርሻን ለገበያ የሚያቀርቡበት እና ሰዎችም ይህንን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነበት መጠን ድርሻቸውን መልሰው በመሸጥ ወይም ከትርፍ ክፍፍል ትርፋማ የሚያደርግ አሠራር ነው። ይህ የድርሻ ገበያ በመቀነሱም ትላልቅ ባለሃብቶች ሳይቀሩ ኪሳራ እየገጠማቸው ነው። ሌሎችም በርካታ ተራ ባለሃብቶችም በማንኛውም ነገር ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ያላቸው ዕድል አነስተኛ ሆኗል። በርካቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በዚህ ጊዜ እንደ ክሪፕቶከረንሲ ተለዋዋጭ እና እንዲህ ነው ተብሎ የማይተነበይ ነገር ላይ ማዋል ትልቅ አደጋ እንደሆነ ያስባሉ። ክሪፕቶከረንሲ፣ በገንዘብ ባለሥልጣናት ቁጥጥር የማይደረግበትና የማይጠበቅ ዲጂታል ገንዘብ ነው። በመሆኑም የቆጠቡትን ገንዘብ እርሱ ላይ ለማፍሰስ እየተጠቀሙበት ከሆነና ዋጋ ካጡበት አሊያም የዲጂታል ገንዘብ ማስቀመጫዎን ( ክሪፕቶ ዋሌት) ካጡት ገንዘብዎ ጠፍቷል ማለት ነው። ባለፈው ወር  ሁለት ብዙም የማይታወቁ ግን በጣም ትልቅ የሆኑ ዲጂታል ገንዘቦች ተንኮታኩተዋል። ይህም በአጠቃላይ በዲጂታል ገበያው ላይ ያለውን አመኔታ አሳጥቷል። በዚህም ምክንያት ያላቸውን ገንዘብ ለመሸጥ የሚወስኑ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በርካታ ሰዎች ቢትኮይናቸውን በሸጡ ቁጥር ደግሞ ያለው ዋጋ እየቀነሰ ይመጣል። ምክንያቱም ዲጂታል ገንዘቦችን ዋጋቸው እንዲዋዠቅ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ይህ በመሆኑ ነው። ዋጋው የሚወደደው የሚገዛ ሰው ሲበዛ እንጂ የሚሸጥ ሰው ሲበረክት አይደለም። ይህ ደግሞ በርካታ ሰዎች የቢትኮይን ዋጋ እየወረደ መምጣቱን በመመልከታቸው ያላቸውን እንዲሸጡ ገፋፍቷቸዋል። ዑደቱም በዚህ መልኩ ይቀጥላል። የፋይናንሻል ታይምስ ማርኬትስ አርታኢ ኬቲ ማርቲን፣ “ቢትኮይን እንደ ሌሎች ባህላዊ አሴቶች እርሱን ለመደገፍ የሚያስችል ሌላ ንግድ፣ የገቢ ፍሰት ወይም ሌሎች ነገሮች የሉትም” ይላሉ። ኬቲ አክለውም “ዋጋው ሰዎች ሊገዙ ያሰቡበት ዋጋ ብቻ ነው” ሲሉ የቢትኮይን ዋጋ የመሸጫ ሂሳቡ ላይ የተንጠለጠለ እንደሆነ አስረድተዋል። “በርካታ ሰዎች ተስፋ ቆርጠው ሸጠው ከወጡ፣ አበቃ። ምንም መቆሚያ የለም። ነገ በ10 ሺህ ዶላር ዋጋ መሸጡን የሚያስቆመው ምንም ነገር የለም” ብለዋል። በመሆኑም ባለፉት ጥቂት ቀናት ቢናንስ የተባለው ዓለም አቀፋዊው ትልቁ የክሪፕቶ መገበያያ መድረክ ለተወሰኑ ሰዓታት ቢትኮይንን እንዳይወጣ አድርጎ ነበር።  “ሁሉም ሰው ላያምን ቢችልም ይህንን ያደረግነው የገንዘብ ዝውውሩ በመቆሙ ነው” ብሏል። የክሪፕቶ አበዳሪ ሴልሲየስም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። ይሁን እንጂ እርምጃውን የወሰደው በቴክኒክ ችግር ሳይሆን በከፍተኛ የገበያ ሁኔታ እንደሆነ ገልጿል። አሁን ላይ ደግሞ የክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ፣ ኮይንቤዝ ሠራተኞቹን በ18 በመቶ መቀነሱን አስታውቋል። በሁኔታው የተደናገጡና ገንዘባቸውን ያፈሰሱ ባለሃብቶችም ቢትኮይናቸውን መሸጥ ጀምረዋል። የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት ቢትኮይን ያላቸው ሰዎች ይዘው መቆየት እና ሌሎች ደግሞ እንደገና መግዛት መጀመር አለባቸው። የክሪፕቶ አድናቂዎችም አዳዲስ ደንበኞችን ለማፍራት ርካሽ በመሆኑ ክሪፕቶ ለመግዛት ጊዜው አሁን እንደሆነ ይናገራሉ። ምክንያቱም ሁልጊዜም ቢትኮይን የሚሰራው በዚህ መልኩ ነው። የዋጋ መዋዠቁ ሁልጊዜም የሚያጋጥም እንጂ አዲስ ነገር እንዳልሆነ ተጠቃሚዎቹ ይገልጻሉ። በክሪፕቶ በአጭር ጊዜ ቱጃር የሆኑ ሰዎች ታሪክ እና የታዋቂ ሰዎች ገበያውን መቀላቀልም አዲስ ዲጂታል ገንዘብን ይስባሉ። ኤሎን መስክ ለክሪፕቶ ያለውን ፍቅር በትዊተር ገጹ አጋርቷል። መስክ በኤሌክትሪክ የሚሰራ መኪና ኩባንያው፣ ቴስላ ባለፈው ዓመት 1.5 ቢሊየን ዶላር ቢትኮይን ላይ አፍስሷል። ሆኖም የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በዩናይትድ ኪንግደም የኢንቨስትመንት አማካሪ ሆኑት አልታፍ ካሳም ስለክሪፕቶከረንሲ መስክ “እውነቱን ለመናገር፣ ደፋር ሰው ብቻ መግባት ያለበት ቦታ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ራዲዮ 5 ተናግረዋል። እውቁ የሆሊዉድ ተዋናይ ማት ዴመን፣ እአአ ጥቅምት 2021 ላይ “ገንዘብ ለደፋሮች ታደላለች” በሚል መልዕክት የክሪፕቶ ማስታወቂያ ሰርቷል። ማስታወቂያው በብሔራዊ የእግር ኳስ ሊግ ‘ሱፐር ቦውል’ ተለቅቆ በትዊተር እና በዩትዩብ 28 ሚሊየን ጊዜ ታይቷል። ሆኖም ማስታወቂያው በተለቀቀበት ወቅት ቢትኮይን የገዙት ‘ደፋሮች’ ምን አልባት አሁን ላይ ምንም ጥቅም እንዳላገኙ ላይሰማቸው ይችላል። አሊያም ደግሞ ደፋር በመሆናቸው የተጠቀሙት ገንዘብ እንደሌለ ሊረዱት ይችላሉ። ምክንያቱም ያኔ ቢትኮይን ዛሬ ከነበረው በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ዋጋ ነበረው።", "ክትባትና ውሃ አምራቹ ከእስያ ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነ ዞንግ ሻንሻን የእስያ ሀብታሞች ዝርዝርን በግንባር ቀደምነት መምራት ጀምሯል። ክትባት እና የታሸገ ውሃ ማምረቻ ባለቤት የሆነው ዞንግ፤ በዚህ ዓመት ሀብቱ ሰባት ቢሊየን ዶላር ጨምሯል። የሕንዱን ሙከሽ አምባኒ እና የቻይናውን ጃክ ማ በልጦም የእስያ ቁጥር አንድ ባለ ጸጋ ሆኗል። አጠቃላይ ሀብቱ ወደ 77.8 ቢሊየን ዶላር ይጠጋል። ይህም የዓለም 11ኛው ሀብታም እንደሚያደርገው የብሉምበርግ ቢሊየነር ኢንዴክስ ያሳያል። “ብቸኛው ተኩላ” በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ባለ ሀብት በጋዜጠኛነት፣ በእንጉዳይ እርሻና በጤናው ዘርፍም ሠርቷል። ሚያዝያ ላይ ክትባት አምራቹ ቤጂንግ ዋንታይ ባዮሎጂካል ተቋምን በቻይና የአክስዮን ገበያ አቅርቧል። ከሦስት ወራት በኋላ ደግሞ ኖንግፊ ስፕሪንግ የተባለውን ውሃ አምራች ኩባንያ ለሆንግ ኮንግ የአክስዮን ገበያ አቅርቧል። ከዚህ ቀደም የእስያ ቁጥር አንድ ሀብታም የአሊባባ መስራቹ ቻይናዊ ጃክ ማ ነበር። ኖንግፊ ስፕሪንግ ሆንክ ኮንግ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የአክስዮን ዋጋው ወደ 155% አድጓል። የኮቪድ-19 ክትባትን ከሚሠሩ አንዱ የሆነው ቤጂንግ ዋንታይ ባዮሎጂካል የሼር ዋጋው ከ2,000% በላይ ደርሷል። እነዚህ ተደማምረው ዞንግ ሻንሻን ከእስያ ሀብታሞች ቁንጮው እንዲሆን አስችለውታል። ብሉምበርግ እንደሚለው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ ያለ ሀብት ንብረት ያፈራ ሰው በታሪክ አልታየም። በወረርሽኙ ወቅት የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስን ጨምሮ ብዙ ሀብታሞች ጥሪታቸው ጨምሯል። የሕንዱ አምባኒ ሀብት ከ18.3 ቢሊየን ወደ 76.9 ቢሊየን ዶላር አድጓል። በተቃራኒው የጃክ ማ ሀብት ጥቅምት ላይ ከ61.7 ቢሊየን ዶላር ወደ 51.2 ቢሊየን ወርዷል። አሊባባ በቻይና ባለሥልጣኖች ተደጋጋሚ ትንኮሳ ደርሶበታል። ድርጅቱ በምርቶች መካከል ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድር በማድረግ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን፤ አጋር ድርጅቱ አንት ግሩፕ ጥቅምት ላይ ከአክስዮን ሽያጭ ታግዷል። አብዛኞቹ የቻይና አዳዲስ ቢሊየነሮች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው። በሌላ በኩል በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ሁዋዌ፣ ቲክቶክ እና ዊቻትን በተመለከተ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የቻይና የአክስዮን ሽያጭ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳርፏል።", "አርጀንቲና በወረርሽኙ የተጠቁትን ለመደጎም የናጠጡ ኃብታሞቿ ላይ ግብር ጣለች አርጀንቲና አገሯ በሚገኙ የናጠጡ ኃብታሞች ላይ ለየት ያለ ግብር ጥላለች። ግብሩ ለኮሮናቫይረስ የሚያስፈልጉ የህክምና ቁሳቁሶች ግብዓትና በወረርሽኙ ምክንያት ክፉኛ ለተጠቁት ኑሯቸውን መደጎሚያ እንዲሆን ነው። የምክር ቤቱ አባላት \"የሚሊዮነሮች ግብር\" ብለው የጠሩት በአንዴ የሚከፈል ገንዘብ ሲሆን በዚህ ሳምንት አርብም 42 ለ 26 በሆነ የድምፅ ብልጫም ፀድቋል። በዚህም መሰረት ከ200 ሚሊዮን ፔሶ (2.5 ሚሊዮን ዶላር) ኃብት ያከማቹ ግለሰቦች መክፈል አለባቸው። በአገሪቱ ይህ የገንዘብ መጠን ያላቸውም ወደ 12 ሺህ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል። አርጀንቲና በወረርሽኙ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ ስትሆን እስካሁን ባለውም መረጃ 1.5 ሚሊዮን በቫይረሱ ሲያዙ 40 ሺህ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የህዝብ ቁጥሯ 45 ሚሊዮን ብቻ የሆነው አርጀንቲና በወረርሽኙ በሚሊዮኖች በተያዙ ተርታ አምስተኛ ደረጃን ይዛለች። ከህዝብ ቁጥሯ ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከሚሊዮን በላይ ካስመዘገቡ ትንሿ አገር አድርጓታል። ወረርሽኙን ለመግታት ያስቀመጠቻቸው መመሪያዎች ከፍተኛ ተፅእኖን አሳርፈዋል። በስራ አጥነት፣ በርካታዎች በድህነት ወለል በሚኖሩባትና አገሪቷ ራሷ በብድር በተዘፈቀበችበት ሁኔታ መመሪያዎቹ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነዋል። አርጀንቲና ከ2018 ጀምሮም በምጣኔ ኃብት ድቀት ላይ ናት። የሚሊዮነሮችን ግብር ካረቀቁት መካከል አንዱ ህጉ 0.8 በመቶ የሚሆነውን ግብር ከፋይ ብቻ ነው የሚመለከተው ብለዋል። በአርጀንቲና ውስጥ ያሉት ሃብታሞች፣ ከአንጡራ ሃብታቸው 3.5 በመቶ እንዲሁም ከአገር ውጭ ያሉ አርጀንቲናውያን ደግሞ 5.25 በመቶ እንዲከፍሉ ውሳኔ ተላልፏል። ከግብሩ የተሰበሰበው ገንዘብም መካከል 20 በመቶ ለህክምና ቁሳቁሶች፣ 20 በመቶ ለጥቃቅንና አነስተኛ ነጋዴዎች፣ 20 በመቶ ለተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ፣ 15 በመቶ ለማህበራዊ ልማትና ቀሪው 25 በመቶ ደግሞ ለተፈጥሮ ነዳጅ ስራዎች እንደሚውል ኤኤፍፒ በዘገባው አስነብቧል። ግራ ዘመሙ ፕሬዚዳንት አልበርቶ ፈርናንዴዝ መንግሥት 300 ቢሊዮን ፔሶም ለማሰባሰብ እቅድ ይዘዋል። ሆኖም የተቃዋሚዎች ፓርቲ ቡድኖች በበኩላቸው ይህ የአንድ ጊዜ ግብር ሊሆን ስለማይችል የውጭ አገራት ኢንቨስትሮችን ፍራቻ ላይ ይጥላል በማለት ተችተዋል። የቀኝ ክንፍ ፓርቲ ጁንቶስ ፖር ኤል ካምቢዮ በበኩሉ የማይገባ ሲል የፈረጀው ሲሆን \"ነጠቃም\" ነው ብሎታል።", "በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናውያን ግላዊ መረጃ ተሰርቆ ለሽያጭ መቅረቡ አነጋጋሪ ሆኗል አንድ የበይነ መረብ መረጃ ሰርሳሪ ከቻይና የፖሊስ ተቋም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መረጃ መዝብሮ ለሽያጭ ማቅረቡን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ አንድ ቢሊየን ይደርሳሉ የተባሉ የቻይናውያን ግላዊ መረጃ ስርቆት ዜና ይፋ ከሆነ በኋላም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የሕዝቡ መረጃ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግለት አሳስበዋል። የበይነ መረብ መረጃ ሰርሳሪዎች (ሃከርስ) ሰርቀነዋል ያሉትን የቻይናውያንን መረጃ የሚገዛቸው ካለ ለመሸጥ ማስታወቂያ ካወጡ በኋላ ነው፣ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ሕዝባዊ ተቋማት “የመረጃ ደኅንነታቸውን እንዲያጠናክሩ” ጥሪ ያቀረቡት። ኋላ ላይ በተነሳ እና በሕገወጥ የበይነ መረብ መድረክ ላይ በወጣው ማስታወቂያ እንደተጠቀሰው ለሽያጭ የቀረቡት ግላዊ መረጃዎች ከሻንግሃይ ብሔራዊ ፖሊስ የተሰረቁ መሆናቸው ተገልጿል። የበይነ መረብ መረጃውን የሰረቀውና ለሽያጭ ያቀረበው ግለሰብ በእጁ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናውያን ስም፣ አድራሻ፣ የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር እና የሞባይል ቁጥራቸውን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎች እንዳሉት አመልክቷል። የበይነ መረብ መረጃ ደኅንነት ባለሙያዎችም ተሰርቀዋል ከተባሉት ግላዊ መረጃዎች ውስጥ ናሙናዎችን በመውሰድ ባደረጉት ማጣራት ስርቆቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ መረጃ 23 ቴራባይት ይሆናል ተብሎ የሚገመት ሲሆን፣ ይህም በ200 ሺህ ዶላር ለሽያጭ የቀረበ ትልቁ መረጃ ነው ተብሏል። ድርጊቱ ወንጀል በመሆኑ ማስታወቂያው ከተለጠፈበት ድረ ገጽ ላይ እንዲነሳ ተደርጓል። ነገር ግን ይህ ተሰረቀ ስለተባለው ግዙፍ ግላዊ መረጃ ክምችትን በተመለከተ የትኛውም የቻይና ባለሥልጣን አስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ፕሬዝዳንቱም ቢሆኑ ጉዳዩን በሚመለከት በቀጥታ ምንም አላሉም። ‘ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት’ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ዢ፣ ዜጎች ለሕዝባዊ አገልግሎቶች ግላዊ መረጃዎችን ሲሰጡ ደኅንት እንዲሰማቸው ለማድረግ ተቋማት “ለግላዊ መረጃዎች እና ለምስጢራዊ የተቋማት መረጃዎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደረጉ” አሳስበዋል። ተሰረቀ ስለተባለው ግዝፍ መረጃ ሽያጭን በተመለከተ የወጣውን የበይነ መረብ ማስታወቂያ ተከትሎ የገጹ ተቆጣጣሪዎች የሚከተለውን ጽሁፍ አስፍረው በኋላም ማስታወቂያውን አንስተውታል። “የተወደዳችሁ ቻይናውያን ተጠቃሚዎች፣ እንኳን ወደ መድረካችን በደህና መጣችሁ። ብዙዎቻችሁ ወደ እዚህ ገጽ የመጣችሁት ከሻንግሃይ ፖሊስ ባፈተለኩ መረጃዎች ምክንያት ነው። መረጃው ከዚህ በኋላ ለሽያጭ አይውልም፣ በተጨማሪም ከዚሁ ጉዳይ ጋር የሚያያዙ ርዕሶች በሙሉ ከገጹ ላይ እንዲሰረዙ ተደርገዋል” ብሏል። የድረ ገጹ ተቆጣጣሪዎች ጨምረውም ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው ሌሎች የቻይና መረጃዎች እጃቸው ላይ እንዳሉና ለሽያጭም ሊያቀርቧቸው እንደሚችሉ አሳውቀዋል። “ያለነው ቻይና ውስጥ አይደለም፣ ቻይናውያንም አይደለንም። ስለዚህም ለቻይና ሕጎች ተገዢ መሆን የለብንም” ሲሉ ስለማንነታቸው ድፍን ያለ ምላሽ ሰጥተዋል። በበይነ መረብ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚከታተለው ‘ዳርክትሬሰር’ የተባለው ቡድን እንዳለው ይህ የመረጃ ምዝበራ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል። ይህም ምናልባት በቻይናውያን መረጃ ላይ ተፈጽሟል በተባለው ስርቆት አማካይነት በተፈጠረው ትኩረት የተነሳሳ ነው የተባለ ሌላ የበይነ መረብ መረጃ መዝባሪ ተመሳሳይ የሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል። በዚህም የበይነ መረብ መረጃ ሰርሳሪው እዚያው ቻይና ውስጥ ከሚገኘው የሄናን ግዛት ብሔራዊ ፖሊስ የመረጃ ቋት የመዘበረው የ90 ሚሊዮን ሰዎች መረጃዎች እጁ ላይ እንዳለ ገልጿል። ነገር ግን ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ በበይነ መረብ ደኅንነት ባለሙያዎች አልተረጋገጠም። ባለሙያዎች ይህ ተሰረቀ የተባለው ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃ ጉዳይ ለቻይና ባለሥልጣናት ዋነኛ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ፣ የሽያጭ ማስታወቂያውን በተመለከተ በአገሪቱ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ማገዳቸውን በመጥቀስ ተናግረዋል። በዘርፉ ደኅንት ጉዳዮች ላይ የሚሰራው የ‘ፎሬንሲክ ፓዝዌይ’ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴብ ሌሪ እንደሚያምኑት፣ መረጃው ከፍተኛውን ክፍያ ላቀረበ ወገን ተሽጧል ወይም የበይነ መረብ ሰርሳሪዎቹ እንዲህ አይነት ግላዊ መረጃን የሚፈልጉ ወደ እነሱ እንዲመጡ ለማስተዋወቅ ተጠቀሙበት ዘዴ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ምክንያቱም “ድርጊታቸው የቻይና መንግሥት ባለሥልጣናትን ሊያስቆጣ እንሚችል ብዙም አላሳሰባቸውም” ብለዋል። ባለፈው ሚያዝያ ወር በይነ መረቦችን ሰብሮ በመግባት መረጃዎችን የሚመዘብረው ‘ራይድ ፎረምስ’ የተባለው ድረ ገጽ በአሜሪካው የፌደራል ደኅንነት መሥሪያ ቤት መሪነት በተካሄደ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ዘመቻ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲዘጋ ተደርጓል። በዚህም ፖርቱጋላዊው የድረ ገጹ መስራች እና አንድ ብሪታኒያዊ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። አሁን ቻይና ውስጥ ተሰርቋል የተባለው አይነት ከፍተኛ መጠን ያለው የግሰቦች ግላዊ መረጃዎች፣ ትክክለኛ ባለቤቶቹን አስመስሎ መልዕክት ለመላክ እና ሌሎች መጥፎ ድርጊቶችን በመፈጸም ወንጀለኞች ገንዘብ ለማግኘት ጥቅም ላይ ሊያውሉት ይችላል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቻይናውያን ግላዊ መረጃ መሰረቁን በተመለከተ የተለያዩ መላምቶች እየቀረቡ ሲሆን፣ በትክክል ይህን ያህል ግዙፍ መረጃ በሰርሳሪዎች እጅ ከገባ አስካሁን ካጋጠሙ የመረጃ ምዝበራዎች ሁሉ የላቀው ነው ተብሏል።", "ቦይንግ ከ737 ማክስ ጋር በተያያዘ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ ቦይንግ ስለ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዲዛይን ከአሜሪካ የደኅንነት እና ጥንቃቄ ባለሙያዎች መረጃዎችን በመደበቅ ለተመሰረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ተስማማ። የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ እንዳለው ከሆነ ኩባንያው \"ከግልጽነት ይልቅ ትርፍን\" አስቀድሟል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በኢትዮጵያ እና በኢዶኔዢያ ተከስክሶ የ346 ሰዎች ህይወት አልፏል። ቦይንግ ለመክፈል ከተስማማው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ በአውሮፕላኑ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ የሚከፋፈል ይሆናል። ቦይንግ እንዳለው ይህ ስምምነት ኩባንያው \"ያለበት ጉድለት\" ምን ያህል መሆኑን ያሳያል። የቦይንግ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ዴቪድ ካልሁን እንዳሉት \"ወደ እዚህ ስምምነት መግባታችን ትክክለኛው ነገር እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ፤ ይህም ከእሴቶቻችን እና ከሚጠበቅብን ምን ያህል ወደ ኋላ መቅረታችንን ያሳያል።\" \"ይህ ስምምነት ሁላችንንም የሚያስታውሰን ለግልጽነት የገባነው ግዴታ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ፤ እንዲሁም አንዳችንም እንኳን እርሱን ሳናሟላ ብንቀር መዘዙ የከፋ መሆኑን ነው።\" የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ እንዳለው ከሆነ የቦይንግ ባለስልጣናት በኢንዶኔዢያ እና በኢትዮጵያ ለአውሮፕላኑ መከስከስ ምክንያት ስለሆነው ኤምካስ የተባለው አውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት ላይ ስላለ ለውጥ መረጃ ደብቀዋል። ይህ ውሳኔ የሚያሳው የአውሮፕላን አብራሪው ስልጠና መመሪያ ስለሥርዓቱ በቂ መረጃ አለመያዙን፣ ይህም በተሳሳተ መረጃ የአውቶማቲክ ሥርዓቱ የአብራሪውን ውሳኔ እንደሚሽረውና፣ ይህም አውሮፕላኑ ከማኮብኮቢያው በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አፍንጫውን አዘቅዝቆ ቁልቁል እንዲምዘገዘግ እንደሚያደርገው ነው። ቦይንግ ከምርመራ ባለሙያዎች ጋር ለስድስት ወር ያህል ትብብር አለማድረጉን የፍትህ ቢሮው ጨምሮ ተገልጿል። \"በላየን አየር መንገድ በረራ 610 እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 አውሮፕላኖች ላይ የደረሰው አሳዛኝ አደጋ፣ በዓለማችን ቀዳሚ የንግድ አውሮፕላኖች አምራች የሆነው ኩባንያ ሠራተኞች የማጭበርበር እና ማታለል ባሕሪያቸውን አጋልጧል\" ያሉት ደግሞ ረዳት ተጠባባቂ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዴቪድ በርንስ ናቸው። \"የቦይንግ ሠራተኞች 737 ማክስ አውሮፕላንን በሚመለከት መረጃን ከተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት በመደበቅ፣ ስህተታቸውን ለመሸፋፈን በመተባበር ከደኅንነት ይልቅ ትርፍን አስቀድመዋል\" ብለዋል። ኩባንያው ሊከፍል ከተስማማው አብዛኛው ገንዘብ፣ 1.7 ቢሊዮን ዶላሩ ለተጎጂ ቤተሰቦች የሚሰጥ ሲሆን፣ የተወሰነውም ተከፍሏል ተብሏል። ኩባንያው 243.6 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈልም ተስማምቷል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሕይወታቸወን ላጡ ቤተሰቦች ጥብቅና የቆሙት ባለሙያዎች ግን ይህ የኩባንያው ውሳኔ የመሰረቱትን ክስ እንዲያቋርጡ እንደማያደርጋቸው ገልፀዋል። ጠበቆቹ አክለውም ሁሉም የኩባንያው 737 ማክስ አውሮፕላኖች ደኅንነት በገለልተኛ ወገን እስኪረጋገጥ ድረስ ወደ በረራ እንዲገቡ መፈቀድ የለበትም ብለዋል። የአሜሪካ ደኅንነት ተቆጣጣሪዎች ከታኅሣስ ወር ጀምሮ አውሮፕላኖቹን ለበረራ ዝግጁ ናቸው በማለታቸው ወደ ሥራ ተመልሰዋል።", "ዘግታችሁ የወጣችሁትን በር እንዳልተዘጋ የሚያሳስባችሁ የአእምሮ ሕመም - ኦሲዲ ምሥራቅ* ለዚህ ታሪክ ሲባል ስሟ የተቀየረ “ለሦስት ዓመታት የማስበውን ሁሉ እንድጽፍ አእምሮዬ ያስገድደኝ ነበር” ትላለች። እንቅልፍ እና እርሷ ተፋትተው ነበር የከረሙት። “ዝም ብዬ መጻፍ ነው። ደብተር፣ ወረቀት፣ ሞባይል ሁሉ ነገር ላይ እጽፋለሁ።” የምትጽፈው ነገር ለሚያነበው ሰው ትርጉም ላይሰጥ ይችላል። ማንኛውንም ነገር በአእምሮዋ ውስጥ ሰንዳ የያዘቸውን ወይም የመጣላትን ጥቃቅን ነገር ሁሉ ካልጻፈች ሰላም ይነሳታል። “ፀጉሬ ላይ ቅባት ተቀብቼ ጥሩ ነው ብዬ ካሰብኩኝ እጽፈዋለሁ።” ይህ የመጻፍ ጉትጎታ ግን አንድ ቀን ተገታ። “አንድ ቀን ለሊቱን ሙሉ ቁጭ ብዬ ስጽፍ አደርኩ፤ የዚያን ቀን ይህ ነገር የወጣልኝ ይመስለኛል።” ምሥራቅ ባይፖላር ዲስኦርደር በተባለ የአእምሮ ሕመም (በሁለት የተለያዩ የስሜት ጽንፎች መካከል መዋለል) እየተቸገረች እያለ ነው ይህ ዕክል የተጨመረባት። ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር) ይባላል ነገሮችን በተደጋጋሚ ለመስራት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ጎትጓች ስሜት መሰማት ነው። “በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው ያሳለፍኩት፤ አሁን በሕይወት መኖሬ በጣም ይገርመኛል፤ ሥራዬን ለቅቄ ነበር። ይህንን በራሴ መቆጣጠር ስላቃተኝ መልሶ ጭንቀት ውስጥ አስገብቶኛል።” ምሥራቅ ሕመሟን ለሌሎች መንገር አልፈለገችም። ምክንያቷ ደግሞ 'ማን ይረዳኛል' የሚል ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ደግሞ ይህ ሕመሟ እንደ አዲስ ተመልሶ አገረሸባት። “የዘጋሁትን በር እንዳልዘጋሁ ይሰማኛል። በተለይ ደግሞ የእሳት ነገር ወደ ጭንቅላቴ እየመጣ ያስጨንቀኛል፤ ስቶቭ ለኩሼ የተውኩ ያህል ይሰማኛል። በዚህ ምክንያት ቀኑን ሙሉ ስብሰለሰል ነው የምውለው።” ምሥራቅ አእምሮ ውስጥ እየመጣ የሚያስጨንቃት ጎትጓች ሃሳብ፣ ሕመም መሆኑን ሳታውቅ ለረዥም ጊዜ ቆይታለች። ይህ ጉዳይ ሕመም እንደሆነ ያወቀችው በቴሌቪዥን ካገኘችው መረጃ የተነሳ ነው። ቢቢሲ ወደ ሕክምና አልሄድሽም ሲል ጠይቋት ነበር። “ሕክምና ለማግኘት ስሄድ አእምሮሽን ዝም አስብይው ይሉኛል። ግን እርሱን ማድረግ ብችል ኖሮ ለምን ወደ ሕክምና እሄዳለሁ” ትላለች። ሐኪም የተሰኘው እና በሕክምና ባለሙያዎች የተመሰረተው ማኅበራዊ ድረ ገጽ ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር)ን በተመለከተ ይህንን ይላል። “ኦሲዲ በአጭሩ ሲገለጽ ጥርጣሬ የሚፈጥር የሚነዘንዝ ሀሳብና እና ሃሳብ ተከትሎ ለማርገብ የሚደረግ ተደጋጋሚ ድርጊት ነው” ሲል አስፍሯል። በዚህ የአእምሮ ሕመም ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሕመሙ በየትኛውም የእድሜ ክልል ያለ ሰው ላይ ሊከሰት ይችላል። የህመሙ መንስዔ ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት የሚታወቅ ነገር የለም። ዶክተር ዮናስ ባሕረጥበብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአእምሮ ሕክምና ክፍል መምህር ሲሆኑ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ደግሞ የአእምሮ ሕመም ሐኪም ናቸው። ሐኪሙ ይህንን ሕመም ሲገልፁት “ከእኛ ፍላጎት ውጪ፣ ወደ አእምሯችን የሚመጣ ሐሳብ ወይንም ደግሞ አንድን ድርጊት በተደጋጋሚ ለመፈፀም መፈለግ፣ በተግባርም ማዋልንም ይጨምራል” ይላሉ። ዶ/ር ዮናስ እንደሚሉት በዚህ የአእምሮ ሕመም የተያዙ ሰዎች ወደ አእምሯቸው የሚመጣውን ሐሳብ መቆጣጠር ካለመቻላቸው በተጨማሪ ያለፍላጎታቸው ወደ ጭንቅላታቸው የሚመጣ ነው። “በተጨማሪም ይህ ያለፍላጎታችን የሚመጣብን ሐሳብ ደስ የማይል እና የሚያስጨንቀን ሊሆን ይችላል” ሲሉ ያክላሉ። በልጅነታቸው ሥነ ልቦናዊም ሆነ አካላዊ ጥቃት ወይንም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሲጎለምሱ ለዚህ ሕመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ይናገራሉ። “አንዳንድ ሰዎች ወደ አእምሯቸው የሚመጣ ተደጋጋሚ ሃሳብ ብቻ ሊኖራቸው ይችላል። ሌሎች ደግሞ አንድን ነገር ደጋግሞ የመፈፀም ጠንካራ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል። ያንንም በመፈፀም ለአጭር ጊዜም ቢሆን እፎይታ ያገኙ ይመስላቸዋል” ይላሉ። ዶ/ር ዮናስ ይህንን በምሳሌ ሲያስረዱ፣ “አንድ ሰው በሃሳቡ እጅህ ላይ ጀርም ወይንም ደግሞ እጅህ ቆሻሻ ነው የሚል ነገር ይመጣበታል። ይህም አንዴ እና ሁለቴ ሳይሆን በተደጋጋሚ ስለሚመጣበት እጁን ንፁህ እንደሆነ ቢያውቅ እንኳ በቀን እስከ 30 ጊዜ ሊታጠብ ይችላል።” “ደምህ ውሰጥ ኤችአይቪ አለ የሚል ሃሳብ የሚመጣባቸው ሰዎች አሉ። ያ ሰው ተመርምሮ በሽታው በደሙ ውስጥ እንደሌለ ቢያውቅ እንኳ ይህንን ተደጋጋሚ ሀሳብ ግን ማቆምም ሆነ ማቋረጥ አይችልም።” ዶ/ር ዮናስ እንደሚሉት ይህ ኦሲዲ የተባለ የአእምሮ ሕመም ሥራ እየሰራን ወይንም በየትኛውም የሕይወታችን እንቅስቃሴ፣ በመካከል ሊመጣብን ስለሚችል የምንሰራውን ወይንም ድርጊታችንን አቁመን በሃሳቡ ልንያዝ እንችላለን። “እኛ የማንፈልገው፣ ፈጣሪያችን የሚያሳዝን ሃሳብ ወደ አእምሯችን ይመጣል፤ ማስቆም አልቻልንም ብለው ለሕክምና ወደ እኛ ይመጣሉ” ሲሉ ባለሙያው ከልምዳቸው ይናገራሉ። ዶ/ር ዮናስ ይህ ሁኔታ ሕክምና ሊያስፈልገው ደረጃ ላይ የሚደርስበት ዕድል ስላለ ምልክቶቹን መረዳት አስፈላጊ ነው ይላሉ። ከዚህ ውጪ ግን ይህ ሁኔታ እንደ ባህርይ ብቻ ያላቸው ሰዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሰሩ ይሆናሉ ይላሉ። “የሂሳብ ባለሙያዎች፣ በተደጋጋሚ የማጣራት እና የማረጋጋጥ ባሕርይ ስላላቸው ስሌት አይሳሳቱም። ሌሎች እንደ ፓይለት እና ሜካኒክ ዓይነት ሥራዎችም ከፍተኛ ጥንቃቄ ስለሚፈልጉ ይህንን ዓይነት ባሕርይ ያላቸው ሰዎች በእነዚህ ሙያዎች ልህቀትን ሊያሳዩ ይችላሉ።” አክለውም ይህ የኦሲዲ ሕመም በራሱ ወደ ሌላ ከባድ የአእምሮ ሕመም ባይቀየርም፣ ነገር ግን ወደ አእምሯችን የሚመጣ ተደጋጋሚ ሃሳብ እና የምንፈጽመው ተደጋጋሚ ድርጊት መልሶ ሊያስጨንቀን ወይንም ደግሞ ድባቴ ሊያመጣ እንደሚችል ዶ/ር ዮናስ ይገልጻሉ። ለዚህ ሕመም የሚሰጠው ሕክምና በቂ አለመሆኑን የምታስረዳው ምሥራቅ፣ “በሩን ክፍቱን አድርጌ ብሔድ፣ ሊፈጠር የሚችለው ክፉ ነገር ምን ሊሆን ይችላል ብዬ በማሰብ፣ ሃሳቡን ለማስቆም እጥር ነበር። ነገር ግን መጨረሻ ላይ ስላልቻልኩኝ መድኃኒት መውሰድ ግድ ሆነ” ትላለች። አሁን በፀሎት እና በተሰጠኝ መድኃኒት ለውጥ እያሳየሁ ነው ስትል የምትናገረው ምሥራቅ፣ ለሕመሟ የተሰጣት መድኃኒት መጀመሪያ አካባቢ ሕመሟን አብሶባት እንደነበር ታስታውሳለች። “በዚህ ምክንያት መድኃኒቱን ከሁለት ጊዜ በላይ ቀይሬያለሁ።” በዚህ ሕመም ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚሰጣቸው የተለያየ ዓይነት ሕክምና አለ። አንዱ የሥነ ልቦና የምክር አገልግሎት ሲሆን በዚህም ሳይፈልጉት የሚመጣባቸውን ሃሳብ ሊቆጣጠሩ የሚችሉበትን ዘዴዎች ይማራሉ። ሁለተኛው ደግሞ አእምሮ እና ሰውነት እንዲፍታታ የማድረግ ሕክምና ነው። “ለምሳሌ ሜዲቴሽን (አርምሞ)፣ እንደ ዮጋ ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ማሳጅ ማድረግ” ናቸው። ከእነዚህ ባሻገር ደግሞ በሽታውን ሊቆጣጠረው የሚችለው መፍትሔ ለሕመሙ የተዘጋጀውን መድኃኒት መውሰድ ነው። እነዚህ የሕክምና ዓይነቶች የሰውየው የሕመም ዓይነት እና ደረጃ ላይ በመመስረት ከበሽታው እንዲድን ሊያደርጉ ይችላሉ ይላሉ ዶ/ር ዮናስ። አሁን እየተሻላት እንደሆነ የምትናገረው ምሥራቅ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ምልክቶችን ካዩ በፍጥነት ወደ ሕክምና እንዲሄዱ ትመክራለች።", "'ባሌ አጫሽ ነበረ፣ በእሱ ምክንያት ካንሰር ያዘኝ' “በአፍንጫዬ መተንፈስ አልችልም። የምተነፍሰው ‘ስቶማ’ በሚባልና አንገቴ ላይ በሚገኝ ቀዳዳ አማካይነት ነው’’ ይላሉ የ75 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋዋ ናሊኒ ሳትያናርያን። ናሊኒ በህይወታቸው እንድም ቀን ሲጋራ አጭሰው አያውቁም። ነገር ግን ላለፉት 33 ዓመታት ባለቤታቸው ከሚያጨሱት ሲጋራ የሚመጣ ጭስ ሲተነፍሱ ኖረዋል። ባለቤታቸው ሕይወታቸው ካለፈ ከአምስት ዓመታት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2010 ላይ ናሊኒ ካንሰር እንዳለባቸው ተነገራቸው። “ባለቤቴ አጫሽ ነበር። የእሱ ሲጋራ ማጨስ እኔን ይሄን ያክል ይጎዳኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ለእሱ ጤና ነበር የምጨነቀው። ሁሌም ሲጋራ ማጨሱን እንዲያቆም ነበር የምነግረው። ነገር ግን ሲጋራ ማጨሱን አልተወም ነበር” ይላሉ በሕንዷ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሀይድራባድ የሚኖሩት ናሊኒ። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ሲጋራ በየዓመቱ እስከ 8 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ይገድላል። ከእነዚህ መካከል ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ሲጋራ አጫሽ አይደሉም። አብዛኞቹ በዙሪያቸው የሚገኙ ሰዎች ሲጋራ አጫሾች የሆኑ ናቸው። በርካቶችም በዚሁ ምክንያት ለተለያዩ ሕመሞች እየተጋለጡ ነው። በየዓመቱ ግንቦት 23 የዓለም የፀረ ትንባሆ ቀን ነው። ናሊኒ በአንድ ወቅት ለልጅ ልጃቸው ታሪክ እያጫወቷት እያለ ነበር ድንገት የድምጻቸውን መቀየር ያስተዋሉት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ደግሞ በትክክል አንዳንድ ድምጾችን ማውጣት እያቃታቸው መጣ። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ደግሞ መተንፈስ ጭምር ከባድ እየሆነ መምጣት ጀመረ። ናሊኒ ወደ ህክምና ቦታ ሲሄዱ ያልጠበቁትን ዜና ሰሙ። ካንሰር እንዳለባቸውና በቀዶ ሕክምና ጉዳቱን መቀነስ እንደሚቻል ተነገራቸው። በቀዶ ሕክምናውም ድምጽ የሚያወጣው የጉሮሯቸው ክፍልና የታይሮይድ ዕጢያቸው እንዲወገዱ ተደረገ። “ከሕክምናው በኋላ መናገር አልቻልኩም። በጣም የሚያሳዝን አጋጣሚ ነበር። ዶክተሮቹ የቀድሞ ድምጼን ደግሜ ማግኘት እንደማልችል ነገሩኝ።” የናሊኒ የልጅ ልጅ የሆነችው የ15 ዓመቷ ጃናኒ ተጨዋች የሆኑት አያቷ ላይ የሆነውን ነገር በደንብ ታስታውሳለች። “ካንሰር እንዳለባት ሲነገራት ለረጅም ጊዜ እኛ ጋር አልነበረችም። ተመልሳ ስትመጣ የአራት ዓመት ልጅ ነበርኩ። ሆዷ አካባቢ ቱቦ ነገር ተለጥፎባት ነበር። ቤታችንን ቶሎ ቶሎ ማጽዳት ነበረብን። አያቴ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንደነበረች በደንብ አይገባኝም ነበር” ትላለች። ናሊኒ በወቅቱ የነበረን ጥሩ ሕክምና ስላገኙ ከጊዜ በኋላ ተመልሰው መናገር ቻሉ። ነገር ግን በተለያዩ መርጃ መሳሪያዎች በመታገዝ ነው ድምጽ የሚያወጡት። “ይሄ ካንሰር የያዘኝ በባለቤቴ ማጨስ ምክንያት ነው” ይላሉ ናሊኒ። “አጫሾች በጣም ጎጂ የሚባለውን የሲጋራውን ጭስ ወደ ውጪ ነው የሚተነፍሱት። በዚህ መሀል በጣም ተጎጂ የሚሆኑት በአቅራቢያቸው የሚገኙና ያንን ጭስ ወደውስጣቸው የሚያስገቡ ሰዎች ናቸው።” የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም አይነት ሲጋራዎች ጎጂ እንደሆኑ ሁሌም ያሳስባል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በማንኛውም የጤንነት ሁኔታ ላይ የሚገኙ ለጭሱ የሚጋለጡ ሰዎችም ተጎጂዎች ይሆናሉ። በዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ቢሮ የትንባሆ ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት አንጄላ ቺባኑ እንደሚሉት፣ የማያጨሱ ሰዎች ለአንድ ሰዓት ያክል ለሲጋራ ጭስ ቢጋለጡ በተለይ በጉሮሯቸው አካባቢ ቀላል የማይባል ጉዳት ይደርስባቸዋል። አክለውም “ከሌሎች ሰዎች ለሚመጣ የሲጋራ ጭስ የሚጋለጡ ሰዎች ከ700 በላይ ኬሚካሎችን ነው ወደ ውስጣቸው የሚያስገቡት። ከእነዚህ ኬሚካሎች መካከል ደግሞ 70 የሚሆኑት ለካንሰር የሚያጋልጡ ናቸው። እነዚህ ሰዎች በሳንባ ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከ20 እስከ 30 በመቶ ከፍ ያለ ነው” ይላሉ ባለሙያዋ። የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ 65 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት በየዓመቱ በሲጋራ ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ይገልጻል። ከዚህ በተጨማሪ ለሲጋራ ጭስ የሚጋለጡ ህጻናት በጆሮ ኢንፌክሽን የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። አንዳንዴ ባስ ሲል ደግሞ  የመስማት ችሎታቸውን ሊያጡ ይችላሉ። “ለሲጃራ ጭስ የተጋለጡ ህጻናት ለመተንፈሻ ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው ከ50 እስከ 100 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ ለአስም እንዲሁም ለድንገተኛ ሞት የመጋለጥ ዕድላቸውም ከፍተኛ ነው” ይላሉ አንጄላ ቺባኑ። ጥቂት የማይባሉ ሲጋራ የሚያጨሱም ሆነ የማያጨሱ ሰዎች ሲጋራ ማጨስ መከልከል አለበት ብለው እንደሚከራከሩ የዓለም ጤና ድርጅት ይገልጻል። “ሙሉ በሙሉ ከሲጋራ ነጻ የሆኑ አካባቢዎች መኖር ውጤታማ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይችላል። ሰዎች አጠገባችሁም ሆነ ልጆቻችሁ አካባቢ እንዲያጨሱ አትፍቀዱላቸው። ንጹህ አየር መተንፈስ ሰዎች ሰብአዊ መብት ነው” ይላሉ አንጄላ ቺባኑ። ነገር ግን ሲጋራ ማጨስን ሙሉ በሙሉ መከልከል በጣም ከባድ ነው። በዘርፉ ላይ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት የሲጋራው ኢንዱስትሪ በአውሮፓውያኑ 2021 ብቻ 850 ቢሊዮን ዶላር አንቀሳቅሷል። ይህ ቁጥር በአፍሪካ ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር ከያዘችው ናይጄሪያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ሁለት እጥፍ ነው። ጥናቱ እንደሚለው በቢሊየኖች ዶላሮችን መድበው የሚንቀሳቀሱት ከፍተኛ ትርፍ የሚያገኙ ትልልቅ ድርጅቶች ሲጋራ ማጨስን ለማስከልከል የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ጫና ያሳድራሉ። አይኑሩ አልቲቤቫ መሰል ሕጎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚሰሩ የሕንድ የሕዝብ እንደራሴዎች አንዷ ናቸው። በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስ እንዲከለከል ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረውም ነበር። እሳቸው እንደሚሉት ሕንድ ውስጥ በየዓመቱ ከሲጋራ ጋር በተያያዘ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው የሚያልፍ ሲሆን መሰል ቦታዎች ላይ ማጨስን መከልከል ደግሞ የሚደርሰውን ጉዳት እስከ 10 በመቶ ድረስ መቀነስ ይቻላል። ነገር ግን የሕዝብ እንደራሴዋ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር። “የሕዝብ እንደራሴዎቹ እራሳቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከትምባሆ ኢንዱስትሪው ጋር ግንኙነት አላቸው። ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስ የሚከለክለው ሕግ ወደተመረጡ ኮሚቴዎች ነበር የተመራው። ነገር ግን ኮሚቴዎቹ ሆነ ብለው እንዲያዘገዩት ነው የተደረገው። የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ቢሆን ከታክስ የሚገኝ ገቢ ላይ ቅናሽ እንደሚኖር በመግለጽ ሀሳቡን አልደገፈውም ነበር’’ ይላሉ። “አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል እኔንም ሆነ ቤተሰቤን ማጥቃት ጀምረው ነበር።” አይኑሩ አልቲቤቫ ላለፉት ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል ካደረጉ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2021 ላይ ሕንድ ውስጥ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስ ተከልክሏል። ነገር ግን ሥራው እዚያ ላይ አላበቃም። አይኑሩ ሲጋራ ማጨስ በጤና ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት እንዲሁም ህጻናት ላይ የሚያመጣውን መዘዝ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶችን ያስተባብራሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በትምባሆ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል በአውሮፓውያኑ 2005 ይፋ የተደረገው የትምባሆ ቁጥጥር ስምምነት ተጠቃሽ ነው። እስካሁን ድረስ 182 አገራት የዚህ ስምምነት አባል ለመሆን ፈርመዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት አገራት ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስን እንዲከለክሉም ይወተውታሉ። ሰዎች ንጹህ አየር የመተንፈስ መብታቸው እንዲጠበቅ ሲባል መሰል ሕጎች ተግባራዊ መሆን አለባቸው የሚሉት ደግሞ በትምባሆ ቁጥጥር ላይ የሚሰራው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩት ዶክተር ሜሪ አሱንታ ናቸው። “ከትምባሆ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ሞቶችን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ የሚችሉ በርካታ እርምጃዎች አሉ። በዋነኛነትም የትምባሆ ምርት ላይ ከፍተኛ ግብር ማስከፈል፣ ማስታወቂያዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ እንዲሁም ስለጉዳቱ ከፍተኛ ትምህርት መስጠት ይጠቀሳሉ።” ምንም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት የሲጋራ አጫሾች ቁጥር ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ነው ቢልም፣ አሁን ላይ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር 1.3 ቢሊየን ነው። ድርጅቱ እንዲመለው ከአስር ሰዎች አንዱ ሲጋራ የሚያጨስ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ የሚያጨሱት ቁጥጥር የማይደረግባቸውና በሕገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱትን ነው። ሕንድ ሃይድራባድ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ናሊኒ አሁን ላይ ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ አቅደዋል። አሁንም ድረስ ጉሮሯቸው ላይ ባለው ቀዳዳ አማካይነት ብቻ የሚተነፍሱት ናሊኒ በሲጋራ ምክንያት የማንም ሰው ሕይወት እንደዚህ ሊበላሽ አይገባም ይላሉ። ናሊኒ ወደ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ማንኛውም ሕዝብ ወደሚሰበሰብባቸው ቦታዎች በመሄድ ስለሲጋራ ጉዳት የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶችን የሚያከናውኑ ሲሆን፣ በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር በመጫወት ያሳልፋሉ። በባለቤታቸው ሲጋራ አጫሽነት ምክንያት ለካንሰር ተጋልጠው ለከባድ የጤና ችግር ቢዳረጉም በሟቹ ባለቤታቸው ላይ ምንም አይነት ቂም አልያዙም። \"በባሌ ላይ ፈጽሞ አዝኜበት አላውቅም። ባጋጠመኝ ነገር ላይ ማዘን ምንም የሚለውጠው ነገር እና የሚቀርፈው ችግር የለም። አሁን እኔ እውነታውን ተቀብዬ ስላጋጠመኝ የጤና ችግር ለመናገር ፈጽሞ አላፍርም” ይላሉ።", "የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ካንዬ ዌስት “ሳትጠራ እና ሳታሳውቅ” መጥተሃል ተብሎ ከስኬቸርስ ቢሮ እንዲወጣ ተደረገ ስኬቸርስ የተባለው የጫማ አምራች ኩባንያ ራፐሩ ዬ፣ በቀድሞ ስሙ ካንዬ ዌስት፣ “ሳያሳውቅ እና ሳይጋበዝ” መጥቷል በሚል ከኩባንያው ሕንጻ እንዲወጣ እንዳደረገው ገለፀ። ድርጅቱ አክሎም ከራፐሩ እና ዲዛይነሩ ዬ ጋር በጋራ የመስራት “ምንም ዓይነት ፍላጎት” የለኝም ብሏል። ይህ ዜና የተሰማው የጀርመኑ ስፖርት ትጥቅ አምራች አዲዳስ፣ ዬ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሰጠውን ፀረ አይሁዳዊ አስተያየት ተከትሎ ያለውን ግንኙነት ካቋረጠ በኋላ ነው። ቢቢሲ የዬን ወኪሎች አስተያየት ቢጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻለም። ስኬቸርስ በመግለጫው ዬ በቢሮው ከሌሎች ጋር ሆኖ ከመጣ በኋላ “ያልተፈቀደ የፊልም ቀረጻ በማድረግ ላይ ነበር” ብሏል። አብረውት መጥተው ከነበሩ ሰዎች ጋርም የተወሰነ ንግግር ከተደረገ በኋላ ሕንጻውን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል። ኩባንያው አክሎም “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሰጣቸውን ከፋፋይ ሀሳቦች የምንቃወም ሲሆን የፀረ አይሁዳዊ ወይንም ማንኛነውንም ዓይነት የጥላቻ ንግግሮች አንታገስም” ብሏል። በተጨማሪም “በድጋሚ አጽንኦት መስጠት የምንፈልገው ዌስት የመጣው ሳያሳውቅ እና ሳይጠራ ነው” ብሏል። ዬ የባይ ፖላር ዲዝኦርደር ታማሚ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትልልቅ ስም ካላቸው ድርጅቶች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ እየገባ ያለው የስራ ውል እየተቋረጠ ይገኛል። እነዚህ እርምጃዎች የዬን ገቢ ክፉኛ የሚጎዱት ሲሆን በቅርቡም ከፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ስር ስሙ እንዲወጣ ሆኗል። መጽሔቱ ዬ ከአዲዳስ ጋር ያለው የስራ ውል በመቋረጡ ብቻ ካለው አጠቃላይ የ1.5 ቢሊየን ዶላር ሀብት ወደ 400 ሚሊዬን ወርዷል ሲል አስፍሯል። ማክሰኞ ዕለት አዲዳስ ከዬዚ ብራንድ ጋር ያለውን ትብብር “የፀረ አይሁዳዊ እንዲሁም የትኛውም ዓይነት የጥላቻ ንግግርን አንታገስም” በማለት ውሉን ማቋረጡ ይታወሳል። አዲዳስ አክሎም ከአሁን ጀምሮ ምርቶቹ ከገበያ አንዲወጡ ይደረጋል ሲል አስታውቋል። ባለፈው ወር በፓሪስ የፋሽን ሳምንት ላይ “ኋይት ላይቭስ ማተር “ የሚል ቲሸርት ለብሶ በመገኘቱ አዲዳስ ጉዳዩን ማጤን ጀምሮ ነበር። ከቀናት በኋላም ራፐሩ በትዊተር ገፁ ላይ ፀረ አይሁዳዊ መልዕክት ያለው ጽሁፍ በማስፈሩ ወዲያው ከማህበራዊ ሚዲያው ታግዷል። ከዚህ ቀደምም የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ካንዬ ዌስት በታዋቂው ኮሜዲያን ትሬቨር ኖዋ ላይ በሰነዘረው ዘር ተኮር ስድብ ምክንያት ከኢንሰታግራም ለ24 ሰዓታት ታገዶ ነበር። አዲዳስ ተወዳጅ ከሆነው ዬ ብራንድ ጋር ያለውን ስምምነት በመሰረዙ ብቻ እኤአ በ2022፣ 217 ሚሊየን ፓውንድ ይከስራል።", "አንድ ውሻ በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዙን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ አንድ ውሻ ከባለቤቱቶቹ በተላለፈ የዝጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ መጠቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የበሽታው ስርጭት ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ራሳቸውን ከቤት እንስሳቶቻቸውም ጭምር ማግለል እንዳለባቸው የሚያሳይ እንደሆነም የጤና ሃላፊዎቹ አስታውቀዋል። ሌሎች እንስሳትን የመበከል አደጋን ለመቀነስ ቆሻሻን በጥንቃቄ ማስወገድ እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። ውሾች በሽታውን ወደ ሌሎች ውሾች ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፉ እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ እስካሁን እንደሌለም ባለሞያዎች ገልጸዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በቆዳ-ለቆዳ ንክኪ እና ሰዎች ጨርቆችን ጨምሮ አልጋ ወይም ፎጣ በቫይረሱ ​​​​ከተያዘ ሰው ጋር በጋራ ሲጠቀሙ የሚተላለፍ በሽታ ነው። በአሁኑጊዜ በዓለም ዙሪያ ወደ 35,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን አብዛኛዎቹ በአውሮፓ፣ በሰሜን እናበደቡብ አሜሪካ ይገኛሉ ። እስካሁን ከበሽታው ጋር በተያያዘ 12 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። የአለም የጤና ድርጅት ባለፈው ሃምሌ ወር ውስጥ ነበር የዝንጀሮ ፈንጣጣን አለማቀፍ የጤና አደጋ ሲል ያወጀው። የመጀመሪያው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ከሰው ወደ ውሻ የተላለፈው በፓሪስ ከተማ ሁለት አንድ ላይ በሚኖሩ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ቤት ውስጥ ነው። ግለሰቦቹ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ማሳየት ከጀመሩ ከ 12 ቀናት በኋላ ነበር በውሻቸው ላይም ምልክቶችን ማየት የጀመሩት። ባለሞያዎች ያደረጉት የዘረመል ትንታኔ እንደሚያሳየው ውሻውን ያጠቃው ቫይረስ ግለሰቦቹን ካጠቃው ጋር ቫይረስ ጋር ተመሳሳይ ነው። የውሻው ባለቤቶችም ውሻው አብሯቸው ሲተኛ እንደነበር ተናግረዋል። በአለም የጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምላሽ ሰጪ ቡድን ውስጥ የቴክኒካል ስራዎች መሪ የሆኑት ዶ/ር ሮሳምንድ ሉዊስ “ይህ ከዚህ በፊት ሪፖርት ያልተደረገ ብሎም ለመጀመሪያ ግዜ የመዘገበ ወደ ውሻ ያጋጠመ ስርጭት ነው ብለን እናምናለን’’ ብለዋል። በተቋሙ የድንገተኛ የጤና አደጋዎች ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ማይክ ራያን “ጉዳዩ ያልተጠበቀ አይደለም” ብለዋል። ነገር ግን በሽታው ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላው መዘዋወሩ እጅግ እንደሚያሳስባቸውም ተናግረዋል። አክለውም አንድ በሸታ ወደ አዲስ የእንስሳ ከተላለፈ በኋላ እንደሚላመድ ብሎም እና በውስጡም ወደ አዲስ ዝርያ እንዲለወጥ እድል እንደሚሰጥ ተናግረዋል። “ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋጠመ ስርጭት ነው። ስለሆነም ውሾች ሊበከሉ ይችላሉ ማለት ነው። ነገር ግን ውሻው ሌሎች ውሾችን ሊበክል ይችላል ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፋል ማለት አይደለም’’ ሲሉ የአለም የጤና ድርጅት የዓለም አቀፍ ተላላፊ በሽታዎች ስጋት ዝግጁነት ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሲልቪ ብሪያንድ ተናግረዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከል በመላው አለም ያለው የክትባት አቅርቦት እስካሁን ድረስ ውስን ነው። ባለፈው ሳምንት ብቻ በበሽታው ተይዘው ሪፖርት የተደረጉ ሰዎች ቁጥር በ 20 በመቶ ጭሯል። ይህም ከሳምንት በፊት ከነበረው በ20 በመቶ ብልጫ አለው። እስካሁን አብዛኛው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሲታይ ወንድ የተመሳሳይ ጾታ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው።", "“ስለ አዕምሮ ጤና በግልፅ መነጋገር ለሁላችንም ጤንነት ነው” ያዕቆብ ተክዔ ያዕቆብ ተክዔ (ዶ/ር) በአሜሪካው ፔንሲልቬንያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ባለሙያ ነው። ያዕቆብ በትምህርቱ ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት፣ በሥራው ቴራፒስትና የሙሉ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነው። ያዕቆብ ተውልዶ ያደገው በኤርትራ ሲሆን የድህረ ምረቃ ትምህርቱን ለመከታተል ከበቃበት ጊዜ አንስቶ የሥራ ዓለሙን እስኪቀላቀል ድረስ ኑሮው በአሜሪካ ነው። የያዕቆብ ሥራ የሚያተኩረው በስደትና በስደተኞች ላይ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከአፍሪካ፣ አብልጦም ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ለተሰደዱ ሰዎችን የአዕምሮ ጤና ድጋፍ እና ክትትል ያደርግላቸዋል። ያዕቆብ ከባድ አደጋ፣ የፆታ ወይም የወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል። ሥራው በይበልጥ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት መክበዱን የሚናገረው ያዕቆብ በነባር አዕምሯዊ ተፅዕኖዎች ላይ ተደርቦ ከወርሽኙ ጋር የመጡ የተለየያዩ ውጥረቶችንም ጭምር ለማቃለል ብዙ ሥራ መሠራት እንደነበረበት ይናገራል። ወረርሽኙ የጀመረበት ወቅት በተለይ ፍራቻ፣ መገለልና የመሳሰሉ ተያያዥ ችግሮች ስለነበሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያን በተለየ መልኩ እገዛ ያስፈልጋቸው እንደነበር ያስታውሳል። በስደተኞች ላይ ተዘውትረው ይታዩ የነበሩ የቋንቋ ቀርነቶች፣ የባህል ልዩነቶችና ከሃገሩ ማህብረሰብ ጋር የመዋሃድ ችግሮች ላይ ወረርሽኙ ያመጣው የመራራቅ፣ ያለ መጠያየቅና የብቸኝነት ኑሮ አዕምሮ ላይ ከበድ ያለ ተፅዕኖ እንደነበረው ገልጿል። ይህንንም ለመቅረፍ ከመንግሥት የሚመጡና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን፣ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሚናገሯቸው ቋንቋዎች እንዲደርሷቸው እናደሚያደርጉ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ወቅት ተናግሯል። በተጨማሪም ለአዕምሮ ጤናም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው በሚረዷቸው ቋንቋዎች እና መንገድ እንደሚያደርስ ይናገራል። ያዕቆብ እነዚህን እና ሌሎች ያሉ ችግሮች በሙሉ በጥሞና ካሰበባቸው በኋላ ሰዎች በቀላሉ፣ ሳይሳቀቁና ሰው አየን አላየን ሳይሉ መረጃዎችን የሚያገኙበትን መንገድ ማሰላሰል ጀመረ። \"በባህላችን ስለ አዕምሮ ጤንነት በግልፅ ማውራት ወይም መነጋገር ከባድ በመሆኑና በግልፅ የሚያወሩም ሰዎች መድልዖ ስለሚገጥማቸው በፈቃደኝነት እርዳታ ለማግኘት የሚጥሩ ኢትዮጵያውያን ወይም ኤርትራውያን የሉም። ይህ ደግሞ ችግሩን አያጠፋውም፣ ማለት ስለችግሩ ስላልተወራ ችግሩ ይሰወራል ማለት አይደለም። በተለይ የአዕምሮ ጤና መጓደል ደግሞ ሥር እየሰደደና እየተባባሰ የሚመጣ በመሆኑ ችግሩን እጥፍ ያደርገዋል። ለዚህም ነው መፍትሄ ማግኘት ፈልጌ የነበረው\" ይላል ያዕቆብ። ኢንተርኔት የበርካቶች ህይወት አካል በሆነት በዚህ ዘመን ቀላሉ መፍትሔ ዩቲዩብ መሆኑ የተገነዘበው ያዕቆብ፣ የራሱን ቻናል በመጀመር ማስተማር፣ አስፈላጊ መረጃዎችንና ምክሮችን ማስተላለፍ ጀመረ። እንደዚህ ማድረጉ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ቢያንስ ከቤታቸውም ሆነው መድልዖን ሳይፈሩ አስፈላጊውን እርዳታ ለማግኘት ያስችላቸዋል ብሎ አስቦ እንደሆነ ይገልፃል። \"በርግጥ አንድ ባንድ እያገኘሁ ጊዜ ወስደን እንደምረዳቸው ሰዎች ያህል በዩቲዩብ ጥልቀት ያለው እርዳታ ለማድረግ ይከብዳል። እንደዚያም ቢሆን ግን ዋና ዋና መልዕክቶችን ስለማስተላልፍበት ሰዎች ሳይሳቀቁ በእራሳቸው ጊዜ የሚጠቅሟቸውን የምክር አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ\" ይላል። ያዕቆብ በዩቲዩብ የሚያሰራጨው መልዕክት የሚኖረውን ጥቅም ሲያስረዳም \"አብዛኛውን ጊዜ ስሜታቸውንና አዕምሮዋቸው ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ነገሮችን አምቀው ስለሚይዙ በጊዜ ሂደት ጉዳቱ የከፋ ይሆንባቸዋል። ለዚህ ነው ሰዎች ቢያንስ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ማወቃቸው በእራሱ የመጀመሪያው እርምጃ የሚሆነው\" ይላል። አክሎም \"እንደ ኮቪድ ዓይነት ወረርሽኝ ደግሞ ሰዎችን ቤት እንዲቀመጡ የሚያደርግ ከሆነ ወይም የለመዷቸውን ማህበራዊ ስብስቦች በሚያስቀርባቸው ጊዜ ተፅዕኖው ይበዛባቸውና ነባር የአዕምሮ ችግሮችን ያባብስባቸዋል\" ይላል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰዎች በአእምሮ ጤና ላይ ያላቸው አመለካከት እየተስተካከለ እንደሆነ የሚናገረው ያዕቆብ፣ ከአምስት ዓመታት በፊት የግንዛቤ መፍጠሪያ ዘመቻዎች በሚያካሄድበት ወቅት የነበረው ምላሽና አሁን የሚሰጠው ምላሽ በጣም ልዩነት እንዳለው ይገልፃል። ያዕቆብ ከአምስት ዓመታት በፊት የነበረበትን መሰናከል በማስታወስ \" ስለ አዕምሮ በሽታዎች ግንዛቤ ለማስፋት በምሠራበት ወቅት ብዙ ሰዎች ዓላማዬን ይጠራጠሩት ነበር። እንደውም በርካታ ሰዎች የአዕምሮ በሽታ መኖሩን እራሱ እንደሚጠራጠሩ ይነግሩኝ ነበር\" ይላል። ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንዳያገኙ የሚያከለክሏቸው በማህበረሰባችን ሊገጥሟቸው የሚችለውን መገለል በመፍራት እንደሆነም ያስረዳል። በተጨማሪም \"የአዕምሮ ችግርን ብዙ ሰው በአንድ ጊዜ ሳይታሰብ እንደ ዱብ ዕዳ የሚወርድ ነገር ይመስላቸዋል። ነገር ግን በሂደትና ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጥረት፣ የመንፈስ ጭንቀት ሲደራረብ ካለበለዚያ በአግባቡና በተገቢው ጊዜ እርዳታ ሳይገኙ ሲቀር የሚከሰት ነው\" ይላል። እንደዚህም ሆኖ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙዎች ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነና ኮሮና ባይመጣ ኖሮ ሙሉውን የ2020ን ዓመት በተለያዩ የአሜሪካና የካናዳ ከተማዎች በመሄድ ንግግር እንዲያደርግና ለኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን እርዳታ እንዲሰጥ ተጠይቆ እንደነበር ይናገራል። \"የአዕምሮ ታማሚ ሲባል እርቃናቸውን እየሮጡ በድንጋያ ሰዎችን የሚያባርሩ ግለሰቦችን ነው ሰዎች በአዕምሮዋቸው የሚስሉት። ይህ ደግሞ በጣም የተሳሳተ አመለካከት ነው\" የሚለው ያዕቆብ አስረግጦ ማስረዳት የሚፈልገው \"የአዕምሮ በሽታ ወይም የአዕምሮ ጤና መጓደል የተለያየ መልክ፣ ዓይነትና መገለጫ\" እንዳለው ነው ይለናል። ከሁሉም በላይ \"በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በቀጣዮቹ የተወሰኑ ዓመታት የአዕምሮ ጤና መጓደል ወረርሽኝ የምናይ ይመስለኛል\" በማለት ይህንንም ለመከላከል በቅድሚያ ከወዲሁ ልናስስባቸው፣ ልንነጋገርባቸውና ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች መኖራቸውን ያስረዳል። አእምሮ ጤና መጓደልን በተመለከተ በዋነኛነት ልንከታተላቸው ከምንችላቸው ምልክቶች መካከል፡ እንደ ያዕቆብ ገለጻ እነዚህ ምልከቶች ቀድሞ ማወቅ \"እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በቶሎ እንድንደርስላቸው ያስችለናል\" ይላል። የአዕምሮ ጤና መጓደል ቋሚ አይደለም የሚለው ያዕቆብ፣ \"አካላዊ በሽታ ሲገጥመን ሆስፒታል/ክሊኒክ ሄደን እንደምንታከመው ሁሉ ለአዕምሯችንም ተመሳሳይ እንክብካቤ ማድረጋችን ተገቢ ነው\" ሲል ይመክራል። \"ለብዙ ሰዎች የአዕምሮ ጤና መሰናከል ቋሚ ችግር ይመስላቸዋል ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው። ምክንያቱም ማንኛውም ሰው በተለያየ ምክንያት የአዕምሮ ጤናው ሊስተጓጎል ይችላል\" በማለት ያብራራል ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን ለመርዳት ብዙ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ያለው ያዕቆብ ሥራው ገና ጅማሬው ላይ መሆኑን ይገልፃል። አክሎም የሰውን ግንዛቤ ከመጨመርና ከማሳደግ ባለፈ ደግሞ የቋንቋ ተግዳሮቱ ላይ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ይናገራል።", "ኮሮናቫይረስ፡ የአስትራዜንካን ክትባት ተጠቀሙ- የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የኮሮናቫይረስ መከላከያ የሆነውን አስትራዜንካ ክትባት ማገዳቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያንና ስፔይንን ጨምሮ ሌሎች አገራት የኦክስፎርዱ አስትራዜንካ ክትባት ደም መርጋት በተያያዘ ችግር አለበት በሚል ክትባቱ እንዳይሰጥ አግደውታል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ይላል። የድርጅቱ የክትባት ደህንነት ልሂቃንም በዛሬው ዕለት ተሰብስበው ስለ ክትባቱ ይመክራሉ ተብሏል። የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ ስለ ክትባቱ በዛሬው ዕለት የሚወያዩ ሲሆን በያዝነው ሃሙስም የደረሱበትን ማጠቃለያ ለህዝብ ያሳውቃሉ ተብሏል። ሆኖም ኤጀንሲው ክትባቱን ተጠቀሙ ብሏል። በአውሮፓ ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ ብሏል። ነገር ግን ባለሙያዎቹ እንደሚሉት በአጠቃላይ ከህዝብ ብዛቱ ጋር ሲነፃፀር የደም መርጋት ያጋጠማቸው ሰዎች ድንገተኛ መጨመር አላሳየም ይላሉ ። በአውሮፓ ህብረት አባላት አገራትና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው አስትራዜንካ አስታውቋል። እየተወሰዱ ያሉ ጥንቃቄዎች ይህንንም ተከትሎ የጀርመን ጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዕለት አስትራዜንካ ክትባት መስጠት በአስቸኳይ እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ክትባቱ የአዕምሮ ደም መርጋት ወይም ሴሬብራል ቬይን ቶርምቦሲስ ችግር ጋር መገናኘቱን አይተናል ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ጄንስ ስፋን እንዳሉት ውሳኔ \"ፖለቲካዊ\" እንዳልሆነ ነው። \"ሁላችንም ቢሆን ይህ ውሳኔ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት እንረዳለን። በቀላሉም የደረስንበት አይደለም\" ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ ውሳኔውን እስኪያሳውቅ ድረስ አገራቸው ክትባቱን ታግዳለች ብለዋል። \"ቀለል ያለ መመሪያ ነው ያለን፤ ሳይንስንና በዘርፉ ላይ ዕውቀት ያላቸውን የጤና ባለስልጣናት ምክር ነው የምንከተለው፤ ይህም የአውሮፓ ስትራቴጂ ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚጠቁም ይሆናል\" ብለዋል። የጣልያን መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ የሚደርስበትን ማጠቃለያ እጠብቃለሁ በማለት አግዳዋለች። የስፔን ጤና ሚኒስትር ካሮሊና ዳሪያስ በበኩላቸው ክትባቱ ለመጪው ሁለት ሳምንት ይታገዳል ብለዋል። አየርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ቡልጋሪያ፣ አይስላንድ፣ ስሎቬኒያ ክትባቱን በጊዜያዊነት ያገዱ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎና ኢንዶኔዥያ የክትባት መስጪያ ጊዜያቸውን አራዝመውታል። ኦስትሪያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራት ለጥንቃቄ ሲሊ ቢያግዱትም ቤልጂየም፣ ፖላንድና ቼክ ሪፐብሊክ ክትባቱን እየሰጡ ነው። የቤልጂየም ጤና ሚኒስትር ፍራንክ ቫንደንብራውኬ እንዳስታወቁት ቤልጂየም ካላት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ቁጥርን በማየት ክትባቱን አለመስጠት አትችልም ብለዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በበኩላቸው አስትራዜንካን ጨምሮ በአገሪቱ እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የጤና ባለስልጣናቱ ነግረውኛል ብለዋል።", "ዓለም ተስፋ የጣለበት የኦክስፎርድ የኮሮና ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ የመጨረሻ የክሊኒካል ሙከራ ላይ የነበረውና ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የቆየው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከመድሃኒት አምራቹ አስትራዜኔካ ኩባንያ ጋር እያበለጸጉት የነበረው የኮሮና ክትባት ነበር። ምርምሩ ለጊዜው ባለበት ይቁም ተብሏል። ምክንያቱ ደግሞ የክትባት ቅንጣቱን የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ ተሳታፊዎች ህመም ስላጋጠማቸው ነው። ይሁን እንጂ ግዙፉ የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ይህ የሚያደናግጥ ሳይሆን የሚያጋጥም ነው ይላል። ህመም የተሰማቸው ተሳታፊዎች ለምን ህመም እንደተሰማቸው ለማወቅ ጊዜ ይፈልጋል። የኦክስትፎርድና የአስትራዜኔካ የምርምር ውጤት የዓለም አገራት ትንፋሻቸውን ውጠው በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ነው። በዓለም ላይ በክትባት ሙከራ ውስጥ እያለፉ ካሉ ደርዘን ከሚሞሉ የምርምር ሥራዎች ሁሉ ይህ ግዙፉና ተስፋም የተጣለበት ነበር። ቀድሞ ለሕዝብ ይደርሳል፣ ዓለምን ይታደጋል ተብሎም ነበር። ይህ የኦክስፎርድና አስትራዜኔካ የጥምረት የክትባት ምርምር ምዕራፍ 3 ደርሶ ነበር። ይህም ማለት ዋናዎቹን የምዕራፍ 1 እና 2 አልፎ፣ ፈዋሽነቱ ተረጋግጦ በብዙ ቁጥር ሰዎች ላይ መሞከር የጀመረ ማለት ነው። በአሜሪካ፣ በዩኬ፣ በደቡብ አፍሪካና በብራዚል የሚገኙ 30ሺ ሰዎች ይህንን ክትባት እንዲወስዱ ተደርጎ ምን ዓይነት ምልክት እንደሚያሳዩ እየተጠበቀ ነበር። ምዕራፍ 3 የመድኃኒት ሙከራዎች በርካታ ሺህ ሰዎች የሚሳተፉባቸው ከመሆናቸው ባሻገር ዓመታትን ይወስዳሉ። አሁን ባለው የዓለም ጉጉት ግን አመታት ይጠበቃሉ ወይ የሚለው አጠያያቂ ነው። ቀጥሎ ምን ይደረጋል? እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥም በሕክምናው ዓለም አዲስ አይደለም። 3ኛ ምዕራፍ የደረሱ የመድኃኒት ሙከራዎች ተሳታፊዎች የተለየ ሕመም ሲያጋጥማቸው ለጊዜው እንዲቆሙ ይደረጋል። አሁን የሆነውም ይኸው ነው። ከዚህ በኋላ ገለልተኛ የተመራማሪዎች ቡድን በጉዳዩ እንዲገባ ይደረጋል። የተወሰዱ ጥንቃቄዎችን ከፈተሸ በኋላ ሁሉም ሂደቶች ትክክል ነበሩ ተብሎ ሲታሰብ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ሙከራውና ምርምሩ እንዲቀጥል ሊወስን ይችላል። \"እንዲህ ሰፊ በሆኑ ሙከራዎች በተሳታፊዎች ላይ ህመም መከሰቱ አዲስ ነገር አይደለም። ነገር ግን ገለልተኛ ወገን ሊያጣራው ይገባል\" ብለዋል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ምርምሩን ለጊዜው እንዲያቆም ሲደረግ ደግሞ ይህ የመጀመርያው አይደለም። ከተሞከረባቸው ሰዎች የተወሰኑት አሟቸው ሆስፒታል ሲገቡ ምርምሮች ሁሉ ባሉበት ይቆማሉ። ይህ የተለመደ አሰራር ነው ይላል፣ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ። እንዲያውም ምርምሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይቀጥል ሊባልም ይችላል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መድኃኒቱን ከኅዳር 3 ምርጫ በፊት አጥብቄ እፈልገዋለሁ ሲሉ ነበር።", "ሕንድ ፡ በአንድ ሆስፒታል ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ 10 አራስ ሕፃናት ሞቱ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በሕንድ አንድ ሆስፒታል ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ህይወት ለማትረፍ የቻሉትን ቢያደርጉም አስር አራስ ሕፃናት ህይወት ማለፉ ተነገረ። የእሳት አደጋ ተከላካዮች በምዕራባዊው ማሃራሽትራ ግዛት ወደምትገኘው የብሃንዳራ አካባቢ ሆስፒታል እሳቱን ለመቆጠጠር ከመድረሳቸው በፊት ሰባት ሕፃናትን ከእሳት አደጋው ማትረፍ ተችሏል። የሕንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ \"ልብ የሚያቆስል አሳዛኝ ክስተት\" ሲሉ አደጋውን ገልጸዋል። የእሳት አደጋው የተከሰተው አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ መሆኑን የሆስፒታሉ ኃላፊዎች የገለጹ ሲሆን መንስኤው ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። በእሳቱ ሳቢያ በሆስፒታሉ ውስጥ የተከሰቱት ተከታታይ ፍንዳታዎች የነፍስ አድን ሥራውን ማሰናከሉን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሥራ ላይ የነበረች አንዲት ነርስ ከሆስፒታሉ አዲስ የተወለዱ አራስ ህጻናት እንክብካቤ ክፍል ውስጥ ጭስ ሲወጣ ካየች በኋላ ለባለስልጣናት ማስታወቋን ተናግራለች። የአካባቢው የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕራሞድ ካንዳቴ እንደገለጹት \"የሆስፒታሉ ባለሥልጣናት ሰባት ህፃናትን ቢያድኑም 10 ህጻናት ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሞተዋል\" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በደረሰባቸው ሐዘን ከሟች ቤተሰቦች ጎን መሆናቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። የሕንድ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሚት ሻህ ስለአደጋው እንዳሉት \"ቃላት የማይገልጹት የማይጠገን ጉዳት ነው\" ብለዋል።", "ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ ከወራት በኋላ በቫይረሱ የተያዘች ሴት አገኘች ከሁለት ወራት በላይ የኮሮናቫይረስ የማህበረሰብ ስርጭት ያልታየባት ኒውዚላንድ ከሰሞኑ በቫይረሱ የተያዘች ሴት አግኝታለች። የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ ከአውሮፓ የተመለሰች የ56 አመት ሴት ቫይረሱ ተገኝቶባታል። ግለሰቧ ከሌላ አገራት ለሚመጡ አስገዳጅ የሆነውን የሁለት ሳምንት ለይቶ ማቆያ ጊዜ ጨርሳ ቤቷ ከሄደች ከቀናት በኋላ ነው ቫይረሱ እንደተገኘባት የታወቀው። ከሴትዮዋ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን እንዲሁም የጎበኘቻቸውን ስፍራዎች ዝርዝር ባለስልጣናቱ እየተከታተሉ ነው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመግታት ዘርፍ ከፍተኛ ሙገሳና ምስጋና ካተረፉ አገራት መካከል ኒውዚላንድ በዋናነት ትጠቀሳለች። አምስት ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሏት ኒውዚላንድ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ የመዘገበችው ቁጥር 1 ሺህ 927 ሲሆን 25 ዜጎቿም ሞተዋል። ግለሰቧ በኦክላንድ የነበራትን የለይቶ ማቆያ ጊዜዋን ከጨረሰች በኋላ ባደረገችው ምርመራ ሁለት ጊዜ ከቫይረሱ ነፃ ነሽ ተብላ ነበር። ከሁለት ቀናት በኋላ ቀለል ያሉ የቫይረሱን ምልክቶች ማሳየት የጀመረች ሲሆን በኋላም እየከፋና እየባሰባት መጥቷል ተብሏል። ምርመራ ባደረገችበት ወቅት በቫይረሱ እንደተያዘች የታወቀ ሲሆን ከዚያ ቀን በኋላ በቤቷ ራሷን ለይታ ተቀምጣለች። በዛሬው ዕለት የጤና ሚኒስትሩ ክሪስ ሂፕኪንስ እንዳሉት የቫይረሱ ዝርያ ከየት እንደመጣ ለመገመት በአሁኑ ሰዓት ከባድ ነው ብለዋል። ነገር ግን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ \" የቫይረሱ ዝርያ አይነት በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ እንደሆነ በማሰብ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረግን ነው\" ብሏል። ከዚህ በላይ ግን ስለ ቫይረሱ ምንም ማለት እንደማይቻል ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የለይቶ ማቆያ ጊዜዋን ከጨረሰች በኋላ በሰሜናዊ ኒውዚላንድ የሚገኙ ቦታዎችን ጎብኝታለች ተብሏል። የጤና ሚኒስቴር ጎብኝታቸዋለች ብሎ የጠቀሳቸውን ሱፐር ማርኬቶች፣ ሬስቶራንቶችና ጋለሪዎች ዝርዝር አውጥቷል።። በነዚህ በተጠቀሱት ቦታዎች ድንገት ተገኝቶ የነበረ ሰው በሙሉ በጥርጣሬ እንደሚታይና ቤታቸውም ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩና እንዲመረመሩም ተነግሯቸዋል። ከሴትዮዋ ጋር ቅርበት አላቸው የተባሉ አራት ሰዎች የተለዩ ሲሆን ምርመራ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።", "የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቶች ኦሚክሮንን መቋቋም አለባቸው አሉ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በአሁን ላይ በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች በአዲሱ ኦሚክሮን የቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ከባድ የጤና እክል እንዳይገጥማቸው መከላከል እንደሚችሉ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ ተናገሩ። ኃላፊው ይህን ያሉት በደቡብ አፍሪካ በተደረጉ ሙከራዎች ይህ ቫይረስ በተለይ የፋይዘር ክትባትን ማሸነፍ እንደሚችል ምልክቶች አሉ መባላቸውን ተከትሎ ነው። ተመራማሪዎች እንደሚሉት ሰዎች በአዲሱ ቫይረስ ሲያዙ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች በሰውነታችን የሚፈጥሩ የመከላከል አቅም በእጅጉ ይቀንሳል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ማይክ ራያን ኦሚክሮን ክትባቶችን ሙሉ በሙሉ የመገዳደር አቅም እንዳለው የሚያሳይ ምንም አይነት ምልክት አልተገኘም ብለዋል። \"እስካሁን ድረስ ሁሉንም አይነት ቫይረሶች መከላከል የሚችሉ ውጤታማ ክትባቶችን አግኝተናል። በኦሚክሮን ምክንያት ከባድ የጤና እክል የሚገጥመው አልያም ሆስፒታል እስከ መግባት የሚደርስ ሰው ይኖራል ብሎ መገመት በጣም ከባድ ነው'' ብለዋል የዓለም ጤን ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊው ዶክተር ማይክ ራይን። ኃላፊው አክለውም ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ከታዩት ሌሎች የኮሮረናቫይረስ ዝርያዎች አንጻር እንደውም ሰዎችም የማሳመም አቅሙ ዝቅተኛ ነው ብለዋል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተሰርቶ እስካሁን በሌሎች ተመራማሪዎች ባልተገመገመ አዲስ ጥናት መሰረት ግን የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት ከኦሚክሮን ጋር ሲገናኝ ውጤታማነቱ 40 በመቶ እንደሚቀንስ አመልክቷል። ነገር ግን ኦሚክሮን ሙሉ በሙሉ ከክትባቱ እንደማያመልጥ ደርሰንበታል ይላሉ በአፍሪካ ሄልዝ ሪሰርች ኢንቲትዩት ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አሌክስ ሲጋል። ተመራማሪው እንደሚሉት ከዚህ በፊት የተያዙ ሰዎች እንዲሁም ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመቋቋም አቅማቸው ከፍተኛ ነው ካሉ በኋላ ሶስተኛ ዙር ክትባት መውሰድ ደግሞ ይበልጥ የመከላከል አቅምን ከፍ እንደሚያደርገው አስረድተዋል። አዲሱ ኦሚክሮን እስካሁን ከ30 በላይ አገራት ውስጥ የተገኘ ሲሆን ሰዎች በክትባትም ሆነ ኮሮናቫይረስ ሲይዛቸው የሚያዳብሩትን በሽታ የመከላከል አቅም ሊቋቋም የሚችል ነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች አንጻር እስካሁን ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ ነው ያሳየው። በዚህም ምክንያት ስለ ቫይረሱ፣ ስለ ስርጭቱ እና ስለሚያደርሰው ጉዳት በርካታ መላ ምቶች እየተሰነዘሩ ነው። መነሻውን በደቡብ አፍሪካ አገራት ያደረገው አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት ለዓለማችን ተጨማሪ ስጋትን ፈጥሮ ቆይቷል። ይህ አዲስ ዝርያ እስካሁን ከታዩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች እጅግ የተለየው ነው ተብሏል። በበርካታ ብዙ የዘረመል ለውጥ ውስጥ በማለፉ በአንድ ሳይንቲስት \"አሰቃቂ\" ተብሎ ሲገለጽ ሌላው ደግሞ እስካሁን ከታዩት የከፋ ዝርያ ነው ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ሴንተር ፎር ኤፒዴሚክ ሪስፖንስ ኤንድ ኢኖቬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ዴ ኦሊቬራ ስለዚህ አዲስ ዝርያ ሲናገሩ፤ \"ያልተለመደ የዘረ መል ለውጥ ያለው\" ሲሆን ከተሰራጩት ሌሎች ዝርያዎችም \"በጣም የተለየ ነው\" ብለዋል። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ደግሞ የፋይዘር ክትባት ኦሚክሮን ላይ የሚኖረው ጥንካሬና ድክምትን በተመለከተ መረጃዎች ይፋ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። እስካሁን ድረስ እንደ ሞደርና፣ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ያሉ እንዲሁም ሌሎች ክትባቶች ከአዲሱ ኦሚክሮን አንጻር ያላቸው ውጤታመነትን በተመለከተ ምንም ጠቃሚ መረጃ አልተገኘም።", "ወላጆቻቸው የሚያጨሱ ልጆች አጫሽ የመሆን ከፍተኛ ዕድል እንዳላቸው ጥናት አመለከተ ወላጆቻቸው የሚያጨሱ ታዳጊዎች እነሱም አጫሽ የመሆን አራት እጥፍ ዕድል እንዳላቸው በዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አማካይነት የተሰራ አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ። በዚህም ምክንያት ዶክተሮች ሲጋራ የሚያጨሱ ወላጆችንና አሳዳጊዎችን ማጨስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። የፀረ ሲጋራ ማጨስ ዘመቻ እንቅስቃሴ እንዳለው ወላጆቻቸው የሚያጨሱ ታዳጊዎች 4.9 በመቶ እነሱም አጫሽ የመሆን ዕድል ሲኖራቸው፣ ወላጆቻቸው የማያጨሱ አቻዎቻቸው ግን የማጨስ ዕድላቸው 1.2 በመቶ ብቻ እንደሆነ አመልክቷል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ባዘጋጀው አዲስ ፊልም ላይ የጤና ባለሙያዎች በአዋቂዎች አጫሾችና ማጨስ በሚጀምሩ ልጆች መካከል ስላለው ግንኙነት ውይይት አድርገዋል። የፀረ ማጨስ ዘመቻው አዋቂ አጫሾች በዙሪያቸው ባሉ ወጣቶች ሕይወት ላይ ስለሚፈጥሩት ተጽዕኖ በጥናት የተደገፈ መረጃን አቅርቧል። አጠቃላይ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ናያት አሪፍ እና የልጆች ሥነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ቤቲና ሆህነን ወላጆች ማጨስን እስከ መጨረሻው በመተው በልጆቻቸው ሕይወት ላይ የሚታይ በጎ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። በውይይቱ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ማጊ ትሮፕ፣ ይህ አዲሱ የጥናት ውጤት ወላጆች ማጨስ እንዲያቆሙ ተጨማሪ መነሳሻ ሊሆናቸው እንደሚችል ተስፋቸውን ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም የተጀመረው አዲሱ ፀረ ማጨስ ዘመቻ \"ሲጋራ በትውልዶች መካከል ያለውን ተያያዥነት በማሳየት ወላጆች በልጆቻቸው ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ያጎላል\" በማለት ይህም \"ከሲጋራ ማጨስ ለመገላገል ጥሩ አጋጣሚን ይፈጥራል\" ብለዋል። የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ለወላጆች፣ ለአሳዳጊዎች እንዲሁም ሲጋራ ማቆም ለሚፈልጉ ሰዎች የሚጠቅሙ የተለያዩ የድጋፍ አገልግሎቶች እንዳሉ ገልጸዋል። ሲጋራ ለማቆም የሚያግዝ መተግበሪያ፣ በፌስቡክ ላይ የሚደረግ ድጋፍ፣ በየዕለቱ የሚላክ የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክት እንዲሁም በኢንትርኔት ላይ የሚገኝ ግላዊ ሲጋራ የማቆም ዕቅድ መዘጋጀቱን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።", "ለሁለት ዓመት ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በሯን ልትከፍት ነው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በስተመጨረሻ በሮቿን ልትከፍት እንደሆነ ይፋ አድርጋለች። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ አውስትራሊያዊያን ምንም ዓይነት በለይቶ ማቆያ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በነፃነት መግባት ይችላሉ። ከ60 ሃገራት የሚመጡ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ደግሞ ከግንቦት ወር ጀምሮ መግባት እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። ከእነዚህ ሃገራት መካከል ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይት ኪንግደም ይገኙበታል። ሁሉም ወደ ኒው ዚላንድ የሚመጡ ተጓዦች ከኮቭድ ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ ወረቀት ማሳየት አለባቸው። ኒው ዚላንድ ድንበሯን ሙሉ በሙሉ ዝግ በፈረንጆቹ መጋቢት 2020 ነበር። ኒው ዚላንድ ለአውስትራሊያ ከሰጠችው ለአጭር ጊዜ የቆየ የጉዞ ፈቃድ ውጭ ድንበሯን ለማንም ሳትከፍት ቆይታለች። አሁን ላይ ወደ ሃገሪቱ መግባትና መውጣት የሚችሉት የኒው ዚላንድ ዜጎች ብቻ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን እንዳሉት ኒው ዚላንድ \"ዓለምን ለመቀበል ዝግጁ ናት።\" \"አሁን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ድንብራችንን ለመክፈት ሁሉም ነገር ምቹ ይመስላል። ቱሪስቶቻችንም ይመለሳሉ\" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ። ወደ ኒው ዚላንድ ለመግባት ቪዛ ቀድሞ ያላቸው ሰዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደልባቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። ኒው ዚላንድ ጠንካራ የሚባል የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣሏ የኮቪድ-19 ስርጭትን በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ይነሳል። ከኒው ዚላንድ ነዋሪዎች 95 በመቶው ተከትበዋል። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በኮቪድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ብቻ ነው። ያልተከተቡ ሰዎች ሥራ አያገኙም መባሉን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ዌሊንግተን ተቃውሞ ተቀስቅሶ እንደነበር አይዘነጋም። ምንም እንኳ ኒው ዚላንድ ድንበሯን ከፍታ፤ እጇን ዘርግታ እንግዶች ለመቀበል ብትዘጋጅም አሁንም ቢሆን በርከት ብሎ መሰባሰብም ሆነ ያለጭንብል መንቀሳቀስ ክልክል ነው።", "ኮሮናቫይረስ : አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ። ኬንት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም ላይ በስርጭቱ ቀዳሚው ሊሆን ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የዘረ መል ክትትል መርሃ ግብር ኃላፊ ገልጸዋል። ኃላፊው ፕሮፌሰር ሻሮን ፒኮክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ ዝርያ \"በአገሪቱ የተሰራጨ\" ሲሆን \"በመላው ዓለም የመሰራጭ ዕድሎችም\" አሉት ብለዋል፡፡ በኬንት የተገኘው ዝርያ ከ50 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል። የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ሲሆን፤ በቀጣይ ወራት በፍጥነት ተስፋፍቶ በጥር ወር በመላው ዩናይትድ ኪንግደም አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ምክንያት ሆኗል። ፕሮፌሰር ፒኮክ \"በእውነቱ ከሆነ እኛን በመጉዳት ላይ የሚገኘው በከፍተኛ ፍጥነት መተላለፉ ነው\" ብለዋል። ለኮሮናቫይረስ የተሠሩ ክትባቶች ቀደም ሲል ለነበረው የቫይረሱ ዙሪያ የተመረቱ ቢሆንም ሳይንቲስቶች አሁንም ቢሆን በአዲሱም ዝርያ ላይ ይሠራሉ ብለው ያምናሉ። ውጤታማነታቸውን ግን ጥሩ ላይሆን ይችላል። በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ክትባቶች በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቫይረስ ዓይነቶች ላይ በጥሩ ሁኔታ የሚሠሩ ይመስላሉ ብለዋል ፕሮፌሰር ፒኮክ።", "ኢኳዶር ለሁሉም ዜጎቿ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ግዴታ አደረገች ኢኳዶር እየተባበሰ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታትና እንደ ኦሚክሮን ያሉ ዝርያዎችን ጉዳት ለመቀነስ በሚል አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወድ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው አጠቃላይ ሕዝቡን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት ክምችት ያለ ሲሆን፣ የሕክምና ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ብቻ ያለመከተብ መብት ይኖራቸዋል። ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥም ማንኛውም ዕድሜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነ ሰው በሙሉ ክትባቱን ይወስዳል ተብሏል። እስካሁን ድረስ ዕድሜያቸው ለክትባት ከደረሱ ሰዎች ውስጥ 77.2 በመቶ ያህሉ ሁለት ዙር ክትባት ሲወስዱ ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ሦስተኛ ዙር ክትባታቸውን ወስደዋል። የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ክትባቱ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል አቅም የፈጠረና ይህም በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር እና ሞትን ለመቀነስ ያገዘ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግሥት የተቀመጠው የዜጎችን ጤንነት የማስጠበቅ ግዴታ በመንግሥት ጫንቃ ላይ የወደቀ መሆኑንና እርሱን ለማስፈጸም ሕጉን መሠረት ተደርጎ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን የኢኳዶር ጤና ሚኒስቴሩ ገልጿል። አውስትራሊያ እና ጀርመን ተመሳሳይ ውሳኔ የመስጠት ዕቅድ ያላቸው አገራት ናቸው። ኢኳዶር ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥቅም ላይ የሚውል የክትባት የምስክር ወረቀት ለዜጎቿ አዘጋጅታለች። ወደ ሲኒማና ቴአትር ቤቶች ወይም የገበያ ማዕከላት ለመግባት ይህንን ወረቀት ማሳየት ግዴታ ይሆናልም ተብሏል። ኢኳዶር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ከተከሰተ ጀምሮ 33 ሺህ 600 ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘ ሞት መዝግባለች።", "ጣልያናዊቷ ለ10 ወራት 'ኮማ' ውስጥ ከቆየች በኋላ ነቃች ጣልያን ውስጥ አንዲት ሴት እራሷን ስታ በሕይወት እና በሞት መካከል ውስጥ ለአስር ወራት ከቆየች በኋላ መንቃቷ ተዘገበ። የ37 ዓመቷ ክሪስቲና ሮሲ ባሳለፍነው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የሰባት ወር ነፍሰ ጡር እያለች ነበር የልብ ድካም አጋጥሟት እራሷን የሳተችው። ሴት ልጇ ካተሪና በወቅቱ በድንገተኛ ሕክምና እንድትወለድ የተደረገ ሲሆን ክሪስቲና ግን ላለፉት ዘጠኝ ወራት ኮማ ውስጥ ቆይታለች። ለህመሟ ምክንያቱ አንጎሏ ውስጥ የደረሰ ጉዳት ሊሆን ይችላል ተብሎ ነበር። በአሁኑ ሰአት ከኮማ ነቅታ የመጀመሪያ ቃሏን ተናግራለች። በመጀመሪያ 'እማዬ' የሚለውን ቃል እንዳወጣች ባለቤቷ ገልጿል። \"ምንም አልጠበቅንም ነበር። ከዚህ ሁሉ ወራት ስቃይ በኋላ ያልተጠበቀ ሀሴት ነው ያጋጠመን\" ብሏል ጋብሪኤል ሱቺ 'ላ ናዚዮን' ለተባለው ጋዜጣ። ክሪስቲና ሮሲ ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ የማገገም ሂደቷን ለማፍጠን በሚል ኦስትሪያ ውስጥ ወደሚገኝ ልዩ ክሊኒክ እንድትዘዋወር ተደርጋ ነበር። ከዘጠኝ ወራት በኋላ ከኮማ ስትነቃም ባለቤቷ እና እናቷ አጠገቧ ነበሩ። እንደነቃችም 'እማዬ' ብላ እናቷን ጠርታለች። ክሪስቲና ከአገር ወጥታ ህክምና እንድታገኝ የሚያስችለው ገንዘብ የተገኘው ደግሞ በበይነ መረብ በተደረገ የእርዳታ ጥሪ ነው። በዚህም ከ208 ሺ ዶላር በላይ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ከዚህ በኋላ ለሚያስፈልጓት ህክምናዎችም እንደሚረዳት ይጠበቃል። \"ክሪስቲና በጣም አዲስ አይነት ሰው ሆናለች\" ብሏለ ባለቤቷ አሬዞ ኖቲዜ ለተባለው ድረ ገጽ ሲናገር። \"በጣም የተረጋጋች ሆናለች። ለመተንፈስ የሚረዳትን መሳሪያ አውልቀውላታል። ከዚህ በኋላ ሌሎች አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ የሚረዷት ህክምናዎች ይደረጉላታል\" ብሏል። ክሪስቲና ኮማ ውስጥ ስትገባ የሰባት ወር ጽንስ የነበረችው ካተሪናም ብትሆን ስትወለድ ባጋጠማት የኦክስጅን እጥረት ምክንያት ለወራት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲደረግላት ነበር።", "ኮቪድ -19፡ ሰሜን ኮሪያ የኮቪድ ወረርሽኝ በመከሰቱ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ጥብቅ ብሔራዊ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች። የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በዋና ከተማዋ ፕዮንግያንግ የኦሚክሮን ወረርሽኝ መከሰቱን የዘገበ ሲሆን ምን ያህል ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ግን አልገለጸም። ኮሪያ ሴንትራል ኒውስ ኤጀንሲ ( ኬሲኤንኤ) የወረርሽኙን መከሰት የአገሪቷን የለይቶ ማቆያ ሕግ የጣሰ \"ትልቅ አደጋ \" ነው ያለ ሲሆን፣ የአገሪቷ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለብሔራዊው አደጋ ምላሽ ለመስጠት አስቸኳይ ስብሰባ እያደረጉ ነው ብሏል። ይሁን እንጂ ታዛቢዎች ቫይረሱ አሁን የተከሰተ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ በአገሪቷ እንደነበር ያምናሉ። ሰሜን ኮሪያ በቻይና የተሰራውን ሲኖቫክስስ እንዲሁም አስትራዜኒካ ክትባትን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኗ የኮቪድ 19 ክትባት ለሕዝቦቿ አልሰጠችም። አገሪቷ ቫይረሱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሥርጭቱን ለመከላከል ያለመችው ድንበሮቿን በመዝጋት ነው። ይህም ወደ አገሪቷ የሚገቡ መሠረታዊ ፍጆታዎች እንዲቀንሱ በማድረጉ አገሪቷን ለከፋ ምጣኔ ሐብታዊ ቀውስ እና የምግብ እጥረት አጋልጧታል። እንዲህም ሆኖ ወረርሽኙ ሊከሰት እንደሚችል ምልክቶች ነበሩ። ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ ያልተረጋገጡና በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተመዝገብዋል። ጎረቤት አገሯ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያም ወረርሽኙ ተከስቶባቸዋል። ቻይና አሁን ላይ የኦሚክሮንን ወጀብ ለመቆጣጠር እየታገለች ነው። ባለፈው ሰኔ ወር የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ፕሬዚደንት ኪም ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ስለተከሰተው አሳሳቢው ክስተት ባለሥልጣናትን መተቸታቸውን የዘገቡ ሲሆን ስለጉዳዩ ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። መስከረም ወር መንግሥት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲሁም የበሽታ መከላከያ ልብስ በመልበስ ወታደራዊ ሰልፍ አድርጓል። ይህንን ተከትሎ አንዳንድ ተንታኖች ልዩ ኃይሉ የተፈጠረው የኮቪድ 19 ሥርጭትን ለመከላከል አንዲሳተፉ እንደሆነ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል።", "የኮቪድ-19 ማጠናከሪያ ክትባት ሆስፒታል የመግባት መጠንን እንደሚቀንስ ጥናት አመለከተ የኮቪድ-19 ማጠናከሪያ ሦስተኛ ክትባት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል እንዳይገቡ ለመከላከል 88 በመቶ በማገዝ ውጤታማ ነው ሲል የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የጤና ጥበቃ ኤጀንሲ አዲስ ጥናት አመለከተ። አስትራዜኒካ፣ ፋይዘር ወይም ሞደርና ክትባቶችን ሁለት ዙር የወሰዱ ሰዎች በኦሚክሮን እንዳይያዙ እምብዛም ባይጠብቃቸውም በጠና ከመታመም እንደሚከላከል ጥናቱ ያሳያል። የጤና ኃላፊዎችም ይህ ጥናት ሦስተኛ ዙር ወይም የማጠናከሪያ ክትባት አስፈላጊነትን ያጎላዋል ሲሉ ተናግረዋል። የዩኬ የጤና ፀሐፊው ሳጂድ ጃቪድ \"ይህ ክትባቶች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ የሚያረጋግጥ እና የበለጠ ተስፋ ሰጪ መረጃ ነው። ሕይወትን ያድናል እንዲሁም ከባድ በሽታን ይከላከላል\" ሲሉ ተናግረዋል። \"ይህ ሳይንሳዊ ትንታኔ ክትባቱን ያልወሰዳችሁ እንደሆነ በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ሆስፒታል የመሄድ ዕድላችሁ እስከ ስምንት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን ያሳያል\" ሲሉም አስጠንቅቀዋል። የዩኬ የጤና ደኅንነት ኤጀንሲ በሠራው በዚህ ጥናቱ ላይ ከ600,000 በላይ የተረጋገጡ እና የተጠረጠሩ በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎችን መረጃ በመተንተን ነው ድምዳሜ ላይ የደረሰው። እንደ ኤጀንሲው ግኝት ከሆን አንድ ዙር የክትባት መጠን የሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልገው ሕመምን በ52 በመቶ ቀንሶታል። ሁለተኛውን ዙር ክትባት መውሰድ ደግሞ ይህንን የመከላከል መጠን ወደ 72 በመቶ ከፍ የሚያደርገው ሲሆን ከ25 ሳምንት በኋላ ይህ የመከላከል አቅም መልሶ ወደ 52 በመቶ ዝቅ እንደሚል ታውቋል። ነገር ግን ሦስተኛው ዙር ክትባት ከተወሰደ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ይህ በሆስፒታል የመተኛትን የመከላከል አቅም ወደ 88 በመቶ ከፍ ብሏል። የኤጀንሲው ጥናት ይህ ጥበቃ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ለማወቅ እስካሁን በቂ መረጃ አለመገኘቱን ነገር ግን ሕመምን በመቀነስ ረገድ ረዘም ላለ ጊዜ እንደሚሠራ ይፋ አድርጓል። ቀደም ሲል የኮቪድ-19 ሕመም ምልክቶች በታየባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ ከእያንዳንዱ ዙር ክትባት በኋላ ያለው የመከላከል መጠን ካልተከተቡ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር 68 በመቶ ያህል ያነሰ መሆኑም ታውቋል። ከካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ የተደረገው ሁለተኛ ጥናት አንድ ሰው በኦሚክሮን ከተያዘ በኋላ ሆስፒታል የመግባት ስጋት ከዴልታ ዝርያ ጋር ሲነጻጸር በግማሽ ያህል ያነሰ እንደሆነ አረጋግጧል።", "በዋግ ኽምራ ዞን ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆኑን ነዋሪዎችና ኃላፊዎች ገለፁ በአማራ ክልል በሚገኘው የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በርካታ ሰዎች በረሃብ ምክንያት እየሞቱ መሆኑን ከአካባቢው ወደ ባሕር ዳር እና እብናት የመጡ ነዋሪዎች እንዲሁም የአካባቢው ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ገብሬ የአካባቢው ማኅበረሰብ ላለፉት አራት ወራት ምንም ዓይነት እርዳታ አግኝቶ እንደማያውቅ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና ከተማ ሰቆጣን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከተሞች በህወሓት አማፂያን ቁጥጥር ሥር በመሆናቸው በብዛት ኑሮውን በእርዳታ የሚደጎመው የአካባቢው ማኅበረሰብ ካለፈው ዓመት ሐምሌ መጀመሪያ አንስቶ ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳላገኘ ጨምረው ተናግረዋል። የዛሬ ዓመት በትግራይ የተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ አማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከተስፋፋ ጀምሮ አብዛኞቹ ወረዳዎች ለሰብዓዊ እርዳታ ዝግ ሆነው መቆየታቸውን ምክትል አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አካባቢውን ከላሊበላም ሆነ ከሰቆጣ የሚያገናኘው መንገድ ከሐምሌ 09/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመዘጋቱ ሰብዓዊ እርዳታም ሆነ የመድኃኒት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ችግሩን አባብሶታል ይላሉ። በዚህም ምክንያት በርካታ የአካባቢው ሕዝብ ለከፋ ችግር መዳረጉን፣ ብዙ ሰዎችም በረሃብ እየሞቱ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ኃላፊዎች ይናገራሉ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ የምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ኮሚሽን፣ በክልሉ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልግ አስታውቋል። እንደ ኮሚሽኑ መግለጫ ከሆነ የህወሓት አማፂያን በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ከ110 በላይ እናቶች፣ ሕጻናት እና ተመላላሽ ታካሚዎች በምግብ፣ በውሃ እና በመድኃኒት እጦት ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ኮሚሽኑ በአካባቢው የመንግሥት መዋቅር በመፍረሱ ምክንያት በምግብ እና በህክምና እጦት የሞቱ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥርን ማወቅ አለመቻሉን ገልፆ፣ ከዚህም ሊጨምር ይችላል ብሏል። የህወሓት አማፂያን በተቆጣጠሯቸው ዞኖች እንዲሁም ከእነዚህ አካባቢ ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያዎች የሚገኙ ሰዎች ለምግብ፣ ለመጠጥ ውሃ እና የመድኃኒት እጦት ተጋልጠዋል ሲል ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል። አክሎም በሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ከፊል ደቡብ ጎንደር እንዲሁም ዋግ ኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው የሚገኙትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግሯል። '. . .ችላ ተብለናል' የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ገብሬ አካባቢውን የህወሓት አማፂያን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸውን ይናገራሉ። \"የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የችግሩን አሳሳቢነት ብናሳውቅም ማንም ሊደርስልን አልቻለም። . . .ችላ ተብለናል\" ብለዋል። ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ 50 ሺህ የሚጠጉ የብሔረሰብ አስተዳደር ዞኑ ነዋሪዎች በአንጻራዊነት ሰብዓዊ እርዳታ እያገኙ ቢሆንም እነሱም በችግር ውስጥ መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ወደ 635 ሺህ ሕዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በረብ ሞተዋል ስለሚባሉት ሰዎች መረጃው ቢኖራቸውም ቁጥሩ ግን ከሚገለጸው በላይ ሊጨምር ይችላል ብለዋል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ የነበረ ቢሆንም የህወሓት አማፂያን ወደ አካባቢው መግባታቸውን ተከትሎ ምንም አይነት እርዳታ ደርሶ እንደማያውቅ ምክትል አስተዳዳሪው ተናግረዋል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ ጋዝጊብላ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ወንድሙ ወዳጅ ሰሞኑን ወደ ባሕር ዳር ከመጡት ተፈናቃዮች መካከል አንዱ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ ረሃብ በመከሰቱ በአሁኑ ወቅት ከአቅመ ደካሞች ውጪ አብዛኛው የወረዳው ነዋሪ ሰብዓዊ እርዳታ ፍለጋ አካባቢውን ለቅቆ እየተሰደደ ነው። \"ቤተሰብ ቢያንስ ልጆቼ ቢተርፉልኝና እርዳታ ቢያገኙ እያለ ልጆቹን ወደ እብናት እና ባሕር ዳር ይልካል። ነገር ግን እዚህም እርዳታ የለም\" ብለዋል። በረሃብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ወንድሙ፣ በወረዳው 21 ቀበሌዎች የሚገኙ ሲሆን በእነዚህ ቀበሌዎች በየቀኑ ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ሰው በረሃብ ምክንያት እንደሚሞት ይናገራሉ። \"እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ሰው ያለውን እየተበዳደረ ይመገብ ነበር፣ ከጊዜ በኋላ ግን አንዳንድ አቅመ ደካሞች የበለጠ በመቸገራቸው ወጣቶች ቤት ለቤት እየለመኑ፣ በጣም የተራቡትን እየመረጥን እንደጉማቸው ነበር። ነገር ግን አሁን ትተናቸው በመምጣታችን ይሙቱ ይኑሩ አናውቅም\" ብለዋል። በዚሁ ወረዳ [ጋዝጊብላ] የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን መዓዛ፣ በወረዳው ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በወረዳው በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች በመገኘት መረጃ ለማጠናቀር አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ሰለሞን፣ ቢያንስ እርሳቸው የሚያውቋቸው ሦስት ሰዎች በርሃብ ምክንያት ሕይወታቸው አልፎ በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ተገኝተዋል። በወረዳው ከ23 ሺህ በላይ ዜጎች የሴፍቲኔት ተጠቃሚ ሲሆኑ አብዛኞቹ የመጨረሻ ሰብዓዊ እርዳታ ያገኙት ከግንቦት ወር በፊት መሆኑን የሚያስታውሱት አቶ ሰለሞን፣ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ቢያንስ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት የከፋ ችግር ውስጥ ስለነበሩ እጅግ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸው ነበር ብለዋል። ነገር ግን ወዲያውኑ ጦርነቱ በመከሰቱ ምንም አይነት እርዳታ ሳያገኙ መንገዶቹ ተዘጋግተዋል ብለዋል። የህወሓት ኃይሎች ወደ አካባቢው መግባታቸውን ተከትሎ የመብራት፣ ውሃ እና ባንክ የመሳሰሉት መሠረታዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው እና የንግድ ልውውጥ ባለመኖሩ ችግሩን የከፋ እንዳደረገውም ይናገራሉ። በዚህም ምክንያት የመሠረታዊ ፍጆታ እቃዎች አቅርቦት እጥረት ከመከሰቱም በላይ የዋጋ ንረቱ ከፍተኛ ሆኗል የሚሉት አቶ ሰለሞን፣ ለአብነትም የአንድ ኪሎ ጨው ዋጋ እስከ 100 ብር መድረሱን ይናገራሉ። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ በረሃብ ከሚሞተው ሕዝብ በተጨማሪ \". . . በንጹሃን ዜጎች ላይ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል እና መረጃ አምጡ በማለት በርካታ ሰዎች በህወሓት ተገድለዋል\" ሲሉ ይከስሳሉ። ቢቢሲ በአካባቢው የህወሓት ኃይሎች ፈፀሙት ስለተባለው ግድያ ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በአጠቃላይ እስከ 7 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ቀውስ ሊጋለጡ ይችላሉ ማለቱ ይታወሳል። ድርጅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት በአማራ እና አፋር ክልሎች ወደ 1.7 ሚሊዮን ሰዎችን ለረሃብ አደጋ ሲያጋልጥ ወደ 300 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብን ደግሞ ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቅሏል ይላል።", "ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ 94 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተያዙ በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 94 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ቀናት በቀሯት አሜሪካ በተለያዩ ግዛቶችም በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሻቅቧል ተብሏል። በዚህ ሳምንት ሃሙስ 91 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከፍተኛ ቁጥር ነው በማለት ሪፖርት አድርጋ የነበረቸው አሜሪካ በተከታታይ ባሉት ቀናትም እንዲሁ ከዚህ በላይ ያለው ቁጥር በየቀኑ ተመዝግቧል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ሚሊዮን መድረሱን ከጆንስ ሆፕኪንስ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ፕሬዚዳንታዊ ስልጣኑን ለመጨበጥ ዶናልድ ትራምፕና ጆ ባይደን እየተፋለሙ ባሉባት አሜሪካ ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም አሸናፊው የሚታወቅ ይሆናል። አሁን ባለውም ሁኔታ 21 የአሜሪካ ግዛቶች በወረርሽኙ ክፉኛ የተመቱ ሲሆን አንዳንድ ግዛቶችም በዚህ ምርጫ ላይ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ተብሏል። በምርጫው ወሳኝ ከሆነችው ግዛት አንዷ ዊስኮንሰን የሚገኙ ሆስፒታሎች አርብ እለት የነበረውን የዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወረርሸኙን ያባብሰዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። \"በአሁኑ ወቅት በተቻለ መጠን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ባይሰበሰቡ ይመረጣል። በተለይም በዊስኮንሰን ግዛት ግሪን ቤይ አካባቢ በአገሪቱ ካሉ ቦታዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወረርሽኙ እየተዛመተ መሆኑን እያየን ነው\" በማለት የግዛቲቱ ሆስፒታሎች በጥምረት መግለጫ አውጥተዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ አርብ ከነበረው የምርጫ ቅስቀሳቸው በፊትም \"ከፍኛ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥርን እያስመዘገበ ነው። ምርጥ የሆነ ምርመራ አለን። ሞት እየቀነሰ ነው\" በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በቅርቡ የነበረው የትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ ተሳታፊው ሙቀት ሲለካ ነበር እንዲሁም ጭምብልም እየታደለ ነበር። በወረርሽኙ ምክንያት ትልልቅ ዝግጅቶችም ከአዳራሽ ውጭ እየተደረጉ ነው። ሆኖም በነዚህ ስፍራዎች አካላዊ ርቀት ሲጠበቅ አይታይም እንዲሁም አንዳንድ ደጋፊዎች ጭምብል አናጠልቅም የሚል እምቢተኝነት አሳይተዋል። ጆ ባይደንም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን እያካሄዱ ሲሆን ዲሞክራቶቹ አካላዊ ርቀትን እያስጠበቁ ነው ተብሏል። ለምሳሌም ያህል ደጋፊዎች በየመኪኖቻቸው ሆነው እንዲከታተሉ አድርገዋል።", "ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 በሁለተኛው ዙር የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል- ተመራማሪዎች ብዙ አገራት በኮሮናቫይረስ በመጀመሪያ ዙር ክፉኛ ተጠቅተው መቆጣጠር ቢችሉም ወረርሽኙ ድጋሚ አገርሽቶ እየፈተናቸው ነው። ከዚህ ቀደም ተከስተው የነበሩ ወረርሽኞች ተሞክሮ እንደሚያሳየው በድጋሚ ሊያገረሽ ይችላል። ከ100 ዓመት በፊት ተከስቶ ቢያንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ እንደጨረሰ የሚነገርለት ስፓኒሽ ፍሉ፣ ከመጀመሪያውም ሆነ ከሦስተኛው ጊዜ በላይ ሁለተኛው ዙር የከፋ ጉዳት አድርሷል። የኮሮናቫይረስም ተመሳሳይ ሂደት ሊከተል እንደሚችል ሳይንቲስቶች እያስጠነቀቁ ነው።", "ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ከሚያዙት መካከል 63 በመቶው ምልክት አያሳዩም በአሁኑ ወቅት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች ውስጥ 63 በመቶው ምልክት የማያሳዩ እንደሆኑ ተገለፀ። ዛሬ የጤና ሚኒስቴርና ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተገለፀው አሁን ላይ አዲስ አበባ በስርጭቱ ቀዳሚ ሰትሆን፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሐምሌ እና ነሐሴ በላይ አሁን ላይ ወደ ፅኑ ሕሙማን የሚገቡ ታማሚዎች ብዛት እየጨመረ መጥቷል። በመግለጫው ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ለማወቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ የአንድ ወር አገር አቀፍ የምርመራ ዘመቻ ከ73 በመቶ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መለየታቸው ተገልጿል። 1.4 በመቶ የሚሆኑት በሆስፒታል የሚገኙ ታማሚዎች በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙም ተመልክቷል። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር አስቻለው አባይነህ እንዳሉት በኢትዮጵያ ሁሉም ወረዳዎች ቢያንስ አንድ በኮቪድ የተያዘ ሰው ሪፖርት አድርገዋል። በዚሁ መግለጫ ላይ እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ ከሚያዙት 57 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ15-34 ሲሆን ከሟቾች ውስጥ ደግሞ 51.9 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ መሆኑን ተገልጿል። ምክትል ዳይሬክተሩ አክለው እንደገለፁት በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተይዘው ለህልፈት የሚበቁ ሰዎች ምጣኔ 1.52 በመቶ ነው። አሁን ላይ የምርመራ መጠን የቀነሰ ቢሆንም ቫይረሱ የሚገኝባቸው እና ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑም ተመልክቷል። ባለፉት ሁለት ሳምንት ውስጥ እንደአገር ያለው የቫይረሱ ስርጭት 10 ነጥብ 4 በመቶ መሆኑም ተገልጿል። አዲስ አበባ ከተማ፣ ኦሮሚያ ፣ ትግራይ ፣ አማራ ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በቅደም ተከተል ከፍተኛ የቫይረሱ ተጠቂዎች የተገኙባቸው ስለመሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ የጤና ሚኒስትርዋ ዶ/ር ሊያ በበኩላቸው ርቀትን ሳይጠብቁና ማስክ ሳያደርጉ አገልግሎት መቀበልም ሆነ መስጠት ለቫይረሱ ተጋላጭነትን ስለሚጨምር ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ቸልተኝነት እና መዘናጋት አሁንም በሰፊው እንደሚስተዋል በመግለጽ ይህ ዋጋ ስለሚያስከፍል ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በቫይረሱ ሊያዝ ስለሚችል ጤናውን ከመጠበቅ ሊዘናጋ እንደማይገባም ነው ሚኒስትሯ ያስጠነቀቁት። በቫይረሱ የሞት ምጣኔ በኢትዮጵያ 1.52 በመቶ ፣ በአፍሪካ 2.4 በመቶ ፣ በዓለም ደግሞ 2.8 በመቶ መሆኑንም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል። በአጠቃላይ በኢትኦጵያ 89 ሺህ 860 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፤ የ1,365 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 43,149 ከበሽታው አገግመዋል።", "የሰሞኑ ጉንፋን መሰል ህመም የኮሮናቫይረስ ሊሆን ስለሚችል ምርመራ ማድረግ እንደሚገባ ተመከረ በኢትዮጵያ አዲስ የኮሮናቫይረስ ማዕበል በመከሰቱ ሰሞኑን የተስተዋለው ጉንፋን መሰል ህመም የሚያሳው ምልክት ከኮሮናቫይረስ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ህመሙ ያላባቸው ሰዎች ምርመራ እንዲያደርጉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መከረ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ባለፉት ሳምንታት በኢትዮጵያ ውስጥ የታየው በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በአገሪቱ አዲስ የወረርሽኙ ማዕበል መከሰቱን እንደሚያሳይ ተቋሙ ገልጿል። ሰሞኑን የተከሰተውን 'ጉንፋን መሰል' ወረርሽኝን በማስመልከት መግለጫ ያወጣው ተቋሙ እንዳለው በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ባደረገው የመስክ ቅኝትና የናሙናዎች ምርመራ ከ59 እስከ 86 በመቶው ላይ ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው አመልክቷል። ጨምሮም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በጤና ተቋማት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉ 55 ሺህ 562 ሰዎች ውስጥ 25 ሺህ 191 ያህሉ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን ገልጿል። እንዲሁም በመላው አገሪቱ ከታኅሣሥ 15 እስከ 21/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የኮቪድ ምልክት ታይቶባቸው ምርመራ ካደረጉ 83 ሺህ 237 ሰዎች ውስጥ 29 ሺህ 279 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ተገኝተዋል። ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ያለው በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ምጣኔ ተከታታይ ጭማሪ አሳይቷል። በዚህም መሠረት ከሁለት ሳምንት በፊት የነበረው የ5 በመቶ ምጣኔ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ሐሙስ (ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም) ላይ ወደ 36 በመቶ ከፍ ማለቱን ተቋሙ አመልክቷል። በዚህም ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳለው እየታየ ያለው የወረርሽኙ መስፋፋት በአገሪቱ አዲስ የኮቪድ-19 ማዕበል መከሰቱን እንደሚያመለክት ገልጿል። ተቋሙ ጨምሮም ሰሞኑን ከሚስተዋለው \"ጉንፋን መሰል\" ህመም ጋር የሚታዩት ምልክቶች ከኮቪድ-19 ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው ሳይዘናጉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መመርመር እንደሚገባ መክሯል። በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ስርጭት በዓለም ዙሪያ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ ይህ ክስተት ኢትዮጵያ ውስጥም መስተዋሉን በመግለጽ ምልክቶች የታዩባቸው ሰዎች ምርመራ እንዲያደርጉ መክሯል። የተቀረው ሕብረተሰብም የኮሮናቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ እራሱንና ሌሎችን ከወረርሽኑ እንዲጠብቅ መክሯል። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ሐሙስ ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው ከ415 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ 6 ሺህ 926 ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታውን ለመከላከል የሚረዳው ክትባት በአገሪቱ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የተከተቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ሕዝብ አንጻር ይህ አሃዝ ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል። የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለመዱትን የመከላከያ ዘዴዎች በአግባቡ ዘወትር ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች እየመከሩ ሲሆን ክትባት መውሰድም እንደሚገባ ያሳስባሉ።", "የአፍሪካ አገራት ግዜው ያለፈበት የኮቪድ ክትባትን እንዳያስወግዱ ተጠየቁ የዓለም ጤና ድርጅት የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈ የኮሮናቫይረስ ክትባት በእጃቸው የሚገኝ የአፍሪካ አገራት ክትባቱን ከማስወገድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ። አገራቱ ቀጣይ መመሪያዎች እስኪሰጡ ድረስ የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶችን ይዘው እንዲያቆዩ ተጠይቀዋል። ማላዊ እና ደቡብ ሱዳን በሚያዚያ ወር አጋመሽ ላይ 70 ሺህ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ክትባቶችን ለማስወገድ ማሰባቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው። ማላዊ 16 ሺህ የአስትራ ዜኔካ ብልቃጦችን፤ ደቡብ ሱዳን ደግሞ 59 ሺህ ተመሳሳይ ብልቃጦችን ለማስወገድ አስበዋል። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ (ሲዲሲ) ግን ምንም እንኳን ክትባቶቹን ለመጠቀም የተቀመጠው ግዜ ቢያልፍም ክትባቶቹ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዓለማችን ያሉ ሌሎች ክትባቶች ከተመረቱ ጀምሮ እስከ 36 ወር ድረስ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን የኮቪድ ክትባት ግን አዲስ መሆኑን ተከትሎ ነው ለምን ያህል ግዜ ውጤታማ ሆኖ መቆየት እንደሚችል ገና ያልተለየው። እነዚህ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች ጥቅም ላይ የማዋል ውሳኔ የሚሰጠው በብሔራዊ የመድሃኒት ተቆጣጣሪዎች እንደሆነ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ርሆዳ ኦዲያምቦ ታብራራለች። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ዋና ዳይሬክተር ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫቸው ላይ፤ \"ለአባል አገራት የማቀርበው ጥሪ ቢኖር፤ እኛ ክትባቱን አስተባብረን ለማቅረብ የራሳችንን ድርሻ እየተወጣን ነው፤ እናንተም ክትባቶቹን በመጠቀም የድርሻችሁን ተወጡ\" ሲሉ ተማጽነዋል። የኮሮናቫይረስ ክትባትን በአፍሪካ በሚፈለገው ፍጥነት እስካሁን ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን፤ ለዚህም የአቅርቦት እጥረት እንዲሁም ስለ ክትባቱ ጥርጣሬዎች መኖራቸው እንደ ምክንያት ይነሳሉ።", "ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ እጥረት አሳስቦኛል አለ በሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ በአካባቢው የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት አለመኖር በእጅጉ እንዳሳሰበው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ። አንድ ዓመት ካለፈው ጦርነት ጋር ተያይዞ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ የሕክምና ተቋማት ውድመት የገጠማቸው ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የአስፈላጊ አቅርቦቶችን ችግር እንደገጠማቸው ተነግሯል። \"የሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች መሠረታዊ ግብዓቶችን እያገኙ አይደለም፤ እንዲሁም በአንዳንድ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል\" ብሏል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ጥር 09/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ። ቀይ መስቀል የመድኃኒት እና ሕክምና መስጫ መሳሪዎች እጥረት ከጤና መሠረተ ልማት ውድመቶች ጋር ተደማምሮ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል ይላል። ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ፤ \"ሰዎች ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ነገር ከመከልከል\" ጋር የሚስተካከል ነው ብሏል። አይሲአርሲ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን የበለጠ ተጎጂ በሆኑት ላይ ትኩረት እያደረኩ ነው በሏል። \"የሕክምና አቅርቦቶች በመቀነሳቸው ምላሽ የመስጠት አቅማችንን ተገድቧል\" ያለው ቀይ መስቀል፤ ጦርነት፣ የደኅንነት እጦት እና ገደቦች የሰብዓዊ እርዳታውን ፈተና ውስጥ ከከተቱት ምክንያቶች መካከል ቀዳሚ መሆናቸውን በትናንቱ መግለጫው አስታውቋል። \"በአማራ ክልል አንዳንድ ሆስፒታሎች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ተዘግተዋል\" ሲሉ በአማራ እና አፋር ክልሎች የቀይ መስቀል ተወካይ ሚቻ ዌዲኪንደ ተናግረዋል። \"ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ እየሞቱ ነው። የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው፤ ውሃ ወይም መብራት ስለማይኖራቸው እናቶች በቤት ውስጥ እየወለዱ ነው\" ብለዋል የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአማራ እና አፋር ክልል ተወካይ። ከአማራ እና አፋር በተጨማሪ በትግራይ ክልልም ከፍተኛ የሆነ መድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩ ቀይ መስቀል በመግለጫ ተመልክቷል። \"በትግራይ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እንደ ጓንት፣ የቀዶ ሕክምና ቁሳቁሶች እና ሰውነት ውስጥ የሚገቡ የሕክምና ቱቦዎች ሳይቀሩ እየታጠቡ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው\" ሲሉ በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ። ከላይ የተጠቀሱት አይነት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን የጤና መሳሪያዎችን ዳግም መጠቀም፤ ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያሰፋል ይላሉ ተወካይዋ። በአንዳንድ አካባቢዎች ታካሚዎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ ሐኪሞች የሰዎችን ቁስል ለማጽዳት ጨው ለመጠቀም መገደዳቸውን ጭምር አፖሎ ባራሳ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት በፍጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩላቸውን እንዲወጡ በመግለጫው ጠይቋል። ኮሚቴው ከኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን እአአ 2021 ላይ በአማራ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ 130 የጤና ተቋማት ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በዚህም ወደ 120 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ድጋፉን ማግኘታቸውን በመግለጫው አመልክቷል። የቀይ መስቀል ኮሚቴ እያደረገ ካለው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ አካባቢዎች ያለው የምግብ እና የኑሮ ሁኔታ ያሳስበኛልም ብሏል። ኮሚቴው በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ እንዲሁም በመቀለ ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በመጨረሻም ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጨምሮም በቅርቡ ንጹሃን ዜጎችን ለጉዳት የዳረገ ግጭት መኖሩ አሳስቦኛል ብሏል። ኮሚቴው የግጭቱ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሕግጋቶችን እንዲያከብሩ ጠይቋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶች ላይ በተለይም የሕክምና ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት መፈጸሙ የተለያዩ መንግሥታዊና የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው ሪፖርቶች አመልክተዋል። የጤና ተቋማት በገጠማቸው ችግርና በመድኃኒትና በሕክምና መገልገያዎች አለመኖር ምክንያት በአካባቢዎቹ ያሉ ነዋሪዎች ከባድ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው እተነገረ ነው።", "አንድ ውሻ በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዙን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ አንድ ውሻ ከባለቤቱቶቹ በተላለፈ የዝጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ መጠቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የበሽታው ስርጭት ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ራሳቸውን ከቤት እንስሳቶቻቸውም ጭምር ማግለል እንዳለባቸው የሚያሳይ እንደሆነም የጤና ሃላፊዎቹ አስታውቀዋል። ሌሎች እንስሳትን የመበከል አደጋን ለመቀነስ ቆሻሻን በጥንቃቄ ማስወገድ እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። ውሾች በሽታውን ወደ ሌሎች ውሾች ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፉ እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ እስካሁን እንደሌለም ባለሞያዎች ገልጸዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በቆዳ-ለቆዳ ንክኪ እና ሰዎች ጨርቆችን ጨምሮ አልጋ ወይም ፎጣ በቫይረሱ ​​​​ከተያዘ ሰው ጋር በጋራ ሲጠቀሙ የሚተላለፍ በሽታ ነው። በአሁኑጊዜ በዓለም ዙሪያ ወደ 35,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን አብዛኛዎቹ በአውሮፓ፣ በሰሜን እናበደቡብ አሜሪካ ይገኛሉ ። እስካሁን ከበሽታው ጋር በተያያዘ 12 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። የአለም የጤና ድርጅት ባለፈው ሃምሌ ወር ውስጥ ነበር የዝንጀሮ ፈንጣጣን አለማቀፍ የጤና አደጋ ሲል ያወጀው። የመጀመሪያው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ከሰው ወደ ውሻ የተላለፈው በፓሪስ ከተማ ሁለት አንድ ላይ በሚኖሩ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ቤት ውስጥ ነው። ግለሰቦቹ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ማሳየት ከጀመሩ ከ 12 ቀናት በኋላ ነበር በውሻቸው ላይም ምልክቶችን ማየት የጀመሩት። ባለሞያዎች ያደረጉት የዘረመል ትንታኔ እንደሚያሳየው ውሻውን ያጠቃው ቫይረስ ግለሰቦቹን ካጠቃው ጋር ቫይረስ ጋር ተመሳሳይ ነው። የውሻው ባለቤቶችም ውሻው አብሯቸው ሲተኛ እንደነበር ተናግረዋል። በአለም የጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምላሽ ሰጪ ቡድን ውስጥ የቴክኒካል ስራዎች መሪ የሆኑት ዶ/ር ሮሳምንድ ሉዊስ “ይህ ከዚህ በፊት ሪፖርት ያልተደረገ ብሎም ለመጀመሪያ ግዜ የመዘገበ ወደ ውሻ ያጋጠመ ስርጭት ነው ብለን እናምናለን’’ ብለዋል። በተቋሙ የድንገተኛ የጤና አደጋዎች ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ማይክ ራያን “ጉዳዩ ያልተጠበቀ አይደለም” ብለዋል። ነገር ግን በሽታው ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላው መዘዋወሩ እጅግ እንደሚያሳስባቸውም ተናግረዋል። አክለውም አንድ በሸታ ወደ አዲስ የእንስሳ ከተላለፈ በኋላ እንደሚላመድ ብሎም እና በውስጡም ወደ አዲስ ዝርያ እንዲለወጥ እድል እንደሚሰጥ ተናግረዋል። “ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋጠመ ስርጭት ነው። ስለሆነም ውሾች ሊበከሉ ይችላሉ ማለት ነው። ነገር ግን ውሻው ሌሎች ውሾችን ሊበክል ይችላል ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፋል ማለት አይደለም’’ ሲሉ የአለም የጤና ድርጅት የዓለም አቀፍ ተላላፊ በሽታዎች ስጋት ዝግጁነት ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሲልቪ ብሪያንድ ተናግረዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከል በመላው አለም ያለው የክትባት አቅርቦት እስካሁን ድረስ ውስን ነው። ባለፈው ሳምንት ብቻ በበሽታው ተይዘው ሪፖርት የተደረጉ ሰዎች ቁጥር በ 20 በመቶ ጭሯል። ይህም ከሳምንት በፊት ከነበረው በ20 በመቶ ብልጫ አለው። እስካሁን አብዛኛው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሲታይ ወንድ የተመሳሳይ ጾታ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው።", "ጠላፊዎች የታዋቂ ሰዎችን የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ፎቶ እንለቃለን ሲሉ ዛቱ የበይነ መረብ ጠላፊዎች የታዋቂ ሰዎችን የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ሂደት የሚያሳይ መረጃ እንለቃለን ሲሉ ዝተዋል። ጠላፊዎቹ የታካሚዎችን የበፊትና የአሁን ፎቶ በመልቀቅ 'ጉድ እንሠራቸዋለን' እያሉ ነው። 'ዘ ሆስፒታል ግሩፕ' የተሰኘውና በታዋቂ ሰዎች ዘንድ እውቅና ያለው ድርጅት ጠላፊዎቹ ክፍያ ካልተፈፀማቸው መረጃዉን እንደሚያሾልኩ ዝተዋል ሲል አረጋግጧል። ድርጅቱ ይህን ጉዳይ ለሚመለከተው ክፍል አሳውቅያለሁ ብሏል። ሪቪል [REvil] በተሰኘ ስማቸው የሚታወቁት ጠላፊዎቹ 'ሚስጢራዊ የሆኑት' እኚህ ፎቶዎች ለተመልካች ብዙም ደስታ የሚሰጡ አይደሉም ብለዋል። ጠላፊዎቹ በኮምፒውተር ልኬት 900 ጊጋባይት መጠን ያላቸው ፎቶዎች እጃችን ገብተዋል እያሉ ነው። ዘ ሆስፒታል ግሩፕ በዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚው የክብደት ቅነሳና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሆስፒታል ነው። ክብደት መቀነሻ ቀዶ ሕክምና፣ ጡት ማሳደግ፣ የጡት ጫፍ ማስተካከል እንዲሁም አፍንጫ ማረም ሆስፒታሉ በ11 ክሊኒኮቹ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶቹ መካከል ናቸው። ሆስፒታል በቀደመው ጊዜ በታዋቂ ሰዎች አማካይነት ማስታወቂያ ይሠራ ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ይህንን ማድረግ አቁሟል። በፈረንጆቹ 2009 'ቢግ ብራዘር' የተሰኘው የሰዎችን የዕለተ ተለት ሕይወት የሚያስቃኝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አባል የነበረችው አይዝሊን ዘ ሆስፒታል ግሩፕ ሄዳ ጡቷን እንዳሳደገች ተናግራ ነበር። ታዋቂዋ ዘፋኝ ኬሪ ካቶና፣ ተዋናይት ቲና ማሎንና የቴሌቪዥን ኮከቡ ጆዊ ኤሴክስ ወደ ሆስፒታሉ ጎራ ብለው ሕክምና ካገኙ ታዋቂ ሰዎች መካከል ናቸው። ሆስፒታሉ ደንበኞቹን ስለተፈጠረው ጉዳይ በኤሜይል አማካይነት ማሳቁንና በጣም ከባድ ሚስጥር ያላቸው ሰዎች አደጋ ላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ እንደነገራቸው በለቀቀው መገለጫ አስታውቋል። ጠላፊዎቹ እንለቃን ያሉት የአሁንና የቀድሞ ገፅታ የሚያሳይ ፎቶ የታካሚዎችን ማንነት ላያጋልጥ ይችላል ተብሏል። ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ ደንበኛ ሚስጢራዊ ፎቶዎቹ በጠላፊዎች እጅ ወድቆ እንዳይሆን ስጋት እንዳለው ይናገራል። ሳይመን ሄይልስ የተሰኘው ደንበኛ ወደ ሆስፒታሉ ሄዱ ደረቱን አስቀንሶ መጥቷል። ነገር ግን ኩባንያው ጠላፊዎቹ ገንዘብ ስለመጠያቃቸው እንዳላሳወቀው ተናግሯል። \"መረጃዎቻችን በጠላፊዎች እጅ ወድቀው ሊሆን እንደሚችል ተነግሮናል። ነገር ግን ዝርዝር መረጃ አልደረሰንም\" ይላል። በዓለም ዙሪያ ያሉ ጠላፊዎች መረጃ ከመዘበሩ በኋላ በምትኩ ገንዘብ ይጠይቃሉ። ይህ በሳይበር ቋንቋ 'ራንሰምዌር' ይባላል። የመረጃ መረብ ደህንነት መሥሪያ ቤቶች መረጃቸው በጠላፊዎች የተወሰደባቸው ድርጅቶች ገንዘብ እንዳይከፍሉ ይመክራሉ። መረጃ መዝባሪዎች በፈረንጆቹ 2020 ብቻ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደመዘበሩ ይነገራል። በዓለም በጣም ታዋቂ ከሆኑ መረጃ ጠላፊዎች መካከል ሪቪል አንዱ ነው። ከዚህ በፊትም ሁለት ትላልቅ ድርጅቶችን ጠልፎ ገንዘብ ተቀብሏል።", "ኮሮረናቫይረስ፡ ብዙ ተስፋ የተጣለበት የኦክስፎርድ ክትባት አስተማማኝነቱ 70 በመቶ ነው ተባለ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሰዎችን 70 በመቶ ከቫይረሱ መጠበቅ ያስችላል ተባለ። ይህ የክትባቱ ውጤት ይፋ የሆነው የክትባቱ ውጤታማነትን ለመፈተሽ የተካሄደው ጥናት ውጤት መታወቁን ተከትሎ ነው። የኦክስፎርድ ክትባት አስተማማኝነቱ 70 በመቶ ነው መባሉ በባለሙያዎች ዘንድ የተለያየ ስሜትን ፈጥሯል። ከዚህ ቀደም ይፋ የተደረጉት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶች አስተማማኝነት 95 በመቶ መሆኑ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የኦክስፎርድ ክትባት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር ዋጋው ርካሽ መሆኑ እንዲሁም ኦክስፎርድ ሰራሽ ክትባትን ማጓጓዝ እና ማከማቸት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር እጅግ ቀላል መሆኑ በመልካም ጎኑ ተጠቃሽ ሆኗል። በዚህም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የኦክስፎርድ ክትባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አስቀድሞ 100 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባት ብልቃጦችን ለመግዛት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር ውል አስሯል። ይህ ማለት ለ50 ሚሊዮን ሰዎች የሚበቃ ነው። ሰዎች ክትባቱን በሶስት ሳምንት ልዩነት ሁለት ጊዜ ይወስዱታል ተብሏል። የዩኬ ጤና ጥበቃ ኃላፊ ማት ሃንኮክ ለቢቢሲ፤ \"ይህ ወደ ተለመደ አይነት ሕይወት ለመመለስ አንድ እርምጃ ነው\" ሲሉ ተናግረዋል። ነዋሪነታቸው በዩናይትድ ኪንግደም እና ብራዚል የሆኑ 20 ሺህ ሰዎች ላይ የኦክስፎርድ ክትባት ሙከራው ተከናውኗል። የክትባቱን ሙከራ በበላይነት እየመሩ የሚገኙት ፕሮፌሰር አንድሩ ፖላርድ በክትባቱ ውጤት እጅግ ደስተኞች ነን ሲሉ ለቢቢሰ ተናግረዋል። የዩናትድ ኪንግደም መንግሥት 4 ሚሊዮን ክትባቶች ተረክቧል። 96 ሚሊዮን ብልቃጦችን ደግሞ በቅርቡ ከአምራቹ ይቀበላል ተብሏል። ክትባቱ ግን የመድሃኒት ተቆጣጠሪዎችን ይሁንታ ሳያገኝ ለሰዎች አይሰጥም። መድሃኒት ተቆጣጣሪዎች የክትባቱን አቅም ለመፈተሽ እና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደማያስከትል ለማረጋገጥ ቢያንስ ሳምንታት ያስፈልጋቸዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን በቅድሚያ ከሚያገኙት መካከል እድሜያቸው የገፉ ሰዎች፣ የአረጋውያን መኖሪያ ውስጥ የሚኖሩ አዛውንቶች እና የተቋማቱ ሰራተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ የሆናቸው አዛውንቶች ተጠቃሽ ናቸው።", "በመቀለ የሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ተነገረ በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛው ሪፈራል ሆስፒታል በገጠመው የግብዓት ችግር ምክንያት ለታካሚዎች ይሰጥ የነበረውን አግልግሎት ማቋረጡን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ተናገሩ። ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በገጠመው የመድኃኒት አቅርቦት ችግር፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ እና በሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን አገልግሎት መስጠት ማቆሙን የሆስፒታሉ ቴክኒካል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገብረሥላሴ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የእርዳታ አቅርቦቶችን ጨምሮ መሠረታዊ አቅርቦቶች በመቋረጣቸው ምክንያት በክልሉ ውስጥ በርካታ ሰዎች በምግብና በህክምና አቅርቦት እጦት ምክንያት ለችግር መጋለጣቸውን ዓለም አቀፍ ተቋማት መግለጻቸው ይታወቃል። ከተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ በርካታ ህሙማንን ያስተናግድ የነበረው ሆስፒታሉ፤ የገጠመው ችግር ከአቅም በላይ በመሆኑ አገልግሎት ማቋረጡ ተነግሯል። ሃያ ወራት ባስቆጠረው ጦርነት ውስጥ የህክምና መገልገያዎችና መሠረታዊ አቅርቦቶች ተቋርጠውበት የቆየው ዓይደር ሆስፒታል፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆኖ ህሙማንን ለማከም ሲጥር መቆየቱን የገለጹት ኃላፊው፣ አሁን ላይ ግን አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ መድረሱን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በመድኃኒት አቅርቦት እጦት እና በህክምና መሳሪያ ችግር ምክንያት የሚሰጠው አገልግሎት ሲቆራረጥ ቆይቷል የሚሉት ዶክተር ክብሮም “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ማደንዘዣ መድኃኒት ስለሌለ፣ ለድንገተኛ ታካሚዎች ብቻ ህክምና ስንሰጥ ቆይተናል” ብለዋል። “አሁን ደግሞ የመብራት አገልግሎት ስለተቋረጠ ኦክስጅን አምርተው የሚሰጡን ተቋማት ሥራቸውን አቁመዋል። ሆስፒታሉ ሲሰጠው የነበረው የኦክስጅን አገልግሎት ከተበላሸ አንድ ዓመት አልፎበታል” ብለዋል። ከዚህ ባሻገር የነዳጅ አቅርቦት እንደሌለ የሚናገሩት ዶክተር ክብሮም፣ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ደሞዝ ከተከፈላቸው ረጅም ጊዜ በመሆኑ በሥራ ገበታቸው ላይ ለመገኘት እና ለታካሚዎች አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻሉ ገልጸዋል። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድንና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር አብዛኞቹ የክልሉ ጤና ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት መውደማቸው እና አገልግሎት መስጠት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከቀላል የድንገተኛ ህክምና ውጪ አግልግሎት እንደማይሰጥና በተለይ ቀናቸው ሳይደርስ ለሚወለዱ ህጻናት እርዳታ መስጠት እንደማይችል ዶክተር ክብሮም ለቢቢሲ ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ሐኪሞች ከአንድ ዓመት በላይ ደሞዝ ሳይከፈላቸው ሲሰሩ ቢቆዩም፣ አሁን ላይ ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን መርዳት ባለመቻላቸው ከባድ ችግር ውስጥ ሆነ አስከ መለመን የደረሱ እንዳሉ ቢቢሲ ባለፈው ዘግቦ ነበር። በመቀለ ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በመቀለና በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ 3600 ያህል ሠራተኞች እንዳሉት ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ለበርካታ ወራት ወደ ትግራይ የሚገባው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ ባለፈው መጋቢት የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ አቁም ካወጀ በኋላ የምግብና መሠረታዊ አቅርቦቶች ወደ ክልሉ መግባት መጀመራቸው ይታወሳል።", "በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ በሕንድ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ በሦስተኛ የኮሮናቫይረስ ማዕበልን ውስጥ የምትገኘው ሕንድ በዋና ከተማዋ ኒው ዴሊሂ እንዲሁም በፋይናንስ ማዕከልዋ ሙምባይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ትላንት ማክሰኞ በአገሪቱ 37 ሺህ 379 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በሳምንት ውስጥ የአምስት እጥፍ ጭማሪ አሳይቷል። ባለሙያዎች የመጨመሩ ምክንያት ኦሚክሮን የተባለው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ነው ብለዋል። በቫይረሱ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛው የሚሆኑት በዴሊሂ እና ሙምባይ የሚኖሩ ሲሆን ይህም በከተሞቹ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ እንደሆነ አመላካች ተደርጓል። በዚህም ሳቢያ የሁለቱ ከተሞች አስተዳደር የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችን ይፋ አድርገዋል። የሕንድ የክትባት ግብረ ኃይል ኃላፊ ዶ/ር ኤንኬ አሮራ ሦስተኛው የወረርሽኙ ማዕበል በአገሪቱ መጀመሩን ገልፀው \"ሙሉው ማዕበሉ በአዲሱ ዝርያ... ኦሚክሮን ምክንያት የመጣ ይመስላል\" ሲሉ ለአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። አገሪቱ እስካሁን ከ1 ሺህ 700 በላይ በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። ከዚህ መካከል ዋና ከተማዋ ሙምባይ 568 ሰው በመመዝገብ ከፍተኛ ቁጥር የያዘች ሲሆን ዴልሂ 382 ሰዎች በመመዝገብ ሁለተኛ ላይ ተቀምጣለች። የዴልሂ የጤና መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሳትየንዳር ጃይን በከተማው ውስጥ 81 በመቶው የኮቪድ ምርመራዎች በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎችን እንደሚያመላክቱ ተናግረዋል። በዴልሂ የሚገኘው እና ከሕንድ ዋና ዋና ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው የመላው ሕንድ የህክምና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የተሰኘው ሆስፒታል ለዶክተሮች የክረምት ፈቃድ የመስጠት ተግባሩን መሰረዙ ተዘግቧል። እየጨመረ የመጣው በቫይረስ የመያዝ ምጣኔ ሕንድ በሚያዝያ እና በግንቦት ወር ያጋጠማትን አስከፊ ሁለተኛ ማዕበል የሚያስታውስ ነው የተባለ ነው። በዚያ ወቅት ማዕበሉ የመጨረሻ ጫፍ ሲደርስ በየቀኑ በአማካይ ወደ 400,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ይያዙ ነበር። በመላ አገሪቱ ያሉ ሆስፒታሎች የአልጋ እና ህይወት አድን ኦክሲጅን እጥረት የገጠማቸው ሲሆን በክፍት ቦታዎች ላይ የጅምላ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ለማከናወን አስገደዷቸው ነበር። ያ ሁኔታ ቀንሶ ለበርካታ ወራት በቀን ከ10,000 በታች የሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ነበር። ሆኖም አሁን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እንደገና ሲያሻቅብ የግዛት መንግሥታት እገዳዎችን መጣል ጀምረዋል። የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ እንደሚያመለክተው በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎች ከሌሎች ዝርያዎች ጋር ሲነጻፀር የሆስፒታል ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ዝቅተኛ ናቸው፤ ነገር ግን በቫይረሱ የመያዝ መጠን መጨመር ሆስፒታሎች ላይ ጫና ስለሚፈጥር ባለሙያዎች ጥንቃቄ ማድረግን ይመክራሉ። ትላንት ማክሰኞ በዴልሂ ከተማ ባለሥልጣናት በእረፍት ቀናት የሚደረጉ ሁሉንም ወሳኝ ያልሆኑ ተግባራት የሚከለክል ገደብ አውጥተዋል። ዋና ከተማዋ ባለፈው ሳምንት የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ሲኒማ ቤቶች እንዲዘጉ እንዲሁም የምሽት የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች። የእረፍት ቀናት ወይም የሳምንት መጨረሻ ላይ የሚተገበረው የሰዓት እላፊ ገደብ የታወጀው የከተማው ዋና አስተዳዳሪ አርቪንድ ኬጅሪዋል ቫይረሱ ከተገኘባቸው ከሰዓታት በኋላ ነው። በሕንድ ውስጥ ከአዋቂዎች 63 በመቶ ያህሉ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቢያንስ የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል። ሕንድ እስካሁን ከ34 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 482 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በኮሮናቫይረስ መሞታቸውን ሪፖርት አድርጋለች። ባለሙያዎች ግን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ የበለጠ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።", "ከኢቦላ ያገገመው ሐኪም፡ “የምሞት መስሎኝ ነበር” ኡጋንዳ በአሁኑ ወቅት የተከሰተውን ገዳዩን የኢቦላ በሽታ ለመቆጣጠር እየታተረች ትገኛለች። ኢቦላን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት በበሽታው ተይዞ የነበረው ሐኪም “የምሞት መስሎኝ ነበር” ይላል። በዚህ ዘገባ ስለ ኢቦላ ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ በሙሉ ተብራርቷል።", "ተጨማሪ ዘጠኝ የኮቪድ-19 ምልክቶች ይፋ ሆኑ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ላይ ተጨማሪ ዘጠኝ ምልክቶች ተጨመሩ። እነዚህ ምልክቶች ከዚህ በፊት የነበሩትን የሚያሰፉና ተጨማሪ ነገሮችን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ናቸው። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው አዲስ መመሪያ ውስጥ የጉሮሮ ህመም፣ የጡንቻ ህመም እና 'ተቅማጥ' ከተካተቱት አዳዲስ የኮሮረናቫይረስ ምልክቶች መካከል ናቸው። ይህ መመሪያ የወጣው ወረርሽኙ ከተከሰተ ሁለት ዓመታት ካለፈው በኋላ ሲሆን እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ይደረግ የነበረው የነጻ ምርመራ ከተቋረጠ ከቀናት በኋላ ነው። ነገር ግን የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልእክት አዳዲሶቹ ምልክቶች ከጉንፋን ብዙም ያልተለዩ መሆናቸውን አሳስቧል። ከዚህ በፊት የሚታወቁት የኮቪድ-19 ምልክቶች ትኩሳት፣ የማያቆም ሳል፣ የሽታ እና የመቅመስ ስሜቶቻችን መጥፋት እንዲሁም ድካም የሚጠቀሱ ናቸው። ወረርሽኙ ባጋጠመበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ወቅት የስርጭቱን አካሄድ መረዳትና ምልክቶቹን መለየት ከባድ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ዓለም ስለቫይረሱ ማወቅ ከሚገባው አብዛኛውን ነገር አውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ቢሆን ከረጅም ጊዜ በፊት ምልክቶች ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በርካታ ናቸው። ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ትክክለኛ ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው እንዲሁም ምን አይነት ምልክቶችን የሚያሳይ ሰው ነው ምርመራ ማድረግ ያለበት የሚሉት ጥያቄዎች መከራከሪያ ሆነው ቆይተዋል። ለምሳሌ ራስ ምታት የኮሮናቫይረስ ምልክት ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል ቢሆንም ራሱን ያመመው ሰው በሙሉ ግን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አይችልም። ምክንያቱም ራስ ምታት ከኮሮናቫይረስ ውጪ በበርካታ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ትኩሳት፣ ሳል፣ ማሽተት ማቆም አልያም ጣእም ማጣት በርካቶችን የማያከራክሩ ምልክቶች ሲሆኑ አሁን ላይ ደግሞ ዘጠኝ ተጨማሪ ምልክቶች እንዲጨመሩ ተደርጓል። እነዚህም ትንፋሽ ማጠር፣ ድካም፣ የሰውነት መላሸቅ፣ ራስ ምታት፣ የጉሮሮ ሕመም፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ [ንፍጥ]፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ተቅማጥ እና አጠቃላይ የጤንነት ስሜት ማጣት ናቸው። ዩኬ ውስጥ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4.9 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን መንግስት በነጻ ሲያከናውነው የነበረው ምርመራም ባሳለፍነው ሳምንት ተጠናቋል። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ እንደሚለው ሰዎች አሁንም ቢሆን በተቻላቸው መጠን ከቤታቸው ላለመውጣት መሞከርና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውንም ንክኪ መቀነስ አለባቸው። በተለይ ደግሞ እነዚህን ምልክቶች የሚያሳይ ሰው ምርመራ ማድረግና እራሱን ከሰዎች መለየት እንዳለበት ኤጀንሲው አሳስቧል።", "ኮሮናቫይረስ ፡ አሜሪካ የኮቪድ-19 ምልክት የማያሳዩ አይመረመሩም የሚለውን ውሳኔ ቀለበሰች ባለፈው ወር አሜሪካ የኮቪድ-19 ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ምርመራ ማድረግ የለባቸውም የሚል አወዛጋቢ ውሳኔ አስተላልፋ ነበር። አሁን ግን ይህ ውሳኔ በጤናው ዘርፍ አመራሮች መቀልበሱ ተገልጿል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ተቋም [ሲዲሲ] እንዳለው በሽታው ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው በአጠቃላይ መመርመር አለባቸው። ተቋሙ ከዚህ ቀደም የነበረው አሠራር ነሐሴ ላይ ለውጥ ተደርጎበት የነበረ ቢሆንም ምርመራን በተመለከተ ወደ ቀድሞው መርህ ተመልሷል። አወዛጋቢ የተባለው ውሳኔ የተላለፈው ያለሳይንቲስቶች ምክረ ሐሳብ ነው ተብሏል። ኒው ዮርክ ታይምስ የጠቀሳቸው ምንጭ እንዳሉት፤ ውሳኔው በሲዲሲ ድረ ገጽ መለጠፉን ባለሙያዎች ተቃውመዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው፤ በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ውሳኔውን አንቀበልም ብለዋል። ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ እንደሚሉት በአወዛጋቢው ውሳኔ ውስጥ የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጅ ሊኖርበት ይችላል። ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎችን ቁጥር በመቀነስ ሪፖርት የሚደረጉ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን አሃዝ ለመቀነስ አስበው እንደሆነም ተጠቁሟል። ፕሬዝዳንቱ ሰኔ ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ደጋፊዎቻቸውን “ባለሥልጣኖችን እባካችሁ ምርመራ ቀንሱ ብያቸዋለሁ” ማለታቸው ይታወሳል። አንድ የዋይት ሐውስ ባለሥልጣን የፕሬዘዳንቱ ንግግር “ቀልድ ነበር” ብለዋል። በሌላ በኩል የሲዲሲ አመራሮች ውሳኔው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንደሌለው ገልጸዋል። ለውጡ ወቅታዊውን የኅብረተሰብ ጤናን የተመረኮዘ ነው ሲሉም ለሮይተርስ ተናግረዋል። የቀድሞው ውሳኔ መቀልበሱ ባለሙያዎችን አስደስቷል። የተላላፊ በሽታዎች ማኅበር ፕሬዘዳንት የሆኑት ቶማስ ፋይል \"ሲዲሲ ሳይንስን መሠረት ወዳደረገ ምርመራ መመለሱ ለኅብረተሰብ ጤና መልካም ዜና ነው። ከወረርሽኙ ጋር የምናደርገውን ትግልም ያግዛል” ብለዋል። ሲዲሲ ውሳኔውን መቀልበሱን በተመለከተ “የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን እንዲሁም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን መመርመር ያስፈልጋል” ብሏል። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በስድስት ጫማ ርቀት ቢያንስ ለ15 ደቂቃ የተገናኙ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ባያሳዩም እንዲመረመሩ ተቋሙ ይመክራል። በአሜሪካ በአሁኑ ወቅት ወደ 7 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ይህም በመላው ዓለም በሽታው ከተገኘባቸው የሰዎች ብዛት አንድ አምስተኛው ነው። በወረርሽኙ ሳቢያም 200,000 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ ይህም ከዓለም አገራት ከፍተኛው ነው።", "ፋይዘር የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ታዳጊ አገራች እንዲያመርቱት ፈቀደ ፋይዘር በሙከራ ደረጃ ያለውን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ እንክብል መድኃኒቱን ታዳጊ አገሮች እንዲሠሩት እና እንዲያከፋፍሉት ፈቀደ። የአሜሪካው መድኃኒት አምራች ፋይዘር በ95 ታዳጊ አገራት እንክብል መድኃኒቱ እንዲመረት የተስማማው የተባበሩት መንግሥታት ከሚደግፈው ሜድስንስ ፔሸንት ፑል ድርጅት ጋር በመጣመር ነው። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ከሠራ በኋላ 53 በመቶ ለሚሆነው የዓለም ሕዝብ ያዳርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ስምምነቱ እንደ ብራዚል ያሉ በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው አገራትን አያካትትም። መድኃኒቱ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ጎልማሶች በጽኑ በሽታ እንዳይያዙ እንደሚከላከል ፋይዘር አስታውቋል። መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት መፍቀዱ \"የመድኃኒቱን ተደራሽነት ያሰፋዋል\" ሲል ገልጿል። በታዳጊ አገራት ከሚመረተው መድኃኒት ፋይዘር የባለቤትነት (ሮያሊቲ) ክፍያ አይወስድም። ወረርሽኙ ለዓለም አስጊ ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ በሁሉም አገራት ትርፍ እንደማይሰበስብም ይፋ አድርጓል። ፋይዘር ለኮቪድ-19 ማከሚያ እየሠራ ያለው ፓክሎቪድ የተባለ መድኃኒት ነው። ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሞትና ሆስፒታል የመግባት እድልን በ89 በመቶ ይቀንሳል ተብሏል። የሜድስንስ ፔሸንት ፑል ኃላፊ ቻርልስ ጎሬ እንዳሉት መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት ፍቃድ መሰጠቱ መልካም ነው። \"ይህ መድኃኒት በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ሕይወት ያድናል\" ብለዋል። መድኃኒቱን እንዲሠሩ ፈቃድ ካገኙ አገራት አብዛኞቹ በአፍሪካ እና እስያ ይገኛሉ። እንደ ብራዚል፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ አርጀንቲና እና ታይላንድ ያሉ ክፉኛ በወረርሽኙ የተጎዱ አገራት በስምምነቱ አልተካተቱም። የኮሮናቫይረስ ሕክምና እንዲሁም ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ ይህ እርምጃ በቂ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ተችተዋል። ፋይዘርን ጨምሮ ሌሎችም የኮቪድ-19 ክትባት አምራቾች የባለቤትነት መብታቸውን አንስተው፤ ክትባቱ በሌሎች አገራት እንዲመረት ፈቃድ እንዲሰጡ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለዋል። ዶክተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ ባወጣው መግለጫ፤ ፋይዘር ለታዳጊ አገራት የሰጠው ፈቃድ የኮሮናቫይረስ መድኃኒት በመላው ዓለም እንዲደርስ እንደማይረዳ ተችቷል። \"ወረርሽኙን መግታት ከፈለግን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒት ለሁሉም ሰው፣ በሁሉም አገር መዳረስ አለበት\" ሲሉ የድርጅቱ የሕግ አማካሪ ዩአንክዮንግ ሁ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም መርክ የተባለው መድኃኒት አምራች ድርጅት ሞልኑፒራቪር የተባለ የኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ከሜድስንስ ፔሸንት ፑል ጋር በጥምረት ለማምረት ተስማምቷል።", "ሦስት ልጆቻቸው ዐይነ ስውር ከመሆናቸው በፊት ዓለምን እየዞሩ ያሉት ቤተሰቦች የኢዲት እና የሴባስቲያን ልጆች አንድ ቀን አይነ ስውር ይሆናሉ። ከአራት ልጆቻቸው ሦስቱ በዘር የሚተላለፍ እና በሂደት የዐይን ብርሃንን የሚያሳጣ በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በመሆኑም ወላጆች ችግሩ ከመከሰቱ በፊት በልጆቻው ላይ ትውስታ ለማስቀመጥ በርካታ የዓለም ክፍልን በመዘዋወር ለማሳየት ወስነዋል። በሽታው ምንም አይነት ምልክት አይታይበትም። ሰዎች ከውልደታቸው ጀምሮ ይዘውት የሚመጡት ነገር ነው። ይህ ችግር በልጆቻቸው ላይ እንደተከሰተ ያወቁት እነዚህ ካናዳውያን ቤተሰቦች የአንድ ዓመት ጉዞ ማድረግ ከጀመሩ ስድስት ወር ሆኗቸዋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥም በሦስት አህጉራት ስድስት አገራትን ጎብኝተዋል።", "ኮሮናቫይረስ፡ የዕድሜ ባለጠጋዎቹ ጥንዶች በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ተሞሸሩ በዊልቲሸር በሚገኝ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል ውስጥ የሚኖሩ የ85 ዓመት አዛውንት 91 ዓመት የሞላቸውን ፍቅረኛቸውን በማዕከል ውስጥ አግብተዋል። ይህ የዕድሜ ባለፀጋዎቹ ጋብቻ ሊፈፀም የቻለው የአካባቢው አስተዳደር በሰጠው ልዩ ፍቃድ መሆኑም ተነግሯል። ሁለቱ ጥንዶች ፒተር ስሚርለስ እና ጄን ሮብሰን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ከዚህ ቀደም ብለው ለማድረግ ያሰቡ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለማራዘም ተገደዋል። ሆኖም ከፈረንጆቹ ገና በኃላ የፒተር የጤንነት ሁኔታ እያሽቆለቆለ ሲመጣ ሀኪማቸው የሰርግ ስነ ስርዓቱ በፍጥነት እንዲከወን መክሯቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ጥንዶቹ በዊልቲሸር፣ ፑተር በሚገኝ ሴደር በተሰኘ የእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ጋብቻቸውን ለመፈፀም በቅተዋል። ሁለቱ ጥንዶች በፍቅር 26 ዓመታት ቆይተዋል። \"የመጀመሪያውን የ'ላግባሽ' ጥያቄ ያቅረበልኝ ከ 25 ዓመታት በፊት ቢሆንም 'ለምን እንጣደፋለን?' ብዬዋለው\" የሚሉት አዲሷ የዕድሜ ባለጠጋ ሙሽራ \"ይህ መቼም የሚሆን አይመስልም ነበር\" ሲሉ ገልፀዋል። የጥንዶቹ የጋብቻ ስነ ስርዓት ከመፈፀሙ አስቀድሞ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ሁኔታ በተመለከተ ምልከታ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ የጥንቃቄ መንገዶች መተግበራቸውም ተገልፃል።", "ኮሮናቫይረስ፡ በአውስትራሊያ የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ከለይቶ ማቆያ ሆቴሎች ጋር የተገናኘ ነው ተባለ በአውስትራሊያዋ ከተማ ቪክቶሪያ የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ከለይቶ ማቆያ ሆቴሎች ጋር የተያያዘ መሆኑ ተገልጿል። ከሌላ አገራት የተመለሱ መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ባቆዩባቸው ሆቴሎች ወረርሽኙ መነሳቱም በምርመራ ተጣርቷል። በዚህ ምርመራ እንደተገኘው የሆቴሉ አጠቃላይ ሰራተኞችም ያልተገባ ስልጠና ወስደዋል ተብሏል። የአውስትራሊያ ሚዲያ እንደዘገበው የሆቴሉ ጠባቂዎች ጭምብልም ሆነ ሌሎች የመከላከያ ቁሳቁሶችን ማድረግ አስፈላጊ አይደለም፤ አካላዊ ርቀታችሁን እስከጠበቃችሁ ድረስ የሚል ምክር ተሰጥቷቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ቪክቶሪያ ላይ አዲስ ዙር ወረርሽኝ ተከስቷል፤ ከተማው እንቅስቃሴዋ እንዲታገድ ትዕዛዝ ተላልፏል። በሌላኛዋ ከተማ ሜልቦርን እንዲሁም ጥብቅ የተባለ የእንቅስቃሴ ገደብ ለስምንት ሳምንታት ተጥሎባታል። በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በቪክቶሪያ 282 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 25ቱ ሞዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮም ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል። መጋቢት መጨረሻ ላይ የአውስትራሊያ ፌደራል መንግሥት በሌላ አገራት የሚኖሩ ዜጎቹ ሲመለሱ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አለባቸው የሚል ውሳኔን አስተላልፏል። ይህንንም ተግባራዊነት የሚያስፈፅሙት የተለያዩ ከተማ አስተዳዳሪዎች ናቸው። በሜልቦርን የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ቤን ሃውደን እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ውስጥ 99 በመቶው ከውጭ አገራት ከመጡ መንገደኞች ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ስለ መንገደኞቹ ማንነትም ሆነ የትኞቹ ሆቴሎች እንደሆኑ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም። ምርመራው ሆቴሎች ለይቶ ማቆያዎቻቸውን እንዴት እያስተዳደሩ እንደነበርም በምርመራው በጥልቀት እየታየ ነው ተብሏል፤ ይህም ለወደፊቱ ለይቶ ማቆያዎች በማሻሻያነት ግብአት እንዲሆን ነው። ለይቶ ማቆያዎቹ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መግታት ሳይሆን የበለጠ ማስፋፊያ ሆነዋልም ተብሏል።", "በአውስትራሊያ በምርመራ ማዕከል ስህተት ብዙዎች ኮሮናቫይረስ እንደሌለባቸው ተነገራቸው በአውስትራሊያ ሲድኒ ውስጥ በሚገኝ የምርመራ ማዕከል በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ኮሮናቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ ናችሁ ተባሉ። በሲድኒ በርካቶች በወረርሽኙ እየተያዙ ቢሆንም በምርመራ ማዕከሉ ስህተት ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቫይረሱ እንደሌለባቸው ተነግሯቸዋል። ስህተቱ የተፈጠረው በፈረንጆች ገና ሰሞን ነው። ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ናሙና ሲፈተሽ በተፈጠረ የመረጃ ስህተት ሳቢያ ውጤቱ የተሳሳተ መሆኑም ተገልጿል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን መስፋፋት ከጀመረ ወዲህ በአውስትራሊያ በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ብዙ ሰዎች ምርመራ እያደረጉ መሆኑ የመረጃ መጨናነቅ መፍጠሩም ተጠቁሟል። ቫይረሱ እያለባቸው የለባችሁም የተባሉት ሰዎች በዓመት በዓል ሰሞን ቫይረሱን ወደ ወዳጅ ዘመዶቻቸው አስተላልፈው ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። ሲድፓዝ የተባለው የምርመራ ማዕከል ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቋል። ወደ 886 ሰዎች የምርመራ ውጤታቸው የተሳሳተ የሆነው ባልተጠበቀ ሁኔታ ምርመራ ያደረጉ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ መሆኑን ቤተ ሙከራው ገልጿል። 400 ሰዎች የገና ዕለት ቫይረሱ እንደሌለባቸው ቢነገራቸውም በነጋታው ግን ትክክለኛ ውጤታቸው ተገልጾላቸዋል። ከእነዚህ ሰዎች በኋላ ተጨማሪ 486 ሰዎች ቫይረሱ ቢኖርባቸውም በስህተት የለባችሁም መባላቸውን ምርመራ ማዕከሉ ይፋ አድርጓል። የሰዎች ናሙና በዲጂታል መንገድ ይመረመር እንደነበረና ከሰሞኑ ግን በሰው ኃይል ምርመራ መደረግ በመጀመሩ የተፈጠረ ክፍተት እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በኋላ ወደ ዲጂታል ምርመራ እንደሚመለሱም አክለዋል። ስታፋኒ ኮሎና የተባለች የሲድኒ ነዋሪ ቫይረሱ እያለባት የለብሽም ከተባለች በኋላ ከቤተሰቦቿ ጋር እንደተገናኘችና ቫይረሱን አስተላልፋባቸው ሊሆን እንደሚችል ተናግራለች። የጤና ሚኒስትሩ ብራድ ሀዛርድ ስህተቱ የተፈጠረው ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር በጣም በመጨመሩ ነው ብለዋል። የቫይረሱ ስርጭት ከጨመረ ወዲህ በየቀኑ ምርመራ የሚደረግላቸው ሰዎች ቁጥር ከ117,000 ወደ 145,000 አድጓል።", "ኮሮረናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት አሻቀበ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ማለፉን ተገለጸ። የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ሐሙስ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም ባወጣው ዕለታዊ የወረርሽኙ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በበሽታው በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 031 መድረሱን አመልክቷል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ባሉት ሦስት ወራት፤ ማለትም ባለፉት ጥር፣ የካቲትና መጋቢት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እያሻቀበ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። የወረርሽኙ በማኅበረሰብ ደረጃ መስፋፋቱ አሳሳቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በወረርሽኙ ሳቢያ በጽኑ የሚታመሙና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎችም ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከወራት በፊት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበሩት ከአምስት መቶ ብዙም ሳይርቅ በመቶዎቹ የሚቆተሩ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በበሽታው ክፉኛ ታመው የጽኑ ህሙማን ክትትልና ድጋፍን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከአምስት መቶ በታች ሆኖ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ወራት ግን አሃዙ ከአምስት መቶ አልፎ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ ደርሷል። በተመሳሳይ በየቀኑ በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስራዎቹ የሚቆጠር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ አሁን ግን ከሃያዎቹ አስከ ሰላሳዎቹ የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እየተመዘገበ ነው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጾ የነበረ ሲሆን ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር \"የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ\" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ \"የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው\" ሲል ገልጿል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጡ እንዳልሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። በየዕለቱ በበወረርሽኙ በጽኑ ታመው ድጋፍ የሚሹት ህሙማን ቁጥር በመቶዎች ከመቆጠር አልፎ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱ የጤና ተቋማት ለህሙማኑ እንክብካቤና ድጋፍ ለመስጠት ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር \"አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል\" ይገኛል ብሏል። ሐሙስ ዕለት በወጣው የበሽታው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረትም 33 ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል። በዕለቱ 8 ሺህ 878 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 2 ሺህ 149ኙ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በበሽታው ተይዘው ከነበሩት መካከል ደግሞ 1 ሺህ 288 አገግመዋል። አስካሁን በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 236 ሺህ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3 ሺህ 285 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 175 ሺህ 879 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።", "ኖርዌይ ፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ ሲዝናኑ የነበሩ ሰዎች በጭስ ታፍነው ሆስፒታል ገቡ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ከመሬት በታች ባለ ዋሻ ውስጥ ተሰባስበው እየተዝናኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ20 የሚበልጡት በካርበን ሞኖክሳይድ ጭስ ታፍነው በመመረዛቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግለሰቦቹ ሊገኙ የቻሉት በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች በዋሻው ውስጥ ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ራሳቸውን ስተው ወደ ጎዳና በመውጣት ወዲያ ወዲህ ሲሉ ካገኟቸው በኋላ ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎቹ ጓደኞቻቸው በጭሱ ታፍነው ከዋሻው ውስጥ በመውጣታቸው አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል። ባለስልጣናቱ የፓርቲው ታዳሚዎችን ለመመረዝ ያበቁት ወደ ዋሻው ይዘው ከገቡት አነስተኛ ጄኔሬተር በሚወጣ ጭስ ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። በጭሱ የመመረዝ ጉዳት ካጋጠማቸው 25 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዋሻው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች ናቸው። ግለሰቦቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተም \"እድለኞች ናቸው፤ የሁሉም የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ ነው። በጤናቸው ላይ ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም\" ሲሉ በኦስሎ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ዋና ሐኪም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ከ20 በላይ ሰዎች በጭስ በታፈኑበት በዚህ ዝግጅት ላይ 200 የሚደርሱ ሰዎች ታድመውበት እንደነበር የኦስሎ ፖሊስ አስታውቋል። በተጨማሪም ታምመው ወደ ሆስፒታል ከገቡት የፓርቲው ታዳሚዎች ውጪ ያሉት ማቅለሽለሽ፣ የራስ ምታት፣ ራስን የመሳት ስሜት ካጋጠማቸው ወደ ሐኪም ቤት እንዲሄዱ ፖሊስ መክሯል። ፖሊሶች በአደጋው ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት ከዋሻው ወጥቶ የሄደ የዝግጅቱ ታዳሚ እንዳለው በስፍራው በነበረው የታፈነ አየር ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ውጪ እየወጣ አየር ሲወስድ ነበር። የኦስሎ ፖሊስ በዋሻው ውስጥ ስለተካሄደው ዝግጅት ቀድሞ ጥቆማ የደረሰው ቢሆንም በወቅቱ ለምን እርምጃ መውሰድ እንዳልቻለ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።", "ኮሮናቫይረስ፡ በሜክሲኮ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክትባቶች ተሰረቁ በሜክሲኮዋ ሞሬሎስ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክትባቶች ተሰርቀዋል ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ጦር ምርመራ ከፍቷል። ሜክሲኮ ይህንንም ስርቆት ለመመርመርና ጥፋተኞቹንም በቁጥጥር ስር ለማዋል በመላው አገሪቷ ጦሯን አሰማርታለች። በዋናነትም በአገሪቷ አድራጊና ፈጣሪ ከሆኑት የማፊያ ቡድን እጅ ክትባቶቹም እንዳይገባ ስጋት ስለፈጠረም ነው ሰራዊቱ የተሰማራው። \"ስርቆቱ ምናልባት የተፈፀመው ታማኝ ባልሆነ የሆስፒታሉ የክትባት ቡድን አባል ሊሆን ይችላል\" የሚል መግለጫም ከመንግሥት በኩል ወጥቷል። የተዘረፈው የክትባት መጠን አልተጠቀሰም። ሜክሲኮ 129 ሚሊዮን ህዝቦቿን በነፃ ክትባት ለመክተብም ቃል ገብታለች። በአለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ የሆነቸው ሜክሲኮ 140 ሺህ ዜጎቿንም በቫይረሱ አጥታለች። ይህም አሃዝ ከአለም አራተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ሶኖራ በምትባለው ግዛት ታጣቂዎች አንድ ሆስፒታል ውስጥ በመግባት ለኮሮናቫይረስ ህሙማን የሚውል የማገዣ መሳሪያ መተንፈሻ (ኦክስጅን) መዝረፋቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል። ዘራፊዎቹ በሆስፒታሉ ሰራተኞች ላይ ጥይት ከደገኑ በኋላ ኦክስጅኑ የት እንደሚቀመጥ ጠይቀዋቸዋል። በመቀጠልም ሶስት ኦክስጅን የተሞላበት መሳሪያና አራት የኦክስጅን ማስቀመጫን ይዘው ሄደዋል ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኦክስጅን ስርቆት በሌላለ አካባቢም እንዲሁ የተከሰተ ሲሆን በቅርቡም የተሰረቀ 44 የኦክስጅን መሳሪያዎችን የያዘ የከባድ ጭነት መኪና ሜክሲኮ ከተማ አቅራቢያ ተይዟል። በርካታ ዜጎች ህሙማን ቤተሰቦቻቸውን በየቤቶቻቸው እንዲያቆዩ በተገደዱበት ወቅት የማገዣ መሳሪያ መተንፈሻ (ኦከስስጅን)ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። አገሪቷ ባጋጠማት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማንም ቁጥር ሆስፒታሎች ሞልተዋል።", "የጉሮሮ ካንሰር ለምን የአርሲ እና የባሌ አካባቢ ማህኅረሰብን በተለየ ያጠቃል? የጉሮሮ ካንሰር፣ ገዳይ ከሆኑ የካንሰር ዓይነቶች መካከል አንዱ ነው። በተለያዩ የዓለማችን አገራት በጉሮሮ ካንሰር የሚጠቁ ሰዎች ቢኖሩም ከሌሎች በተለየ ግን ስርጭቱ ሰፋ ብሎ የሚታይባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። እነዚህ አገራትም በምሥራቅ እና በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በእስያ የሚገኙ አገራት ናቸው። ኢትዮጵያም የጉሮሮ ካንሰር በስፋት ከሚስተዋልባቸው አገራት መካከል ትገኛለች። ምንም እንኳ እርግጠኛው የጉሮሮ ካንሰር መነሻ ምክንያቶች እነዚህ ናቸው ተብሎ ባይበየኑም፣ በበርካታ አገራት የአልኮል መጠጥን የሚያዘወትሩ፣ በሲጋራ ሱስ የተጠመዱ ሰዎች በጉሮሮ ካንሰር እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ። በተጨማሪም የሚፋጁ ምግቦች እና መጠጦችን የሚያዘወትሩ ለጉሮሮ ካንሰር የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን እነዚህ ጥናቶች ጠቁመዋል። ካንሰር ምንድን ነው? ካንሰር ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ሴሎች ያለ አግባብ ሲበዙ የሚፈጠር በሽታ ነው። ይህ ያለ አግባብ የሴሎች መባዛት፣ ሰውነት ላይ እብጠት ይፈጥራል። ይህ እባጭም በጊዜ ሂደት እያደገ የሚሄድ ነው። ዶ/ር ጂልቻ ድሪባ የካንሰር ስፔሻሊስት እና በበሽታው ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን በመስራት ላይ ይገኛሉ። \"ካንሰር ከተፈጠረበት የአካላችን ክፍል በመነሳት እየተስፋፋ የሚሄድ ሲሆን፣ የሰውነታችንን ምግብም ይሻማል። በዚህ ሂደትም በሙሉ ሰውነታችን ላይ በመስፋፋት ሕይወትን እስከ ማሳለፍ ይደርሳል\" ይላሉ ዶ/ር ጂልቻ። ስለጉሮሮ ካንሰርም ሲያብራሩ በኢትዮጵያ ከሌሎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በተለየ በአርሲ እና በባሌ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ይናገራሉ። እርሳቸውም የባሌ እና የአርሲን ማኅበረሰብን በስፋት እየጎዳ የሚገኘውን ይህንን የጎሮሮ ካንሰር ላይ አራት ጥናቶችን ይፋ አድርገዋል። የአርሲን እና የባሌን ማኅበረሰብን ለምን? ይህ የካንሰር ዓይነት የጉሮሮ ቱቦን የሚያጠቃ ሲሆን 'የጎሮሮ ካንሰር' በመባል ይታወቃል። ኢትዮጵያ ውስጥም በተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ ላይ ይስተዋላል። \"በአገር ደረጃ በዚህ የካንሰር ዓይነት ተይዘው በብዛት ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች በተለይ ከባሌ እና ከአርሲ አካባቢ ነው። እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ ለዓመታት ጥናት ሳደርግ ቆይቻለሁ። ምሥራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቡታጅራ እና ስልጤ አካባቢዎችም እንደ አርሲ እና ባሌ ባይሆንም ይህ በሽታ ከሚታይባቸው አካባቢዎች መካከል ናቸው።\" ይህ የካንሰር ዓይነት ለምን በእነዚህ ሁለት አካባቢዎች በስፋት ይከሰታል? እንደ ዶ/ር ጂልቻ ጥናት ከሆነ ዋናው ምክንያት በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩት ማኅበረሰቦች አዘውትረው ከሚመገቡት ምግብ ጋር የሚያያዝ ነው። \"ለዚህ የካንሰር ዓይነት ጥናቶች እንደምክንያት የሚጠቅሱት ሁለት ነገሮች አሉ። እነርሱም አልኮል እና ትኩስ [የሚፋጁ] ምግቦችን መመገብ ናቸው። በአርሲ እና በባሌ አካባቢ ደግሞ አልኮል ብዙም የማይዘወተር ነገር ነው። ስለዚህ ምክንያቱ ሊሆን የሚችለው የሚመገቡት ምግብ ነው ማለት ነው\" ይላሉ። ልክ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ሰዎች እንጀራ በየዕለቱ እንደሚመገቡት ሁሉ በባሌ እና በአርሲ ማኅበረሰብ ባህላዊ ምግብ የሆነው ገንፎ የዚህ ካንሰር መነሻ መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ ማስረጃዎች እንዳሉ ዶ/ር ጂልቻ ይናገራሉ። \"የእነዚህ አካባቢ ነዋሪዎች በብዛት ገንፎ ይመገባሉ። ገንፎ ደግሞ በባህሪውም በባህልም ትኩሱን ነው የሚበላው። ይህ ደግሞ በጊዜ ሂደት ለዚህ የካንሰር ዓይነት እንድንጋለጥ ያደርጋል ማለት ነው\" በማለት ስለዚህም እንደመፍትሄ ሰዎች ይህንን ምግብ ሲመገቡ አቀዝቅዘው እንዲበሉ ባለሙያው ይመክራሉ። በተጨማሪም በአመጋገብ ልማድ ምክንያት ለዚህ የጤና ችግር ተጋላጭ የሆኑ አካባቢ ነዋሪዎችን የአመጋገብ ሥርዓትን መቀየር አስፈላጊ መሆኑንም ዶ/ር ጂልቻ ጠቅሰዋል። ባለሙያው ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ገንፎ በየዕለቱ መመገብ ለጉሮሮ ቱቦ ካንሰር የመጋለጥ እድልን እነደሚያሰፋ ይገልጻሉ። ይህ የጉሮሮ ቱቦ ካንሰር ምን ያህል አስከፊ ነው? ዶ/ር ጂልቻ እንደሚሉት ይህ የካንሰር ዓይነት ከሌሎች የካንሰር ዓይነቶች አንጻር ለማከም የሚያስቸግር እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕይወትን ሊያሳጣ የሚችል ነው። \"አሁን አሁን ብዙ የካንሰር ዓይነቶችን ማዳን እየተቻለ ነው። የጎሮሮ ቱቦ ካንሰር ግን በጣም አስከፊ ነው። አንዴ ከያዘ ተመልሶ የዳነን ሰው ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው\" ይላሉ። \"በየጎሮሮ አካባቢ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ እንኳ በጣም አስቸጋሪ ነው። በቱቦ አካባቢ ያሉት ሌሎች የሰውነታችን አካላት በጣም ወሳኝ ናቸው። ልባችን የሚገኘው በዚያ አቅራቢያ ነው። ሳንባችንም እንደዚሁ። ከዚያ በተጨማሪ ትልቁ የደም ቧንቧ፣ አኦርታ የሚባለውም የሚገኘው በዚሁ አካባቢ ነው። ስለዚህ ይህ ካንሰር ከያዘ ቶሎ ወደ እነዚህ የአካል ክፍሎች ይስፋፋል ማለት ነው\" በማለት የሚያስከትልውን ውስብስብ ችግር ይገልጻሉ። ስለዚህ ይህ የካንሰር ዓይነት አንዴ ከያዘን ረዥም ጊዜ ሳይሰጥ በወራት ጊዜ ውስጥ ሊገድል ይችላል ይላሉ። የዚህ ካንሰር ዓይነት ምልክቶች ምን ምንድን ናቸው? በዚህ ካንሰር ዓይነት የተያዘ አንድ ታማሚ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያየው ምልክት የደረት ማቃጠል ነው። ይኹን እንጂ ብዙ ሰዎች ይህ ምልክት የቀላል ሕመሞች ምልክት አድርገው ስለሚያስቡ ወደ ሆስፒታል ከመሄድ ይልቅ፣ አቅልለው በመመልከት የጨጓራ መድኃኒት እንደሚወስዱ በጥናታቸው ማረጋጋጣቸውን ይናገራሉ። \"በዚህ የካንሰር ዓይነት የተያዘ ሰው ደረቱ አካባቢ የማቃጠል ስሜት ከመሰማት ባሻገር፣ በሂደት ምግብ መዋጥ ሊያስቸግረው ይችላል። መጀመሪያ ላይ ጠጣር ምግቦችን ከዚያ ደግሞ ፈሳሽ፣ መጨረሻ ላይ ምራቁን ጭምር መዋጥ ይቸገራል። ከዚያም ክብደቱ በጣም ይቀንሳል\" ይላሉ።", "ሕንድ ፡ በአንድ ሆስፒታል ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ 10 አራስ ሕፃናት ሞቱ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በሕንድ አንድ ሆስፒታል ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ህይወት ለማትረፍ የቻሉትን ቢያደርጉም አስር አራስ ሕፃናት ህይወት ማለፉ ተነገረ። የእሳት አደጋ ተከላካዮች በምዕራባዊው ማሃራሽትራ ግዛት ወደምትገኘው የብሃንዳራ አካባቢ ሆስፒታል እሳቱን ለመቆጠጠር ከመድረሳቸው በፊት ሰባት ሕፃናትን ከእሳት አደጋው ማትረፍ ተችሏል። የሕንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ \"ልብ የሚያቆስል አሳዛኝ ክስተት\" ሲሉ አደጋውን ገልጸዋል። የእሳት አደጋው የተከሰተው አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ መሆኑን የሆስፒታሉ ኃላፊዎች የገለጹ ሲሆን መንስኤው ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። በእሳቱ ሳቢያ በሆስፒታሉ ውስጥ የተከሰቱት ተከታታይ ፍንዳታዎች የነፍስ አድን ሥራውን ማሰናከሉን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሥራ ላይ የነበረች አንዲት ነርስ ከሆስፒታሉ አዲስ የተወለዱ አራስ ህጻናት እንክብካቤ ክፍል ውስጥ ጭስ ሲወጣ ካየች በኋላ ለባለስልጣናት ማስታወቋን ተናግራለች። የአካባቢው የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕራሞድ ካንዳቴ እንደገለጹት \"የሆስፒታሉ ባለሥልጣናት ሰባት ህፃናትን ቢያድኑም 10 ህጻናት ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሞተዋል\" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በደረሰባቸው ሐዘን ከሟች ቤተሰቦች ጎን መሆናቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። የሕንድ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሚት ሻህ ስለአደጋው እንዳሉት \"ቃላት የማይገልጹት የማይጠገን ጉዳት ነው\" ብለዋል።", "ኮሮናቫይረስ ፡ አሜሪካ የዩናይትድ ኪንግደም መንገደኞች ኮቪድ እንዲመረመሩ የሚያስገድድ ደንብ አወጣች አሜሪካ ከዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚመጡ የሁሉም አየር መንገድ ተሳፋሪዎች በ72 ሰዓታት ውስጥ ከኮቪድ- 19 ነፃ መሆናቸውን ማሳየት አለባቸው አለች። ይህ ውሳኔ የተላለፈው በዩኬ በተገኘው አዲስ የኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ነው። በመሆኑም ከመጭዎቹ ሁለት ቀናት በኋላ መንገደኞች የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን የሚያሳይ የጽሁፍ ማስረጃ ለአየር መንገዶች ማሳየት አለባቸው ተብሏል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) መንገደኞች ምርመራ እንዲያደርጉ የወሰነው ለአዲሱ የቫይረስ ዝርያ ምላሽ ለመስጠት የኒው ዮርክ ከተማ ለዓለም አቀፍ ተጓዦች የለይቶ ማቆያ ሕግ ማስተዋወቋን ተከትሎ ነው። ሲዲሲ እንዳለው መንገደኞች በ'ፒሲአር' ወይም እንግዳ አካል ወደ ሰውነታችን ስለመግባቱ የሚጠቁሙ ሞለኪዩሎች [አንቲጂን] ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ማረጋጋጥ አለባቸው። በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሌሎች አገራትም ድንበሮቻቸውን ከዩኬ ለሚነሳ በረራ ዝግ አድርገዋል። ይሁን እንጂ ዩኬም በቫይረሱ ፈጣን ስርጭት ሳቢያ የበርካታ እንግሊዛዊያን የውጭ አገር ጉዞ ክልከላን ጨምሮ ሌሎች ጥብቅ ገደቦችን ለመጣል ተገዳለች። አሜሪካ ወረርሽኙ በተከሰተ መጀመሪያ አካባቢ አብዛኞቹ የውጭ አገር ዜጎች ወደ አገሯ እንዳይገቡ ካገደች በኋላ፤ የአሜሪካ አየር መንገዶች ወደ ዩኬ እና አውሮፓ የሚያደርጉት በረራ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በጣም ገዳይ ስለመሆኑ ወይም ቫይረሱ ለክትባቱ የተለየ ምላሽ እንደሚሰጥ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ነገር ግን ከነባሩ ቫይረስ በ70 በመቶ የመሰራጨት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ተነግሯል። ዩናይትድ እና ዴልታ አየር መንገድም በዩኬ በረራዎች ላይ ያሉ ሁሉም ተሳፋሪዎች ምርመራ እንዲያደርጉ እንደሚጠይቁ ያስታወቁት ሐሙስ ዕለት ነበር።", "ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ መመሪያ አዘጋጀች ኢትዮጵያ በአገር አፍ ደረጃ በበሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ማዘጋጀቷን ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል። በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሞት መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ለማዘጋጅት መነሻ የሆነው የኮሮኖቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑም ተገልጿል። መመሪያወው በማህበረሰቡ ውስጥ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን ጭምር ማካተት እንደሚኖርበት ታምኖ የአገሪቱን የሞት መጠን የሚያሳውቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል። በተለይም እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሞቱን መጠን በትክክል ለማወቅ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሞት መጠን ለመገምገም፣ በሽታው የትኛውን የማህበረሰብ ክፍል በፆታ፣ በእድሜና ሌሎች መስፈርቶች አስመልክቶ የትኛውን አካል ነው እያጠቃ ነው የሚለውን በተመለከተ መመሪያው ምላሽ ይሰጣል ተብሏል። መመሪያው ይፋ የተደረገው ግንቦት 11፣ 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ነው። መመሪያው ይፋ መሆኑን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የጤና ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ መስጠት ዳይሬክቶሬት የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ዳሰሳ እና ምላሽ መስጠት ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ሮዚና ታሪኩ ከመረጃዎች አሰባሰብና መለኪያ ጋርም ተያይዞ ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች በመመሪያው መካተታቸውን አስታውቀዋል። መመሪያው መጠናቀቁን አስመልክቶ አዳማ በነበረው ዝግጅት ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደተናገሩት መመሪያው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጉዳት ሳያደርሱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል። መመሪያውን በማዘጋጀቱ በኩል የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የክልሎች የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር እና የአጋር ድርጅት ተወካይ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውም ከመረጃው መረዳት ተችሏል።", "ኮሮናቫይረስ፡ የሟቾች ቁጥር 500,000 መድረሱ ‘ልብ ሰባሪ ምዕራፍ ነው’- ባይደን አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 500,000 ዜጎቿን ማጣቷን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል። \"እንደ አንድ ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የተሞላበት ዕጣ ፈንታ መቀበል አንችልም። በሀዘኑ መቆዘምን መከልከል አለብን\" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና የትዳር አጋሮቻቸው ከንግግሩ በኋላ በኋይት ሃውስ በነበረው የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ወቅት የህሊና ፀሎት አድርገዋል፡፡ አሜሪካ ከ 28.1 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ በመያዛቸውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ሆናለች። ፕሬዝዳንቱ \"ዛሬ ሁሉም አሜሪካውያን እንዲያስታውሱ እጠይቃለሁ፡፡ ያጣናቸውን እና ወደ ኋላ የተውናቸውን ዳግም አስታውሱ\" ሲሉ አሜሪካኖች ኮቪድን በጋራ እንዲዋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በፌደራል መንግሥቱ ሥር የሚገኙ ሁሉም ቦታዎች ላይ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ባይደን አዝዘዋል፡፡ ጆ ባይደን በኋይት ሃውስ ተገኝተው ንግግራቸውን የከፈቱት፣ በኮቪድ-19 የደረሰው አሜሪካውያን ሞት ከአንደኛው በዓለም ጦርነት፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና በቬትናም ጦርነት ከሞቱት ሰዎች ድምር ቁጥር የበለጠ መሆኑን በመጥቀስ ነው። \"ዛሬ በእውነት አስከፊ እና ልብ ሰባሪ ምዕራፍ ነው- 500,071 ሰዎች ሞተዋል\" ብለዋል፡፡ በመቀጥለም \"ብዙ ጊዜም እንደ ተራ አሜሪካዊ ሰዎች ሲገለጹ እንሰማለን። እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም። ምንም ተራ ብሎ ነገር የለም፡፡ ያጣናቸው ሰዎች እጅግ የተለዩ ነበሩ፡፡ በአሜሪካ የተወለዱ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ ናቸው\" ብለዋል። \"ብዙዎቹም የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን በአሜሪካ ወስደዋል\" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጆ ባይደን ሚስታቸው እና ሴት ልጃቸው በጎርጎሮሳዊያኑ 1972 በመኪና አደጋ የተገደሉ ሲሆን ወንድ ልጃቸው ደግሞ በ 2015 በካንሰር ህይወቱ ማለፉን በማንሳት የራሳቸውንም የሃዘን ተሞክሮ ጠቅሰዋል። \"ለእኔ በሀዘን ውስጥ ያለው መንገድ ዓላማን መፈለግ ነው\" ብለዋል። ባይደን በወረርሽኙ ላይ የወሰዱት እርምጃ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተለየ ነው። ትራምፕ በአደገኛው ቫይረስ ተጽዕኖ ላይ ጥርጣሬ ያሳደሩ እና የቫይረሱ ስርጭትን ለመከላከል ጭምብሎችን መልበስ እና ሌሎች እርምጃዎችን ፖለቲካዊ አድርገውት እንደነበር ይነገራል፡፡ ባይደን ስልጣኑን ከመረከባቸው ከአንድ ቀን በፊት 400,000 አሜሪካውያን በቫይረሱ ምከንያት የሞቱበትን ክስተት አስበው ውለዋል፡፡ በሌላ በኩል በዋሽንግተን በብሔራዊ ካቴድራል ደወሎች 500 ጊዜ ተደውሏል- በወረርሽኙ ህይወታቸው ላለፈው ለአንድ ሺህ አሜሪካዊ አንድ ጊዜ ማለት ነው፡፡ በኮሮቫይረስቫይረስ የተያዙት አሜሪካውያን ቁጥር በሁለተኛ ደረጃ ከያዘች ህንድ (11 ሚሊዮን) እና ብራዚል (10.1 ሚሊዮን) ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ብራዚል በ 244,000 የሟቾችን ቁጥር ሁለተኛ ስትሆን ሜክሲኮ 178,000 ሰዎችን አጥታ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ \"ከአስርተ ዓመታት በኋላ በመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን ምክንያት የደረሰውን የብዙዎች ሞት በሃገሪቱ ታሪክ ውስጥ እንደ ታላቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ይገልጹታል\" ሲሉ የበሽታ መከላከያ ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ለሲ.ኤን.ኤን ገልጸዋል። \"አስገራሚ ቁጥር ነው። ከአንድ ዓመት በፊት ግማሽ ሚሊዮን አሜሪካውያን በዚህ በሽታ ሕይወታቸውን ያጣሉ የሚል ግምት አልነበረኝም\" ብለዋል በብራውን ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት ዶ/ር አሺሽ ጅሃ። \"በዚህች ሀገር ውስጥ ብዙ አቅም፣ ብዙ ሀብት አለን ... የምንከላከለው ስለነበር መከሰት አልነበረበትም፡፡ አሁን እዚህ ደርሰናል፡፡ የምንሰጠው ምላሽ የተሳሳተባቸውን መንገዶች ሁሉ ማንፀባረቅ ያለብን ይመስለኛል\" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ትንበያ መሠረት ቢያንስ 90,000 የሚሆኑ ተጨማሪ አሜሪካውያን እስከ ሰኔ 1 ቀን ድረስ በቫይረሱ ይሞታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በግምቱ መሠረት በግንቦት መጨረሻ ቫይረሱ በየቀኑ 500 ገደማ አሜሪካውያንን እንደሚገድል ይገምታል። በአሁኑ ወቅት በየቀኑ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚሞቱ ይገመታል። በየቀኑ ወደ 1.6 ሚሊዮን የሚጠጋ ክትባት ለአሜሪካዊያን እየተሰጠ በመሆኑ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች መጠን ለ40ኛ ተከታታይ ቀናት ቀንሷል፡፡ ሆኖም ባለሙያዎች በአገሪቱ ውስጥ እየጨመረ በሄደው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የሟቾችን ቁጥር ሊጨምር ይችላል በሚል አሳስቧቸዋል፡፡ አኃዞች ቢሻሻሉም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአሜሪካኖች በሕይወት የመኖር ዕድሜን በአንድ ዓመት ቀንሷል ሲል የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ባለፈው ሳምንት አስታውቋል፡፡ በቫይረሱ እጅግ በተጎዱትና በቁጥር አናሳ በሆኑት ማህበረሰቦች ዘንድ ደግሞ ለውጡ ከፍተኛ ነው ተብሏል። በህይወት የመኖር ዕድሜያቸው በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰባቸው ጥቁር ወንዶች ሲሆኑ ከጥር እስከ ሰኔ 2020 ባለው ጊዜ ብቻ በሦስት ዓመት ቀንሷል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሂስፓኒኮች በህይወት የመኖር ዕድሜ በ 2.4 ዓመት ቀንሷል፡፡", "ኮሮናቫይረስ፡ ሕንድ ዕድሜያቸው ከ18 በላይ ለሆኑ ዜጎቿ የኮቪድ ክትባት ልትሰጥ ነው ሕንድ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የክትባት መርሀ ግብሯን በስፋት ማዳረስ ጀምራለች። ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሁሉም አዋቂዎች በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ ክትባቱን መውሰድ እንደሚጀምሩ ተገልጿል። ነገር ግን በሕንድ በበርካታ ግዛቶች የክትባት እጥረት መኖሩ ችግር ሊሆን እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ተጨማሪ ክትባቶችን መንግሥት ከየት ሊያቀርብ እንደችሚል የተገለጸ ነገር የለም። የሕንድ መንግሥት ባለፈው ሳምንት እንዳለው 27 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦች ብቻ ነበር ያሉት። ይህ ማለት ደግሞ አሁን አገሪቱ ዜጎቿን እየከተበችበት ካለው ፍጥነት አንጻር ለ9 ቀናት ብቻ የሚበቃ ነው ማለት ነው። ሕንድ በአሁኑ ሰዓት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎቿን በበርካታ ግዛቶች እየከተበች ሲሆን የክትባት እጥረት ግን እንዳጋጠመ ተገልጿል። ጥቂት በማይባሉ ግዛቶችም ክትባቱን ለመስወድ የመጡ ሰዎች ሰይከተቡ መመለሳቸው ተዘግቧል። እንደ ሴረም ያሉ ትልልቅ የክትባት አቅራቢ ድርጅቶች በመላው ዓለም ያለውን የክትባት ፍላጎት ማርካት እንደከበዳቸውና ክትባቱን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች እጥረት እንዳጋጠማቸውም ገልጸዋል። ይህም የሆነው አሜሪካ ክትባቱን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ወደሌላ አገራት እንዳይላኩ በማገዷ ነው። በሕንድ ክትባቱ ሲሰጥበት የነበረው መንገድ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ነበር፤ ነገር ግን መንግሥት ሕጉን በመቀየር ላይ ነው። ይህ ለውጥም የክትባት ምርት እና አቅርቦትን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምረው ታምኖበታል። የሕንድ የክትባት አምራቾች አገሪቱ ከሚያስፈልጋት 50 በመቶ የሚሆነውን ለማዕከላዊ መንግሥት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ቀሪው 50 በመቶ ደግሞ በግዛቶችና በነጻ ገበያ ዋጋው የሚወስ ይሆናል። መጀመሪያ ላይ በሕንድ ሶስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቃድ አግኝተው ነበር። ሁለቱ ክትባቶች በሕንድ ክትባት አምራች ድርጅቶች ሴረም ኢንስቲትዩትና ባራት ባዮቴክ የተዘጋጁ ሲሆን ሶስተኛ ደግሞ የሩሲያው ስፑትኒክ ቪ ነው። መንግሥት ግን በሌሎች አገራት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ ተጨማሪ ክትባቶቸ በሕንድም ይጀመራሉ ብሏል። በተጨማሪም መንግሥት ለሁለቱ የሕንድ ክትባት አምራች ድርጅቶች 600 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል። ሕንድ ከያዝነው ወር ጀምሮ እስካሁን በየቀኑ ቢያንስ 200 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙባት እንደሆነ ሪፖርት አድርጋለች። በሕንድ ከአንድ ዓመት በፊት በየቀኑ 93 ሺ ሰዎች ነበር የሚያዙት። የሟቾችም ቁጥር ቢሆን አየጨመረ ነው። ትናንት ሰኞ ዕለት ብቻ በሕንድ 1 ሺ 619 ሰዎች በኮሮረናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው እንዳለፈ መንግሥት አስታውቋል።", "ኢራን የሕዝብ ቁጥሯን ለማሳደግ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ማቅረብ አቆመች ኢራን የሕዝብ ቁጥሯን ከፍ ለማድረግ በሚል በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ይቀርብ የነበረው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አቅርቦትን ውስን አደረገች። በዚህም በመንግሥት በሚተዳደሩ ሆስፒታሎች ውስጥ እርግዝና በጤናቸው ላይ እክል ለሚያስከትልባቸው ሴቶች ብቻ የእርግዝና መከላከያዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ በወንዶች ላይ ይደረግ የነበረው ቫሴክቶሚ የተባለው ቀዶ ህክምና እንዳይካሄድ ተደርጓል። ነገር ግን የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶቹ በግል ሆስፒታሎች ውስጥ እንደሚሰጡ ታውቋል። የኢራን መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚመዘገበው ዝቅተኛ የወሊድ መጠንና እየጨመረ የመጣው እድሜያቸው እየገፋ የሚሄድ ሰዎች ቁጥር አሳስቦታል። የኢራን አመታዊ የሕዝብ ቁጥር እድገት በአንድ በመቶ እየቀነሰ ሲሆን፤ በቶሎ ርምጃ ካልተወሰደ አገሪቱ በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ በርካታ በእድሜ የገፉ ዜጎች ካላቸው አገራት ተርታ ውስጥ እንደምትገባ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከሁለት ዓመት በፊት ኢራን የሕዝብ ብዛቷ 1.4 በመቶ ማስመዝገቧ ተገልጾ ነበር። ይህ አሃዝ በጎረቤቷ ኢራቅ ውስጥ 2.3 በመቶ ሲሆን ባላንጣዋ ሳኡዲ አረቢያ ደግሞ 1.8 በመቶ የሕዝብ ቁጥር እድገት ማስመዝገባቸውን የዓለም ባንክ መረጃ ያመለክታል። የአገሪቱ መንግሥት የዜና ተቋም የሆነው ኢርና እንደዘገበው ጋብቻ እና በጋብቻ ውስጥ የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ቀንሷል፤ ለዚህም ምክንያቱ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንደሆነ አመልክቷል። ግንቦት ወር ላይ የጤና ጥበቃ ምክትል ሚኒስትሩ ሰይድ ሐሚድ ባራካቲ እንደተናገሩት በኢራን ውስጥ ያለው የጋብቻ መጠን በአስር ዓመት ውስጥ በ40 በመቶ ቀንሷል። \"በዚሁ የምንቀጥል ከሆነ በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ በዕድሜ የገፉ በርካታ ሕዝብ ካላቸው አገራት አንዱ እንሆናለን\" ብለዋል ምክትል ሚኒስትሩ። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1979 የተካሄደው እስላማዊ አብዮትን ተከትሎ የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ መጠን ጨምሮ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ውጤታማ የሕዝብ ብዛት መቆጣጠሪያ ፖሊሲ በመከተሏ አሁን የታየው ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል። የአገሪቱ የበላይ መሪ የሆኑት አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሕዝቡ በርካታ ልጆች እንዲኖሩት ሲያበረታቱ ቆይተዋል። እንደ እሳቸው ፍላጎት ኢራን አሁን ካላት 80 ሚሊዮን ሕዝብ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ጭማሪ አድርጋ ቁጥሩ ወደ 150 ሚሊዮን ከፍ እንዲል ይሻሉ።", "“የጥርሴ ቢጫ መሆን ሕልሜን አመከነው” በልጅነት ፍሎራይድ የበዛበትን ውሃ መጠቀም የጥርስ ቀለምን ወደ ቢጫ እንዲቀየር እና እንዲበልዝ ያደርጋል። ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ያጋጥማል። ፍሎራይድ የጥርስን የላይኛውን ክፍል በመጉዳት ቀለሙ እንዲቀየር እና እንዲሸራረፍ ምክንያት ይሆናል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች በጥርሳቸው ቀለም እፍረት እና መገለል ይገጥማቸዋል። የወደፊት ዕቅዳቸው ተሰናክሎብናል የሚሉም አሉ። የታንዛኒያዋ አሩሻ በውሃ ውስጥ ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ካለባቸው ስፍራዎች መካከል አንዷ ስትሆን፣ እዚያ የአሩሻ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣት ሴቶች ስለገጠማቸው ችግር ይናገራሉ። ሁለቱ ወጣቶች በጥርሳቸው ቀለም መቀየር ምክንያት መድሎ እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል። መፍትሔ ይኖረው ይሆን የጥርስን ቀለም የሚቀይረውን ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ያለውን ውሃ ማጣራት እጅግ ከባድና ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ነው። አሁን ግን ቀላል የውሃ ጣሪያ ዘዴ ተፈጥሯል።", "በኢንግላንድ ኮኖናቫይረስ የሚመረመሩ ልጆች ቁጥር ጨምሯል ኮሮናቫይረስ በዋነኛነት የሚጎዳው አረጋውያንን መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሕፃናት ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው? የሚለው ጥያቄ መነሳቱ ግን አልቀረም። ኢንግላንድን እንደ ማሳያ ብንወስድ በአገሪቱ የኮቮድ-19 ምርመራ የሚያደርጉ ልጆች ቁጥር በዚህ ወር ጨምሯል። ከተመረመሩት መካከል አንድ በመቶው ብቻ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በመጀመሪያዎቹ የመስከረም ሳምንታት ከ200,000 በላይ እድሜያቸው ከዘጠኝ ዓመት በታች የሆነ ታዳጊዎች ተመርምረዋል። ይህም ካለፉት ወራት አንጻር ሦስት እጥፍ ይሆናል። ጥናት እንደሚያሳየው ልጆች ከአዋቂዎች አንጻር ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ጠባብ ነው። ሆኖም ግን ሕፃናት በሽታውን ያስተላልፋሉ? ለሚለው ጥያቄ አሁንም ቁርጥ መልስ አልተገኘም። የኢንግላንድ አሃዝ እንደሚጠቁመው፤ ምርመራ የሚያደርጉ ከ40 ዓመት በታች ያሉ ግለሰቦች ቁጥር ጨምሯል። አብላጫውን ድርሻ የሚይዙት በ20ዎቹ እድሜ ክልል ያሉት ናቸው። ምርመራ የሚያደርጉ ልጆች ቁጥር የጨመረው ኢንግላንድ ውስጥ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በመጀመሩ ነው። የተመርማሪዎች ቁጥር መናር የቤተ ሙከራ ውጤት እንዲዘገይ አድርጓል። ከሚመረመሩት ታዳጊዎች መካከል ኮቪድ-19 የሚገኝባቸው አንድ በመቶው ብቻ ናቸው። በሌላ በኩል ከጎልማሶች 3.5% ቫይረሱ ይገኝባቸዋል። ይህ ቁጥር በ20ዎቹ እና በ30ዎቹ እድሜ ክልል ያሉትንም ያካትታል። ለምን የሚመረመሩ ልጆች ቁጥር ጨመረ? የብርድ እንዲሁም ጉንፋን ምልክት የሚያሳዩ ልጆች ከሌሎች ታዳጊዎች ጋር መቀላቀል ጀምረዋል። ኢንግላንድ ወደ ቀዝቃዛ ወቅት እየገባቸው እንደመሆኗ የተለያዩ የመተንፈሻ አካሎች ህመሞች ይቀሰቀሳሉ። የእነዚህ በሽታዎች ምልክት ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተቀራራቢ ነው። ስለዚህም የኮሮናቫይረስ ምርመራ የሚያደርጉ ልጆች ቁጥር ንሯል። በእርግጥ ልጆች በቫይረሱ ቢያዙም በጠና አይታመሙም። ጃማ ፔዲያትሪክስ የሚባለው የዩናይትድ ኪንግደም የጥናት ቡድን ከ20 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎች ለወረርሽኙ የመጋለጥ እድላቸው 44% ነው። በተለይም ከዓሥር ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት እምብዛም ለበሽታው አይጋለጡም። ቡድኑ ከምሥራቅ እስያ፣ አውሮፓና ሌሎችም የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ 21 አገሮች ውስጥ የተካሄደ ጥናትን ዳሷል። በጥናቱ 42,000 ሕጻናት እና 270,000 አዋቂዎች ተሳትፈዋል። ጥናቱ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም። ልጆች በበሽታው ከተያዙ ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። ሳል ከሌላቸው ወይም በጠና ካልታመሙ ምናልባትም በሽታውን አያስተላልፉ ይሆናል የሚል መላ ምት አለ። ስለዚህም በሽታውን የማሰራጨት መጠን ምን ያህል ለበሽታው ተጋልጠዋል? ምን ያህል ቫይረስ ተሸክመዋል? ከምን ያህል ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው? በሚሉት ጥያቄዎች ይወሰናል። ቫይረሱ በልጆችና በጎልማሶች ምን ያህል እንደተሰራጨ ለማወቅ በበሽታው ከተያዙ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያስፈልግ አጥኚዎቹ ጠቁመዋል።", "ዩኬ በ11 የአፍሪካ አገራት ላይ ጥላ የነበረውን የጉዞ ዕቀባ አነሳች የዩኬ መንግሥት ከአዲሱ ኦሚክሮን የኮቪድ ተህዋሲ ዝርያ ጋር በተያያዘ በ11 የአፍሪካ አገራት ላይ ጥላ የነበረውን የጉዞ ዕቀባ ማንሳቷን አስታወቀች፡፡ አገራቱም አንጎላ፣ ቦትስዋና፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሴቶ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ናቸው፡፡ እነዚህ አገራት በዩኬ የጎዞ ዕቀባ የተጣለባቸው ባለፈው ኅዳር ወር የኦሚክሮን ተህዋሲ ዝርያ ከዚሁ ደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ መገኘቱን ተከትሎ ነበር፡፡ የዩኬ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሳጂድ ጃቪድ እንዳሉት ዕቀባውን ማንሳት ያስፈለገው ተህዋሲው አሁን በስፋት በሌሎች ቦታዎችም መሰራጨቱ ስለተረጋገጠ በነዚህ አገራት ላይ ጫና አድርጎ መቆየቱ ትርጉም ስለሌለው ነው፡፡ ሚኒስትሩ ለዩኬ ፓርላማ እንዳብራሩት፣ የኮቪድ ተህዋሲ አዲሱ ዝርያ ኦሚክሮን በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሳይቀር ገብቶ እያለ፣ እንዲሁም በሌሎች በርካታ የአውሮጳ አገራት መዛመቱ እየታወቀ እነዚህን ዐሥራ አንድ የአፍሪቃ አገራት በዕቀባ ዝርዝር ማቆየት ትርጉም አልባ ነው፡፡ ለወረርሽኝ ተጋላጭ አደገኛ አካባቢ በሚል ከተዘረዘሩ አገራት ወደ ዩኬ የሚገቡ ተጓዦች ለ10 ቀናት ራሳቸውን ለይተው መንግሥት ባዘጋጃቸው ሆቴሎች መቆየት ይኖባቸዋል፡፡ ወጪውን የሚችሉትም ተጓዦቹ ይሆናሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በርካታ ተጓዦች ለሆቴል ቆይታ ብዙ ገንዘብ ወጪ እንዲያደርጉ መገደዳቸው ቅሬታ ፈጥሮባቸው እንደነበር ሲዘገብ ነበር፡፡ በዩኬ ከአዲሱ የኦሚክሮን የኮቪድ ዝርያ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው መሞቱ የተዘገበው ትናንት ነበር፡፡", "በሽታን በሚከላከሉ ክትባቶች መካከል ለምን ልዩነት ተፈጠረ? የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አንድን ሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ከበሽታው ሊከላከል እንደሚችል ማንም እርግጠኛ አይደለም። አንዳንድ ክትባቶች እስከ እድሜ ልክ በሽታን የመከላከል አቅም ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የተገደበ የመከላከል አቅምን ያዳብራሉ። ይህ ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ይህ ቪዲዮ ምላሽ አለው።", "አንሶላችንን መቀየር ያለብን በምን ያህል ቀናት ልዩነት መሆን አለበት? ነገሩ በአደባባይ አይወራም የሚሉ ብዙ ናቸው። ግን የአንሶላ ቅያሪ ጉዳይ የሁላችንንም ደጅ ያንኳኳል። ብዙዎች በምን ያህል ቀናት አንሶላ ይቀየር? በሚለው ቁጥር ላይ አይስማሙም። እርስዎ ግን በምን ያክል ጊዜ አንሶላዎ ይቀይራሉ/ ያጥባሉ? አንሶላ በምን ያህል ቀናት ልዩነት መቀየር አለበት የሚለውን ከጤና ጋር የሚያስተሳስሩ አሉ። ስለጉዳዩ ጥናት የሠራችው ዩናይትድ ኪንግደምን እንደ ማሳያ እንውሰድ። አንሶላ በየስንት ቀኑ ይቀየር ለሚለው ጥያቄ የተሰጠው መልስ በጥናቱ በተሳተፉ 2 ሺህ 250 ዜጎች መካከል የአቋም ልዩነት እንዳለ ጠቁሟል። ግማሽ ያህሉ ወንደላጤዎች አንሶላቸውን ለአራት ወር እንዳላጠቡ ተናግረዋል። 12 በመቶው ደግሞ አንሶላ የሚያጥቡት ትዝ ሲላቸው ነው። ይህም ከአራት ወራት ሊበልጥ ይችላል። የሥነ ልቦና ባለሙያ፣ ኒውሮሳይንቲስትና የእንቅልፍ ተመራማሪዋ ዶ/ር ሊንዚ ብሮውኒንግ \"ይሄ ትክክል አይለም\" ትላለች። ከሴተላጤዎች 62 በመቶዎቹ በየሁለት ሳምንቱ አንሶላ እንደሚቀይሩ ይናገራሉ። የተወሰኑት ደግሞ በየሦስት ሳምንቱ። አንሶላ መቀየር ለምን ይጠቅማል? አንሶላ በየሳምንቱ ወይም በየሁለት ሳምንቱ መቀየር አለበት ትላለች ዶ/ር ሊንዚ። ይህ የሚደረገው ለንጽህና ሲባል ነው። ከሰውነታችን የሚወጣውን ላብ የሚሰበስበው አንሶላችን እንደመሆኑ በላብ ተጠቅልሎ መተኛት ያስቸግራል። \"ላብ አንሶላን ያሸታል፣ ይጨመድደዋለም\" ትላለች ዶክተሯ። ስንተኛ ምቾት እንዲሰማን በአካባቢያችን ነፋሻማ አየር ቢኖር ይመረጣል። አንሶላ አለመቀየር የሚያስከትለው በላብ ተዘፍቆ መተኛትን ብቻ አይደለም። ከሰውነታችን ላይ የሚነሱ ሙት ህዋሳት እንቅልፋችንን እንዲያስተጓጉሉትም ያደርጋል። ስንተኛ ከቆዳችን ላይ ሙት ህዋሳት ይወድቃሉ። ይህም አንሶላችን ላይ ይሰበሰባል። አንሶላ በቀናት ልዩነት የማንቀይር ከሆነ እነዚህን ሙት ህዋሳት አናስወግድም ማለት ነው። \"አንሶላችንን ቶሎ ቶሎ የማናጥብ ከሆነ ሙት ህዋሳት አንሶላው ላይ ይከማቻሉ\" ትላለች ዶክተር ሊንዚ። ችግሩ በዚህ ብቻ አያከትምም። ማይት የሚባሉ ጥቃቅን ነፍሳት ህዋሳቱን ለመመገብ አንሶላችን ላይ ይሰበሰባሉ። ይህም ለቆዳ በሽታ ያጋልጣል። በእንቅልፍ ወቅት ምቾትም ይነሳል። አንሶላ በምን ያህል ጊዜ ይቀየር? ዶክተሯ እንደምትለው፣ አንሶላ ከተቻለ መቀየር ያለበት በየሳምንቱ ነው። ግን በቀዝቃዛ ወቅት ከሳምንት ጥቂት አለፍ ሊልም ይችላል። ከሁለት ሳምንት በላይ አንሶላ ሳይቀይሩ መቆየት ግን አስጊ እንደሆነ ታስጠነቅቃለች። ስንተኛ እጃችን በመጠኑም ቆሽሾ እንደመሆኑ አንሶላ ማቆሸሻችን አይቀርም። ከትንፋሻችን የሚመወጣውም አየር ሁሌ ንጹህ አይደለም። አንዳንዶች ከመተኛት በፊት ሰውነት መታጠብ አንሶላ እንዳይቆሽሽ ይረዳል ቢሉም ሁነኛው መፍትሄ አንሶላ መቀየር እንደሆነ ባለሙያዎች ይመክራሉ። ቶሎ አንሶላ የማንቀይረው ለምንድን ነው? መልሱ እንደየሰዉ ይለያያል። መግቢያችን ላይ የጠቀስነው የዩናይትድ ኪንግደም ጥናት እንደሚለው ግን፣ 67 በመቶ የአገሪቱ ዜጎች አንሶላ ቶሎ ቶሎ የማይቀይሩት ስለሚረሱት ነው። 35 በመቶው ግድ አይሰጣቸውም። 22 በመቶው ንጹህ ተለዋጭ አንሶላ አያገኙም። 38 በመቶ ያህሉ ደግሞ አንሶላ በየጊዜው መታጠብ አለበት ብለው አያስቡም። ዶ/ር ሊንዚ፣ መኝታ ቤት እንደተቀደሰ ስፍራ ሊጠበቅ ይገባል ትላለች። \"መኝታ ቤት የምንወደው ቦታ መሆን አለበት። ወደ መኝታ ቤት ስንገባ በደስታ ልንሞላም ይገባል።\" እንቅልፍ የማጣት ችግር ያለባቸው ታካሚዎቿን ከምትመክራቸው ነገሮች መካከል አንሶላችሁን አጽዱ የሚለው አንዱ ነው። \"ንጹህ አንሶላ አንጥፈን ስንተኛ ምቾት ይሰማናል። ደስ ይለናል። እንረጋጋለን።\"", "ኮቪድ-19፡የትራምፕ ታዳጊ ልጅ በኮሮናቫይረስ ተይዞ እንደነበር ተገለፀ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ14 ዓመት ልጅ፣ ባሮን በኮሮናቫይረስ ተይዞ እንደነበር እናቱ፣ ቀዳማዊት እመቤት ሜላንያ ትራምፕ ገልፃለች። በአሁኑ ወቅት ግን ተመርምሮ ነጻ መሆኑንም አስረድታለች። ሚላንያ ልጇ ባሮን ተመርምሮ በኮሮናቫይረስ መያዙን ስታውቅ \"የፈራሁት ደረሰ\" ማለቷን ትናገራለች። ፕሬዝዳንት ትራምፕና ባለቤታቸው ሜላንያ እንዲሁም ሌሎች የዋይት ሐውስ ሰራተኞች በኮሮናቫይረስ ተይዘው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አገግመዋል። ልጇ በቫይረሱ ተይዞ የነበረበት ወቅት እነሱም ታመው ከነበረበት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ መሆኑንም ሜላንያ ትራምፕ በዋይት ሃውስ ድረ-ገፅ አስፍራለች። ሜላንያ ስለ ልጇ በቫይረሱ መያዝ ይፋ ማውጣቷን ተከትሎም የምረጡኝ ቅስሳ ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ \"ለአጭር ጊዜ ቫይረሱ ይዞት ነበር\" ሲሉ የልጃቸውን የጤና ሁኔታ በአዮዋ ለተሰበሰበው ደጋፊያቸው ተናግረዋል። \"መያዙን ሁሉ የሚያውቅ አይመስለኝም፤ ምክንያቱም ገና ታዳጊ ስለሆነ እና የመከላከል አቅሙ ጠንካራ በመሆኑ በቀላሉ መክቶታል\" ብለዋል። አክለውም \" ባሮን መልከ መልከ መልካምና ነጻ ነው\" ሲሉ ተናግረዋል። የልጃቸውንም ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ ማገገምም እንደ ምክንያት በመጥቀስ አሜሪካ ትምህርት ቤቶቿችን በቅርቡ ልትከፍት ይገባል ሲሉም ሞግተዋል። በርካታ የመምህራን ማህበራት ግን በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ቤቶች መከፈት እንደሌባቸውና በርካታ መምህራን በተማሪዎች ሊጠቁ ይችላሉም እያሉ ነው። በአዮዋ ለተሰበሰው ደጋፊዎቻቸውም \"ባሮን በኮሮናቫይረስ መያዙ ተነገረን። ከሁለት ሰኮንዶች በኋላ ተሻለው። አሁን ነፃ ነው አልተባለም? ተብሏል። ሰዎች በኮሮናቫይረስ ይያዛሉ፣ ይሻላቸዋል። ልጆችን ትምህርት ቤት መልሱ\" ብለዋል። በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የአለም መነጋገሪያ ሆነው የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ተመልሰዋል። ፕሬዚዳንቱ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተነገረ ሁለት ሳምንታት ባልሞላ ጊዜም ውስጥ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በፍሎሪዳ፣ ሳንፎርድ ከአዳራሽ ውጭ በነበረው የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ የተገኙት። ደጋፊዎቻቸው የተለመደውን \"አራት ተጨማሪ አመታትን ይምሩ\" በማለት የዘመሩላቸው ሲሆን ፤ በዝግጅቱ ላይ የተገኙትም ደጋፊዎች ሙቀታቸው እየተለካና ጭምብል እየተሰጣቸው ወደተዘጋጀው ቦታ አቅንተዋል። ደጋፊዎቻቸው ፕሬዚዳንቱ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ወቅት በመምጣታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል። በኮሮናቫይረስ ክፉኛ የተጠቃችው አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7.8 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን 216 ሺህ ዜጎቿንም መነጠቋን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።", "አሜሪካዊያን ከ20 ቀን በኋላ የኮቪድ ክትባት መከተብ ይጀምራሉ ተባለ የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባት መርሐግብር ቢሮ ኃላፊ የመጀመርያው አሜሪካዊ ተከታቢ በዲሴምበር 11 (ታኀሣሥ 2) ክትባት ሊያገኝ እንደሚችል ጠቆሙ። ይህም ማለት የመጀመርያው ተከታቢ የኮቪድ ክትባት ለመውሰድ ከ20 ቀናት ያነሰ ጊዜ ነው የቀረው ማለት ነው። ኃላፊው ዶ/ር ሞንሴፍ ስሎይ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት መሥሪያ ቤታቸው እያቀደ ያለው ይህ ክትባት ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፍቃድ ባገኘ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክትባቱን ወደ ጤና ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ነው። ይህም ክትባቱን ወደ ዜጎች ለማድረስ አንዲትም ሰኮንድ እንዳትባክን ለማድረግ ነው። አሜሪካ በአሁን ሰዓት ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ፍጥነት በተህዋሲው ወረርሽኝ እየተጠቃች ነው። አሁን በተህዋሲው የተያዙት አሜሪካዊያን ቁጥር ከ12 ሚሊዮን ማለፉ ብቻ ሳይሆን በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 200ሺ አካባቢ መጠጋቱ አገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷታል። ወረርሽኙ አሜሪካ ከገባ ወዲህ 255ሺ ዜጎች ሕይታቸውን አጥተዋል። በዚህን ያህል ቁጥር ተህዋሲው ነፍስ ያጠፋበት ሌላ አገር የለም። ፋይዘር የተባለው እውቅ የመድኃት አምራች ኩባንያ ከጀርመኑ ባዯንቴክ ጋር በመሆን ላመረተውን መድኃኒት የእውቅና ጥያቄን ለሚመለከተው ክፍል ያቀረበው ባለፈው አርብ ነበር። ፋይዘርና አጋሩ ያመረቱት የክትባት ዓይነት የፈውስ ምጣኔው 95 ከመቶ ነው ተብሏል። አንድ ሰው ከኮቪድ ተህዋሲ ለመጠበቅ ይህን ክትባት በተለያየ ጊዜ ሁለት ጠብታ መውሰድ ይኖርበታል። ፋይዘርና አጋሩ እስከዚህ እስከያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ 50 ሚሊዮን የሚሆን ጠብታ ለማምረት ሁሉን ዓቀፍ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህም ማለት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ሊገባደድ አንድ ወር ገደማ ብቻ ነው ስለቀረው በአንድ ወር 50 ሚሊዮን ጠብታ ያመርታል ማለት ነው። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የአማካሪዎች ምክር ቤት ልዩ ኮሚቴ በዲሴምበር 10 ይህን ክትባት ፍቃድ በመስጠት ጉዳይ ላይ ስብሰባ ይቀመጣል። ይህ ማለት ከ17 ቀናት በኋላ ነው የሚሆነው። ዶ/ር ስሎይ የሚሉት ታዲያ ይህ ኮሚቴ በተሰበሰበና መድኃኒቱ የምርት ይሁንታን ባገኘ በነገታው ክትባቶች ወደ ጤና ጣቢያዎች ይደርሳሉ። ሞዴርና የተሰኘው ሌላው የመድኃኒት አምራች በበኩሉ እንደ ፋይዘር ሁሉ የፈውስ ምጣኔው 95 ከመቶ የሆነ ሌላ ክትባት መሥራቱን ይፋ አድርጓል። ሞዴርና እንደ ፋይዘር ሁሉ በሚቀጥሉት ሳምንታት እውቅናና ፈቃድ እንዲሰጠው ማመልከቻ ያስገባል ተብሎ ይጠበቃል። ሀብታም አገራት ከነዚህ ሁለት ኩባንያዎች ጋር የመድኃኒት ምርት ስምምነት እያደረጉ ነው። ድሀ አገራት በዚህ ረገድ እጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አሁንም እያነጋገረ ነው።", "የለንደኑ ነዋሪ የመጀመሪያው በ3ዲ የታተመ ሰው ሰራሽ ዓይን ሊተከልለት ነው የለንደን ከተማ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በ3ዲ የታተመ ሰው ሰራሽ ዓይን ለመጀመሪያው ጊዜ ሊተከልለት ነው። ስቲቭ ቬርዜ ለንደን ከተማ በሚገኘው የሞርፊልድ የዓይን ሆስፒታል በ3ዲ ቴክኖሎጂ የታተመው ዓይን ይተከልለታል። አዲሱ ዓይን ከዚህ ቀደም ከነበረው ሰው ሰራሽ ዓይን የበለጠ ተፈጥሯዊ እንደሚመስል ተስፋ ተደርጓል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ለታካሚዎች ሰው ሰራሽ ዓይን ለመግጠም ይፈጅ የነበረውን የስድስት ሳምንታት ጊዜ የ3ዲ ቴክኖሎጂው በግማሽ ይቀንሳዋል ተብሏል። ምንም እንኳ ይህ ሰው ሰራሽ ዓይን የማየት ችሎታን ባይመልስም የተፈጥሮ ዓይን ስለሚመስል የሰዎችን በራስ መተማመን ከፍ ያደርጋል ተብሏል። ዕድሜ በ40ዎቹ ውስጥ የሚገኘው ቬርዜ \"ከ20 ዓመቴ ጀምሮ ሰው ሰራሽ ዓይን ያስፈልገኝ ነበር። . . . ከቤቴ ስወጣ በመስታወት ውስጥ ዓይኔን እመለከታለሁ። እናም የማየው አያስደስተኝም\" ብሏል። \"አዲሱ ዓይን ድንቅ ይመስላል። በ3ዲ ዲጂታል ማተሚያ ቴክኖሎጂ በመሠራቱ የተሻለ ይሆናል\" ብሏል። ለአንድ ግለሰብ ሰው ሰራሽ ዓይን ከመተከሉ በፊት በዓይኑ ልክ ሰው ሰራሸ አይኑ መቀረጽ ይኖርበታል። በ3ዲ የታተመ ሰው ሠራሽ ዓይን የማምረት ሂደትን ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንታት ይቀንሳል። የመጀመሪያ ቀጠሮው ግማሽ ሰዓት ብቻ እንደሚወስድም ተገልጿል። በሞርፊልድስ የዓይን ሆስፒታል የዓይን ሕክምና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ማንዲፕ ሳጎ ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በሆነው የሰው ሰራሽ ዓይን በማግኘታቸው ባልደረቦቻቸው \"ደስተኛ\" ነበሩ ብለዋል። \"መጪው ሙከራ የዚህን አዲስ ቴክኖሎጂ ጥቅም በተመለከተ ጠንካራ ማስረጃዎችን እንደሚሰጠን ተስፋ እናደርጋለን። ለታካሚዎች ምን ያህል ልዩነት እንዳለው ያሳያል\" ብለዋል።", "ኮሮናቫይረስ፡ ስፔን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማገርሸቱ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች የስፔን መንግሥት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ በወረርሽኙ ክፉኛ በተጠቁት በመዲናዋ ማድሪድና አካባቢዋ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘ። አዲስ በተጣለው ገደብም ወሳኝ የሆነ ጉዞ ማድረግ ከሌለባቸው በስተቀር ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው እንዲወጡ አይፈቀድላቸውም። ይሁን እንጅ የማድሪድ ክልል መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቡ ሕጋዊ አይደለም ብሏል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በስፔን በቫይረሱ ከተያዙት 133 ሺህ 604 ሰዎች መካከል ከሲሶ በላይ የሚሆነው የተገኘው በማድሪድ ነው። በዚህም መሰረት ረቡዕ ዕለት አብዛኞቹ የስፔን የክልል ባለሥልጣናት፤ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙባቸው አካባቢዎች ሦስት መመዘኛዎችን ካሟሉ ገደብ እንዲጣልባቸው ድምፅ ሰጥተዋል። ሦስቱ መመዘኛዎች፤ ከ100 ሺህ ነዋሪዎች ውስጥ 500 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ካሉ፣ 35 በመቶ የሚሆኑት የበሽታው ታማሚዎች ፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ከገቡ እና ከሚደረገው ምርመራ በ10 በመቶው ላይ ቫይረሱ ከተገኘበት የሚሉ ናቸው። በዚህ መስፈርት መሰረትም ከ100 ሺህ ነዋሪዎች 780 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ያሉባት ማድሪድ፤ መመዘኛውን አሟልታለች ተብሏል። ይሁን እንጅ አዲስ የተጣለው ገደብ መቼ ተግባራዊ እንደሚሆን አልታወቀም። ገደቡን ለመጣል ድምፅ ያልሰጠው በወግ አጥባቂው ተቃዋሚ ፓርቲ የሚመራው የማድሪድ ክልል መንግሥት ግን የእንቅስቃሴ ገደቡ ሕጋዊ አይደለም ብሏል። የክልሉ የጤና ኃላፊ ኢንሪኪው ሩይስ እስኩደሮ 'የማስጠንቀቂያና የሚረብሽ መልዕክት' በመላክ ማዕከላዊ መንግሥቱን ከሰዋል። የማድሪድ መንግሥት በከተማዋና አካባቢዋ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣል ይልቅ፤ በ45 ዋና ዋና የጤና ተቋማት አካባቢዎች ገደቡን በመጣል የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ነበር ምርጫው ያደረገው። ይሁን እንጅ ገደቦቹ በከተማዋ በአብዛኛው በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ነዋሪዎች ያሉባቸውን አካባቢዎችን ይበልጥ ይጎዳል በሚል አከራካሪ ነበሩ። ከዚህ ቀደም የእንቅስቃሴ ገደቡን በመቃወም በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸው ይታወሳል። የስፔን ማዕከላዊ መንግሥት ግን \"ከዚህ ቀደም የተጣሉት ገደቦች በቂ አልነበሩም\" በማለት በመላ ከተማዋ የሚደረግ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ እንዲቆም አሳስበዋል። የእንቅስቃሴ ገደቡ ተግባራዊ ሲደረግ የማድሪድ ድንበሮች ወሳኝ ወይም አስፈላጊ የሆነ ጉዞ ለሌላቸው ጎብኝዎች ዝግ ይሆናሉ። ድንበሯን እንዲያቋርጡ የሚፈቀደው ለሥራ ፣ ለሕክምና እና ለሸመታ እንደሆነም ተነግሯል። መናፈሻዎችና የመጫወቻ ሜዳዎችም ይዘጋሉ። ከስድስት በላይ ሰዎች አንድ ላይ መሰባሰብም አይችሉም። በስፔን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፤ እስካሁን ከ31 ሺህ 411 ሰዎች በላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው አልፏል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፤ እስካሁንም ከ748 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በአውሮፓ አገራት ወረርሽኙ 'በአስጊ ሁኔታ' እየተስፋፋ መሆኑን አስታውቋል።", "ኮሮናቫይረስ ፡ ባንነካካ፣ ባንተቃቀፍ፣ ባንሳሳም በጤናችን ላይ የሚጎድል ነገር ይኖር ይሆን? ያለፈው የፈረንጆች ዓመት በጥቅሉ ካየነው መልካም ዓመት አልነበረም። አራራቀን እንጂ አላቀራረበንም። ለመሆኑ ባንተቃቀፍ ምን ይቀርብናል? ትዝ ብሎንስ ያውቃል? ለምን አልተጨባበጥኩም ብሎ የከፋውስ አለ? ለነገሩ ልጆችንን አቅፎ መሳም፣ ፍቅረኛችንን መሳም፣ ባሎቻንን ማቀፍ. . . እንዴት አንናፍቅም? በዓለም ላይ በርካታ ሰዎች የፈረንጆቹን 2020 የማኅበራዊ መራራቅ ዓመት ብቻ ሳይሆን ቤት ተከርችሞብን የታሸግንበት ዝጋታም ዓመት ሆኖ ነው እያበቃ ያለው። ከኮቪድ-19 መከሰት በፊት ማንም ሰው መቼስ ወደፊት መጨባበጥ ይከለከላል፣ መተቃቀፍ ያስቀስፋል ብሎ ያሰበ ይኖራል ተብሎ አይገመትም። ለመሆኑ አለመተቃቀፋችን አለመጨባበጣችን የራሱን ችግር ይዞ ብቅ ይል ይሆን? ተመራማሪዎች አዎ ይላሉ። መነካካት ተራ ነገር አይደለም። በፍቅር መነካት ወይም መታቀፍ ሕጻን ሳለን የመጀመርያ ቋንቋችን ነው። ፍቅርን የምንማርበት ቋንቋ። መግቢያቢያችን። ደግነትን፣ ሰው መውደድን፣ ለሆነ ፍጡር እምነታችንን መስጠትን የምንሰለጥነው በእቅፍ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። በጊዜ ሂደት ረስተነው ይሆናል እንጂ ድሮ ድሮ ካልታቀፍን ብለን አልቅሰናል። ካላመናችሁ እናታችሁ ጋር ደውሉ። ለዕድገታችንም እንደ እናት ጡት ወተት ሁሉ መታቀፍ አስተዋጽኦ ነበረው። በጊዜ ሂደት ክደውን ነው እንጂ. . . ። \"የሰዎች ተቀራርቦ መነካካት የዋዛ ነገር አይደለም። ማኅበራዊ ሙጫ ማለት ነው። አስተሳስሮናል። ከምንወደው ሰው ጋር ገምዶናል። እንደ ሰው የሚያቀራርበን አንድ ነገር ቢኖር ይኸው ነው\" ይላሉ ዴቪድ ሊንደን። ዴቪድ 'ዘ ኒው ሳይንስ ሂዩማን ኢንዲቪጁዋሊቲ' ደራሲ ናቸው። በዚህ የንክክኪ ሳይንስ ውስጥ ብዙ አጥንተዋል። \"የመነካካት ነገር እና ፋይዳው እምብዛምም አልተጠናም። ቸል ያልነው፤ ገሸሽ ያደረግነው ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም\" ይላሉ ደራሲ ዴቪድ። ለመሆኑ ሌሎችን ሰዎችን ስንነካ አእምሯችን ውስጥ ምንድነው የሚፈጠረው? አንዳንድ ጥናቶች መነካት፣ መታቀፍ፣ ልክ ሕመም ማስታገሻን የመውሰድ ያህል ፈውስ ይሰጣል ይላሉ። ይህ የተጋነነ አረፍተ ነገር ከመሰላችሁ፣ አንድ ሕጻን ልጅ ሲነካ እንዴት እንደሚሆን ለማየት ሞክሩ። አንድ ሕጻን ልጅ በእናቱ ጭንቅላቱ ቢዳበስ የልብ ምቱ መረጋጋት ይጀምራል። ይህን ያሉት በሕጻናት አንጎል [ኒውሮሳይንስ] ላይ ተመራማሪ የሆኑት ሬቤካ ስላተር ናቸው። አንዳንድ ጥናቶች ይህንን ነገር ከዚህም በላይ ገፋ ያደርጉታል። ለምሳሌ ክብደታቸው ከአማካይ በታች ሆነው የተወለዱ ልጆች በእናቶቻቸው ሲነካኩና ሲታቀፉ መጠናቸው እየተስተካከለ እንደሚመጣ ተደርሶበታል። የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪ ሮቢን ደንበር እንደሚሉት የሰው ልጅ ከእንሰሳት ጋር ከሚያመሳስሉት ነገሮች አንዱ ንክኪና ለዚያ የሚሰጠው ትርጉም ነው። የሰው ልጅ ያለበት የነ ዝንጀሮና ዝርያቸው ጨምሮ አጥቢዎች በሕይወት ዘመናቸው 20 ከመቶውን የሚያሳልፉት እርስ በርሳቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በመነካካት ነው። ከዝርያቸው ጋር ወዳጅነታቸውን የሚገልጹትም በብዛት በንክኪ ነው። ለምሳሌ አንድን ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ስንነካ በመዳፋችን ያለው የነርቭ ብልጭታ ለጭንቅላታችን 'ከአዲስ ሰው ጋር አዲስ ግንኙነት እየፈጠርክ ነው' የሚል መልዕክት ያደርስለታል። ያ ስሜት ደግሞ ብዙ እጢዎች መልካም የሰውነት ፈሳሾችን እንዲያመነጩ ያደርጋል። በንክኪ ውስጥ አእምሯችን ዘና ይላል፤ በተለይም ደግሞ አብረነው በንክኪ እየተግባባነው ያለውን ሰው የምናምነው ሲሆን እፎይታን ይመግበናል ይላሉ እኚሁ ተመራማሪ። ከመነካካት ጋር የነበረን የመጀመሪያ ቁርኝት ፈዋሽ ብቻ ሳይሆን ስሜትን ሰቅዞ የሚይዝ ነው። መጀመሪያ የሳምናትን ኮረዳ፣ መጀመሪያ የዳበስነውን መልከ መልካም ልጅ፣ የመጀመሪያ የፍቅር ግንኑነቶች ሁሌም በአእምሯችን የማይጠፉት ከንክኪ በሚያገኙት ኃያል የተነሳ ነው። ለመሆኑ መነካካት ይህን ያህል ትርጉም ካለው አለመነካካት ምን ሊያደርገን ይችላል? መነካት፣ መታቀፍ ይህን ያህል አእምሯችን ላይ በጎ ተጽእኖ አለው ብለናል። ያረጋጋናል፣ ያስደስተናል፣ ሕይወታችንን እንድንወዳት ያደርገናል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሕመማችንን ያስወግድልናል። አልተጋነነም። በንክኪ ደዌ ይፈወሳል። የንክኪ ሕክምና ያለውም ለዚህ ሳይሆን ይቀራል? አሁን እንዳትነካኩ፣ እንዳትጨባበጡ፣ እንዳትስሙ ስንባል ሳናውቀው የሆነ ነገራችን እየተጎዳ ነው። \"እርግጥ ነው አትነካኩ በተባልን ማግስት ሕመም አልጀመረንም። ራሳችንን አልሳትንም፣ መፈጠራችንን አልጠናል ይሆናል. . .\" ይላሉ ደራሲው ሊንደን። . . . ነገር ግን ከሰው ጋር የነበረን የቁርኝት ገመድ ለእኛ ባይታየንም ተበጥሷል፤ በስሜት ተለያይተናል። ቀስ በቀስ መጎዳታችንን ሳናውቀው ተጎድተናል።\" ለምሳሌ አንዳንድ እንሰሳትን በፍጹም እንዳይነካኩ ብንከለክላቸው ወዲያውኑ ሊታመሙ ይችላሉ። ታመሙ የምንለው በመንፈስ ብቻ ሳይሆን በአካልም ጭምር ነው። በጭንቀት ይወጠራሉ፤ አዳዲስ የአውሬነት ባህሪን እያሳዩ ሊመጡ ይችላሉ። በጊዜ ሂደት ደግሞ ጤናቸው እየተቃወሰ ሊመጣ ይችላል። እስከመሞትም ሊያደርሳቸው ይችላል። ወረርሽኙ የገባ ሰሞን፣ በተለይ ደግሞ ብዙ አገሮች ማኅበራዊ መራራቅን ግዴታ ባላደረጉበት ወቅት እንኳ ብዙ ሰዎች ከሰዎች ጋር መቀራረብን፣ መነካካትን እንደናፈቁ ይናገሩ ነበር። አሁን ዓለም እንዲህ በተራራቀበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ሲብስበት ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ነው። ምናልባት ነገሩን ትተነዋል። ቅርርቦሽንና ፋይዳውን የምናስብበት ጊዜ እንኳን አጥተን ይሆናል። ሕይወት እያራወጠን ዘንግተነው ይሆናል። ያ ማለት ግን ውስጣችን አልተጎዳም ማለት አይደለም። ጎልድስሚዝ ዩኒቨርስቲ በቢቢሲ ራዲዮ ፎር በኩል አንድ ጥናት አድርጎ ነበር። በጥናቱ በ110 አገሮች የሚኖሩ 40ሺህ ሰዎች ተጠይቀው ነበር። 20ሺህ የሚሆኑት መተቃቀፍን እጅግ አድርገው መናፈቃቸውን አምነዋል። መነካትን መናፈቅ ከባድ ናፍቆት ነው። ታዲያ ምን ተሻለ? ፕሮፌሰር ስሌተር እንደሚሉት ከሆነ ከዚህ በኋላ በሰዎች መካከል ተህዋሲው ቢጠፋ እንኳን ከተህዋሲው በፊት እንደነበረው ጊዜ ንክኪዎች አይኖሩም ይላሉ። ሰዎች በመጨባበጥ ውስጥ የሚለዋወጡት ወዳጅነት እንደነበረው አይዘልቅም ነው የሚሉት። ነገር ግን የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪና ሳይኮሎጂስት ሮቢን ደንበር ይህ ነገር አያሳምናቸውም። እሳቸው የሚያምኑት ወዳጅነትና መነካካት ሰዋዊ ነው። ሰዋዊ ባህሪ ደግሞ እንዴትም ቢሆን ካቆመበት ይቀጥላል። መዳፋችን የውስጠኛው አካሉ ሲፈጠር ራሱ እንዲነካ፣ እንዲዳስስ ተደርጎ ነው። የነርቮቹ ብዛት የሚያመላክቱትም ያንኑ ነው። እኛ ባናውቀውም ሰውነታችን ልክ እንደ ጥልፍልፍ የኤሌክትሪክ ገመድ ያለ ነው። ንክኪ ቶሎ ብሎ ወደ አእምሮ መልዕክት ይልካል። ስለዚህ ያለ መነካካት ጤናችን ልክ አይመጣም። በሚወዱት ሰው መነካትን የመሰለ የአእምሮ ፈውስ የለም። ለረዥም ጊዜ በናፈቅነው ሰው እቅፍ ውስጥ የመግባትን ያህል ደስታ የለም። በናፈቅነውና በምንወደው ሰው እቅፍ ውስጥ ለሰከንዶች መቆየት ትንሽዬ የገነት ጎጆ ውስጥ ገብቶ የመውጣት ያህል ነው። \"አንድ ሰው ስለእናንተ የሚሰማውን በትክክል ለማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ . . . የሚነግሯችሁን ከመስማት ይልቅ እንዴት እንደሚነካችሁ ስሜቱን ለመረዳት ሞክሩ\" ያላሉ ባለሙያው። ብዙ ሰዎች ከልጅነታቸው ጋር በነበራቸው የእናት ፍቅር ውስጥ ምን ትዝ ይላችኋል ሲባሉ፤ እናታቸው ፀጉራቸውን ስትነካካቸው የነበራቸው ስሜትን በይበልጥ ያስታውሳሉ። ለምን? የፈረጆቹ 2021 ዳግም የምንተቃቀፍበት ዘመን ይሆን ይሆን?", "ኮሮናቫይረስ ፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናገሩ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል የገቡት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደህና መሆናቸውንና ቀጣዮቹ ቀናትም ለጤንነታቸው ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት ጤንነታቸውን አስመልክቶ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎችን ተከትሎ ቅዳሜ ምሽት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ነው። የፕሬዚደንቱ ሐኪምም ትራምፕ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ሕክምናውን ከጀመሩ አንስቶ ለውጥ እንዳሳዩ ተናግረዋል። ሐኪማቸው ዶ/ር ኮንሊ በሰጡት መግለጫ ላይ ፕሬዚደንቱ ከተጋረጠባቸው አደጋ ሙሉ ለሙሉ ባይላቀቁም፤ የሕክምና ቡድኑ ግን በሁኔታቸው ተስፋ እንዳለው ተናግረዋል። ከሰዓታት በፊት ትራምፕ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ላይ ያለ ከረቫት የሱፍ ኮት በሸሚዝ ለብሰው ታይተዋል። በንግግራቸውም በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በዋልተር ሪድ ብሔራዊ ወታደራዊ ሕክምና ማዕከል የሚሰሩ ዶክተሮችና ነርሶችን አመስግነዋል። \"እዚህ ስመጣ ደህና አልነበርኩም ፤ አሁን ላይ ግን እየተሻለኝ ነው\" ብለዋል ትራምፕ። የሚቀጥሉት ቀናት ወሳኝ እንደሆኑ ገልፀው፤ \" በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ምን እንደሚፈጠር እናያለን\" ብለዋል። ፕሬዚደንቱ በኮቪድ-19 መያዛቸውን በትዊተር ገፃቸው ለሕዝብ ይፋ ያደረጉት ባሳለፍነው አርብ ነበር። ይህም የምረጡኝ የቅስቀሳ ዘመቻቸውን ያቋረጠባቸው ሲሆን ከምርጫው በፊት አዲስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ለመሰየም መሞከራቸው ላይም ጥርጣሬን አሳድሯል። ትራምፕ በከሮናቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል ከገቡ ሁለተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። ስለ ትራምፕ ጤንነት የምናውቃቸው ነገሮች ቅዳሜ ዕለት ጠዋት የፕሬዚደንቱ ሐኪም ዶ/ር ኮንሊ በሰጡት መግለጫ ለፕሬዚደንቱ ተጨማሪ ኦክስጅን አለመሰጠቱንና ለ24 ሰዓታትም ትኩሳት እንዳልነበራቸው ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ፕሬዚደንቱ ለመጭዎቹ 'ጥቂት ቀናት' በሆስፒታሉ እንደሚቆዩ ዋይት ሃውስ ገልጿል። ዶ/ር ኮንሊ ስለትራምፕ የጤንነት ሁኔታ ሲናገሩም ተስፋ እንዳላቸው ገልፀው፤ ከሆስፒታል ሊወጡ የሚችሉበትን ጊዜ ግን አልገለፁም። ሆኖም የዋይት ሃውስ ቺፍ ኦፍ ስታፍ (የቢሮ ኃላፊ) ማርክ ሚዶውስ፤ ፕሬዚደንቱ የማገገም ሂደት ላይ እንዳልነበሩ ጠቅሰው፤ ጤንነታቸው ላይ ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል። ፕሬዚደንቱ ላለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የበሽታው ወሳኝ ምልክቶች እንደታዩባቸው በመግለፅም ቀጣዮቹ 48 ሰዓታት አስጊ እንደሚሆኑ አክለዋል። የ74 ዓመቱ ትራምፕ እድሜያቸውና የሰውነታቸው ክብደታቸው ግዙፍ የሚባሉ ዓይነት በመሆናቸው ለኮቪድ-19 ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ይመደባሉ። እስካሁን በሙከራ ላይ ያለ መድሃኒት እና የፀረ ቫይረስ መድሃኒት እየወሰዱ ነው። ሐኪማቸው ቅዳሜ እለት በሰጡት መግለጫ ፕሬዚደንቱ ኦክስጅን ይወስዱ ነበር ወይ? ተብሎ በተደጋጋሚ ለተነሳላቸው ጥያቄ \" በዚህ ሰዓት እየወሰዱ አይደለም ፤ አሁን ሁላችንም እዚህ ባለንበት ሰዓት ኦክስጅን አልተገጠመላቸውም\" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ይሁን እንጅ በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ፕሬዚደንቱ አርብ ዕለት ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት በዋይት ሃውስ ኦክስጅን ተገጥሞላቸው እንደነበር ዘግበዋል። ቅዳሜ ምሽት በተሰጠው መግለጫ ግን የሕክምና ቡድኑ ትራምፕ 'ሬምዲሲቫየር' የተሰኘውን መድሃኒት ሁለተኛውን ዶዝ መጨረሳቸው ተገልጿል። ከሰዓቱንም በደህና ሁኔታ ሲያሳልፉ ነበር ተብሏል። ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና በዋይት ሃውስ እረፍት እያደረጉ መሆናቸው ተነግሯል። የምርጫ ዘመቻውስ? ፕሬዚደንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ \"ዘመቻውን በተጀመረበት መንገድ ለማጠናቀቅ በቅርቡ እመለሳለሁ ብየ አስባለሁ\" ሲሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል። የፕሬዚደንቱ የምርጫ ዘመቻ ቡድን ትራምፕ ወደ ምርጫ ዘመቻው መመለስ እስከሚችሉ ድረስ ባላቸው ፍጥነት ቅስቀሳውን እንደሚቀጥል አስታውቋል። በመሆኑም አሁን ላይ የፕሬዚደንቱ ወንድ ልጆች ዶናልድ ጀር እና ኤሪክ እንዲሁም ምክትል ፕሬዚደንቱ ማይክ ፔንስ ዘመቻውን ያስቀጥላሉ ተብሏል። የዘመቻው ቃል አቀባይም የመጀመሪያው ዝግጅት ሰኞ የሚካሄደው 'ቨርቹዋል'[ ኦንላይን] ሰልፍ እንደሆነ ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል። አርብ ዕለት ተመርምረው ከቫይረሱ ነፃ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንት ፔንስ የዴሞክራቲክ ምክትል ፕሬዚደንት እጩ ካማላ ሃሪስ ጋር ረቡዕ ክርክር ለማካሄድ ፕሮግራም ይዘዋል። የዴሞክራቲኩ ጆ ባይደንም ዘመቻቸውን ቀጥለዋል። ቅዳሜ እለትም 'ቨርቹዋል' ዝግጅት አሰናድተዋል። ትራምፕ ለወባ በሽታ ፈዋሽነቱ የሚታወቀውን ሀይድሮክሲክሎሮኪውን መድኃኒትን በተደጋጋሚ ሰዎች እንዲወስዱ ሲወተውቱ ነበር። ከዚህ በፊት ይህንኑ መድኃኒት እንደወሰዱትና ጥሩ እንደሆነም ተናግረው ያውቃሉ። አሁን እርሳቸው ሀይድሮክሲክሎሮኪውንን ወስደው ይፈወሱ ይሆን ወይ የሚለው የጠላትም የወዳጅም ጥያቄ ሆኗል። ትራምፕ አሁን የሚወስዱት መድኃኒት ረምዴስቪር የተባለ ጸረ-ቫይረስ መድኃኒት ነው። ይህ መድኃኒት በኢቦላ ፈዋሽነቱ ይታወቃ። የትራምፕ በተህዋሲው መያዝን ተከትሎ ሴናተሮችና ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንዲሁም ረዳቶቻቸው ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል። እስከአሁን ምክትል ፕሬዝዳንቱና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተህዋሲው እንደሌለባቸው ተረጋግጧል። ሆኖም የቀድመው የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ኬሌያን ኮንዌይ፣ ሁለት የሪፐብሊካን ሴናተሮች ማይክ ሊ እና ቶም ቲሊስ ቫይረሱ ተግኝቶባቸዋል። የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ቢል ሰቴፒን በተመሳሳይ ቫይረሱ ተገኝቶበታል።", "ኮሮናቫይረስ፡ የፊት መከለያ መሳሪያ ያመረቱት የሥነ ሕንጻ ባለሙያ አቶ አሸናፊ ዘመቻ በሙያቸው የሥነ ሕንጻ ባለሙያ ናቸው። ለሥራቸው የሚያግዟቸውን የተለያዩ ነገሮችም ዲዛይን በማድረግ ይሰራሉ። ለዚሁ ስራቸውም እንዲረዳቸው በሚል የ3ዲ ፕሪንተር ያላቸው ሲሆን በዚያም የተለያዩ ባሕላዊ የሆኑ እቃዎችን፣ መብራቶችን ለማተም ይገለገሉበታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ በቅርበት ጉዳዩን ሲከታተሉ እንደነበር የሚገልፁት አቶ አሸናፊ፣ በወቅቱ ወረርሽኙ ስጋት ውስጥ ከትቷቸው እነደነበር ያስታውሳሉ። በወቅቱ ከመደናገጥ ይልቅ ምን ዓይነት አስተዋፅኦ ላበርክት የሚል ሃሳብ ይዘው ዙሪያቸውን ሲቃኙ ባላቸው 3ዲ ፕሪንተር የተወሰነ አገለግሎት መስጠት እንደሚችሉ አሰቡ። ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከቻይና አልፎ አውሮፓ፣ አሜሪካ እንዲሁም አፍሪካን ሲያዳርስ ግለሰቦችንም ሆነ የሕክምና ባለሙያዎችን ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ለማድረግ በሙያቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያስቡም ባላቸው ሕትመት መሳሪያ የፊት መሸፈኛ መስራት እንደሚችሉም ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ቻይና ላይ ቫይረሱ መከሰቱ በተሰማበት ወቅት ጀምሮ ጉዳዩ ያሳስባቸው እንደነበር ለቢቢሲ የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ በወቅቱበአገር ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ዋጋ በፍጥነት መናሩ እንዲሁም የአቅርቦት ችግር መኖሩ ማስተዋላቸው ምን ማድረግ አለብኝ ወደሚል ጥያቄ እንደመራቸው ይገልጻሉ። 3ዲ ፕሪንተር ካላቸው እና በእንግሊዝ አገር ከሚገኙ ሌሎች ባለሙያዎች ጋር በኢንተርኔት ላይ በነጻ የሚገኙ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ለአገራቸው የሚጠቅም ነገር ለማበርከትም አቀዱ። በዚህ የፊት መሸፈኛ የሕክምና ባለሙያዎችም ሆኑ ሌሎች ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ፊታቸውን የሚከልሉበትን መሳሪያ ከበይነ መረብ ላይ በመመልከት ሰሩ። እርሳቸው በ3ዲ ፕሪንተር ተጠቅመው ያመረቷቸውን የፊት መከለያዎች፣ ለሆስፒታሎችና ለሕክምና ባለሙያዎች በነጻ ሲሰጡ የፊት መከለያ መጠቀም በስፋት በባለሙያዎች ዘንድ አለመለመዱን ያስታውሳሉ። መጀመሪያ ላይ ያመረቷቸውን የፊት መከለያዎች በነጻ ለተወሰኑ ሆስፒታሎችና የሕክምና ባለሙያዎች ለግሰዋል። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች፣ እንዲሁም በግል ለሚያውቋቸው ሕክምና ባለሙያዎች በነጻም በሽያጭም መስጠት የጀመሩት አቶ አሸናፊ፣ ይህ የሕክምና ባለሙያዎች ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚከልሉበትን (ፌስ ሺልድ) መሳሪያ በበርካታ ባለሙያዎች ዘንድ ፍላጎትን በመፍጠሩ በክፍያ ለማቅረብ ተነጋገሩ። ይህንን የፊት መከለያ ማንም የ3ዲ ፕሪንተር ያለው ግለሰብ በቀላሉ በሚጫኑ ሶፍት ዌሮችን በመጠቀም ማተም የሚችል ቢሆንም ህትመቱ ግን ዘገምተኛ በመሆኑ በብዛት ለማዳረስ አስቸጋሪ እንዳደረገው ይገልጻሉ። በአገር ውስጥ 3ዲ ፕሪንተር ያለው ግለሰብ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የገለፄት አቶ አሸናፊ ዘመቻ፣ ለህትመት የሚያገለግለው ቁስ በቀላሉ አለመገኘቱ ደግሞ ሌላ ፈታኝ ነገር ነበር። ፊትን የሚሸፍነው ማይካ በቀላሉ ገበያ ላይ የሚገኝ ቢሆንም እርሱን አቅፎ የሚይዘው ፍሬም ግን በ3ዲ ፕሪንተር መታተም እንዳለበት ጨምረው ያብራራሉ። ይህ መሸፈኛውን የሚያቅፈው ፍሬም ፀጉር ላይ እንደሚቀመጥ ቲያራ ዓይነት ሲሆን፣ ተበስቶ የፊት መሸፈኛውን እንዲታሰርበት ይደረጋል። በ3 ዲ ፕሪንተር ላይ ለማተም ይጠቀሙበት የነበረው ቁስ አንዴ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ እንደማያገለግል የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ ልጠቀምበት ቢባል እንኳ በቀላሉ ባክቴሪያ እንደሚስብ በተጨማሪም የአቅርቦት እጥረት መኖር ፈታኝ ማድረጉን ያስረዳሉ። ይህ የፊት መከለያ ማይካ ከቻይና እንደሚገባ የሚገልፁት ባለሙያው፣ ነገር ግን ግንባር ላይ የሚያርፈው የፊት መሸፈኛ አካሉ ስፖንጅ መሆኑን ይገልጻሉ። ይህ ደግሞ በቀላሉ ባክቴሪያን ስለሚይዝ በየጊዜው በፀረ ተህዋሲያን ኬሚካል ለማጽዳት አስቸጋሪ መሆኑን አብራርተዋል። ነገር ግን ይህንን ከ3ዲ ፕሪንተር ውጪ መስራት አስፈላጊመሆኑን እንዲሁም በአገር ውስጥ በቀላሉ በሚገኝ ቁስ ቢሰራ መልካም መሆኑን ማስተዋላቸው የራሳቸውን የፊት መሸፈኛ ዲዛይን አድርገዋል። በዚህም ወቅት መሳሪያው ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጎ ቢሰራ መልካም መሆኑን ማስተዋላቸውንም ይገልጻሉ። በዚህም የተነሳ የሰሩት የፊት መሸፈኛ ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፣ ፊትን የሚከላከለው ማይካ ደግሞ በትንፋሽ አማካኝነት በቀላሉ ጭጋግ አይለብስም ሲሉ ያብራራሉ። እርሳቸው የሰሩት የፊት መከለያ ወጥ የሆነ ከፕላስቲክ የተሰራ ሲሆን ተቆርጦ በሌዘር ውስጥ እንደሚገባ ገልፀዋል። ለማጽዳት በሚፈለግበትም ወቅት ተፈትቶ በኬሚካል በቀላሉ ለማጽዳት እንዲቻል ተደርጎ መሰራቱን ያስረዳሉ። እነዚህ መሳሪያዎች ለየት የሚያደርጋቸው በቀላሉ ተፈታትተው መገጣጠማቸው ብቻ ሳይሆን፣ አገር ውስጥ በቀላሉ ከሚገኙ ቁሶች መሰራታቸውም ሌላው ለየት የሚያደርጋቸው ነገር መሆኑን ይገልጻሉ። አቶ አሸናፊ የሰሩት የፊት መሸፈኛ ቅርፁን ጠብቆ እንዲቆይ እና በቀላሉ እንዳይሰብ ተደርጎ መሰራቱን ጨምረው ተናግረዋል።", "ረመዳን፡ ጾም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥና የሚሰጠው ጥቅም ታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት እነሆ ተጀምሯል። በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት የሚተበቀው ይህ ወቅት ቀኑ በጾም ምሽት ላይ ደግሞ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ተሰብስቦ በአንድነት ማፍጠር የተለመደ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በገጠማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ላይ ተሰብስቦ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን መካፈልና ከተለያዩ ሰዎች ጋር መሰባሰብ እንዲቀር ይመከራል። ስለዚህም በሐይማኖት አባቶች የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ይህንን ቅዱስ የጾም ወቅት እራሳችንንና ሌሎችን በመጠበቅ ልናሳልፈው ይገባል። በወረርሽኙ ምክንያት ምዕመናን ቀደም ሲል ሲያከናውኗቸው የነበሩ የጋር ሥርዓቶችን ማድረግ ባይችሉም፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከቅርብ የቤተሰብ አባላቸው ጋር የተለመደውን ሥርዓት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። መጾም ታላቅ መንፈሳዊ ጸጋ እንደሚያስገኝ የሐይማኖት አባቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገር ደግሞ የጤና ባለሙያዎች ጾም ከሚያስገኘው መንፈሳዊ በረከት በተጨማሪ ለአካላዊ ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታ አለው ይላሉ። ዝርዝሩን እነሆ. . . በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ረመዳንን በጾም ያሳልፋሉ። ጀንበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ። ሰውነታችን ከጾም ጋር የሚተዋወቀው ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ከቀመስን ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም ማለት አንጀታችን ከተመገብነው ምግብ የሚያገኛቸውን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አሟጦ ከጨረሰ በኋላ ነው የሚሆነው። ከዚህ በኋላ ሰውነታችን ተስፋ ይቆርጥና ፊቱን ጡንቻችንና ጉበታችን ውስጥ ወደተከማቸ ጉሉኮስ ያዞራል። የተቀረው የሰውነታችን አካል ጉልበት የሚያገኘውም ከዚህ የመጠባበቂያ 'ግምጃ ቤት' ከሚያገኘው ኃይል ይሆናል ማለት ነው። ከጡንቻና ከጉበት የጉሉኮስ ክምችት ሲያልቅ ሰውነታችን ሌላ አማራጭ ስለማይኖረው ስብን (Fat) ማቃጠል ይጀምራል። ከዚህ በኋላ ሙቀትና ጉልበትን የሚያገኘውም ከሌላ ሳይሆን ስብን በማቃጠል ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ። የሚቃጠለው ስብ በመሆኑ ክብደት መቀነስ፣ የኮሌስትሮል መጠን መውረድ ይኖራል። የስኳር መጠናችን በዚህ ወቅት ዝቅ ማለቱ አይቀርም። ሆኖም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ድካምና መዛልን ያስከትልብናል። ይህን ተከትሎ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና መልካም ያልሆነ የአፍ ጠረን ሊከተል ይችላል። ይህ የሚሆነው በረሀብ ምክንያት ሆዳችንን ሲሞረሙረንና ያለ ምግብ መቆየቱ ለሰውነታችን እየከበደው ሲመጣ ነው። ከ3-7ኛ ቀን፤ ሰውነታችን በፈሳሽ እጥረት የሚጎዳበት ጊዜ ሰውነታችሁ ጾሙን እየተለማመደ ሲመጣ በውስጣችን የሚገኘው የስብ ክምችት እየተሰባበረ ራሱን ወደ የደም ስኳርነት (Blood sugar) ይለውጣል። የምንወስደው ፈሳሽ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደመሟጠጥ (ዲሃይድሬሽን) ስለሚያመራ በ\"ማፍጠሪያ\" ሰዓትና ከዚያም በኋላ ባለው የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በርከት ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ ይመከራል። በጾም መግደፊያ ሰዓት የምትወስዱት የምግብ መጠን ጉልበት ሰጪ የሆኑ ተመጣጣኝ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በፕሮቲን ከበለጸጉ ምግቦች ባሻገር ጨው እና በርከት ያለ ውኃ ከሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦች ጋር ማግኘት ለሰውነታችን መልካም ሁኔታን ይፈጥራል። ከ8ኛ-15ኛ ቀናት በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጾሙን ተላምዶታል። በዚህም የተነሳ ድካምና መዛሉ እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። ዶክተር ራዚን ማህሩፍ የአኔስቴሺያና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አማካሪ ናቸው። በኬምብሪጅ አዴንብሩክ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሠሩት። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ጊዜ ጾሙ ለሰውነታችን ሌላም በጎ ጎን ይዞ ይመጣል። ለምሳሌ በሌላው ጊዜ በርከታ ያለ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን የምንወስድ ከነበረ ሰውነታችን ሥራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ፈተና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ወይም ደግሞ እክል ይገጥመዋል። በጾም ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ይስተካከላል። \"ምክንያቱም የካሎሪ ክምችት ስለማይበዛበት ሰውነታችን ወደ ሌሎች ሥራዎች ትኩረቱን ያደርጋል\" ይላሉ ሐኪሙ። ለዚህም ነው \"ጾም ኢንፌክሽን በመዋጋትና ጤናን በመመለስ አስተዋጽኦ የሚኖረው።\" ከ16ኛ- 30ኛ ያሉ ቀናት በረመዳን ሁለተኛው ምዕራፍ (ከ15ኛው ቀን ጀምሮ) ሰውነት ሙሉ በሙሉ ጾሙን ይላመዳል። በዚህ ጊዜ እነ ደንዳኔ፣ ጉበት፣ ኩላሊት እንዲሁም ቆዳ ሁሉም ራሳቸውን በማጽዳት ሂደት (ዲቶክሲፊኬሽን) ውስጥ ነው የሚሆኑት። ዶክተር ማህሩፍ እንደሚሉት በዚህ ወቅት ጤና ተመልሶ፣ ሰውነታችን የቀድሞውን ጉልበቱን የሚያገኝበትና የማስታወስ አቅምና ትኩረት የማድረግ ብቃት ወደ ቀድሞው ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ፕሮቲን መሄድ አይኖርበትም። ይህ የሚሆነው ብዙውን ጊዜ ረሀብ ሲሰማንና ሰውነታችን ከጡንቻዎቻችን እየቀሰመ የሚወስደውን ምግብ ማደን ሲጀምር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀጥለው ግን ለቀናትና ለሳምንታት በተከታታይ ስንጾም ነው። የረመዳን ጾም የሚጸናው የየዕለቱ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ብቻ ስለሆነ ሰውነታችን ጉልበት ከምግብ እንዲያገኝ የ\"ኢፍጣር\" ሰዓት ዕድል ይሰጠዋል። ፈሳሽም እንደልብ ያገኛል። ይህ ጡንቻዎቻችን ውስጥ ያለን ክምችት ለመጠባበቂያነት ያቆይልናል። የተወሰነ ኪሎ እንድንቀንስም ይረዳናል። ይህም ለሰውነት መልካም ነገር ነው። ጾም ጤናን ይጎዳል? የካምብሪጁ አዲንብሩክ ሆስፒታል ሐኪም ዶክተር ማሕሩፍ ምላሻቸው \"እንደሁኔታው\" የሚል ነው። እንደርሳቸው አመለካከት በርከት ያሉ ሁኔታዎች ጾምን ለሰውነታችን ጎጂም ጠቃሚም ሊያደርጉት ይችላሉ። ጾም ለሰውነታችን መልካም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት መቼ ምን መብላት እንዳለብን ትኩረት እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው። ሁለተኛው ክብደታችንን መቆጣጠርና፣ የካሎሪ መጠን መወሰን ስለሚያስችል ነው። ለወር ያህል መጾም እምብዛምም የሚያመጣው የጤና እክል ባይኖርም ከዚያ በኋላ ግን ለተከታታይ ጊዜ ያለማቋረጥ መጾም ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ሐኪሙ ሳይጠቁሙ አያልፉም። እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ ያለማቋረጥ መጾም በቋሚነት ኪሎ ለመቀነስ አይረዳም። ምክንያቱም ከሆነ ጊዜ በኋላ ሰውነታችን ስብን ወደ ጉልበት መቀየር ያቆምል። ከዚያ ይልቅ ፊቱን ወደ ጡንቻዎቻችን ነው የሚያዞረው። ይህ ደግሞ ጤናማ አይደለም። ምክንያቱም ሰውነታችን ከሆነ ወቅት በኋላ \"በመራብ ስሜት\" ላይ ስለሚቆይ ነው። ሐኪሙ እንደሚሉት ከረመዳን ውጭ መጾም ቢያስፈልግ እንኳ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያፈራረቁ መጾም በመደዳ ለተከታታይ ቀናት ከመጾም እጅግ የተሻለ ጤናማ ተግባር ነው። \"ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል\" ይላሉ እኚሁ ሐኪም።", "በእስራኤል ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱ መንትዮች በቀዶ ህክምና ተለያዩ ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱ የአንድ ዓመት መንትዮች በእስራኤል ያልተለመደ በተባለለት ቀዶ ሕክምና ተለያይተው ለመጀመሪያ ጊዜ ለመተያየት በቁ። ባለፈው ሳምንት በቢርሼባ ከተማ በሶሮካ የሕክምና ማዕከል 12 ሰዓታት የፈጀውን ቀዶ ህክምና ለማከናወን የወራት ዝግጅት ተደርጓል። በደርዘን የሚቆጠሩ የእስራኤል እና የሌሎች ሃገራት ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። በስም ያልተጠቀሱት መንትያ እህትማማቾች ከህክምናው በኋላ በጥሩ ሁኔታ እያገገሙ ነው ተብሏል። \"በራሳቸው እየተነፈሱ እና እየተመገቡ ነው\" ሲሉ የሶሮካ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ክፍል ኃላፊ ኤልዳድ ሲልበርስተይን ለእሥራኤሉ ቻናል 12 ተናግረዋል። በዓለም ላይ 20 ጊዜ ብቻ የተደረገው ይህ መሰል ቀዶ ህክምና በእስራኤል ሲደረግ የመጀመሪያው ነው። ቀዶ ህክምናው ከመደረጉ ከወራት በፊት የሲሊኮን ከረጢቶች ወደ ጭንቅላታቸው ገብተው በጊዜ ሂደት ቆዳቸው እንዲለጠጥ ተደርጓል። የራስ ቅሎቹ እንደገና ከተሠሩ በኋላ ተጨማሪ ቆዳቸው የራስ ቅላቸውን እንዲሸፍን ጥቅም ላይ ውሏል። የመንትዮቹ የ 3ዲ ምናባዊ እውነታን የሚያሳይ ዝግጅት መደረጉንም የሶሮካ ዋና የነርቭ ቀዶ ህክምና ባለሙያ የሆኑት ሚኪ ጊዶን ተናግረዋል ። አክለውም \"ደስተኛ ያደረገን ሁሉም ነገር እንዳሰብነው መሆኑ ነው\" ብለዋል። ከአንድ ዓመት በፊት የተወለዱት ልጆች ወደፊት ሙሉ በሙሉ መደበኛ ሕይወት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።", "ኮሮናቫይረስ ፡ ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? - የኮቪድ-19 ፀር ማነው? ውሃን ሳሙና እንደ ዘንድሮ ከብረው አያውቁም ብንል ማጋነን አይሆንም። በውሃና ሳሙና መሪነት ስንቱ ኮሮናቫይረሰን ከመዳፉ ጠራረገ። እርግጥ ነው ሳሙናና ውሃ ለመዳፋችን ብርቅ አይደሉም። እንዲህ በሕይወታችን አስፈላጊ ይሆናሉ ብሎ የተነበየ ካለ ግን እሱ ሐሰተኛ ነው። ውሃና ሳሙና አሁን ከነርቫችን ጋር ተናኝተዋል። ሳናስበው ሁላ መታጠብ ጀምረናል። ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ብዙ መሣሪያ ታጥቀናል። ጭምብል ቢሉ ጓንት፤ ራስን ማግለል ቢሉ በጸረ ተህዋስ ቫይረስን መግደል። ከሁሉም በላይ ቀላሉ መሣሪያ ግን እጅን በሳሙና እሽት አድርጎ መታጠብ ነው። ኮሮናቫይረስ ገዳይ ወረርሽኝ ነው ተብሎ ወርሃ የካቲት ላይ ሲታወጅ የጤና ሰዎች አዲሱን ቫይረስ እንዴት እንደምትከላከከሉ እንንገራችሁ ብለው ብቅ አሉ። እንዲህም አሉ፤ የመጀመሪያውና የመጀመሪያው እጅን መታጠብ ነው። ለዚያውም በሳሙና። ከተገኘ ሞቅ ባለ ውሃ። ቢያንስ ለ20 ሰከንድ መታጠብ። በኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴድሮስ የሚመራው የዓለም ጤና ድርጅት እጃችን እንዴት መታጠብ እንደምንችል የሚያሳይ ምስል ሠራ። ይኸው ይህ በቫይረስ የሚተላለፈውን ወረርሽኝ ስድስት ወር አለፈው። በርካታ ከተሞች ተዘግተው ተከፈቱ። እንደገና የተዘጉም አሉ። ሰዓት እላፊም ያወጁም መቶዎች ናቸው። ቫይረሱ ግን እንዲህ በቀላሉ አልተበገረም። ለዚህም ነው አሁንም እጃችሁን ታጠቡ እየተባለ የሚመከረው። ነገር ግን እጃችንን በአግባቡ እየታጠብን አይደለም የሚሉ ቅሬታቸው አሁንም ይደመጣሉ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሠራ አንድ ጥናት የሕክምና ማዕከሎችን ከሚጎበኙ 1 ሺህ ሰዎች 1 በመቶ ብቻ ናቸው በአግባቡ እጃቸውን የታጠቡት ይላል። እውን ውሃና ሳሙና ቫይረሱን ሙልጭ አድርገው ያጠፋሉ? በደንብ ነዋ! ይላሉ የቦስተን ማሳቹሴትስ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ቶማስ ጊልበርት። ባለሙያው እንደሚሉት ኮሮናቫይረስ የተሠራበት የኬሚካል ውህድ በትንሽ ሳሙናና ሙቅ ውሃ ብትንትኑ ይወጣል። \"ቫይረሶች ቅባታማ ባህሪ ያለው ሽፋን ያላቸው ናቸው። ይህ ቅባትነት ያለው ሽፋን ውስጥ ያለውን ዋና ቫይረስ የሚከላከል ነው። ይህ ሽፋን በሳሙናና ውሃ መሰበር ይችላል። ሽፋኑ ተሰበረ ማለት ውስጥ ያለው ቫይረስ ተጋለጠ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ቫይረሱን ያጠፋዋል\" ይላሉ ባለሙያው። “ከዚህ በኋላ በውሃና ሳሙና መታጠብ አያስልፍግም የሚባልበት ጊዜ ቅርብ ነው ብዬ አላስብም።” “መጀመሪያን እጅዎን ያርጥቡ፤ ከዚያ ሳሙናው አረፋ ከሰራ በኋላ ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች ያህል እጅን ማሸት ነው“ ሲሉ ባለሙያው ይመክራሉ። ጊልበርት እንደሚሉት ሳሙናው የቫይረሱን ሽፋን ሰብሮ ለመግባት 20 ሰከንድ ይበቃዋል። ሙቅ ውሃ ከታከለበት ደግሞ ሳሙናውን ሥራውን በፍጥነት እንዲያከናውን ያግዘዋል። በኬንት ዩኒቨርሲቲ የሞለኪዩላር ሳይንስ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ማርቲን ሚካየሊስ ደግሞ ውሃ ብቻውን የቫይሱን ሽፋን ለመስበር በቂ አይደለም ይላሉ። “ኩሽና ውስጥ ስናበስል ዘይት እጃችንን ከነካው በውሃ ብቻ ለማስለቀቅ እንደሚከብደን ሁሉ የኮሮናቫይረስን ለማግኘት ሳሙና የግድ ነው።“ ነገር ግን የውሃና ሳሙና ድል በእንግሊዝኛው ሳኒታይዘር እየተባለ ከሚጠራው ፀረ-ተህዋስ ፈሳሽ ጋር ሲምታታ ይስተዋላል። ዘንድሮ ሳኒታይዘርና ጭምብል ረስቶ ከመውጣት ሞባይል ስልካችንን ረስቶ መውጣት የተሻለ ነው። ነገር ግን ባለሙያዎቹ ሳኒታይዘር ለችግር ጊዜ ነው መሆን ያለበት ይላሉ። ቤት ውስጥ ውሃና ሳሙና ካለ ሳኒታይዘር መጠቀም አይመከርም። ጊልበርት በትንሽዬ ብልቃጥ ሳኒታይዘር ይዞ መንቀሳቀስ አይከፋም ይላሉ። ነገር ግን እኔን ብትጠይቁኝ ይላሉ ባለሙያው “እኔን ብትጠይቁኝ የምመርጠው ውሃና ሳሙና ነው።” እጃችንን ምን ያክል እንታጠብ? ወረርሽኙ የጀመረ ሰሞን በርካታ አገራት ዜጎቻቸው በየጥቂት ሰዓቱ እጃቸውን እንዲታጠቡ ይመክሩ ነበር። ቤት ብትውሉ እንኳ እጃችሁን መታጠብ እንዳትረሱ የሚል መልዕክት መስማት የተለመደ ነበር። ፕሮፌሰር ጊልበርት ግን ቤት የምንውል ከሆነ አስር ጊዜ እጅን መታጠብ አስፈላጊ አይደለም ባይ ናቸው። ቢሆንም ሽንት ቤት ከተጠቅምን በኋላም ሆነ ማዕድን ከማዘጋጀትችንና ከመቁረሳችን በፊትና በኋላ እጅን መታጠብ ግድ ይላል። ባለሙያው በጭራሽ እንድነዘጋ አይፈልጉም። እጃቸውን በተደጋጋሚ መታጠብ ያለባቸው ሰዎች አሉ። ለምሳሉ ቤታቸው ውስጥ የኮቪድ-19 ታማሚ የሚንከባከቡ ሰዎች ውሃና ሳሙና ወዳጃቸው ሊሆን ይገባል። አሊያም ቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላሉ የተባሉ ዕቃዎችን የነኩ ሰዎችን በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። መኖሪያ ቤታችሁ ብዙ ሰዎች ካሉም እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ ይመከራል። አንድ ጥናት ሰዎች ቫይረሱ ያለበት ሰው ወይም ዕቃ ከነኩ ወዲያውኑ እጃቸውን መታጠባቸው በጣም አዋጭ መሆኑን ይጠቁማል። አንዳንድ ሰዎች ከዚህ በፊት ከምንጠቀመው ሳሙና ይልቅ ፀረ-ተህዋስ ሳሙናዎች የበለጠ ኮቪድ-19ኝን ይከላከላል በማለት ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ። ይሁንና እንደ ሚካየሊስ ከሆነ የትኛውም ሳሙና የኮሮናቫይረስ አምጪ ተህዋስን የመግደል አቅም አለው። ሁለቱም ባለሙያዎች ኮሮናቫይረስን ከመዳፋችን ጠራርጎ ለማጥፋት የግድ ለመጠጥ የሚሆን ንፁህ መጠቀም እንደሌለብን ይመክራሉ። የውሃ አቅርቦት በቂ ባልሆነባቸው የዓለማችን ክፍሎች በውሃና በሳሙና በቀላሉ እጅን መታጠብ ቀላል ላይሆን ይችላል። የዶክተር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት በቅርቡ ያወጣው አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በዓለማችን ከአምስት ትምህርት ቤቶች ሁለቱ ብቻ ናቸው በቂ የውሃ አቅርቦት ያላቸው። ይህ ጥናት የተሰራው ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ነው። ሌላው አስገራሚ የኮሮናቫይረስ ተፅዕኖ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን መቀነሱ ነው። ለምሳሌ የኢንፍሉዌንዛ በሽታ ከሌላው ጊዜ በተለይ ዘንድሮ እጅግ ቀንሷል። ባለፈው ዓመት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መጋቢትና ነሐሴ ወር ላይ ቢያንስ 700 ሰዎች በጉንፋን ነክ በሽታዎች በጠና ይታመሙ ነበር። ዘንድሮ ግን አንድ ሰው ብቻ ነው መሰል በሽታ የታየበት። ለዚህም ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ሰዎች አካላዊ ንክኪ መቀነሳቸው ነው። ወጣም ወረደ ኮሮናቫይረስ ክትባት እስኪገኝለት ድረስ እጅ መታጠባችን፤ ንክኪ መቀነሳችንን መቀጠሉ አዋጭ ነው። መቼም ሚሊዮኖች የተጠቁበት፤ አእላፍ ያለቁበትን በሽታ በዓይናችን እያየን መዳፈሩ አዋጭ አይደለም።", "በኮቪድ ወረርሽኝን ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የተሻለ ቆጥበዋል ዓለም አቀፉን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተከትሎ በዩናይትድ ኪንገደም ከስድስት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ወጪያቸውን በመቀነስ የተሻለ ገንዘብ ቆጥበው መገኘታቸውን እንድ ጥናት አመላከተ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝነት ተከትሎ በርካቶች ሥራ አጥ አልያም በእዳ ተዘፍቀው ቁጠባቸውን ያጡ እንዳሉት ሁሉ፤ በወረርሽኙ ምክንያት ወጪያቸውን ቀንሰው ቁጠባቸውን የጨመሩ ሰዎች አሉ ብሏል ኤልሲፒ የተባለው የፋይናንስ አማካሪ ድርጅት የሰራው ጥናት። እንደ ጥናቱ ከሆነ፤ በወረርሽኙ ወቅት የትራንስፖርት ወጪ መቀነስ፣ ለመዝናናት የሚደረግ ጉዞ መገደቡ እና ለምግብ ይወጣው የነበረው ወጪ መቀነሱ ከስድስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ሰዎች ቁጠባቸው እንዲጨምር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። ሰዎች ወረርሽኙን ተከትሎ የተዋወቀው ከቤት ሆኖ መስራት እንዲቀጥል የሚደረግ ከሆነ የመሰል ሰዎች የቁጠባ መጠን ሊጨምር እንደሚችል ጥናቱ አመላክቷል። የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍጆት እና ልጆች በቤት በመቆየታቸው ተያይዘው የሚመጡ ወጪዎች የቁጠባ መጠን እንዲቀንስ ካደረጉ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል። በአጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ዝቀተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ክፉኛ ተጎድተዋል። በዩናይትድ ኪንገደም ብቻ 9 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ገቢያቸው በመቀነሱ ቋሚ ወጪያቸውን ለመሸፈን ብድር መውሰዳቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ስታስቲክስ ድርጅት ይፋ አድርጓል። ኤልሲፒ የተባለው የፋይናንስ አማካሪ ድርጅት የሰራው ጥናት እንዳሳየው ከወረርሽኙ መከስት ወዲህ የተሻለ ቆጥበው የተገኙት እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ናቸው። ጥናቱ እንዳመላከተው ከሥራ ገበታቸው ያልፈተናቀሉት እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑት ሰዎች የትራንስፖርት እና ለሽርሽር የሚያወጡት ወጪ በከፍተኛ መጠን ቀንሷል። ሪፖርቱ ጭማሪ የታየበት ቁጠባ ብድር ለመሸፈን እና በጥሩታ ወቅት ወጪን ለመሸፈን ሊውል ይችላል ብሏል።", "ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት ለበርካቶች ፕሮስቴት ሲባል ሁለቱ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች አካባቢ ወይም የዘር ፍሬ ከረጢቱ ውስጥ ያለ አካል እንደሆነ ነው የሚያስቡት። የኩላሊት፣ የፕሮስቴት፣ የሽንት ፊኛ እና ቧንቧ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፍፁም ሠለሞን ግን ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች ያለ አካል ነው ይላሉ። እንደ ዶ/ሩ ገለጻ ከሆነ ፕሮስቴት በወንድ ልጅ ብልት እና ፊኛ መካከል የሚገኝ እጢ ነው። ፕሮስቴት የዘር ፈሳሽ የማመንጨት ጥቅም አለው። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ወደ ውጪ ሲፈስ ሰባ በመቶ ያህሉን የሚያመነጨው ፕሮስቴት መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ሀዋስ የሚዋኘው እንዲሁም ምግቡን የሚያገኘው ከዚህ ፈሳሽ መሆኑን አክለው ይጠቅሳሉ። ታድያ የፕሮስቴት ችግር ያለበት ወንድ የዘር ፈሳሹ ወደ ውጪ መፍሰሱን ትቶ የሚመለሰው ወደ ፊኛው ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም ፕሮስቴት፣ የዘር ፈሳሹ ወደ ፊኛ እንዳይመለስ እና ወደ ውጪ እንዲወጣ ይረዳል። ፕሮስቴት ልክ እንደ ምራቅ አመንጪ እና ታይሮይድ እጢዎች ሁሉ እጢ (ግላንድ) ነው። የፕሮስቴት እጢ የሚገኘው ወንድ ላይ ብቻ ነው። እንደ ዶ/ር ፍፁም ገለጻ በየትኛውም የሰውነታችን ክልፍ ላይ ካንሰር ሊከሰት ይችላል፣ ስለዚህም ፕሮስቴትም ለካንሰር  ይጋለጣል። በዓለም ላይ ከስምንት ወንዶች መካከል አንዱ በሕይወት ዘመኑ በፕሮስቴት ካንሰር ይያዛል። ፕሮስቴት አጥቢ እንስሳት ላይ በሙሉ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስም ካንሰሩ ከሰው ውጪ የታየው ውሾች ላይ ብቻ ነው። 80 በመቶ ያህሉ ፕሮስቴት ካንሰር ቀስ ብሎ የሚያድግ እንዲሁም ህመም ሳያስከትል ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ነው። በብዛት የፕሮስቴት ካንሰር በመጀመሪያ ከፕሮስቴት እጢ ላይ ተወስኖ ይቆይና ከባድ ጉዳት በማያስከትል መልኩ ቀስ እያለ የሚያድግ ችግር ነው። ለፕሮስቴት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ እድሜ ነው። እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑ፣ ጥቁር ወንዶች እንዲሁም በቤተሰባቸው ውስጥ የፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚገኝ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎችም እድሜያቸው 40 የሞላቸው ወንዶች በየዓመቱ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ዶ/ር ፍፁም በበኩላቸው ፕሮስቴት ካንሰር ከ40 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ የመገኘት እድሉ እጅጉን በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። እድሜያቸው ከ20 እስከ 30 የሆነ ወንዶች በፕሮስቴት የመያዝ እድላቸው አንድ በመቶ ብቻ ነው። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የፕሮስቴት ካንሰር የሚከሰተው እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ወንዶች ላይ ነው ይላሉ ዶ/ር ፍፁም። አፍሪካውያን ከነጮች አንጻር ሲታይ በዚህ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው ግለሰቦች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። ወንድም፣ አባት፣ አያት እንዲሁም አጎቱ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘበት ግለሰብ የተጋላጭነት ዕድሉ ሰፊ ነው። ከቅርብ ቤተሰብ መካከልም አባቱ በዚህ ካንሰር የተያዘ እና አያቱ የተያዘ ወንድ እኩል የተጋላጭነት ልክ እንደሌላቸው ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። አባቱ ወይንም ወንድሙ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ወንድ፣ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከሁለት እና ሦስት እጥፍ በላይ ተጋላጭ ነው። ሌላኛው መታየት ያለበት በቤተሰብ ውስጥ ካንሰር የተያዘው ሰው በስንተኛው ዕድሜው ላይ ተገኘበት የሚለው ወሳኝ ነጥብ መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። ይህንንም ሲያብራሩ ከ65 ዓመት በታች የፕሮስቴት ካንሰር የተገኘበት አባት፣ ልጁ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል ሲሉ ያስረዳሉ። ይህም ማለት ልጁ እስከ 5 እጥፍ ድረስ የተጋለጠ ነው። ሌላኛው ደግሞ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም፣ አባቱ እና አያቱ በፕሮስቴት የተጠቁ እና አባቱ ብቻ የተያዘ ልጅን ብናወዳድር፣ ይህ ሁለቱም የቤተሰብ አባላት የተያዙበት ግለሰብ የበለጠ ተጋላጭ ነው ይላሉ። የዘረመል እክል (ጄኔቲክ ሚውቴሽን) ላይ እክል ካለ የበለጠ ለዚህ ካንሰር ያጋልጣል። ካንሰር በአብዛኛው ሲታይ ህዋሱ በተነሳበት አካል ወይንም ስፍራ ከመጠን በላይ ይራባል። ከዚያም በመቀጠል ባለበት አካል ላይ ብቻ ተገድቦ ሳይቀመጥ ወደ ሌላ የአካል ክፍል ይሰራጫል። ፕሮስቴት ካንሰር ተገቢውን ሕክምና በተገቢው ሰዓት ካላገኘ የሽንት ፊኛን ሊያፍን ያችላል። የፕሮስቴት እጢ ከተራባ በኋላ ፕሮስቴት አጠገብ ያሉ የሽንት ቧንቧ እና ፊኛ ላይ ይዛመታል። ከዚያም አልፎ በደም ስር ተሰራጭቶ ወደ ጀርባ ይሄዳል። ፕሮስቴት ካንሰር ብዙ ጊዜ በደም ስር አድርጎ ወደ ጀርባ፣ አከርካሪ አጥንት እና ሆድ ውስጥ ወዳሉ ንፍፊቶች ይሰራጫል። የፕሮስቴት ካንሰርን ለመከላከል አመጋገብን ማስተካከል ዋነኛው መፍትሄ ነው። አትክልት እና ፍራፍሬ የበዛበት፣ ዓሳ፣ የዓሳ ዘይት፣ ኦሊቭ ኦይል ያለው ምግብ መመገብ ለመከላከል ይረዳል። ከእነዚህ በተጨማሪ አረንጓዴ ሻይ እነዲሁም ቫይታሚን ዲ መጠቀም የመከላከል አቅምን ያጎለብታል። የፕሮስቴት ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ ቀስ ብሎ የሚያድግ በመሆኑ፣ ከጀመረበት አንስቶ ለመሰራጨት እና ሕይወትን አደጋ ላይ ለመጣል ረዥም ጊዜ ይወስድበታል። ስለዚህም ቢያንስ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው። በተለይ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው፤ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ። ቅድመ ምርመራ ለመጀመር የተለያዩ አገራት፣ የተለያዩ መመርያዎች እንዳላቸው የሚናገሩት ዶ/ር ፍፁም፣ አንድ ሰው እድሜው ከ50 አስከ 55 ዓመት ሲሆን ቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል። ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያለው ግለሰብ ደግሞ እድሜው ከ40 አስከ 45 ላይ እያለ ምርመራውን ቢጀመር መልካም መሆኑን ገልፀዋል። “ቢያንስ ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ይመከራል” ሲሉ ያክላሉ። ከሁሉ በፊት በቤተሰብ ውስጥ ያለን የፕሮስቴት ካንሰር ታሪክን ማወቅ እንዲሁም ወደ አርባዎቹ የእድሜ ክልል ሲገባም በተወሰ ጊዜው ውስጥ ምርመራ ማድረግ ችግሩ ካለ ስር ሳይሰድ ለማከም ይረዳል። ምርመራው ተደርጎ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ዓይነት ሕክምናዎች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከእነዚህም ውስጥ በቀዶ ሕክምና ካንሰሩን ማውጣት፣ የጨረር ሕክምና ወይንም ደግሞ የወንድ ልጅ ቴስቴስትሮን ካንሰሩን በዋነኛነት ስለሚመግብ በሰውነት ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን መጠንን ለመቀነስ ሕክምና ይሰጣል።", "የኮቪድ ወረርሽኝ ትልቅ አደጋ ነው - ኪም ጆንግ ኡን በሰሜን ኮሪያ በፍጥነት እየተዛመተ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለሀገሪቱ \"ትልቅ አደጋ\" ነው ሲሉ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን መናገራቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሞት መመዝገቡን ያስታወቀችው ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሁለንተናዊ ትግል እንዲደረግ ጠይቀዋል። ባለስልጣናቱ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው መረጋገጡን አስታውቀዋል። ባለሙያዎች በበኩላቸው አሁን ተያዙ የተባሉት የመጀመሪያ እንዳልሆኑና ለተወሰነ ጊዜ እየተዛመተ ነበር ይላሉ። በሰሜን ኮሪያ ወረርሽኙ ከፍኛ ሊሆን እንደሚችልና አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋትም ጭሯል። 25 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ በክትባት መርሃ ግብር እጥረት እና በደካማ የጤና አጠባበቅ ስርአት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውም ተገልጿል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በማይታወቅ ትኩሳት እንደተጠቁ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ቅዳሜ እለት ዘግበዋል። የሃገሪቱ የመመርመር አቅምም የተገደበ በመሆኑ በኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። ይህ አኃዝ አርብ እና ሐሙስ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም ሁኔታ በሰሜን ኮሪያ እየተከሰተ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አንዳንድ ፍንጮችን ይሰጣል ተብሏል። \"የከፋው ወረርሽኝ በአገራችን ላይ የወደቀ ትልቅ አደጋ ነው\" በማለት መሪው መናገራቸውን የኬ ሲ ኤንኤ የዜና ወኪል ዘግቧል። ኪም ለዚህ ችግር መንስኤ ያሉትን የቢሮክራሲ ቀውስ እና የህክምና ብቃት ማነስ እንደሆነ ጠቁመው እንደ ጎረቤት ቻይና ካሉ ሀገራት ምላሽ መማር እንደሚቻልም ጠቁመዋል። ከሚያዝያ ወር ጀምሮ 27 ሰዎች ትኩሳት ካጋጠማቸው በኋላ መሞታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በኦሚክሮን ልውጥ ከሞተው አንድ ሰው በስተቀር እነዚህ ግለሰቦች ኮቪድ- 19 ተይዘው ነበር ወይ ስለሚለው ጉዳይ ሪፖርቶቹ ያሉት ነገር የለም።", "‘የዓለም ምርጧ የጽዳት ባለሙያ’ ለምንድን ነው በነጻ አገልግሎት የምትሰጠው? አውሪ ካታሪና እጅግ የቆሸሸ ቤት ስታጸዳ የተቀረጸው ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ተሰራጭቷል። አሁን በመላው ዓለም ቤቶችን በነጻ እያጸዳች ነው። በዓለም ምርጧ የጽዳት ባለሙያ ነኝ የምትለው አውሪ “በጣም የቆሸሸ ነገር የሥራዬን ውጤትነት ለማየት ስለሚረዳኝ እመርጠዋለሁ” ትላለች። ለምን እና ለማን ነው የጽዳት አገለግሎቷን በነጻ የምትሰጠው?", "ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ሥራውን ማቋረጡን አስታወቀ የፈረንሳዩ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ ሠራተኞቹ ትግራይ ውስጥ ከተገደሉ በኋላ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን ገለጸ። ሰኔ 17/2013 ዓ.ም ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ እየተጓዙ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ጥቃት ፈጻሚዎች የተገደሉት የእርዳታ ድርጅቱ ሠራተኞች ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ ደግሞ የስፔን ዜግነት ያላት ናት። ድርጅቱ እንዳለው በሠራተኞቹ ላይ በተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ዙሪያ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግና በክልሉ ውስጥ የእርዳታ ሠራተኞች ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ እንዲፈቀድ ጠይቋል። በሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ኤምኤስኤፍ በትግራይ ክልል ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት አቢ አዲ፣ አዲግራትና አክሱም ውስጥ የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን አስታውቋል። ነገር ግን ከእነዚህ አካባቢዎች ውጪ ባሉ ሌሎች አካባቢዎች አባላቱ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሥራቸውን ማከናወን እንደሚቀጥሉ ገልጿል። \"በባልደረቦቻችን ላይ ግድያው ከተፈጸመ ሁለት ሳምንት ሊሆነው ቢቃረብም ማንም ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን በተጨማሪም በግድያው ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ምንም ግልጽ ያለ ነገር የለም\" ሲሉ የድርጅቱ ኃላፊ ቴሬሳ ሳንክሪስቶቫል ተናግረዋል። ጨምረውም በባልደረቦቻቸው ላይ በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምርመራ አድርገው ምን እንደተከሰተና ተጠያቂው ማን እንደሆነ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በዚህም ሳቢያ \"በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በጣም ከባድ ነገር ግን አስፈላጊ የሆነውን በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች የምናካሂዳቸውን ሥራዎቻችንን ለማቋረጥ ወስነናል\" ብለዋል። የእርዳታ ሠራተኞቹ ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በጉዞ ላይ እንዳሉ የነበራቸው ግንኙነት መቋረጡንና በተከታዩ ቀን የሁለቱ ኢትዮጵያውያንና የስፔናዊቷ አስከሬን ይጓዙበት ከነበረው መኪና ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ መገኘቱንም የድንበር የለሽ ሐኪሞች በወቅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቶ ነበር። በጥቃቱ የተገደሉት የህክምና እርዳታ ድርጅቱ ባልደረቦች በየካቲት ወር ላይ በድርጅቱ በረዳት አስተባባሪነት ሥራ የጀመረው የ31 ዓመቱ ዮሐንስ ሃለፎም፣ በግንቦት ወር ለግብረ ሰናይ ድርጅቱን መሥራት የጀመረው የ31 ዓመቱ ሹፌር ቴድሮስ ገብረ ማሪያም እና ለዓመታት በድንገተኛ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪነት የሠራችው የ34 ዓመቷ ስፔናዊት ማሪያ ኽርናንዴዝ ናቸው። አስካሁን ድረስ ለሦስቱ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሠራተኞች ግድያ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን ስለግድያው የወጣ ምንም አይነት ተጨመሪ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግድያውን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው አቢ አዲ ተብሎ በሚጠራ \"ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አካባቢ\" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም እንዲህ አይነቱን \"ኃላፊነት በማይሰማው ቡድን የሚፈጸምን ጥቃት ለማስቀረት የእርዳታ ድርጅቶች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወታደራዊ እጀባ እንዲደረግላቸው መንግሥት ያቀረበው ጥሪ ትክክል መሆኑን ያመለክታል\" ብሏል። ከመንግሥት ሠራዊት ጋር ለስምንት ወራት በጦርነት ውስጥ የቆየው የህወሓት ኃይልም በበኩሉ በእርዳታ ሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ ድርጊቱ በመንግሥት ወታደሮች የተፈጸመ ነው ሲል ገልጾ ነበር። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በመደገፍና በማቋቋም እንዲሁም የህክምና ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች እርዳታን እያደረገ ያለ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በባልደረቦቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም አገልግሎቱን አሁን ለማቋረጥ በወሰነባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የተለያየ አይነት የጤና አገልግሎቶች ሲያርብ መቆየቱን ገልጿል። የአገልግሎቱ መቋረጥም በርካታ ሰዎች ከረድኤት ድርጅቱ ሲያገኙት የነበረውን የሰብአዊና የጤና ድጋፎችን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል ተብሏል።", "ኮሮናቫይረስ ፡ ሲሼልስ የኮቪድ -19 ክትባት መስጠት ጀመረች በርካቶች ለመዝናናት የሚመርጧት አፍሪካዊቷ ደሴታማ አገር፣ ሲሼልስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጠት መጀመሯን አስታወቀች። ይህንን በማድረግም ከጊኒ ቀጥላ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት አገር ሆናለች። ጊኒ የሩሲያውን ስፑትኒክ ቪ ክትባት አነስተኛ ዶዝ ያገኘችው ባለፈው ወር ነበር። የሲሼልስ ፕሬዚደንት ዋቨል ራምካላዋን ዕሁድ እለት የመጀመሪያውን ክትባት በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት እየታዩ ተከትበዋል። ፕሬዚደንቱ \"የተሰማኝ ልክ እንደማንኛውም ክትባት ነው\" በማለት ሌሎች ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ አበረታተዋል። ደሴታማዋ አገር ሲሼልስ ቻይና ያበለፀገችውን ክትባት ከተባበሩት አርብ ኤምሬትስ 50 ሺህ ዶዝ [መጠን] በእርዳታ አግኝታለች። ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ዛሬ የጤና ባለሙያዎች መከተብ እንደሚጀምሩ እና ከዚያ በኋላ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ክትባቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ይህ ሲጠናቀቅም ክትባቱ ለሌሎች ሕዝቦቿ ይዳረሳል ተብሏል። አገሪቷ ከሁለት ወር እስከ ሦስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካሏት 98 ሺህ ሕዝብ 70 በመቶውን ለመከተብ አቅዳለች። ይህንን ለማሳካትም በአንድ ቀን 1 ሺህ ሰዎችን መከተብ ይጠይቃል። ሲሼልስ እስካሁን 508 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ያስተናገደችው አንድ ሞት ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት በቅርቡ የታየው የቫይረሱ ሥርጭት አስግቷቸዋል። ቅዳሜ ዕለት ብቻ በአገሪቷ 57 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።", "በአፍሪካ ኮቪድ-19ን እንዴት መቆጣጠር ተቻለ? አፍሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ እየቀነሰ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የቫይረሱ ስርጭት የቀነሰባቸው ምክንያቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ባለሙያዎቹ በምክንያትነት ከጠቀሷቸው መካከል የአህጉሪቷ ነዋሪዎች ወጣት መሆናቸው፣ ሞቃታማ የአየር ንብረት፣ ከዚህ ቀደም የዳበረ በሽታ የመከላከል አቅም መኖሩ እና በከተማ ቀመስ አካባቢዎች ጥቂት ሕዝብ መኖሩ ይጠቅሳሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ እስከ 190,000 ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ብሎ መላ ምት ቢያስቀምጥም በርካታ የአፍሪካ አገሮች የወረርሽኙን ስርጭት መቆጣጠር ችለዋል። አህጉሪቱ እንዴት በሽታውን መቆጣጠር እንደተቻለ በተደረገው የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች ውይይት ላይ እንደተገለጸው ወረርሽኙ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ካሳየው የተለየ ባህሪ በአፍሪካ ታይቷል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍረካ ኃላፊ ዶ/ር ማቲሺዲሶ ሞይቲን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት እንደተጠቀሰው ከሆነ፤ የወረርሽኙ ስርጭት ሲጀመር እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣሉ ውጤት አሳይቷል። ከሌሎች አህጉሮች አንጻር አፍሪካ ውስጥ ገደብ የተጣለው ቀድሞ ነበር። ይህም በርካታ አገሮች ላይ የምጣኔ ሀብት ጫና ማሳደሩ አልቀረም። በአፍሪካ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት ወጣቶች ናቸው። ኮሮናቫይረስ በግንባር ቀደምነት የሚያጠቃው ደግሞ አረጋውያንን ነው። የአውሮፓ አገራትን በማነጻጸሪያነት ብንወስድ፤ ሰዎች እድሜያቸው ሲገፋ አረጋውያን ማቆያ ውስጥ ይገባሉ። በአፍሪካ ግን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖራሉ። ይህ አኗኗር የበሽታውን ስርጭት ከቀነሱ ምክንያቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። ሌላው ምክንያት በርካታ ሰዎች በከተማ ስለሚኖሩ በሽታው ወደ ገጠር እንዳይሰራጭ መገታቱ ነው። የመሠረተ ልማት ዝርጋታው ውስን በመሆኑም ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳልተዘዋወሩ ተጠቅሷል። ዶ/ር ማቲሺዲሶ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም እንደ ኢቦላ ያሉ ወረርሽኞችን ለማስወገድ የተደረገው እንቅስቃሴ ኮቪድ-19ን በመከላከል ረገድ ጠቃሚ ሆኗል። ሆኖም ግን ወረርሽኙ በአህጉሪቱ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ለመፈተሽ ጥናት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በአፍሪካ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 34,000 ሞተዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።", "ኮሮናቫይረስ ፡ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ100 በላይ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተነገረ በሲዳማ ክልል በሚገኘው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ ለቢቢሲ ገለፁ። ክልሉ ባለፉት 12 ቀናት በኢንዱስትሪ መንደሩ ባደረገው ምርመራ የኢንዱስትሪ መንደሩ ሠራተኞች በኮሮናቫይረስ መያዛችን ያረጋገጠ ሲሆን፤ ቫይረሱ በተለይ በሁለት ማዕከላት (ሼዶች) ውስጥ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ዶ/ር ማቴ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በኢንደስትሪ ፓርኩ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ያረጋገጡት አንድ ሠራተኛ ከ12 ቀን በፊት ታሞ በፓርኩ በሚገኝ ክሊኒክ ለሕክምና በመሄዱና ምልክቶቹ የኮሮናቫይረስ መሆናቸው በመረጋገጡ ጥቆማ ደርሷቸው መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ግለሰብ እንዲሁም ከባሕር ማዶ የመጡ የድርጅቱ ሠራተኛ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ሲመረመሩ ከ100 በላይ ሰዎች ተይዘው መገኘታቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። እንደ ዶ/ር ማቴ ከሆነ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ንክኪ አላቸው ተብሎ ከሚታመኑ ሰዎች በአጠቃላይ ናሙና እየተወሰደ ነው። ከፍተኛ ንክኪ አለው ተብሎ የተገመተው አንድ ሼድ ሲሆን ስምንት መቶ ያህል ሠራተኞች እንዳሉት ገልፀው፤ ሁሉንም ሠራተኞች ለመመርመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። \"በአባታችን ቀብር ላይ ሆነን የእናታችንን ሞት ሰማን\" በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ ቻይና ዜጎቿን ለኮሮናቫይረስ የባሕል መድኃኒት እንዲወስዱ ለምን ታበረታታለች? ዶ/ር ማቴ አክለውም ከሁለተኛው ሼድ ግን ሙሉ በሙሉ አለመወሰዱን ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት ሠራተኞች መካከል የውጭ አገር ዜጎች፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ላይ የሚሰሩ ሠራተኞችና፣ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ኦፕሬተሮች መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል። እነዚህ በቫይረሱ ተይዘው የሚገኙት ሰዎች የኢንዱስትሪ ማዕከሉ ውስጥ ባሉ በሁለት ሼዶች ውስጥ ሚሰሩ እንደሆኑ ተናግረዋል። \"በኢንደስትሪ ፓርኩ ያለውን ስርጭት ተቆጣጥረናል ማለት ይቸግረና\" ያሉት ዶ/ር ማቴ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውንና ንክኪ ያላቸውን ለመለየት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉ ኮሮናቫይረስ መከላከል ባለሙያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለውን ንክኪ ለመለየት፣ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ትምህርት መስጠት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ በተሻለ ግን የቫይረሱን ስርጭት ባለበት ለማቆም ከኢንደስትሪ ፓርኩ ጋር በመነጋገር ቫይረረሱ በስፋት የታየበት ሼድ ለተወሰነ ገዜ ሥራ እንዲያቆምና ሠራተኞች ራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ ለማድረግ ቢታሰብም ውጤታማ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ዶ/ር ማቴ አክለውም እስከ ዛሬ ድረስ በሲዳማ ክልል 13 የሕክምና ባለሙያዎች እና ሁለት ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል ወደተለያየ ስፍራ ሄደው ራሳቸውን ለቫይረሱ ያጋለጡ፣ በሚሰሩባቸው ተቋማት አካባቢ ባለ የጥንቃቄ ጉድለት እንዲሁም የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ የተነሳ የተጋለጡ እንደሚገኙበት አብራርተዋል። የሲዳማ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሩ በክልሉ እስካሁን ድረስ 452 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፀው፤ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘም አምስት ሰዎች መሞታቸውን ገልፀዋል። የሐዋሳ የሚገኘው ኢንዱስትሪያል ፓርክ በአገሪቱ ካሉ መሰል ተቋማት መካከል ከትልልቆቹ ጋር የሚመደብ ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርቱ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት ይገኙበታል። ፓርኩ በአሁኑ ጊዜ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያሉበት ሲሆን ከጥቂት ዓማት በፊት ተከፍቶ ሥራውን በጀመረበት ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በውስጥ ያሉት ሁሉም ፋብሪካዎች ሥራ ሲጀምሩ ከ60 ሺህ በላይ ሠራተኞችን ይቀጥራል ተብሎ እምነት ተጥሎበት ነበር።" ]
[ 0, 0, 0, 0, 0, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2 ]
[ "ኮሮናቫይረስ፡ የውጭ አገር ተጓዦች የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ ፈተና ሆኖባቸዋል አገራት ድንበሮቻቸውን በጥንቃቄ እየከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የአየር በረራ መጀመርን ተከትሎ በወጡ አዳዲስ ደንቦች ምክንያት ተጓዦች ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ መሆናቸውን በምርመራ እንዲያረጋግጡ ይገደዳሉ። በኢትዮጵያ ይህንን ምርመራ በማድረግ ውጤት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የሆነውና አብዛኞቹ የውጭ አገር ተጓዦችን የሚያስተናግደው ተቋም የምርመራ ፈላጊዎች ቁጥርና አገልግሎቱ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተገልጋዮች እየተናገሩ ነው። የአየር በረራ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ ለወራት ሲጠባበቁ የነበሩ ተጓዦች ይህንን ምርመራ ለማድረግ ከባድ ፈተና ሆኖብናል ይላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ምርመራውን የሚያከናውነው ተቋም የወሰደውን ናሙና ውጤት ለማሳወቅ ቢያንስ 48 ሰዓታትን ይፈልጋል። አገራት ደግሞ ተጓዦች ከመሳፈራቸው በፊት ምርመራ እንዲያደርጉ የሚፈልጉበት የሰዓት ገደብ ከ48 ሰዓት እስከ 96 ሰዓት እንደየአገሩ ይለያያል። ምርመራውን ከብዙ ጥበቃ በኋላ ባለፈው አርብ ዕለት ማድረግ የቻሉ ተጓዦች ውጤት አልደረሰም በመባላቸው በረራቸውን ለመሰረዝ እንደተገደዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክሊኒኩ ለተመርማሪዎች ውጤት የሚሰጠው የጉዞው ዕለት ወይም ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በ10 ሰዓት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት የጉዞ ቀን፣ የሚጓዙበት አገር የምርመራ ደንብና የክሊኒኩ ውጤት መስጫ ዕለት ለማጣጣም ፈታኝ እንደሆነ ተጓዦቹ ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ሰኞ ማለዳ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ምርመራ በሚሰጠው ተቋም ደጃፍ ላይ ተሰልፈው ያገኛቸው ተጓዦች ተቋሙ ስለምርመራው በቂ መረጃ እንዳልሰጣቸው፣ በረራቸውን በተደጋጋሚ ለመሰረዝ እንደተገደዱና ላልተጠበቀ ወጪና መጉላላት እንደተዳረጉ ገልጸዋል። አገልግሎቱን ፈልገው ወደተቋሙ የሄዱ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ምርመራውን የሚያደርገው ላቦራቶሪ ሥራውን የሚያስኬድበት ግልጽ አሰራር እንዳልዘረጋም ተናግረዋል። አገልግሎት ፈላጊዎች የሚስተናገዱት በቅድሚያ በኢሜይልና በስልክ ከተመዘገቡና የጉዞ ትኬታትና የፓስፖርታቸውን ቅጂ ከሰጡ በኋላ ነው የሚል ማስታወቂያ በክሊኒኩ ደጃፍ ላይ የተለጠፈ ቢሆንም፤ በክሊኒኩ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተጠቀሱት የስልክ መስመሮች ከአገልግሎት ወጪ ናቸው አልያም ተዘግተዋል። የኢሜይል ምላሽም ከክሊኒኩ ማግኘት አልተቻለም። የቢቢሲ ዘጋቢዎችም ይህንኑ ማረጋገጥ ችለዋል። የክሊኒኩ ሠራተኞች በበኩላቸው ሰዎች ከተመዘገቡ በኋላ በራሳቸው ምክንያት ሊቀሩ ስለሚችሉ ይህንን የቅድመ ምዝገባ አሰራር ትተን ሰዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ጀምረናል ይላሉ። ሰኞ ማለዳ በስፍራው ተሰልፈው ከነበሩ ተጓዦች ቢቢሲ እንደተረዳው አንዳንዶቹ ተገልጋዮች እሑድ ከቀትር ጀምሮ ለረዥም ሰዓት አገልግሎቱን ለማግኘት በዝናብ ተሰልፈው የጠበቁ ቢሆንም \"አሁን ደክሞናል ከዚህ በላይ አናስተናግድም\" በሚል እንዲበተኑ ተደርገዋል። ሌሎች ደግሞ ነገ በአዲስ መልክ አንሰለፍም በሚል ቅሬታ በማንሳታቸውና የክሊኒኩን በር አናዘጋም በማለታቸው ስም ዝርዝራቸው ተጽፎ በቀጣይ ቀን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንደሚስተናገዱ ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል። ክሊኒኩ በዚህ መንገድ ተገልጋዮቹን ካሰናበተ በኋላ የተወሰኑ ሰዎችን \"አሾልኮ እንዳስገባና አገልግሎት እንደሰጣቸው\" በቦታው ነበርኩ ያሉ እማኝ ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ የመኪና አስተናባሪዎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች የችግሩን ስፋት በመረዳት በጠዋት ወረፋ በመያዝ ሰልፋቸውን እስከ 200 ብር እየሸጡ እንደሚገኙ ተገልጋዮች ይናገራሉ። የምርመራ አገልግሎት ሰጪው ተቋም በርካታ ለምርመራ የሚመጡ ሰዎች በሚስተናገዱበት በአንደኛው ቅርንጫፉ በሁለት ነርሶችና በሁለት ናሙና ሰብሳቢዎች ብቻ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነና የሚሰጠው ምርመራው አገልግሎቱን ከሚፈልገው ሰው ጋር ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ቢቢሲ ለመታዘብ ችሏል። የቢቢሲ ዘጋቢ ሰኞ ማለዳ በስፍራው እንደተመለከተ የአገልግሎት ደረሰኝ ወረቀት ማተሚያ ማሽን ብልሽት ገጥሟል በሚልም ክሊኒኩ ለግማሽ ሰዓት ያህል ሥራውን አቁሞ ነበር። ክሊኒኩ ምንሊክ ሆስፒታል አካባቢና ቡልጋሪያ ባሉት ቅርንጫፎቹ የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል ቢባልም የሌሎች ቅርንጫፎቹ ተገልጋዮች ከሌሎች ቅርንጫፎች ይልቅ ወደ አንደኛው ክሊኒክ በብዛት ሄደው ምርመራ ለማግኘት እየጣሩ ነው። \"ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ሄደን እድላችንን እንሞክር ስንላቸውም መልስ አይሰጡንም፣ መረጃ እንኳን ማግኘት ብርቅ ነው\" ይላሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ተገልጋይ። ሰኞ በዚህ ቅርንጫፍ ረዣዥም ሰልፎች የነበሩ ሲሆን በምንሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የክሊኒኩ ቅርንጫፍ ግን የተገልጋዩ ቁጥር አነስተኛ ሆኖ ታይቷል። ክሊኒኩ ተመርማሪዎችን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ብር ለአገልግሎቱ ካስከፈለ በኋላ ውጤቱን የሚሰጠው ከ48 ሰዓታት በኋላ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ቅርንጫፉ ብቻ ነው። ጠዋት በረራ ያላቸው ሰዎች ውጤት ስለማይደርስላቸው በብዛት ለድጋሚ የትኬት ማስቀየሪያ ወጪ፣ እንዲሁም ለሌላ አዲስ ምርመራ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን ቢቢሲ ካናገራቸው ሰዎች ለመረዳት ችሏል። ቢቢሲ ምርመራውን ከሚሰጠው የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪስ ምላሽ ለማግኘት በማስታወቂያ ሰሌዳቸው ላይ ባሰፈሩት የስልክ አድራሻ በተደጋጋሚ ቢደውልም ቁጥሩ ስለማይሰራ መልስ ማግኘት አልቻለም።", "ከበርካታ ሕጻናት ሞት በኋላ በ4 የሕንድ ምርት በሆኑ ሽሮፖች ላይ ማስጠንቀቂያ ወጣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕጻናት ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የሕንድ ምርት በሆኑ አራት የሽሮፕ አይነቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ። የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው በአፍሪካዊቷ ጋምቢያ የ66 ሕጸናት ሕልፈት ከሽሮፖቹ ጋር ሳይገናኝ አይቀርም ከተባለ በኋላ ነው። ሽሮፖቹ ለከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት እና ለ66 የሕጻናት ሞት ምክንያት ሳይሆኑ አይቀርም ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የዓለም ጤና ድርጅት ወላጆች ለልጆቻቸው ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ያላቸው ሽሮፖች ፕሮመታዚን ኦራል ሶሉሽን (Promethazine Oral Solution)፣ ኮፌክስማሊን ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Kofexmalin Baby Cough Syrup)፣ ማኮፍ ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Makoff Baby Cough Syrup) እና ማግሪፕ ኤን ኮልድ ሲረፕ (Magrip N Cold Syrup) የሚባሉት ናቸው። እነዚህ የሕጻናት ሽሮፖችን ያመረተው ማይደን ፋርማሱቲካልስ የሚባል የሕንድ ኩባንያ ሲሆን፤ ለሽሮፖቹ የደኅንነት ማስረጃ ማቅረብ አለመቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት ጨምሮ አስታውቋል። አምራቹ ኩባንያ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ቢቢሲም ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። የሕንድ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሽሮፖቹ ለሕጻናቱ ሞት ምክንያት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሰጣቸው የዓለም ጤና ድርጅትን መጠየቃቸው ተገልጿል። ሽሮፖቹን መጠቀም በተለይ በሕጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ወይም ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሽሮፖቹ የጤና ጉዳት እንደሚያስከትሉ ማወቅ የቻለው የጎብኚዎች መዳረሻ በሆነችው በጋምቢያ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት የሚያጋጥማቸው ሕጻናት ቁጥር መጨምሩን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ የአገሪቱ መንግሥት ዜጎች ፓራሲታሞል ሽሮፖችን መጠቀም በማቆም በምትኩ የሚዋጥ ኪኒኒ እንዲጠቀሙ አሳስቧል። የጋምቢያ ጤና ኃላፊዎች ባለፈው ወር ትክክለኛውን ቁጥር ሳይጠቅሱ በርካታ ሕጻናት ሕይወታቸው አልፏል ብለው ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሽሮፖቹ ላይ በተደገረ ምርመራ ዳይታይለን ግላይኮል እና ኢታይለን ግላይኮል የተሰኙ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች ተገኝተዋል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች መርዛማ ሲሆኑ የሆድ ሕመም፣ ትውከት፣ ተቅማጥ፣ ራስ ምታት እና ለሞት የሚዳርግ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ረቡዕ መስከረም 25/2015 ዓ.ም. በጄኔቭ ንግግር ሲያደርጉ፤ “የእነዚህ ጨቅላ ሕጻናት ሕልፈት ለወላጆቻቸው ልብ የሚሰብር ነው” ብለዋል። የሕንድ ማዕከላዊ የመድኃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ ድርጅት ሽሮፖቹ ለጋምቢያ ብቻ መላካቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት መግለጹን ኤአፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ምንም እንኳ እነዚህ አራት የሕጻናት ሽሮፕ አይነቶች የተሰራጩት በጋምቢያ ብቻ ነው ቢባልም መደበኛ ባልሆነ የገበያ ስንሰለት ወደ ተቀሩት ጎረቤት አገራትም ሳይሰራጩ አይቀርም ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት አምራቹ ሽሮፖቹ ውስጥ የተገኙትን መርዛማ ኬሚካሎች በሌሎች ምርቶቹ ላይ በመጠቀም ሕንድ ውስጥ እና ወደተቀረው ዓለም ልኮ ሊይሆን ይችላል ብሏል።", "በኮቪድ-19 ማዕከላት የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች የተገባልን ቃል አልተፈጸመም አሉ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር በሚተዳደሩ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተቋቋሙ የሕክምና መስጫዎች ውስጥ የሰሩ እና የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ የተገባላቸው ቃል እንዳልተፈጸመ በመግለጽ ቅሬታቸውን አቀረቡ። ኮሮናቫይረስ ወረርሽን በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ መንግሥት በሕክምና ባለሙያዎችን ላይ የሚኖረውን ጫና ከግምት በማስገባት ከባለሙያዎቹ ጎን እንደሚቆም አስታውቆ ነበር። በዚህ መሠረትም የሚንስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 14/2012 ዓ. ም ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ የኮቪድ-19 ወረርሽንን በመከላከል እና የህክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ የጤና ባለሙያዎች ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ውሳኔ ማሳለፉን ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ምክር ቤቱ እንደሙያቸው እና ሥራቸው ሁኔታ ከ1ሺህ150 ብር ጀምሮ እስከ 300 ብር በየቀኑ እንዲከፈላቸው ነው የወሰነው። በዚህ መሠረትም በፌደራል ደረጃ የሚተዳደሩት እንደ ኤካ ኮተቤ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ሚሊኒየም ሆስፒታል ያሉት የጤና ተቋማት እና አንዳንድ ክልሎች ወሳኔውን መሠረት በማድረግ ለባለሙያዎቻቸው ልዩ አበል እንደከፈሉ ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል። ሆኖም በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር ከሚተዳደሩ ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች መከካከል የተወሰኑት የኮሮናቫይረስ ህክምና መስጫ ማዕከል ሆነው እያገለገሉ ቢሆንም ለባለሙያዎች እስካሁን ምንም ዓይነት ከፍያ እንዳልተፈጸመ የጤና ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። \"ግንቦት አጋማሽ መመሪያው ከወጣ በኋላ የባለሙያ እና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የአበል ዝርዝር በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ደረጃ አልወጣ ሲል ጠብቀን መታገል ጀመርን\" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት በጉለሌ ክፍለ ከተማ የጉቶ ሜዳ ኮቪድ -19 ማዕከል ሠራተኛ የሆኑት አቶ ዲኖ ጀማል ናቸው። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ከእያንዳንዱ የኮቪድ -19 ህክምና ማዕከል 3 ተወካይ በመምረጥ አቤቱታቸውን ለተለያዩ የመንግሥት ተቋማት አስገብተዋል። ወኪሎቻቸውን ያላሳወቁትን ሳይጨምር 1158 ሠራተኞች ወኪሎቻቸውን መርጠው ልዩ አበሉ ለምን እንዳልተከፈላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል። ኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ ተብሎ ሰዉ በሚሸሽበት ወቅት ጭምር ሙያዊ ግዴታ በሚል ወደ ሥራ መግባታቸውን የገለጹት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ባልደረባ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰሩ ጤና ባለሙያዎች ተወካይ የሆኑት አቶ ከድር ሳሊህ ናቸው። . ኮቪድ-19 ያስተጓጎለው የኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና . በኢትዮጵያ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ምን ያመላክታል? \"ሁሉም እኛን ማሞካሸት ጀመረ። በመሃል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኮቪድ -19 ላይ ለሚሰሩ ልዩ አበል ይከፈል አለ። እኛ ሙያዊ እና ሰብዓዊነት ነው ያስገባን። ክፍያ አይተን አይደለም። አንዳንድ ቦታ ይከፈላል ሌላ ቦታ አይከፈልም\" ብለዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ጠቅላላ ሐኪም በበኩላቸው በኮሮናቫይረስ ማዕከል ከአምስት ወር በላይ እንደሠሩ እና አሁን ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል። መጀመሪያ ላይ ህብረተሰቡ በነበረው ፍራቻ እና በተለያየ ምክንያት ብዙዎች ከቤት እና ለተወሰነ ቀን ብቻ ከሥራ ቦታቸው እንዲሠሩ በተደረገበት እና ትርፍ ክፍያ ባልነበረበት ወቅት ጭምር መሥራት መጀመራቸውን ገልጸዋል። ሆኖም ሥራ ጀምረው ከሁለት ወራት በኋላ ተግባራዊ እንዲሆን የወጣው መመሪያ ተባግባራዊ አለመሆኑ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው አስታውቀዋል። \"ማህበረሰቡ ባለሙያው ብዙ ክፍያ እንዳለው ነው የሚያውቀው። የማይከፍሉ ከሆነ ማህበረሰቡ ማወቅ አለበት። ቢከፍሉን ጥሩ ነው። የማይለከፍሉ ከሆነ ግን አንከፍልም ግን እናመሰግናለን የሚል ደብዳቤ ቢሰጠን። ከህክምና ጣቢያው ስወጣ በግሌ የሚያስጠሉ ፈተናዎች ነበሩት። 'የት ነበርሽ?' ምናምን የሚሉት ነገሮች ትንሽ ቅስም ይሰብራል\" ብለዋል ሐኪሟ። እንደ አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ልዩ አበሉ ባይከፈልም በፌደራል ስር በሚገኙ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከላት እና በአንዳንድ ክልሎች ተግባራዊ መደረጉን ግን እነዚህ ባለሙያዎች ገልጸዋል። \"አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሄደው ያነጋገሩ ባልደረቦች አሉ። እነሱ ግን በቃ እንደማይገባን ነገሩን ያሉት። በጀት የለንም አሉ። በጀት ከሌለ መጀመሪያም ውሳኔው (የሚንስተሮች ምክር ቤት) አይፈቅድም\" ብለዋል። ውሳኔውን መሠረት በማድረግ ጤና ቢሮው ክፍያውን እንዲፈጽምላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተገቢውን ምላሽ አላገኙም። ክፍያው ሁለት ቢሊዮን ብር ገደማ ስለሚሆን እንደሚክብዳቸው፤ ከኮቪድ-19 ማዕከላት ውጭ ያሉት ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጭምር በመግለጽ እነሱን ስለማያካትት ለአፈጻጸም አመቺ አይደለም ተብሎ ከጤና ቢሮው እንደተመለሰላቸው አቶ ዲኖ አስታውቀዋል። የጤና ጥበቃ ሚንስትር ደግሞ ጉዳዩ እንደማይመለከተው እንዳስታወቃቸው እና ለከተማው ካቢኔ ደብዳቤ አስገብተው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሚንስትሮች ምክር ቤት በመመሪያው ያወጣው በኮሮናቫይረስ የተያዙን የሚያክሙ፣ በለይቶ ማቆያ ህክምና በመስጠት ላይ የሚገኙ፣ ቀጥታ ተጋላጭ ሆኑ ባለሙያዎች በሚል በዝርዝር ለይቶ ማስቀመጡን ገልጸዋል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ግን አሠራሩን በመቀየር ቢሮ የሚሠሩትን ተጠቃሚ በማድረግ ሌላ ውሳኔ ተግባራዊ መደረጉን ኮንነዋል። 'የወጣው ውሳኔ ሁሉንም ባያካትትም ሁሉም የህክምና ባለሙያ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ነው' በሚል ቢሮ ውስጥ ያሉትንም ለመጥቀም የሚመስል ሁሉንም የሚያካትት አሠራር ለመፍጠር መሞከሩን አቶ ከድር አስታውቀዋል። ስለ ጉዳዩ ለሲቪል ሰርቪስ ያቀረቡት ቅሬታ ደግሞ 'ካልተስማማችሁ መልቀቅ ትችላላችሁ ብዙ ሥራ የሚፈልግ ባለሙያ አለ' በሚል ምላሽ አንደተሰጣቸውም ገልጿል። የጤና ባለሙያዎቹ ሌላ ቅሬታ ደግሞ የቤት ጉዳይ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ተገንብተው የተጠናቀቁና በግንባታ ላይ ያሉ በርካታ ቤቶች መኖራቸውን ጠቅሶ፤ በራሳቸውም ሆነ በባለቤቶቻቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚገልጽ ማስረጃ እንዲያቀርቡ መጠየቁን አስታውሰዋል። መረጃውን ለሟሟላትም ውጣ ውረድ በማሳለፍ በተሰጣቸው ጥቂት ቀናት መረጃውን ማስገባታቸውን ገልጸዋል። ዕጣ እንደሚወጣላቸው በተነገራቸው ሰሞን የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው ችግር ምክንያት መደናቀፉን አስታውቀዋል። ምላሽ እንገኛለን በሚል ቢጠብቁም የቀድሞው ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከቦታቸው ተነስተው ወደ ሌላ ቦታ ተቀይረዋል። . የያዘዎት ጉንፋን ወይስ ኮሮናቫይረስ መሆኑን እንዴት መለየት ይችላሉ? . በለይቶ ማቆያ ያሉ የጤና ባለሙያዎች መሠረታዊ ፍላጎታችን እየተሟላ አይደለም አሉ . በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኋላ የተሰጣቸው ምላሽ 'ዳታ' ለመስብሰብ ነው የሚል ነበር። ቤት እናገኛለን በሚል መረጃ ለማቅረብ ተሯሩጠው 'ለዳታ ነው' መባላቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ጠቅሰዋል። መጀመሪያ ተስፋ ስለተሰጣቸው እንጂ ያሰቡት ባይሆንም ቃል ከተገባ ደግሞ ሊፈጸም ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። ሰኔ 2012 ዓ. ም የጤና ባለሙያው በሦስት ቀን ውስጥ በራሳቸው እና በትዳር አጋራቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚገልጽ ማስረጃ አምጡ መባላቸውን አቶ ዲኖ ገልጸው \"አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ለህክምና ባለሙያዎች ቤት ሊሰጥ ነው ሁሉ ብለዋል\" ሲሉ ተናግረዋል። \"አንዳንድ ታካሚዎች ቤት ተሰጣችሁ ደስ ብሎናል እስከሚሉ ድረስ። እኛ ላይ የማታለል ሠራ ነው የሰረቡን\" ብለዋል። በራሳቸውም ሆነ በትዳር አጋሮቻቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚያሳይ ማስረጃ አስገብተው ዕጣው ሊወጣ አካባቢ በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ምክንያት ዘገየ ሲሉ ያስታወሱት አቶ ከድር ናቸው። ከህክምና ቦታቸው ወጥተው ሰዎች ከኮቪድ-19 ማዕከላት በመምጣታቸው ብቻ እያገለሏቸው እና በአጭር ቀናት ውስጥ ያስገቡትን ማስረጃ \"ለዳታ ነው። ምን ያህል ቤት እንደሌላችሁ ለማወቅ ነው እንጂ ቤት ይሰጣችኋል አልተባለም\" መባሉ እንዳሳዘናቸውም አስታውቀዋል። የህክምና ዶክተሯ በበኩላቸው \"ቤት እንሰጣለን ብለው ወከባ ፈጠሩ። እንደ ግለሰብ ሳይሆን እንደ ጤና ባለሙያ ግን ከቤት ውጣ የተባለ ሃኪም አለ። በኮቪድ-19 ጊዜ ቤት ልንሰጥ ነው ብለው የኑሮ ውድነት እንዲመጣ፤ ጤና ባለሙያዎች የሚከራየውን ቤት በእጥፍ እንዲጨመረበት ነው ያደረጉት። ይከፈላቸዋል በሚል ብቻ የኑሮ ውድነት እንዲጨምርበት ተደርጓል\" ብለዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት ጠቅላላ ሐኪም የገቢ ግብር እስካሁን እንዳልተነሳ እና በየትኛውም ህክምና ተቋም የሚከፈለው 'ዲዩቲ' (የሥራ) አበል አንኳን በአግባቡ እንዳልተከፈላቸው አስታውቀዋል። \"ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ናቸው ከተባለም ይህ መሸፈን ያለበት በጤና መድህን ነው። ቤተሰቦቻችን እየተከፈላችሁ ነው። ቤተሰብ እና ጓደኞቻችን የት አደረጋችሁት እያሉ ነው። እነሱ ባወጡት ህግ ነው የጠየቀውነው። ለምን ይሸራርፉታል በሚል። ህዝቡ በአዋጁ እየተጠቀማችሁ ነው እያለ ነው። ቤተሰብም ጓደኛም ግብርም ቀርቶላችኋል ይላል\" ብለዋል አቶ ከድር። ይህም ሆኖ ግን እስካሁን የገቢ ግብር ቅነሳውም ቢሆን ተግባራዊ አለመደረጉን ጠቁመዋል። ቢቢሲ በመጨረሻም ለባለሙያዎቹ ምላሽ ካላገኛችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል? በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ የሚከተለውን መልሰዋል። \"ሥራ ለማቆም አላሰብንም። ባለሙያው ሥራ እንዳያቆም ነው ተወካይ የተላከው። ተወካዮች ኮሚቴ መረጡ። እነሱ ናቸው የሚንቀሳቀሱት። ኮሚቴዎቹ ሥራም እየሠሩ ነው። በሚዲያ እያሳወቅን ነው ህዝቡ እንዲያውቅልን። በኮሚቴም በአባላትም ደረጃ ወደፊት ወደ ፍርድ ቤት ልናመራ እንችላለን የሚል ሃሳብ ነው ያለው\" ያሉት አቶ ዲኖ ናቸው። \"አገራዊ እና ሙያዊ ግዴታ ነው። እኔ ሥራ ባቆም የሚሞቱ ሰዎች አሉ። ይሄ ባለሙያው ምሎ የወጣበት ስለሆነ ሥራ ማቆም አይችልም። አመጽም አይኖርም። እየተረገጥክ ጥቅመህን አሳልፈን እንድትኖር ነው የሚያደርጉት\" ያሉት ደግሞ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሐኪም ናቸው። ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ናቸው። እንደ ዶ/ር ሙሉጌታ ከሆነ ልዩ አበሉን ለማስፈጸም መመሪያ ከወጣ በኋላ አፈጻጸም ላይ ችግር ገጥሟቸዋል። በመጀመሪያው የልዩ አበሉ የተፈቀደው የኮቪድ -19 ማዕከላት ውስጥ ለሚሠሩ እና በመከላከል ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች በሚል ነው። እንደ ምክትል ኃላፊው ከሆነ ግን በዚህ ውስጥ ሁሉም የጤና ሠራተኞች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተሳተፉ ነበር አሁንም በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት ለማስፈጸም አስቸግሮናል ይላሉ። በተጨማሪም ደግሞ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በራሳቸው አውድ እንዲጠቀሙበት መመሪያው እንደሚፈቅድ ገልጸው የተለያዩ አማራጮችን በመውሰድ ለመተግበር ሙከራ መደረጉን አስታውቀዋል። ሆኖም ሙከራዎቹ ጥቂት ሠራተኞችን ብቻ የሚጠቅሙ ሆነው ተገኝተዋል ይላሉ። \"መሬት ላይ ስናወርደው ጽዳቱም፣ ሹፌሩም ድንገተኛ ክፍል የሚሠራው ይገባዋል። ተመላላሽ ህክምና፣ ቀዶ ጥገና ክፍል፣ ማዋለጃ የሚሠሩና ሁሉም ላይ ያሉ ሠራተኞቻችን ከኮቪድ -19 ጋር ተጋፍጠው እየተከላከሉ እየሠሩ ነው። እንተግብረው ካልን ደግሞ ለሁሉም ነው መተግበር ያለብን\" ሲሉ ያስረዳሉ። ሌላው ደግሞ ለትግበራ ያስቸገረው የበጀት ጥያቄ ነው። \"የከተማ አስተዳድሩ ላይ ትልቅ ወጪ አለ። ከተማ አስተዳደሩ ያንን መሸከም የሚችል አይደለም\" ብለዋል። ከዚህ በተሻለ አማራጭ ተደርጎ የተወሰደው ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ከገባበት ወቅት አንስቶ በከተማ መስተዳድሩ በጤና ዘርፍ ለሚሠሩ ባለሙያዎች በሙሉ የግብር ቅነሳ ማድረግ ነው። \"ሁሉም የጤና ዘርፍ ሰራተኞች ራሳቸውም አደጋ ላይ ጥለው ነው እየሠሩ ያሉት። ኮቪድ-19 ላይ ቅዳሜ እና እሁድ ገብተው የሚሠሩ አሉ። ገብተው የሚያድሩ አሉ። ይሄንን የትርፍ ሰዓት ክፍያቸውን እንሰጣለን\" ሲሉ ተናግረዋል ። አክለውም \"ከተማ መስተዳድሩ ታክስ ቅነሳ ወይም ራሱ መስተዳድሩ ታክሱን ይከፍላል ማለት ነው። ስለዚህ ኮቪድ-19 ከጀመረበት ከመጋቢት ጀምሮ ኮቪድ-19 ከስጋትነት እስከሚወጣበት ድረስ ሁሉም የጤና ሠራተኞቻችን ያንን ከግብር ተቀንሶላቸው መስተዳድሩ ራሱ እየሸፈነ በዚያ መንገድ እናስተናግድ ተብሎ ተወሰነ\" ብለዋል። መመሪያው ሲወጣ መጀመሪያ ድንገተኛ የአደጋ መቆጣጠር ዘርፍ ላይ የሚሠሩ የተወሰኑ ሠራተኞችን ብቻ ታሳቢ አድርጎ እንደነበር ዶ/ር ሙሉጌታ አስታውቀው፤ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ ሲሄድ ብዙ ባለሙያዎችን ከማሳተፉም በላይ መመሪያዎችም መቀያየራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኮሮናቫይረስ ላይ የሚሠሩ ሠራተኞች ቁጥር መጨመርም ሌላው ምክንያት ነው። ቸግሩን ለመቅረፍ ከሠራተኞች ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸውን አንስተው \"ብዙ የጤናው ዘርፍ ሠራተኛ በውሳኔው ላይ ጥሩ እይታ እንዳለው ነው ያየነው\" ብለዋል። ሆኖም ቅሬታዎች መኖራቸውን ጠቁመው ጤና ቢሮው የወሰደውን እርምጃ ሌሎችም (ክልሎች እና ጤና ጥበቃ) የመከተል ነገር እንዳለ መመልከታቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ በተቃራኒ ሁላችንም ለአደጋ ተጋልጠን በምንሠራበት ለጥቂቶች ብቻ መከፈል የለበትም የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸውን በተመለከተ፤ \"እኛም አደጋ ላይ ወድቀን እየሠራን ለጥቂቶች ብቻ እየተከፈለ ታሳቢ አለመደረጉ ተገቢ አይደለም ብለው ደግሞ በተቃራኒው የሚጠይቁ አሉ። የግድ ኮቪድ-19 ማከሚያ ቦታ ብቻ ነው ወይ እኛም እየተጋፈጥን ነው የሚሉ አሉ\" ሲሉ አስረድተዋል። ገቢ ግብርን በተመለከተ ደግሞ በከተማ መስተዳድሩ ሥር በሚገኙ ሁሉም ጤና ተቋማት መረጃ የማሰባሰብ ሥራ መከናወኑን አስታውቀው በጥቂት ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል። ህክምና ባለሙያዎቹ ቤት ይሰጣችኋል ተብለን በተገባልን ቃል መሠረት አልተፈጸመልንም ለሚለው ቅሬታቸውም ምላሻውን እንደሚከተለው ሰጥተዋል። \"ቤት ይሰጣል የሚል እንደ መስተዳደርም እንደ ቢሮም የለም። መረጃ ሊሰበሰብ ቤት ያለውን እና የሌለው የጤና ባለሙያ መረጃ እንዲያዝ ከተማ መስተዳደሩ መጠየቁን ነው እኔ የማውቀው። መረጃውን ጠይቁ አለ መረጃውን ሰብስበን ልከናል። ቤት ይሰጣቸዋል የሚል ነገር ግን የለም\" ብለዋል።", "\"በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ የጤና ባለሙያዎች አሉ\" አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛ የሕክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በቀን ከ4 እስከ 6 አስክሬኖች የሚሸኝበት ደረጃ እንደደረሰ ለቢቢሲ ገለጸ። በመድኃኒትና ሕክምና አገልግሎት እጥረት ከሞቱት መካከል የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የሆስፒታሉ የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊ ቴዎድሮስ ካህሳይ ከጦርነቱ በፊት ከትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ሆስፒታል አሁን ግን እጅግ መዳከሙን ገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው የሰሜኑ ጦርነት ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል እና ከዓለም ተቆራርጣ ባለችው ትግራይ ክልል በሕክምና ቁሳቁሶች፣ መድሃኒቶችን እና የሰብዓዊ እርዳታዎች እጥረት በርካቶች ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ሲዘገብ ቆይቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ የጤና ማዕከላት በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ ማቆማቸውን ያስታወቀ ሲሆን በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንያት እየሞቱ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማድረስ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታውቆ፤ የትግራይ ኃይሎች ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች አፋር ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ ጠይቆ ነበር። ይህንን ተከትሎም የትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም እንዳደረጉና ከአፋር ክልል ኤረብቲ መውጣታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ህወሓት ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ለመውጣት ዘላቂ፣ ያልተገደበ፣ ወቅታዊ እና በቂ የሆነ እርዳታ ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት ተከትሎም ከሁለት ሳምንት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም 47 ምግብና ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ማድረሱን ገልጿል። አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችና የምግብ እርዳታ የጫኑ መኪኖቹ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ መጋቢት 24፣ 2014 ወደ ትግራይ መግባታቸውን አስታውቋል። አሜሪካም በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ችግር የሚውል 313 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጓን ከትናንት በስቲያ አስታውቃለች። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊው ቴዎድሮስ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ ለሆስፒታሉ ሲሰጥ የነበረው ድጎማ እና የሕክምና ቁሳቁስ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው ላለፈው አንድ ዓመት ግን ሆስፒታሉ ካለምንም በጀት እየሠራ እንደሆነ ተናግሯል። \" በአሁኑ ሰዓት 30 በመቶ በሚሆን አቅም ነው አገልግሎት እየሰጠን ያለነው፤የመድሃኒት ክምችታችን ወደ 10 በመቶ ወርዶ ነበር። ከዓለም ጤና ድርጅት የመጣ እርዳታ ተጨምሮበት ክምችቱ ወደ 20 በመቶ ደርሶ ነበር። ነገር ግን ይህ ለሆስፒታሉ የተሰጠው መድሃኒት ያለቀው በሁለት ሳምንት ውስጥ ነው\" ይላል። ኃላፊው እንደሚሉት ድጋፍ የተደረጉላቸው መድሃኒቶች በዓይነትም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ጠቁመዋል። ኃላፊው እንደ ካንሰር፣ ደም ግፊት ላሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች ምንም ዓይነት መድሃኒት አለመግባቱን በመግለፅም ለሳንታት ታይቶ የነበረው የሆስፒታሉ አገልግሎት መሻሻል ተመልሶ መውረዱን አክለዋል። ለላብራቶሪ የሚውሉ ግብዓቶች ፣ መድሃኒቶች፣ ማሽኖችን ማንቀሳቀሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ ተኝተው ለሚታከሙ የሚቀርብ ምግብ ፣ ለሠራተኞች የሚከፈል በሌለበት መስራትም አስቸጋሪ አንደሆነ ቴዎድሮስ ገልጿል። \"በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን አሉ\" በሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ነርስ የሆነው ገብረይ አቢዩ \" ሰዎች ለሕክምና መጥተው እያየናቸው ሕይወታቸውን ሲያጡ እጅግ እናዝናለን\" ይላል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆነው እየሠሩ እንደሆነ የሚናገረው አቶ ገብረይ \"በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን ግን አሉ\" ይላል። \"ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ሰዎች ሙያዊ ድጋፍ ፈልገው ሲመጡ ምንም ሳይደረግላቸው ሲቀር ሥራ ቦታ ብቻ ሳይሆን ቤት ሄደህም ሰላም አታገኝም። ለሊት ተኝተህ ወደ ህሊናህ የሚመጣ ብዙ ነገር አለ። ሕጻናት መጥተው በኦአርኤስ ወይም በሌላ ትንሽ ነገር ሕይወታቸውን ማትረፍ እየተቻለ ይህ ባለመኖሩ ስታጣቸው በጣም ከባድ ነው። እጆችህን አጣጥፈህ ነው ቆመህ የምታየው። ልብህን የሚያደማ እንጂ ደስ ብሎህ የምትሠራው ሥራ አይደለም።\" ሲሉ በሆስፒታሉ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፤ ድርብርብ ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩም ለ11 ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው ሠራተኞች እስከ 2 ሰዓት የሚወስድ መንገድ በእግር ተጉዘው ሆስፒታሉ እንደሚደርሱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። \"የጤና ባለሙያዎችም በሕክምና አገልግሎት እጦት ሕይወታቸው አልፏል\" ቴዎድሮስ እንደሚለው የመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎት እጥረት የታካሚዎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የጤና ባለሙያዎችንም ሕይወት እየቀጠፈ ነው። \"በዚህ ሁለት ወር 2 ነርሶች ሞተውብናል። መዳን ይችሉ ነበር፤ ግን መድኃኒት ማግኘት አልቻሉም። በተለይ አንደኛዋ ነርስ ኤምአርአይ ማሽኑ እየሠራ ስላልሆነ በሽታዋን በግልጽ ማወቅ አልተቻለም። በዚህ ምክንያት ሕመሟ ጸንቶ ሞታለች። ሁለተኛው ነርስ ደግሞ ሊወስደው የሚገባ መድኃኒት እዚህ ሆስፒታል ስለሌለ ያጣነው ባልደረባችን ነው። አሁን በቀን እስከ 4 አልፎም እስከ 6 አስክሬን ከዚህ ሆስፒታል ይሸኛል። ከዚህ በፊት ግን በሁለት ወይም ሦስት ቀን አንድ ሬሳ ነበር የሚወጣው\" ይላል። በሕክምና እጦት ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ የጤና ባለሙያዎች መካከል አብዛኞቹ የክሮኒክ በሽታዎች ተጠቂ መሆናቸውንም ኃላፊው ገልጿል። ትግራይ ባለው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሆስፒታሉ ለሚሰጠው አግልግሎት ከታካሚዎች የሚጠይቀው ገንዘብም እጅግ ዝቅተኛ ክፍያ [ከቀድሞው ከ90 በመቶ ያነሰ) ነው። \"በሆስፒታሉ የማይገኙ መድኃኒቶችን ከውጭ ለመግዛት የተቸገሩ ሰዎች፣ ከሩቅ የትግራይ አካባቢ መጥተው መመለሻ ያጡ ሰዎች፣ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ለመውሰድ የሚቸገሩ ሰዎችን ማየት የሠራተኞቹን ልብ በሐዘን ይሰብራል\" ብሏል። ለታካሚዎችና ለተወሰኑ ሠራተኞች ይቀርብ የነበረ ምግብ ላለፉት 10 ቀናት ውስጥ ስለተቋረጠ እስከ 240 ታካሚዎች ወደ ቤታቸው እንደተሸኙም አክሏል። ከዚህ ቀደምም የአይደር ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ (intravenous fluids) እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች ተቋርጠው ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። አስራ ስምንት ወራት ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ያወጁ ሲሆን ይህም ለሰላም በር ሊከፈትና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማብቃት ወደሚያስችል ውይይት መሄድ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።", "መንግሥት በትግራይ ክልል ረሃብ አለ መባሉን አጣጣለ በትግራይ ክልል ረሃብ እንደሌለ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ተናገሩ። ረቡዕ ዕለት በትግራይ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ከጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ለጋዜጠኞች በተሰጠ ማብራሪያ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር የሰብዓዊ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት በቅርቡ በትግራይ ክልል ያሉ ነዋሪዎች በረሃብ ቋፍ ላይ ናቸው የሚል መግለጫ ያወጣ ሲሆን የከፋው የ1977ቱ ረሃብ ሊደገም እንደሚችል አስጠንቅቋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በትግራይ ክልል በረሃብ ሰዎች እየሞቱ ነው የሚለውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሪፖርትን በመጥቀስ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ምትኩ ምላሽ ሰጥተዋል። በአንዳንድ ሪፖርቶች በኮረም ኦፍላ ወረዳ በረሃብ ሞተዋል ተብሎ የወጣ ሪፖርት እንዳለ ጠቁመው \"ሐሰት ነው\" ብለዋል ኮሚሽነሩ። \"አካባቢው ሰላማዊ ነው\" ያሉት አቶ ምትኩ በትግራይ ክልል በሚሰሩ አንዳንድ ድርጅቶች ሆን ብሎ የተደረገ ነው በማለትም ወንጅለዋል። በተጨማሪም \"መንግሥት በክልሉ ውስጥ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ነው\" የሚሉ በሚዲያም ሆነ በተለያዩ አካላት የወጡ ሪፖርቶችን ያጣጣሉት አቶ ምትኩ በአብዛኛው የትግራይ ክልል እርዳታ በመስጠት የሚንቀሳቀሱት አጋር ድርጅቶች ናቸው ብለዋል። በእነዚህ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የአርዳታ ድርጅቶች አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ አቅሙም እንዳላቸው ጠቁመዋል። የፌደራሉ መንግሥት በአብዛኛው በምዕራብ ትግራይ ሁመራ፣ ማይካድራና ሌሎች አካባቢዎችን ጨምሮ በ40 ወረዳዎች ውስጥ በዋነኝነት የእርዳታ አቅርቦቱ ስርጭት እንደሚያከናውን አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ረሃብ (ፋሚን) ብሎ ለማወጅ ሦስት ዓለም አቀፍ መስፈርቶች በአንድነት መሟላት እንዳለባቸው አቶ ምትኩ ጠቁመዋል ይህ ሁኔታ በትግራይ እንዳልተከሰተ ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ መስፈርቶች ብለው የጠቀሷቸው በአንድ አካባቢ 20 በመቶ ቤተሰቦች የምግብ እጥረት ሲገጥማቸውና ለመኖር አሰቸጋሪ ሲሆን፣ ከ30 በመቶ በላይ ህፃናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት ሲሰቃዩ እና ረሃብ ከአስር ሺህ ነዋሪዎች መካከል በየቀኑ ከሁለት ሰው በላይ ሲገድል የሚል ነው። አሁን ባለው ሁኔታ 20 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የምግብ እጥረት እንዳጋጠመው ነው ሪፖርቶች የሚያሳዩት ቢሉም \"በክልሉ ምንም አይነት የምግብ እጥረት የለም ምክንያቱም 91.3 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ በአምስት እርዳታ ድርጅቶች እየተረዱ ይገኛሉ\" ብለዋል አቶ ምትኩ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በትግራይ ክልል ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ እንደተጋለጡ በመግለጽ የከፋ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበበ ገብረ ህይወት በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አርሶ አደሮች እንዳያርሱ ተከልክለዋል ያሉትም ጉዳይ በጋዜጠኞች የተነሳ ሲሆን ይህ ተፈፅሟል ወይ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ምትኩ በምላሹ \"ሐሰት ነው\" በትግራይ ክልል 70 በመቶ የሚሆነው አካባቢ ታርሷል ብለዋል። አቶ ምትኩ ይህንን ያሉት የግብርና ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተሻሻለ ዘርና ማዳበሪያም በክልሉ እንደተከፋፈለ በዚሁ አጋጣሚ አስረድተዋል። ምክትል የትግራይ አስተዳደሩ ይህንን ቢናገሩም ከሚዲያ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ በነበራቸው ቆይታ ይህንን ማስተካከላቸውን አቶ ምትኩ ለጋዜጠኞቹ ገልፀዋል። የሰብዓዊ እርዳታን በተመለከተ በክልሉ ውስጥ እስካሁን ለ4.5 ሚሊዮን ሕዝብ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች በመጀመሪያው ዙር፣ በሁለተኛውና በሦስተኛው ዙር ለ5.2 ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ መቅረቡን አቶ ምትኩ ይናገራሉ። በዚህም መሰረት ኮሚሽነሩ እንደሚሉት በ5.4 ቢሊዮን ብር የሚገመት 170 ሺህ 798 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለክልሉ ተከፋፍሏል። በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር የተከፋፈለውን የምግብ ወጪ 70 በመቶ መንግሥት የሸፈነ ሲሆን ሰላሳ በመቶውን ደግሞ አጋሮች ሸፍነዋል ተብሏል። በሦስተኛው ዙር ግን መንግሥትን ጨምሮ ስድስት አካላት ማለትም የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ወርልድ ቪዥን፣ ኬር ኢንተርናሽናል፣ ሪሊፍ ሶሳይቲ ኦፍ ትግራይ፣ ፉድ ፎር ሃንግሪ እርዳታ እያደረሱ እንደሚገኙም ተጠቁሟል። እነዚህ የአጋር ድርጅቶች 84.9 በመቶ የትግራይ ወረዳዎችን በመሸፈን 91̄.3 በምግብ አቅርቦትና ስርጭት አያደረሱ እንደሚገኙም ተነግሯል። መንግሥት በእነዚህ አካባቢዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ፣ እርዳታው እንዲሰራጭ ምቹ ሁኔታንም ለመፍጠር ከአጋሮች ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም አቶ ምትኩ ጠቁመዋል። የተለያዩ የሰብዓዊ አርዳታ አጋሮች በክልሉ 5.2 ሚሊዮን ወይም ደግሞ 90 በመቶ የሚሆነው የክልሉ ሕዝብ አስቸኳይ የሰብዓዊ አርዳታ ያስፈልገዋል ቢሉም አቶ ምትኩ በበኩላቸው ከነዚህ ውስጥ 1 ሚሊዮን 10 ሺህ 752 ሰዎች የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ ናቸው፤ እንዲሁም 40 ሺህ 336 ደግሞ ኤርትራውያን ስደተኞች ናቸው ብለዋል። እነዚህ የጠቀሷቸው ፕሮግራሞች \"የራሳቸው ፈንድ አላቸው\" አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸውም ጋር በቅንጅት ሊታዩ እንደማይገባም ይናገራሉ። ሆኖም አቶ ምትኩ በክልሉ እርዳታ ለማቅረብ ተግዳሮቶች እንዳሉ የጠቆሙ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ውጊያና ተኩስ በመኖሩ የፀጥታውና የደኅንነት ሁኔታውን ስጋት ላይ መጣሉን ጠቁመው በዚህም የወታደሮች እጀባ ያስፈልጋል ብለዋል። በሌላ በኩል አስቸኳይ መጠለያና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እጥረት ሌሎችም ችግሮችም እንዳሉ ጠቁመዋል። \"ምግብ ነክ ባልሆኑ ቁሶች እርዳታ ላይ ከፍተኛ የሚባል ክፍተት አለ\" የሚሉት አቶ ምትኩ ለዚህም በዋነኝነት የሚያነሱት አጋሮች እየሸፈኑ ያሉትም 33 በመቶ ወጪውን መሆኑን ነው። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮችን በተመለከተ፤ አቶ ምትኩ በክልሉ ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ሦስት አማራጮች የቀረበላቸው ሲሆን ሰላማቸው በተረጋገጡ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በፈቃዳቸው ዓለም አቀፉን ድንጋጌ መሰረት ባደረገ መልኩ ወደመጡበት እንዲመለሱ፣ በሁለተኛ ደረጃ አካባቢያቸው ያልተረጋጋ ከሆነም የቅርብ ቤተሰብና ዘመዶች ካሏቸው ከእነሱ ጋር እንዲቆዩ፣ ሁለቱን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ በመጠለያዎች እንዲቆዩ የሚል ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ ምላሽ የሰጡት አቶ ምትኩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት አርባ አባላት ያሉት ኮሚቴ መቋቋሙን አመልክተዋል። እነዚህን ተፈናቃዮች የክረምት ወር ከመጀመሩ በፊት ወደመጡባቸው ቦታዎች ለመመለስ እቅድ የተያዘ ሲሆን ኮሚቴውም የአማራ ክልል ፕሬዚዳንትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንቶችንም በአባልነት እንዳካተተ ተጠቁሟል። በክልሉ የጤና ሥርዓትን በተመለከተ በትግራይ የጤና ሥርዓቱን ወደነበረበት ለመመለስ የጤና ሚኒስቴርና የተለያዩ ኤጀንሲዎች እየሰሩ ነው የተባለ ሲሆን ይህንንም ለማከናወን አንድ ግብረ ኃይል መሰማራቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል። የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ከብሔራዊ ተቋማት ተሰማርተው የክልሉን የጤና ቢሮ እየረዱ እንደሚገኙም ተገልጿል። የክልሉን ጤና ሥርዓት ከመመለስ ጋር በተያያዘ ዋነኛ የተባለውም ሥራ የጤና ተቋማቱ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ 55 በመቶ የሚሆኑት ሆስፒታሎች እንዲሁም 52 በመቶ የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል። አገልግሎት በሚሰጡ ሆስፒታሎችም ሆነ የጤና ማዕከላት 95 በመቶ የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች በየቀኑ አገልግሎት መስጠት መቀጠላቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ የቀሩት የጤና ተቋማት ላይ የደረሰባቸው ጉዳት ተግመግሞ መልሰው እንዲቋቋሙና አገልግሎት እንዲጀምሩ ከፌደራል መንግሥት በኩል ለ14 ሆስፒታሎችና 58 የጤና ማዕከላት ገንዘብ ተመድቧል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ አስፈላጊ የሚባሉ የጤና ቁሳቁስ ግብዓቶች እንደ አልትራ ሳውንድ፣ ቬንትሌተር፣ ማይክሮስኮፖች መላኩን የገለፁት ሚኒስትሯ፤ እስካሁንም ባለው ከ310.8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መድኃኒቶችና ሌሎች ግብዓቶች ወደ ክልሉ መላኩን አስረድተዋል። በአጠቃላይ በክልሉ ለጤና አገልግሎት አስፈላጊ ግብዓቶች 215 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል ተብሏል። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) መጋቢት ወር ላይ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል በሚገኙ የህክምና ተቋማት ላይ ሆን ተብሎ ዘረፋ እና ጥቃት ተፈጽሟል ሲል ገልፆ ነበር። ድርጅቱ በዚሁ መግለጫው አንዳንዶቹ ዘረፋዎች የተፈፀሙት በወታደሮች ጭምር ነው ያለ ሲሆን 13 በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ብቻ በአግባቡ እየሰሩ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው። በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የጤና ተቋማትን አገልግሎት ከማስጀመር ጋር ተያይዞ ተንቀሳቃሽ የጤና የህክምና አገልግሎትን መመለስ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ተቋማቱ በውስን ደረጃም አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በተለይም እናቶችና ህፃናት ላይ አተኩሮ የክትባትና ሌሎች የህክምና አገልግሎት በተለያዩ ወረዳዎች እየተሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ በባለፉት ሁለት ወራት ከ75 ሺህ የሚበልጡ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ህፃናት ወደ ጤና ማዕከላትና ተንቀሳቃሽ የህክምና መስጫ ማዕከላት መምጣታቸውን ሚኒስትሯ ተቋማቱን ዋቢ አድርገው ተናግረዋል። ከነዚህም መካከል 4 በመቶዎቹ ለከፋ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን አስፈላጊው የህክምና እንክብካቤና አገልግሎት አግኝተዋል ያሉት ሚኒስትሯ፤ በአጠቃላይ አገልግሎት በሚሰጡት የጤና ተቋማት 409 ሺህ የክልሉ ነዋሪዎች በባለፉት ወራት አገልግሎት እንዳገኙም ተገልጿል። ክልሉ በርካታ የአምቡላንስ አገልግሎቶቹን ከማጣቱ አንፃር በአሁኑ ጊዜ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ከሌሎች አካላት በተገኘ እርዳታ 58 አምቡላንሶች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ 65 ጥገና ላይ ሲሆኑ ሌሎቹንም በተጨማሪነት ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። በተጨማሪም ተፈናቃዮች ባሉበት ቦታ አስፈላጊ የሚባሉ የጤና አገልግሎቶች በነፃ እየተሰጡ እንደሆነ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ይህንንም ለማገዝ በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት ተጨማሪ ባለሙያዎችን በማሰማራትና ጊዜያዊ የጤና ማዕከላትን በማቋቋም እየተረዱ እንደሚገኙም ተነግሯል። በዚህ ጦርነት የተደፈሩ ሴቶችን አስፈላጊ ህክምና ለመስጠት የሥነ አዕምሮ ህክምናን ጨምሮ የማማከር ሥራ የሚሰሩ ባለሙያዎች በስድስት ከተሞች ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። በክልሉ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የክልሉ የጤና ቢሮ ከ28 አጋሮች ጋር እየሰሩ ነው ቢባልም እንደዚያም ሆኖ በርካታ ችግሮች ተደቅነዋል ብለዋል።", "ኮሮናቫይረስ፡ ኮሮናቫይረስ ውሸት ነው ብሎ የሚያምነው ጎልማሳ ባለቤቱ በበሽታው ተቀጠፈች ብራየን ሊ ይባላል፡፡ በፍሎሪዳ ውስጥ ታክሲ ነጂ ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ ኮሮና የሚባል ነገር የለም፤ ፍጹም ቅጥፈት ነው ሲል ነበር፡፡ ይህን የሚለው ግን ለጨዋታ ድምቀት ሳይሆን የምሩን ነበር፡፡ እንዲያውም ወደ ፌስቡክ እየወጣ ሰዎች በዚህ እልም ያለ ውሸት እንዳይታለሉ ይሰብክ ነበር፡፡ ባለቤቱ ኤሪን ትባላለች፡፡ ወይም ‹ትባል ነበር› ማለቱ ይሻላል፡፡ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወተወን አጥታለች። ለብራይን ይህ ትልቁ ቅጣት ሆኖበታል፣ ዛሬ፡፡ ብራይንም ሆነ ባለቤቱ ኤሪን በበይነ መረብ የሚሰራጩ መላምቶች ሰለባ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ‹ኮሮና ብሎ ነገር የለም፡፡ ካለም ጉንፋን ነው፤ ካለም 5ጂ ቴክኖሎጂ የፈጠረው ነገር ነው› ሲሉ ነበር የሚያምኑት፡፡ ለዚህም ይመስላል ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ እንኳን ሐኪም የሚላቸውን ነገር ለመስማት ያልፈቀዱት፡፡ ሁለቱም ግንቦት ላይ ነበር የታመሙት፡፡ ብራይን በለስ ቀንቶት አገገመ፡፡ ሚስቱ ግን አሸለበች፤ 46 ዓመቷ ነበር፡፡ ብራይን በሐምሌ ወር ላይ የቢቢሲ እንግዳ ነበር፡፡ ቢቢሲ ያኔ በኮቪድ-19 ዙርያ በሚሰሩ መላምቶችና የሴራ ወሬዎች ዙርያ አንድ ዘገባ እየሰራ ነበር፡፡ ያን ጊዜ የብራይን ሚስት አልሞተችም ነበር፡፡ ሆኖም በጽኑ ሕሙማን ማገገምያ ክፍል ገብታ ትተነፍስ የነበረው በቬንትሌተር ነበር፡፡ ኤሪን በፍሎሪዳ ፓስተር ነበረች፡፡ ጤናዋ ግን መልካም የሚባል አልነበረም፡፡ አንደኛ አስም ነበረባት፤ ሁለተኛ የእንቅልፍ እጦት ያሰቃያት ነበር፡፡ ባሏ ባደረሰባት የአስተሳሰብ ተጽእኖ ምክንያት እና በወቅቱ በቫይረሱ ዙርያ በነበራቸው እምነት ምክንያት ጥንቃቄ እንዳላደረጉ ነው የሚናገረው ብራያን፣ ለቢቢሲ፡፡ ስለዚህ ቫይረሱ እንደያዛቸው ቢያውቁም ሁለቱም ሥራቸውን ቀጥለው ነበር፡፡ እሷም ፓስተርነቷን፣ እሱም ሹፍርናውን፡፡ እሷ አልጋ ከያዘች ወዲህም ቢሆን ብራይን መደንገጥ በነበረበት ደረጃ አልደነገጠም፡፡ መድኃኒት ግዛ ሲባል በመድኃኒቶቹ እምነት ባይኖረውም እያቅማማም ቢሆን ታክሲው እያሽረከረ ይሄዳል፡፡ በጉዞው ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አያደርግ? ማኅበራዊ ርቀቱን አይጠብቅ፡፡ ለነገሩ ሁለቱም ግንቦት ላይ የታመሙ ጊዜ ራሱ ቶሎ ሐኪም ለማየት አልሄዱም፡፡ በብዙ ጥርጣሬና ማመንታት ነበር ምርመራ ያደረጉት፡፡ አለባችሁ ሲባሉም አልደነቃቸውም፡፡ ምክንያቱም ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም ብለው በውስጣቸው ያምኑ ስለነበረ፡፡ ብራይን አሁን ለቢቢሲ እንደተናገረው ‹ያን ጊዜ ሰው የሚለኝን ሰምቼ ቢሆን ኖሮ…› የሚል ጸጸት አድሮበታል፡፡ ‹‹ቫይረሱ እውነት ነው፡፡ ሰዎችን በተለያየ ደረጃ ቢያጠቃም ኮቪድ-19 ሐቅ መሆኑን አምኛለሁ፡፡ አሁን ወደኋላ ሄጄ የምቀይረው ነገር ግን የለም፡፡ አሁንን መኖር ነው የሚኖርብኝ፤ አሁን ላይ ለወደፊት የተሻለ ምርጫ እያደረጉ ከመኖር ሌላ ምን ማድረግ እችላሁ?›› ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ‹‹ባለቤቴ ላትመለስ ሄዳለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትናፍቀኛለች፡፡ ወደ ተሻለ ዓለም ተሸጋግራለች ብዬ ማመን ነው የምመርጠው፡፡ ›› ይላል ብራይን፡፡ ብራይን እንደሚለው እሱም ሆነ ሟች ባለቤቱ ቫይረሱ ሐሰት ነው ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ በግልጽ ለመናገር ይከብደዋል፡፡ መጀመርያ አካባቢ 5ጂ ያመጣው መቅሰፍት ነበር የሚመለስላቸው፡፡ ቀጥለው ደግሞ እንዲሁ መንግሥታት ሕዝቦቻቸውን ለማታለል የፈጠሩት አድርገው መውሰድ ጀመሩ፡፡ ይህን እምነት ያዳበሩት ደግሞ በፌስቡክ ላይ በሚያነቡት ነገር ነው፡፡ ‹‹እውነቱን ለመናገር እኛ በዋናነት ይመስለን የነበረው መንግሥት ሕዝቡን ለማስቀየስና በሌላ ጉዳይ ወጥሮ ለመያዝ የፈጠረው ወሬ እንጂ ቫይረሱ የምር አይመስለንም ነበር፡፡ ብራይን ባለቤቱ ጽኑ ሕሙማን ማገገምያ ከገባች በኋላ ወደ ፌስ ቡክ ተመለሰና ‹‹በኛ ይብቃ፣ ትውልድ ይዳን›› ብሎ መጻፍ ጀመረ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ድረስ ቫይረሱ ፈጠራ ነው፤ ወሬ ነው ብለው ከልባቸው ያምናሉ፡፡ ቢቢሲ ባለፈው ግንቦት በሰራው አንድ ጥናት በርካታ ሰዎች 5ጂ የቴሌኮሚኒኬሽን የስልክ መስመሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በሕክምና ባለሞያዎቸ ላይ እንዲሁ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በጤና ተቋማትም ላይ እንዲሁ፡፡ የብዙዎቹ የተሳሳተ እምነት ተኮትኩቶ ያደገው ታዲያ በማኅበራዊ ሚዲያ ነው፡፡ የፌስቡክ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ሲናገር እንዲህ ዓይነት አሳሳች መረጃዎች ሲመጡ ፌስቡክ እርምጃ ይወስድባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ባለፉት ወራት 7 ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ ሐሳዊ መረጃዎች ከገጹ እንዲወገዱ አድርገናል ብሏል፡፡ ሆኖም ተቺዎች ፌስቡክ ሐሳዊ መረጃዎችን ለማጥፋት ዳተኛ ነው ይላሉ፡፡ ቫይረሱ አሁን በመላው ዓለም 24 ሚሊዮን ሰዎችን አዳርሷል፡፡ የ800ሺህ ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ሐሰትና የተቀነባበረ ወሬ የሚመስለው ሰው ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ አሁንም ሚሊዮኖች ኮቪድ-19 ብሎ ነገር የለም፤ ወይም መንግሥታት የፈጠሩት ቅንብር ነው ብለው ነው የሚያስቡት፡፡ በተለይም ከክትባት ጋር በተያያዘ ብዙ መላምቶች ማኅበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀውታል፡፡ ቢልጌትስ የሕዝብ ቁጥርን ለመቀነስ የዘየደው ነው ከሚለው ጀምሮ፣ ገንዘብ በክትባት መልክ ለማፈስ የተፈጠረ በሽታ ነው ብለው ዛሬም ሚሊዮኖች ያምናሉ፡፡ ብዙዎች እንደ ብራያን የሚወዱትን እስኪያጡ ድረስ ከዚህ ቅዥብርብር እምነታቸው ንቅንቅ የሚሉ አይመስሉም፡፡", "ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ሥራውን ማቋረጡን ገለጸ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በተጣለበት ዕገዳ መሠረት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚያከናውናቸውን ሥራዎቹን ማቋረጡን አስታወቀ። የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ከኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተጣለበትን የሦት ወራት ዕገዳን በማክበር በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌና በደቡብና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሥራውን አቁሟል። ድርጅቱ በተጠቀሱት አካባቢዎች ያለውን ሥራውን ቢያቋርጥም \"በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ጉጂ፣ በደቡብ ክልልና በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ውስጥ የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎቱን ይቀጥላል\" ብሏል። የእገዳ ትዕዛዙ ከተሰጠው በኋላ የሚደረገው ምርመራ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚሰጠውን የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ ሥራዎችን ጨምሮ ሁሉንም ተግባራቱን ለሦስት ወራት ማቋረጡን አስታውቋል። በዚህም መሠረት ኤምኤስኤፍ ባሉት ክሊኒኮች ውስጥ የነበሩ ታካሚዎች በአጭር ማስጠንቀቂያ እንዲወጡ መደረጉንና አንድ ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞቹ ከቤታቸው ሆነው እንዲጠባበቁ እንዲሁም ሁሉም በሚባል ደረጃ የውጭ አገር ዜጋ የሆኑ ሠራተኞቹ ከአገሪቱ እንዲወጡ መደረጋቸውን አመልክቷል። ድርጅቱ እነዳለው የሚያካሂደው የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ ሥራ እንዲያቋርጥ የታዘዘው በአገሪቱ ያለው የተለያየ አይነት የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት ከፍተኛ በሆነበት ጊዜ መሆኑን ገልጿል። የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ሥራውን ማከናወን ባቆመባቸው በምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ለሕዝቡም ሆነ ለእርዳታ ሠራተኞች አደገኛና ተለዋዋጭ ነው ሲል ገልጿል። በሶማሌና በአማራ ክልል ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ሰዎች እንዲሁም በጋምቤላ ውስጥ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሁኔታ እንደሚያሳስበው የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድኑ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። ድርጅቱ ከሦስት ወራት በፊት ትግራይ ውስጥ ስለተገደሉት ሠራተኞቹ ጉዳይ አስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደም ሆነ ስለግድያው ሁኔታ ምንም ግልጽ ያለ ነገር እንደሌለና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተደረገ ስላለው ምርመራ የሚያደርግውን ክትትል መቀጠሉን ገልጿል። ኤምኤስኤፍ የባልደረቦቹን ግድያ ተከትሎ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙት ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ዞኖች ውስጥ ሲያከናውን የነበረውን እንቅስቃሴ ማቋረጡ ይታወሳል። ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ ለ37 ዓመታት ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከክልል መስተዳድሮች ጋር በመተባበር በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች በገለልተኝነትና በሰብአዊነት የህክምና ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱን አመልክቷል። ድርጅቱ የሚሰጠውን ሰብአዊ አገልግሎት ለመቀጠል ያለውን ፍላጎት ገልጾ ለዚህም የተጣለበት ዕገዳ እንዲነሳና ሥራውን ለመቀጠል ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ መሆኑንም ገልጿል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በቅርቡ በአገሪቱ ይሰሩ የነበሩ ሦስት የበጎ አድራጎት ተቋማትን ማገዱን መግለጹ ይታወሳል። በዚህም መሠረት የሆላንድ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን፣ ኖርዌጂያን ሪፊዩጂ ካውንስል እና አል ማክቱም ፋውንዴሽን ለሦስት ወራት እገዳ እንደተጣለባቸው አስታውቆ ነበር። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ሦስቱ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ከመንግሥት በሰጣቸው ፍቃድ በተለያዩ የሰብዓዊ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ኤጀንሲው በሚያደርገው ክትትል መሠረት ድርጅቶቹ ከተቋቋሙለት አላማ ውጪ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው እግዱ እንደ ተጣለባቸው አመልክቷል።", "ኮሮናቫይረስ፡ ጳጳሳቷን በኮቪድ-19 እያጣች ያለችው የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደ ሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳትና ጫና ያሳረፈባቸው የእምነት ተቋማት በጣም ጥቂት ናቸው። በባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በሰርቢያና ሞንቴኔግሮ የሚገኙ የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ኃላፊዎችን በኮሮናቫይረስ አጥታለች። የቤተክርስቲያኗ ኃላፊዎች ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ በተለመደው መንገድ የአምልኮና ሌሎች አገልግሎቶችን በመቀጠላቸው ለወረርሽኙ መዛመትና ለሞቱ ምክንያት እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ባለፉት ወራትም በቤተ ክርስቲያኗ የተከሰተው ተከታታይ ሞት አስደንጋጭ ሆኗል። የቤተ ክርስቲያኗ አመራሮች በኮሮናቫይረስ የታመሙም ሆነ የሞቱ ቢኖሩም በአሁኑ ወቅት ቤተክርስቲያኗ በአብዛኛው ሰርቢያውያን ዘንድ የህይወታቸው ማዕከል ናት። በሰርቢያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የማስተማር ሥራውን በወረርሽኙ ምክንያት በበይነ መረብ እንዲያደርጉ መመሪያ ቢወጣም ቤተክርስቲያኗ የቁርባን ሥርዓቷን አልተወችም። የአገሪቱ መንግሥት ወረርሽኙን ለመቆታጠር ከአምስት በላይ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ እንዳይሰባሰቡ ያስተላለፈውን ትእዛዝ በመተላለፍ ቤተ ክርስቲያኗ የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ማካሄዷን ቀጥላለች። \"ምንም እንኳን የምዕመናን ቁጥር በተወሰነ መልኩ መቀነስ ቢያሳይም አሁንም ቢሆን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች የሚደረገው የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት አልተስተጓጎለም፤ በየጊዜው ይደረጋል\" በማለት የእምነት ጉዳዮች ተንታኝ ዜልጅኮ ኢንጃክ ይናገራሉ። \"በሰርቢያውያን ዘንድ ቤተ ክርስቲያኗ ትልቅ ክብር አላት። ከአገሪቷም ሆነ ከየትኛው ብሔራዊ ተቋማት በበለጠ ትልቅ ክብር አላት\" ይላሉ ተንታኙ። \"በባልካን አገራትም ሆነ በምሥራቅ አውሮፓ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች፣ ርዕዮተ ዓለማትም ሆነ መንግሥት በተደጋጋሚ ቢቀያየርም ሕዝቡ በፖለቲካውም ሆነ በምጣኔ ሀብቱ ይህ ነው የሚባል ማሻሻያ አላሳየም። ለሕዝቡ ቋሚና ዋነኛዋ ነገር ቤተ ክርስቲያኗ ናት\" በማለትም ያስረዳሉ። ሆኖም ሁለት ትልልቅ ጳጳሳት የቀብር ሥነ ሥርዓት ጋር ተያይዞ በቤተ ክርስቲያኗ አሰራር ላይ ትችቶች እየተሰሙ ነው። በሞንቴግሮ መዲና ፖዶጎሪጋ ለቅስተኛ ምዕመናን የኤጲስ ቆጶስ አምፊሎሂጄ ራዶቪች አስከሬን እጅና ግንባር በመሳምና በመሳለም ሲሰናበቱ ነበር። ኤጲስ ቆጶሱ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ከማለፉ በፊት የእምነት ተግባራት \"የአምላክ ክትባት\" ናቸው ብለው ነበር። ለቀስተኛ ምዕመናን በቤልግሬድ ሴይንት ሳቫ ቤተክርስቲያን የተካሄደውን ፓትርያርክ ኢሪነጅ የቀብር ሥነ ሥርዓት በርቀት እንዲከታተሉት ተደርገዋል። ሆኖም ከቀብራቸው በፊት በነበረው የፓትርያርኩ የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ መመሪያዎች አልተከበሩም ተብሏል፤ የእምነቱ ተከታዮች የሬሳ ሳጥኑ ላይ የተገጠመውን መስታወት በመሳምና በመሳለምም ክብራቸውን ሲገልፁም ነበር። በነበረውም የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ቁርባኑ ሲፈፀም የነበረው በአንድ ማንኪያ እንደሆነም ተገልጿል። ይህም ሁኔታ ለኮሮናቫይረስ የማጋለጥ እድሉም ከፍተኛ እንደሆነም የተላላፊ በሽታዎች አጥኚ ዶክተር ጁሪክ ለቢቢሲ ሰርቢያ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኗ ሥነ ሥርዓቷንና አሰራሯን እንድታሻሻልና ካልሆነም መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ባለሙያው ጥሪ አድርገዋል። ዶክተር ጁሪክ በተጨማሪም ስብሰባዎች የታገዱበት መመሪያ ወጥቶ ባለበት ሰዓት በቤተ ክርስቲያኗ ለምን ይህ ተግባራዊ እንደማይሆን ይጠይቃሉ። \"ሕግና መመሪያዎች ለአንዳንዶች ተግባራዊ እንደማይደረግ መጥፎ መልዕክትን አስተላልፏል። ይህ ሁኔታ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በተጠየቀው ሕዝብ ዘንድ አመኔታን ያሳጣልም\" ይላሉ። ከፓትርያርኩ የስንብት ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኙ መዛመት ሊኖር ይችላል በሚልም የጤና ባለሙያዎች ዝግጅት እያደረጉ ነው። በቅርብ ቀናት ውስጥ በሰርቢያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱንም በመጥቀስ ሁኔታው የሚያሳዝን ነው ተብሏል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩሲክ በበኩላቸው \"ሁላችንም ቢሆን ኃላፊነታችን ካልተወጣን ለሚያሳዝን ከፍተኛ አደጋ መጋለጣችን አይቀርም\" በማለት አስጠንቅቀዋል። ቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎት መቀጠሏን በማስመልከት ምንም ከማለት የተቆጠበች ቢሆንም የቤተ ክርስቲያኗ ኃላፊዎችም ሆኑ ቁሶች ከቅዱስ ሲኖዶሱ አቅጣጫ እንዲቀመጥላቸው እየጠበቁ መሆኑን አሳውቀዋል። ምንም እንኳን የፓትርያርኩን ሞት እንዲሁም የኤጲስ ቆጶስ ዴቪድን ሆስፒታል መግባት ተከትሎ አገልግሎት የሚሰጡ ኃላፊዎች ቁጥር ቀንሷል። ነገር ግን አሁንም ዝርዝር አቅጣጫ ይሰጣል በሚል እየተጠበቀ ነው ያለው። እስከዚያው ግን ቤተ ክርስቲያኗ ፓትርያርኳን ለማስታወስ የምታደርገውን የሰባት ቀን እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ቀጥለዋል። በዚህ ሳምንት መጨረሻ አርብ በነበረው ስነ ስርአትም ቄሶች ጭምብል አላጠለቁም ነበር።", "ኮሮናቫይረስ ፡ በሞባይል ስክሪን ላይ የምናሳልፈው ጊዜና የዓይናችን ጤና በኮቪድ-19 ዘመን ኮሮናቫይረስ ያስከተለውን የእንቅስቃሴ እገዳ ተከትሎ የሰዎች በስልክና በኮምፒውተር ስክሪን ላይ ያላቸው የቆይታ ጊዜ የጨመረ በመሆኑ ለዓይናቸው ደኅንነት መጠበቅ የ\"20-20-20\" ደንብን እንዲለማመዱ አንድ የዓይን ጤና በጎ አድራጎት መክሯል። 'ፋይት ፎር ሳይት' ለ20 ደቂቃዎች ስክሪን ላይ አንዳች ነገር እያደረጉ ከቆዩ በኋላ 20 ጫማ ርቀት ላይ ያለን ነገር ለ20 ሰከንድ መመልከት ይመክራሉ። ከ2,000 ሰዎች መካከል ግማሾቹ ከኮቪድ-19 መከሰት በኋላ ከፍ ያለ ጊዜን ስክሪን ላይ እያጠፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሦስተኛው (38 በመቶ) የሚሆኑት የዓይን ችግራቸው መባባሱን አንድ ጥናት አመልከቷል። የዓይን ሐኪሞች ደግሞ እርዳታ ለሚገፈልጉ ሰዎች ሁሌም ክፍት ሆነው ቆይተዋል ሲል የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ገልጿል። ነገር ግን በ2 ሺህ ጎልማሶች ላይ የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው በቫይረሱ መያዝን ወይም ማሰራጨትን በመፍራት ከአምስቱ ውስጥ አንዱ ከወረርሽኙ በፊት እንደነበረው የዓይን ምርመራ የማድረግ ዕድሉ አነስተኛ ነው ብሏል። የጥናቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት የማንበብ ችግር፣ እንዲሁም ራስ ምታት፣ በተወሰነ የጭንቅላት ክፍል ላይ የሚከሰት ከባድ የራስ ምታት [ማይግሬን] እና ደካማ የማታ ዕይታ እንዳለባቸው ሪፖርት አድርገዋል። ሰዎች መደበኛ የዕይታ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ማስታወስ እንደሚያስፈልግ እና \"አብዛኞቹ የዓይን ሐኪሞች የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለባቸው ወቅቶችም ለቀጠሮ ክፍት ሆነው ቆይተዋል\" ተብሏል። የፋይት ፎር ሳይት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽሪን ክራውስ \"የዓይን ችግር ከሚያስከትሉ ጉዳዮች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ቀደም ብሎ በመለየትና የመከላከል ዘዴዎችን በመተግበር ሊወገዱ ይችላሉ። መደበኛ የዓይን ምርመራዎች ብዙውን ጊዜ ምልክት የሌላቸውን የዕይታ ችግሮች ለይተው ማወቅ ያስችላሉ\" ብለዋል። በየመካከሉ ቀላል ዓይንን ከስክሪን ዕይታ ዞር በማድረግ እረፍት ማግኘት ዓይን ላይ የሚፈጠር ጫናን ለመከላከል ይረዳል ሲል የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አመልክቷል። የዓይን ሐኪሞች ቀጠሮዎች ተፈቅደዋል በመንግሥት መመሪያ መሠረት ሰዎች በዕገዳ ወቅትም ቢሆን ለህክምና ቀጠሮ ከቤት መውጣት እና \"ጉዳትን፣ ህመምን ወይም የመጎዳት አደጋን ማስወገድ\" ይችላሉ ይላል። የዓይን ህክምና ኮሌጅ አባላት ማንኛውም የዕይታ ለውጥ ወይም ችግር ላጋጠማቸው ሰዎች በእገዳው ጊዜ የዓይን እንክብካቤ መስጠቱን መቀጠል አለባቸው ብሏል። መደበኛ ቀጠሮዎችም \"አቅም በፈቀደ መጠንና ለህሙማን ጥቅም እስከሆነ ድረስ\" በቀላሉ ሊመቻቹ ይገባል ይላል መመሪያው። የዓይን ህክምና ክሊኒክ አማካሪ ፓራምዴፕ ቢልኩ እንደተናገሩት የኮሌጁ ጥናት የተወሰኑ ሰዎች በመጀመሪያው ዕገዳ ወቅት ዕይታቸው መታወኩን አስተውለዋል። \"ብዙ ሰዎች በስክሪኖች ፊት ብዙ ጊዜ ማሳለፋቸው ዕይታ ችግራቸውን እንዳባባሰው እንደሚያምኑ ያደረግነው ጥናት አሳይቷል\" ብለዋል። \"መልካሙ ዜና እንዲህ ያሉት ችግሮች በዕይታ ላይ ዘላቂ ጉዳት የማያስከትሉ መሆናቸው ነው። ሆኖም ግን ዕይታዎ እንደተዳከመ ከተሰማዎት ወይም ዓይኖችዎ ሲቀሉ ወይም ህመም ሲሰማዎ በቅርብዎ የሚገኙ የዓይን ሐኪሞችን በስልክ ወይም በድረገጽ ላይ በማግኘት ማማከር ያስፈልጋል\" ሲሉ ገልጸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የጤናና ደኅንነት ሕግ አሠሪዎች ሠራተኞች በቀን ከአንድ ሰዓት በላይ ለሥራ ስክሪን መጠቀም ካለባቸው ለሠራተኞቻቸው የዓይን ምርመራ ማድረግ አለባቸው። በበጋ ወቅት ቢያንስ 10,000 ያህል ሰዎች በብሪታንያ አስፈላጊ የሆነ የዓይን እንክብካቤ እንዳላገኙ ተልጿል። አስከፊው ጉዳይ የሮያል ብሔራዊ ዓይነ ስውራን ኢንስቲትዩት በወረርሽኙ ወቅት ሆስፒታል መሄድን በመፍራት አንዳንድ ሰዎች ዕይታቸውን የማጣት አደጋ ተጋርጦባቸዋል የሚል ስጋት እንዳለው ተናግሯል። የሮያል ኮሌጅ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች ቃል አቀባይ \"በዕይታቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ የተመለከቱ ሰዎች የዓይን ሐኪም ምክር መጠየቁ እና ለውጦቹ የዓይን ሐኪም ተጨማሪ ምርመራ የሚፈልግ መሆኑን መወሰን አስፈላጊ ነው\" ብለዋል።", "በርካታ ልጆች ከመጠን ካለፈ ውፍረት ጋር በተገናኘ በስኳር በሽታ እየተያዙ ነው በዩናይትድ ኪንግደም በሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም የሚጠቁ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የጤና ባለሙያዎችን እንዳሳሰባቸው አንድ የበጎ ድርጅት አስጠንቅቋል። ህፃናቱ የስኳር ህመም ተጠቂ ያደረጋቸው ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንደሆነና ይህም ከኑሮ ውድነት ጋር በተገናኘ ያለው ደካማ የአመጋገብ ስርዓት መሆኑንም የዩናይትድ ኪንግደም የስኳር ህመምተኞች ማህበር አስታውቋል። በተለይም የኑሮ ውድነቱ በከፍተኛ መጠን ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ጤናማ የሚባሉ የምግብ አይነቶች በመወደዳቸው የበለጠ ሁኔታውን ሊያባብሰው እንደሚችልም ተገልጿል። በተለይም የኑሮ ዝቅተኛነት በሚስተዋልባቸው የእንግሊዝና ዌልስ አካባቢዎች ጫናው ከፍተኛ መሆኑንም መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም ከተጠቁ አስሩ ወስጥ አራቱ የኑሮ ዝቅተኛነት ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ነው። ይህም አሃዝ የኑሮ ከፍተኛነት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ከ19ኙ አንዱ እንደሚጠቃ ያሳያል። በእንግሊዝ ዕድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከአስሩ አንዱ ከመጠን ያለፈ ውፍረት አለው። ከመጠን በላይ ውፍረት በሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። በተጨማሪም ከዘር  እንዲሁም ከቤተሰብ ታሪክ ጋር በተገናኘ በህመሙ የመጠቃት እድል አለ። የስኳር በሽታ ምንድነው? -       የስኳር በሽታ ሰዎች በደም ውስጥ ከመጠን በላይ ስኳር (ግሉኮስ) እንዲኖራቸው ያደርጋል። -       በአንደኛው አይነት ስኳር የተጠቁ ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ ኢንሱሊን አያመነጩም። -       በሁለተኛው ዓይነት ስኳር ህመም የተጠቁ ደግሞ የማይጠቅም ወይም በቂ ያልሆነ ኢንሱሊን ሰውነታቸው ያመነጫል። በእንግሊዝ እና በዌልስ የህጻናት የስኳር ህመም ክፍል ውስጥ ህክምና ከሚያገኙ ህፃናት መካከል በሁለተኛው የስኳር ህመም የሚጠቁ ህፃናት ቁጥር ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከ 50 በመቶ በላይ መጨመርን ያሳያል ።", "ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ገና አልሰለቸንም- የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዓለም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደማግኘት እየተቃረበ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ መከላከያዎችን ማላላት የለበትም ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው አሳሰቡ። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ አሁንም የዛሬ ስምንት ወር እንደነበረው አስጊ ወረርሽኝ መሆኑን እንደቀጠለ ነው ብለዋል። በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ደርሷል። በፓሪስ እየተካሄደ ባለው የሰላም ጉባዔ ላይ \"በኮቪድ-19 ታክቶን ይሆናል ነገር ግን እርሱ ገና አልሰለቸንም\" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም። \"የአውሮፓ አገራት እየታገሉ ነው ነገር ግን ስርጭቱን ለማቆም የተወሰዱት እርምጃዎች እንዲሁም ቫይረሱ ምንም ለውጥ አላሳየም\" ሲሉም አክለዋል። ከቅርብ ቀናት ወዲህ በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ላይ የተሻሉ ግኝቶች እየታዩ መጥተዋል። ሰኞ ዕለት ፋይዘር እና ባዮንቴክ እየሰሩት ያለው ክትባት በተደረገለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍተሻ 90 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው አረጋግጠናል ብለዋል። ረቡዕ ዕለት ደግሞ የሩስያ ተመራማሪዎች የሰሩት የመከላከያ ክትባት 92 በመቶ ውጤታማ መሆኑን አስታውቀዋል። ነገር ግን ሁለቱም ክትባቶች የሚደረግላቸውን የቁጥጥር ፍተሻ ማለፍ አለባቸው ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ ገና ደህንነቱ እና ውጤታማነቱ መፈተሽ ባለበት ክትባት ላይ መተማመን አደገኛ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። \"ክትባት በፍጥነት ያስፈልጋል፣ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን ቁጭ አንልም\" ብለዋል።", "ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማንን የሚከታተሉ ሐኪሞች ስጋትና ጭንቀት በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ገለጸ። ትናንት ሐሙስ በተደረገ ምርመራ በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከፍተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሃዝ ተመዝግቧል። በዚህም ምርመራ ከተደረገላቸው 8,055 ሰዎች መካከል በሽታው በ2,057 ሰዎች ላይ መገኘቱን ኢኒስቲቲዩቱ ያወጣው መረጃ አመልክቷል። ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች ውስጥ 26 ወይም 25.5 በመቶው የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል በማለት \"በማኅበረሰብ አቀፍ የምርመራ ዘመቻ ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አልተመዘገበም\" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በኮቪድ-19 ክፉኛ ታመው በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ክትትል የሚደረግላቸው ሰዎች ቁጥርም ከዚህ በፊት ከተመዘገበው በበለጠ ከፍተኛው ቁጥር ላይ ደርሷል። በዚህም ሐሙስ ዕለት 600 ሰዎች በጽኑ የታመሙ ሰዎች እንዳሉ ተገልጿል። ከሰሞኑ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ \"በአስደንጋጭ ሁኔታ\" እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የሰጧቸው መግለጫዎች ያመለክታሉ። ቢሆንም ግን ወረርሽኙ እየፈጠረ ያለውን ከባድ አደጋ ከግንዛቤ በማስገባት ተገቢውን የመከላከያ ጥንቃቄ \"ከማድረግ ይልቅ መዘናጋት በሰፊው እንደሚታይ\" ቢቢሲ ያናገራቸው የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈባቸው የተለያዩ ስብሰባዎችና ዝግጅቶችን የታዘቡት የጤና ባለሙያዎች ችግሩ ሕብረተሰቡ ጋር ብቻ ሳይሆን መንግሥት የጤና ሚኒስቴር የሚያስቀምጣቸውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች \"ለማስፈፀም ተነሳሽነት ይጎድለዋል\" አስብሏቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበሽታው መስፋፋት እጨመረ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በወረርሽኙ የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከመድረሱ ባሻገር የጤና ተቋማት ህሙማንን ለማስተናገድ ፈተና እየገጠማቸው ነው። በዚህም ሳቢያ በመላው አገሪቱ በጽኑ ለታመሙ ሰዎች አጅጉን አስፈላጊ የሆኑት የኦክስጅንና የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እጥረት በመከሰቱ በርካታ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ህይታቸውን እንዲያጡ ሊያደርግ እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። \"በአንድ ጊዜ በርካታ ኦክስጅን የሚፈልጉ ህሙማን ወደ ህክምና ተቋማት ይመጣሉ\" የሚሉት ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ ኦክስጂን ባለመኖሩ ብቻ ህሙማን ወደ ቤታቸው ለመመለስ የሚገደዱበት ጊዜ ላይ መደረሱን ይናገራል። \"በርካታ ሰዎች በግላቸው የኦክስጂን ሲሊንደር እየገዙ ወደ ቤታቸው እየገቡ ነው\" በማለት፣ ሆስፒታል አልጋ ይዘው የሚታከሙም ቢሆኑ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለማግኘት ረዥም ወረፋ እንደሚጠብቁ ይገልጻሉ። በኮቪድ-19 ተይዘው በቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ ከሚደረጉት ባሻገር ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጡ ህሙማንን የመቀበል አቅማቸው እየተሟጠጠ መሆኑንም አልሸሸጉም። በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል የጽኑ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ህሩይ አርዓያ ለፋና እንደተናገሩት ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር እንዲሁም ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ታካሚዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው ብለዋል። የሚሊኒየም ኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ወደ ማዕከላቸው ከሚመጡ ሕሙማን መካከል ከ75 በመቶ በላይ ኦክስጅን የሚፈልጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በማዕከሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር መበርከቱን ገልፀው \"በመካኒካል ቬንትሌተር እጥረት ምክንያት የማንቀበላቸው ህሙማን ይኖራሉ\" ብለዋል። ዶ/ር ውለታው ጨምረውም የኦክስጅን እጥረት ስለገጠማቸው ድጋፉን ፈልገው የሚመጡ ሁሉንም ጽኑ ህሙማን ማስተናገድ አለመቻላቸውን ገልፀዋል። የጽኑ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ መጨመር እያሳየ መምጣቱን እነዳስተዋሉ የጠቆሙ ሲሆን፤ ዶ/ር ውለታው ጫኔም በበኩላቸው በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በኮቪድ-19 በጠና ታምመው ወደ ማዕከላቸው የሚመጡ ሰዎች በመርከቱን ተናግረዋል። በየተቋማቱ ለህሙማን አልጋ በመጥፋቱ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን የሚናገሩት ዶ/ር ብሩክ፣ ይህም በህክምና ባለሙያዎች ላይ ጫና መፍጠሩን አስረድተዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ-19 የተያዙ ሕሙማን እየበዙ በመምጣታቸው በሌላ የሕክምና ክፍል ያሉ አልጋዎችን እስከ መሻማት ተደርሷል። ዶ/ር ብሩክ በሚሰሩበት ህክምና ተቋም ከዚህ በፊት አንድ ታካሚ በኮቪድ-19 ተይዞ ኦክስጂን ባያስፈልገው እንኳን ተኝቶ ህክምና እንዲያገኝ ይደረግ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን አስተኝቶ ለማከም ህሙማኑ ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው መሆን አለመሆኑ ይወስነዋል ይላሉ። \"አሁን የምናስተኛቸው ታካሚዎች በሙሉ ኦክስጂን ፈላጊዎች ናቸው።\" እንደ ዶ/ር ብሩክ ከሆነ ሁሉም ተኝተው የሚታከሙ ሰዎች ኦክስጂን የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልጸው፤ በአሁኑ ጊዜም የኦክስጂን ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ብለዋል። ይህንን ሲያብራሩም በአሁኑ ጊዜ ተኝተው የሚታከሙ ህሙማን በሙሉ ኦክስጅን ፈላጊ ሲሆኑ የሚፈልጉት የኦክስጅን መጠን ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል። \"ከአምስት እና ከአስር ሊትር በላይ መጠን ያለው ኦክስጂን፣ የመተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ የሚፈልጉ ህሙማን ቁጥር ጨምሯል።\" ይህ የግብአት እጥረት በተወሰኑ ተቋማት ላይ ብቻ የታየ ሳይሆን ዶ/ር ብሩክ እንደሚሉት የኮቪድ-19 ህሙማንን በተለይ በሚያክሙት በሚሌኒየም እና ኤካ ኮተቤ ሆስፒታሎች ጭምር እንደሚስተዋል ከባልደረቦቻቸው ተረድተዋል። በተጨማሪም በግል ሆስፒታሎች የረር፣ ቤተዛታ፣ ሃሌሉያ የሚሰሩ ባለሙያዎችም ተመሳሳይ ነገሮችን ማስተዋላቸውን እንደነገሯቸው ይጠቅሳሉ። ዶ/ር ብሩክ እርሳቸው የሚሰሩበት ተቋም ከፍተኛ የኦክስጂን ተጠቃሚ ህሙማንን መቀበል የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም ይናገራሉ። ይህ የኦክስጂን እጥረት በአዲስ አበባ እና በክልል በሚገኙ ሆስፒታሎች እንደሚስተዋል የሚናገሩት ዶ/ር ብሩክ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንቅስቀሴ እያደረገ መሆኑን እንደሚያውቁ አስረድተዋል። ዶ/ር ብሩክ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቀነስ ከተቀመጡ መመሪያዎች ሁሉ ቢያንስ ቢያንስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀምን መጨመር በወረርሽኙ ስርጭት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ይመክራሉ። የበሽታው መስፋፋት ከዚህም በላይ እንዳይጨምር በግለሰብ ደረጃ የመከላከያ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር በርካታ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸውን ዝግጅቶችና ሥነ ሥርዓቶችን በተመለከተ የተቀመጡ መመሪያዎችን አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳስበዋል። አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ ተከስቶ ይሆን? ዶ/ር ብሩክ በሚሰሩበት እና በሌሎች የኮቪድ-19 ህክምና በሚሰጥባቸው ተቋማት የሚሰሩ ባልደረቦቹ ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች መጨመር አንዱ ምክንያት የጥንቃቄ ጉድለትና መዘናጋት ነው ይላሉ። በዚህ ወቅት እንዲህ በሽታው እንዲንሰራፋ ያደረገው ሌላም ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ጥርጣሬ አላቸው። \"ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ውስጥ እንደተደረገው በቫይረሱ ላይ ጥናት ቢደረግ አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሊኖር ይችላል\" ሲሉ ይሰጋሉ። ይህንንም ሲያስረዱ መጀመሪያ ላይ በኮቪድ-19 ተይዘው እና ታመው ወደ ህክምና ተቋማት ከሚመጣ ሰዎች መካከል ህመሙ የሚጠናባቸው በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው እንደነበሩ ይጠቅሳሉ። በተጨማሪም በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ሰው ታሞ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ሳይታመሙ ይገኙ እንደነበርም አስታውሰው፤ ምልክት የማያሳዩ ህሙማን ቁጥርም በርካታ እንደነበሩ ጠቅሰዋል። አሁን ግን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መታመማቸው፣ በእድሜም ሲታይ በርካታ ወጣቶች በበሽታው መያዛቸውና ወደ ህክምና ተቋማት መጥተው አልጋ መያዛቸውን ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቢኖሩም በሚሰጣቸው ህክምና በፍጥነት የማገገም ይታይባቸው እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ብሩክ፣ በዚያን ወቅት አልጋ ይዘው የሚቆዩ ሰዎች ቁጥር በጣም አነስተኛ ነበር ይላሉ። በአሁኑ ጊዜ የቫይረሱ የመተላለፍ አቅም እና የመግደል አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው \"በእርግጥ ጥናት ያስፈልገዋል፤ በእኔ እይታ አዲስ ዓይነት የቫይረስ ዝርያ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለኝ\" ብለዋል። ጨምረውም በዚህ ወቅት ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ሦስት ሰው የሚታመምበት እና አልጋ የሚይዝበት አጋጣሚ ተደጋጋሚ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ ይናገራሉ። ለበሽታው እንዲህ በአሳሳቢ ሆኔታ መስፋፋት ሁሉም ሰው ማድረግ ያለበት የመከላከያ ጥንቃቄን አለመተግበር መሆኑን ዶ/ር ውለታው ጫኔ እና ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። በአዲስ የወረርሽኙ ዝርያ ተከስቶ ሊሆን ይችላል የሚለው የዶ/ር ብሩክ ጥርጣሬ እነዳለ ሆኖ፤ ሁለቱም የህክምና ባለሙያዎች እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ተገቢው ምርመራ መደረግ እንዳለበት ይናገራሉ።", "እንግሊዛዊው 35 ኪሎግራም የሚመዝኑ ኩላሊቶቹ በቀዶ ህክምና ተወገዱለት በአንግሊዝ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ ሁለቱም ኩላሊቶች በከፍተኛ ደረጃ ትልቅ መሆናቸውን ተከትሎ እንዲወጡለት መደረጉን ሐኪሞች ተናገሩ። የ 54 ዓመቱ ዋረን ሂግስ በአጠቃላይ 35 ኪሎ ግራም የሚመዝኑትን የአካል ክፍሎቹን ለማስወገድ የሁለት ሰዓት ቀዶ ጥገና አድርጓል። ግለሰቡ ኩላሊቶቹ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ትልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ክብረ ወሰንም ይዟል ተብሏል የአንድ ወድ ልጅ አባት የሆነው እና ፖሊሲስቲክ የተባለ የኩላሊት በሽታ ያለበት ግለሰቡ \"በየትኛውም መንገድ ቢለካ\" ትልቅ ኩላሊት ያለው በመሆን ክብረ ወሰን እንደሚሰብር ሐኪሞቹ እንደነገሩት አስታውቋል። በሆዱ መጠን ላይ ያለውን ልዩነት \"አስገራሚ ነው\" ብሏል። ከእንግሊዟ ዊንድሶር የመጣው ሂግስ ትልቁ የቀኝ ኩላሊቱ 15 ኪሎ ሲመዝን ተጨማሪ 5 ኪሎ የሚመዝን ፈሳሽም በላዩ ላይ ነበር ብሏል። ቀደም ሲል በዓለም ላይ ትልቅ የነበረው ኩላሊት በሕንድ በቀዶ ጥገና የተወገደው እና 7.4 ኪ.ግ የሚመዝነው እንደሆነ ይታመን ነበር። \"የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ሁሉንም አረጋግጦ ነበር። እናም አዎ በእያንዳንዱ መለኪያ ክብረ ወሰኑን አሻሽለነዋል።\" ብሏል። \"ርዝመቱ በሚለካበት ጊዜ፣ ከያዘው ፈሳሽ ጋር ሲመዘን እና ፈሳሹ ከተወገደ በኋላም አሻሽዬዋለሁ።\" ያለው ግለሰቡ ሆኖም \"ይህ የምኮራበት ነገር አይደለም።\" ይላል ፒኬዲ በኩላሊት ውስጥ ሲስቲክ የሚባሉ ትናንሽ ፈሳሽ የተሞሉ ከረጢቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ከአምስት ዓመት በፊት በውርስ የሚመጣው ህመም ኩላሊቶቹ ከሚገባው በላይ አምስት እጥፍ እንዲያድጉ አድርጓቸዋል ሲሉ ዶክተሮቹ ተናግረዋል። ኩላሊቶቹ ሳንባውን፣ ሆዱን እና ልቡን መጉዳት ስለጀመሩ \"ሕይወት አድን\" ቀዶ ጥገና መደረጉ አስፈላጊ መሆኑ እንደተነገረው ሂግስ አስታውቋል። በተጨማሪ ትልቅ የሆድ እብጠት እንዲኖረው ምክንያት ሲሆን እብጠቱ ከሐምሌው ቀዶ ጥገና በኋላ \"አስደናቂ\" ለውጥ አምጥቷል ብሏል። ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት ወደ ጂምናዚየም የተመለሰ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመትም በኤሌክትሪክ ብስክሌት ትሪያትሎን (ሩጫ፣ ዋና እና ሳይክልን ያካተት ውድድር) ላይ ለመወዳደር በጉጉት እየተጠበቀ ነው። የቀድሞው የሂሳብ ባለሙያው በየሁለት ቀኑ የዲያሊሲስ ማድረጉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት መሆኑን ጠቅሷል። \"በዲያሊሲስ ማለፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መግለጽ አልችልም\" ብሏል። በሚቀጥለው ዓመት ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ብቁ ለመሆን በመዝገቡ ውስጥ እንደሚገባ ተስፋ ያደርጋል።", "ኮሮናቫይረስ ፡ በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ኮቪድ-19 የሚይዛቸውና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሆኗል። ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል። እስካሁን በቫይረሱ ከ186 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። በበሽታው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተያዙና ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተገኝተው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለሰዎች እየተሰጡ ይገኛሉ። ነገር ግን አሁንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ዋነኞቹ መንገዶች መሆናቸውን ባለሙያዎች አጥብቀው ይመክራሉ። በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ፣ ከበሽታው የሚያገግሙና በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን አሃዝ ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የኮሮናቫይረስ ሁለት ዋነኛ ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ እነዚህ ምልክቶች ወደ ትንፋሽ ማጠር ይወስዳሉ። ደረቅ ሳል ሲባል በጣም ጠንካራ የሆነ አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ ነው። ከዚህ በፊት ደረቅ ሳል ካለብዎ የኮሮናቫይረስ ሳል በጣም ለየት ያለና ከባድ መሆኑን ማስተዋል ይችላሉ። ከፍተኛ ትኩሳት የሚባለው ደግሞ የሰውነት ሙቀት መጠን ከ37.8 ዲግሪ ሴልሲየስ ሲልቅ ነው። ይህ ትኩሳት ሰውነት እንዲግል ወይም ደግሞ ከፍተኛ ብርድና መንቀጥቀጥ እንዲሰማን ያደርጋል። ከእነዚህ ሁለቱ ዋነኛ ስሜቶች ባለፈ ራስ ምታትና ተቅማጥ አንዳንድ የበሽታው ታማሚዎች ያሳይዋቸው ምልክቶች ናቸው። የማሽተትና የመቅመስ አቅም ማጣትም ምልክቶች ሆነው ተመዝግበዋል። ምልክቶቹ ቫይረስ ሰውነት ውስጥ በገባ በአምስት ቀናት ሊታዩ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ ምልክቶቹ እስከ 14 ቀናት ድረስ ሳይታዩ ሊቆዩ እንደሚችሉ ያስረዳል።", "ሰዎች ለምን ራሳቸውን ስለማጥፋት ያስባሉ? ራስን ማጥፋት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ትልቅ የሞት መንስኤ የሚታይ ጉዳይ ነው። በመላው ዓለም በሚገኙ ወጣቶች ዘንድም ሶስተኛው ትልቁ የሞት መንስኤ ራስን ማጥፋት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ቢያንስ 700 ሺህ ሰዎች ራሳቸውን የሚያጠፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከሶስት አራተኛው በላይ የሚሆኑት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች እንደሆነ ከኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ድረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በምስራቅ አፍሪካ አገራትም ራስን የማጥፋት አኃዝ በዓመት ከ100 ሺህ ህዝብ ከ5.02-15.71 እንደሚደርስ የተባበሩት መንግሥታትን ዋቢ አድርጎ ማህበሩ ከጥቂት ወራት በፊት ባወጣው ጽሁፍ አመልክቷል። በኢትዮጵያ ያለው አመታዊ ራስን የማጥፋት መጠን መካከለኛ እንደሆነ የሚጠቅሰው በድረ-ገጹ የወጣው ፅሁፍ በዓመት ከ100,000 ህዝብ 9.63 ሲሆን ይህም ማለት በየቀኑ 30 ሰዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ ማለት ነው። እዚህ ጋር በጉዳዩ ላይ በቂ በሚባል ደረጃ ጥናቶችና ምርምሮች አለመደረጋቸው እንዲሁም ማህበረሰቡ ስለ ጉዳዩ ያለው እውቀት ዝቅተኛ መሆኑና እንደ ችግር የሚወራ ባለመሆኑ የበርካቶች ሞት መንስኤ ሳይወራ ወይም ተደብቆ ያልፋል። አንድ የቤተሰብ አባል እራሱን ሲያጠፋ ማህበረሰቡ ሰዎች ምን ይሉኛል? በሚል ፍራቻ የሞቱን መንስኤ ይደብቃል አልያም ሌላ ምክንያት ለመስጠት ይሞክራል። ይህ ደግሞ ችግሩን ይበልጥ ያባብሰዋል። ስለጉዳዩ በግልጽ አለመወራቱ አንድ ሰው እራሱን ሲያጠፋ ሰዎች ለምን ብለው እንዳይጠይቁና ከሌሎች ተሞክሮዎች እንዳይማሩ ያደርጋቸዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ መምህር የሆኑት ዶክተር ኤሊያስ ገብሩ እንደሚሉት ምንም እንኳን በቂ በሚባል ደረጃ ጥናቶች ባይሰሩም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሐይማኖቶች ጠንካራ አማኞች ባሏቸው አገራት እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያቱ በእስልምናም ሆነ በክርስትና ሐይማኖቶች እራስን ማጥፋት እንደ ሀጢያት መቆጠራቸው ነው። በሌላ በኩል ራስን ማጥፋት በሁሉም ሐይማኖቶች መከልከሉ ሰዎች እራሳቸውን ሲያጠፉ የተጎጂ ቤተሰቦች ጉዳዩን ለሰዎች እንዳያጋሩና እንዲደብቁት ያደርጋቸዋል። በአጠቃላይ የኮቪድ-19 ወረርሽን ተከትሎ እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ ጨምሮ እንደነበር የሚገልጹት ዶክተር ኤልያስ ፣ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ይፋዊ የሆነ ጥናት ባይካሄድበትም እንደ ባለሙያ ሲታይ ግን ቀላል የማይባሉ ሰዎች ወረርሽኙን ተከትሎ እራሳቸውን ስለማጥፋት አስበዋል፣ ሞክረዋል አልያም ራሳቸውን አጥፍተዋል ይላሉ። ''እኔ ባለሁበት አካባቢ እንኳን 7 የሚሆኑ ወጣቶች በሁለት ወር ውስጥ እራሳቸውን አጥፍተው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች የማያወሯቸውና ሌሎች ሰዎች ሊሰሟቸው የማይችሉ በርካታ ሞቶች ሊመዘገቡ እንደሚችሉ መገመት ቀላል ነው'' ሰዎች እራሳቸውን ወደማጥፋት የሚገፋቸው ምንድነው? ባለሙያው እንደነገሩን እራሳቸውን ከሚያጠፉ ሰዎች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ጊዜያዊም ሆነ ቀጣይነት ባለው የስነ አእምሮ ጤና መቃወስ ተጠቂ ናቸው። ስለዚህ እራስን ማጥፋት አልያም ስለማጥፋት ማሰብ አብዛኛውን ጊዜ ከስነ አእምሮ ጤና ጋር የተያያዘ ነው ማለት እንችላለን። ለመሆኑ የትኞቹ የአእምሮ ጤና መቃወሶች ናቸው ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ አልያም እራሳቸውን ስለማጥፋት እንዲያስቡ የሚያደርጋቸውን ስንል ለዶክተር ኤልያስ ጥያቄ ሰነዘርን። ''በተለይ ከፍተኛ ድብርትና ጭንቀት ሰዎችን ወደዚህ መስመር የሚገፉ ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው። እነዚህን የአእምሮ ጤና እክሎች በአግባቡ መረዳትና ማከም ስንችል እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ እንችላለን።\" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ከፍተኛ ድብርት ምክንያት የሌለው ጭንቀት፣ የባዶነት ስሜት፣ ደጋግሞ እራስን መውቀስ፣ ምንም የማልጠቅም ሰው ነኝ እያሉ ማሰብ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የሚረዳኝ ሰው የለም ብሎ ማሰብ፣ ከባድ ድካምና አቅም ማጣት፣ የእንቅልፍ መዛባት (ብዙ መተኛት አልያም እንቅልፍ ማጣት)፣ ስራና የግል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማጣት እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋነኛ ምልክቶቹ ናቸው። በሌላ በኩል ከባድ ጭንቀት በዋነኛነት የወደፊቱን ነገር ካለማወቃችን ጋር ተያይዞ ምን ይፈጠር ይሆን እያልን የምንጨነቀው ነው። በአንድ ጊዜ ስለብዙ ነገሮች አብዝቶ መጨነቅ፤ ነገን እንዴት ነው የምሆነው ብሎ ሌሎች ስራዎችን ትቶ ቁጭ ብሎ ማሰብና ሕይወታችንን እስከ ማወክ ሊደርስ ይችላል። እነዚህ የአእምሮ ጤና እክሎች ደግሞ በሰዎች የስራ ሕይወት፣ ትምህርት፣ የፍቅር ግንኙነት እንዲሁም ከቤተሰብና ጓደኞች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት በእጅጉ ያበላሸዋል። ከባድ ጭንቀትና ከባድ ድብርት አብዛኛውን ጊዜ ተያይዘው የሚመጡ ነገሮች ሲሆኑ በአግባቡና በጊዜ ካልታከሙ ደግሞ ሰዎችን እራስን ማጥፋት ወደሚለው ጎዳና ሊመሩ ይችላሉ። የትኞቹ የማህበረሰብ አባላት ተጋላጭ ናቸው? ዶክተር ኤልያስ እንደሚሉት ከእድሜ አንጻር አፍላ እድሜያቸው ላይ የሚገኙ ወጣቶችና በአርባዎቹና ሀምሳዎቹ ውስጥ የሚገኙ ጎልማሶች አካባቢ እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር ከፍ ይላል። በተለይ በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች ማንነታቸውን ማወቅ የሚጀምሩበትና በርካታ የሕይወት ጥያቄዎችን መመለስ የሚጀምሩበት ወቅት መሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ''ታዳጊዎች ላይ የምናያቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ። ታዳጊዎች 20 ዓመት እስከሚሞላቸው ድረስ እራሳቸውን የሚያገኙበት፣ ማንነታቸውን የሚቀርጹበት ጊዜ እንደመሆኑ ብዙ ጊዜ ግራ መጋባት ውስጥ ሊከታቸው ይችላል። ከትምህርት፣ ከቤተሰብ ግንኙነት፣ ከጓደኞች እንዲሁም ከተቃራኒ ጾታ ግንኙነት አንጻር ብዙ አይነት መቀያየሮችና ግራ መጋባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ'' እነዚህን መቀያየሮችና እራስን የማግኘት ሂደት ውስጥ ደግሞ ታዳጊዎች ስሜታዊ መሆን፣ ራሳቸውን መቆጣጠር አለመቻል፣ ቶሎ ተስፋ መቁረጥ እንዲሁም ማንም ሰው አይረዳኝም ብሎ ማሰብ ውስጥ ይገባሉ። ታዳጊዎች በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ ብዙ ነገሮችን ይሞክራሉ፤ ይጠይቃሉ። እነሱ በሚገባቸውና በሚረዱት ልክ መልስ የማያገኙ ከሆነ ደግሞ የህይወት ትርጉሙ ሊጠፋባቸውና ከዚህ ሁሉ ጭንቀት ብገላገልስ የሚል አስተሳሰብ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ''ይህ የእድሜ ክልል ከማህበረሰቡ ከፍተኛ ክትትልና ተጽዕኖ የሚደረግበት ነው። በተጨማሪ ደግሞ በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች ከጓደኞቻቸውና ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር ከራሳቸው በላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ነገር ነው። በአጭሩ በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች በቀላሉ ተፅእኖ ውስጥ ይገባሉ። በራሳቸው ብዙ ነገሮችን መወሰን አይችሉም''ይላሉ። ይህንን ተከትሎ አንድ አስጨናቂና ከእነሱ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው በቶሎ ተስፋ የመቁረጥና ራስን ወደ ማጥፋት ሊያመሩ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የእድሜ ክልል ጥቂት የማይባሉ የአእምሮ ህመሞች እራሳቸውን የሚገልጡበት ወቅት ነው። በዘር የሚመጡት ህመሞችም ሆነ ሌሎች የአእምሮ ህመሞች በትክክል ህመም ሆነው መታየት የሚጀምሩት በዚህ እድሜ ውስጥ ነው። ሌላ መረሳት የሌለበት ጉዳይ ብለው ዶክተር ኤልያስ ያነሱት ጉዳይ ደግሞ ወጣቶች በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ በራሳቸውም ሆነ በጓደኞቻቸው ገፋፊነት ወደተለያዩ ሱሶች ውስጥ መግባታቸው አስተዋጽኦ እንዳለው ነው። ከታዳጊዎች ጋር በተገናኘ በተለይ ወላጆችና ማህበረሰቡ በእዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆችን በአግባቡ መረዳትና በተቻለ መጠን ድጋፍ ማድረግ ያለበት ወቅት እንደሆነ ዶክተር ኤልያስ ያሳስባሉ። ''እነዚህ ታዳጊዎች የራሳቸው ፈቃድ እንዳላቸውና በራሳቸው ነገሮችን ማመዛዘን እንደሚችሉ ማህበረሰቡ መረዳት አለበት። ያለአግባብ አዳዲስ ነገሮችን እንዳይሞክሩ መከልከልና ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ እንዲያውም ወዳልሆነ ውሳኔ እንዲሁም ባህሪ ነው የሚገፋቸው'' ይላሉ። አክለውም '' በህይወታቸው የራሳቸውን መንገድ እንዲያገኙ መደገፍና ትክክለኛውን አካሄድ ማሳየት ነው እንጂ በጭፍን መከልከልና እኛ የምንለውን ነገር ብቻ አድርጉ ማለት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊዎች ነጻነትና እምነት ወሳኝ ናቸው'' በማለት ያስረዳሉ። ታዳጊዎች አእምሯቸው እያደገና ጥያቄዎችን መጠየቅ ሲጀምሩ በተለይ ከሃይማኖት፣ ትምህርት፣ የፍቅር ግንኙነትና የወደፊት እቅዶች ጋር በተያያዘ ብዙ ግራ መጋባት ውስጥ ይወድቃሉ። ቤተሰብና ማህበረሰቡ ይህንን ተረድቶ ተገቢውን ድጋፍ ባላደረገላቸው ቁጥር ነገሮች እንዳሰቡት ሳይሆኑ ሲቀሩ በቶሎ ተስፋ መቁረጥና እጅ መስጠት ውስጥ ይገባሉ። ሌላኛው ራስን በማጥፋት ትልቅ ቁጥር የሚመዘገብበት የእድሜ ክልል የጎልማሶች ነው። በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በህይወታቸው ባደረጓቸው ነገሮች ደስተኛ አለመሆንና ቁጭት ይስተዋልባቸዋል። ''ወደ ኋላ መለስ ብለው ህይወታቸውን የመቃኘትና ሀዘን ውስጥ መግባት ይስተዋላል። በውሳኔዎቻቸው መጸጸትና ከፍተኛ ጭንቀትና ድብርት ውስጥ መግባትም ይታይባቸዋል'' የማህበረሰብ ኃላፊነት ዶክተር ኤልያስ እንደሚሉት ሰዎች ራሳቸውን ሊያጠፉ የሚችሉት አልያም ራሳቸውን ስለማጥፋት የሚያስቡት በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው ከላይ በተጠቀሱት ሌሎች የአእምሮ ጤና መታወክ ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድንገተኛ የሆነ አሳዛኝ ወይም አስደንጋጭ ክስተት ሲያጋጥም ነው። ''በሆነ አጋጣሚ ከሰዎች ጋር ሲጣላ ወይም የሚያስጨንቅ ነገር ሲያጋጥማቸው በቃ እኔ ብሞት ይሻለኛል። ምንም የማልጠቅም ሰው ነኝ የሚሉ ሰዎች ስናገኝ በቀላሉ ማለፍ የለብንም። ጓደኞችም ሆነ ቤተሰቦች ቀርበው ለምን መሞት እንደሚፈልግ ወይም ብዙ ጊዜ ስለመሞት ያስብ እንደሆነ መጠየቅና መረዳት አለባቸው። መርዳት በሚችሉት ሁሉ መንገድ ለመርዳት መጣር ኃላፊነታቸው ነው'' ''በማህበረሰባችን ውስጥ እንደ ቀልድ የሚባሉ ለምሳሌ ፈጣሪዬ ውሰደኝ በቃ፤ የኔ ሕይወት ትርጉም የለውም አይነት ንግግሮችን ሰዎች ሲያዘወትሩ በጊዜያዊ ንዴት ውስጥ ሆነው ነው ወይስ የምር መሞት ይፈልጋሉ ብለን ማጣራት አለብን'' ሲሉ ያሳስባሉ። በሌላ በኩል ከዚህ በፊት እራሱን ለማጥፋት ሞክሮ የሚያውቅ ሰው ከሆነ ቤተሰብም ሆነ ሌሎች የቅርብ ሰዎች ሁሌም ቢሆን በንቃት መጠበቅ አለባቸው። ግለሰቡ ከሌላ ጊዜው በተለየ መልኩ የጸባይ መለዋወጥ፣ ዝምታ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ጭንቀት የሚያበዛ ከሆነ ቀረብ ብሎ መጠየቅና በግልጽ ማውራት እጅግ ጠቃሚ እንደሆኑ ባለሙያው ያስረዳሉ። የሚወዱትን ሰው ያጡ ሰዎች፣ ሀብት ንብረታቸው የጠፋባቸው ሰዎች ወይም ከፈተና የወደቁ ተማሪዎች እራስን ስለማጥፋት የማሰብ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ሊከታተሏቸው ይገባል። ለምሳሌ አንድ ፈተና የወደ ተማሪ ወደ ሱቅ ሄዶ ገመድ አልያም በረኪና ለመግዛት ቢሞክር ባለሱቆች እንኳን የተማሪውን የፊት ሁኔታ ማጤንና ለምን እየገዛው እንደሆነ መጠየቅ አለባቸው።", "ኮሮናቫይረስ፡ የአውሮፓ ሕብረት አስትራዜኔካ የተሰኘው ክትባት የደም መርጋት አያመጣም እያለ ነው ኮቪድ-19 እንዲከላከል ተብሎ የተሠራው የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል የተባለው ሃሰት ነው ሲል የአውሮፓ ሕብረት አስታወቀ። መግለጫውን ያወጣው የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው። ባለሥልጣኑ እንደሚለው የደም መርጋት የታየባቸው የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ካልተከተቡ ሰዎች ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው። የአውሮፓ ሕብረት ይህን ማለት ያሻው ዴንማርክና ኖርዌይን ጨምሮ አንዳንድ ሃገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው መስጠት ማቆማቸውን ተከትሎ ነው። ሃገራቱ ክትባቱን መስጠት ያቆሙት ጥቂት ሰዎች ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ምልክት አሳይተዋል ተብሎ ነው። አንድ የ50 ዓመት ጣልያናዊ ክትባቱን ከወሰደ በኋላ 'ዲፕ ቬይን ትሮሞቦሲስ' [ከደም መርጋት ጋር ተያያዥነት ያለው] የተሰኘ በሽታ ታይቶበት ሞቷልም ተብሏል። \"በአሁኑ ወቅት ክትባቱና የደም መርጋት ግንኙነት እንዳላቸው የሚያሳይ ነገር የለም። የደም መርጋትም የክትባቱ ጎንዮሽ ጉዳት አይደለም\" ብሏል የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ። \"ክትባቱ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል። ስለዚህ ታዩ የተባሉትን ጉዳቶች እየመረመርን ክትባቱን መስጠት እንቀጥላለን\" ብሏል ኤጀንሲው። ኤጀንሲው እንደሚለው አውሮፓ ውስጥ ክትባቱን ከወሰዱ አምስት ሚሊዮን ሰዎች መካከል 30 ሰዎች የደም መርጋት ምልክት ታይቶባቸዋል። አስትራዜኔካ በቃል አቀባዩ አማካይነት የክትባቱ ደህንነት በብዙ ምርምርና ፈተና የተረጋገጠ ነው ብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም የመድኃኒት ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ክትባቱን ከደም መርጋት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም ብሏል። ስለዚህ ሰዎች በተጠየቁ ጊዜ ሄደው ክትባቱን እንዲወስዱ እንመክራለን ይላል። \"የደም መርጋት ክትባት ባይኖርም የሚከሰት ነገር ነው። አዲስ ነገር አይደለም። እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች ዩኬ ውስጥ ተሰጥተዋል\" ይላሉ የባለሥልጣኑ ሠራተኛ የሆኑት ፊል ብራያን። በክትባት መዘግየት ምክንያት ችግር ላይ የነበረው የአውሮፓ ሕብረት አሁን ደግሞ አስትራዜኔካ ክትባትን በተመለከተ የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ ዜናዎች ማነቆ ሆነውበታል። የአውሮፓ ሕብረት አሁን ፊቱን ወደ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ወደተሰኘውና አንድ ጊዜ ብቻ ወደሚሰጠው ክትባት ማዞር የፈለገ ይመስላል። \"ደህንነታቸው ይበልጥ አስተማማኝ የሆኑ ክትባቶች ወደ ገበያው እየመጡ ነው\" ብለዋል የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኧርስላ ቮን ደር ለየን። ከዚህ አልፎ ኖቫክስ የተሰኘው ክትባት ዋናውን የኮቪድ ዝርያ በመከላከል ረገድ 96 በመቶ አዲሱን ዝርያ ደግሞ 86 በመቶ ውጤታማነት ማሳየቱ ተነግሯል። ዴንማርክና ናሮዌይ የአስትራዜኔካን ክትባት መስጠት ሙሉ በመሉ ሲያቆሙ ኦስትሪያና ጣሊያን ደግሞ አንዳንድ ብልቃጦችን ማስወገድ ይዘዋል። ኢስቶኒያ፣ ላትቪያ፣ ሊቱኔያ እንደ ላግዘምበርግ ልክ እንደ ኦስትሪያ ለጊዜው የተወሰኑ የአስትራዜኔካ ክትባቶችን መስጠት አቁመዋል።", "ኮሮናቫይረስ፡አማዞን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞቹ በኮሮና እንደተያዙ አስታወቀ አማዞን ኩባንያ 19 ሺህ 816 ሰራተኞቹ በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ገልጿል። ይህ ቁጥር ከመጋቢት ወር ጀምሮ የተመዘገበ ሲሆን በአሜሪካ ያሉት ሰራተኞቹም ናቸው። በአጠቃላይ ኩባንያው 1.37 ሚሊዮን ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በኮሮናቫይረስ የተያዙትም ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ቁጥር ጋር ሲሰላ 1.44 በመቶ ነው ተብሏል። የኩባንያው ሰራተኞች፣ የሰራተኛ ማህበራትና ኃላፊዎችም የሰራተኞችን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል በሚልም ኩባንያው ከፍተኛ ትችት እየቀረበበት ነው። ሆኖም ኩባንያው በበኩሉ በቫይረሱ የተያዙት ሰራተኞች ቁጥር ከተጠበቀው በታች ነው ብሏል። ኩባንያው ባወጣው መግለጫም በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ከግምት ውሰት በማስገባት 33 ሺህ 952 ሰራተኞቹ በቫይረሱ እንደሚያዙ ጠብቆ እንደነበር አስታውቋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ኩባንያዎች ለተወሰነ ጊዜ ስራቸውን ቢያቆሙም አማዞን በበኩሉ የትኞቹንም ቅርንጫፎች አልዘጋም። በዚህ ወረርሽኝ ወቅትም ትርፋማ ከሆኑት ኩባንያዎች አንዱ መሆን ችሏል። አገራት ወረርሽኙን ለመግታት በሚል ያወጧቸውን መመሪያዎች ተከትሎ በርካቶች ቤታቸው በመቀመጣቸው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ግብይይት ሁነኛ አማራጭ ሆኗል። ይህም ሁኔታ ለግዙፉ ኩባንያ አማዞንና በአለም አንደኛ ለሆነው ባለቤቱ ጄፍ ቤዞ በትርፍ ላይ ትርፍ ሆኖለታል። በባለፉት ሶሰት ወራትም ውስጥ ኩባንያው 40 በመቶ ሽያጩ ጨምሯል። ከመጋቢት እስከ ሰኔ ወራት ባሉትም 88.9 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭን ሲያስመዘግብ፣ ከዚህም ውስጥ 5.2 ቢሊዮን ዶላሩ ትርፍ ነው። ኩባንያው ከተመሰረተበት ከጎሮጎሳውያኑ 1994 ጀምሮም እንዲህ አይነት ትርፍ አስመዝግቦ አያውቅምም ተብሏል።", "በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶሮዎችን የገደለው በሽታና የተጣለው የገበያ እግድ ከሰሞኑ የዶሮ እርባታ ማዕከል በሆነችው በቢሾፍቱ፣ በአዲስ አበባና በአንዳንድ አጎራባች አካባቢዎች በተከሰተ ያልታወቀ የዶሮ በሽታ በበርካታ ሺህ የሚቆጠሩ ዶሮዎች መሞታቸውን ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር ዶሮና የዶሮ ውጤቶች ለገበያ እንዳይቀርቡ ሰኔ 03/2014 ዓ.ም እግድ ጥሏል። በአንዳንድ የዶሮ እርባታ ጣቢያዎች ውስጥ መቶ በመቶ በሚባል ሁኔታ ዶሮዎችን ገድሏል የተባለው ያልታወቀ የዶሮ በሽታ፣ ምንነትና መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ዶሮ፣ ጫጩቶችና እንቁላሎች ከተለያዩ ክልሎች ማጓጓዝ አይቻልም። በተጨማሪም ዶሮ አርቢዎች ዶሮና የዶሮ ውጤቶችን ለገበያ ማቅረብ እንደማይችሉ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተለይ በሽታው በዋነኝነት በተከሰተባቸው በቢሾፍቱ፣ በአዲስ አበባና በአጎራባች አካባቢዎች ዶሮና የዶሮ ውጤቶችን ማጓጓዝ እንዲሁም ከውጭም ማስገባትም ሆነ ወደ ውጭ መላክ አይቻልም። በሽታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች ብቻ ተወስኖ እንዲቀርና ወደሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት የእንቅስቃሴው ገደብ እንደተጣለ የሚናገሩት ዶክተር ፍቅሩ፣ ለተለያዩ ክልሎችም የየራሳቸውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። በአሁኑ ጊዜ መጀመሪያ ላይ እንደነበረው የዶሮዎች ሞት እየተከሰተ እንዳልሆነና የመቀነስ አዝማሚያ እንዳሳየ የሚናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው ሆኖም ሙሉ በሙሉ አለመገታቱን አመልክተዋል። ይህንንም ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈለፈሉ ጫጩቶች፣ እንዲሁም የደረሱ እንቁላሎች ለገበያ እንዳይውሉ እግድ በመጣሉ በርካታ ዶሮ አርቢዎች ለችግር ተጋልጠናል ብለዋል። የዶሮ በሽታው የተከሰተው ከሳምንት በፊት ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የተሻሻለ የዶሮ እርባታ ያላቸው በሚባሉት ስፍራዎች በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በአጎራባች አካባቢዎች መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል። የበሽታው መዛመትም ከቢሾፍቱ እስከ አዳማ ባለው ኮሪደር በስፋት ተከስቶ የነበረ መሆኑንም ብርሃኑ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ምንም እንኳን የዶሮ በሽታዎች በተደጋጋሚ ቢከሰቱም በሽታው በፍጥነት የመተላለፍና የመዛመት ባህርይ በማሳየቱ እንዲሁም በገባባቸው የዶሮ እርባታ ማዕከላት በብዛት እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ዶሮዎችን መግደሉን ዶክተር ፍቅሩ ይናገራሉ። በተለይም ያጠቃው አነስተኛ እና መካከለኛ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ሲሆን ሁሉም ዶሮዎች ያለቁባቸው ማርቢያዎችም ታይተዋል። እስካሁን ባለው መቶ ሺህ ወይም ከዚያ በላይ ዶሮዎች ሞተዋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተጣራ መረጃ ላይ እንዳልደረሰና ገና ስለሁኔታ ግምገማም እያደረገ ነው። “በዚህ አይነት ፍጥነት መዛመቱና ዶሮዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መግደሉ ስጋት ፈጥሯል። ዝም ከተባለም ከአንድ እርባታ ማዕከል ወደ ሌላ እርባታ ማዕከል የመዛመት ሁኔታ ሲያሳይ ወደ እንቅስቃሴ ገደብ ገብተናል” ይላሉ ዶክተር ፍቅሩ። ከሰሞኑ የተከሰተው ያልታወቀ የዶሮ በሽታ ትልልቅ የዶሮ ማርቢያዎችን ያላጠቃ ቢሆንም፣ እነዚህ ማዕከላትም ቢሆን ዶሮና የዶሮ ግብዓቶች ማጓጓዝም ሆነ መሸጥ አይችሉም። የእንስሳት ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ደመቀ ወንድማገኝ መንግሥቴ፣ በሽታው በአነስተኛና በመካከለኛ ዶሮ እርባታ ማዕከል ያስከተለውን ከፍተኛ ሞት በማየት ክስተቱ ከበድ ያለ ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። በሽታው ሁሉንም አይነት ዶሮዎች፣ ጫጩቶችን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ሞት በማድረሱና ሰፊ ቦታ በመሸፈኑ የዶሮ በሸታ ወረርሽኝ ሊባል እንደሚችል ዶክተር ደመቀ ያስረዳሉ። አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው በሽታው እያጠቃ ያለው በበለጠ የእንቁላል ዶሮዎችን እንደሆነና ጫጩቶችን ወይም የሥጋ ዶሮዎችን እየገደለ እንዳልሆነ ይገልጻሉ። እስካሁን ስለበሽታው የታወቀ ነገር ስለሌለ ምንነቱን ለመለየት የግብርና ሚኒስቴር የምርምር ሥራዎችን በዋነኝነት እያከናወነ ይገኛል። ሆኖም በተደረገው ዳሰሳና ከበሽታው ባህርይ በመነሳት በንክኪ ስለሚተላለፍ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በኦሮሚያ ክልል የዶሮና የዶሮ ውጤቶች ገቢም ሆነ ወጪ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ውሳኔ ተላልፏል። ለዚህ ውሳኔ ምክንያቱም አንዳንድ አርቢዎች ዶሮዎች ሲታመሙባቸው ከማስወገድ ይልቅ የመሸጥ ሁኔታ በመታየቱና በሌሎች ስፍራዎች ተዛምቶ በአጠቃላይ በአገሪቱ የዶሮ እርባታ ዘርፍን እንዳይጎዳ በሚል የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ሚኒስትር ዲኤታው ይጠቅሳሉ። አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው ጠበቅ ያለና ሙሉ እገዳ ነው የተጣለው ያሉ ሲሆን፣ እሳቸውም ሲጠቅሱ በኢትዮጵያ ደረጃ ከክልል ወደ ክልል ዶሮና የዶሮ ግብዓቶችን እንቁላልና ጫጩቶችን ማጓጓዝ አይቻልም። ከዶሮና የዶሮ ውጤቶች በተጨማሪ ከዶሮ ጋር ንክኪ የሚኖራቸውን መገልገያዎችን መኖን ጨምሮ ማጓጓዝ እንደተገደበ ያስረዳሉ። ከዚህ ባለፈ ዶሮ፣ ጫጩቶች፣ ቄቦች፣ የዳበረ (የለማ) እንቁላል ከውጭ አገራትም እንዳይገቡ እንዲሁም ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳው ይከለክላል። ለገበያ ማቅረቡም ሆነ የእንቅስቃሴ ገደቡ በሽታው ተለይቶ በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስም የሚቀጥል እንደሚሆን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተገልጿል። ባለፈው ሳምንት የሞት መጠኑ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፉት ቀናት ግን ጋብ የማለት ምልክት እንዳሳየም ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ፍቅሩ፣ አቶ ብርሃኑ እንዲሁም ዶክተር ደመቀ ያስረዳሉ። “ሞት ቆሟል ማለት በሽታው አይዛመትም ማለት ስለማይቻል፣ ምን አይነት ተፅእኖ እንደሚያመጣ ስለማይታወቅ፤ የኅብረተሰብ ጤና ጉዳይም ስለሚኖረው ያንን ማጣራት ያስፈልጋል” ይላሉ ዶክተር ደመቀ። ሆኖም በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና አጎራባች አካባቢዎች ያሉ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቻቸውን ማጓጓዝ እና ለገበያ ማቅረብ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገናል ይላሉ። በተለይም አቶ ብርሃኑ እንደሚናገሩት አብዛኞቹ አነስተኛ የዶሮ አርቢዎች በመሆናቸው ከዶሮ ምርታቸው በሚያገኙት ገቢ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው ከፍተኛ ጉዳት አስከትሎባቸዋል። በዶሮዎች ላይ ከተከሰተው በሽታ ጋር በተያያዘ በተጣለው ገደቡ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ 40 ሺህ የሚሆኑ ጫጩቶች በአንድ የእርባታ ስፍራ ተቀብረዋል ይላሉ። አቶ ብርሃኑ እንደሚሉት አንዳንድ ማዕከላት ዋነኛ ተግባራቸው ጫጩት እያስፈለፈሉ መሸጥ ስለሆነ ይህም በሺዎች የሚቆጠሩ ጫጩቶች ያስፈለፈለው ማዕከል ማጓጓዝ ባለመቻሉ ለማስወገድ ተገዷል። ሌላኛው አቶ ብርሃኑ የሚጠቅሱት የዶሮ እርባታና ማቀናበሪያ ማዕከል መፈልፈል የነበረባቸው 50 ሺህ እንቁላሎች እንደያዘ በመቆየቱ ከጥቅም ውጪ እንደሚሆን ነው። በተጨማሪም ከውጭ አገራት በዶላር ከፍተኛ ክምችት አስገብተው እንቁላል መፈልፈልና መሸጥ ቢኖርባቸውም እነዚህ ማዕከላት ይህንን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውንም ያስረዳሉ። በርካታ የዘር እንቁላሎችም ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ይህ ሁኔታ አርቢዎችን በተለይም አነስተኛ አርቢዎችን ከሥራ እያስወጣ መሆኑንም ይገልጻሉ። ሌላኛው የሚያነሱት ችግር እነዚህ አርቢዎች ከሚያገኙት ገቢ መኖ መግዛት ባለመቻላቸው፣ እገዳው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ዶሮዎቹ በረሃብ ያልቃሉ የሚል ስጋትም ተጋርጦባቸዋል። “ዶሮዎቹ ከበሽታው በበለጠ በረሃብ ሊያልቁ ይችላሉ” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። የአገሪቱን ከሃምሳ በመቶ በላይ የሆነ የእንቁላል አቅርቦት የሚይዙት አነስተኛ አርቢዎች ናቸው የሚሉት አቶ ብርሃኑ፣ ከሞቱ በላይ ምርት አለመሸጥ ከፍተኛ ጉዳት ስላላው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ያስረዳሉ። “ነገ ከነገ ወዲያ የእነዚህ የዶሮ እርባታ ማዕከላት ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። ቅሬታቸውንም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በአጭር ጊዜም መፍትሄ ያገኛል የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በርካታ አባሎቻቸውም ከፍተኛ ቅሬታ እያነሱ ሲሆን አፋጣኝ ጥናት ተደርጎ በሽታው ከተለየና ሌላ ችግር የማያስከትል ከሆነ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ወደ ሥራ የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንደሚፈልጉ አመልክተዋል። ለአቶ ብርሃኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጣላቸው የእንቅስቃሴ ገደቦች ከባድ የሚባሉ መሆናቸውን ነው። በተጨማሪም በሽታው የከፋ ስጋት እንደማይደቅን ከሚጠቅሷቸው ምክንያቶች ዋነኛው ወደ ሰው አለመተላለፉን ነው። የበሽታው ምንነት በአሁኑ ወቅት እየተመረመረ ቢሆንም ሚኒስትሩም ሆነ አቶ ብርሃኑ በሽተኛ ዶሮዎችን ሲንከባከቡ ከነበሩ ግለሰቦች እንዲሁም በማዕከላቱ ከተደረገው አሰሳ ወደ ሰው እንደማይተላለፍ ነው። በሽተኛ ዶሮዎችን ሲንከባከቡ የነበሩ ግለሰቦች ምንም አይነት የህመም ምልክት አላሳዩም። ሌላኛው አቶ ብርሃኑ የሚጠቅሱት ምክንያት በአንዳንድ የእርባታ ማዕከላት አቅራቢያቸው ያለው ማዕከል በበሽታ ቢጠቃም ወደሌሎች አለመዛመቱ ሌላው የሚጠቅሱት ምክንያት ነው። በተጨማሪም በባለፉት ሦስት እና አራት ቀናት ሞት እንዳልተከሰተ፣ በሽታውም የለም በሚባልበት ደረጃ ላይ እንዳለ እንዲሁም በትልልቅ የማራቢያ ማዕከላት ባለመከሰቱ መሆኑ ሌላኛው በጎ ምልክት ነው ይላሉ። በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ ባሉ ጣቢያዎች መከሰቱ የጥንቃቄ መላላት (ባዮ ሴኩሪቲ ደካማ) መሆን ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ሲሉም ይጠቁማሉ። “በሽታ አለ። ዶሮ ሁልጊዜም ከበሽታ ጋር ነው የሚኖረው። ለሰው ጤና ጉዳት የማያመጣ ከሆነ ሌላውን በክትባትም እየተቋቋምን መኖር እንችላለን። ለምሳሌ ኒውካስትል የሚባለው የዶሮ በሽታ 70 አስከ 80 በመቶ ገዳይ ነው። ይህም ተመሳሳይ በሽታ ከሆነ ማዕከላቱ ጥንቃቄ እያደረጉ ወደ ሥራ መመለስ ይኖርባቸዋል። አሁን በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ ናቸው” ይላሉ። ሚኒስትሩ የተጣሉት ገደቦች ከባድ ነው በሚለው አይስማሙም “ከባዱ ነገር ዶሮዎቹ ማለቃቸው ነው” ይላሉ። ምንነቱ ያልታወቀው በሸታ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የማርቢያ ማዕከላት ተዛምቶ ዶሮዎችን ቢጨርስስ? ብለው የሚጠይቁት ሚኒስትር ዲኤታው በአጠቃላይ የዶሮ እርባታና ማቀናበር ሥርዓቱን ሊገድል ይችላል ይላሉ። ሆኖም በዶሮ አርቢዎች ላይ ያለውን ተፅእኖና ኪሳራ እንደሚረዱ ገልጸዋል። “ወደን ሳይሆን ከመጥፎው የተሻለ መጥፎን መምረጥ ነው። ለጊዜው እንቁላሉንም ሽያጩንም ያዝ አድርገው እኛ ደግሞ የተከሰተባቸው ቦታዎች ላይ እርምጃ ወስደን ከተቆጣጠርን በኋላ የተሻለ ነገር ይኖራል” ይላሉ። እንዲህ አይነት እርምጃዎች በበርካታ አገራት የሚወሰዱ የተለመዱ አሰራሮችም መሆናቸውንም አፅንኦት ይሰጣሉ። ለዶክተር ደመቀም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጣለው እገዳ ሳይንሱን ተከትለው ነው ይላሉ። የትኛውም አገር ላይ ወረርሽኝ ሲያጋጥም እንቅስቃሴ መገደብ የተለመደ መሆኑን የሚጠቅሱት ዶክተር ደመቀ፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ይጠቅሳሉ። መሥሪያ ቤቱ በንክኪ መዛመትን ለመግታት እንቅስቃሴን መገደብን በዚህም ሕዝቡንም ሆነ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ለመጠበቅ፣ እንዲህ አይነት እርምጃ በበርካታ አገራት ተግባራዊ ይደረጋል ይላሉ። ሆኖም ሳይንሱ ይህንን ቢልም በኢትዮጵያ አንድምታ አብዛኛው ዶሮ አርቢ መኖና የተለያዩ መገልገያዎች የሚገዛው ከቢሾፍቱ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ በሽታ ያልገባባቸው አካባቢዎች በመኖና በሌሎች መገልገያዎች ጥገኛ ስለሚሆኑ በሎጂስቲክ መቋረጥ ምክንያት ችግር ውስጥ እንደሚገቡም ያስረዳሉ። ሆኖም ይላሉ ዶክተር ደመቀ “እንዲህ አይነት ውሳኔዎች ሲወሰኑ በጣም መጥፎ ከሚባለው፣ የተሻለውን መጥፎ መምረጥ የሚለውን አሰራር ተከትሎ ነው።\" ዶክተር ደመቀ እንደሚያስረዱት የዶሮ በሽታ ወረርሽኝ አለ የሚባለው ከሁለት በላይ የሆኑ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ሲያጠቃ ነው። በዚህም ወቅት የተከሰተው በሽታ በርካታ ማዕከላትን ማጥቃቱ ወደ አጎራባች አካባቢዎች መዛመቱ የዶሮ ወረርሽኝ ሊባል ይችላል ይላሉ። ከዚህ በፊት አጋጥሞ ቢያውቅም በዚህ ደረጃ እንዳልነበርና መለስ ያሉ የዶሮ መሞት መጠን እንደነበረና የተወሰነውንም መርጦ እንዳጋጠመ ያወሳሉ። ዶክተር ፍቅሩም በአንዳንድ የዶሮ እርባታ ማዕከላት መቶ በመቶ ዶሮዎቹን በመጨረሱ ወረርሽኝ ነው ለማለት እንደሚያስችል ያስረዳሉ። ወረርሽኝ በሚያጋጥምበት ወቅት እንቅስቃሴዎችን መገደብን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፣ ወረርሽኝ ነው ተብሎ የሚታሰብ ከሆነ በፍጥነት መለየት እንዳለበት ያስረዳሉ። “የዶሮ እርባታ ዘርፉ በቋፍ ላይ ነው” የሚሉት አቶ ብርሃኑ በርካታ ችግሮች ያሉበትና እድገት የማያሳይ ነው የሚሉትን ዘርፍ ሊያቀጭጨው እንደሚችልም ያስጠነቅቃሉ። አሁን ባለው ሁኔታም ላይነሳ ከሚወድቅበት ደረጃ ላይ በመሆኑ እግዱ ላላ ሊል ይገባል ይላሉ። ወረርሽኝ ተከስቶ እንደማያውቅ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ በ1997ም ‘በርድ ፍሉ’ ነው በሚል እሳቤ በርካታ ዶሮዎች መገደላቸውን አስታውሰው። የላብራቶሪ ውጤቱ ግን ወረርሽኝ እንዳልሆነ በማሳየቱ የተወሰደው ትክክለኛ እርምጃ እንዳልነበር ያወሳሉ። በዚህም ወቅት ተመሳሳይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የሚናገሩት ሥራ አስኪያጁ በሽታው ታውቆ ለዚያ የሚሆን ትክክለኛ እርምጃ ቢወሰድ ችግር እንደሌለውም ያስረዳሉ። ነገር ግን “በአሁኑ ወቅት ውጤቱ ባልታወቀበትና አመላካች ሁኔታዎች ብዙ ወረርሽኝ በማይመስሉበት ሁኔታ” ወደ እገዳ እርምጃ መገባቱ ትክክል እንዳልሆነም አፅንኦት ይሰጣሉ። የዶሮ እርባታ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣ ዘርፍ ነው የሚሉት ዶክተር ፍቅሩ፣ ይህም እንዳይጎዳ ስለ በሽታው ምንነት በማያሻማ መልኩ ውጤቱ አስኪታወቅ ድረስ ገደቡ የሚቀጥል ሲሆን፣ አሁን በተያዘው ሁኔታ ረጅም ጊዜ ሊቆይ እንደማይችልም ያስረዳሉ። የዶሮ አርቢዎች ማኅበር በተጨማሪ የሚያነሱት ቅሬታ በግብርና ሚኒስቴር እየተላለፉ ያሉ ውሳኔዎች ማኅበሩን ያገለሉ መሆናቸውን ነው። ማኅበሩ እንደ ዋና ባለ ድርሻ አካል በምርምሮቹና በመፍትሄዎቹ ላይ ተሳታፊ ቢሆን ለመከላከያ እርምጃውም የተሻለ ግብዓት እንዲሁም በተቀላጠፈ ጊዜ ቶሎ ውጤት ላይ ለመድረስ ይቻላል ብለው ያምናሉ። ከተከሰተው የዶሮ በሽታ ጋር በተያያዘ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጣ ግብረ ኃይል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አቋቁሟል። ግንዛቤ የማስጨበጥ እንዲሁም በሸታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች የክትትል ሥራ፣ ምርምሮች፣ ምላሽ የመስጠት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በርካታ ዶሮዎች በየጢሻው ተጥለው በመገኘታቸው በሽታው እንዳይስፋፋና በድጋሚ እንዳይከሰት እነዚህን የሞቱ ዶሮዎችን አሰባስቦ የማስቀበርና የማቃጠል ሥራዎች እየተሰሩ ነው። በሽታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች ሌላ በሽታ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ኬሚካል የመርጨት ተግባር እየተከናወነ ነው። ትልልቆቹ የዶሮ እርባታ ማዕከላትም የደኅንነት አጠባበቃቸውን በማሳደግ በዚያው ምርቶቻቸውን እንዲይዙ ተደርጓል። የዶሮ እርባታ ማዕከላት ላይ በሽታዎች የመከሰት ነገር የተለመደ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ፍቅሩና ዶክተር ደመቀ፣ በሽታዎች ሲከሰቱ ሊያደርሷቸው የሚችሉ ጉዳቶችን በተመለከተ አስቀድመው መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች (የባዮ ሴኩሪቲ ደኅንነት) ቢኖርም አንዳንዶች በትክክል ተግባራዊ እንደማያደርጉ ይናገራሉ። በተጨማሪም ኬሚካሎችና የጽዳት ግብዓቶች (ዲስኢንፌክታንት) የማይጠቀሙ፣ ክትባትም ጊዜውን ጠብቀው በአግባቡ የማይሰጡ የእርባታ ማዕከላት ሲኖሩ በሽታዎች እንደሚከሰቱ ጠቅሰው፣ በአሁኑ ወቅት ጥንቃቄዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ዶክተር ፍቅሩ ለአርቢዎች የሚመክሩት በአካባቢያቸው የሞቱና የተጣሉ ዶሮዎች ካሉ በአግባቡ ማስወገድ፣ የኬሚካል ርጭትም ካለ ያንን ማከናወን ከተሰማራው ግብረ ኃይል ጋር በከላከል ሥራው ላይ እንዲሳተፉ መክረዋል። ኅብረተሰቡም ቢሆን ጥቆማ እንዲያደርግ የሚመክሩት ዶክተር ፍቅሩ፣ በተባባረ መንገድም በፍጥነት ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ይረዳል ይላሉ። በተለያዩ መንገዶች እየወጡ ያሉ መረጃዎች ኅብረተሰቡን ዶሮና እንቁላል ከመመገብ ፍርሃት ውስጥ የሚከቱ ናቸው የሚሉት አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ለሰው ጤና አስጊ ባልሆነበት ሁኔታ ለመረጃዎች ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ይላሉ። “ይሄንን ያህል የሚያስፈራ ነገር የለም። ነገር ግን በደንብ ያልታወቀ ጉዳይ ደግሞ እንዲህ አድርጉ ማለት አይቻልም። ምንም አይነት የገጠመ ወይም ሪፖርት የተደረገ የለም። ነገሮችን እስከምናውቅ ብሉ አትብሉ ልንል አንችልም” ይላሉ ዶክተር ፍቅሩ በበኩላቸው። ዶክተር ደመቀ ሕዝቡ ዶሮንም ሆነ የዶሮ ተዋፅኦ የሚጠበቅበት መንድ አብስሎ ስለሆነ፣ በደንብ ማብሰልና ንፅህናውን የመጠበቅ ሁኔታ ካለ ተጠቃሚውን የሚያሰጋ ነገር ሊኖር ይችላል ብለው እንደማያስቡ ያስረዳሉ። ሆኖም በአጠቃላይ ባለሙያው የሚያስተላልፉት መልዕክት የዶሮ እርባታ ወደ ኢንዱስትሪ ሊያድግ እንደሚችል ጠቅሰው፣ ይህም የራሱ ችግር ስለሚያመጣ ተገቢ የሆነ የዶሮ በሽታ መከላከልና መቋቋም ሥራ በተገቢው መንገድ መሰራት እንዳለበት ነው። ይህንንም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆነ የግል ሴክተሩ አንድ ላይ ሆነው ፕሮግራም ቢቀርጹ ጥሩ ነው በማለት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።", "የአውስትራሊያው ምክትል ጠ/ሚ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ዩኬ አቅንተው በኮቪድ ተያዙ የአውስትራሊያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም አቅንተው በኮቪድ መያዛቸው አሜሪካ በደረሱ ወቅት ተረጋገጠ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባርናቢ ጆይስ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ጉብኝት ባደረጉት ወቅት በቫይረሱ ሳይያዙ እንዳልቀሩ ተናግረዋል። አክለውም በአሁኑ ሰዓት እራሳቸውን ለይተው እንደሚገኙና ቀለል ያሉ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን እንዳስተዋሉ ገልጸዋል። ባርናቢ ጆይስ ረቡዕ ዕለት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመጓዛቸው አስቀድመው በዩናይትድ ኪንግደም በነበራቸው ቆይታ የካቢኔ ሚኒስትር ከሆኑት ዶሚኒክ ራብ እና ግራንት ሻፕስ ጋር ተገናኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እስካሁን ድረስ ለቫይረሱ ስርጭት ምን ያክል ስጋት እንደሆኑ አልታወቀም። እስካሁን ድረስ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር አብረው እየተጓዙ ካሉ የልዑክ ቡድን አባላት መካከል በቫይረሱ የተያዘ አልተገኘም። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሉት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሲሄዱ ተመርምረው ኮሮናቫይረስ እንደሌለባቸው አረጋግጠው የነበረ ቢሆንም ልክ አሜሪካ ሲደርሱ ግን ድካምና እግራቸው አካባቢ የመዛል ስሜት አስተውለዋል። ከዚህ በኋላ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ10 ቀናት እራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ የተገለጸ ሲሆን ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ሊያደርጉት የነበረውም ውይይት ተሰርዟል። ባርናቢ ጆይስ ከአውስትራሊያ መገናኛ ብዙኀን ጋር ባደረጉት ቆይታ ለገና በዓል ለንደን ውስጥ አንዳንድ እቃዎችን ለመግዛት ወደ ትልልቅ የገበያ ማዕከላት ማቅናታቸውን ያልደበቁ ሲሆን በርካታ ሰዎችም ትከሻ ለትከሻ ተጠጋግተው እንደነበር አስረድተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙ የአውስትራሊያ ኃላፊ ናቸው። የአውስትራሊያው መከላከያ ሚኒስትር ባሳለፍነው ዓመት ወደ አሜሪካ ጉዞ ካደረጉ በኋላ በቫይረሱ መያዛቸው የሚታወስ ነው። አውስትራሊያ እስካሁን ድረስ በወረርሽኙ ምክንያት ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ያስታወቀች ሲሆን ይህም ካደጉት አገራት ጋር ሲነጻጸር በጣም ዝቅተኛ ቁጥር ነው።", "በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተመዘገቡ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በየዕለቱ የሚደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን መሠረት በማድረግ ማክሰኞ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ. ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ አሐዝም ከዚህ በፊት በአንድ ቀን ከተመዘገቡት በጣም ከፍተኛው ነው። በየዕለቱ በ24 ሰዓት ይፋ የተደረጉ ቀደም ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ዕለታዊ አሐዝ ከ500 እስከ 1000 ባለው መካከል የቆየ ነበር። የማክሰኞ ዕለቱ ሪፖርት እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው በዕለቱ ምርመራ ካደረጉ 10,016 ሰዎች መካከል ነው። እስካሁን በአገሪቱ በወረርሽኙ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 379,379 የደረሰ ሲሆን፣ ትናንት ለተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ምክንያቱ ምን እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። እስካሁን በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከነበሩ መካከል 351,168 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ 6,877 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በዓለም ዙሪያ ክትባት እየተሰጠ ቢሆንም፤ በቅርቡ የተከሰተው ኦሚክሮን የተባለው አዲስ ዓይነት ዝርያ የበሽታውን የመስፋፋት ፍጥነትና አደገኝነት እንዳባባሰው የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። ይህ መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ የተነገረው ኦሚክሮን በርካታ ሰዎች ላይ እየተገኘ ሲሆን አገራት በሽታውን ለመቆጣጠር ጥብቅ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ይህ የወረርሽኙ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመገኘቱ በጤና ባለሥልጣናት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።", "ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስፎርዱ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ ሰው ቢሞትም የደህንነት ስጋት የለበትም ተባለ በአስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥምረት እየበለጸገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ሙከራ በሚደረግባት ብራዚል የአንድ በጎ ፈቃደኛ ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ ክትባቱ ምንም አይነት የድህንነት ስጋት እንደሌለበት ተገለጸ። የብራዚል ጤና ባለስልጣን ከሙከራው ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ስላለፈው በጎ ፈቃደኛ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንደሚደረግና ክትባቱ ግን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለበት አስታውቋል። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በጎ ፈቃደኘው ክትባቱን አልወሰደም። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው ክትባት ላይ ከሚሳተፉት በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ሲሆን ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው ቀሪዎቹ ደግሞ ማረጋገጫ የተሰጠው የማጅራት ገትር ክትባት ነው የተሰጣቸው። የሙከራው ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም እራሳቸው የሚሰጣቸው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ይሁን የማጅራት ገትር የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ የሚደረገውም በገዛ ፈቃዳቸው ነው ተብሏል። ግዙፉ የመድሀኒት አምራች አስትራዜኔካ በበኩሉ በእያንዳንዱ የግለሰብ የሙከራ ሂደት ላይ አስተያየት እንደማይሰጥና ሙከራው ሲካሄድ ግን አስፈላጊው ጥንቃቄና የደህንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ''ሁሉም ወሳኝ የጤና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ተመርምረዋል፤ ከግምት ውስጥም ገብተዋል። ሙከራውም ሆነ የምርምር ሂደቱ ምንም አይነት አሳሳቢ ነገር አልተገኘባቸውም፤ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሂደቱን እንዲከታተሉት አድርገናል'' ብሏል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የክትባት ሙከራዎች መካከል ይሄኛው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ለገበያ እንደሚበቃም ይጠበቃል። እስካሁን ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙከራ ሂደቶችን በስኬታማነት ያጠናቀቀው ይኸው ክትባት ደረጃ ሶስትን ለማጠናቀቅ ደግሞ በዩኬ፣ ብራዚልና ሕንድ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራውን እያካሄደ ይገኛል። ባሳለፍነው ወር በዩኬ ይካሄድ የነበረው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል በሚል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ሙከራውን ለማከናወን ምንም ስጋት እንደሌለ በመገለጹ ሂደቱ በድጋሚ እንዲጀመር ሆኗል። የብራዚል ጤና ባለስልጣን በጎ ፈቃደኛው ሕይወቱ ስለማለፉ ከትናንት በስትያ መስማቱን አስታውቋል። የብራዚል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው ሕይወቱ ያላፈችው ግለሰብ የ28 ዓመት የህክምና ባለሙያ እንደሆነና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወቱ እንዳለፈች ዘግበዋል። ይህ ክትባት ሙሉ ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ብራዚል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብልቃጦችን ለመግዛት ወስናለች። በአገሪቱ እስካሁን 5.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከአሜሪካና ሕንድ በመቀጠል በዓለማችን ሶስተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ እስካሁን 155 ሺ መድረሱ ተረጋግጧል።", "ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት ምርጫ ለምን የተለያየ ሆነ? አሜሪካ ሦስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የፈቀደች ሲሆን ሰዎች የሚፈልጉትን እየመረጡ ነው። ሦስቱም የኮቪድ-19 ክትባቶች በቫይረሱ መያዝና ተይዞ ሆስፒታል መግባትን እንዲሁም ሞትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናት ለዜጎች የሚሰጠው የተሻለው ክትባት ነው ብለዋል። ቢሆንም ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይልቅ ፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶችን የሚመርጡ ብዙዎች ናቸው። በመጋቢት መጀመሪያ የዲትሮይት ከንቲባ ማይክ ዱጋን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትን ውድቅ አድርገው በአሜሪካ የቀረቡት ሌሎች ሁለት ክትባቶች የተሻሉ መሆናቸውን ለከተማዋ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት \"የዲትሮይት ከተማ ነዋሪዎች የተሻለውን እንዲያገኙ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ\" ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች አስተያየት ከሰጡ በኋላ ከንቲባው ክትባቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ስለመሆኑ \"ሙሉ እምነት አለኝ\" በማለት ገልጸዋል። እንደ ዱጋን ሁሉ አንዳንድ አሜሪካውያን ስለ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት እና ስለ አጠቃላይ ውጤታማነቱ ጥያቄ አንስተዋል። የጤና ባለሥልጣናት ግን እነዚህ ቁጥሮች ሙሉውን ገጽታ እንደማያሳዩ አስጠንቅቀዋል። አንዳንዶች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ከመውሰድ ሳይከተቡ ቢዘገዩ እንደሚመርጡ ይናገራሉ። አንድ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ለቢቢሲ ሲናገሩ \"የክትባት ቀጠሮ በነበረኝ ጊዜ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን እየሰጡ እንደሆነ ስለሰማሁ ሰርዤዋለሁ። ያንን ክትባት በጭራሽ አልወስድም\" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ማይክል አንድራሲክ ያሉ የጤና ባለሥልጣናት ማንኛውንም ፈቃድ ያገኘ ክትባት መውሰድ ጥሩ መሆኑን አሜሪካውያንን ለማሳመን እየሞከሩ ነው። \"በአንድ በኩል ሰዎች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ በጣም ተደስተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ውጤታማነቱን በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባት አለ። ይህ ደግሞ ጥሩ አይደለም\" ሲሉ በፍሬድ ሃች የክትባትና ተላላፊ በሽታ ክፍል ከፍተኛ የሳይንስ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንድራሲክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠውን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት በይፋ ያጸደቁት በየካቲት ነው። ይህም ፍቃድ ያገኘ የመጨረሻው ክትባት አድርጎታል። አዲስ የኤም አር ኤን ኤ ክትባት ቴክኖሎጂን ከሚጠቀሙት እና ሁለት ጊዜ ከሚሰጡት ከፋይዘር እና ከሞዴርና ክትባቶች በተለየ መልኩ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጉዳት እንዳያደርስ የተደረገ ቫይረስን ይጠቀማል። ከዚያ የኮሮናቫይረስን ዘረ መል በከፊል ወደ ሰውነት ይወስዳል። ይህም ሰውነት አደጋውን ለይቶ እንዲያውቅ እና ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት እንዲዘጋጅ ያደርጋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በክትባቱ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በዚህ ወር ለአሜሪካኖች ከቀረበው በእጥፍ 100 ሚሊዮን ተጨማሪ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባቶች እንደምታዝ አስታውቀዋል። የብሔራዊ አለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በበኩላቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሁሉም ክትባቶች ጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትም \"ደካማ ክትባት አይደለም\" ብለዋል። አሳሳቢው ነገር ከሙከራዎች የሚወጣው የውጤታማነት መረጃ መለያየት ነው። የጤና ባለሥልጣናት ሦስቱም ክትባቶች መቶ በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅም አላቸው ሲሉ አሳስበዋል። የፋይዘር እና የሞደርና ክትባቶች አዳዲሶቹ የቫይረሱ ዝርያዎች ከመስፋፋታቸው በፊት የተሞከሩ ሲሆን አዳዲሶቹ ዝርያዎች በሙከራዎች ላይ ልዩነት ይፈጥራሉ። በተጨማሪም የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ሁሉም ክትባቶች ከዓመታዊው የጉንፋን ክትባት የበለጠ ውጤታማ ናቸው ሲል ይገልጻል። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ከሆነ \"ዋናው ነገር ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ ሞደርና እና ፋይዘር ከባድ በሽታን በመከላከል፣ ሆስፒታል መተኛትን በመቀነስ፣ ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን በመቀነስ ወይም መሞትን በመከላከል በማይታመን ሁኔታ ውጤታማ ናቸው።\" የማኅበረሰብ ጤና ተሟጋቾች እንደሚሉት ከሆነ ሌላው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጠቃሚ ጎን በአሜሪካ ውስጥ ብቸኛው አንድ ጊዜ የሚሰጥ ክትባት መሆኑን ነው። ራቅ ወዳሉ እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎችም ለማሰራጨት የበለጠ ምቹ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ያንን ክትባት ብቻ ወደ አካባቢዎቹ መላክ መገለልን ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ። አክለውም \"ሁሉም ክትባቶች ለሁሉም ሊደርሱ ይገባል ብዬ አስባለሁ። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ወደ ገጠር እና ድሃ ማኅበረሰቦች የመላክ ምክንያታዊነት በእንክብካቤ ተደራሽነት ምክንያት ነው ብዬ አስባለሁ\" ብለዋል ዶ/ር አንድራስክ። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ያሉ የማኅበረሰብ አመራሮች እና የጤና ባለሙያዎች በክትባቱ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋፋት እና የተሳሳተ መረጃን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ \"የእኔ ተራ ሲደርስ ማንኛውንም ክትባት እወስዳለሁ\" ይላሉ። ሌሎቹ አሳሳቢ ጉዳዮችስ ምንድን ናቸው? ዩ ኤስ ኮንፈረንስ ኦፍ ካቶሊክ ቢሾፕስ የተባለው እና በአሜሪካ የሚገኘውን ቤተክርስትያን የሚወክለው ጉባኤ በክትባቱ ዙሪያ \"የሞራል ስጋት\" መኖሩን መግለጹ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የስጋቱ ምንጭ ጽንስ በማስወረድ ከሚገኙ ሕዋሶች ክትባቱ ተመርቷል መባሉ ነው። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኢቦላ ክትባትን ለማዘጋጀት የዋለውን ተመሳሳይ ዘዴ ተጠቅሟል። በተጨማሪም የትኛውም የኮቪድ -19 ክትባት ምንም ዓይነት የሰው ህዋሳትን አልያዘም። ጉባኤው ምርጫ እስካለ ድረስ ካቶሊኮች አማራጭ ክትባቶች መውሰድ እንዳለባቸው መክሯል። በአሜሪካ ጉባኤ የተሰጠው ምክር ከቫቲካን አቋም ጋር የሚቃረን ይመስላል። ምክንያቱም ቫቲካን እንዲህ ያሉት ክትባቶች \"ከሞራል አንጻር ተቀባይነት አላቸው\" ስለምትል ነው። ሌሎች የካቶሊክ መሪዎችም የቤተክርስቲያኗ አባላት ከዚህ ክትባት መራቅ አለባቸው የሚለውን ሐሳብ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የሐርትፎርድ ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች የአካባቢው የሐይማኖት አባቶች በሰጡት መግለጫ ሁሉም ነዋሪዎች ለራሳቸው ጤና እና ለጋራ ጥቅም ሲሉ \"ማንኛውንም ክትባት ለመቀበል የህሊና ነፃነት ሊሰማቸው ይገባል\" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ዶሮ በሽታ እና ሩቤላ ያሉ ሌሎች ብዙ ክትባቶች በተመሳሳይ መልኩ የተሠሩ ቢሆንም የካቶሊክ መሪዎች ስለ ለጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ያሰሙት ስጋት በአንዳንድ አሜሪካውያን ዘንድ ጥርጣሬ እንዲጨምር አድርጓል። ስጋቶችን የሚጋፈጠው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ብቻ አይደለም። አሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ለመፍቀድ እየተዘጋጀችበት የሚገኘው የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር በተያያዘ የአውሮፓ አገራት ታግዶ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ባሥልጣን ክትባቱ \"ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው\" ብሎ መግለጹን ተከትሎ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ስፔን ክትባቱን መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል።", "የቬትናም ፖሊስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የነበሩ ኮንዶሞች ያዘ የቬትናም ፖሊስ ከ320ሺህ በላይ ታጥቦ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውል የነበረ ኮንዶም መያዙን አስታወቀ። የቬትናም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ኮንዶሞች ሊሸጡ የነበረው በኮንዶሞቹ ጥራት ላይ ጥያቄ ለማያነሱ ግለሰቦች ነው። ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ታጥበው ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ በተዘጋጁ ኮንዶሞች የተሞሉ ሻንጣዎች ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። ፖሊስ እንዳለው ከሆነ ሕገ-ወጥ ኮንዶሞቹ የተያዙት በአገሪቱ ደቡባዊ አቅጣጫ በአንድ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ነው። የመጋዘኑ ባለቤት ነች የተባለችው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ተዘግቧል። ጥቅም ላይ የዋሉት ኮንዶሞች ከታጠቡ በኋላ የወንድ ልጅ ብልት ቅርጽ ባለው አንጨት ላይ ይለጠጡ እና ዳግም ታሽገው ለገበያ ይቀርባሉ ተብሏል። በቁጥጥር ሥር የዋለችው የመጋዘን ባለቤት በአንድ ኪሎ ግራም ኮንዶም 0.13 ዶላር ተስማምታ ወደ ሥራው መግባቷን ለፖሊስ ቃሏን ሰጥታለች። ጥቅም ላይ ውለው ዳግም ለገበያ የሚቀርቡት ኮንዶሞች ዋጋ እንዲሁም ጥቅም ላይ የዋሉ ኮንዶሞች እንዴት እንደሚሰበሰቡ የተባለ ነገር የለም።", "ኔዘርላንድ ከ12 አመት በታች ላሉ ታዳጊዎች የፈቃድ ሞትን ፈቀደች የኔዘርላንድ መንግሥት በማይድን በሽታ የተጠቁ ታዳጊዎች በፈቃድ ሞት ወይም በእንግሊዝኛው ዩቴኔዥያ (euthanasia) ተግባራዊ እንዲሆን ከሰሞኑ ፈቅዷል። ታዳጊዎች ብሎ የጠቀሰው ከአስራ ሁለት አመት በታች የሆኑ ህፃናትን ሲሆን የጤና ሚኒስትሩ ሁጎ ደ ጆንጌም ይህ ህግ \"መቋቋም በማይችሉትና ተስፋ በሌለው ሁኔታ የሚሰቃዩ\" ህፃናትን ይታደጋቸዋል ብለዋል። በኔዘርላንድ የፈቃድ ሞት ከአስራ ሁለት አመት በላይ ለሆኑ ታዳጊዎች የሚፈቀድ ሲሆን ይህም የሚፈፀመው ከህመምተኞችና የቤተሰቦች ፈቃድ ሲገኝ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከአንድ አመት በታች ያሉ ህፃናትን በማይድን በሽታ ከተጠቁና በቤተሰብ ፈቃድ እስከተገኘ ድረስ እንዲሞቱ ይፈቀዳል። በ አንድ አመትና በ12 አመት መካከል የሚገኙ በማይድን በሽታ እየተሰቃዩ የሚገኙ ታዳጊዎችን በተመለከተ ምንም ህግ ያልነበረ ሲሆን የአሁኑ ይፈቀድ የሚለው ጥያቄም አገሪቷን በሚመሯት አራት ጥምር ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ ውዝግብን ፈጥሯል። ለወራትም ያህል የፓርላማ አባላቱ ሲነታረኩ ነበር። በተለይም ወግ አጥባቂው የክርስቲያን ፓርቲዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውመውታል። ሆኖም በመጨረሻ የፈቃድ ሞት ይፈቀድ የሚለው አሸንፎ ህግ እንዲሆን ፀድቋል። ከዚህ በኋላ ህጉን በተግባር ላይ ለማዋልም መመሪያዎች እንደሚወጡ የጤና ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የዚህ ህግ መቀየር አስፈላጊ መሆኑንም አንድ በባለሙያዎች የቀረበ ጥናት ማስረጃ ነው ይላሉ የጤና ሚኒስትሩ። በዚህ ጥናት መሰረት አዲሱ ህግ በአመት አስር የሚሆኑ በማይድን በሽታ የሚሰቃዩ ህፃናትን ህይወት ይቀይራል። በስራ ላይ ያሉት ህጎች ሙሉ በሙሉ ይቀየራሉ ማለት እንዳልሆነ የጠቀሱት የጤና ሚኒስትሩ ነገር ግን ፍቃድ ያለው የፈቃድ ሞት ዶክተሮች ቢያከናውኑ ከመከሰስ ይከላከልላቸዋል። በተሻሻለው ህግ መሰረትም ከ12 አመት በላይ ያሉ ታዳጎጊዎች የቤተሰብ ፈቃድ፣ ከፍተኛና መቋቋም የማይችሉት ህመምና ይህንን ተግባር ማከናወን የፈቀዱ ሁለት ዶክተሮች መስፈርቶች መሟላት አለባቸው። እነዚህ ህጎችም በሚቀጥሉት ወራት ተግባራዊ ይሆናሉ። የፈቃድ ሞት በኔዘርላንድ ህግ ሆኖ የፀደቀው በጎሮጎሳውያኑ 2002 ሲሆን ከወራት በኋላም ቤልጅየም በመፍቀድ ተከትላታለች።", "ዐይናችንን ሊጎዱ እና ዕይታችንን ሊያጨልሙ የሚችሉ አራት ምክንያቶች የህመም አለመኖር ጤንነትን አያረጋግጥም ይባላል። ፍጹም ጤነኛ እንደሆኑ እያሰቡ ድንገት በአንዱ የሰውነት ክፍልዎ ላይ ስር የሰደደ በሽታ እንዳለ ማወቅ ሌላ ህመም ነው። ከ23 ዓመታት በፊት ሥራ የጀመሩት የዐይን ህክምና ስፔሻሊሰቱ ዶክተር ዮናስ ጥላሁን እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችን ተመልክተዋል። “አንዳንድ ታካሚዎች ‘ድንገት ጠዋት ተነስቼ አንዱ ዐይኔን ሳሸው ጠፋ’ ይላሉ” በማለት አልፎ አልፎ ስለሚያጋጥማቸው ነገር ይናገራሉ። ዐይን በድንገት ሊጠፋ ይችላል? መልሱን እንመለሰበታለን! ከዚያ በፊት ዐይናችንን ስለሚጎዱ እና የዕይታ መጠናችንን ስለሚቀንሱ ምክንያቶች እናውራ! ዐይንን የሚጎዱ በርካታ ምክንያቶች አሉ። እኛ ግን ዶክተር ዮናስ ጥላሁን የነገሩን አራት ምክንያቶች ብቻ እንመልከት። ዶክተር ዮናስ ዐይን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ባሉ የጤና ችግሮች ምክንያት ሊጎዳ የሚችልበት አጋጣሚዎች እንዳሉ ያስረዳሉ። እንደ ስኳር እና ደም ግፊት ያሉ በሽታዎች በቀጥታ የዐይን ጤንነት ላይ ጉዳት በማድረስ እስከ ዐይነ ስውርነት ሊደርሱ ይችላሉ። የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መካለከል ማዕከል ወይም ሲዲሲ እንደሚለው የስኳር በሽታ ከዐይን ጋር የተሳሰሩ የደም ቧንቧዎች ላይ ጉዳት በማድረስ የዕይታ መጠናችን እጅግ እንዲያሽቆለቁል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ከዚህም ባሻገር በክትባት በቀላሉ ሊወገዱ በሚችሉ ችግሮች ምክንያት ዐይን በከፋ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችልም ነው ዶክተር ዮናስ የሚናገሩት። “እንደ ኩፍኝ ያሉ በሽታዎች ክትባት ካልተወሰደ ጠበሳ በማምጣት ዐይንን እስከማጥፋት ይደርሳሉ” የሚሉት የዐይን ስፔሻሊስቱ “በተመጣጠነ ምግብ፣ ቫይታሚን ኤ እጥረት የዐይን ብሌን መቁሰል አጋጥሟቸው ብዙ ህጻናት ዐይናቸውን ሊያጡ የሚችሉበት ሁኔታ አለ” ብለዋል። በሌላ በኩል በህጸናት ዐይን ላይ “መንሸዋረር” የመሰሉ ችግሮችን ችላ ብሎ ማለፍ በዕይታቸው ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ጠቁመዋል። የዐይን ንጽህናንን ባለመጠበቅ ደግሞ እንደ ትራኮማ ያሉ በሽታዎች ተከስተው “ውለው አድረው” የዐይን ብርሃንን ሊያሳጡ የሚችሉ ሲሆን የዐይን በሽታ ከቤተሰብ ሊወረስበት የሚችልበት አጋጣሚም አለ። በጤና ምክንያት የሚመጡ የዐይን ችግሮችን ምርመራ በማድረግ የከፋ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት ሊደረስባቸው ይችላል። ስኳርን የመሳሰሉ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች እና በቤተሰብ ውስጥ የዐይን ችግር እንዳለ ከታወቀ የዐይን ምርመራን በቋሚነት ማድረግ ይመከራል። ለህጻናት ደግሞ የተመጣጠነ ምግብ መስጠት እና ክትባቶችን እንዲወስዱ ማድረግ እንደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሁሉ ለዐይናቸውም ጠቃሚ መሆኑን ነው ይላሉ ዶክተር ዮናስ። ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ዐይናቸው ላይ “ነጭ ነገር ጣል ካለ”፣ ሳያለቅሱ እንባ ከፈሰሰ፣ የዐይን መጠን መለያየት ካለና ዐይናቸውን ደጋግመው ካሹ ወደ ህክምና ተቋማት እንዲሄዱ ዶክተር ዮናስ ይመክራሉ። የቫይታሚን ኤ እና ኦሜጋ 3 ይዘት ያላቸው ምግቦችን ማዘውተር የዐይን ጤናን በእጅጉ ይጠብቃሉ። እንደ ፓፓያና ማንጎ ያሉ ፍራፍሬዎችን፣ እንደ ቆስጣና ጎመን ያሉ አትክልቶችን እንዲሁም አሳን ማዘውተር ለዐይን ጤና ጠቃሚ ነው። የዐይን ስፔሻሊስቱ “በስክሪን ላይ የሰዎች ዐይን ተተክሎ በመዋሉ የተነሳ፣ የዐይን ጤና መታወክ ደርሶ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መመላለሳቸው መጨመሩ ይታያል” ይላሉ። በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ከሞባይል እና ከኮምፒውተር ጋር ያለን ቁርኝት እየጨመረ በመሄዱ የተነሳ፣ በዲጂታል ቁሶች ምክንያት የሚመጡ የዐይን ውጥረቶች (Digital Eye Strain/Computer Vision Syndrome) በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። እንደ ሐኪሙ ገለጻ በቀን በስክሪኖች ላይ ያለ ቆይታ ከ2 ሰዓታት ከዘለለ ረጀም የስክሪን ቆይታ ተብሎ የሚገለጽ ነው። ማን ያውቃል?! ከሞባይሉ ጋር ቁርኝት ላለው ግለሰብ በቀን ለሁለት ሰዓት መጠቀም እጅግ ትንሽ ሊሆን ይችላል። ቢቢሲ በአንድ ወቅት የተመለከተው ሪፖርት በ20 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሰዎች ስክሪን ላይ የሚያጠፉት ጊዜ መጨመሩን ያመላክታል። ሪፖርቱ ከ5 እስከ 16 ዓመት ያሉ ህጻናት በቀን በአማካኝ 6 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ስክሪን ላይ እንደሚያጠፉ ይጠቁማል። ታዲያ ዐይንን ለረጅም ሰዓት ስክሪን ላይ ማንከራተት ጊዜያዊ ችግሮችን እንደሚያስከትል ነው ዶክተር ዮናስ የሚያስረዱት። ይህም የዐይን ብዥታ፣ መወጠር፣ መቅላት፣ ማሳከክ፣ መደረቅ፣ ማቃጠል እንዲሁም ቶሎ መድከም፣ እንቅልፍ እንቅልፍ ማለትና ራስ ምታትን ያካትታል። ሐኪሙ አንዳንድ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ ረጅም የስክሪን ቆይታ ህጻናት ላይ የዕይታ ችግር (Short-sightedness) ሊፈጥር እንደሚችል ተናግረዋል። መፍትሄው ምንድን ነው? ስክሪን በምንጠቀምበት ጊዜ “የሃያ ሃያ ሕግ”ን መተግበርን ዶክተር ዮናስ ይመክራሉ። “የሃያ ሃያ ሕግ” እንደ ኮምፒውተር፣ ሞባይል ወይም ቴሌቪዢን ያሉ ቁሶችን ለ20 ደቂቃ ከተጠቀምን በኋላ ለ20 ሰኮንድ ሥራ በማቆም 20 ጫማ ወይም 6 ሜትር ርቀት አካባቢ በመመልከት ዐይንን የማሳረፍ ሕግ ነው። ይህም ቀላል የሚመስል ቢሆንም ለዐይን ጠቃሚ መሆኑን ነው የሚያስረዱት። መነጽርን ከተገኘበት ቦታ “ለስክሪን፣ ለፀሐይ አልያም ለዝነጣ” መሸመት ለዐይናችን ጤና ጠንቅ ሊሆን ይችላል። ዶክተር ዮናስ “አንዳድ መነጽሮች ጠቃሚነታቸው የተረጋገጠ አይደለም። አንዳንዶች ደግሞ ጎጂም ሊሆኑ ይችላሉ” ያሉ ሲሆን፣ ለምሳሌ ሰማያዊ ብርሃኖችን ያጣራሉ በሚል እና ለኮምፒውተር በሚል በውድ ዋጋ የሚሸጡ መነጽሮችን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። “እርግጥ ኮምፒውተር ለመጠቀም መነጽር አይጠቅምም እያልኩ አይደለም። በሐኪም ምርመራ ታይቶ የሚጠቅምባቸው አስፈላጊ እና የግድም የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ” ይላሉ። ከዚያ ውጪ ግን አንዳንዶቹ የ‘ሳይት’ ቁጥራቸው ከተጠቃሚው ዐይን ጋር ባለመናበቡ ምክንያት ዐይን ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ለፀሐይ ወይም ለዝነጣ በሚል የሚሸመቱት ደግሞ “ዐይናችን እንደጨለመ ስለሚቆጥር የዐይን ብሌናችን ይሰፋል።” የዐይን ብሌን መስፋት ደግሞ ዐይናችን ለጎጂ እና አላስፈላጊ ጨረር እንዲጋለጥ ያደርገዋል። ዕድሜ ከሚያዳክማቸው የሰውነት ክፍሎች አንዱ ዐይን ነው። በተለይ እድሜ ከአርባ ሲሻገር ዐይን ይደክማል። የዕይታ መጠን እየቀነሰ ይሄዳል። ዶክተር ዮናስ የዚህን ምክንያት ሲያስረዱ ዐይን ጉልበቱን የሚያስተካክልበት፣ ቅርጽ የሚቀይርበት ጡንቻዎች እያረጁ ስለሚሄዱ ነው ይላሉ። በወጣትነት ዘመን ብሌን ለርቀት፣ ለመካከለኛ እና ለቅርበት ዕይታ የሚሰጠው ቀላል ምላሽ ዕድሜ ሲገፋ ለመታዘዝ ይደክማል። በዚህ ጊዜ አጋዥ መነጽሮች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። በሌላ በኩል ዕድሜ ሲገፋ ሞራ (Cataract) የተሰኘው የዐይን ክፍል “ጉም በመያዝ” ብርሃን ለማስተላለፍ ይቸገራል። ይህም “ጭጋግ የሆነ ዕይታ ሊያመጣ ይችላል። በተወሰነ ደረጃ በመነጽር ሊረዳ ይችላል። ግን እየገፋ ሲሄድ ደግሞ በቀዶ ህክምና ብቻ የሚስተካከል ሊሆን ይችላል” ይላሉ - የዐይን ህክምና ስፔሻሊስቱ። በዕድሜ ምክንያት ዐይን ላይ የሚመጡ ችግሮች አንዳንዶቹ በህክምና መመለስ የሚችሉ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ ህክምና ላይመልሳቸው ይችላል። ዶክተር ዮናስ “ሰዎች ዐይናቸው ሥራ እንዳቆመ ድንገት ሊያውቁ ይችላሉ እንጂ ዐይን ድንገት አይጠፋም” ይላሉ። ቀደም ብሎ የነበረ እና በህክምና ያልታየ ችግር በሂደት ዐይንን እስከ ማሳወር ሊያደርስ ይችላል። በተለይ “የዐይን ብርሃን ሌባ” ተብሎ የሚታወቀው ግላኮማ ምንም ምልክት ሳይሰጥ ለረጅም ጊዜ የዐይን ነርቭን ጎድቶ ሥራውን ሊያቆም ይችላል። ለዚህ ነው ሰዎች ከ40 ዓመት ዕድሜ በኋላ በየዓመቱ የጤና ምርመራ ማድረግ እንዲያደርጉ የሚመከረው።", "የቬትናም ፖሊስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የነበሩ ኮንዶሞች ያዘ የቬትናም ፖሊስ ከ320ሺህ በላይ ታጥቦ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውል የነበረ ኮንዶም መያዙን አስታወቀ። የቬትናም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ኮንዶሞች ሊሸጡ የነበረው በኮንዶሞቹ ጥራት ላይ ጥያቄ ለማያነሱ ግለሰቦች ነው። ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ታጥበው ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ በተዘጋጁ ኮንዶሞች የተሞሉ ሻንጣዎች ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። ፖሊስ እንዳለው ከሆነ ሕገ-ወጥ ኮንዶሞቹ የተያዙት በአገሪቱ ደቡባዊ አቅጣጫ በአንድ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ነው። የመጋዘኑ ባለቤት ነች የተባለችው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ተዘግቧል። ጥቅም ላይ የዋሉት ኮንዶሞች ከታጠቡ በኋላ የወንድ ልጅ ብልት ቅርጽ ባለው አንጨት ላይ ይለጠጡ እና ዳግም ታሽገው ለገበያ ይቀርባሉ ተብሏል። በቁጥጥር ሥር የዋለችው የመጋዘን ባለቤት በአንድ ኪሎ ግራም ኮንዶም 0.13 ዶላር ተስማምታ ወደ ሥራው መግባቷን ለፖሊስ ቃሏን ሰጥታለች። ጥቅም ላይ ውለው ዳግም ለገበያ የሚቀርቡት ኮንዶሞች ዋጋ እንዲሁም ጥቅም ላይ የዋሉ ኮንዶሞች እንዴት እንደሚሰበሰቡ የተባለ ነገር የለም።", "ለ78 ጊዜ የኮቪድ ምርመራ አድርጎ 'ፖዘቲቭ' የሆነው ግለሰብ ቱርካዊው ሙዛፈር ካያሳን የደም ካንሰር ህመምተኛ ሲሆን ከዓመት በፊት ባደረገው ምርመራ የኮሮናቫይረስ እንዳለበት ሲነገረው ተስፋ ቆርጦ ነበር። ነገር ግን ኮቪድ ከነበረበት የካንሰር ህመም ጋር ተደምሮ የከፋ ችግር ሳያስከትልበት ወራት ተቆጥረው ከዓመት በላይ ሆኖታል። ኮቪድ-19 የያዛቸው አብዛኞቹ ሰዎች ለጥቂት ሳምንታት ከታመሙ በኋላ አገግመው ከቫይረሱ ነጻ ይሆናሉ፤ የተወሰኑት ተደግሞ በሚፈጠርባቸው የጤና እክል ለሞት ሊዳረጉ ይችላሉ። የሙዛፈር ግን የተለየ ነው፤ ባለፉት 14 ወራት ለ78 ጊዜ ምርመራ አድርጎ አስካሁን ድረስ ፖዘቲቭ ነው። ከዚህ አንጻር በኮቪድ ተይዞ ለረጅም ጊዜ ቫይረሱ ከሰውነቱ ሳይጠፋ የቆየ የመጀመሪያው ሰው ሳይሆን አይቀርም።", "ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ውጤትን በ30 ደቂቃ ውስጥ ማወቅ ሊቻል ነው ኮቪድ-19ን በደቂቃዎች ውስጥ የሚለይ ምርመራ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመለየት ስራን በእጅጉ ያሳድጋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ። አምስት ዶላር ብቻ የሚያስወጣው ይህ ምርመራ ሃብታም ባልሆኑ እና የጤና ባለሙያዎችና የላብራቶሪ እጥረት ባለባቸው አገራት የኮቪድ-19 ሕሙማንን ለመለየት በእጅጉ ይረዳል ተብሏል። መመርመሪያውን ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር የተደረገ ስምምነት በስድስት ወር ውስጥ 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ያስችላል። ይህንን እርምጃ የጤና ድርጅቱ የበላይ ኃላፊዎች \"ጉልህ ሚና የሚጫወት\" ብለውታል። በበርካታ አገራት ምርመራ ከተደረገ በኋላ ውጤት ለማወቅ የሚፈጀው ጊዜ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚያርጉትን ትግል ጎድቶት ቆይቷል። እንደ ሕንድና ሜክሲኮ ባሉ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ በተሰራጨባቸው አገራት በፍጥነት መርምሮ ውጤቱን ማወቅ አለመቻል የወረርሽኙን የመስፋፋት ፍጥነት ትክክለኛ ምስል ማሳየት አልቻለም ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ አዲሱ \"ተንቀሳቃሽ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ\" መመርመሪያ ውጤትን ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰኞ እለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ግን የኮሮናቫይረስን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት ካልሆነም ቀናት እንደሚፈጅ ይታወቃል። አቦት እና ኤስዲ ባዮሴንሰር የተባሉ መድሃኒት አምራቾች ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ስምምነት መድረሳቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረው ገልፀዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት የሚመረቱ መመርመሪያዎች በቫይረሱ በጣም የተጎዱ የላቲን አሜሪካ አገራትን ጨምሮ ለ133 አገራት ይሰጣል ተብሏል። \"ይህ በተለይ ከፍተኛ ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች የመመርመር አቅም ላይ ትልቅ እመርታ የሚፈጥር ነው\" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። አክለውም \"ላቦራቶሪ በሌላቸውና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ወይንም ምርመራውን ለማካሄድ በቂ የሰለጠነ ባለሙያ በሌለበት አካባቢ የመመርመር አቅምን ያሰፋል።''", "ኮሮናቫይረስ፡ የአውሮፓ አገራት በአስትራዜኒካ ክትባት ጉዳይ ለሁለት ተከፍለዋል የአውሮፓ አገራት አስትራዜኒካ ክትባትን ለሕዝባቸው በማደልና ባለማደል ጉዳይ ለሁለት እንደተከፈሉ ናቸው፡፡ ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ ክትባት የደም መርጋትን አስከትሏል የሚለው መረጃ ነው አገራቱን እያወዛገባቸው ያለው፡፡ የተወሰኑ አገራት ክትባቱን መስጠት እንደቀጠሉ ሲሆን አንዳንድ አገራት ግን ነገሮች እስኪጠሩ በሚል ያዝ አድርገውታል፡፡ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ስፔንና ጣሊያን የአውሮፓ ኅብረት ክትባቱን ፈትሾ ችግር የለውም የሚል ሪፖርት ካልሰጠን ለሕዝባችን አናድልም ብለው አቋም ወስደዋል፡፡ ነገር ግን እነ ፖላንድና ቤልጂየም ክትባቱን ለሕዝባቸው መስጠታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲ አስትራዜኒካ ክትባት በእርግጥም የደም መርጋት ያስከትላል ወይ የሚለውን እየመረመረ ሲሆን ነገ ሐሙስ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ትናንት ማክሰኞ የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲ በሰጠው መግለጫ ክትባቱ የከፋ የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው እና ክትባቱን ካለመውሰድ፣ መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ እንደሚያምን ተናግሮ ነበር፡፡ የኤጀንሲው ኃላፊ ኤመር ኩክ እንዳሉት የደም መርጋት የተከሰተው ከጠቅላላው ክትባት ወሳጅ እጅግ በተወሰኑ ሰዎች ሲሆን ይህም መከተብን ተከትሎ ስለመሆኑ ገና አልተጣራም ብለዋል፡፡ \"ማሳሰብ የምፈልገው ነገር ቢኖር ደማቸው ረጋ የተባሉት ሰዎች ክትባቱን በመውሰዳቸው ነው ያ የሆነው የሚለው ገና አልተረጋገጠም\" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የኤጀንሲውን አስተያየት 'ተስፋን የሚሰጥ' ብለውታል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የዓለም ጤና ድርጅት የሊቃውንት ቡድን ትናንት ማክሰኞ በጉዳዩ ላይ አንዳች ውሳኔ ላይ ለመድረስ ተሰብስቦ የነበረ ሲሆን የደም መርጋቱ ክትባቱን ከመውሰድ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው አገራት ክትባቱን መስጠት ማቆም አይጠበቅባቸውም፡፡ ክትባቱን መስጠቱ ነው የሚበጀው ሲል መክሯል፡፡ በታላቋ ብሪታኒያ እስከአሁን ወደ 11 ሚሊዮን ሰዎች ቢያንስ አንዲት ቀንጣት አስትራዜኒካ ክትባትን መውሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡ ከ11 ሚሊዮን ዜጎች እስከአሁን የደም መርጋትም ሆነ ሞት ስለመመዝገቡ መረጃ የለም፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ 13 የአውሮጳ አገራት ክትባቱ ‹ለማንኛውም ይቆየን› ብለው እደላውን ያቆሙ ሲሆን ይህን እርምጃ በመውሰድ ረገድ ዴንማርክን የቀደማት የለም፡፡ ከዴንማርክ ሌላ ኖርዌይ አይስላንድ ጀርመን ፈረንሳይ ጣሊያን፣ ሳይፕረስ ስፔን ላቲቪያና ስዊድን ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጀርመን ፈረንሳይና ጣሊያን የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ይፋ አድርገዋል፡፡ ሁሉም የአውሮፓ አገራት የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲን ግምገማ ተከትሎ አስትራዜኒካ ክትባትን ለሕዝቦቻቸው ማደላቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡", "ኮቪድ ያሰራጨው የቬትናም ዜጋ አምስት ዓመት ተፈረደበት አንድ ቬትናማዊ ግለሰብ የኮቪድ-19 መመሪያዎችን በመጣስ እና ቫይረሱን በማሰራጨት ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደበት። ሊ ቫን ትሪ አደገኛ እና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ በሽታን በስምንት ሰዎች ላይ በማሰራጨት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈበት። ግለሰቡ ኮቪድ ካስያዛቸው ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ተብሏል። እስከ ቅርብ ጊዜያወት ድረስ ቬትናም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በመቆጣጠርና ጥብቅ መሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ አገር ነበረች። ነገር ግን ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ አዲሱ ዴልታ የተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ በአገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። እስካሁን ድረስም በቬትናም ከ530 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 13ሺህ 300 ሰዎቸው ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ከዚህ ቁጥር አብዛኛው የተመዘበው ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ መሆኑ ነገሮች ምን ያክል አሳሳቢ ስለመሆናቸው ማሳያ ነው ተብሏል። በስርጭት ደረጃ ደግሞ ሆ ቺ ሚኒ ከተማ ውስጥ በርካቶች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ የተባለው የ28 ዓመቱ ሊ ከሆ ቺ ሚኒ ከተማ ተነስቶ ወደ ትውልድ አካባቢው ካ ማው ግዛት በሞተር ሳይክል ተጉዟል። ካ ማው ከደረሰ በኋላ ደግሞ ስለ ጉዞ ታሪኩ እና ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለተጠየቀው ጥያቄ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥቷል፤ በተጨማሪም እራሱን መለየት ሲገባው ይህንን መመሪያ ተግባራዊ አላደረገም። የአካባቢው ባለስልጣናት ከወራት በፊት እንዳስታወቁት ማንኛውም ተጓዥ ወደ ካ ማው ግዛት ሲገባ እራሱን ለ21 ቀናት ላይቶ ማቆየት ግዴታ ነው። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሊ የኮቪድ19 ምርመራ ሲደረግለት በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን በወቅቱም ቫይረሱን ለቤተሰቡ አባላት እንዲሁም ለህክምና የሄደበት የጤና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አስይዟል። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ሊ አምስት ዓመት እስራት እና 880 ዶላር መቀጮ ፈርዶበታል።", "አዲሱ ክልል አራት ዋና ከተሞች እንዲኖሩት ማድረጉ የሚኖረው አንደምታ በይፋ ተመሰረተ የወራት ዕድሜ ያለው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዲስ የከተሞች ማዕከላትን ለመስተዳደሩ ተቋማት ለማደራጀት ወስኗል። ሌሎቹ ክልሎች ማዕከላቸውን በአንድ ዋና ከተማ አድርገው ቢሮዎቻቸው በአንድ ስፍራ ላይ እንዲዋቀሩ በማድረግ ይታወቃሉ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ግን ከሌሎቹ በተለየ ለየት ያለ አደረጃጀትን ለመከተል መርጧል። በዚህም ከትናንት በስተያ ረቡዕ ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም. የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አራት ዋና ከተሞች እንዲኖሩት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለክልሉ ምክር ቤት አቅርቧል። ይህ ረቂቅ ሕግ የሚጸድቅ ከሆነ በክልሉ ካሉ ስድስት ዞኖች በአራቱ የዞን ከተሞች የክልሉ መስተዳደር ዋና ዋና አካላት መቀመጫ ይሆናሉ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል አካል የነበሩት ስድስት ዞኖች ተባብረው የመሠረቱት ክልል ነው። በረቂቁ መሠረትም ቦንጋ የፖለቲካ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት መቀመጫ ትሆናለች። ተርጫ የክልሉን ምክር ቤት መቀመጫ፣ ሚዛን አማን የዳኝነት መዋቅሩ የሚገኝበት እንዲሁም ቴፒ የብሔረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫን ይይዛሉ። ሥራ አስፈጻሚ ቢሮዎች ደግሞ በአራቱም ከተሞች ፍትሃዊ ሆነው ይመደባሉ ተብሏል። ይህ አዲስ የክልል አደረጃጀት የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩበት ነው። አንዳንዶች የክልሎችን ሥራና ሃብት በአንድ ከተማ ላይ ብቻ በማከማቸትን በማፍሰስ ከሌሎች ከተሞች በበለጠ አንድ ከተማ ብቻ በላቀ ሁኔታ እንዲያድግና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያደርገውን አሰራር ይለውጣል ሲሉ ይደመጣል። ሌሎች ደግሞ ይህ የክልል መስተዳደር ተቋማትን በተለያዩ ከተሞች ውስጥ እንዲቀመጡ ማድረግ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚፈልጉ ነዋሪዎችን ለወጪ እና እንግልት ከመዳረጉ ባሻገር፣ በክልሉ ተቋማት መካከል በቅርበት በትብብር የመስራት ዕድልን ከማጓደል ባሻገር አባካኝ ሊሆን ይችላል በማለት ስጋታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ደያሞ ዳሌ ቀደም ሲል በደቡብ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ይሰሩ የነበሩ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ናቸው። ይህ የክልሉ አስተዳደር እቅድ የክልሉን ነዋሪዎች ሊያጉላላ ይችላል ሲሉይናገራሉ። የክልሉ መንግሥት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደው “በፖለቲካዊ ውሳኔ” ነው የሚሉት አቶ ደያሞ፤ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አንድ ክልል ከአንድ በላይ ከተማ ሲኖረው ታይቶ እንደማይታቅ በማስታወስ ነው። ጨምረውም እንዲህ አይነቱ ልምድ ያለው በሰለጠኑት አውሮፓ አገራት ውስጥ ነው ይላሉ። “እንዴት ተግባራዊ ያደርጉታል የሚለውን ባለቤቶቹ ናቸው የሚያውቁት። ይህም ወደፊት የምናየው ይሆናል። ወጪው ከፍተኛ ይሆናል” ይላሉ አቶ ደያሞ። ረቂቅ ሕጉ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠትም ሆነ፤ አገልግሎት ለማግኘት ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ ነው የሚሉት አቶ ደያሞ አራቱ ከተሞቹም የተመረጡበት መስፈርትም ግልጽ አይደለም ይላሉ። “አራቱ ከተሞች በምን ተመረጡ? ትላልቅ ስለሆኑ ነው የተመረጡት ወይስ ከዞኖች ተወጣጥተው ነው? ያልደረሳቸው ከተሞች ቅሬታስ እንዴት ይፈታል?” ሲሉ ይጠይቃሉ። የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው፤ በክልሉ ያሉ ነዋሪዎችን ፍላጎት ለማማከል ሲባል ከዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን ይናገራሉ። ይህ ክልል ሲመሰረት ማዕከላዊ ከተማው ማን ይሆናል የሚለው ብዙ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ነበር ይላሉ አቶ ፀጋዬ። “አንዳንድ ከተሞች ማዕከላዊ ከተማው እኛ ጋር ካልሆነ ክልሉን አንቀላቀልም የሚል አቋም ይዘው ስለነበር፤ በወቅቱ የነበረው አመራርም ሆነ ክልሉ ሲመሰረት የነበረው አመራር ከአንድ በላይ የማዕከል ከተማ ይኖራል በሚል ተነጋግረው ነበር” ይላሉ። “ሰው ሳይጉላላ እና ሥራ ሳይጎዳ እንዴት አድርገን ነው ብዘሃ ከተሞችን የምንፈጥረው በሚለው ላይ ተነጋግረን አጠናቀናል” ይላሉ። አንድ ነዋሪ ጉዳይ ለማስፈጸም ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ሳይጓዝ ጉዳዩን ባለበት መጨረስ የሚያስችሉ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮዎችም ታስበዋል ይላሉ። “ከአንድ ቢሮ ወደ ሌላ ቢሮ የሚሸጋገሩ ተግባራት ካሉ፤ አገልግሎቱን የሚሰጡ ላይዘን ጽ/ቤቶች አብረን ለመፍጠር ነው ያሰብነው” ይላሉ። በክልሉ የመንግሥት ተወካይ የሆኑት አቶ ፀጋዬ፤ ክልሉ አራት መዲናዎች እንዲኖሩት መደረጉ ተጨማሪ ወጪ ያስከትላል የሚል እምነት የለንም በማለት ይናገራሉ። “ለምሳሌ አንድ ቢሮ በጀት ቢፈልግ ለፋይናንስ ቢሮ ወረቀት ይልካል እንጂ፣ በአካል ወደ አንድ ከተማ መጥቶ ገንዘብ አይወስድም፤ ስለዚህ የተለየ ወጪ አይኖርም” በማለት ያስረዳሉ። በየትኛው ከተማ ምን አይነት ቢሮዎች ይኑሩ የሚለው ቀድሞ በስምምነት የተደረሰበት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ፀጋዬ፤ “በዚህ ከተማ ይህ ቢሮ ይኑር የተባለው በስምምነት እንጂ በሳይንሳዊ ምክንያት አይደለም” ይላሉ። የክልሉ ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁን ተወያይቶ ካጸደቀው በኋላ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር አቶ ፀጋዬ ገልጸዋል። ይህ በአገሪቱ ካሉ ሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ የተደራጀው የአዲሱ ክልል አስተዳደር መዋቅር ድጋፍም ጥያቄም ከተለያዩ ወገኖች እየተነሱበት ነው። ነገር ግን ከክልሉ ብዝሃነት አኳያ ማዕከሉን በአንድ ስፍራ አድርጎ የእድገትም ሆነ ሌሎች ዕድሎችን በአንድ ከተማ ላይ ከማከማቸት ይልቅ በተለያዩ ስፈራዎች መሆኑን በአዎንታ የሚመለከቱት አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የክልሉ የመንግሥት ሥራዎችና አገልግሎቶችን በተለያዩ ስፍራዎች ላይ እንዲሆኑ መደረጋቸው ለሕዝቡ እንግልት፣ በክልሉም ላይ ከፍተኛ ወጪን ሊያስከትላል የሚችል ነው ይላሉ። ቢሆንም ግን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ያስተዋወቀው አዲስ የከተሞችና የአስተዳደር ተቋማት አወቃቀር ሊኖረው የሚችለው ጥቅምም ሆነ የሚገጥመው ተግዳሮት ወደ ፊት የሚታይ ነው።", "ሩሲያ ዩክሬን ድንበር ላይ ወታደር እያሰፈረች ያለችው ለምንድነው? ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ሩሲያ ባልተለመደ ሁኔታ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋቷ አዲስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ፍርሃት ፈጥሯል፡፡ ሩሲያ በበኩሏ ዜጎቼን ለመታደግ ነፍጥ ላነሱ ተገንጣይ ቡድኖች እገዛ አደርጋለሁ ብላለች፡፡ አንድ የሩሲያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን እንዲያውም ‹ሞስኮ በምሥራቅ ዩክሬን ሩስኪ ተናጋሪ የሆኑ ተገንጣዮችን ለመደገፍ ሁሉንም እገዛ ታደርጋለች› ብለዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ጨምረውም ዩክሬን በተገንጣዮቹ ላይ እጇን ካነሳች ደግሞ ሞስኮ ሳታወላውል ጦር ታዘምታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሩሲያ የሚደገፉ ተገንጣዮች በምሥራቅ ዩክሬን ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ ከገቡ ሰነባብተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ሩሲያ ወታደሮቿን ወደዚያው ድንበር ማስጠጋቷን ገፍታበታለች፡፡ ባለሥልጣኑ ዲምትሪ ኮዛክ ሩሲያ ዜጎቿን የመጠበቅ ግዴታና ኃላፊነት አለባት ብለዋል፡፡ ‹‹ሁሉም ነገር የሚወሰነው በዩክሬን ጠብ አጫሪነት መጠን ነው› ሲሉም ሊወሰድ ስለሚታሰበው እርምጃ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ እኚሁ ባለሥልጣን ዩክሬን በሩሲያ ተናጋሪ ሕዝቦች ላይ እጇን ካነሳች ምናልባትም የዩክሬን መጨረሻ ሊሆን ይችላል ሲሉ ነገሩ የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡ ዩክሬን ላይ ከተኮስን እግር ላይ ሳይሆን ፊት ላይ ነው የሚሆነው ሲሉም በወታደራዊ ቋንቋ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡ ሩሲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ብታስጠጋም ለክፋት እንዳልሆነ ስትናገር ነበር የቆየችው፡፡ የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጄን ወደ ድንበር የተጠጉ የሩሲያ ወታደሮች ብዛት በ2014 ከነበሩት በላይ ናቸው ብለዋል፡፡ ሩሲያ በዚህ ዓመተ ምሕረት ዩክሬንን መውረሯ አይዘነጋም፡፡ ዋይት ሐውስ ጉዳዩን አሳሳቢ ብሎታል፡፡ አንድ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች እየተጋራ የሚገኝ ተንቀሳቃሽ ምሥል ሩሲያ ከባባድ መሣሪያዎችን ወደ ዩክሬን ድንበር ስታመላልስ የሚያሳይ ነው፡፡ በዩክሬን ወታደሮችና በሩሲያ የሚደገፉት ምሥራቅ ተገንጣዮች መካከል በዶንባስ ግዛት ወታደራዊ ግጭቶች ባለፉት ወራት ጨምረው ነበር፡፡ ባለፈው ሐሙስ አንድ የዩክሬን ወታደር በግጭት መሞቱ በዚህ ዓመት የተገደሉ ወታደሮችን ቁጥር 25 አድርሶታል፡፡ ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ በግጭቱ 50 ወታደሮች ሞተው ነበር፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲመር ዘለኔስኪ ሐሙስ ወታደራቸው ከተገደለ በኋላ አካባቢውን መጎብኘታቸው ሌላ ውጥረት ፈጥሯል፡፡ ያንኑ ቀን ሐሙስ ነገሮች መስመር እንዳያልፉ በሚል የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንግላ ሜርክል ወደ ፑቲን ስልክ መተው ነገር እናብርድ ሲሉ ተማጽነዋል፡፡ ሜርክል ሩሲያ ወታደሮቿን ከድንበር ዘወር እንድታደርግ ነበር ቪላድሚር ፑቲንን የጠየቁት፡፡ በ2014 ሩሲያ የዩክሬን አካል የነበረችውን ክሪሚያ ግዛትን በኃይል በቁጥጥር ሥር ማድረጓ ይታወሳል፡፡ ይህ ክስተት ምዕራባዊያንን ፍጹም ያስደነገጠ ነበር፡፡ የሩሲያን ወረራ ተከትሎም የአውሮጳ ኅብረትና አሜሪካ በሩሲያ ላይ ከባድ ያሉትን ማዕቀብ ጥለው ቆይተዋል፡፡ ይህን የሩሲያን ወረራ ተከትሎ እነዚህ ተገንጣዮች በዶንባስ ክልል የዶኔስክ እና ሉሃነስክ ግዛትን ተቆጣጥረዋል፡፡ በዶንባስ በአመዛኙ የሩስኪ ተናጋሪዎች ናቸው የሚበዙት፡፡ ሩሲያና ዩክሬን በነበራቸው የተራዘመ ግጭት ቢያንስ 14ሺ ወታደሮች እንደሞቱ ይገመታል፡፡", "በፖሊስ የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ቤተሰቦች 15 ሚሊዮን ዶላር ሊከፈላቸው ነው የአሜሪካዋ ኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ባለሥልጣናት ከፖሊስ ጋር በነበረ እሰጣገባ ምክንያት የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ቤተሰቦች 15 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንደሚከፈላቸው አስታውቀዋል። የ23 ዓመቱ ኢላይጃህ ሸነን ማክሌይን በፈረንጆቹ 2019 አውሮራ በምትባል ሥፍራ ነው ሕይወቱ ያለፈው። ግለሰቡ ሕይወቱ ከማለፉ ከሶስት ቀናት በፊት ሶስት ፖሊሶች አስቁመውት አደገኛ ማደንዘዣ መደኃኒት ሰጥተውት ነበር። የሟች ቤተሰቦች ባለፈው ዓመት ክስ መሥርተው ፖሊስ ለኢላይጃህ ሞት ኃላፊነቱን እንዲወስድ ሲጠይቁ ነበር። የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት በስህተት በተፈፀመ ሞት አማካይነት ይህን ያክል ገንዘብ ለከሳሽ ስትከፍል የመጀመሪያዋ ነው። የኢላይጃህ እናት ሺና የሕግ አማካሪ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው እናቱ ሕዝቡ ባሳያቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውንና የልጃቸው ሞት \"ከባድ ለውጥ ለሚያስፈልገው\" ፖሊስ እንደምክንያት እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። በሟች ቤተሰብ በፖሊስ መካከል የተገባው ስምምነት ምን እንደሚያካትት እስካሁን ይፋ አልተደረገም። የኢላይጃህ ጉዳይ ይበልጥ ትኩረት ያገኘው ምንም ዓይነት መሣሪያ ሳይታጠቅ ባለፈው ዓመት በፖሊስ የተገደለው ጆርጅ ፍሎይድ ክስተት አሜሪካን ካናወጠ በኋላ ነው። ወጣቱ ኢላይጃህ ነሃሴ 24/2019 ዴንቨር ውስጥ በምትገኘው አውሮራ ካለ አንድ ጎዳና ላይ ብቻውን ሲራመድ ሶስት ፖሊሶች ያስቆሙታል። አንድ ተጠርጣሪ እያፈላለጉ ያሉት ፖሊሶች በተሰጣቸው ጥቆማ መሠረት ኢላይጃህ \"ተጠርጣሪውን መስሎን ነበር\" ሲሉ ተናግረው ነበር። ሶስቱ ፖሊሶች ኢላይጃህ ታጥቆ እንደሆን ለመፈተሽ ቢሞክሩ ወጣቱ ግን እንዳይነኩት በመፈለግ ይሸሻል። ከፖሊስ ካሜራ ላይ የተገኘው ምስል እንደሚያሳየው ኦቲዝም ያለበት ኢላይጃህ \"እኔ ከቤት ብዙ አልወጣም፤ እባካችሁ ብዙ አትቅረቡኝ\" እያለ ነበር። ነገር ግን የፖሊስ መኮንኖቹ በግድ ይዘውት ከመሬት ያጣብቁታል። የኢላይጃህ ቤተሰብ ፖሊስ አላስፈላጊና ከመጠን በላይ የሆነ ኃይል ተጠቅሟል፤ ይህ ሲሆን ልጃችን እያስመለሰ ነው፤ መተንፈስ አቃተኝ እያለ ነበር ሲሉ ከሰዋል። ፖሊሶቸ ተጨማሪ እርዳታ ከጠሩ በኋላ 500 ግራም ኬታሚን የተባለ አደንዛዥ መድኃኒት እንደወጉት ተነግሯል። ከሶስት ቀናት በኋላ የኢላይጃን አእምሮ ሙሉ በመሉ መሥራት አቆመ። ከሁለት ዓመታት በኋላ ሶስቱ ፖሊሶችና መድኃኒቱን የወጉት ሁለት የሕክምና ሰዎች በ23 መዝገቦች ተከሰዋል። የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦች ተመሳሳይ ክስ ፖሊስ ላይ መሥርተው 27 ሚሊዮን ዶላር እንደተከፈላቸው ይታወሳል።", "የአንጎላ “የሰላም መሃንዲስ” በ79 ዓመታቸው አረፉ በማዕድን የበለጸገችውን አንጎላን ለአራት አስርት ዓመታት ያህል የገዙት ሁለተኛው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ሆሴ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። ዶሳንቶስ ስፔን ውስጥ የልብ ህመም በሽታ ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ሕይወታቸው አልፏል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶስ ሳንቶስ በአውሮፓውያኑ 2000 መጀመሪያ ላይ በአንጎላ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ የቆየውን የእርስ በርስ ጦርነት በመቋጨት ታሪክ ይዘክራቸዋል። ለዚያም ነው ደጋፊዎቻቸው “የሰላም መሃንዲስ” እያሉ የሚጠሯቸው። ነገር ግን በሥልጣን ዘመናቸው በተፈጸሙ መጠነ ሰፊ ሙስና እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ ምክንያት በርካቶችም የሚተቿቸው አልጠፉም። ዶስ ሳንቶስ በቀድሞዋ የሶቭየት ኅብረት በፔትሮሊየም ምህንድስና ዲግሪያቸውን ያገኙት በአውሮፓውያኑ 1969 ነበር። የመጀመሪያው የአንጎላ ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ አጎስቲንሆ ኔቶ ከሞቱ ከአስር ዓመታት በኋላ ሁለተኛው ፕሬዚዳንት በመሆንም አንጎላን መርተዋል። ሥልጣን ሲቆናጠጡ ገና የ37 ዓመት ወጣት ነበሩ። ከቅኝ ግዛት ነጻነቷን በአውሮፓውያኑ 1975 የተጎናጸፈችው አንጎላ ከአራት ዓመታት በኋላ የፖርቹጋል ቅኝ ግዛትን የተዋጉት የዶስ ሳንቶስ ኤምፒኤልኤ እና ዩኒታ በሚባሉ ቡድኖች በተፈጠረው ቁርሶ አገሪቷ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገባች። ለ27 ዓመታት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነትም አገሪቷን አፈራረሳት። በጦርነቱ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም በዚህ ጦርነት የውጭ አገራት ኃይሎች ተሳታፊ ሆነዋል። በአፓርታይድ የነጮች አገዛዝ ስር የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ወታደሮች አማጺው ዩኒታ የተሰኘውን ቡድን እንዲደግፉ ስትልክ፣ የኩባ ኃይሎች ደግሞ ለመንግሥት ወግነው ጣልቃ ገብተዋል። ዶስ ሳንቶስ ሶቭየት ኅብረት እስትክትፈርስ እንዲሁም የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተሚያ ድረስ በማርክሲስት ርዕዮተ ዓለም ላይ ያተኮረ የአንድ ፓርቲ መንግሥትን መርተዋል። ኤምፒኤልኤ እና ዩኒታ የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ግን ሁኔታዎች መቀየር ጀመሩ።", "የታይዋን ፓርላማ አባላት የአሳማ ስጋ በመወርወር ተቃውሟቸውን ገለፁ የታይዋን የተቃዋሚ ፓርላማ አባላት የአሳማ ስጋ በመወርወርና በቡጢም በመደባደብ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። ከአሜሪካ የሚገባው የአሳማ ስጋ ምርት ጋር የተያያዘው መመሪያ ቀለል ብሏል በሚልም ነው ፓርላማው ውስጥ ይህ የተፈጠረው። በቅርቡም የታይዋን መንግሥት ከአሜሪካ እንዲገባ የፈቀደው የአሳማ ስጋ ራክቶፓሚን የሚባል ሱስ የሚያስይዝና በታይዋንና በአውሮፓ ህብረት የታገደ ንጥረ ነገር የያዘ ነው ተብሏል። ንጥረ ነገሩ ለጤና ስጋትም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ታይዋንም ለአሳማ ስጋዎች ጥቅም ላይ እንዳይውል ከልክላዋለች። ገዢው ፓርቲው በበኩሉ ይህን ክስ ያስተባበለ ሲሆን ምክንያታዊ ወደሆኑ ንግግሮችም እንዲመለሱ ጠይቋል። እንዲህ አይነት ቁጣዎችና ድብድቦች ለታይዋን ፓርላማ አዲስ አይደሉም። የታይዋን ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ኩዎሚንታ (ኬኤምቲ) ፓርቲ የአሳማ አንጀትና ስጋ በባልዲ ይዘው ወደ ፓርላማ በማምጣትና በመወርወር ጠቅላይ ሚኒስትር ሱ ሴንግ ቻንግ ጥያቄና መልስ እንዳያካሂዱም ለማድረግ ሞክረዋል። የአሳማ አንጀት መወርወር ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚው ፓርቲ ኬኤምቲና ቼን ፖ ዌይ በተባለው ፓርቲ አባላት መካከልም ቡጢ እንደተሰነዘረም ሮይተርስ የዜና ወኪል አስነብቧል። ገዢው ዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ \"አፀያፊ ተቃውሞ\" በሚል ያወገዘው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ምግብ መባከኑና ፓርላማውም በመጥፎ ጠረን መታወዱን የማይገባ ተግባር ነው ብሎታል ። ፓርላማው ወደ ምክንያታዊ ክርክር እንዲገባም ጥያቄ ቀርቧል። የታይዋን ፕሬዚዳንት ትሳይ ኢንግ ከአሜሪካ የሚገባውን የአሳማ ስጋ ምርት በማስመልከት የተጣለውን መመሪያ ያቀለሉት ነሐሴ ወር ላይ ሲሆን፤ ከጥር ጀምሮም ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። ውሳኔው አሜሪካን ሲያስደስት የታይዋን ተቃዋሚዎች ግን ህዝቡ ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን የጤና እክል በማንሳት ተግባራዊ እንዳይሆን ይሞግታሉ። ከዚህ ቀደምም በርካታ ሰልፈኞች ተቃውሟቸውን ገልፀው ነበር። ሱስ ያስይዛል የሚባለው ራክቶማፖን በታይዋል፣ በቻይናና በአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ለሰው ልጅና ለእንስሳት ከሚያስከትለው የጤና ስጋት ጋር ተያይዞም እግድ ተጥሎበታል። ዩዋን የተባለው የታይዋን ፓርላማ ቡጢ መሰነዛዘር፣ ፀጉር መጎተት፣ የውሃ ፕላስቲክ መወርወርንም በአመታት ውስጥ አስተናግዷል። በተለይም ከሶስት አመት በፊት የመሰረተ ልማት ፍሰት ላይ በተነሳ ክርክር የፓርላማ አባላቱ ወንበር አንስተው ሲወራወሩ ነበር።", "ትግራይ ፡ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም (አምባዬ) መስፍን በትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ወታራዊ ግጭትን ተከትሎ በተፈላጊነት የስም ዝርዝራቸውን ካወጣው ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን በአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች ረቡዕ ጥር 05/2013 ዓ.ም መገደላቸው ተገልጿል። አቶ ስዩም መስፍን ከፍተኛ የህወሓት አመራር ሆነው ከሃያ ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የአገሪቱ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን ከህወሓት የትጥቅ ትግል ጀምሮ ከፍተኛ ተጽእኖ የነበራቸው ግለሰብ እንደነበሩ ይነገራል። ስዩም (አምባዬ) መስፍን ስዩም መስፍን በ1940ዎቹ መጀመሪያ ትግራይ ውስጥ አዘባ ተብሎ በሚጠራ የአጋሜ አውራጃ ቀበሌ ነው የተወለዱት። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲ ግራት ከተማ አግአዚ ትምህርት ቤት በመከታተል፤ በባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዲፕሎማ ምሩቅ ናቸው። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡት አቶ ስዩም፤ በዩኒቨርሲቲው የትግራይ ተማሪዎች ማኅበርን ካቋቋሙት መካከል አንዱ ናቸው። በ1965 ዓ.ም ማኅበሩ በድብቅ ወደ ተመሰረተው የትግራይ ብሔር የፖለቲካ ቡድንነት ሲሸጋገር ስዩም ፓርቲውን ከመሰረቱት ሰባት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አንዱ ነበሩ። የንጉሡ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመመስረት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ፤ የትግራይ ብሐር ፓርቲ አባላትም \"የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች በትጥቅ ትግል ነው የሚፈቱት\" በማለት ጠመንጃ አንስተው ትግል ለመጀመር ወደ ትግራይ በረሃማ አካባቢዎች ሄዱ። አቶ ስዩም መስፍንም የዚህ ውሳኔ አካል ሆነው ከጓዶቻቸው ጋር ወደ ትግራይ አቀኑ። ስዩም - በትጥቅ ትግል የትግራይ ሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ ትጥቅ ትግል እንዲጀመር ከተወሰነ በኋላ የንቅናቄው አመራር በሦስት የተለያዩ መንገዶች የተሰጠውን ዓላማ እንዲፈጽም ተወሰነ። አንዱ ቡድን ወደ ደደቢት በረሃ በመሄድ የትጥቅ ትግሉ መጀመርን ይፋ እንዲያደረግ፣ ሁለተኛው ወደ ኤርትራ በመሄድ የትጥቅ ትግል ተሞክሮ እንዲወስድ፣ ሦስተኛው ደግሞ በከተማ ውስጥ ፖለቲካዊ ሥራዎች እንዲመራ ተደረገ። በዚህም አቶ ስዩም መስፍን ወደ በረሃ በመሄድ የትጥቅ ትግሉን ከጀመሩት አስራ አንድ ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ቤተሰባቸው አምባዬ ብሎ መጠሪያ ስም ያወጣላቸው አቶ ስዩም፤ ወደ ትጥቅ ትግል ከሄዱ በኋላ ግን ሁሉም ስማቸውን ሲቀይሩ አብረዋቸው ከነበሩት ጓዶች መካከል አንዱ የሆነው ታጋይ ስሑል 'ስዩም' የሚለውን ስም ሰጣቸው። በ1970ዎቹ አጋማሽ ድርጅቱን ከሚመሩት አንዱ በመሆን የተመረጡት አቶ ስዩም፤ አድያቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከመንግሥት ሠራዊት ጋር በተደረገው ከባድ ውጊያ ጭንቅላታቸውን ተመትተው ኤርትራ ውስጥ ህክምና እንደተደረገላቸው \"ጽናት\" በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል። ታጋይ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) ከኤርትራ ህወሓት ወደ ሚመራው የትጥቅ ትግል ከተቀላቀሉት ጥቂት ቀደምት ታጋዮች በመንግሥት ተይዞ በሽረ እንዳሥላሴ ከታሳረ በኋላ፤ ስዩም ሙሴን ጨምሮ የታሰሩትን ታጋዮች ለማስፈታት የተዘጋጀውን \"የሙሴ ኦፕሬሽን\" ለመፈጸም የአዕምሮ ህመምተኛ በመምሰል ስለላ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ታሪካቸው ያትታል። ስዩም- የህወሓት መልዕከተኛ አቶ ስዩም ከ1969 ዓ.ም መጨረሻዎቹ ጀምሮ የህወሓት የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው ለ15 ዓመታት በሱዳን የሰሩ ሲሆን፤ በካርቱም ቆይታቸውም ስማቸው ወደ 'ሙሳ' ተቀይሮ እንደነበረም ይነገራል። አቶ ስዩም በ1983 ዓ.ም ከመለስ ዜናዊና ከብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር በመሆን በለንደን ከመንግሥት ጋር ሲደረግ በነበረው ድርድር ላይ ተሳትፈዋል። ህወሓት/ኢህአዴግ የደርግ ሥርዓትን ጥሎ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የወቅቱ የሱዳን ፕሬዝደንት የነበሩት ኦማር አልበሽር ባዋሷቸው አውሮፕላን ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙበት ጊዜ የቴክኒክ ችግር አጋጥሟቸው ነበር። በዚህ ምክንያት አውሮፕላኑ ከባድ አደጋ እንደገጠማት በተረዱ ጊዜ ለ17 ዓመታት የመሩት ትግል በድል ተጠናቆ ማየት አለመቻላቸው ከባድ ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸው እንደነበር ይነገራል። ነገር ግን የፈሩት ሳይደርስ በሰላም አዲስ አበባ ገቡ። ስዩም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በህወሓት መሪነት ኢህአዴግ የአገሪቱን ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ አንስቶ አቶ ስዩም መስፍን ለ20 ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን በቁልፍ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ከኢትዮ ኤርትራ የድንበር ጦርነት ማብቃት በኋላ በ1993 ዓ.ም በህወሓት አመራሮች መካከል ክፍፍል ሲፈጠር አቶ ስዩም ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጎራ ከተሰለፉት መካከል አንዱ ነበሩ። ከድንበር ጦርነቱ ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ለደም አፋሳሹ ጦርነት ዋነኛ ምክንያት የነበረችው ባድመን ለኤርትራ ወስኖ እያለ ለኢትዮጵያ እንደተወሰነ አድርገው በቴሌቪዥን መግለጫ በመስጠት ሕዝብ የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ በማድረጋቸው በተአማኒነታቸው ላይ ዘወትር የሚጠቀስ ጠባሳ ጥሏል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ካሉ ጎረቤት አገራት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራት ለማድረግ አስችለዋል ቢባልላቸውም፤ ከኤርትራ ጋር ግን የድንበር ግጭቱ ሳይፈታ እንዲቆይ በማድረግ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያደረጉት ጥረት የለም ተብለው ይተቻሉ። በተጨማሪም ህወሐት በኢሕአዴግ ውስጥ በነበረው ጠንካራ የበላይነት ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂ ናቸው ተብለውም ይከሰሳሉ። በሌላ በኩል አቶ ስዩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በቆዩባቸው ዓመታት የእስያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸው እንዲያፈሱ ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ እንደነበረ ይነገራል። በዚህም ምክንያት የሚኒስትርነት ቦታቸውን ሲለቁ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ለስድስት ዓመታት ሰርተዋል። ስዩም - ከለውጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ አቶ ስዩም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተመልሰው ማገልገል ጀምረው ነበር። ነገር ግን በተመደቡበት ክፍል ደስተኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ ወደ መቀለ እንደሄዱ ይነገራል። በፌደራል መንግሥቱና በህወሐት መካከል የተፈጠረው መካረር በበረታበት ወቅት፤ አቶ ስዩም በተለያዩ አጋጣሚዎች በመገናኛ ብዙሃን ላይ በመቅረብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አጥብቀው ሲተቹ ቆይተዋል። በአንድ ቃለ ምልልሳቸውም የኖቤል ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጠው የሠላም ኖቤል ሽልማት ላይ እየተወዛገበ መሆኑን በመግለጽ ሽልማቱን ለማንሳት እያሰበ መሆኑን በመግለጻቸው መነጋገሪያ ሆነው ነበር። የሽልማት ኮሚቴውም በእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ላይ እንዳልተነጋገረና አንድ ጊዜ የተሰጠ የኖቤል ሽልማት እንደማይመለስ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን በቁጥጥር ስር ከማስገባቱ ቀደም ብሎ እስካለው ጊዜ ድረስ አቶ ስዩምና የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የቆዩ ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ግን ከተማዋ ወጥተው ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች መሄዳቸው ተነግሮ ነበር። የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የነበሩት አቶ ስዩም መስፍንና ሌሎች ጓዶቻቸው ያሉበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ተከቦ እጅ እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል ጥር 05/2013 ዓ.ም በተወሰደባቸው እርምጃ መገደላቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። መቀለ በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ከነበሩት ጥቂት ቀናት ውጪ የህወሓት አመራሮች ለየትኛውም የመገናኛ ብዙሃን ምንም አይነት መግለጫ ሰጥተው ስለማያውቁ ስለተገደሉት አመራሮቹ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ወገን የተሰማ ነገር የለም።", "በእስር ላይ ያሉ የኦነግ አመራሮች በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገለጸ በእስር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ። በእስር ላይ የሚገኙ የኦነግ አመራሮችን ከሚወክሉት ጠበቆቻቸው መካከል አንዱ የሆኑት ቱሊ ባይሳ፤ የረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት ሚካኤል ቦረን፣ ኬነሳ አያና፣ ዳዊት አብደታ፣ ለሚ ቤኛ፣ ገዳ ገቢሳ እና በቴ ኡርጌሳ የተባሉት የኦነግ አመራሮች መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። እንደ ጠበቃው ከሆነ የተያዙበት ሁኔታ ሕጋዊ አይደለም በሚል ላለፉት አምስት ቀናት በረሃብ አድማ ላይ የቆዩት አመራሮቹ በአገር ሽማግሌዎች ተማጽኖ የረሃብ አድማቸውን ለማቆም ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ወደ ሆስፒታል ተወስደው አስፈላጊው የሕክምና መሳሪያ የለም ተብሎ ወደ እስር ቤት ከተመለሱ በኋላ በረሃብ አድማቸው መቀጠላቸውን አስረድተዋል። \"የረሃብ አድማውን ለማቆም ከአገር ሸማግሌዎች የቀረበላቸውን ተማጽኖ ተቀብለው ነበር። ነገር ግን ምግብ መውሰድ ከመጀመራቸው በፊት ወደ ሆስፒታል መወሰድ ነበረባቸው። ይሁን እንጂ በፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል አስፈላጊ የሆነ የሕክምና መሳሪያ የለም በመባሉ ወደ ቡራዩ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለሱ ተደርገዋል። አሁንም በረሃብ አድማ ላይ ናቸው\" ብለዋል ጠበቃ ቱሊ ባይሳ። የኦነግ አመራሮች በእስረኞች ላይ ያለውን አግባብ የሌለው አያያዝ በመቃወም የረሃብ አድማ እያደረጉ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በትናንትናው ዕለት ረቡዕ የካቲት 3፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። እስረኞቹ በአግባቡ እንደማይያዙና \"እንግልትና ጥሰት ይፈጸምባቸዋል\" ያለው መግለጫው ምግብ፣ ውሃና ሌሎች መሰረታዊ ሰብዓዊ አገልግሎቶችንም መነፈጋቸውንም አክሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ምግብ በማቆማቸው \"በጤንነትና አጠቃላይ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ደህንነት በየቀኑ እየተጎዱ ነው\" ብሏል መግለጫው ጠበቆችም ሆኑ የቤተሰብ አባላት እስረኞቹን ማግኘት ፈጽሞ አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው የሚናገሩት ጠበቃው የእስረኞቹን ሁኔታም ከደንበኞቻቸው ሳይሆን ታስረው ከሚለቀቁ ከሌሎች ሰዎች በተዘዋዋሪ የሚሰሙበት አጋጣሚዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። \"እኛ (ጠበቆች) ከባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ እስካሁን አግኝተናቸው አናውቅም\" በማለት ጠበቆች ከደንበኞቻቸው ጋር ከተገናኙ ወራቶች መቆጠራቸውን ያስረዳሉ። ኦነግ በመግለጫውም የእስረኞቹ ቤተሰቦች እንዳይጠይቋቸው እንደሚከለከሉና አልፎ አልፎም ትንኮሳም እንደሚደርስባቸው በትናንትናው መግለጫ ሰፍሯል። ጠበቃ ቱሊ እንደሚሉት ዐቃቤ ሕግ የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሆኑት ሚካኤል ቦረን እና ኬነሳ አያና ላይ የማቀርበው ክስ የለኝም ብሎ መዝገባቸውን ከዘጋ አንድ ዓመት ቢያልፈውም አሁንም ሁለቱ ግለሰቦች በእስር ላይ እንደሚገኙ ያስረዳሉ። ለሚ ቤኛ እና ዳዊት አብደታ የተባሉት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ደግሞ በፍርድ ቤት በነጻ የተሰናበቱ ናቸው ይላሉ ጠበቃው። \"ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠይቆ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ተከራክረን ነጻ የወጡ ሰዎች ናቸው። ፖሊስ ግን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዟቸው ይገኛል\" በማለት ቱሊ ያስረዳሉ። እንደ ጠበቃው ከሆነ የኦነግ ቃል አቀባይ በሆኑት በቴ ኡርጌሳ እና የፓርቲው አመራር በሆኑት ገዳ ገቢሳ ደግሞ እስከነ ጭራሹ ክስ አልተመሰረተባቸወም፤ ሲከናወንባቸው የነበረው የወንጀል ምርመራ ተቋርጧል። ኮሎኔል ገመቹ አያና እና የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አብዲ ረጋሳ ከትናንት በስቲያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ፍርድ ቤቱ በነጻ ቢያሰናብታቸውም ዐቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ግለሰቦቹ እንዳይለቀቁ አድርጎ አስቀምጧል ይላሉ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ በትናንትናው መግለጫ ላይ\" መንግሥት የኦነግ አመራሮችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማሰር እና በእስር ቤቶች ውስጥ በማስቀመጥ እያሰቃየ ይገኛል\" ብሏል። ባለስልጣናቱ በኦነግ ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ አልሰጡም። መግለጫው አክሎም በእስር ላይ ያሉ አመራሮቹ በቡራዩ ፣ ሰበታ እና ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው እንደሚገኙ አመልክቷል። \"የተያዙበት ሁኔታ ከሞራልም ከሕግም ውጪ ነው\" ክስ ያልተመሰረተባቸውን፣ በፍርድ ቤት በነጻ የተሰናበቱና በሕግ መሠረት በእስር ላይ መቆየት የማይገባቸውን ከእስር ለማስፈታት \"ሪፖርት ያላደረግንበት ቦታ የለም።\" በማለት ጠበቃው ቱሊ ይናገራሉ። \"ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አሳውቀናል። አካልን ነጻ ማውጣት መዝገብ አስከፍተናል። . . . ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት አድርገናል\" ይላሉ። ቢቢሲ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገረው አካል ስለመኖሩ ለመጠየቅ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ጠበቃው ደንበኞቻቸው \"የተያዙበት ሁኔታ ከሞራልም ከሕግም ውጪ ነው። . . . ከባድ ወንጀል ነው እየተፈጸመባቸው ያለው። ጉዳዩን ለቤተሰብም ማስረዳት በጣም አስቸጋሪ ሆኖብናል።\" ይላሉ። አብዛኞቹ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ሁከትና ሽብርተኝነትን በማነሳሳት ተከሰው ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም በእስር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። መንግሥት በቅርቡ ለሚካሄደው አገራዊ ምክክር መንዱን ለማመቻቸት በሚል በእስር ላይ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ከእስር ፈትቷል። ኦነግ ለአገራዊ ምክክሩ እንዳልተጠራ የገለጸ ሲሆን በዚህም ምክክር ለመሳተፍም አመራሮቹ እንዲፈቱ እየጠየቀ ነው።", "ሰሜን ኮሪያ፡ ታመዋል ሲባሉ የነበሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ድንገት ተከሰቱ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታመዋል ከሚለው ጀምሮ፣ አብቅቶላቸዋል፣ ሞተዋል እየተባለም ብዙ ይወራባቸው ነበር፡፡ ድንገት በፓርቲ ስብሰባ ተከስተው መመርያ ሰጥተዋል፣ ትናንት፡፡ ሰሜን ኮሪያ ትልቅ አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል ያሉት ኪም ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲሆን አዘዋል፡፡ ትልቅ አደጋ እየመጣ ነው ያሉት ኪም አደጋዎቹ በዋናነት ሁለት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ አንዱ ኮሮና ቫይረስ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውሎ ንፋስ ነው፡፡ ኪም ከሰሞኑ ጠፍተው ስለነበር የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ስለነበረ ምናልባት ሞተው ይሆን? ሲባል ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን አንድም ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘብኝም ስትል ታስተባብላለች፡፡ አይበለውና ወረርሽኙ ወደዚያች አገር ቢገባ ባላት ደካማ የጤና መሰረተ ልማት ከፍተኛ አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ባቪ የሚሰኝ አደገኛ አውሎ ነፋስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሰሜን ኮሪያን ሊመታት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የፖሊትቢሮ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኪም በስብሰባው ላይ ንግግር እያደረጉ ሲያጨሱ ይታዩ ነበር፡፡ በዚህ ንግግራቸው ኮቪድን በተመለከተ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለዋል ብለዋል፡፡ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ ፒዮንግያንግ ለረዥም ጊዜ ወረርሽኙ እኔ ጋ ድርሽ አላለም ስትል እያስተባበለች ቆይታለች፡፡ ነገር ግን ይህን የሰሜን ኮሪያን አስተያየት ብዙዎች በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት፡፡ አንድም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የለም ስትል የነበረው ሰሜን ኮሪያ በቫይረሱ አጠባበቅ ዙርያ ችግሮች ታይተዋል ማለቷ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከጥርጣሬ የተነሳ አንዲት የድንበር ከተማ ሰዎች ተገለው እንዲቀመጡ ያደረገች ሲሆን ነገር ግን ከዚህ የዘለለ ስለተያዘ አንድም ሰው ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ ኪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክብደት እየጨመሩ ስለሆነ በወጣትነታቸው ሊቀጠፉ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች በስፋት ይሰነዘሩ ነበር፡፡ በቅርቡም ለእህታቸው ኪም ዮ ጆንግ በርከት ያሉ ሥልጣኖችን ሰጥተዋት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ እንደ ኑዛዜ የወሰዱት ሚዲያዎችም ነበሩ፡፡ ሰሜን ኮሪያ 25 ሚሊዮን ዜጎች አሏት፡፡ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ የረሀብ አደጋ ገጥሟቸዋል ይላል የተባበሩት መንግሥታት፡፡ የረባ የንግድ ግንኙነት ከአገራት ጋር ያልመሰረተችው ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር የምታደርገው ንግድ ወሳኝ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህም በኮሮና ምክንያት እክል ገጥሞታል፡፡ በፒዮንግያንግ መቀመጫቸውን ያደረጉ በርካታ ግብረሰናይ ድርጅቶችና የኤምባሲ ሰራተኞች አገሪቱን ለቀው እንደወጡ ተዘግቧል፡፡", "በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሰየሙት ዐቢይ አሕመድ ማን ናቸው? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በተመሰረተው ምክር ቤት አማካይነት ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን እንዲመሩ ተሰይመዋል። አገሪቱ ውስጥ ተከሰተን ፖለቲካዊ ቀውስን ተከትሎ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነበር ዐቢይ አሕህመድ (ዶ/ር) የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ኃላፊነት ተረከቡት። ባለፉት ሦስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ዐቢይ አሁን ለሙሉ የሥልጣን ዘመን ኃላፊነቱን ትተረክበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማን ናቸው? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን የመጡት ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ነበር። በወቅቱ ኢትዮጵያ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት ለመግባት ከጫ ደርሳለች ተብሎ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን እንደተረከቡ ታሪካዊ የሚባሉ የለውጥ እርምጃዎችን ወስደዋል፤ አንዳንዶቹ ለውጦችም በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ይሆናሉ ተብለው የማይታሰቡ ነበሩ። ኢትዮጵያ ዘወትር ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻናት እንዳይገልጹ ታደርጋለች፣ ተቃዋሚዎች የሚታሰሩባት እና ለተቃውሞ አደባባይ በሚወጡ ዜጎች ላይ የማያዳግም እርምጃ የምትወስድ አገር ናት እየተባለች በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ የምትተች አገር ነበረች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ግን ይህ ሁሉ ተቀየረ። ከኤርትራ ጋራም ሰላም ወረደ። ለዚህ ጥረታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእርሳቸው በፊት ሥልጣን ላይ ከነበሩት እና \"ጠላት\" ከሚባሉት ጋር ለመገናኘት እንዲሁም ስላም ለማውረድ ቁርጠኛ መሆናቸው ተስተውሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አባት ሐምሌ 2011 ላይ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ \"ከሁሉም ጋር ጓደኛ የሆነ ልጅ ነው\" ሲሉ ልጃቸውን ገልጸው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ማን ናቸው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦሮሞ ሕዝብ የተገኙ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ያመጣቸው ለሦስት ዓመታት የዘለቀው ተቃውሞ በኦሮሚያ ውስጥ መሠረት ያደረገ ነበር። ለዓመታት በዘለቀው ታውሞ በርካቶች ተገድለዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል። ተቃዋሚዎች ከሚያነሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የኦሮሞ ሕዝብ የኢትዮጵያ ትልቁ ብሔር ሆኖ ሳለ ሕዝቡ ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ለዓመታት ተገሎ ቆይቷል የሚል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ወደ ስልጣን ሲመጡ ይህ መቀየር ጀመረ። ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አካል የሆነው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢህዴድ) ሊቀመንበር ተደርገው ተሹመው ነበር። ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ተቆጣጥሮ የቆየውን ኢሕአዴግ በማክሰም ብልጽግና የተሰኘና ከቀድሞው ገዢ ፓርቲ ሰፋ ያለ መሰረት ያለውን ፓርቲ መስርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት በኢሕአዴግ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ የቆየው ህወሓት ብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል አልፈለገም። የ44 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ክርስቲያን እና ሙስሊም ከሆኑ ወላጆች የተገኙ ሲሆን የተወለዱት ደግሞ በአሉአባቦራ ኦሮሚያ ነው። ዐቢይ አሕመድ በውትድርና ሕይወታቸው አስከ ሌፍተናንት ኮሎኔል ማዕረግ ለመድረስ ችለዋል። ከዚያም የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተባለው ተቋምን መስርተው ይመሩም ነበር። በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርግ በነበረው መንግሥት ውስጥ፤ ይህ ተቋም በአገሪቱ የሚደፈጸሙ የሳይብር - ሴኩሪቲ ጥቃቶችን መከላከል ዋና ዓላማው ነበር። በተከታይነት ደግሞ ዐቢይ የአገሪቱ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙም በኋላ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሚገኘው የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ሌሌች እንዲሰማሩ በመፍቀድ ዘርፉን ለማዘመን ቃል ገብተዋል። ቁልፍ እውነታዎች፡ ዐቢይ አሕመድ ኦሮሞ ከሆኑት ሙስሊም አባላታቸው እና አማራ ከሆኑት ክርስቲያን እናታቸው በአጋሮ ከተማ ተወለዱ። ዐቢይ ገና በአስራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ እያሉ ደርግን መታገል ጀምሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰላም እና ደኅንነት ጥናት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል። የማስተርስ ዲግሪያቸውን ደግሞ 'በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ' ከለንደኑ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ግሪንዊች አግኝተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። እአአ 1995 ላይ በሩዋንዳ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል ሆነ አገልግለዋል። 1999 ላይ የኢትዮጵያን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲን አቋቁመዋል። የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቦርድ አባል ሆነውም አገልገለዋል። 2002 ላይ የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅትን (ኦህዴድ) በአባልነት ተቀላቅለው 2007 ላይ የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል መሆን ችለዋል። 2008 ላይ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። 2010 ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። 2011 ላይ ኢሕአዲግ አንዲከስም ተደርጎ የልጽግና ፓርቲን መሠረቱ። 2012 ላይ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም እንዲሰፍን ላደረጉት ጥረት የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተሸለሙ። 2013 ላይ በትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸውን አስታወቁ። የኖቤል የሰላም ሽልማት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐቢይ ከኤርትራ ጋር የደረሱት የሰላም ስምምነት በሁለቱ አገራት መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነትም ሰላምም የሌለበት ሁኔታን የቀየረ ነበር። ይህ ተግባራቸውም የ100ኛው የኖቤል ሽልማት አሸናፊ እንዲሆኑ አደርጓቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦስሎ የኖቤል ሽልማታቸውን ሲቀበሉ የሚከተውን ንግግር አድርገው ነበር። \"ጦርነት ለመቀስቀስ የሚያስፈልገው የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው። ሰላም ለመገንባት ግን መንድር እና ሕዝብ ያስፈልጋል። \"ለእኔ ሰላምን መንከባከብ ማለት ዛፍ እንደመትከል እና ማሳደግ ነው። ዛፎች ለማደግ ጥሩ አፍር እና ውሃ እንደሚፈልጉት ሁሉ፤ ሰላምም ያልተቋረጠ ትጋት፣ ያልተቆጠበ ትዕግስት እና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል።\" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማታቸውን ከተረከቡ በኋላ በአገሪቱ የተከሰተውን \"ሞት እና መፈናቀል\" ምክንያት በማድረግ የኖቤል ኮሚቴው የሰጠውን ሽልማት እንዲሰርዝ ጥያቄ ያቀረቡ ነበሩ። ይህን ተከትሎም የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴው መግለጫ ለማውጣት ተገዶ ነበር። ኮሚቴው በመግለጫው ለጠቅላይ ሚንስትሩ የኖቤል ሽልማት መስጠቱ ትክክል አልነበረም ብሎ እንደማያስብ አስታውቋል። መደመር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ 'መደመር' የሚለው ቃል በበርካቶች ዘንድ ጥቅም ላይ ሲውል የቆየ ቃል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ችግር መፍታት የሚያስችል አካሄድ እንደሆነ ይናገራሉ። መደመር የተሰኘው የጠቅላይ ሚንስትሩ መጽሐፍም በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ከታተመ በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ኮፒ መሸጡ ተነግሯል። 280 ገጽ እና 16 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍልስፍና ያትታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዘር የተከፋፈለችው ኢትዮጵያን በአንድነት ስሜት እንድትቆም ይሻሉ፤ በተመሳሳይ ብዝሃነት እንዲከበር ይሻሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ፍልስፍና የተለያዩ ወይም የሚቃረኑ ሃሳቦችን አንድ ላይ በማምጣት መግባባት ላይ መድረስ ይቻላል የሚል መሠረት አለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እአአ 2017 ላይ በደኢህዴን ስበሰባ ላይ \"አንድ አማራጭ ነው ያለን። ይህም አንድ መሆን ነው፤ መተባበር እና እርስ በእርስ መተጋገዝ ብቻ ሳይሆን መኖር እንዲቻለን አንድ መሆን አለብን። ሌላኛው አማራጭ መገዳደል ነው\" ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ቀውስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸውን ያስታወቁት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ላይ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከዚህ ውሳኔ እንዲደርሱ ያደረገው ምክንያት የህወሓት ኃይሎች የአገር መከላከያ ሠራዊት አንድ አካል በሆነው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል። \"ስለዚህ የፌደራሉ መንግሥት ወታደራሚ አማራጭ እንዲወስድ ተገዷል\" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር እና በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ከለውጡ በኋላ ለርካታ ወራት ቆይቷል። የስልጣን ሽኩቻ፣ ምርጫ እና የተወሰዱ ፖለቲካዊ የለውጥ እርምጃዎች በሁለቱ ወገን መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ ህወሓት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ ኃይል ሆኖ ቆይቷል። የህወሓት አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን ከስልጣን ተገፍተናል ሲሉ ይከሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥና ማሻሻያዎችን ሲያደርጉ የህወሓት ኃይሎች ግን ደስተኛ አልነበሩም፤ ይህም ፖለቲካዊ ቀውስ አስከተለ። የህወሓት አመራሮች የጠቅላይ ሚንስትሩን ፈጣን የለውጥ እርምጃ ስልጣንን ለማማከል የሚደረግ ጥረት እንደሆነ እና የኢትዮጵያን የፌደራል ሥርዓት ለማፍረስ የሚደረግ ጥረት እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል። ቀጠናዊ ተጽእኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር የሥልጣን ዘመናቸውን አለመግባባት በተፈጠረባቸው ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በማሸማገል ተልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በሱዳን ከአል-በሽር መወገድ በኋላ የአገሪቱ ሠራዊትና ተቃዋሚዎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ይህም ድርድር በሱዳን ሠራዊቱና እና ሲቪሎች ሥልጣን ተጋርተው አገሪቷ በሽግግር መንግሥት እንድትመራ አስችሏል። ጂቡቲ እና ኤርትራም ዲፕሎማሲያዊ ግነኙነታቸውን እንዲሰያሻሽሉ ጥረት አድርገዋል። ሶማሊያ እና ኬንያም በሚጋጩበት የባሕር ጠረፍ ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱን አገራት አሸማግለዋል። ይህን ብቻም ሳይሆን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር እና የአማጺያኑ መሪ ሬክ ማቻር ከስምምነት እንዲደርሱ የተቻላቸውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ እየተወሰደ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ \"ሕግ የማስከበር እርምጃ ነው\" ቢሉትም ከሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ከእርዳታ አቅርቦት አንጻር ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት በመንግሥታቸው ላይ ተለያዩ ግፊት እያደረጉ ነው። ቢሆንም ግን መንግሥታቸው ከአማጺያኑ ጋር ድርድር እንደማይደረግ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ በተደጋጋሚ አሳስበዋል።", "የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በፈቃዳቸው ሥልጣን ለቀቁ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ለተከታታይ ሳምንታት ሲካሄድ በቆየውና እሁድ ዕለት ካርቱም ውስጥ የተደረገውን ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ከጦር ሠራዊቱ ጋር የተደረሰውን የሥልጣን ክፍፍል በመቃወም ነበር አደባባይ ሲወጡ የነበሩት። ተቃዋሚዎች ሥልጣን ወደ ሕዝቡ ተመልሶ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ በሲቪል መሪዎች እንድትደታዳር የሚጠይቁ መፈክሮችን ሲያሰሙ ነበር። ነገር ግን ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ ትናንት እሁድ ሁለት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ተገድለዋል። በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ከተወገዱ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ወደ ኃላፊነታቸው ተመልሰው የነበሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ የሥልጣን መልቀቅ ውሳኔ የሱዳን መንግሥት ሙሉ ለሙሉ በጦር ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር እንዲገባ ያደርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ሥልጣን መልቀቃቸውን በተመለከተ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር፣ \"የአገሪቱ አጠቃላይ ህልውና ከባድ አደጋ ላይ\" መሆኑን ገልጸዋል። በሥልጣን ቆይታቸው ሱዳን \"ወደ አደገኛ ሁኔታ\" ውስጥ እንዳትገባ ለማድረግ የቻሉትን እንዳደረጉ፣ ነገር ግን \"አስፈላጊው ሁሉ ጥረት ቢደረግም ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም\" ስለዚህም \"የተሰጠኝን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ሱዳንን ወደ ሲቪሊ አስተዳደር ለማሸጋገር ለሚችል ሰው ለመልቀቅ ወስኛለሁ\" ብለዋል። ትናንት እሁድ በተደረገው ወታደራዊውን አስተደደር በሚቃወም ሰልፍ ላይ የፀጥታ ኃይሎች ሁለት ሰዎችን መግደላቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ የሕክምና ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የተቃውሞ ላይ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ተኩሶ ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን የዶክተሮች ቡድን የገለጸ ሲሆን ካለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ በፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 56 መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል። ሱዳን ውስጥ ለሳምንታት በቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ የፀጥታ ኃይሎች የሚወስዱት አደገኛ እርምጃ በእጅጉ እንዳሳሰባትና እርምጃ እንደምትወስድ አሜሪካ በሳምነቱ ማብቂያ ላይ አስጠንቅቃ ነበር። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እንዳሉት የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እየወሰዱ ያለውን እርምጃን በተመለከተ የሚወጡ ሪፖርቶች በጣሙን እንዳሳሰባቸው በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ ጨምረው መንግሥታቸው በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን አደገኛ የኃይል እርምጃ እንደሚያወግዘውና ሱዳን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዳትሸጋገር እንቅፋት በሆኑት ላይ ደግሞ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቀዋል። እሁድ ዕለት ካርቱም ውስጥ በቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ ላይም የፀጥታ ኃይሎች ወታደራዊ አስተዳደርን በመቃወም አደባባይ የወጡ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዥ ተኩሰዋል። መንግሥት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ከሰልፉ ቀደም ብሎ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ያደረገ ሲሆን፣ ወደ ካርቱም የሚያመሩ ዋነኛ መንገዶችና ድልድዮች ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የታጠቁ ፖሊሶችን በማሰማራት እንዲዘጉ አድርጎ ነበር። ባለፈው ጥቅምት ወር ጄኔራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን በሲቪሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ካደረጉ ወዲህ የእሁዱ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ 12ኛው ሲሆን ለአዲሱ የፈንጆች ዓመት ደግሞ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። እሁድ ጠዋት ተቃዋሚዎች በሱዳን ጦር ሠራዊት መሪዎች ላይ ለወራት ሲያሰሙት የነበረውን ተቃውሞ ለመቀጠል ወደ አደባባይ መውጣት ሲጀምሩ አንስቶ የኢንርኔት አገልግሎት መቋረጡን በዓለም ዙሪያ የኢንተርኔት አገለግሎትን የሚከታተለው ኔትብሎክስ አስታውቋል። ለወራት የቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪዎች እንደሚሉት ዋነኛ ጥያቄያቸው ጦር ሠራዊቱ ሥልጣን በሲቨሎች ለሚመራ መንግሥት አስረክቦ ከመሪነት መንበሩ ገለል እንዲል ነው። ተቃዋሚዎቹ ባለፈው ሳምንት በካርቱም አቅራቢያ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ በተካሄዱት ተመሳሳይ ሰልፎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በተገደሉት አምስት ሰልፈኞች ሞት ቁጣቸው ጨምሯል። ከሞቱት በተጨማሪ በተለያዩ የሱዳን ከተሞች ውስጥ በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ፖሊስ በተከሰው አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል። ሱዳንን ሰላሳ ዓመታት ለመጠጋ ጊዜ በፈላጭ ቆራጭነት የመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር በሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ አገሪቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በተቃውሞ ስትናጥ ቆይታለች። ከአልበሽር ከሥልጣን መወገድ በኋላ ሥልጣን በአገሪቱ ጦር ሠራዊትና በሲቪል ፖለቲከኞች መካከል ተከፋፍሎ የሽግግር መንግሥት ቢቋቋምም ሁለቱ ወገኖች ሳይስማሙ ተቃውሞው ቀጥሎ ቆይቷል። ሕዝባዊውን ለውጥ የመሩት ኃይሎች ጦር ሠራዊቱ ከአገሪቱ የመንግሥት ሥልጣን ውጪ ሆኖ ሲቪል አስተዳደር እንዲቋቋምና ሱዳን በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት እንዲኖራት ግፊትና የተቃውሞ ሰልፎች ሲያደርጉ ቆይተዋል። ነገር ግን በአገሪቱ የሽግግር ሲቪል መሪዎችና በወታደሮች መካከል ያለው አለምግባባት እየተባባሰ ሄዶ ባለፈው ጥቅምት ወር የሽግግር መንግሥቱ ሊቀመንበር የነበሩት ጄነራል አል ቡርሐን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት አስወግደው ነበር። ከሦስት ዓመት በፊት በተደረሰውና ባልተከበረው የሥልጣን ክፍፍል ስምምነት መሠረት የሱዳን የሽግግር መንግሥት መሪ ጄነራል አል ቡርሐን ሥልጣናቸውን ለሲቪል ፖለቲከኞች ማስረከብ የነበረባቸው መፈንቅለ መንግሥት ባደረጉ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኅዳር ወር ላይ ነበር። ጄነራሉ መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱት ፖለቲከኞች ሰላማዊ ሰዎችን በፀጥታ ኃይሎች ላይ እያነሳሱ በመሆናቸው የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይከሰት ለመከላከል ነው ሲሉ የእርምጃቸውን ተገቢነት ገልጸው ነበር። ጄነራሉ ሱዳን አሁንም በሽግግር ሂደት ላይ እንደሆነችና አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለማሻገር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው ከሁለት ዓመት በኋላ ምርጫ እንደሚካሄድ አመልክተዋል። ጄነራል አልቡርሐን በአገር ውስጥና ከዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በመፈንቅለ መንግሥት ያነሷቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ወደ መንበራቸው ቢመሉሱም ተቃውሞው አሁንም እንደቀጠለ ነው። ለወራት ወታደራዊውን መንግሥት በመቃወም በሱዳን ጎዳናዎች ላይ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የቆዩ ሱዳናውያን በጦር ኃይሉ ላይ እምነት ስለሌላቸው ጄነራሎቹ ከመንግሥታዊ አስተዳደር ሥልጣን እንዲገለሉ እየጠየቁ ነው። ጥቅምት ወር ላይ በጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ቀውስ ያባባሰው ሲሆን፣ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲ እንድትሸጋገር የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች ጦር ኃይሉ በሕዝባዊ ትግል የመጣውን ለውጥ ጠልፏ በሚል ይከሳሉ።", "ሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት 'ሞካሪዎቹ በሙሉ' በቁጥጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀች ሱዳን የተሞከረውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ማክሸፏንና \"ተሳታፊዎቹ በሙሉ\" በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀች። የሱዳን መንግሥት ቃል አቀባይ ለአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት የመንግሥት ግልበጣ ሴራውን የወጠኑት ከሁለት ዓመት በፊት ከሥልጣን ከተወገዱት ከኦማር አል ባሽር ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። የመንግሥት ግልበጣ ሙከራውን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ካርቱም እና በቅርበት በምትገኘው ኦምዱርማን ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳለና በናይል ወንዝ ላይ ያለው ግዙፉ ድልድይ ተዘግቶ እንደነበር ተዘግቧል። ወደ ካርቱምና ወደ ወደቦች የሚወስዱት ጎዳናዎች ተዘግተዋል። የመፈንቅለ መንግሥቱ ሞካሪዎች የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የሚገኙበትን ህንጻ ለመቆጣጠር ሙከራ ማድረጋቸውን የፈንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል። የሱዳን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው ማክሰኞ ማለዳ በአገሪቱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፉን ይፋ ያደረገው። የመንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት መሐመድ አል ፋኪ ሱሌይማን በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የተጠረጠሩ አካላት ላይ ምርምራ እንደሚደረግባቸው ተናግረዋል። የመንግሥት ግልበጣውን የሞከሩት ሰዎች በኡምዱርማን የሚገኘውን የአገሪቱን ብሔራዊ ሬዲዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሙከራ ተደርጎ ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከካርቱም የተቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች አውራ መንገዶች ላይ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች የመኪናውን ፍሰት ሲቆጣጠሩ ታይተዋል። በካርቱም ለዛሬ ሊካሄድ የታቀደ የተቃውሞ ሰልፍ የነበረ ሲሆን የመከላከያ ኃይሉ የከተማዋን የፀጥታ ሁኔታ አጠናክሮታል። ሱዳን ፕሬዝዳንት አል ባሽር እኤአ በ2019 ሚያዚያ ወር ላይ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራ የሽግግር መንግሥት እየተዳደረች ትገኛለች። የቀድሞውን መሪ ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል ከቆዩበት ሥልጣን እንዲወገዱ ምክንያት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ የጀመረው የዳቦ እና የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ ነበር። አል ባሽር ከስልጣን የተነሱት ለወራት የዘለቀ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ሲሆን ራሳቸውን ወደ ስልጣን ያመጣቸውን የ1989 መፈንቅለ መንግሥት በሚመለከት የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ ነው። የመፈንቅለ መንግሥቱ መከራውን ተከትሎ ሁኔታውን ለመቆጣጠር መንግሥት እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ተነግሯል። የመንግሥት ግልበጣው በማን እንደተሞከረ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ጉልህ ሚና ባላቸው ወታደራዊና ሲቪል አመራሮች መካከል በየወቅቱ አለመግባባትና ውጥረት በተደጋጋሚ ሲከሰት መቆቱ ይነገራል። ከሲቪል አመራሮች መካከል ዋነኛ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከአንድ ዓመት በፊት ካርቱም ውስጥ በመኪናቸው እተጓዙ ሳለ መንገድ ላይ በተጠመደ ፈንጂ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር ይታወሳል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ ያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። የሱዳን መንግሥት ዜና ወኪል ሱና የአገሪቱን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጠቅሶ እንደዘገበው ከተሞከራው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ በአገሪቱ ያለው ሁኔታ በመንግሥት ቁጥጥር ስር መሆኑን አመልክቷል። አል በባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሱዳን ውስጥ በርካታ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች እንደነበሩ ሪፖርት ተደርጓል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣው ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅት ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል።", "እስራኤል የረጅም ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሯ አሰናብታ አዲስ መረጠች የእስራኤል ፓርላማ ለረጅም ዓመታት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ላይ የቆዩት ቤንያሚን ኔታኒያሁ የሚተኩ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠ። አዲሱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት በሁለት ዓመት ውስጥ በተደረጉ አራት ምርጫዎች ምክንያት ውዝግብ የተጫነውን የእስራኤልን ሕዝብ አንድ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ናፍታሊ ቤኔት ከ12 ዓመታት በኋላ በእልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ከስልጣን ገሸሽ የተደረጉትን ቤንያሚን ኔታንያሁ ተክተዋል። እሁድ በኢየሩሳሌም ፓርላማ ውስጥ በተደረገው ክርክርም ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚስተር ኔታንያሁ \"ተመልሰን እንመጣለን\" በማለት ቃል ገብተዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም መንግሥታቸው ለሁሉም ሕዝብ ጥቅም እንደሚሰራ ገልፀው በተለይም በትምህርት፣ በጤና እና አሳሪ የሆኑ አሰራሮችን በማሻሻል ላይ እንደሚያተኩርም ተናግረዋል። ትላንት እሁድ በተደረገው ድምፅ የመስጠት ሂደትም የአንድ ድምፅ ብልጫ (60 ለ 59) በማግኘት ያሸነፈው የቀኝ አክራሪ ብሔረተኛው ክንፍ በእስራኤል ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የተባለለትን የፓርቲዎች ጥምረት በመመስረት አገሪቱን ይመራል። የያሚና ፓርቲ መሪ የሆኑት ቤኔት በሥልጣን መጋራት ስምምነቱ መሰረት እስከ መስከረም 2023 እኤአ ድረስ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለግላሉ። በቀጣይ ላሉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የለዘብተኛ ፓርቲው መሪ ያሺር አቲድ ስልጣኑን ተረክበው ይመራሉ። በእስራኤል ታሪክ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩት ኔታኒያሁም የፓርቲያቸው መሪ ብሎም በምክር ቤቱ የተቃዋሚ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ። የፓርላማ አባላቱ ለአዲሱ የጥምረት መንግሥት ድምጽ ከሰጡ በኋላ ኔታንያሁ ወደ ቤኔት በመሄድ እጃቸውን ሲጨብጧቸው ታይተዋል። የ49 ዓመቱ ቤኔት በንግግራቸው ላይ \"ይህ የልቅሶ ቀን አይደለም። በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመንግሥት ለውጥ ተደርጓል። ይኸው ነው። ማንም ሰው ፍርሃት እንዳይሰማው የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። እና ዛሬ ማታ ይህንን ደስታ ለማክበር ላሰባችሁም፤ እኛ ጠላቶች አይደለንም፣ አንድ ሕዝብ ነን በሌሎች ህመም ላይ አትጨፍሩ\" ሲሉ ተሰምተዋል። የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ቃል አቀባይ በበኩላቸው \"ይህ የእስራኤል ውስጣዊ ጉዳይ ነው። አቋማችን ሁል ጊዜ ግልፅ ነው፣ የምንፈልገው የፍልስጤም መንግሥት በ1967 ድንበሯ ከነ ዋና ከተማዋ ኢየሩሳሌም ጋር ነው\" ሲሉ ተናግረዋል። ጋዛን የሚቆጣጠረው የእስላማዊው ቡድን ሀማስ በበኩሉ \"ይህ የወረራ እና የቅኝ ግዛት ኃይል ነው፤ መብታችንን ለማስመለስ በኃይል እንቃወማለን\" ብለዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ቢደን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ለቤኔት ገልፀው \"የመቀራረብ እና ዘላቂ\" የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር በጉጉት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።", "የተባበሩት መንግሥታትበሁከት በምትናጠው ሄይቲ አነስተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭን አገደ በተደራጁ ወሮበሎች ጥቃት በከፍተኛ ሁከት እና ግጭት በምትናጠው ሄይቲ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ ክልከላን በሙሉ ድምፅ ወሰነ። ውሳኔው የመንግሥታቱ ድርጅት አባል አገራት መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት ቀላል የጦር መሳያዎችን እና ጥይቶችን መሸጥ እንዲከለክሉ ይጠይቃል። ነገር ግን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ላይ ሙሉ እገዳ በአገሪቷ ላይ እንዲጣል የቀረበው ሃሳብ በቻይና ውድቅ ተደርጓል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በመዲናዋ ፖርት ኦ ፕሪንስ ብቻ 89 ሰዎች ተገድለዋል። የረድዔት ድርጅቶች በአሁኑ ጊዜ በሄይቲ ያሉ አካባቢዎችን ለመድረስ አደገኛ ነው ይላሉ። ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2014 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀው ከሐምሌ 1 አስከ 5 ባለው ጊዜ ውስጥ በወሮበሎች ቡድን ጥቃት 234 ሰዎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ብሏል። \"አብዛኞቹ ሟቾች ወይም ተጎጂዎች በእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ተሳታፊ ባይሆኑም የጥቃቱ ኢላማ ሆነዋል” በማለት የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ጄረሚ ሎሬንስ ተናግረዋል። በተጨማሪም ለጽህፈት ቤታቸውም የወሲባዊ ጥቃት ሪፖርቶች እንደደረሳቸውም አክለዋል። በሜክሲኮና በአሜሪካ አማካኝነት የቀረበው የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሳሪያ ሽያጭን የሚከለክለው የውሳኔ ሃሳብ ባለፈው አርብ ተቀባይነት አግኝቷል። ውሳኔው በሄይቲ የወሮበሎች ቡድን መሪዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ግለሰቦች ላይ የጉዞና የንብረት እገዳ ማዕቀብ እንደሚጣል ያሳያል። እንዲሁም በሄይቲ ተቀማጭነቱን ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት ልዩ የፖለቲካ ተልዕኮ ተቋምን የሚቆይበትን ጊዜ ለአንድ ዓመት ያራዝመዋል። ከዓመት በፊት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆቬኔል ሞይስ በቅጥረኞች ከተገደሉ በኋላ በሄይቲ የወሮበሎች ጥቃት በሰፊው ተንሰራፍቷል። ከቅርብ ቀናት ወዲህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች የቤንዚን አቅርቦቱ ወደነበረበት እንዲመለስ አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ አለበት ሲሉ ጎማዎችን እያቃጠሉ እንዲሁም መንገዶችን እየዘጉ ነው። የሄይቲ ዋና የነዳጅ ማከማቻ ባለፈው ሳምንት የነበረውን ከባድ የወሮበሎች ጥቃት ተከትሎ ሥራውን ለማቆም ተገዷል። የቫርሬክስ የነዳጅ ማከማቻ በሁለት ተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል ፍልሚያ በሚደረጉባት በሲቴ ሶሌይል ከተማ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ሥራውን ማቆሙ በአገሪቱ የነዳጅ እጥረት አስከትሏል። በሄይቲ ያለው ድህነት እንዲሁም ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በርካታ ዜጎች ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ እና አሜሪካ እየተሰደዱ ነው።", "ስለኮቪድ-19 የጻፉትን ተከትሎ ትዊተር የአወዛጋቢዋን አሜሪካዊት ፖለቲከኛ ገጽ አገደ ትዊተር የአወዘጋቢዋን አሜሪካዊት ፖለቲከኛ ማርጆሪ ቴይለር ግሪን የግል ገጽ ማገዱን አስታወቀ። የሪፐብሊካ ፓርቲ አባልና የአሜሪካ ሕግ አውጪ ገጻቸው የታገደባቸው የትዊተርን ሕግጋት በመተላለፋቸው፣ በተለይ ደግሞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን አስመልክተው የሚለጥፉት መልዕክት አደጋ ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ነው ሲል ድርጅቱ ገልጿል። ትዊተር ከዚህ በፊት የፖለቲከኛዋን ገጽ አራት ጊዜ በጊዜያዊነት ማገዱ የሚታወስ ነው። የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት አባል የሆኑት ማርጆሪ ቴይለር ግሪን ኩባንያው \"የአሜሪካ ጠላት ነው\" ሲሉ ገጻቸው በመዘጋቱ የተሰማቸውን በጠንካራ ቃላት ገልፀዋል። ቴሌግራም በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ ረዘም ያለ መግለጫ የለጠፉት ፖለቲከኛዋ \"ማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች እውነቱን ማፈን አይችሉም\" ብለው ትዊተር \"የኮሚዩኒስት አብዮትን እያገዘ ነው\" ሲሉ ወቅሰዋል። ምንም እንኳ የአዋዘጋቢዋ ፖለቲከኛ የግል ገጽ ይዘጋ እንጂ ኦፊሴላዊ የኮንግረስ ገጻቸው ግን አሁንም እየሰራ ሲሆን፣ እዚህ ገጽ ላይ መልዕክት የሚለጥፉት ለሥራው የተመደቡ ሙያተኞች ናቸው። የ47 ዓመቷ ማርጆሪ ቴይሌር ግሪን ባለፈው ቅዳሜ \"አሜሪካ ውስጥ በርካታ ክትባት የወሰዱ ሰዎች እየሞቱ ነው\" ሲሉ ያልተረጋገጠ ወሬ ማጋራታቸው ነው ገጻቸውን እንዲዘጋ ያደረገው። የጆርጂያ ግዛት ሕዝብ እንደራሴዋ ከትዊተር የታገዱት የኮሮናቫይረስ የተሳሳተ መረጃ ፖሊሲን \"በተደጋጋሚ በመጣሳቸው ነው\" ሲሉ የትዊተር ቃል አቀባይ ለቢቢሲ በጽሑፍ አሳውቀዋል። ቃል አቀባዩ እንደሚሉት ኩባንያው አራት ጊዜ ሕግ ጥሰው የሚገኙ ሰዎችን ገጽ በጊዜያዊነት ያግዳና ቆይቶም በቋሚነት ሊያግድ ይችላል። \"ሰዎች በተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ ገፃቸውን እስከወዲያኛው እናግዳለን\" ብለዋል አፈ ቀላጤው። ባለፈው የአሜሪካ ምርጫ ድምፅ አግኝተው ወደ ዋሺንግተን የመጡት ግሪን በአወዛጋቢ ድርጊታቸው ይታወቃሉ። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ የሆኑት ግሪን፤ ትራምፕ ባለፈው ምርጫ አልተሸነፉም ምርጫው ተጭበርብሮ እንጂ ከሚሉት መካከል ናቸው። አልፎም ሴትየዋ 'ኪውኤነን' ከተባለው የነጭ አሜሪካዊያን የሴራ ፅንሰ ሐሳብ አራማጅ ድርጅት ጋር ስማቸው ሲያያዝ ይሰማል። ፖለቲከኛዋ፤ ምንም እንኳ አገራቸው አሜሪካ በቫይረሱ ምክንያት 825 ሺህ ሰዎች ብታጣም ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረጉ እርምጃዎችን አጥብቀው በመቃውም ይታወቃሉ። የክትባቶችን የመከላከል አቅም በተደጋጋሚ ሲወቅሱ የሚደመጡት ማርጆሪ ቴይለር ግሪን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አልጠቀመም ብለው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ውስጥ ግርግር እስከመፍጠር ደርሰው ነበር።", "ቤተ መንግሥታቸው በተቃዋሚዎች የተወረረው የሲሪላንካ ፕሬዚዳንት ከሥልጣን ሊለቁ ነው ተቃዋሚዎች የሲሪላንካውን ፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ። ተቃዋሚዎቹ በደረሱበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ፕሬዚዳንቱ በቅጥር ግቢው ውስጥ አልነበሩም። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በመዲናይቱ ኮሎምቦ አደባባይ ወጥተው ፕሬዚዳንት ራጃፓክሳ ሥልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል። ይህም በአገሪቱ በኢኮኖሚ አስተዳደር እጦት ምክንያት ለወራት ከዘለቀው የተቃውሞ ሰልፍ በኋላ መሆኑም ተዘግቧል። ፕሬዚዳንት ራጃፓክሳ ከቀናት በኋላ ሥልጣን ይለቃሉ ተብሏል። ከእሳቸው በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዊክሬሜሲንጌ ከሥልጣን ለመልቀቅ ተስማምተዋል። የፓርላማው አፈ-ጉባዔ ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት “በሰላማዊ መንገድ የሥልጣን ርክክብ እንዲኖር ነው” ሲሉ ሕዝቡም “ሕግ እንዲያከብር” ጠይቀዋል። የፕሬዚዳንቱ ውሳኔ በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ ፈንጠዝያን ፈጥሯል፤ በርካቶችም ርችቶችን በተኮስ ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በትናንትናው ዕለት ተቃዋሚዎች የፕሬዚዳንቱን መኖሪያ ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ አሜሪካ የአገሪቱን የምጣኔ ሀብት ችግር ለመፍታት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ የሲሪላንካ አመራሮችን ጠይቃ ነበር። በፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ለተቃውሞ ወጥታ የነበረች ፊዮና ሲርማና የተባለች ግለሰብ “ፕሬዚዳንቱን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን በማስወገድ ለሲሪላንካ አዲስ ዘመን የምንቀዳጅበት ጊዜ አሁን ነው” ስትል ተናግራለች። “ቀደም ብለው ከሥልጣን ባለመውረዳቸው በጣም አዝኛለሁ፤ ምክንያቱም ቀደም ብለው ቢሰናበቱ ምንም አይነት ውድመት ባልደረሰም ነበር” ስትል ለሮይተርስ ዜና ወኪል አስረድታለች። በቅዳሜው ተቃውሞ በርካታ ዜጎች የቆሰሉ ሲሆን፣ የኮሎምቦ ዋና ሆስፒታል ቃል አቀባይ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት ሦስት ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ሲሪላንካ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተናጠች ሲሆን በአገሪቱ በ70 ዓመታት ውስጥ ያልታየ በተባለው አስከፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ምግብ፣ ነዳጅ እና መድኃኒት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየታገለች ነው። የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ተመናምኖ ያለቀ ሲሆን፣ ለግል ተሽከርካሪዎች ቤንዚን እና ናፍታ ሽያጭ ላይ እገዳ ተጥሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞም ነዳጅ ለማግኘት ለቀናት በርካቶች ረጃጅም ሰልፎች ላይ ታይተዋል። የቅዳሜው ያልተለመደ ክስተት በሲሪላንካ ውስጥ ለወራት የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ማክተሚያ ይመስላል። በፕሬዚዳንት ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአገሪቱን ሰንደቅ አላማ የያዘ ሕዝብ መፈክሮችን በማሰማት አጥሩን ጥሰው ገብተዋል። ከስፍራው የወጣ ቪዲዮ ተቃዋሚዎች በግቢው ውስጥ ሲዘዋወሩ እና በፕሬዚዳንቱ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ሲዋኙ፣ ሌሎች ደግሞ የፕሬዚዳንቱን እቃዎች ሲበረብሩ እንዲሁም አንዳንዶች የቅንጦት መታጠቢያ ቤታቸውን ሲጠቀሙ ያሳያል። ቅንጡ የሚባለው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት እና  22 ሚሊዮን ሕዝብ ነዋሪ ያሳለፈው የመከራ ወራት ልዩነት ተቃዋሚዎች በዝምታ ሊያልፉት አልፈለጉም። “መላው አገሪቱ እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ ባለበት ወቅት ሰዎች የተሸከሙት ጫና ለማስተንፈስ ወደዚህ መጥተዋል። በዚህ ቤት ውስጥ ያለውን የቅንጦት ሁኔታ ስንመለከተው ለአገር ለመስራት ጊዜ እንደሌላቸው ግልፅ ነው” በማለት ቻኑካ ጃያሱሪያ የተባሉ ግለሰብ ለሮይተርስ ተናግረዋል።", "ትራምፕ የካፒቶል ሂል አመጽን እንዲያወግዙ ቢጠየቁም ፍቃደኛ አልነበሩም ተባለ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አመጸኞች ካፒቶል ሂልን በኃይል ጥሰው ሲገቡ እርምጃውን ከማውገዝ ይልቅ ክስተቱን ዋይት ሃውስ ሆነው በቴሌቪዥን መስኮት መከታተልን መርጠዋል ተባለ። ሪፓብሊካኑ አደም ኪንዚንግለር፤ ትራምፕ አመጸኞቹን እንዲያወግዙ ልጆቻቸው እና አማካሪዎቻቸው “ቢለምኗቸውም” ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ሲሉ ክስተቱን እየመረመረ ላለው ኮሚቴ ተናግረዋል። “ምንም አይነት እርምጃን አለመውሰድን መርጠዋል” ሲሉ የሪፓብሊካን ፓርቲ አባሉ ኪንዚንግለር በዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ለሚመራው ኮሚቴ ተናግረዋል። የካፒቶል ሂል አመጽን እየመረመረ የሚገኘው ኮሚቴ ትራምፕ ሁከቱን ለማስቆም ለሕግ አስከባሪ አባላትም ይሁን ለብሔራዊ ደኅንነት አማካሪዎቻቸው ስልክ እንዳልደወሉ ተነግሮታል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዋይት ሃውስ ባለው መመገቢያ ክፍል ከ2 ሰዓት በላይ የዘለወቀውን የፎክስ ኒውስ ዘገባ ሲከታተሉ ነበር ተብሏል። የቨርጂኒያው ዴሞክራት ፓርቲ አባል ኤልይን ሉሪያ፤ “የፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪዎች እና የቤተሰብ አባላት ከየትኛውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚጠበቀውን እንዲያደርጉ ቢለምኗቸውም ትራምፕ መመገቢያ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለው ጥቃቱ ሲፈጸም በቴሌቪዥን መስኮት ሲከታተሉ ነበር” ብለዋል። ትራምፕ አመጹን ለማስቆም እርምጃ ከመውሰድ የተቆጠቡት “በስልጣን ላይ ለመቆየት ያላቸውን የግል ፍላጎት” ለማሳካት ነው ተብሏል። ትናንት ሐሙስ ሐምሌ 14/2014 ዓ.ም. በአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው ኮሚቴ ከአንድ ዓመት በፊት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂልን በኃይል ሲወሩ በነበሩት 187 ደቂቃዎች ዶናልድ ትራምፕ ምን ሲያከናውኑ ነበር የሚለውን ለመለየት ለ8ኛ ጊዜ ምስክሮችን ሰምቷል። ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት በአሜሪካ የተደረገውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ማሸነፋቸውን ተከትሎ የሕዝብ እንደራሴዎች የባይደንን የምርጫ ውጤት ለማረጋገጥ ስበሰባ ላይ ሳሉ፤ የትራምፕ ደጋፊዎች ወደ ሕንጻው በኃይል በመግባት የሕዝብ እንደራሴዎችን ስብሰባ አውከዋል። ትራምፕ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ በአውሮፓውያኑ 2020 የተካሄደው ምርጫ የተጭበረበረ ነው በማለት ሽንፈታቸውን አልተቀበሉም። ይህ በአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው ኮሚቴ፤ ሪፐብሊካኑ ትራምፕ፤ በዴሞክራቱ ጆ ባይደን የደረሰባቸውን ሽንፈት ለመቀልበስ ሕጋዊ ያልሆኑ እርምጃዎችን ወስደዋል የሚል ክስ ለመመስረት የሚያስችለውን መረጃ እያስባሰበ ነው። በቀጣይ 2024 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ያመላከቱት ትራምፕ፤ ጉዳያቸውን እየመረመረ የሚገኘውን ኮሚቴ አጥብቀው ይተቻሉ። ትራምፕን እየመረመረ የሚገኘው ኮሚቴ እስካሁን የተቀበላቸውን ምስክርነቶች ይዞ ትራምፕ ላይ ‘የኮንግረሱን ይፋዊ ሥራ ማደናቀፍ’ እና ‘የአሜሪካን ሕዝብ ለማጭበርበር ማሴር’ የሚሉ ክሶችን መመስረት ይቻላል ሲል ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።", "የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ምርጫና ቀጠናዊ አንደምታው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2012 እስከ 2017 የሶማሊያ ስምንተኛው ፕሬዝዳንት የነበሩት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በድጋሚ ተመርጠዋል። በሦስት ዙር በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 214 አብላጫ ድምጽ በማግኘት፣ ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆን አሸንፈው ሥልጣነ መንበሩን ተረክበዋል። በሥልጣን ዘመናቸው፣ በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ አልፎም ሶማሊያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት እንዲሁም ከምዕራቡ ዓለም አገራት ጋርም እርቀ ሰላም እንድታወርድ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በ2017 በድጋሚ ሲወዳደሩ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ እንደረቷቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ መልሰው ሥልጣኑን ከፈርማጆ ተረክበዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ከዓመት በላይ ተራዝሞ የነበረው ምርጫ በሶማሊያ ለወራት የዘለቁ ውዝግቦች መጫሩ አይዘነጋም። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የምርጫ ማራዘሚያ ውሳኔን በማጽደቅ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆን የሥልጣን ዘመን ለሁለት ዓመት ማራዘሙን ተከትሎ በሶማሊያ ፖለቲከኞች መካከል የተፈጠረው ስንጥቅ በመዲናዋ ሞቃዲሾ ሁከት ማስከተሉ ይታወሳል። በፌደራል መንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል በተነሳ ግጭት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። በተለይም በፈርማጆ እና በጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሑሴን ሮብሌ መካከል የተፈጠረው እሰጣ ገባ ተካሮ፣ ፈርማጆ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን እስከማገድ ደርሰዋል። የፖለቲካ ውጥንቅጡ ያሰጋቸው የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ ፈርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም መወሰናቸውን ኮንነዋል። እንዲያውም አሜሪካ \"በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት\" ላይ ማዕቀብ እንደምትጥልም ዝታ ነበር። በሌላ በኩል ትላንት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች እንደገና በሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠታቸው ተገልጿል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ 700 የሚጠጉ ሶማሊያ ውስጥ ሰፍረው የነበሩ ሁሉም ወታደሮቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያሳለፉትን እርምጃ ባይደን ቀልብሰው፣ የአሜሪካ የልዩ ተልዕኮ ኃይል አባላት በድጋሚ እንደሚሰማሩ ተነግሯል። የ30 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ያሽመደመዳት ሶማሊያ በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የተወጠረች አገር ናት። በዚያ ላይ ስር የሰደደ ሙስና እንዲሁም የጎሳ ክፍፍል ይንጣታል። አክራሪው ታጣቂ ቡድን አል-ሸባብ ሶማሊያን ከጥግ ጥግ ከማናጋት አልፎ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት ከሆነም ሰነባብቷል። የመካከለኛው ምሥራቅም ይሁን የምዕራቡ ዓለም አገራት ሶማሊያ ላይ ካላቸው ልዩ ፖለቲካዊ ፍላጎት ባሻገር፣ አሳሳቢው ድርቅ እና ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ሕዝቡን እየፈተነው ይገኛል። ለመሆኑ የሐሰን ሼክ ሞሐሙድ መመረጥ ለሶማሊያ፣ ለአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነትስ ሊለወጥ ይችላል? ዳሰሳችንን ከኢትዮጵያ ጀምረን ወደ ቀጠናው ከዚያም ወደ ሶማሊያ እናደርጋለን። አዲሱ ፕሬዝዳንት እና ኢትዮጵያ በአዲሱ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ምን ሊመስል ይችላል? የሚለውን ለመገመት ከኢትዮጵያ እና ከቀድሞው ሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ግንኙነት ጋር የተያያዙ ሁለት ቁልፍ ነጥቦችን እናንሳ። አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከፈርማጆ ጋር የደረሱት ሦስትዮሽ ስምምነት ነው። ሁለተኛው ቁልፍ ነጥብ ደግሞ የሶማሊያ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተሳትፎ ነበራቸው የሚለው ያልተረጋገጠ ክስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ፈርማጆ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እአአ በ2018 መባቻ ላይ የሦስትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። በእርግጥ ይህ ስምምነት ዝርዝር ይዘቱ ምንድን ነው? ለሚለው ግልጽና ይፋዊ መረጃ ባይወጣም፣ ስምምነቱ ሲፈረም ፈርማጆ በትዊተር ገጻቸው \"በአስመራ ከተማ ስምምነት በመፈረማችን ኩራት ይሰማኛል። ስምምነቱ የምጣኔ ሀብት፣ የፖለቲካ፣ የደኅንነት፣ የባህልና የማኅበረሰብ ትብብርን የሚያጎለብት ነው\" ብለው ነበር። በቀጣይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁለቱን መሪዎች ወደ ጎንደር ከተማ ጋብዘዋቸው በአስመራ ስለተፈረመው የሦስትዮሽ ስምምነት ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቧል። ይህንን የሦስቱ መሪዎች ስምምነት በጥርጣሬ የተመለከቱ የፖለቲካ ልሂቃን ድምጻቸውን ማሰማታቸው አይዘነጋም። ይህ የሦስትዮሽ ግንኙነት በአዲሱ ፕሬዝዳንት ሊቀጥል ይችላል? ስንል የአፍሪካና ኦሪየንታል ስተዲስ አጥኚና የምሥራቅ አፍሪካን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ነዓምን አሸናፊን ጠይቀናል። የሦስትዮሽ ግንኙነቱ ቀጠናዊ ትስስርን \"ገሸሽ ያደረገ ነው\" ተብሎ ሲተች እንደነበረ በመጥቀስ \"አዲሱ ፕሬዝዳንት የሦስትዮሽ ስምምነቱን ጥለው ሊወጡ ይችላሉ\" ይላሉ። በሶማሊያ ልሂቃን ዘንድ ይህ ስምምነት ሲተች እንደነበር በማንሳት፣ ምናልባትም አዲሱ ፕሬዝዳንት ስምምነቱን እንደማያስቀጥሉ ያብራራሉ። \"የሦስትዮሽ ግንኙነቱ ቀርቶ ሁለቱ አገራት [ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ] አዲስ የሁለትዮሽ ግንኙነት መጀመር ይኖርባቸዋል። ግንኙነቱ አል-ሸባብ የሚፈጥረውን የፀጥታ ስጋት እንዲሁም የተከሰተውን ድርቅ ያማከለ መሆን አለበት\" ሲሉም በኢትዮጵያ በኩል መወሰድ ስለሚኖርባቸው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አቅጣጫ ለውጦች ያስረዳሉ። በሌላ በኩል፣ የሶማሊያ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተሳትፎ ነበራቸው ስለሚለውን ያልተረጋገጠ ክስ አቶ ነዓምንን ጠይቀናል። \"ክሱ እውነት ከሆነ ከዚህ በኋላ [ስምሪቱ] አይኖርም። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እንደ ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ጦርነቱ ውስጥ ጣልቃ ከመግባት ይልቅ የማደራደር፣ የማሸማገል ሚና ሊኖራቸው ይችላል\" ሲሉ መልሰዋል። ለዚህ መከራከሪያ ነጥብ እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ሁለት ነጥቦችን ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዲሁም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለአዲሱ ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ያጣቅሳሉ። \"ሁለቱም መግለጫ ማውጣታቸው [አዲሱ ፕሬዝዳትን] አንዳች ሚና በቀጠናው እንደሚኖራቸው ጠቋሚ ነው\" ይላሉ አቶ ነዓምን። በሁለተኛነት የሚጠቅሱት ሶማሊያ ለአገር ውስጥ ደኅንነቷ የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪዎች መፈለጓን ነው። በኢትዮጵያ ጦርነት ከተፋፋመ፣ በአሚሶም ስርና ውጭም ሶማሊያ ውስጥ የተሰማሩት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ወደ አገር ቤት ሊመለሱ የሚችሉበት ዕድል እንደሚሰፋ በመጥቀስ አዲሱ መሪ \"የኢትዮጵያ ጦር እዛው ሆኖ ሶማሊያን የማረጋጋት ሥራ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ይመስለኛል\" በማለት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን ጥሎ እንዳይወጣ በሚል ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥትና በትግራይ ኃይሎች መካከል ሰላም እንዲወርድ የመደገፍ ሚና እንደሚኖራቸው ነው አቶ ነዓምን የሚጠብቁት። የሁለቱ አገራት ግንኙነት ምን ሊመስል ይችላል? የሚለው በጠቅላላው ሲቃኝ በአንድ በኩል አብዛኞቹ የሶማሊያ ፖለቲካ ልሂቃን አገራቸው አሁን ለገባችበት ቀውስ ኢትዮጵያን ተጠያቂ በማድረግ ጥላቻ አዘል አስተያየት ቢሰነዝሩም፣ በሌላ በኩል አዲሱ ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት እንደነበራቸው ያስረዳሉ። \"ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው። አዲስ አበባ በተደጋጋሚ ይመጡ ነበር። ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የቀረበ ግንኙነት ነበራቸው። ከዚህ ቀደም ሥልጣን ላይ ስለነበሩና አካባቢውን ስለሚያውቁትም መመረጣቸው እንደ ጸጋ ሊወሰድ ይችላል።\" በተቃራኒው ግብፅና ሌሎችም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የሶማሊያን \"እጅ መጠምዘዝ\" እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ ይህም በተለይም ከግብፅ በኩል ወደ ኢትዮጵያ አደጋ እንደሚቃጣ ያስረዳሉ። \"የመካከለኛው ምሥራቅን ሚና ለማስፋት ሶማሊያን እንደ መነሻ ይጠቀሟታል። ቱርክ የሶማሊያን ምጣኔ ሀብትና ፖለቲካ ስለምትቆጣጠርም የአዲሱ ፕሬዝዳንት ምርጫ አስጊ ሊሆን ይችላል።\" የአፍሪካ ቀንድና አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ከውስጣዊ የፖለቲካ ቀውስ አልፎ በአገራት መካከል በሚነሳ የወሰን፣ የጥቅማ ጥቅምና ሌሎችም ግጭቶች ይታመሳል። ኬንያ እና ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሌሎችም የቀጠናው አገራት በተጠንቀቅ ይጠባበቃሉ። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ \"ሰላምን በመስበክ\" እንደሚታወቁ የሚጠቅሱት አቶ ነዓምን \"ለንግግር ክፍት ይመስላሉ። እንደ ፈርማጆ በሌላ አገር ጣልቃ የመግባት አዝማሚያ ሳይሆን ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሰላም የመፍጠር አዝማሚያ ያላቸው ይመስላል\" ሲሉ ያስረዳሉ። በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መሪዎች መካከል የተፈረመው ሦስትዮሽ ስምምነትን በተመለከተም \"ምንነቱ የማይታወቅ፣ ኢጋድን የዘለለ ስምምነት ነው። ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ ወይም ምጣኔ ሀብታዊ ለማለት የሚቸገር ስምምነት መሰል ነው። [አዲሱ ፕሬዝዳንት] በዚህ በማያውቁት ስምምነት ላይ ይገባሉ ብዬ አላምንም\" ሲሉ ያክላሉ። ይህ ስምምነት ከተገታ፣ በቀጣይ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያም የተሳተፉበት ቀጠናዊ ትስስር ለመፍጠር ዕድል ሊፈጥር እንደሚችል ያምናሉ። አዲሱ ፕሬዝዳንት በተለይም ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚሹ በበዓለ ሲመታቸው ገልፈዋል። ስለዚህም በሶማሊያ እና በኬንያ እንዲሁም በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚከሰቱ የድንበር ግጭቶች እንደሚረግቡ ተስፋ አለ። \"የቀጠናውን አሰላለፍ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከቱርክ እና ከምዕራቡ አገራት ፍላጎት ጋር አጣጥመው ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሰላም እንደሚያወርዱ ይታመናል\" ይላሉ አቶ ነዓምን። ለሶማሊያ አዲስ ጅማሮ? ተንታኞች እንደሚሉት፣ የሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በድጋሚ መመረጥ ሶማሊያን እንደ አዲስ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት መነሻ ተደርጎ ይቆጠራል። በሌላ በኩል የሶማሊያን ውስብስብ ፖለቲካ፣ የውስጥና የውጭ ጠንካራ ፍላጎቶችን ከግምት በማስገባት የፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመን በፈተና እንደሚሸበብ ይገመታል። አቶ ነዓምን በበኩላቸው፣ በከፍተኛ ሙስና እና የፖለቲካ ንቅዘት ሲታማ የነበረውን የፈርማጆ አስተዳደር አውርዶ የመጣ አዲስ አመራር እንደመሆኑ \"ለሶማሊያ አዲስ ተስፋ ያጭራል\" ሲሉ አዲሱን አስተዳደር ይገልጹታል። በፈርማጆ እና በጠቅላይ ሚኒስትራቸው መካከል ተፈጥሮ የነበው ውዝግብ ከጎሳ አባላት ባለፈ በፖለቲካ ልሂቃኖች መካከል ክፍተት ፈጥሮ እንደነበር በማስታወስ፣ አዲሱ ጅማሮ የሶማሊያን የፖለቲካ ተዋናዮች ወደ አንድ ጠረጴዛ አምጥቶ ሰላም ለማውረድ በር እንደሚከፍት ይጠብቃሉ። ፈርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በመሞከራቸው የተነሳው ውዝግብ ሶማሊያ ካሳየችው ማንሰራራት እየተንሸራተተች ነው የሚል ስጋት እንደጫረ ጠቅሰው፣ ቀውሱን ከማርገብ አንጻር ፕሬዝዳንቱ ተስፋ እንደሚጣልባቸው ያክላሉ። የተባበሩት መንግሥታት ወደ ረሃብ ሊሸጋገር ይችላል ላለው ድርቅ መፍትሄ ከማበጀትና አል-ሸባብን ከመዋጋት አንጻር እንደ አሜሪካ ካሉ አጋር አገራት ጋር በትብብር ለመሥራት የአዲሱ ፕሬዝዳንት መመረጥ ከፍተኛ ሚና አለው። \"ውስብስቡ የሶማሊያ ፖለቲካ በአንድ ምሽት፣ በአንድ ፕሬዝዳት ይፈታል ባይባልም አዲስ ጅማሮ ነው ማለት ይቻላል\" ይላሉ አቶ ነዓምን። በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በ329 የጎሳ ወኪሎች የተካሄደ እንጂ ሕዝቡ የተሳተፈበት አለመሆኑን በማንሳት፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዳልተረጋገጠ ያስረዳሉ። ጥቂት ስለ ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲሱ ፕሬዝዳንት በትምህርት ዘርፍ ይታወቃሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ማጠንጠኛ ሶማሊያን ከተቀረው ዓለም ማስታረቅና የሕዝቡን አንድነት ማረጋገጥ ነው። የተወለዱት እአአ በ1955 ሂራን ግዛት ነው። በሞቃዲሾ በመካከለኛው መደብ ሰፈር አድገው ከሶማሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርስቲ በምህንድስና በ1981 ተመርቀዋል። በቅርብ የሚያውቋቸው ዝምተኛና የማይታበዩ ሰው ናቸው ይሏቸዋል። ሶማሊያ ለ30 ዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥ አገሪቱን ጥለው ካልሄዱ ጥቂት መሪዎች መካከልም አንዱ ናቸው። ሁለተኛ ዲግሪ ከመሥራታቸው በፊት በሕንድ ቦሆፓል ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ነበሩ። ወደ ሶማሊያ ሲመለሱ በተባበሩት መንግሥታት የተዘረጋውን የመምህራን ሥልጠና ለመምራት በትምህርት ሚኒስቴር ተቀጠሩ። በ1991 ማዕከላዊው መንግሥት ሲንኮታኮት፣ በዩኒሴፍ የትምህር ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ። ከሦስት ዓመታት በኋላ፣ በሞቃዲሾ ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ግንባር ቀደም ከሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱን ከፈቱ። የሙስሊም ወንድማማችነት (Muslim Brotherhood) የሶማሊያ ቅርንጫፍ የሆነው አል-ኢላህ ጋር ግንኙነት አላቸው። የጎሳ ግጭት በተነሳበት ወቅት ለማኅበረሰቡ የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ቡድኑ ከግብፅና ሱዳን ጋር ተመሳሳይ በሆነ የእስልምና አስተምህሮት የሚተዳደር ትምህርት ቤቶች ከፍቷል። እንደ አል-ሸባብ እና አል-ቃይዳ ያሉ አክራሪዎችንም ያወግዛል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ \"ለዘብተኛ ሙስሊም\" ተብለው ይታወቃሉ። በጦርነት የደቀቀችውን ሶማሊያ ለመደገፍ በንግድ ሰዎች የተቋቋመው 'ዩኒየን ኦፍ ኢስላሚክ ኮርትስ' ከተባለው ፍርድ ቤት ጋርም ትስስር አላቸው። የአዲሱ ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች እንደሚሉት፣ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ የሚሠሩ መሪ ናቸው። በ1990ዎቹ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ ከፍተኛ ንቅናቄ ያደርጉ ነበር። የጎሳ ግጭትን በማርገብም ይታወቃሉ። ሞቃዲሾን ለሁለት ሰንጥቆ በሁለት ተፎካካሪ ጎሳዎች እንድትመራ ያደረጋት \"ግሪን ላየን\" የተባለውን አካሄድ ለማፍረስ በተደረገው ድርድር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ከፍተኛ ድርቅን ጨምሮ በበርካታ ችግሮች የተሸበበች አገር ነው ከፈርማጆ የሚረከቡት። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፣ ድርቁ ካልተገታ ወደ ረሃብ ከፍ ሊል ይችላል። ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ሆነው አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ይጠብቃሉ። ሶማሊያን የኑሮ ውድነትና የዩክሬን ጦርነት ያባባሰው የዋጋ ግሽበትም ይፈትናታል። በፌደራል መንግሥቱና በክልሎች መካከል እየሰፋ ያለው ልዩነትም ሌላው የሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ የቤት ሥራ ይሆናል። ሙስና ሌላው የሶማሊያ ማነቆ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት አገራቸው ከኬንያ፣ ጂቡቲ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር ያላትን ግንኙነት የማደስ ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ 2012 ላይ ሲመረጡ አገራቸው ከምዕራባውያን እና ከአፍሪካ አገራት ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ትስስሯን እንድታድስ አስችለዋል። በሌላ በኩል በአስተዳደራቸው ስር ያለውን ሙስና ማስወገድ አልቻሉም ተብለው ይታማሉ።", "በእስራኤል የተካሄደውን ምርጫ የቤንያሚን ኔታኒያሁ ጥምር ፓርቲ አሸነፈ በእስራኤል የተካሄደውን ምርጫ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጥምር ፓርቲ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችለውን  ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በምርጫው ተቀናቃኛቸው የነበሩት ያሪ ላፒድ፣ ኔታኒያሁን እንኳን ደስ አልዎት ብለዋል። ላፒድ ለተፎካካሪያቸው ደውለው መልካም እድልን የተመኙላቸው ሲሆን፣ ሥርዓቱን የተከተለ የሥልጣን ሽግግር እንደሚኖር አረጋግጠውላቸዋል። ሊኩድ የተባለው የኔታኒያሁ ፓርቲ እና የቀኝ አክራሪው ሃይማኖታዊ ፓርቲ አጋሩ በጣምራ ከእስራኤል 120 የፓርላማ መቀመጫ 64ቱን እንዳሸነፈ ባለፈው ማክሰኞ ይፋ የሆነው የመጨረሻ ውጤት አሳይቷል። ውጤቱም ባልጠበቀ ሁኔታ የቀድሞን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣን የመለሰ ሆኗል። ውጤቱም እንደ አውሮፓውያኑ በ2019 ኔታኒያሁ ላይ የተከፈቱት እና እሳቸው ግን የማይቀባሏቸውን የሙስና፣ ማጨበርበር እና እምነትን ማጉደል ክሶች እንዲያበቁ ያደርጋል። ከዋናው ውጤት በፊት የነበሩ ቅድመ ውጤቶች ኔያኒያሁ እየመሩ እንደሆነ ካመላከቱ በኋላ፣ ባደረጉት ንግግር ለፓርቲያቸው ደጋፊዎች ባደረጉት ንግግር ያለምንም ልዩነት ሁሉንም እስራኤላዊ የሚያገለግል መንግሥት አቋቁማለሁ ብለዋል። “ደኅንነታችንን መልሰን እናረጋግጣለን፣ የኑሮ ውድነትን እንቀንሳለን፣ ሰላማችንን ይበልጥ እናጠናክራለን እስኤልን በአገራት መካከል ኃያል የሚያደርጋትን ጥረት እንመልሳለን” ብለዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን በዘገቡት የመጨረሻ ውጤት መሠረት የኔታኒያሁ ሊኩድ ፓርቲ 32 መቀመጫ፣ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላፒድ ፓርቲ ደግሞ 24 መቀመጫ ያገኙ ሲሆን የቀኝ አክራሪው ብሔርተኛ ጽዮናዊ ፓርቲ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ የአንድነት ፓርቲ ደግሞ 12 መቀመጫ አግኝቷል። የተቀረሩትን መቀመጫዎች ደግሞ የተለያዩ ፓርቲዎች ይዘዋቸዋል። ኔታኒያሁ በንግግራቸው ጥምረታቸው የሚያካትቷቸውን ፓርቲዎች ባይጠቅሱም የጽዮናዊ ፓርቲን እንደሚያካትት ይጠበቃል።", "ዩክሬን፡ ሩሲያ ወታደሮቼን ከዩክሬን ድንበር አስወጥቻለሁ ማለቷን አሜሪካ ሐሰት ነው አለች የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሩሲያ ከዩክሬን ድንበር ወታደሮቼን አንቀሳቅሻለሁ ማለቷ ሐሰት ነው አሉ። ባለሥልጣኑ አክለውም የሩሲያ ተጨማሪ 7 ሺህ ወታደሮች በቅርብ ቀናት ድንበር ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ ሩሲያ ዩክሬንን \"በማንኛውም ሰዓት\" ለመውረር \" የሐሰት\" ምክንያት ልትከፍት ትችላለች ብለዋል። ሞስኮ በበኩሏ ወታደሮቿ የጦር ልምምዳቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከዩክሬን ድንበር ለቀው መውጣታቸውን ገልጻለች። ይሁን እንጂ ምዕራባውያን ባለሥልጣናት ሩሲያ ወታደሮቿን ማስወጣቷን የሚያረጋግጥ ምንም ማስረጃ የለም ብለዋል። እንደ ጀርመን ቻንስለሪይ ከሆነ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ስኮልዝ ረቡዕ ዕለት ባደረጉት የስልክ ውይይት ሩሲያ የተባባሰውን ውጥረት ለማርገብ ትክክለኛ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባት ተስማምተዋል። ሩሲያ ዩክሬንን የመውረር እቅድ እንደሌላት በተደጋጋሚ ብትገልጽም ከ100 ሺህ የሚበልጡ ወታደሮቿን በድንበር አካባቢ ማስፈሯ ድንገት ወረራ ልትፈፅም ትችላለች በሚል ምዕራባውያንን አስግቷል። ረቡዕ ዕለት የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ታንኮች ክሬሚያን ለቀው ሲወጡ ለማሳየት ተንቀሳቃሽ ምሥል አውጥቷል። ይሁን እንጂ እንደ ዋይት ሃውስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከሆነ ረቡዕ ዕለት የደረሱትን ጨምሮ በቅርብ ቀናት በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ የሩሲያ ወታደሮች ድንበር ላይ ደርሰዋል። ከፍተኛ ባለሥልጣኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ \"ይህ ሩሲያ ጦሯን ከዩክሬን ጋር ከምትዋሰንበት ድንበር እያስወጣሁ ነው ማለቷን ጥርጣሬ ውስጥ ከትቷል\" ብለዋል። \" ሩሲያ ወታደሮቼን አስወጥቻለሁ ማለቷ ከዚህ እና ከመላው ዓለም ከፍተኛ ትኩረት እንድታገኝ አድርጓታል፤ ነገር ግን አሁን ይህ ሐሰት መሆኑን አውቀናል\" ብለዋል ከፍተኛ በላሥልጣኑ። ባለሥልጣኑ ይህንን ያሉት የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ \" እስካሁን ወታደሮች ወጡ ሲባል ነው የሰማነው እንጂ፤ ሲወጡ አላየንም\" ሲሉ ለቢቢሲ ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላ ነው። ፕሬዚደንቱ ይህ የተናገሩት ረቡዕ ዕለት ዩክሬን \"የአንድነት ቀን\" በሚል በዓል ስታከብር ነው። በዕለቱ በመላ አገሪቷ ሰማያዊ እና ቢጫ ቀለም ያላቸው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማዎች ተሰቅለዋል። ፕሬዚደንት ዜለንስኪ ዕለቱን \"የአርበኝነት በዓል\" ሲሉ ያወጁት የአሜሪካ ደህንነት ቢሮ በዚያን ዕለት ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጥቃት ልትፈፅም ትችላለች በሚል ላወጣው ሪፖርት ምላሽ ነው። ረቡዕ ዕለት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ የሩሲያ ጦር ውጥረቱን ማርገቡን የሚያሳዩ ምልክቶች እንደሌሉ ገልጸው፤ ከሩሲያ የሚሰነዘረው ማስፈራሪያ \"እየተለመደ መጥቷል\" ሲሉ ተናግረዋል። በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው የኔቶ መከላከያ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትር ስቶልተንበርግ፣ ድርጅቱ አዳዲስ የውጊያ ቡድኖችን ማለትም ብቃት ያላቸውና ራሳቸውን የሚችሉ ትናንሽ ወታደራዊ ቡድኖች በመካከለኛው እና በደቡብ ምሥራቅ አውሮፓ ለማቋቋም እያሰበ ነው ብለዋል። ኔቶ ለሩሲያ ስጋት አለመሆኑን ለማርጋገጥ የሞከሩት ሚኒስትሩ፤ ይህ ሃሳብ እአአ ከ2014 ጀምሮ 270 ቢሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የአውሮፓ መከላከያን ለማጠናከር እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች አካል መሆኑን አስረድተዋል። ፈረንሳይ በሮማኒያ ውስጥ አንድ የጦር ቡድን ለመምራት ሃሳብ አቅርባ እንደነበርም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ሚኒስትር ስቶልተንበርግ በሰጡት መግለጫ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።", "የፈረንሳይ ዜጎች በማዳጋስካር መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተፈረደባቸው በማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆኤሊና ላይ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ በማቀድ ሁለት የፈረንሳይ ዜጎች የ10 እና 20 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል። ፖል ራፋኖሃራና እና ፊሊፕ ፍራንኮይስ የተባሉት ግለሰቦች የመንግስትን ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል፣ ፕሬዚዳንቱን ለመግደር በማሴርና የወንጀል ማህበር በመፍጠር በሚል ተከሰው ነበር። ሌሎች 20 ተከሳሾችም በእስር ተቀጥተዋል። የግለሰቦቹ ጠበቃ ቅጣቱን በመቃወም ይግባኝ ለማቅረብ ማቀዱን ተናግሯል። \"እኔ እንደጠበቅኩት ሳይሆን ፍትሃዊ ያልሆነ ፍርድ ነው...የፖለቲካ ክስ ነው\" ሲሉ ጠበቃ ሶሎ ራድሰን መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ባለሥልጣናቱ እንዳሉት በሐምሌ ወር በግለሰቦቹ ላይ ባደረጉት ብርበራ ማስረጃ የሚሆኑ \"ኢሜይሎችን ፣መሳሪያዎችን እና ገንዘቦችን ከያዙ በኋላ \"አፖሎ 21\" የተሰኘውን የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ ማግኘታቸውን ተናግረዋል ። በመረጃውም መሰረት ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን \"የማጥፋት እና የማስወገድ\" ዕቅዶችን እንዳካተተም ተናግረዋል። ፊሊፕ ፍራንኮይስ የተባለው የፈረንሳይ ጦር የቀድሞ ኮሎኔል በ10 አመት እስራት ተቀጥቷል። በአንድ ወቅት የፕሬዚዳንት ራጆኤሊና አማካሪ ሆኖ ያገለገለውና የፈረንሳይና የማዳጋስካር ጥምር ዜግነት ያለው ፖል ራፋኖሃራና የ20 አመት እስር ተፈርዶበታል። ባለቤቱም የአምስት አመት እስር ተፈርዶባታል። የቀድሞ የማዳጋስካር ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ራማሃትራ የአምስት አመት የእስር ቅጣት ተበይኖባቸዋል። ማዳጋስካር ከቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ ነፃነቷን ከተጎናፀፈችበት ከአውሮፓውያኑ 1960 ጀምሮ በርካታ መፈንቅለ መንግሥቶችን አስተናግዳለች።", "እንደ አዲስ የተቀሰቀሰው የኢትዮ-ሱዳን ውዝግብ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮቼን ገድሏል ስትል ሱዳን ክስ አሰምታለች። የሱዳን መንግሥት ድምፅ የሆነው ሱና እንደዘገበው አንድ ሲቪልን ጨምሮ ሰባት ወታደሮች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተገድለዋል። የሱዳን መከላከያ ኃይል ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሱዳናውያኑን ከገደሉ በኋላ “አስክሬናቸውን ለሕዝብ በአደባባይ አሳይተዋል” ሲል ከሷል። የሱዳን መንግሥት በመግለጫው ለድርጊቱ “ምላሽ እሰጣለሁ” ሲል ዝቷል። ኢትዮጵያ ግን ይህ ሆን ተብሎ በሱዳን በኩል የተፈጸመ ጠብ ጫሪነት ያስከተለው ጉዳት መሆኑን በመግለጽ፣ ውጥረቱ ረግቦ አለመግባባቶች በንግግር መፍትሔ እንዲገኝላቸው ጠይቃለች። በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ለዘመናት በቆየው ውዝግብ ምክንያት በሁለቱ አገራት ሠራዊቶች መካከል ግልጽ ወታደራዊ ግጭት ከዚህ በፊት እምብዛም ባይስተዋልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ውጥረቱ እያየለ መጥቷል። ቢቢሲ ሱዳን አጋጥሟል ላለችው ክስተት ከኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ወር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ መንግሥት የአልፋሻጋን ጉዳይ \"በወዳጅነት ለመፍታት ሰላማዊ የውይይት መንገድን ይመርጣል” ማለታቸውን ይታወሳል። ሆኖም \"የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜኑ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ በነበረበት ወቅት ሱዳን የድንበር ማካለሉን መጣሷ በጣም አሳዛኝ ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሱዳን ኃይሎች ኢትዮጵያውያንን አፈናቅለዋል፤ ንብረታቸውንም አውድመዋል ሲሉ ከሰዋል። ሱዳን ትሪቡን የተሰኘው የግል አውታር ባለፈው ሳምንት ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የሱዳን ወታደሮች በድንበር አካባቢ በምትገኘው አል-ቁሬይሻ ከተማ ላይ እርምጃ ከወሰዱ በኋላ ነው ግጭት የተቀሰቀሰው። ሱዳን፤ የኢትዮጵያ ሠራዊት እና ሚሊሻዎች በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገበሬዎችን ለመጠበቅ በሚል ሠፍረዋል መባሉን ተከትሎ እርምጃ የሚወስዱ ወታደሮች መላኳ ይነገራል። በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የወጡ ዘገባዎች ከሰዱን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው የምዕራብ ጎንደሯ መተማ ከተማ ግጭቶች እንደነበሩ ይጠቁማሉ። በመተማ ከተማ በሚገኘው ሽመት መገዱቃ በተባለው ቀበሌ፤ በሱዳን ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የአካባቢው አርሶ አደሮች የግብርና ሥራቸው እንደተስተጓጎለ ተገልጧል። የአሜሪካ ድምጽ፤ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቁን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ “በአንድ ዓመት ውስጥ በእርሻ ሥራ የተሰማሩ 246 ባለሀብቶች ሥራቸውን አቁመዋል” ብሏል። እንደ አልጀዚራና ሮይተርስ ያሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሱናን ጠቅሰው የሱዳን መንግሥት \"እርምጃ እውስዳለሁ\" ማለቱን ዘግበዋል። በዚህም ሳቢያ ሱዳም በአዲስ አበባ ያሏትን አምባሳደር የጠራች ሲሆን፣ በተጨማሪም በካርቱም ያሉትን የኢትዮጵያን አምባሳደር በመጥራት ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠያቋ ተዘግበወል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኞ ከሰዓት በኋላ ባወጣው መግለጫ የሱዳን ወታደሮች ድንበር አልፈው በመግባት ግጭቱን መቀስቀሳቸውን ገልጾ፣ በሱዳን በኩል የቀረበውን ውንጀላ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አድርጎታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ግጭቱ የተከሰተው በህወሓት ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች መሆኑን በመግለጽ የሱዳንን ክስ አጣጥሎታል። ጨምሮም በሱዳን ሠራዊትና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል በተከሰተው ግጭት በጠፋው ህይወት የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያዝን ገልጾ ምርመራ እንደሚደረግ አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ክስተት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለማደናቀፍ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን በማመልከት፣ የሱዳን መንግሥትም ከስተቱን የበለጠ ከሚያባብስ እርምጃ እንደሚቆጠብ ተስፋ እንዳለው ገልጿል። የትግራይ ጦርነት በተቀሰቀሰ በቀናት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የይገባኛል ውዝግብ ከሚነሳባት የአልፋሻጋ አካባቢ ለቆ ወጣ። ጦርነቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ድንበሬ ነው የምትለው አልፋሻጋ በሱዳን ጦር እጅ ወደቀ። ለዘመናት ኢትዮጵያ፤ የሱዳን ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው በመግባት ቆስቋሽ ድርጊት ፈፅመዋል ስትል ትከሳለች። የቀድሞው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በቅርቡ \"የሱዳን ወታደራዊ ኃይል በድንበር አካባቢ ወደ ተጨማሪ ቦታዎች ዘልቆ ለመግባት የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው\" ሲሉ ተደምጠው ነበር። አምባሳደሩ አክለው፤ ችግሩን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት መሞከር \"ፍርሃት ወይም መወላወል አይደለም\" ብለዋል። \"አካባቢውን ከግጭት ለመጠበቅ ሲባል ኢትዮጵያ ነገሮች እንዳይካረሩ ለማድረግ እየጣረች ቢሆንም ይህ ታጋሽነት ገደብ አለው\" የሚል አስተያየት አክለዋል። ኢትዮጵያ አለመግባባቱን በድርድር ለመፍታት ሱዳን የያዘችውን መሬት መልቀቅ አለባት የሚል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች። ሱዳን በበኩሏ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ያለውንና በቅርቡ መልሳ የወሰደችውን መሬት እንደማትለቅ አስታወቃ ነበር። \"ሱዳን ከአልፋሻጋ ይዞታ ቅንጣት ታህል እንደማትሰጥ ሜጀር ጀነራል ሀይደር አልቲራፊ አረጋግጠዋል። ለወታደራዊ ኃይል ምልመላ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል\" ይላል የሱዳን መንግሥት ድምፅ የሆነው ሱና ዘገባ። ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በይገባኛል የምትወዛገብብት አካባቢ ረዥም የግዛት ድንበር ነው ያላት። ሁለቱም አገሮች ለም ነው የሚባለውን ፋሻጋ አካባቢን እጅጉኑ ይፈልጉታል። ይህ በሁለቱ አገራት ዐይን ውስጥ ያለው አካባቢ የአልፋሻጋ ማዕዘን ወይም የአልፋሻጋ ጥግ ተብሎ ይጠራል። በዚህ ድንበር ሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙ ገበሬዎች ባሻገራቸው ያሉ ለም መሬቶች ላይ ያማትራሉ። የአልፋሻጋ ማዕዘን በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን የምሥራቃዊ ገዳሪፍ በአዋሳኝ የሚገኝ ለም መሬት ነው። የአልፋሻጋ መሬት 250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 600 ሺህ ኤክር አሊያም ከ240 ሺህ በላይ ሄክታር ለም መሬትን የሚሸፍን ነው። ለለምነቱ ምክንያት የሆኑት እንደ አትባራ፣ ሰቲት እና ባስላም ወንዞችም በቅርብ ይገኛሉ። ሁለቱ መንግሥታት ከዚህ ቀደም ይህንን አወዛጋቢ ድንበር በድጋሚ ለማስመር፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ድንበሮች ብዙውን ጊዜ ውዝግብ ሲያነሱ ይስተዋላል። ከአስርት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያና ሶማሊያ በኦጋዴን የተነሳ ጦርነት አድርገዋል። እንዲሁም ከ20 ዓመታት በፊት በባድመ ይገባኛል ምክንያት ኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያና ሱዳን ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን 744 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ድንበራቸውን ለይቶ ለማመላከት የሚያስችል ንግግርን መልሰው ጀመሩ። በዚህ መፍትሄ ለመስጠት አስቸጋሪ የሆነው አካባቢ ፋሻጋ የሚባለው ነበር። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1902 እና በ1907 በነበረው የቅኝ ግዛት ስምምነት መሰረት ዓለም አቀፉ ድንበር ወደ ምሥራቅ ይዘልቃል። በዚህም ሳቢያ መሬቱ ወደ ሱዳን የሚካተት ይሆናል። ነገር ግን ቦታው ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ሲሆን የግብርና ሥራ በማከናወንም የሚጠበቅባቸውን ግብር ለኢትዮጵያ መንግሥት ሲከፍሉም ቆይተዋል። ሁለቱ አገራት ሲደረጉ በነበሩ የድንበር ድርድሮች አማካይነት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 2008 ከመግባባት ደርሰው ነበር። በዚህም ኢትዮጵያ ለሕጋዊው ድንበር ዕውቅና ስትሰጥ ሱዳን ደግሞ ኢትዮጵያውያኑ በስፍራው ያለችግር ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ ፈቀደች። ይህም አስከ ቅርብ ጊዜ በድንበር አካባቢ ያሉ የነዋሪዎችን ህይወት ሳያደናቅፍ ኢትዮጵያ ግልጽ የድንበር መለያ እንዲኖር እስክትጠይቅ ድረስ ቀጥሎ ነበር። በሁለቱ አገራት መካከል ከስምምነት የተደረሰበትን የዚህ የድርድር ልዑክ የተመራው የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣን በሆኑት በአባይ ፀሐዬ ነበር። ህወሓት ከማዕከላዊው መንግሥት የሥልጣን መንበር ሲወገድ የአማራ ክልል መሪዎች ከሱዳን ጋር የተደረሰው ስምምነት በአግባቡ ሳያውቁት የተደረገ ድብቅ ውል ነው ሲሉ ተቃውመውታል። ቱርክ ባለፈው ዓመት፤ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ያላቸውን የድንበር ውዝግብ በውይይት እንዲፈቱ ለማሸማገል ጥያቄ አቅርባ ነበር። ነገር ግን ሱዳን ሠራዊቷን ከተቆጣጠረቻቸው አካባቢዎች እንደማታስወጣ ስትገልጥ ኢትዮጵያ ደግሞ የሱዳን እርምጃ ወረራ መሆኑን በመግለጥ ድርድር ከመደረጉ የሱዳን ኃይሎች ድንበሯን ለቃ እንድትወጣ ትጠይቃለች።", "ኔቶ ከቻይና ተደቅኗል ስላለው ወታደራዊ ስጋት አስጠነቀቀ በብራሰልስ የተገናኙት የየሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች በቻይና ተደቅኗል ስላሉት ወታደራዊ ስጋት ያስጠነቀቁ ሲሆን \"ስልታዊ እንቅፋት\" ሲሉ የአገሪቷን ባህሪይ ገልጸውታል። ቻይና የኒኩለር የጦር መሳሪያዋን በፍጥነት እያሰፋች መሆኗን ጠቅሰው የወታደራዊ አቅሟን በማዘመን ረገድ ግልፅ ነበረች ብሎም ከሩሲያ ጋርም በወታደራዊ ትብብር እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል። የኔቶ ዋና ሃላፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ቻይና በወታደራዊ እና በቴክኖሎጂ ረገድ ወደ ኔቶ \"እየቀረበች\" እንደሆነ አስጠንቅቀዋል ። ነገር ግን ጥምረቱ ከቻይና ጋር አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ መግባት እንደማይፈልግ አጥብቀው ተናግረዋል ። ኔቶ በ 30 የአውሮፓ አገራት እና በሰሜን አሜሪካ ሀገሮች መካከል የተመሰተ ጠንካራ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ጥምረት ነው ። የተቋቋመውም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ሲሆን በተለይም ለኮሚኒስት ስርአት መስፋፋት ስጋት ምላሽ ለመስጠት ያሰበ ነበር። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መሪዎች በዓላማው ብሎም የገንዘብ መዋጮን በተመለከተ ያለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ጥምረቱ ውጥረት ውስጥ ከርሟል ። በዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ወቅት ሀገራቸው ለህብረቱ በምታዋጣው የገንዘብ መጠን ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ የቆዩ ሲሆን አሜሪካ የአውሮፓ አገራትን ለመከላከል ያላትን ቀርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነበር። የእሳቸው ተተኪ ጆ ባይደን ስልጣኑን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያ የኔቶ ስብሰባ ሲሆን አዲሱ ፕሬዝዳንት ለ 72 ዓመቱ ህብረት የአሜሪካን ድጋፍ በድጋሚ ለማሳየት ሞክረዋል ። ባይደን ኔቶ \"ለአሜሪካ ፍላጎቶች\" ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው እና አባላት የጥመረቱን የመመሰረቻ ውል አንቀጽ 5 ን በመተግበር እርስ በእርስ ከጥቃት ለመከላከል የተቀመጠውን \"የተቀደሰ ግዴታ\" እንዲተገብሩ ጠይቀዋል ። መጪው ረቡዕ ከሩሲያው መሪ ከቭላድሚር ፑቲል ጋር በጄኔቫ ስለሚያካሂዱት ስብሰባ ሲጠየቁ ‹‹ጠንካራ ተፎካካሪ›› ሲሉ ፑቲንን ገልፀዋቸዋል።", "ቀጣይ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ እኩለ ቀን ይለያል ተሰናባቹን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት በመወዳደር ላይ ከሚገኙት ሊዝ ትረስ ወይም ሪሺ ሱናክ መካከል አሸናፊው ዛሬ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ቀን ላይ ይታወቃል። አሸናፊው ግለሰብ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለ ኢኮኖሚን እና በ40 ዓመታት ከፍተኛው የተባለለትን የዋጋ ግሽበት የሚረከብ ይሆናል። ቀጣዩ መሪ የተከማቸ ኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያን መሰረዝን ጨምሮ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን ለመርዳት እቅድ መያዙን ቢቢሲ ከምንጮቹ ተርድቷል። ይህን ምርጫ ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ሊዝ ትረስ ኃላፊነቱን በተረከቡ በአንድ ሳምንት ግዜ በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጫና ውስጥ የሚገኙ ሸማቾችን መደገፍ የሚያስችሉ እገዛዎችን ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። እንዲሁም በመስከረም ወር መጨረሻ ወደ 30 ቢሊዮን ፓውንድ ገደማ የግብር ቅነሳ ይፋ ለማድረግ ማሰባቸውንም ትረስ አስታውቀዋል። ተቀናቃኛቸው ሱናክ ውድድሩን ተሸንፌአለሁ ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመው “አሁን ዋና ስራዬ ወግ አጥባቂው ፓርቲ የሚመራውን መንግሥት መደገፍ ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ትረስ ከኃይል አቅርቦት ዋጋ ቅናሽ እንዲሁም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከማቀዳቸው ባሻገር ዝርዝር የእርምጃ እቅዳቸውን እስካሁን ድረስ ይፋ አላደረጉም። በአሁን ወቅት የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን በመምራት ላይ የሚገኙት እጩዋ እሁድ በቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የእቅዳቸውን ዝርዝር ሁኔታ ይፋ ለማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ተቀምጠው ተጨማሪ ግዜ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል። ዕቅዳቸው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው ሰዎች ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም ዜጎች የሚለውን ሳይመልሱም ቀርተዋል። ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታም ባለፉት 20 ዓመታት ለነበረው ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገት ተጠያቂው ፍትሃዊ የሃብት ስርጭትን ማስፈን በሚል ሲተገበር የቆየው የግብር ፖሊሲ ነው ብለዋል። የሠራተኛ ፓርቲ፣ ሊበራል ዴሞክራቶች እና ኤስኤንፒ መንግሥት ቢሊዮን ፓውንዶችን አውጥቶ የኃይል ዋጋ ድጎማ እንዲያደርግ የጠየቁ ሲሆን የግሪን ፓርቲ አባላት ደግሞ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አምስት ግዙፍ የኃይል አቅራቢ ተቋማትን ባለቤትነቱን ከግለሰቦች እንዲረከብ ጠይቀዋል። የመሪነቱን ቦታ ይረከባሉ ተብለው የሚጠበቁት ትረስ የተከማቸ የኃይል ክፍያን መሰረዝን ውድቅ ባያደርጉም ከዚህ ቀደም ባደረጉት ክርክር አገራቸው እንግሊዝ የአገር ውስጥ የኃይል አቅርቦት ምንጮቿን ማሳደግ ግድ እንደሚላት ትኩረት ሰጥተው ነበር። ለሰባት ሳምታት የዘለቀው የዩኬ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለመያዝ የተደረገው ፉክክር የቦሪስ ጆንሰንን የሶስት ዓመት የስልጣን ዘመን ቆይታ ማብቂያ የሚያሰምር ይሆናል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ቦሪስ ጆንሰን ከፓርቲያቸው መሪነት ለመልቀቅ የወሰኑት ሪሺ ሱናክን ጨምሮ በርካታ ሚኒስትሮቻቸው አመራራቸውን በመቃወም በ48 ሰዓታት ውስጥ በፈቃዳቸው ሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ነው። በመጀመሪያው ዙር 11 ተወዳዳሪዎች የወግ አጥባቂውን ፓርቲ ለመምራት አቅደው ወደ ውድድር ግብተው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ወደ ሁለት ዝቅ ብሏል። ምንም እንኳን የሕንድ የዘር ግንድ ያላቸው ሱናክ በፓርላማ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ቢኖራቸውም የውጪ ጉዳይ ኃላፊዋ ትረስት አሸናፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ትንበያዎች ያሳያሉ። ተሰናባቹ ቦሪስ ጆንሰን የስልጣን ርክክብ ከመደረጉ በፊት ማክሰኞ የስንብት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የሚያሸንፈው ተወዳዳሪ እስካሁን ባለው ባህል መሠረት በባኪንግሃም ፓላስ ሳይሆን ወደ ስኮትላንድ በመጓዝ በባልሞራል ቤተ-መንግሥት ሲመቱን ከንግስቲቱ የሚቀበል ይሆናል። ለዚህም ምክንያቱ ንግስቲቱ በጤና ምክንያት እንደልባቸው መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ባለፈው ሳምንት ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነው።", "\"የተጠየቅኩባቸው ጉዳዮች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር የሚገናኙ አልነበሩም\" እያስፔድ ተስፋዬ ማኅበራዊ አንቂና በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ሲሰራ የቆው ከኢያስፔድ ተስፋዬ ከ43 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ ከቀናት በፊት ተለቋል። ኢያስፔድ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አስር ዓመታት ያህል በተለያዩ ወቅቶች የቅርቡን ጨምሮ ለዘጠኝ ጊዜያት ያህል ታስሯል። ነገር ግን ከአንድ ወር በላይ ሲታሰር የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ ነው። ከአንድ ባልደረባው ጋር በቅርብ በመሰረቱት 'ኡቡንቱ' በተሰኘ ዩቲዩብ ቴሌቪዥን ላይ ሲሰራ ከነበረው ኢያስፔድ ከአስር ከወጣ ከቀናት በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፡ በታሰርክበት ወቅት ታመህ እንደነበር ከቤሰተቦችህ እና ከወዳጆችህ ስንሰማ ነበር። ህክምና እንዳላገኘህም ጭምር። ምን ነበር ያጋጠመህ? እያስፔድ፡ የኢትዮጵያ እስር ቤቶች እንደሚታወቀው በጠባብ ቦታ ውስጥ በርካታ ሰው ይታሰራል። ከንጽህና ጉድለት የሚመጡ በሽታዎች እና በትንፋሽ የሚተላለፉ በሽታዎች ያሉ ናቸው። የተለየ ነገር ከመታሰሬ ከጥቂት ቀናት በፊት የጥርስ ህክምና ጀምሬ ነበር። ይህ እንደሚታወቀው ሂደት አለው። የመጀመሪያ ቀን ህክምናውን ጀምሬ እሱን አቋርጬ ነው የታሰርኩት። በእሱ በጣም ተቸግሬ ነበር። ወደተሻለ ህክምና ለመሄድ ብጠይቅም ፈቃደኛ አልነበሩም። በ43 ቀን ውስጥ ከ7 ኪሎ በላይ ቀንሼ ነው የወጣሁት። ቢቢሲ፡ በታሰርክበት ቀን ስለ ነበሩ ነገሮች የተወሰኑ ነገሮች ሰምተናል። በአጭሩ ግን እንዴት እንደነበር ንገረን? እያስፔድ፡ ቤት ውስጥ ነበርኩ በአጋጣሚ። በዚያ ሰሞን በርካቶች ይታሰር እያሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ዘመቻ ያደርጉ ነበር። እናም ያን ያህል እንቅስቃሴ አላደርግም ነበር። ስለዚህ በጣም በርካታ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም በርካታ መኪኖች ነበሩ። በጣም ትልቅ ወንጀለኛ የሚያዝ ነበር የሚመስለው። ያው አብዛኛው ሰው በተያዘበት መልኩ የቤትና የቢሮ ብርበራዎች ተደርገው ነበር። ብዙ የተለየ አልነበረም። ቢቢሲ፡ በጠቀስከው የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ምክንያት ነው ብለህ ታምናለህ? ወይም በአጠቃላይ ከታሰርክ በኋላ ለምን እንደታሰርክ የተሰጠህ ምክንያት አለ? እያስፔድ፡ በአጠቃላይ ሁለት ቀን ለምርመራ ተጠርቼ ነበር። አንደኛው የገባሁ ቀን ሌላ ቀን ደሞ ከታሰርኩ ከአንድ ወር በኋላ። ሁለቱም ቀን የተነገሩኝ ነገሮች ይለያያል። የመጀመሪያ ቀን አንድ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታወቅ አካውንት አለ። መረጃ ደርሶናል እሱ አንተ ነህ ወይ? የሚል ነው። ለማስረዳት ሞክሬ የተቀበሉኝ ይመስለኛል። ከ30 ቀን በኋላ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሰራው እና ለክስ መነሻ የሚሆን የሚዲያ ሞኒተሪንግ (ክትትል) ሰነድ ልኮላቸው ነበር። በጣም የደነቀኝ ነገር ከወቅታዊ ነገሮች ጋር አይገናኝም። ወደ ኋላ የዛሬ ሦስት ዓመት ተመልሶ በአዲስ ቲቪ አንድ የክርክር መድረክ ላይ የተናገርኳቸውን ነገሮች የሚዘረዝር ሰነድ ነው። እኔ እንደጠረጠርኩት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ብዙም የሚገናኝ ነገር የለውም። ቃል የሰጠሁበት የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጻፈው ክስ ላይ ነው። ለምሳሌ የዛሬ ሦስት ዓመት \"የሶማሌ ሕዝብ ባሕል፣ ማንነት እና ወዘተ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ አልተገለጸም ብሎ በአዲስ ቲቪ ላይ በመናገር አንድን ሕዝብ በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሞክሯል\" የሚል ይገኝበታል። የዛሬ ሁለት ዓመት ቢቢሲ ላይ ይመስለኛል ቀርቦ አንድን ሕዝብ ሊያነሳሳ ሞክሯል የሚሉ ወደ 10 ገጽ የሚሆኑ፣ ወቅታዊ ያልሆኑ እና ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ ስናገራቸው የቆዩ ነገሮች እየተለቀሙ ክስ በሚመስል መልኩ ነው የመጡት። በእርግጥ በቅርብ የተናገርኳቸው ነገሮችም ተጨምረዋል። አጠቃላይ ይዘቱ ግን እኔ እንደሚታወቀው አሁን ያለው የፌደራል ሥርዓት ደጋፊ ነኝ። ያንን በተመለከተ የተናገርኳቸው ነገሮች ናቸው ሕዝብን ከሕዝብ እንደማጋጨት የታዩት። ቢቢሲ፡ ስትፈታስ በምን ምክንያት ነው እንድትለቀቅ የተወሰነው? እያስፔድ፡ ፖሊስ የመታወቂያ ዋስ የሚለው ነገር አለ፤ በእሱ ነው የወጣሁት። እንደሚመስለኝ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንም ይሁን ከተለያዩ አካላት የደረሳቸው ነገሮች ክስ ለመመስረት በቂ አለመሆኑን ተረድተው ነው ብዬ አስባለሁ። ሚዛን የሚያነሳ ነገር ስላልነበረ ተለቅቄያለሁ ብዬ አምናለሁ። ቢቢሲ፡ ተባባሪ መስራች የሆንክበት ኡቡንቱ ቲቪ ንብረቶቹ ተመልሰዋል ወይ? በቅርቡ ወደ ሥራ የመመለስ እቅድስ አላችሁ? እያስፔድ፡ ሚዲያችን ተበርብሮ ነበር። እቃዎቹም ተወስደዋል። እንደሚታወቀው የሚዲያ እቃዎች ውድ ናቸው። በርካታ ካሜራዎች እና ቁሳቁሶች ተወስደውብናል። ሲወሰዱ በቃለ ጉባኤ ምስክር ባለበት ተፈርሞ ነው የተወሰዱት። እነዚህ እቃዎች የሚመለሱት ዐቃቤ ሕግ እቃዎቹ ከዚህ በኋላ አያስፈልጉም ለባለቤቱ ይመለስ ካለ በኋላ በመሆኑ እንደተፈታሁ እቃዎቹን ለማግኘት አልቻልኩም። ፖሊስ ለመመለስ ፈቃደኛ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ የሥነ ሥርዓት ጉዳይ ስለሆነ እሱ እንዳለቀ ይመለሳል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን እቃዎቹ ተመለሱም አልተመለሱም ሚዲያችን በሚቀጥሉት ሁለት እና ሦስት ቀናት ውስጥ ይመለሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ተመልሰን ሥራችንን ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ ነን። ቢቢሲ፡ ታስረህበት በነበረው ጣቢያ ሌሎች ጋዜጠኞች ነበሩ? እነማን ናቸው? ሁኔታውስ ምን ይመስላል? እያስፔድ፡ የተለያዩ ቦታዎች ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ከወጣሁ በኋላም ውስጥም ሆኜ ሰምቻለሁ። እኔ የታሰርኩበት ቦታ የኤፒ ጋዜጠኛ የነበረው አሚር አማን እና የካሜራ ባለሞያው ቶማስ እንግዳ ይገኙ ነበር። እስካሁን በእስር ላይ ነው ያሉት። እንደሚታወቀው የጋዜጠኝነት ሥራ ብዙ ውጣ ውረድ ያለው እና ብዙ ሪስክ (አደጋ) ተወስዶ የሚሰራ ሥራ ነው። እነሱም ያንን የጋዜጠኝነት ሥራ ነው ሲሰሩ የቆዩት። ምን አልባት መንግሥት የማይወዳቸውን አካላት አናግረው ሊሆን ይችላል። ይህ ግን በጋዜጠኝነት ሥራ እንደ ወንጀል ይሚታይ ነው ብዬ አላስብም። ወንጀል ነው ከተባለም ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት ሊኖራቸው ይገባል። እኔ እስከምወጣ ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። ስለዚህ መንግሥት የቀሩትን ጋዜጠኞች በሙሉ መፍታት ይገባዋል። ለእኛ ደረሰው እድል ለእነሱም እንዲደርስ አደራ እላለሁ። ቢቢሲ፡ በእስር ላይ የነበሩ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ዘመቻዎችን ስታስተባብር እንደነበር ይታወቃል። በታሰርክበት ወቅት ነው እነዚህ ሰዎች የተፈቱት። እንዴት ነበር ዜናውን የሰማኸው ምን ነበር ስሜቱ? እያስፔድ፡ እርግጥ ነው ላለፈው አንድ ዓመት በላይ ዘመቻዎችን እና እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ ቆይተናል። መንግሥት በመጨረሻም ወደዚህ አቋም መምጣቱ በራሱ የሚያስደስት ነው። በተፈቱ በማግስቱ ነው ዜናውን የሰማነው። አብዛኛው ሰው ራሱ እንደተፈታ ነው የቆጠረው። እኔ ራሴ በጣም ደስተኛ ነበርኩ። ራሴ የተፈታሁ ያህል ነው ደስ ያለኝ። አንዳንዶቹ ከፖለቲካ አቋምም ባለፈ ወዳጆቼ ስለሆኑ ደስ ብሎኛል። በአጠቃላይ ግን ሁለት እንድምታዎችን ማንሳት አለብኝ። አንደኛው ለረጅም ጊዜ ስንለው እንደነበር እስረኞች ተፈተው ሁሉም ነገር ወደ ጠረጴዛ መምጣት አለበት የሚለውን፤ የፖለቲካ ልዩነቶች በሰላም በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈቱ የሚለው እኔ በግሌም በሚዲያችንም ስንለው ቆየነው ነው። መንግሥት ይህንን እርምጃ መውሰድ መጀመሩ የሚበረታታ ተግባር ነው። ነገር ግን አሁንም በርካታ እስረኞች ይቀራሉ። እኔ እንኳን ታስሬ በነበርኩበት ቦታ በርካታ ጋዜጠኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች አሉ። በተለያዩ እስር ቤት የተለያዩ የፓርቲ አመራሮች አሉ። እርምጃው የተቆራራጠ ባይሆን ጥሩ ነው። ያ ካልሆነ የተወሰነ የፖለቲካ ነጥብ ለማግኘት የሚደረግ እና ተመልሰን ወደነበርበት አዘቅት ውስጥ እንዳንገባ እላለሁ። ነገሩ ካፊያ ሳይሆን ለሁሉም መዝነብ አለበት። ከእስር ስወጣ በርካታ ነገር ተቀይሮ ነው የጠበቀኝ። አንዱ የአገራዊ ምክክር ጉዳይ ነው። ይህ መልካም ነገር ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ነገር ሞክረናል። ለመሞከር ያህል ብቻ የምናደርገውከሆነ ማግኘት ያለብንን ነገር እንዳናጣ እሰጋለሁ። ለምሳሌ ምርጫ ተደርጓል። ለማድረግ ያህል ማድረግ እና በትክክለኛ መንገድ ማድረግ ይለያያል። እድሉን እንዳናባክነው እፈራለሁ። ብሔራዊ መግባባበትን ለመፍጠር የሚደረግ ውይይት ገና ያልተሞከረ ነገር ነው። ከተሞከረ አይቀር በደንብ ተጠንቶ እና ታስቦበት ሁሉንም ወገን ያሳተፈ ካልሆነ የአገራችንን እድል እያስመለጥን ነው ብዬ አስባለሁ። ከመነሻው ጀምሮ የኮሚሽነሮችን ምርጫ፣ ተሳታፊ መምረጥ ብሎም መርሃ ግብሩን ማዘጋጀት ላይ የተለያዩ አመለካከቶችን ያሳተፈ መሆን አለበት። ሰርቶ እና ጨርሶ \"ኑ እና እኔ ያቦካሁትን ጋግሩ\" መሆን የለበትም። ቢቢሲ፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንደሚከታተል ሰው ጦርነቱን በተመለከተም ያሉ ለውጦችን ጨምሮ አሁን ያሉ የፖለቲካ እውነታዎች በአጠቃላይ በምኅዳሩ ላይ ምን ውጤት ይዘው የሚመጡ ይመስልሃል? እያስፔድ፡ በእስር ላይ ስለነበርኩ በጉዳዩ ላይ ያልበሰለ እና የማይመጥን ትንታኔ እንዳልሰጥ ስለምሰጋ አንድ ነገር ብቻ ልበል። ጦርነቱን በተመለከተ መስከረም አንድ ላይ ምን ሊመጣ ይችላል የሚሉ የቢሆን መላምቶችን አስቀምጠን ነበር። አንዱ ካስቀመጥናቸው ግምቶች ውስጥ በጦርነቱ ውስጥ በቆዩ ቁጥር በሁለቱም አካላት ዘንድ ዝለት ይመጣል ብለን ነበር። ጦርነት ኢኮኖሚንም ሆነ የሰው ህይወትን የሚበላ አድካሚ ነገር ነው ብለን ነበር። ሁለቱም ወገኖች አሁን ወደ ዝለት ሲመጡ ለድርድር ይቀመጣሉ የሚል ትንታኔ ሰጥተን ነበር። አሁን ወደዚያ ዝለት እየሄዱ ይመስለኛል። ሁለቱም አካላት ይህንን እድል እንደ ጊዜ መግዣ እና ትንፋሽ መሰብሰቢያ እንደማይወሰዱት፣ ብሎም ባግባቡ እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ። በመጣው ነገር ደስተኛ ያልሆኑ አካላት እንዳሉ ይሰማኛል። ከደረሰው ውድመት ብሎም ወደፊት ከሚደርሰው ውድመት ይልቅ አሁን የተወሰዱ እርምጃዎች ይሻላሉ ሊበረታቱም ይገባል ብዬ ነው የማስበው። በተጀመረው ቅድመ ውይይት ላይ ትኩረት ቢደረግ መልካም ይመሰለኛል።", "ባይደን እና ፑቲን የጄኔቫውን ንግግር ቢያወድሱም አለመግባባቱ እንደቀጠለ ነው የአሜሪካ እና የሩሲያ ፕሬዚዳንቶች በጄኔቫ ያደረጉትን ውይይት ቢያደንቁም እአአ ከ 2018 ወዲህ በተደረገው የመጀመሪያ ስብሰባ ብዙም ተጨባጭ ውጤት አልተገኘበትም፡፡ አለመግባባቶች እንደተነሱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ገልጸው ሩሲያም አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት እንደማትፈልግ ተናግረዋል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው ባይደን ልምድ ያካበቱ የሀገር መሪ እንደሆኑና ሁለቱም \"ተመሳሳይ ቋንቋ\" ስለመናገራቸው አስረድተዋል፡፡ ውይይቱ ከተያዘለት ጊዜ አጥሮ ለሦስት ሰዓታት ያህል የተካሄደ ነበር፡፡ ባይደን ለመነጋገር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ እንደማያስፈልጋቸውና ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል አሁን እውነተኛ ተስፋ አለ ብለዋል፡፡ ባይደን ለሩስያው መሪ መነጽር ማበርከታቸው ታውቋል። ፑቲን በተመሳሳይ ለባይደን ስጦታ ስለመስጠታቸው አልታወቀም። የሩሲያው መሪ በ 2018 ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተደረገ ውይይት በኋላ የእግር ኳስ ኳስ በስጦታ ሰጥተዋቸዋል። ሁለቱ ወገኖች በኒውክሊየር ቁጥጥር ዙሪያ ውይይት ለመጀመር ተስማምተዋል፡፡ አምባሳደሮችን ወደ ሁለቱም ሃገሮች መዲናዎች እንመልሳለን ብለዋል። አሜሪካ እአአ በ 2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች በሚል ከከሰሰች በኋላ መልዕክተኞቻቸው በመጋቢት ወር ምክክር እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ የሳይበር ደህንነት፣ ዩክሬን እና የሩሲያ ተቃዋሚ መሪው አሌክሲ ናቫልኒ ዕጣ ፈንታን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ስምምነት ስለመደረሱ ምልክት የለም። ናቫልኒ ሁለት ዓመት ተኩል ቅጣት ተላልፎበት በእስር ላይ ይገኛል። ባይደን ናቫልኒ በእስር ቤት ውስጥ ቢሞት ለሩስያ \"አስከፊ መዘዞች\" እንደሚኖሩት ተናግረዋል፡፡ መሪዎቹ ምን ተወያዩ? ከጉባኤው በፊት ሁለቱም ወገኖች ግንኙነታቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ፑቲቲን እስረኞችን መለዋወጥ በሚቻልበት ስምምነት ላይ እንደሚደረስ ፍንጭ ሰጥተው ነበር፡፡ ፑቲን በሳይበር ጥቃቶች ላይ ሩሲያን ነጻ በማድረግ በሃገራቸው የሚፈጸሙ አብዛኛዎቹ የሳይበር ጥቃቶች መነሻቸው ከአሜሪካ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባይደን እንደ ውሃ ወይም ኢነርጂ ያሉ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ለጠለፋም ሆነ ለሌላ ጥቃት \"የተከለከሉ\" መሆን አለባቸው ብለው ለፑቲን መናገራቸውን አስታውቀዋል፡፡ \"ተመለከትኩትና በነዳጅ ቱቦዎቻችሁ ላይ ላይ ጠለፋ ቢደረግ ምን ይሰማዎታል? አልኩኝ። ይህ ችግር አለው ብሎኛል\" ሲሉ ባይደን ተናግረዋል። ሩሲያ እነዚህን \"መሠረታዊ ደንቦች\" ብትጥስ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ ገልጸዋል ፡፡ የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ መብትን ጨምሮ ሁለቱም ወገኖች በሰብዓዊ መብቶች ላይ ልዩነት ነበራቸው። ፑቲን በቅርቡ የ 24 ቀናት የረሃብ አድማ ስላደረገው ናቫልኒ አሜሪካ ያላትን ስጋት አጣጥለዋል፡፡ ናቫልኒ ህጉን ችላ በማለት ጀርመን ህክምና ካገኘ በኋላ ወደ ሩሲያ ሲመለስ እስራት እንደሚገጥመው ያውቅ ነበር ብለዋል፡፡ ናቫልኒ በፑቲን ትዕዛዝ ነርቭ በሚጎዳ ኬሚካል መመረዙን ቢገልጽም ፑቲን ክሱን አጣጥለዋል። ሩሲያ በግዛቷ ላይ ከካፒቶል አመፅ ወይም 'ከብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ሁከት አትፈቅድም ብለዋል፡፡ ፑቲን ስለ ስለ ብላክ ላይቭስ ማተር እንቅስቃሴ የሰጡትን አስተያየት ባይደን \"አስቂኝ\" ሲሉ አጣጥለው የሰብዓዊ መብቶች \"ሁል ጊዜም ዋነኛ ጉዳይ ነው\" ብለዋል፡፡ ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር ለመተባበር ለምን እንደምትፈልግ የተጠየቁት ባይደን \"[ሩሲያ] በአሁኑ ሰዓት በጣም አስቸጋሪ በሆነ ቦታ ላይ\" መሆኗን ተናግረዋል፡፡ \"በቻይና ግፊት እያደረባቸው ነው፡፡ ዋነኛ ኃያል ሃገር ሆነው ለመቀጠል በጣም ይፈልጋሉ\" ብለዋል ጄኔቫን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት በጋዜጣዊ መግለጫቸው መሃል በፑቲን ይተማመኑ እንደሆነ ለጠየቃቸው ጋዜጠኛ ራሳቸውን ላይ ታች በመወዝወዝ ምላሽ የሰጡ መስለው ታይተዋል፡፡ በኋላ ግን ኋይት ሃውስ ባይደን \"በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ለማንኛውም ጥያቄ ምላሽ የሰጡ ሳይሆን በአጠቃላይ ለመገናኛ ብዙሃን እውቅና ሰጥተዋል\" ሲል በትዊተር መልዕክቱን አስታላልፏል። አንድ የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ፑቲን ባህሪያቸውን እንደሚለውጡ በምን እንደሚተማመኑ ባይደንን ሲጠይቅ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት \"ያንን ካልተገነዘብክ በተሳሳተ ሥራ ውስጥ ነህ\" በማለት በብስጭት መልሰዋል። በኋላም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡", "ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር ወደ ግል ሆስፒታል ተወሰዱ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አደነ ወደ መረጡት የግል ሆስፒታል ዛሬ ረፋዱ ላይ ተወሰዱ። ከ30 ቀናት በላይ በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የተነገራለቸው ተከሳሾች፤ የተወሰዱት ላንድማርክ ተብሎ ወደሚጠራው ሆስፒታል መሆኑን ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች እና የቤሰተብ አባላት መረዳት ችሏል። ተከሳሾቹ ታሰረው ይገኙበት ከነበረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በአምቡላንስ ተጭነው በጸጥታ ኃይሎች ታጅበው ወደ ሆስፒታሉ ተወሰደዋል። የቤተሰብ አባላት እና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ እንደሚሉት፤ የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት ወደ ሆስፒታሉ እንዳይገቡ መከልከላቸውን እና ተከሳሾቹ ስለሚገኙበት የጤና ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ ከግል ሃኪሞቻቸው ጋር እንደሚገኙ የቤተሰብ አባላቱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በሆስፒታሉ ዙሪያም በርካታ የጸጥታ አካላት ተሰማርተው እንደሚገኙ ምንጮቹ ተናግረዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እና የቤተሰብ አባላት እንደሚሉት ከሆነ፤ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ እና ሐምዛ አዳነ የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ዛሬ 34ኛ ቀናቸው ላይ ይገኛሉ። ተከሳሾቹ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰው ወከባ ይቁም እንዲሁም የቤተሰብ አባላት ችሎት እና ማረሚያ ቤት ለጥየቃ ሲመጡ የሚደርስባቸው ወከባ ይቁም በማለት የረሃብ አድማውን እያደረጉ እንደሆነ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። በተከሳሽ ጠበቆች አቤቱታ የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾች በመረጡት የጤና ተቋም እና ሆስፒታል ይታከሙ ሲል ፈቅዶ ነበር። ይሁን እንጂ ከአንድ ሳምንት በፊት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ይግባኝ ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የላንድማርክ ሆስፒታል ሃኪሞች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝተው ለተከሳሾች ሕክምና እንዲሰጥ በይኖ ነበር። ጠበቆች በበኩላቸው የሆስፒታሉ ሠራተኞች በቃሊቲ ማረሚያ የህክምና አገልግሎት ይስጡ መባሉ አግባብ አይደለም በሚል ተከራክረው ነበር። ጠበቆች ደንበኞቻቸው የ24 የህክምና ክትትል አልያም የሕክምና ማሽን ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው፤ አገልግሎቱን በማረሚያ ቤቱ ማግኘት አይችሉም በማለት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብለዋል። ሰበር ሰሚ ችሎቱም ትናንት በዋለው ችሎት ተከሳሾች በሆስፒታሉ ተገኝተው የሕክምና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ በይኗል። ሰበር ሰሚ ችሎቱ ይህን ብይን ትናንት ከሰዓት የሰጠው፤ ትናንት ረፋድ ላይ ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የነበራቸው ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ከተሰጠበት በኋላ ነው። ትናንት ረፋድ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። ከእነዚህ መካከል እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር። ይኹን እንጂ ጠበቆች ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ለፍርድ ቤት ተናግረው፤ ደንበኞቻቸው አሁን ባሉበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት አይችሉም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግም ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥ እንደማይቃወም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚህም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለመጋቢት 6/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህ ችሎት ላይ የተገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር፤ ተከሳሾች አካላቸው ደክሞ እና ከስተው ተመልክቷል። አንዳንድ ተከሳሾች በሰዎች ድጋፍ ወደ ችሎቱ ሲገቡ እና የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት መካከል አንዳንዶቹ በችሎት ውስጥ ሲያለቅሱ ሪፖርተራችን ተመልክቷል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል።", "ኦብነግ ከምርጫው ራሱን ያገለለው ለቦርዱ ያቀረበው አቤቱታው መፍትሄ ባለመግኘቱ እንደሆነ ገለጸ በተራዘመውና መስከረም 20 ሊካሄድ በታቀደው የሶማሌ ክልል ምርጫ ላይ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) እንደማይሳተፍ አስታወቀ። ግንባሩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ መፍትሄ ባለማግኘቱ እንደሆነ፣ የኦብነግ የአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብዱላሂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኦብነግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በክልሏ ዋና ከተማ ጅግጅግጋ ውስጥ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ነው ከምርጫው እራሱን ማግለሉ ያሳለፈበት ውሳኔ ላይ ደረሰው። ፓርቲው ከምርጫው ራሱን ለማግለል የወሰነበትን ሁኔታ አቶ አህመድ ሲያስረዱ \"ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ችግሮች እንዳሉና የምርጫ ካርድም የተሰራጨው ለሕዝቡ ሳይሆን ለገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች እንደሆነ እንዲሁም ገዥው ፓርቲ ለራሳቸው ወገኖች ሲያድሉ ነበር\" ይላሉ። ይህንንም በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ ከተለያዩ ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ ማስገባታቸውን ገልጸዋል። በሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ በምርጫ ቦርድ አጣሪ ቡድን ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን በክልሉ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ ድጋሚ የመራጮች ምዝገባ እንዲካሄድ መወሰኑንና ምርጫ ቦርድም ይህንን ውሳኔ ማሳለፉን ያስረዳሉ። \"በዚህም ምርጫ ቦርድ ለችግሩ መፍትሄ የሚሆን ውሳኔ አላስተላለፈም። ያቀረብናቸው በርካታ አቤቱታዎችና ማስረጃ በመራጮች ምዝገባ ላይ የነበሩ ችግሮች መፍትሄ ያገኛሉ ብለን ነበር። ነገር ግን መፍትሄ ይሆናል የምንለውን ነገር አላገኘንም\" በማለት ተናግረዋል። ኦብነግ ውሳኔውን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የመራጮች የምዝገባ ሂደት ማጭበርበር የተሞላበት እንደሆነ ጠቅሶ ማስረጃዎችን ማስገባቱንና አቤቱታዎችን በተደጋጋሚ ቢያስገባም አልተስተካከለም ብሏል። በሶማሌ ክልል ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ቀርተዋል ብሏል። \"ምርጫውን ለሦስት ወራት በማራዘም የተፈጠረው የሕዝብ ተስፋ፣ ምርጫ ቦርድ የተበላሸውን አሰራር ባለማስቆሙ ሂደቱ ጠልሽቷል\" በማለት መግለጫው አስፍሯል። ኦብነግ በዚህ ውሳኔ ማዘኑንና በቀላሉም እዚህ ላይ እንዳልደረሰ ገልጿል። ኦብነግ የትጥቅ ትግሉን ለማቆም ዋናው ምክንያት የሶማሌ ሕዝብ መብቶችን በሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማስከበር በመሆኑ ነው ቢልም ከምርጫው ተገዶ መውጣቱን ገልጿል። መግለጫው አክሎም በኦብነግ እና በሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የዕጩዎች ምዝገባን ማገድ፣ ዕጩዎችን እና አባላትን ማጥቃትና ማዋከብ እንዲሁም ትክክለኛ የመራጮች ምዝገባ በመደናቀፉ \"ለእውነተኛ ፍትህ ምንም መንገድ ባለመኖሩ በመጨረሻ ኦብነግን ከምርጫው እንዲወጣ ተገዷል\" በማለት አስፍሯል። አቶ አህመድ በበኩላቸው በአጠቃላይ የአገሪቱ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ በሶማሌ ክልል በበለጠ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ ነበር ይላሉ። ነገር ግን ከሰሞኑ ከምርጫው ጋር ተያይዞ ችግሮች መጉላታቸውን ያስረዳሉ። በክልሉ ዕጩዎች የሚታሰሩበትና እንዳይመዘገቡ የሚደረጉበት እንቅስቃሴዎች ነበሩ ይላሉ። ከዚህም ጋር ተያይዞ ኦብነግ ብቻ ሳይሆን ሶማሌ ክልል ላይ ሲወዳደሩ የነበሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ተናግረዋል። ምናልባት ውሳኔያቸውን አስቀልብሶ በምርጫ የሚሳተፉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችል ይሆን ወይ? ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ አህመድ ሲመልሱ \"ምርጫው አስር ቀን እንደመቅረቱ ይህ ሁኔታ የሚስተካከልበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም\" ብለዋል። በሶማሌ ሕዝብ ላይ ሲደርስ የነበረውን ግፍና በደል ሰላማዊ በሆነ መንገድ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድርና መፍትሄም እንዲመጣ የሚገኝበትን ርብርብና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ በክልሉ በመንግሥትና ፓርቲ መካከል ልዩነት ባለመኖሩ በምርጫው ሂደት ላይ ችግሩን እንዳጎላው ይናገራሉ። ለአስርት ዓመታት በትጥቅ ትግል የቆየ ፓርቲ እንደ መሆኑ መጠን ከዚህ በኋላ ፓርቲው ምን አይነት አካሄድ ይኖረዋል ለሚለው ጥያቄም፤ የሶማሌን ሕዝብ መብት ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ ትግሉን እንደሚቀጥልና በእውነተኛ ብሔራዊ ውይይትም ለመሳተፍ ፈቃደኛ ነው በማለት መግለጫው የወደፊቱን አቅጣጫ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ መንግሥትና በኦብነግ መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ፓርቲው በርካታ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም ሰላማዊ በሆነ መንገድና በውይይት ለመቀጠል ቁርጠኝነት እንዳለው አስታውቋል። ሆኖም በሶማሌ ክልል ውስጥ አሁን ያለውን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል ሁሉም ወገኖች ሰላሙን ለማስጠበቅ ሊሰሩ ይገባል ብሏል። \"በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ጦርነት ባለበት ወቅት ሰላም በአንድ ግዛት ውስጥ ስለማይሰፍን፣ ኦብነግ አሁን ባለው አጥፊ ጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና በሚቀጥሉት ጊዜያት የሚጎዱትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለማዳን\" ጥሪ አቅርቧል። ጥቂት ስለ ኦብነግ ለበርካታ ዓመታት በምሥራቃዊው የአገሪቱ አካባቢ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ወደ አገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ለመሳተፍ መወሰኑ ይታወሳል። ኦብነግ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ትግል ያደርጉ ከነበሩ አማጺ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1984 ነበር የተመሰረተው። ቡድኑ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙ ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ሦስት የፖለቲካ ቡድኖች ከሽብር ቡድን ዝርዝር ውስጥ በፓርላማው ውሳኔ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ በውጭ የሚገኙ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ወደ አገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል። አብነግ የኦጋዴን ሕዝብ ብሎ የሚጠራውን በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘው የሶማሌ ሕዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለማስከበር በፖለቲካዊና ወታደራዊ መስኮች ትግል ሲያደርግ ቆይቷል። ኦብነግ ከምስረታው አስራ አራት ዓመታት በኋላ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ሊግ ጋር በመዋሃድ የሶማሊ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን መስርተው ነበር። መስከረም 20 ሶማሌ ክልልን ጨምሮ የሚካሄደው ምርጫ ስድስተኛው አጠቃላይ ብሔራዊ ምርጫ በዋናነት ሰኔ 14/2013 ዓ.ም የተካሄደ ቢሆንም በፀጥታ ችግር፣ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዩ ግድፈቶች፣ በመራጮች ምዝገባ ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ የድምፅ መስጫው ቀን በአንዳንድ ክልልሎችና የምርጫ ክልሎች እንዲራዘም መወሰኑ ይታወቃል። ምርጫ የተራዘመባቸው ሶማሌ፣ ሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መስከረም 20 ምርጫ እንዲካሄድ ተወስኗል። ምርጫ ያልተደረገበት የሶማሌ ክልልንም በተመለከተ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ በነበረበት ወቅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቱታ ቀርቦ ነበር። ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ መጣራት እንደሚገባው አምኖ የመራጮች ምዝገባ እንዲቆም በመወሰን 10 የምርጫ ክልሎች ላይ ምርመራ ተደርጓል። ከተለያዩ ሲቪል ማኅበራት የተውጣጣ አጣሪ ቡድን በመላክ ምዝገባ ሂደቱ ላይ የቀረቡትን አቤቱታዎች አጣርቷል። የቡድኑንም ግኝት መሰረት በማድረግ ጅጅጋ 1፣ በጅጅጋ 2 የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በድጋሚ እንዲከናወን ተወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ በቀብሪደሃር ከተማ፣ በቀብሪደሃር ወረዳ፣ በመኢሶ፣ በአፍደም የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች እንዲሁም የመራጮች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በድጋሚ የሚካሄድባቸው ስፍራዎች ናቸው ተብሏል። በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እንዲደገምባቸው የተላለፈባቸው ደግሞ በዋርዴር ምርጫ ክልል ውስጥ በ2 ምርጫ ጣቢያዎች፤ በፊቅ ምርጫ ክልል በ1 ምርጫ ጣቢያ፣ በገላዴን ምርጫ ክልል በ1 ምርጫ ጣቢያ፣ በጎዴ ከተማ ምርጫ ክልል በ4 ምርጫ ጣቢያዎች ፣ በምሥራቅ ኢሜ ምርጫ ክልል በ3 ምርጫ ጣቢያዎችና በቤራኖ ምርጫ ክልል በ3 ምርጫ ጣቢያዎች እንደሆነም ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።", "ሰሜን ኮሪያ ወጣቶች የደቡብ ኮሪያን መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቀች የሰሜን ኮሪያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ወጣቶች የደቡብ ኮሪያ መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ እንዳይጠቀሙና የሰሜን ኮሪያን መደበኛ ቋንቋ እንዲገለገሉ አሳሰቡ። ወጣቶች ከደቡብ ኮሪያ የተቀዱ የፋሽን፣ የፀጉር ስታይል እንዳይጠቀሙ እና ሙዚቃ እንዳያዳምጡ የሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጋዜጦችም አዲስ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር። ይህ የውጭ ጫናን ለማስቆም ያለመና ከባድ ቅጣት የሚያስከትለው አዲስ ሕግ አካል ነው። ሕጉን ጥሰው የተገኙም ከእስራት እስከ ሞት ድረስ ሊቀጡ ይችላሉ። ሮዶንግ ሲንመን ጋዜጣ ወጣቶች የደቡብ ኮሪያን የፖፕ ባህል መከተላቸው የሚያደርስባቸውን ተፅዕኖ አስጠንቅቋል። \"በተዋበና በቀለም ባሸበረቀ ስክሪን ሰርስረው የሚገቡ ርዕዮተ ዓለሞችና እና ባህሎች የጦር መሣሪያ ከያዙ ጠላቶች ይበልጥ አደገኛ ናቸው\" ብሏል ጋዜጣው። ጋዜጣው አክሎም ወጣቶች ኮሪያ ላይ የተመሠረተ የፕዮንግያንግ ቋንቋን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስቧል። የውጭ ተፅዕኖው ኪም የሚመሩት የሰሜን ኮሪያ ኮሚዩኒስት ሥርዓት ስጋት ተደርጎ ይታያል። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን 'ኬ ፖፕ' [ደቡብ ኮሪያ መሰረቱ የሆነ የሙዚቃ ስልት] የሰሜን ኮሪያ ወጣቶችን አዕምሮ ጨምድዶ የያዘ 'የማይለቅ ካንሰር' ሲሉ መጥራታቸውን ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል። ከደቡብ ኮሪያ፣ ከአሜሪካ ወይም ጃፓን ከፍተኛ መጠን ያለው ሙዚቃ ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው የሞት ቅጣት ይጠብቀዋል። ይህንን ሲመለከት የተያዘ ሰውም የ15 ዓመታት እስር ይተላለፍበታል። ቅጣቱ ከባድ ቢሆንም ወደ ሰሜን ኮሪያ የሚገባው የውጭ ጫና ግን አሁንም አልቆመም። ጉዳዩም እጅግ ውስብስብ ሲሆን በዚህ ሳቢያ የታገዱ ሚዲያዎችም በሕገ ወጥ መንገድ መስራታቸውን ቀጥለዋል። አንዳንድ ሰሜን ኮሪያውያን ተገንጣዮች የደቡብ ኮሪያ ድራማ ማየታቸው አገራቸውን ጥለው ለመውጣታቸው አንዱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በሰሜን ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ያንግ ሞ ጂን በስዊትዘርላንድ የተማሩት ኪም ጆንግ ኡን \"ኬ ፖፕ ወይም የምዕራባውያን ባህል በቀላሉ ወደ ወጣቶች ሊገባ እንደሚችልና በሶሻሊስት ሥርዓት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ያውቃሉ\" ሲሉ ለኮሪያ ሄራልድ ተናግረዋል። \"መሪው ይህ ባህልም ለሥርዓቱ ጫና እንደሚሆን ያውቃሉ። ስለዚህም ነው ይህንን ማስቆም የፈለጉት። ኪም ወደፊት የሚመጡ ችግሮችን ለመከላከል እየሞከሩ ነው\" ብለዋል ፕሮፌሰሩ።", "ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተሾሙ ከእስር የተፈቱት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተሾሙ። የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ በዛሬው ዕለት ባወጣው መረጃ የክልሉ ርዕሰ መስታድር አገኘሁ ተሻገር ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ አድርገው መሾማቸውን ነው። ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥትና ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞ አንደኛው ተጠርጣሪ ነበሩ። ከሰኔ 15 ክስተት በፊት የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩ ሲሆን የነ ዶክተር አምባቸውና ሌሎች ባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል። ብርጋዴር ጄኔራሉ ከተጠረጠሩበት ክስም ነጻ ሆነው ከወራት እስር በኋላ ተፈትተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪም ለሌሎች ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም ልዩ ልዩ የፀጥታ ተቋማትን እንዲመሩ መመደባቸውም ተጠቁሟል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ልዩ ረዳት ሆነው መሾማቸውን ዘግቧል። ጄኔራል አዳምነህ የትግራይ ጦርነት እስከተከሰተበት ወቅት የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ነበሩ። ርዕሰ መስተዳደሩ የክልሉን ጸጥታ መዋቅር ለማጠናከር ከብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ እና ከጄነራል አዳምነህ መንግሥቴ በተጨማሪ ሌሎች ሰባት ሰዎችን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መሾማቸው ተገልጿል።", "ባይደን በፑቲን ላይ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ሩሲያ አምባሳደሯን ጠራች ሩሲያ ዋሽንግተን የሚገኙ አምባሳደሯን ለውይይት በሚል ከሰሞኑ ጠርታለች። ከአሜሪካ ጋር ያለው የሻከረ ግንኙነት የማይቀለበስ ደረጃ ላይ እንዳይደርስም ለመምከር ነው ተብሏል። የሩሲያ መንግሥት እንዳሳወቀው አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ ወደ ሞስኮ የተጠሩበት ምክንያት አገሪቷ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት መጥፎ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ያንን አቅጣጫ ለማስያዝ ነው ብሏል። ይህንን ውሳኔ ሩሲያ ያሳወቀችው ፕሬዚዳንት ባይደን በአሜሪካ ምርጫ ላይ ጣልቃ ገብተዋል የሚባሉትን ቭላድሚር ፑቲንን \"ዋጋ ይከፍላሉ\" ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ከቅርብ ወራት በፊት የአሜሪካ መንበረ ስልጣንን የተቆጣጠሩት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከኤቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፕሬዚዳንት ፑቲን \"ነፍሰ ገዳይ ናቸው\" ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል። በጥቅምት ወር መጨረሻ በተደረገው የአሜሪካ ምርጫ ላይ ጣልቃ የመግባት ዘመቻን ፕሬዚዳንት ፑቲን መፍቀዳቸውን አንድ የአሜሪካ ደህንነት ሪፖርት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው ባይደን ይህንን የተናገሩት። ሪፖርቱ ሩሲያ ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊ እንዲሆኑ ጣልቃ በመግባት አስተዋፅኦ አድርጋለች በማለት ወንጅሏታል። ሩሲያ ጣልቃ በመግባቷ ምን አይነት ውጤቶች ሊኖሩ ይችላሉ ተብለው የተጠየቁት ፕሬዚዳንት ባይደን\"በቅርቡ ታዩታላችሁ\" ብለዋል። የፕሬዚዳንት ፑቲን ቃለ አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በበኩላቸው ውንጀላው በመረጃ ያልታገዘና የሁለትዮሽ ግንኙነቱንም በቀጣዩ የሚጎዳ ነው ብለውታል። የሪፖርቱ ማጠቃለያን ተከትሎ አሜሪካ በሚቀጥለው ሳምንት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ትጥላለች ተብሎ ይጠበቃል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ምን አለ? \"በአሜሪካ የሚገኙት የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ ወደ ሞስኮ የተጠሩት ለምክክር ነው። የሁለቱን አገራት ግንኙነት በተመለከተ አውዱ ምን ሊሆን ይገባል የሚለው ላይ ትንታኔም ይሰጣል\" በማለት መግለጫው አትቷል። ሩሲያ አክላም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት መሻከር የማይቀለበስ ደረጃ ከመድረሱ በፊትም መካላከል እንደምትፈልግ አስታውቃለች።", "በናይጄሪያ ከ1800 በላይ ታራሚዎች ከእስር ቤት ማምለጣቸው ተሰማ በናይጄሪያ የሚገኝ እስር ቤት በታጣቂዎች ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ከ1 ሺህ 800 በላይ ታራሚዎች ማምለጣቸው ተገልጿል። ክስተቱ ያጋጠመው በደቡብ ምስራቅ በምትገኘው ኦውሪ ግዛት ሲሆን ታጣቂዎች የእስር ቤቱን ሰብረው በመግባቱ የህንፃውን የተወሰነ ክፍልም በቦንብ አፈንድተውታል ተብሏል። ኦውሪ ማረሚያ ማዕከል ተብሎ በሚታወቀው እስር ቤት ታጣቂዎቹ በጭነት መኪናና በአውቶብስ ተጭነው የመጡት በትናንትናው እለት ነው። ፖሊስ ጥቃቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ታጣቂዎች ተወንጫፊ ሮኬቶችን ጨምሮ፣ ከባድ መሳሪያዎችና ቦንቦችን ይዘው ነበር ብሏል። በዚህም አጋጣሚ በርካታ ታራሚዎች ማምለጥ እንደቻሉም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። ለዚህ የእስር ቤት ጥቃት አድራሹ የቢያፍራ ቀደምት ህዝቦችን በመወከል የሚታገለውና በናይጄሪያ የታገደው ተገንጣዩ ቡድን ነው ሲል ፖሊስ አስታውቋል። የናይጄሪያ ማረሚያዎች ማዕከል እንዳስታወቀው እስካሁን ድረስ ያመለጡ የታራሚዎች ቁጥር 1 ሺህ 844 መሆኑን ነው። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ጥቃቱን \"በስርዓት አልበኞች የተፈፀመ የሽብር ጥቃት\" ሲሉ አውግዘውታል። ከዚህም በተጨማሪ የፀጥታው ሁኔታ እንዲጠናከር የተጨማሪ ሃይል አስፈላጊነትን አፅንኦት በመስጠት ከመናገር በተጨማሪ፤ ጥቃቱን ያደረሱት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዲሁም ያመለጡት ታራሚዎችም በአስቸኳይ እንዲያዙ ብለዋል። ኢንዲጂኒየስ ፒፕል ኦፍ ባያፍራ ተብሎ የሚታወቀው የተገንጣዩ ቡድን እንቅስቃሴ ቃለ አቀባይ በበኩላቸው የሰኞውን ጥቃት አድርሰዋል መባላቸው \"ሃሰት\" እንደሆነ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። በማዕከላዊው መንግሥትና በአካባቢው በሚኖሩ ኢግቦ ህዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት የባላንጣ መሆኑን ተከትሎ ግዛቲቷ የተገንጣዮች ቡድን መፈልፈያ ሆናለች። ከጥር ወር ጀምሮ በርካታ የፖሊስ ጣቢያዎች ጥቃትን ያስተናገዱ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ የፖሊስ መኪኖች ተቃጥለዋል እንዲሁም ቦምቦችና ተቀጣጣይ ፈንጆች ተዘርፈዋል። ለዚህኛው ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።", "በጀርመን በተካሄደው ምርጫ የአንጌላ ሜርክል ፓርቲ ተሸነፈ የጀርመኑ ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ የመራሄተ መንግሥቷ አጌላ ሜርክልን ፓርቲ በጠባብ ውጤት ማሸነፉን ቀዳሚ የምርጫ ውጤቶች አመላከቱ። ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ 25.7 በመቶውን ድምጽ ሲያገኝ ገዢው ወግ አጥባቂው ፓርቲ ደግሞ 24.1 በመቶ ድምጽ አግኝቷል። የግሪን ፓርቲ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን 14̇ በመቶ ድምጽ ማግኘቱም አነጋጋሪ ሆኗል። በቀጣይም መንግሥት ለመመስረት የሚያስፈልገውን አብላጫ ድምጽ አንድ ፓርቲ ባለማግኘቱ ፓርቲዎቹ ጥምር መንግሥት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። ምርጫው ከጅማሮው ውጤቱን ለመገመት የሚያስቸግር መሆኑን በርካቶች ሲናገሩ ነበር። ጥምር መንግሥት በቀላሉ መመስረት የሚቻል እንዳልሆነም ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ። ጥምር መንግሥት እስከሚመሰረት ድረስ ተሰናባቿ መራሄተ መንግሥት ሜርክል በሥልጣናቸው ላይ መቀጠላቸው አይቀሬ ነው። ይህም እስከ መጪው ጥር ወር ድረስ ሊቆይ ይችላል። አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችውን ጀርመን ለቀጣይ አራት ዓመታት በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳን በዋናነት በመያዝ ይመራል። ከፍተኛውን ድምጽ ያገኘው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ መሪ ኦላፍ ሾልትስ በቴሌቪዢን በተላለፈ ንግግራቸው መራጮች \"ለጀርመን መልካም ብሎም ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ መንግሥት\" የመመስረት ሥራ ሰጥተውኛል ሲሉ ተደምጠዋል። የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪው በበኩላቸው ጥምር መንግሥትን የመመስረት እንዲሁም ያሸነፈው ሁሉንም ጠቅልሎ የማይወስድበት ሂደት ነው ሲሉ ሾልትስን የሚቃረን ንግግር አድርገዋል። የሊበራል እና የግሪን ፓርቲዎች ከ30 ዓመት በታች ባሉ ወጣቶች ዘንድ ዝነኛ ናቸው። ጥምር መንግሥት ሊመሰረት የሚችለውም በእነዚህ ሁለት ፓርቲዎች አማካኝነት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። ውጤቱን ተከትሎም አራት የተለያዩ የጥምር መንግሥት አማራጮች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው አማራጭ \"የትራፊክ መብራት\" ቀለሞችን የያዘ ነው። የሶሻል ዴሞክራቶችን ቀይ ቀለም፣ የኤፍዲፒን ቢጫ እንዲሁም የግሪን ፓርቲ አረንጓዴ የያዘ የጥምረት አማራጭ ነው። ሁተኛው \"ጃማይካ\" የተሰኘው አማራጭ ሲሆን ይህም የጃማይካን ባንዲራ ቀለሞች ያያዙትን ሦስቱን ፓርቲዎች የያዘ ጥምረት ነው። ሾሳል ዴሞክራቶችን፣ ኤፍዲፒን እንዲሁም ግሪን ፓርቲን። ይህ በጀርመን ታሪክ ሦስት አማራጮችን የቀረቡበት የጥምር መንግሥት የመመስረት ሂደት መሆኑ ተነግሯል።", "የሕንድ የዘር ግንድ ያላቸው ሪሺ ሱናክ ቀጣዩ የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ፉክክሩን እየመሩ ነው ተሰናባቹን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት እየተደረገ ያለውን ትንቅንቅ የሕንድ የዘር ግንድ ያላቸው ሪሺ ሱናክ እየመሩ ይገኛሉ። ሱናክ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ለመሆን እስካሁን የተካሄዱ ሁለት ተከታታይ ምርጫዎችን አሸንፈዋል። ከሕንዳውያን ወላጆች የተወለዱት ሪሽ ሱናክ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ 88 ድምጽ ያገኙ ሲሆን የንግድ ሚንስትሯ ፔኒ ሞርደንት 67 ድምጽ በማግኘት ሁለተኛ ሆነው ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ሊዝ ትረስ ደግሞ በ50 ድምጽ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ነበር በመጀመሪያው ዙር ምርጫ። በሁለተኛው ምርጫ ሱናክ 101 ድምጽ ሲሰበስቡ ሞርደንት 83፤ ትረስ ደግሞ 64 ድምጽ አግኝንተዋል። እስካሁን በተካሄደው ምርጫ ቻንስለር ናዲም ዛሃዊ እና የቀድሞው የጤና ሚንስትር ጀረሚ ሃንት ከውድድሩ ተሰናብተዋል። አሁን ውድድሩ ላይ ያሉት ዕጩዎች ሌላ ፉክክር ይጠብቃቸዋል። በተጨማሪም ዛሬ አርብ ሐምሌ 15/2014 ዓ.ም. አምስት እጩዎች በቀጥታ የቴሌቪዥን መስኮት ክርክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ውድድሩ በዚህ መልኩ ከቀጠለ በኋላ በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ሁለት ተወዳዳሪዎች ብቻ እንዲቀሩ ይደረጋል። ሁለቱን ተወዳዳሪዎች ደግሞ 160 ሺህ አካባቢ የቶሪ አባላት ድምጽ ሰጥተውባቸው አሸናፊው የፓርቲ መሪ እና ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናል። ውጤቱ በአውሮፓውያኑ መስከረም አምስት ይፋ ይደረጋል። አሁን ውድድሩ ላይ የቀሩት ተፎካካሪዎች ቀጣዩን ዙር ለማሸነፍ ከሁለቱ ተሰናባች መራጮች [ጀረሚ ሃንት እና ዛሃዊ] ተጨማሪ ድምጽ ለመቀራመት ይፎካከራሉ። ተሰናባቹ ጀረሚ ሃነት ሱናክን እንደሚደግፉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት የቦሪስ ጆንሰንን አመራር በመቃወም ከቻንስለርነታቸው የለቀቁት ሱናክ በውጤቱ ደስተኛ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የትረስ ቃል አቀባይ “አሁን ወዳጆች ተሰባስበው ታክስ የሚቀንስ፣ እውነተኛ የምጣኔ ሃብት ለውጥ የሚያመጣ እና ዩክሬን ውስጥ የፑቲንን ሽንፈት የሚያፋጥን መሪ ያስፈልገናል” ብለዋል። “ሊዝ የብሬግዚትን ጉዳይ በማፋጠን እና የምጣኔ ሃብት እድገት በማምጣት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል” ብለዋል። ለረጅም ጊዜ የፓርላማ አባል የሆኑት ቱጌንዳት በትዊተር ገጻቸው “በጣም ደስ የሚል ውጤት ነው። አገራችንን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ በሚቀጥለው የምርጫ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ። አገራችን ግልጽ የሆነ አጀማመር ሊኖራት ይገባል” ብለዋል። በአውሮፓውያኑ 2019 በነበረው ውድድር ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ጀረሚ ሃንት ወግ አጥባቂ ፓርቲ በቀጣይ “አስደናቂ ዘመን” ይኖረዋል ብለዋል። ለተወዳዳሪዎቹም ምክር ለግሰዋል። “መሞካሸት እና መዘላለፍ ለአጭር ጊዜ እምርታ ሊያመጣ ይችላል፤ በረጅም ጊዜ ሂደት ግን አደጋ አለው” ብለዋል።  ሌላኛው የውድድሩ ተሰናባች ዛሃዊ ደግሞ “አሁን ጣልቃ መግባት ባልፈልግም ለሁሉም ተወዳዳሪዎች መልካም ዕድል እመኛለሁ” ብለዋል። ይህ ውድድር እየተካሄደ ያለው ባለፈው ሳምንት ቦሪስ ጀንሰን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ካሳወቁ በኋላ ነው። ቦሪስ ጆንሰን በኮሮናቫይረስ እገዳ ወቅት መመሪያ በመጣስ ጎዳና ዘግተው ድግስ አዘጋጅተዋል በሚል እና በሌሎች ክሶች ሲወቅሱ ሰነባብተዋል።", "የሱዳን ጦር የተባበሩት መንግሥታትን ድጋፍ ጠየቀ የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የተባበሩት መንግሥታት የሽግግር መንግሥቱን እንዲደግፍ ጥሪ አቀረቡ። ጀነራል አል-ቡርሃን ይህን ጥያቄ ያቀረቡት የተመድ የሱዳን ተወካይ የሆኑትን ቮልከር ፔርዝስ አግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት ነው። የተመድ ተወካዮ ከአል-ቡርሃን ጋር መገናኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው የገለጹ ሲሆን፤ ምንም አንኳ ሱዳን ሕገ መንግሥታዊው ሥርዓት እንዲመለስ ብትስማም፤ ሌሎች ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮች መከናወን አለባቸው ብለዋል። ጀነራል አል-ቡርሃን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት የሲቪል መንግሥት መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር አብሮ ለመሥራት እና ምርጫ እስኪከናወን ድረስ አብደላ ሐምዶክ ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ከጥቂት ወራት በፊት የሱዳን ጦር በጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራውን የቪሲል መንግሥት ገልብጦ ሥልጣን ተቆጣጥሮ እንደነበረ ይታወሳል። በቁም እስር ላይ የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከቀናት በፊት ከሱዳን ጦር ጋር ከስምምነት ደርሰው ወደ ሥልጣናቸው ተመልሰዋል። ከሁለት ዓመት በፊት አብደላ ሐምዶክን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾመው የሲቪል ፖለቲከኞች ስብስብ ግን ከወታደሮች ጋር የሚደረግን ማንኛውንም አይነት አዲስ ስምምነት አልቀበልም ሲል ነበር። ይሁን እንጂ በሱዳን የመንግሥት ግልበጣ ማግስት የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ድምጻቸውን በአደባባይ ለማሰማት የሚወጡ ሰዎች በሱዳን ጦር መሪዎች ላይ ያላቸው ተቃውሞ እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላቸውን ድጋፍ ሲገልጹ ቆይተዋል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ የአገሪቱ ዜጎች ሱዳን ወደ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ሽግግር እንድትመለስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት በ18 ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲያካሂድ ጫና እየተደረገበት ነው።", "ከጀርመኑ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጀርባ ያለው ግለሰብ እና ቡድን ማነው? ቱሪንጋ የሚባለው የምሥራቅ ጀርመን ቀጠና ውስጥ ነው የሚኖሩት። እስከ ዛሬ እምብዛም ያልተወራለት ቡድን ነው። ባለፈው ሳምንት በጀርመን ከተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ጋር ተያይዞ ግን ስማቸው ይነሳ ጀምሯል። የጀርመንን ምክር ቤት ተቆጣጥረው የዘመናዊ ጀርመን ሥርዓተ መንግሥትን በንጉሣውያን አስተዳደር ለመቀየር ነበር የወጠኑት። የውጥኑ መሪ ቤተሰቦች አካባቢውን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በፊት መርተዋል። መሪው አሁን ዘብጥያ ወርዷል። ሆኖም ግን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የጀርመን ፖሊሶችን አስደንብሯል። ከጀርመን አልፈው በኦስትሪያ እና በጣልያን ጭምር ፍተሻ እያደረጉ ይገኛሉ። ለፍተሻው 3 ሺህ ፖሊሶች ናቸው የተሰማሩት። 150 ቦታዎችን አስሰው እስካሁን 25 ሰዎችን አስረዋል። ምርመራው ስለሚቀጥል ተጨማሪ ሰዎች እንደሚታሰሩም የደኅንነት ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የጀርመን የፌደራል እና የክልል ምክር ቤቶች ጥበቃ ተጠናክሯል። ቢቢሲ በቱሪንጋ የጎበኘው ሹሎስ ዋልድማንሺል የተባለ መዝናኛ ነው። መዝናኛውን የሚያዘወትሩ ሰዎች ከሕዝብ ዕይታ የራቁ እንደሆኑ የቱሪንጋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ሊመሠርቱ ላሰቡት አዲስ የጀርመን መንግሥት፣ ሚኒስትሮች እስከ መሾም እና ወታደራዊ ክንፍ እስከማዋቀር ደርሰዋል። ቡድኑን የሚመራው ልዑል ቤተሰቦች የሚኖሩት ኦስትሪያ ነው። “በሰማነው ነገር ደንግጠናል። ሐሳቡ የተጠነሰሰው ከዓመታት በፊት ነው። ፀረ ሴማዊ አካሄድ ያለው የሴራ ትንታኔ ገፍቶት ነው ይህን የፈጸመው። የእኛን ቤተሰብ አይወክልም” ሲል ቤተሰቡ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል። ልዑሉ ሄንሪሽ 13ኛ ይባላል። ሬሲንግ ሄንሪሽ በሚል ቅጽል ስም ይጠራል። ሄንሪሽ በተባለው የቤተሰብ ስም የሚጠሩ 30 ሰዎች በሕይወት አሉ። ‘ሬሲንግ’ የሚለው ስም ለሄንሪሽ የተሰጠው ለፈጣን መኪኖች ባለው ፍቅር እንደሆነ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። ቢቢሲ የጎበኘው መዝናኛ ለ100 ዓመታት የቤተሰቡ ንብረት ሆኖ ቆይቷል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ግን በምሥራቅ ጀርመን ኮምኒስት መንግሥት ተወርሷል። ሄንሪሽ በዓመታት ውስጥ ቁጡ ሰው እየሆነ መምጣቱን ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። ልጁ በጠና ታማለች። የሪል ስቴት ንግዱም ስኬታማ አልሆነም። የቀድሞ ንብረቶችን ከጀርመን መንግሥት ለማስመለስ ያደረገው ጥረት በፍርድ ቤት አወንታዊ ብይን አልተሰጠውም። በሕይወቱ ለደረሱበት ምስቅልቅሎች የጀርመን መንግሥትን ተጠያቂ ያደርጋል። ፉርስት የተባለው ቤተሰቡ ለቢቢሲ እንደገለጸው፣ በምሥራቅ ጀርመን የሚገኘውን መዝናኛ መልሶ ከገዛ በኋላ “ከአልባሌ ሰዎች ጋር መዋል አብዝቷል።” ልዑሉ 71 ዓመቱ ነው። ወጣት ሩሲያዊት ሴት ጓደኛ አለችው። ሴት ጓደኛው ለመፈንቅለ መንግሥቱ ከክሬምሊን ድጋፍ ለማግኘት ሞክራ ነበር። ስብስቡ ውስጥ የቀድሞ የጀርመን ልዩ ኃይል አባል፣ የቀድሞ የፖሊስ አመራር፣ የቀድሞ ዳኛ እና በቀኝ ዘመም ፓርቲ የቀድሞ የምክር ቤት አባል አሉበት። ብሪጅት ማልሳክ-ዊንክማን የፍትሕ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብሎ ነበር። የመፈንቅለ መንግሥቱ ቀን የተቆረጠው ሥነ ፈለክን ተከትሎ እንደሆነ የፖሊስ ምርመራ አጋልጧል። ከገና በዓል በፊት በተወጠነው መፈንቅለ መንግሥት “ሊሞቱ የሚችሉ ሰዎች” እንዳሉ ቡድኑ መምከሩም ታውቋል። ለጀርመን ደኅንነት አስደናቂ የሆነው ይህ ቡድን ያዋቀረው ወታደራዊ ክንፍ ነው። ሩጀር ቮን ፒ በተባለ ግለሰብ ነው የሚመራው። ቡድኑ የአገሪቱን ምክር ቤቱን ጥሶ እንዲገባና ፖሊሶችን እንዲከላከል ኃላፊነት ተሰጥቶታል። የቀድሞ ሉተነንት ኮሎኔሉ ሩጀር በሥራ ላይ ሳለ መሣሪያ ያከማች እንደነበር ፖሊሶች ያምናሉ። አንድሬስ ኤም የተባለ የልዩ ኃይል አመራር እና ማክሲሚላን ኤደር የተባለ ኮሎኔል በሥሩ ይገኛሉ። በሴራ ትንታኔ የሚታወቀው ማይክል ኤፍ እና አፍቃሪ-ናዚው ፒተር ደብሊውም አሉበት። ፖሊስ ከፈተሻቸው ቤቶች በ50ው መሣሪያ አግኝቷል። የቀኝ ዘመም ዘረኝነት ላይ ጥናት የሠሩት ኒኮላስ ፖተር ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ የዚህ ቡድን ጽንፈኛ ሐሳብ ምን ያህል ደጋፊዎች እንዳሉት በትክክል አለመታወቁ አስጊ ነው። በጀርመን ልዩ ኃይል ውስጥ የሚገኝ ኬኤስኬ የተባለ ክፍል ቀኝ ዘመም አስተሳሰብ በማንጸባረቁ እንዲበተን መደረጉን ጠቅሰው “መሣሪያ እየተመዘበረ በቀኝ ዘመሞች እጅ ሲገባ እናያለን። ይህ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ትንሹ ስጋታችን ነው። ችግሩ ከዚህም እንደሚብስ እጠረጥራለሁ። በጣም አስጊ ነው” ይላሉ። በመፈንቅለ መንግሥቱ ከተሳተፉ መካከል ሪችስቡርገር የተባለ ቡድን አባላት ይገኙበታል። እነዚህ ወደ 21 ሺህ ገደማ የሚሆኑት የቡድኑ አባላት ለጀርመን ፌደራል መንግሥት ዕውቅና አይሰጡም። ግብር አይከፍሉም። በጀርመን ዳኞች የተላለፈ ውሳኔን አይቀበሉም። የጀርመን የተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥርም አይጠቀሙም። ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ ትክክለኛው የጀርመን አስተዳደር እንደፈረሰ ነው የሚያምኑት። እአአ በ2016 ከዚህ ቡድን አባላት የአንዱ ቤት ሲፈተሽ የቤቱ ባለቤት ፖሊሶች ላይ ተኩሶ አንድ ፖሊስ ገድሏል። ይህ ጽንፈኛ ቡድን አስጊነቱ እየጨመረ እንደመጣ የሚገልጸው የጀርመን ፖሊስ፣ ከመካከላቸው ወደ ነውጥ ሊገቡ የሚችሉ ግን በቁጥር ውስን እንደሆኑ ያስረዳል። ልዑል ሄንሪሽ ከዚህ ቀደም በበተነው በራሪ ወረቀት የጀርመን ፌደራል መንግሥት መታወቂያ ያላቸው ሰዎች ‘ትክክለኛ ጀርመናዊ’ እንዳልሆኑ ተናግሮ ነበር። በራሪ ወረቀቱን በበተነበት አካባቢ የሚኖሩ አዛውንት “ጤነኛ አይመስለኝም። በራሪ ወረቀቱ ላይ በቀድሞው የጀርመን አርማ ቀይ፣ ጥቁርና ነጭ የተሠራ መታወቂያ የምናገኝበት ድረ ገጽ ተጽፏል። አነስተኛ ግዛት ለመፍጠር ድምጽ እንድንሰጥም ይጠይቃል። በራሪ ወረቀቱን ቀዳድጄ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ከተትኩት” ብለዋል። ልዑሉን የሚነቅፉት ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች አይደሉም። ሐሳቡን የሚደግፉም አሉ። “ጀርመን አሁን ባለችበት ሁኔታ ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች ይደግፉታል። ያሳዝናል። ሌላ ዓይነት ጀርመን ማየት ነው የሚፈልጉት” ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል። በአገሪቱ ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ላይ ጥናት የሚሠራው ጆሴፍ ሆልንበርገር እንደሚለው፣ 20 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ለሴራ ትንታኔ ተጋላጭ ናቸው። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ ከምጣኔ ሀብት መሽመድመድ እና ከኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ጋር በተያያዘ መንግሥታቸውን ይወቅሳሉ። የደኅንነት ኃላፊው ስቴፈን ክሬመር “አክራሪዎች እንደ ኮሮናቫይረስ ባለ ወረርሽ ወቅት ይበረታታሉ። ከወረርሽኙ ጋር የተያያዙ የተቃውሞ ሰልፎች መበራከታቸው ቀኝ አክራሪዎችን አደፋፍሯል” ይላሉ። እነዚህ ቡድኖች የጀርመን ፌደራል መንግሥት የመጣል ዒላማ አስተሳስሯቸዋል። ከመካከላቸው የፌደራል መንግሥቱን ዕውቅና የማይሰጡና፣ ዕውቅና ቢሰጡም ነቅለው መጣል የሚፈልጉ እንዳሉ የደኅንነት ኃላፊው ያስረዳሉ። ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የተጣሉ ክልከላዎችን በመቃወም ከተካሄዱ ሰልፎች በአንዱ 40 ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት የበርሊን ተቃውሞ ይጠቀሳል። በወቅቱም ምክር ቤቱን ጥሰው ለመግባት ውስን እንቅስቃሴም አድርገው ነበር። እነዚህ ግለሰቦች የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አድናቂ ናቸው። ሁለቱም መሪዎችም ‘ወግ አጥባቂና ክርስቲያናዊ’ አስተዳደር ተምሳሌት አድርገው ነው የሚመለከቷቸው። ‘ኪውአኖን’ የተባለው የሴራ ትንታኔ ቡድን መነሻውን ያደረገው አሜሪካ ሲሆን፣ ለትራምፕ ጽኑ ፍቅር አለው። ከእንግሊዝኛ ተናጋሪ አገራት ውጭ ኪውአኖን ከፍተኛ ድጋፍ ያለው በጀርመን ነው። ክትባት የሚያጣጥሉ፣ አፍቃሪ-ናዚ ተከታዮች አሉት። የጀርመን አስተዳደር ባለበት እንዲቀጥል የሚፈልጉ አመራሮች የግድያ ዛቻ ሲደርስባቸው እንደሚስተዋል ቢቢሲ ተረድቷል። የቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ተንታኙ ኒኮላስ ፖተር እና የፀረ ፋሺዝም አቀንቃኟ ማርቲና ሬነር በተደጋጋሚ ዛቻ ከሚሰነዘርባቸው መካከል ይጠቀሳሉ። ቡድኑ ግድያን ጨምሮ አካላዊ ጥቃቶችም ያደርሳል። እንደ ማንኛውም ሰው ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ስለሚሳተፉ ቀኝ አክራሪዎችን በቀላሉ የደኅንነት አባላት መለየት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ቀኝ አክራሪዎች የሚፈጽሟቸው ጥቃቶች ‘የተናጠል’ እርምጃ እንደሆኑ እንደሚነገር የሚገልጸው ተንታኙ ኒኮላስ ፖተር፣ ስጋቱ ሥር እየሰደደ እንደመጣና የጀርመን አንዱ ገጽታ እንደሆነ እንዲታወቅ ያሳስባል። የደኅንነት ኃላፊው ስቴፈን ክራመር “እጅግ የከፋ ነገር ይመጣል ብዬ ብሰጋም በጎ ነገር ይመጣል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ” ይላሉ።", "የፊደል ካስትሮ ወንድም ራውል ካስትሮ ከኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ መሪነት ለቀቁ የፊደል ካስተሮ ወንድም ራውል ካስትሮ ከኩባ ብቸና ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበርነት ለቀቁ። ራውል ካስትሮ ከደሴቲቱ አገር ኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ መሪነታቸው መነሳታቸውን ሲገልጹ ቤተሰቦቻቸው ለስድስት አስርት ዓመታት የቆየበትን የሥልጣን ጊዜ አጠናቋል። የ89 ዓመቱ ካስትሮ አመራሩን \"በጋለ ስሜት እና በፀረ-ኢምፔሪያሊዝም መንፈስ ለተሞላ\" የወጣቱ ትውልድ እንደሚያስተላልፉ ለፓርቲው ጉባኤ ተናግረዋል። ተተኪያቸውም ለአራት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ መገባደጃ ላይ ይመረጣል። እርምጃው በ1959 አብዮት የጀመረው የእርሳቸው እና የወንድማቸው ፊደል ካስትሮ የመሪነት ዘመን ማብቂያ ይሆናል። ካስትሮ አርብ ዕለት በሃቫና ለተገኙ የፓርቲው ልዑካን \"እኔ በአገሬ ሰዎች ጥንካሬ እና አርአያነት ባለው ተፈጥሮ እና ግንዛቤ በጣም አምናለሁ\" ብለዋል። ካስትሮ ተተኪያቸውን ባያሳውቁም የፓርቲው አመራር እአአ በ2018 የደሴቲቱን ፕሬዝዳንትነት ለተረከቡት ሚጉኤል ዲያዝ-ካኔል ኃላፊነቱን ይተላለፋል የሚል ሰፊ እምነት አለ። የዘመን ፍጻሜ የእርሳቸው ከኃላፊነት መነሳት ከስድስት አስርት ዓመታት በኋላ፤ ኩባ ለመጀመሪያ ጊዜ የካስትሮ ቤተሰብ አባል የፖለቲካ መሪዋ አይሆንም ማለት ነው። ራውል እአአ በ2011 ታላቅ ወንድማቸው ፊደልን በመተካት የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል። ፊደል ካስትሮ እአአ በ1959 የኩባን መንግሥት ከሥልጣን ያወረደውን የኮሚኒስት አብዮት የመሩ ሲሆን ራውል ደግሞ ከአዛዦቻቸው አንዱ ሆነው አገልግለዋል። ፊደል ካስትሮ በ2006 እስከታመሙበት ጊዜ ድረስ የአገሪቱ መሪ ነበሩ። ይሁን እንጂ በ2008 ፕሬዝዳንትነቱን ለወንድማቸው አስረክበዋል። ከዚያም እአአ በ2016 ፊደል ካስትሮ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኩባ በራውል ስር ራውል ካስትሮ እንደ መሪ የኮሚኒስትን የአንድ ፓርቲ የሥልጣን ጉዞ እንዲቀጥል አደረጉ። በ2014 ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር የተደረገውን ታሪካዊ ውይይትን ጨምሮ ከ 2014 እስከ 2016 መካከል ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነቶች መሻሻልን በበላይነት መርተዋል። ማዕቀቡን ባጠናከረው በዶናልድ ትራምፕ ዘመን ግን ውጥረቱ ተባብሷል። የዋይት ሐውስ በኩባ ፖሊሲ ላይ የሚደረግ ለውጥ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አለመሆኑን ቢጠቅስም፤ የወቅቱ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተወሰኑትን የትራምፕ ማዕቀቦችን ለማቃለል ቃል ገብተዋል። አርብ ዕለት በተካሄደው ኮንግረስ ላይ ራውል ካስትሮ አገራቸው ከአሜሪካ ጋር \"መከባበር ያለበት ውይይት ለማዳበር ፈቃደኛ መሆኗን\" ገልፀው፤ ነገር ግን \"የውጭ ፖሊሲዋን እና ሀሳቧን በተመለከተ ለውጥ ማድረግን\" እንደማትቀበል ተናግረዋል። ቀጥሎ ምን ይሆናል? በኩባ አስተዳደር ፓርቲ አመራር ላይ የተደረገው ለውጥ ደሴቲቱ በአስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ አስከፊ የሆነውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመቋቋም በምትሠራበት ወቅት ነው። በትራምፕ አስተዳደር የተላለፈው ማዕቀብ፣ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ኢኮኖሚው ባለፈው ዓመት በ11 በመቶ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል። በጥር 1 የተጀመረው እና ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የገንዘብ ማሻሻያ ኢኮኖሚውን እና የመንግሥት ኩባንያዎችን ውጤታማ ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም የኩባ ዜጎችን በጀት ጎድቷል። ብዙዎችም በአገሪቱ የበለጠ ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እንዲኖር ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሌላው ተግዳሮት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን የዜጎችን የርዕዮተ ዓለም አንድነትና ድጋፋቸውን ጠብቆ ማስቀጠል ነው። በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ በማሰማት እና በቀጥታ ሥርጭት ታዳሚዎችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ። የአመራር ለውጥ ቢኖርም በፖሊሲ አቅጣጫው ላይ ለውጥ ያመጣል ብለው የሚጠብቁት ጥቂቶች ናቸው። የ2019ቱ አዲስ ሕገ-መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ የመንግሥት የበላይነት እና \"ሶሻሊዝም\" የማይቀለበስ መሆኑን አረጋግጧል። የ60 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዲያዝ-ካኔል አርብ ዕለት ባሰፈሩት የትዊተር ጽሑፍ ጉባኤውን \"ጠንካራ ሐሳቦች፣ የታሪክ እውቅና እና የወደፊቱ የሚወያዩበት ይሆናል\" ብለዋል። ቀጣይነት እንደሚኖርም አክለው ገልጸዋል። ራውል ካስትሮ በጉባኤው \"መደበኛ አብዮታዊ ታጋይ\" ተብለው ጡረታ እንደሚወጡ ተናግረዋል። \"እናም በሕይወት እስካለሁ ድረስ የአባት አገርን፣ አብዮቱን እና ሶሻሊዝምን ለመከላከል በሚነሳው ችግር ውስጥ ለመግባት አገሬን አዘጋጃለሁ\" ብለዋል።", "የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ ይጠበቃሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት ለአራት ቀናት ወደ አዲስ አበባ፣ ካርቱም እና ሪያድ በመጓዝ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ። ባለሥልጣናቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና በአምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ምትክ በቅርቡ የተሾሙት አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ናቸው። ከሰኞ ጥር 09 እስከ ጥር 12/2014 ዓ.ም በሚደረገው በዚህ የዲፕሎማቶቹ ጉዞ በኢትዮጵያና በሱዳን ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። ባለሥልጣናቱ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ፕሬዝዳንት ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ሰኞ ጥር 02/2014 ዓ.ም ያደረጉት \"ገንቢ የስልክ ውይይት ተከታይ ጉዳዮችን\" ያነሳሉ ብሏል። በዚህም ዲፕሎማቶቹ የአየር ጥቃቶች እና ሌሎች ግጭቶች እንዲቆሙ፣ በድርድር ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻችና ለሁሉ አቀፍ ብሔራዊ ውይይት የሚያስፈልጉ ነገሮች እንዲመቻቹ በአሁኑ ወቅት የተከፈተውን የሰላም ዕድል እንዲጠቀሙበት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትን ያበረታታሉ ተብሏል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣኗ ሞሊ ፊ እና ልዩ መልዕክተኛው ሳተርፊልድ ወደ አዲስ አበባ ከመሄዳቸው በፊት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድና ወደ ጎረቤት ሱዳን እንደሚያመሩ ተገልጿል። በዚህም ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በቀውስ ውስጥ ለምትገኘው ሱዳን በሲቪሎች የሚመራ ዴሞክራሲያዊ ሽግግርን በተመለከተ በተባበሩት መንግሥታት አማካይነት በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ። ከሳዑዲ በማስከተልም ሁለቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ኃላፊዎች ወደ ሱዳን ካርቱም በማቅናት ከዴሞክራሲ ደጋፊ አክቲቪስቶች፣ ከሴቶችና ከወጣቶች ቡድኖች፣ ከሲቪል ማኅበራት፣ ከጦር ኃይሉ መሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ይወያያሉ ተብሏል። ከዚያ በማስከተል የመጨረሻ የጉዟቸው መዳረሻ የምትሆነው አዲስ አበባ ስትሆን፣ እዚያም ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ወይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለቱ መሪዎች በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነትና በአገሪቱ ስላሉ ፖለቲካዊ ጉዳዮች መወያየታቸውን የወጡ መግለጫዎች አመልክተዋል። ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀስ ተከትሎ አሜሪካ በያዘችው አቋምና በወሰደቻቸው እርምጃዎች ምክንያት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የነበረው መልካም ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል። የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ጨምሮ በጦርነቱ ተሳታፊዎች ላይ ከጣለው የቪዛ እገዳ እንዲሁም ከሁለት ሳምንት በፊት ተግባራዊ የሆነው ኢትዮጵያ ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ ምርቶችን ወደ አሜሪካ ታስገባበት የነበረው የአጎዋ ተጠቃሚነት የእገዳ እርምጃ ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ መንግሥትም አሜሪካ ለአማጺያኑ የሚያደላ መግለጫና እርምጃ እየወሰደች ነው በማለት አሜሪካን በወገንተኝነት ሲከስ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት ተሰናባቹ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን አዲስ አበባ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስልክ መነጋገራቸው የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማሻሻል ጅማሬ ሊሆን እንደሚችል በስፋት ተነግሯል። አሜሪካ ጦርነቱ በድርድር መቋጫ እንዲያገኝ ልዩ መልዕክተኛ በመሰየም ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት ስታደርግ ብትቆይም እስካሁን ውጤት ሳይገኝ ቆይቷል። ከሰኞ ጀምሮ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚያቀኑት ሁለቱ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ሙያ ያዳበሩ ዲፕሎማቶች መሆናቸው ይነገራል። ሜሪ ካትሪን ሞሊ ፊ ሜሪ አሁን ያሉበትን የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊነት የተረከቡት ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን ከዚያ በፊት ለሦስት ዓመታት ያህል በደቡብ ሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ውስጥም በከፍተኛ ኃላፊነት አገልግለዋል። አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ዴቪድ ሳተርፊልድ ደግሞ በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በመካከለኛው ምሥራቅ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ለአራት አስርት ዓመታት የዘለቀ ልምድ እንዳካበቱ ይነገርላቸዋል። አምባሳደር ሳተርፊልድ በቱርክ፣ በሶሪያ፣ በቱኒዚያ፣ በሳዑዲ አረቢያ እና ሊባኖስ ውስጥ አገራቸውን ወክለው በዲፕሎማትነት ሰርተዋል። አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ማይክ ፖምፔዮ ከፍተኛ አማካሪ ነበሩ።", "ታሊባን በርካታ ግዛቶችን መቆጣጠሩን ተከትሎ የሰዓት እላፊ ታወጀ የታሊባን ታጣቂዎች በርካታ ግዛቶችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የአፍጋኒስታን መንግሥት የሰዓት እላፊ አውጇል። የአፍጋኒስታን መንግሥት ይህንን የሰዓት እላፊ ያወጀውም የታሊባን ታጣቂዎች ሌሎች ከተሞችን ከመውረር ለማስቆም ነው ብሏል። ከመዲናዋ ካቡልና ሌሎች ሁለት ግዛቶች ውጭ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ሌሊት 10 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ አይችልም። በባለፉት ሁለት ወራት በታሊባንና በአፍጋኒስታን የመንግሥት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያው ተባብሷል። በቅርብ ሳምንት ዓለም አቀፍ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል። ታሊባን ከአገሪቱ ግዛቶች ውስጥ እስከ ግማሽ ያህሉን እንደተቆጣጠረ ይገመታል። በተለይም የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የድንበር መሸጋገሪያዎችንና በርካታ ገጠራማ ቦታዎችን መቆጣጠራቸው ተገልጿል። ከ 20 ዓመታት ገደማ በፊት በአሜሪካ ወረራ ከስልጣን ተገፍተው የወጡት ታሊባን እንዲሁ የአቅርቦት መንገዶችን ለመቁረጥ በመፈለግ ቁልፍ ጎዳናዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል ተብሏል። የታሊባን ተዋጊዎች ወደ በርካታ ቁልፍ ከተሞች የሚሄዱ መንገዶችን ቢዘጉም እስካሁን ዋና ዋና ከተሞችን መቆጣጠር አልቻሉም። ካቡል ፣ ፓንጅሺር እና ናንጋርሃር ነፃ መሆናቸውን በመግለፅ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ \"አመፅን ለመግታት እና የታሊባንን እንቅስቃሴ ለመገደብ በ 31 ግዛቶች የሰዓት እላፊ አዋጅ ተጥሏል\" ብለዋል። ታሊባን ወደፊት እየገሰገሰ ባለበት በዚህ ሳምንት በካንዳሃር ከተማ ዳርቻ ላይ ከባድ ወጊያዎች ተካሂደዋል። በምላሹ የአሜሪካ መንግሥት ታሊባን በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ላይ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ የአየር ጥቃት መፈፀሙን አስታውቋል። ነገር ግን አሜሪካ በአፍጋኒስታን ውስጥ ታደርገው የነበረው ዘመቻ ይፋዊ በሆነ ሁኔታ በአውሮፓውያኑ ነሐሴ መጨረሻ የሚጠናቀቅ ቢሆንም በመጪዎቹ ወራቶች ምን ሊከሰት ይችላል በሚለው ሁኔታ ላይ ስጋቶች አሉ ተብሏል።", "ማክሮን “የአዕምሮ ጤና ምርመራ” ያስፈልጋቸዋል ሲሉ የቱርኩ ኤርዶጋን ተናገሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኤማኑኤል ማክሮን “የአዕምሮ ጤና ምርመራ” ያስፈልጋቸዋል ማለታቸውን ተከትሎ ፈረንሳይ የቱርክ አምባሳደሯን ጠራች። ኤርዶጋን የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት የአዕምሮ ጤና ምርመራ ያስፈልጋቸዋል ያሉት ፕሬዝደንት ማክሮን ጽንፈኛ እስላማዊነትን ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ፈረንሳያዊው መምህር አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድን የካርቱን ምስሎች ክፍል ውስጥ ማሳየቱን ተከትሎ አንገቱ ተቀልቶ መገደሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ማክሮን በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያለ አቋም እየንጸባረቁ ይገኛሉ። የፈረንሳይ መንግሥት የአንድን ማህበረሰብ ወይም እምነት ተከታዮችን ስሜት ለመጠበቅ ሲባል የሰዎች የመናገር መብት ሊገደብ አይደባም የሚል ጠንካራ አቋም ይዟል። ፈረንሳይ የሰዎች የመናገር መብትን መገደብ የፈረንሳይን አንድነት ጥያቄ ውስጥ ይጥላል የሚል አቋም አላት። ማክሮን ይህን የፈረንሳይ እሴትን ለመጠበቅ ዘመቻ ላይ ናቸው። የቱርኩ ፕሬዝደንት በዚህ ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፤ “ማክሮን የሚባለው ግለሰብ ከእስልምና እና ሙስሊም ጋር ያለው ችግር ምንድነው?” ሲሉ ጠይቀዋል። “ማክሮን የአዕምሮ ጤና ሕክምና ያስፈልገዋል” ሲሉም ጨምረዋል። የቱርኩ ፕሬዝደንት ይህን ማለታቸውን ተከትሎ በቱርክ የፈረንሳይ አምባሳደር ለምክክር ወደ ፓሪስ መጠራታቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል አንድ የፈረንሳይ ከፍተኛ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። አምባሰደሩ ከማክሮን ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ ተብሏል። እኚህ የፈረንሳይ ከፍተኛ ባለስልጣን “የፕሬዝደንት ኤርዶጋን አስተያየት ተቀባይነት የለውም” ስለማለታቸው ኤኤፍፒ ጨምሮ ዘግቧል። ይህ የኤርዶጋን አስተያየት በፈረንሳይ እና ቱርክ መካከል ያሉ ልዩነቶች እየሰፉ ስለመምጣታቸው አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል። ሁለቱም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት ይሁኑ እንጂ የማይሰማሙባቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። በሊቢያ እና ሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ሁለቱ አገራት በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ይገኛሉ። በአርሜኒያ እና አዘርባጃን ግጭት ውስጥም የሁለቱ አገራት ፍላጎት የተለያየ ነው።", "ሩሲያ ዩክሬንን 'መውረር ጀምራለች' ያሉት ባይደን ሞስኮ ላይ ማዕቀብ ጣሉ አሜሪካ ሩሲያ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን ጣለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ዩክሬንን 'መውረር ጀምራለች' ካሉ በኋላ አስተዳደራቸው በሞስኮ ላይ ጠንካራ መዕቀብ መጣሉን ያስታወቁት። \"ሩሲያን ከምዕራቡ ዓለም አገራት የፋይናንስ ፈሰስ እንቆርጣታለን\" ብለዋል። ውሳኔው ላይ የደረሱት ሩሲያ ወታደሮቿን ወደ ሁለት የዩክሬን ክልሎች ከላከች በኋላ ነው። ሁለቱ ክልሎች በአማጽያን የተያዙ ሲሆኑ፤ ሩሲያ ከሰሞኑ ራሳቸውን የቻሉ ግዛቶች ናቸው ስትል እውቅና ሰጥታለች። ሁለቱ በአማጽያን የተያዙ ክልሎችን ሩሲያ ነጻ ብላ ማወጇን ዩክሬን በጥብቅ ተቃውማለች። በተመሳሳይ በርካታ ምዕራባውያን አገራት በፑቲን እርጅማ ተበሳጭተዋል። ሩሲያ ወደ ሁለቱ ክልሎች የገባችው ወረራውን ለማስፋፋት እንደሆነ ምዕራባውያኑ ሰግተዋል። ዶንቴስክ እና ሉሀንስክ ወደተባሉት ክልሎች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወታደሮቻቸውን የላኩት \"ሰላም ለማስከበር ነው\" ብለዋል። ከሳተላይት የተገኘ ምስል እንደሚያሳየው ባለፉት 24 ሰዓታት አዳዲስ ወታደሮች እና መሣሪያዎች ወደ ምዕራብ ሩሲያ ተጠግተዋል። በዩክሬን ጎረቤት ቤላሩስ ውስጥ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎችም ታይተዋል። በጉዳዩ ላይ ሩሲያ አስተያየት አልሰጠችም። \"ሩሲያ ከዩክሬን ግዙፍ ክፍል ልትወስድ እንደሆነ አስታውቃለች\" ሲሉ ባይደን ተናግረዋል። የጣሉት ማዕቀብ የሩሲያን የውጭ ብድር የሚገታ ሲሆን፣ ሩሲያ ከምዕራባውያን የፋይናንስ ተቋማት መበደር አትችልም ማለት ነው። ባይደን የሩሲያ አመራሮችም \"ሊቀጡ ይገባል\" ብለው ማዕቀብ ጥለውባቸዋል። በዩክሬን በአማጽያን የተያዙት ሁለት ክልሎች ውስጥ አሜሪካውያን እንዳይነግዱ ውሳኔ ተላልፏል። 17ቱ የአውሮፓ ኅብረት አገራት የሩሲያ ምክር ቤት አባላት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ተስማምተዋል። ይህም ሁለቱ የዩክሬን ክልሎችን ነጻ ግዛት ብለው ውሳኔ ያሳለፉ አመራሮችን ይጨምራል። የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እንዳሉት በአምስት ባንኮች የሩሲያውያን ሀብታሞች ተቀማጭ ገንዘብ ታግዷል። በተጨማሪም ዩኬ የጉዞ እገዳ ጥላለች። ጀርመን ከሩሲያ ወደ አውሮፓ ነዳጅ የሚያስተላልፈውን ግዙፍ ትቦ ሥራ አቋርጣለች። አሜሪካ ጦሯን በሩሲያ አቅራቢያ ወደሚገኙት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) አባል አገራት ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ እን ሊቱኒያ እያስጣጋች ነው። ጣልያንም ተዋጊ ጀቶችና ሄሊኮፕተሮችን ጨምሮ በፖላንድ ጦር እያሰፈረች ትገኛል። የሩሲያ እና ዩክሬንን ፍጥጫ ለማርገብ የተሞከሩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ፍሬ አላፈሩም። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዲፕሎማሲን ፊት የነሳችው ሩሲያ አቋሟን ከለወጠች አሜሪካ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናት ብለዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር አገራቸው ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚያቋርጡ ተናግረዋል። ዩክሬን አሁንም ዴፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደምትሻ ቢናገሩም ለጥንቃቄ ሲሉ ወታደሮችን ወደ ሥልጠና ጠርተዋል።", "ዴሞክራቶች የትራምፕ ደጋፊ የሆኑትን ሴት ከኮንግረስ ለመፈንገል እያሴሩ ነው በአሜሪካ ፖለቲካ ቁንጮ ከሆኑት ሁለት ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዴሞክራቶች፤ የትራምፕ ደጋፊ የሆኑትን ሕግ አውጭ ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ እየጣሩ ነው። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ወግ አጥባቂዋ ፖለቲከኛ በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቿ ላይ በጻፉት ጉዳይ ነው ከኃላፊነቷ ትነሳ እየተባለ ያለው። ማርጆሪ ታይለር ግሪን የተባሉት ሪፐብሊካን በሴራ ትንተና ያምናሉ። የመስከረም 9/11 የሽብር ጥቃት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነው ብለው ከሚያምኑ አሜሪካዊያን መካከልም አንዷ ናቸው። ጆርጂያ ግዛት ወኪል የሆኑት የኮንግረስ አባል ባለፈው ወር አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ለመክሰስ ደፋ ቀና ሲሉ ነበር። ማርጆሪ ግሪን ባሳለፍነው ሰኞ በትዊተር ገጻቸው ላይ \"ዴሞክራቶች ከተወከልኩበት ኮሚቴ ካባረሩኝ ቃል እገባላችኋለሁ እኛ በ2022 [በቀጣዩ የምክር ቤት ምርጫ] አብላጫ ድምፅ ስናገኝ አፀፋውን እጥፍ ድርብ አድርገን እንመልሳለን\" ሲሉ ጽፈው ነበር። \"አብላጫ ድምፅ ማግኘታችን የማይቀር ነው፤ እሱን እንዳትሳሳቱ\" ሲሉም ዝተዋል። ባለፈው ኅዳር ወደ አሜሪካ ኮንግረስ የሚያስገባትን ድምፅ ያገኘችው ማርጆሪ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የትምህርትና ሰው ኃይል እንዲሁም የበጀት ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል። የኮሚቴው አባል እንዲሆኑ የመረጧቸው በምክር ቤቱ የሪፐብሊካኖች መሪ የሆኑት ኬቪን ማካርቲ ናቸው። ዴሞክራቶቹ ለምን ሊያስወግዷቸው ፈለጉ? ዴሞክራቶች የትራምፕ ደጋፊ የሆኑት ግለሰብ ከዚህ በፊት የፈፀሟቸው ድርጊቶች የኮሚቴ አባል እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው አይደለም ሲሉ ይከራከራሉ። በተለይ ደግሞ ከትምህርት ኮሚቴው እንዲፈነገሉ ነው ፍላጎታቸው። ሴትዬዋን ከኮሚቴው የመፈንገል ሂደቱን እየመሩ ያሉት ዴሞክራቷ ዴቢ ሹልትዝ \"ሪፐብሊካኖች እሷን መተካት ካልቻሉ እኛ እንተካላቸዋለን\" ሲሉ ተደምጠዋል። ትላንት [ሰኞ] በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ ያላቸው ዴሞክራቶች መሪ የሆኑት ስቴኒ ሆዬር ለሪብሊካኖች መሪ 'ግለሰቧን ያውርዱልን' የሚል ጥሪ አቅርበዋል። ማርጆሪ ከኮሚቴዎቹ በ72 ሰዓታት ውስጥ ካልወረዱ ግን ዴሞክራቶች ይህንን ጉዳይ በራሳቸው እንደሚወጡ ዝተዋል። ዴሞክራቶች ግለሰቧ ከኮሚቴዎቹ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ከኮንግረሱ እንዲባረሩ ይፈልፈጋሉ። ከወግ አጥባቂነታቸው አልፈው አክራሪ ሆነዋል ብለው የሚያምኑ ሪፐብሊካኖችም ጭምር ማርጆሪ ከኮንግረስ እንዲባረሩ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሴኔቱ አናሳ ድምፅ ያላቸው ሪብሊካኖች መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ሴትዬዋ የምታምንባቸውን የሴራ ትንተናዎች 'ለሪብሊካን ፓርቲ ካንሰር ናቸው' ሲሉ ወርፈዋል። በፈረንጆቹ 2019 በኮንግረሱ የአዮዋ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሰው በአንድ ቃለ መጠይቅ ወቅት የነጭ የበላይነትን አጣጥለው አስተያየት በመስጠታቸው ከሁለት ኮሚቴዎች መወገዳቸው አይዘነጋም። ነገር ግን ሪፐብሊካኖች አሁንም በፖርቲ አጋራቸው ላይ ይህን ዓይነት እርምጃ ይወስዳሉ ወይ የሚለው እርግጥ አይደለም። አንድ የኮንግረስ አባልን ከኮንግረሱ ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ሁለት ሶስተኛ ድምፅ ያሻል። በአሜሪካ ታሪክ ከኮንግረስ አባልነታቸው የተወገዱ ሰዎች ቁጥር አምስት ብቻ ነው። ማርጆሪ የኮንግረስ አባል ሆነው አነጋጋሪ አስተያየት የሰጡ የመጀመሪያዋ ሴት አይደሉም። በ2019 የሚኒሶታዋ ኢልሃን ኦማር ፀረ-አይሁድ ናቸው ተብለው በተፈረጁ አስተያየታቸው ምክንያት ብዙ ትችት ደርሶባቸው ነበር። በወቅቱ ኢልሃን ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው ነበር። የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊዋ ማርጆሪ ግሪን ግን በተደጋጋሚ አነጋጋሪ አስተያየት ከመስጠት ባለፈው በይፋ የሴራ ትንተና አማኝ መሆናቸው ነው ለየት የሚያደርጋቸው። ማርጆሪ፤ በ2016 የአሜሪካ ምርጫ የትራምፕ ተፎካካሪ የሆኑት ሂላሪ ክሊንተን ሕፅናትን ይገርዛሉ ብለው ያምናሉ። አልፎም በፈረንጆቹ 2001 የደረሰው የ9/11 አደጋ የአሜሪካ መንግሥት ሴራ ነው ብለው ነው የሚያምኑት። ይህም አልበቃ ብሏቸው ካሊፎርኒያ ውስጥ የተከሰተው የሰደድ እሳት ሆን ተብሎ ከሕዋ ላይ በተለቀቀ ጨረር የተነሳ ነው ይላሉ። በአንድ ወቅት 'ጥቁሮች የዴሞክራቲክ ፓርቲ ባሪያዎች ናቸው'፤ ነጭ ወንዶች ደግሞ አሜሪካ ውስጥ በጣም በደል የሚደርስባቸው ናቸው ሲሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር።", "ጆን ማጉፉሊ፡ ኮሮናቫይረስን ከአገር አባረዋለሁ ያሉት መሪ የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮረናቫይረስን በተመለከተ በሚሰጧቸው አስተያየቶችና በሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆነው ለመመረጥ እየሰሩ ነው። ኮቪድ-19 ታንዛኒያ ሲደርስ ፕሬዚዳንቱ ሰዎች በቤታቸው መቆየት የለባቸውም ብለው አጥብቀው ይከራከሩ ነበር። እንዳውም ቫይረሱ እንዲጠፋ ቤተክርስቲያን እና መስጂድ ሄደው እንዲጸልዩ አበረታትተዋል። ''ኮሮናቫይረስ እርኩስ መንፈስ ነው፤ በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ ሊቆይ አይችልም. . . . . ወዲያውኑ ይቃጠላል'' ሲሉም ተደምጠዋል አጥባቂ ክርስቲያኑ መሪ ጆን ማጉፉሊ። ፕሬዚዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ስለማድረግ በተመለከተ ሲናገሩ ምንም አይጠቅመንም ብለዋል። አክለውም የምርመራው እውነተኛነት ላይ ጥርጣሬ እንዳለቸው በመግለጽ በተለያዩ ፍራፍሬዎችና አንዲት ፍየል ላይ ምርመራ ተደርጎ ቫይረሱ በፓፓዬና በፍየሏ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ጎረቤት አገራት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸውን በመተቸትም እሳቸው ግን በዚህ መልኩ ኢኮኖሚውን መጉዳት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በርካታ አወዛጋቢና አነጋጋሪ ውሳኔዎችንም በማሳለፍ ይታወቃሉ። በአገሪቱ ታሪክ ከ54 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን ብዙ ገንዘብ እያስወጣን ስለሆነ በህዝባዊ በአል አናከብረውም ማለታቸው የሚታወስ ነው። በአሉን በማክበር ፋንታም ህዝቡ ወጥቶ አካባቢውን እንዲያጸዳ ኣደረጉ ሲሆን እራሳቸውም በመንገድ ላይ በመውጣት በእጃቸው ቆሻሻ ሲሰበስቡ ውለዋል በነጻነት ቀን ላይ። ጆን ማጉፉሊ ፕሬዚዳንቱ በሆኑበት የመጀመሪያ ዓመት ላይ የሚወስዷቸው እርምጃዎች በበርካቶች ዘንድ ሙገሳን አስገኝቶላቸው ነበር። እንዳውም ታንዛንያውያን በትዊተር በኩል ማጉፉሊ ቢሆኑ ምን ያደርጉ ነበር እያሉ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ሲጋሩት ከርመዋል። ጉዳዩን ወደ ቀልድ የወሰዱት በርካቶች ቢሆንም ለጊዜውም ቢሆን ፕሬዚዳንቱ የአገሬውን ዜጋ መነጋገሪያ ጉዳይ ሰጥተውት ነበር። ከአገራቸው አልፎም በጎረቤት አገራት ከፍተኛ ተጽዕኖ መፍጠር ችለው ነበር። በአውሮፓውያኑ 2017 አንድ ኬንያዊ ፕሮፌሰር በዳሬሰላም ዩኒቨርሲቲ ንግግር ሲያደርጉ አፍሪካ በማጉፉሊ አስተሳሰብ መቃኘት አለባት ሲሉ ተደምጠው እንደነበር የሚታወስ ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ፕሬዚዳንቱ የነበራቸው ድጋፍና ተቀባይነት እየተሸረሸረ መጥቷል። የማጉፉሊ አስተዳደር ያልተለመዱና በድፍረት የሚወሰዱ በርካታ ሕጎችንና መመሪያዎችንም ሲያወጣ ነበር። በተለይ ደግሞ ከዓለምአቀፍ የማዕድን አውጭ ተቋማት ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ ያለሙ ሕጎች ተጠቃሽ ናቸው። 2017 ላይ 'አኬሺያ ማይኒንግ' የተባለው ዓለምአቀፍ የማዕድን አውጭ ድርጅት 190 ቢሊየን ዶላር ግብር እንዲከፍል ተጠይቆ የነበረ ሲሆን ከብዙ ክርክር በኋላ ግን ድርጅቱ 300 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል ተስማምቷል። በመቀጠልም የታንዛንያ መንግሥት በድርጅቱ 16 በመቶ ድርሻ እንዲኖረውና ወደፊት ለሚገኙ ትርፍና መሰል ጥቅማትቅሞች እኩል ለመካፈል ተስማምተዋል። ፕሬዚዳንቱን በእጅጉ ከሚያስተቿቸው ውሳኔዎች መካከል ደግሞ ሴት ተማሪዎች በትምሀርት ላይ እያሉ ካረገዙ ተመልሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት አይችሉም የሚለው ነበር። ኢኮኖሚውን ከማነቃቃት አንጻር ደግሞ ፕሬዚዳንቱ በርካታ ስራዎችን መስራት ችለዋል። ታንዛንያን ከጎረቤት አገራት የሚገናኘው የባቡር መስመርን ጨምሮ በአገሪቱ አሉ የሚባሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲሰሩ አድርገዋል። በመንግሥት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ብሄራዊ አየር መንገድም ከእዳው ተላቆ በአዲስ መልክ እንዲዋቀርና ወደ ገበያ እንዲገባም የሰሩ ሲሆን በአገሪቱ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከ አራተኛ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ድረስ ትምህርት በነጻ እንዲሰጥ አድርገዋል። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ኮሮረናቫይረስን በመቆጣጠር ረገድ ለወራት ይወስዷቸው የነበሩ እርምጃዎች ከአገሬው ዜጋም ሆነ ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትችትን አስከትሎባቸዋል። ምንም እንኳን አገሪቱ የመጀመሪያውን የኮሮረናቫይረስ ምልክት ካየች በኋላ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋትና ገደቦችን ማስቀመጥ ብትጀምርም የዓለም ጤና ድርጅት ግን ታንዛንያ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የወሰደችው እርምጃ የዘገየና ውጤታማ ያልነበረ ነው ብሏል። በወቅቱ ገበያዎችና የስራ አካባቢዎች ክፍት የነበሩ ሲሆን የእምነት ቤቶችም ቢሆኑ ለአማኞች ክፍት ሆነው እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ''በአገራችን በርካታ በቫይረስ የሚተላለፉ በሽታዎች አሉ፤ እንደ ኤችአይቪ ኤድስ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል። ሁሌም ቢሆን ኢኮኖሚያችን መቅደም አለበት። ኢኮኖሚው እንዲተኛ መፍቀድ የለብንም፤ ሕይወትም መቀጠል አለባት'' ብለው ነበር ፕሬዚዳንቱ። በተጨማሪም ''ሌሎች የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ቸኩለው በመዝጋታቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለሚገቡ በቅርብ ዓመታት ምግብ ከእኛ ለመግዛት መምጣታቸው አይቀርም'' ሲሉም ተደምጠው ነበር። በአሁኑ ሰአት ታንዛንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ስትሆን ፕሬዝዳንቱም በድጋሚ ለመመረጥ እንደሚፈልጉ እየገለጹ ነው። ዋነኛ ተቀናቃኞቻቸው ደግሞ የቻዴማ ፓርቲ ተወካዩ ቱንዱ ሊሱ ናቸው። ሰውዬው በአውሮፓውያኑ 2017 ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የነበረ ሲሆን ላለፉት ሶስት ዓመታት በውጪ አገር በሕክምናና ማገገም ላይ አተኩረው ቆይተዋል። በአገሪቱ ታሪክ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የሚመሩት ፓርቲ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሸንፎ አለማወቁ እሳቸውም በድጋሚ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በርካቶች ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ተቀናቃኛቸው ቱንዱ ሊሱ ደግሞ በአገሪቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚያደርጉና ሰብአዊ መብት እንዲከበር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። ሌላኛው ተፎካካሪ በርናርድ ሜምቤ ደግሞ የቀድሞ ሚኒስትር ሲሆኑ እሳቸውም በምርጫው ካሸነፉ በርካታ ለውጦችን እንደሚያደርጉ እየገለጹ ነው። ጆን ማጉፉሊ በምርጫው የሚያሸንፉ ከሆነ በአገሪቱ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እንደሚያተኩሩና የዜጎችን ኑሮ ለመቀየር በርካታ ፖሊሲዎች ማርቀቅና ተግባራዊ ማድረግ ላይ ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።", "በሶማሊያ ምርጫ ዋዜማ አንድ አጥፍቶ ጠፊ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ ሶማሊያ ውስጥ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። አጥፍቶ ጠፊው ጥቃቱን ያደረሰው ሶማሊያ ምርጫ ለማካሄድ አንድ ቀን ሲቀራት ነው። ፍንዳታው የደረሰው በልደወይኔ በተሰኘችው ማዕከላዊ ሶማሊያ በምትገኝ ከተማ ሲሆን የከተማዋ ባለሥልጣና በሚያዘወትሩት አንድ ሬስቶራንት ውስጥ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው። ሮይተርስ የተሰኘው የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል ለሶማሊያ ፓርላማ ለመመረጥ ዕጩ የነበሩ ግለሰብ ይገኙበታል። የአል-ሸባብ ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈፀምነው እኛ ነን ብለዋል። ፅንፈኛው ቡድን አል-ሸባብ የሶማሊያ መንግሥትን ከአስር ዓመት በላይ ሲዋጋ ቆይቷል። በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎችም ጠንካራ ይዞታ መሥርቷል። ቡድኑ በተለይ በቅርብ ጊዜያት በርካታ ጥቃቶችን እየሰነዘረ ይገኛል። ኤኤፍፒ የተባለው የዜና ወኪል፤ የፓርላማ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች ባለችው በልደወይኔ ከተማ የፀጥታ ኃይሎች በርከት ብለው ተሰማርተዋል ሲል ፅፏል። የሶማሊያ ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፕሬዝደንቱ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ለወራት ሲጓተት ቆይቷል። የፓርላማ ምርጫው በሚቀጥለው ሳምንት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። በሶማሊያ ምርጫ መሠረት የጎሳ መሪዎችና ሌሎች ተወካዮች ሕግ አውጭዎችን ከመረጡ በኋላ እኒህ ተመራጮች ደግሞ በተራቸው ፕሬዝደንት ይመርጣሉ።", "ዕጸ ፋርስ እና የእባብ መርዝ የወጪ ንግድን አቀላጥፋለሁ የሚሉት የኬንያ ዕጩ ፕሬዚዳንት በልጅነታቸው የኬንያ ጎዳና ተዳዳሪ በኋላም በአንድ ወቅት በዩናይትድ ኪንግደም የመቃብር ቆፋሪ የነበሩት የአሁኑ የኬንያ ዕጩ ፕሬዝዳንት፣ ጆርጅ ዋጃኮያህ ለአገራቸ ዕጸ ፋርስ፣ የእባብ መርዝ እና የጅብ ዘር ፍሬን የወጭ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ አቀላጥፋለሁ እያሉ ነው። ብዙዎች የዕቅዳቸውን ተግባራዊነት ቢጠራጠሩትም የኬንያው ዕጩ ፕሬዚዳንት የምርጫ ቅስቀሳ በርካቶችን አስደምሟል። የ63 ዓመቱ ፕሮፌሰር እንዲሁም 17 ዲግሪ እንዳላቸው የሚናገሩት ዋጃኮያህ በመጪው ነሐሴ በሚካሄደው የኬንያ ምርጫ ከሚወዳደሩት አራት ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች መካከል እንደ እንግዳና ድንቅ ነገር በመታየት ቀልብን ስበዋል። የብዙዎችን ትኩረት ቢስቡም በምርጫው ያሸንፉ ይሆን? የሚለው ላይ የተሰበሰበው የሕዝብ አስተያየት ያንን አያሳይም። ከቀናት በፊት በወጣው የሕዝብ አስተያየት መሰረት 'ሩትስ' የተሰኘ ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩት ዋጃኮያህ፣ 4 በመቶ ድምፅ ብቻ እንደሚያገኙና በደረጃም ደካማ በሚባል ሁኔታ ሦስተኛ ላይ ነው የተቀመጡት። ነገር ግን የዘርፉ ባለሙያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዕጩ ተወዳዳሪ ለሆኑ ግለሰብ ጥሩ ደረጃ ላይ ናቸው ይላሉ። በተለይም ግንባር ቀደም ተፎካካሪዎቹ 43 በመቶ የተሰጣቸው የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ እና 39 በመቶ የተተነበየላቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ምንም አይነት ድምፅን ማጣት ባይፈልጉም ዋጃኮያህ የተወሰነውን መውሰድ እንደሚችሉ ተገምቷል። “ዋጃኮያህ ከዚህ ቀደም በርካቶች ሊስቁበት የሚችሉበትን ሃሳቦች አንስቶ እየሞገተ ነው ቅስቀሳ እያደረገ ያለው። ነገር ግን በከተማም ሆነ በገጠር የተናደዱ፣ ምጣኔ ሀብቱ ያጎሳቆላቸው ወጣቶችን ቀልብ መግዛት ችሏል። በተለያየ ብሔር፣ እምነትና ፓርቲ አባላት ወጣቶችም እየተሰማ ነው” በማለት በኬንያ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ዋና አምደኛ የሆነው ማቻሪያ ጋይቶ ጽፏል። በምርጫ ቅስቀሳ ጎዳናዎች ላይ በሚወጡበት ወቅት ሙሉ ሱፍ ኮትና ሱሪ ከማድረግ ይልቅ ቲሸርት፣ ኮፍያ፣ ስካርፍ፣ ጂንስ፣ ቱታ በማድረግ ነው። በዚህም በአገሪቱ የሰፈነው የሚወቅሱት እና የሚጠየፉት መጠነ ሰፊ ሙስና አካል አለመሆናቸውን ያሳያሉ። በተጨማሪም ዕጸ ፋርስ እንደሚያጨስ በማስመሰል በጣቶቻቸው ምልክት ያሳያሉ፤ በሬጌ ዘፈኖችም በሚጨፍሩበት ወቅት የተሰበሰበው ሕዝብም በደስታ ይዘላል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ የፕሬዝዳንቱን መንበር ካሸነፉ የኬንያ ሁለቱን ትላልቅ ችግሮች፣ ሥራ አጥነትን ለመፍታት እና ብሔራዊ ዕዳዋን ለማቃለል፣ ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ለህክምና አገልግሎት የሚውል የዕጸ ፋርስ ግብርና እና ምርቱን የሚቆጣጠር ሕግ እንደሚያወጡ ተናግረዋል። እሳቸው እንደሚሉት ይህ እርምጃ ኬንያን በዓመት ከዘጠኝ ትሪሊዮን ሽልንግ በላይ ወይም 76 ቢሊዮን ዶላር ያስገኝላታል፣ በዚህም መንግሥት እንደገና “አንድ ሳንቲም መበደር የለበትም\" ይላሉ። “የምዕራባውያን አገሮች ዕጸ ፋርስን (ማሪዋና) ሕጋዊ አድርገውታል። እኛስ ለምንድን ነው ሕጋዊ የማናደርገው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። ምንም እንኳን የሚሏቸውን ጉዳዮች በጥናት ባያስደግፉም ዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ለመድኃኒትነት ለመጠቀም ሕጋዊ ማድረግ የምርጫ ቅስቀሳቸው ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው። የአፍሪካ ቼክ ድረ ገፅ ዕቅዶቻቸውን አሳሳች ናቸው ሲል ገልጾታል። ሆኖም በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ መነጋገሪያ መሆናቸው ቀጥሏል፣ እንዲሁም በሥራ አጥነት ክፉኛ የተጎዱ የአገሪቱ ወጣቶችን ደስ አሰኝቷል። የፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ሃሳብ የሚሳካ ከሆነ ኬንያን ዓለም አቀፍ የዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እየሞከሩ ካሉት የአፍሪካ አገራት ከሌሶቶ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዛምቢያ እና ከዚምባብዌ ጋር ያሰልፋታል። የዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) በአንዳንድ ግምቶች መሰረት በአውሮፓውያኑ 2028፣ 70 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ማሪዋና አጭሰው እንደማያውቁ ቢናገሩም፣ ነገር ግን ኬንያ ዕጹን ሕጋዊ ካደረገችው ደስታቸውን ለመግለፅ ማሪዋና የሚያጨሱ የመጀመሪያው ሰው እንደሚሆኑ ተናግረዋል። “ዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) ሕጋዊ ከሆነ፣ ተቆጣጣሪ አካላትም የሚፈቅዱ ከሆነ ማጨሱ ምንም ችግር የለውም” ይላሉ። የፕሮፌሰር ዋጃኮያህ አስተያየት በኬንያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውግዘት ደርሶበታል። ቤተ ክርስቲያኗ ማሪዋና ሕጋዊ ከሆነ ወጣቶች የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚነታቸው ይባባሳል ስትል ወቅሳለች። “ቤተሰቦች የአደንዛዥ ዕጽ ስጋት ተደቅኖባዋል። ይህም ወደ መለያየት፣ ሁከት አልፎ አልፎም ለሞት ይዳርጋል” ሲሉ ጳጳስ ጄምስ ማሪያ ዋይናና አስጠንቅቀዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ በተጨማሪም በፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መንግሥት ለቻይና ኩባንያዎች የተሰጡ ውሎችን በሙሉ እንደገና እንደሚገመግሙም ቃል ገብተዋል። ኬንያ ካለባት የውጭቻ ዕዳ 21 በመቶውን ከቻይና የተወሰደ ሲሆን ይህም ብሔራዊ ቅሬታን አስከትሏል። በተለይም በአብዛኛው እንደ መንገድ እና ባቡር ያሉ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት አገራቱ የገቧቸው ውሎች ሲሆኑ፣ ለሕዝብ ይፋ አለማሆናቸው የዕጩው ፕሬዝዳንት የሚያነሱት ጥያቄ ነው ነው። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ የእባብ እርባታን እንደ ሌላው የኬንያ ምጣኔ ሀብት ዋና ምሰሶ አድርገው ይመለከቱታል። “ከወርቅ የበለጠ ውድ ነው” የሚሉትን የእባብ መርዝ፣ ለመድኃኒትነት የሚውል ፀረ-የእባብ መርዝ ለማምረት እንዲሁም የእባብ ሥጋን ደግሞ እንደ ጣፋጭ ምግብ ለሚቆጥሩት እንደ ቻይና ላሉ አገራት እንደሚላክ ይናገራሉ። “ምጣኔ ሀብቱን በተረጋጋ ሁኔታ ለማስቀጠል በየዓመቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊኖረን ይችላል” ይላሉ ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ። በተጨማሪም በቻይና ለመድኃኒትነት የሚያገለግለውን የጅብ የዘር ፍሬን ኬንያ ወደ ውጭ መላክ አለባት በማለት ከማሪዋና የበለጠ ገቢ እንደሚያስገኝ ያስረዳሉ። ይህ ንግግራቸው ከዱር እንስሳት ጥበቃ ቡድኖች እና ከኬንያ የእንስሳት ሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር በኩል ቁጣን አስከትሏል። “የጅብ ዘር ፍሬዎች እና እባቦች ንግድ የተከለከለ እና ለዱር ዝርያዎች ህልውና ስጋት ነው” ሲል የእንስሳት ማኅበር በመግለጫው አስታውቋል። የዕጩው ፕሬዝዳንት ዕቅድ “ለሌላ ወረርሽኝ ግብዓት ነው” ምክንያቱም ቫይረሶች፣ ባክቴሪያዎች እና ጥገኛ ተህዋሲያን ከጅብ እና ከእባቦች ወደ ሰው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲዛመቱ ሊያደርግ ይችላል ብሏል መግለጫው። ምንም እንኳን ተቺዎች ተወዳጅነትን ፍለጋ ነው በሚል የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን ቢያወግዙትም፣ የፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ደጋፊዎችና ወዳጆች ፈታኝ የሚባል የሕይወት ችግሮችን ድል በመንሳት ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር በመነሳታቸው ያደንቋቸዋል። ፕሮፌሰሩ ትውልዳቸው በምዕራብ ኬንያ ገጠር ሲሆን፣ ወላጆቻቸው መፋታታቸውን ተከትሎ ወደ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ ወጡ። የሃሬ ክሪሽና ቤተ ምኩራብ አገልጋዮች ቤት የተቸገሩና የሚበሉት የሌላቸውን እየመገቡ በነበረበትም ወቅት ነው ታዳጊውን ያገኙት። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ በቤተ ምኩራቡም መኖር ጀመሩ በኋላም የሃሬ ክሪሽና ካህን ሆኑ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁ ድጋፍ ተደረገላቸው። ከተመረቁ በኋላም የኬንያ ፖሊስን ተቀላቀሉ። በደረጃም ከፍ በማለት የደኅንነትና የስለላ ክፍሉን ተቀላቀሉ። ምንም እንኳን ለዝርዝር መረጃው ግልፅ ባይሆኑም ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ በአውሮፓውያኑ 1990 በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮበርት ኦኮ ግድያ ዙሪያ ምስጢራዊ መረጃ ካገኙ በኋላ ችግር እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ እንደታሰሩ እና እንደተሰቃዩ የተናገሩ ሲሆን፣ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ናይሮቢ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እርዳታ ከኬንያ መሰደዳቸውን አስረድተዋል። በአውሮፓውያኑ 2010 የፓርላማ አጣሪ ኮሚቴ ባደረገው ምርመራ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተገደሉት በፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ አንደኛው መኖሪያ ቤት መሆኑን ይፋ እስካደረገበት ድረስ የባለሥልጣኑ ግድያ ለሕዝብ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ኬንያን ጥለው ከወጡ በኋላ ወደ እንግሊዝ አመሩ። እዚያም ዝቅተኛ የሚባሉ ሥራዎችን እየሰሩ በለንደኑ ሶአስ ዩኒቨርሲቲ፣ በዋርዊክ ዩኒቨርሲቲ እና በዎልቨርሃምፕተን ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በዎልቨርሃምፕተን ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት ኑሮን ለማሸነፍ ሲሉ የጥበቃ ሠራተኛ፣ የመቃብር ቆፋሪ እና የሬሳ አጥቢ ሆነው ሰርተዋል። እነዚህ ሥራዎች “ትሁት እንዳደረጓቸውና ዕይታቸውንም እንዳሰፋላቸው” ለዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ተናግረዋል። በወቅቱም ለትምህርት እና ለሥራ የሚሆናቸውን ጊዜ አመጣጥኖ መሄድ ፈታኝ ነበር ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም ሳሉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለውጥ ለማምጣት በፖለቲካ ዘመቻዎች ውስጥ ተሳትፈዋል። በአውሮፓውያኑ 1981 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ይዘው እስከ 2000 ድረስ ጋናን ከመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጄሪ ራውሊንግስ ጋር በቅርበት ሰርተዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ መኖሪያቸውን ወደ አሜሪካ ካደረጉ በኋላም፣ አፍሪካ አሜሪካዊት ባለቤታቸውን ተዋወቁ። ጥንዶቹ ሦስት ልጆች እንዳሏቸው ተነግሯል። ከዋልደን ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ጨምሮ፣ በተለያዩ የአሜሪካ ተቋማትም ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በአጠቃላይ 17 ዲግሪዎች እንዳላቸው የሚናገሩ ሲሆን፣ ትምህርታቸውም ስደት፣ ዓለም አቀፍ እና የስደተኛ ሕግን ያካትታል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ወደ ኬንያ የተመለሱት በአውሮፖውያኑ 2010 ሲሆን፣ ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር። ሆኖም በወቅቱ የነበረውን ሃሳባቸውን የተውት ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ነሐሴ ወር ላይ በሚደረገው ምርጫም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ለመሆን ለየት ያሉ ሃሳቦችን እያነሱ መራጩን ሕዝቡ እየቀሰቀሱ ይገኛሉ። የፕሮፌሰሩ ሌላ አወዛጋቢ የምርጫ ቅስቀሳ ተስፋ የተባለው ሠራተኞች በሳምንት አራት ቀን ብቻ እንዲሰሩ በማድረግ የሥራ እና የሕይወት ሁኔታን እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ለሙስሊሞች አርብን፣ ቅዳሜ ለአድቬንቲስቶች እና ለሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ እሁድን የአምልኮ ቀናት እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ የሞት ቅጣትን ለመመለስ ቃል የገቡ ሲሆን  በሙስና የተከሰሱ ሰዎች “ኡጋሊ [የኬንያ ባህላዊ ምግብ] ከተመገቡ በኋላ” በጥይት ወይም በመሰቀል ሞትን መርጠው ቅጣቱ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።", "ቦሪስ ጆንሰን ከምርጫ ራሳቸውን በማግለላቸው በተፎካካሪያቸው ተሞገሱ ሪሺ ሱናክ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንን በይፋ አሞገሱ። ሙገሳው የመጣው ጆንሰን ለጠቅላይ ሚንስትርነት በድጋሚ እንደማይወዳደሩ ካስታወቁ በኋላ ነው። “ቦሪስ ጆንሰን ብሬግዚት እና የክትባት ስርጭት ላይ ስኬታማ ነበሩ” ሲሉ ሪሺ ሱናክ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። “ፈታኝ ከሆኑ ጊዜያቶች በአንዱ አገራችንን መርተዋል። ፑቲን በዩክሬን የጀመሩት አረመኔያዊ  ጦርነት ወቅትም ነበሩ። ለዚህም ሁሌም እናመሰግናቸዋለን።\" በቀጣይ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን የተሻለ ዕድል አላቸው የተባሉት ሪሺ ሱናክ “በድጋሚ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ፍላጎት ባይኖረውም በአገር ውስጥ እና በውጭ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አምናለሁ” ብለዋል። በተሾሙ በ45 ቀናት ስልጣን በቃኝ ያሉትን የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስን ለመተካት የሚደረገው ውድድር ቀነ ገደብ ተቃርቧል። ሪሺ ሱናክ የቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አጋሮችን ጨምሮ ከፓርቲያቸው 128 የፓርላማ አባላትን ድጋፍ በመሰብሰብ ውድድሩን እየመሩ ይገኛሉ ተብሎ ነበር። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በ53 የድምጽ ድጋፍ ሁለተኛ ሆነው እየተከተሉ ስለመሆናቸው ቢቢሲ መረጃ አግኝቷል። ሆኖም ደጋፊዎቻቸው ወደ ውድድሩ ለመግባት የሚያስፈልገው የድምፅ ድጋፍ እንዳላቸው በመጥቀስ 100 የፖርላማ አባላት የድጋፍ ድምጽ እንዳገኙ ይከራከራሉ። ቦሪስ ጆንሰን የህዝብ እንደራሴዎች ድጋፍ ቢኖረኝም “አሁን ይህንን የማድረጊያው ትክክለኛ ጊዜ አይደለም። በፓርላማ ውስጥ የተዋሃደ ፓርቲ ሳይኖር ማስተዳደር ይከብዳል” ብለዋል። እስከ 102 የሚደርሱ የሕዝብ እንደራሴዎች ድጋፍ እንዳላቸውም አስታውቀዋል። ቢቢሲ 57 የሕዝብ እንደራሴዎች እንደሚደግፏቸው በይፋ ቢያረጋግጡም የቀሪዎቹን ለማረጋገጥ አልቻለም። ፔኒ ሞርዳውንት ውድድሩ መቀላቀላቸውን በይፋ ያሳወቁ ብቸኛ እጩ ናቸው ነገር ግን በ23 የፓርላማ አባላት ድጋፍ ወደ ኋላ ቀርተዋል። የቢቢሲዋ ላውራ ኩንስስበርግ ቦሪስ ጆንሰን እና ሪሺ ሱናክ ቅዳሜ አመሻሹ ላይ ተገናኝተው እንደነበር  ገልጻ  ነገር ግን በውይይታቸው ላይ መግለጫ ይወጣ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበረችም። ቢቢሲ ድጋፍ የሰጡ የፓርላማ አባላትን መረጃ ሲሰበስብ ቆይቷል። ከ357 ወግ አጥባቂ የፓርላማ አባላት መካከል የ204ቱ የመምረጥ ፍላጎታቸው የሚታወቅ እና በቢቢሲ የተረጋገጠ ሲሆን የበርካቶች ፍላጎት ግን እስካሁን ግልጽ አልሆነም። ለውድድሩ በቂ ድጋፍ ለማግኘት እስከ ፊታችን ሰኞ  8 ሰዓት ድረስ ጊዜ አላቸው። በዚህም ለሚቀጥለው የውድድር ደረጃ ብቁ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። የፓርቲው የፓርላማ አባላት አንድ እጩን ብቻ የሚደግፉ ከሆነ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ዩናይትድ ኪንግደም አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኖራት ይችላል። ካልሆነ ግን የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ምርጫ በኦንላይን የሚያካሂዱ ሲሆን ውጤቱም በመጪው ሳምንት አርብ ይፋ ይሆናል። የምርጫ አስተያየቶች እንደሚያሳዩት በዚህ ኦንላይን ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከምርጫው ራሳቸውን ባያገሉ ኖሮ የአባላቱን ድምጽ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር።" ]
[ 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 2, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3 ]
[ "የዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ማልያ ሩስያን አስቆጣ የዩክሬን የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ማልያ ላይ በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትኘው ክሬሚያን ያካተተ ካርታ መካተቱን ተከትሎ ሞስኮ ቁጣዋን እየገለጸች ነው። ዩክሬን በዩሮ 2020 የምትጫወትበትን ማልያ ይፋ ያደረገች ሲሆን ማልያውም የከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት የሆነችው ክሬሚያን ያካተተ ነው። በማልያውም ላይ ‘ድል ለዩክሬን’ የሚል መልዕክት ተጸዕፏል። ሩሲያ በአውሮፓውያኑ 2014 ነበር የክሬሚያን አካባቢ ከዩክሬን ወስዳ የራሷ ያደረገችው። በዚህም ሩሲያ አካባቢውን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥረው ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግን እስካሁን እውቅና አልሰጠም። የዩክሬንን ብሄራዊ ቡድን መለያ በተመለከተ መልዕክት ያስተላለፉ አንድ የፓርላማ አባል ጉዳዩን ‘’ፖለቲካዊ ትንኮሳ’’ ነው ብለውታል። የዩክሬን እግር ኳስ ማህበር ኃላፊው አንድሬይ ፓቬልኮ ነበሩ ትናንት እሁድ ዕለት የብሄራዊ ቡድኑን መለያ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ያስተዋወቁት። የአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር ወይም ዩሮ 2020 ከቀናት በኋላ ይጀመራል። በቢጫው የብሄራዊ ቡድኑ መለያ ፊትለፊት ላይ በነጭ መስመር የአገሪቱን ክልል የተገለጸ ሲሆን ክሪሚያንም ያካተተ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በተገንጣይ ቡድኖች ቁጥጥር ስር የሚገኙት ዶኔስክ እና ሉጋንስክም ጭምር በማልያው ላይ እንዲካተቱ ተደርጓል። በማልያው ጀርባ ደግሞ ‘ድል ለዩክሬን’ የሚል መፈክር ሰፍሯል። ይህ መፈክር በአውሮፓውያኑ 2014 ሩሲያን የሚደግፉት ፕሬዝደንት ቪክቶር ያኑኮቪችን ከስልጣን ያስወገዱት ሰልፈኞች በተደጋጋሚ ይጠቀሙበት የነበረ ነው። ‘’ይህ የዩክሬን ሁኔታ ተጫዋቾቹ ጥንካሬ እንዲያገኙና ለሁሉም ዩክሬን እንዲጫወቱ እንደሚያደርግ እምነት አለን’’ ብለዋል የዩክሬን እግር ኳስ ማህበር ኃላፊው አንድሬይ ፓቬልኮ። ነገር ግን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የብሄራዊ ቡድኑን መለያ ተችተዋል። ‘’ብሄራዊ ቡድኑ የሩሲያ አካል የሆነችውን ክሪሚያን ማካተቱ ሊሆን የማይችልን ነገር እንደ ማሰብ ነው’’ ብለዋል። የተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዲሜትሪ ስቪሽኮቭ በበኩላቸው የብሄራዊ ቡድኑ መለያ ‘’ከነጭራሹ ተገቢ ያልሆነ’’ ነው ያሉ ሲሆን የየዑሮ 2020 አዘጋጆችና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። የዘንድሮው ዩሮ 20202 በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ 11 የአውሮፓ ከተሞች ከሰኔ 4 ጀምሮ ለአንድ ወር ይካሄዳል። ውድድሩን ከሚያስተናግዱት ከተሞች መካከል ደግሞ የሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ትገኝበታለች።", "የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ወቅት ወታደሮች ሚኒስትሮችን አግተው ነበር ተባለ የደቡብ አፍሪካ ግብረ ኃይል በኦፓርታይድ አገዛዝ ወቅት ላደረጉት ትግል ካሳ ይከፈለን በሚል የነፃነት ወቅት ወታደሮች ሁለት ሚኒስትሮችን አግተው እንደነበርና ነፃ መውጣታቸውንም አስታውቋል። ኤኤንሲ ከነጮች አፓርታይድ አገዛዛዝ ወቅት ነፃ ለመውጣት በሚደረገው ትግል ወታደራዊ ክንፍ አቋቁሞ የነበረ ሲሆን የዚህም ክንፍ አባላት ናቸው በአሁኑ ወቅት ለቤተሰቦቻቸው የመኖሪያ ቤት እና የህክምና መድን የሚሆን 280 ሺህ ዶላር የአንድ ጊዜ ክፍያ እየጠየቁ ያሉት። ትናንት ማምሻውን በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ በሚገኝ ሆቴል የካሳ ጥያቄያቸውን ለመደራደር የፕሬዚዳንት ሚኒስትሩ ሞንድሊ ጉንጉቤሌ ፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ታንዲ ሞዲሴ እና ምክትላቸው ታባንግ ማክዌትላ ተገናኝተው ነበር። ድርድሮቹ ፍሬ አለማፍራታቸውን ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናቱ ታግተው ነበር። በኋላ ላይ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ለመደራደር የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ የቀረ ሲሆን ከ50 በላይ ሰዎች ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ተዘግቧል። ሁኔታው ከመጋጋሉም ጋር ተያይዞ በፀረ-ሽብርተኝነት እና በታጋቾች ሁኔታዎች ውስጥ የሰለጠነው ልዩ ግብረ ኃይል መጠራት ነበረበት። ሚኒስትሩ ሞንድሊ ጉንጉቤሌ ድርጊቱ \"የማይታለፍ\" እና \"በሕግ ተቀባይነት የሌለው\" ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም እነዚህ የነፃነት ታጋዮች ች በጭካኔ የተሞላውን የአፓርታይድ መንግስት ለመዋጋት ላደረጉት አስተዋፅኦ ካሳ ስላልተከፈላቸው በኤኤንሲ መንግሥት እንደተከዱ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል። ነገር ግን፣ ወታደራዊ አርበኞቹ በየወሩ በመንግሥት የሚደገፍ ጡረታ ይሰጣቸዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይቡድኑ ከገዥው ፓርቲ ኤኤንሲ ዋና መሥሪያ ቤት ውጭ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ በማሰማታቸው ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገዋል።", "የደቡብ ሱዳን የውሃ ሚኒስትር ግብፅ ውስጥ ሕይወታቸው አለፈ የደቡብ ሱዳን ውሃ ሃብት እና መስኖ ሚኒስትር ማናዋ ፒተር ጋትኩት ጉአል በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉን የአገራቸው መንግሥት አስታወቀ። ሚኒስትሩ በደረታቸው አካባቢ የነበረው ህመም ጸንቶባቸው ባለፈው አርብ ወደ ግብፅ ለህክምና ተጉዘው እንደነበር የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ገልጸዋል። የታመሙት የውሃ ሚኒስትር ግብፅ ከደረሱ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ቀዶ ሕክምና የተረገላቸው ቢሆነም የዚያኑ ዕለት ማምሻውን ሕይወታቸው ማለፉን ነው ሪክ ማቻር የተናገሩት። “ማናዋ በዩኒቨርሲቲ በነበሩበት ጊዜ ጠንካራ የተማሪዎች መሪ ነበሩ። በሱዳንም የወጣቶች ንቅናቄ ላይ ጥሩ መሪ ነበሩ። ቆራጥ እና አገራዊ ፍቅር ያላቸው ነበሩ። በደቡብ ሱዳን ላይ ጠንካራ እምነት የነበራቸውም ሰው ነበሩ” ብለዋል ማቻር ለቤተቦቻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳለቫ ኪር በበኩላቸው የውሃ ሚኒስትሩን ሞት ሲሰሙ “ታላቅ ሐዘን” እንደተሰማቸው ገልጸዋል። የደቡብ ሱዳን ውሃ ሃብት እና መስኖ ሚኒስትር ማናዋ ከመንግሥታዊ ሥልጣናቸው ባሻገር የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ [ኤስፒኤልኤም - አይኦ] የተባለው ቡድን የፖለተካ ዘርፍ አባልም ነበሩ። የሚኒስትሩ አባት ፒተር ጋትኩት ጉአል በደቡብ ሱዳን ሰፊ እውቅና ያላቸው ፖለቲከኛ ነበሩ።", "'የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች' 11ኛው ክልል በመሆን ሊቋቋም ነው የኢትዮጵያ አስራ አንደኛው ክልል እንዲዋቀር የሚያስችል ድምጽ በቅርቡ ከተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ውጤት መገኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። መስከረም 20/2014 ዓ.ም ከተካሄደው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ጋር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን ለማወቀር በተሰጠው የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ መሠረት በአብላጫ ድምጽ ክልል የመሆን ድጋፍ አግኝቷል። በዚህም መሠረት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር በተለያየ የአወቃቀር ደረጃ ላይ የነበሩት የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የካፋ፣ የዳውሮ እና የሸካ ዞኖች በአንድነት የአገሪቱ አስራ አንደኛ ክልል ሆነው ይመሠረታሉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅዳሜ መስከረም 28/2014 ዓ.ም ከአንድ ሳምንት በፊት የተካሄደውን የሕዝበ ውሳኔ ውጤት ባሳወቀበት ውቅት እንደገለጸው፤ በሕዝበ ውሳኔው ላይ ድምጽ ለመስጠት ከ1.3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተመዝግበው 1.2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ድምጽ ሰጥተዋል። ድምጽ ከሰጡት መካከልም አምስቱ ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ከደቡብ ብሔር፣ ቤሔረሰብና ሕዝቦች ክልል ስር ወጥተው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመባል መዋቀራቸውን በመደገፍ 1ሚሊየን 221 ሺህ 92 ሰዎች ድምጽ ሰጥተዋል። በዚህም ከ50 በላይ ብሔረሰቦች ከሚገኙበት የደቡብ ክልል ከሁለት ዓመት በፊት በመውጣት በሕዝበ ውሳኔ የራሱን ክልል የመሠረተውን የሲዳማ ክልልን በመከተል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሁለተኛው ሲሆን የአገሪቱም 11ኛ ክልል ይሆናል። የሕዝበ ውሳኔው ውጤት ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርባና 11ኛው ክልል እንደሚዋቀር ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኙ በርካታ ዞኖች በክልልነት ለመዋቀር ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። ለረጅም ጊዜ በክልልነት የመዋቀር ጥያቄን ሲያነሳ የነበረው የሲዳማ ክልል በቀዳሚነት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ሕዝበ ውሳኔ ተዘጋጅቶለት ነበር ክልል ሆኖ ለመደራጀት የበቃው። በደቡብ ክልል ለቀረቡ ክልል የመሆን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፌደራል መንግሥቱና በክልሉ አማካይነት ጥናቶች መካሄዳቸው የተነገረ ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እንዲቋጭ ተደርጓል። ከዚህ ውጪ ያሉና ጥያቄ ያቀረቡ ዞኖች ጉዳይን በተመለከተ አስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም። የደቡብ ምዕራን ኢትዮጵያ ብሔሮች ክልል እንዲመሰረት በሕዝበ ውሳኔ አስፋለጊው ድምጽ በመገኘቱ ክልሉን ለማደራጀት የሚያስፈልጉ ሥራዎች በደቡብ ክልልና በዞኖቹ አማካይነት እንደሚከናወን ይጠበቃል።", "የካፒቶሉን ነውጥ ተከትሎ ኩባንያዎች ፖለቲካዊ የገንዘብ ልገሳቸውን ሰረዙ በባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን የተነሳውን ነውጥ ተከትሎ በአሜሪካ ምክር ቤት ያሉ ሪፐብሊካኖች ከአገሪቱ ኩባንያዎች ዘንድ ከፍተኛ ውግዘትን አትርፈዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው የአሜሪካ ኩባንያዎች ለምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያበረክቱት የነበረውንም ልገሳ እንሰርዛለን ብለዋል። በተለይም ጆ ባይደን እንዳይመረጡ ለማድረግ ልገሳ ያበረከቱት ኩባንያዎች ለምርጫ ቅስቀሳ ገንዘብ ከአሁን በኋላ አንለግስም ብለዋል። የፖለቲካ ልገሳዎችን ከሰረዙት ኩባንያዎች መካከል በሆቴል ዘርፉ ስመ ጥር የሆነው ማሪዮት፣ ሲቲ ባንክ እንዲሁም ስመ ገናናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል ይገኙበታል። የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶልን ሰብረው መግባታቸውን ተከትሎ ሌሎች ኩባንያዎችም እንዲሁ ስትራቴጂያቸውን እያጤኑት እንደሆነ ተናግረዋል። ተመራጩን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን የፕሬዚዳንትነት ማረጋገጫ ለማስቆም ባለመው በዚህ ነውጥ የአምስት ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል። በርካታ ቁጥር ያላቸው የአሜሪካ ኩባንያዎች ለሁለቱም ፓርቲ አባላት የሚሆን ልገሳ ማድረግ የተለመደ ነው። ሆኖም በቅርቡ የደረሰውን ነውጥ ተከትሎ ከህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት በመፈጠሩ እነዚህም ኩባንያዎች ልገሳቸውን እንደገና እንዲያጤኑት በር ከፍቶላቸዋል። በአካውንቲንጉ ዘርፍ የታወቀው ዴሎይቴ፣ የቴሌኮሙ ኤቲ ኤንድ ቲ እንዲሁም የክሬዲት ካርድ ኩባንያዎቹ አሜሪካን ኤክስፕረስና ማስተር ካርድ ማንኛውንም አይነት ልገሳ ለጊዜው አንሰጥም ብለዋል። \"ፖሊሲያችን እንዲህ አይነት የጥላቻ ቡድኖችን አባልነት አይቀበልም፤ ስለዚህ እነዚህን ግለሰቦች አባል መሆናቸውን ካወቅን እናግዳቸዋለን\" በማለትም በአለም አቀፍ ዘንድ ግለሰቦች ቤቶቻቸውን እንዲያከራዩ የሚያስችለው ኤይርቢኤንቢ የተባለው ኩባንያ አስታውቋል። ኩባንያው የ ጆ ባይደንን የመጪው ፕሬዚዳንትነት ማረጋገጫን የተቃወሙትን በሙሉ ምንም አይነት ድጋፍ አልሰጥም በማለትም አስታውቋል። የሰላምታ ካርዶች አምራች ሆልማርክ በበኩሉ የጆ ባይደንን ፕሬዚዳንትንት ተቃውመዋል ያላቸውን ሁለት የሪፐብሊካን ሴናተሮች የሰጣቸውን ልገሳ እንዲመልሱ ጠይቋል። ኩባንያው በካንሰስ ዋነኛ የሚባልም ቀጣሪ ነው። የኬሚካል ንጥረ ነገሮች አምራቹ ዶውም ከሌሎች ኩባንያዎች በተለየ መልኩ ለሪፐብሪካኖች የምክር ቤት አባላት በስልጣን ባሉበት አመታት ሁሉ ማንኛውም የገንዘብ ልገሳ አላድርግም ብሏል። የአንዳንዶቹ ኩባንያዎች የገንዘብ እገዳ እስከተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ሲሆን ከነዚህም መካከከል ጄኔራል ኤሌክትሪክ እስከ አውሮፓውያኑ 2022 ይዘልቃል ብሏል።", "\"ሕዝብን ከማገልገል በላይ ክብር የለም\"- አዲሱ የባህርዳር ምክትል ከንቲባ በትናንትናው ዕለት፣ ጥቅምት 6፣ 2013 ዓ.ም ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል። የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በስራ አመራርና ፍልስፍና ቻይና አገር ከሚገኘው ኋጁንግ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ አጠናቀው የመጡት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የምሁራን ተሳትፎና አደረጃጀት ዘርፍ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማካሪ፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ፣ የሕዝብ ግንኙነትና የከተማ አደረጃት አማካሪና በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ምክትል አስተዳደሪና ግብርና ጽኅፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ካገለገሉባቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በመልክዓምድርና አካባቢ ጥናት ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲና ሁለተኛ ዲግሪ በመልካም አስተዳደርና በአመራር ጥበብ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በተለያዩ የአመራር ቦታዎችም ላይ ሆነው አገልግለዋል። በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነታቸውን ሹመት፣ ሊያከናውኗቸው ያሰቧቸውን እቅዶችና ሌሎች ጉዳዮች በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፦ በትናንትናው ዕለት ሹመቱን ሲቀበሉ ምን እሰራለሁ? ምን ለውጥ አመጣለሁ ብለው ነው ሹመቱን የተቀበሉት? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደርን በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነት እንድመራ የድርጅትና የመንግሥት ኃላፊነት ሲሾመኝ፣ አንደኛ ይሄ ተልእኮ ነው። የፓርቲው አባል ነኝ፤ ከፓርቲዬ የተሰጠኝን ተልዕኮ መቀበል የግድ ስለሚል ይህንን የተሰጠኝን ተልዕኮ ተረክቤ ከዚህ በፊት በግንባር ላይ እየሰሩ ካሉ አመራሮች ጋር በመካከር፤ በቀጣይ ባህር ዳር የኢንቨስትመንት መዳረሻ፣ ኢንዱስትሪ የተስፋፋባት፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ፍትሃዊነት የተረጋገጠባት እና የሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ ስራዎችን ህዝብ ጋር በመካከር ለመስራት ነው። የባህር ዳር ከተማ እንድታድግ እንድትበለፅግ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍላጎት ነው። እኔም ይህንን ኃላፊነት የከተማዋን ነዋሪ ፍላጎት ለማሳካት በበኩሌ የሚጠበቅብኝን አስተዋፅኦ ለማበርከት ነው። በቀጣይ አመራሩ ጋር ተነጋግረን፤ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሂደን ከዚህ በፊት የተጀመሩ ስራዎችን፣ የታቀዱ እቅዶችንና ጅምሮችን ለማስቀጠል እናስባለን። በአዳዲስ የከተማ አስተዳደር ስርአቱን ዘመኑ በሚጠይቀው ልክ ለማዘመን አቅሜ የፈቀደውን ያህል የተጣለብኝን አደራና ለመወጣት ዝግጁነት የያዝኩ ብቻ መሆኔን ነው የማረጋግጠው በዚህ ሰዓት። ምክንያቱም አሁን ገና ወደ ስራ እየገባሁ ነው። ከዚህ በፊት ይሄ ስራ እንደሚሰጠኝ ባለማወቄ እንዲሁም ይሄ ተልእኮ በመሆኑም ጊዜ ወስጄ ችግሮችን ለይቼ ከአመራሩ እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ ተወያይተን የከተማዋን አጠቃላይ እድገት አንድ ደረጃ ወደፊት የሚያራምድ የአመራር ስርአት ለመዘርጋት ነው በግሌ ለማድረግ ያሰብኩት። ቢቢሲ፡ በተለያየ የስራ ኃላፊነት ከመስራትዎ አንፃር እንዲሁም ከተማዋን ያውቁታል ብዬ ከማሰብም ከዚህ በፊት በነበሩ ሂደቶች ምን ክፍተት አዩ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ከዚህ በፊት የሰራሁባቸው የአመራር ተልእኮዎች በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ውስጥ አይደለም። በምእራብና ምስራቅ ጎጃም የሚባሉ ዞኖች ነው ሳገለግል የቆየሁት፤ በመሃልም የውጭ የትምህርት እድል አግኝቼ ትምህርቴንም ተከታትዬ ነው የተመለስኩት። አሁን ገና ትምህርቴን አጠናቅቄ ከምረቃ በኋላ የተሰጠኝ አዲስ የስራ ስምሪት ነው። በአሁኑ ወቅት ባህርዳር ከተማ ላይ እንዲህ አይነት ጉድለቶች አሉ ብሎ ለመናገር ግምገማ ያላካሄድኩበት በመሆኔ ገና የተሰጠኝን ተልዕኮ ተቀብዬ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነኝ። ክፍተቶቹን ወይም ጠንካራ ጎኖች እነዚህ ናቸው ብዬ አሁን ባለሁበት ሰዓት ላይ ልናገር አልችልም። ምክንያቱም ገና ያልተገመገመ ነገር ይዤ በዚህ ላይ አስተያየት መስጠት ይከብደኛል። ቢቢሲ፡ የድህረ ምረቃዎን ትምህርት የተከታተሉት በቻይና ነው። የተለያዩ የቻይና ከተሞችን ለማየት እድል አግኝተው ከሆነ ከዛ የቀዱት ነገር አለ ወደዚህ ባመጣው ብለው ያሰቡት? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ቻይና የደረሰችበት የከተማ ልማት እና የኛ አገር ምንም እንኳን ለማወዳደር ልዩነቱ የሰፋ ነው። እዚያ ያየሁዋቸውን አንዳንድ ነገሮች በተለይም የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ፤ የዘመናዊና ቀልጣፋ የአሰራር ስርአት ከመዘርጋት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የአገልግሎት አቅርቦት ላይ የተሻለ ነገር አይቻለሁ። አቅም በፈቀደ መጠን ከኛ አገር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ስርአት ጋር የተገናዘበ የከተማ ስርአት አገልግሎት አቅርቦት ለማድረግ የዩኒቨርስቲ ምሁራንን እንዲሁም በዘርፉ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን በማማከር አሰራርን ለማዘመን ጥረት ማድረግ የሚገባ መሆኑ ይሰማኛል። እዚህ ላይም አቅሜ የፈቀደውን አስተዋፅኦ ለማድረግ ጥረት አደርጋለሁ ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፡ ምክትል ከንቲባ ሆነው በትናንትናው ዕለት ተሾመዋል። በስልጣን ላይ ሆኜ እሰራለሁ ብለው ቅድሚያ የሚሰጧቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ በትናንትናው ዕለት ቃለ መሃላ ከፈፀምኩ በኋላ ለምክር ቤቱ ያቀረብኩት የመክፈቻ ንግግር ነበር። ከአመራሩም ሆነ ህብረተሰቡን በማሰለፍ ብንረባረብባቸው አጠቃላይ የከተማይቱን እድገት ያፋጥናል ብዬ የማምንባቸውን አቅጣጫዎች አቅም በፈቀደ መጠን ለማስቀመጥ ሞክሬያለሁ። ከነዚህም መካከልም በተለይ በከተማ የመጀመሪያው ስራ- ኢትዮጵያ በሽግግር ላይ ያለች አገር ናት። ፖለቲካዊ ለውጦች እያካሄደችም ትገኛለች። አሁን ያለው ፓርቲ ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና የተሸጋገረበት፣ አመራሩ ከላይ እስከ ታች በአዲስ እየተደራጀና እየተጠናከረ ያለበት፣ አዳዲስ አስተሳሰቦች ወደ መንግሥት አሰራር የገቡበት ማግስት ላይ ነው ወደ ስራ እየገባሁ ያለሁት። ከዚህ ጋር የተጣጣመ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን አስቀምጫለሁ። ከነዚህም መካከል በተለይም የከተማው አስተዳደር ውስጥ የህግ የበላይነትን ማስፈን፣ ሰላምን ማረጋገጥ የመልካም አስተዳደሮችን ለይቶ በህዝቡ ተሳትፎ መፍታት የሚሉት ይገኙበታል። የከተማዋ ያላትን ስመ ገናናነትና የከተማዋ እድገትን ሊመጥን የሚችል የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ስራ ላይ በተለይም የእንጨት ልማት ፕሮጀክቶች ላይ አተኩረን የእለት ተግባራችን አድርገን መንቀሳቀስ ይገባል። የከተማውን የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግር፣ ከዚህም የዘለሉ ሌሎች ተደራራቢ ጥያቄዎችን የህዝብ መድረኮች እየፈጠርን በመልቀም እንደ መንግሥት አቅም መፈታት የሚገባቸውን ቅድሚያ እየሰጠን እንሰራለን የሚሉ አቅጣጫዎች ነው ለማስቀመጥ የተሞከረው። በተለይም የወጣቱን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ የስራ እድል መስኮችን በመፍጠር ላይ ያተኮረ ስራ እንሰራለን። የስራ እድል ፈጠራ ለሰፊው ህዝብ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው ይሄ ከተማ ላይ ያለ የድህነት ቅነሳ አካል ነው። እነኚህ ጉዳዮች መልክ ከያዙ ከተማዋ ወደተሻለ ህይወት ውስጥ የምንገባበት አጋጣሚ ስለሚኖር እነዚህ ላይ አተኩረን ብንሰራ የሚል እሳቤ ይዤ ነው ወደ ስራ እየገባሁ ያለሁት። እንግዲህ ቀጣዩን ከእግዚአብሔር ጋር ከህብረተሰቡ፣ ከቅርብ አመራር ጋር በመሆን የምንችለውን ሁሉ በቅንነት ግልፅ (ትራንስፓረንት) በሆነ መንገድ፣ ህዝቡን አሳታፊ በሆነ መንገድ የከተማ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎቱ አለኝ። ያው ውጤቱን የምናየው ይሆናል። ቢቢሲ፡ የጠቀሷቸውን ተግባሮች ለማከናወን ምን አይነት ተግዳሮት ይገጥመኛል ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ በባለፉት ሶስት አመታትና ከዚያ በላይ ከአመራር ስርአት ውጭ ብሆንም በተለምዶ የሚታወቁ የከተማ ስራን ለመስራት የሚገዳደሩ ችግሮች አሉ። እኛንም ትንሽ ይፈትነናል ብለን የምናስበው ከተማ የተለያዩ ፍላጎቶች አሉት። ግማሹ ህጋዊ በሆነ መንገድ ከተማ እንዲለማ የመፈለግ፤ ግማሹ ደግሞ በህገወጥ ወይም በአቋራጭ መንገድ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተቃራኒ ፍላጎቶች የሚሳተፉበት መድረክ ነው። ፖለቲካዊ ፍላጎቱ ብዙና የተለያዬ የሆነበትና ሌሎች እንዲሁም ውስብስብ ችግሮች ያሉበት ነው- የከተማ ስራ። ስለዚህ እነዚህን ችግሮች አጣጥሞ ለመምራት የሚያስችል ብቁና ቅቡልነት ያለው በስነ ምግባር የታነፀ አመራር የመፍጠር፣ የማሰማራትና ከህብረተሰቡ ጋር አዋህዶ የማሰራት ሂደት ፈታኝ ሊሆን ይችላል። እዚህ ላይ እኛም አተኩረን እንረባረባለን። ነገር ግን የሰው ልጅ ፍላጎት የተወሰነ ባለመሆኑ ህጋዊ ስርአት ተከትሎ በሚሰራበት ጊዜ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሊነኩ ይችላሉ። በዚያን ጊዜ ማማረር ሊከሰት ይችላል።እኛ እነዚህን አስቀድመን ስለምናውቅ በተቻለ መጠን ከአመራሩ ጋር ተነጋግረን የሁሉንም ዜጎች ፍላጎት አጣጥሞ ከህግና ስርአት ውጭ ሳይሆን ከተማዋን በከተማ እቅድ (ፕላን) ማስተዳደር። በዚያም መሰረት እንድትመራ የማድረግ ስራ እንሰራለን። እንግዲህ እዚህ ላይ ህብረተሰቡም ያግዘናል ብዬ ተስፋ የማደርገው ህጋዊነትን ብቻ ተከትለን ስንሰራ ከጎናችን የሚሆን ከሆነ ለውጥ እናመጣለን። ነገር ግን በመሃል አንዳንድ መንጠባጠቦች፤ ከዚህ ባፈነገጠ መንገድ መጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎች ትንሽ ያስቸግሩን ይሆናል፤ በውይይት እየፈታን እንሄዳለን። እንሻገራለዋን የሚል ተስፋ እንዲሁም እምነት አለኝ። በመወያየት የማይፈታ ችግር የለም ተብሎ ስለሚታሰብ ዋናው ነገር አመራሩንም ህዝቡንም ያሳተፈ የአመራር ዘይቤን መከተል፤ እነዚህን ተግዳሮቶች እናልፋቸዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከዚህ በዘለለ በስራ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች ይኖራሉ እንደዬ አፈጣጠራቸውና እንደ አመጣጣቸው እንመልሳለን ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፡ባህርዳር ከተማን የተለያየ ከንቲባዎች መርተዋታል፤ ባለን መረጃ ቶሎ ቶሎ የመቃየየር ሁኔታም አለ። ከዚህ ቀደም የነበሩት ከንቲባ በውበት፣ በፅዳት ጋር ተያይዞም ይወደሳሉ። እርስዎስ በየትኛው በኩል እወደሳለሁ ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ከዚህ በፊት የነበሩ ከንቲባዎች ባህርዳር ዛሬ ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ የየበኩላቸውን አሻራ ጥለው አልፈዋል። በርካታ ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ከተማዋን ወደፊት ያራመዱ ተግባራትን ፈፅመዋል። ይሄም የሚያስመሰግናቸው ነው። በዚያኑ ልክ ግን የሰው ልጅ ወደ ስራ በሚሰማራበት ወቅት ጥንካሬዎች እንዳሉ ድክመቶችም ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ መከተል የምንፈልገው እነሱ ሰርተውት በሄዱት ላይ ተጨማሪ ስራ እየሰራን ጥሩውን እያስቀጠልን ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መቀጠል። ድክመት ነበሩ ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ደግመው እንዳይፈፀሙ እያስተካከልን ነው ለመሄድ ያሰብነው። በቅርብ ከለቀቁት ከንቲባ ጋር ተያይዞ በርካታ ተስፋ ሰጭ ብዙ ደስ ደስ የሚሉ ስራዎችን ጀምረው የሄዱ መስሎ ነው የሚሰማኝ። እርሳቸው የጀመሯቸውን በጎ ተግባራት አጠናክረን እንቀጥላለን። ከዚህ ውጭ ደግሞ ክፍተት በምንላቸው ነገሮችን እንሞላለን። እሱ በምን ይሳካልዎታል ለሚለው? እሱን በቀጣይ በተግባር ብናየው ይሻላል። ምክንያቱም አሁን ወደ ስራ ባልተገባበት ሰዓት ላይ በዚህ ስራ የተሳካልኝ እሆናለሁ ማለት የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ ሳላይ፣ ገምግሜ ክፍተቱን በጥሩ ሁኔታ ለይቼ ባልገባሁበት ወቅት ላይ ይሄ ውጤታማ ያደርገኛል፣ አያደርገኝም ብሎ ለመናገር የሚያስቸግረኝ ይመስለኛል። ቢቢሲ፦ ሹመቱ ያልጠበቁት ይመስላል። በርግጥ እሾማለሁ ብለው ላያስቡ ይችላሉ። ለዚህ ሹመት የሚታጩ ሰዎች አካባቢውን በደንብ የሚረዳ ፣ ከተማውን በደንብ የሚያውቅ፣ ክፍተት ሊሞላ የሚችል፣ ጎዶሎውን ሊያውቅ ይችላል ተብሎ የሚታሰብ ሰው ነው ብዬ አስባለሁ…. ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ልክ ነው፤ ሹመት በሚሰጥበት ጊዜ በበለጠ አካባቢውን የሚያውቅ ሰው ቢሆን ይመረጣል። አካባቢውን በማወቅ ብዙ ችግር ያለብኝ አይመስለኝም። ከዚህ በፊት ባህርዳር ላይ የተወሰነ ጊዜ ሰርቻለሁ። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ እንዲሁም አሁን ካለው አመራር ጋር በመቀናጀት በአመራርነት ብዙ ጊዜ ስላሳለፍኩኝ መረጃዎቹም አሉኝ። እውነት ለመናገር እሾማለሁ ብዬ አልጠበቅኩም። እኔ ትምህርቴን ጨርሸ ስመጣ፤ በድርጅታችን አሰራር መሰረት የፖለቲካ ሹመት የሚሰጠው ተነግሮ አይደለም። የትምህርት እድል ተሰጥቶኝ ተምሬ ስመጣ አመራር ቦታ ላይ እንደምመደብ አውቃለሁ፤ የትኛው ቦታ እንደሆነ የሚወስነው የፓርቲው ፅህፈት ቤት ነው። አንድ ሰው ካለው የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ባህርይና ሌሎችም ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ገብተው ነው ሹመት የሚሰጠው። እንግዲህ ፓርቲው በዚህ ቦታ ላይ ሲመድበኝ ለዚህ ስራ ይመጥናል የሚል እምነት ይዟል ማለት ነው። እኔ ግን እንደ አንድ አመራርና አባል የተሰጠኝን ተልእኮ ስፈፅም ቆይቼ፣ ትምህርቴን አጠናቅቄ መምጣቴንና ሌላ ተጨማሪ ተልዕኮ ፓርቲዬ እንዲሰጠኝ እየጠበቅኩ ስለነበር የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ሆኜ እሾማለሁ ብዬ አልጠበቅኩም። ይሄ ተልእኮ ሲሰጠኝ ግን ህዝቡን ከማገልገል በላይ ሌላ ክብር ስለሌለ ፤ ህዝብን ማገልገል ኩራት ስለሆነ፤ ከዚህም በላይ ኃላፊነት ስለሌለ ከታመነብኝና ይህንን ስራ ይሰራል ብሎ ሹመቱን የሰጠኝ አካል አለ። ምክር ቤቱም ይህንን የቤት ሰራ ወስዶ ተቀብሎ ካፀደቀው በኔ በኩል ባገለግል ምንም ችግር የለውም። የተማርኩትም ህዝቡን ለማገልገል ነው። ቢቢሲ፡ ነፃ ሆኜ እስራለሁ፤ ነፃ ሆኜ ያሰብኳቸውን ነገሮች አሳካለሁ ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ፈተናዎች ይኖራሉ። ይሄ ግልፅ ነገር ነው። ከተማ ላይ ብዙ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አሉ። ያንን ሁሉ ፍላጎት ለሟሟላት ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቄ አውቃለሁ። ነገር ግን አቅም በፈቀደ መጠን ህሊናዬ የሚገፋኝን ለመስራት ዝግጁ ነኝ። ከዚህ በፊትም የአመራር ህይወቴ ልምዱም ስላለኝ የምችለውን ሁሉ ለመስራት እሞክራለሁ። የፓርቲ አመራሮችም ድጋፍ እንደሚያደርጉልኝም ሙሉ ቃል ገብተውልኛል። በተቻለ መጠን ህሊናዬ የሚያምንበትን ነገር ለመስራት እንቅስቃሴ አደርጋለሁ፤ እታገላለሁ። ከአቅም በላይ ሲሆን ደግሞ ብዙ አማራጮች አሉ ማለት ነው። ግን እኔ ከአቅም በላይ የሚሆን ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብም። በአሁኑ ሰዓት ፓርቲውም ሆነ መንግሥት የሚፈልገው የህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት ነው። የህብረተሰቡን ፍላጎት ተረድተን በምንቀሳቀስበት ወቅት የሚመጣውን እንቅፋት የሚታገል በርካታ ኃይል ከጎን አለ።ይህንን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የምሞክረው ይሆናል ማለት ነው። ቢቢሲ፡ ነፃ ሆነው እንዳይሰሩ ችግር ሊገጥምዎት ይችላል በስራ አጋጣሚ የሚገጥም ነው። እነዚህ ችግሮች ከየት በኩል ይመጣል ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ወደ ስራ ሳይገባ እንደዚህ አይነት ትንበያዎች (ፕሪዲክሽን) መስጠት ያሳስታል (ሚስሊድ ያደርጋል)። ምክንያቱም እኔ ዛሬ ተንብዬ ከዚህ አካባቢ ችግር ይመጣብኛል ብዬ ብናገር፤ ይመጣብኛል ብለሽ የምታስቢውን አካባቢ ማሳሰብም ስለሚሆን ወደ ስራ ገብቶ በተግባር ላይ የሚገጥም ችግርን ፊት ለፊት መጋፈጥ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ይመስለኛል። ችግር የሌለው ስራ የለም። ህዝብን መምራት ትልቅ ከባድ እና አስቸጋሪ ነው። እያንዳንዱ አመራር ይህንን አውቆ ነው የሚገባው ። ምንጊዜም ወደ ስራ ስንገባ ችግሮች እንደሚኖሩ አውቃለሁ። እንደየአመጣጣቸው ለመመለስ ራሴን አዘጋጅቻለሁ።", "በሄይቲ ፕሬዝደንት ግድያ 'ዋነኛው' የተባለ ተጠርጣሪ ተያዘ ባለፈው ሳምንት በፕሬዝደንት ጆቨኔል ሞይዝ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በማቀናጀት ቁልፍ ተጠርጣሪ ነው ብሎ ያመነውን ዶክተር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሄይቲ ፖሊስ ገለጸ። የ63 ዓመቱ የሄይቲ ተወላጅ ክርስቲያን ኢማኑኤል ሳኖን ሰኔ መጀመሪያ ላይ \"በፖለቲካዊ ዓላማዎች\" ምክንያት በግል አውሮፕላን ወደ ሄይቲ መብረሩን ይናገራሉ። የ53 ዓመቱ ሞይዝ ሐምሌ 7 መኖሪያ ቤታቸው በ 28 የውጭ ቅጥረኞች መገደላቸውን ፖሊስ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር። ቀዳሚ እመቤቷ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለህክምና ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። ማርቲን ሞይዝ ነፍሰ ገዳዮች እኩለ ሌሊት ወደ ቤታቸው ከገቡ በኋላ ባለቤታቸውን በጥይት \"የመቱበትን\" ቅጽበት ገልጸዋል። ጥቃቱ በፍጥነት በመከናወኑ ባለቤታቸው ጆቨኔል \"አንዲትም ቃል ለመናገር\" አልቻሉም ብለዋል። የተልዕኮ ለውጥ ሳኖን መያዙ የተዘገበው እሁድ አመሻሽ ላይ በዋና ከተማው ፖርቶ ፕሪንስ በፖሊስ በሰጠው መግለጫ ነው። የሄይቲ የፖሊስ አዛዥ ሊዮን ቻርለስ \"ይህ ለፖለቲካ ዓላማ በግል አውሮፕላን ሄይቲ የገባ ግለሰብ ነው\" ብለዋል። የመጀመሪያ ዕቅዱ ፕሬዝዳንት ሞይዝን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቢሆንም \"ተልዕኮው በኋላ ላይ ተቀይሯል\" ብለዋል። ስለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ግን አልሰጡም። \"ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ እኛ ፖሊሶች የእነዚህን ሽፍቶች እንቅስቃሴ በገታንበት ጊዜ ከጥቃት አድራሾቹ አንዱ ለክርስቲያን አማኑኤል ሳኖን ነው የደወለው\" ብለዋል ቻርለስ። \"የፕሬዚዳንት ጆቨኔል ሞይዝ የግድያ አቀናባሪዎች ናቸው የምንላቸውን ሌሎች ሁለት ሰዎችም አነጋግሯል።\" የፖሊስ አዛዡ ሌሎች ሁለት ሰዎች እንማን እንደሆኑ አልተናገሩም። የአሜሪካ ድጋፍ የሃገሪቱን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም እሑድ ዕለት የአሜሪካ ከፍተኛ የደህንነት እና የፍትህ ባለስልጣናት ልዑክ ሄይቲ ገብቷል። ቡድኑ ሦስት የሄይቲ ፖለቲከኞችንም አግኝቶ ያነጋግራል። ሦስቱም የአገሪቱ ህጋዊ መሪ ነን እያሉ ነው። ከጥቃቱ በኋላ የሄይቲ ባለሥልጣናት ቁልፍ የመሠረተ ልማት አውታሮችን ለመጠበቅ አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ወታደሮችን እንዲልኩ ጠይቀዋል። የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጥያቄውን በመጀመሪያ ውድቅ ቢያደርገውም አሁን ግን ሁኔታውን በጥልቀት ለመመርመር ወስኗል። ጆቨኔል ሞይዝ እአአ ከ2017 ጀምሮ በአሜሪካ በጣም ድሃ የሆነችውን ሄይቲን ሲመሩ ቆይተዋል። በስልጣን ዘመናቸውም በሙስና ክስ ሲመሰረትባቸው ቆይቶ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይም በዋና ከተማው እና በሌሎች ከተሞች ሰፊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። የፓርላማ ምርጫ ጥቅምት 2019 መካሄድ የነበረበት ቢሆንም አለመግባባቶች ተከስተው ምርጫ ሳይካሄድ ቆይተዋል። በዚህም ጆቨኔል ሞይዝ በአዋጅ ሃገሪቱን እያስተዳደሩ ነበር ማለት ነው። በቀረቡ የሕገ-መንግስት ለውጦች በመጪው መስከረም ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ታቅዶ ነበር። ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን ጥቃት ማን እና ለምን ዓላማ እንደደረሰ አሁንም ድረስ ግልፅ አይደለም። ገዳዮች ናቸው የተባሉት እንዴት ወደ ግቢው ለመግባት ቻሉ የሚለውን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎች እስካሁን አልተመለሱም። ሄይቲን ማን እየመራት ነው? ህገ-መንግስቱ ብሔራዊው ምክር ቤት ሌላ ፕሬዝዳንት መምረጥ አለበት ይላል። 2019 ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ ባለመካሄዱ ጆቨኔል ሞይዝ በአዋጅ እየመሩ ነበር። ሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ባይኖረውም በሕገ-መንግስቱ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦታውን መረከብ እንዳለባቸው ይጠቁማል። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ክላውድ ጆሴፍ እና አዲሱ ተሿሚው ኤሪየል ሄነሪ ስልጣኑ ይገባናል እያሉ ነው። አርብ ዕለት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድን ሄንሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ እና አዲሱን ፕሬዝደንት ደግሞ ጆሴፍ ላምበርት እንዲሆኑ በማወጅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተፈራርመዋል። የመፍትሔ ሃሳቡ አገሪቱ ለረጅም ጊዜ ሲያምሳት የኖረውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ለመፍታት እምብዛም እየሠራ አይደለም።", "አዲስ የተመሰረተው የተቃዋሚዎች ጥምረት እና የመንግሥት አስተያየት የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች ጥምረት በሚል በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ለመተካት በሚል ዘጠኝ የፖለቲካ ቡድኖች ዋሽንግተን አንድ ጥምረት መመስረታቸውን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ፣ ጥምረቱ ይህ ነው የሚባል የፖለቲካ መሰረት የሌለው ደካማ ስብስብ ነው ሲል አጣጥለውታል። በጥምረቱ ውስጥ ትብብር ለመፈጠር ከፈረሙት መካከል ህወሓት፣ የኦሮሞ ነጻነት ጦር፣ የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ይገኙበታል። ይህም ጥምረት በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት የመመሥረት ዓላማ እንዳለው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይ ኦዳ ታርቢ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህ አዲስ የተመሰረተው ጥምረት በትናንትናው ዕለት በዋሺንግተን የፊርማ ስነስርዓት ሲያካሂድ፣ የሕወሓት አማፂያንን በመወከል የተገኙት አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትን በኃይል አልያም በድርድር በማስወገድ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል። የአዲሱን ስብስብ መመስረት ያጣጣለው የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ፣ ከበደ ዴሲሳ፣ ከቢቢሲ ኒውስ አወር ጋር በነበራቸው ቆይታ \"ደካማ የፖለቲካ ኃይል ነው\" በማለት ገልጸውታል። በተጨማሪም ሚኒስትር ዲኤታው በዚህ ጥምረት መመስረት \"አለመደነቃቸውን\" አመልከተዋል፤ ጥምረቱ በአገሪቱ ውስጥ ይህ ነው የሚባል ድጋፍ የሌለው ነው ብለዋል። \"እነዚህ አማጺያን ቡድኖች መሠረት የላቸውም። ምንም አይነት ማኅበራዊ መሠረት የላቸውም፤ ምንም ለውጥ ሳያመጡ ላለፉት 40 ዓመታት እዚያው የቆዩ ናቸው።\" አቶ ከበደ ዴሲሳ ጨምረውም \"በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት በሚያስፈልግበት ጊዜ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች መንግሥት ተዳክሟል፣ ሥልጣን ላይ መቆየት አይችልም ብለው ሲያስቡ ተሰባስበው ትብብር ይፈጥራሉ\" በማለት ሁኔታው የተለመደ መሆኑንም ተናግረዋል። የጥምረቱ አባላት ይህንን ስብስብ የፈጠሩት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየተባባሰ ባለበት ወቅት ሲሆን፤ ወደፊት በአገሪቱ ይመጣል ብለው ለሚያስቡት የሽግግር መንግሥት እና ጊዜያዊ መንግሥት የመጀመሪያ ሂደት ነው ብለዋል። ይህ ጥምረት በውስጡ ዘጠኝ ቡድኖችን ያካተተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ጋምቤላ፣ ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሊ፣ ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ ቅማንት፣ አገውን የፖለቲካ ቡድኖች ይወክላል ተብሏል። ስብስቡ እነዚህን ቡድኖች ብቻ በመያዝ የሚቀጥል አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሌሎችም ቡድኖች እንደሚቀላቀሏቸውና ውይይትም እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተዋል። ጥምረቱ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስ የሆኑ ኃይሎች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አሁን ያለውን የአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሰረት ባደረገው የፌደራሊዝም ሥርዓት ለመቀጠል መስማማታቸው ተነግሯል። \"በረዥም ጊዜ ሂደትም ሁላችንም የምናስበው ኮንፌደራሊስት ወደሆነ ሥርዓት መሻገር ነው። እዚያ ላይ ተስማምተናል\" ብለዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አንድ ዓመት በቆየ ጦርነት ውስጥ የሚገኘው ህወሓት፣ ከዚህ በፊት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር በትብብር ለመንቀሳቀስ ከስምምነት መድረሳቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ህወሓት እና ጦር መንግሥት ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ባለፈው ዓመት ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድኖች ተብለው መፈረጃቸው ይታወሳል። አሁን ጥምረት እንደፈጠሩ ያስታወቁት ቡድኖቹ በቀጣይ ስለሚያከናውኑት እንቅስቃሴ በዝርዝር ያሉት ነገር የለም።", "“ታይዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትገለል ቻይና ስትሞክር ቆይታለች” ታይዋን የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በአገራቸው ያደረጉትን አወዛጋቢ ጉዞ ትክክል ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የናንሲ ፔሎሲን ጉብኝት ተከትሎም ቻይና በታይዋን ደሴት ዙሪያ የምታደርገውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ው አውግዘዋል። ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት “በጣም ጠቃሚ ነው” እና ቻይና እያደረገቸው ባለው “የጠብ አጫሪነት” ምላሽ ዲሞክራቶችን ወደ ታይዋን ከመጋበዝ አያስቆማቸውም ብለዋል። የቻይና ግዛት የማስፋፋት ከታይዋን በላይ እንደሚሄድም አስጠንቅቀዋል። ላለፉት ስድስት አመታት የታይዋኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ው አገሪቷ ለበለጠ አለም አቀፍ እውቅና የምታደርገው ዘመቻን ሲመሩ ነበር። የአሜሪካን የአፈ ጉባኤ ጉብኝትንም ተደራድረው ሲሆን ያመጡት በአሁኑ ወቅት ቻይና የምታደርገውን ወታደራዊ ምላሽ አስፈሪ ሁኔታም መጋፈጥ አለባቸው። ሆኖም የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቅርታ የመጠየቅ እቅድ የላቸውም። የአፈ ጉባኤዋ ጉብኝት በርካቶች የረሷት እናም ብዙም መረዳት ያላገኘችውን የታይዋን ደሴት ትኩረት እንድታገኝ ማድረግ ላይ ነው። ቻይና ታይዋንን እንደ ተገንጣይ ግዛቷ ነው የምታያት ውሎ አድሮም እንደገና በቁጥጥሬ ስር ትሆናለችም በሚልም ነው የምታስባት። ታይዋን በበኩሏ ራሷን እንደ ነጻ ሃገር ነው የምትመለከተው። የአለም መሪዎች ለታይዋን እውቅና መስጠታቸው ቻይናን ያስቆጣታል በቅርቡ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና ቤተሰባቸው ላይ ማዕቀብ መጣሉም በዛሬው ዕለት ታውቋል። “ታይዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትገለል ቻይና ስትሞክር ቆይታለች። “ ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ \"የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ፔሎሲ ያለ ከፍተኛ መሪ ታይዋንን መጎብኘታቸው ትልቅ ጠቀሜታ አለው። የታይዋንን ገፅታ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ታይዋን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የምትመራ መሆኗን እንዲረዳ እድል ይፈጥራል” ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን ቀውስ የቀሰቀሰችው ታይዋን ሳትሆን እውነታዎችን ለመቀየር እየሞከረች ያለችው ቻይና ናት ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል። “ታይዋን ነጻ ሃገር ናት። ታይዋን በቻይና ላይ ስልጣን እንደሌላት ሁሉ ቻይናም በታይዋን ላይ ምንም አይነት ስልጣን የላትም። እውነታው ይህ ነው” ብለዋል።", "\"የአማራ ብቻ ሳይሆን የጋምቤላ፣ የሲዳማና ደቡብ ክልል ልዩ ኃይሎች ቤንሻንጉል ጉሙዝ ገብተዋል\" ከሰሞኑ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ቡለን ወረዳ መግባቱን የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል። ከአማራ ክልል በተጨማሪ የጋምቤላ፣ የሲዳማ እንዲሁም የደቡብ ክልል ልዩ ኃይሎች ወደ አካባቢው መግባታቸውን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የሰላም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ ለቢቢሲ ገልፀዋል። እነዚህ ኃይሎች በክልሉ በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ስር ሆነው የሰላም ማስከበር ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን አቶ አብዮት ተናግረዋል። በተለይም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ክልሉ ከመግባቱ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን አስመልክተው የጸጥታ ኃላፊው \"ከአማራ ክልል ጋር ሰፊ አስተዳደራዊ ወሰን እንጋራለን፣ የተለያዩ ሥራዎችን በጋራ እናከናውናለን። በተጨማሪም ወንድማማች ሕዝቦች ነን። ስለዚህ በሰላምም ሆነ በልማት ሥራዎች ላይ በመቀናጀት እንሰራለን\" በማለት አስረድተዋል። በየትኛውም ክልል ያለ የልዩ ኃይል በኮማንድ ፖስቱ ስር ሆኖ ሊሳተፍ እንደሚችል የሚገልጹት አቶ አብዮት ይህ የሆነውም አካባቢው የሕዳሴው ግድብ መገኛ በመሆኑም ነው ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኃላፊው እንደ ምክንያት የሚያነሱት \"ህወሓት በሱዳን በኩል ሰርጎ እየገባ በዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽመበት ብሎም የሕዳሴ ግድቡን ለማጥቃት የሚሞክርበት አካባቢ በመሆኑ የሁላችንንም ትብብር የሚፈልግ አካባቢ ነው\" ነው ሲሉ ተናግረዋል። የመተከል ዞን በኮማንድ ፖስት የሚመራ እንደመሆኑ የኃይል ስምሪት በሚያስፈልግበት ጊዜ ከክልሉ ጸጥታ ኃይል ጋር ተቀናጅቶ እንዳይሰራ የሚከለክል ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። በተለያዩ ጊዜያት በመተከል ዞን ውስጥ በታጣቂዎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ነዋሪዎች የተገደሉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመቆጣጠር ከአንድ ዓመት በፊት በክልሉና በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት የዕዝ ማዕከል (ኮማንድ ፖስት) ተቋቁሞ እየሰራ ቢሆንም አሁን ድረስ ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው። በቅርቡም ከሱዳን በኩል ወደ ክልሉ ሰርገው በመግባት ጥቃት ሊፈጽሙ ነበር የተባሉ ታጣቂዎች በአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንደተወሰደባቸው መዘገቡ ይታወሳል። በክልሉ ውስጥ መረጋጋት ለማምጣት ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ የልዩ ኃይል አባላት መሰማራታቸውን የገለጹት ኃላፊው ጉዳዩ ከጸጥታ ጋር ስለሚያያዝ የሠራዊቱን ቁጥርና እንቅስቃሴ መግለጽ እንደማይችሉ አስረድተዋል። ከሰሞኑ የክልሉ መንግስት እና የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ከአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከክልሎች የልዩ ኃይል አባላት፣ ከሚሊሺያ አባላትና ከግል ታጣቂዎች ጋር በመሆን \"የጥፋት ቡድን\" ብለው በጠሩት ታጣቂ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ክልሉ አስታውቋል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂ የነበረው ኃይል ጋር ሰላማዊ ድርድር ለመፍጠር ቢሞከርም በአሁኑ ወቅት የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱት ጭምር ወደ ጫካ መግባታቸውን ከሰሞኑ በክልሉ መንግሥት ተገልጿል። \"ምንም እንኳን ቡድኑ በፈጠረው የጸጥታ ችግርና ጥቃት በሰው ህይወት፣ በአካል በንብረት ከፍተኛ ጉዳት ቢያደርስም የክልሉ መንግሥት ችግሩን በሰላማዊ መንገድና በውይይት ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ የበጀት፣ የጊዜ፣ የሰው ኃይል በመመደብ ለወራት የዘለቀ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል\" በማለት ክልሉ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የክልሉ መንግሥት በመተከልና ካማሺ ዞኖች ከሚንቀሳቀሰው የታጣቂ ቡድኑ አባላት መካከል የተወሰኑት የቀረበውን ሰላማዊ ድርድር በመቀበላቸው የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ክልሉ አመልክቷል። የክልሉ መንግሥት ታጣቂውን ቡድን \"ጸረ- ሰላም ኃይልና የህወሓት ተላላኪ\" በሚል ከመጥራት ውጪ በስም አልጠቀሰውም። ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥትና ታጣቂው በጉሙዝ ሕዝብ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ቡድን በክልሉ በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።", "የፈረንሳዩ ማክሮን የሩሲያና ዩክሬንን ፍጥጫ ለማርገብ እየጣሩ ነው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መጪዎቹ ቀናት እጅግ ወሳኝ ናቸው አሉ፡፡ ማክሮን ይህን ያሉት ትናንት ሰኞ ከሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሰዓታት የቆየ ንግግር ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ማክሮን ከፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት ፍሬ እንደሚያፈራ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ምዕራብ አገራት ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ዝግጅቷን ጨርሳለች በሚል በአካባቢው ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል መናገር ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ አንዳንድ ከአሜሪካ ምድር የሚወጡ መረጃዎች ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ከሚያስችላት ወታደራዊ አቅም 70 ከመቶውን ወደ ድንበር ማስጠጋቷን እየገለጡ ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ሩሲያ መቶ ሺህ የታጠቁ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር አስጠግታ ማስፈሯን ተናግረዋል፡፡ ሩሲያ ግን ምንም ዓይነት የወረራ ፍላጎት የለኝም ብላለች፡፡ ሰኞ ዕለት የአሜሪካኑ ጆ ባይደን ከጀርመኑ መራሒ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ጋር በዋሺንግተን ተገናኝተው በሩሲያ ጉዳይ ላይ በዝግ መክረዋል፡፡ ጆ ባይደን ለሩሲያ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ የሰጡ ሲኾን እንደተፈራው ፑቲን ዩክሬንን በወረራ ለመያዝ ከሞከሩ ሩሲያ ወደ ጀርመን የዘረጋችውን የጋዝ መስመር እንደሚዘጉ ዝተዋል፡፡ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በበኩላቸው ፑቲን አይተውና ሰምተው የማያውቁት ዓይነት ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ቦሪስ ጆንሰን ለዘታይምስ ጋዜጣ በጻፉት መጣጥፍ እንዳሉት በዩክሬን ላይ ወረራ ከተፈጸመ አገራቸው ዩኬ የሮያል አየር ኃይልን ብቻም ሳይኾን የባሕር ኃይሏንም ጭምር በአካባቢው እንደምታሰማራ አረጋግጠዋል፡፡ ዩኬን ጨምሮ ምዕራብ አገራት ዩክሬንን ከወረራ ለማዳን ያላቸውን አቅም ሁሉ እያስተባበሩ ይገኛሉ፡፡ ሩሲያ በበኩሏ እንዲያ ያለ ሐሳብ እንደሌላት ብትጎተጉትም ቁልፍ የደኅንነት ስጋቶቿ እንዲቀረፉላት ግን ትሻለች፡፡ ከነዚህ መካከል ዋንኞቹ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ወደ ምሥራቅ አውሮጳ የሚያደርገውን መስፋፋት እንዲያቆም፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ዩክሬንን በአባልነት የማካተት ሐሳቡን እርግፍ አድርጎ እንዲተው የሚሉ ናቸው፡፡ ትናንት ወደ ሞስኮ ያቀኑት የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ከፑቲን ጋር ለአምስት ሰዓታት ያህል የእራት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ቆይታቸው ተስፋ ሰጪ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ ማክሮን ከፑቲን ጋር በነበራቸው ዘለግ ያለ የእራት ሰዓት ውይይት የአጋዘን ሥጋ፣ ስኳር ድንችና ብላክቤሪ ጭምር እንደተቋደሱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ፑቲን በበኩላቸው ከእራት ግብዣው በኋላ በሰጡት አጭር አስተያየት የማክሮን ነጥቦች ሊዳብሩ የሚችሉና ተስፋ ሰጪ ናቸው ብለዋል፡፡ ኾኖም ዝርዝር ጉዳዮችን ለመናገር ጊዜው ገና ነው ሲሉ አስተያየታቸውን በአጭር ቋጭተዋል፡፡ ማክሮንና ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይታቸውን ነገ የሚቀጥሉ ሲሆን ይህም የሚሆነው ማክሮን ወደ ኪያቭ አቅንተው የዩክሬኑን አቻቸውን አነጋግረው ሲመለሱ ነው፡፡ ሩሲያ ከምታነሳቸው የደኅንነት ስጋቶች አንዱና ዋንኛው ዩክሬን ኔቶን ከተቀላቀለች ክሬሚያን ለማስመለስ ታልማለች የሚል ነው፡፡ ሩሲያ የክሬሚያን ባሕረ ገብ ግዛት በወረራ የወሰደችው የዛሬ ስምንት ዓመት ግድም ነበር፡፡ ፑቲን ከሁለትዮሹ ንግግር በኋላ በአቅራቢያቸው ለተሰበሰቡ የፈንሳይ ጋዜጠኞች፣ ‹ፈረንሳይ ከሩሲያ ጋር እንድትዋጋ ትሻላችሁን?› ሲሉ ድንገቴ ጥያቄ የሰነዘሩላቸው ሲሆን፣ ‹ጦርነት ከተጀመረ ማንም አሸናፊ አይሆንም› ሲሉ ያልተጠበቀ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ይህ በአንዲህ ሳለ አዲሱ የጀርመን መራሒ መንግሥት ሾልዝ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ዋሺንግተን አቅንተው ከባይደን ጋር በሩሲያ ጉዳይ መክረዋል፡፡ ሩሲያ ዪክሬንን ከወረረች ፍጹም የማትቋቋመው ብቻ ሳይሆን አከርካሪዋን የሚሰብር ማዕቀብ ይጠብቃታል ሲሉም ዝተዋል፡፡ ባይደን በበኩላቸው ፑቲን ወረራ ከፈጸሙ ኖርድ ስትሪም2 ተብሎ የሚጠራውንና ወደ ጀርመን የተዘረጋውን የጋዝ መስመር እንደሚያቆሙት ዝተዋል፡፡ የዚህ መስመር መዘጋት ሩሲያን እንደሚጎዳት ሁሉ አውሮጳዊያኑንም በኃይል አቅርቦት በእጅጉ ይጎዳል ይላሉ ተንታኞች፡፡ ጆ ባይደን ይህን እንዴት ያሳካሉ ተብለው ሲጠየቁ በቀጥታ ለመመለስ ባይችሉም ለጋዜጠኞች፣ ‹እመኑኝ እናደርገዋለን› ሲሉ በድፍኑ ዝተዋል፡፡ ከ1ሺህ 225 ኪሎ ሜትር በላይ የተዘረጋው የኖርድ ስትሪም2 የጋዝ መስመር ከሞስኮ ወደ ጀርመን የሚደርስ ነው፡፡ መስመሩን ለመዘርጋት ድፍን 5 ዓመት የወሰደ ሲሆን 11 ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበታል፡፡ ሆኖም እስከዛሬ ሥራ አልጀመረም፡፡ እንደተፈራው በሩሲያና በዩክሬን መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮጳ ምድር የሚደረግ ሰፊ ጦርነት ሊሆን ይችላል ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች፡፡", "ጄኔራል ባጫ እና ኢንጂነር ስለሺን ጨምሮ ለ27 ግለሰቦች የአምባሳደርነት ሹመት ተሰጠ ጄኔራል ባጫ ደበሌ፣ ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂምና፣ ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ለ27 አምባሳደሮች ሹመት መሰጠቱን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የአምባሳደርነት ሹመት የሰጡት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም መሆኑም ተገልጿል። ከፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ጽህፈት ቤት የወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቷ የሰጡት ሹመት ለ16 ግለሰቦች የባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እንዲሁም ለሌሎች 11 ግለሰቦች ደግሞ የአምባሳደርነት ሹመቶች ናቸው። በሙሉ አምባሳደርነት ከተሾሙት ውስጥ በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ጋር ተያይዞ ስማቸው የሚነሳው የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጦር ጄኔሎቹ ጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም ተካትተውበታል። ጄኔራል ባጫ ደበሌ ወደ ጦሩ እንደገና እንዲካተቱ የተደረጉት የትግራይ ጦርነት በተቀሰቀበት ዕለት ነበር። በቅርቡም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅራቢነት በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የጄነራል ማዕረግ ከተሰጣቸው ወታደራዊ መኮንኖች መካከል አንዱ የነበሩትና በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ የሆኑት ጄነራል ባጫ ደበሌ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙ ሲሆን የሚላኩበት አገር እስካሁን አልተገለጸም። እንዲሁም የቀድሞው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የሕዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ያሉት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለም ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነዋል። በተጨማሪም በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ በአጠቃላይ 27 ሰዎች በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነትና በአምባሳደርነት ሹመት ተሰጥቷቸዋል። በባለሙሉ ባለስልጣን አምባሳደርነት የተሾሙት ግለሰቦች በአምባሳደርነት የተሾሙት ግለሰቦች", "የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስትሮቻቸው በምሽት ክበቦች በመገኘታቸው ይቅርታ ጠየቁ በጃፓን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የወጣውን መመሪያ ተላልፈው ወደ ምሽት ክበቦች የሄዱ የአገሪቱ ባለስልጣናት ጉዳይ ከፍተኛ ትችትን አስከትሏል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚኒስትሮቻቸው ስም ለህዝቡ ይቅርታ ለመጠየቅ ተገደዋል። መንግሥት በተደጋጋሚ አላስፈላጊ የሆኑ ስብሰባዎችን ህዝቡ እንዲያስወግድ ሲናገር የነበረ ሲሆን ይህንንም ሁኔታ ሚኒስትሮቹ አለማክበራቸው አወዛጋቢ ሆኗል። \"ዜጎቻችንን ከምሽት ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ሬስቶራንቶች ወጥታችሁ አንዳትበሉ እንዲሁም አላስፈላጊ የሆኑና አስቸኳይ ካልሆነ ከቤታችሁ አትውጡ በምንልበት ወቅት ይህ በመፈጠሩ በጣም አዝኛለሁ\" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋ በዛሬው እለት ለፓርላማው አስረድተዋል። የጃፓን የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ሪፖርት ባደረጉት መሰረት አንደኛው ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት የጣልያን ሬስቶራንት ውስጥ እራት ከበሉ በኋላ ሞቅ ደመቅ ባለው የመዲናዋ ቶክዮ ማዕከል በሆነው ጊንዛ ወደሚገኙ ሁለት የምሽት ክበቦች አምርተው ነበር ብለዋል። እንዲሁ ሌላኛው ሚኒስትር ጊንዛ በሚገኝ ታዋቂ ክለብ በተደጋጋሚ መሄዳቸውን የአገሪቱ ሚዲያ አስነብቧል። የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ ለሁለተኛ ዙር እያገረሸ ባለባት ቶክዮ ባለስልጣናቱ የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል። በጃፓን ከ370 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ5 ሺህ በላይ ዜጎቿንም አጥታለች።", "ምርጫ 2013፡ ዛሬ ድምጽ የሚሰጥባቸው ቦታዎች መኖራቸው ተገለጸ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከረፋድ 5 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ የሚሰጥባቸው ቦታዎች መኖራቸውን አስታወቀ። ቦርዱ ይህን ያለው ትናንት ምሽት 5፡30 ላይ በሰጠው መግለጫው ነው። በመግለጫው ላይ የምርጫ ቦርድ አምስት አባላት መግለጫ ለመስጠት የተገኙ ሲሆን የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱኳን ሚደቅሳ ምርጫ \"ከሞላ ጎደል እጅግ ጥሩ ነበር\" ብለዋል። የድምጽ መስጫ ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንዲራዘም ስለመወሰኑ ያስታወሱት ሰብሳቢዋ፤ የድምጽ መስጫ ሰዓት ማራዘም ሳያስፈልጋቸው የድምጽ አሰጣጥ ስነ-ስርዓታቸውን ያካሄዱ ምርጫ ጣቢያዎች ትናንት ምሽት ድምጽ ቆጠራ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ከምርጫ ጣቢያዎች ከፍተኛ ቁጥር አንጻር ሁሉም ሊባል በሚችል መጠን የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ ሲያሰጡ ውለው አጠናቅቀዋል ብለዋል። ኢትዮጵያ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ከትግራይ፣ ሶማሊ እና ሐረሪ ክልሎች በስተቀር በትናንትናው ዕለት፣ ሰኔ 14 2013 ዓ.ም ማከናወኗ ይታወሳል። በሶማሊ እና በሐረሪ ክልሎች ደግሞ ጳጉሜን 1 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የምርጫ ቦርድ መረጃ ያሳያል። በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተነሳ ላልተወሰነ ጊዜ ምርጫ አይካሄድም። ከ37 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተመዘገቡበት እና 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተፎካከሩበት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ትናንት ከምሽቱ 3፡00 መጠናቀቁን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለህዝባቸው አስተላልፈዋል። ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ ከ40ሺህ በላይ የአገር ውስጥ እና ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ተሰማርተዋል። የምርጫ ቦርድ አባላትም የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን መጎብኘታቸውን የገለፁ ሲሆን፣ ምርጫው ሴቶች እና ወጣቶችን ያሳተፈ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ታዛቢዎቹ በቀጣይ ጥቂት ቀናት የቅደሚያ ሪፖርት ዋና ዋና ግኝት የሚሏቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ትናንት በተካሄደው ምርጫ ይህ ነው የሚባል የጸጥታ ችግር አላጋጠመም ሲሉ ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ በተመሳሳእ ምርጫው በሰላም ተካሄዶ መጠናቀቁን በሰጠው መግለጫው ላይ አመልክቷል። በአማራ ክልል በአንድ ምርጫ ጣቢያ ላይ ያልታጠቁ ሰዎች እርስ በእርስ ግጭት ፈጥረው የምርጫው ሂደት የተቋረጠበት ሁኔታ እንደነበር ሰብሳቢዋ አስታውሰዋል። በአማራ ክልል ጎንጂ ምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ የአካባቢው ባለስልጣናት ገብተው አልወጣም ማለታቸው ስጋት ፈጥሮ፣ አንድ የምርጫ ቦርድ ምርጫ አስፈጻሚ አካባቢውን ለቅቆ ሊወጣ ችሏል። ይህን ለሚመለከተው አሳውቀናል ሲሉም አክለዋል። በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ምርጫ አስፈጻሚዎች ስጋት ገብቷቸው ምርጫ ጣቢያ ያልከፈቱባቸው ቦታዎች እንደነበሩ ተናግረዋል። አክለውም ምስራቅ ሐረርጌ ምርጫ ክልል ውስጥ ያልተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች አሉ። ይህ የመጀመሪያ ሪፖርት ነው ጉዳዩን እንመለከተዋለን ሲሉም አብራርተዋል። በምዕራብ ሸዋ ኖኖ ምርጫ ክልል ሁለት ጣቢያዎች ላይ የታጠቁ ሰዎች ሂደቱን ረብሸው የድምጽ አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ተቋርጦ እንደነበር የተናገሩት ወ/ት ብርቱካን \"ከዚህ ውጪ ይህ ነው የሚባል የጸጥታ ችግር የለም\" ሲሉ አረጋግጠዋል። በአዲስ አበባ የድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት አጋጥሞ እንደነበር ያስረዱት የቦርዱ ሰብሳቢ፣ ይሁን እንጂ ይህ ችግር ማጋጠሙ እንደታወቀ በተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ ችግሩ መቀረፉ ተመልክቷል። ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሲዳማ ክልሎች የቁሳቁስ እጥረት ማጋጠሙን ወ/ት ብርቱካን ተናግረዋል። የድምጽ መስጫ ወረቀቶች በባለ 100 ተደርጎ መታሸግ ሲኖርባቸው በባለ 50 ተደርገው በመታሸጋቸው እጥረት ማጋጠሙን ያስረዱት ሰብሳቢዋ፣ 19 የምርጫ ክልሎች ላይ የምርጫ ወረቀት ብዛት በ50 በመቶ አጥረት ማጋጠሙን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት በሲዳማ ክልል ሁሉም ምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደት መቋረጡን አብራርተዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስፈልገው ሰነድ ለ19 የምርጫ ክልሎች እንዲደርስ መደረጉንም አስረድተዋል። ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለማድረስ ግን ከመሰረተ ልማት እና ከርቀት አንጻር አስቸጋሪ ነበር ያሉት ሰብሳቢዋ፣ ቦርዱ 1162 የምርጫ አዋጁ በሚፈቅደው መሠረት ምርጫው እንዲቋረጥ አድርጎ ዛሬ ማክሰኞ፣ ከረፋዱ 5 ጀምሮ በሲዳማ የምርጫ ክልሎች በሙሉ ሂደቱ ይቀጥላል ብለዋል። የምርጫ አዋጅ 1162 ምርጫ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በሚቋረጥበት ጊዜ፣ ለጊዜው ምርጫው እንዲቋረጥ ተደርጎ ሁኔታዎች የሚስተካከሉበት ሰዓት ተወስዶ ሂደቱ መቀጠል እንደሚቻል ይደነግጋል። ጋምቤላ በአራት የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት አጋጥሞ ነበር። በእነዚህ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ በቁሳቁስ እጥረት ምርጫው ተቋርጦ እንደነበረ የቦርዱ ሰብሳቡ ወ/ት ብርቱካን ተናግረዋል። የድምጽ አሰጣጡ በተቋረጠባቸው አራቱ የምርጫ ክልሎች ጉዳይ ቦርዱ የሚሰጠው ውሳኔ ግልጽ ይደረጋል ብለዋል። በጋምቤላ ያሉ ሌሎች ምርጫ ክልሎች ግን ድምጽ አሰጥተው ወደ ቆጠራ መግባታቸውን እና ውጤትን በሂደት እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። በሁለት የምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት በማጋጠሙ ምርጫ መቋረጡን የተናገሩት ሰብሳቢዋ፣ ቻርተር አውሮፕላን በመጠቀም ቁሳቁሶች ወደ ጋምቤላ መላካቸውን ተናግረው በጉዳዩ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ ግልጽ ይደረጋል ብለዋል። ሰብሳቢዋ በዚህ ረገድ ለተፈጠሩ ጉድለቶች ሕዝቡን ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ አክለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዛሬ ጀምሮ በየምርጫ ጣብያው ውጤት መግለጽ እንደሚጀመር አስረድቷል። አክሎም ቆጠራ ያጠናቀቁ ጣብያዎች በሙሉ በምርጫው የተገኘውን ውጤት ከዛሬ ጀምሮ መግለጽ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል። ምርጫ ክልሎች ቢበዛ አምስት ቀን ድረስ ውጤት ለማሳወቅ ጊዜ እንደሚፈጅባቸው የተናገረው ቦርዱ፣ ነገር ግን በጊዜያዊነት ከስር ከስር እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምርጫ ቦርድ በ አስር ቀን ውስጥ ውድድር በተደረገባቸው የምርጫ ክልሎች ቢያንስ በጊዜያዊነት ውጤቶችን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።", "ያልተከተቡ ሰዎችን ከህዝብ አገልግሎት የሚያግድ ህግ የደገፉ የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው በርካታ የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ያልተከተቡትን ሰዎች በሀገሪቱ ከበርካታ ህዝባዊ አገልግሎት እንዲታገዱ የሚያዘውን ረቂቅ መደገፋቸውን ተከትሎ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። የፈረንሳይ መንግሥት ሰዎች ወደ የጋራ ስፍራዎች ላይ ለመገልገል እና በትራንስፖርት ለማጓጓዝ መከተባቸውን የሚያረጋገጥ ሰነድ እንዲያሳዩ የሚያስገድድ ሕግ በማውጣት ላይ ይገኛል። ህጉ በዚህ ሳምንት በድምጽ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ክትባትን አንፈልግም የሚሉትን አስቆጥቷል። ፈረንሳይ በአውሮፓ ህብረት በከፍተኛ ምጣኔ የኮቪድ19 ክትባትን አዳርሳለች። የሀገሪቱ መንግሥት እንደገለጸው በፈረንሳይ ቢያንስ 91 በመቶው የሚሆኑት አዋቂዎች ሙሉ በሙሉ ተከትቧል። ባለፈው እሁድ የፓርላማ አባል የሆኑት አጀንስ ፊርሚን ክትባት በአንዳንድ ስፍራዎች አስገዳጅ እንዲሆን ደግፈው በመከራከራቸው ሊገደሉ እንዲችሉ የሚያሳይ ስዕላዊ ማስፈራሪያ የያዘ እና በኢሜል የተላከላቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረው ነበር። የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት እና የኮቪድ 19 ክትባትንም የሚሰጡት እኚሁ የፓርላማ አባል \"ዲሞክራሲያችን አደጋ ላይ ነው\" ሲሉም ጽፈዋል። ቢኤፍኤም ቲቪ ከተሰኘ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዛቻውን ለፖሊስ ሪፖርት እንዳደረጉ እና ክትባቱን አስገዳጅ ለማድረግ ከመደገፍ እንደማይገታቸው አብራርተዋል። ሌላዋ የፓርላማ አባል የሆኑት ናኢማ ሙችቹ በኢሜል የተላከላቸውን ማስፈራሪያ የሚያሳይ ከስክሪን የተወሰደ ምስል በትዊተር አማካኝነት አሰራጭተዋል። ትላንት በፓርላማ የተገኙት የጤና ሚኒስትሩ ኦሊቪየር ቬራን የክትባት ተቃዋሚዎችን እያደረሱ ያሉትን የሞት ዛቻ እና \"ራስ ወዳድነት\" አውግዘዋል። ባለፈው ሳምንት የፈረንሳይ ሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጄራልድ ዳርማኒን ክትባትን የተመለከተው ህግ ላይ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት ፖሊስ ለተመረጡት ባለስልጣናት ጥበቃውን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል። የገዢው ፓርቲ እና የፓርላማው አባል የሆኑት ባርባራ ቤሶት \"ነጻነታችንን በማጥቃት\" የፓርላማ አባላት እንደሚገደሉ የሚያስፈራራ መልዕክቶች እንደደረሳቸው ፓርቲው ገልጿል። በትዊተር ገጻቸው ላይ ደግሞ \"እነዚያ የግድያ ዛቻዎች ተቀባይነት የላቸውም\" ሲሉ ጽፈዋል። በፈረንሳይ ወረርሽኙ በተስፋፋበት ጊዜ ተቺዎች የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሚመሩት መንግስት ኮቪድ ለመቆጣጠር ህጎችን በመጣል ነፃነቶችን ጥሷል ሲሉ ከሰዋል። በዚህም ምክንያት እነዚህን ህግጋት የሚቃወሙ ሰልፎች በየጊዜው ተካሂደዋል። በፈርንሳይ በበርካታ የጋራ ቦታዎች ለመገልገል ሰዎች የክትባት ማረጋገጫ ወይም ከኮቪድ ነጻ መሆንን የሚያረጋግጭ ሰነድ እንዲያሳዩ ለወራት ስትጠይቅ ቆይታለች። ሆኖም የፈረንሣይ መንግሥት በከፍተኛ ፍጥነት የሚዛመቱት የኦሚክሮን እና ዴልታ ዝርያዎች ተከስተው በቫይረሱ የሚያዙሰዎችን መጨመር ተከትሎ ከቫይረሱ ነጻ መሆንን የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብን ከምርጫ ውጪ አድርጋዋለች። የፈረንሳይ መንግሥት ክትባቱን አስገዳጅ የሚያደርገው ህግ በፓርላማ ከፀደቀ ከተያዘው ወር አጋማሽ ጅምሮ ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ይዟል። ነገ በሀገሪቱ ሴኔት ውስጥ በጉዳይ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በፊት አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታችኛው ምክር ቤት ባደረጉት ምክክር በህዝብ አገልግሎት ለመጠቀም አስገዳጅ መሆኑን ይደግፋሉ።", "በምዕራብ ኦሮሚያ 'ሦስት ቻይናውያን ታግተዋል የተባለው ሐሰት ነው' በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ሦስት ቻይናውያን የማዕድን አውጪ ኩባንያ ሠራተኞች በታጣቂዎች ታግተዋል መባሉን ሐሰት ነው ሲሉ የዞኑ ባለሥልጣን አስተባበሉ። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራ ቡድን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አቅራቢያ ሦስት የቻይና ዜጋ የሆኑ የማዕድን ሠራተኞችን አግቼ ይዣለሁ ብሎ ነበር። ይሁን እንጂ የምዕራብ ወላጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ የውጭ ዜጋ የለም በማለት ቡድኑ ያወጣው መግለጫ ሐሰት ነው ብለዋል። አቶ ኤልያስ ጨምረውም \"በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ ቻይናዊ አለመኖሩን አረጋግጫለሁ\" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ ጥቃቶችን እንደሚፈጽም የሚነገረውና መንግሥት 'ሸኔ' እያለ የሚጠራው ቡድን በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተብሎ መፈረጁ ይታወሳል። ይህ ቡድን ባለፈው ቅዳሜ በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ አቅራቢያ በማዕድን ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሦስት የቻይና ዜጎችን አግቼ ይዣላሁ ማለቱ ይታወሳል። በመግለጫው ተፈጸመ ላለው እገታ ምክንያቱ \"በመንግሥት እና በማዕድን አውጪዎቹ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ሕጋዊ አይደለም\" የሚል ነው። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተገንጥሎ የትጥቅ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የሚገልጸው ይህ ቡድን በአካባቢው የሚደረገው የማዕድን ቁፋሮ በርካቶችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፣ በአካባቢያዊ ላይም ጉዳት እያስከተለ ነው ብሏል። ይህ ቡድን ሦስት ቻይናውያን ማዕድን አውጪ ሠራተኞችን አግቼ ያዝኩ ይበል እንጂ ሦስቱ ቻይናውያን የሚሰሩበት ድርጅት ማንነት፣ በየትኛው የማዕድን ማውጣት ተግባራት ላይ ተሰማርተው እንደነበረና የቻይናውያኑ ኃላፊነት ምን እንደሆነ ያለው ነገር የለም። የታጣቂ ቡድኑ ነው ከተባለው መግለጫ ጋር ታግተዋል የተባሉ የሦስት ሰዎች ፎቶግራፍ የተሰራጨ ቢሆንም ስለግለሰቦቹ ማንነት የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ ግን አልተገኘም። ጉዳዩን በተመለከተ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ አዲስ አበባ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ የተባለ ነገር የለም። የአካባቢው ባለስልጣናት ምን ይላሉ? በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የምዕራብ ወላጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ፤ እገታውን በተመለከተ \"በማኅበራዊ ሚዲያ የተባለውን አንብበናል፤ ውሸት ነው። አረጋግጠናል\" ብለዋል። \"በወረዳችን፣ በቀበሌያችን መሰል ነገር አለመከሰቱን አረጋግጠናል\" ያሉት አቶ ኤልያስ፤ ጨምረውም በአካባቢው የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ ቻይናውያን አለመታገታቸውን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል። መንዲ ከተማ የቱርክ እና የሕንድ ዜጎች ማዕድን የማውጣት ሥራ ተሰማርተው እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ ኤልያስ፤ በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ዘወትር በሥራ ገበታቸው እንደማይገኙ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የመነ ሲቡ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ ታመነ ይህ ክስተት እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ አለመከሰቱን ተናግረው፤ \"በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኦዳ ቢልዲጊሉ ወረዳ እገታው ተፈጽሟል\" የሚል መረጃ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህን በተመለከተ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው ነገር የለም። የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው ስለ ጉዳዩ የማውቀው የለም ብለዋል። \"ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የውጭ አገር ዜጎች ታፍነዋል የሚል መረጃ የለኝም። ኦሮሚያ ውስጥ ቢሆን ኖሮ መረጃው ይደርሰን ነበር\" ብለዋል። ከሁለት ዓመት በፊት መንዲ ከተማ አቅራቢያ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ሁለት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ አምስት ማዕድን አውጪዎች መገደላቸው ይታወሳል። በምዕራብ እና ደቡብ የኦሮሚያ አካባቢዎች ባለፉት ጥቂት ዓመታት በታጣቂዎች በሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናት እና ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም ለረጅም ዓመታት በትጥቅ ትግል ላይ ከነበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ተለይቶ የወጣውና እራሱን 'የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት' ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ደግሞ 'ሸኔ' የተባለው ቡድን ስም በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡድኑን የሽብር ቡድን አድርጎ ከጥቂት ሳምንታት በፊት መሰየሙ ይታወሳል። በኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 18 የመንግሥት ባለስልጣናት፣ 112 የፖሊስ አባላት እና 42 የሚሊሻ አባላት በታጣቂዎች መገደላቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል።", "በምዕራብ ኦሮሚያ ላለው የሰላም እጦት አምስት ምክንያቶች *ባለፉት ሦስት ዓመታት የምዕራብ ኦሮሚያ ክፍል ሰዎች በግፍ የሚገደሉበት፣ የሚፈናቀሉበት እና ንብረት የሚወድምበት አካባቢ ሆኖ እስካሁን ቀጥሏል። በ2013 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ በተከታታይ ለቀናት በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መገደላቸው መዘገቡ ይታወሳል። ከዚህ ጥቃት በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና ሌሎችም የጥቃቶቹ ሰለባዎች ሆነዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙት ግድያዎች፣ ማፈናቀሎች እና ዝርፊያዎች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄድ በሚገኘው ጦርነት ምክንያት የሚገባውን ትኩረት ሳያገኝ እንደቀጠለ ነው። መልኩን እየቀያየር የሚያጋጥመው ጥቃት ለበርካታ ዓመታት በሰላም አብሮ ሲኖር የነበረን ማኅበረሰብ በዓይነ ቁራኛ እንዲተያይ ምክንያት እየሆነ ነው። ከትግራዩ ጦርነት በፊት የጀመረው በአካባቢው ያለው የሰላም መደፍረስ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ለመሆኑ ቀደም ሲል በሰላማዊነቱ የሚታወቀው የምዕራብ የኦሮሚያው ክፍል ወለጋን መረጋጋት እንዲርቃትና በርካቶችን ሰለባ እንዲሆኑ ያደረጉት ጥቃቶች እንዲቀጥሉ ያደረጉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? አምስቱ ዋነኛ ምክንያቶችን እነሆ። የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መንግሥት 'ሸኔ' የሚለውን እና እራሱን 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር' ብሎ የሚጠራው ቡድን በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ በስፋት በመንቀሳቀስ ለክልሉ እና ለፌደራል መንግሥት ፈተና ሆኖ ቆይቷል። 'ሸኔ' ወይም 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር' የሚንቀሳቀስባቸው ስፍራዎች የደኅንነት እጦት ያጋጠማቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች ሆነዋል። ከሦስት ዓመት በፊት ይህ ቡድን ተጠያቂ በሆነበትና በካማሺ ዞን አስተዳዳሪዎች ላይ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ ከ100 ሺህ በላይ ሕዝብ ከመኖሪያው እንዲፈናቀል እና በርካቶች በጥቃቱ እንዲገደሉ ምክንያት ሆኖ ነበር። የሸኔ ወይም የኦሮሞ ነጻነት ጦር በጀምላ ግድያ፣ ዘረፋ፣ በንጹሃን እና በመንግሥት ባለሥልጣናት ግድያ፣ መንገድ በመዝጋት፣ የሕዝብ እና የመንግሥት ንብረት በማውደም፣ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ እና በሌሎች ወንጀሎችም ይከሰሳል። በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ እና ባቦ ጋምቤል ወረዳዎች እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ዞን አቤ ዶንጎሮ፣ አሙሩ እና አባያ ጮመን ግፍ ከተፈጸመባቸው ወረዳዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። በተመሳሳይ በተቀሩት ሁለት የወለጋ ዞኖች፤ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ወንጀሎች ተፈጽመዋል። ሰኔ 2013 ዓ.ም. በኪራሙ በተፈጸመው እና ከ100 በላይ ሰዎች ከተገደሉበት ጥቃት በሕይወት መትረፍ የቻለው አርሶ አደር ለቢቢሲ እንደተናገረው በአሁኑ ወቅት በሽሽት በአማራ ክልል ውስጥ ይገኛል። ለደኅንነቱ ሲባል ስሙን የማንጠቅሰው ይህ አርሶ አደር ትውልድ እና አድገቱ ወለጋ ውስጥ መሆኑን በመናገር በአካባቢው ለተፈጠረው የሰላም እጦት ዋነኛው ምክንያት 'የሸኔ' ታጣቂዎች ናቸው ይላል። \"ይሄን ሁሉ የሚያደርገው ሸኔ ነው። ኦነግ ሸኔ ነው ይህን ችግር ያመጣው እንጂ እኛማ ተጋብተን፣ ተዛምደን አይደል እንዴት አብረን ስንኖር የነበረው?\" በማለት ይናገራል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉት የፖለቲካ ተንታኝም፤ በአካባቢው ያለውን የደኅንነት እጦት ያባባሰው \"የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ነው\" በማለት ከአርሶ አደሩ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ይሰነዝራሉ። ጨምረውም \"ዘንድሮ ሳይታረሰ የቀረ ሰፊ መሬት አለ\" በማለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአማራ ብሔር ተወላጅ ከአካባቢው ተፈናቅለው መውጣታቸውን ይገራሉ። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚሰነዘሩት በርካቶቹ የታጣቂዎች ጥቃቶች ኢላማቸውን የሚያደርጉት በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ይሁን እንጂ በጥቃቶቹ ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎችም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል። መሰል ጥቃቶች የበቀል እርምጃ እንዲወስድም ምክንያት እየሆኑ ነው። የአማራ ታጣቂዎች በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ጥቃቶች መሰንዘር ከጀመሩ በኋላ የአማራ ታጣቂዎችም በበቀል እርምጃዎችን በመወሰድ መከሰስ ጀምረዋል። በሁለቱ ዞኖች ውስጥ በደርግ መንግሥት ወቅት የሰፈሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአማራ ብሔር ተወላጆች ይኖራሉ። ከዚህ ቀደም በነበሩት ዓመታት የኦሮሞ እና የአማራ ብሔር ተወላጆች በሰላም እና በመተጋገዝ ይኖሩ ነበር። ይሁን እንጂ ከታጣቂዎች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት በሁለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል ግጭት መከሰት ጀምሯል። \"ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች ብዙ ሰው ገድለዋል (የአማራ ብሔር ተወላጆችን)። አሁን ላይ ታጣቂዎች የገደሉትን ለመበቀል ያገኙትን ኦሮሞ በመግደል በቀል እየተወጡ ነው። 'ትናንት አብሮን የበላው እራሱ ነው ያስገደለን' ይላሉ። በየቀኑ ሰው እየተገደለ ነው\" በማለት የምዕራብ ኦሮሚያን የፀጥታ ሁኔታን በቅርበት የሚከታተሉት ተንታኝ ይናገራሉ። ታኅሣሥ 2014 ዓ.ም. በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የአማራ ታጣቂዎች የወሰዱት የበቀል እርምጃ ነው በተባለ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ንብረትም ወድሟል። በሆሮ ጉዱሩ ዞን፤ የጃርዳጋ ጃርቴ ወረዳ ሃርቡ ነጋሶ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት ግለሰብ በዚህ ጥቃት ንብረታቸው ስለወደመባቸው አካባቢውን ጥለው ተሰደዋል። \"ዘጠኝ ሰዎች ተገድለው ነበር። ሟቾቹ ደግሞ መሸሽ የማይችሉ ሰዎች ናቸው። የ90 ዓመት አዛውንት ከሟቾቹ መካከል ይገኙበታል\" በማለት ተፈናቃዩ ይናገራሉ። ሌላ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደር፤ በሁለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል እርቅ ለማውረድ ለውውይት በተቀመጡ ወቅት፤ የአማራ ብሔር ተወላጆች 'ለደኅንነታችን ሰግተን ፋኖን አስመጥተናል' ብለው ስለመናገራቸው ይገልጻሉ። ሌላኛው ንብረታቸው ወድሞ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ እንደሚሉት የአማራ ታጣቂዎች ጥቃት ሲፈጽሙ የቆዩት መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን ሲንቀሳቀስ በነበረበት ቦታ ነው ይላሉ። \"ሲንቀሳቀሱ በነበሩት ቦታ ነው ያቃጠሉት። አሁን እነሱ (የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቡድን) በቦታው የሉም። ይህ የብሔር ግጭት ሳይሆን የፖለቲካ መልክ ነው ያለው። በቀል የሚወጡም ይመስላል\" በማለት ያስረዳሉ። የቀድሞው የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አለማሁ ተስፋ ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በአካባቢው 'በአማራ ታጣቂዎች' ጥቃት ተፈጽሟል ሲሉ ተናግረው ነበር። ከዚህ አንጻር ከጥቃቶቹ ጋር በተያያዘ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ 'የአማራ ታጣቂዎች' የተባሉትን ሃሳብ አግኝቶ ለማካተት አልተቻለም። የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን በበኩላቸው በቅርብ ጊዜያት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችን ዒላማ ባደረገው ጥቃት ተሳታፊ የሆኑት በዚያው በክልሉ ውስጥ የሚኖሩት ናቸው ይላሉ። እንደ ኃላፊው ከሆነ ታጣቂዎቹ የመንግሥት እንቅስቃሴን ተከትለው ከቦታ ቦታ እንደሚንቀሳቀሱ ያስረዳሉ። መንግሥት ከመንግሥት ቀዳሚ ኃላፊነቶች መካከል የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ እንዱ ቢሆንም፤ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚኖሩ የሁለቱም ብሔር ተወላጆች መንግሥት ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አልቻለም ይላሉ። \"የመንግሥት አካል ሁኔታውን መቆጣጠር ነበረበት። ለጠፋው ሕይወት እና ንብረት መንግሥት ተጠያቂ መሆን አለበት\" በማለት የጃርዳጋ ጃርቴ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር ይናገራሉ። ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ግጭት እየተበራከተ ሲሄድ እንኳን መንግሥት 'ዝምታን' መርጧል ይላሉ። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ግን በዚህ አይስማሙም። አቶ ሻፊ፤ \"እንደውም ያለን ኃይል በምዕራብ ነው ያለው። መንግሥት የተለያየ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል\" ይላሉ። በሌላ በኩል በክልሉ መንግሥት ላይ የሚነሳው ቅሬታ፤ አርሶ አደሩ እራሱን ሊከላከል የሚችልበትን ትጥቅ ያስፈታል የሚለው ነው። በአንዳንድ ስፍራዎች መንግሥት ጦር መሳሪያ በታጣቂዎች እጅ ሊገባ ይችላል በሚል ስጋት ነዋሪዎችን ትጥቅ ሲያስፈታ ነበር ተብሏል። አንድ አርሶ አደር \"ሸኔን ምክንያት ያደርጋሉ እንጂ እንዴት አንድ ሰው ለሸኔ እንካ ብሎ መሳሪያ ይሰጣል?\" ሲሉ ይጠይቃሉ። አቶ ሻፊ ግን መንግሥት ሚሊሻውንም ሆነ አንድ ወገንን ለይቶ ትጥቅ አያስፈታም ይላሉ። ይሁን እንጂ በጦር መሳሪያ አማካኝነት ጉዳት እንደሚደርስ ይናገራሉ። ሌላ መንግሥት ላይ የሚነሳው ትችት፤ የወታደራዊ እርምጃ አማራጭን በመጠቀም በምዕራብ ኦሮሚያ ሰላም ማምጣት ባለመቻሉ የእርቅ መንገድን መጠቀም አለበት የሚለው ይገኝበታል። አቶ ሻፊ ግን መንግሥት ለዚህ በሩ ክፍት ነው ይላሉ። ይሁን እንጂ \"ታጣቂው እንዲሁ ለቃል ካልሆነ በቀር ለሰላም ዝግጁ አይደሉም\" ሲሉ ይከሳሉ። የፖለቲካ ፍላጎት የኦሮሚያ ክልል በአገሪቱ ካሉት ክልሎች በቆዳ ሰፋቱም ሆነ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚው ነው። በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች የክልሉ መንግሥት የአገሪቱን ፖለቲካ መቆጣጠር የሚፈልጉ አካላት ክልሉን ዒላማ ሊያደርጉት ይችላሉ የሚል ስጋት አለው። አቶ ሻፊም ይህን ሁኔታ \"የፖለቲካ ፍላጎት ነው\" ሲሉ ይገልጹታል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ፍላጎታቸው ምንም ቢሆን ግባቸው ግን ተመሳሳይ መሆኑን ያስረዳሉ። \"አገር ማፍረስ፣ ሕዝብ ማፈናቀል፣ ንብረት ማውደም፣ ሁከት መፍጠር፣ ከተቻለም ይህን መንግሥት አፍርሰው የሽግግር መንግሥት መመስረት ነው\" በማለት ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን በይፋ ሲኮንኑ አይስተዋልም። በዚህም ታጣቂዎች የልብ ልብ እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗቸዋል ይላሉ። ሌሎች ምክንያቶች ለዓመታት የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በየአካባቢው የሚስተዋሉ ብሔር ተኮር ግጭቶች ተበራክተዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚታየውም ከዚህ የሚለይ አይደለም። ለበርካታ ዓመታት በሰላም አብረው ይኖሩ የነበሩ ማኅበረሰቦች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን አዲስ ነገር እንዳጋጠማቸው ይናገራሉ። ሰዎች እርስ በእርሳቸው እንዲጠራጠሩ እና በሕዝቦች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት እንዲሻክር የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የማኅበረሰብ አንቂዎች አሉታዊ ሚና እንደተጫወቱ በርካቶች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለሦስት አስርት ዓመታት በበላይነት ሲመራ የቆየው ህወሓት በሕዝቦች መካከል መጠራጠርና ግጭት በመፍጠር በመሆኑ አሁን የሚታየው ሁኔታም የዚያ ተከታይ እንደሆነ ባለሥልጣናት ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ሰፊውን የአገሪቱን ሕዝብ ቁጥር በሚሸፍኑት ወጣቶች ዘንድ የተንሰራፋው ሥራ አጥነት እና የእርሻ መሬት እጥረትን የመሳሳሉ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ለሰላም እጦት እንደ ምክንያት ይቀርባሉ። * በዚህ ታሪክ ውስጥ የተካተቱት ሰዎች ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል", "የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ ኢትዮጵያ ላይ ምን አንድምታ ይኖረው ይሆን? የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ያሳወቁት እሁድ ምሽት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን መልቀቂያ የተሰማው በአገሪቱ ውስጥ ለተከታታይ ሳምንታት ሲካሄድ በቆየውና እሁድ ዕለት ካርቱም ውስጥ የተደረገውን ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን መልቀቅ ከአብደላ ሐምዶክ ጋር ስምምነት መስርተው ለነበሩት ወታደራዊ መሪዎች ራስ ምታት ነው ሲሉ የአገሪቱን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ከሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣኑን ሊጠቀልል፣ አገሪቱም ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸገገር የምታደርገውንም ጥረት ሊያኮላሽ ይችላል። ይህ ብቻ ሳይሆን አሁን በአገሪቱ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ፣ ወታደራዊ ኃይሉን ወደ አምባገነናዊ አስተዳደር ሊመራው የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። አብደላ ሐምዶክ አብደላ ሐምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሐላ ፈጽመው ሥልጣን ሲረከቡ ዋነኛ ግባቸው የነበረው አገሪቱን ማረጋጋትና ለገጠማት ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ መፍትሄ መፈለግ ሲሆን በዚያውም በሕዝብ የሚመረጥ መንግሥት ለመመስረት መንገድ ማመቻቸት ይገኝበታል። የአብደላ ሐምዶክ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ለረጅም ዘመን ከወታደሩ በወጡ መኮንኖች ስትመራ የነበረችውን ሱዳንን፣ ከጦር ኃይሉ ተጽዕኖ በማላቀቅ ወደ ሲቪል መንግሥት ይመልሳታል የሚል ተስፋን በሕዝቡ ውስጥ ፈጥሮ ቆይቷል። በ60ዎቹ አጋማሽ የሚገኙት አብደላ ሐምዶክ በምጣኔ ሀብት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ አህጉራዊ ተቋማት ውስጥ በሙያቸው የረጅም ጊዜ ልምድ አላቸው። አገራቸው በወሳኙ የሽግግር ወቅት እንዲያገለግሏት ስትጠራቸው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ እያገለገሉ ነበር። ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት አልበሽር መሪ በነበሩበት ወቅት፣ ሐምዶክ ለገንዘብ ሚኒስትርነት ታጭተው የነበረ ሲሆን እርሳቸው ግን ሳይቀበሉት መቅረታቸው ይነገራል። በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል የነበረው አለመግባባት ረግቦ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት ከስምምነት የተደረሰ ቢሆንም፣ በጦር ኃይሉና በሲቪል ባለሥልጣናት መካከል የነበረው ግንኙነት የሰመረ አልነበረም። ይህ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲዋቀር በሚፈልጉ ለውጥ ጠያቂዎች ዘንድ ጥርጣሬን ፈጥሮ ቆይቷል። በተለይ የጦር ኃይሉ ጄነራሎች ጎልተው መውጣት አገሪቱን መልሶ ወደ ወታደራዊ አስተዳደር አዙሪት ውስጥ ሊከታት ይችላል የሚል የዘወትር ስጋት ነበረ። የኢትዮጵያ ሚና ፕሬዝዳንት አልበሽር ከሥልጣን ተወግደው በሱዳን ፖለቲካዊ ኃይሎች መካከል አለመግባባቱ በጦዘበት ጊዜ፣ ጦር ኃይሉና ሲቪል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከስምምነት ደርሰው የተሳካ የሽግግር ሂደት እንዲኖር የኢትዮጵያ ሚና የጎላ እንደነበር ይታወሳል። በሕዝባዊው ተቃውሞ ወቅት በተገደሉ ሰዎች ምክንያት የተቃዋሚ መሪዎች የጦር ኃይሉን መሪዎች ተጠያቂ በማድረግ በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ እንዳይሳተፉ ሲጠይቁና ጄነራሎቹም የአገሪቱን ደኅንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደወስዱበት በሚናገሩበት ጊዜ ሌላ ዙር ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ተሰግቶ ነበር። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ካርቱም በማምራት ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን አጥብበው ሱዳን ወደ ተረጋጋ የሽግግር ሂደት እንድታመራ ጥረት አድርገዋል። በዚህም በተቀናቃኞቹ ኃይሎች መካከል ስምምነት ተደርሶ አሳሳቢው ውጥረት ለጊዜውም ቢሆን ለመርገብ ችሎ ነበር። ከኢትዮጵያ ጋር ረዥም ድንበር የምትጋራው ሱዳን በአል በሽር ትመራ በነረበት ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መምጣት በፊት ከነበረው አስተዳደር ጋር ጠንካራ ግንኙነት ገንብታ የቆየች ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የአመራር ለውጥ ከመጣ በኋላም ይህንኑ ለማስቀጠል ፍላጎት እንዳለ ታይቷል። በተለይ አልበሽር ከሥልጣን ወርደው የሽግግር መንግሥት በሚቋቋምበት ጊዜ ለሱዳን መረጋጋት ኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ ለማሳየት ጥረት አድረጋለች። በተመሳሳይም ሱዳንን ከጎኗ ለማሰለፍ የምትፈልገው ግብፅም የበኩሏን ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል። ውጥረት የነገሰበት የድንበር ጉዳይ ኢትዮጵያና ሱዳን ለረጅም ጊዜ መፍትሔ ሳያገኝ የቆየውን የድንበር ጥያቄያቸውን ለመፍታት ዓመታት የቆየ የድንበር ኮሚሽን አዋቅረው አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርጉም የመጨረሻ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቆይተዋል። ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የሚገኙበትና ሱዳን ይገባኛል የምትለው አል ፋሽቃ የተባለው ሰፊ ለም መሬት፣ አንድ ጊዜ አጀንዳ ሲሆን ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲተው ቆይቶ ነበር። ሁለቱም አገራት የራሳቸው እንደሆነ ቢገልጹም ግንኙነታቸውን ከሚያበላሽ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ለአመታት ቆይቷል። ነገር ግን ትግራይ ውስጥ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ጊዜ የኢትዮጵያ ወታደሮች የድንበር አካባቢውን ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የሱዳን ሠራዊት በኃይል ቦታውን መቆጣጠሩ በኢትዮጵያ በኩል ቁጣን አጭሯል። በውስጣዊ አለመረጋጋር ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ ወረራ ያለችውን ድርጊት ለመከላከል እርምጃ ሳትወስድ ቆይታለች። የሱዳን ከፍተኛ ባለሥልጣናት በይፋ ወጥተው በኢትዮጵያ የተያዘባቸውን መሬት ማስመለሳቸውን ሲገልጹ፣ በኢትዮጵያ በኩል ግን ለችግሩ በውይይት መፍትሔ እንዲፈለግ በተደጋጋሚ እየጠየቀች ነው። በዚህም ሳቢያ በሁለቱ መንግሥታት መካከል የነበረው መተማመን ከዚህ በፊት በነበረው ደረጃ ላይ እንዳይገኝ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪ በሕዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደትን በተመለከተ ለዓመታት ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራራቢ አቋም የነበራት ሱዳን ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ለውጦችን አሳይታለች። ግድቡን በተመለከተ ከመጀመሪያው አንስቶ ተቃውሞ የነበራት ግብፅ የምታነሳቸው ሐሳቦችን በመደገፍ ወይንም ከዚህ በፊት ስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት ሱዳን ጫና ለመፍጠር ሙከራ ስታደርግ ተስተውሏል። እንደ ኢትዮጵያ መንግሥት ገለጻ በዚህ ሳቢያ ሲካሄዱ የነበሩ ድርድሮች ግብፅ ወይም ሱዳን በሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ምክንያት ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል። በተጨማሪም የግድቡ ጉዳይ አስከ ፀጥታው ምክር ቤት ድረስ እንዲሄድ ለማድረግ ችለዋል። ስለዚህም ኢትዮጵያና ሱዳን ካላቸው ረዥም የጋራ ድንበር በተጨማሪ ግንባታው እየተጠናቀቀ ሥራ ሊጀምር በተቃረበው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ መፍትሔ የሚፈልጉለት ነገር ነው። ተቀማጭነታቸው ለንደን የሆነው የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አብዱራህማን ሰይድ እንደሚሉት ሱዳን በጄነራል ቡርሐን በሚመራ ወታደራዊ መንግሥት እጅ ከገባች የድንበርም የሆነ የሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ የማለቁ ነገር የጠበበይሆናል። የሱዳንና የግብፅ ጦር በሱዳን የሽግግር መንግሥት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የያዘው የሱዳን ጦር ኃይል ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ነበረው። ይህ አካል ከኢትዮጵያ ጋር በማያስማማው የድንበር አካባቢ ተሰማርቶ አወዛጋቢ ቦታዎች ከመቆጣጠሩ ባሻገር ከግብፅ አቻው ጋር ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ የቀረበ ግንኙነት ለመመስረት ችሏል። በዚህም የሁለቱ አገራት ሠራዊት የጦር ልምምድ ከማድረግ ባሻገር አስፈላጊ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል ስጋት እንዲፈጠር በማድረግ በአካባቢው ያለውን ውጥረት ያብሰዋል። የአማጺያንና ወታደራዊ እንቅስቃሴ በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነትና በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የደኅንነት ስጋቶች እንዳሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ይገልጻሉ። በይፋ ከሱዳን በኩል ድጋፍ ያገኛሉ ባይሉም የኢትዮጵያ ወታደራዊ ባለሥልጣንት ከሱዳን በኩል ድንበር አቋርጠው ለመግባት የሚሞክሩ ታጣቂ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን በተለያዩ ጊዜያት ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህም ኢትዮጵያ በምዕራባዊ ድንበሯ በኩል ለሚፈጸሙ ጥቃቶችና የጥቃት ሙከራዎች በሱዳን በኩል መተላለፊያ እንዳገኙ ያመለክታል። ይህንንም አገራቱ ከወዲሁ መፍትሔ ካላበጁለት ለአለመግባባት የሚያበቃ የፀጥታ ስጋት ሊሆን መቻሉ አይቀርም። የድንበር ጉዳይን በተመለከተ ቢሆን፣ ኢትዮጵያ የሱዳን ጦር ወደነበረበት ተመልሶ ሲካሄድ በነበረው ውይይት አማካኝነት መፍትሔ እንዲፈለግ ብትጠይቅም ሱዳን ግን በመሠረተ ልማት ግብታ ይዞታዋን እያጠናከረች ነው። በተደጋጋሚ እንደተዘገበውም የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ኃይሎች ጥቃት እንደደረሰበት እንዲሁም በቅርቡ ኢትዮጵያ ሠራዊቷን በድንበር አካባቢ እያሰፈረች ነው የሚል ክስ ሲቀርብ ይሰማል። ይህ ደግሞ ሁለቱ አገራት ድንበር አካባቢ ያለውን ውጥረት ሊያባብሰው ይችላል። ከሐምዶክ በኋላ ከሐምዶክ ሥልጣን መልቀቅ በኋላ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንበር ማን እንደሚመጣ አስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ጦር ኃይሉ የሱዳን መንግሥት ሥልጣንን ጠቅልሎ የሚይዝ ከሆነ በአገሪቱ ውስጥ ያለው ቀውስ የበለጠ ሊባባስ ይችላል። እንዲሁም ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ግንኙነት ላይ የጦር ኃይሉ ምን አይነት መንገድ እንደሚከተል በትክክል ባይታወቅም፣ ከዚህ በፊት በነበሩት የድንበር፣ የሕዳሴው ግድብ እና ከግብፅ ጋር ባዳበረው ግንኙነት የተነሳ ያለው ሁኔታ ላይረግብ የሚችልበት ዕድል አለ። የምሥራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኙ አብዱራህማን እንደሚሉት በቀጣናው የተለያየ ፍላጎት ያላቸው አገራት ጥቅማቸውን ለማስከበር ሲሉ የሚችሉትን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ እንዳማይሉ ይጠቅሳሉ። ይህም ጄነራል አል ቡርሐን በሥልጣን ላይ ለመቆየት በአካባቢውና በሌሎች አገራት ተጽእኖ ስር ሆነው ያልጠተበቁ እና ሰላምን የማያመጡ ውሳኔዎችን ሊሰጡ የሚችሉብት ዕድል እንዳለ ያስረዳሉ። በአጠቃላይ ግን የአብደላ ሐምዶክ ከሥልጣን መልቀቅ የሱዳን ጦር ኃይልን ከመንግሥት ኃላፊነት ገለል እንዲል የማድረጉን ተስፋ ከማጨንገፉ በተጨማሪ በአካባቢው ሰላምና ደኅንነት ላይ ተጽእኖ ይናረዋል ብለዋል የፖለቲካ ተንታኙ።", "ጠ/ሚ ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ መሪዎች ማክሮንን እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ሌሎችም የአፍሪካ መሪዎች ኢማኑኤል ማክሮን በድጋሚ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው ደስታቸውን እየገለጹ ነው። ማክሮን ትናንት በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ ተቀናቃኛቸው ማሪን ሌ ፔንን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋቸዋል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ከማክሮን ውጭ ለሁለተኛ ጊዜ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠ መሪ አልነበረም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው \"ወዳጄ ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠህ ታሪክ በመሥራትህ እንኳን ደስ አለህ! በአገራችን መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ\" ብለው ጽፈዋል። ማክሮን ቀኝ አክራሪዋን ማሪን ሌ ፔንን ማሸነፋቸው በአውሮፓ ኅብረት አባላት ዘንድ እፎይታን መፍጠሩ ተዘግቧል። ሌ ፔን ስደተኞችን የማባረር፣ ፈረንሳይን ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እንዲሁም ከአውሮፓ ኅብረት የማስወጣት ዕቅድ እንዳላቸው ሲገልጹ ቆይተዋል። ማክሮን ያሸነፉት ከድምጽ ሰጪው ሕዝብ 58.55 ከመቶ በማግኘት ሲሆን፣ ሌ ፔን ድምጽ ማግኘት የቻሉት ግን 41.45 የሚሆነውን ብቻ ነው። ለማክሮን የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ካስተላለፉ አፍሪካውያን መሪዎች መካከል የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር የሆኑት የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ይገኙበታል። የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜም በትዊተር ገጻቸው ላይ \"የማክሮን አመራር ከክፍፍል ይልቅ አንድነትን ያሰፍናል\" ብለዋል። ማክሮን ከድል በኋላ ባደረጉት ንግግር የተከፋፈለውን የፈረንሳይ ሕዝብ አንድ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ ማክሮን በተለይም በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ዘንድ ሲተቹ ቆይተዋል። የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር አለመቻላቸውም ከፍተኛ ተቃውሞን አስነስቶባቸዋል፡፡ የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ሌ ፔን ሽንፈታቸውን የተቀበሉ ሲሆን ያገኙት ድምጽ በራሱ ለፓርቲያቸው ትልቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡", "ህወሓት ተኩስ ለማቆም ቅድመ ሁኔታዎቹን አሻሽሎ አቀረበ የፌደራል መንግሥቱ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን አቅርበው የነበሩት የትግራይ ኃይሎች በድርድር ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም ለማድረግ የተሻሻለ አዲስ ቅድመ ሁኔታ አቀረቡ። በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ \"የትግራይ መንግሥት አቋም\" በሚል የወጣው መግለጫ፤ “በፍጥነት እየተቀያየረ ያለው ወታደራዊ እና ፖሊቲካዊ ሁኔታ በአገሪቱ ሰላም እና ደኅንነት ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ ከግምት በማስገባት የትግራይ መንግሥት ከዚህ ቀደም የተኩስ አቁም ለማድረግ ያቀረባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሻሻል አስፈልጎታል\" ብሏል። ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎቱን አለኝ ያለው ህወሓት፤ ዳግም ባወጣው የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት እና የሽግግር ሂደት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል። የአቋም መግለጫው የትግራይ መንግሥት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎቱን እና ምርጫውን ሲያንጸባርቅ ቆይቷል ብሏል። የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ትግራይን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የትግራይ ኃይሎች በርካታ የክልሉን ስፍራዎች ተቆጣጥረው የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ማውጣታቸው ይታወሳል። ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በወጣው ቅድመ ሁኔታ ላይ በኤርትራ ወታደሮች እና በአማራ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን ምርመራ እንዲደረግባቸው እና እነዚህ ኃይሎች የትግራይ ስፍራዎችን ለቀው ይውጡ ብሎ ነበር። የተቋረጡ መሠረተ ልማቶችን መልሰው ሥራ እንዲጀምሩ፣ ዓለም አቀፍ በረራዎች ትግራይ ከሚገኙ አየር ማረፊያዎች በቀጥታ በረራ ያደርጉ፣ ያለ ምንም ገደብ የሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብበት መንገድ እንዲመቻች እና የክልሉ በጀት እንዲለቀቅ የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አቅርቦ ነበር። በአዲሱ ቅድም ሁኔታ ህወሓት ምን አለ? ዛሬ የአቋም መግለጫው ይፋ የተደረገው በፓርቲው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ይፋዊ የትዊተር ገጽ ሲሆን፤ ከአቋም መግለጫው በታች ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም. የሚል ቀን ተመልክቷል። የትግራይ መንግሥት ወቅታዊ የአቋም መግለጫ በሚል ርዕስ በወጣው መግለጫ ላይ፤ \"አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት አገሪቱን መምራት የሚያስችለው ሕገ መንግሥታዊ መብት የለውም\" ካለ በኋላ፤ በአገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ እና ሕገ መንግሥታዊ ችግሮችን ለመፍታት ዋና የፖለቲካ ተዋናዮችን ያቀፈ አካታች ፖለቲካዊ ሂደት እና የሽግግር ሥርዓት እንዲካሄድ ጥሪ እናቀርባለን ይላል የመጀመሪያው ነጥብ። ከዚህ በተጨማሪም የትግራይ መንግሥት በድርድር የሚደረስ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው አለባቸው ሲል ከዚህ ቀደም ካወጣው የአቋም መግለጫ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ስድስት ነጥቦችን ዘርዝሯል። ከእነዚህ ነጥቦች የመጀመሪያው በትግራይ ተቋርጠው የቆዩ እንደ ኤሌክትሪክ፣ ቴሌኮምዩኒኬሽን፣ የባንክ፣ የትራንስፖርት፣ የጤና እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በፍጥነት መጀመር አለባቸው የሚለው ነው። የአገር መከላከያ አባላት የሆኑትን ጨምሮ ማንነታቸውን መሠረት ተደርጎ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ በመላው አገሪቷ የትግራይ ተወላጆች የጅምላ እስር ይቁም ይላል። የ2013 ዓ.ም. እና የ2014 ዓ.ም. በጀት በፍጥነት መለቀቅ አለበት፣ የኤርትራ ጦር እና የአማራ ኃይሎች ከትግራይ ይውጡ (ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ መረጋገጥ አለበት) ብሏል። የሰብዓዊ እርዳታ ለማድስ ለሁሉም አይነት የትራንስፖርት አማራጮች በርካታ መተላለፊያ ኮሪደሮች ክፍት መደረግ አለባቸው የሚሉት ቅድመ ሁኔታዎች በአቋም መገለጫው ላይ ሰፍሯል። የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ተፈጻሚ ሆነው ይህም በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት ይላል መግለጫው። በህወሓት የሚመራው የክልሉ መንግሥት ከመንበሩ ከተወገደ በኋላ በፌደራል መንግሥቱ የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሰኔ 21/2013 ዓ.ም የአገሪቱ ፌዴራል መንግሥት \"ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ\" የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቀረቡ ይታወሳል። የፌደራሉ መንግሥትም የጊዜያዊ አስተዳደሩን ጥያቄ ተቀብሎ በክልሉ የሚገኙ አርሶ አደሮች በክረምቱ ወራት የእርሻ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ እና የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንዲቻል የተናጠል ተኩስ አቁም አውጃለሁ ብሎ ነበር። የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው የህወሓት ኃይሎች በአገሪቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በተካሄደ ወታደራዊ ዘመቻ ከሥልጣኑ ተወግዶ የነበረ ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳደር ሕገወጥ ብሎ መበተኑ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክልሉ ገዢ ፓርቲ የነበረውን ህወሓትን ሽብርተኛ ቡድን ብሎ ሰይሞታል። የፌደራል መንግሥቱ የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ሠራዊቱን ከትግራይ ካስወጣ በኋላ ወደ መቀለ ተመለሱት የህወሓት አመራሮች ግን \"በሕዝብ የተመረጥን ሕጋዊ የክልሉ አስተዳዳሪዎች ነን\" ማለታቸው ይታወሳል።", "\"ፈጣሪ ብቻ ነው ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችለው\"የብራዚሉ ፕሬዚዳንት የብራዚሉ ቀኝ ዘመም ፕሬዝዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ የአገሪቱ ነጻነት በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር በርካቶችን ያስገረመና አንዳንዶችን ደግሞ ያበሳጨ መልእክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንቱ በሳኦ ፖሎ ባደረጉት ንግግር '' ፈጣሪ ብቻ ነው ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችለው'' ብለዋል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ላይ ትችት የሰነዘሩ ሲሆን እነዚህ ተቋማት እሳቸውን እና የፖለቲካ ወዳጆቻቸውን እያጠቁ እንደሆነ ገልጸዋል። በቅርቡ የአገሪቱ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ላይ ምርምራ እንዲደረግ ፈቃድ መስጡ የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንት ቦልሶናሮ በሚያደርጓቸው በስሜት በተሞሉ ንግግሮች ትችት የሚሰነዝሩባቸውን ሰዎች ከማብጠልጠል ባለፈ የተለያየ አይነት ስም በመስጠትና ሁሌም ተጠቂ እንደሆኑ ለማመላከት ሲጥሩ ይታያሉ። ደጋፊዎቻቸው ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ይህንን ንግግራቸውን በሚያደርጉባት ሳኦ ፖሎ ከተማ የብራዚልን ባንዲራ በመያዝ ተሰባስበዋል። ድጋፋቸውንና ሁሌም አብረዋቸው እንደሆኑም ሲገልጹ ታይተዋል። ነገር ግን በቅርቡ የተጀመረባቸው ምርመራ እና እየጨመረ የመጣው ከስልጣን ይውረዱ ጥያቄ ፕሬዝዳንቱ በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ጠንከር ያለ እና ቁጣ የተቀላቀለበት መልዕክት እንዲያስተላልፉ አድርጓቸዋል። ምንም እንኳን ብራዚል ምርጫ የምታካሂደው በመጪው የፈርንጆቹ ዓመት 2022 ጥቅምት ወር ላይ ቢሆንም ከወዲሁ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ተቀባይነታቸውና ድጋፋቸው እየቀነሰ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። እንዳውም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅተኛ ድጋፍ እንዳላቸው መረጃዎች ጠቁመዋል። አትላስ ኢንስቲትዩት የተባለው ተቋም በሰራው ጥናት መሰረት 61 በመቶ የሚሆኑት ብራዚላውያን የአገራቸውን መንግስት መጥፎ አልያም እጅግ በጣም ጥፎ ነው ብለው የሚያስቡ ናቸው። ይህ ቁጥር ደግሞ ፕሬዝዳንቱ በአውሮፓውያኑ 2019 ወደ ስልጣን ሲመጡ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ23 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ፕሬዝዳንቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በአግባቢ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ከስልጣናቸው ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም የታችኛው ኮንግረስ አፈ ጉባኤ ውሳኔውን በመቃወማቸው ቦልሶናሮ በስልጣን እንዲቆዩ ሆኗል። ይህንን ተከትሎም ፕሬዝዳንቱ ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነና ኮንግረሱም ሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እሳቸውን ከስልጣን ለማስወገድ እየሰሩ እንደሆነ በተጋጋሚ ይገልጻሉ። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንቱ በርካታ ደጋፊዎቻቸውን የሚወክሉ የኢቫንጀሊካል ሃይማኖታዊ መሪዎችን ባገኙበት ወቅት ሶስት ምርጫዎች እንዳላቸው ነግረዋቸው ነበር። ''ወደፊት ሶስት ምርጫዎች ብቻ ናቸው ያሉኝ፤ በቁጥጥር ስር መዋል፣ መገደል ወይም ደግሞ ማሸነፍ'' ብለዋል። የብራዚል የነጻነት ቀን ላይ ባደረጉተው ንግግርም ይህንኑ አስተያየታቸውን የደገሙ ሲሆን ''ከዚህ በኋላ እኔን ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችለው ፈጣሪ ብቻ ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል። እስከ 140 ሺ የሚደርሱ የፕሬዝዳንቱ ደጋፊዎችም በስነስርአቱ በመገኘት የአገራቸውን ባንዲራ እያውለበለቡ ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ድጋፊ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ ቀደም ብለዋ ወደ ዋና ከተማዋ ብራዚሊያ ተጉዘው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸውን አግኝተዋል። በወቅቱም በርካታ ፖሊሶች በቦታው የነበሩ ሲሆን ደጋፊዎቻቸውም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። ነገር ግን ከነበረው የፖሊስ ቁጥር አንጻር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን መቆጣጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። በርካታ የቦልሶናሮ ደጋፊዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ኮንግረስ እንዲዘጉ የጠየቁ ሲሆን ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ፕሬዝዳንቱን እያጠቁ ነው ሲሉም ይከሳሉ።", "በቶማስ ሳንካራ ግድያ በቀድሞው የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝደንት ላይ የ30 ዓመት እስር ተጠየቀ በቀድሞ በቡርኪና ፋሶ መሪ ቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ ናቸው የተባሉት የቀድሞው የአገሪቱ መሪ ብሌስ ኮምፓዎሬ ላይ የ30 ዓመት የእስር ቅጣት ተጠየቀባቸው። የቡርኪና ፋሶ ዐቃቤ ሕግ የቀድሞው ፕሬዝደንት በለውጥ ሃዋሪያው ቶማስ ሳንካራ ግድያ ተሳታፊ በመሆናቸው የሦስት አስርት ዓመታት እስር ሊበየንባቸው ይገባል ብሏል። ቶማሳ ሳንካራ እአአ 1987 ላይ መገደላቸው ይታወሳል። የፈረንሳይ መንግሥት የቶማስ ሳንካራን ግድያ የሚመለከት ዝርዝር የጦር ሠራዊት ሰነድ ይፋ ለማድረግ መስማማቱን ተከትሎ በቀድሞው መሪ ግድያ ዙሪያ ባለፈው ዓመት ምርመራ መጀመሩ ይታወሳል። የቀድሞ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝደንት ቶማስ ሳንካራ በአገሪቱ መዲና ዋጋዱጉ ውስጥ በ37 ዓመታቸው ከተገደሉ በኋላ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዷል። ይህንንም ተከትሎ በዚያው ዓመት ብሌስ ኮምፓዎሬ በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን መጥተዋል። ፕሬዝደንት ኮምፓዎሬ በሕዝባዊ አመጽ ከመንበራቸው እስተወገዱበት እአአ 2014 ድረስ ለ27 ዓመታት ቡርኪና ፋሶን መርተዋል። ኮምፓዎሬ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ከአገር ተሰደው መኖሪያቸውን በጎረቤት አገር አይቮሪ ኮስት አድርገዋል። ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን እየተመለከተ ያለው የጦር ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝደንት በሌሉበት \"በአገር ደኅንነት ላይ ጥቃት በማድረስ\" ወንጀል ጥፋተኛ እንዲላቸው ጠይቋል። ከዚህ በተጨማሪም የቶማስ ሳንካራ እና 12 የሳንካራ ባልደረቦች ግድያን በማቀነባበር ኮምፓዎሬ እንዲጠየቁ ከሳሾች ጠይቀዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት የሳንካራ የቅርብ ወዳጅ የነበሩ ሲሆን በሳንካራ ግድያ ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ የለኝም ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ ቶማስ ሳንካራን የገደለ የኮማንዶ ቡድን መርተዋል የተባሉት ሃይሲንዝ ካዳንዶ በ30 ዓመት እስር እንዲቀጡ እና ቶማስ ሳንካራ ከሥልጣን ባስወገደው መፈንቅለ መንግሥት ውስጥ ተሳታፊ ነበሩ የተባሉት ጊልበርት ዲኤንዴሬ በ20 ዓመት እንዲቀጡ ጠይቋል። ጊልበርት ዲኤንዴሬ እአአ 2015 ላይ በተፈጸም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጥፋተኛ ተብለው የ20 ዓመት እስር ተበይኖባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በቶማስ ሳንካራ ጉዳይ በአካል ከችሎት ፊት ቀርበዋል።", "ከደኅንነት ኃላፊው ጉብኝት በኋላ ጠ/ሚ ዐቢይ ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት አባላት ጋር መወያየታቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያው የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ወደ ሱዳን አቅንተው ከአገሪቱ ምክትል ወታደራዊ መሪ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የልዑካን ቡድኑን አባላት ሰኞ ኅዳር 12/2015 ዓ.ም. በጽህፈት ቤታቸው ባገኙበት ወቅት በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች መነጋገራቸው ተገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በታላቁ ሕዳሴ ግድብና በድንበር ይገባኛል ምክንያት እንዲሁም በትግራይ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ ግንኙነታቸው ሻክሮ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ ከሚካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሱዳንን አንስተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ሱዳን ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ባገረሸው ጦርነት ውስጥ ምንም አይነት ሚና እንዳልነበራት ተናግረው ነበር። የሁለቱ አገራት መሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገናኝተው በግንኙነታቸው ዙሪያ መወያየታቸው የተዘገበ ሲሆን፣ የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን ባለፈው ጥቅምት ወር በጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ ባሕር ዳር በመገኘት ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸው ይታወሳል። ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ካርቱም ውስጥ ከአገሪቱ ምክትል ወታደራዊ መሪ ሌፍተናንት ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሐሜቲ) ጋር መነጋገራቸውን የሱዳን መንግሥት ዜና ወኪል ዘግቧል። በውይይታቸውም በአገራቱ መካከል በደኅንነት እና በሌሎች ዘርፎች ስለሚደረግ ትብብር መወያየታቸውንና ሱዳንም በመንግሥት እና በህወሓት መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት ጄኔራሉ አድናቆታቸውን መግለጻቸው ተዘግቧል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሚዋሰኑበት የአል ፋሽካ ለም የእርሻ መሬት ላይ ለዓመታት የቆየ የይገባኛል ጥያቄ የነበረ ሲሆን፣ ከሁለት ዓመት በፊት ትግራይ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ጊዜ ሱዳን ሠራዊቷን አሰማርታ አካባቢውን መቆጣጠሯ ይታወሳል። በጦርነቱ ወቅትም ከሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው የሚገቡ ታጣቂዎች እንዳሉ በባለሥልጣናት ወቀሳ ሲሰነዘር ነበር። በትግራይ ጦርነት ተወጥራ የቆየችው ኢትዮጵያ የሱዳን ሠራዊት ከያዛቸው የድንበር አካባቢዎች ለቅቆ እንዲወጣ እና በንግግር ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ የቆየች ቢሆንም፣ ከሱዳን በኩል ግን ግዛቱ እራሷ መሆኑን በመግለጽ ይዞታዋን ስታጠናክር ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ጄኔራል አል ቡርሐን ባለፈው ዓመት ኬንያ ውስጥ በተደረገው በኢጋድ ስብሰባ፣ ከወር በፊት ባሕር ዳር ላይ በጣና ፎረም እና ባለፈው ሳምንት ደግሞ ግብፅ በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ መገናኘታቸው ተዘግቧል።", "ምርጫ 2013፡ የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን መክሰሱን አስታወቀ ከሐረሪ ክልል ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅ አባላት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አባላት ምርጫ ላይ መሳተፍ አይችሉም የሚለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱን የሐረሪ ክልል አስታወቀ። የሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊና የፖለቲካና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ኡመር ለቢቢሲ እንደገለፁት ቦርዱ \"ሕጋዊ አግባብን አልተከተለም፤ የሕግ ጥሰት ፈፅሟል\" በማለት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት መክሰሳቸውን አስታውቀዋል። የሐረሪ ክልል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ከመውሰዱ በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት \"ለምርጫ ቦርድ የላካችሁት ሰነድ ማህተም የሌለውና ፍትሃዊ ባለመሆኑ ውድቅ ተደርጓል\" በሚል አቤቱታ ማቅረባቸውን ይናገራሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰነዶቹን ማህተም አድርጎ ለምርጫ ቦርድ ቢልክም ውሳኔው ባለመቀልበሱ ወደ ፍርድ ቤት ማምራታቸውን ይናገራሉ። የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት፣ የሐረሪ ሕዝባዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የሐረሪ ሕዝብ የክልሉ ምክር ቤት አካል ለሆነው ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ እንዲመርጡ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄያቸውን አቅርበው ነበር። ጥያቄው መነሻውን ያደረገው መጋቢት 6/1987 የሽግግር መንግሥቱ የተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን ውሳኔ ተንተርሶ መሆኑንም ከምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ የሐረሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 50 ቁጥር 2 እንደሚያትተው የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሆኑትና 14 አባላት ያሉት \"የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አባላት በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎችና ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ይመረጣል\" የሚለውን መሰረት ያደረገ እንደሆነ አቶ አብዱልሃኪም ያስረዳሉ። ምርጫ ቦርድም ክልሉ ያቀረባቸውንና በ1987 የሽግግር መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት የወሰናቸውን ውሳኔዎችና ሰነዶቹን ከሕገ መንግሥት አንፃር እንደመረመረ አስታውቆ፤ ከክልሉ ውጭ ያሉ የሐረሪ ተወላጆች በመጪው ምርጫ የመሳተፋቸውን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን ሚያዝያ 1/2013 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ቦርዱ ለዚህም ሕገ መንግሥቱን የጠቀሰ ሲሆን \"ቦርዱ በሕገ መንግሥቱ መሰረት በአንድ ክልል የመንግሥት መዋቀር ውስጥ የሚገኙ የምክር ቤት አባላት መመረጥ የሚኖርባቸው በክልሉ ድምፅ መስጠት በሚችሉ ነዋሪዎች ነው\" በማለት ገልጿል። ጨምሮም \"ከዚህ ውጭ ሕገ መንግሥቱ አንድ ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ ብሔረሰብ ለክልል ምክር ቤቶች ሲያስመርጥ ከክልሉ ውጭ ያሉ የብሔረሰብ አባላት እንዲመርጡ የደነገገው እንዲሁም ለዚህ ብሔረሰብ አባላት ለብቻው የተለየ አሰራር መተግበር የሚያስችል በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለ ድንጋጌ በምርመራው ቦርዱ ያገኘው ነገር የለም\" ብሏል። የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ጉባኤ ሚያዝያ 3/2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር። \"ምርጫ ቦርድ ይህንን የመወሰን ስልጣን የለውም\" የሚሉት አቶ አብዱልሃኪም እንደ ምክንያትነት የሚያቀርቡትም የሽግግር መንግሥቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወሰነውን ውሳኔና የክልሉን ሕገ መንግሥት በመጥቀስ ሲሆን \"በሕግ የተደነገገ ነው\" ይላሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1987 ውሳኔ ባልተሻረበት ሁኔታ የክልሉ ሕገ መንግሥት በግልፅ ባስቀመጠበት ሁኔታ \"እነዚህን ሕጎች መፃረሩ ከአንድ ትልቅ ተቋም የሚጠበቅ አይደለም\" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫ ቦርዱ የሽግግር መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከክልሉ ውጭ ነዋሪ በሆኑ የብሔረሰቡ አባላት ይመረጣል የሚለውን ውሳኔ የሚደግፍ ሕገ መንግሥታዊ አንቀፅ አለመጠቀሱን ምርጫ ቦርድ ገልጿል። ይህንን በተመለከተም አቶ አብዱልሃኪም እንደሚሉት ምርጫ ቦርድ የአገሪቱንና የክልሎችን ሕገ መንግሥት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰራ ጠቅሰው፤ አንዳንድ የፌደራል ሕገ መንግሥት ላይ ያልተጠቀሱ ጉዳዮች በክልል ሕገ መንግሥቶች ላይ በዝርዝር ሊቀመጡም እንደሚችሉ ይናገራሉ። እንደ ምሳሌነትም የደቡብ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤትን ይጠቅሳሉ። የብሔረሰቦች ምክር ቤት በፌደራል ሕገ መንግሥት ባይቀመጥም በክልሉ ሕገ መንግሥት የተቀመጠና ምርጫ ቦርድም ይህንኑ መነሻ አድርጎ ነው ምርጫውን እያስፈፀመ ነው ያለው ይላሉ። ቦርዱ የክልሎችን ሕገ መንግሥቶች ባከበረ መልኩ ነው ሲሰራ የነበረው። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛውም የአገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ክልሎችን (ጣቢያዎችን) ሲያቋቁም መነሻው የፌደራል እንዲሁም የክልሉ ሕገ መንግሥት እንደሆነ ያወሳሉ። ምርጫ ቦርድ ከዚህም በተጨማሪ መጋቢት 6/1987 የሽግግር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ የምክር ቤቱ ማህተም ያረፈበት ስላልሆነ ውሳኔው አግባብ አለመሆኑ አመልካች ነው፤ እንዲሁም የሰነዱን ተቀባይነት ችግር ላይ ጥሎታል ብሏል። ሰነዱ ማህተም የለውም ወይ? የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የቀረበላቸው አቶ አብዱልሃኪም በበኩላቸው ለምርጫ ቦርድ ስለቀረቡ ሰነዶች ምላሽ አላቸው። ስድስት ገፆች ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር የተያያዘ ሲሆን መሸኛ ደብዳቤው ላይ ቀን፣ ቁጥርና ማህተም አለው። ከዚህም በተጨማሪ በጊዜው የነበረው ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት 17 ገጽም ተያይዟል። የተያያዙት ሰነዶች ላይ ምንም አይነት ማህተም እንደሌለው የሚናገሩት አቶ አብዱልሃኪም \"በዚህኛው ውሳኔ ብቻ የተፈጠረ ነው? ወይስ ከዚህም በፊት የነበሩ ውሳኔዎች ተመሳሳይ ሂደት ነው ያላቸው? አሰራሩን መፈተሽ ያለበት ምርጫ ቦርድ ነው\" ይላሉ። እንደ አቶ አብዱልሃኪም ምርጫ ቦርድ ሰነዶቹ ማህተም የላቸውም ከተባለ ውሳኔውን ከማሳለፉ በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት አቅርቦ ጠይቆ፣ ፈትሾና መርምሮ በዚያ መሰረት መወሰን ይገባው ነበር ይላሉ። \"በዚያ መነሻነት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ መሆን አለመሆኑን ሲያረጋግጥላቸው ምላሹን ከሰሙ በኋላ ውሳኔ መወሰን በተገባቸው ነበር። ተቋማዊ አሰራር ያልተከተለ ነው\" ይላሉ። የሐረሪ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰነዶቹ ተቀባይነት እንደሌላቸው ጠቅሶ አቤቱታ ማስገባቱን ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ የ1987 ሰነዶችን መነሻ በማድረግ የራሱንም ውሳኔ ጨምሮ ክልሉ ያቀረበለትን ደብዳቤ ጨምሮ ወደ 39 ገጽ በራሱ ማህተም ለምርጫ ቦርድ መላኩንም ይናገራሉ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ \"የወሰንነውን ውሳኔ መልሰን የምናይበት አግባብ ስለማይኖር ሌላ ውሳኔ የሚሰጥ አካል ውሳኔ የሚሰጥበት መንፈስ ያለው አይነት ምላሽ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ልኳል\" ይላሉ። በሕዝብ ተወካዮች በኩል ያለው ጉዳይ በራሱ እየሄደ ቢሆንም በፍርድ ቤትም በኩል እንዲወሰን በመሻት ክልሉ መክሰሱን ይናገራሉ። በሌላ በኩል አቶ አብዱልሃኪም ምርጫ ቦርድ ባለፉት አምስት ብሔራዊ ምርጫዎች ይጠቀምበት የነበረውን መመሪያ \"በዚህ ውሳኔ እውቅናን ነፍጓል\" ቢሉም ቦርዱ በበኩሉ መመሪያውን ከጽህፈት ቤቱ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ዝርዝር መመሪያው የ1987ቱን የተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት ያደረገና የባለፉትንም አምስት ምርጫዎች በዚሁ መልኩ ሲያስፈጽም የነበረ መሆኑ ተጠቅሷል። አቶ አብዱልሃኪም በዚህ አባባል አይስማሙም \"ሥራ ላይ ያሉት መመሪያዎች የእኔ አይደሉም፤ አላውቃቸውም ማለቱ ትክክል አይደለም\" ይላሉ። ነገር ግን ቦርዱ በፃፈው ደብዳቤ እንደጠቀሰው ምንም እንኳን ለሐረሪ ጉባኤ የሚመረጡ ተወካዮች ከክልሉ ውጭ ባሉ የብሔረሰብ አባላት ምርጫ ቦርድ ሲያስመርጥ ቆይቶም ከሆነ ሕገ መንግሥታዊና የምርጫ ሕጉ መሰረት የሌላቸውን አሰራሮች እንደማይከተል አስታውቋል። ቦርዱም በምርጫ ማሻሻያው እንዲህ አይነት ልምዶች እንዲቀሩ እየሰራ ነው ብሏል። ምንም እንኳን ላለፉት አስርት ዓመታት የተተገበረ ጉዳይ ነው ብሎ ቦርዱ ቢወስን \"ሌሎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሔረሰቦች ከክልላቸው ውጭ ያሉ አባሎቻቸው በምርጫው እንዲሳተፉ ቢጠይቁ ቦርዱ ልፈፅም አልችልም ቢል የቦርዱን በፍትሐዊነት እና በገለልተኛነት ምርጫን የማስተዳደሩ ጉዳይ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል\" ይላል። አቶ አብዱልሃኪም በበኩላቸው \"ባለው ነገር ላይ መጨመር ነው እንጂ ሌሎች አናሳ ብሔሮችም እንዲህ አይነት የመብት ጥያቄ ቢጠይቁኝ መመለስ ስለማልችል የናንተንም በዚህ ወቅት ማስተናገድ አልችልም የሚለው ትክክል አይደለም\" ይላሉ። ኢትዮጵያም ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአካባቢያቸው የሚመርጡበት አሰራር እንዳለና በሌሎች አገራትም እንዲሁ በየኤምባሲዎቻቸው የሚመርጡበት ሁኔታ ልምድ መኖሩን ጠቅሰው የ \"ሃረር የተለየ እንዳዳልሆነ\" ይናገራሉ። \"አገራችን ላይ ሕጉ አለ፤ ይሄንንም በተመለከተ ምርጫ ቦርድ መመሪያ ያወጣል የሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ አለ፤ የምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅም ላይ አለ\" ይላሉ አቶ አብዱልሃኪም። \"ያንን ከመተግበር አንፃር የኢኮኖሚ አቅማችንና የእድገታችን ደረጃ ገና ስለሆነ ይሄ የመተግበርና ያለ መተግበር ጉዳይ ነው\" ሲሉ ያክላሉ። የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት ከሁለት ጉባኤዎች የተዋቀረ ሲሆን እነዚህም የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ናቸው። የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ 22 አባላት ሲኖሩት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ደግሞ 14 የሐረሪ ብሔረሰብ አባላትን የያዘ ነው። ምርጫ ቦርዱ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆች በጉባኤው ምርጫ መሳተፍ አይችልም የሚል ውሳኔን ቢያስተላልፍም የሐረሪ ጉባኤ 14 መቀመጫ በሐረሪ ብሔረሰብ አባላት የመያዙን ሁኔታ አይቀይረውም። ጉባኤው ከሐረሪዎች ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ በተያያዘ ማንነትና ህልውናቸው እንዲቀጥል ከማድረግ ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን የሚያስተላልፍና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆችን የሚያስተሳስር እንደሆነ አቶ አብዱልሃኪም ይናገራሉ።", "የቤንያሚን ኔታንያሁ የሙስና ክስ በቅጣት ድርድር ሊቋጭ እንደሚችል ተገለጸ በሙስና የተከሰሱት የእስራኤል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የፍርድ ሂደቱን ለማስቆም የቅጣት ድርድር እያደረጉ እንደሆነ ቢቢሲ ከቅርብ ምንጭ ተረድቷል። በቅጣት ድርድሩ መሰረት የ72 አመቱ ቤንያሚን ኔታንያሁ በተወሰነ ደረጃ ጥፋተኝነታቸውን ማመን የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህም ከሆነ ወንጀላቸው ተቀንሶ በእስር ፋንታ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሳተፉ ሊያደርግ የሚያስችል ነው። ኔታንያሁ በበኩላቸው ጥፋተነኝነታቸውን ካመኑ ከፖለቲካው ዓለም እንዲገለሉ የሚያስገድደውን ይህንን የቅጣት ድርድር ለመቀበል መቃወማቸውን በተመለከተ ሪፖርቶች ወጥተዋል። እስራኤልን ለረዥም ዘመን ያስተዳደሯት ቤንያሚን ኔታንያሁ ባለፈው አመት ከተካሄደው ምርጫ በኋላ ራሳቸውን ከፖለቲካው ገለል አድርገዋል። በእስራኤል ፓርላማ ውስጥ ትልቁ ፓርቲ የሆነው የቀኝ ክንፉ ሊኩድ መሪ ሲሆኑ አገራቸውንም ለ15 ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል። ባለፉት አምስት አመታት የስልጣን ዘመናቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች ፖሊስ ምርመራ የከፈተባቸው ሲሆን የፍርድ ሂደቱም በአውሮፓውያኑ 2020 ተጀምሯል። በጉቦ፣ በማጭበርበር እና እምነት በማጉደል የተከሰሱት ቤንያሚን ኔታንያሁ እሳቸው ግን ክሶቹ ፖለቲካዊ አላማ አላቸው በማለት ውድቅ አድርገዋቸዋል። ኔታንያሁ ከጠቅላይ አቃቤ ህግ አቪቻይ ማንደልብሊት ጋር በቅጣት ድርድር ላይ መወያየታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች በቅርብ ቀናት ውስጥ ከእስራኤል ሚዲያዎች ተስምተዋል። ለቅጣት ድርድሩ ጋር ቅርበት ያላቸውና ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጭ እሁድ እለት የቅጣት ድርድሩ መካሄዱን አረጋግጠዋል ሲሉ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል። የእስራኤሉ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ኔታንያሁ በተወሰነ መልኩ የጥፋተኝነት ደረጃን መቀበላቸውን ቤተሰቦቻቸው ቢቃወሙም ጠበቆቻቸው ውይይቱን እንዲቀጥሉ ማዘዛቸውን ተናግረዋል። የመጀመሪያው ክስ ከሀብታም ወዳጃቸው ሻምፓኝ፣ ሲጋራና ሌሎችም ውድ ስጦታዎች በጉቦ ተቀብለዋል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዜና ሽፋን ለማግኘት ከጋዜጣ አሳታሚ ጋር ተዋውለዋል የሚል ነው። ከሁሉም ክሶች ከባዱ የተባለው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ለዜና ሽፋን ሲሉ አውራ የቴሌኮም ድርጅትን የሚጠቅም ሕግ አስተዋውቀዋል የሚለው ነው። በወቅቱ ሕጉ በባለሙያዎች የተደገፈ እንደሆነ የገለጹት ኔታንያሁ ይህ ክስ እስከ አስር ዓመት የሚሆን እስር እንዲሁም የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣቸዋል ተብሎ ነበር። እኚሁ ምንጭ እንደተናገሩት ክሶቻቸው እንዲቋረጡ ጥፋተኝነታቸውን እንዲያምኑና \"የሞራል ውድቀት\" የተባለውን ክስ እንዲቀበሉ ተጠይቀዋል። በዚህም መሰረት ለሰባት ዓመታት በፖለቲካው የሚታገዱ ሲሆን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን እየተቃወሙ ነው ተብሏል። በፖለቲካዊ መሰረታቸው ጠንካራ ድጋፍ ያላቸው ኔታንያሁ አሁን ያለውን ጥምር መንግሥት ተቃውመው በቅርቡም ወደ ስልጣን የመመለስ አላማ እንዳላቸው ተናግረዋል።", "ሩሲያ ኒዩክሌር የመታጠቅ አቅም ያላቸው ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለቤላሩስ ለመስጠት ቃል ገባች ሩሲያ በሚቀጥሉት ወራት ኒዩክሌር የመታጠቅ አቅም ያላቸውን አጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለመተኮስ የሚያስችል ሥርዓት ወደ አጋሯ ቤላሩስ እንደምትልክ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ። ፕሬዚደንቱ እንዳሉት ኢስካንድር- ኤም የተበላው ሥርዓት የባልስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን መተኮስ የሚያስችል ሲሆን እስከ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ኢላማዎችን መምታት ይችላል። የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቱን ባለፈው የካቲት ወር ላይ በዩክሬን ላይ ወረራ ማወጃቸውን ተከትሎ በሩሲያና በምዕራባውያኑ መካከል ያለው ውጥረት ጨምሯል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ፑቲን ስለ ኒዩክሌር የጦር መሣሪያዎች ብዙ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህንን ንግግራቸውን አንዳንዶች የምዕራብ አገራት ጣልቃ እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ያለመ ነው ብለውታል። ፑቲን  የሩሲያ የወደብ ከተማ በሆነችው ሴንት ፒተርስበርግ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ከቤላሩስ ፕሬዚደንት ሉካሽንኮ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ሩሲያ የቤላሩስ ኤስዩ-25 የጦር አውሮፕላኖች የኒዩክሌር የጦር መሣሪያዎችን መያዝ እንዲችሉ ለማድረግ ትረዳለች ብለዋል። ፕሬዚደንት ፑቲን ከአቻቸው የቤላሩሱ ፕሬዚደንት አሌክሳንደር ሉካሸንኮ ጋር ባደረጉትና ቅዳሜ ዕለት በቴሌቪዥን በተላለፈው ስብሰባ ላይ “ ወስነናል። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ለቤላሩስ ኢስካንደር- ኤም የተባለውን የሚሳኤል መተኮሻ ሥርዓት እናስረክባለን” ብለዋል። መሣሪያዎቹን የማስረከብ ዝርዝር ሂደቱን በተመለከተ የሁለቱ አገራት መከላከያ ሚኒስትሮች እንደሚሰሩም ፕሬዚደንቱ አክለዋል። ኢስካንደር ሚሳኤሎች የኔቶ አባል በሆኑት ሉትዌንያ እና ፖላንድ መካከል በምትገኘው የሩሲያ ባልቲክ ባህር ዳርቻዋ ካሊኒንግራድ ተሰማርተዋል። ሁለቱ ፕሬዚደንቶች የሉትዌኒያ አንዳንድ እቃዎች ወደ ካሊኒንግራድ እንዳይጓዙ ለመከለካል ባደረገችው ውሳኔ ላይ የተወያዩ ሲሆን እርምጃው ሞስኮን አስቆጥቷል። የቤላሩሱ ፕሬዚደንትም የሉትዌንያ እርምጃ “ የጦርነት አዋጅ እና ተቀባይነት የሌለው ነው” ብለዋል። ሉትዌንያ ግን እርምጃዋ ተፅዕኖ የሚያሳድረው ለወትሮው በወደቡ ከሚተላለፉ የሩሲያ ምርቶች መካከል አንድ በመቶ በሚሆነው ላይ  ነው ስትል ሩሲያ ካሊኒንግራድ እንቅስቃሴውን አግዳለች ስትል ያቀረበችውን ክስ አጣጥላለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ እሁድ ዕለት ጠዋት በዩክሬን ኪዬቭ በርካታ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን የከተማዋ ከንቲባ ቫይታሊ ክሊሽኮ ተናግረዋል። “አምቡላንሶችና የነፍስ አድን ሰራተኞች በሥፍራው ይገኛሉ። በሁለት ሕንጻዎች ላይ የነፍስ ማዳንና ሰዎችን የማስወጣት ሥራ እየተከናወነ ነው “ ብለዋል ከንቲባው። ኤኤፍፒ የዜና ወኪል በከተማ የሚገኘው የመኖሪያ ቤት ሕንጻ መመታቱን ዘግቧል። ለሳምንታት ከባድ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ ዩክሬን የሩሲያ ኃይሎች ቅዳሜ ዕለት ምሥራቃዊ ከተማዋን ስቨሮዶንስክ “ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን” አስታውቃለች። ይህ ማለት ሩሲያ የዩክሬንን ሰፊውን የኢንደስትሪ ግዛት፣ዶንባስን የሚፈጥሩትን ሉሃንስክ ክልል ሙሉ በሙሉ በሚቻል ደረጃ እንዲሁም አብዛኛውን ዶንስክ ክልል ተቆጣጥራለች ማለት ነው። የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ቅዳሜ ዕለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ በሩሲያ የተያዙ ከተሞቻቸውን ለመመለስ ቃል ገብተዋል። ሆኖም ከሩሲያ ጋር ያለው ጦርነት በስሜታዊነት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ መድረሱንና ምን ያህል ድብደባዎች እና ኪሳራዎች እንደሚኖሩ እንደማያውቁ ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ ተናግረዋል። አርብ ዕለት ምሽት ሩሲያ ኢላማዋ ወደሆኑት ሰሜንና ምዕራብ ዩክሬን አካባቢዎች የሚሳኤል ጥቃት ከፍታለች። በዚህ ጥቃት በምዕራብ ኪዬቭ ሳርኒይ በተባለች ከተማ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች በፍርስራሽ ሥር ሳይቀበሩ እንዳልቀረ የአካባቢው ባለሥልጣን ተናግረዋል። ዩክሬን የተወሰኑት ሮኬቶች የተተኮሱት ከቤላሩስ ነው ብላለች። ቤላሩስ ለሩሲያ የሎጂስቲክስ ድጋፍ እያደረገች ሲሆን ጦሯ ግን በይፋ በጦርነቱ ላይ አልተሳተፈም። የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት የሚሳኤል ጥቃቱ ሩሲያ ቤላሩስን ወደ ጦርነቱ ለማስገባት የምታደርገው ጥረት አካል ነው ብለዋል። ሩሲያ ሴቬሮዶኔትስክን በቁጥጥር ሥር ማዋሏ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በኔቶ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለጂ7 ስብሰባ ወደ ጀርመን ከማቅናታቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ነው። በቅርብ ወራት ውስጥ የምዕራቡ ዓለም ጥምረት ጭንቀትና ድካም ታይቶበታል። ይሁን እንጂ ቅዳሜ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዩክሬን ጦርነቱን እንደምታሸንፍ ተናግረዋል። “ አሁን በዩክሬን ተስፋ የምንቆርጥበት ሰዓት አይደለም” ብለዋል ቦሪስ ጆንሰን። እሁድ እለት የኢንዶኔዥያ ፕሬዚደንት ጆኮ ዊዶዶ፣ የዩክሬንና የሩሲያ መሪዎች ንግግራቸውን እንደገና እንዲጀምሩ አሳስበዋል። “ ጦርነት መቆም አለበት፤ የዓለም የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትም ማንሰራራት አለበት” ብለዋል ፕሬዚደንት ጆኮ።", "ሩሲያ የኒውክሌር መሳሪያዎቿ ላይ አሜሪካ ፍተሻ እንዳታደርግ አገደች ሩሲያ 'ስታርት' ተብሎ በሚታወቀው ስምምነት መሰረት አሜሪካ በስትራቴጅያዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቿ ላይ የምታደርገውን ፍተሻ \"ለጊዜው\" ማገዷን አስታወቀች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሜሪካ እየተጠቀመችብን ነው ባለውና፣ ሩሲያ በአሜሪካ ግዛት ውስጥ የምታደርገውን ተመሳሳይ የፍተሻ መብቷን በመንፈጓ መሰል እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል። አሜሪካ በበኩሏ የዩክሬን ወረራን ተከትሎ በሩሲያ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በአገራቱ መካከል ያለውን ሁኔታ ቀይሯል ብሏል። ሁለቱ አገራት የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎቻቸውን በተመለከተ ፍተሻዎችን የሚያደርጉበትን ስምምነት እኤአ በ2011 ነበር ተግባራዊ የሆነው። ስታርት በቀድሞ የቀዝቃዛ ጦርነት ተቀናቃኞች አሜሪካ እና ሩሲያ መካከል ተግባራዊ እየተደረገ ያለ የመጨረሻው የጦር መሳሪያ ቅነሳ ስምምነት ነው። ስምምነቱ ሁለቱ አገራት ሊያሰማሩ የሚችሉትን የረዥም ርቀት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ 1,550 ላይ የገደበ ስምምነት ነው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እገዳው የተላለፈው በስምምነቱ ላይ በተቀመጠው \"ልዩ ሁኔታዎች\" መሰረት ነው ብሏል። እገዳው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር አዲስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ስምምነት ላይ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ከገለጹ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው። አሁን በሥራ ላይ ያለው ስምምነት እኤአ 2026 የሥራ ጊዜው ያበቃል። ሚኒስቴሩ አሜሪካ የአየር ግንኙነትን ማቋረጥን የመሳሰሉ \"ከዚህ ቀደም የነበሩ እውነታዎችን\" ወደ ጎን ብለላች ሲሉ ከሰዋል። የስታርት ስምምነት በቀድሞዋ ሲቪየት ኅብረት እና አሜሪካ መካከል ለዓመታት የተካሄዱ የኒውክሌር ጦርነትን ለማስቀረት ያለሙ የጦር መሳሪያ ቅነሳ ንግግር ተከትሎ ነበር የጸደቀው። ሩሲያ በየካቲት ወር ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ በሁለቱም ወገኖች ግጭቱ ወደ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ሊሸጋገር እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መስጠትን ጨምሮ፣ ጠብ አጫሪ ፕሮፖጋንዳዎች ሲሰሙ ቆይተዋል። በአንዳንድ የሩሲያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሩሲያ ከኔቶ ጋር ውጥረት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ተንታኞች ስለሞስኮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፉክክር አዘል ንግግሮችን ሲያደርጉ ተደምጠዋል።", "ምርጫ 2013፡ ቦርዱ ለ54 የምርጫ ክልሎች የታተሙ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ጉድለቶች አለባቸው አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ54 የምርጫ ክልሎች በታተሙ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ላይ የተለያዩ ጉድለቶችን ማግኘቱን አስታወቀ። ቦርዱ ረቡዕ ሰኔ 2/2013 ዓ.ም ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ባደረገበት ወቅት ይህንን ማሳወቁን በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመትን አስመልክቶ ያጋጠሙ ችግሮችን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፖርት አቅርቧል። የዕጩዎችን ቁጥር መሰረት አድርጎ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ወቅት ፓርቲዎች የዕጩዎች ቁጥር ላይ ባቀረቡት አቤቱታ፣ በድምፅ መስጫ ወረቀት እና በውጤት ማሳወቂያ ፎርሞች ላይ የማስታረቅ ሥራ ሲሰራ በድምፅ መስጫ ወረቀቶቹ ላይ ጉድለቶች መገኘታቸውን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መግለፃቸው ተጠቅሷል። ቦርዱ ባደረገው ማጣራት ጉድለት የተገኘባቸው የድምፅ መስጫ ወረቆች ድጋሚ ህትመት ያስፈልጋቸዋልም ተብሏል። ጉድለት የተገኘባቸው የምርጫ ክልሎች በአፋር ስድስት፣ በአማራ 11፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ 2፣ በጋምቤላ 3፣ በኦሮሚያ 2፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች 15፣ በሶማሌ 14 እና በድሬዳዋ 1 ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ምርጫ ክልሎች መሆናቸው ተመልክቷል። በዚሁ ምክክር ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ለተፈጠረው ችግር በቦርዱ የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን አቅርበዋል። ጉድለቶች በተፈጠሩባቸው ምርጫ ክልሎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን አትሞ ለማድረስ የሚኖረው ችግርና የሚያመጣውን የእሸጋ እና የስርጭት ተፅእኖንም በተመለከተ ብርቱካን አብራርተዋል። በእነዚህ 54 የምርጫ ክልሎች የድምጭ መስጫ ወረቀቶችን ሰኔ 14 ለሚደረገው ምርጫ ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችንም በተመለከተ ፓርቲዎች ሃሳብ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ በበኩላቸው የድጋሚ ህትመቱ በአገር ውስጥ ቢደረግ እንዲሁም ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ምርጫ የማይደረግባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር አብረው ድምፅ እንዲሰጡ ቢደረግስ የሚሉ አማራጭ ሃሳብ ማቅረባቸውም ተገልጿል። ይህንንም መሰረት በማድረግ ቦርዱ በእነዚህ የምርጫ ክልሎች ላይ ያጋጠመውን የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ጉድለት ችግር ለመፍታት በመጀመሪያ ደረጃ የድምፅ መስጫ ወረቀቶቹን አገር ውስጥ ማሳተም ሲሆን በሌላ አማራጭ ደግሞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ድምፅ ከማይሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር አብሮ ማካሄድ የሚሉትን አቅርቧል። በመጪው አገር አቀፍ ምርጫ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሌና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ምርጫ የማይካሄድባቸው ቦታዎችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በእነዚህ ስፍራዎች ምርጫ የማይካሄደው በጸጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ባለመጀመሩ፣ የመራጮች ምዝገባ ተጀምሮ በመቋረጡና የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበ መሆኑን ቦርዱ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ ላይ ጉልህ የአሰራር ችግር በማየቱ ማጣራት እንዲካሄድ የወሰነባቸው ቦታዎችም እንዲሁ ምርጫው እንደማይከናወን አስታውቋል። ግንቦት 28/2013 ዓ.ም ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ብሔራዊ ምርጫ፣ የመራጮች ምዝገባ እና ሌሎች ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠነቃቀቸው የተነሳ ምርጫው ለሁለት ሳምንታት እንዲገፋ ሆኖ ሰኔ 14 እንዲካሄድ ተወስኗል። ኢትዮጵያ በየአምስት ዓመቱ የምታካሂደው ምርጫ መካሄድ የነበረበት ባለፈው ዓመት ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫው እንዲራዘም መደረጉ የሚታወስ ነው።", "ኬንያ ምርጫ፡ የኬንያው ፕሬዚደንት ምክትላቸው ሥልጣን እንዲለቁ ጠየቁ የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠየቁ። ፕሬዚደንቱ ይህንን የጠየቁት በነሐሴ ወር ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በፊት በሁለቱ መካከል ያለው ውዝግብ እየከረረ በመምጣቱ ነው። ፕሬዚደንት ኡሁሩ ምክትላቸው ሩቶ አገሪቷን እየተፈታተነ ያለውን የምጣኔ ሃብት ችግር ለመፍታት በቂ ጥረት አላደረጉም ሲሉ የከሰሷቸው ሲሆን መንግሥትን ከውስጥ ሆነው መተቸት እንደሌለባቸውም ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ምክትል ፕሬዚደንት ሩቶ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ካቢኔው ከሁለት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ስብሰባ እንዳላደረገ እና ነገሮች ለፕሬዚደንቱ ስልክ በመደወል ብቻ እንደሚቀሩ ተናግረዋል። በአገሪቷ ሕግ መሠረት ፕሬዚደንት ኡሁሩ ምክትላቸውን ለማባረር ሥልጣን የላቸውም። በመሆኑም ምክትል ፕሬዚደንቱ ሩቶ ከሥልጣን ሊነሱ የሚችሉት ክስ ከቀረበባቸው አሊያም ሥራቸውን ለማከናወን የሚያስችል ብቃት ከሌላቸው ነው። በፕሬዚደንት ኡሁሩ እና በምክትላቸው መካከል ያለው ልዩነት አገሪቱ በቀድሞው የአገሪቷ ፕሬዚደንት ምዋይ ኪባኪ ሞት ሀዘን ላይ ባለችበት ወቅት በግልጽ ተስተውሏል። አርብ ዕለት በተካሄደው የቀድሞ ፕሬዚደንቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ፕሬዚደንት ኡሁሩ የምክትላቸውን ሩቶን እጅ ለመጨበጥ ፈቃደኛ አልነበሩም። በሁለቱ ባለሥልጣናት መካከል ያለው አለመግባባት የተፈጠረው ነሐሴ ላይ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ምክንያት ነው። ምክትል ፕሬዚደንት ሩቶ በመጪው ምርጫ ለፕሬዚደንትነት መወዳደር የሚፈልጉ ሲሆን ፕሬዚደንት ኡሁሩ የሚደግፉት ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪውን ራይላ ኦዲንጋን ነው። በዘንድሮው ምርጫ መዳረሻ ወቅቶች የአገሪቷ ምጣኔ ሃብት ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። ኬንያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት እያጋጠማት ሲሆን በተለይ እንደ የምግብ ዘይት እና ነዳጅ ያሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ ጨምሯል።", "የጋዳፊን ልጅ ጉዳይ በሚመለከተው ፍርድ ቤት ላይ የደረሰው ጥቃት አሳስቦኛል - ተመድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞ የሊቢያ መሪ ልጅ ሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ይግባኝ ባቀረበበት ፍርድ ቤት ላይ የተፈጸመው ጥቃት አሳስቦኛል አለ። ሰይፍ አል-ኢስላም በሊቢያ ለሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንዳይሳተፍ መከልከሉን ተከትሎ ጠበቃው ይግባኝ ባሉበት ፍርድ ቤት ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ነው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉዳዩ እንዳሳሰበው የገለጸው። የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ ጋዳፊ ከሳምንታት በኋላ በአገሪቱ ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ውጪ የተገደረገው ሐሙስ ዕለት ነበር። የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን እአአ 2015 ከቀረቡበት የጦር ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ነበር ከምርጫ ተሳታፊነቱ ያገደው። ኮሚሽኑ ከጋዳፊ ልጅ በተጨማሪ በርካታ ዕጩዎችን \"በሕጋዊ ምክንያቶች\" በምርጫው እንዳይሳተፉ ማገዱን አሳውቋል። አል ኢስላም ጋዳፊ አባቱ የሰሜን አፍሪካዊት አገር ሊቢያን በሚያስተዳደሩበት ወቅት በተፈጸሙ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል እና በነፍስ ግድያ የሚፈለግ ሰው ነበር። በዚህም ሳቢያ የጋዳፊ ልጅ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ከተሰማ በኋላ ውዝግብ አስነስቷል። የሰይፍ አል-ኢስላም ጠበቃ ካህሊ አል-ዛኢዲ ሴባህ ከተማ በሚገኘው ፍርድ ቤት የደንበኛውን አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ እንዳያቀርብ የታጠቁ ሰዎች እንደከለከሉት ተናግሯል። ሴባህ ከተማ ሊቢያን ለመቆጣጠር ነፍጥ ካነሱት አንዱ በሆኑት ጄነራል ኻሊፍ ሃፍጣር ቁጥጥር ሥር ትገኛለች። በተመሳሳይ በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ክስ የቀረበባቸው ዝነኛው ኻሊፍ ሃፍጣር ለዚሁ ምርጫ ለመወዳደር መዘጋጃታቸው በአገሪቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል። ነገር ግን ምርጫ ኮሚሽኑ ኻሊፍ ሃፍጣርን ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ውጪ ያድርጋቸው አይድርጋቸው የታወቀ ነገር የለም። የሊቢያ ወታደራዊ ዐቃቤ ሕግ የጋዳፊ ልጅ እና የሃፍታር በቀረበባቸው ክስ ላይ ተገቢ መልስ እስኪያቀርቡ ድረስ የምርጫ ኮሚሽኑን በዕጩነት ለማሳተፍ የሚያደርገውን ሂደት እንዲያቆም ጠይቀው ነበር። ሰኞ በተጠናቀቀው የዕጩዎች ምዝገባ ስልሳ ሰዎች ሊቢያን በፕሬዝዳንት ለመምራት የተመዘገቡ ሲሆን የ46 ዓመቷ የሴቶች መብት ተሟጋች ሊላ ቤን ካሊፋ ብቸኛዋ ሴት ተወዳዳሪ ናቸው።", "የእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ የኢራንን ጥብቅ የደኅንነት መዋቅር እንዴት ዘልቆ ገባ? እአአ በጥቅምት 2020 ታዋቂው ኢራናዊ የኒውክሌር ሳይንቲስት ሞህሴን ፋክኽሪዛደህ ይጓዝበት የነበረው መኪና ጋየ። በሰው ሠራሽ ክህሎት [አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ] አማካይነት በርቀት ቁጥጥር ከሚደረግበት መትረየስ በተተኮሰ ጥይትም ተገደለ። ጉዞ ላይ ባለ መኪና ውስጥ የተሳፈረን ኢላማ ከሌሎች ሰዎች ለይቶ በዚህ መንገድ መግደል እጅግ ጠንካራ የስለላ ክህሎትን ይጠይቃል። ሳይንቲስቱ ከተገደለ በኋላ የኢራን የደኅንነት ኃላፊ ማሕሙድ አልቪ ይህን መሰል ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደነበር ተናግረዋል። ግድያው ከመፈጸሙ ከሁለት ወራት በፊት፤ ሳይንቲስቱ በተገደለበት ስፍራ አንዳች ጥቃት እንደሚደርስ መሐሙድ አስጠንቅቀው ነበር። የደኅንነት ኃላፊው እንዳሉት ግድያው የተፈጸመው \"በአገሪቱ ጦር ሠራዊት አባል ሲሆን፣ የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ደግሞ በወታደራዊ ኃይል ውስጥ ለመንቀሳቀስና እርምጃ ለመውሰድ አይችልም።\" ኃላፊው በቀጥታ ባይናገሩም በተዘዋዋሪ ተጠያቂ ያደረጉት በኢራን እስላማዊ የአብዮታዊ ዘብ ጓድ (ኢስላሚክ ሪቮሉሽን ጋርድ ኮርፕስ) ውስጥ ያለ ሰርጎ ገብን ነው። ይህ ቡድን በኢራን እጅግ የተከበረ ወታደራዊ ስብስብ ነው። የደኅንነት ኃላፊው እንደሚሉት ለሳይንቲስቱ ግድያ ተጠያቂው የዚህ ቡድን አባል የሆነ ግለሰብ ከሆነ ያ ሰው የቡድኑ ከፍተኛ አመራር ደረጃ ሳይደርስ አይቀርም። ይህ ሰው ከደኅንነት ኃላፊው የተሰጠውን ጥቆማ ችላ ብሎ ጥቃቱ በታቀደው ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት እንዲከናወን መንገድ ጠርጓል። ሟቹ ሳይንቲስት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ አባል እንደነበር ይነገራል። በእርግጥ የኢራን መንግሥት የቡድኑን አባላት ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ አያደርግም። በቴህራን በሚገኘው ኤርቪን እስር ቤት የሚገኝ የቢቢሲ ምንጭ እንደጠቆመው፤ ለውጭ አገራት በመሰለል የተጠረጠሩ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በእስር ቤቱ ታግተዋል። በዚህ ቡድን የውጭ አገራት ቅርንጫፍ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ የቀድሞ የደኅንነት ባለሙያ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ በውጭ አገራት ባሉ በበርካታ የኢራን አምባሳደሮች እንዲሁም የቡድኑ አባላት ላይ መረጃ ሰብስበዋል። ይህ መረጃ እነዚህ ግለሰቦች ከሴቶች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይጨምራል። ከሴቶች ጋር ስላላቸው ግንኙነት የሚሰበሰበው መረጃ ኋላ ላይ ኢራናውያኑ ከውጭ አገራት ሰላዮች ጋር እንዲተባበሩ ጫና መፍጠሪያ ይሆናል። እአአ በ2018 ከቴህራን በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ቀጠና ውስጥ ያለ መጋዘን በበርካታ ሰዎች በድንገት ተወረረ። መጋዘኑን ጥሰው የገቡት ሰዎች ውድ እቃ የተቀመጠባቸውን ሳጥኖች መርጠው ቁልፋቸውን አቀለጡ። ከሰባት ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በመጋዘኑ ውስጥ ከነበሩት 32 ሳጥኖች የ27ቱን ቁልፍ ሰበሩ። ከዚያም ከባድ የኒውክሌር ምስጢር የያዙ ሰነዶች መዝብረው ተሰወሩ። ዘረፋው በኢራን ታሪክ እጅግ አሳፋሪው ቢሆንም የኢራን መንግሥት ስለጉዳዩ ብዙ ከማውራት ተቆጠበ። ከዘረፋው ከሦስት ወራት በኋላ የተዘረፉት ሰነዶች ከኢራን 2,000 ኪሎ ሜትር ርቀው ቴል አቪቭ፣ እስራኤል ተገኙ። የያኔው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተዘረፉትን ሰነዶች አስጎበኙ። ሰነዶቹ የሞሳድ ኦፕሬሽን ውጤት እንደሆኑም በይፋ ተናገሩ። የኢራን ባለሥልጣናት ግን እነዚህ ሰነዶች ሐሰተኛ እንደሆኑና የኢራን መጋዘን እንዳልተዘረፈ አስተባበሉ። ነሐሴ 2021 ላይ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሮሀኒ በመጨረሻው የሥልጣን ቀናቸው እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ሰነዶች ዘርፋ ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሳየች አመኑ። ኔታንያሁ በ2018 የተሰረቁትን የኢራን ሰነዶች ሲያስጎበኙ የኒውክሌር ሳይንቲስቱ ሞህሴን ፋክኽሪዛደህ በኢራን ምስጢራዊ ኒውክሌር ማብላያ ከሚያስገነቡት ዋነኛው መሆናቸውን ተናግረዋል። \"ዶ/ር ሞህሴን ፋክኽሪዛደህ የሚለውን ስም እንዳትዘነጉ\" ሲሉም ኔታንያሁ ተደምጠዋል። ይህን ካሉ ከሁለት ዓመታት በኋላ ሳይንቲስቱ ተገደለ። \"አታውሩ፣ ተኩሱ\" ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ብዙ የኢራን ታዋቂ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ተገድለዋል። የኢራን ኒውክሌር ማብላያ ፋብሪካዎች ሥራቸውን የሚያስተጓጉል ስውር ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል። ኢራን እስካሁን ድረስ ጥቃት አድራሾችን ወይም አቀነባባሪዎችን መያዝ አልቻለችም። የፀጥታ ኃይሏ ጥቃቶቹን ማስቆምም ተስኖታል። በማሕሙድ አሕመዲንጃድ የመጨረሻው የፕሬዝዳንትነት ዘመን (2013 ገደማ) የኢስላማዊ አብዮት ጠባቂ ቡድን ኮማንደሮች፣ ሃይማኖታዊ አባቶች እንዲሁም የደኅንነት አመራሮች ለሞሳድ በመሰለል ተጠርጥረው ታስረው ነበር። ስለእስሩ በይፋ የተባለ ነገር ግን የለም። ተጠርጣሪ ከተባሉት አንዱ በኢራን የእስራኤል ስለላ ቡድን አመራር ነበሩ። በሚስጥር ተከሰው፣ የሞት ፍርድ ተወስኖባቸው፣ በአደባባይ ተገድለዋል። ማሕሙድ ባለፈው ዓመት \"ሞሳድ የደኅንነት ሚኒስቴራችንን ጥሶ መግባቱ እሙን\" ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም \"የእስራኤል ሰላዮችን እንዲቆጣጠር የተመደበው እና የእስራኤል ሰላዮችን ያጋልጣል የተባለው ሰው የእስራኤል ሰላይ ሆኖ ተገኝቷል\" ብለዋል። እስራኤል ስለ ሞሳድ እንቅስቃሴ እምብዛም በይፋ ምላሽ አትሰጥም። ከእስራኤል መከላከያ ጡረታ የወጡት የቀድሞው አመራር አሞስ ጊላድ እስራኤል ስለ ሞሳድ መረጃ የማትሰጠው ምክንያት ስላላት ነው ይላሉ። \"መረጃን ይፋ ማድረግን እቃወማለሁ። መተኮስ ካስፈለገ ዝም ብሎ መተኮስ ነው። አታውሩ፣ ተኩሱ!\" ብለዋል አሞስ። ጨምረውም \"ሞሳድ የሚታወቀው ብዙ በማይወራላቸው ድንቅ ኦፕሬሽኖቹ ነው\" ሲሉ ተናግረዋል። የቀድሞው የኢራን አመራሮች ሞሳድ በኢራን የፀጥታ እና የደኅንነት ክፍል እስከ ከፍተኛ አመራሮች የሚደርስ መዋቅር ዘርግቷል ብለው ይሰጋሉ። የቀድሞው የኢራን የደኅንነት ሚኒስትር እና የሮሐኒ አማካሪ አሊ ዩኒሲ ከዚህ ቀደም ባለደጉት ቃለ ምልልስ \"ሞሳድ በኢራን ውስጥ ያለው መዋቅር እስከ ከፍተኛ አመራሮች ስለሚደርስ እያንዳንዱ የኢራን ባለሥልጣን ለሕይወቱ እና ለደኅንነቱ መፍራት አለበት\" በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።", "ካማላ ሐሪስ የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ለአንድ ሰዓት ተኩል መሩ ካማላ ሐሪስ በአሜሪካ ታሪክ ለ85 ደቂቃዎች ያህልም ቢሆን አገሪቱን በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት ሆኑ። ምክትል ፕሬዝዳንቷ ሐሪስ የፕሬዝዳንትነት መንበሩን የጨበጡት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሕክምና ላይ ስለነበሩ ነው። ባይደን ለሕክምና የማደንዘዥ መድኃኒት መውሰዳቸውን ተከትሎ ሥልጣናቸውን ለ57 ዓመቷ ምክትላቸው ሐሪስ አስተላልፈው ነበር። የባይደን ሐኪም ፕሬዝዳንቱ ደህና እንደሆኑና ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ባይደን 79ኛ ዓመት ልደታቸውን ከሰሞኑ ያከብራሉ። ፕሬዝዳንቱ ሕክምና ላይ በነበሩበት ጊዜ ምክትሏ ሐሪስ ከዋይት ሐውስ የምሥራቅ ክንፍ ካለው ቢሯቸው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር ተብሏል። ካማላ ሐሪስ ለአጭር ጊዜ በቆየው የመሪነት ሥልጣናቸው የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ብቻ ሳይሆኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር እና ደቡብ እስያዊት ሴት ፕሬዝዳንትም ናቸው። በጊዜያዊነት የመሪነት ሥልጣንን ማስተላለፍ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት የተለመደ እንደሆነ የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ተናግራለች። ከዚህ በፊት እአአ በ2002 እና 2007 ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ሕክምና ሲያደርጉ ሥልጣናቸውን ለምክትላቸው አስተላልፈው ነበር። የጆ ባይደን ሐኪም ኬቨን ኦኮነር \"የ78 ዓመቱ መሪ ጤናማና ጠንካራ ናቸው። ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይችላሉ\" ብሏል። ባይደን ከሆስፒታል ወደ ዋይት ሐውስ ሲመለሱ \"ጥሩ ስሜት ይሰማኛል\" ብለው መናጋረቸው ተዘግቧል። ባይደን በአሜሪካ ታሪክ በዕድሜ ትልቁ መሪ ናቸው። አምና ሕክምና ሲደረግላቸው \"ጤናማ እና ብርቱ\" ተብለዋል።", "ሩሲያ በማንኛውም ቅጽበት ዩክሬንን ልትወር እንደምትችል አሜሪካ አስጠነቀቀች ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ሁሉን ነገር አጠናቃለች ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች፡፡ እንደ አሜሪካ ባለሥልጣናት ከሆነ ሩሲያ ወታደሮቿን ከዛሬ ጀምሮ በማንኛውም ቅጽበት ልታንቀሳቅስና ወረራውን ልትፈጽምት ትችላለች፡፡ በመሆኑም ዜጎቿ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መክራለች፡፡ ወረራው የሚጀምረው በአየር ድብደባ ሊሆን እንደሚችልም የተነበየች ሲሆን ይህም የሚያመላክተው ጦርነቱ አንዴ ከተጀመረ በኋላ ከሩሲያ ምድር መልቀቅ ቀላል እንደማይሆን ነው፡፡ ሞስኮ በአንጻሩ ወረራ የሚባል ነገር በሐሳቤም የለም ትላለች፡፡ ይሁንና ከ100 ሺህ የሚልቁ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋቷን አላስተባበለችም፡፡ ከአሜሪካ ባሻገር ሌሎች የምዕራብ አገራትም ዜጎቻችን እባካችሁ የሩሲያ ምድርን ልቀቁ ሲሉ መክረዋል፡፡ ዩኬ፣ ካናዳ፣ ኔዘርላንድስ፣ ላቲቪያ ለዜጎቻቸው መመሪያን የሰጡ ሲሆን ጃፓንና ደቡብ ኮሪያም ዜጎቻችን ከሩሲያ ብትወጡ ነው የሚሻለው ሲሉ መክረዋል፡፡ የሩሲያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ምዕራብ አገራት ሐሰተኛ ዜና እያሰራጩ ሕዝብ ያሸብራሉ ሲል ከሷል፡፡ የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት ከፍተኛ አማካሪ ጄክ ሰሊቫን \"በሚቀጥሉት ደቂቃዎች ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ከባድ ነው፤ የሩሲያ ወታደሮች ጥቃት ለመሰንዘር ተጠንቀቅ ላይ ናቸው\" ብለዋል፡፡ የደኅንነት አማካሪው ጨምረው፣ ቭላድሚር ፑቲን በወረራው ዙርያ የመጨረሻ ውሳኔ ይስጡ አይስጡ አሜሪካ መረጃ የላትም ያሉ ሲሆን፣ ይሁንና ክሬምሊን ወረራውን ቅቡል ለማድረግ አንድ አሳማኝ ሰበብ እየፈለገች መሆኑን መረጃ እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡ የደኅንነት አማካሪው ጄክ ሩሲያ የመጀመርያውን ጥቃት የምትሰነዝረው ከአየር እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊከን የሩሲያ ጠብ አጫሪነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቀደም ሲል ተናግረው ነበር። ብሊንከንም በተመሳሳይ የሩሲያ ጥቃት በማንኛውም ቅጽበት ሊጀመር እንደሚችል ጠቁመው በተለይ በፌብሩዋሪ 20 የኦሎምፒክ ፍጻሜ ዕለት ሊሆን እንደሚችል ምልክቶች እንዳሉ አብራርተዋል፡፡ አሜሪካ ለዚህ ጥቃት ምላሽ 3 ሺህ የሠራዊት አባላትን ከኖርዝ ካሮላይና ቀጠና ወደ ፖላንድ አንቀሳቅሳለች፡፡ ይሁንና እነዚህ ወታደሮች ከዩክሬን ወታደሮች ጋር ተሰልፈው አይዋጉም ተብሏል፡፡ ሆኖም ከአጋር አገራት ጋር ኾነው በተጠንቀቅ አካባቢውን ይቃኛሉ የሚል ግምት አለ፡፡ የፈረንሳዩ ማክሮን ከሰኞ ጀምሮ፣ ኪያቭ፣ ሞስኮና በርሊን ሲመላለሱ ነው የሰነበቱት፡፡ የማክሮን ወዲያ ወዲህ ማለት አይቀሬ ነው ለሚባለው ጦርነት የዲፕሎማሲ መፍትሄ ለመሻት ነበር፡፡ አንጌላን የተኩት የጀርመኑ መራሒ መንግሥት ሾልዝ በበኩላቸው ማክሰኞ ዕለት በዋሺንግተን ከባይደን ጋር መክረው ሩሲያ እንደተፈራው ወረራ ከፈጸመች በምን መልኩ ልንቀጣት ይገባል በሚለው ላይ ከመግባባት ደርሰው ነው የተመለሱት፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት የፈረንሳዩ ማክሮንና የአሜሪካው ባይደን ከቭላድሚር ፑቲን ጋር የመጨረሻ ሊሆን ይችላል የተባለ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሩሲያ በተለይ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በምህጻሩ ኔቶ፣ ወደ ምሥራቅ አውሮጳ አይስፋፋብኝ፣ በተለይ ደግሞ ባላንጣዬን ዩክሬንንም አባል አድርጎ አይመዝግባት ስትል በጥብቅ ስትጠይቅ ኖራለች፡፡ ይህ ቁልፍ የደኅንነት ጥያቄዋ ግን በምዕራብ አገራት ገሸሽ ሲደረግባት ነው የኖረው፡፡", "የሲሪላንካ ፓርላማ የሕዝብ ድጋፍ የሌላቸውን ፖለቲከኛ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ የሲሪላንካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸውን ራኒል ዊክርሜሲንግህ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ። ዊክርሜሲንግህ ፕሬዝዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት የቀድሞ ፕሬዝደንት አገር ጥለው መሸሻቸውን ተከትሎ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ከዚያ በፊት ደግሞ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ግለሰቡ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው በአገሪቱ ሌላ ተቃውሞ እና አለመረጋገትን ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል። አዲሱ ፕሬዘዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር እና ተጠባበቂ ፕሬዝዳንት ሳሉ፤ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስሪላካውያን ሲጠይቁ ቆይተዋል። በአገሪቱ የተከሰተውን ከፍተኛ ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ተከትሎ ሕዝባዊ አመጽ በርትቶባቸው የነበሩት የቀድሞ የሲሪላንካው ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ በጦር አውሮፕላን ከአገር ከሸሹ በኋላ ሥልጣናቸውን በይፋ መልቀቃቸው ይታወሳል። ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ሲሪላንካውያን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አስተዳደር አካል የሆኑት እና አሁን ፕሬዝዳንት ተብለው የተሾሙት ዊክርሜሲንግህ ለምጣኔ ሃብታዊ ቀውሱ ተጠያቂ ናቸው ይላሉ። ዊክርሜሲንግህ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተሾሙ በመላው አገሪቱ የሚጸና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር። ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተላልፈውታል። በወቅቱ ዊክርሜሲንግህ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉትን “ፋሺስቶች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል። ዊክርሜሲንግህ እራሳቸውን ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ አድርገው ከማቅረብ እንዲቆጠቡ ቢጠየቁም ፕሬዝዳንት ሆኖ ከመሾም ያገዳቸው የለም። አዲሱ ፕሬዝዳንት አገሪቱን ከምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ የማውጣት እና የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት መዘርጋት ቀዳሚው ኃላፊነታቸው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ሲሪላንካ የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን የጨረሰች ሲሆን፣ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት አጋጥሟታል። እንደ መድኃኒት፣ ነዳጅ እና ምግብ የመሳሰሉ መሠረታዊ ቁሶችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባትም ተስኗታል። ሲሪላንካውያን ለዚህ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የአገሪቱን መንግሥት ተጠያቂ ያደርጋሉ። አዲሱ ፕሬዝዳንትም የቀድሞ መንግሥት አስተዳደር አካል ናቸው ይላሉ። ከፍተኛ ሃብት ካካበቱ ፖለቲከኛ ቤተሰብ የተገኙት ዊክርሜሲንግህ፤ የሕዝብ ተወካዮች አባል የሆኑት ከአራት አስርት ዓመታት በፊት እአአ 1977 ነበር። ከእአአ 1993 ጀምሮ ዊክርሜሲንግህ በተለያዩ ጊዜያት የሲሪላንካ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።", "የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ ኦነግ ከምርጫው መውጣቱን ሲያሳውቅ ሌሎች አመራሮች ደግሞ የመሳተፍ ፍላጎት አለን አሉ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከጥቂት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ ባወጣው መግለጫ አሳወቀ። በሌላ በኩል በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ሌላኛው የግንባሩ ቡድን ግን በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ቢገልፅም ዕጩ ስለማስመዝገቡ ግን ምንም ያለው ነገር የለም። በአቶ ዳውድ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በምርጫው ለመሳተፍ የሚያስችሉት አመቺ ሁኔታዎች አለመኖራቸውን ገልጾ፤ በገዢው የብልጽግና ፓርቲ ዘንድ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊ መስፈርቶች ለማሟላት ፍላጎት አለመኖሩ ከምርጫው ለመውጣቱ ምክንያት መሆኑን አመልክቷል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 2013 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ደግሞ ሰኔ 5 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ያስረዳል። በዚህ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳሉ። በበርካታ የአገሪቱ ክፍል ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን የዕጩዎች ምዝገባ በተራዘመባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ የካቲት 30/2013 ዓ.ም ያበቃል። ኦነግ በምርጫው ውስጥ እንደማይሳተፍ ባመለከተበት መግለጫው ላይ ለአገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ተግባራዊ ቢደረጉ ይጠቅማሉ ያላቸውን እርምጃዎችን ጠቅሷል። በዚህም መሠረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉም የፓለቲካ እስረኞችን እንዲለቀቁ፣ የተዘጉና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጽ/ቤቶች እንዲከፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ሁሉም ጦርነቶች በማቆም ሁሉን ያካተተ ድርድር እንዲደረግ፣ የአገሪቱ ቁልፍ ተቋማት ገለልተኛና ከአድልዎ የፀዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉበት የፓለቲካ ውይይት ሂደት እንዲጀመር ጠይቋል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ በመግለጫው በምርጫው እንደማይሳተፍ ይግለጽ እንጂ፤ ሌላኛው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የግንባሩ አካል ግን በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ለቢቢሲ ገልጿል። ባለፈው ዓመት ጥር በኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ግንባሩ በሁለት ወገን በመሆን የተለያዩ አቋሞችን እያንጸባረቀ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም የረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ በአንድ ወገን ሆነው ድርጅቱን እየመሩ ሲሆን፤ በሌላ ወገን ደግሞ በአቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመሩ ሌሎች የግንባሩ አመራር አባላት በግንባሩ ስም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ አስገብተው የነበረ ሲሆን፣ ቦርዱም በግንባሩ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባትና ልዩነት ሁለቱም ወገኖች በሕገ ደንባቸው መሠረት ተነጋግረው እንዲፈቱ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። በአቶ አራርሶ የሚመራው የኦነግ አመራር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሉት ግንባሩ ከምርጫው መውጣትን በተመለከተ ውሳኔ ላይ አልደረሰም። \"ሊቀ መንበሩ ማለት ድርጅቱ ማለት አይደለም\" ያሉት አቶ ቀጀላ፣ ድርጅታቸው የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩበትም በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል። \"በአሁኑ ጊዜ እንቅፋት የሆነብን የውስጣችን ችግር ነው። የፓርቲው ሊቀ መንበር የሚጠበቅባቸውን እያደረጉ አይደለም\" በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ግንባሩ አሁን ባለበት ሁኔታ እንዴት በምርጫው እንደሚሳተፍ አቶ ቀጀላ ሲገልጹ \"የድርጅቱን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተን አዲስ አመራር ለመምረጥ እየሰራን ነው\" በማለት ሊቀ መንበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠሩ ግፊት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኦነግ ባወጣው መግለጫ ላይ ግንባሩ ተዘግተውብኛል ያላቸውን ጽህፈት ቤቶቻቸውን በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ቀጀላ አዲስ አበባ የሚገኘው ጽህፈት ቤቱ በግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር እጅ ስር መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ያሉት የግንባሩ ጽህፈት ቤቶች የተዘጉት በአቅም ማጣት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸውና አለ ባሉት የአስተዳደር ችግር ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል። \"ችግር የለም ማለት አይደለም ነገር አብዛኞቹ የራሳችን የውስጥ ችግሮች ናቸው። እኛ የፈጠርናቸው የውስጥ ችግሮችና አመራሮች ተገቢውን አመራር ባለመስጠቱ ነው\" በማለት ከምርጫው ተገፍተን ነው የወጣነው የሚለውን ሃሳብ አይቀበሉትም። በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍላጎቱ ውጪ በደረሱበት ጫናዎች ለመውጣት መገደዱን ማስታወቁ ይታወሳል። ኦፌኮ ይህን ውሳኔውን ያሳወቀው በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የሚገኙት ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋትና የአመራርና የአባላቱ መታሰርን እንደምክንያት በማስቀመጥ ከመጪው ምርጫ ተገፍቼ ወጥቻለሁ በማለት ነው። ከምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን የገለጹ ፓርቲዎችን በተመለከተ በሚቀርቡ ቅሬታዎች ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢቢሲ ከቀናት በፊት የገዢው የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳን (ዶ/ር) ጠይቆ ነበር። ቢቂላ (ዶ/ር) እንደሚሉት በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመሳተፍ ታግሎ ከማሻሻል ይልቅ፣ በትንሹም በትልቁም ምክንያት ከምርጫ መውጣት ሕዝቡ የፖሊሲ አማራጭ እንዳያገኝ የሚያደርግ ውሳኔ ነው ብለዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎቹ አባላትና ጽህፈት ቤቶች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተመለከተም \"እነዚህን የቀረቡ ስሞታዎች በዝርዝር ቀርበው ማጣራት ተደርጎ አብዛኞቹ ክሶች መሰረተ ቢስ ሆነው ተገኝተዋል\" ሲሉ ተናግረዋል። ችግሮች አያጋጥሙም ማለት እንደማይቻል የገለጹት ቢቂላ (ዶ/ር)፤ እነዚህንም ለማረምና ለማስተካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና የአስተዳደር መዋቅሩ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።", "ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ፡ 'ቡልዶዘር' የተባሉት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ማን ነበሩ? ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ነው ሙሉ ስማቸው። ቡልዶዘር ነው ቅጽል ስማቸው። ሲወለዱ የጭሰኛ ልጅ ነበሩ። ሲሞቱ ግን ፕሬዝዳንት ነበሩ። ቡልዶዘር የሚለው ቅጽል ስም ከየት መጣ? ቡልዶዘር (ሺዶማ) የተባሉት ያለምክንያት አይደለም። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት የሥራና ከተማ ሚኒስትር ነበሩ። መንገድ በስፋት ያሠሩ ነበር ያን ጊዜ። የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ነፍሳቸው ነበር ማጉፉሊ። ሕዝቡ ቡልዶዘር ሲል ቅጽል አወጣላቸው። ይህ ቅጽል ስም ግን ኋላ ላይ እየሰፋ ሄዶ መነሻውን ሳተ። ቡልዶዘር የሚለው ስም ሰውየው የመንግሥት ወጪን በመቀነስና ሙሰኞችን መጠራረግ ስለሚወዱም ነው ተባለ። የአስተዳደር ዘያቸው መጠራረግ ስለነበር ስሙ የተስማማቸው ይመስላል። ማጉፉሊ ሚዲያ ማስደንበር ይወዳሉ፤ ነጻ ድምጾችን ያፍኑም ነበር። ተቃዋሚዎችን አሸብረዋል። ሆኖም ሞታቸውን ያጀበው ያ ሳይሆን ለኮሮናቫይረስ ያሳዩት የነበረው ንቀት ነበር። ምናልባት እሱው ይሆን ከዚህ ዓለም ያሰናበታቸው? \"ኮሮናቫይረስ ጂኒ ነው\" ኮሮናቫይረስ ታንዛኒያ ሲገባ ማጉፉሊ ተበሳጩ። ሕዝቡ ቀን ተሌት እንዲሠራ እንጂ ቤቱ እንዲቀመጥ በፍጹም አይፈልጉም። አንድ መላ ዘየዱ። \"ሕዝቤ ሆይ! ለዚህ ተህዋሲ አትንበርከክ! ቤተክርስቲያን ሄደህ ጸልይ እንጂ በፍጹም ቤት አትቀመጥ\" አሉ። ሕዝቡም ያን አደረገ። \"ኮሮና ጂኒ ሰይጣን ነው እንጂ ተህዋሲ አይደለም\" የሚለውን ሐሳብ በሕዝባቸው ውስጥ አሰረጹ። ሳይንስ ግን ሰውየውን ታዘባቸው። ቫይረሱም ሳይናደድባቸው አልቀረም። ከሰኔ 2020 ጀምሮ ማጉፉሊ አገሬ ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ ነች ሲሉ አወጁ። ጭምብል ማጥለቅን ተሳለቁበት። ኮቪድ-19ን ንቀው የዜና ማድመቂያ አደረጉት። በአገራቸው አልበቃ ብሎ ጎረቤት አገሮች የእንቅስቃሴ ገደብ ሲያደርጉ \"የማይረቡ ፈሪዎች\" አሏቸው። ለምዕራቡ ተንበርካኪ አድርገው ሳሏቸው። ማጉፉሊ በ2015 የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ፣ ታንዛኒያ የሚያስፈልጓት ዓይነት ፕሬዝዳንት ሆነው ነበር የተገኙት። ሙስናን የሚጸየፉና በሥራ የሚያምኑ። ቀን ተሌት ቢሠሩ አይደክማቸውም። ቡልዶዘራዊነታቸውን አጠናክረው ቀጠሉበት። ውጤት ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ነድፎ የማስፈጸም አቅማቸው ተደነቀላቸው። ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ምሳሌ መሆን ጀመሩ። ገና ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በመጀመርያው ቀን የገንዘብ ሚኒስቴር ቢሮ ሄዱ። ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ተሟልተው አልተገኙም ነበር። ማጉፉሉ ጦፉ። ይህን በፍጹም እንደማይታገሱ እቅጩን ተናገሩ። ከሥራ የቀረ አለቀለት። ለደመወዝ ቀን ብቅ እያለ የሚጠፋ \"ጎስት ዎርከርስ\" እየተባለ የሚጠራን ታንዛኒያዊ ጠራርገው አባረሩ። ሥራውን የማይፈልግ የመንግሥት ሠራተኛ ብቻ ነው ከዚያ ወዲህ ከቢሮ ሥራ የሚቀር። ማጉፉሊ የዛቻ ብቻ አይደለም፤ የድርጊት ሰው ናቸው። ከሥራ የሚቀሩትን ብቻ ሳይሆን ሙሰኛ አለቆችን ጠራርገዋል። አንዳንድ ጊዜ ሹመኞችን የሚያባርሩት ታዲያ በቀጥታ በብሔራዊ ቴሌቪዥን እየታዩ ጭምር ነበር። ለሌላው መቀጣጫ እንዲሆኑ። በዚህ ጊዜ ቡልዶዘር ኑርልን አላቸው አገሬው። እሳቸውም ተበረታቱ። ማጉፉሊ ገና ድሮ ወጪ የሚባል ነገር ያበሳጫቸዋል። በተለይ ያልተገባ ብልጭልጭ ወጪ ታንዛኒያ ማውጣት የለባትም ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር። \"ምክንያቱም ድሆች ነን\" ይላሉ። በዚህ የተነሳ በድምቀት ይከበሩ የነበሩ በርከት ያሉ ክብረ በዓላትን አስቀርተዋል። በ54 ዓመታት የታንዛኒያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን እንዳይከበር ያደረጉት እሳቸው ናቸው። \"ቸበርቻቻ አያስፈልግም ሥራ ነው እንጂ\" አሉ። \"ሕዝቤ ሆይ! ነጻ የምትወጣው የነጻነት በዓልን በማክበር ሳይሆን ተግቶ በመሥራት ነው፤ ስለዚህ እጅህ መቁሸሽ አለበት\" ሲሉ ጮኹ። ማጉፉሉ ሕዝቡን በማዘዝ ወደ ቅንጡ ቤተ መንግሥት የሚገቡ ሰው አልነበሩም። እሳቸውም በዘመቻ ይሳተፉ ነበር። ሠርተው ያሳያሉ። ለምሳሌ የቤተ መንግሥቱን ደጅ የሚጠርጉት እሳቸው ራሳቸው ነበሩ። ኃላፊዎቻቸው በሆነ ባልሆነው ወደ አሜሪካና አውሮፓ ይጓዙ ነበር። ለሕክምና፣ ለጉብኝት፣ ወዘተ። ይህ ሁሉ የሚሆነው በሕዝብ ገንዘብ ነበር። አንድ ኃላፊ የውጭ አገር ጉዞ ቢያደርግ ወዮለት ብለው ደነገጉ። ተፈጻሚም ሆነ። ይህ እርምጃቸው በታንዛኒያውያን ዘንድ እጅግ ተወዶላቸው ነበር። እንዲያውም በማኅበራዊ የትስስር መድረክ መነጋገርያ ሆነው ነበር። \"ማጉፉሊ ቀጥሎ ምን ያደርጋሉ\" የሚል የድራምባ ሐረግ (Hashtag) ተፈጥሮም ነበር። ማጉፉሊ ከአገራቸው ባሻገር በሌሎች አፍሪካውያን ዘንድ ውስጥ ውስጡን አድናቆት ማግኘት ጀማምረውም ነበር። ለምሳሌ በ2017 አንድ እውቅ የኬንያ ፕሮፌሰር በዳሬ ሰላም ዩነቨርስቲ ተገኝተው በሰጡት የአደባባይ ዲስኩር \"አፍሪካ አዲስ አስተዳደር ያሻታል\" ካሉ በኋላ ይህ አፍሪካን የሚለውጠውን የአስተዳደርም ዘዬ \"ማጉፉሊኬሽን\" ሲሉ ሰይመውታል። ማጉፉሊ በዚህን ያህል ተጽእኖ መፍጠር ቢችሉም የዲሞክራሲ ጸር ሆነው ነበር የሚታዩት። ተቃዋሚ በማሽመድመድ፣ ነቃፊዎቻቸውን ነቅሶ በማሰር፣ ነጻ ሚዲያን በማፈን ስማቸው ይነሳል። ጆን ማጉፉሊ በአጭሩ ማጉፉሊ መጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በሁለተኛ ወራቸው የፓርላማ የቀጥታ ሥርጭት እንዳይተላለፍ አገዱ። ያን ጊዜ ሰበብ ያደረጉት ወጪ ቅነሳን ነበር። ተቃዋሚዎች ግን ይህ ነገር ለሳንሱር እንዲመች አድርጎ የፓርላማን ክርክር ለሕዝብ ለማቅረብ ነው ብለው ከሰሷቸው። እንዲያውም ይህን እርምጃ ተቃውመን ሰልፍ እንወጣለን አሉ። ሆኖም ሰልፉ በማጉፉሊ ሰዎች እውቅና ተነፈገውና ታገደ። በ2017 ደግሞ ማጉፉሊ የታንዛኒያው ራፐር ናይ ዋ ሚቴጎ ዘፈን ዘፈነባቸው። ሚቴጎ ሙዚቃውን በለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ራሱን እስር ቤት አገኘው። ይህ ዘፋኝ በራፕ ሙዚቃው ያዜመው ግጥም በደምሳሳው ሲተረጎም እንዲህ የሚል ስንኞች ነበሩበት፣ እስኪ ንገሪኝ አገሬ፣ ነጻነት አለ ወይ በሰፈሬ ያሻኝን ብዘፍን ጉራማይሌ አገኘው ይሆን ራሴን ከርቸሌ? ማጉፉሊ ራፐሩን እንደምኞቱ ከርቸሌ ወረወሩት። በዳሬ ሰላም ማዕከላዊ እስር ቤት ታጎረ። በዚህም ማጉፉሊ ለትችት ቦታ እንደሌላቸው አሳዩ። ማጉፉሊ ለሚዲያ ርዕስ የሚመቹና አንዳንዴም አስቂኝ ሰው ነበሩ። ለምሳሌ ይህን ተቺ ሙዚቃ ያቀነቀነውን ናይ ዋ ሚቴጎን ከአንድ ቀን በኋላ ከእስር ሲያስፈቱት አንድ ምክር መከሩት። \"ስለ ግብር አጭበርባሪዎች ሙዚቃ ሥራልኝ\" በማለት። ፕሬዝዳንት ማጉፉሊን ግብር አጭበርባሪዎች በጣም ያናድዷቸው ስለነበር ነው ለዘፋኙ ይህን ምክር የሰጡት። በ2017 ደግሞ ዋንኛ ተቃዋሚያቸውና የምክር ቤት አባሉ ቱንዱ ሊሱ ቤታቸው ሳሉ ተተኮሰባቸውና ክፉኛ ቆሰሉ። የማጉፉሊ ሰዎች እንዳደረጉት ይታመናል። ሆኖም ሰውየው እንደምንም ድነው ከ3 ዓመት በኋላ ተገዳዳሪያቸው ሆነው ለፕሬዝዳንትነት ተወዳደሩ። ሚስተር ሊሱ የግድያ ሙከራ እንደተረገባቸውና ታንዛኒያን እየመሯት ያሉት ሰው አምባገነን እንደሆኑ በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር። ማጉፉሊ እስከወዲያኛው ያሰናብቱታል ቢባልም ተፎካካሪያቸው እንዲሆን ፈቀዱለት። ምዕራብ ጠልነትና ማጉፉሊ ማጉፉሊ ምዕራባዊያን አፍሪካን በዝብዘዋታል ብለው ያምናሉ። ስለዚህ በተራችን እነሱን መበዝበዝ አለብን ሲሉ ያስባሉ። በዚህ ረገድ በየጊዜው የውጭ ድርጅቶችን የሚያስጨንቁ አዳዲስ መመርያዎችን ያወጡ ነበር። ከነዚህ መሐል የካናዳው ባሪክ ወርቅ እህት ኩባንያ የሆነውን አካሺያ ማዕድን ድርጅትን 190 ቢሊዮን ዶላር ለመንግሥት ክፈል ብለው አነቁት። ለምንድነው የምከፍለው ቢላቸው፣ በቃ እስከዛሬ የከበሩ ማዕድናትን ከታንዛኒያ ስታወጣ ነበር። ገቢህን ስንደምረው ታንዛኒያ ይህን ያህል ማግኘት እንዳለባት ደረስንበት አሉት። ኩባንያው ደነገጠ። ከብዙ ድርድር በኋላ 300 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ። ከዚህ ዕለት በኋላም ይህ የካናዳው ባሪክ ወርቅ አውጪ ኩባንያ ከሚያወጣቸው ማዕድናት 50 ከመቶውን ለመንግሥት ገቢ እንዲያደርግም ተገደደ። ማጉፉሊ የአስተዳደር ዘይቤያቸው የተቀዳው ከአገሪቱ የነጻነት አባት ጁሊየስ ኔሬሬ እንደሆነ ይነገራል። እሳቸውም ይህንን ብለውት ያውቃሉ። ማንም እንዴት አገሬን መምራት እንዳለብኝ ሊነግረኝ አይገባም ይሉ ነበር። በአንድ ወቅት ኮሮናቫይረስ የእንቅስቃሴ ገደብን በተመለከተ የተናገሩት ይህንኑ የሚመሰክር ነበር። \"አባቶቻችን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እየተነገራቸው አይደለም ያስተዳደሩን።…እንዲህ ዓይነት ቤት ዘግታችሁ ተቀመጡ የሚል መመርያ የሚያወጡ ሰዎች ከሩቅ ሊያስተዳድሩን ነው የሚሹት። የእኛ አባቶች እንዲህ አይነቱን ነገር አይቀበሉም ነበር\" ሲሉ ምዕራባዊያንን ተችተዋል። \"ድህነት ምን ማለት እንደሆነ አውቀዋለሁ\" ማጉፉሊ ከጭሰኛ ቤተሰብ በሰሜን ምዕራብ ቻቶ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነው የተወለዱት። \"ድህነትን በደንብ አውቀዋለሁ\" ይሉም ነበር። እሳቸው ልጅ እያሉ ታንዛኒያን የሚያስተዳድሯት ጁሊየስ ኔሬሬ ነበሩ። \"ቤታችን ከጭቃ ነበር የተሰራው፣ በልጅነቴ ከብቶችን አግድ ነበር። ቤተሰቤን ለመታደግ ወተትና ዓሳ እያዞርኩ ነበር የምሸጠው። ድህነት ምን ማለት እንደሆነ ለእኔ አትነግሩኝም፤ ለዚህ ነው ድሆችን ለማገዝ ፖለቲካ ውስጥ የገባሁት\" ሲሉም ተናግረዋል። ማጉፉሊ ጭሰኛ ሆነው ተወልደው ፕሬዝዳንት ሆነው ሞቱ። በተወለዱ በ61 ዓመታቸው።", "የትራምፕ የክስ ሂደት እስከሚቀጥለው ወር ተራዘመ ሁለተኛው የዶናልድ ትራምፕ ክስ በቀጣዩ ወር እንዲታይ የዲሞክራት እና ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ተስማሙ። ዲሞክራቶች ሰኞ ዕለት \"አመፅ በማስነሳት\" የተከፈተውን ክስ ይልካሉ፡፡ ክርክሮች እስከ የካቲት 8 ድረስ የማይጀመሩ ሲሆን፤ ይህም የትራምፕ ጠበቆች በሁለት ሳምንት መከላከያቸውን እንዲያዘጋጁ ያስችላቸዋል፡፡ ዲሞክራቶች የቀድሞውን ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ካፒቶል ሂል ሞት ያስከተለውን አመፅ በማነሳሳት ይከሳሉ፡፡ አምስት ሰዎች የሞቱበትን ሁከት በማነሳሳት ትራምፕን በመክሰስ ባለፈው ሳምንት ምክር ቤቱ ለክሱ ሂደት መንገድ ከፍቷል፡፡ ሁለተኛው የሕግ ጥሰት ክስ በሴኔቱ ሥልጣን አላግባብ በመጠቀማቸው እና ኮንግረስን በማደናቀፋቸው ክስ ከተመሰረተባቸው ከአንድ ዓመት በኋላ ይጀምራል፡፡ የጆ ባይደንን እና የልጃቸውን ስም ለማጥፋት እንዲረዷቸው ዩክሬይን ላይ ጫና አድረሰዋል በሚል ነበር ጉዳዩ፡፡ ትራምፕ የሥልጣን ዘመናቸው ረቡዕ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የተተኪውን ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ነጩን ቤተ መንግሥት ለቀዋል፡፡ የሴኔቱ አመራሮች በምን ተስማሙ? የሴኔቱ ከፍተኛ ዲሞክራት ቹክ ሹመር አርብ ዕለት እንዳሉት ምክር ቤቱ ሰኞ ዕለት ክሱን ያቀርባል። \"ሴኔቱ የዶናልድ ትራምፕን ክስ ይመለከታል። ሙሉ የፍርድ ሂደትም ይከናወናል፡፡ ፍትሐዊ የፍርድ ሂደት ይሆናል\" ሲሉ ሹመር ለሴኔቱ ተናግረዋል፡፡ የምክር ቤቱ ዲሞክራቶች አንቀጹ ሰኞ ወደ ላይኛው ኮንግረስ ይተላለፋል ብለዋል፡፡ በሴኔቱ የፍርድ ሂደት ወቅት እንደ አቃቤ ሕግ ሆነው የሚያገለግሉ የዲሞክራቶቹ የክሱ ኃላፊዎች እና የሕግ ባለሙያዎች ማክሰኞ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ፡፡ ሹመር በቅድመ ችሎት ሂደት ለተጨማሪ ጊዜ ጥያቄያቸውን ፍቃድ መሰጠቱ እንዳስደሰታቸውና የፍርድ ሂደቱ የካቲት 9 ቀን እንደሚጀመር የሴኔቱ የሪፐብሊካን መሪ ሚች ማኮኔል ተናግረዋል፡፡ \"ዓላማው ተሳክቷል፡፡ ይህም ለፍትሕ ሂደቱ እና ለፍትሐዊነት ድል ነው\" ብለዋል፡፡ የኋይት ሀውስ አቋም ምንድነው? ፕሬዚደንት ባይደን የፍርድ ሂደቱን እንዲዘገይ እንደሚመርጡ ጠቆም አድርገዋል፡፡ ለጋዜጠኞችም \"እነዚህን ቀውሶች ለመፍታት ጊዜ በወሰድን ቁጥር የተሻለ ይሆናል\" ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን ዋይት ኃውስ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጥፋተኛ ስለመሆናቸው ባይደን ማሰባቸውን በተመለከተ ያለው ነገር የለም። ቃል አቀባዩ ጄን ፕሳኪ አርብ ዕለት \"[ጆ ባይደን] ከአሁን በኋላ በሴኔት ውስጥ ስለሌሉ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ተጠያቂ የማድረግ ጉዳይ በሴኔት እና በኮንግረሱ ላይ የሚጣል ነው\" ብለዋል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡፡ ትራምፕ ይፈረድባቸዋል? ምንም እንኳን ዲሞክራቶች በሴኔቱ አነስተኛ አብላጫ ድምፅ ቢይዙም ትራምፕን ጥፋተኛ ለማድረግ ቢያንስ የ17 ሪፐብሊካኖች ድጋፍ ይፈልጋሉ። ምክንያቱም የሴኔቱ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ ያስፈልጋቸዋል። የሚሲሲፒው ሪፐብሊካን እንደራሴ ሮጀር ዊከር አርብ ዕለት ለሲኤንኤን እንደተናገሩት \"የጥፋተኝነት ፍርድ የማግኘት ዕድሉ ወደ ዜሮ የሚጠጋ ነው።\" ሚት ሮምኒ፣ ሊዛ ሙርኮቭስኪ፣ ቤን ሳሴ፣ ሱዛን ኮሊንስ እና ፓት ቶሚ አምስቱ የሪፐብሊካን እንደራሴዎች ብቻ ናቸው ክሱን በመደገፍ ከዲሞክራቶች ጋር ይቆማሉ የሚባሉት፡፡ ትራምፕ በሴኔቱ የተከሰሱ የመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው የተጠናቀቀ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ፡፡ በእንደዚህ አይነት ክሶች ጥፋተኛ ተብሎ የተከሰሰ ፕሬዝዳንት የሌለ ሲሆን ትራምፕም ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከዚህ በኋላ ሥልጣን እንዳይዙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ አርብ ዕለት ትራምፕ፤ በዋሽንግተን ኤግዛማይነር ዘጋቢ በትራምፕ ዓለም አቀፍ የጎልፍ ክበብ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። ስለ ወደፊት ዕቅዳቸው ሲጠየቁ \"የምንሠራው ነገር ቢኖርም ገና አልተወሰነም\" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።", "ምርጫ 2013፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኤርትራና ሱዳን ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ እየሰሩ መሆኑን ገለጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ድምጻቸውን በትውልድ አካባቢያቸው በሻሻ ከሰጡ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኤርትራ እና የሱዳን ወታደሮች ከኢትዯጵያ ድንበር ለቅቀው እንዲወጡ ከመንግሥታቱ ጋር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።", "የቀድሞ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ገላሳ ዲልቦ አረፉ በኢህአዴግ የሽግግር ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀ መንበር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባሉ አቶ ገላሳ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን አንድ የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። እኚሁ የቤተሰብ አባል \"ሌሊት ላይ በድንገተኛ ህመም መሞታቸውን\" ለቢቢሲ አስረድተዋል። ሞታቸው ከተሰማ በኋላም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሃዘናቸውን በክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ማኅበራዊ ትስስር ገፅ አስፍረዋል። \"ኦሮሚያ አንድ ዋርካ አጥታለች። በኦሮሞ የነፃነት ትግል ውሰጥ ትልቅ ስም የነበራቸው፤ በአስቸጋሪ ወቅቶች እድሜያቸውን ለአሮሞ ህዝብ እየታገሉ ያሳለፉት ገላሳ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በመለያታቸው የተሰማኝን ሃዘን እየገለፅኩ ለኦሮሞ ሕዝብ መፅናናትን እመኛለሁ\" ብለዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ መስራች የሆኑት አቶ ገላሳ ዲልቦ ባለፈው ዓመት በነበረው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎላኦዳ ቁምቢ መልካ በሎ ወረዳዎችን በመወከል በግል ተወዳድረው በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ። አቶ ገላሳ ዲልቦ ለረጅም ዓመታት በስደት ኑሯቸውን በለንደን አድርገው የነበሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በውጭ አገራት የነበሩ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ወደ አገር ቤት ከተመለሱ አንጋፋ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ነበሩ። አቶ ገላሳ ከቢቢሲ በነበራቸው ቆይታ ከ27 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ ኢህአዴግ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ በነበረው የሽግግር መንግሥቱ ጉባኤ ላይ መሳተፋቸውንና ከሁለት ቀናት በኋላ በህመም ምክንያት ወደ አውሮፓ ሄዱ። ህክምና አግኝተው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቢመለሱም የወቅቱ ሁኔታ እንደጠበቁት አላገኙትም \"ሁኔታዎች ስለተበላሹ ተመልሰን ወደ ትጥቅ ትግል ለመግባት ተገደድን። በሽግግሩ ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር የነበርኩት እኔ ነበርኩኝ\" ብለዋል። በአሁኑ ሊቀ መንበር ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው የኦነግ ፓርቲ የወጡት በአውሮፓውያኑ 1998 የኦነግ መከፋፈልን ተከትሎ ሲሆን፣ \"አባኦ ቃማ ጨኡምሳ\" የሚባል ሌላኛውን የኦነግ ፓርቲን መስርተው በሊቀ መንበርነት ለረጅም ዓመታት ሲያገለልግሉ ነበር። አቶ ገላሳ ዲልቦ የተወለዱት ምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ሲሆን አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው ነበር የተከታሉት። በአውሮፓውያኑ 1974 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የገቡ ቢሆንም የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ደርግ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ ለትግል ወደ ሶማሊያ መሄዳቸውን በወቅቱ ተናግረው ነበር። ሆኖም የሶማሊያ መንግሥት ወደ አገር ቤት ስለመለሳቸው በአገር ቤት የነበረውን የትጥቅ ትግል መቀላቀላቸውንና የትግል ሕይወታቸውም በዚያው እንደተጠነሰሰም በወቅቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።", "በቤንሻንጉል ጉሙዝ የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ዕርምጃዎች መወሰድ እንዳለበት ተገለፀ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በከማሽ ዞን ምንጅጋ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 8፣ 2013 ዓ.ም በደንቤ ቀበሌ 8 ነዋሪዎች በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። ኢሰመኮ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ስጋት ያደረባቸው ከአራት ሺህ ያላነሱ የቀበሌው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውንና ምጅንጋ (በሎይጂንጋፎይ) ወረዳ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙም ጠቅሷል። ኢሰመኮ መግለጫውን እስካወጣበት ድረስ የተኩስ ድምፅ አየተሰማ መሆኑንና የፀጥታ ኃይሎች ወደ ቦታው ያልደረሱ መሆኑንም ተፈናቃዮች ለኮሚሽኑ መናገራቸውን ገልጿል። ኢሰመኮ የሲቪል ሰዎች ደህንነትን ለማረጋገጥ አስቸኳይ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸውም አፅንኦት ሰጥቷል። ከቀናት በፊት ሐምሌ 3 እና 4 2013 ዓ.ም በተከሰተም ግጭት ቢያንስ 16 ነዋሪዎች መገደላቸውንም በመግለጫው ተጠቁሟል። በክልሉ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ በምትገኘው ኢማንጅ ቀበሌ ነው ግጭቱ የደረሰው ብሏል ኢሰመኮ በደረሰው መረጃ ኢሰመኮ ክትትል ሲያደርግና ከአካባቢው የፀጥታና አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ሲነጋገርም እንደቆየ በመግለጫው አስፍሯል። በታጠቁ ኃይሎች ተገድለዋል ተብሎ በሚነገር አንድ የኢማንጅ ቀበሌ ነዋሪ የቀብር ስነ ስርዓት በደረሰ ጥቃትም ተጨማሪ 15 ሰዎች ህይወት እንዳለፈም ተገልጿል። ሐምሌ 4፣ 2013 ዓ.ም የደረሰው የአፀፋ ጥቃት ስለመሆኑም መነገሩን ኢሰመኮ ገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ሐምሌ 4፣ 2013 ዓ.ም በክልሉ መንግሥት እና በኮማንድ ፖስት የማረጋጋትና የደህንነት እርምጃ ተወስዷል ብሏል። ሆኖም ከዚህም በተጨማሪም በምጅንጋ ተጠልለው ለሚገኙ ነዋሪዎች ጥበቃ እንዲደረግም ኢሰመኮ አሳስቧል። የክልሉን ሰላምና ደህንነትም በዘላቂነት ለመመለስ አጥፊዎች በአፋጣኝ ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል ብሏል። እንዲሁም የነዋሪዎችን ሰላም እና ደህንነት በተሟላ መልኩ ማረጋገጥ አስፈላጊነቱንም አስምሯል።", "ፋኖ ማን ነው? በማንስ ይደገፋል? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ፋኖ ስሙ ይነሳ የነበረው በህቡዕ ትግል ነበር። በወቅቱ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የነበሩ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ፋኖም በአማራ በተለይ ደግሞ በጎንደር አካባቢ የወጣቶች የህቡዕ አደረጃጀት እንደነበር ይነገራል። ከዚያ በኋላ ግን በአገሪቱ የተከሰቱ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ ስሙ በተደጋጋሚ የሚነሳው 'የታጣቂዎች ኢመደበኛ አደረጃጀት' በሚል ሆኗል። ፋኖ የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ኃይሎች ጋር ባደረገው ትግል በተለይ ደግሞ የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል የተወሰኑ ስፍራዎችን ተቆጣጥረው በነበረበት ወቅት ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጎን በመሆን በቀጥታ ተሳትፏል። ምንም እንኳን ፋኖ የሚለው ስያሜ አሁን ካለው ታጣቂ ኃይል ጋር ተያይዞ በብዙዎች ዘንድ ቢታወቅም የፋኖ ፅንሰ ሃሳብ ዘመናትን ያስቆጠረ እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ያስቃኛሉ። ስለ ፋኖ ትንታኔ የሚሰጡ ሰዎች ትርጓሜው በበደል ተገፍቶ ዱርን የመረጠ፣ መጨቆንን ጠልቶ ጠመንጃ የጨበጠ ሰው 'ፋኖ' የሚል መጠሪያ እንደሚሰጠው ይናገራሉ። እንደ እነዚህ ሰዎች አባባል ፋኖ መገፋት የወለደው የለውጥ ኃይል ሲሆን ለዘመናትም ይህንን የሚያንጸባርቁ ፉከራዎች፣ ግጥሞችና ዘፈኖች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲቀባበሉ እዚህ ደርሰዋል። ፋኖ የሚለው ስያሜ 'ለበርካታ ሺህ ዓመታት የአማራ ህዘብ ማስተሳሰሪያ ክሩ ሆኖ፣ ለችግር ጊዜ መፍትሄ ማፍለቅያ እሴቱ ሆኖ የመጣ እንደሆነም ሲናገሩ ይደመጣል። ከጥንት ጀምሮ ብዙ ሲባልለት የቆየው የፋኖ እሳቤ አሁን ያለውን ቡድን ይገልጸው ይሆን? ቡድኑ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የተለያዬ ስያሜ ተሰጥቶታል። ቡድኑ በአማራ ክልል መንግሥት የህዝብ ደጀን ተደርጎ ሲቀርብ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ደግሞ 'አንዳንድ የአማራ ጽንፈኛ ታጣቂዎች' በሚል ይወገዛል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ ቡድኑን በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመፈፀም ይወነጅሉታል። የፋኖ አደረጃጀት በአማራ ክልል በተለያዩ ስፍራዎች ይገኛል። በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎንደር እና በጎጃም የራሱ አመራር ያለው ፋኖ የተደራጀበት ጊዜ እና ባህርያትም እንዲሁ የተለያዩ ናቸው። በጎጃም የሚንቀሳቀው ፋኖ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ እንደሚባልም ሰብሳቢው አቶ ዘመነ ካሴ ይናገራሉ። ፋኖ በአማራ ክልል በአራት የተለያዩ ሥፍራዎች ሲደራጅ እርሳቸው ላለፉት ስምንት ወራት በጎጃም የሚንቀሳቀሰውን ፋኖ በማደራጀት እና በመምራት ላይ ይገኛሉ። የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ውጊያ በከፈቱበት ወቅትም በአቀስታ በኩል ተሰልፈው መዋጋታቸውንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ራሳቸውን የአማራ ህዝባዊ ኃይል በሚል ለምን ማደራጀት እንደፈለጉ ሲጠየቁም \"ሕዝባዊ ጦርነት ታውጆብናል፤ ሕዝባዊ ጦርነት ማድረግ አለብን። ሕዝባዊ ዘመቻ ተካሄዶብናል፤ ሕዝባዊ ምላሽ መስጠት አለብን'\" በማለት ያስረዳሉ። ከጎጃም ወደ ወሎና ሸዋ ስንመጣ ደግሞ የነዚህ ኃይሎች ጥምረት የምስራቅ አማራ ፋኖ በሚል አደረጃጀት ስር መሰባሰባቸውን የቡድኑ ትምህርት ሥልጠናና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ ፈንታው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስለ ፋኖ አመሰራረትም ሲያስረዱ በ2008 በአገር አቀፍ ደረጃ የነበረውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በራያ ፋኖ በህቡዕ ተደራጅተው መንቀሳቀስ መጀመሩን ነው። በትግራይ ተነስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተውን ጦርነት በተለይም የትግራይ ኃይሎች በነሓሴ ወር ወደ አማራ ክልል ማቅናታቸውን ተከትሎ ደሴ ላይ የወሎ ፋኖን ማቋቋማቸውን ያስረዳሉ። እስከ 2011 ዓ.ም. ድረስ በይፋ መሳርያ ታጥቀው ይንቀሳቀሱ እንዳልነበርም አቶ አበበ ገልፀዋል። ሥልጠናም ቢሆን በ2014 ዓ.ም. የትግራይ ኃይሎች ጋር ከነበረው ውጊያ ጋር ተያይዞ የክልሉ መንግሥት እና የፌደራል መንግሥት ጥሪ ተከትሎ የተጀመረ እንጂ ቀድሞ እንዳልነበር ያስታውሳሉ። የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን ተከትሎ በደቡብ እና በሰሜን ወሎ በርካታ ግንባሮች ከመከላከያ እና ከልዩ ኃይሉ ጎን በመሆን መዋጋታቸውን አቶ አበበ ይናገራሉ። አቶ ዘመነ ከስምንት ወር በፊት፣ ነሐሴ 2013 ዓ.ም. ፋኖን ማደራጀት የፈለጉበትን ምከንያት ሲያስረዱ የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል መገስገስ በመጀመራቸው መሆኑን በቀዳሚነት ያነሳሉ። ነገር ግን 'በሌሎች አካባቢዎች የአማራን ሕዝብ በጠላትነት የፈረጁ ቡድኖች እና ኃይሎች ራሳቸውን ማፈርጠም እና ማደራጀት ሲጀምሩ' የአማራን ሕዘብን ለመታደግ መደራጀት እና መሰልጠን ያስፈልግ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ የአጭር ጊዜ ግብ ነው የሚሉት አቶ ዘመነ ከረዥም ጊዜ ግብ አንጻር ደግሞ ላለፉት አስርት ዓመታት 'የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማጠንጠኛ አማራ ጠልነት ነው' ይላሉ። ይህ ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስር የሰደደ አስተሳሰብ በአንድ እና በሁለት ዓመት ትግል ብቻ ይገታል ብለው እንደማያምኑ የሚናገሩት አቶ ዘመነ፤ \"በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሁሉም ሕዝቦች እንደ ዜጋ በነጻነት፣ በእኩልነት፣ በመከባበር፣ በፍትህ የሚኖሩበት ዘመን እስኪመጣ. . .የአማራ ህዘብ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ አንገቱን ቀና አድርጎ በእኩልነት መኖር እስኪችል ድረስ' ሕዝብን ማደራጀት፣ ማንቃት፣ ማሰልጠን አስፈላጊም ሲሆን ማስታጠቅ የሚችል አደረጃጀት ያስፈልጋል ብለው በማመናቸው የአማራ ህዝባዊ ኃይል በሚል መሰባሰባቸውን ያስረዳሉ። የአማራ ህዝባዊ ኃይል በመላው አማራ የሚንቀሳቀስ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዘመነ ይኹንና ጠንከር ያለ አደረጃጃት ያለው በጎጃም መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የፋኖ አመራሮች የአማራን ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱም መፃኢ እድል በትከሻቸው ላይ እንደሆነ ያምናሉ። የአማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አገሪቱ ከገባችበት ውጥንቅጥ ለማውጣትም እየታገሉ እንደሆነ የህዝባዊ ኃይሉ አመራሮች በልበ ሙሉነት የሚናገሩት ነው። \"ይህ ትውልድ አዲስ ቀመር ይፈልጋል። ያ አዲስ ቀመር ተምጦ መወለድ ካለበት አዲሱ 'ሜተዶሎጂ' አስተሳሰብን መሰረት ያደረገ፣ አላማን መሰረት ያደረገ፣ የአማራን ሕዝብ መሰረት ያደረገ፣ . . .ኢትዮጵያንም ከመፍረስ መታደግ ላይ መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ ላይ የቆመ ትግል\" ነው ይላሉ አቶ ዘመነ አቶ ዘመነ ትግላቸው አዲስ ቀመርና የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ አስተሳሳብ ላይ ያተኮረ ከሆነ ነፍጥ አንስቶ እየታገሉ ይህንን አስተሳሰብ ማስፈፀም አይቃረንም።ለዚህ ትግል የፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ መንቀሳቀስ አይሻልም ተብለው በቢቢሲ የተጠየቁ ሲሆን እርሳቸው እና አማራን ህዝባዊ ኃይል ፋኖን የሚመሩ አመራሮች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከፓርቲ ፖለቲካ የዘለለ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። \"በተለይ ለአማራ ህዘብ ጥያቄዎች የፖለቲካ ፓርቲ በዚህ ወቅት ያን ያክል አመርቂ ውጤት ያመጣል ብለን አናምንም\" ሲሉ ያስረዳሉ። አቶ ዘመነ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ታግለው ከተፈቱ የእነርሱ መሳሪያ አላስፈላጊ እንደሆነና እስከዚያው ግን በትጥቅ መታገላቸውን እንደሚቀጥሉ ይናገራሉ። \"የመሳሪያን አፈሙዝ የሚደፍነው ፍትህ ነው፣ የመሳሪያን አፈሙዝ የሚደፍነው በእኩልነት በአንድነት በፍቅር እንደ ዜጋ ተቻችሎ መኖር ነው። አንዱ አንበርካኪ ሌላው ተንበርካኪ ሆኖ በሚኖርነት ዓለም ውስጥ መሳሪያ አፈሙዝ ሁሌም ክፍት ነው። ሁሌም ምላጭ ይሳባል። \" በማለት የትጥቅ ትግልን አስፈላጊነት ያብራራሉ። በተለያዩ አካባቢዎች ስሙ የሚነሳው 'ፋኖ' ፋኖ በተደጋጋሚ በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና ምዕራብ ሸዋ ዞን ንፁኀንን በመግደል፣ ቤት ንብረትን በማቃጠል ውንጀላ ይቀርብታል። በቅርቡ ደግሞ ሰሜን ሸዋ አካባቢ ላጋጠመው ክስተት በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና ነዋሪዎች ውንጀላ ቀርቦበታል። ባለፈው ወር የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሚዋሰኑበት አካባቢ ጥቃት ተፈጽሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የአካባቢ ሚሊሻዎችና በነዋሪዎች ላይ ሞትና ጉዳት ደርሷል። ቢቢሲ በኦሮሚያ ውስጥ በመንቀሳቀስ ጥቃት ያደርሳሉ በሚል ስለሚወነጀሉት 'ፋኖዎች' ምላሽ የሚሰጥ አካል አላገኘም። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ለተከሰተው ግጭት ተጠያቂ ሆነው ከቀረቡት ኃይሎች መካከል አንዱ ፋኖ ነው። ለዚህ ጥፋት የአካባቢው የአማራ ክልል አመራሮች 'ሸኔ'ን ተጠያቂ ሲያደርጉ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ደግሞ ተጠያቂዎቹ የፋኖ ታጣቂዎች ናቸው ይላሉ። በፋኖዎች ላይ የሚቀርበው ውንጀላ ከኦሮሚያ ክልል አልፎ በቤንሻንጉል መተከል ዞንም ይሰማል። በቅርቡም ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ፣ የትግራይ ተወላጆች ላይ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ተፈጽመዋል በሚል ባወጡት ሪፖርት ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ስማቸው ተነስቷል። በዚህ ሪፖርት ላይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ መንግሥት ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን ያፍርስ ሲሉ ጠይቀዋል። የፋኖ ታጣቂዎች ከክልሉ ውጪ የተለያዩ ጥቃቶች በመፈፀም ስማቸው እንደሚነሳ የተጠየቁት የአማራ ህዝባዊ ኃይል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዘመነ 'እኛ የምናውቃቸው የሉም፤ ይኖራሉ ብለን አናምንምም' ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የአማራ ህዘብ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚኖር አንስተው አማራ በየደረሰበት ተከባብሮ፣ ተቻችሎ የሚኖር እንጂ ራሱን በፋኖነት አደራጅቶ፣ በታጣቂነት ራሱን አደራጅቶ. . .አብሮት ከኖረው ማህበረሰብ ጋር የሚናቆር ወይንም አብሮት የሚኖረውን ማህበረሰብ መሳሪያ አንስቶ የሚታገል፣ የሚረብሽ ማህበረሰብ አይደለም እሴቱም አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። አቶ አበበ በበኩላቸው ከወለጋ፣ ከመተከል እንዲሁም ከተለያዩ የደቡብ ክልል አካባቢዎች እነርሱ ጋር በመምጣት ስልጠና የወሰዱ የአማራ ተወላጆች መኖራቸውን ይናገራሉ። አቶ ዘመነ ግን ከክልሉ ውጪ መጥተው እነርሱ ጋር ስልጠና የወሰዱ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደሌሉ ያስረዳሉ። አቶ ዘመነ አክለውም በክልሉ ከሚንቀሳቀሱት ከጎንደር፣ ከሸዋ እና ወሎ የፋኖ አመራሮች ጋር እንደሚገናኙ ፣ እንደሚነጋገሩ እና እንደሚመካከሩ ያስረዳሉ። አቶ አበበም ቢሆኑ በተለያዩ የክልሉ ስፍራዎች የሚገኙ የአማራ አደረጃጀቶች በተለያየ ጊዜ እየተገናኙ እንደሚመካከሩ ገልፀዋል። አቶ ዘመነም ሆኑ አቶ አበበ በቅርቡ አንድ መዋቅር በመፍጠር በአንድ ጥላ ስር የመሰባሰብ ፍላጎት መኖሩን ለዚህም በጋራ እየሰሩ መሆኑን ይናገራሉ። በዚህም ይላሉ አቶ ዘመነ \"ከአንድ እዝ ሰንሰለት የሚታዘዝ ፋኖ እንፈጥራለን ብለን ነው የምናስበው\" ይላሉ። ይህ በአንድ እዝ ስር የሚታዘዝ ፋኖ ግን መቼ ይፋ እንደሚሆን አቶ አበበም ሆኑ አቶ ዘመነ ቁርጥ ያለ ቀን አላስቀመጡም። 'ስልጠናና ምልመላዎች ቀጥለዋል' የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል ከወጡም በኋላ በክልሉ አሁንም እንደ አዲስ ለፋኖ አባልነት የሚመለመሉ እና የሚሰለጥኑ መኖራቸው ይናገራል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ተብለው የተጠየቁት የፋኖ አመራሮች አሁንም የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ አለመውጣታቸውን ይናገራሉ። ለዚህም ማስረጃ ሲያቀርቡ ከፊል ራያ እና ከፊል ዋግ በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አቶ አበበም ሆኑ አቶ ዘመነ ይናገራሉ። አቶ ዘመነ \"የትግራይ ኃይሎች በወልቃይት እና ሁመራ ምሽግ እየቆፈሩ ጦር እያደራጁ ነው\" በማለት \"የወረራ ስጋት መኖሩንም\" ያነሳሉ። አቶ አበበ በበኩላቸው \"የምንዘጋጀው ለታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶችም ጭምር ነው፤ በአቅማችን አገራችን በፈለገችን ልክ ለመገኘት እንሰለጥናለን፤ እንታጠቃለን' ይላሉ። ቀድሞ መዘጋጀት ቀድሞ ስጋትን ያስወግዳል የሚሉት አቶ ዘመነ 'ስለዚህ ፋኖ መመልመሉ፣ ፋኖ ማሰልጠኑ፣ ፋኖ ማስታጠቁ ይቀጥላል\" ሲሉ ያስረዳሉ። ከዚህም ባሻገር \"አማራ እንደ ሌሎች ዜጎች በእኩልነት ተከብሮ ሌሎችንም አክብሮ . . . የሚኖርበት ዘመን እስኪመጣ ራስን ማዘጋጀት እና ራሰን ማስታጠቅ አስፈላጊ ነው ብለን ነው የምናምነው\" ይላሉ። የፋኖ አመራሮቹ የሚያስቡት እና ለአማራ ህዝብ ይገባዋል የሚሉት ሰላም ቢሳካ እቅዳቸው ምን እንደሆነ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሁለቱም በአንድነት ሁላችንም ወደ የሙያችን እንመለሳለን ሲሉ ይናገራሉ። አቶ አበበ ደግሞ ልዩ ኃይሉም ሆነ መከላከያ ስልጠና እንዳይሰጡ አግደዋቸው እንደማያውቁ በመግለጽ ስልጠናው እንደሚቀጥል ገልፀዋል። የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች በተለያየ ጊዜ መከላከያ እና ልዩ ኃይሉ የመሳሪያ ድጋፍ እንዳደረገላቸው ይናገራሉ። አቶ አበበ የአገር መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን ተከትሎ 30 ክላሽ አራት ላውንቸር፣ ብሬን እና ስናይፐር መስጠቱን ይናገራሉ። የአማራ ክልል መንግሥትም አንድ ዲሽቃ እንደ ሸለማቸው ይናገራሉ። ከዚህ አልፎ የስንቅ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ያስረዳሉ። አቶ አበበ 'አጠቃላይ ትዕዛዝ፣ አመራር የምንቀበለው ከአገር መከላከያ ሠራዊት ነው' ይላሉ። አልፎ አልፎ ከልዩ ኃይሉ ትዕዛዝ መቀበል ቢኖርም በዋናነት ግን ግንባሩን የሚመራው የአገር መከላከያ ሠራዊት መሆኑን ያስረዳሉ። አቶ ዘመነ በበኩላቸው \"ሙሉ በሙሉ ድጋፋችን ከህዝብ ነው\" በማለት ከክልሉ ልዩ ኃይልም ሆነ ከመከላከያ አንድም የመሳርያ እና የስንቅ ድጋፍ አግኝተው እንደማያውቁ ያብራራሉ። አቶ ዘመነ የክልሉ መንግሥት በተለያየ ጊዜያት ፋኖ ትጥቁን አይፈታም ማለቱን አንስተው \"ይህ ግን እናስታጥቀዋለን ማለት አይደለም፤ እናሰለጥነዋለን ማለት አይደለም\" በማለት ከክልሉም ሆነ ከአገር መከላከያ ሠራዊት የሚደረግላቸው ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደሌለ ተናግረዋል። አቶ ዘመነ ምንም ዓይነት መሳርያ እንደታጠቁ ሲጠየቁ \"በቂ ልብ ስላለን እኛ ቤት ቁመህ ጠብቀኝም ቢሆን ቁም ነገር አለው\" በማለት ዝርዝር ጉዳይ ከመመለስ ተቆጥበዋል። የምስራቅ አማራ ፋኖ አደረጃጀትን በሚመለከትም አቶ አበበ ሲናገሩ፣ አንድ በብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ስም የተሰየመ ብርጌድ ስር ኃይሎቻቸውን ማደራጀታቸውን ይናገራሉ። ይህ አንድ ብርጌድ ግን ምሽግ ላይ ያለ ብቻ መሆኑን እና ከኋላ ያለው ተደራጅቶ ቢመጣ 'ብዙ ብርጌዶች' እንደሚሆን ያስረዳሉ። አቶ ዘመነን በስራቸው ምን ያህል ፋኖዎች ስልጠና ወስደው እንደሚገኙ ተጠይቀው \"በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ፤ ነገ ደግሞ በብዙ ሚሊዮኖች እንሆናል\" በማለት በደፈናው መመለስን መርጠዋል። አደረጃጀታቸውንም በሚመለከት ለየት ያለ ራሱን የቻለ አደረጃጀት ያለው ከማለት ውጪ ዝርዝሩን ከመመለስ ተቆጥበዋል። አቶ አበበ በበኩላቸው \"ሙሉ ወሎ እና ሙሉ ሸዋ ሰልጥኗል ማለት ትችላለህ\" በማለት በወሎ ብቻ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልጥነው እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ገለጻና የሥራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅን ማስፈታት እንደሚያስፈልግ ተናግረው ነበር። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትይዩ የቆሙ ኃይሎች (Parallel Forces) በማለት ስሙን የጠሩት \"ሸኔ\"ን ብቻ ሲሆን እነዚህ ኃይሎች 'ተቋም በሚገዳደር' መልኩ መሄድ እንደሌለባቸውም አብራርተዋል። ቢቢሲ በቅርቡ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኞች ከዚህ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ጋር ተመሳሳይ የሆነ ኃሳብ አንስተዋል። እነዚህ ምሁራን አሁን በየአካባቢው የሚታየውን የታጠቁ ኃይሎች መብዛት በማንሳት፣ በአንድ አገር የጦር መሳሪያ የበላይነት መያዝ ያለበት መንግሥት ብቻ ነው ይላሉ። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ከባሕር ዳር ሕዝብ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የትግራይ ኃይሎች ወደ ደሴ እየተቃረቡ በሚመጡበት ወቅት የአማራ ክልል ወጣቶች እንዲዘምቱ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውሰዋል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ተሰልፈው መሞታቸውን፣ መቁሰላቸውን፣ ጊዜና ጉልበታቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። አክለውም \"ለእነዚህ ትልቅ ክብር አለን፤ እውቅና እና ሽልማት እያዘጋጀን ነው\" ብለዋል። \"ከዚህ አንጻር ለአገር መስዋዕትነት የከፈሉ ፋኖዎች ለክልሉ ብርቅ ድንቅ ናቸው\" በማለት ትጥቃቸውን እንደማይፈቱ እንዲሁም እንደማይዋከቡ በይፋ ተናግረዋል። በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ የትግራይ ኃይሎች ከክልሉ መውጣታቸውን ተከትሎ በርካቶች ፋኖ ነን በማለት መነሳታቸውን ጠቅሰዋል። ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) \"ፋኖ ነን ብሎ ይቁም ጥሩ ነው፤ ነገ ችግር ሲያጋጥመን ሊጋፈጥ ይችላል። ሊዋጋ ይችላል፤ መከታ ሊሆን ይችላል ብለን እናስባለን\" ካሉ በኋላ በተለያየ አካባቢ በፋኖ ስም ተነስተው ጥፋት ያደረሱ አካላትን ኮንነዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ \"የሕግ የበላይነት፣ የክልሉ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ\" እንዳለበት አሳስበው \"በየትኛውም መንግሥት ባለበት አገር ከመንግሥት ውጪ ወታደራዊ ሙያ የለም፤ አይኖርም\" ብለዋል። ከኖረም የሚኖረውን አደጋም ሲያስረዱ ልክ እንደ ሶማሊያ፣ የመንና ሊብያን በመጥቀስ አገር በተለያዩ 'ጎበዝ አለቆች ስር' ትሆናለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ርዕሰ መስተዳደሩ ፋኖ ለሚያካሄደው ሥልጠና የጠነከረ ወታደራዊ ሥነ ምግባር እንደሚያስፈልግ በመግለጽ እንደዚህ ከሕግ እና ሥርዓት ውጪ የሚሆኑ እና ስርዓት አልበኝነት የሚያሰፍኑ አካላት የፋኖ ስም አይገባቸውም ሲሉ ኮንነዋቸዋል።", "የሶማሊያ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ውዝግብ ወዴት ያመራ ይሆን? የሶማሊያ ምርጫ መራዘሙን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በፖለቲከኞች መካከል አለመተማመንን ከፈጠረ ሰነባበተ። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የምርጫ ማራዘሚያ ውሳኔ በማጽደቅ የፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የሥልጣን ዘመን ለሁለት ዓመት ማራዘሙን ተከትሎ ነበር አለመግባባቱ የተባሰው። የሶማሊያ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሥልጣን ማራዘሚያውን ውድቅ ከማድረግ ባለፈ ፋርማጆን በሥልጣን ቅሚያ ከሰዋል። ይህን ተከትሎ በርዕሰ መዲናዋ ሞቃዲሾ የሰዎችን ህይወት የነጠቀ ሁከትና ብጥብጥ ተከስቶ ነበር። ባለፈው ሚያዝያ በፌደራል መንግሥቱ ደጋፊዎችና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል። የውዝግቡ ቁልፍ ተዋናዮች ተቃዋሚዎች የፕሬዝዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ዘመን ስላበቃ ከእንግዲህ እውቅና አንሰጥም ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ ናሽናል ሳልቬሽን ፎረም የተባለ ተሰሚነት ባላቸው የተቃዋሚዎች ብሔራዊ መድረክ አቋቋሙ። ይህም የፋርማጆ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የሴኔቱ አፈ ጉባኤ አብዲ ሀሺ አብዱላሂ፣ የጁባላንድ እና ፑንትላንድ መሪዎችን ያካተተ ጥምረት ነው። ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም ያሉት የስልጣን ማራዘሚያ ላይ \"አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን\" ሲሉም ዛቱ። የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ እና የጁባው አቻቸው አህመድ መሐመድ ኢስላም በሞቃዲሾ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ነበር። ተወካዮቹን \"ሶማሊያን ከማይቀረው የትርምስ አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ እንዲያድኑ\" ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ምክር ቤት ፋርማጆን ለመተካት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ጥምረት ነው። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼክ አህመድ የሚመራ ሲሆን ፕሬዚዳንቱን \"የጦር አበጋዝ\" ብለዋቸዋል። በወቅቱ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና የአውሮፓ ሕብረት የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ጊዜ የማራዘሙ ውሳኔ ሶማሊያ ወደ ሠላምና መንግሥት ግንባታ የምታደርገውን ጉዞ የሚያደናቅፍ ብለዋል። ግንኙነታቸውን በድጋሚ እንደሚያጤኑትም አስጠንቅቀዋል።አሜሪካ \"ሰላምን እና መረጋጋትን በማደናቀፍ\" በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥልም ዝታ ነበር የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት የሥልጣን ጊዜ ማራዘሙን ውድቅ አድርጎታል። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ መሪዎች በምርጫ ውዝግቡ ዙሪያ ውይይት እንዲቀጥሉ ያቀረበውን ሃሳብ እንደሚደግፍም አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም በታችኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች እና በጋልሙዱግ፣ በሂውማሌ እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ሰፊ ድጋፍ አላቸው። የፌዴራል መንግሥት ፈተና የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሥር የሰደደውን የጎሳ ግጭት ለማስቆም እና አሃዳዊ መንግሥት ለመመስረት የሚደረገው ጥረት በመሰናከሉ የተመሠረተ ነው። የተከፋፈለና ደካማ ቢሆንም የብሔራዊ ደኅንነት ግንባታው እያዘገመም እንዲጓዝ መንገዱን ጠርጓል። አገሪቱ ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት ሥርዓት ለመቀላቀልም የፋይናንስ ተቋማቷን እንደገና አደራጅታለች። ምርጫው ያስከተለው አለመረጋጋት በማዕከላዊ መንግሥት እና ቀድሞውንም የፋርማጆን ሥልጣንን 'በሚያኮስሱት' አንዳንድ የክልል መንግሥታት መካከል ውዝግቡን አጡዞታል። እአአ መስከረም 2018 አምስት የአገሪቱ የክልል ፕሬዚዳንቶች በሥልጣን እና በሃብት ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እንደማይተባበሩ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆም ለምላሽ አልዘገዩም። ክልሎችን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ማድረግ ጀመሩ። ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን በማንሳት አጋሮቻቸውን በጋልሙዱግ እና በደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አስቀምጠዋል። የፌዴራሉ መንግሥት በፑንትላንድ እና በጁባላንድ ባሉ ምርጫዎች ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ ማሳደር ግን አልቻለም። የእነዚህ አካባቢ መሪዎች ፋርማጆ እንደገና እንዳይመረጡ እየሠሩ ነው። መስከረም ላይ የተደረገው ስምምነት ፕሬዝዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ጊዜ በይፋ ያበቃው በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ ቢሆንም አዲስ ፕሬዝዳንት እንዴት እንደሚመረጥ በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ምርጫው ተራዝሟል። ለምርጫው መስተጓጎል ፕሬዝዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እርስ በእርሳቸው እየተወነጃጀሉም ነው። ብሔራዊው የምርጫ ኮሚሽን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ ለማድረግ እንደማይቻል አስታወቀ። ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማዘጋጀት እስከ 13 ወራት ድረስ እንደሚያስፈልገው እአአ ሰኔ 2020 ለሕዝብ እንደራሴዎች ገለጸ። የጁባላንድ፣ ፑንትንትላንድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን መዘግየት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ እአአ ሐምሌ 2020 አስደንጋጭ ነበር የተባለለት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሃሰን አሊ ኬይሬ ከሥልጣን መነሳት በምርጫው ሂደት ላይ ያላቸውን እምነት ይብስ ሸረሸረው። የጁባላንድ እና የፑንትላንድ መሪዎች በማዕከላዊው ዱሳማሬብ ከተማ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። በስብሰባው ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ስምምነት ተደርሷል። እአአ መስከረም 17 ቀን 2020 ከሳምንታት የዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ በምርጫ ሁኔታዎች ላይ ስምምነት ተፈረመ። በስምምነቱ መሠረት ሁለት የምርጫ ክልሎች በእያንዳንዱ ክልል ይኖራሉ። ምርጫዎች የሚካሄዱት በየክልል ተሰብሳቢዎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ውስጥ 101 የምርጫ ልዑካን ድምጽ ይሰጣሉ። በአማጽያን ጥያቄ መሠረት ምርጫውን በበላይነት የሚቆጣጠር ብሔራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ተወሰነ። የጁባላንዱ ማዶቤ እና የፑንትላንዱ ዴኒ በፌዴራል መንግሥት የተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ባለመቀበላቸው የስምምነቱ ትግበራ ድጋሚ እንቅፋት ገጠመው። የፀጥታ አዛዦች እንዲነሱ እና ፓርላማው እንዲበተንም ጠየቁ። የምርጫውን መዘግየት አስቀድሞ የገመተው የፌዴራልሉ ፓርላማ እአአ ኅዳር 2020 አዲስ ተመራጮች እስኪተኩ ድረስ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። የጎሳ ፖለቲካ እና ግጭት አለመተማመኑ እየጠነከረ ሲሄድ ፖለቲከኞች እና ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ወደ ጎሳቸው መመሸግ ጀመሩ። እነዚህም በጎሳ ሚሊሻዎች፣ በጎበዝ አለቆች እና በቀድሞ የጦር መሪዎች የሚጠበቁ ናቸው። የተወሰኑ የተቃዋሚ የፓርቲ አመራሮች ለትጥቅ ትግል መዘጋጀት ያዙ። የጦር መሳሪያዎችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የገዙም አሉ። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የዘገየውን ምርጫ የሚቃወሙ ሰልፈኞችን በሚደግፉ ወታደሮች እና በፖሊስ መካከል መጋቢት 15 ግጭት ተፈጠረ። የፖሊስ መኮንኖቹ በቱርክ የሰለጠነው ልዩው የሃርማድ የፖሊስ ኃይል አባላት ነበሩ። ከዚህ በፊት መንግሥት ፍላጎቱን በክልል መንግሥታት ላይ ለመጫን ይህን ልዩ ኃይል ይጠቀም ነበር። የቀድሞው የሞቃዲሾ የፖሊስ አዛዥ ሳዲቅ ኦማር ሐሃሰን (ሳዲቅ ጆን) እአአ ሚያዝያ 13 በምርጫ ውዝግብ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀውን የፓርላማ ስብሰባ በማገድ ፊታቸውን መንግሥት ላይ አዞሩ። ከኃላፊነት ተነስተው ማዕረጋቸውም ተገፈፈ። የቀድሞው የፖሊስ አዛዥ ከቀናት በኋላ በጎበዝ አለቆች እና ከጎሳቸው በተገኙ ሚሊሺያዎች እየተጠበቁ በከተማው ዳይናል አካባቢ ካምፕ መሠረቱ። መንግሥት የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ አካባቢዎች በማሰማራቱ ውጥረቱ ዋና ከተማዋን አዳርሷል። በኋላ ላይ ሁኔታው ተረጋጋ። ምርጫው መፍትሔ ያገኘ መሰለ ሚያዝያ ላይ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ለሁለት ዓመታት ለማራዘም ያደረጉትን ሙከራ ማቆማቸውን ይፋ አደረጉ። ለሕዝቡ ባደረጉት ንግግርም አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበው ጠቅላይ ሚኒስትራቸው ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል። በቀጣይ ቀናትም የሶማሊያ የፖለቲካ መሪዎች ምርጫ ለማካሄድ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተስማሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሁሴን ሮብሌ እና የክልል ፕሬዝዳንቶች በ60 ቀናት ውስጥ ሂደቱን ለመጀመር የሚያስችል ስምምነትም ተፈራርሙ። ምርጫው በተለያየ የጊዜ ሰሌዳ እንደመካሄዱ ሐምሌ ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ምርጫው ተጀመረ። የሶማሊያ የጁባላንድ ክልል ምክር ቤት ኢሊያስ ባዳል ጋቦሴን የመጀመርያው የሶማሊያ ሴኔት አባል አድርጎ መርጧል። የጎሳ መሪዎች የፓርላማ አባላትን የሚመረጡበት የተወሳሰበው የሶማሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ከኅዳር ወር ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን ከቀናት በፊት መጠናቀቅ ነበረበት። ግን እሳካሁን አላለቀም። የደኅንነት ሠራተኛዋ መጥፋት መስከረም ላይ ደግሞ ሌላ ውዝግብ ተከተለ። በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ኢክራን ታህሊል የተባለች የደኅንነት ሠራተኛ በመጥፋቷ ምክንያት በፕሬዝዳንቱ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ውዝግብ አገረሸ። የደኅንነት ቢሮው ኢክራን ታህሊል በአልሸባብ ታግታ መገደሏን ቢገልጽም፣ አሸባሪው ቡድን ጉዳዩን አስተባብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሁሴን ሮብሌ የደኅንነት ቢሮው ኃላፊ ጉዳዩን የያዙበት መንገድ ቅር አሰንቶኛል በማለት ከሥራ አግዷቸው። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ደግሞ የደኅንነት ኃላፊው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ አዘዙ። ከጠፋችው የደኅንነት ሠራተኛ በተጨማሪ በደኅንነት ቢሮው ተጠሪነት ጉዳይ ጭምር ነው የሁለቱን አውራ ፖለቲከኞች ልዩነት ያሰፋው። በሁለቱ መሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎችን የመከፋፈል አደጋም አስከትለ። ጥቅምት ላይ ሁለቱ ባለሥልጣናት የአገሪቱን ምርጫ ሊያደናቅፍ ይችላል የተባለለትን አለመግባባት ለማቆም ተስማሙ። የጠፋችውን የደኅንነት ቢሮ ባልደረባ ጉዳይም ለፍርድ ቤት እንደሚተው ተስማምተዋል። አዲሱ ውዝግብ ከቀናት በፊት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ ፋርማጆ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሁሴን ሮብሌን ከሥልጣናቸው ማገዳቸውን አስታወቁ። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታገድ እንደ ምክንያት የቀረበው ሥልጣንን አላግባብ መጠቀምና የመንግሥት የሆነ መሬትን መቀራመት የሚል ነው። ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሶማሊያ ብሔራዊ ሠራዊት ይዞታ የሆነን የሕዝብ መሬትን ወስደዋል እና የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር በሚያካሂደው ምርመራ ውስጥ ጣልቃ ገብተዋል ሲሉ ከሰዋቸል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የሶማሊያ ባሕር ኃይል አዛዥ የሆኑትን ጄነራል አብዲሃሚድ ሞሐመድ ዲሪርንም ከኃላፊነታቸው አግደዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሁሴን ሮብሌ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርገው ፕሬዚዳንቱ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሞክረዋል በማለት የወነጀሏቸው ሲሆን በሥልጣናቸው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል። ከዚያም አልፈው የአገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ትዕዛዝ መቀበል ያለባቸው ከፕሬዝዳንት ፋርማጆ ሳይሆን ከእሳቸው እንደሆነም አሳስበዋል። አዲሱ ውዝግቡ በሶማሊያ ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳያስከትል ስጋት ፈጥሯል። በሶማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ መሪዎቹ \"ከጸብ ጫሪ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እና የኃይል እርምጃዎችን እንዲያስወግዱ\" አሳስቧል። አገሪቱ በተለያዩ ጎራ በተሰለፉ ፖለቲከኞች እና በጎሳዎች መካከል ፈተና ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ካለው አልሸባብ አማጽያን ጋርም እየተዋጋች ነው።", "በጋምቢያው ምርጫ ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው አሸንፊያለሁ አሉ የጋምቢያው ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው በአገሪቱ የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ አሸንፊያለሁ ሲሉ አዋጁ። አዳማ ባሮው የጋምቢያ የረዥም ጊዜ መሪ ያህያ ጃሜህ ሳይወዳደሩ የቀሩበትን ምርጫ በቀላሉ በድጋሚ ማሸነፋቸውን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ባሮው ከቅዳሜውን ምርጫ ድምጽ 53 በመቶ አካባቢ ያገኙ ሲሆን፣ የቅርብ ተቀናቃኛቸው የሆኑት ጠበቃ ኦሳኢኖ ዳርቦ 28 ከመቶውን ድምጽ አግኝተዋል። ዳርቦ እና ሌሎች ተቃዋሚ ዕጩዎች የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ ቀደም ብለው አስታውቀው ነበር። ምርጫው የጋምቢያን የዴሞክራሲ ሥርዓት የሚፈተንበት ነውም ተብሎለታል። ባለፈው ምርጫ ያህያ ጃሜህ በባሮው የተሸነፉ ሲሆን ውጤቱን ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በስደት ለመኖር መርጠዋል። የጃሜህ የ22 ዓመታት የሥልጣን ዘመን በበርካታ የበደል ውንጀላዎች የታጀበ ሲሆን በቅርቡ ለአገሪቱ የእውነት አፈላላጊ ኮሚቴ ቃላቸው የሰጡ የዓይን እማኞች በያያ ጃሜህ አስተዳደር ወቅት በመንግሥት የሚደገፉ ግድያዎች ስለመኖራቸው እንዲሁም የኤድስ ታማሚዎች የማይፈውስ የውሸት ሕክምና እንዲወስዱ ይገደዳሉ ብለዋል። ጃሜህ በውጭ አገር ቢሆንም ተጽእኖ ፈጣሪነታቸው እንደቀጠለ ነው። ከአገር ውጪ ሆነው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ደጋፊዎቻቸው ለባሮው ድምጻቸውን እንዳይስጡ ሲወተውቱ ነበር። አዳማ ባሮው የተሳካላቸው የሪልስቴት አልሚ ሲሆኑ በአንድ ወቅት ለንደን ውስጥ የጥበቃ ሠራተኛ እንደነበሩ ይነገራል። እ.ኤ.አ. 2017 ላይ በተደረገው ምርጫ ጃሜህን ማሸነፋቸው ግርምትን የፈጠረ ነበር። የማሸነፋቸው ዜና ሲሰማም ደጋፊዎቻቸው በጎዳናዎች ላይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለጹ ነው። ባሮው በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል ባደረጉት የድል ንግግር በአገሪቱ የፖለቲካ አንጃዎች መካከል አንድነት እንዲኖር ጠይቀዋል። \"የእናንተ የፖለቲካ ልዩነት ምንም ይሁን ምን ሁሉም የጋምቢያ ተወላጆች የፖለቲካ እና ሌሎች ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን እንደ አንድ ሕዝብ በመሰባሰብ ለአገራችን እድገት እንድንረባረብ ጥሪዬን አቀርባለሁ\" ብለዋል። ጋምቢያ በአፍሪካ ከሚገኙ ትንሽ አገራት መካከል አንዷ ሰትሆን፤ 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ ብቻ አላት።", "የዩናይትድ ኪንግደም ምክር ቤት አባል በስለት ተወግተው ተገደሉ ወግ አጥባቂው የዩናይትድ ኪንግደም የፓርላማ አባል ሰር ዴቪድ አሜስ አርብ ዕለት በስለት ተወግተው ተገደሉ። የምክር ቤት አባሉ ለንደን በሚገኘው ኢሴክስ የምርጫ ክልላቸው ውስጥ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ሊይ ኦን ሲ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመራጮች ጋር በነበሩበት ወቅት በስለት ወግቷቸዋል በሚልም ፖሊስ አንድ የ25 አመት ወጣት ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሏል። የወጋበትን ስለት እንዳገኙና ከምክር ቤቱ አባል ግድያ ጋር በተያያዘ ሌላ ተጠርጣሪ እንደማይፈልጉ ፖሊሶች አስታውቀዋል። የ69 ዓመቱ ሰር ዴቪድ ከአውሮፓውያኑ 1983 ጀምሮ በምክር ቤት አባልነት ያገለገሉ ባለትዳር እና የአምስት ልጆች አባት ነበሩ። \"ታላቅ ሰው፣ ታላቅ ጓደኛ እና ታላቅ የፓርላማ አባል፣ ዴሞክራሲያዊ ሚናውን ሲወጣ ተገድሏል\" በማለት የጤና ሚኒስትሩ ሳጂድ ጃቪድ ሐዘናቸውን ገልፀዋል። \"ከሁሉ የከፋው የአመፅ ገጽታ ኢሰብአዊነት ነው። ከዓለም ደስታን ይሰርቃል እናም እኛ በጣም የምንወደውንም ሰው ከእኛ ወስዷል\" በማለት ቻንስለር ሪሺ ሱናክ ተናግረዋል። \"ዛሬ አባት፣ ባል እና የተከበረ ባልደረባችንን ተነጠቅን። ለሚወዱት በሙሉ በጸሎት አስባቸዋለሁ። መፅናናትንም እመኛለሁ\" በማለት አክለዋል። የሳውዝ ኢንድ ዌስት ተወካይ የሆኑት ሰር ዴቪድ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው በምርጫ ወረዳቸው የመረጧቸው አባላቶቻቸው አሳሳቢ የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲሁም ቃል የገቡትን ሁኔታ የሚያነሱበት ውይይት እያካሄዱ ነበር። ውይይቱም እየተካሄደ የነበረው በሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ነበር። የኢሴክስ ፖሊስ እንደገለጸው አንድ ሰው በስለት ተወግቶ መጎዳቱ ሪፖርት የደረሰው በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር አርብ 6፡05 ነበር። በስፍራው በአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ ህክምና ቢደረግላቸውም ህይወታቸው ያለፈው ወዲያው ነው። ሰር ዴቪድ በአውሮፓውያኑ 2016 የፓርላማ አባል ጆ ኮክስን ግድያ ተከትሎ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የተገደሉ ሁለተኛው የምክር ቤት አባል ናቸው። ጆ ኮክሰን የምርጫ ውይይት ለማድረግ በምዕራብ ዮርክሻዮር ባቀኑበት ወቅት ነበር ከቤተ መጽሃፍት ውጪ የተገደሉት።", "አሜሪካ የሳን ሱ ቺ እስርን ተከትሎ ሚያናማር ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ስትል አስጠነቀቀች በሚያናማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን በሚያናማር ላይማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ። በቀድሞዋ በርማ በዛሬዋ ሚያናማር የነበረውን አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግሥት ተከትሎ በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ ማዕቀብ ተጥሎ ቆይቶ ነበር። ትናንት በሚያንማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት አከናውኗል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል። የተባበሩት መንግሥታት፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ሕብረት በበርማ የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት አጥብቀው ኮንነዋል። ከእአአ 1989-2010 በእስር ቆይተው የነበሩት ሳን ሱ ቺ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት ለደጋፊዎቻቸው በጻፉት ደብዳቤ “መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃወሙ” ብለዋል። ሳን ሱ ቺ መፈንቅለ መንግሥቱ በአገሪቱ ወታደራዊ አምባገነናዊ ስርዓትን ያመጣል ሲሉ ጽፈዋል ተብሏል። በሚያንማር በወታደሩ እና በሲቪል አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት ተከስቶ ነበር። ባለፈው ሕዳር በተደረገ ምርጫ የሳን ሱ ቺ ፓርቲ 'ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ' መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን የመቀመጫ ቁጥር ማግኘት ችሎ ነበር። ሆኖም የአገሪቱ ጦር ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ቆይቷል። ጦሩ መፈንቅለ መንግሥቱን ካደረገ በኋላ የ11 ሚንስትሮችን እና ሚንስትር ዲኤታዎችን ሹም ሽር አድርጓል። በሌሎች እንዲተኩ ከተደረጉ ሚንሰትሮች መካከል የፋይናንስ፣ የጤና እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ይገኙበታል። ፕሬዝደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም ብለዋል። አሜሪካ ከ10 ዓመታት በላይ በበርማ ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ ያነሳችው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገሯን ተከትሎ ነው። ባይደን፤ “በየትኛውም ስፍራ በዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ሲደርስ አሜሪካ ወደጎን አትልም” ብለዋል። ይሁን እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥቱን ለማደረግ ሲነሳ አሜሪካ ማዕቀብ እንደምትጥል ቀድሞ ያውቃል። ከአሜሪካ ማዕቀብ ይልቅ መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ ቻይና፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ የሚሰጡት ምላሽ ለጦሩ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም ቻይና የሚያንማር ጉዳይ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን ተቃውማ ነበር። በቀጠናው ከሚገኙት አገራት መካከል ካምቦዲያ፣ ታይናላንድ እና ፊሊፒንስ በበኩላቸው የበርማ ጉዳይ የአገሪቱ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ጣልቃ መግባት እንደማይሹ ገልጸዋል። ይህ መፈንቅለ መንግሥት በአገሪቷ ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃትን ፈጥሯል። በርማ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትእንደምትሸጋገር ተስፋን ሰንቀው ለነበሩት ዜጎች የሳን ሱ ቺ እና ሌሎች ሲቪል ፖለቲከኞች እስር እና መፈንቅለመግሥት የዲሞክራሲ ተስፋን ያጨለመ ሆኖባቸዋል። አውራ ጊዳናዎች ጸጥ እረጭ ብለው ታይተዋል። በዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ ብዛት ያላቸው የአገሪቱ ጦር አባላትተሰማርተው ታይተዋል። ሰኞ ዕለት ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት ግነኙነት ማክሰኞ ንጋት ላይ ተመልሷል። የአገሪቱ ዋነኛ አየር ማረፊያ ግን አሁንም ዝግ እንደሆነ ነው። ትናንት [ሰኞ] ወታደሮች የአገሪቱን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውና መሪያቸውም ኮማንደር ሚነ ኦንግ ሌይንግመሆናቸውን ተናግረዋል። በርካታ ወታደሮች በአገሪቱ ዋና ከተማ ናይፒታው እና በሌላኛዋ ትልቋ ከተማ ያንጎን ጎዳናዎች በብዛት ታይተዋል። የሞባይልና ኢንተርኔ አገልግሎት እንዲሁም ስልክ በስፋት የተቋረጠባቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሲሆን የአገሪቱብሔራዊ ቴሌቪዥን ሥርጭት ለማድረስ እክል ገጥሞኛል በማለት ተቋርጧል። በርካታ ወታደሮችም በተለያዩ ቦታዎች እየሄዱ የሲቪል አስተዳደሩ ሚኒስትሮች የነበሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውሉነበር። የቢቢሲዋ የደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ወኪል እንደምትለው ከሆነ ሳን ሱ ቺ በአገሪቱ ዜጎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትአላቸው። ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ ያላትን ሳን ሱ ቺን የመሰሉ ፖለቲከኞችን ማሰር ትልቅ ውሳኔ ነው። ይህ ምርጫ የወታደራዊ መንግሥት አስተዳደር ካበቃበት ከ2011 ወዲህ ሲካሄድ ለ2ኛ ጊዜ ነው። ነገር ግን ይህን ምርጫ ወታደሩ ሳይቀበለው ቀርቶ ነበር። ይህን ተከትሎም ምናልባት ወታደሩ መፈንቅለ መንግሥት ያደርግ ይሆናል የሚል ፍርሃት ነግሶ ቆይቶ ነበር። ሳን ሱ ቺ የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦንግ ሳን ሴት ልጅ ናቸው። አባቷ የተገደሉት እሷ ገና የ2 ዓመት ልጅ ሳለች ነበር። የተገደሉትም በርማ ከእንግሊዝ ነጻነቷን ከመቀዳጀቷ ጥቂትቀደም ብሎ በፈረንጆቹ በ1948 ነበር። ሳን ሱ ቺ በአንድ ወቅት ለዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ትልቅ ተምሳሌት ተደርገው ነበር የሚታዩት። ምክንያቱምምሕረት አያውቁም ከሚባሉት የምያንማር ወታደራዊ ኃይሎች በተጻጻራሪ በመቆም በአገሪቱ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንበመታገል ረዥም ዓመታት ሳልፈዋል። ይህን ተከትሎም በ1991 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፍ ችለው ነበር። ሳን ሱ ቺ ሽልማቱን ያሸነፉት በቁም እስር ላይ ሳሉ ነበር። ሳን ሱ ቺ ለ15 ዓመታት በእስር ከቆዩ በኋላ በ2010 ነጻ ወጥተዋል። በ25 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገ ምርጫም ፓርቲያቸው ትልቅ ድል አግኝቶ ወደ ሥልጣን መምጣት ችሎነበር። ሆኖም የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሳን ሱ ቺ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ አልፈቀደም። ምክንያቱም የሳን ሱ ቺ ልጆችየውጭ ዜጎች ስለሆኑ ነበር። በዚህም የተነሳ መንግሥትን የሚመሩት ከጀርባ ሆነው ነው። ሳን ሱ ቺ አሁን 75 ዓመትሆኗቸዋል። የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆኑት ሳን ሱ ቺ በሚያናማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ለደረሰው ግፍና መከራ ቸልተኝነትበማሳየታቸው ከበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያገኟቸው ክብርና እውቅናዎችን ተነጥቀዋል። ሆኖም በአገሯ ውስጥ ሳን ሱ ቺ በቡድሃ ብዙኃን ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት አላት።", "“በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ የታቀዱ የሽብር ጥቃቶች ከሽፈዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ ሳምንት ብቻ በአዲስ አበባ ከስድስት በላይ የሽብር ጥቃቶች መክሸፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። በዛሬው ዕለትም አሶሳ ላይ የሽብር ጥቃት የመፈጸም እቅድ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄ አስመልክቶ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው የተናገሩት። የዛሬው ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሎን ረዘም ባለ መልኩ የፈጀው ከሰሞኑ በቄለም ወለጋ የደረሰውን ጭፍጨፋ ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰሞኑ በደረሱ የጅምላ ግድያዎች ላይ አተኩሯል። ከፓርላማ አባላትም ዘንድ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋ እልባት የሚያገኘው መቼ ይሆን? የመንግሥት መዋቅሮች ተሳትፎ አለበት? የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ችላ ብለውታልና ሌሎች ጥያቄዎች ቀርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግራቸውን የጀመሩት በግፍ ሕይወታቸውን ላጡ፣ ለተገደሉ ንጹሃን ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ነው። “ሕይወታቸውን ለመታደግ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ፣ እንደ መንግሥት ባለመቻላችን ጥልቅ ሐዘን ይሰማናል” ብለዋል። በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የደረሰው ጥቃት ኢላማ ያደረገው ከወሎ ወደ ወለጋ በ1977 ዓ.ም ረሃብ ወቅት ወደ ስፍራው የሄዱትን ሲሆን፣ እነዚህ ግለሰቦች ለአስርት ዓመታት የኖሩበትና ቀያቸው አገራቸው ነው ብለዋል። ሰሞኑን በሕዝብ ላይ ከተፈጸሙት ጥቃቶች ባሻገር “በአዲስ አበባ በዚህ ሳምንት የታቀዱ የሽብር ጥቃቶች ከሽፈዋል” ብለዋልጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ። “እነዚህን ሰዎች በግፍ መግደል የሚያሳካው የፖለቲካ አላማ የለም። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሹ ወገኖች የደቀኑት አላማ ማሳያ ነው” ብለዋል። በአዲስ አበባ ላይ በየቀኑ ሰፋፊ ጥቃቶች ታቅደው ቦምቦች፣ መሳሪያዎች፣ መሳሪያዎችና የሰለጠኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል። በኦሮሚያ ክልል የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከሦስት ቀን በኋላ ሃምሳ አምስት ሰዎች ወደ ከተማዋ ለመግባት ሲሞክሩ ለገጣፎ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስረድተዋል። በትናንትናው ዕለትም በቁጥጥር የዋሉ እንዳሉም አስረድተዋል። ከሰሞኑ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሱ የጅምላ ግድያዎች የመንግሥት ፀጥታ ተቋማት በቸልታ እየተመለከቱት ነው፤ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚለው አስተያየት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይስማሙም። “በርካታ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወታቸውን እየገበሩ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች መስዋዕትነት ከመክፈላቸው በተጨማሪ በዝቅተኛ ደመወዝና በፈታኝ ሁኔታ እየሰሩ ነው ብለዋል። “ዜጎቻቸውን ለመታደግና ሕዝባቸውን ስለሚወዱ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው” በማለትም አክለዋል። ለዚህም እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በደራሼ ላይ በነበረው ግጭት ፖሊስና የአካባቢው አስተዳሪዎች ከ80 በላይ ሞተዋል፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል፣ በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች በርካታ የፀጥታ ኃይሎች እንደተገደሉም ገልጸዋል። በዚህም በርካታ ዜጎችን መታደግም እንደተቻለ አበክረው ተናግረዋል። ሆኖም \"የንጹሃንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውም ስብስብ ሸኔም ይሁን የትኛውም አሸባሪ ኃይልን ለማጥፋት በጀመርነው ጥረት የምንቀጥል ከሆነ ይጠፋሉ።\" ሲሉ የመንግሥታቸውን አቋም አስረድተዋል። “አሸባሪዎች የራሳቸው ጭንቅላት የላቸውም ታስቦ ሥራ ሲሰጣቸው ጥቃት ይፈፅማሉ፣ ሕዝቡ አሸባሪውን ከለየ በኋላ ከመንግሥት ጎን ቆሞ ጥፋት እንዲቀንስ ማድረግ ይኖርባታል። የንጹሃንን ደም በከንቱ የሚያፈስ የትኛውም አሸባሪ ኃይል እስኪጠፋ የጀመርነው እርምጃ ይቀጥላል” ሲሉም አጠናክረዋል። ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል በደረሱ ጥቃቶችም የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች ተሳትፎ አለበት በሚል የተለያዩ አካላት ወቀሳዎችን ሲያቀርቡ ተሰምቷል። በዛሬውም ዕለት አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ይህንን ጉዳይ ያነሱ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ \"በመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የተገዙ ሰዎች አሉ\" ሲሉ “መዋቅር ውስጥ ችግር አለ” በማለት አምነዋል። ከዚህ ቀደም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ 5 ሺህ ያህል የተባረሩ፣ የታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሰው የማጥራት ሥራው እንደሚቀጥልም በዚህ ወቅት ተናግረዋል። በጅምላ ግድያዎቹ ላይ የተጠረጠሩ ሰዎች ምን ያህል ለፍርድ ይቀርባሉ በሚል በርካታ የፓርላማ አባላት የሽብር ህጉን አንቀፅ እየጠቀሱ ጥያቄ አቅርበዋል። በባለፉት ዓመታት በተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎች ላይ 11 ሺህ ክስ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። ከእነዚህም ውስጥ ከሙዚቀኛ ሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ በደረሱ ጥቃቶች በሺዎች ላይ ክስ ቀርቦ በብዙዎች ላይ መፈረዱንም አስረድተዋል። ከሰሞኑ የደረሱ ጥቃቶችን ያደረሰው መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ነው በማለት መንግሥትና ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በበኩሉ ጥቃቱ በመንግሥት ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው በማለት አስተባብሏል። \"ሸኔ የሚያደርሳቸውን ጥቃቶችን አላወገዙም የሚል ሃሜት ይቀርብብዎታል?\" ተብለው የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄው ተገቢ አይደለም ብለዋል። \"ሃሜት በምክር ቤት አባላት መቅረቡ ተገቢ አይደለም\" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሸኔን አሸባሪ ያለው ይህ ምክር ቤት ሳይሆን እኛ ነን፤ ቸል እንዳልነው አታስመስሉት” ሲሉም ወቅሰዋል። በቅርቡ አባቱን ያቃጠለ የሸኔ አባልን ጠቅሰው እንዲሁም ልጆቻቸውን ወደ ጦርነቱ የላኩ ቤተሰቦችን የገደሉ የሸኔ አባላት አሉ በማለት “እንደነዚህ አይነት አውሬዎች የኦሮሞ ተወካይ አይደሉም። ህፃናትንና ቤተሰብን የሚገድሉት አካላት የፖለቲካ አላማ የላቸውም፣ አገርም ማስተዳደር አይችሉም” ብለዋል። ጉዳዩን ከዘር (ብሔር) ጋር የምታይይዙ ሰዎች ሸኔ በኦሮሞነቱ ብቻ ሳይሆን “የኦሮሞ ጠላት ነው” ሲሉ ወቅሰዋል። ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ከተሰለፉት ውስጥ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ከደቡብና ከትግራይ የማረክናቸው አሉ በማለት “ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ጠላት ሁሉ ስብስብ ነው” ብለዋል። ወለጋ ላይ በመቶ የሚቆጠሩ የወረዳና የዞን አመራሮች መገደላቸውን በመጥቀስ እንዲሁም ወለጋ ላይ የሚሰሩ መሠረተ ልማቶች መቆማቸውን በማንሳት የኦሮሞ ሕዝብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ ነው ብለዋል። \"ብልጽግናን “እኛን” በብሔር መነጽር ማየቱ ትክክል አይደለም\" ሲሉ በወቀሳ መልኩ ተናግረዋል “በሰፈር የተደራጃችሁና ያልኖራችሁበትና በዘር ለማየት የምትፈልጉ ትክክል አይደለም። እኛ ከዘር በላይ ነን። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖርባት አገር ነው የምንፈልገው። እኛ ኢትዮጵያዊ ነን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ጨምረውም “ሳናቅ የምናበላሸው ነገር ካለ በእናንተ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብና በእናቶች ምክር እንታረማለን እንጂ ሆን ብለን አንዱን ብሔር የበላይ በማድረግ የማፋጀት ሥራ አንሰራም” ብለዋል። ሽብርተኝነት ዓለም አቀፉ ፈተና እንደሆነ ለምክር ቤቱ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለኢትዮጵያ ተለይቶ የሚያጋጥማት ፈተና አይደለም ብለዋል። በበርካታ አገራትም ቀዳሚና ዋነኛም አጀንዳም እንደሆነ ጠቅሰው፣ ጠንካራ የፀጥታ ኃይል፣ የላቀ ቴክኖሎጂና ሃብታም በሆኑ እንደ አሜሪካ ያሉ አገራትም ሽብርተኝነት እየፈተናቸው ነው ብለዋል። ሽብርተኝነት በዓለም ላይ ባሉ ሃገራት የሚከሰትና የኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች መግታት ያልቻሉት የሚል አንድምታ መሰጠት የለበትም ብለዋል። \"ሽብርን መገንዘብ ያስፈልጋል\" የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት በተሻለ መንገድ መረጃ ስላለው የተሻለ ሥራ መስራት እንደሚችል ሕዝቡ መገንዝብ ያስፈልጋል ብለዋል። የመከላከያና የፀጥታ ኃይል ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ከነበረው በላይ ቁመና ላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም የሆነው አገሪቷ የሽብር ጥቃት ስለተደቀነባት እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህንንም በመገንዘብ መከላከያን፣ ፖሊስን፣ የፌደራል ፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች ተጠናክረዋል ብለዋል። እነዚህ የፀጥታ ኃይሎች በሚጠናከሩበት ወቅት ከዘር፣ ከእምነት እና ከፖለቲካ አመለካከት ነፃ በሆነ መልኩና በጥቅም እንዳይገዛ ባደረገ ሁኔታ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል። “ትናንት ከነበረው በተሻለ ሁኔታና በማይወዳደር መልኩ በደህንነት ተቋማት ላይ ባተኮረ መልኩ ለወደፊቱ ትውልድ የሚሆንና ኢትዮጵያን በሚታደግ መልኩ ተገንብቷል” ብለዋል። በዚህም 95 በመቶ ተሳክቶለታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም መቶ በመቶ ማድረግ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል። \"በየትኛውም አገር የሽብር ጥቃቶችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም\" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያም ከዚያ ማዕቀፍ ውጭ ባትሆንም አገሪቱ መከላከል፣ መከታተል፣ መጠበቅ፣ መዘጋጀት በሚሉ አራት ዕቅዶችን ይዛ እየተንቀሳቀች ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ፈተና በሁለት ፈርጆች መታዬት አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ይህም ኢትዮጵያ ለዓለም ያላት አስተዋፅኦና ኢትዮጵያ ለማደግ ያላት አቅም ነው” ብለዋል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት የግራጫ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም ሲያብራሩ የመረጃ ጦርነት አንደኛው ነው ብለዋል። ጭፍጨፋዎች ወይንም ግድያዎችን አጀንዳ ያደረገና የኢትዮጵያን ልማት ባላየ መልኩ የመረጃ ጦርነት ይደረጋል የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም አገሪቱ የተከፈተባት መጠነ ሰፊ ጥቃት ነው ይላሉ። በተጨማሪም ዲፕሎማሲያዊ፣ የሳይበር ጥቃትና የተልዕኮ ውጊያም እንደተጋረጠባት አስረድተዋል። በተልዕኮ ውጊያ “እግር አልባ ባንዳዎች” ብለው የጠሯቸው ኃይላት የሕዝቡን ስሪት እያፈራረሱ ነው በማለት፣ በዚህም አማራና ኦሮሞን ማፋጀት፣ አማራን እርስ በርስ፣ ኦሮሚያን እርስ በርስ፣ ሶማሌና አፋርና፣ እንዲሁም ክርስቲያንና እስላምን ማፋጀት በዋነኝነት አጀንዳቸው ነው ይላሉ። \"ሰው አብሮ ከተዋለደው፣ ከኖረው ጎረቤቱ ጋር ጠላት መሆን አይቻልም። አማራና ኦሮሞ በጠላትነት ተሳስበው መቀጠል አይቻልም።\" በማለትም የማህበረሰቡን ስሪት አስረድተዋል “በዚህ ሁሉ መጠነ ሰፊ ጥቃት ኢትዮጵያን ማፍረስ አልተቻለም። ኢትዮጵያን ማጋደል፣ ማሸበር፣ በኢኮኖሚ ጫና ለማንበርከክ ቢሞከርም  ማፍረስም አይቻልም” ብለዋል። \"ሆኖም የኢትዮጵያ ጠላቶች አጥብቀው አይተኙም\" በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። “በየቀኑ እየተወጋን፣ መስዋዕትነት እየከፈልን፣ በማይታመኑ ነገሮች ውስጥ እያለፍን ቢሆንም እየጠነከርን ነው፤ ወደፊት እየተጓዝን ነው።” \"ከማበልጸግና አገር ከማሻገር አላማችን ንቅንቅ አንልም አስፈላጊ ከሆነም መስዋዕት እየከፈልን፣ በየቀኑ እየቀበርን፣ የሕፃናቱ ደም ቢጣራም በዚህ ፈተና ውስጥ እናሸንፋለን፤ ኢትዮጵያ ዳገት ላይ ናት” ሲሉ አስተዳደራቸው እያለፈበት ያለውን ሁኔታ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል። ሌላኛው ከምክር ቤት አባላት የቀረበው ጥያቄ ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ከህወሓት ጋር ድርድር ማድረግ ብቻውን ለምን ወሰነ? የሚል ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲመልሱ ገዥው ፓርቲና ሕዝቡ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሰላም ነው ብለዋል። የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ደኅንነትን በሰላም ለማስጠበቅ ካልተቻለ ብቻ ነው ወደ ጦርነት የሚገባው በማለት “ሰላምን እንዴት እንጠላለን” ሲሉም ጠይቀዋል። ሆኖም ለውይይቱ አጠቃላይ የመንግሥት ሠራተኞችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተወያዩም አስታውሰዋል። ህወሃት በፓርላማ አሸባሪ ተብሎ ከመፈረጁም ጋር ተያይዞ “ከአሸባሪ ጋር ድርድር አይካሄድም የሚለውን በጥልቀት ሊታይ ይገባል ብለዋል። በርካታ አገራት በጦርነት ወቅት ሆነው አሸባሪ ብለው ከፈረጇቸው አካላት ጋር ድርድር እንደሚያደርጉም የተለያዩ ሃገራትን ተሞክሮ ጠቅሰዋል። ሁልጊዜም ድርድር ይደረጋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደርግ ከህወሓትና ከሻዕቢያ ጋር ያደረገውን ድርድር በምሳሌነት ጠቅሰዋል። ሌላው በምክር ቤት አባላቱ የተነሳው ጥያቄ የሽግግር መንግሥት ምስረታ ያስፈልጋታል የሚሉ አካላትን አስመልክቶ ነው። የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ ለዓመታት ሲንከባለል የመጣ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን የሚጠይቁ ሥርዓት የማፍረስ አደጋ አልታያቸውም ብለዋል። “የሽግግር መንግሥት ሃሳብ የሚያነሱ ግለሰቦች ቀበሌ መርተው የማያቁና ስለተቋምም የማያቁ ናቸው” ሲሉ ተችተዋል። ገለልተኛ የሆነ የምርጫ ቦርድ ማቋቋምን ጨምሮ፣ በምርጫ እንዲወዳደሩ መድረክ ክፍት በማድረግ ምህዳሩ ሰፍቷል ብለዋል። \"ያለፈው ምርጫ በዲሞክራሲያዊነቱ እስካሁን ካለው የተሻለ መሆኑን ዓለም መስክሮከለታል\" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚህ ምርጫም ብልጽግና በከፍተኛ ድምፅ መንግሥት መመስረት ችሏል ብለዋል። “ሆኖም ከተሸነፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማምጣት አብረን እንስራ በሚል ብልጽግና ሥልጣን አጋርቷል” ሲሉ ተናግረዋል። እነዚህም ተግባሮች ተከናውነው ችግሮች ባለመፈታቱ እየተንከባለሉ ያሉ ጥያቄዎች በተገቢው መልኩ እንዲፈታ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መቋቋሙን በማንሳት “በሕዝብ ድምፅ የመጣ ኃይልን በጋጋታ ማፍረስ አይቻልም” በማለት አስረድተዋል።", "የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጀዋር የህክምና ቦታ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የሕክምና ቦታ ክርክር ላይ ብይን ለመስጠት በዛሬው ዕለት፣ የካቲት 12/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀጠሮ ሰጥቷል። ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እነ አቶ ጀዋር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ክርክር ተካሂዷል። ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቶ ጀዋርን ጨምሮ አምስት ሰዎች በመረጡት የላንድ ማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ ማዘዙን በመቃወም ማክሰኞ የካቲት 9/ 2013 ዓ.ም ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ በመደረጉ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስዶታል። በዛሬው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ እንዲገኙ ቢያዝም ማረሚያ ቤቱ ሳያቀርባቸው መቅረቱን ከተከሳሾቹ ጠበቆች መካከል አንዱ አቶ ሚልኪያስ ቡልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የማረሚያ ቤቱ ተወካዮችም እንዲሁ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሲሆን ተከሳሾችን እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ቢደርሳቸውም፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ በአካል በማቅረብ ፈንታ በማረሚያ ቤቱ እንዳሉ በቪዲዮ እንዲሳተፉ እንዲያደርጉ መታዘዛቸውን ጠበቃቸው ጨምረው አስረድተዋል። በመቀጠልም እነ አቶ ጀዋር በሌሉበት ጉዳዩ መታየት የለበትም በሚለው ላይ በጠበቆችና በዓቃቤ ሕግ መካከል ክርክር መካሄዱንም አቶ ሚልኪያስ ተናግረዋል። የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የግራ እና ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ እነ አቶ ጀዋር በሌሉበት ጉዳዩ እንዲታይ ማዘዙን ተናግረዋል። የሕክምና ጉዳይ ክርክር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ በላንድ ማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት መወሰኑ ትክክል እንዳልሆነ በመጥቀስ አቤቱታ አቅርቧል። \"የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የሕግ ክርክርን ያልተከተለ፣ የእኩልነትን መብትና ሕገ መንግሥቱን የተቃረነ፣ የፌደራል ማረሚያ ቤት የተመሰረተበትን አዋጅ የሚፃረር ነው\" በማለት አቃቤ ሕጉ መከራከሪያ ማቅረባቸውን አቶ ሚልኪያስ ይናገራሉ። ጠበቆች በበኩላቸው \"የታችኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ትክክል ነው። ጊዜው ያለፈበት ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም። ደንበኞቻችንም በግል ሀኪማቸው እና ራሳቸው በመረጡት የሕክምና ተቋም እንዲታከሙ ትዕዛዝ የተሰጠው በመስከረም 2013 ዓ.ም ነው ብለዋል። ስለዚህ ዓቃቤ ሕጉ በጊዜው አቤቱታ አላቀረበም በማለት የአቃቤ ሕጉ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ መከራከራቸውን ይናገራሉ። ጀዋርን ጨምሮ የሌሎች 24 ተከሳሾች ጠበቆች ከሆኑት መካከል አንዱ አቶ ሚልኪያስ ቡልቻ፤ ዓቃቤ ሕግም ሆነ ግለሰብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ አቤቱታ ካላቸው በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንዲችሉ ወይንም ደግሞ አቤቱታ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቅ እንዳለባቸው ሕግ እንደሚያዝ ይናገራሉ። ከዚህም ውጪ ደንበኞቻቸው በተለያየ የግል ሕክምና ተቋም ሲታከሙ እንደቆዩ የተናገሩት አቶ ሚልኪያስ፤ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 21 ቁጥር 2 በሕግ ጥላ ስር የዋሉ ሰዎች በግል ሐኪም የመታከም መብት እንዳላቸው እንደሚገልጽ በመጥቀስ መከራከራቸውን ይናገራሉ። የሁለቱንም ወገን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት ለየካቲት 16፣ 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤቱ በግል ሃኪም ቤት እንዲታከሙ የወሰነላቸው ሲሆን፤ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ የፀጥታና ደህንንነት በተመለከተ ያለውን ሁኔታ አቅርቦ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም የካቲት 2፣ 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲወሰዱ ወስኖ ነበር። በወቅቱ ማረሚያ ቤቱ ታሳሪዎቹ የረሃብ አድማ ላይ በመሆናቸው \"ታመው ከወደቁ ዝም ብለን ማየት ስለማንችል፣ ቀደም ብለው ስለማይነግሩንና በዛ አጭር ሰዓት ውስጥ እነሱ የፈለጉት ሆስፒታል ላይ ሃይል አሰባስበን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስለምንቸገር ድንገት ከወደቁ ግን ጦር ሃይሎች ሆስፒታል እንድናሳክም ይፈቀድልን\" ብለው በማመልከታቸው ለጊዜው ፍርድ ቤቱ ይኼንን ፈቅዶላቸው እንደነበር ከጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሃመድ ጅማ ያስረዳሉ። ጠበቆቻቸው በበኩላቸው ሆስፒታሉን ከስምንት ሰዓት በፊት እንደጠየቁና ደንበኞቻቸው በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲያስተላልፍና ከዚህ ቀደም የነበረውን ውሳኔ እንዲያፀና ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ሰኞ እለት የካቲት 8፣ 2013 ዓ.ም እነ አቶ በቀለ ገርባን የግል የጤና ተቋም በሆነውና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዲታከሙ ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ አቶ በቀለ ገርባ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ መንግሥታዊው የጤና ማዕከል ጦር ሃይሎች ሆስፒታል መወሰዳቸውን ሃኪማቸውና ጠበቃቸው ተናግረዋል። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመተላለፍ አቶ በቀለ ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በኃይል መወሰዳቸው \"ከህግ አግባብ ውጭ ነው\" ሲሉ ከአቶ በቀለ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሃመድ ጅማ ለቢቢሲ አስረድተዋል። እነ አቶ በቀለ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነ ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። ከጥር 19፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ውሃ ምንም የማይቀምሱትና የረሃብ አድማ ላይ ናቸው የተባሉት እነ አቶ በቀለ ገርባ የጤና ሁኔታም አሳሳቢ ነው ተብሏል። እነ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል።", "የኬንያ ፖለቲከኞች ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል ያደረጉት ጥረት በፍርድ ቤት ታገደ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በገዢው መንግሥት ድጋፍ ያገኘውን የሕገ-መንግሥት ማሻሻል ሐሳብ ውድቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ የወሰነው ውሳኔ በፈረንጆቹ 2017 ኡሁሩ ኬንያታ ምርጫውን አላሸነፉም ብሎ ፍርድ ቤት ከሰጠው ፍርድ በኋላ ትልቁ ነው ተብሏል። ዳኛው በተለምዶ ቢቢአይ እየተባለ የሚጠራው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ዕቅድ ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም ሲሉ ብይናቸው ሰጥተዋል። ዳኛው አክለው ማሻሻያው ሕገ ወጥና ቅርፅ አልባ ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ዋነኛ ተቀናቃኛቸው የነበሩት የአሁኑ ጓደቸው ራይላ ኦዲንጋ ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያው እውን እንዲሆን ደፋ ቀና ሲሉ ነበር የከረሙት። ሁለቱ መሪዎች ማሻሻያው ሕግ አውጪው የመንግሥት ክንፍ እንዲስፋፋና የሃገሪቱ ፖለቲካ የበለጠ አሳታፊ እንዲሆን ያስችላል ሲሉ ይሞግታሉ። ነገር ግን ተቺዎች ማሻሻያው የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስ በርስ ለመጠቃቀም ያመቻመቹት ነው ሲሉ ይከራከራሉ። ነቃፊዎቹ አክለው ማሻሻያው የሕዝብ እንደራሴዎች ቁጥርን ከፍ ያደርገዋል፤ ይህ ደግሞ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃ ለምትገኘው ኬንያ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው ይላሉ። ቢቢአይ በተሰኘ ቅፅል ስሙ የሚታወቀው የማሻሻያ ሐሳብ ወደ ብሔራዊው ሸንጎና ሴኔት ተልኮ በአብላጫ ድምፅ አልፎ ነበር። ነገር ግን ወደ ፕሬዝደንቱ ጠረጴዛ ተልኮ የመጨረሻው ፊርማ ከማረፉ በፊት ነው ሐሙስ ዕለት በፍርድ ቤት የታገደው። ማሻሻያው ፀደቀ ማለት ኬንያዊያን በሚቀጥለው ዓመት ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለሕዝበ ውሳኔ ድምፃቸውን ይሰጣሉ ማለት ነው። ዳኞች ምን አሉ? ለአራት ሰዓታት በቴሌቪዥን መስኮት ቀጥታ በተላለፈው ችሎት ዳኞቹ ፕሬዝደንት ኬንያታ የሃገሪቱን ሕገ-መንግሥት ጥሰዋል ብለዋል። አክለው ኡሁሩ የመሠረቱት የቢቢአይ ኮሚቴ ሕገ-ወጥ ነው፤ ፕሬዝደንቱ የተሰጣቸውን የመሪነት ሚና በአግባቡ አልተወጡም ብለዋል። ዳኞቹ፤ ፕሬዝደንቱን በግላቸው ሊከሷቸው እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። ፖለቲከኞቹ ማሻሻያውን ለማፅደቅ በሚል የሰበሰቡት 5 ሚሊዮን ድምፅ ይህንን ሐሳብ የዜጎች አያደርገውምም ብለዋል ዳኞቹ። የፍርደ ቤቱ ውሳኔ ፕሬዝደንቱን ከሥልጣናቸው ሊያስነሳቸው የሚችል ቢሆንም ነገር ግን የማሻሻያውን ሐሳብ በአብለጫ ድምፅ ያሳለፈው ፓርላማ ይሄን ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም። ቢቢአይ፤ ኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲኖራት፤ ቢያንስ 70 አውራጃዎችና 300 ተጨማሪ የፓርላማ መቀመጫዎች እንዲጨመሩ ሐሳብ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱ የማሻሻያ ሐሳቡን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ መንግሥት ይግባኝ ይጠይቃል ተብሎ ቢጠበቅም ሕግ አዋቂዎች ግን ውጤቱ ከዚህ የተሻለ ይሆናል ብለው አያምኑም።", "ሱዳናውያን ተቃዋሚዎች ከግብፅ ጋር የሚያገናኘውን አውራ ጎዳና ከዘጉ ከሳምንት በላይ ሆነ በሰሜናዊ ሱዳን ያሉ ተቃዋሚዎች ሱዳንን ከግብፅ ጋር የሚያገናኘውን አውራ ጎዳናን ከዘጉ ከሳምንት በላይ እንደሆናቸው ተዘገበ። ሱዳናውያኑ ተቃዋሚዎች ሁለቱን አገራት የሚያገናኘውን መንገድ በርካታ ቦታዎች ላይ በመዝጋታቸው ምክንያት ከሱዳን የቁም ከብቶችንና ሌሎች ሸቀጦችን የጫኑ የግብጽ የጭነት መኪኖች ድንበሩን ተሻግረው መሄድ አልቻሉም። አብዛኞቹ አርሶ አደር የሆኑት ተቃዋሚ ሰልፈኞች በመጀመሪያ ላይ አውራ ጎዳናውን የዘጉት መንግሥት የኤሌክትሪክ ዋጋ ላይ ጭማሪ ካደረገ በኋላ ውሳኔውን ለማስቀየር ነበር። ነገር ግን ተቃውሞው ቀስ በቀስ እየሰፋ በመሄድ በሱዳን ጦር ሠራዊቱ ያካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ወደ መቃወምና የጦር ኃይሉን በሚደግፉ የአካባቢው የፖለቲካ ኃይሎች እና ግብፅ ላይ አነጣጥሮ ለቀናት ዘልቋል። ተቃዋሚዎቹ ሱዳንን ከሰሜናዊ ጎረቤቷ ግብፅ ጋር የሚያገናኛትን ዋነኛ መንገድ ከዘጉት አሁን ዘጠነኛ ቀኑ እንደሆነ ተዘግቧል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት ከካርቱም ተነስቶ አስከ ድንበር ከተማዋ ኢርጊን ድረስ ባለው የበረሃ መንገድ ላይ ማለፍ ያልቻሉ የግብፃውያን ከባድ ተሽከርካሪዎች ቆመዋል። በተመሳሳይ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወደ ግብፅ በሚያመሩት ተሽከርካሪዎች ላይ ተቃውሞዎች እየተሰሙ ሲሆን መኪኖቹ ከሱዳን እንዳይወጡ እየቀሰቀሱ የሚገኙ ሰዎችም በርካታ ናቸው። በሰሜናዊው የሱዳን ክፍል ያሉ የዴሞክረሲ ለውጥ አቀንቃኞች ወደ ግብፅ የሚላኩት የቁም ከብቶችና ሌሎች የግብርና ምርቶች በሥልጣን ላይ ያለውን ወታደራዊ ኃይልና የሚያንቀሳቅሳቸውን ተቋማት የሚጠቅሙ በመሆናቸው ከአገር መውጣታቸውን አጥብቀው ይቃወማሉ። ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ወደ ከፋ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ የገባችው ሱዳን፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሥልጣን ላይ ያሉትን የጦር ኃይሉን መሪዎች የሚቃወሙ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን እያስተናገደች ነው። በዋና ከተማ ካርቱምም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን ለሲቪሎች እንዲያስረክቡ የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች መካሄድ ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል። በዚህም ሳቢያ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው የዶክተሮች ቡድን አስታውቋል።", "የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ \"ተገፍቶ መውጣቱን\" ገለፀ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከሦስት ወራት በኋላ ይካሄዳል ከተባለው ምርጫ ከፍላጎቱ ውጪ በደረሱበት ጫናዎች ለመውጣት መገደዱን አስታወቀ። የፓርቲው ፀሐፊ የሆኑት አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ \"ተገፍቶ ለመውጣት ተገድዷል\" ብለዋል። ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያወጣቸው በነበሩ መግለጫዎች የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ፣ በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች የተዘጉ ቢሮዎቻቸው እንዲከፈቱ፣ እንዲሁም ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አገራዊ ምክክር እንዲደረግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። ኦፌኮ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱ አገራዊ ምርጫዎች ላይ ተሳታፊ የነበረ ሲሆን ከምርጫ ውድድር እራሱን ሲያገል ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። አቶ ጥሩነህ ገምታ ባለፈው ሳምንት ከምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ጋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የዕጩ ምዝገባን በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ መሳተፋቸውን አስታውሰው፤ ኦፌኮ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ዕጩ እያስመዘገበ እንዳልሆነ እና ማስመዝገብም እንደማይችል፣ ስለዚህም ምርጫው ላይ መሳተፍ እንደማይችል ለምርጫ ቦርድ አስታውቋል ብለዋል። በተጨማሪም የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ እና ምርጫው ላይ አገራዊ መግባባት አለመኖር ምርጫው ፍትሃዊ እና ተዓማኒነት እንዲኖረው እንደማያደርግ በስበሰባው ላይ መናገራቸው አስታወሰዋል። ሆኖም ግን ፓርቲያቸው ላነሳው ሃሳብም ሆነ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምንም ምላሽ አለማግኘታቸውን አቶ ጥሩነህ ተናግረዋል። በመሆኑም እነዚህ ጥያቄዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ፓርቲው በምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደማይችል አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስካሁን ድረስ ቢሮዎቻቸው በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ተዘግተው እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ጥሩነህ፣ ከዋናው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምርጫውን እንዲያስፈጽሙ ከተመደቡ አምስት ሰዎች አራቱ እስር ቤት መሆናቸውን ተናግረዋል። ስለዚህም \"አፌን ሞልቼ መናገር የምችለው ከዚህ ምርጫ የወጣነው ተገፍተን እንደሆነ ሕዝባችንም ሆነ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሊያውቅልን እንደሚገባ ነው።\" እስር ቤት ካሉ የኢፌኮ አመራሮች መካከል የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ እንዲሁም ባለፈው ዓመት ፓርቲውን የተቀላቀሉት አቶ ጃዋር መሐመድን እና ሐምዛ አዳነ (ቦረና) ይገኙበታል። \"አንድ ፓርቲ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ቢያንስ ነጻ ሆኖ መንቀሳቀስ መቻል አለበት። እኛ ግን አሁንም አባላቶቻችን፣ በወረዳና በዞን ደረጃ ያሉ አመራሮች፣ እጩ ተወዳዳሪ እና ታዛቢ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች እስር ቤት ነው ያሉት። ስለዚህ እንሳተፍ እንኳ ብንል መሳተፍ አንችልም፤ ከምርጫው የመውጣት ውሳኔ ላይ የደረሰነው ተገደን ነው\" ብለዋል። እነዚህ የምናነሳቸው ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ስንጠይቅ የቆየን ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ግን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካልተመለሱ ምርጫው ላይ ላለመሳተፍ ወስኗል ብለዋል። ከኦፌኮ በተጨማሪ በኦሮሚያ ካሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮቹ መታሰር እና የቢሮዎች መዘጋትን በማንሳት ምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር ከዚህ በፊት ለቢቢሲ መናገሩ ይታወሳል። በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ ኦፌኮ እስከ ትናነትናው ዕለት ድረስ ምንም ዓይነት ዕጩ እንዳላስመዘገበ ለቢቢሲ አረጋግጧል። አቶ ጥሩነህም የዕጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቅ መሆኑን ጠቅሰው ያነሷቸው ጥያቄዎች፤ የፓርቲ አመራሮቻቸው መፈታትን ጨምሮ ምላሸ የሚያገኙ ከሆነ እና የዕጩ ምዝገባ ጊዜ የሚራዘም ከሆነ ድርጅቱ አሁንም በምርጫው ውስጥ ለመቆየት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። አቶ ጥሩነህ ከዚህ ቀደም የኦነግም ሆነ የኦፌኮ አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ እንደተወያዩ ተናግረው ከዚህ ውይይት በኋላ ግን ምንም ዓይነት ለውጥ አለማየታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከምርጫ ቦርድም ሆነ ከመንግሥት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም። በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱና ዋነኛ ከሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ ዮነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፤ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ በነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) እና በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሚመራው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦሕኮ) መካከል በሐምሌ 2004 ዓ.ም በተደረገ ውህደት የተመሰረተ ድርጅት ነው።", "የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢው ፕ/ር መስፍን አርአያ ማን ናቸው? ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቀረቡ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮችን ሲያጸድቅ፣ ፕ/ር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል። ከአስራ አንዱ ኮሚሽነሮች መካከል በሰብሳቢነት ፕ/ር መስፍን ሲሾሙ፣ ወይዘሮ ሒሩት ገብረሥላሴ ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዋል። ለመሆኑ ፕ/ር መስፍን አርአያ ማናቸው? እስካሁንስ በሙያቸው ምን አበርክተዋል? ፕ/ር መስፍን ከሩሲያ ትምህርት ቤት እስከ ኢትዮጵያ ሆስፒታሎች የተወለዱት በአዲስ አበባ ከተማ ነሐሴ 1946 ዓ. ም. ነው። በ1972 ዓ. ም. ከሩሲያው ቅዱስ ፒተርስበርግ የሕክምና ትምህርት ቤት በሕክምና የዶክትሬት ዲግሪ (MD) አግኝተዋል። ከዚያም በ1982 ዓ. ም. ኔዘርላንድስ ከሚገኘው ግሮኒንገን ዩኒቨርሲቲ በአእምሮ ሕክምና ስፔሻሊቲ ዲፕሎማ (DPM) ተቀብለዋል፡፡ በተጨማሪም በ2000 ዓ. ም. ስዊድን ከሚገኘው ኡሜዮ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ኦፍ ፊሎሶፊ ዲግሪ (PhD) አግኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች እንዲሁም የሕክምና ተቋሞች ለዓመታት አገልግለዋል። ከእነዚህም መካከል ከ1974-75 ዓ. ም. በትግራይ፣ አዲግራት ከተማ በራስ ስብሐት ሆስፒታል በጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተርነት እንዲሁም ደሴ በሚገኘው ደሴ ሆስፒታል ከ1975-76 ዓ. ም. በጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተርነት ማገልገላቸው ይጠቀሳል። ከ1976-79 ዓ. ም. በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ በጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተርነት ሠርተዋል። ከ1982 እስከ 1987 ዓ. ም. ደግሞ በዚያው ሆስፒታል በአእምሮ ሐኪምነት አገልግለዋል። ፕ/ር መስፍን፣ ከ1987 አንስቶ ለዓመታት በዘውዲቱና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች በአእምሮ ሐኪምና መምህርነት ሠርተዋል። ከ1997 ዓ. ም. ጀምሮ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም መምህር ሆነው አገልግለዋል። ከ2001-2003 ዓ. ም. የቅዱስ ጳውሎስ የሕክምና ትምህርት ቤት ዲን እንዲሁም ከ2003-2006 ዓ. ም. የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ከፍተኛ የትምህርት አመራር ሆነዋል። የፕ/ር መስፍን ተሳትፎና አበርክቶ ፕ/ር መስፍን በተለይም በጤናው ዘርፍ በርካታ ማኅበራትን በመመሥረት፣ በአባልነት በማገልገልና እና በመምራትም ይታወቃሉ። ለአብነት የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባባቅ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ የአእምሮ ሕክምና ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይጠቀሳሉ። የብሔራዊ ኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት አደራጅ ግብረ ኃይል አባል፣ የብሔራዊ ኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት መሥራችና አባል በተጨማሪም የተስፋ ጎሕ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ወገኖች ማኅበር የአማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሠርተዋል። ፕ/ር መስፍን የብሔራዊ ይቅርታ ቦርድ አባል፣ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ጆርናል ዋና አዘጋጅ፣ የመድኃኒትና ሕክምና አቅራቢ ድርጅት (ፋርሚድ) የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአእምሮ ጤና ክብካቤ ማኅበር በኢትዮጵያ የቦርድ አባልም ናቸው። በተጨማሪም የፌዴራል ሆስፒታሎች አመራር ቦርድ አባል፣ የአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራር ቦርድ አባል እንዲሁም የመድኃኒትና ምግብ ቁጥጥርና አስተዳደር የአማካሪ ቦርድ አባል ሆነው ሠርተዋል። ወደ 30 በሚጠጉ ታዋቂ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የሕክምና መጽሔቶች ጽሑፎቻቸውን አሳትመዋል። ፕ/ር መስፍን ያገኟቸው ሽልማቶች ፕ/ር መስፍን ከአገራዊው የበጎ ሰው ሽልማት አንስቶ በአገር ውስጥና በውጭ አገራትም የተለያዩ የዕውቅና ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል። የበጎ ሰው ሽልማት መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ነበር የሸለማቸው። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላከናወኗቸው የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ከአሜሪካው ቴዎዶርና ቫዳ ስታንሊ ፋውንዴሽን ሽልማት አግኝተዋል። ፒፕል ቱ ፒፐል፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር፣ ተስፋ ጎህ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ወገኖች ማኅበር፣ ፋርሚድ እና ራድዮ ፋናም ለአበርክቷቸው እውቅና ሰጥተዋል። በተጨማሪም በ1998 ዓ.ም. የአእምሮ ጤናን ለማሻሻል ባበረከቱት አስተዋጽኦ የሮበርት ጊል የወርቅ ሜዳሊያን አግኝተዋል። የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር በ2003 ዓ. ም. ለተምሳሌታዊ የሕክምና አገልግሎት የወርቅ ሜዳሊያ ሰጥቷቸዋል። በ2006 ዓ. ም. የጤና ሚኒስቴር ለረዥም ጊዜ ተምሳሌታዊ የጤና አገልግሎት የወርቅ ሜዳሊያ አበርክቶላቸዋል። በተጨማሪም የምግብና መድኃኒት ቁጥጥርና አስተዳደር ለዓመታት የጤናው ዘርፍ አገልግሎታቸው በ2006 ዓ. ም. የወርቅ ዋንጫ ሰጥቷቸዋል። የበጎ ሰው ሽልማት መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ነበር የሸለማቸው።", "ኢትዮጵያ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያግዝ የምክክር ኮሚሸን ልታቋቁም ነው የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሸን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ረቂቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። ሚኒስትሮች ምክር ቤት አርብ ታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ብልጽግና ፓርቲ ምርጫ አሸንፎ መንግሥት ሲመሰርት ለማከናወን ከወሰናቸው ተግባራት መካከል ኮሚሽኑን ማቋቋም እንደሚገኝበት ገልጿል። በዚህም \"ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል\" ይላል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ። መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያየ ጎራ የተሰለፉ ፖለቲከኞች እና ሕዝቡ ተቀራራቢ እና አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ተቀባይነት ያለው ተቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ መሠረትም የሚንስትሮች ምክር ቤት 'የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን' ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቦ ተቀባይነት በማግኘቱ ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ ተፈጻሚነት ይኖረዋል። ሐሙስ ዕለት ኅዳር 30/2014 ዓ.ም. የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውይይት ባደረገበት ወቅት በኢትዮጵያ የፖለቲካ የሽግግር ሂደት ተወያይቶ እንደነበረ የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። አደም ፋራህ ፓርቲው በውይይቱ አስፈላጊ ነው ያለው አገራዊው ምክክር ስኬታማ እንዲሆነ ገለልተኛ እና ብቃት ባለው ተቋም መመራት እንዳለበት ሥራ አስፈጻሚው አምኖበታል ስለማለታቸው ፋና ዘግቧል።", "በኢትዮጵያ፣ በዩክሬን እና በሌሎችም አገራት የቱርክ ድሮኖች የጦርነት ቅርጽን እንዴት ቀየሩ? በመላው ዓለም ያሉ ወታደራዊ ግጭቶች በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) አማካይነት አካሄዳቸውን እየለወጡ ነው። ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት አንስቶ የተለያዩ አገራት ግጭቶች በሰው አልባ አውሮፕላን ምክንያት የኃይል ሚዛን ለውጥ ታይቶባቸዋል። ከሰሞኑ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተከሰተው ውጥረትም የድሮን ሚና ቀላል አይደለም። ከእነዚህ ሁለት አገራት በስተ ደቡብ የምትገኘው ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላን ምርት ስሟ በተደጋጋሚ ይነሳል። ዩክሬን ራሷን ከሩስያ የምትከላከለው በቱርክ ሠራሽ ድሮኖች ሊሆን ይችላል። በእርግጥ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ከሞላ ጎደል የቱርክ ድሮኖችን ማግኘት እየተለመደ መጥቷል። ቱርክ በድሮን ምርት ምን ያህል ገናና ናት? ቱርክ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) አባል ናት። በምዕራባውያኑ ወታደራዊ ስብስብ ኔቶ ውስጥ ያለች ብቸኛው ሙስሊም አገር ናት ቱርክ። በቱርክ የሚኖሩት ገለልተኛ ወታደራዊ ተንታኝ አርዳ ሜቭሉቶግሉ \"የአንካራው መንግሥት ላለፉት 20 ዓመታት አስተማማኝ የድሮን ኃይል አዘጋጅቷል\" ይላሉ። ቱርክ ሰው አልባ አውሮፕላኖቿን የአገር ውስጥ ደኅንነት ለማስጠበቅና ከድንበሯ በዘለለም ጥቅም ላይ እንዳዋለችው ይናገራሉ። እአአ ከ1990ዎቹ አጋማሽ ወዲህ የኩርድ ተገንጣይ ታጣቂዎች ላይ የደረሰው ጥቃት በዋነኛነት ይጠቀሳል። የቱርክ መከላከያ አቅም ግንባታ ዋነኛ ትኩረት የሚሰጠው ለድሮን እንደሆነ ተንታኙ ያስረዳሉ። \"በምርት ጥራትና ብዛት ድሮን ቅድሚያ ይሰጠዋል። ቱርክ በቀጠናው በአስተማማኝ አቋም በመገንባት ከእስራኤል ውጭ የሚበልጣት\" ይላሉ ቱርክ ውስጥ ሰው አልባ በራሪ መሣሪያዎች ወይም በእንግሊዘኛው unmanned aerial vehicles (UAVs) የሚያመርቱ ሁለት ግዙፍ ፋብሪካዎች አሉ። ባይካር መከላከያ የተባለው ፋብሪካ ባይራክታር ቲቢ2 (Bayraktar TB2) እና ባይራክታር አኪንቺ (Bayraktar Akinci) ድሮኖች ያመርታል። የፋብሪካው ዋና የቴክኒክ ኃላፊ ሴልሁክ ባይራክታር የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ልጅ ባል ነው። ሌላው ግዙፍ ድሮን አምራች ተርኪሽ ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ ሲሆን፤ ታይ አንካ (TAI Anka) እና ታይ አኩሱንገር (TAI Aksungur) የተባሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ያመርታል። የወታደራዊ ጉዳዮች ተንታኙ አርዳ ሜቭሉቶግሉ እንደሚሉት፤ የቱርክ መከላከያ እና ደኅንነት ተቋሞች ከእነዚህ ድሮኖች 150 የሚሆኑትን ያበራሉ። ይህም ከአነስተኛ የስለላ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ካሚካዚ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተጨማሪ ነው። ቱርክ እና ዩክሬንን ምን አገናኛቸው? እአአ በ2019 ቱርክ ለዩክሬን ብዙ ባይራክታር ቲቢ2 ድሮኖች ሸጣላታለች። ዩክሬን ከቱርክ ጎን ኔቶን መቀላቀል ትፈልጋለች። ዩክሬን ሩሲያ ከምትደግፋቸውና በምሥራቃዊ ክፍል ከሚንቀሳቀሱ አማጺያን ጋር ትግል ገጥማለች። ከሩሲያ ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትም ያሰጋታል። ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ወታደሮቿን በተጠንቀቅ አሰልፋ ትገኛለች። ያለፈው የካቲት ኤርዶዋን ወደ ዩክሬን አቅንተው በሁለቱ አገራት መካከል ተጨማሪ የድሮን ግብይት የሚፈቅድ ስምምነት ፈርመዋል። የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስተር ስምምነቱ የቱርክ ድሮን አምራቾች ዩክሬን ውስጥ እንዲሠሩ መንገድ የሚከፍት እንደሆነ ለሮይተርስ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ያሳለፍነው ጥቅምት ዩክሬን የቱርክን ድሮን ተጠቅማ ሩሲያ የምትደግፋቸው ተገንጣዮች ይገለገሉበት የነበረ ዲ30 የአየር መሣሪያን ማውደሟን አስታውቋለች። ሩሲያ ይህንን ተከትሎ ቱርክ የምትሸጣቸው ድሮኖች ቀጠናውን \"ሰላም እየነሱ\" እንደሆነ ኮንናለች። በሌላ በኩል ደግሞ ቱርክ ሩሲያ እና ዩክሬንን ላሸማግላችሁ ብላለች። ሽምግልናው ከድሮን ሽያጭ ጋር መጋጨቱ ግን አይቀርም። የሶርያ ጦርነት ከተነሳ ወዲህ የቱርክ እና የሩሲያ ግንኙነት ውጥረት የነገሠበት ነው። ሁለቱ አገሮች ሶርያ ውስጥ የተለያየ ፍላጎት ቢኖራቸውም ለመስማማትም ፍላጎት አሳይተዋል። ቱርክ ኤስ400 (S-400) የተባለ የአየር መከላከያ ከሩሲያ መግዛቷ የወዳጅነት መጀመሪያ ተደርጎ ተወስዷል። የመሣሪያ ግዢውን ኔቶ እና አሜሪካ ተችተውታል። ዩክሬን ስንት ባይራክታር ቲቢ2 እንዳላት በውል አይታወቅም። ነገር ግን ድሮኖቹ በዶንባስ ቀጠና ያሉትን አማጽያን ለመዋጋት እንደሚረዳት ይታመናል። እነዚህ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ዘመነኛ ካሜራ፣ ከተቆጣጣሪ ሥርዓት ጋር የሚያስተሳስር መሣሪያ እንዲሁም ኢላማ አስተካካይ ቁልፍ ተገጥሞላቸዋል። ይህም ኢላማን አስተካክሎ ፈንጂ ለመጣል ያስችላቸዋል። ወታደራዊ ተንታኙ አርዳ ሜቭሉቶግሉ እንደሚሉት፤ እነዚህ ድሮኖች ተንቀሳቃሽ ቡድንን ኢላማ ለማድረግ ይመረጣሉ። \"ሆኖም የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል በብዛትም በቴክኖሎጂ ረቂቅነትም ከዩክሬን ይልቃል\" ይላሉ። የቱርክን ድሮኖች የሚጠቀሙት የትኞቹ አገራት ናቸው? ቱርክ ሠራሽ ድሮኖች የሚገዙ አገራት ቁጥር እየናረ መጥቷል። የአገሪቱ የኤክስፖርት ዝርዝር ምን ያህል ድሮን እንደሚሸጥ አይጠቁምም። ነገር ግን ከ15 አገራት በላይ ቱርክ ሠራሾቹን ባይራክታር እና ታይ ድሮኖች እንዳዘዙ ይታወቃል። ባይራክታር ቲቢ2 ድሮኖች በሶሪያ፣ ሊቢያ እና በናጎርኖ-ካራባግህ (በአርሜኒያ እና በአዘርባጃን መካከል ለ44 ቀናት ውጊያ የተካሄደበት) ጦርነቶች ውጤታማ ከሆኑ በኋላ ፈላጊያቸው ተበራክቷል። በዚህ ጦርነት የአዚሪ ኃይሎች የአርሜኒያን ወታደሮች፣ የውጊያ ተሽከርካሪዎች እና የአየር ኃይል የመቱት በቱርክ ሠራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ነው። ይህም አወዛጋቢው ግዛት በእጃቸው እንዲገባ አግዟቸዋል። አምና የፖላንድ መከላከያ ሚኒስትር ከቱርክ 24 ተዋጊ ድሮኖች እንደሚገዙ አስታውቀዋል። ግዢው ፖላንድን ከኔቶ አባል አገራት የመጀመሪያዋ ያደርጋታል። ለቱርክ አፍሪካም ትልቅ ገበያዋ ናት። በቱርክ የሚኖሩት ገለልተኛ ወታደራዊ ተንታኝ አርዳ ሜቭሉቶግሉ \"በአፍሪካ ገበያ የቻይና አምራቾች ዋነኛ ተቀናቃኝ ቱርክ ነች። የቱርክ ርካሽ ድሮኖች የኔቶን የጥራት ልኬት የጠበቁም ናቸው\" ይላሉ። የቱርክን ድሮኖች ከገዙ መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ሩዋንዳ እና ናይጄርያም ይጠቀሳሉ። ቱርክ እና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ሆኖም ስለ ድሮን ግብይት በግልጽ ይፋ አልተደረገም። አምና የቱርክ ኤክስፖርት ሪፖርት የበረራ ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እንዳሳየ ይጠቁማል። ያሳለፍነው ጥቅምት ላይ አሜሪካ፤ ቱርክ ለኢትዮጵያ ድሮን እየሸጠች መሆኑ እንዳሳሰባት ተናግራለች። ወጣም ወረደ ቱርክ ለምታመርታቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖች አዲስ ገበያ ከማፈላለግ የምትቦዝን አይመስልም። ወታደራዊ ጉዳዮች ተንታኙ \"የድሮን ሽያጭ ዘላቂነት ያለው ወታደራዊ የንግድ ትስስር እንዲፈጠር ያስችላሉ። ይህም ቱርክ ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጫና እንድትፈጥር ያግዛታል\" ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ያለውን የገበያ ፍላጎት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጠንቅቀው ተገንዝበዋል። ጥቅምት ላይ \"አፍሪካ ውስጥ የትም አገር ስሄድ የምጠየቀው ስለ ሰው አልባ አውሮፕላን ነው\" ብለው መናገራቸው ይታወሳል።", "ትግራይ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በትግራይ ረሃብ አሉ የሚሉ ሪፖርቶችን አስተባበሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ ክልል ውስጥ ረሃብ አለ የሚሉ ሪፖርቶችን አስተባበሉ። አገሪቱ ብሔራዊ ምርጫዋን ባደረገችበት በትናንትናው ዕለት በምርጫ ጣቢያ ላይ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ችግር መኖሩን አምነው ይህ ግን መንግሥት የሚፈታው ነው ብለዋል። ስምንተኛ ወሩን ያስቆጠረው የትግራይ ጦርነት አምስት ሚሊዮን የክልሉን ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ ፈላጊ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያስረዳል። ከ350 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች ደግሞ በረሃብ ቋፍ ላይ መሆናቸውን በቅርቡ የወጣ ተባበሩት መንግሥታት ግምገማ ሪፖርት ያሳያል። \"በትግራይ ረሃብ የለም\" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድምፃቸውን በትውልድ ስፍራቸው ከሰጡ በኋላ ለቢቢሲዋ ካትሪን ባያሩሃንጋ ተናግረዋል። \"ችግር አለ ነገር ግን መንግሥት ይህንንም መቅረፍ ይችላል\" በማለት አክለዋል። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በፀጥታው ምክር ቤት ዝግ ስብሰባ ላይ በትግራይ ረሃብ አለ ብለው ነበር። ኃላፊው በትግራይ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጎን ተሰልፎ እየተዋጋ ያለው የኤርትራ ሠራዊት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅሞበታል ብለዋል። ኤርትራ ይሄንን ውንጀላ አትቀበለውም። በዚሁ ወቅትም ስለ ኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መቼ እንደሚወጡ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ የኤርትራ ወታደሮችን ገፍታ እንደማታስወጣና ሁኔታውንም በሰላም ለማጠናቀቅ ከኤርትራ ጋር እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ከአስር ቀናት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ የወጣ ኢንተግሬትድ ፉድ ሴኩሪቲ ፌዝ ክላሲፊኬሽን የተባለ ግምገማ መሰረት 350 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች \"ካታስትሮፍ\" በሚባል ሁኔታ በረሃብ ቋፍ ላይ እንደሚገኙ አትቷል። በወቅቱም የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ረሃብ የለም እንዲሁም እርዳታ እየተዳረሰ ነው ብለዋል። ይሄው ግምገማ ተጨማሪ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች በቀውስ ላይ ወይም አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በበኩላቸው ምግብ እያዳረሱ እንደሆነና የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች እንዳይገቡ ከልክለዋል የሚለውንም ሪፖርቶች ተቀባይነት የለውም ብለዋል። \"ምንም የምንበላውነገር የለም\" በምዕራብ ትግራይ ቃፍታ ሁመራ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለቢቢሲ በቅርቡ እንደተናገሩት መራባቸውን ነው። \"ምንም የምንበላው ነገር የለንም\" በማለት አንድ ግለሰብ በስልክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይኸው ግለሰብ ለወራት በዘለቀው ጦርነት እህላቸው እንዲሁም ከብቶቻቸው እንደተዘረፈ ነው። ጥቅምት 24 የተጀመረው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉን ነዋሪዎች አፈናቅሏል፤ የእርሻ ተግባሩንም አስተጓጉሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረውን ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ ወታደራዊ ዘመቻ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሚያደርጓቸው የፖለቲካ ማሻሻያዎች ጋር ተያይዞ ከህወሓት ጋር ያለው ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የሻከረ ሲሆን ግጭቱንም ያቀጣጠለው የህወሓት የፌደራል መከላከያ ዕዝን መቆጣጠሩን ተከትሎ ነው። \"የሱዳን ወታደሮችም በኢትዮጵያ አሉ\" በዚሀ ጦርነት ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ተባብራለች። የኤርትራ ሠራዊት ድንበሩን አቋርጦ በመግባት የሰብዓዊ ጥሰት ፈፅመዋል ተብለው ይወነጀላሉ። ከዚህም ውስጥ የምግብ ዕጥረት እንዲፈጠር ሆን ብለው እየሰሩ ነው የሚል ሲሆን ኤርትራ ግን ይህንን አስተባብላለች። በግጭቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮችም ሆነ ሌሎች አካላት ጥሰቶችን በመፈፀም ተወንጅለዋል። መጋቢት ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች ይወጣሉ ቢሉም ቀኑን አልጠቀሱም። በቅርቡም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃለ አቀባይ በበኩላቸው መከላከያ ሚኒስትርን ዋቢ አድርገው የኤርትራ ሠራዊት ለቀው እየወጡ ነው ብለው ነበር። \"ገፍተን አናስወጣቸውም በሰላም ነው እንዲወጡ የምንፈልገው። ይሄም እርግጠኛ ነኝ ይሆናል\" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቢቢሲ። \"ከኤርትራ ጋር ጉዳዩን በሰላም ለመቋጨት አብረን እየሰራን ነው\" በማለትም አክለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳን ወታደሮችም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዳሉም ተናግረዋል። የሱዳን ወታደሮች ሁለቱም አገራት ግዛቴ ነው የሚሉት የአል ፋሽጋ ትሪያንግልን መቆጣጠራቸው ይታወሳል። ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በብልጽግና ስም ሲወዳደሩ የመጀመሪያቸው ነው። በስልጣን ማግስት ያሳዩት የለውጥ መንፈስ አገሪቱ ዲሞከራሲያዊና ክፍት እንድትሆን ማድረጋቸው በአገሪቱ ባሉ በርካታ ዜጎች ድጋፍን አስገኝቶላቸው ነበር። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠውበት የነበረውን የኤርትራና የኢትዮጵያን የድንበር ፍጥጫ መቋጨታቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት የኖቤል ተሸላሚ ሆነዋል። ነገር ግን በትግራይ ያለው ጦርነት ይህንን ምስላቸውን አጠልሽቶታል። በክልሉም ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርጫ አይካሄድም።", "መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ሱዳናውያን በአደባባይ ድምጻቸውን ማሰማት ቀጥለዋል የሱዳን ጦር ኃይል መፈንቅለ መንግሥት ማካሄዱን ተከትሎ የአገሪቱ ዜጎች ለሁለተኛ ቀን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል። በመዲናዋ ካርቱም እንዲሁም በሌሎችም ከተሞች መንገድ ዘግተው የሱዳንን ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ተቃውሟቸውን ገፍተውበታል። መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም ለሁለተኛ ቀን አደባባይ ከወጡት ዜጎች መካከል ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መጎዳታቸው ተዘግቧል። ፖሊሶች በተቃዋሚዎች ላይ እንደተኮሱ እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል ተሰማርቶ ካርቱምን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች እንደተዘጉም ተገልጿል። የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን የሲቪል አመራሩን በትነው፣ አመራሮቹን በቁጥጥር ስር አውለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገጉት ትናንት ነበር። የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ በሱዳን ጉዳይ ላይ እንደሚመክር የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ጄነራል ቡርሐን ፖለቲካዊ ስምምነት ባለመኖሩ ምክንያት መፈንቅለ መንግሥቱ እንደተካሄደ ተናግረዋል። ወታደሮች ካርቱም ውስጥ ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ የሕዝባዊ ተቃውሞ መሪዎችን እያሰሩ ይገኛሉ። የካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከመዘጋቱም ባሻገር አብዛኛው የስልክ መስመር እና ኢንተርኔት ተቋርጧል። የሱዳን ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ እንደመቱ የተዘገበ ሲሆን፤ የጤና ባለሙያዎች በወታደራዊ ኃይሉ በሚመሩ ሆስፒታሎች ውስጥ አገልግሎት አንሰጥም ማለታቸውም ተሰምቷል። እአአ በ2019 የቀድሞው መሪ ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በሲቪል የሚመራው እና ወታደራዊው የሽግግር አስተዳደር መካከል እምብዛም ስምምነት አልነበረም። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ወታደራዊ ኃይሉ የወሰደውን እርምጃ \"የሱዳንን ሰላማዊ አብዮት የከዳ\" ሲሉ ገልጸውታል። አሜሪካ 700 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለሱዳን ላለመስጠት ወስናለች። ትናንት ለሊቱን በሙሉ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ሱዳናውያን ዛሬም የሲቪል አመራሩ እንዲመለስ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። \"ሕዝቡ የሚፈልገው የሲቪል አመራር ነው\" \"ወታራዊ አስተዳደር አንፈልግም\" ሲሉ መፈክር አሰምተዋል። ከተቃዋሚዎቹ መካከል በርካታ ሴቶችም ይገኙበታል። ፖሊሶች ተቃዋሚዎች ላይ ቢተኩሱም እንኳን ሕዝቡ ድምጹን ማሰማቱን ቀጥሏል። አንድ ጉዳት የደረሰበት ተቃዋሚ ለሮይተርስ የዜና ወኪል በወታደራዊው አስተዳደር ጽህፈት ቤት አቅራቢያ በወታደሮች እግሩን በጥይት መመታቱን ገልጸዋል። ወታደሮች መጀመሪያ ላይ የፕላስቲክ ጥይት ቆየት ብለው ግን እውነተኛ ጥይት መተኮስ እንደጀመሩ ሌላ ተቃዋሚ ተናግሯል። አልታይብ ሞሐመድ አሕመድ የተባለ ግለሰብ \"ሁለት ሰዎች ሞተው አይቻለሁ\" ብሏል። የሱዳን የሐኪሞች ማኅበር እና የማስታወቂያ ሚንስቴር ከወታደራዊ አስተዳደር ዋና መቀመጫው ቅጥር ጊቢ ውጪ ተኩስ እንደነበር በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። ከሆስፒታሎች የወጡ ምስሎች ሰዎች የተለያየ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው እና ልብሳቸው በደም ተነክሮ ያሳያሉ። የአፍሪካ ሕብረት፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የተባበሩት መንግሥታት የሲቪል አመራሮች ከቁም እስር እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክን ጨምሮ እነዚህ በቁም እስር ላይ ያሉት አመራሮች አሁን ላይ የት እንደታሰሩ አይታወቅም። ሐምዶክ መፈንቅለ መንግሥቱን ለመደገፍ ባለመስማማታቸው ትላንት ከመኖሪያ ቤታቸው ጦር ኃይሉ ልዩ ኃይል መወሰዳቸው ይታወሳል። እአአ 2019 ላይ በወታደራዊው እና በሲቪሉ አመራር መካከል የተደረሰው ስምምነት ሱዳንን ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማሸጋገር ያለመ ነበር። ነገር ግን የአመራሮች አለመስማማት እና የመፈንቅለ መንግሠት ሙከራን ጨምሮ ብዙ መሰናክሎች ገጥመውታል። የሽግግር ወቅት ሥልጣን የመጋራት ሉአላዊ ምክር ቤትን ይመሩ የነበሩት የአሁኑ የመፈንቅለ መንግሥት መሪ ጄነራል ቡርሐን ናቸው። ሱዳንን ወደ ሲቪል አመራር ለማሸጋገር ቁርጠኛ እንደሆኑ ሲናገሩም ተደምጠዋል። በሱዳን እአአ በሐምሌ 2023 ምርጫ ይደረጋል ተብሏል።", "የአምናው ሻምፒዮና ሲሳይን ጨምሮ ቀነኒሳ ስለሚሳተፉበት የለንደን ማራቶን በጥቂቱ በአለም ላይ ከሚጠበቁ የአትሌቲክስ ዝግጅቶች አንዱ የሆነው የለንደን ማራቶን በዛሬው ዕለት መስከረም 22፣ 2015 ዓ.ም እየተካሄደ ነው። አምና አንደኛ በመውጣት ሻምፒዮና የነበረው ሲሳይ ለማን ጨምሮ በአትሌቲክስ ዘርፉ ስመ ጥር የሆነው ቀነኒሳ በቀለ ኢትዮጵያን ወክለው ለ42ኛ ጊዜ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ይወዳደራሉ። በሴቶች የማራቶን ውድድር ደግሞ በማራቶን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት ያላት ያለምዘርፍ የኋላው ኢትዮጵያን ወክላለች። በዛሬው ዕለት ወደ 42 ሺህ የሚጠጉ ሯጮች ከግሪንዊች አስከ ዘ ሞል ድረስ ድረስ ያለውን 42 ኪሎሜትር በመሸፈን ይሮጣሉ። በዚያውም ሚሊዮን ፓውንዶችን ለእርዳታ ያሰባስባሉ። የዘንድሮው የማራቶን ውድድር በአውሮፓውያኑ ጥቅምት ወር የሚካሄደው ሶስተኛው እና የመጨረሻው ነው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በጥቅምት ወር እንዲካሄድ ቢደረግም በሚቀጥለው ዓመት በአውሮፓውያኑ 2023 ወደተለመደው የጸደይ ወቅት ይመለሳል። ስለ 2022 የለንደን ማራቶን በጥቂቱ የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህ በዘንድሮው የማራቶን ውድድር ተስፋ ከተጣለባቸው አንዱ አትሌት መሆኑ ይዘገብ የነበረ ቢሆንም በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ባጋጠመው የዳሌ ጉዳት ምክንያት ራሱን አግልሏል። የሴቶች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤትና በለንደን ማራቶን ሁለት ጊዘተ አሸናፊ ብሪጊድ ኮስጌይ ከውድድሩ ራሷን ለማግለል ተገዳለች። ባለፈው ሳምንት በርሊን ላይ በራሱ ተይዞ የነበረውን የወንዶች ማራቶን የአለም ክብረ ወሰን የሰበረው ኢሊዩድ ኪፕቾጌ በዚህ ውድድር ባይሳተፍም ቅዳሜ በነበረው ሚኒ ማራቶን ውድድር ለአሸናፊዎች ሜዳሊያ ለማበርከት ለንደን ይገኛል። ኪፕቾጌ በሌለበርት የአምናው የለንደን ማራቶን ሻምፒዮና ሲሳይ ለማ እና ሌላኛው ስመ ጥር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በወንዶች የማራቶን ሻምፒዮናነት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ናቸው። ሲሳይ ለማ የአምናውን የለንደን ማራቶን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ 01 ሴኮንዶች በመግባት ነበር። በማራቶን ታሪክ ሶስተኛው ፈጣን ሰአት ያለው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ብርሃኑ ለገሰ ዛሬ በለንደን ጎዳናዎች እየሮጠ ይገኛል። ብርሃኑ በአውሮፓውያኑ 2019 በነበረው የበርሊን ማራቶን 2፡02፡48 በሆነ ሰዓት ቀነኒሳ በቀለን በመከተል ሁለተኛ መውጣቱ ይታወሳል። በዚህ ውድድር ላይ ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የአምናው የለንደን ማራቶን አሸናፊ ሲሳይ ለማ ነበር። የሴቶች የማራቶን ወድድር ያለፈው አመት ሻምፒዮና ጆይሲሊን ጄፕኮስጌ እንዲሁም በማራቶን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት ያላት ኢትዮጵያዊቷ ያለምዘርፍ የኋላው በውድድሩ ስፍራ ተሰጥቷቸዋል። የሁለቱም የወንዶች እና የሴቶች ውድድር አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 55 ሺህ ዶላር የሚሸለሙ ሲሆን በዊልቸር ለሚወዳደሩ 35 ሺህ ዶላር ሽልማት ይሰጣቸዋል። በዘንድሮው የለንደን ማራቶን በአለም አቀፉ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ጊነስ ለማስመዝገብ 28 ሙከራዎች እየተደረጉ ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል እንደ ጠርሙስ በመልበስ፣ ሁከቶችን ለመከላከል የሚደረጉ አልባሳት እንዲሁም በክራንች የሚወደዳሩ አሉ።በዚህ ውድድር ላይ የ89 አመቱ ጃፓናዊው ኮይቺ ኪታባታኬ የሚወደዳር ሲሆን እንግሊዛዊው አሌክስ ሆርስሌይ 18ኛ ልደቱን በማራቶን ውድድር ያከብራል። በዛሬው ውድድር ላይ አሌክስን ጨምሮ 205 ግለሰቦች ልደታቸውን በሩጫ ያከብራሉ። ሆኖም በለንደን የተከሰተው የባቡር የስራ ማቆም አድማ ወደ ለንደን ለሚመጡ ተወዳዳሪዎች እንቅፋት እንደሆነ ተገልጿል። በባቡር ሰራተኞች በታቀደው የስራ ማቆም አድማ ምክንያት የጉዞ መስተጓጎል የሚገጥማቸው ሯጮችን ለመርዳት \"የምንችለውን ሁሉ\" እያደረግን ነው” ብለዋል አዘጋጆቹ። የባቡር አገልግሎቶች ቅዳሜ እለት አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበረ ሲሆን በዚህም ምክንያት ጥዋት ለሚደረገው ሩጫ በርካቶች ላይደርሱ ይችላሉ ብለዋል። የሩጫው ዳይሬክተር ሂዩ ብራሸር ለቢቢሲ ስፖርት እንደተናገሩት ዘግይተው የሚመጡ ሯጮች በኋላ እንዲጀምሩ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል።", "ኤርትራዊው የጌንት-ዌል የብስክሌት ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በቤልጂየም የሚካሄደውን የጌንት-ዌል የብስክሌት የዕለት ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ። ቢንያም ግርማይ እሑድ በተካሄደው የጌንት-ዌል የብስክሌት ውድድር የዕለቱ አሸናፊ በመሆን ታሪክ ሠርቷል። ማሸነፉን ተከትሎ በሰጠው ቃለ ምልልስ \"የማይታመንና የሚገርም ነው። ይህን አልጠበቅኩም ነበር\" ብሏል የ21 ዓመቱ ኤርትራዊ። \"አርብ ነበር ዕቅዴን የቀየርነው። የመጣነው ለጥሩ ውጤት ነው። ውድድሩ አስደናቂና የማይታመን ነው\" ብሏል ቢንያም። ቢንያም 30 ኪሎ ሜትር ሲቀር መምራት ከጀመሩት አራት ብስክሌተኞች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን፤ የውድድሩ መጠናቀቂያ 250 ሜትር ርቀት ሲቀረው አፈትልኮ በመውጣትም ማሸነፍ ችሏል። የኢንተርማርቼ-ዋንቲ ጎበርት ጋላቢው ቢኒያም ግርማይ \"ድሉ በተለይም ለአፍሪካውያን ብስክሌተኞች ትልቅ ለውጥ ያመጣል\" ሲል ሃሳቡን ገልጿል። የጃምቦ ቪስማው ብስክሌተኛ ክሪስቶፍ ላፖርት እስከመጨረሻው ከቢኒያም ጋር ቢታገልም ፈረንሳዊው ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። 248.8 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የጌንት-ዌል በሚቀጥለው ሳምንት ለሚጀመረው እና ቱር ኦፍ ፍላንደርስ ለሚባለው የቤልጂየም ትልቁ ውድድር እንደመዘጋጃ ይቆጠራል። በድንጋይ ንጣፍ፣ ኮብል መንገድ፣ ላይ የመጀመሪያ ውድድሩን ያደረገው ቢኒያም \"በኮብል ላይ ተቸግሬ ነበር። አልተመቸኝም ነበር\" ብሏል። \"መጨረሻ ላይ ሌሎቹ ጠንካሮች እንደሆኑ ባውቅም በራስ የመተማመን ስሜት ተሰማኝ።\" ቢንያም በፍላንደርስ ለመሳተፍ አልተመዘገበም። የሴቶቹን ውድድር በጎዳና ውድድር ሻምፒዮን የሆነችው የትሬክ-ሴጋፍሬዶዋ ኤሊሳ ባልሳሞ አሸንፋለች። ኮሎምቢያዊው ሰርጂዮ ሂጉይታ የቮልታ ሲክሊስታን ካታሎንያ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል። ኢኳዶራዊው ሪቻርድ ካራፓዝ በሁለተኝነት አጠናቋል። ሂጉይታ አንድ ሳምንት የፈጀውን ውድድር ከካራፓዝ በ16 ሰከንዶች ቀድሞ አጠናቋል። ፖርቹጋላዊው ጆአዎ አልሜዳ ደግሞ ሦስተኛ ሆኗል።", "ናኦሚ ኦሳካ ከፈረንሳይ ውድድር ራሷን አገለለች የአለም ቁጥር ሁለት የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ከፈረንሳይ ውድድር ራሷን እንዳገለለች አስታወቀች። ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ለመናገር ፈቃደኛ ካልሆነች ትታገዳለች የሚል ውዝግብን ተከትሎ ነው በፈረንሳይ ኦፕን እንደማትወዳደር ያሳወቀችው። ይህንን ባሳወቀችበት የትዊተር መልዕክትም ናኦሚ በጭንቀት (ዲፕረሽን) ህመም እየተሰቃየች እንደሆነ አስፍራለች። ህመሟም የጀመረው ከሶስት አመት በፊት በሜዳ ቴኒስ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን የመጀመሪያዋን ግራንድ ስላም ካሸነፈች ጀምሮ ነው። የ23 አመቷ አትሌት የአዕምሮ ጤንነቷን ለመጠበቅ በሮላንድ ጋሮስ ጋዜጣዊ መግለጫ አልሳተፍም ያለችው ባለፈው ሳምንት ነበር። ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሮማኒያዊቷ ፖትሪሺያ ማሪያ ቲግ ጋር በነበረው ውድድር በአሸናፊነት ያጠናቀቀችበት ጨዋታ ተከትሎ ከሚዲያዎች ጋር ቆይታ አላደርግም በማለቷ 15 ሺህ ዶላር ተቀጥታለች። በዚያኑ ቀን የግራንድ ስላም ውድድር አዘጋጆች ባወጡት የጋራ መግለጫ አትሌቷ ሚዲያ አላናግርም በሚል ባህርይዋ ከቀጠለች ከጨዋታዎች እንደምትታገድ አስጠንቅቀው ነበር። አትሌቷም በትናንትናው ዕለት ከፈረንሳይ ኦፕን ራሷን እንዳገለለች ገልፃ \"ለተወሰነ ጊዜም ከሜዳ ራሴን አርቄያለሁ \" ብላለች። \"ትክክለኛው ወቅት ሲመጣ ከውድድር አዘጋጆች ጋር ለአትሌቶች፣ ለሚዲያዎችና ለተመልካቾች በምን መንገድ ውድድሮችን ማሻሻል እንችላለን የሚለው ላይ መወያየት እፈልጋለሁ' ብላለች። የፈረንሳይ ቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጊለስ ሞሬቴን የናኦሚን ራሷን ከውድድር ማግለል አስመልክቶ \"አሳዛኝ\" ብለውታል። \"ናኦሚ በገጠማት ሁኔታ ሃዘን ተሰምቶናል። በፍጥነትም እንድታገግም ምኞታችንን እየገለፅን በሚቀጥለው አመት ውድድራችን እናያታለን ብለን እንጠብቃለን\" ብለዋል ። \"ሁሉም የግራንድ ስላምስ ውድድሮች ማለት ደብልዩ ቲ ኤ፣ ኤቲፒና አይቲኤ ለአትሌቶች ጤና ቅድሚያ በመስጠት በሌሎችም ዘርፎች አትሌቶች የሚሻሻሉበትን መንገድ እንቀይሳለን። ከዚህም ጋር ተያይዞ አትሌቶች ከሚዲያዎች ጋር ያላቸው ግንኙነቶች እንዲሻሻሉ ስንሰራ ነበር። አሁንም እንሰራለን\" በማለት አስረድተዋል።", "የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል. . . .ግምቶችን ይዘናል የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀምራል። ለአዲሱ የውድድር ዘመን ቢቢሲ ሳምታዊ የውጤት ግምት የሚሰጥ አዲስ ባለሙያ ይዞ መጥቷል- ታዋቂው ክሪስ ሱቶን። ሱቶን ቀደም ሲል ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። ቼልሲ፣ አስቶን ቪላ እና ሴልቲክ የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው። በኋላም በአሰልጣኝነት እና በተንታኝነት ሰርቷል። ለመሆኑ የ2022/23 ውድድር ዘመን የመክፈጫ ጨዋታዎች በምን መልኩ ይጠናቀቃሉ? ክሪስታል ፓላስ ከ አርሰናል አርሰናል ጥሩ የቅድመ ውድድር ዘመን ነበረው። ኮኖር ጋላገር ወደ ቼልሲ ከተመለሰ በኋላ ክሪስታል ፓላስ እንደቀድሞው ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑ ላይ ጥያቄ አለኝ። ለሚኬል አርቴታ ቡድን ጠንካራ ጨዋታ ይሆናል። ብዙ ነገሮች ግን መድፈኞቹ እንደሚያሸንፉ ይቁማሉ። ግምት፡ 1- 2 ፉልሃም ከ ሊቨርፑል እንደ ላውሮ በየሳምንቱ ሊቨርፑል ያሸንፋል እያልኩ መገመት የለብኝም። እንደዚህ አይነት መድሎ ማቆም አለብኝ። ይህንን ጨዋታ ግን ሊቨርፑል ይሸነፋል ብሎ መገመትም ስህተት ነው። ሊቨርፑል በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ወቅት ድንቅ ነበር። ቅዳሜ ለፉልሃም ከባድ ጨዋታ ይሆናል። ዓመቱን ሙሉም የሚከብዳቸው ይመስለኛል። ግምት፡ 0-3 ሊድስ ከ ዎልቭስ ከፉልሃም እና በርንማውዝ ጋር ሦስተኛው ቡድን ሆኖ የሚወርደው ቡድን ሊድስ ይመስለኛል። ባለፈው ዓመትም ለጥቂት ነው የተረፉት። ካልቪን ፍሊፕስ እና ራፊንሃን የመሰሉ ድንቅ ተጫዋቾቻቸውን ሸጠዋል። ዎልቭስ ደግሞ ድንቅ ኳስ አቀጣጣይ ተቻዋቾች አሉት። የተጎዳው ራዉል ሂሚኔዝ ባለመኖሩ የአጥቂ ችግር አለባቸው። ስለዚህ የፊት መስመሩን ማን ይመራል? ይህ ለመገመት ከባድ ጨዋታ ነው። ግምት፡ 1-1 በርንማውዝ ከ አስቶን ቪላ በርንማውዝ ያስፈራኛል። ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደጉ በኋላ ዝውውሮች ላይ በስፋት አልተሳተፉም። አስቶን ቪላም በምጠብቀው ልክ ተጫዋቾችን አላስፈረመም። ግን በጣም ብዙ ምርጥ ምርጥ ተጫዋቾች አሏቸው። በጥሩ ውጤት ለመጀመርም ዕድል ያላቸው ቪላዎች ናቸው። ግምት፡ 0-1 ኒውካስል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ፎረስት ከ23 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ መምጣቱ አስደሳች ነው። ቡድኑ ሮበርትሰንን የመሳሰሉ ጥሩ ተጫዋቾች አሉት። ሄዜ ሊንጋርድ እና ኦሬል ማንጋላን የመሰሉ ድንቅ ተጫዋቾችንም አስፈርመዋል። ኒውካስል ደግሞ ዘንድሮ መውረድ ስጋት የለበትም። ኤዲ ሃው ድንቅ ሥራ አከናውነዋል። ዘንድሮም ይህንኑ ያስቀጥላሉ ብዬ አስባለሁ። ጀምስ ማዲሰንን ከሌስተር ለመግዛት እየሞከሩ ሲሆን ለምን እንደዘገዩ ግልጽ አይደለም። ይህም ለመገመት የሚከብድ ጨዋታ ይሆናል። ግምት፡ 1-0 ቶተንሃም ከ ሳውዝሃምፕተን በቶተንሃም ዙሪያ ብዙ አስደሳች ዜናዎች አሉ። ይህ ግን በየውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ላይ የሚፈጠር ነገር ነው። ሪቻርልሰን በቅጣት በዚህ ጨዋታ ባይሰለፍም እንዴት ከዚህ ቡድን ጋር እንደሚዋሃድ ማየት እፈልጋለሁ። ዴያን ኩሉስቭስኪ በጥር ወር ቡድን ከተቀላቀለ በኋላ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ነው። እነዚህን ሁሉ እንዴት አንድ ላይ እንደሚያቀናጁ አላውቅም። ሳውዝሃምፕተኖች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግምት ሳይሰጣቸው ሜዳ ገብተው ብዙዎችን እያስገረሙ ይወጣሉ። ከባድ ሽንፈት እና አስደናቂ ድሎችንም አስመዝግበዋል። ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ ተለያይተው የኮንቴው ቶተንሃም አሸንፈዋል። ይህ ግን የሚደገም አይመስለኝም። ግምት፡  2-1 ኤቨርተን ከ ቼልሲ ቼልሲ ለውድድር ዓመቱ የተዘጋጀ አለመመስሉ አስገራሚ ነው። ቡድኑ ገና ተጫዋቾችችን አስፈርሞ አላጠናቀቀም። የተዘጋጀ ቡድንም አይመስለም። ኤቨርተንም ክፍተቶች አሉበት። ዶምኒክ ካልቨርት-ልዊን በጉዳት ሳሎሞን ሮንዶን እና ሪቻርሊሰን ደግሞ ተዘዋውረዋል። ስለዚህ አጥቂ መስመሩን የሚመራ የለም። ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ የጉዲሰን ፓርክን ደጋፊ እገዛ ይፈልጋሉ። ደጋፊው ሊያግዛቸው እንጂ ጎል ሊያስቆጥርላቸው ግን አይችልም። ግምት፡ 0-2 ሌስተር ከ ብሬንትፎርድ ያለፈው ዓመት ለሌስተር መጥፎ የውድድር ዘመን አልነበረም። ከሁለት ዓመት የአምስተኛነት ደረጃ የኋሊት ተንሸራተዋል።። በረኛቸው ካስፐር ሺማይክል ቡድኑን ለቋል። ዌስሊ ፎፋና እና ማዲሰንም ከለቀቁ ለቡድኑ ከባድ ይሆናል። በሬንትፎርድ ከሳምፕዶሪያ ያስፈረመው አማካዩ ሚኬል ዳምስጋርድ ጥሩ ዝውውር ይመስላል። ከታች ለመጡ ቡድኖች ሁለተኛው የውድድር ዓመት ከባድ ሲሆን ይታያል። የብሬንትፎርድም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ይህ ጨዋታም ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል። ግምት፡ 1-1 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብራይተን ከማንችስተር ዩናይትድ ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። የክርስቲያኖ ሮናልዶ ጉዳይ አለመረጋጋትን ይፈጥራል። አዲሱ አሰልጣን ኤሪክ ቴን ሃግ ያለ አጥቂውም ሊሠሩ ይችላሉ። በፊት በፊት ኦልድ ትራፎርድ ላይ መጫወት ከባድ ነበር። አሁን አሁን ግን ነገሮች ተለውጠዋል። አሜክስ ስታዲየም ላይ ባለፈው ዓመት 4 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል። ስለዚህ አይፈሯቸውም። በግራሀም ፖተር የሚመራውን ብራይተን ይመቸኛል። ከዚህ ጨዋታም ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1-1 ዌስት ሃም ከ ማንቸስተር ሲቲ ዌስት ሃም አጥቂውን ጂያንሉካ ስካማካን ከሳምፕዶሪያ አስፈርሟል። ወደ ሙሉ የጨዋታ አቋም የደረሰ ግን አይመስለኝም። የቡድኑ ችግር የሚመስለኝ የተከላካይ ክፍሉ ነው። በቅርቡ ያስፈረሙት ተከላካዩ ናይፍ አጉዋርድ በጉዳት አይሰለፍም። ባለፈው ዓመት እንደደረጉት ከሲቲ ጋር አቻ የሚለያዩ አይመስለኝም። ከሁለት ዓመት በፊት ማንቸስተር ሲቲ በሊጉ መክፈቻ 5 ለ 0 ዌስት ሃምን አሸንፎ ነበር። አሁንም ድሉ የሲቲ ይመስላል። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ከሊቨርፑል ጋር ጥሩ አልነበረም። ቡድኑ በዚህ ጨዋታ የሚነቃቃ ሲሆን ኤርሊንግ ሃላንድም የጎል ካዝናውን ይከፍታል የሚል ግምት አለኝ። ግምት፡ 0-3", "\"በኳስ ወቅታዊ አቋም እንጂ ታሪክ ብዙም ቦታ የለውም\" ጋቶች ፓኖም ሐሙስ ሰኔ 02/2014 ዓ.ም. ዋሊያዎቹ በግሩም ብቃት ፈርዖኖቹን አንበረከኩ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም እግር ኳስ ስሟ ከገነነው ግብፅ ለመግጠም ሲሰናዳ ብዙ ተባለ። በርካቶች ሽንፈት ጠበቁ። \"አቻ ብንወጣ በምን ዕድላችን\" ሲሉ አንሾካሾኩ። ዋሊያዎቹ ግን የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው በባዳ ሜዳ ግብፅን ገጠሙ። ብሩንዲያዊው የዕለቱ የመሃል ዳኛ ፊሽካቸውን ነፉ። ጨዋታው ተጀመረ። ዋሊያዎቹ የግብፅን በር ያንኳኩ ጀመር። ፈርዖኖቹ ኳስ መግፋት ከበዳቸው። አቡበከር ሲሸልል፣ ሽመልስ ሲያታልል፣ ጋቶች ሜዳውን ሲያካልል ቆመው ይመለከቱ ጀመር። ጨዋታውን በስጋት የጀመረው ደጋፊ የልቡ ምት መለስ ይልለት ጀመር። 21ኛው ደቂቃ ደረሰ። ዳዋ ሆቴሳ ወደ ግብፁ ግብ ጠባቂ ሞሐመድ አቡጋባል ገሰገሰ። በዚህች ደቂቃ በኢትዮጵያውያን ደጋፊዎች ዘንድ ድቅድቅ ዝምታ ሰፈነ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ኳሷ ተንከባላ መረቡን ስትነካ ምድር ተንቀጠቀጠ። ኢትዮጵያ 1 - ግብፅ 0። ዋሊያዎቹ በአንድ ጎል ተማምነን ለዕረፍት ከሜዳ አንወጣም ያሉ ይመስላሉ። የግብፅን የሜዳ አጋማሽ ፈነጩበት። ተረኛው አምበሉ ሽመልስ በቀለ ነው። ለግብፁ ክለብ ኤል ጉና የሚጫወተው ሽመልስ የፈርዖኖቹን ነገር ለኔ ተዉት ያለ ይመስላል። ከአማኑዔል ገብረሚካዔል የተሻገረለትን ኳስ በአቡጋባል አናት አሻግሮ የዋሊያዎቹን የጎል ድርሻ እጥፍ አደረገው። ፈርዖኖቹ ከወራት በፊት በተረገው የአፍሪካ ዋንጫ ለፍፃሜ ደርሰው በሴኔጋል ተረተው የአህጉሪቱ ሁለተኛ ኃያል ቡድን ለመሆን ችለዋል። በፊፋ የዓለም እግር ኳስ ሚዛን ግብፅ 32ኛ ናት። ኢትዮጵያ ደግሞ 140ኛ። የእግር ኳስ ውጤት ተንታኞች ግብፅ ትረታለች ብለው ቢገምቱ አይገርምም። ከውጤቱ በኋላም ኢትዮጵያ ረታች ሳይሆን፣ ግብፅ ተረታች ብለው ቢፅፉም በውጤቱ ደንግጠው መሆኑን እሙን ነው። ግን ግን ዋሊያዎቹ ለጨዋታው የሰጡት ግምት ምን ነበር? \"ኧረ እኛ ምንም ዓይነት ፍራቻ አልነበረንም\" ይላል ጋቶች። \"ማሸነፍ እንደምንችል ራሳችንን አሳምነን ነው የገባነው። በእግር ኳስ ወቅታዊ አቋም እንጂ ታሪክ ብዙ ቦታ የለውምና ዓላማችን የነበረው ማሸነፍ ነበር።\" አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከሚታወቁበት የ4-3-3 ፍልስፍና ፈቀቅ ብለው በአዲስ አሰላለፍ ነበር ግብፅን የገጠሟት። ውበቱ በግብፁ ጨዋታ 4-2-3-1 በተሰኘው አጨዋወት ነው የተከሰቱት። አቡበከር ናስር የፊቱን መስመሩን እንዲሾፍር፤ ጋቶችና አማኑዔል ዮሐንስ ተከላካዩንና አጥቂውን ክፍል እንዲያሳልጡ በማሰብ ያደረጉት ነበር። የአሠልጣኙ ውበቱ ያደረጉት ለውጥ ግን ፍሬያማ ነበር። \"ከማላዊ ሽንፈት መልስ ነው ግብፅን የገጠምነው። ጨዋታው ቀላል እንደማይሆን እናውቃለን። ይኸው አሸንፈን እኛም ደስ ብሎን የኢትዮጵያም ሕዝብ ተደስቷል\" ይላል ጋቶች ፈገግታ በሚነበብበት ድምፅ። በአስገራሚ ብቃቱ መሃል ሜዳውን በብቸኝነት ሲሾፍር የነበረው ጋቶች ፓኖም፣ በቋሚ አሰላለፍ ኢትዮጵያን ከወከለ ሰንበትበት ብሏል። በአፍሪካ ዋንጫ ጋቶችን ለማየት የቋመጡ ዓይኖች አልተሳካላቸውም። ጋቶችን ግን ለታሪካዊው የግብፅ ፍልሚያ ደረሰ። \"እርግጥ ነው በአፍሪካ ዋንጫ አንድም ጨዋታ አልተጫወትኩም። ይህ የአሠልጣኙ ውሳኔ ነው። ነገር ግን እኔ ወደ ሜዳ ግባ ስባል ለመግባት ሁሌም ዝግጁ ነኝ።\" ጋቶች ይህን ይላል. . . \"ወደ ሜዳ ግባ ስትባል ያለህን አቅም ነው ማሳየት ያለብህ።\" እነሆ በቃል ያለውን በግብፅ ጨዋታ ለብዙዎች አሳይቷል። ከግብፅ 27 ክልሎች አንዱ የሆነው ሬድ ሲ ገቨርኔት የኤል ጉናን መቀመጫ ነው። ኤል ጉናን ለኢትዮጵያዊያን እግር ኳሰኞች አዲስ አይደለም። ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾችም ለግብፅ ሊግ ባዳ አይደሉም። ጋቶች ፓኖም አንድ የእግር ኳስ ዘመን በኤል ጉናን አሳልፏል። ለሃራስ ኤል ሆዱድም ተሰልፎ ያውቃል። ሽመልስ በቀለ ደግሞ የወቅቱ የኤል-ጉና የወቅቱ የቡድኑ አማካይ ነው። ሌሎችም ስማቸው የከበደ ኢትዮጵያውያን ኳስ ተጫዋቾች የግብፅን ሊግ ያውቁታል። ዋሊያዎቹ ግብፅን ለመርታታቸው ይሄ አንዱ ምክንያት ይሆን? \"አብዛኛዎቹ የግብፅ ተጫዋቾች ከአል-አህሊና ዛማሌክ የተመረጡ ናቸው። እዚያ ሳለሁ ተቃራኒ ሆኜ የተፋለምኳቸው ናቸው\" ይላል ጋቶች። \"ይሄ ረድቶኛል ብዬ አስባለሁ።\" የግብፅ ድል ለቀጣይ ጨዋታዎች ጠንካራ መንፈስ እንደሚፈጥር ጋቶች ያምናል። \"በስኬትም በደረጃም ከእኛ ላቅ ያሉ ናቸው። ግብፅን መርታታችን ጠንከር ካልን ማንንም ማሸነፍ እንደምንችል ያሳየን ነው።\" የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ካፍ፤ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ጨዋታ ለማድረግ የሚችል ሜዳ የላትም ብሏል። ይሄ ዜና የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ጨምሮ ደጋፊውን አንገት ያስደፋ ነበር። ፌዴሬሽኑ የባሕር ዳር ስታድዬምን አድሻለሁ ቢልም ካፍ ተወካይ ልኮ ካስፈተሸ በኋላ መመዛኛዬን አላሟላችሁም የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ለዚህ ነው ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ማድረግ የሚገባቸውን ጨዋታ በማላዊ ስታድዬም ሊያደርጉ የተገደዱት። ቢሆንም በማላዊው ሊሎንግዌ ስታድዬም ለዋሊያዎቹ የነበረው ድጋፍ ደመቅ ያለ ነበር። \"እርግጥ ነው በሜዳችን ቢሆን የተሻለ የራስ መተማመን ይኖረን ነበር\" ባይ ነው ጋቶች። ነገር ግን ይላል የመሃል ሜዳው ሞተር \"ነገር ግን በማላዊ የነበረው ድጋፍ ሜዳችን ላይ እየተጫወትን ያክል እንዲሰማን አድርጎናል።\" ጋቶች ጨዋታው ሲገባደድ ከስታድዬሙ ግዙፍ ድምፅ ማጉያ በሚወጣው ሙዚቃ ከደጋፊዎች ጋር ሲቦርቁ እንደነበር ያወሳል። \"እንግዲህ የእኛ ሜዳ ከደረሰ ቀጣዩን ጨዋታ [ኢትዮጵያ ከጊኒ] በደጋፊያችን ፊት እንደምናደርግ ተስፋ አደርጋለሁ\" ይላል። ፈርዖኖቹ አለን የሚሉት ኮከብ ተጫዋቻቸውን በኢትዮጵያው ጨዋታ ማሰለፍ አልቻሉም። የሊቨርፑሉ አጥቂ ሞሐመድ ሳላህ በጉዳት ምክንያት ይህ ጨዋታ አምልጦታል። ቁጥሩ አንዱ ግብ ጠባቂ ኤልሻናዊና ትሬዝጌም እንዲሁ አገራቸውን መወከል ሳይችሉ ቀርተዋል። እውን የሞሐመድ ሳላህ አለመኖር ለዋሊያዎቹ መልካም አጋጣሚ ነበር? \"እርግጥ ነው ሞሐመድ ሳላህ ትልቅ ተጫዋች ነው\" የጋቶች አስተያየት ነው። \"ነገር ግን ሳላህ ብቻውን ምንም ሊያደርግ አይችልም። ምክንያቱም እኛ በዕለቱ የተሻልን ነበርን። የሚገባንን ውጤት ነው ያገኘነው።\" አሠልጣኝ ውበቱ አባተም አገር ቤት ከገቡ በኋላ በሰጡት መግለጫ ያሉት ይሄንኑ ነው። \"እኛ በልጠን እንጂ ግብፅ ደክማ አይደለም\" ብለዋል። በግብፅ ሽንፈት የደነገጡ በርካታ ዓለም አቀፍ የኳስ አውታሮችም የዋሊያዎቹን ውጤት ከማድነቅ አልቦዘኑም። የግብፅ መገናኛ ብዙኃን አዲሱን የፈርዖኖቹን አሠልጣኝ ኢሃብ ጋላልን የሚወቅስ ፅሑፍ አስነብበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ማጣሪያ በሚቀጥለው ወር ደቡብ ሱዳንን ይገጥማል። ቻን አገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሰለፉበት አህጉራዊ ውድድር ነው። ይህም አሠልጣኝ ውበቱ አዳዲስ ተጫዋቾች እንዲሞክሩበት ዕድል የሚሰጣቸው ነው። ከዚያ ቀጥሎ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ይከተላሉ። ዋሊያዎቹ በወርሃ መስከረም በደርሶ መልስ ጨዋታ ጊኒን ይገጥማሉ። መጋቢት ደግሞ ሁለቱ ቀሪ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከማላዊና ከግብፅ ጋር ይደረጋሉ። አሁን ኢትዮጵያ የምድብ 'መ' ቁንጮ ናት። ምንም እንኳ ሁሉም የምድቡ ቡድኖች ተመሳሳይ 3 ነጥብ ቢያካብቱም ዋሊያዎቹ በአንድ ንፁህ ጎል ከምድቡ አናት ተቀምጠዋል።", "እግር ኳስ ፡ ከማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ ፖሊስ ሐኪሙ ላይ ምርመራ ጀመረ የአርጀንቲና ፖሊስ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ሞት ጋር ተያይዞ የዝነኛውን እግር ኳስ ተጫዋች ሐኪም እየመረመረ ይገኛል። ፖሊስ በዋና ከተማዋ ቦነስ አይረስ የሚገኘውን የዶ/ር ሊዮፖልዶ ሉኮን መኖርያ ቤትና የግል ክሊኒክ በርብሯል። ምርመራው ሊጀመር የቻለው ማራዶና የተሳካ የተባለ ቀዶ ህክምና ማድረጉን ተከትሎ በድንገት መሞቱ ምናልባት የሕክምና ቸልተኝነት ተጫዋቹን ለሞት ዳርጎታል የሚል ጥርጣሬ በመፈጠሩ ነው። የ60 ዓመቱ የእግርኳስ ኮከብ የሞተው ከ4 ቀናት በፊት በልብ ድካም ነው። ማራዶና ከሕመሙ እያገገመ ሳለ ነበር በድንገት የሞተው። ዶ/ር ሊዮፖልዶ እስካሁን ክስ አልተመሰረተበትም። ሆኖም አንድም ጥፋት የለብኝ ሲል እንባ እየተናነቀው ለጋዜጠኞች ተናግሯል። ማራዶና ከመሞቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የተሳካ የተባለ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና አድርጎ ነበር። ቀዶ ጥገናው ያስፈለገው በጭንቅላቱ ውስጥ የደም መርጋት ምልክቶች በመታየታቸው ነበር። በሚቀጥለው ወር ደግሞ ከአልኮል ሱስ ለመውጣት አዲስ ሕክምና ይጀምራል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር። የማራዶና ሴት ልጆች ስለ አባታቸው የሕክምና ሁኔታ ምርመራ እንዲደረግ ግፊት አድርገዋል ተብሏል። ትናንት እሑድ ወደ 30 የሚሆኑ ፖሊሶች የማራዶና የግል ሐኪም ወደ ሆነው የ39 ዓመቱ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ቤት በድንገት በመድረስ ብርበራ አድርገዋል። ሌሎች 20 የሚሆኑ ፖሊሶች ደግሞ ክሊኒኩን ፈትሸዋል። ፖሊስ የማራዶና የመጨረሻ ቀናት ሕክምና ምን ይመስል እንደነበር ለመፈተሽ ነው ፍላጎቱ። ኮምፒውተሮችን፣ ስልኮቹንና የሕክምና ማስታወሻዎችን ጭምር አንድ በአንድ እየመረመሩ ነው ተብሏል። ፖሊስ ጥርጣሬ አለኝ የሚለው የማራዶና ቀዶ ጥገናን ተከትሎ ምናልባት ሐኪሙ ሊያደርጋቸው ይገቡ የነበሩ ጥንቃቄዎችን ሳያደርግ ቀርቶ ከሆነ በሚል ነው። ማራዶና ቀዶ ጥገናውን አሳክቶ ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ እንዲያገግም የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ነበሩ ወይ? የሚለው በምርመራው ይካተታል። ለምሳሌ 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚንከባከቡት ነርሶች መኖር፣ በአደገኛ እጽ ሱስ ለሚሰቃይ ሰው ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች መኖር፣ በአስቸኳይ ሊጠሩ የሚችሉ ሐኪሞች እና በተጠንቀቅ የሚቆም አምቡላንስ ነበረ ወይ? የሚለው ይፈተሻል። መርማሪ ፖሊስ ዶ/ር ሊዮፖልዶ እነዚህ ሁኔታዎች ለታማሚው አሟልቶ ነበር ወይ፣ የሐኪሙ የመጨረሻ ቀናትን ምን ይመስላሉ የሚለውን እየመረመረ ነው። የ39 ዓመቱ የማራዶና የግል ሐኪም ዶ/ር ሊዮፖልዶ ደንበኛው ከሞተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት ዝምታውን ሰብሯል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ ስሜታዊ ሆኖ በእንባ እየታጠበ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የማራዶናን ሕይወት ለማትረፍ የሚችለውን ሁሉ እንዳደረገለት ተናግሯል። ማራዶና በመጨረሻ ቀናት ከፍተኛ ሐዘን ይሰማው እንደነበረም ጠቅሷል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ በጋዜጠኞች በእንዝህላልነት ለደንበኛው መሞት ተጠያቂ ይሆን እንደሆነ ሲጠየቅ በቁጣ እንዲህ መልሷል፣ \"እኔ ተጠያቂ የምሆነው በምን ምክንያት እንደሆነ ልናገር? ማራዶናን በጣም በመውደዴ፣ ለእሱ በጣም እንክብካቤ በማድረጌ፣ በአጭር ይቀጭ የነበረውን ሕይወቱን በማራዘሜ፣ እስከመጨረሻው ከእሱ ጋር በመሆኔ ነው መጠየቅ ካለብኝ\" ሲል በድንገተኛ ቁጣ ገንፍሎ ምላሽ ሰጥቷል። ፖሊስ በበኩሉ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ለማራዶና ቀዶ ጥገና ካደረገለት በኋላ ክትትል ማድረግ ሲገባው አላደረገለትም ብሎ ጠርጥሮታል። በዚህ ረገድ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ሲመልስ \"የእኔ ሙያ የአንጎል ቀዶ ህክምና ነው። እኔ ህክምናውን ጨርሻለሁ\" በማለት ማራዶና ከእሱ ክሊኒክ ከወጣ በኋላ ላለው ነገር ተጠያቂ እንዳልሆነ አስገንዝቧል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ እንደሚለው ማራዶና ከቀዶ ህክምናው በኋላ መሄድ የነበረበት ወደ አደገኛ እጽ ማገገሚያ ማዕከል እንጂ ወደ ቤት አልነበረም። ማራዶና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሳለ ቤቱ የተዘጋጀና የሕክምና ቁሶች የተሟሉለት አምቡላንስ እንዴት ላይኖር ቻለ የሚለው እያነጋገረ ነው። ማራዶና በመጨረሻው ሰዓት ልጆቹንም፣ ቤተሰቡንም ማስጠጋት አልፈለገም፣ ከፍ ያለ ሐዘን ይሰማው ስለነበር ብቻውን መሆን ፈልጓል ሲል ሐኪሙ አብራርቷል። ማራዶና የድኅረ ዝና መስቅልቅልና የኮኬይን ሱሰኝነት ለሕይወቱ ማጠር ሚና እንደነበራቸው ይታመናል።", "በ38 ዓመት ከብር ሜዳልያ ወደ ወርቅ የተሻገረችው ዋናተኛ የሲንጋፖር ተወላጇ ክርስቲና ታም ለመጀመሪያ ጊዜ አገሯን ወክላ ሜዳልያ ያገኘችው የ12 ዓመት ታዳጊ ሳለች ነበር። ያኔ የብር ሜዳልያ ያገኘችው ክርስቲና፤ ከ38 ዓመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት ሁለት የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። የ50 ዓመቷ ክርስቲና፤ በፊሊፒንስ እየተካሄደ ባለው የደቡብ ምዕራብ እስያ ውድድር ከተሳተፉ አንዷ ናት። የወርቅ ሜዳልያ ያገኘችው ከውሀ በታች በሚካሄድ የ 'ሆኪ' (የገና ጨዋታን የሚመስል) ውድድር ነው። \"ወደ ውድድሩ ተመልሼ የወርቅ ሜዳልያ አገኛለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር\" ሰትልም ክርስቲና የተሰማትን ገልጻለች። • ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ ያለማቋረጥ የዋኘችው የጡት ካንሰር ታማሚ • ውሃ ውስጥ ለፍቅረኛው የአግቢኝ ጥያቄ ያቀረበው ግለሰብ ሰጥሞ ሞተ • ገንዘብ ያለው ሊገዛው የሚችለው 'ወርቃማው' ፓስፖርት ለምን ተፈላጊ ሆነ? ወደ ዋና ስፖርት የገባችው በሰባት ዓመቷ ከአንድ አጋጣሚ በኋላ ነበር። ያኔ በ40ዎቹ መጨረሻ ላይ የነበሩ አባቷ ዋና ባይችሉም፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጀልባ ሲጓዙ ነፍስ አድን ጃኬት ለመልበስ ፍቃደኛ አልነበሩም። ቤተሰቡ ለሽርሽር በጀልባ ወደ ማሌዢያ ለመጓዝ ሲወስን፤ የክርስቲና አባት በባለቤታቸው ጉትጎታ ነፍስ አድን ጃኬት ለመልበስ ተስማሙ። ጉዞ ላይ ሳሉ፤ የክርስቲና አባት ከጀልባ መውደቃቸውን ታስታውሳለች። አባቷ በነፍስ አድን ጃኬቱ አማካይነት ሕይወታቸው ከተረፈ በኋላ፤ መላ ቤተሰቡ ዋና እንዲማር ያደረጋሉ። አጋጣሚውም ክርስቲናን ከስፖርቱ ጋር አስተዋወቃት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1981 ሲንጋፖርን ወክላ ስትወዳደር 12 ዓመቷ ነበር። የብር ሜዳልያም አግኝታለች። \"ያኔ ብዙም ለውጤቴ ቦታ አልሰጠሁትም ነበር። እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ ግን የድሉ ዋጋ ገባኝ\" ትላለች። ከሁለት ዓመት በኋላ በ200 ሜትር ስትወዳደርም የብር ሜዳልያ ብታገኝም፤ ስፓርቱን ለሠላሳ ዓመት አቋርጣ በሕግ ዘርፍ ተሰማራች። 2005 ላይ ስለ 'አንደር ዋተር ሆኪ (ከውሀ በታች የሚካሄድ የ 'ሆኪ') አንድ ጽሑፍ ስታነብ ግን፤ ለ38 ዓመት ወደተወችው ስፖርት የመመለስ ፍላጎት አደረባት። ፊሊፒንስ በተካሄደው ውድድር ተሳትፋም፤ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ አስመዝግባለች። \"ልምምድ ማድረጉን እወደዋለሁ፤ የምፈልገው ቦታ እስክደርስ ያለው ሂደትም ያስደስተኛል\" ያለችው ክርስቲና፤ 2021 ላይ በሚካሄደው ውድድር መካፈል እንደምትፈልግም ተናግራለች።", "ቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020፡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው ውድድሮች የትኞቹ ናቸው? መቼስ ይካሄዳሉ? ባለፈው ሳምንት አርብ የተጀመረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በድምቀት መካሄዱን ቀጥሏል። በቶኪዮ ኦሊምፒክ 33 አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄዱ ሲሆን ኢትዮጵያም በአራት አይነት የስፖርት አይነቶች ማለትም በአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ውሃ ዋናና በቴኳንዶ ትሳተፋለች። በጉጉት በሚጠበቀው የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ለተሰንበት ጊደይ፤ ሹራ ቂጣታ፤ ሰለሞን ባረጋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ በሚወዳደሩባቸው ርቀቶች ሜዳሊያ ያስገኛሉ ተበሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው ውድድሮች የትኞቹ ናቸው? መቼስ ነው የሚካሄዱት? የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ነገ አርብ ሐምሌ 23 የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል የማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ሦስት ኢትዮጵያውን አትሌቶች ይሰለፋሉ። ተወዳዳሪዎቹ አትሌቶችም ታደሰ ታከለ፣ አብረሃም ስሜ እና ኃ/ማርያም አማረ ናቸው። የማጣሪያ ውድድሩ በሦስት ቡድን ተከፍሎ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ሌሊት 9፡30 እስከ 4፡05 ድረስ ይካሄዳል። የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በተመሳሳይ የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በስድስት ቡድን ተከፍሎ አርብ ከ10፡25 እስከ ንጋት 11፡05 ድረስ ይካሄዳል። ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩት አትሌቶች ሀብታም አለሙ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና ነጻነት ደስታ ናቸው። የሴቶች 5ሺህ ሜትር ማጣሪያ በዚሁ ቀን ሌላኛው የሴቶች 5ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር በሁለት ቡድን ተከፍሎ ይካሄዳል። የመጀመሪያው ቡድን የማጣሪያ ውድድሩን ቀን 7 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን ሁለተኛው ማጠሪያ ደግሞ 7፡26 ደቂቃ ሲል ይጀምራል። በ5ሺህ ውድድር ላይ ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን እነሱም ጉዳፍ ጸጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ሰምበሬ ተፈሪ ናቸው። ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ በፈረንሳይ በተካሄደ የ1ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላለች። በዚህ ምድብ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሰን ቀንደኛ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የወንዶች 10ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ነገ ከሚካሄዱት ውድድሮች እጅግ በጉጉት ከሚጠበቁት አንዱ የወንዶች 10ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ነው። ኢትዮጵያ በዚህ መስክ በሰለሞን ባረጋ፣ በዮሚፍ ቀጄልቻ እና በበሪሁ አረጋዊ የምትወከል ሲሆን ውድድሩም ከቀኑ 8፡30 ላይ እንደሚካሄድ የቶኪዮ ኦሊምፒክ መርሃ ግብር ላይ ተመልክቷል። ሰለሞን ባረጋ ከሁለት ዓመት በፊት በዶሃ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች የ5ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ በተመሳሳይ የውድድር መድረክ በ10 ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። ሰለሞን እና ዮሚፍ በኦሊምፒክ መድረክ ሲሳተፉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። ሌላኛው አትሌት በሪሁ አረጋዊ በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ሦስተኛ ሆኖ መጨረስ ችሏል። የወንዶች የ800 ሜትር ማጣሪያ ቅዳሜ ሌሊት ከ9፡50 እስከ 10፡30 ድረስ በስድስት ቡድኖች ተከፍሎ የወንዶች የ800 ሜትር ማጣሪያ ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ላይ ብቸኛው አትሌት መለሰ ንብረት ኢትዮጵያን ወክሎ ይወዳደራል። የሴቶች 800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ በተመሳሳይ የፊታችን ቅዳሜ የሴቶች 800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ ውድድር በሦስት ቡድኖች ተከፋፍሎ ይካሄዳል። የመጀመሪያውን ማጣሪያ ማለፍ የሚችሉ ከሆነ አትሌት ሀብታም አለሙ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና ነጻነት ደስታ የግማሽ ፍጻሜ ውድድሩ ተሳታፊ የሆናሉ። የሴቶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ እሁድ ለሰኞ አጥቢያ የሴቶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ሌሊት 3፡40 እስከ 10፡10 ድረስ በሦስት ቡድን ተከፍሎ ውድድሩ ይከናወናል። በዚህ ማጣሪያ ኢትዮጵያም በመቅደስ አበበ፣ በሎሚ ሙለታ እና በዘርፌ ወንድማገኝ ትወከላለች። የወንዶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ አትሌት መለሰ ንብረት የመጀመሪያውን የ800 ሜትር ማጣሪያ የሚያልፍ ከሆነ በዚሁ ቀን የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ያደርጋል። የ1500 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 26 ደግሞ የ1500 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ይደረጋል። በዚህም ኢትዮጵያውያኑ ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ለምለም ኃይሉ ይወዳደራሉ። ይህ የማጣሪያ ውድድር ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ለሊት 9፡35-10፡00 ድረስ ይካሄዳል። የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ታደሰ ታከለ፣ አብራሀም ስሜ እና ኃ/ማርያም አማረ የ3ሺህ ማጣሪያን የሚያልፉ ከሆነ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 9፡15 ላይ ለፍጻሜ ይወዳደራሉ። የሴቶች 5ሺህ ሜትር ፍጻሜ በጉጉት በሚጠበቀውና ሰኞ ቀን 9፡40 ሲል በሚደረገው የ5ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑ ጉዳፍ ጸጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ሰምበሬ ተፈሪ ማጣሪያውን ካለፉ ተጠባቂ አትሌቶች ይሆናሉ። ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ እንዲሁም ሲፋን ሐሰን ሌሎች ተጠባቂ አትሌቶች ናቸው። የወንዶች 1500 ሜትር ማጣሪያ የፊታችን ማክሰኞ የወንዶች 1500 ሜትር ማጣሪያ የሚደረግ ሲሆን ታደሰ ለሚ፣ ሳሙኤል አባተ እና ሳሙኤል ተፈራ አገራቸውን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ናቸው። ይህ ውድድር ማክሰኞ ለዕረቡ አጥቢያ ከለሊቱ 9 ሰዓት እስከ 9፡30 ድረስ በሦስት ቡድኖች ተከፋፍሎ የሚደረግ ይሆናል። የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ በተመሳሳይ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ በተመሳሳይ ቀን ይካሄዳል። በማጣሪያውም ጌትነት ዋለ፣ ንብረት መላክ እና ሚልኬሳ መንገሻ የሚሳተፉ ይሆናል። በሁለት ቡድን ተከፍሎ የሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከቀኑ 7 ሰዓት እና 7፡20 ላይ ይካሄዳል። የወንዶች 800 ሜትር ፍጻሜ የወንዶች 800 ሜትር ፍጻሜም የሚካሄደው ማክሰኞ ዕለት ይሆናል። አትሌት መለሰ ንብረት የመጀመሪያውን ዙር ማጣሪያ እና ግማሽ ፍጻሜን የሚያልፍ ከሆነ የፊታችን ማክሰኞ የ800 ሜትር ፍጻሜ ተወዳዳሪ ይሆናል። የሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ የሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ የፍጻሜ ውድድር ረቡዕ ዕለት የሚካሄደው ይሆናል። ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ለምለም ኃይሉ በዚህ ርቀት አገራቸውን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ናቸው። የሴቶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ አትሌት መቅደስ አበበ፣ ሎሚ ሙለታ እና ዘርፌ ወንድማገኝ ማጣሪያውን የሚያልፉ ከሆነ የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ። ውድድሩ ከቀኑ 8 ሰዓት ሲል ይጀምራል። የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ፍጻሜ አርብ ዕለት በጉጉት የሚጠበቀው የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ቀን 9 ሰዓት ላይ ይካሄዳል። አትሌት ጌትነት ዋለ፣ ንብረት መላክ እና ሚልኬሳ መንገሻ ማጣሪያውን አልፈው በ5ሺህ ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ላይ እንደሚኖሩ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። የሴቶች ማራቶን ቅዳሜ ጠዋት 1 ሰዓት ላይ የሴቶች ማራቶን ይካሄዳል። ኢትዮጵያውያኑ ትዕግስት ግርማ፣ ብርሀኔ ዲባባ እና ሮዛ ደረጄ ደግሞ ለአገራቸው ሜዳሊያ ለማስገኘት የሚፋለሙት አትሌቶች ናቸው። የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ቅዳሜ ከቀኑ 7፡45 ላይ የሴቶች 10ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል። በመድረኩም ኢትዮጵያ በአትሌት ለተሰንበት ጊደይ፣ ጽጌ ገ/ሰላማ እና ፀሐይ ገመቹ ትወከላለች። የ23 ዓመቷ ወጣት አትሌት ለተሰንበት ጊደይ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ክብረ ወሰን ባለቤት ስትሆን በቅርቡም የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን አሻሽላለች። በዚህ ውድድር የለተሰንበት ግደይ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሰን ፉክክር በበርካቶች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። የወንዶች ማራቶን በቀጣዩ ቀን እሁድ ነሐሴ 01/2013 ዓ.ም ደግሞ የወንዶች ማራቶን ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሏት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ ናቸው። አትሌት ሹራ ቂጣታ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በኦሊምፒክ የሚወዳደረው። አትሌት ሹራ \"በዚህ ውድድር ለአገርም ለግልም ወርቅ ማምጣት አለብን በሚል ነው እየተዘጋጀን ያለነው\" ብሎ ነበር ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። ከአንድ ዓመት በፊት በለንደን ማራቶን የኬንያውን ኢሉድ ኪፕቾጌን ያሸነፈው ሹራ፤ በቶኪዮ ኦሊምፒክም የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ከኪፕቾጌ ጋር ይወዳደራል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊው የማራቶን ሯጭ ሌሊሳ ዴሲሳ ከሁለት ዓመት በፊት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፉ ይታወሳል።", "በሩሲያ በእስር ላይ ያለችው አሜሪካዊት የቅርጫት ኳስ ኮከብ ባይደንን ተማፀነች በሩሲያ በእስር ላይ የምትገኘው አሜሪካዊት የቅርጫት ኳስ ኮከብ  ብሪትኒ ግሪነር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንዲረዷት በደብዳቤ ተማጸነች። ብሪትኒ በአደንዛዥ እፅ ክስ ሩሲያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ከዋለች ከአራት ወራት በላይ ተቆጥረዋል። ብሪትኒ ለባይደን በጻፈችውና ሰኞ ዕለት በደረሳቸው ደብዳቤ ላይ፣ የአሜሪካን ምድር ዳግም ላልረግጥ እችላለሁ የሚለውን ስጋቷን ገልጻለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፊኒክስ ሜርኩሪ የቅርጫት ኳስ ቡድን ተጫዋች የሆነችውን የብሪትኒንን ደብዳቤ እንዳነበቡት ዋይት ሐውስ አረጋግጧል። ሰኞ ዕለት የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ፣ ባይደን ብሪትኒ ግሪነርን ጨምሮ በውጭ አገራት ታግተው አሊያም ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በእስር ላይ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች መለቀቅ አለባቸው የሚል አቋም አላቸው ሲሉ ተናግረዋል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ያሉትን ሁሉ መንገዶች ተጠቅመው ብሪትኒን ወደ አገሯ ለመመለስ እየሰሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ብሪትኒ ለፕሬዝዳንት ባይደን የጻፈችው ደብዳቤ አብዛኛው ክፍል በምስጢር ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም፤ አንዳንድ ተቀንጭበው የወጡ ሃሳቦች በእስር ላይ ያለችበትን የአዕምሮ ጤና ሁኔታዋን ያሳያሉ ተብሏል። “እዚህ በሩሲያ እስር ቤት ተቀምጬ፣ ያለ ባለቤቴ፣ ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ ጥበቃ፣ ያለ ኦሊምፒክ ማሊያ እና ያለ ስኬት ብቻዬን ከሃሳቤ ጋር እየተሟገትኩ ነው ያለሁት። እዚህ ለዘላለም ልቆይ እችላለሁ ብዬ ፈርቻለሁ” ስትል ስጋቷን በደብዳቤዋ ላይ አስፍራለች። “ባለቤቴ፣ ቤተሰቦቼ፣ የቡድን አባሎቼ ናፍቀውኛል። ከዚህ በላይ ደግሞ አሁን ላይ በእኔ ምክንያት እየተሰቃዩ መሆኑን ማወቄ ደግሞ ጭንቀቴን አባብሶታል። እኔን ወደ ቤት ለመመለስ ለምታደርጉት ጥረት ክብር ይሰማኛል” ብላለች ብሪትኒ። ከዚህም በተጨማሪ ብሪትኒ ለፕሬዝዳንቱ በጻፈችውና በአሜሪካ የነጻነት ቀን መታሰቢያ ዕለት በደረሰው ደብዳቤ ላይ አባቷ በቬትናም የሰጡትን ወታደራዊ አገልግሎት አስታውሳለች። ፕሬዝዳንት ባይደን በሩሲያ በእስር ላይ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎችን እንዳይረሱም ብሪትኒ ጠይቃለች። “እባክዎን ሁላችንንም ወደ አገራችን ውሰዱን። ለመጀመሪያ ጊዜ ምርጫ የመረጥኩት በ2020 ነው ። የመረጥኩትም እርስዎን ነው። በእርስዎ እተማመናለሁ” ብላለች። ብሪትኒ በቁጥጥር ሥር የዋለችው እንደ አውሮፓውያኑ የካቲት 17 በሞስኮ፣ ሽረሜትየቮ አየር ማረፊያ ውስጥ የካናቢስ እጽ ዘይት ሻንጣዋ ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ ነበር። አሁን ላይ የፍርድ ሂደቷን እየተከታተለች ሲሆን ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች እስከ አስር ዓመት በሚደርስ እስራት ልትቀጣ ትችላለች። በሩሲያ ውስጥ በወንጀል ጉዳዮች ከተከሰሱት ውስጥ ከአንድ በመቶ የሚያንሱት ተከሳሾች ነጻ ናቸው። ሆኖም ነጻ ብትባልም ከአሜሪካ ፍርድ ቤቶች አሰራር በተለየ የሩሲያ መንግሥት ማንኛውንም ውሳኔ በመሻር ወደ እስር ቤት የመላክ ሥልጣን አለው። ሰኔ ወር ላይ የአሜሪካ ኮንግረንስ አባል የሆኑት ጆን ጋራሜንዲ “ብሪትኒ በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም እየተካሄደ ባለው የፖለቲካ ጦርነት መጠቀሚያ እንድትሆን አንፈልግም” ብለው ነበር። ሩሲያ ግን የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿ እስር “በአሜሪካ እና በሩሲያ ውጥረት የተነሳ አይደለም” ስትል አስተባብላለች።", "የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ግምት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ ይካሄዳሉ። የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ለዚህ ሳምንት ጨዋታዎች ግምቱን አካፍሏል። እንደ ሱቶን ከሆነ ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድ በሊቨርፑል እንደሚሸነፍ ገምቶ ነበር። ይህ የብዙዎች ግምት ቢሆንም ጨዋታውን ማንቸስተር አሸንፏል። “ቀለል አድርጌ ነበር ያሰብኳቸው። ዩናይትድ በጨዋታው ላይ ድንቅ ነበሩ። አሁን ዋናው ጥያቄ በዚሁ ይቀጥላሉ ወይ የሚለው ነው” ይላል። “አስገራሚ ሳምንታት ያለፉ ሲሆን ቡድኖችም ወጥ አቋም ማሳየት አልተቻላቸውም።” ለዚህ ሳምንትም ሱቶን የሊጉን ጨዋታዎች ግምት አዘጋጅቷል። ቅዳሜ ሳውዛምፕተን ከ ማንቸስተር ዩናይትድ ሳውዛምፕተን ባለፈው ሳምንት ከሌስተር ጋር በነበረው ጨዋታ መጀመሪያ ላይ ቢበለጥም የኋላ ኋላ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ችሏል። በመጨረሻም በማሸነፍ ሦስት ነጥቡን ማግኘት ችሏል። ለማንቸስተር ዩናይትድም ቀላል ተጋጣሚ አይሆኑም። ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ ራሱን አሻሽሎ ይቀርባል ብዬ አላሰብኩም ነበር። የብዙዎችም አስተሳሰብ ተመሳሳይ ነበር። በዚህ ጨዋታ ዩናይትድ ሦስት ነጥቡን ያሳካል። ግምት፡ 1-2 ብሬንትፎርድ ከ ኤቨርተን ኤቨርተን በተወሰነ ደረጃ ዕድለኛ አይደለም። ባለፈው ሳምንት ከኖቲንገሃም ፎረስ ጋር ብዙ ዕድል ቢፈጥሩም ማሸነፍ አልቻሉም። ዴማራይ ግራይ በጨዋታው ጥሩ በመንቀሳቀስ ጎል ቢያስቆጥርም ቡድኑ የአጥቂ ችግር አለበት። ብሬንትፎርድ ባለፈው ሳምንት በፉልሃም ተሸንፏል። በዚህ ሳምንት በሜዳው እንደመጫወቱ በጠባብ ውጤት ያሸንፋል። ግምት፡ 1-0 ** ብራይተን ከ ሊድስ ሊድስ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ከወዲሁ አስደንቆኛል። አዳዲስ ፈራሚዎቻቸው ጥሩ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ዓመት ሁለቱንም የሊግ ጨዋታቸውን አቻ አጠናቀዋል። ሁለቱም ጎል አስቆጥረው አቻ ይለያያሉ። ግምት፡1-1 ** ቼልሲ ከ ሌስተር ቼልሲ ከተቀናቃኛቸው ሌስተር ተከላካዩን ዌስሊ ፎፋናን ለማስፈርም የሚያደርጉት ጥረት እስከ ቅዳሜ የሚሳካ አይመስልም። ቼልሲ በኤላን ሮድ ከደረሰበት አስደንጋጭ ሽንፈት እንደሚያንሰራራ እገምታለሁ። በጨዋታው ሊድስ የበላይ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ቼልሲ ግን ተቀዛቅዞ ነበር ያመሸው። የቶማስ ቱሄል ቡድን ጎል አስቆጣሪ ችግር ቢኖርበትም ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 2-1 ** ሊቨርፑል ከ ብርንማውዝ ሊጉ ገና ረዥም ርቀት ቢቀረውም ሊቨርፑል በዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ማሳካት ይኖርበታል። አማካይ ስፍራ ላይ የፈጣሪ ተጫዋች ችግር ያለባቸው ሲሆን አጥቂው ዳርዊን ኑኔዝ በቅጣት አለመሰለፉም እንደጎዳቸው በዩናይትድ ጨዋታ ታይቷል። ወደ ድል ለመመለስ ደግሞ በሜዳቸው ከበርንማውዝ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ ዕድል ይዞላቸው መጥቷል። በርንማውዝ ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ሲቲ ቢሸነፍም ተከላካይ ክፍሉ ጠንካራ ነው። በዚህ ጨዋታ ሊቨርፑል ቀድሞ ጎል ማስቆጠር ይገባዋል። ግምት፡ 3-0 ** ማንቸስተር ሲቲ ከ ክሪስታል ፓላስ ክሪስታል ፓላስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲቲን በሜዳው ማሸነፍ ችሏል። ፓላስ በመልሶ ማጥቃት ጠንካራ ከሆኑ የሊጉ ክለቦች አንደኛው ቢሆንም ሲቲ ላይ አይሳካለትም። ኒውካስል ነጥብ ለማግኘት ከሲቲ ጋር ኣደረገው ፉክክር ጠንካራ ሲሆን ፓላስ ግን ይህንን ያደርጋል ብዬ አለሳብም። ጎል ግን ያስቆጥራል። ግምት፡ 3-1 ** አርሴናል ከ ፉልሃም አርሴናል ደጋፊዎች በቡድናቸው ተስፋ መሰነቅ ጀምረዋል። ጋብርኤል ጂሰስ ድንቅ አጀማመር ያደረገ ሲሆን አርሴናል እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ፉልሃም ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ ተገቢ የሆነ ድል አስመዝግቧል። ውድድር ዓመቱ ሲጀመር ማንም ባይገምትም ፉልሃም ጠንካራ መሆኑን እያሳየ ነው። የባለፈው ሳምንቱ ውጤታቸው ጥሩ ቢሆንም በዚህ ሳምንት በአርሴናል ይፈተናሉ። ግምት፡ 2-0 አስቶን ቪላ ከ ዌስት ሃም ሁለቱ ቡድኖች ውድድር ዓመቱን ተመሳሳይ መልክ ይዘው ነው የጀመሩት። አስቶን ቪላ ባለፈው ሳምንት ከክሪስታል ፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ሽንፈት ገጥሞታል። ኤቨርተንን ቢያሸንፉም ከበርንማውዝ ጋር በነበራቸው ጨዋታም በመሸነፋቸው የዚህን ሳምንት ጨዋታ ይጠብቃሉ። ዌስት ሃምም ውጤታማ መሆን አልቻለም። የመጀመሪያዎቹን ሦስት ጨዋታወች የተሸነፉ ሲሆን አሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬስም ጫና እየመጣባቸው ነው። ቡድናቸው ከፎረስት ጋር ጥሩ ቢጫወትም ውጤታማ አልሆኑም። ከብራይተን ጋር ጥሩ አልተጫወቱም። የተከላካይ መስመር ችግርም አለባቸው። ግምት፡ 1-1 ** ዎልቭስ ከ ኒውካስል ዎልቭስ ጎል ማስቆጠር እየከበደው ነው። ጥሩ ዕድል በመፍጠር እና ጥሩ ተጫዋቾችን በመያዝ በኩል ባይታሙም አፈጻጸም ላይ ችግር አለባቸው። ይህ በተደጋጋሚ የተባለ ነው። በዚህ ምክንያት ተንከር ብለው የሚጫወቱ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ ከተለያየው ኒውካስል ጠንካራ ፉክክር ይጠብቃቸዋል። አጨዋወታቸው፣ ወደ ፊት በከሚሄዱበት መንገድ እና ከማጥቃት ሂደታቸው አንጻር ኒውካስል ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1-2 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቶተንሃም በፎረስት አጀማመር ተደንቄያለሁ። ቡድኑ ከፍተኛ ገንዘብ ለተጫዋቾች ዝውውር ያወጣ መሆኑ መረሳት የለበትም። ስቲቭ ኩፐርን የመሰለ ጥሩ አሰልጣኝ ቢኖራቸውም አጨዋወታቸው ለስፐርስ የተመቸ ነው። በቶተንሃም ባልከፋም ከቼልሲ ነጥብ ተጋርተው ዎልቭስን በጠባብ ውጤት በማሸነፍ ጥሩ ውጤት አስመዝግበዋል። የፎረስት አጨዋወት ለኮንቴ ቡድን የሚመች ይመስለኛል። ግምት፡ 0-5", "አሜሪካዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች በሩሲያ የዘጠኝ ዓመት እስር ተፈረደባት ሩሲያ አሜሪካዊቷን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነር ለመልቀቅ ስምምነት ላይ እንድትደርስ አሜሪካ ጠየቀች። አደንዛዥ እጽ ይዛ ወደ ሩሲያ በመግባቷ የታሰረችው ብሪትኒ፣ በሩሲያ ፍርድ ቤት የዘጠኝ ዓመት እስራት ተፈርዶባታል። ሀለት ጊዜ የኦሎምፒክ ባለድል የሆነችው ቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ የካናቢስ ዘይት ይዛ መገኘቷን በፍርድ ቤት አምናለች። የዋይት ሀውስ ብሔራዊ ደኅንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ፣ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር የምትችልበት የስምምነት ሰነድ እንዳዘጋጀች ገልጸዋል። መገናኛ ብዙኃን እንደሚሉት፤ አሜሪካ ብሪትኒን በሩሲያዊው የመሣሪያ አዘዋዋሪ ልትለውጣት ትችላለች። “የሞት ነጋዴው” እየተባለ የሚጠራው ቪክተር ቦውት በአሜሪካ የ25 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። የእስረኛ ልውውጡ ይሄንን መሣሪያ አዘዋዋሪ በቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ እንዲሁም በቀድሞው የአሜሪካ ባሕር ኃይል ፖል ዌላን የሚቀይር ነው። የአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ እና አየርላንድ ፓስፓርት ያለው ግለሰቡ፣ በስለላ ተከሶ 16 ዓመት እስር በሩሲያ ፍርድ ቤት ተፈርዶበታል። የዋይት ሀውስ ብሔራዊ ደኅንነት ቃል አቀባይ ጆን፤ ሁለቱ አሜሪካውያን ያለአግባብ እንደታሰሩና መለቀቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል። “ያቀረብነውን የስምምነት ሐሳብ ከሳምንታት በፊት መቀበል ነበረባቸው” ብለዋል። ሮይተርስ እንደሚለው፣ ሩሲያ ስምምነቱን ያልተቀበለችው ጀርመን እስር ቤት ያለው ቫዳም ክራስኮቭ በእስረኛ ልውውጡ እንዲካተት ስለምትፈልግ ነው። የ31 ዓመቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ “ስህተት መሥራቴን አምናለሁ። ሕግ ለመጣስ ብዬ አልነበረም” ብላለች። ምርጥ ከሚባሉ ተጫዋቾች አንዷ ስትሆን ወደ ሩሲያ ያቀናችው ለቅርጫት ኳስ ጨዋታ ነበር። አውሮፕላን ማረፊያ ሳለች ሻንጣዋ ውስጥ የካናቢስ ዘይት ተይዞ ነው በቁጥጥር ሥር የዋለችው። ታስራ ብዙም ሳይቆይ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ተነሳ። ብሪትኒም በአሜሪካ እና በሩሲያ የዲፕሎማሲ ሽኩቻ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች። ጠበቆቿ ለሩሲያ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚሉ ገልጸዋል። የብሪትኒ ቡድን ፊኒክስ ሜርኩሪ፣ ኮኒክቲክት ሰን ቡድንን ሲገጥም ለብሪትኒ ያለውን ድጋፍ ለማሳየት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾቹ ለ42 ሰከንድ በጥሞና አሳልፈዋል። መታሰቢያነቱ ብሪትኒ ለምትለብሰው 42 ቁጥር መለያ ነው። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፍርድ ቤቱን ብይን “ተቀባይነት የሌለው” ብለውታል። “ሩሲያ በአፋጣኝ ለቃት ብሪትኒ ከባለቤቷ፣ ከጓደኞቿ፣ ከቡድን ጓደኞቿና ከወዳጆቿ ጋር እንድትቀላቀል እጠይቃለሁ” ሲሉም አቋማቸውን ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን “ሩሲያም ትሁን ሌሎች አገራት ያልተገባ እስር የሚፈጽሙ ከሆነ ወደተለያዩ አገራት እየሄዱ የሚሠሩ ሰዎች ደኅንነት ስጋት ውስጥ ይወድቃል” ብለዋል። ብሊንከን ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ሳምንት በስልክ ተነጋግረዋል። አሁን ሁለቱም ለደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ውይይት ካምቦዲያ ይገኛሉ።", "በኳታር የዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች ቢራ እንዳይሸጥ ታገደ የዓለም ዋንጫ ውድድሮች በሚካሄድባቸው የኳታር ስታዲየሞች ቢራን ጨምሮ ማንኛውም የአልኮል መጠጦች እንዳይሸጥ ታገደ። ፊፋ ውድድሩ ሊጀመር ሁለት ቀናት ሲቀረው ፖሊሲውንም ቀይሮ የአልኮል ሽያጭን አግዷል። የአልኮል ሽያጭ በሙስሊም አገራት ውስጥ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት ቢሆንም “በስታዲየሞች ውስጥ በተመረጡ ቦታዎች” እንዲቀርብ ተወስኖ ነበር። የዓለም ዋንጫ ውድድር ኅዳር 11/2015 ዓ.ም. የሚጀመር ሲሆን፣ በመክፈቻው ዕለትም አስተናጋጇ ኳታር ከኢኳዶር ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የፊፋ ዋነኛ ስፖንሰር የሆነው ቡድዌይዘር የተባለው የቢራ ጠማቂው ድርጅት ኤቢ ኢንቤቭ ስር ሲሆን በዓለም ዋንጫ ላይ ቢራ የመሸጥ ብቸኛ መብት ነበረው። “በአዘጋጇ አገር ባለሥልጣናት እና በፊፋ መካከል የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የአልኮል መጠጦች ሽያጭ በፊፋ የደጋፊዎች ፌስቲቫል፣ በሌሎች የደጋፊዎች መዳረሻዎች እና ፍቃድ በተሰጣቸው ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል። “የቢራ ሽያጭ በኳታር የዓለም ዋንጫ ስታዲየሞችም ሆነ ግቢው ውስጥ አይቻልም” ይላል የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል መግለጫ። ሆኖም በሁሉም የኳታር የዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች ላይ የቢራ ጣዕም ያለውና አልኮል የሌለው በድ ዜሮ ሽያጭ እንደተለመደው ይከናወናል ተብሏል። መግለጫው አክሎም “የአስተናጋጇ አገር ባለሥልጣናት እና ፊፋ ስታዲየሞች እና አካባቢዎቻቸው ለሁሉም ደጋፊዎች አስደሳች እንዲሆኑ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ” ብሏል። “የውድድሩ አዘጋጆች በኳታር በሚደረገው የዓለም ዋንጫ 2022 ሁሉንም ደጋፊዎች ባማከለ መልኩ ለምናደርጋቸው የጋራ ውሳኔዎች ኤቢ ኢንቤቭ ተረድቶ የሚያደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ያደንቃሉ” ብሏል። ቡድዌይዘር በበኩሉ በዛሬው ዕለት በትዊተር ገጹ “ይህ ትንሽ ያሳፍራል” የሚል መልዕክት ቢለጥፍም ወዲያውኑ ሰርዞታል። የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማኅበር (ኤፍኤስኤ) ለአብዛኞቹ ደጋፊዎች የቢራ ሽያጭ የተከለከለበትን ጊዜ ተችቷል።", "ኡጋንዳ የጠፉት ኤርትራውያን ኳስ ተጫዋቾች ስጋት ላይ ነን አሉ ኡጋንዳ ውስጥ የጠፉት አራት ኤርትራውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ስጋት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፈው ወር በደቡብ ምዕራብ ኡጋንዳ ጂንጋ ከተማ ከሆቴላቸው የጠፉት የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን አባላት ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦብናልም ብለዋል። የእግር ኳስ ቡድኑን ትተው ኡጋንዳ ውስጥ በመጥፋታቸው ድረ ገጽ ላይ ማስፈራሪያዎች እየደረሷቸው እንደሆነ ተጫዋቾቹ ገልጸዋል። የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ውድድር ግማሽ ፍጻሜ ላይ መሰናበቱ ይታወሳል። • አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ ጠፉ • ኢትዮጵያና ግብፅ በአሜሪካ ለውይይት እንጂ ለድርድር አይገናኙም ተባለ • የአማራ ክልል ረዳት ፖሊስ ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነ ተጫዋቾቹ ታፍነው ወደ ኤርትራ ሊወሰዱ እንደሚችሉ ስጋት እንደገባቸው ገልጸው፤ ከኡጋንዳ አስወጡን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ከተጫዋቾቹ አንዱ፤ \"ስለኛ ግድ የሚሰጠው አካል ካለ ከዚህ አገር እንዲያወጣን እንለምናለን። በየሳምንቱ ከቤት ቤት እየቀየርን፣ እየተሽሎኮሎክን እየኖርን ነው\" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ተጫዋቾቹ ወደ ኤርትራ ከተመለሱ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ገልጸዋል። አሜሪካዊ ጠበቃቸው ኪምበርሊ ሞተሊ እንዳሉት፤ ተጫዋቾቹ ኡጋንዳ ውስጥ እየተፈለጉ እንደሆነ ሰምተዋል። በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተራድኦ ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) ጥገኝነት ቢጠይቁም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙም ጠበቃዋ ተናግረዋል። ተጫዋቾቹ እንዳሉት፤ ሰዎች ስለሚያውቋቸውና ሊለይዋቸው ስለሚችሉ ከቦታ ቦታ በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻሉም። ሕይወታቸውን እየገፉ ያሉትም ከበጎ ፍቃደኞች በሚያገኙት እርዳታ ነው። ኤርትራ በተሳተፈችባቸው ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ኤርትራውያን ተጫዋቾች ሲጠፉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።", "የሊቨርፑሉ ሳዲዮ ማኔ በቫይረሱ በመያዙ እራሱን ለይቶ እያቆየ ነው ተባለ የሊቨርፑል እና የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋቹ ሳዲዮ ማኔ በኮሮናቫይረስ መያዙን ክለቡ አረጋገጠ። ይህንንም ተከትሎ ማኔ እራሱን ለይቶ እያቆየ እንደሚገኝ ክለቡ አስታውቋል። የማኔ ኮቪድ-19 ውጤት የተሰማው አዲሱ የሊቨርፑል ፈራሚው ቲአጎ አልካንትራ በኮሮናቫይረሱ መያዙ ይፋ ከተደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው። ማኔ \"መለስተኛ የበሽታው ምልክት ከማሳየት ውጪ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል\" ሲል ሊቨርፑል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ማኔ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ሊቨርፑል ከአርሰናል በነበራቸው የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያ ለክለቡ ተሰልፎ ጎልም አስቆጥሮ እንደነበረ ይታወሳል። ከሁለት ቀናት በፊት በተካሄደው እና ሊቨርፑል እና አርሰናል ባገናኘው የካራባኦ ካፕ ግጥሚያ ላይ ደግሞ ማኔ የሊቨርፑል ቡድን አባላት ውስጥ አልተካተተም ነበር። ማኔ የመንግሥት ምክረ ሃሳብን በመከተል ከበሽታው እስኪያገግም ድረስ እራሱን ለይቶ ይቆያል ሲል ሊቨርፑል የእግር ኳስ ክለብ አስታውቋል። በአዲሱ የውድድር ዘመን ለሊቨርፑል ሶስት ጊዜ ኳስን ከመረብ ማገናኘት የቻለው ሳዲዮ ማኔ በኮቪድ በመያዙ ምክንያት ቢያንስ አንድ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ያመልጠዋል ተብሏል። ሰኞ ዕለት ፕሪሚየር ሊጉ በሊጉ የሚጫወቱ 10 ተጫዋቾች በቫይረሱ ተይዘዋል በማለት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።", "በዓለም ዋንጫ ታሪክ ታላቅ የተባሉት የውድድሩ አስር አሸናፊ አገራት እነማን ናቸው? ታላቁ የእግር ኳስ መድረክ የዓለም ዋንጫ በአየራት ዓመቱ እየመጣ የማይረሳ ክስተት ትቶ ያልፋል። ነገር ግን አስካሁን በተካሄዱት ዓለም ዋንጫ ውድድሮች ታሪክ ታላቁ ድል የማነው? ጋሪ ሊኒከር፣ አለን ሺረር እና ሚካህ ሪካርድስ እነሆ አስሩ ድንቅ የዓለም ዋንጫ ድሎች እነዚህ ናቸው ይላሉ። አርጀንቲና ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ያነሳችው በፈረንጆቹ 1978 ነበር። የማራዶና ቡድን በወቅቱ ኔዘርላንድስን 3 ለ 1 በማሸነፍ ታላቁን የእግር ኳስ ዋንጫ ማንሳት የቻለው በማሪዮ ኬምፔስ እና በዳኒኤል ቤርቶኒ ጎሎች ነው። እንግሊዛዊው እግር ኳስ ተጫዋች ሊኒከር በወቅቱ ማሪዮ ኬምፔስ ብዙ ጎሎች አስቆጥሮ የወርቅ ጫማ ሲቀበል ያስታውሳል። አርጀንቲና ዋንጫውን ለማንሳት ከኔዘርላንድስ የገጠማት ፈተና ቀላል የሚባል አልነበረም። የወቅቱ የዓለም ዋንጫ ባለቤት ፈረንሳይ ክሮሺያን 4 ለ 2 አሸንፋ ነው ዋንጫውን ያነሳችው። ሩሲያ ባዘጋጀችው በዚህ የዓለም ዋንጫ በአሠልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ የተመራው ቡድን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ፣ አልፎም በዙር 16 አርጀንቲናን 4 ለ 3 በመርታት ነው ለፍፃሜው የደረሰው። አለን ሺረር የ2018ቱ የፈረንሳይ ቡድን በጣም ጠንካራ እንደነበር የሚረሳ አይደለም፤ ዋንጫውን ማንሳትም ይገባቸው ነበር ይላል። ሚካህ ሪካርድስ በበኩሉ በፈረንሳይ ቡድን ውስጥ ከበረኛው አንስቶ እስከ አጥቂው መልካም ብቃት ላይ እንደነበሩ ያወሳል። ሊነከርም በሙያ አጋሮቹ ሐሳብ ይስማማል። ጣልያን በ1982 የዓለም ዋንጫን በማንሳት ከብራዚል ጋር እኩል ሦስት ጊዜ ዋንጫውን የግሏ ያደረገች ሆና ተመዝግባለች። ጣልያን በወቅቱ ስፔን ማድሪድ ላይ በተስተናገደው የፍፃሜ ጨዋታ ምዕራብ ጀርመንን 3 ለ 1 በመርታት ነው ባለድል የሆነችው። በጊዜው የጣልያን ግብ ጠባቂ እና አምበል የነበረው የ40 ዓመቱ ዲኖ ዞፍ በዕድሜ ትልቁ የዓለም ዋንጫ ተሰላፊ ሆኖ ታሪክ ሠርቷል። በ1982 የወርቅ ጫማውን የወሰደው ፓውሎ ሮሲ ነበር። ሺረር እንደሚያስታውሰው ጣልያን በጊዜው የመጀሪያዎቹን ሦስት ጨዋታዎች አቻ ከወጣች በኋላ አርጀንቲና እና ብራዚልን በመርታት ነው ለፍፃሜው የደረሰችው። ቲኪ-ቲካ በተሰኘው የእግር ኳስ ስልት የሚታወቀው የ2010 የስፔን ብሔራዊ ቡድን የተመልካቾችን ቀልብ የሳበ ነበር። ስፔን ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋን በስዊትዘርላንድ ተሸንፋ ነው የጀመረችው። በፍፃሜው በተጨማሪ ሰዓት ኔዘርላንድስን 1 ለ 0 በመርታት የዋንጫ ባለድል የሆነችው ስፔን አንድሬስ ኢኒዬስታ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ነው። ሺረር እንደሚያስታውሰው ስፔን ከመጀመሪያ ጨዋታቸው በኋላ በጣም ልዩ ሆነው ነው የቀረቡት። ምዕራብ ጀመርን ከምሥራቁ ክፍል ጋር ከመዋሃዷ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያነሳችው የዓለም ዋንጫ ሲሆን፣ ከዚያ ቀድም ሁለት ጊዜ ዋንጫ አንስታለች። በፍፃሜው ከአርጀንቲና የገጠመችው ምዕራብ ጀርመን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት ነው ዋንጫውን ከፍ ያደረግችው። ምዕራብ ጀርመን ለዋንጫ ለመድረስ በነበረው የግማሽ ፍፃሜ ፍልሚያ እንግሊዝን በፍፁም ቅጣት ምት መርታቷን ሊኒከር ያስታውሳል። “ጨዋታውን እንግሊዝ ልታሸንፍ እንደምትችል ሳስብ ምናልባት ለፍፃሜ ደርሰንስ ቢሆን ኖሮ ብዬ አስባለሁ” ይላል ሊኒከር። ፈረንሳይ በ1998 ያዘጋጀችውን የዓለም ዋንጫ ራሷ በማንሳት ለመጀመሪያ ጊዜ ባለድል መሆኗን ብዙዎች ያስታውሱታል። በፍፃሜው ከተቆጠሩት ሦስት ጎሎች ሁለቱን ዚነዲን ዚዳን ነበር ማስቆጠር የቻለው። ፈረንሳይ በዚህ የዓለም ዋንጫ በአንድም ጨዋታ ሽንፈት አላጋጠማትም። ነገር ግን በሩብ ፍፃሜው እና በዙር 16 ከ90 ደቂቃ አልፎ ተጨማሪ 30 ደቂቃ እንዲሁም የፍፁም ቅጣት ምት አስፈልጓት ነበር። አርጀንቲና ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማንሳት የቻለችው በ1986 ነበር። በሜክሲኮ የተዘጋጀውን የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና ምዕራብ ጀርመንን 3 ለ 2 በመርታት ዋንጫውን አንስታለች። ይህ የዓለም ዋንጫ የማይዘነጋው ማራዶና ‘የእግዚያብሔር እጅ’ የተሰኘችውን ጎል በሩብ ፍፃሜው እንግሊዝ ላይ ያስቆጠረበት በመሆኑ ነው። ጋሪ ሊኒከር በወቅቱ ስድስት ጎሎች በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ አጠናቋል። ሊኒከር እንደሚያስታውሰው አርጀንቲና፤ ማራዶና ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ድንቅ የነበሩ ተጫዋቾች የነበሩበት ቡድን ይዛ ነው የመጣችው። የማራዶና ተዓምር ግን የሚረሳ አልነበረም ይላል ሊኒከር። ብራዚል አምስተኛ የዓለም ዋንጫዋን ያነሳችበት ዓመት ነበር 2002። በውድድሩ ሰባቱንም ጨዋታዎች በመርታት ዋንጫውን ያነሱት ብራዚሎች አሠልጣኝ የነበሩት ሉዊዝ ፊሊፔ ስኮላሪ ነበሩ። በአምበሉ ካፉ እየተመሩ አምስተኛ ዋንጫቸውን ያጣጣሙት ብራዚሎች በፍፃሜው ጀርመንን 2 ለምንም ረትተዋል። ጃፓን ባዘጋጀችው በዚህ የዓለም ዋንጫ ሮናልዲንሆ እንግሊዝ ላይ ያስቆጠራት የቅጣት ምት የምትታወስ ናት። እንግሊዝ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያነሳችው በ1966 ነበር። በወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ አልፍ ራምሴ፤ አምበሉ ደግሞ ቦቢ ሙር ነበሩ። በገዛ አገሯ የተጫወተችው እንግሊዝ በፍፃሜው ምዕራብ ጀርመንን 4 ለ 2 በመርታት ዋንጫውን ከፍ አድርጋለች። ሊኒከር፤ “ምናልባትም ምርጡ እንግሊዛዊ አጥቂ ነው ብዬ የማምነው ጂሚ ግሪቭስ በወቅቱ ድንቅ ነበር” ይላል። ብራዚል ሦስተኛ የዓለም ዋንጫውን ያነሳችው በአሠልጣኝ ካርሎስ አልቤርቶ እና በአምበሉ ፔሌ እየተመራች ነበር። የወቅቱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ምናልባትም የምንም ጊዜም ታላቁ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ አስተያየቶች ይሰማሉ። ሁሉንም ጨዋታዎች አሸንፈው ለፍፃሜ የደረሱት ብራዚሎች ጣልያንን 4 ለ 1 በመርታት ዋንጫውን ከፍ አድርገዋል። በርካታ ያልተጠበቁ ነገሮች የታዩበት በኳታር የተስተናገደው የዓለም ዋንጫስ ስንተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጥ ይሆን?", "ሎዛ አበራ በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦችን አስቆጠረች ለማልታው ቢርኪርካራ እግር ኳስ ቡድን የምትጫወተው ኢትዮጵያዊቷ እግር ኳሰኛ ሎዛ አበራ ቡድኗ ትናንት ከሂበርኒያንስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሰባት ግቦችን በስሟ ማስመዝገብ ችላለች። ጨዋታው በቢርኪርካራ 17 ለምንም አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን ቡድኑ በ19 ነጥብ ሊጉን በአንደኛነት እየመራው ይገኛል። ሰባት ልጆች ላፈሩት እናት እና አባቷ አምስተኛ ልጅ የሆነችው ሎዛ ተወልዳ ያደገችው የከንባታ ጠምባሮ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ዱራሜ ነው። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' • የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ባደገችበት ሠፈር ካሉ ወንድ እኩዮቿ ጋር እየተጋፋች ኳስን ተጫውታለች። የሎዛ ፕሮፌሽናል ኳስ ተጫዋችነት ጉዞ የተጀመረው የከንባታ ዞንን ወክላ ስትጫወት ባይዋት መልማዮች አማካይነት ነው። ብዙም ሳትቆይ ሎዛ የሐዋሳ ሴቶች እግር ኳስ ቡድንን ተቀላቀለች። ከሐዋሳ ጋር ዋንጫ ባታነሳም እዚያ በቆየችባቸው ሁለት ተከታታይ ዓመታት የክለቡ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች። ሐዋሳን ከለቀቀች በኋላ በደደቢት አራት ዓመታትን ያሳለፈችው ሎዛ በሁሉም ዓመታት በተከታታይ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች።። ለሶስት ተከታታይ ዓመት ደግሞ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮን ሆናለች ከደደቢት ጋር። በአሁኑ ሰአት በማልታ ደሴት ከፍተኛ ሊግ ላይ ለሚሳተፈው ቢርኪርካራ የምትጫወተው ሎዛ በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልእክት ''ዛሬ በነበረን ጨዋታ በማልታ ሊግ ላይ በአንድ ጨዋታ ብቻ ሰባት ጎል በማስቆጠር ሌላ ታሪክ መፃፍ እና መስራት ስለቻልኩ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ላይ በአንድ ጨዋታ ብቻ ዘጠኝ ጎል አግብቼ ነበር'' ብላለች።", "አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ ጠፉ አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ መጥፋታቸው ታወቀ። ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ እግር ኳስ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ኡጋንዳ ካቀኑት ተጫዋቾች መካከል አራቱ ወደ ሆቴላቸው ያልተመለሱ ሲሆን፤ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ በተዘጋጀው ልምምድ ላይም አልተገኙም ተብሏል። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ • የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው የቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ከምንጮቹ ማረጋገጥ እንደቻለው ከሆነ አራቱም ተጫዋቾች በኡጋንዳ የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበዋል። የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ የሆኑት ኤማብል ሃቢማና የተጫዋቾቹን መጥፋት ማረጋገጣቸውን የኡጋንዳ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን፤ እስካሁን የት እንደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል። ዋና ጸሃፊው ''አራቱም ተጫዋቾች ከማረፊያቸው ጠፍተዋል። ከክስተቱ በኋላ በሆቴሉ አካባቢ ያለውን ጥበቃ አጠናክረናል። ውድድሩ በጥሩ መንፈስ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ነው የምንፈልገው'' ማለታቸውን ደይሊ ሞኒተር የተባለው የኡጋንዳ ጋዜጣ ዘግቧል። የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ጥሩ እየተጫወተ የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ ከሰአት ላይ በግማሽ ፍጻሜ ከኬንያ አቻው ጋር ተጫውቶ 1 ለምንም ተሸንፏል። በሴካፋ ውድድር ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ጎል አግቢነቱን እየመራ የሚገኘው ኤርትራዊው ማወል ተስፋይ በጉዳት ምክንያት በጨዋታው ላይ እንደማይሰለፍ ታውቋል። ምናልባትም ጥገኝነት ከጠየቁት አራት ተጫዋቾች መካከል ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል። የተጫዋቾቹ መጥፋት ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል እስካሁን ባይታወቅም በውድድሩ እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች ተጫዋቾቹ ሊጠፉ የቻሉት \"ጉዳት አጋጥሞናል\" ብለው በሆቴላቸው ከቀሩ በኋላ መሆኑንም ደይሊ ሞኒተር ዘግቧል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ በቀሪ 14 ተጫዋቾች ውድድሩን የሚጨርሱ ሲሆን፤ የቀሩት ተጫዋቾች ግን በህምም ምክንያት ሊገኙ አልቻሉም ሲሉ ተደምጠዋል። በተመሳሳይ እ.አ.አ. በ2015 አሥር የዋና ብሔራዊ ቡድኑ አባላት ወደ ቦትስዋና ከሄዱ በኋላ አንመለስም ማለታቸው ይታወሳል። በ2013ትም ዘጠኝ የሚሆኑ የቡድኑ አባላትና አሰልጣኙም ጭምር ኬንያ ውስጥ ተሰውረው ነበር።", "ታይሮን ሚንግስ፡ ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን መጠጥ ቀጅነት፤ ቤት አሻሻጭ፤ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን። ከ10 ዓመት በፊት ሳውዝሃምፕተኖች ቀጫጫ ነው በማለት ያሰናበቱት ወጣት ዛሬ [እሁድ ኅዳር 7] ደግሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ ይጫወታል፤ ታይሮን ሚንግስ። ታድያ በእነዚህ 10 ዓመታት ብዙ አሳልፏል። ለጠጪዎች መጠጥ ቀድቷል። የ100 ፓውንድ መኪናውን እያሽከረከረ ሰዎች ከባንክ የቤት መሥሪያ ብድር እንዲወስዱ አስማምቷል። ኢፕስዊች ታውን ለተሰኘው ክለብ መጫወት ፈልጎ ሳይታመም አሞኞል ብሎ ከሥራ ቀርቷል በሚል ቅጣት ድርሶበታል። ከአየርላንድ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ጋር ቡጢ ቀረሽ ቁርሾ ነበረው። ሚንግስ አሁን ለሚጫወትበት አስቶን ቪላ የፈረመው በውሰት ከመጣበት ቦርንመዝ ነው። የ26 ዓመቱ ተከላካይ ዘንድሮ የተቀላቀለው ፕሪሚዬር ሊግ ብዙ የከበደው አይመስልም። 195 ሴንቲሜትር የሚረዝመው ተከላካዩ ሚንግስ በፕሪሚዬር ሊግ ብዙ ኳሶችን ከግብ ክልሉ በማራቅ [ክሊራንስ] ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የአካዳሚ ጓደኛው አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን ነገሮች ተመቻችተውለት ታላላቅ ክለቦችን እየቀያየረ አሁን ሊቨርፑል ሲደርስ ሚንግስ ግን ብዙ ክለቦች አንፈልግህም እያሉ አባረውታል። ብሪስቶል ሮቨርስ አታዋጣንም ብለው ያባረሩት ሚንግስ ወደ ተማረበት ት/ቤት ተመልሶ መጫወት ጀመረ። በወቅቱ አንድ ባር ውስጥ መጠጥ ቀጅ ነበር። ቀን ቀን ደግሞ ለባንክ ቤት በኮሚሽን ተቀጥሮ የቤት ኪራይ ብድር ያስማማ ነበር። ታድያ በዚህ ጊዜ ያልተለየችው በደጉ ዘመን የሸመታት የ100 ፓውንድ [በአሁኑ ገበያ 3,700 ብር ገደማ] መኪናው ነች። ከዚያ ኢፕስዊች ታውን ለሙከራ ጊዜ ብሎ ወሰደው። ነገር ግን የወቅቱ የቡድኑ አሠልጣኝ ከነበሩት ሚክ ማካርቲ ጋር ሊስማማ አልቻለም። ቢሆንም ችሎታውን ያስተዋሉት አሠልጣኝ ለ18 ወራት አስፈረሙት። ይህ የሆነው ከዛሬ ስድስት ዓመታት በፊት ነበር። ፊርማውን ካኖረ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢፕስዊች ተሰለፈ። ከዚያ በኋላ ባሉት 18 ጨዋታዎችም ይህን ያህል የመሰለፍ ዕድል አላገኘም። የወቅቱ የክለብ ጓደኞቹ 'ለምን አልተሰልፍኩም?' ብሎ ከአሠልጣኞች ጋር ይጋጭ ነበር ይሉታል። 2015 ላይ ለቦርንመዝ ፈረመ፤ በ8 ሚሊዮን ፓውንድ። ነገር ግን የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማድረግ በገባ በ6 ደቂቃ ውስጥ ተጎድቶ ወጣ። ለ17 ወራትም ምንም ዓይነት ጨዋታ ማድረግ አልቻለም ነበር። ይሄኔ ነው ቦርንመዝ ለአስቶን ቪላ አሳልፈው በውሰት የሰጠው። ቪላ ፕሪሚዬር ሊጉን እንዲቀላቀል ሚንግስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ክለቡ በቋሚነት እንዲያስፈርመውም ሆነ። ሚንግስ ለአንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መጫወት እንደሚፈልግ እና ህልሙ እውን እንደሚሆንም በዙሪያው ላሉ ሰዎች ይነግራቸው ነበር። እነሆ ህልሙ እውን ሆኖ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተመርጧል። እንግሊዝ ዛሬ ምሽት ከኮሶቮ ጋር በምታደርገው ጨዋታም ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል። አልፈልግህም ያለው ሳውዝሃምፕተን በዚህ ዓመት በጣም ብዙ ጎል ተቆጥሮበታል። በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ 19ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት። ብዙዎች እንደው ሳውዝሃምፕተኖች ታይሮን ሚንግስን ቀጫጫ ነው ብለው ማሰናበታቸው ይቆጫቸው ይሆን? ሲሉ ይጠየቃሉ። ሚንግስ ግን ምንም ዓይነት ቁጭትም ቂምም የለበትም።", "ጣሊያን በደረሰ የስለት ጥቃት የአርሰናሉ ተጫዋች ፓብሎ ማሪ ጉዳት ደረሰበት በጣሊያኗ ሚላን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል በትንሹ አምስት የሚሆኑት ቆስለዋል። አንዳንዶቹ ከፍተኛ ጉዳት እንዳስተናገዱ ፖሊስ አስታውቋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል በውሰት ጣሊያን በመጫወት ላይ የሚገኘው ፓብሎ ማሪ ይገኝበታል። አሳጎ በሚባል ስፋራ በደረሰው ጉዳት አንድ የ30 ዓመት የሱፐር ማርኬት ገንዘብ ተቀባይ ሕይወቱ አልፏል። የ46 ዓመቱ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል። ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብረተኝነት ጋር አይያያዝም ብሏል። ግለሰቡ የአእምሮ ጤና ችግር እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን ስለቱን ከሱፐርማርኬቱ መደርደሪያ ወስዶ መጠቀሙን ተናግሯል። ግለሰቡ በከተማዋ በሚገኘው ካርፉር ሱፐርማርኬት ጥቃቱን መፈጸሙ ተነግሯል። ጥቃቱ ሲፈጸም የደንገጡ ሰዎች ከአካባቢው እየጮኹ ሲሸሹ ታይተዋል። ብዙ ሰዎች ተጋግዘው ግለሰቡን ለመያዝ የቻሉ ሲሆን ፖሊስ ሲመጣም ማስረከባቸው ታውቋል። ጀርባው ላይ በስለት የተወጋው ስፔናዊው የ29 ዓመት ተከላካይ ማሪ ለሕይወቱ የሚያሰጋ ነገር አለመኖሩ ተጠቁሟል። ወኪሉ አርቱሮ ካናሌስ በበኩላቸው ወሳኝ የሰውነት ክፍሉ ላይ ጉዳት አለመድረሱን እና ራሱን እንደሚያውቅ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ማሪ ከባለቤቱ እና ወንድ ልጃቸው ጋር ለግብይት ወጥቶ እንደነበር በውስት የሚጫወትለት የሞንዛ ክልብ ሥራ አስፈጻሚ አድሪያኖ ጋሊያኒ ተናግረዋል። “ልጁን ተሽከርካሪ እቃ መያዣ ላይ አድርጎ ሚስቱ ደግሞ ከጎኑ ነበረች። ምንም ነገር አላየም ነበር።” ብለዋል ጋሊያኒ። “በሚያሳዝን ሁኔታ ጥቃት አድራሹ የሌላ ሰው አንገት ላይ ጥቃት ሲፈጽም ተመልክቷል። የተፈጸመውን ሁሉ በመመልከቱ በጣም የሚረበሽ ስሜት ነገር ነው” ሲሉ አክለዋል። ጀርባው ላይ የደረሰበት ጥቃት ጠለቅ ላይ ቁስል ቢፈጥርም ሕይወቱ አደጋ ላይ ካለመሆኑም በላይ  በፍጥነት እንደሚያገግምም ተስፋቸውን ገልጸዋል። ማሪ ለአርሰናል የፈረመው ከብራዚሉ ፍላሚንጎ እአአ በ2020 ነበር። 19 ጨዋታዎችን ለመድፈኞቹ ከተጫወተ በኋላ ለጣሊያኑ ሞንዛ ክለብ በውሰት ፈርሟል። “አሁን መስማቴ ነው። ኤዱ [የአርሴናል ቴክኒካል ዳይሬክተር] ከቤተሰቦቹ ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ አውቃለሁ። ” ሲል የአርሴናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግሯል።", "ሮናልዲንሆ በ800 ሺህ ዶላር ዋስ ሆቴል ውስጥ እንዲታሠር ታዘዘ ብራዚላዊው የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆ ጎቹ ፓራጓይ ከሚገኘው እሥር ቤት ተለቆ ውሳኔ እስኪሰጠው ድረስ ሆቴል ውስጥ እንዲሰነብት ታዟል። ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ውስጥ ሃሰተኛ ፓስፖርትና ሌሎች ሰነዶች ይዘው ተገኝተዋል በሚል በፖሊስ ተይዘው ከአንድ ወር በላይ እሥር ቤት ውስጥ መሰንበታቸው አይዘነጋም። ወንድማማቾቹ ከዚህ በፊት እንዲለቀቁ ይግባኝ ቢያመለክቱም ሰሚ ጠፍቶ ነበር። አሁን ግን እያንዳንዳቸው 800 ሺህ ዶላር ዋስ ጠርተው የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን የሚገኝ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ውስጥ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተላልፏል። የ40 ዓመቱ የእግር ኳስ ሰው ሮናልዲንሆና ወንድሙ አሲስ እኛ ሃሰተኛ ሰነድ መሆኑን አላወቅንም ነበር ሲሉ ይሟገታሉ። ጠበቃቸውም የወንድማማቾቹ እሥር ሕገ-ወጥ ነው ሲል ይከራከራል። • ብራዚላዊው ሮናልዲንሆ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀረበ • ሮናሊዲኒሆ ሃሰተኛ ፓስፖርት ፓራጓይ ውስጥ በፖሊስ ተያዘ ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛ ገንዘቡ ጫን ያለ እንዲሆን የተደረገው ግለሰቦቹ ሃገር ጥለው እንዳይጠፉ በማሰብ ነው ብለዋል። ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ አቅንቶ የነበረው መፅሐፉን ለማስተዋወቅና አቅመ ደካማ ሕፃናትን የሚረዳ ድርጅትን ለመደገፍ ነው ተብሏል። ሮናልዲንሆ የ2005 ባለንደኦር [የዓለም ኮከብ ተጫዋች ሽልማት] አሸናፊ ነበር። አልፎም በግሪጎሪ አቆጣጠር 2002 ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችሏል። ተጫዋቾቹ በኮከብነት ዘመኑ ለስፔኑ ባርሴሎና፣ ለጣልያኑ ክለብ ኤሲ-ሚላንና ለፈረንሳዩ ፒኤስጂ ተጫዋቷል። የእግር ኳስ ዕድሜው ሲጃጅ ደግሞ ወደ ትውልድ ሃገሩ ብራዚል በማቅናት ጫማዬን ሰቅያለሁ ሲል የዛሬ አምስት ዓመት ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።" ]
[ 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 3, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5 ]
[ "አርጀንቲና: የ22ኛው የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ድራማዊ ነው በተባለለት የፍጻሜ ጨዋታ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ታላቁን የዓለማችን የእግር ኳስ ውድድር አሸናፊ ሆነ። ልብ በሚያንጠለጥል ሁኔታ አርጀንቲና በመሪነት ጀምራ ፈረንሳይ አቻ እየሆነች ጨዋታው ከመደበኛው ሰዓት ወደ ጭማሪ ሰዓት ዘልቆ ነው በመለያ ምት የተለየው። በአረቡ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር የተስተናገደውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አርጀንቲና ያነሳችው ተቀናቃኟን ፈረንሳይን ያሸነፈችው በመደበኛ ሰዓት ጨዋታው 2 ለ 2 ተጠናቆ በተጨማሪ ሰዓት ሁለቱም ቡድኖች ተጨማሪ ጎል በማስቆጠራቸው በመለያ ምት 4 ለ 2 ከተለያዩ በኋላ ነው። ለአንድ ወር ያህል በኳታር የተስተናገደው የዓለም ዋንጫ ዛሬ በፍጻሜው ጨዋታ ሲቋጭ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በዓለም የእግር ኳስ መድረክ ላይ የበላይነቱን አስምስክሯል። በፍጻሜው ጨዋታ መሪነቱን የያዘችው አርጀንቲና ስትሆን ሁለት ለምንም በሆነ ውጤት ቡድኖቹ ለእረፍት የወጡ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ግብ ሊዮኔል ሜሲ በፍጽም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር፣ ሁለተኛው ጎል ደግሞ በዲ ማሪያ ተቆጥሮ ነው የመጀመሪያው አጋማሽ የተጠናቀቀው። ከእረፍት መልስ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከመመራት ለመውጣት ጥረት አድርጎ በኮከቡ ኪሊያን ምባፔ አማካይነት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው ሙሉው የጨዋታ ጊዜ ተጠናቋል። በተጨማሪ ሰዓት ሁለቱም ቡድኖች ለዋንጫ የሚያበቃቸውን ግብ ለማስቆጠር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቆይተው፣ አርጀንቲናዊው ኮከብ ሜሲ ለእራሱ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል። ጨዋታው በአርጀንቲና የበላይነት ሊጠናቀቅ ነው ተብሎ በተጠበቀባቸው የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ኪሊያን ምባፔ በጨዋታው ሦስተኛውን ግብ በማስቆጠር ፈረንሳይን አቻ ያደረገውን ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው ወደ መለያ ምቶች ተሸጋግሯል። በዚህም አርጀንቲና 4 ለ 2 በመሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ሆናለች። በዓለም ዋንጫው ውድድር ከተለያዩ የምድራችን ክፍል ካሉ አገራት የተወጣጡ 30 ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉባቸው የዛሬውን ጨምሮ 64 ጨዋታዎች ተደርገዋል። ከምድብ ጨዋታ አንስቶ ታላቅ ፉክክር እና የተለየ ክስተቶችን ያስተናገደው የኳታር የዓለም ዋንጫ በመጨረሻም አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ እና ደቡብ አሜሪካዊቷ አርጀንቲ ለዋንጫ ደርሰው ዛሬ ውድድሩ ተቋጭቷል። ከዚህ ቀደም በተካሄዱት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ለበርካታ ጊዜያት የተሳተፉት ፈረንሳይ እና አርጀንቲና ሁለት፣ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ለማግኘት ችለዋል። አርጅንቲና የአሁኑን ውድድር አሸናፊ በመሆኗ ዋንጫውን አምስት ጊዜ ካነሳችው ከብራዚል እና አራት ጊዜ ካሸነፈችው ከጣሊያን በመከተል ን በዓለም ዋንጫ ታሪክ ሦስተኛ ደረጃን ለመያዝ ችላለች።", "ቀነኒሳ ያሰብኩን ያላሳካሁት በጤና እክልና በአየር ንብረት ምክንያት ነው አለ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን ቀድሞ ያሰበውን ሳያሳካ የቀረው በጤና እክል እና በአየር ንብረት ምክንያት መሆኑን ተናገረ። አትሌት ቀነኒሳ ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር አቅዶ የነበረ ቢሆንም ውድድሩን ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በወንዶች ውድድሩን ኢትዮጵያዊው ጉዬ አዶላ በ2፡05፡45 አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ኬኒያዊው ቤትዌል ዬጎን ቀነኒሳ በቀለን አስክትሎ በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል። ቀነኒሳ ከሁለት ዓመት በፊት እአአ 2019 በተካሄደው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ለመሻሻል ሁለት ሰኮንዶች ብቻ ቀርተውት ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል። ከውድድሩ በኋላ ቀነኒሳ ለቢቢሲ እንደተናገረው በበርሊን ከተማ የነበረው የአየር ሁኔታ ሞቃት በመሆኑ በውድድሩ ላይ በፈለገው ፍጥነት መሄድ እንዳልቻለ ገልጿል። \"ከስምንት ወር በፊት በኮቪድ ታምሜ ነበር\" ያለው አትሌት ቀነኒሳ፤ በሕመሙ ምክንያት ለአንድ ወር ያህል ልምምድ ሳያደርግ መቆየቱ ያሰበውን እንዳያሳካ እንዳደረገው ተናግሯል። \"ከዚያ ሕመም አገግሜ ተመልሼ ይሄን ውጤት ማስመዝገቤ ለእኔ ጥሩ ነው። ምክንያቱም ከሁለት ዓመት በኋላ ነው ማራቶን ላይ የተወዳደርኩት\" በማለት በበርሊኑ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውን በጥሩ ጎኑ አንስቷል። ቀነኒሳ \"ውድድር እስከሆነ ድረስ ያጋጥማል። ለቀጣይ ደግሞ በደንብ ተዘጋችቼ ጥሩ ውጤት አስመዘግባለሁ ብዬ ገምታለሁ\" ብሏል። አትሌት ቀነኒሳ ከስድስት ሳምንታት በኋላ በሚካሄደው የኒው ዮርክ ማራቶን ተሳታፊ እንደሚሆን ቀደም ሲል ይፋ ተደርጓል።", "ስፖርት፡ የታዋቂው ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን ጫማ በ23 ሚሊዮን ብር በጨረታ ተሸጠ ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን የተጫማው ጫማ 615 ሺህ ዶላር (23 ሚሊዮን ብር በሚገመት) በጨረታ ተሸጧል። በዚህ ሳምንት በበይነ መረብ በነበረው ጨረታ ላይ ናይክ ኤይር ጆርዳን 1 የተባለው የስፖርተኛው ጫማ መሸጡም ተገልጿል። ጫማውም በቺካጎ ቡልስ ቡድን ይጫወት በነበረበት ወቅት በጎርጎሳውያኑ 1985 ያጠለቀው ነው ተብሏል። በዚህ ጫማም ወደላይ በመዝለል በርካታ ኳሶችን በመረቡ በማስቆጠርም በታሪካዊነቱ የተመዘገበ ነው። በርካታ ስፖርታዊና የስነ ጥበብ ጨረታዎችን በማካሄድ የሚታወቀው ክርስቲስ የተባለው ኩባንያ እስካሁን ድረስ ዘጠኝ የማይክል ጆርዳን ጫማዎችን ሸጧል። እነዚህ ጫማዎችም ማይክል ጆርዳን ለአስራ አራት አመታት የነገሰበትን የቺካጎ ቡልስ ቡድን ቆይታውን ለመዘከርም ነው። ጫማው ስታዲየም ጉድስ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ንብረት ሲሆን፤ ከማይክል ጆርዳን ታሪካዊ ጫማዎች ውስጥ ምርጡም ነው ተብሏል። ሁሉም ጫማዎች ማይክልን ስፖንሰር ያደርገው በነበረው ናይኪ የአልባሳትና ጫማ አምራች ኩባንያ የተመረቱ ናቸው። ብርቅና ድንቅ የተባለውን ይህንን ጫማ ጨምሮ ሌሎች ጫማዎችን መሰብሰብ የሚፈልጉ ስላሉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስም እየሸመቱ መሆናቸውንም ኩባንያው አስታውቋል። ከዚህ ጫማም በተጨማሪ በጎርጎሳውያኑ 1992 ኦሎምፒክስ ላይ አሜሪካን ለድል ያበቃትን ጨዋታ የተጫወተብትን ኤይር ጆርዳን 7 በ11 ሺህ 500 ዶላር (413 ሺህ ብር) ተሸጧል። ሌሎች ስብስቦችም እንዲሁ በ21 ሺህ 500 ዶላርና (772 ሺህ ብር)፣ 8 ሺህ 750 ዶላር (314 ሺህ) ለሽያጭ ቀርበዋል። በገበያው ላይ ያለው ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜም እየጨመረ መሆኑንም ኩባንያው አመላክቷል። በቅርጫት ኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ማይክል ጆርዳን የቅርጫት ንጉስና ድንቅ ተጫዋችም ተብሎ ይሞካሸል። በአለም ስፓርትም ዘንድ ከፍተኛ ዝናን የተጎናፀፈው ማይክል በተለይም በጎርጎሳውያኑ 1980ዎቹና 90ዎቹ የቅርጫት ኳስ ስፖርትን በአለም አቀፉ መድረክ በማስተዋወቅ ረገድም ሚናን በመጫወቱም ስሙ ይወሳል። በቅርቡ በስፖርተኛው ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጠነው 'ዘ ላስት ዳንስ' የሚል ርዕስ የተሰጠውም ተከታታይ ፊልም በኔትፍሊክስ መውጣቱን ተከትሎ የማይክል ጆርዳን ዝናም እንደገና እየተነሳ ይመስላል።", "የኳታር የዓለም ዋንጫ፡ በሞት ምድብ ስፔን እና ጀርመን ተገናኙ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ትናንት አርብ መጋቢት 23/2014 ዓ.ም. ምሽት ተከናውኗል። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአረብ አገር የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ በ28 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል። በምድብ አንድ (A) አዘጋጇ ኳታር፣ ከኔዘርላንድስ፣ ሴኔጋልና ኢኳዶር ጋር ተደልድላለች። በምድብ ሁለት (B) እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና ኢራን የተመደቡ ሲሆን ከዌልስ፣ ስኮትላንድ አልያም ዩክሬን አንዳቸው አራተኛ ቡድን ሆነው ምድብ ሁለትን ይቀላቀላሉ። በሩሲያ ወረራ ምክንያት ዩክሬን ከስኮትላንድ ጋር የነበራትን የጥሎ ማለፍ ውድድር ማከናወን ባለመቻሏ ጨዋታዎቹ ከሁለት ወራት በኋላ እንዲካሄዱ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል። በምድብ ሶስት (C) ደግሞ አርጀንቲና፣ ሜክሲኮ፣ ፖላንድ እና ሳኡዲ አረቢያ ተቀምጠዋል። በምድብ አራት (D) ያለፈው ዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ፈረንሳይ፣ ዴንማርክ፣ ቱኒዚያ እንዲሁም ከፔሩ፣ አውስትራሊያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አሸናፊ ከምድባቸው ለማለፍ ይፋለማሉ። ምድብ አምስት (E) በርካቶች የሞት ምድብ ብለውታል። በዚህ ምድብ ስፔን እና ጀርመን ተፋጠዋል። ሦስተኛዋ አገር ጃፓን ስትሆን፤ የኮስታሪካ እና ኒውዚላንድ አሸናፊ በዚህ ምድብ ተደልድለዋል። ምድብ ስድስት (F) ደግሞ ቤልጂየም፣ ያለፈው የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ ክሮሺያ፣ ሞሮኮና ካናዳን የያዘ ሲሆን በምድብ አባት (G) ብራዚል፣ ስዊዘርላንድ፣ ሰርቢያና ካሜሩን ተመድበዋል። በመጨረሻው ምድብ ስምንት (H) ደግሞ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አገር ፖርቹጋል፣ ዩራጓይ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጋና አንድ ላይ ተመድበዋል። የኳታር የዓለም ዋንጫ ሕዳር 12/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታህሳስ 9/2015 የሚቆይ ሲሆን ተሳታፊዎቹ 32 ቡድኖች ለ28 ቀናት ይፋለማሉ። ከዚህ በኋላ በዓለም ዋንጫው የሚሳተፉ ቡድኖች ቁጥር ወደ 48 ከፍ እንደሚል ፊፋ ያስታወቀ ሲሆን የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ ነው 32 ቡድኖችን ብቻ የሚያሳትፈው። ያለፈውን የዓለም ዋንጫ ያሸነፈችው ፈረንሳይ በኳታሩም የዓለም ዋንጫ ሊሳካላት እንደሚችል ከፍተኛ ግምት የተሰጣት ቢሆንም በአውሮፓውያኑ 1962 ብራዚል ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን ካነሳች በኋላ ማንም አገር በተከታታይ ዋንጫ ባለማንሳቱ ፈረንሳይ በኳታር ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃታል ተብሏል። ብራዚልና አርጀንቲን ከምድባቸው እንደሚያልፉ ከወዲሁ የሚጠበቅ ሲሆን ሴኔጋል ደግሞ ከሌሎቹ የአፍሪካ አገራት በተሻለ ረጅም ርቀት የመጓዝ ተስፋ ተጥሎባታል። ስፔንና ጀርመንን አንድ ላይ ባደረገው ምድብ አምስትም ቢሆን ትልቅ ፉክክር እንደሚኖርበት ይጠበቃል። ኳታር ለዚህኛው የዓለም ዋንጫ እጅግ የተዋቡና ዘመናዊ ስታዲየሞችን የገነባች ሲሆን በአጠቃላይ ስምንት ስታዲየሞችን ለውድድሩ ማካሄጃነት ትጠቀምባቸዋለች። ከእነዚህ ስታዲየሞች ትልቁ በሌሴይል ከተማ የሚገኘው ሉሴይክ አይኮኒክ ስታዲየም 80ሺህ ተመልካቾችን ያለምንም ችግር ማስተናገድ ይችላል። አነስተኛ የሚባለው አል ዋክራህ አል ጃኑብ የተሰኘው ስታዲየም ሲሆን የመያዝ አቅሙ ደግሞ 40 ሺህ ነው። የመክፈቻው ቀን ወደ ስታዲየም ገብተው ጨዋታዎችን መከታተል የሚፈልጉ ሰዎች ለቲኬት እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ዋጋ ከ42 እስከ 472 ፓውንድ ድረስ ነው። ለምድብ ጨዋታዎች ደግሞ ከ8 ፓውንድ እስከ 168 ፓውንድ ድረስ የሚከፈል ሲሆን የመጨረሻውን የዋንጫ ጨዋታ ማየት የፈለገ ሰው ደግሞ ከ157 ፓውንድ እስከ 1227 ፓውንድ ድረስ መክፈል ግድ ይለዋል።", "ሱፐር ሊግ፡ 'ታላላቆቹ ስድስት' የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ተስማሙ አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም በአውሮፓ ሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ተስማሙ። የአውሮፓ እግር ኳስን ባልተጠበቀ መልኩ የነቀነቀው ይህ ውሳኔ በርካቶችን ያስገረመ ሲሆን ከጣልያን ኤሲ ሚላን፣ ኢንተር ሚላን እና ጁቬንቱስ በሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ወስነዋል። ከስፔን ደግሞ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይቀላቀላሉ። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደገለጸው መስራች ቡድኖቹ የሳምንቱ ግማሽ ላይ ጨዋታዎቹን ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን የአገራቸው ሊግ ጨዋታ ላይ ግን መሳተፋቸውን አያቆሙም። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ አክሎም' \"እቅዱ ተግባራዊ መደረግ ሲችል የመጀመሪያው የውድድር ዓመት ወዲያውኑ ይጀመራል። ሶስት ተጨማሪ ቡድኖች ደግሞ ሊጉን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል'' ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የወንዶቹ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ውድድር ከተጀመረ በኋላ የሴቶች ሱፐር ሊግም እንደሚጀመር ተገልጿል። እሁድ ዕለት የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ዜና መሰማቱን ተከትሎ የዩናይትግ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውሳኔውን አውግዘውታል። የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪው ፊፋ በበኩሉ ቀደም ብሎ ለመሰል ውድድሮች እውቅና እንደማይሰጥና በውድድሩ የሚሳተፉ ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫ ላይ ላይሳተፉ እንደሚችሉ አስታውቋል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ዜና ከተሰማ በኋላ ፊፋ \"ለእግር ኳስ ሲባል በዚህ ውሳኔ ላይ የተሳተፉት አካላት በሙል የተረጋጋ፣ ጠቃሚና ሁሉንም የሚጠቅም ውይይት ሊያደርጉ ይገባል\" ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርም ትናንት ባወጣው መግለጫ በአውሮፓ ሱፐር ሊግ የሚሳተፉ ተጫዋቾች ከሁሉም የአገር ውስጥ ውድድሮች ሊታገዱ እንደሚችሉ ያስታወቀ ሲሆን በአውሮፓም ሆነ በዓለም መድረክ ከብሔራዊ ቡድን ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጿል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ደግሞ በመግለጫው \"ወደፊት መስራች ክለቦቹ ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና ፊፋ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ'' ብሏል። ሊጉ 20 ተሳታፊ ብድኖችን የሚያካትት ሲሆን 12ቱ መስራች ክለቦች እና እስካሁን ስማቸው ያልተጠቀሰው ሶስት ክለቦች በፍጥነት ይቀላቀላሉ። ከአገር ውስጥ የሊግ ውድድሮች ደግሞ አምስት ቡድኖች ተወዳድረው የአውሮፓ ሱፐር ሊግን ይቀላቀላሉ። በእቅዱ መሰረት የአውሮፓ ሱፐር ሊግ በየዓመቱ ነሀሴ ወር ላይ የሚመጅር ሲሆን ጨዋታዎቹም የሳምንቱ አጋማሽ ላይ ይደረጋሉ። ተሳታፊዎቹ 20 ቡድኖችም በሁለት ምድቦች ተከፍለው በደርሶ መልስ ጨዋታ ይፋለማሉ። ከሁለቱ ምድቦች ከአንድ እስከ ሶስት ሆነው የሚጨርሱት ቡድኖች ለእሩብ ፍጻሜ የሚያልፉ ሲሆን አራተኛና አምስተኛዎቹ ደግሞ እርስ በርስ ተጋጥመው አሸናፊው እሩብ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደሚለው ይህ ውድድር ከአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በተሻ መልኩ ገንዘብ የሚያስገኝ ሲሆን ተሳታፊ ክለቦችም ጠቀም ያለ ትርፍ ያገኙበታል።", "ጋና በታዳጊ ተጫዋቾች እድሜ ማጭበርበር እግድ ተጣለባት ጋና ከ17 ዓመት በታች የዕግር ኳስ ተጫዋቾችን ዕድሜ በማጭበርበር የውድድር እገዳ እና የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት ተጣለባት። ጋና ከ17 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾቿን ዕድሜ ማጭበርበሯ ተረጋግጧል። በዚህ ምክንያትም የውድድር እገዳ እና የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት ተጥሎባታል። ቅጣቱን ውድቅ ለማስደረግ ጋና ይግባኝ ለማለት እየተሰናዳች ነው። ባለፈው የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ጋና ከሞሮኮ ባደረገችው ጨዋታ በመለያ ምት ተሸንፋ ነበር። ከጨዋታው በኋላ አሸናፊው የሞሮኮ ቡድን በጋና ስብስብ ላይ የዕድሜ ጥያቄ በማቅረብ ክስ መስርተው ነበር። ሞርኮ ቢያንስ ሁለት ተጫዋቾች ከዕድሜው ገደብ በላይ መሆናቸውን ባቀረበችው ክስ ጠቁማለች። ክሱን የተመለከተው ካፍ ጋና ጥፋተኛ መሆኗን አረጋግጫለሁ ብሏል። በመሆኑም ጋና በቀጣዮቹ ሁለት የማጣሪያ ውድድሮች እንዳትሳተፍ እና የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት እንድትከፍል ካፍ በይኖባታል። የጋና ስፖርት ፌደሬሽን ጉዳዩን አስመልክቶ ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። አንድ ከፍተኛ የጋና የስፖርት ኮሚሽን ባለስልጣን ለቢቢሲ አፍሪካ ስፖርት “ክሱ ሲጀመር የመከላከያ ደብዳቤ ጽፈናል” ብለዋል። “እኛ ካፍ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔውን እንደሚቀለብስ እርግጠኞች ነን” ብለዋል ባለስልጣኑ። ጋና የወጣት ተጫዋቾችን ዕድሜ በማጭበርበር ስትከሰስ ይህ የመጀመሪያ አይደለም። እአአ 2014 ጋና ከካሜሮን ጋር ባደረገችው የወንዶች ከ17 ዓመት በታች ጨዋታ ዕድሜ ማጭበርበሯ በመረጋገጡ ከ2015ቱ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ታግዳለች። በዚህም ምክንያት ኒጀር ላይ በተካሄደው ዝግጅት ጋናን በመተካት ማዕከላዊ አፍሪካ እንድትሳተፍ ተደርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የካሜሮን እግር ኳስ ፌደሬሽን በ44 ተጫዋቾች ላይ የቀረበውን ክስ እየመረመረ ነው። ተጨዋቾቹ የቀረበባቸው ክስ ዕድሜያቸውን እና ማንነታቸውን ደብቀዋል በሚል ነው። በታዳጊዎች እና በዋናው ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋች ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በርካታ የክለብ ፕሬዝዳንቶችም ማጭበርበሩ ውስጥ አሉበት በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። አንድ የካሜሮን እግር ኳስ ፌደሬሽን ባለስልጣን እንዳሉት የዕድሜ ማጭበርበር ክስ ውሳኔ እስከ አርብ የሚጠናቀቅ ሲሆን ጥፋተኛ የተባሉት እስከ 6 ወር እገዳ ይጣልባቸዋል። የዕድሜ ማጭበርበር እና ማንነትን መደበቅ በተለይም በታችኛው ዕድሜ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች በአፍሪካ ትልቅ ችግር ሆኖ ቢቆይም አቤቱታ መስማቱ የተለመደ አልነበረም። የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማሕበራት ፌደሬሽን ፊፋ ከ17 ዓመት በታች ተጫዋቾችን ትክክለኛ ዕድሜ ለማስላት በ2017 ናይጄሪያ ውስጥ የኤምአርአይ ምርመራ ጀምሯል።", "የብራዚል እና አርጀንቲና ጨዋታ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተቋረጠ ትናንት እሁድ ዕለት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ብራዚል እና አርጀንቲና ሲያደርጉት የነበረው ጨዋታ አንዳንድ ተጫዋቾች የኮቪድ-19 መመሪያዎችን ተላልፈዋል በሚል እንዲቋረጥ ተደረገ። ሶስት የአርጀንቲና ተጫዋቾች የለይቶ ማቆያ መመሪያዎችን ተላልፈዋል በሚል የብራዚል ጤና ኃላፊዎች ጥያቄ መሠረት ዳኞች ጨዋታው በተጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እንዲቋረጥ ወስነዋል። የዳኞቹ ውሳኔ የተላለፈው ጨዋታው ከመካሄዱ አራት ሰዓታት በፊት የብራዚል የጤና ኃላፊዎች አራት እንግሊዝ ውስጥ የሚጫወቱ የአርጀንቲና ቡድን አባላት ለይቶ ማቆያ መግባት አለባቸው ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ምንም እንኳን የብራዚል ባለስልጣናት የትኞቹ ተጫዋቾች እንደሆኑ በስም ባይገልጹም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሚጫወቱት ኤሚሊያኖ ቡዌንዳ እና ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ከአስቶን ቪላ እንዲሁም ጂዮቫኒ ሎሴልሶ እና ክርስቲያን ሮሜሮ ከቶተንሀም ናቸው። ከእነዚህ ተጫዋቾች ደግሞ ማርቲኔዝ፣ ሎ ሴልሶ እና ሮሜሮ ሳኦ ፖሎ በተደረገው ጨዋታ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ መግባት ችለው ነበር። እስካሁን ድረስ የተቋረጠው ጨዋታ መቼ እንደሚካሄድ ምንም የተባለ ነገር የሌለ ሲሆን የአርጀንቲና ተጫዋቾች የፊታችን አርብ ከቦሊቪያ ለሚያደርጉት ሌላኛው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ጉዟቸውን ያደርጋሉ። ፊፋ በበኩሉ ጨዋታው መቋረጡን ያረጋገጠ ሲሆን ወደፊት ደግሞ ቀጣይ እርምጃዎችና መረጃዎች ይፋ እንደሚደረጉ አስታውቋል። የቀድሞው የባርሴሎና የአሁኑ የፒኤስጂ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ጨዋታው ከተቋረጠ በኋላ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን መፍትሄ ለመፈለግ ሲነጋገር ታይቷል። ጨዋታው ከተቋረጥ ከአንድ ሰዓት በኋላ የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል የሆነው 'ኮንሜቦል' ባወጣው መግለጫ የዕለቱ ዳኛ ባስተላለፉት ውሳኔ መሰረት የብራዚል እና የአርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ መቋረጡን ይፋ አድርጓል። \"የዕለቱ ዳኛ እና የጨዋታ ኮሚሽነሩ ለፊፋ የዲሲፕሊን ኦሚቴ ሙሉ ሪፖርት ያቀርባሉ። በዚህም በቀጣይ ምን እንደሚደረግ ይወሰናል። እነዚህ አካሄዶች አሁን ላይ ካለው የኮቪድ መመሪያ ጋር የተጣጣሙ ናቸው'' ብሏል በመግለጫው። በብራዚል ሕግ መሰረት ወደ አገሪቱ መግባት የሚፈልግ ሰው ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቆይታ አድርጎ ከነበረ ብራዚል ከደረሰ በኋላ ለ14 ቀናት እራሱን ለይቶ ማቆየት አለበት። \"አራቱ ተጫዋቾች ብራዚል ከደረሱ በኋላ እራሳቸውን ለ14 ቀናት እንዲያገሉ ተነግሯቸው ነበር። ነገር ግን ይህንን መመሪያ አልተከተሉም። በቀጥታ ወደ ስታዲየም በመሄድ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር ተቀላቅለዋል። በዚህም በርካታ መመሪያዎችን ነው የጣሱት'' ብለዋል የብራዚል የጤና ጉዳዮች ተቆጣጣሪው አንቶኒዮ ባራ ቶሬስ። የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ በበኩላቸው ጨዋታው ከመካሄዱ በፊት ቀድሞ መፍትሄ ማግኘት አለመቻሉ በጣም እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማህበር ደግሞ ቡድኑ ከሶስት ቀናት በፊት ብራዚል መድረሱን እና ሁሉንም የኮቪድ-19 መመሪያዎች ማክበሩን ገልጿል። የብራዚል እግር ኳስ ኮንፌደሬሽንም ቢሆን በዚሁ ውሳኔ ደስተኛ አለመሆኑን ገልጿል። በመግለጫውም የጤና ኃላፊዎቹ እርምጃውን የወሰዱበት ሰአት አላስፈላጊ እንደሆነ አስታውቋል።", "'የአሜሪካዊ ፉትቦል' አሰልጣኝ ቡድናቸው በሰፊ ውጤት በማሸነፉ ተቀጡ አሜሪካዊያን 'ፉትቦል' እያሉ የሚጠሩት ስፖርት አሰልጣኝ የሆኑት ግለሰብ ቡድናቸው ተቀናቃኙን 61 ለ 13 በማሸነፉ ለጊዜው ከሥራ ታግደዋል። የአሜሪካዋ ሎንግ አይላንድ ከተማ ትምህርት ቤት ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ሮብ ሼቨር በከፍተኛ ውጤት በማሸነፍ የከተማይቱን ሕግ ጥሰዋል ተብለው ነው የታገዱት። ሕጉ አሸናፊ ቡድን ከ40 በላይ ነጥብ ካስቆጠረ የአሸናፊው ቡድን አሠልጣኝ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ ያዛል። ይህ ሕጉ ከወጣ ሦስት ዓመት ሆኖታል። ዓላማው ደግሞ ስፖርታዊ ጨዋነትን ማስረፅ ነው። አሰልጣኝ ሼቨር በዚህ ሕግ የተቀጡ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ናቸው። የተሸናፊው ቡድን አሰልጣኝ እኔ በውጤቱም ሆነ በጨዋታው ምንም ቅሬታ አልተሰማኝም፤ አሰልጣኙም ቢሆን ምንም ስህተት አልፈፀሙም ሲሉ የሙያ አጋራቸውን ተከላክለዋል። አጣሪ ኮሚቴው ፊት ቀርበው ለምን ቡድንዎ በሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ዝም ብለው ተመለከቱ? ቢያንስ ሁለተኛ ቡድንዎን አያጫውቱም ነበር ወይ? ተብለው የተጠየቁት አሰልጣኝ ሼቨር አጥጋቢ ምላሽ አልሰጡም ተብለዋል። አሰልጣኙ ቅጣቱ ተገቢ አይደለም ብለው ቢከራከሩም ኮሚቴው አንድ ጨዋታ ሜዳ እንዳይገቡ ሲል በይኖባቸዋል። ቅጣቱ ብዘዎችን ቢያስገርምም ወጣቶች በከፋ ውጤት ቅስማቸው እንዳይሰበር ስለሚያደርግ ተገቢ ነው ብለው የተከራከሩም አልጠፉም። የአንድ ጨዋታ ቅጣት የተላለፈባቸው አሰልጣኝ ሼቨር የቡድናቸውን ቀጣይ ጨዋታ በአካል ተገኝተው መታደም እንዳይችሉ ታግደዋል።", "ሴኔጋል፣ ኔዘርላንድ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ወደ ቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ዙር ማለፋቸውን አረጋገጡ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ወደ ጥሎ ማለፉ የተሸጋገሩ የምድብ አንድ እና ሁለት ቡድኖች ትላንት ማክሰኞ ምሽት በተደረጉ ጨዋታዎች ተለዩ። ሴኔጋል፣ ኔዘርላንድ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ለቀጣዩ ዙር መብቃታቸውን አረጋገጠዋል። ሴኔጋል ለሁለተኛ ጊዜ ለጥሎ ማለፉ መብቃቷን ያረጋገጠችው ኢኳዶርን በካሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው። ኢስማሊአ ሳር ከፍጹም ቅጣት ምት አገሩን ቀዳሚ ያደረገች ኳስ በ44ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳረፈ። በሁለተኛው አጋማሽ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ያደረጉት ኢኳዶሮች በሞይሰስ ካሲዬዶ አማካይንት አቻ ለመሆን በቅተዋል። ከሦስት ደቂቃ በኋላ የሴኔጋሉ አምበል ካሊዱ ኩሊባሊ ሁለተኛዋን ጎል በማስቆጠር አገሩን ቀዳሚ አደረገ። ጨዋታው በዚሁ በመጠናቀቁ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ሴኔጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ አገር ሆናለች። በዚሁ ምድብ አስተናጋጇ ኳታር እና ኔዘርላንድም በአል ባይት ስታዲየም ተገናኝተዋል። ቀድማ ከውድድሩ ውጪ መሆኗን ያረጋገጠችው ኳታር ሦስተኛ ተከታታይ ጨዋታዋን ተሸንፋለች። ኔዘርላንድ 2 ለ 0 ስታሸንፍ ጎሎቹን ኮዲ ጋክፖ እና ፍራንኪ ዲ ዮንግ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። በዚህም ኔዘርላንድ ምድቧን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ሴኔጋል ሁለተኛ ለመሆን በቅታለች። ምሽት ላይ ደግሞ የምድብ ሁለት ጨዋታዎች ተከናውነዋል። ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ጨዋታ ነበር። ጨዋታውን ዩናይትድ ስቴትስ 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችላለች። ብቸኛዋን ጎል ክርስቲያን ፑሊሲች አስቆጥሯል። አቻ መውጣት ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፋት ኢራን ዕድሉን ሳትጠቀምበት ቀርታለች። በዚሁ ምድብ በተደረገ ሌላ ጨዋታ እንግሊዝ ዌልስን 3 ለ 0 አሸንፋለች። ማርከስ ራሽፎርድ ለእንግሊዝ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር፣ ቀሪዋን ፊል ፎደን ከመረብ አሳርፏል። በዚህም እንግሊዝ በሰባት ነጥብ ምድቧን በመምራት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። አሜሪካ በአምስት ነጥብ ሁለተኛ ሆናለች። በጥሎ ማለፉ እንግሊዝ ከሴኔጋል ትጫወታለች። አሜሪካ ደግሞ ኔዘርላንድን ትገጥማለች። የዓለም ዋንጫው የምድብ ሦስት እና አራት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። በምድብ አራት ቱኒዝያ እና ፈረንሳይ እንዲሁም አውስትራሊያ እና ዴንማርክ ምሽት 12 ሰዓት ይጫወታሉ። ከምድብ አራት ፈረንሳይ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ቀሪዎቹ ሦስት አገራት ለጥሎ ማለፉ መብቃት ዕድል አላቸው። አውስትራሊያ ሦስት ነጥብ ሲኖራት፣ ዴንማር እና ቱኒዝያ በተመሳሳይ አንድ ነጥብ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል። ምድብ ሦስት የሚገኙት ፖላንድ እና አርጀንቲና እንዲሁም ሳዑዲ አረቢያ እና ሜክሲኮ ምሽት አራት ሰዓት ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። በምድብ ሦስት የሚገኙ ሁሉም አገራት የማለፍ ዕድል አላቸው። ፖላንድ ምድቡን በአራት ነጥብ ትመራለች። አርጀንቲና እና ሳዑዲ አረቢያ እኩል ሦስት ነጥብ ይዘዋል። ሜክሲኮ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።", "እንግሊዝ የአፍጋኒስታን ሴት የእግር ኳስ ቡድን አባላትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ልትቀበል ነው ከታሊባን ሸሽተው በፓኪስታን የሚገኙ የአፍጋኒስታን ታዳጊ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሊመጡ እንደሚችሉ ተነገራቸው። ከ13-19 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት 35 አባላት ያሉት ቡድኑ ባለፈው ወር ካቡልን ሸሽቶ ለጥቂት ሳምንታት ፓኪስታን በሚገኝ ሆቴል ቆይቷል። የቡድን አባላቱ የፓኪስታን ጊዜያዊ ቪዛቸው በሰዓታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ቃል አቀባይ \"ለአፍጋኒስታን የሴቶች ቡድን ቪዛ ለመስጠት እየሰራን ነው። በቅርቡ ወደ በእንግሊዝ ልንቀበላቸው በጉጉት እየጠበቅን ነው\" ብለዋል። የእግር ኳስ አባላቱ ሌላ ሃገር ካልተቀበላቸው ወደ አፍጋኒስታን የመመለስ ግዴታ ነበረባቸው። ሴቶቹ እወንዲሸሹ ያገዘው የሮኪት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ሲኡ-አን ማሪ ጂል \"ይህ አስደናቂ ዜና ነው። ለዚህ ህይወት አድን ውሳኔያቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን እና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓቴልን በጣም እናመሰግናል\" ብለዋል። ከአፍጋኒስታን በአውቶቡሶች እንዲወጡ እና በላሆር እንዲቆዩ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የፋውንዴሽኑ ሊቀመንበር ጆናታን ኬንድሪክ \"በህይወት ሁለተኛ ዕድል በማግኘታቸው በጣም ተደስቻለሁ። ይህ ለእነሱ አዲስ ዓለም ነው። የእግር ኳሱ ማህበረሰብ እንደሚደግፋቸው እርግጠኛ ነኝ። ተረጋግተው ሕይወት የሚሰጠውን ደስታ ሁሉ ለመለማመድ ይችላሉ\" ብለዋል። ጂል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሴቶቹ ሊደርስባቸው ስለሚችለው ነገር ተጨንቀው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከፍተኛ እፎይታ አግኝተዋል ሲሉ ገልጸዋል። ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ እንግሊዝ እንደሚገቡ ተናግረዋል። ሊድስ ዩናይትድ እና ቼልሲ በእንግሊዝ ሲደርሱ እንደሚደግፏቸው ቃል ከገቡ በርካታ የእንግሊዝ የእግር ኳስ ክለቦች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የወጣቶቹ የቡድን አባላት ሁሉም ባልተለመደ ሁኔታ ውስጥ አልፈዋል። አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከምዕራብ አፍጋኒስታኗ ሄራት የመጡ ሲሆን ምዕራባዊያን ሰዎችን በአውሮፕለን ማስወጣት ሲጀምሩ ካቡል ወደሚገኙ እና ጥበቃ ወደሚደረግላቸው ቤቶች ተጉዘው ነበር። ጂል \"70 በመቶዎቹ የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል። በፍርሃት ተሸብረዋል\" ብለዋል። የአፍጋኒስታን የቀድሞ የሴቶች ቡድን ወደ አውስትራሊያ በአውሮፕላን አቅንቷል። የሴቶቹ ቡድን በኋላ በፖርቱጋል ጥገኝነት ተሰጠው። የታዳጊ ቡድኑ ዕጣ ፈንታ ግን እስካሁን እርግጠኛ አልነበረም። ሴቶቹ፣ ከአሰልጣኞቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በነሐሴ ወር መጨረሻ ወደ ኳታር ሊወሰዱ ነበር። በደህንነት ማስጠንቀቂያ ምክንያት በራራቸው እንዲዘገይ ሆነ። ከሁለት ሰዓታት በኋላ ደግሞ አውሮፕላን ማረፊያው በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ተሰነዘረበት። ለ10 ቀናት ተደብቀው ከቆዩ በኋላ ወደ አፍጋኒስታን ድንበር ተጓጓዙ። በጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን የመግቢያ ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ ወደ ፓኪስታን ተሻገሩ። ነገር ግን የፓኪስታን ቪዛቸው ሊያልቅ በመሆኑ ወደ አፍጋኒስታን መመለስ ለእነሱ በጣም አደገኛ ነበር ሲሉ ጂል ተናግረዋል። ታሊባን ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ ሴቶች በማንኛውም ስፖርት መሳተፍ አልቻሉም። የታሊባንን ቅጣት በመፍራት የቀድሞው የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን አምበል ካሊዳ ፖፓል ተጫዋቾች ማሊያቸውን እንዲያቃጥሉ እና ማህበራዊ ድር አምባ ላይ የለጠፉትን ምስሎች እንዲያጠፉ አስጠንቅቃ ነበር።", "ቼልሲ ለፍጻሜ መድረሱን ተከትሎ የቻምፒንስ ሊግ ዋንጫ ከእንግሊዝ እንደማያልፍ እርግጥ ሆነ ቼልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ ሪያል ማድሪድን በአሳማኝ ሁኔታ በማሸነፍ ለኢስታንቡሉ የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል። ቼልሲ በፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ይገጥማል። ይህም የእንግሊዝ ክለቦች ብቻ የሚሳቱፉበት የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ ይሆናል። ከአንድ ሳምንት በፊት ቼልሲ ወደ ሪያል ማድሪድ ተጉዞ ጨዋታው አንድ አቻ መጠናቀቁ አይዘነጋም። የቶማስ ቱሄል ቡድን ምስጋና ለግብ ጠባቂው ኤድዋርድ ሜንዲ ይሁንና ሁለት የካሪም ቤንዜማ ጥሩ አጋጣሚዎችን አድኗል። በጨዋታው ቲሞ ቨርነር በ28 እኛ ሜሰን ማውንት ደግሞ በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ቼልሲ 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል። ቼልሲ በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን በበላይነት አጠናቋል። ቼልሲ በአዲሱ አሰልጣኝ ቱማስ ቱሄል ስር እያንሰራራ ይገኛል። በሃቨርት እና በቨርነር ፈጣን እንቅስቃሴ ዕድሜ የተጫነው የሚመስለው ማድሪድ ላይ የበላይነት አሳይተዋል። ግብ ጠባቂው ሜንዲ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን ሲያድን አንቶንዮ ሩዲገርም በጨዋታው የኋላ ደጀንነቱን አስመስክሯል። ጉዞ ወደ ኢንስታንቡል ፍጻሜ ቼልሲዎች ከሲቲ ወቅታዊ አቋም አንጻር ዝቅተኛ ግምት ያገኘ ቡድን በመሆን ወደ ፍጻሜው ቢያቀኑም ዕድላቸውን ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠቃል። ቼልሲዎች የኋላ መስመራቸው ጠንካራ ሲሆን መሐሉ ደግሞ ውጤተማ የሚባል ነው። አሰልጣኙ ቱሄል እና አምበሉ ቲያጎ ሲልቫ ባለፈው ዓመት ከፒኤስጂ ጋር ለፍጻሜ ደርሰው የነበረ ሲሆን ዘንድሮም በሌላ ቡድን ውስጥ ሆነው ለፍጻሜ ደርሰዋል። ቱሄል ባለፈው ዓመት በባየር ሙኒክ የደረሰባቸውን ሽንፈት ለማካካስ ወደ ቱርክ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዘንድሮ ዌምብሌይ ላይ በኤፍኤ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ቼልሲ 1 ለ 0 ማንችስተር ሲቲን በማሸን ለፍጻሜ ደርሷል። በፍጻሜው ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል። አሰልጣኞቹ ምን አሉ? የቼልሲው ቶማስ ቱሄል ለቢቲ ስፖርት \"[ተጫዋቾቹ] ማሸነፍ ይገባቸዋል። ሪያል ኳስ ብዙ በመያዙ አስቸጋሪ ቢሆንም የነበረው የመልሶ ማጥቃት ጥሩ ነበርን። የመከላከል ፍላጎት ነበራቸው\" ብለዋል። \"ሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ነበር። ከመከላከል በተጨማሪ ጎል ማስቆጠር ችለናል። ይህ አስደናቂ ስኬት በመሆኑ ለቡድኑ ትልቅ ደስታ ነው\" ብለዋል። የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ለሞቪስታር \"ድሉ ይገባቸዋል። በልጆቼ እኮራባቸዋለሁ። ሞክረናል፣ ከፍጻሜውም በአንድ ጨዋታ ብቻ ርቀናል። ቼልሲዎች ጥሩ ተጫውተው በማለፋቸው ውጤቱ ይገባቸዋል\" ብለዋል።", "ፈረንሳይ የሞሮኮን ግስጋሴ በመግታት ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አለፈች የአፍሪካና የአረቡ ዓለም ብቸኛ ተስፋ የነበሩት ሞሮኮዎች ትናንት ምሽት ተስፋቸው ተቀጭቷል። ትልቅ ወኔ፣ ትልቅ ልብና በራስ መተማመን ይዘው ወደ ሜዳ የገቡት ሞሮኮዎች ገና ጨዋታው በተጀመረ በ5ኛው ደቂቃ የገባባቸው ጎል ወሽመጥ በጣሽ የሚባል ነበር። ጎሏ የተቆጠረችው በሃርናንዴዝ ነበር። ሞሮኮዎች ቁልፍ ተከላካይ መሥመር ተጫዋች ናይፍ አጉዋርድ እንደሚሰለፍ አሳውቀው የነበሩ ቢሆንም የደረሰበት ጉዳት ግን ለመጫወት አላበቃውም። ይህ ለሞሮኮዋያን ትልቅ ሐዘን ነበር። ሞሮኮዎች ከድንገተኛና ፈጣን የሃርናንዴዝ ጎል አገግመው ወደፊት ተጭነው መጫወት ቢችሉም ወደ ጎል የሚቀይሩት ኳስ ግን አላገኙም። የፈረንሳዩ ተቀያሪ ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ በመጪው እሑድ በሉሳይል ስታዲየም ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ኒዯኔል ሜሲን ላያፈናፍነው ይችላል እየተባለ ነው። ትናንት ምሽት ቡድኑን ለታሪካዊ ድል ያበቃውም እሱ ነው። ሞሮኮዎች ከእረፍት በፊት ሮማይን ሳይሲን በጉዳት ቢያጡም ሙሉ ስታዲየም ያልተቋረጠ ድጋፍ እያገኙ ወደፊት ጫና ፈጥረው ተጫውተው ነበር። ከአሁን አሁን ጎል አስቆጥረው አቻ አስቆጠሩ ሲባል ግን እየመከነባቸው ተቸግረው አምሽተዋል። ለምሳሌ ጃዋድ ኤል ያሚቅ በ43ኛው ደቂቃ በመቀስ ምት ያደረገው ሙከራ የፈረንሳዩን ግብ ጠባቂን የሁጎ ሎሪስን ልብ ማስደንገጥ የቻለች ነበረች። ሆኖም አንግል ገጭታ መክናለች። ሁለቱም ቡድኖች ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል ሲመለሱ በፈረንሳይ 1-0 መሪነት ቢሆንም ሞሮኮ ታሪክ የመሥራት ዕድሏ ፈጽሞ አልተመናመነም ነበር። ሆኖም ከእረፍት መልስ በ78ኛው ደቂቃ ምባፔ ተቀይሮ ከገባው ኮሎ ሙዋኒ ጋር በፈጠሩት ቅንጅት ከምባፔ የተላለፈለትን ኳስ ሙዋኒ በቀላሉ ወደ ጎልነት ቀይሯታል። ይህቺ ጎል በስታዲየሙ ከፍተኛ ድጋፍ የነበራቸውን ሞሮኮዎች ተስፋቸውን ያጨለመች ነበረች። በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎችና በተጨማሪው 6 ደቂቃ ሞሮኮዎች ያለቀላቸው የሚባሉ ኳሶችን አምክነዋል። የትናንት ምሽቱን ድል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በስታዲየም ተገኝተው ተከታትለውታል። ደስታቸውን በተደጋጋሚ ሲገልጹም ታይተዋል። የፊታችን እሑድ የሜሲና የምባፔ ፍልሚያን ቢሊዮኖች ይመለከቱታል ተብሎ ይጠበቃል። ፈረንሳይ በፈረንጆቹ 2018 የሞስኮው የዓለም ዋንጫ በፍጻሜ ክሮሺያን የረታችበትን ታሪክ ትደግም ይሆን? ሜሲ ዋንጫ ለአገሩ በማንሳት የዓመታት ሕልሙን ያሳካ ይሆን?", "በኦሊምፒክ መድረክ ኢትዮጵያን በቴኳንዶ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወክለው ወጣት አትሌት ሰለሞን ቱፋ ዛሬ በሚጀመረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ስፖርት መድረክ ይወክላል። የቴኳንዶ ውድድር ከአውሮፓውያኑ 2000 ጀምሮ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ መካተት የጀመረ ሲሆን የ23 ዓመቱ ወጣት ሰለሞን በዚህ ውድድር ለአገሩ ጥሩ ውጤትን ለማምጣት ማቀዱን ይናገራል። ሰለሞን በቶኪዮ ኦሊምፒክ መሳተፍ የቻለው እአአ 2020 በአፍሪካ ደረጃ ሞሮኮ ላይ በተካሄደው ውድድር ስኬታማ መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ ያስረዳል። በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ መሳተፍ \"የረዥም ጊዜ ህልሜ ነበር\" የሚለው ሰለሞን፤ ይህን ህልሙን ለማሳካት ትምህርቱን ከማቋረጥ ጀምሮ ብዙ እልህ አስጨራሽ ጥረቶችን ማድረጉን ያስረዳል። \"በዚህ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ብዙ ውድድሮችን ማድረግ ነበረብኝ፤ ከአገር ውጪ ብዙ ውድድሮችን አሸንፊያለሁ። ጉዳት ሁሉ አጋጥሞኝ እዚህ ደርሻለሁ\" ይላል። \"የሚቻለኝን ሁሉ አድርጌያለሁ። ፈጠሪ ከረዳኝ የሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ ገብቼ የአገሬን ሰንደ ዓላማ ማንሳት እፈልጋለሁ\" በማለት ሰለሞን ከቢቢሲ ተናግሯል። ቴኳንዶ (Taekwondo) የኮሪያ ማርሻል አርት ሲሆን እጅ እና እግርን መጠቀምን ይጠይቃል። ሰለሞን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከ58 ኪሎ ግራም በታች በሚባለው ምድብ ውስጥ የሚወዳደር ይሆናል። በዚህ የውድድር መስክ 16 ስፖርተኞች ይወዳደራሉ። \"ውድድሩ በአንድ ቀን ነው የሚጠናቀቅ ነው። ጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት ሊዘልቅ ይችላል። አንድ ዙር ካሸነፍክ ወደ ቀጣይ ዙር እያለፍ ትሄዳለህ።\" የኦሊምፒክ ውድድር እንደመሆኑ መጠን ሁሉም አትሌት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ የሚናገረው ሰለሞን፤ \"ተዘጋጅቻለሁ ምንም የምፈራው ነበር የለም\" በማለት ይናገራል። ባለፉት ስምንት ወራት በሳምንት ስድስት ቀናት ጠዋት እና ማታ በየቀኑ ከ5 አስከ 6 ሰዓታት ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የሚያስረዳው ሰለሞን ያለፈውን አንድ ወር ደግሞ ወደ ጀርመን አገር በመሄድ የመጨረሻ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበረ ይናገራል። ሰለሞን ውድድሩን ቅዳሜ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም ያደርጋል። ሰለሞን ቱፋ ማነው? ትውልዱ አርሲ በቆጂ ቢሆንም እድገቱ ግን አዲስ አበባ ከተማ ነው። መስታወት ቱፋ እና ትዕግስት ቱፋ የተባሉት ሁለት እህቶቹ በማራቶን ውድድር ይታወቃሉ። \"ከእኛ ቤተሰብ ሦስት ሰው በኦሊምፒክ ተሳትፏል። ቤተሰቦቼ ይህን ሲያስቡ በጣም ደስ ይላቸዋል\" በማለት ከዚህ በፊት ሁለት እህቶቹ በኦሊምፒክ መወዳደራቸውን ያስታውሳል። ከሩጫው ይልቅ ወደ ቴኳንዶ ውድድር ፍላጎት ያደረበት፤ ታላቅ ውንድሙ ይህን ስፖርት ሲሰራ ከተመለከተ በኋላ በቴክዋንዶ ስፖርት ፍቅር መውደቁን ይናገራል። ሰለሞን እስካሁን በበርካታ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ የተለያዩ ውጤቶችን ቢያስመዘግብም ሞሮኮ ላይ ተወዳድሮ ያመጣው ውጤት ግን \"ትልቁ ስኬቴ ነው\" ይላል። እ አአ 2018 ላይ በሞሮኮ ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ ቴኳንዶ ሻምፒዮን በ54 ኪሎ ግራም ምድብ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፉን ይናገራል። ዎርልድ ቴኳንዶ ፕሬዝደንትስ ካፕ በተባለ ውድድር ላይ የወርቅ ተሸላሚ በመሆኑ 'ምርጡ የአፍሪካ አትሌት' ተብሎ መሸለሙን ሰለሞን ለቢቢሲ ተናግሯል።", "ከአሸናፊነት የተሰረዘው ኢትዮጵያዊው የማራቶን ሯጭ እንዴት ያልተፈቀደ ጫማ አደረገ? እሁድ መስከረም 02/2014 ዓ.ም በአውሮፓዊቷ አገር ኦስትሪያ ዋና ከተማ ቪየና በተደረገው የማራቶን ውድድር ላይ ተሳትፎ አንደኛ በመውጣት ያሸነፈው ኢትዮጵያዊው ደራራ ሁሪሳ ከታላቁ ድሉ ጋር መቆየት የቻለው ከ45 ደቂቃዎች ያልበለጠ ነበር። የደራራ አሸናፊነት በውድድሩ ላይ ከተረጋገጠ በኋላ የሩጫው ሥነ ሥርዓት ተቆጣጣሪዎች ውጤቱን ሙሉ ለሙሉ ከማጽደቃቸው በፊት አትሌቱ ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አግኝተው ምርመራ ካደረጉ በኋላ ውጤቱን ውድቅ ማደረጋቸው ተነገረ። ለዚህም ምክንያቱ ደራራ ተጫምቶት የተወዳደረበት ጫማ መርገጫ (ሶል) ለውድድሩ ያልተፈቀደ ውፍረት አለው ነው የሚል ነበር። አትሌት ደራራ ውድድሩን 2፡09፡22 በሆነ ሰዓት ቢያጠናቅቅም ማንም ባልጠበቀው ሰበብ ከእጁ የገባው ታላቅ ድልን ለመነጠቅ ተገዷል። ይህ ክስተት የአትሌቱን ልብ ብቻ የሰበረ አልነበረም የአሰልጣኙ ገመዶ ደደፎን ጭምር እንጂ። ደራራ አዲስ አበባ ሳለ የሚሮጥበትን ትክክለኛውን ጫማ አዘጋጅቶ እንደነበር የሚናገሩት አሰልጣኙ ችግሩ የተከሰተው ኦስትሪያ ከሄደ በኋላ በተላከለት ሻንጣ ውስጥ በነበረው የልምምድ ጫማ ሰበብ ነው ነው። \"ከሩጫው ዕለት በፊት ማታ ላይ የሰጠነውን የውድድር ጫማ ትቶ ለልምምድ እንዲሆን የተላከውን ጫማ አደረገ\" ይላሉ። በ39ኛው የቪየና ማራቶን ላይ ተሳትፎ በማሸነፍ አምስተኛው ኢትዮጵያዊ ለመሆን ችሎ የነበረው የ23 ዓመቱ ወጣት አትሌት ደራራ ድሉ ከእጁ ወጥቶ የአንደኛ ደረጃ አሸናፊነቱ ሁለተኛ ለወጣው ኬንያዊ አትሌት ተሰጥቷል። \"ሰይጣን አትብላ ሲልህ እንደዚህ አይነት ነገር ይፈጠራል\" ይህ ክስተት አሰልጣኙን በእጅጉ አስቆጭቷል \"እኛ ምንም እንኳን አጠገቡ ባንኖርም ለሩጫ በሚሆነው ጫማ ሩጥ ብለነዋል። ለሩጫው የሚያደርገውን የጫማ አይነትም ለውድድሩ አዘጋጆች አስመዝግበን ነበር። እንግዲህ ሰይጣን አትብላ ሲልህ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ነገር ይፈጠራል።\" ይላሉ። አሰልጣኙ ገመዶ እንደሚሉት ደራራ የማይፈቀደውን ጫማ ያደረገው ጠዋት ተነስቶ ለውድድሩ ሲዘጋጅ የሩጫ እና የልምምድ ጫማው ተመሳስሎበት የልምምዱን ጫማ አድርጎ ወጥቷል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንንም ክስተትና የተፈጠረውን ስህተት ለውድድሩ አዘጋጆች ለማስረዳት እንደተሞከረ የሚገልጹት አሰልጣኙ \"ነገር ግን አንዴ የወጣ ሕግ አለ። አትሌቱ ሕጉን ማክበር አለበት። በሩጫ ውድድር የሚፈቀድ እና የማይፈቀድ ጫማ አለ\" ስለዚህም የደራራን አሸናፊነት ከመነጠቅ ማዳን አልተቻለም። በሩጫ ውድድሮች ወቅት አትሌቶች ሊጫሙ የሚገባቸው ጫማዎች ዝርዝር ያለ ሲሆን በዚህም መሠረት ለልምምድ፣ ለእርምጃ፣ ለትራክ፣ ለአስፋልት እና በጫካ ውስጥ ለሚደረግ ሩጫ የሚደረጉ ጫማዎች የተለያዩ ናቸው። አትሌት ደራራ ለዚህ ውድድር ሲል ለረዥም ጊዜ ሲዘጋጅ ከመቆየቱ አንጻር የአሸናፊነቱ መነጠቅ የሚፈጥርበት ስሜት ቀላል አይሆንም። አሰልጣኙ እንደሚሉት ግን አሁን የተፈጠረውን ነገር ወደኋላ መመለስ ስለማይቻል ስለወደፊቱ ማሰብና መዘጋጀት ላይ ያተኩራል ብለዋል። \"አትሌቱ ገና ልጅ ነው። አሁኑ ስለተከሰተው ነገር ምንም ማድረግ ባይችልም ለወደፊት መዘጋጀት ነው የሚጠበቀው። ሌሎች አትሌቶችም እንዲህ አይነቱ ችግር እንዳይገጥማቸው መጠንቀቅ አለባቸው\" ብለዋል። አትሌት ደራራ ሁሪሳ የቪየናው ማራቶን ላይ ከመሳተፉ በፊት ሕንድ ውስጥ በተካሄደው ተመሳሳይ ውድድር ላይ በመሳተፍ ሁለተኛው የማራቶን ውድድሩ ነው። የውድድር ጫማ ልዩነት የዓለም አትሌቲክስ ውድድሮች የበላይ አካል እንደሚለው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ የመጣው የመሮጫ ጫማዎች ምርት በውድድሮች ውጤት ላይ ተጽእኖ እንዳይኖረው ለማድረግ በተለያዩ የሩጫ ወድድሮች ላይ የሚደረጉ ጫማዎችን በተመለከተ መስፈርቶችን አስቀምጧል። በዚህም ምክንያት ነው ደራራ ለልምምድ ሲጫማው የነበረውን ጫማ በውድድር ላይ አድርጎ በመገኘቱ በልፋት ያገኘውን የከባዱን ውድድር የአሸናፊነት ክብር እንዲያጣ ሆኗል። በአህጉረ አውሮፓ በየዓመቱ ከሚካሄዱ ዋነኛ የማራቶን ውድድሮች መካከል የሚመደበው የቪየናው ማራቶን ላይ ለሚያሸንፉ አትሌቶች የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል። የደራራ የአንደኝነት ውጤት መሰረዝን ተከትሎ ሁለተኛ የሆነው ኬንያዊው አትሌት ሌዮናርድ ላንጋት አንደኛ፣ ኢትዮጵያዊው በተስፋ ጌታሁን ከሦስተኛ ወደ ሁለተኛ እንዲሁም አራተኛ ወጥቶ የነበረው ሌላኛው ኬንያዊ ኤድዊን ኮስጌይ ሦስተኛ ሆነው ተሸጋሽገዋል። የጫማው መርገጫ ውፍረት በውድድሩ ላይ አትሌቶች መጫማት ያለባቸው የውድድር ጫማዎች የሶል ውፍረት ከ40 ሚሊሜትር መብለጥ የለበትም። የውድድሩ አዘጋጆች ባደረጉት ማጣራት የደራራ ጫማ 50 ሚሊሜትር ውፍረት እንዳለው ካረጋገጡ በኋላ ውጤቱ እንዲሰረዝ አድርገዋል። \"ውሳኔው ግልጽ ነው፤ በጣም እናዝናለን። ደራራ ለልምምድ ብቻ በሚውለው ጫማ ነው የሮጠው። በቴክኒክ ስብሰባ ላይ ለሁሉም አትሌቶች አሳውቀን ነበር\" በማለት ከውድድሩ ኃላፊዎች አንዱ ተናግረዋል። \"ደራራን ልደርስበት አልቻልኩም\" ደራራን ተከትሎ ሁለተኛ የወጣው የ25 ዓመቱ ኬንያዊ አትሌት ሊዮናርድ ላንጋት ከውሳኔው በኋላ የአንደኝነትን ቦታ እንዲይዝ ተደርጓል። \"የደራራ ውጤት መሰረዙን አላወቅሁም ነበር። መጀመሪያ ላይ ለማመን ተቸግሬ ነበር\" ብሏል የውጤቱን ለውጥ ባወቀ ጊዜ የተሰማውን ሲናገር። \"የመጨረሻው አሯሯጭ ከ32ኛው ኪሎሜትር በኋላ ሲወጣ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ነበር። ሁሉንም ነገር በመጨረሻው ኪሎሜትር ላይ ለመሞከር ወስኜ ነበር ግን ደራራን መከተል አልቻልኩም\" በማለት ተስፋ ቆርጦ በቀጣይ አመት ለማሸነፍ እንደሚዘጋጅ ወስኖ ነበር። ላንጋት በቪየናው ውድድር ላይ ለመሳተፍ የበረራ መዘግየትና በኳታሯ መዲና ዶሃ ውስጥ በሚገኝ አየር ማረፊያ ውስጥ አንድ ሌሊት ማደሩን በመግለጽ በከባድ ጫና ውስጥ ሆኖ በውድድሩ መሳተፉን ተናግሯል ሲል የውድድሩ አዘጋጅ ድረ ገጽ አመልክቷል።", "በሊቨርፑልና በማን. ዩናትድ ጨዋታ ምክንያት ኬንያውያን ተማሪዎች የመኝታ ክፍላቸውን አቃጠሉ አራት ኬንያውያን ተማሪዎች የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታን እንዳይመለከቱ በመከልከላቸው የትምህርት ቤታቸውን የተማሪዎች የመኝታ ክፍል ማቃጠላቸው ተነገረ። ተማሪዎቹ ባለፈው እሁድ በሊቨርፑል እና በማንችስተር ዩናይትድ ቡድኖች መካከል የተካሄደውን ጨዋታ \"እንዳንመለከት ተከለከልን\" በሚል ነው የተማሪዎች የመኝታ ክፍልን በእሳት ማቃጠላቸው የተዘገበው። በዚህ ድርጊት የተጠረጠሩት አራቱ ተማሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ዴይሊ ኔሽን የተባለው የኬንያ ጋዜጣ ዘግቧል። የኬንያ የባሕር ዳርቻ ግዛት በሆነችው ኪሊፊ ውስጥ የሚገኘው የወንዶች ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪ የሆኑት አራቱ ልጆች ንብረትን በእሳት በማቃጠል ወንጀል ዛሬ ረቡዕ ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ እንደሚመሰረትባቸው ፖሊስ አስታውቋል። አራቱ ተማሪዎች በመኝታ ክፍላቸው ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ አድርሰዋል ተብለው ተለይተው የተያዙት ተጠርጥረው በፖሊስ ምርመራ ከተደረገባቸው 14 ተማሪዎች መካከል መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ ምርመራውን ካደረገ በኋላ ቀሪዎቹን አስር ተማሪዎች የለቀቀ ሲሆን አራቱን ግን በወንጀሉ እንደጠረጠራቸው በመግለጽ ክስ እንደሚመሰርትባቸው አስታውቋል። ተማሪዎቹ ይህንን ድርጊት እንዲፈጽሙ ምክንያት የሆናቸው በእግር ኳስ ተከታታዮች ዘንድ ትልቅ ግምት የተሰጠውን የሁለቱን የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኃያል ቡድኖችን ጨዋታ እንዳይመለከቱ በመከልከላቸው ነው። በትምህርት ቤቱ ሕግ መሠረት ተማሪዎች እግር ኳስ እንዲመለከቱ የሚፈቀድላቸው ቅዳሜ ዕለት የሚደረጉትን ውድድሮች ብቻ መሆኑን የአካባቢው የፖሊስ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ፍሬድሪክ አቡጋ ተናግረዋል። በተማሪዎች የመኝታ ክፍል ላይ በተፈጸመው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት ትምህርት ቤቱ እንዲዘጋ መደረጉም ተገልጿል። ባለፈው ዕሁድ በማንችስተር ዩናይትድ ሜዳ ኦልድ ትራፎርድ በተካሄደው የሊቨርፑልና የማን ዩናይትድ ጨዋታ ሊቨርፑል በሰፊ የግብ ልዩነት 5 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል። በጨዋታው ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞሐመድ ሳላህ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር በፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ከፍተኛውን ግብ ያስቆጠረ አፍሪካዊ ለመሆን ችሏል።", "የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ፡ ግጥሚያዎች እና የጨዋታዎች የቀጥታ ውጤት በኳታር የሚካሄደውን የ2022 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የጨዋታዎች መረሃ ግብር እና የግጥሚያዎችን ውጤት በቀጥታ በዚህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽ ላይ በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ። ውድድሩ በሚካሄድበት ጊዜ ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች በየዕለቱ ስለሚኖራቸው ግጥሚያ፣ የጨዋታ ሰዓት እና በየትኛው ስታዲየም ውስጥ ጨዋታው እንደሚካሄድ እዚህ ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም ጨዋታዎች በሚካሄድበት ጊዜ ጭምር የጨዋታ ውጤቶችን በየደቂቃው የምናቀርብ ሲሆን፣ ቀደም ብለው የተደረጉ ግጥሚያዎችን ውጤትንም ማግኘት ይችላሉ።", "የ22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ የማይረሱ 12 ምስሎች እና ታሪካቸው ምስል አቅራቢው ጌቲ ኢሜጅ ከ50 በላይ የፎቶ ባለሙያዎቹ አስደናቂ ምስሎችን እንዲያስቀሩለት ወደ ኳታር ልኮ ነበር። ፎቶ አንሺዎቹም ለታሪክ የሚቀመጡ አስደናቂ ክስተቶችን የሚያሳዩ በሺዎች የሚቆጠሩ ምስሎችን አንስተዋል። የጌቲ ፎቶ አንሺዎች ምርጥ የሚሏቸውን ፎቶዎች እንዲህ አጋርተዋል። ዳን ሙላን፡ ይህ ቅጽበት የሞት ሽረት የተደረገበት ነበር። በዚህ ጨዋታ ጃፓን ጀርመንን አሸንፋ ዓለም ጉድ ያለበት ነው። በጨዋታው ማብቂያ የጀርመኑ ግብ ጠባቂ ሳይቀር የአቻነት ጎል ለማስቆጠር የተቻለው አድርጎ ነበር። ፎቶ አንሺው ዳን ሙላን ሁለት ግብ ጠባቂዎችን በአንድ ምስል ማስቀረት ሁሌም የሚገኝ ዕድል አይደለም ይላል። ስለዚህ ፎቶ ሌላው የመውደው ነገር ይላል ዳን፤ የትኛው ቡድን እያጠቃ የትኛው እየተከላከለ እንደሆነ ማወቅ አይቻልም። በዚህ የምድብ ጨዋታ ጃፓን ጀርመንን 2 ለ 1 ማሸነፏ ወደ ሩብ ፍጻሜ እንድታልፍ አስችሏት ነበር። ጀርመን ደግሞ ከምድቧ ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። ማይክል ስቲል፡ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ከተመዘበጉ ድንቅ፤ አስደማሚ ጎሎች አንዷ ሪቻርልሰን ሰርቢያ ላይ ያስቆጠረት ትገኝበታለች። ፎቶግራፈሩ ማይክል ይህን ጎል ለታሪክ በምስል ያስቀረችው ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን በሚቀመጡበት ቦታ ላይ ተዘጋጅታ የተቀመጠችው ካሜራ ናት ይላል። ብራዚል በዚህ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ሰርቢያን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላ ነበር። ዴቪድ ራሞስ፡ የጌቲ ኢሚጄስ ፎቶ አንሺዎች በሜዳ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪ የሚታዩ ክስተቶችንም በካሜራቸው አስቀርተዋል። ይህ ምስል የጋና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከደቡብ ኮሪያ ጋር ጨዋታ ለማድረግ በኤጁኬሽን ሲቲ ስታዲየም እየጨፈሩ ሲገቡ ያሳያል። ዴቪድ ራሞስ የጋና ተጫዋቾች ስታዲየም ሲመጡ የተለየ ክስተት እንደሚኖር እርግጠኛ ነበርኩ ይላል። በመልበሻ ክፍሉ እና ከአውቶብስ ከሚወርዱበት አማካይ ቦታ ላይ ሆኖ ከተጠበቃቸው በኋላ ተጫዋቾቹ ሲጨፍሩ የሚያሳየውን አስደናቂ ምስል ማንሳቱን ይገልጻል። ጋና ይህን ጨዋታ 3 ለ 2 ብታሸንፍም ከምድቧ ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። ሾን ቦትሪል፡ ድል ያደረጉ የቡድን አባላትን ፎቶ ግራፍ ማንሳት እንደሚያስደስት ሁሉ፤ ተሸናፊ ተጫዋችን ፎቶ ማንሳት ከባዱ የሥራ አካል ነው ይላል ፎቶግራፈር ሾን። ከርቀት ፎቶ ማንሳት የሚያስችሉ ሌንሶችን በመግጠም ፎቶ እናነሳለን እንጂ የሐዘን ስሜት ውስጥ ያሉ ተጫዋቾች ፊት ቆሞ ፎቶ ማንሳት ከባድ ነው ይላል። ጀርመኖች የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ከተሸነፉ በኋላ ከፍተኛ ጫና ውሰጥ ነበሩ። የመጨረሻ የምድብ ጨዋታቸውን ቢያሸንፉም ከውድድሩ ቀድመው ተሰናብተዋል። ማጃ ጂቲጅ፡ ተጫዋቾች ሁሌም ከመልበሻ ክፍል ሲወጡ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል። በተለይ ደግሞ ሜሲ ሲጫወት ተጫዋቾችን አጅበው ለሚወጡት ታዳጊዎች ሌላ ዓለም ነው። ቡድኖች ወደ ሜዳ ከመውጣታቸው በፊት የሚጠባበቁበት ቦታ ሁሌም የካሜራ ዐይን የሚበዛበት ቦታ ነው። ስለዚህም የቀጥታ ሥርጭት ውስጥ ላለመግባት ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን ይላል ፎቶግራፈሩ ማጃ ጂቲጅ። ሜሲ ለታዳጊዎች ሰላምታ ሲሰጥ ነበር። ከእርሱ በተቃራኒ የተሰለፈ ቡድንን አጅባ ለመውጣት የተዘጋጀት አንዲ ሴት ልጅ ሾልካ ወደፊት በመምጣት አድናቂው እንደሆነች ገለጸችለት። በዚህ ቅጽበት ነበር በምስሉ እንደምትታየው ልብ የሚያሞቅ ፈገግታዋን እየቸረችው በሁለት አውራ ጣቶቿ አድናቆትን የገለጸችለት። ላውረንስ ግሪፊታስ፡ በዚህ ውድድር አስደናቂ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ ትኩረትን በሙሉ መስረቅ የሚችሉ ለኳስ ብቻ የተፈጠሩ የሚመስሉ ተዓምራዊ ተጫዋቾች ነበሩ። የፈረንሳዩ ኪሊያን ምባፔ ይህን መስፈርት ያሟላል። ፈረንሳይ ከፖላንድ በነበራት ጨዋታ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ድንቅ አቋም አሳይቷል። የምባፔን ፍጥነት እና ክህሎት የሚያሳይ ፎቶ ማስቀረት ነበረብኝ ይላል ፎቶ አንሺው ላውረንስ። የካሜራ ጥበብን በመጠቀም ይህን አስደናቂ ምስል ማስቀረት ችያለሁ ይላል። ፍራንኮይስ ኔል፡ ብራዚላውያን ጎል ካስቆጠሩ በኋላ በሚያሳዩት ድንቅ ጭፈራ ይታወቃሉ። ኔይማን ከፍጹም ቅጣት ምት ሁለተኛውን ጎል ካስቆጠረ የቡድኑ አባላት በተለየ ዳንስ ደስታቸውን እንደሚገልጹ ቀድሜ ገምቼ ስለነበረ ካሜራን አስተካክዬ ስጠብቃቸው ነበር ይላል ፍንኪይስ ኔል። ብራዚል በስታዲየም 974 ደቡብ ኮሪያን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለው ነበር። አሌክስ ግሪም፡ ሞሮኮ የዚህ ዓለም ዋንጫ ክስተት ነበረች። እንደ ቤልጂየም፣ ስፔን እና ፖርቹጋል ያሉ ኃያል ቡድኖችን ማሸነፍ ችላለች። አሌክስ ግሪም ፎቶ ከማንሳታችን በፊት እንዴት ማንሳት እንዳለብን ልናቅድ እንችላለን ይላል። ነገር ግን፤ የትኛው ቡድን በደስታ ስሜት እንደሚፈነጥዝ፣ የትኛው ደግሞ ባለማመን ስሜት ፈዞ እንደሚቀር መገመት ከባድ ነው ይላሉ። ይህ አጋጣሚ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ስፔንን ማሸነፋቸው እርግጥ ከሆነ በኋላ ደስታቸውን ሲገልጹ፤ የስፔን ብሔራዊ ቡድን አባላት ደግሞ ባለማመን ስሜት ውስጥ ሆነው በአንድ ላይ ያሳያል። ማይክል ሬጋን፡ በዚህ የዓለም ዋንጫ ጌቲ ኢሜጅስ ከጨዋታ በኋላ ወደሜዳ ገብቶ ምስሎችን እንዲወስድ ፍቃድ አግኝቶ ነበር። እኛ ፎቶግራፈሮች ይላል ማይክል ሬጋል፤ “እኛ ፎቶግራፈሮች ወደ ሜዳ በመግባት ተጫዋቾች ጥልቅ ስሜት ውስጥ ሆነው ፎቶግራፍ ለማንሳት እንሞክራለን።” እኔም ምባፔ ፊት ሂጄ ‘የስስስስ ኪሊያያያያንንንን’ ስለው እርሱም ወደ ካሜራዬ ሌንስ እየተመለከተ በዚህ መልኩ ደስታውን ሲገልጽልኝ ምርጥ ፎቶ ግራፍ ማስቀረት ችያለሁ ይላል። ኪሊያን ምፓቤ በዚህ ምስል ላይ የለበሰው የክለብ አጋሩን አሽራፍ አኪሚን መለያ ልብስ ነው። ፈረንሳይ ሞሮኮን በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷ ይታወሳል። ፓትሪክ ስሚዝ፡ ፖርቹጋል ከውድድሩ መሰናበቷ እርግጥ እየሆነ ሲመጣ የሮናልዶን እያንዳንዱን ስሜታዊ እንቅስቃሴ መከታተል ዋና ትኩረቴ አድርጌ ነበር ይላል ፓትሪክ ስሚዝ። ይህ ምስል የተነሳው ሮናልዶ ተቀይሮ ገብቶ ያገኛትን ዕድል ወደ ጎል ለመቀየር ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ሲቀር ሲሜቱን የገለጸበትን ሁኔታ ነው። ፖርቹጋል በሩብ ፍጻሜውን በሞሮኮ 1 ለ 0 ከተሸነፈች በኋላ ከውድድሩ መሳናበቷ ይታወሳል። አሌክሳንደር ሃሴንሰቲያን: ይህን ጨዋታ ከፍ ብሎ ከሚገኘው የመገናኛ ብዙኃን ቦታ ሆኜ እንድዘግብ ዕድል ተሰጥቶኝ ነበር። እኔ ካለሁበት ቦታ የሜዳው አካል በሙሉ በግልጽ ይታያል። ይህም የሞሮኮው ሶፊያን ቡፋል ከእናቱ ጋራ በደስታ ሲጨፍር ፎቶግራፍ የማንሳት ዕድሉን ሰጥቶኛል። ይህን አስደናቂ ክስተት ተጫዋቹ እና እናቱ በተቀረው ሕይወታቸው መቼም የሚረሱት አይመስለኝም። ዴቪድ ራሞስ፡ ይህ ሜሲ ዋንጫ ይዞ በሰርጂዮ አጉዌሮ ትከሻ ላይ ሆኖ የሚያሳየው ምስል ማራዶና እአአ 1986 ላይ ያደረገውን ያስታውሳል። ሜሲ ጨንቅላቱ በግቡ አግዳሚ እንዳይመታ እየተከላከለ ቢሆንም በደስታ ስሜት ውስጥ የነበሩት አርጀንቲናውያን የምንጊዜም ምርጡ ተጫዋቻቸው ጭንቅላት አደጋ ላይ ስለመሆኑ አለማየታቸው ፈገግ የሚያስብል ክስተት ነው።", "ሲፈን ሐሰን፡ ''ለኢትዮጵያ የመሮጥ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም'' \"የምፈራው አትሌት የለም። ማሸነፍ እንጂ ለቅጽበትም ቢሆን መሸነፍን አላስብም\" ትላለች የ26 ዓመት ወጣት የዓለም ሻምፒዮኗ አትሌት ሲፈን ሐሰን። \"ለኢትዮጵያ እንድሮጥ የጠየቁኝ ሰዎች አሉ። እኔ ግን ለኢትዮጵያ የመሮጥ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። ኦሮሚያ ነጻ ካልወጣች በቀር\" በማለት አትሌት ሲፈን ሃሰን ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች። ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፈን በአሁኑ ወቅት በዓለም አትሌቲክስ የሴቶች አጠቃላይ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። • ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? • አየር መንገዱ ለመንገደኞቹ የሚበላ ኩባያን አቀረበ በቅርቡ በኳታር ዶሃ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10 ሺህ፣ በ1 ሺህ እና 5 መቶ ሜትር ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆኗ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ ዓመት በሦስት የተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በበላይነት አጠናቃለች። በአዳማ ከተማ የተወለደችው ሲፈን፤ ገና የ15 ዓመት ወጣት ሳለች በስደት ከሃገር እንደወጣች እና በለጋ ዕድሜዋ ብዙ ውጣ ውረዶችን ለማለፍ መገደዷን ትናገራለች። ወደ ትምህርት ቤት በሩጫ ትሄድ እንደነበረ እና ለአትሌቲክስ ስፖርት ፍቅር ያደረባት ገና ታዳጊ ሳለች እንደሆነ ታስረዳለች። ወደ ኔዘርላንድስ ካቀናች በኋላ አትሌቲክሱን አጠናክራ እንደያዘችም ትናገራለች። እዚያም የአዲሱ አገር የኑሮ ዘይቤ እና የአየር ሁኔታ ለአንድ ዓመት ፈተና ሆኖባት እንደቆየ ሲፈን ታስረዳለች። ሆኖም ብዙም ሳትቆይ በአትሌቲክሱ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደጀመረች ታስታውሳለች። ሲፈን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ 'የእኔ ጀግና ነው' ትላለች። ለዚህም ምክንያቷ በሪዮ ኦሊምፒክ የማራቶችን ውድድር ሁለተኛ ሆኖ ሊያጠናቅቅ ሲል ያሳየው ምልክት በውስጧ ልዩ ስሜት ፈጥሮባታል። \"ፈይሳ ለኦሮሞ ህዝብ ብዙ ነገር አድርጓል። ያን ምልክት ካሳየ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ እኔ እየመጡ 'እጅን ማጣመር ምን ማለት ነው?' እያሉ ይጠይቁኝ ነበር። ትርጉሙን ስነግራቸው ብዙዎች በጣም አድንቀውታል።\" በአንድ ወቅት ነርስ ለመሆን ትምህርት ቤት ገብታ የነበረችው ሲፈን፤ ለሁለት ዓመታት ያህል ትምህርቷን ከተከታተለች በኋላ አቋርጣ ሙሉ ትኩረቷን ለአትሌቲክሱ ማድረጓን ታስረዳለች። በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የ1ሺህ 5መቶ ሜትር የወርቅ ባለቤት ከመሆኗም በላይ ኢትዮጵያዊያን የሚታወቁበትን የ10 ሺህ ሜትር ውድድር አሸንፋ የወርቅ ባለቤት መሆኗ ልዩ ስሜት እንደፈጠረባት ትናገራለች። \"የቤት ውስጥ ረዥም ርቀት ውድድር አልወድም፤ አሰልቺ ይመስለኛል። እንደውም አልወዳደርም ብዬ ትቼው ነበር። አሰልጣኜ ነው ካልተወዳደርሽ ያለኝ። እኔም የ1ሺህ 5መቶ ሜትር ሩጫዬ ደካማ ስለነበር 'እራሴን መቅጣት አለብኝ' ብዬ ነው ወደ ትራኩ የገባሁት። ከዚያም ወርቅ አገኘው። በጣም ተደስቼበታለሁ\" ትላለች ሲፈን። ሲፈን ለኢትዮጵያ እንድትሮጥ እንደተጠየቀች ትናገራለች። \"ለኢትዮጵያ እንድሮጥ የጠየቁኝ ሰዎች አሉ። እኔ ግን ለኢትዮጵያ የመሮጥ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። ኦሮሚያ ነጻ ካልወጣች በስተቀር\" የሚል አቋም አላት። \"ኢትዮጵያ ብዙ ልጆች አሏት። ለእነርሱ ድጋፍ ቢደረግ እና ቢሰራባቸው ኖሮ እኔም ለኢትዮጵያ የመሮጥ ፍላጎት ይኖረኝ ነበር። ግን ባሉት ላይም አልተሰራም። ለምሳሌ ዮሚፍ ቀጄልቻ ጋር አብረን ልምምድ እናደርጋለን። ዮሚፍ ብዙ ችግሮችን ነው እያለፈ ያለው። ስለዚህ ለኢትዮጵያ ለመሮጥ ፍላጎቱ የለኝም። እንዲያውም እንኳን ወጣሁ እላለሁ።\" በተለያዩ ርቀቶች እየተወዳደረች አመርቂ ውጤት የምታስመዘግበው ሲፈን ለዚህ ምሥጢሩ ጠንክሮ ልምምዶችን ማድረግ እና ትዕግስተኛ መሆን ነው ትላለች።\"አሸነፍኩም አላሸነፍኩም የውድድሩን ቪዲዮ ቁጭ ብዬ እመለከታለሁ። ትኩረቴን እና ሙሉ ጊዜዬን ለአትሌቲክሱ ነው የምሰጠው\" ትላለች። በኔዘርላንድም አመርቂ ውጤት ለሚያስመዘግቡ አትሌቶች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ሲፈን ትናገራለች። • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች \"ከፌዴሬሽን ሰዎች ጋር መጣላት ብሎ ነገር የለም። 'ምን እናድርግልሽ?' 'ወደየትኛው የልምምድ ማዕከል መሄድ ትፈልጊያለሽ?' ነው የሚሉት። ለልምምድ ወደ ሌላ አገር ብሄድ እንኳ 'የሆቴል እና የምግብ ወጪሽን እኛ ነን የምንከፍለው' ይላሉ።\" ከአትሌቲክስ ጎን ለጎን በኢንቨስትመንት ተሰማርታ እራሷን እና ሌሎችን የመርዳት ጅማሬ ላይ እንዳለች ሲፈን ትናገራለች። በአዲስ አበባ ሩፋኤል ተብሎ በሚጠራው ስፍራ እና ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ሱሉልታ ከተማ ኢንቨስት ለማድረግ ጥረት እየደረገች መሆኗን ትናገራለች። \"ያው እኔ ገና ታዳጊ አትሌት ነኝ። እንደሌሎቹ ያስቀመጥኩት ሚሊዮን እና ቢሊዮን ገንዘብ የለኝም\" የምትለው ሲፈን ወደፊት በኢንቨስትመንቱ ላይ መሰማራት እንደምትፈልግና በተለይ ደግሞ ባደገችባት አርሲ ውስጥ በሚገኙ ትንንሽ ከተሞች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ዕቅድ አላት። \"ተጨቁነው የሚገኙ ሴቶችን እና ታዳጊ ሴት ህጻናትን መርዳት እፈልጋለሁ። ለእራሴ ገንዘብ ማጠራቀም እና ሃብት ማካበት ብቻ ሳይሆን ሌሎችን መርዳት እና ተደስተው መመልከትም ሌላ ሃብት ነው ብዬ ነው የማስበው።\" የምፈራው አትሌት የለኝም የምትለው ሲፈን \"የምፈራው አትሌቶችን ሳይሆን እሩጫን ነበር። ሁሌም ማሸነፍ ነው የምፈልገው። ለቅጽበትም ቢሆን መሸነፍን አላስብም። ጠንካራ አትሌት ነች ብዬ የማስባት አትሌት አልማዝ አያናን ነው። አደንቃታለሁ።\" ከስድስት ወር በፊት በእስልምና ሥርዓት መሰረት ኒካህ ያሰረችው ሲፈን፤ ከኦሮምኛ በተጨማሪ የደች እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን እንደምትችል አማርኛም ትንሽ ትንሽ እንደምትሞክር ትናገራለች። የሲፈን የቀድሞ አሰልጣኝ አልቤርቶ ከአበረታች እጽ ጋር በተያያዘ ከአሰልጣኝነት መታገዳቸው ይታወሳል። የቀድሞ አሰልጣኟ ከአትሌቲክሱ እንዲታገዱ መደረጉ በእርሷ ላይ ያስከተለው አሉታዊ ተጽእኖ ስለመኖሩ የተጠየቀችው ሲፈን፤ \"ይህ ከእኔ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። እሱ የታገደበት ምክንያት የተፈጠረው ከአስር ዓመት በፊት ነው። እኔ አልቤርቶ መልካም ሰው መሆኑን እና አትሌቶችን ለመርዳት ብዙ የሚጥር ሰው መሆኑን ነው የማውቀው። እኔ በንጹህ ስፖርት ነው የማምነው። ይሁን እንጂ የአልቤርቶ ነገር በጣም አሳዝኖኛል።\" ጃፓን ቶኪዮ ውስጥ በሚካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ለመወዳደር ከ800 እስከ 10 ሺህ ሜትር ባሉት የውድድር መስኮች ላይ ለመወዳደር ዕቅድ አላት። \"ጊዜው ሲቃረብ ጠንካራ የሆንኩበትን እመርጣለሁ። ግን 5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር የምመርጥ ይመስለኛል\" ትላለች ሲፈን።", "የ53 ዓመቱ ፕሮፌሽናል እግር ኳሰኛው ካዙ እርግጥ ነው የጃፓን ሊግ ካፕ ጨዋታዎች ይህን ያህል የዓለም አቀፍ ዘገባዎች ርዕስ አይሆኑም። በሃገሪቱ ዋናው ሊግ የሚጫወተው ዮካሃማ የስፖርት ክለብ ባለፈው ወር ያሰለፈው ተጫዋች ግን የብዙዎችን ዓይን ስቧል። የዮካሃማ አምበል ካዙዮሺ ሚውራ 53 ዓመቱ ነው። ካዙዮሺ ከክለቡ ጋር የነበረውን ውል ሲያራዝም ቢቢሲና ሴኤንኤንን ጨምሮ በርካቶች አስደናቂ ዜና ሲሉት አውርተዋል። ሰውዬው በዕድሜ ትልቁ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ የጊነስ አስደናቂ ድርጊቶች መዝገብ ላይ መሥፈር ችሏል። ወዳጆቹ ‘ንጉስ ካዙ’ እያሉ የሚጠሩት ካዙዮሺ ማነው? እንዴትስ ይህን ሁሉ ዓመት እግር ኳስ ሊጫወት ቻለ? ካዙ ታሪኩ የሚጀምረው 1970 [በአውሮፓውያኑ] ነው ይላል። ምክንያቱ ደግሞ ፔሌ እና የአባቱ 8 ሚሊሜትር ካሜራ። የካዙ ቤተሰቦች እግር ኳሰኞች ናቸው። ታላቅ ወንድሙ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። አባቱ ደግሞ በእግር ኳስ ፍቅር የወደቁ ሰው ነበሩ። “አባቴ 1970 ሜክሲኮ የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ ለማየት ሄዶ ነበር። ጨዋታዎቹን በ8 ሚሊሜትር ካሜራው ይቀርፃቸው ነበር።” ወቅቱ ብራዚላዊ ፔሌ የገነነበት ነበር። የካዙ አባት ፔሌ ኳሷን ሲያንቀረቅብ የቀረፁትን ይዘው መጥተው ለካዙ ያሳዩታል። ካዙም በእግር ኳስ ፍቀር ተነደፈ። ካዙ በወቅቱ ገና የ3 ዓመቱ ልጅ ነበር። ነገር ግን አባቱ የቀዱትን የፔሌ ቪድዮ አይቶ አይጠግብም ነበር። እያደገ ሲመጣ ከብራዚል እግር ኳስ በቀር ሌላ ነገር አታሳዩኝ ይል ጀመር። “ገና ከልጅነቴ ጀምሮ እግር ኳስ በጣም እወድ ነበር። ወደፊት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች እሆናለሁ እያልኩ እመኝ ነበር።“ የካዙ አባት ብራዚል ውስጥ ሥራ አገኙ። ቤተሰቡም ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ሳዎ ፓውሎ አመራ። ካዙ በልጅነቱ ሳዎ ፓውሎ ውስጥ ለሚገኝ አንድ ጁቬንቱስ ለተሰኘ ክለብ መጫወት ጀመረ። ነገር ግን ሕይወት ቀላል አልነበረችም። አብረውት የሚኖሩት ዕድሜያቸው ከ15-20 የሚሆኑ ብራዚላዊያን ናቸው። ካዙ ደግሞ ፖርቼጊዝ [የብራዚል መግባቢያ ቋንቋ] ገና አልለመደም። “ቋንቋው ሊገባኝ አልቻለም። ባሕሉም ለኔ እንግዳ ነበር። በጣም ብቸኝነት ይሰማኝ ነበር። በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት እጅግ ከባድ ነበሩ።” ቢሆንም ካዙ ተስፋ አልቆረጠም። በየቀኑ ልምምድ ያደርግ ጀመረ። ቋንቋ ማጥናቱንም ተያያዘው። እንደው በእግር ኳስ ባይሳካልህ ኖሮ በምን ሙያ ትሰማራ ነበር? ከቢቢሲ ለካዙ የቀረበ ጥያቄ። ካዙ ትንሽ ከቆዘመ በኋላ “እውነት ለመናገር ምንም አላውቅም። ሁሌም ምኞቴ እግር ኳሰኛ መሆን ነበር። ይህ በጣም ከባድ ጥያቁ ነው።” ከሶስት ዓመታት በኋላ ለሳንቶስ ፈረመ። በአባቱ ካሜራ ያየው የነበረው ፔሌ ልጅነቱን ያሳለፈበት ሳንቶስ። ካዙ ብራዚል ውስጥ ለተለያዩ ክለቦች ተጫውቷል። ወደ ጃፓን የተመለሰው 1990 [በአውሮፓውያኑ] ነበር። 1993 ላይ ጄ-ሊግ [የጃፓን ፕሪሚዬር ሊግ] ተመሠረተ። በወቅቱ ካዙ እጅግ ውድ ተጫዋች ነበር። በሚቀጥለው ዓመት ወደ ጣልያን አምርቶ ለጄኔዋ በመጫወት ታሪክ ሠራ - በሴሪአው የተጫወተ የመጀመሪያው ጃፓናዊ በመሆን። በመጀመሪያ ጨዋታው ከወቅቱ የጣልያን ኮከብ ፍራንኮ ባሬሲ ጋር ተጋጭቶ ተጎዳ። ከጄኖዋ ጋር የነበረው ጊዜም ይህን ያህል ውጤታማ አልነበረም። ወደ ሃገር ቤት ሲመለስ ግን ብዙዎች በአድናቆት ተቀበሉት። የጃፓን የስፖርት ጋዜጠኞች ካዙ ማለት ለጃፓን እግር ኳስ መዘመን ትልቅ ሚና የተጫወተ ሰው ነው ይላሉ። አርጀንቲና ማራዶና እንዳላት ሁሉ ጃፓንም ካዙ አላት ይላል የስፖርት ጋዜጠኛው ሾን ካሮል። ካዙ አሁን ለሚጫወትለት ዮካሃማ ክለብ የፈረመው 2005 ላይ ነው። በ38 ዓመቱ። ክለቡ በሱ መሪነት ከታችኛው ሊግ ወደ ዋናው ጄ-ሊግ በአንድ ዓመት አደገ። ነገር ግን ክለቡ ተመልሶ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ታችኛው ሊግ ወረደ። ካዙ ግን ከክለቡ ጋር መቆራረጥ አልመረጠም። ካዙዮሺ በሚሠራቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እጅጉን ይታወቃል። “እርግጥ ነው እንደ ወጣት ተጫዋቾች ለኔ ሁሉም ነገር ቀላል አይደለም። ነገር ግን እግር ኳስን በጣም ስለምወድ አደርገዋለሁ።“ ካዙ ይህን ሁሉ ዓመት በእግር ኳስ መቆየት የቻለው የሰውነት ብቃቱን በመጠበቁ ብቻ አይደለም። ባሕሪውም አስተዋፅዖ አድርጎለታል። ብዙዎች ከሱ ጋር የተጫወቱም ሆኑ እሱ ሲጫወት የተመለከቱ ፀባዩ እጅግ መልካም እንደሆነ ተናግረው አይጠግቡም። ለዚህም ነው ጃፓናውያን እጅግ የሚወዱት ይላሉ። በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት ለሌለው ዮካሃማ የእግር ኳስ ቡድን እየተጫወተ እንኳ እሱ ይሰለፋል ሲባል ተጨማሪ 3 ሺህ 4 ሺህ ሰዎች ወደ ስታድየም ይመጣሉ። ካዙ አሁን ለሚጫወትበት ክለብ ብዙ ጊዜ ሲሰለፍ ባይስተዋልም ክለቡ ግን ልምዱን በጣም ይፈልገዋል። ለዚህም ነው ውሉን ያራዘሙለት ይላሉ የጃፓን ስፖርት ጋዜጦች። “መልበሻ ክፍል ውስጥ የሱ መኖር ትልቅ ለውጥ ይፈጥራል። ጃፓን ደግሞ በዕድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች የሚከበሩባት ሃገር ናት” ይላል ጋዜጠኛው ሾን። በዚህ ዕድሜህ እግር ኳስ ለመጫወትህ ሚስጥሩ ምንድነው የሚለው ጥያቄ ለካዙ ብርቅ አይደለም። እሱ ግን እንዲህ ይላል፤ “ምንም ሚስጢር የለውም - ጠንክሮ መሥራትና መሰጠት እንጂ።”", "በአውስትራሊያ የውድድር ፈረሶች እየታረዱ ነው በሚል የቀረበው ውንጀላ ላይ ምርመራ ተጀመረ በአውስትራሊያዋ ኩዊንስላንድ ግዛት ውስጥ በሚገኝ የእርድ አገልግሎት መስጫ- ቄራ ውስጥ ፈረሶች ሲጉላሉና ሲጎሳቆሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በኤቢሲ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከተላለፈ በኋላ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። በቴሌቪዥን ጣቢያ የተሰራ ዘገባ እንደሚያሳየው ከግልቢያ ውድድር የሚገለሉ ፈረሶች እየታረዱ መሆናቸውን ነው። በአውስትራሊያ ፈረሶችን ማረድ ሕጋዊ ቢሆንም በአንዳንድ ግዛቶች ግን ከውድድር በጡረታ የተገለለ ፈረሶች ወደ ሌላ የእንስሳት ማቆያ እንዲዛወሩ ብቻ ይፈቅዳሉ። በአውስትራሊያ የፈረስ ግልቢያ ተወዳጅ ስፖርት ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብም ይገኝበታል። • የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አንደማይልክ አስታወቀ • ሜክሲኮ ውስጥ የኤል ቻፖን ልጅ ለመያዝ ከባድ ውጊያ ተደረገ • \"አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው\" አቦይ ስብሃት ባለስልጣናት በቅርቡ ከሚካሄደው የፈረስ ግልቢያ ውድድር አስቀድሞ የቀረበውን ይህንን ውንጀላ አስመልክተው በሰጡት ምላሽ \"አስደንጋጭ\" ብለውታል። \"እንስሳትን ማጎሳቆልና ማንገላታት አስነዋሪ ተግባር ነው\" ያሉት የኪዊንስላንድ የግልቢያ ውድድር ሚኒስትር ስተርሊንግ ሂንቺልፍ ናቸው። የአካባቢው አስተዳደር በኤቢሲ ዘገባ ላይ ወደ ተጠቀሰው የእርድ አገልግሎት መስጫ ባለሙያዎችን ወዲያውኑ መላካቸውን አስታውቀዋል። የእርድ አገልግሎት በሚሰጠው በዚህ ቄራ ውስጥ በ22 ቀን ብቻ 300 የውድድር ፈረሶች መታረዳቸው በቴሌቪዥን ጣቢያው ዘገባ ላይ ተጠቅሷል። ዘገባው አክሎም ፈረሶች በዚህ ቄራ ውስጥ ይመታሉ፤ ይንገላታሉ ሲል ይጠቅሳል። የአውስትራሊያ የፈረስ ግልቢያን የሚያስተዳድረው አካል ፈረሶች ጡረታ ወጥተው ከውድድር ከራቁ በኋላ እምጥ ይግቡ ስምጥ ማወቅ አልቻልኩም ሲል ተናግሮ ነበር። ይህንን መዝግቦ በመያዝ የሚከታተል አካል በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲቋቋምም ሃሳብ አቅርቦ ነበር። የፈረስ ግልቢያ ውድድር የሚያካሂደው አካል በእንስሳት መብት ተሟጋቾች ለዓመታት ይብጠለጠል ነበር። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቅርቡ የሚካሄደውን የፈረስ ግልቢየያ ውድድር ይታደሙታል ተብሎ ይጠበቃል።", "ኢትዮጵያውያኑ ጎተይቶም ገብረ ስላሴና ጉዬ አዶላ በበርሊን ማራቶን አሸናፊ ሆኑ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ጎተይቶም ገብረ ስላሴና ጉዬ አዶላ በዛሬው ዕለት በጀርመኗ መዲና በርሊን በተካሄደውን የማራቶን ውድድር በሴቶችና በወንዶች ዘርፍ በአንደኛነት አጠናቀዋል። በሴቶች የማራቶን ውድድር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ስፍራ የያዙት ኢትዮጵያውያን ናቸው። በወንዶች የማራቶን ውድድር ከፍተኛ ግምት የተሰጠውና ከወራት በፊት ከኮሮናቫይረስ ህመም ያገገመው ቀነኒሳ በቀለ በሶስተኛነት አጠናቋል። ጉዬ አዶላ በ2፡05፡45 ሰዓት የአሸናፊነቱን ስፍራ ሲይዝ ኬንያዊው የጎን ቤትዌል ሁለተኛ፣ ቀነኒሳ በቀለ ሶስተኛ፣ ታዱ አባተ አራተኛ ስፍራን ይዟል። የ30 አመቱ ጉዬ አዶላ ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የመጀመሪያ በሆነው ውድድን የአለም ክብረ ወስንንና ሁለት ጊዜ የአለም ሻምፒዮና ከሆነው ኢሉይድ ኪፕቾጌን በመከተል ሁለተኛ ወጥቷል። በሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነችው ጎተይቶም ገብረሥላሴ የበርሊን የማራቶን ውድድር የመጀመሪያዋ ነው። ጎተይቶም ይህንን ውድድር በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ09 ስታጠናቀቅ ሕይወት ገብረ ኪዳን በ2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ሁለተኛ በማሸነፍ የብር ሜዳሊያዋን አሸንፋለች። በሶስተኛ ደረጃም ኢትዮጵያዊቷ ቶላ በሶስተኛነት ውድድሩን አጠናቃለች። ጉዮ ማነው? ብዙ ያልተባለለት የ26 አመት እድሜ ያለው ጉዬ አዶላ ድንገት ከየት ተገኘ? በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ቢሉ በምትባል አካባቢ የተወለደው ጉዬ፤ እንደ ቀደሙት አትሌቶች ሩጫን የጀመረው በህፃንነቱ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ነው። ዕድሜው 17 ሲሞላ ለቀጣይ ስልጠናዎች አዲስ አበባን መዳረሻው አደረገ። የአምቦ አትሌቲክስ ክለብ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ተፈሪ መኮንን በሩጫ ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ አበክሮ የሚናገረው ጉዬ፤ የሩጫ ህይወቱ ግን ማንሰራራት የጀመረው በኦሮሚያ የውሃ ሥራዎች ክለብ ቆይታው ነበር። የመጀመሪያው ትልቅ ውድድር የነበረው ከሦስት ዓመታት በፊት ማራኬሽ ከተማ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ነው። ይህም ለቀጣይ ውድድሮቹ ፈር የቀደደለት ሲሆን፤ በዚያው ዓመትም በተመሳሳይ ርቀት እንዲሁም በ10 ኪ.ሜ ብዙ ውድድሮችን አድርጓል። ነገር ግን ብዙ የሚያስደስት ውጤት ማምጣት አልቻለም። \"የጤና እክል ደርሶብኝ ስለነበር ምግብ መመገብ ከብዶኝ ነበር\" በማለት የሚናገረው ጉዬ፤ \"ሰው ካልበላ ደግሞ መሮጥ ከባድ ነው፤ ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ቀላል የማይባሉ የእግር ጉዳቶች ደርሰውብኝ ነበር\" ይላል። ብዙዎች አትሌቶች ከድህነት በመውጣት የተሻለ ህይወትን ለማግኘት ሩጫን እንደ መውጫ መንገድ ያዩታል። የጉዬም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። \"ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ምን አይነት ህይወት እንደሚመሩ ከዚያው የመጡ ያውቁታል። ከደሃ ቤተሰብ ነው የመጣሁት፤ ሩጫ ከጀመርኩ በኋላ ግን የቤተሰቦቼ ህይወት ላይ መሻሻል አለ\" በማለት ይናገራል። ከእሱ በፊት የመጡ የሩጫ ጀግኖች የሚላቸውን የእነ ቀነኒሳ በቀለ እንዲሁም የጥሩነሽ ዲባባን ስኬት ማየቱ ትምህርቱን ዘጠነኛ ክፍል ላይ አቋርጦ ለሩጫ ሙሉ ትኩረቱን እንዲሰጥ አደረገው። የእሁድ ዕለቱ ድልም በሩጫ ዘመኑ ሁለተኛ የሚባለውን የ24 ሺህ ዶላር ሽልማትን አስገኝቶለታል። ከሦስት ዓመታት በፊት ከፍተኛ የሚባለውን ብር ያገኘው ህንድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሲሆን፤ ከማሸነፉ በተጨማሪ አዲስ ክብረ-ወሰንም አስመዝግቧል። በወቅቱ የተከፈለውም 35 ሺህ ዶላር ነበር። ከበርሊን ውድድር በኋላ ጣልያናዊው ማኔጀሩ ዝናውም ሆነ የሚያገኘው ብር ይቀየራል በማለትም አስተያየቱን ይሰጣል። \"በዚህ ውድድር ላይ ያሸንፋል ተብሎ ስላልተጠበቀ፤ በአዘጋጆቹ የተሰጠው ክፍያ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።\" በማለት የሚናገረው ጂያኒ ዲማዶና \"ከዚህ በኋላ ግን ጠቀም ያለ ክፍያ ይሰጡታል\" ይላል። ተጨማሪ የማራቶን ተስፋዎች ጉዬ የእራሱ ቤት የለውም፤ አላገባም። ነገር ግን በበርሊን ላይ ካሸነፈ በኋላ ብሩህ ተስፋ እንደሚታየው ተናግሯል። ጂያኒ ዲማዶናም የአሁኑን የጉዬን ድል እንደ ትልቅ ስኬት በማየት፤ ቀጣዩ ዝግጅታቸው በሚያዝያ ወር ላይ ለሚካሄደው ትልቁ የለንደን ማራቶን መሆኑን ይናገራል።", "ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ሦስቱ ዕጩዎች እነማን ናቸው? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ እና ነገ ጠቅላላ ጉባዔውን በማካሄድ የሚመራውን ፕሬዝዳንት ምርጫ እንደሚያካሄድ የወጣው መረጃ ያሳያል። ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት በዕጩነት ሦስት ሰዎች ቀርበዋል። እነዚህም በአሁን ወቅት በፕሬዝዳንትነት ፌዴሬሽኑን እያገለገሉ ያሉት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ አቶ ቶኪቻ አለማየሁ እንዲሁም አቶ መላኩ ፈንታ ናቸው። ከፕሬዝዳንት ምርጫ ውጪ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለመሆን 32 ዕጩዎች ቀርበዋል። እነዚህ ዕጩዎች በምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ መታየታቸው ተግልጿል። የሚመረጠው ፕሬዝዳንት ስፖርቱን ማሳደግ፣ ማዘመን እንዲሁም ብሔራዊ ቡድኑ ደረጃውን የጠበቀ መጫወቻ ሜዳ እንዲኖረው ማድረግ ከሚጠበቁበት ዐበይት ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ። ይህ ጠቅላላ ጉባኤ መጀመሪያ ጎንደር ከተማ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጓል። ሦስቱ ለፕሬዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎች ሁለት ክልልን እና አንድ የከተማ አስተደደርን ወክለው ይወዳደራሉ። ስለዕጩዎቹ ከምናውቀው በጥቂቱ . . . አቶ ኢሳያስ ጅራ ላለፉት አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት የመሩ ሲሆን፣ ለቀጣይ አራት ዓመታት በአመራርነት ለመቀጠል እየተወዳደሩ ይገኛሉ። ከፌደሬሽኑ ውጪ የሴካፋ፣ የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ውድድር ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። አቶ ኢሳያስ የኦሮሚያ ክልልን ወክለው ነው የሚወዳደሩት። ከአራት ዓመት በፊት በ2010 ዓ.ም፣ የጂማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ሥራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገሉ ባለበት ወቅት ነው ተወዳድረው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት። ከ20 ዓመታት በላይ በስፖርት አመራርነት የቆዩት አቶ ኢሳያስ፣ በጂማ እና በሰበታ እግር ኳስ ቡድኖች በአመራርነት ሠርተዋል። ባለፉት ዓመታት “ደረት የሚያስነፋም ባይሆን አንገት የማያስደፋ ሥራ” መስራታቸውን ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት ተናግረው ነበር። “ተጨባጭና በአይን የሚታይ ሥራ ሰርተናል” የሚሉት አቶ ኢሳያስ ዳግም ቢመረጡ የጀመሯቸውን መልካም ነገሮች ማስቀጠል፣ ሊሰሯቸው አቅደው በተለያየ ምክንያት ያልተሳኩትን ደግሞ ማከናወን እቅዳቸው ነው። ከእቅዳቸው መካከል ዐቢይ የሆነው “የክለቦች አደረጃጀት ላይ መሥራት” መሆኑን ይናገራሉ። ከሦስቱ ዕጩዎች መካከል በዕድሜ ትንሹ አቶ ቶኪቻ፣ 39 ዓመታቸው ነው። በ1975 ዓ.ም በኢሉ አባ ቦራ በጎሬ ከተማ የተወለዱት ቶኪቻ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን በመወከል ነው የቀረቡት። በእንግሊዝ አገር፣ ሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ በሲቪል ምህንድስና የተመረቁት አቶ ቶኪቻ፣ በሥራ ፈጠራ ስማቸውን የተከሉ ናቸው። በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሠሩ ሲሆን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። የድሬ ዳዋ ከነማ እግር ኳስ ቡድንን በገንዘብ የሚደግፉት አቶ ቶኪቻ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ መሠረታዊ ለውጥ እንደሚያስፈልገው ያምናሉ ። የስፖርት ተቋማት ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ቡድኖች (ክለቦች) ድረስ በጥምረት መስራት አለባቸው ይላሉ። ቀጣይ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ፌዴሬሽኑን በፋይናንስ ማጠንከር፣ እንዲሁም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሚሰማሩ ገልፀዋል። በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እና የዓለም እግር ኳስ የበላይ አካል ውስጥ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በአመራርነት እንዲሳተፉ ማድረግ ከእቅዶቻቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። አቶ መላኩ ፈንታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ለመሆን የሚወዳደሩት የአማራ ክልልን ወክለው ነው። አቶ መላኩ ኢኮኖሚክስ እና ቢዝነስ አስተዳደር ያጠኑ ሲሆን በገቢ እና ጉምሩክ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው። በሠራተኛ እና ማኅበራዊ ሚኒስቴር እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ሠርተዋል። አቶ መላኩ የቀድሞ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው ለበርካታ ዓመታት አገለግለዋል። አቶ መላኩ ፈንታ ፖለቲካዊ ነው በሚሉት በከፍተኛ ሙስና ክስ ከሥልጣናቸው ተነስተው ለአምስት ዓመታት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ነው የተፈቱት። ባለፉት አራት ዓመታት በአማራ ልማት ማኅበር ከዚያም በቅርቡ ተመስርቶ ሥራ በጀመረው የአማራ ባንክ ውስጥ በግንባር ቀደምትሲሰሩ ቆእተዋል። በእግር ኳስ ዘርፍም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ካሉ ጠንካራ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብን በቦርድ አባልነት ያገለግላሉ። ከተመረጡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ውስጥ ያላትን ተሰሚነት ለመጨመር እንደሚሰሩ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። በተጨማሪም የተመረጡ ስታዲየሞች በአጭር ጊዜ ተጠናቅቀው “ስደተኛው የእግር ኳስ ቡድናችን በሜዳው እንዲጫወት እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል። “እግር ኳሳችን ትንሳዔ ያስፈልገዋል” ያሉት አቶ መላኩ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩም ተናግረዋል።", "ቼልሲ ከ ዩናይትድ ማን ያሸንፋል? የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች የ26ኛው ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረግ ግጥሚያ ይጀምራሉ። በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ የተባለው ቼልሲን ከማንችስተር ዩናይትድ ያፋጥጣል። ማን ያሸንፋል? የቢቢሲው ስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶቹን አስቀምጧል። ዎልቭስ እና ሌስተር በዘንድሮ የውድድር ዓመት ድንቅ አቋም እያሳዩ ይገኛሉ። ሁለቱም በመጀሪያዎች አራት ውስጥ ሆነው የመጨረስ ዕድል አላቸው። ዛሬ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሲል ፕሪሚየር ሊጉ ዎልቭስን ከሌስተር ያገናኛል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ድንቅ ጨዋታ እንደሚታይበት ይጠበቃል። ባለፈው የውድድር ዓመት ዲኦጎ ጆታ ሦስታ (ሃትሪክ) በሠራበት ግጥሚያ ዎልቭስ ሌስተርን አስተናግዶ 4-3 ማሸነፍ ችሎ ነበር። ዛሬስ? ላውሮ የዎልቭስ ልጆች ሌስተርን 2ለ1 አሸንፈው በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ከቶተንሃም አናት 6ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ ብሏል። ነገ ቅዳሜ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። 09፡30 ሲል ሳውዝሃምፕተን ከበርንሌይ ይገናኛሉ። ላውሮ ይህ ጨዋታ በባለ ሜዳዎቹ ሳውዝሃምፕተኖች በድል ይጠናቀቃል ብሏል። ቅዳሜ ምሽት 02፡30 ላይ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ የሆኑት ሊቨርፑሎች ወደ ካሮ ሮድ አቅንተው በፕሪሚየር ሊጉ መጨረሻ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ኖርዊች ጋር ይገናኛሉ። ላውሮ አይበገሬዎቹ ሊቨርፑሎች ቢያንስ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸንፋሉ ይላል። ቶተንሃሞች ከማንችሰተር ሲቲ ወሳኝ የሆኑ 3 ነጥቦችን መሰብሰባቸው ይታወሳል። አሁንም ቢሆን አስተማማኝ የሆነ ወጥ አቋም ላይ ባይገኙም ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ ጥርጥር ይለኝም ይላል ላውሮ። አስቶን ቪላ 0 ቶተንሃም 2 ሲል ግምቱን ያስቀመጠው ላውሮ ነው። ሌላው በጉጉት የሚጠበቀው ጨዋታ ኢምሬትስ ላይ የሚካሄደው የአርሴናል እና ኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ነው። አርሰናሎች የአቻ ባለሙያዎች የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷቸዋል። በዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ካደረጓቸው 25 ጨዋታዎች 13ቱ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቁት። ይህን ጨዋታ ግን በደጋፊዎቻቸው ፊት እንደሚያሸንፉ ተስፋ አደርጋለሁ ይላል ላውሮ። ውጤት አርሰናል 2 ኒውካስል 0 ። የሳምንቱ ሌላው ወሳኝ ጨዋታ ቼልሲን ከ ማንችስተር ዩናይትድ ያገናኛል። ሰኞ ምሽት በሚካሄደው ጨዋታ ላውሮ ቼልሲ የበላይነት ይዞ እንደሚያጠናቅቅ ግምቱን አስቀምጧል። የላውሮ ግምት ቼልሲ 2 ማንችስተር ዩናይትድ 0 ። ረቡዕ የካቲት 11 ከምሽቱ 4፡30 ላይ ሲቲዎች የለንደኑን ክለብ ዌስት ሃም ዩናይትድን ያስተናግዳል። ሲቲ ይህን ጨዋታ በብዙ የጎል ልዩነት እንደሚያሸንፍ ተገምቷል። ላውሮ ሲቲ ይህን ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ያሸንፋል ብሏል።", "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ውጤት ካሳጡ ምክንያቶች መካከል አምስቱ ኢትዮጵያ ካሜሩን በተዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፋ ሦስት ጨዋታዎችን አድርጋ ከነበረችበት ምድብ ማለፍ ባለመቻሏ ከውድድሩ ተሳናብታለች። በምድብ 'ሀ' ከካሜሩን፣ ቡርኪናፋሶ እንዲሁም ኬፕ ቬርድ ጋር ተደልድላ የነበረችው ኢትዮጵያ በሁለቱ ጨዋታዎች ተሸንፋ በአንድ አቻ በመውጣት በአንድ ነጥብ ውድድሩን አጠናቃለች። በአፍሪካ ዋንጫ ከተሳተፉ 24 አገራት መካከል በአማካይ ወጣት የሚባሉ ተጨዋቾችን ከያዙ ቡድኖች ውስጥ የተመደበችው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዙር 16 መሻገር ተስኖት ወደ አገሩ ተመልሷል። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በተሳተፈችበት የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ በተመሳሳይ በሁለት ጨዋታዎች ተሸንፋ በአንድ አቻ ውጤት መሰናበቷ የሚታወስ ነው። ለመሆኑ ዋሊያዎቹ በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፏቸው ወደ ቀጣይ ዙር እንዳይልፉ ያገዳቸው ምንድነው? ልምድ? ተጫዋቾች የሚፈፅሙት ስህተት? ወይስ ሌላ? ከዚህ በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደፊት እንዳይገሰግስ ያደረጉ የተባሉ አምስት አበይት ምክንያቶችን እናያለን። ልምድ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከመጨረሻው ጨዋታ በኋላ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ወደቀጣዩ ዙር ላለማለፋቸው እንደ አንደኛው ምክንያት አድርገው የጠቀሱት የተጫዋቾች ልምድ ማነስ ነው። \"ብዙ ወጣት ተጫዋቾች አሉን። እነዚህ ተጫዋቾች ልምድ እያገኙ ሲሄዱ ነገሮች ይሻሻሉ። በሚቀጥለው የአፍሪካ ዋንጫ ተመልሰን እንመጣለን የሚል ተስፋ አለኝ\" ብለዋል። ለተለያዩ የስፖርት ትንታኔ አውታሮች በመፃፍ የሚታወቀው ፍሬው አሥራት ይህንን የአሰልጣኑን ሐሳብ ትክክል ነው በማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ልምድ ያንሳቸዋል ይላል። \"ሦስት ተጫቾች ብቻ ናቸው ቀደም ባለው የአፍሪካ ዋንጫ የተጫወቱት። ከእነዚህ መካከል ጀማል በሦስተኛ ግብ ጠባቂነት ቢሄድም አልተሰለፈም። ሽመልስንም በጉዳት ምክንያት አልሄደም። ጌታነህ ብቻ ነው መሰለፍ የቻለው።\" አሁን ካሜሩን ሄዶ በመጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ጥቂት ተጫዋቾች ሩዋንዳ ተካሂዶ በነበረው የቻን ውድድር ላይ እንደተሳተፉ ፍሬው ያስታውሳል። ነገር ግን እንደ አፍሪካ ዋንጫ ዓይነት ትልቅ ውድድር ላይ የተሳተፉ ብዙ ተጫዋቾችን ያቀፈው ብሔራዊ ቡድኑ ልምድ ያንሰዋል ቢባል ስህተት አይደለም ይላል ፍሬው። አሠልጣኝ ውበቱ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የተገኙ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ከዚህ ውድድር አንድ ያገኙት ነገር ቢኖር ልምድ እንደሆነ ይናገራሉ። \"ልምድ በአንድ ጀንበር አይገኝም። ለዚህም ነው ጨዋታዎችን በማድረግ የተሻለ ልምድ ማግኘት አለብን ብዬ የማስበው።\" ነገር ግን ፍሬው \"በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ታላላቅ ቡድኖችን ያሸነፉት ኢኳቶሪያል ጊኒና ኮሞሮስን ስንመለከት አብዛኞቹ ተጫዋቾች በፈረንሳይ፣ በጣልያንና በስፔን በሚገኙ ትናንሽ ዲቪዚዮኖች የሚጫወቱ ናቸው\" ይላል። \"ይሄን ተመልክተን የእኛ ልጆች አገር ቤት በመጫወታቸው ነው የተጎዳነው ማለት ላያሳምን ይችላል። ምናልባት የእኛ ሊግ ትናንሽ ናቸው ከሚባሉት ዲቪዚዮኖች ያነሰ ይሆን? እኔ አላውቅም።\" ስህተት ዋሊያዎቹ ከዚህ በፊትም የሚታሙበትን በ2021 የአፍሪካ ዋንጫም የተስተዋለባቸው አንድ ችግር ቀላል የሚባሉ ስህተቶችን መፈፀም ነው። በፈረንጆቹ 2013 በደቡብ አፍሪካ ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ከዛምቢያ ጋር የተፋለሙት የዋሊያዎቹ ግብ ጠባቂ ከክልሉ ውጪ በፈፀመው ስህተት በቀይ ካርድ እንደተሰናበተባቸው የሚታወስ ነው። ፍሬው ይህ በመጀመሪያው ጨዋታ የቡድን አባልን በቀይ ካርድ የማጣት ክስተት በዚህኛው የአፍሪካ ዋንጫ መደገሙ አሳሳቢ ነው ይላል። \"ቀይ ካርዱን [ያሬድ ባየህ የኬፕ ቬርድ ተጫዋች ላይ የፈፀመው ጥፋትን ተከትሎ የተሰጠው] ማንሳት ትችላለህ። ንቁ አለመሆኑ እና አደገኛ ኳሶችን ተመልክቶ በፍጥነት እርምጃ አለመውሰድ ይታይብናል።\" ቡድኑ በካሜሩን አራት ለአንድ እንዲሁም በኬፕ ቬርድ አንድ ለዜሮ ሲሸነፍ የተመዘገቡት እንዲሁም ከቡርኪና ፋሶ ጋር አቻ ሲለያይ የተቆጠረበት ግብ ሊወገዱ በሚችሉ ቀላል ስህተቶች የተፈጠሩ ናቸው ሲል ፍሬው ያምናል። ፍሬው እንደሚለው ብሔራዊ ቡድኑ ተቀባብሎ ወደ መሃል ሜዳ ያሻገረው ኳስ ተመልሶ ዋሊያዎቹ ላይ አደጋ ሲፈጥር በተደጋጋሚ ይታያል። ዋሊያዎቹ በማጣሪያ አሊያም የዋንጫ ውድድር ጨዋታዎች ላይ ሊወገዱ የሚችሉ ስህተቶች ሲፈፅሙ እንዲሁ የትኩረት ማጣት ሲታይባቸው ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። አሠልጣኝ ውበቱ አባተም በዚህ የሚስማሙ ይመስላሉ። ከካሜሩን ጨዋታ በፊት ለጋዜጠኞች አሠልጣኙ ሲናገሩ ኬፕ ቬርድ በመጀመሪያዋ አጋማሽ መገባደጃ ያስቆጠሩት ጎል የተጫዎች የትኩረት ማነስ እንደሆነ ተናግረው ነበር። የአጨዋወት ስልት የዋሊያዎቹን የምድብ ጨዋታዎች በአሃዝ ስንመለከት ከካሜሩንና ከኬፕ ቬርድ ጋር በነበሩ ጨዋታዎች ብልጫ እንደተወሰደባቸው መመልከት ይቻላል። ምንም እንኳ በመጀመሪያው ጨዋታ ቡድኑ አብዛኛውን ክፍለ ጊዜ አንድ ተጫዋች ጎድሎበት በ10 ተጫዋቾች ቢጫወትም ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ኳስን ተቆጣጥሮ የመጫወት ስልት ብዙ አልተስተዋለም። በካሜሩን ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ብዙዎችን ያስደነቀ ብቃት ያሳዩት ዋሊያዎቹ በሁለተኛው አጋማሽ ፍፁም ብልጫ ተወስዶባቸው ታይተዋል። \"በተለይ በተጋጣሚዎች የግብ ክልል አቅራቢያ ብዙም አመርቂ ነገር አላሳየንም\" ይላል ፍሬው። ቡርኪና ፋሶ ተዳክማ በቀረበችበት፤ ዋሊያዎቹ ደግሞ የተሻለ ብቃት ያሳዩበትን የመጨረሻው ግጥሚያ የድኅረ-ጨዋታ ትንተናን ስንመለከት ዋሊያዎቹ ኳስን ቢቆጣጠሩም በተቀናቃኝ ግብ አካባቢ የነበራቸው ድርሻ ቀዝቀዝ ያለ ነበር። \"ኳስን መሥርቶ መጫወት የሚፈልግ ቡድን ቢሆንም ብዙዉን ጊዜ ኳሷን በራሱ ሜዳ የሚያንሸራሽር ስብስብ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ወደፊት ያደርግ የነበረው እንቅስቃሴም ይህን ያህል አስፈሪ አልነበረም።\" ፍሬው ሌላው በቡድኑ ላይ ያስተዋለው ነገር ቢኖር \"ፕላን ቢ እንኳን እንደሌለን ነው\" በማለት፤ አንድ ተጫዋች በጉዳት አሊያም በካርድ ሲወጣ አሊያም ሲቀየር ሙሉ በሙሉ የቡድን የጨዋታ ስልት ይቀየራል በማለት ይናገራል። የተጨዋቾች አቅም አሠልጣኝ ውበቱ ከካሜሩን ሽንፈት በኋላ ተጫዋቾቼ የአቅም ማነስ የለባቸውም ምናልባት የሥነ ልቡና መዳከም ይሆናል ያለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ነገር ግን ፍሬው \"ግልፅ የሆነ መደካም ነበር\" በማለት በዚህ የአሰልጣኙ ሐሳብ አይስማማም። \"ጨዋታዎቹ ላይ 50/50 የሆኑ ኳሶችን ታግሎ መቀማት፣ በአየር የሚመጡ ኳሶችን ተሻምቶ ማሸነፍ፣ በመስመር በኩል ፈጣን አጥቂዎችን መቋቋም የሚችል ተከላካይ ነበረን?\" ፍሬውን ጨምሮም በርካታ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሐሳባቸውን ሲሰጡ የነበሩ የእግር ኳስ ወዳጆች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት በተክለ ሰውነት ከሌሎቹ አነስ እንደሚሉ ትዝብታቸውን ሲያሰፍሩ ነበር። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌላው ሲነሳ የነበረው ጉዳይ ጋቶች ፓኖምን የመሰሉ ተጋጣሚዎችን መቋቋም የሚችል ተክለ ሰውነት ያላቸው ተጫዋቾች የመሰለፍ ዕድል አለማግኘታቸው የኳስ ወዳጆች መነጋገሪያ ነበር። የአሠልጣኙ አሠላለፍ ስልት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ በተለምዶ 4-4-3 አሠላለፍ በመጠቀም ይታወቃሉ። ይህም አራት ተከላካዮች፤ ሦስት አማካዮች እና ሦስት አጥቂዎች ማለት ነው። በዚህ አሠላለፋቸው አምበሉን ጌታነህ ከፊት ለፊት የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው አቡበከር ናስርን በግራ አማኑዔል ገብረሚካኤል አሊያም ዳዋ ሆጤሳን በቀኝ ማሠለፍን ይመርጣሉ። ነገር ግን ከቡርኪና ፋሶ ጋር በነበረው የመጨረሻው የምድ ጨዋታ አሠልጣኙ በአራት ተከላካይ፤ በሁለት የተከላካይ አማካይ፤ በሦስት ወደፊት በሚገፉ አማካዮችና በአንድ አጥቂ ነው ወደሜዳ የገቡት። በርካታ የእግር ኳስ ተንታኞችና ጋዜጠኞች እንደሚስማሙት ለምሳሌ አቡበከር ከኬፕ ቬርድ በቀኝ፣ ከካሜሩን ፊት ለፊት ከቡርኪና ጋር በግራ እንዲጫወት መደረጉ ያለውን አቅም አሟጦ እንዲያጠቀም አድርጎታል። አቡበከር ብቻ ሳይሆን ሌሎቹም ተጫዋቾች በክለብ ደረጃ ከሚጫወቱበት በተለየ መልኩ ለብሔራዊ ቡድን እንዲሰለፉ መደረጋቸው አግባብ አይደለም የሚሉ ደምፆች ተሰምተዋል። ፍሬው ከዚሁ ትይዩ ሊነሳ ይገባል የሚለው ወቅታዊ ብቃታቸው መልካም ያልሆነ ተጫዋቾች በቡድኑ መካከተታቸው አሊያም ጥሩ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች አለመጠራታቸው ነው። የዋሊያዎቹ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ዋሊያዎቹ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የመሳተፍ ዕድል አላቸው። በእነዚህ ማጣሪያዎች ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ሌሎች ቡድኑ ያሉበትን ችግሮች መቅረፍ አስፈላጊ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። \"የግድ ውድድር አሊያም ማጣሪያ መጠበቅ የለብንም። ከዚያ ይልቅ ቡድኑ እየተሰበሰበ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማድረግ አለበት\" ይላል ፍሬው። ፍሬው አክሎም በሌሎች አገራት የሚጫወቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች ተፎካክረው የአገር ውስጥ ተጫዋቾችን የሚበልጡ ከሆነ ሊጠሩ ይገባል ይላል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ከተሳተፉ ቡድኖች ከአፍሪካ ውጪ የመጣ ተጫዋች ያላካተተ ብቸኛው ስብስብ ነበር። ፍሬው ጨምሮ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች ከአገር ቤት ውጭ ሄደው መጫወት እንዳለባቸው ይሄ ደግሞ ለልምድ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ይጠቁማል። የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው ዓመት በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ውድድሩ ከቀደሙት በተለይ በክረምት ወራት ሰኔና ሐምሌ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ የማጣሪያ ጨዋታዋን ከየትኞቹ ቡድኖች ጋር እንደምታደርግ በቅርቡ ይታወቃል።", "በአውሮፓ እግር ኳስ ከሜዳው ውጪ ግብ ያስቆጠረ የሚለው ሕግ እንዲቀር ተወሰነ በአውሮፓ የክለቦች ውድድር ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ከሜዳ ውጪ ግብ ያስቆጠረ የሚለው ሕግ ከሚቀጥለው የውድድር ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ እንደሚቀር የአህጉሪቱ የእግር ኳስ አስተዳደር ዩኤፋ ገለጸ። እአአ ከ1965 ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ በቆየው ሕግ መሠረት ሁለት ቡድኖች በደርሶ መልስ ጨዋታ እኩል ጎሎችን ካስቆጠሩ ከሜዳው ውጪ ብዙ ጎል ያስቆጠረው ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፍ ይደረግ ነበረ። በአዲሱ ሕግ መሠረት ሁለት ቡድኖች በደርሶ መልስ ጨዋታ አቻ ከሆኑ ወደ ተጨማሪ ሰዓት እንዲያመሩ ይህ ካልሆነም ወደ መለያ ምት እንዲያቀኑ ይደረጋል ተብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ የበላይ አካል ዩኤፋ ፕሬዝዳንት አሌክሳንድር ሴፌሪን \"ከሜዳ ውጪ ያገባ የሚለው ሕግ ከእንግዲህ የበለጠ ክብደት እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ አይደለም\" ብለዋል። የዩኤፋ የክለብ ውድድሮች ኮሚቴ ሃሳቡን በግንቦት ወር ላይ ያቀረበ ሲሆን አሁን በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ጸድቋል። የቀድሞው ሕግ በሻምፒዮንስ ሊግ፣ በዩሮፓ ሊግ፣ በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ እና በሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተግባራዊ አይደረግም ማለት ነው። ዩኤፋ እንደሚለው አዲሱ ውሳኔ በአውሮፓ ውድድሮች ላይ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ ሚደረግ ማሸነፍን እና ጎል ማስቆጠር ያለውን ልዩነትን ያጠበዋል። ለዚህ ደግሞ የሜዳ ጥራት፣ የተሻሻለ የስታዲየም መሠረተ ልማት እና እንደ ቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት (ቫር) ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮች በምክንያትነት ይነሳሉ ብሏል። \"የሕጉ ተጽእኖ ከመጀመሪያ ዓላማው ጋር የሚጋጭ ነው ተብሏል። በሜዳቸው የሚጫወቱ ቡድኖች በተለይም በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ወቅት ተጋጣሚዎቻቸው ጎል እንዳያስቆጥሩባቸው በመስጋት ከማጥቃት ይልቅ ወደ መከላከሉ እንዲያዘነብሉ ይሆናሉ\" ብሏል። \"በተለይ ደግሞ በተጨማሪ ሰዓት ከሜዳ ውጪ የሚጫወተው ቡድን ጎል ሲያስቆጥር ባለሜዳው ሁለት ጎሎችን እንዲያስቆጥር በማስገደድ አድልዎ ይፈጥራል\" ሲልም የቀድሞውን ደንብ ተችቷል። \"ስለዚህ በሜዳ መጫወት እንደቀደመው ጊዜ ሁሉ አሁን አስፈላጊ አይደለም\" ብሏል። አያክስ ከቶተንሃም (እአአ በ2019)፣ ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም (እአአ በ2019)፣ ፓሪስ ሴንትዠርሜን ከማንቸስተር ዩናይትድ (እአአ በ2019) እና ሮማ ከባርሴሎና (እአአ በ2018) በቅርብ ዓመታት ከሜዳ ውጭ ግብ ያስቆጠረ በሚለው ሕግ መሠረት ውጤታቸው ከተለዩ የቅርብ ጊዜ ጨዋታዎች መካከል ይጠቀሳሉ።", "ሂሩት እና ለሜቻ በሮም ዳይመንድ ሊግ ደምቀው አመሹ ትላንት ስኔ 2/2014 ዓ.ም. ምሽት በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ ሂሩት መሸሻ እና ለሜቻ ግርማ አሸናፊ ሆነዋል። በተለያዩ ከተሞች በዙር የሚከናወነው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ትናንት በጣሊያኗ ሮም ተከናውኗል። በምሽቱ ውድድር በሴቶች 1500 ሜትር ሂሩት መሸሻ ወድድሩን በበላይነት አጠናቃለች። ሂሩት ውድድሩን 4 ደቂቃ 03.79 በመጨረስ ቀዳሚ ሆናለች። አክሱማዊት አምባዬ በአንድ ሰከንድ ዘግይታ ውድድሩን በሁለተኛነት አጠናቃለች። ሂሩት የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ናት። በዓለም አቀፍ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ደግሞ ነሐስ ሜዳሊያ ማጥለቅ ችላለች። ለሜቻ ግርማ ደግሞ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ውድድር ነው አሸናፊ የሆነው። ለሜቻ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 7 ደቂቃ 59.23 ሰከንድ ፈጅቶበታል። ለሜቻ ባለፉት አስር ቀናት በኦስትራቫ፣ ራባት እና ሮም ያደረጋቸውን ውድድሮች በሙሉ ከስምንት ደቂቃ በታች ማጠናቀቅ ችሏል። ኬንያዊው አብረሃም ኪብዎት ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ፈጽሟል። ጌትነት ዋለ ሦስተኛ ሆኖ የትላንት ምሽቱን ውድድር አጠናቋል። ለሜቻ በቶኪዮ ኦሎምፒክ እና በዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ማሳካት ችሏል። በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናም ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለ አትሌት ነው። በአምስት ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር ኬንያዊው ኒኮላስ ኪፕኮሪር አሸናፊ ሆኗል። የሃገሩ ልጅ ጃኮፕ ክሮፕ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ዮሚፍ ቀጄልቻ ውድድሩን ሦስተኛ ሆኖ ጨርሷል። ሰለሞን ባረጋ አራተኛ ሲወጣ ጥላሁን ሃይሌ እና ሙክታር እንድሪስ ስድስተኛና ሰባተኛ ሆነው አጠናቀዋል። በ800 ሜትር የተወዳደረችው ፍሬወይኒ ሃይሉ አምስተኛ ሆና ውድድሩን ጨርሳለች። ዳይመንድ ሊግ በ2010 ተጀመረ ውድድር ነው። ውድድሩ ጎልደን ሊግ የተሰኘውን ውድድር ተክቶ ነው መካሄድ የጀመረው። በተለያዩ ከተሞች ለአንድ ቀን ብቻ የሚሄድ ውድድር ዓይነት ነው። የውድድሩ አሸናፊዎች በተለያዩ ከተሞች በሚያስመዘግቡት ውጤት ዳጎስ ያለ ሽልማት ይበረከትላቸዋል። ቀጣዩ አስተናጋጅ የኖርዌይዋ ኦስሎ ስትሆን ውድድሩ ከሳምንት በኋላ ይከናወናል።", "ስድስቱ 'ኃያላን' የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከአዋዛጋቢው ሱፐር ሊግ እራሳቸውን አገለሉ ስድስቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሃሳባቸውን በመቀየር እርሳቸውን አዲስ ከሚመሰረተው የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ማግለላቸውን አስታወቁ። በአዲስ መልክ ሊዘጋጅ በታሰበው የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ለመሳተፍ መስራች አባል የነበሩት አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ሊቨርፑል፣ ማንችስተር ዩናይት፣ ማንችስተር ሲቲ እና ቶተነሃም በውድድሩ እንደማይሳተፉ ይፋ አድርገዋል። ማንቸስተር ሲቲ ከአውሮፓ ሱተር ሊግ እራሱን ያገለለ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ ሲሆን ቼልሲ ቀደም ብሎ ለመልቀቅ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ ነበር ተብሏል። ቀሪዎቹ አራት ክለቦችም በውድድሩ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። 12 የአውሮፓ ክለቦች በመስራችነት የአውሮፓ ሱፐር ሊግን እንጀምራለን የማለታቸው ዜና የተሰማው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ነበር። የአርሰናል ቦርድ በሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ማቀዴን አቁሜያለሁ ብሎ ባወጣው መግለጫ ላይ፤ በሊጉ ለመሳተፍ መወሰኑ በደጋፊዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አለመገመቱን እና ሱፐር ሊጉን ለመቀላቀል የወሰነውም ክለቡ ብቻውን ላለመቅረትና የክለቡን ቀጣይነት ለማረጋገጥ አንደሆነ ገልጿል። \"ዓላማችን ሁሌም ለዚህ ታላቅ የእግር ኳስ ክለብ ትክክለኛውንና ጠቃሚ ውሳኔ ማስተላላፍ ነው። አሁን ላይ ትክክለኛውን ውሳኔ አላስተላለፍንም፤ ኃላፊነቱንም እንወስዳለን\" ብሏል ቦርዱ። ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ እግር ኳስ እያጋጠሙት ያሉትን ጋሬጣዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመፍታትና መፍትሄዎችን ለማበጀት ከሁሉም የእግር ኳስ ማህበረሰብ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል። ሌላኛ ክለብ ሊቨርፑል የአውሮፓ ሱፐር ሊግን ለመቀላለቀል መወሰኑን ተከትሎ ከክለቡ ውስጥም ሆነ ውጪ የሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ሃሳባቸውን ሲያጋሩ እንደነበርና በመጨረሻም ይህ አዲሱን ሊግ ላለመቀላለቅ መወሰኑን ገልጾ ሁሉንም አካላት ለአበርክቷቸው አመስግኗል። የቶተንሀም ሊቀመንበር ዳንኤል ሌቪ በበኩሉ የክለቡን የገቢ ምንጭ ለመጨመርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በአዲስ መልክ የተዘጋጀው ውድድር ላይ ለመሳተፍ እንደተወሰነ ገልጿል። \"ውሳኔያችንን ተከትሎ የሚመለከታቸው በሙሉ ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው ገልጸውልናል። ልናመሰግናቸው እንወዳለን\" ብሏል። ቼልሲ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩን ለማጤን ጊዜ እንወሰደና ለእግር ኳሱና ለደጋፊዎች ጥቅም ሲል ላለመሳተፍ መወሰኑን አስታውቋል። የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ጫፍ የደረሱት ማንችስተር ሲቲዎች የአውሮፓ ሱፐር ሊግን ለመመሠረት የተጀመረውን ሂደት ለመልቀቅ በይፋ ሰነድ ማዘጋጀት እንደጀመሩ ገልጸዋል። 12ቱ ክለቦች የራሳችን የሆነ ሊግ እንጀምራለን ማለታቸው ደግሞ በመላው ዓለም በተለይ አውሮፓውያንን በጣም ያስገረመና ያሳሰበ ጉዳይ ሆኖ ነበር። የቀድሞ ተጫዋቾች፣ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች እና መሪዎችም ጭምር ውሳኔውን በመቃወም ድምጻቸውን አሰምተዋል። በአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደሚሳተፉ ያስታወቁ ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱ በርካታ ተጫዋቾች በበኩላቸው በውሳኔው ደስተኞች እንዳልሆኑ ሲገልጹ ነበር። የሊቨርፑሉ አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፈው መልዕክት ሁሉም የክለቡ ተጫዋቾች በአውሮፓ ሱፐር ሊግ መሳተፍ እንደማይፈልጉ ገልጿል። አሰልጣኙ የርገን ክሎፕም ቢሆኑ በዚህ ሀሳብ ደስተኛ እንዳልሆኑ እና ለእግር ኳስ እድገት እንደማይጠቅም ገልጸው ነበር። በአዲሱ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እቅድ መሰረት መስራቾቹ ክለቦች ማለትም አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ ሪያል ማድሪድ፣ አትሌቲኮ ማድሪድና ባርሴሎና ከስፔን እንዲሁም ጁቬንቱስ፣ ኤሲ ሚላን እና ኢንተር ሚላን ከጣልያን በውድድሩ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ነበር። አዲሱ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ከቴሌቪዥን ሽያጭ ብቻ በዓመት እስከ 4.8 ቢሊየን ዶላር ድረስ ሊያስገኝ እንደሚችል ተገምቶ የነበረ ሲሆን ይህም አሁን ላይ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከሚገኘው ከእጥፍ በላይ ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሴፍሪን የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች እንደማይሳተፉ መግለጻችውን በደስታ ተቀብለውታል። \"አሁን ወደቀደመው የእግር ኳስ አካሄድ እንመለሳለን። እነዚህ ክለቦች ለምናዘጋጃቸው ውድድሮች ብቻ ለመላው የአውሮፓ እግር ኳስ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖራቸው አውቃለሁ\" ብለዋል። \"በዚህ ሰአት ወሳኙ ነገር ወደፊት መጓዝ ነው። አደጋ አጋጥሞት የነበረውን አንድነታችንን መመለስና እግር ኳስን ማጣጣም መጀመር አለብን\" ሲሉም ጨምረዋል። በእቅዱ መሠረት የአውሮፓ ሱፐር ሊግ በየዓመቱ ነሀሴ ወር ላይ የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታዎቹም የሳምንቱ አጋማሽ ላይ ይደረጋሉ። ተሳታፊዎቹ 20 ቡድኖችም በሁለት ምድቦች ተከፍለው በደርሶ መልስ ጨዋታ ይፋለማሉ የሚል እቅድ ተይዞ ነበር። ስድስቱ የእንግሊዝ ክለቦች ከዚህ ሊግ እራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ የሊጉ እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ግልጽ አይደለም።", "ግብፅ ከአስደንጋጩ የኢትዮጵያ ሽንፈቷ በኋላ አሰልጣኟን አሰናበተች የግብፅ እግር ኳስ ማኅበር የብሔራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ኤሃብ ጋላልን ፊርማቸው ሳይደርቅ ከኃፊነት አነሳ። ጋላል ብሔራዊ ቡድኑን ለሦስት ጨዋታዎች ብቻ ነው የመሩት። የ54 ዓመቱ ጋላል ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ ነበር ካርሎስ ኬሮዥን በመተካት ኃላፊነቱ የተሰጣቸው። ኬሮዥ ብሔራዊ ቡድኑን ለዓለም ዋንጫ ባለማብቃተቸው ነበር ከኃላፊነት የተነሱት። ጋላል በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በኢትዮጵያ 2 ለ 0 ተሸንፈዋል። ከዚህ አስደንጋጭ ውጤት በተጨማሪ ቡድኑ በወዳጅነት ጨዋታ በደቡብ ኮሪያ 4 ለ 1 ተሸንፏል። የማኅበሩ ቦርድ አባል የሆኑት ሃዜም ኤማም የውጭ አገር አሰልጣኝ እንደሚሾሙ አስታውቀዋል። ጋላል በአሰልጣኝነት ዘመናቸው ዛማሌክ፣ ኤል ማስሪ እና አልአህሊ ትሪፖሊን የመሳሰሉ ቡድኖችን አሰልጥነዋል። ብሔራዊ ቡድኑን ከመረከባቸው በፊት የፒራሚድስ አሰልጣኝ ሆነው አገልግለዋል። ብሔራዊ ቡድኑን በያዙ መጀመሪያ ጨዋታቸው በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጊኒን ባለቀ ሰዓት ባስቆጠሩት ጎል 1 ለ 0 አሸንፈዋል። በቀጣይ ያደረጓቸውን ሁለት ጨዋታዎች ባለማሸነፋቸው ሥራቸውን አሳጥቷቸዋል። “ከበርካታ የውጭ አገር አሰልጣኞች ጋር እየተነጋገርን ነው” ያሉት ኤማም ቴክኒካል ዳይሬክተር እንደሚሾሙም ጠቁመዋል። “ለተከበረው አሰልረጣኝ ኤሃብ ጋላል ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ሥራውን በከባድ ሁኔታ ውስጥ ሲያከናውን ነበር። ይቅርታ ልጠይቀው እወዳለሁ። አንዳንዴ ግፊቱ ከባድ ነው። ለውጡ ለሁሉም ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ” ብለዋል። ከጋላል በፊት የግብፅ አሰልጣኝ የነበሩት ኬሮዥ በሰር አሌክስ ፈርጉሰን የአሰልጣኝት ዘመን በማንቸስተር ዩናይትድ ምክትል ሆነው የሰሩ ሲሆን፣ በተጨማሪም በዋና አሰልጣኝነት ፖርቹጋል እና ኢራንን መርተዋል። ኬሮዥ የሰባት ጊዜ የአህጉሪቱ እግር ኳስ ሻምፒዮኗን ግብፅ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ቢያደርሱም በመለያ ምት በሴኔጋል ተሸንፈዋል። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በተደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ግብፅ በተመሳሳይ በሴኔጋል በመለያ ምት ተሸንፋ ከኳታሩ ውድድር ውጪ ሆናለች።", "አርሰናል፣ ሊቨርፑል እና ዩናይትድ ወደ ድል ይመሰሉ ይሆን. . . የሳምንቱ የፕሪሚየር ሊግ ግምቶች ባለፈው የካቲት ሊድስ ወደ ሊቨርፑል አቅንቶ ነበር። 6 ለ 0 ተሸነፈ። ከቀናት በኋላ ደግሞ አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳን አሰናበተ። በዚህ ሳምንትም ታሪክ ራሱን ይደግም ይሆን? የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን  “ጄሴ ማርሽ አደጋ ውስጥ ነው። የሊድስ ደጋፊዎች የቤልሳን ስም ሲጠሩ መስማት ለማርሽ የሚጠቅመው ነገር የለም” ይላል። “ዘንድሮ ሊድስ በአንዳንድ ጨዋታዎች ማግኘት የሚገባውን ነጥብ አላገኘም። ሌላ ጊዜ ደግሞ አቋሙ ወርዷል። አስልጣኙን የጎዳው ሌላው ነገር ከአንዳንድ ሸንፈቶች በኋላ ጥሩ ሳይሆኑም መልካም ጎኖችን አይቻለሁ ማለታቸው ነው” ሲል ያክላል። ለመሆኑ 13ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች በምን መልኩ ይጠናቀቃሉ? ሱቶን ግምቶቹን አስቀምጧል። ሌስተር ከ ማንቸስተር ሲቲ ኤርሊንግ ሃላንድ መጫወቱ እርግጥ አለመሆኑ ይህንን ግምት ከባድ ያድርገዋል። ሲቲ ካለአጥቂው በተለየ መንገድ መንቀሳቀስ አለበት። ሌስተር በሳምንቱ አጋማሽ ካለመጫወቱም በላይ ተከላካይ ክፍሉን ጨምሮ ጀምስ ማዲሰን እና ሃርቪ ባርነስ ድንቅ አቋም ላይ ይገኛሉ። ይህም ቢሆን ግን ሲቲ የበላይነቱን የሚይዝበት ስብስብ አለው። ግምት፡ 1 – 3 ብርንማውዝ ከ ቶተንሃም ከቶተንሃም ምን መጠበቅ እንዳለብኝ ማወቅ ስለሚያስቸግር ይህንንም ጨዋታ ለመገመት ከባድ ያደርገዋል። በሳምንቱ አጋማስ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር አቻ ተለያይቷል። ለዚህ ጨዋታ ደካማውን መጀመሪያ አጋማሽ ወይስ ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሶ የነበረው የሁለተኛው አጋማሽ አጨዋወት ይታያል የሚለው አይታወቅም። አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ቡድናቸው መድከሙን መናገራቸው ጥሩ መልዕክት አያስተላልፍም። በርንማውዞች በዌስትሃም በተሸነፉበት ጨዋታ ቫር ከጎናቸው የቆመ አይመስልም። ከተከታታይ ሽንፈት በኋላ አንድ ነገር ማግኘት ቢጠበቅባቸውም ከሽንፈት አያመልጡም። ግምት፡ 0 – 1 ሁለቱም ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ቢሸነፉም ብሬንትፎርድ የሚያንሰራራ ይመስለኛል። በሜዳቸው ጥሩ የሆኑት ብሬንትፎርዶች ውጤጥ እንደሚያገኙ እገምታለሁ። የዎልቭስ ጊዜያዊ አሰልጣኝ የሆኑት ስቲቭ ዴቪስ እስከ ፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በሥራቸው የሚቆዩ መሆናቸው ቢረጋገጥም አሁንም ስጋት ቡድኑ ላይ እንዳንዣበበ ነው። ጥሩ ጥሩ ተጫዋቾችን ቢይዙም በሌስተር ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ ምን ያጋጥማቸው ይሆን የሚል ስጋት ፈጥሯል። ግምት፡ 2 – 1 ብራይተን ከ ቼልሲ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ደ ዜርቢ የመጀመሪያ ድላቸውን ከብራይተን ጋር ለማስመዝገብ እየጠበቁ ነው። ለዚህ ደግሞ የቀድሞውን አሰልጣኝ ግራህም ፖተርን በሜዳቸው ያስተናግዳሉ። ፖተርም ያለፉትን ዘጠኝ ጨዋታዎች ባይሸነፉም ይህ ጨዋታ ቀላል አይሆንላቸውም። ብዙ ቡድኖች በሲቲ ሲሸነፉ የሚወሰድባቸውን ዓይነት የበላይነት ብራይተኖች ላይ አላሳዩም። ግምት፡ 1 – 1 ክሪስታል ፓላስ ከ ሳውዝ ሃምፕተን ሳውዝሃምፕተኖች ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ጋር በነበራቸው ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ ነበሩ። መድፈኞቹ በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታውን ማጠናቀቅ ነበረባቸው። ይህ ግን የቡድን አቋም ነው። 90 ደቂቃ ወጥ አቋም አያሳዩም። ክሪስታል ፓላሶች ባለፈው ሳምንት በኤቨርተን ቢበለጡም በሜዳቸው ጠንክረው እንደሚመለሱ እገምታለሁ። ዊልፍሬድ ዛሃ ባለፈው ዓመት ሳውዝሃምፕተን ላይ በሜዳውም ሆነ ከሜዳው ውጭ ጎሎችን አስቆጥሯል። በዚህ ጨዋታውም  ልዩነት ሊፈጥር እንደሚችል ምልክት ሊሆን ይችላል። ግምት፡ 2 – 1 አስቶን ቪላ ኡናይ ኤምሬን አስለጣኙ አድርጎ ሾሟል። ቡድኑ ግን በተጠባባቂ አለስጣኝ አሮን ዳንክስ ባለፈው ሳምንት ብሬንትፎርድን 4 ለ 0 አሸንፏል። ይህ ለቪላ ትልቅ ድል ነው። ኒውካስል በአሰልጣኝ ኤዲ ሆዊ ስር እያሳየ ያለው ለውጥ አስደምሞኛል። ዕድለ ቢስ ባይሆኑ ከዚህም የተሻለ ነጥብ መሰብሰብ ይችሉ ነበር። ግምት፡ 2 – 0 ፉልሃም ከ ኤቨርተን ኤቨርተኖች በአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ስር ጥሩ መንቀሳቀስ ጀምረዋል። ዘንድሮ በተደጋጋሚ ይሸነፋሉ ብልም ፉልሃሞችም ጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉ። የማርኮ ሲልቫ ቡድን በሜዳውም ሆነ ከሜዳው ውጭ ጥሩ ቡድን ነው። ሁለቱም ቡድኖች ሊያሸንፉ ይችላሉ ማለት ቢቻልም እኔ አቻ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 – 1 ሊቨርፑል ከ ሊድስ የሊድስ መጥፎ ውጤት በጄሴ ማርስ ላይ ብቻ የሚሳበብ አይመስለኝም። ከዚህ ጨዋታ ግን ጥሩ ነገር ይጠብቃሉ። ዘንድሮ ሊቨርፑል አለ ሲባል የሌለ ቡድን መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በቻምፒዮንስ ሊግ ከአያክስ ጋር ድንቅ ምሽት ያሳለፉ ሲሆን ይህም ጨዋታ በሜዳቸው መሆኑ ያግዛቸዋል። ይህን ጨዋታ ሊቨርፑል በቀላሉ ያሸንፋል የሚል ግምት አለኝ። ግምት፡ 6 – 1 እሑድ አርሰናል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ይህ ጨዋታ በሊጉ መሪ እና በግርጌ በሚገኙ ክለቦች መካከል የሚከናወን ነው። አርሰናል በሳውዝሃምፕተኑ ጨዋታ ሁለተኛ አጋማሽ የደከመ ይመስላል። በዚያ ላይ ሐሙስ ዕለት ከፒኤስቪ ጋር ተጫውቷል። ይህም ቢሆን ጨዋታውን ያሸንፋል። ፎረስቶች ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በመከላከል ረገድ የተሻሉ በመሆናቸው ጎል አላስተናገዱም። ይሁን እንጂ ጨዋታው በመድፈኞቹ ሜዳ የሚካሄድ ስለሆነ መድፈኞቹ ያሸንፋሉ ብዬ እገምታለሁ። ቀጣይ ጨዋታዎች ግን ቡድኑን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ግምት፡ 2 – 0 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ዌስት ሃም የራፋኤል ቫራን መጎዳት እና ጂያንሊካ ስካማካ አቋም ስጋት ቢፈጥርም ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታውን የሚያሸንፍ ይመስለኛል። ዌስትሃም ጠንካራ የመከላከል አቋም ላይ ቢገኝም ማንቸስተርን የማጥቃት እንቅስቃሴ የሚቋቋም አይመስልም። የዩናይትዱ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ መሻሻሎችን ቢያስመዘግቡ የሮናልዶ ጉዳይ ትኩረት እየሳበ ነው። ሮናልዶም በኦልድትራፎርድ ያለውን ስም እያጠለሸ ይመስላል። ግምት፡ 2 – 1", "አውስትራሊያዊቷ ኬክ በፍጥነት በመብላት ውድድር ላይ ሳሉ ሞቱ በአውስትራሊያ አንዲት ሴት ብዙ ኬክ በፍጥነት በመብላት ውድድር ላይ ሳሉ ሕይወታቸው አልፏል። ሴትየዋ 60 ዓመታቸው ሲሆን በኪውንስላንድ ሃርቬይ ቤይ ውስጥ በሚገኝ ቢች ሃውስ በተባለ ሆቴል ኬክ ቶሎ በልቶ የመጨረስ ውድድር ላይ ሳሉ ነበር ራሳቸውን ስተው የወደቁት። ተወዳዳሪዎቹ ቀደም ብለው ላሚንግተን የተሰኘውን ከቼኮሌትና ከኮኮነት የተሠራ ኬክ ሲበሉ ነበር። ሴትዮዋ በወቅቱ የመጀመርያ እርዳታ ተደርጎላቸው ሆስፒታል በፍጥነት የተወሰዱ ቢሆንም ሕይወታቸን ማትረፍ ግን አልተቻለም። • የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ጩኸት • በትራምፕ የድጋፍ ደብዳቤ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት የዐይን እማኞች እንደሚሉት ሴትየዋ በውድድሩ ላይ አንዱን ኬክ ጎርሰው ሌላ ለመድገም ሲሞክሩና ሲታገላቸው እንደነበር መመልከታቸውን ተናግረዋል። ኋላ ላይ በወጡ የተንቀሳቃሽ ምሥሎች መረዳት እንደተቻለው በሆቴሉ ውስጥ የተገኙ ጠጪዎች ለተወዳዳሪዎቹ እያጨበጨቡ ድጋፍ ሲሰጡ ነበር። ተወዳዳሪዎቹ ከሚመገቡት ኬክ በተጨማሪ በብርጭቆ ውሃ ቀርቦላቸው እንደነበረም ተንቀሳቃሽ ምሥሉ መስክሯል። በሃርቬይ ቤይ የሚገኘው የቢች ሃውስ ሆቴል ፌስቡክ ገጽ ለሴትዮዋ ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል። በአውስትራሊያ የድል ቀን ምግብ በፍጥነት በልቶ የመጨረስ ውድድር እጅግ የሚዘወተር መዝናኛ ነው። የአውስትራሊያ የድል ቀን አውሮፓዊያኑ አውስትራሊያ የደረሱበትን ቀን የሚዘክር በዓል ነው። በዚህ የድል ቀን ተወዳዳሪዎች ሆትዶግ፣ ኬክ፣ ወይም ሌሎች ምግቦችን በፍጥነት ከተመገቡ ዳጎስ ያለ ሽልማትን ያሸንፋሉ።", "ሮቦቲክስ፡ በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው የሮቦት ውድድር አሸናፊ የሆነው ኢትዮጵያዊ በቻይና ቤይጂንግ በተካሄደ የሮቦት ውድድር በቲያንዢን ቴክኖሎጂ እና ኢጁኬሽን ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆኑ አምስት ኢትዮጵያውያን የወርቅ፣ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆን ችለዋል። በውድድሩ የተሳተፉት ሰላሙ ይስሃቅ፣ አባኩማ ጌታቸው፣ ፀጋዬ አለሙ፣ ዮሐንስ ኃ/መስቀልና ሄኖክ ሰይፉ የተባሉ ኢትዮጵያውን ነበሩ። ኢትዮጵያውያኑ በተወዳደሩበት ዘርፍ፣ ሰላሙ ይስሃቅ የወርቅ፣ አባኩማ ጌታቸው እና ፀጋዬ አለሙ የብር ሜዳሊያ አግኝተዋል። በተጨማሪም ዮሐንስ ኃ/መስቀል እና ሄኖክ ሰይፉ የነሐስ ሜዳሊያ እንዲሁም የዋንጫ ተሸላሚዎች ሆነዋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የወርቅ ተሸላሚው ሰላሙ ይስሃቅ ስለውድድሩ ሲያብራራ ኢትዮጵያውያኑ በትራይ ኮ ሮቦትስ ኤንድ አፕሊኬሽን (\"Tri-Co\" Robots and Robot Application) ዘርፍ መወዳደራቸውን ያስረዳል። ውድድሩ ሦስት ሰዓታት የተሰጠው ነው። በእነነዚህ ሰዓታት ተነጣጥለው የተቀመጡና ግዑዝ የሆኑ አካላትን ገጣጥሞ 'ህይወት መዝራት'ና የሚሰጠውን ተልዕኮ የሚፈጽም ሮቦት ዝግጁ ማድረግ ደግሞ ውድድሩ ነው። በቻይና ቤይጂንግ በተደረገው በዚህ ውድድር የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኘው ሰላሙ ይስሃቅ ይህንን ተግባር በአንድ ሰዓት ከ53 ደቂቃ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኖ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል። ከቀናት በፊት በተካሄደው በዚህ ውድድር ከ20 ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርምርና የንግድ ተቋማት የተወጣጡ 2000 ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰላሙ ያሸነፈው በኢንደስትሪያል ሮቦቲክስና ሰው ሰራሽ ልህቀት ዘርፍ ነው። ስለውድድሩ ምን ይታወቃል? እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 የተጀመረው ዓለም አቀፍ የሮቦት ኮንፈረንስ አካል የሆነው የሮቦትና የሰው ሰራሽ ልህቅ ውድድር በአራት ዘርፎች ይከናወናል። በቻይና ቲያንጂን ግዛት በቲያንጂን ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኘው ሰላሙ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ ውድድር በኢንደስትሪያል ሮቦቲክስ ሥርዓት ዘርፍ ተወዳዳሪ ሲሆን በሌሎች ዘርፎች ከተሳተፉ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ነው። ሰላሙ የተሳተፈበት ውድድር \"የተፈታታ\" እና የኮፒውተር ፕሮግራም ያልተጫነበትን ሙሉ ሮቦት ገጣጥሞ ማዘጋጀት ነው። ውድድሩ እያንዳንዱን ነገር በሚያስፈልግበት ቦታ አስቀምጦ [ሮቦቱ] የሚሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። እያንዳንዱን የሮቦት አካል ገጣጥሞ በዚያ ላይ ሶፍትዌር መጫን ሌላው የውድድሩ አካል ነው። \"አጋጣሚ ከቻይናዊ ጋር ነበር የተወዳደርኩት. . . በውድድሩ የሠራሁት ነገር በሙሉ በሚፈለገው ሁኔታ የሚሰራ መሆኑን ዳኞቹ አረጋግጠው ነው አሸናፊ መሆኔ ይተገለጸው\" ሲል ያስረዳል። ሮቦቱ \"ሙሉ ለሙሉ በሚጠበቅበት ሁኔታ እንደሚሰራ፣ ከሌላ ቦታ ዕቃ እንዴት እንደሚያዟዙር፣ በታዘዘው መሰረት እንዴት ይንቀሳቀሳል የሚለውን በሙሉ ተፈትሿል። ይህንን ነው ሙሉ ለሙሉ የሰራነው።\" የኢንዱስትሪ ሮቦት ለኢትዮጵያ ምን ይጠቅማል? ሰላሙ እያጠና ያለውን እና ያሸነፍበትን ኢንደስትሪያል ሮቦቲክስ አስፍላጊነትን ሲያስረዳ የቻይና እና የጀርመንን የመኪና ፋብሪካዎች በምሳሌነት ያስቀምጣል። በእነዚህ አገራት መኪና ሲመረት \"አብዛኛውን ነገር የሚገጣጥሙት ሮቦቶች ናቸው። ሰዎች መጨረሻ ላይ ውጤቱን እና ጤንነታቸውን ለማረጋገጥ ካልሄዱ በስተቀር ሙሉ ሥራውን ሮቦት ነው የሚከውነው\" የሚለው ሰላሙ በኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ምርቶችን ለማቅረብ መሰል ቴክኖሎጂ አስፈላጊ መሆኑን ያነሳል። \"በኢትዮጵያ በቂ የሆነ በርካታ ጥሬ ዕቃ አለ። ያን ጥሬ ዕቃ እዚያው ፕሮሰሰ አድርገን ለዓለም ማቅረብ የምንችልበት ሂደት ላይ ግን ገና ነን። የሰለጠነ የሰው ኃይል ያስፈልገናል።\" እንደ ሰላሙ ገለጻ በአገር ውስጥ ያሉ ምርቶችን በዚህ የቴክኖሎጂ ሂደት እንዲያልፉ ማድረግ ከፍተኛ ጥቅም አለው። ቡናን አብነት ያደርጋል \"ኢትዮጵያ አንድ ኪሎ ቡና 200 ወይም 300 ብር ነው። እዚህ ግን የተዘጋጀ ግማሽ ኪሎ ቡና ስምንት መቶ የቻይና ገንዘብ ነው የሚሸጡት፤ በኢትዮጵያ ስምንት ሺህ ብር እንደማለት ነው። ኢትዮ ፍሌቨር ብለው ነው የሚሸጡት። ኢትዮጵያ ውስጥ ያ ቡና ተዘጋጅቶ ቀጥታ ወደ ቻይና ኤክስፖርት የሚደረግ ቢሆን የውጭ ምንዛሪ ገቢው ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል\" ሲል ያስረዳል። ከዚህም አልፎ እንደ ብረትና ሲሚንቶ ባሉ ፋብሪካዎች ኢንደስትሪያል ሮቦቲክስና ሰው ሰራሽ ልህቀትን ሥራ ላይ በማዋል በዝቅተኛ ወጪና ጉልበት ተወዳዳሪ ምርቶችን ማቅረብ ይችላልም ብሏል። የሰላሙ ዕቅድ ሰላሙ ይስሃቅ ወደ ቻይና ለትምህርት ከማቅናቱ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምህርነት ይሰራ ነበር። እናም አሁን ትምህርቱን የሚከታተልበትና ቀድሞ ያስተምርት የነበረው ተቋም ኢንደስትሪያል ሮቦቲክስን ጨምሮ በአራት የትምህርት መስኮች በጋራ የመስራ ስምምነት ያላቸው በመሆኑ ወደ አገሩ ሲመለስ በዚሁ ዘርፍ ዜጎችን ለማፍራት ያልማል። አራቱ የትምህርት መስኮች በቴክኒካል ዩኒቨርሲቲው በአንድ ማዕከል ስር የሚጠቃለሉ ሲሆን፣ ሰላሙና ሌሎች በቻይና በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ያሉ ኢትዮጵያውን ወደ አገራቸው ተመልሰው በማዕከሉ በመሪ አሰልጣኝነት ይሰራሉ። እንደ ሰላሙ ገለጻ ዩኒቨርሲቲው ከሚሰጣቸው መደበኛ የትምህርት መርሃ ግብሮች በተጨማሪ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን በመውሰድ ለዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ዝግጅት እያደረጉ ነው። በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ እየተስፋፋ እንደሆነ የሚጠቅሰው ሰላሙ፣ ይህ ኢንድስትሪ ደግሞ በሰው ሰራሽ ልህቀት መታገዙ አይቀሬ ነው ይላል። \"ዓለም ወደ ዘመነበት አቅጣጫ ኢትዮጵያ እያደገች ነው ያለው። ለዚያ ደግሞ የተማረና ብቃቱ የተረጋገጠ ሰው ያስፈልጋል\" እናም ይህን አይነት ሰው በአገሩ ውስጥ ለማብቃት እንደሚተጋ ገልጿል።", "የአውሮፓ ሻምፒየኗ ጣሊያን ዳግም ለዓለም ዋንጫ ሳታልፍ ቀረች ሐሙስ ምሽት ከሰሜን መቂዶኒያ ጋር የተጋጠመችው የአውሮፓ እግር ኳስ ኃያሏ ጣሊያን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ተሸንፋ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሳታልፍ ቀርታለች። የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ ጣሊያን፤ ከዚህ ቀደም በሩሲያ አዘጋጅነት ተካሂዶ በነበረው የዓለም ዋንጫም ተሳታፊ አልነበረችም። የሰሜን መቂዶኒያው አሌክሳንድር ትራሆቭስኪ መደበኛ የጨዋታው ሰዓት ተጠናቆ የመጨረሻ ጭማሪ ሰዓት ላይ በጣሊያን ተጫዋቾች የተሰራውን ስህተት በመጠቀም አስደናቂ ግብ በማስቆጠር ነው አገሩን አሸናፊ ማድረግ የቻለው። 92ኛው ደቂቃ ላይ ግቡ ሲቆጠር የሰሜን መቂዶኒያ ተጫዋቾችና የአሰልጣኞች ቡድን እራሳቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ደስታቸውን ሲገልጹ፣ በደጋፊዎቻቸው ፊት በሜዳቸው የተጫወቱት ጣሊያኖች በሐዘን ተንበርክከው መሬት ሲደበድቡ ታይተዋል። ይህንን ተከትሎም የዓለም ዋንጫን አራት ጊዜ ማሸነፍ የቻለችው ጣሊያን ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ በዓለም ዋንጫው እንደማትሳተፍ ተረጋግጧል። በሮቤርቶ ማንቺኒ የሚመሩት 'አዙሪዎቹ' በሚል ቅጽል የሚታወቀው የጣሊያን ቡድን የ2020 የአውሮፓ ዋንጫን ሲያሸንፍ፣ ይህ ቡድን በዓለም ዋንጫውም ያልተጠበቁ በርካታ ድሎችን እንደሚያስመዘግብ ተስፋ ተጥሎበት ነበር። ነገር ግን ሐሙስ ዕለት የሰሜን መቂዶኒያን ግብ መድፈር አቅቷቸው በሽንፈት ከቀጣዩ የአለም ዋንጫ ውጪ ሆነዋል። በዓለም እግር ኳስ ደረጃ 67ኛ ላይ የተቀመጡት ሰሜን መቂዶኒያዎች 6ኛ ላይ የምትገኘው ጣሊያንን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከወሳኝ 90 ደቂቃዎች በኋላ በዓለም ዋንጫው መሳተፍ አለመሳተፋቸውን ያረጋግጣሉ። ቀጣይ የመጨረሻ ተጋጣሚያቸው ደግሞ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አገር ፖርቹጋል ነች። ምንም እንኳ በርካቶች ጣሊያን ይህንን ጨዋታ በቀላሉ አሸንፋ ከፖርቹጋል ጋር የሚኖረው ፍልሚያ ተጠባቂ ይሆናል ብለው ቢገምቱም፣ የእግር ኳስ ነገር ሆኖ ጣሊያን በደጋፊዎቿ ፊት አምስት ጊዜ ብቻ ወደ ግብ ሙከራ በማድረግ ያልተጠበቀ ሽንፈትን አስተናግዳለች። የሰሜን መቂዶኒያ ቀጣይ ተጋጣሚ ፖርቹጋል ደግሞ ሐሙስ ምሽት ከቱርክ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ፖርቹጋል የዓለም ዋንጫ ተስፋዋን በእጅጉ ያለመለመውን ድል ስታስመዘግብ በቀላሉ አልነበረም። ምንም እንኳን ፖርቹጋሎች በኦታቪዮ እና በዲዮጎ ጆታ ግቦች ሁለት ለባዶ መምራት ቢችሉም ጨዋታው ሊጠናቀቅ 25 ደቂቃዎች ሲቀሩት የቱርኩ ቡራክ ዪማዝ ግብ አስቆጥሮ ደጋፊዎቹን አስፈንጥዟል። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ቱርክ የፍጹም ቅጣት ምት ያገኘች ቢሆንም የመጀመሪያዋን ግብ በማስቆጠር ደጋፊዎቹን ያስፈነጠዘው ቡራክ ዪማዝ ዕድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ቱርካውያን አቻ ሊያደርጋቸው የሚችል የግብ ዕድል ባገኙ ጊዜ በደስታ ቢጨፍሩም አጥቂው ግን ኳሷን ከግቡ ከአግዳሚ በላይ በመጠለዝ አንገታቸውን አስደፍቷቸዋል። የፍጹም ቅጣት ምቱ ወደ ግብነት አለመቀየሩ ያነቃቃቸው ፖርቹጋሎች አጥቅተው መጫወት በመጀመር በፈርናንዶ ኑኔዝ አማካይነት ሦስተኛ ግብ አስቆጠሩ። ፖርቹጋሎች ቀጣይ ተጋጣሚያቸውን ሲያውቁ ደግሞ ይበልጥ ደስታ ሆኖላቸዋል። ምክንያቱም ፖርቹጋሎችን ጨምሮ ሁሉም ደጋፊ ጣሊያን እንደምታሸንፍና ቀጣይ ተጋጣሚዎቻቸው አዙሪዎቹ እንደሚሆኑ ነበር የገመቱት። ነገር ግን ባልተጠበቀ መልኩ ሰሜን መቂዶኒያ ጣልያንን ማሸነፏን ተከትሎ የፖርቹጋል የመጨረሻ ተጋጣሚ ሆናለች። ''እንደዚህ አይነት ጨዋታዎች በጣም ፈታኝ ናቸው። የመጀመሪያውን ፈተና አልፈናል። አሁን ሙሉ ትኩረታችን ቀጣዩ ጨዋታ ላይ ነው። ሰሜን መቂዶኒያ ጣሊያንን አሸንፋለች። ጣሊያንን ካሸነፉ ደግሞ እኛን እንዴት ሊከብዱን እንደሚችሉ እናውቃለን'' ብለዋል የፖርቹጋሉ አሰልጣኝ ሳንቶስ። በሌሎች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ስዊድን ቼክ ሪፐብሊክን አንድ ለባዶ ያሸነፈች ሲሆን ዌልስ ኦስትሪያን በተመሳሳይ አንድ ለባዶ ማሸነፍ ችላለች። የሩሲያን ከውድድሩ መታገድ ተከትሎ በቀጥታ ወደ መጨረሻው ዙር ያለፈችው ፖላንድ በቀጣይ ከስዊድን ትፋለማለች። ከሁለቱ አሸናፊው ቡድን ደግሞ በኳታር የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናል ማለት ነው። ስኮትላንድና ዩክሬን ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ወደ ሰኔ መዘዋወሩን ተከትሎ ኦስትሪያን ያሸነፈችው ዌልስ ተጋጣሚዋን ለማወቅ ለወራት መጠበቅ አለባት።", "ያለምዘርፍ በለንደን የማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች በዛሬው ዕለት መስከረም 22፣ 2015 ዓ.ም በለንደን በተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊ ሆነች። ያለምዘርፍ 32 ኪሎሜትር አካባቢ ወድቃ የነበረ ሲሆን ከዚያ አገግማም 2፡17፡26 በሆነ ሰዓት አስደናቂ ድል አስመዝግባለች። በዚህ ውድድር ላይ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መገርቱ አለሙ በሶስተኛነት አጠናቃለች። መገርቱ በ2፡18፡32 ሰዓት ውድድሩን በማጠናቀቅ ነው በለንደን ማራቶን የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው። በወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ልዑል ገብረ ስላሴ በጠንካራ ፉክክር ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ልዑል በኬንያዊው አሞስ ኪፕሩቶ ተበልጦ በ2፡05፡12 ውድድሩን በሁለተኛነት አጠናቋል። የቡድን አጋሮቹ  ቀነኒሳ በቀለ አምስተኛ እና ብርሃኑ ለገሰ በስድስተኛነት ውድድሩን አጠናቀዋል። ያምናው የለንደን ማራቶን አሸናፊ ሲሳይ ለማ በሰባተኝነት ውድድሩን አጠናቋል። የ23 ዓመቷ ያለምዘርፍ በውድድሩ መሃል የደረሰባትን ችግር ተቋቁማ ውድድሩንም ማሸነፍ የቻለች ሲሆን በዕድሜም ትንሿ ማራቶን አሸናፊ በመሆን ታሪክም ሰርታለች። ያለምዘርፍ አሸናፊነቷ የተረጋገጠው በመጨረሻው 5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲሆን በከፍተኛ ፍጥነትም በመስፈንጠር ከፍተኛ ግምት የተሰጣትን የአምናዋን የለንደን ማራቶን አሸናፊ ጆይሲሊን ጄፕኮስጌይን አስከትላ ገብታለች። ያለምዘርፍ ከዚህ ቀደም ካስመዘገበችው ከፍተኛው ሁለተኛው የማራቶን ፈጣን ሰዓት ሶስት ሰኮንዶች ዘግይታ ነው የገባችው። በከፍተኛ ደስታ ተውጣ የነበረችው ያለምዘርፍ “በለንደን ማራቶን በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ። ለዚህ ውድድር ዝግጅት በጣም ጠንክሬ ሰርቻለሁ እናም ድሉን ማግኘቴ በጣም አስደናቂ ነው” ብላለች። በማራቶን ታሪክ ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት እንዲሁም የአለም የ10 ኪሎሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው ያለምዘርፍ በሚያዝያ ወር በሃምቡርግ በነበረው ማራቶን በከፍተኛ ፍጥነት ውድድሩን በማጠናቀቅ በዓለም ታሪክ ፈጣን ሰዓት ካስመዘገቡ አትሌቶች በሰባተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል።", "የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞችን በጠቅላላ አባረረ የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኖች አልጣኞች ከሥራ አባሯል። ሐሙስ ምሽት ውሳኔውን ይፋ ያደረገው ፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ኩዊሲ አፒያህን ጨምሮ የሥራ አጋሮቹ መበተናቸውን አሳውቋል። ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ለምን እንዳሳለፈ ሲያስረዳ የጋናን እግር ኳስ ለማነቃቃትና ወደ ቅድሞ ክበሩ ለመመለስ ነው ሲል አትቷል። አፒያህና አጋሮቹ ብቻ ሳይሆኑ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች እንዲሁም ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች አሠልጣኞችም እንዲበተኑ ተደርጓል። በሙስና ምክንያት ባለፈው ጥቅምት ተበትኖ እንደአዲስ የተቋቋመው የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲሱ አመራር ሥር በርካታ ለውጦችን እያከናወነ ይገኛል። ፌዴሬሽኑ ባወጣው መግለጫ፤ «የብሔራዊ ቡድኖቻችን አሠልጣኞች እስከዛሬ ላደረጉልን ሁሉ እናመሰግናለን። በሄዱበት ሁሉ እንዲቀናቸውም እንመኛለን» ሲል የስንብት ቃሉን አሰምቷል። በውጤት ቀውስ የነበሩት የጥቁር ኮከቦቹ አሠልጣኝ አፒያህ ከብሔራዊ ቡድኑ ሊባረሩ እንደሚችሉ ግምቶች ቢኖሩም በእንደዚህ መልኩ ይሆናል ብሎ የጠበቀ አልበረም። የሴቶችም ሆነ የወንዶች ከ17 ዓመታች፣ ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም ከ23 ዓመት በታች አሠልጣኞችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ጠቅላላ ተበትነዋል። የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደ አዲስ ከተቋቋመ ወዲህ በርካታ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። የቀድሞው የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ፌዴሬሽኑ ቀልጦ እንደ አዲስ መሠራቱ አይዘነጋም።", "ማንችስተር ሲቲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ አለፈ የእንግሊዙ የእግር ኳስ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ የፈረንሳዩን ፒኤስጂ በመርታት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቻምፒየንስ ሊግ ለፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል። ፓሪስ ላይ በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንችስተር ሲቲዎች 2 ለ 1 ማሸነፋቸው ይታወሳል። በትናንት ምሽቱ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ ደግሞ ሲቲዎች በሜዳቸው 2 ለ 0 ፒኤስጂን በመርታት 4 ለ1 በሆነ ድምር ውጤት ነው ያሸነፉት። በትናንት ምሽቱ ጨዋታው ድንቅ አቋም ላይ የሚገኘው አልጄሪያዊው ሪያድ ማህሬዝ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ አገናኝቷል። ፒኤስጂዎች ጨዋታው ከመካሄዱ በፊት የሚተማመኑበት ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ በጉዳት ምክንያት እንደማይጫወት ይፋ አድርገው ነበር። በጨዋታው ፒኤስጂዎች የቀድሞ ፈጣን አጨዋወታቸውን መከተል አቅቷቸው የነበረ ሲሆን ማንችስተር ሲቲዎች ደግሞ ጨዋታውን ተቆጣጥረው ነበር ያመሹት። ልክ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ የፒኤስጂው ኢድሪሳ ጌይ በቀይ እንደወጣው በሁለተኛው ዙር ደግሞ ከእረፍት መልስ አርጀንቲናዊው አንሄል ዲማሪያ ፈርናንዲንሆ ላይ በፈጸመው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዲወጣ ዳኛው ወስነዋል። ሲቲዎች በሜዳቸው ግብ ላለማስተናገድ በጥንቃቄ ሲጫወቱ የነበረ ሲሆን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላም ልፋታችን መና አልቀረም ብሏል። ክለቡም በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ይጫወታል። ዛሬ በሚደረገው ሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ደግሞ ከቼልሲ እና ሪያል ማድሪድ ይገናኛሉ። የዚህ የደርሶ መልስ አሸናፊ በፍጻሜው ማንችሰተር ሲቲን የሚገጥም ይሆናል። ቼልሲና ሪያል ማድሪድ ባደረጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በማድሪድ ሜዳ አንድ አቻ ተለይየተዋል። ማንረችሰተር ሲቲዎች በጋርዲዮላ እየተመሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ስኬትን እያስመዘገቡ ሲሆን ዘንድሮም ለሶስተኛ ጊዜ ዋነጫውን ለማንሳት ከጫፍ ደርሰዋል። በመጪው ቅዳሜ በፕሪምየር ሊጉ ከቼልሲ የሚያደርጉትን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ ደግሞ የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። ማንችሰተር ሲቲ ለአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ በመድረስ ዘጠነኛው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለብ መሆን የቻለ ሲሆን ዋንጫውን የሚያነሳ ከሆነ ደግሞ በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።", "ሞሐመድ ሳላህ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በርካታ ጎል ያስቆጠረ አፍሪካዊ ተጫዋች ሆነ ትናንት እሑድ ዕለት የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሃትሪክ መሥራቱን ተከትሎ፤ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ በርካታ ግቦችን ያስቆጠረ አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኗል። ግብፃዊው ሳላህ ትናንት ጨዋታውን ሲጀምር ከአይቮሪ ኮስታዊው የቼልሲ አጥቂ ዲዲየር ድሮግባ ጋር በ104 ግቦች እኩል ሆኖ ነው። ነገር ግን ሞሐመድ ሳላህ ቡድኑ ሊቨርፑል በኦሌ ጎነር ሶልሻየር የሚመራው ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ በመጀመሪያው አጋማሽ አራት ግቦችን ሲያዘንብ እሱ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል። በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ጨዋታው በተጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ለራሱ ሦስተኛ እንዲሁም ለሊቨርፑል አምስተኛ የሆነችውን ግብ ማስቆጠር ችሏል። በዚህም የ29 ዓመቱ ሳላህ፤ ከዲዲየር ድሮግባ ጋር ሲጋራው የነበረውን የምንጊዜም የፕሪምየር ሊጉ አፍሪካዊ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ክብረ ወሰንን በሦስት ግብ አሻሽሏል። ሳላህ በአውሮፓውያኑ 2017 ላይ ከሮማ ወደ ሊቨርፑል ከተዘዋወረ በኋላ በፕሪምየር ሊጉ ከታዩ ምርጥ የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ መሆን ችሏል። የቀድሞው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋችና በፕሪምየር ሊጉ 95 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ያኩቡ እንደሚለው፤ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ግብ ማስቆጠር የሚችል ተጫዋች የትኛውም ሊግ ሄዶ ግብ ማስቆጠር አይከብደውም። ሞሐመድ ሳላህ ደግሞ ወደ ሊቨርፑል በመጣ በመጀመሪያው ዓመት 32 ግቦችን በማስቆጠር በርካቶችን አስገርሟል። ባለፈው ዓመት ቡድኑ ሊቨርፑል የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሲሆን ሳላህ 19 ግቦችን በስሙ ማስመዝገብ ችሎ ነበር። እንደውም ያን ዓመት በጥሩ አቋም ላይ አለመሆኑ በርካታ ግቦችን እንዳያገባ አደረገው እንጂ በዛኑ ዓመት ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ሊወስድ ይችል ነበር። ሞሐመድ ሳላህ ሁለት ጊዜ የቢቢሲ እና የካፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ሽልማቶችን ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ በሊቨርፑል ቆይታውም እስካሁን በዓመት ከ15 ግቦች በታች አስቆጥሮ አያውቅም። ሳላህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሲመጣ የተጫወተው ለሌላኛው የፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ ቼልሲ ሲሆን ማስቆጠር የቻለው ግን ሁለት ግቦችን ብቻ ነበር። \"በጣም አስተዋይ ነው። እንቅስቃሴው የማይታመን ነው። ትክክለኛ የፊት መስመር አጥቂ አይደለም። ስለዚህ በክንፍ በኩል እየተሳበ ወደ መሐል በመግባት ግቦችን ያስቆጥራል። የት መሄድ እንዳለበት ያውቃል፤ መቼ መሮጥ እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል\" ሲል ያኩቡ አድናቆቱን ገልጿል። ጨምሮም \"እንደ ሳላህ ያሉ ተጫዋቾች በዘመናዊ እግር ኳስ ጥቂት ናቸው። እውነት ለመናገር በጣም የተለየ ድንቅ አጥቂ ነው። ባርሴሎና በሜሲ ነበር የሚታወቀው፤ ሊቨርፑል ደግሞ በሞሐመድ ሳላህ። ሁለቱም ለክለቦቻቸው በርካታ ነገሮችን አድርገዋል፤ ትልቅ የሆነ ተጽዕኖ መፍጠር ችለዋል\" ብሏል።", "አሜሪካ፡ ትዊተር ቲክቶክን ለመግዛት ፍላጎት አሳየ ትራምፕ የቻይናው ቲክቶክ ለአሜሪካው ኦራክል እንዲሸጥ እንደሚፈልጉ ተናገሩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የአሜሪካው ኦራክል ቲክቶክን ቢገዛው መልካም ነገር ነው አሉ፡፡ ይህን የተናገሩት ኦራክል የቻይናውን ዝነኛ የማኅበራዊ ትስስር መተግበሪያ ቲክቶክን ለመግዛት እየተነጋገረ ባለበት ሰዓት ነው፡፡ ኦራክል ቲክቶክን የሚገዛው በአሜሪካ፣ በአውስትራሊያና በኒዊዚላንድ ያለውን ድርሻና ገበያ ነው፡፡ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ለቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ ኩባንያ የአሜሪካ ድርሻውን በ90 ቀናት ውስጥ እንዲሸጥ አስጠንቅቀው ካልሆነ ግን ቲክቶክ በአሜሪካ ይዘጋል ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ የኦራክል ሊቀመንበር ላሪ ኤሊሰን የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ ሲሆኑ ለምርጫ ቅስቀሳ የገንዘብ መዋጮ ከሚያሰባስቡላቸው ሰዎች አንዱ ነው፡፡ አሁን እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ኦራክል ቲክቶክን ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት አድሮበታል፡፡ ከተቻለም ከአውስትራሊያ፣ አሜሪካና ኒውዚላንድ ገበያው በተጨማሪ የካናዳን ለማካተት ይፈልጋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ወር መጀመርያ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ቲክቶክ ለአሜሪካ ኩባንያ ሲሸጥ መንግስት የተወሰነ ገንዘብ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ይህ በአሜሪካ የነጻ ኢኮኖሚ ሥርዓት የተለመደ ነገር አይደለም፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክ ከአሜረካ ድርሻውን ሽጦ ይውጣ በሚል 90 ቀናትን ያስቀመጡት ድርጅቱ የዜጎችን መረጃ እየቃረመ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አሳልፎ ይሰጣል በሚል ነው፡፡ ባይትዳንስ በበኩሉ ክሱን አስተባብሏል፡፡ ብዙዎች ቲክቶክ በቻይናና በአሜሪካ የንግድ ጦርነት ውስጥ የጦስ ዶሮ ሆኗል ብለው ያስባሉ፡፡ ከኦራክል ሌላ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ለመግዛት ከባለቤቱ ባይትዳንስ ኩባንያ ጋር ንግግር መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ከሁለቱ ግዙፍ ኩባንያዎች ሌላ ትዊተርም ቲክቶክን ለመግዛት ፍላጎት አሳይቷል፡፡ ቲክቶክ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ተወዳጅ የስልክ መተግበሪያ መሆኑን የሚያሳየው በዚህ ዓመት ብቻ 2 ቢሊዮን የዓለማችን ሰዎች ስልካቸው ላይ ጭነውታል፡፡", "የአፍሪካ ዋንጫ የአራት ጊዜ አሸናፊዋ ጋና ከምድቧ ሳታልፍ ቀረች ትላንት በአፍሪካ ዋንጫ የመጨሻ የምድብ ጨዋታዋን ከኮሞሮስ ጋር ያደረገችው ጋና ሁለት ለሦስት ተሸንፋ ከ2022 የአፋሪካ ዋንጫ መሰናበቷ እርግጥ ሆኗል። የአፍሪካ ዋንጫ የአራት ጊዜ ባለ ድል ጋና በመጀመርያው ዙር በእግር ኳስ እምብዛም በማትታወቀው ኮሞሮስ አሳፋሪ የተባለ ሽንፈትን ነው ያስተናገደችው። የኮሞሮሱ ኤል ፋርዱ ቤን ናቦውሃኔ ያስቆጠራት ጎል የደሴቷን አገር በጨዋታውን እንድትመራ አድርጓታል። የክንፍ ተጫዋቿ አንድሬ አየው በቀጥታ ቀይ ካርድ የተሰናበተባት ጋና ጨዋታውን በአስር ሰው ለማካሄድ ተገዳለች። ጥቋቁር ከዋክብት የሚሰኘው የጋና ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ከተቆጠረባቸው ግብ በኋላ ሁለት አቻ ላይ መድረስ ችለው ነበር። ሆኖም መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ሊጠናቀቅ 5 ደቂቃ ሲቀር ሞግኒ ለኮሞሮስ ሦስተኛውን ግብ አስቆጥሯል። ሽንፈቱ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2006 በኋላ የጋና ብሔራዊ ቡድን በጊዜ ከውድድሩ የተሸኘበት ሆኖ ተመዝግቧል። ጋና እና ኮሞሮስ በተካተቱበት ሦስተኛው ምድብ ኮሞሮስ በውድድሩ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባ ምርጥ ሶስተኛ ሆና ወደ ጥሎ ማለፍ የመሸጋገር እድል አላት ተብሏል። የኮሞሮስ ብሔራዊ ቡድን በዓለም የእግር ኳስ ደረጃ 132ኛ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ከጋና ብሔራዊ ቡድን ቁልቁል ርቆ የሚገኝ ነው። ምንም እንኳን ቡድኑ በዘንድሮ ውድድር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጨዋታዎች በሽንፈት ቢያጠናቅቅም በትላንቱ ድሉ ግን ምርጥ ሦስተኛ በመሆን ወደ ጥሎ የማለፍ ዕድል ሊያገኝ ይችላል። ከአንድ ሚሊዮን በታች ሕዝብ ያላት ትንሿ ደሴት አገር ኮሞሮስ እንደ አውሮፓውያኑ በ1996 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጋጠው አደጋ ብዙዎች ያውቋታል። የተቀረው ዓለም ደግሞ በመፈንቅለ መንግሥት ታሪኳ የሚያነሳት ሲሆን በእግር ኳሷ እምብዛም የምትታወቅ አይመስልም። ትላንት በ2022 አፍሪካ ዋንጫ የውድድሩን የአራት ጊዜ ባለ ድል ጋናን ያሸነፈችበት ጨዋታ በእግር ኳስ ታሪኳ ትልቅ ክስተት ሆኖ ተመዝግቦላታል።", "ፊፋ ፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በፊፋ ለአምስት ዓመት ታገዱ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት አህመድ የተለያዩ የሥነ ምግባር ደንቦችን በመጣስ ፊፋ የአምስት ዓመት ዕገዳ ጣለባቸው። የፊፋ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት የ60 ዓመቱ አህመድ የፊፋን የታማኝነት ግዴታን፣ ስጦታ መቀበልና መስጠትን፣ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀምና የተቋሙን ንብረት አላግባብ መጠቀምን የመሳሰሉትን ደንቦች በመጣሳቸው ነው የታገዱት። ፊፋ ያወጣው መግለጫ አንዳለው \"በአህመድ ላይ በሦስት ዓመታት ዓመታት ውስጥ ወደ መካ ለተደረጉ ሐይማኖታዊ ጉዞዎች የወጣ ወጪንና የስፖርት ቁሳቁሶች አምራች ድርጅት ከሆነው ታክቲካል ስቲል ከተባለው ተቋም ጋር የተደረሰውን ስምምነት ጨምሮ ከካፍ አስተዳደር ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች ላይ ምርመራ ተደርጓል።\" በአህመድ ላይ ከዕገዳ በተጨማሪ የ200 ሺህ ዶላር ቅጣትም ተጥሎባቸዋል። ነገር ግን እሳቸው ምንም አላጠፋሁም ሲሉ ይከራከራሉ። የማዳጋስካር ዜጋ የሆኑት አህመድ የዕገዳ ውሳኔው ከደረሳቸው በኋላ ለዓለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት (ካስ) አቤት ማለት የሚችሉ ሲሆን ሂደቱም እስከ ሁለት ወራት ሊወስድ ይችላል ተብሏል። የቀድሞው የማዳጋስካር የእግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝዳንት የነበሩት አህመድ ባለፈው ወር በሚመጣው መጋቢት በሚካሄደው የካፍ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውድድር ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳለቸው አሳውቀው ነበር። ለድጋሚ ምርጫ የመወዳደር ዕድላቸው ግን የሚወሰነው ለፍርድ ቤት በሚያቀርቡት አቤቱታ በመርታት ብቻ ሳይሆን፤ የጉዳያቸው የዕጩዎች መቀበያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ዕልባት ካገኘ ብቻ ነው። አህመድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከዳኑ በኋላ የጤና ሁኔታቸውን በመግለጽ ለማገገሚያ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልጉ አሳውቀው የካፍ ኃላፊነታቸውን ለምክትላቸው አስተላልፈዋል። የካፍ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ኮንስታንት ኦማሪም ኃላፊነቱን በመያዝ የአህጉሪቱን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን እየመሩ ይገኛሉ።", "ለአፍሪካ ዋንጫ የሚፋለሙት ኃያላን እንስሳት ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ግብጽ ብምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የ24 ሃገራት ቡድኖች ይሳተፋሉ። ቡድኖቹ ከነገቡት የሃገር ባንዲራና ስም ባሻገር መጠሪያ ቅጽል አላቸው። በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ቅጽል ስሞች ጉልህ ቦታ አላቸው። እነዚህ ስሞች ለቡድኖቹ ደጋፊዎች መለያ ከመሆን በተጨማሪ ተጫዋቾችን በማነቃቃት በኩልም ይጠቅማሉ። የብሔራዊ ቡድኖች ቅጽል ስም፣ በቀለማት ካሸበረቁ ደጋፊዎችና የከበሮ ድምፅ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ መለያ ድምቀቶች ናቸው። በሚቀጥሉት ሳምንታት ግብጽ ውስጥ ንስሮቹ ጎልተው ይታያሉ ተብለው ይጠበቃል። • የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ውጤት ይገምቱ • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በሚለብሰው አረንጓዴ ማሊያ ተለይቶ የሚታወቅ ቢሆንም ንስሮቹ የሚለው ስያሜያቸው ግን የበለጠ መለያቸው ነው። ብድኑ ይህን ስያሜ የወሰደው ከሃገሪቱ ብሔራዊ መለያ ላይ ነው። ቱኒዚያ ከካርቴጅ ሥልጣኔ ጋር በነበራት ግንኙነት የተነሳ ቡድኗ የካርቴጅ ንስር የሚል መጠሪያን አግኝቷል። ብሔራዊ መለያቸውም ንስር ነበረ። እዚህ ጋር የማሊ ንስሮችም ሊዘነጉ አይገባም። በተጨማሪም ኡጋንዳም የበራሪ አእዋፍ (ሽመላ) መለያ ነው ያላት። የጫካው ግብግብ እዚህ የእግር ኳስ ሜዳውም ውስጥ ልክ እንደጫካው ዓለም የበላይነት ለማግኘት የሚደረግ ፍልሚያ አለ። ከአንበሳ እስከ እባብ፣ ከአቦሸማኔ እስከ ዝሆን ያሉት የዱር እንስሳት በዚህ ዓመቱ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ቦታ አላቸው። መሪዎችን የማክበር ጠንካራ የአፍሪካዊያን ባህል መሠረት አንዳንድ ቡድኖች ስያሜያቸውን ከእነርሱ ወስደዋል። ሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን በመውሰድ የውድድሩ ንጉሥ የሆኑት ግብጻዊያን ለውጤታቸው የሚመጥን ፈርዖኖቹ የሚለውን ስያሜ ከቀደምት ንገሥታቶቻቸው ወስደዋል። ፈርዖኖቹ የዚምባብዌ ጦረኞች ከተባሉት የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አድርገው ድል ቀንቷቸዋል። • የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል የጨዋታዎቹን ዝርዝር እዚህ ያገኛሉ • የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ውጤት ይገምቱ የኬንያ ብሔራዊ ቡድን ስያሜያቸውን ከዱር እንስሳትና ከመሪዎች ውጪ ካደረጉ ቡድኖች መካከል ነው። የሃራምቤ ከዋክብት ይባላሉ፤ ሃራምቤ የሚለው የስዋሂሊ ቃል ሕብረት መፍጠር ሲሆን ጥሪው ከቡድኑ አልፎ በሃገር ደረጃ ለአንድ ዓላማ መሰባሰብን ያመለክታል። የዝነኞቹ የጋና ብሔራዊ ቡድን መጠሪያ ጥቋቁሮቹ ከዋክብት ሲሆን ይህም የተወሰደው ሃገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ካልው ጥቁር ኮከብ ነው። ይህም አንድነትን ለማመልከት እንደዋለ ይነገራል። ከሳምንታት በኋላ የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ሲጠናቀቅ ንስሮቹ ከሁሉ ከፍ ብለው መብረራቸው፤ አንበሶቹ ኃያልነታቸውን እንዳስከበሩ መቆየታቸውን ነገሥታቱም የበላይ ሆነው በመሪነት መዝለቃቸው የሚለይ ይሆናል። • ከእግር ኳስ ሜዳ ወደ ኮኛክ ጠመቃ", "ማይክ ታይሰን ወደ ቦክስ መድረክ ሊመለስ ነው የቀድሞው የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻምፒዮን ማይክ ታይሰን ወደ ቡጢው ዓለም ሊመለስ ነው። ዝነኛው የቦክስ ተፋላሚ ማይክ ታይሰን ዕድሜው 54 ደርሷል። ወደ ቦክስ መፋለሚያ መድረክ የመመለሱ ዜና እያነጋገረ ነው። ማይክ ታይሰን ለአጭር ደቂቃ በሚቆየው ፍልሚያ የሚገጥመው የአራት ጊዜ የቀድሞው የዓለም ሻምፒዮን የነበረውን ሮይ ጆንስ ጁኒየርን ይሆናል። ሁለቱ ዝነኞች ለዚሁ ግጥሚያ የሚገናኙት መስከረም 12 ላይ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ነው። ማይክ ታይሰን ለመጨረሻ ጊዜ ደንበኛ የቦክስ ግጥሚያ አደረገ የሚባለው እንደ አውሮፓዊያኑ በ2005 ነበር። በዚያ ውድድር ላይ በአየርላንዳዊው ተወዳዳሪ ኬቪን ማክብራይድ ክፉኛ ተደብድቦ ነበር። ይህም ታይሰን ካደረጋቸው 58 የቡጢ ፍልሚያዎች 6ኛው ሽንፈቱ ነበር። በመጪው መስከረም ወር ታይሰንን የሚገጥመው ጆንስ ዕድሜው 51 ሲሆን በየካቲት 2018 ቡጢኛ ስኮት ሲግመንን ካሸነፈ ወዲህ ውድድር አድርጎ አያውቅም። የካሊፎርኒያ ግዛት የአትሌቲክስ ኮሚሽን ይህ የቡጢ ፍልሚያ ሰዎች በተገኙበት እንዳይካሄድ ያዘዘ ሲሆን፤ ውድድሩ በክፍያ ብቻ በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል። ፍልሚያው 8 ዙሮች ይኖሩታል። ማይክ ታይሰን የዓለም የከባድ ሚዛንን ሻምፒዮና የሆነው ገና በ20 ዓመቱ ነበር። ይህም የሆነው በፈረንጆቹ በ1986 ትሪቨር በርቢክን ማሸነፉን ተከትሎ ነው። በቅርቡ ታይሰን በማኅበራዊ ሚዲያ የቦክስ ልምምድ ሲያደርግ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መውጣታቸውን ተከትሎ ወደ ቦክስ ስፖርት ሊመለስ ነው የሚሉ ጉምጉምታዎች እዚያም እዚህም መሰማት ጀምረው ነበር። በ2006 ታይሰን ተመሳሳይ አራት ዙር የቦክስ ግጥሚያ ከኮሪ ሳንደርስ ጋር ማድረጉ ይታወሳል። ያም የሆነው ማይክ ታይሰን በ2003 የገንዘብ ኪሳራ ገጥሞት ስለነበረና ገንዘብ ስላስፈለገው ነበር። በቅርብ ጊዜ ደግሞ ማይክ ታይሰን ከኢቫንደር ሆሊፊልምድ ጋር ዳግም ሊገጥም ይችላል የሚሉ ወሬዎች መውጣት ጀምረው ነበር። የ57 ዓመቱ ሆሊፊልድ ከቡጢ ራሱን ያገለለው በ2016 ነበር። ከታይሰን ጋር በ1990ዎቹ ሁለት ጊዜ በቦክስ መድረከረ ላይ ተገናኝተው ሁለቱንም ጊዜ ሆሊፊልድ ድል ቀንቶት ነበር። ከዚህ ውስጥ በብዙዎች አእምሮ የቀረው በ1997 ታይሰን የሆሊፊልመድን ጆሮ መንከሱ ነበር። የታይሰን የአሁኑ ተጋጣሚ ጆንስ ጁኒየር ስለ ውድድሩ በለቀቀው የቪዲዮ ማስታወቂያ \"የታይሰንና የእኔ ወድድር የዳዊትና የጎሊያድ ፍልሚያ ነው የሚሆነው\" ሲል ቀልዷል።", "የዓለም ዋንጫ፡ ቤልጂየም በሞሮኮ መሸነፏ ቁጣ ሲቀሰቅስ ስፔን እና ጀርመን አቻ ተለያይተዋል በድራማዎች በተሞላው የኳታር የዓለም ዋንጫ ሞሮኮ በፊፋ የአገራት የደረጃ ሠንጠረዥ ሁለተኛ የሆነችውን ቤልጂየምን በማሸነፍ ታሪክ ጽፋለች። አብድልሃሚድ ሳቢሪ እና ዛካሪያ አቡክላል ያስቆጠሯቸው ጎሎች አፍሪካዊቷን አገር ወደ ድል መልሰዋል። ሳቢሪ ከፍጹም ቅጣት ምት በቀጥታ በመምታት ነው ኳሷን ከመረብ ያገናኘው። የቤልጂየሞችን ተስፋ ያሟጠጠችው ጎል በተጨማሪ ሰዓት በአቡክላል ተቆጥራለች። ድሉ በአል ቱማማ ስታዲም ለተገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሞሮኳዊያን ፈንጠዝያን ፈጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ ሞሮኮዋ ራባት በደስታዋን ስትገልጽ አምሽታለች። ብራስልስ ደግሞ ደጋፊዎች ባስነሱት ግጭት ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል። የቤልጂየም ደጋፊዎች የሱቆችን መስታዎቶች ሰባብረዋል። ርችቶችን ከመወርወር በተጨማሪ መኪኖችንም ማቃጠላቸው ታውቋል። ፖሊስ 11 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። በምድቡ ሌላ ጨዋታ ክሮሺያ ምድቡን መምራት የሚያስችላትን ድል አስመዝግባለች። ካናዳን 4 ለ 1 በማሸነፍ ነው ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋዋን ያለመለመችው። ካናዳ በአልፎንሶ ዴቪስ የጎል ቀዳሚ መሆን የቻለችው በሁለተኛው ደቂቃ ነበር። የካናዳን በላይነት ተቋቁመው ወደ ጨዋታው ተመለሱት ክሮሺያዎች በ36ኛው ደቂቃ አቻ ለመሆን ቻሉ። ክሮሺያ ካርማሪች፣ ሊቫያ እና ማዬር ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሦስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል። ካናዳ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አለመቻሏን አረጋግጣለች። ክሮሺያ እና ሞሮኮ ምድቡን በአራት ነጥብ ተከታትለው ይመራሉ። ቤልጂየም አንድ ነጥብ ሲኖራት ካናዳ ያለምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። በቀጣይ ካናዳ ከሞሮኮ እና ክሮሺያ ከቤልጂየም በሚያደርጉት ጨዋታ የምድቡ አላፊ አገራት ይለያሉ። በምድብ አምስት ሲጠበቅ ነበረው የስፔን እና የጀርመን ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል። ጨዋታውን በመቆጣጠር የጀመሩት ስፔኖች ጎል በማስቆጠርም ቀዳሚ ሆነዋል። ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው አልቫሮ ሞራታ ባስቆጠራት ጎል ስፔን ቀዳሚ ሆነች። ከጎሉ በኋላ ጫና ፈጥረው መጫወት ቻሉት ጀርመኖች እነሱም ተቀይሮ በገባው ኒክላስ ፉልኩግ አማካይነት አቻ ለመሆን በቅተዋል። ሌሮይ ሳኔ ባለቀ ሰዓት ጀርመንን አሸናፊ የምታደርግ ዕድል አግኝቶ ሳይጠቀምባት ቀርቷል። በምድቡ ሌላ ጨዋታ ጃፓን በኮስታ ሪካ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። ጀርመንን በማሸነፍ አስደናቂ ድል ያስመዘገበችው ጃፓን በሁለተኛው ጨዋታ እጅ ሰጥታለች። የኮስታ ሪካን የተከላካይ መስበር የተሳናት ጃፓን በኬይሸር ፉለር ጎል ተሸንፋለች። ጃፓን ጀርመንን እንደማሸነፏ እና ኮስታ ሪካ ደግሞ በስፔን 7 ለ 0 መሸነፏን ተከትሎ እስያዊቷ አገር በቀላሉ አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን ታረጋግጣለች ተብሎ ነበር። ሆኖም በ81ኛው ደቂቃ በተቆጠረባት ጎል ጃፓን ለመሸነፍ ተገዳለች። ምድቡን ስፔን በአራት ነጥብ ትመራለች። ጃፓን እና ኮስታ ሪካ በሦስት ነጥብ ይከተላሉ። ጀርመን በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አራቱም አገራት ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አላቸው። የዓለም ዋንጫው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። በምድብ ሰባት የሚገኙት ካሜሩን እና ሰርቢያ ሰባት ሰዓት ይገናኛሉ። ጨዋታው በአል ጃኑብ ስታዲየም ይከናወናል። አስር ሰዓት ላይ ደቡብ ኮሪያ እና ጋና ይጫወታሉ። ይህ ምድብ ስምንት ጨዋታ ኤጁኬሽን ሲቲ ስታዲየም ላይ ይደረጋል። በጉዳት ኔይማርን ጨምሮ ተጫዋቾቿን ያጣችው ብራዚል ከስዊዘርላንድ ትጫወታለች። ጨዋታው አንድ ሰዓት ላይ በዕቃ መጫኛ ኮንቴነር በተገነባው በስታዲየም 974 ይከናወናል። ሉሳይል ስታዲየም ምሽት አራት ሰዓት የሚከናወንን የምድብ ስምንት ሁለተኛ ጨዋታ ያስተናግዳል። በጨዋታው ፖርቹጋል እና ኡራጓይ ይገናኛሉ።", "የዓለም ዋንጫ፡ የኢራን ተጫዋቾች ብሔራዊ መዝሙራቸውን ሳይዘምሩ ቀሩ የኢራን ተጫዋቾች በሃገራቸው ያለውን ጸረ መንግስት ተቃውሞ በሚደግፍ መልኩ በዓለም ዋንጫው ከእንግሊዝ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ብሔራዊ መዝሙራቸውን ሳይዘምሩ ቀርተዋል። ብሔራዊ መዝሙሩ ሲጀምር አንዳንዶች ሲጮሁ ሌሎች ደግሞ “ሴት፣ ህይወት፣ ነጻነት” የሚል ጽሑፍ ከፍ አድርገው አሳይተዋል። የኢራን ቴሌቪዥን ብሔራዊ መዝመሩ ሲጀምር ቀጥታ ስርጭቱን ገታ አድርጎ ቀደም ብሎ የተቀረጸ የስታዲየሙን ምስል አሰራጭቷል። ባለፉት ወራት ቴህራን ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ አስተናግዳለች። የጭንቅላት መሸፈኛ በትክክል አላደረግሽም በሚል በስነ ምግባር ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ህይወቷ ያለፈው ማህሳ አሚኒ የተባለች የ22 ዓመት ኢራናዊት ጉዳይ አመጹን ማቀጣጠሉ ይታወሳል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይናገራሉ። 16 ሺህ 800 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መታሰራቸውን ገልጸዋል። ተቃውሞዎቹ በውጭ ጠላቶች የተቀናበሩ “አመጾች” ናቸው ሲሉ የኢራን መሪዎች ተናግረዋል። ኢስላሚክ ሪፐብሊኳን በመተቸት የሚታወቀው የቀድሞ ተጫዋች ስም በማንሳት ደጋፊዎች በእረፍት ሰዓት “አሊ ካሪሚ” ሲሉ ተደምጠዋል። ብዙ የኢስላሚክ ሪፐብሊኩ ተቃዋሚዎች ተጫዋቾቹ በይፋ ተቃውሞውን ባለመደገፋቸው እና ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን በማግኘታቸው ሲተቿቸው ነበር። ከጨዋታው በፊት አስተያየቱን የሰጠው ቡድኑ አምበል ኤህሳን ሃጅሳፊ ተጫዋቾቹ ህይወታቸውን ያጡትን “እንደሚደግፉ” ተናግሯል። “በጨዋታው መርህ እና በዓለም ዋንጫው ህግጋት መሠረት ከሆነ” ተጫዋቾቹ “የመቃወም ነጻነት” አላቸው ሲሉ አሰልጣኝ ካርሎስ ኬሮዥም ገልጸዋል። ብሔራዊ ቡድኑ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን በመስከረም ወር ሲያከናውን ተጫዋቾች የቡድኑን አርማ ሸፍነዋል። በእንግሊዝ 6 ለ 2 ከተሸነፉ በኋላ አሰልጣኝ ኬሮዥ ቡድኑ በሃገር ቤቱ አለመረጋጋት ጫና እንዳደረገበት ገልጸዋል። “እግር ኳሳዊ ያልሆነ ሃሳብ በማምጣት ቡድኑን ለመበጥበጥ የሚመጡትን አናስተናግድም። ምክንያቱም እነዚህ እግር ኳስ ተጫዋቾች ናቸው” ብለዋል ፖርቹጋላዊው። “ልጆቹ ይጫወቱበት። ዓላማቸው ይህ ነው። እንደሌሎች ቡድኖች ሁሉ ሃገራቸውን እና ህዝባቸውን ለመወከል ይፈልጋሉ።ሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች በየሃገሮቻቸው ችግር አላቸው” ብለዋል። ቀድሞውየማንቸስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝ አክለውም “ኃላፊነታቸው ያልሆንን ነገርመጥቶ በዚህ የዓለም ዋንጫ ወቅት መጠየቅ ተገቢ አይደለም። ለህዝቡ ደስታ እናክብር ለማስገኘት ነው ዓላማቸው።“ “እንደ ተጫዋች ራሳቸውን ለማሳየት በመፈለጋቸው ባለፉት ጥቂት ቀናት ምን ዓይነት ነገሮች እንዳሳለፉ ማሰብ ያቅታችኋል” ብለዋል። ስለጉዳዩ አስተያየቱን የሰጠው ቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ጋሪ ሊንከር “በጣም ሃይለኛ እና ትልቅ መልዕክት ነው” ብሏል። “እግር ኳስ ጉልበቱን ለመልካም ነገር ለማዋል እየሞከረ ነው” ሲል ገልጿል።", "የዓለም ዋንጫን የምታስተናግደው የኳታር ፈታኙ ሙቀት በመጪው ዓመት ኅደር ወር የሚጀመረውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ያለችው ኳታር ከባድ ወቀሳ እየቀረበባት ነው። ኳታር ያላት ከፍተኛ ሙቀት ለስፖርት ውድድሮች አዳጋች መሆኑ ከሦስት ዓመት በፊት በተደረገው የአትሌቲስክስ ሻምፒዮና ወቅት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ ስፖርተኞችን አስቸግሮ ውጤት ለማስመዝገብ ሳይችሉ ቀርተዋል። የቢቢሲ የአረብኛ ቋንቋ አገለግሎት በቅርቡ ባደረገው ምርመራ ኳታር ውስጥ በተለያዩ የሙያ መስኮች ላይ የተሰማሩ የውጭ አገር ዜጎች ሕይወታቸውን አስከሚያሳጣ ችግር እየተዳረጉ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። በተለይ የአገሪቱ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሁኔታ ውስጥ በሚሠሩበት ጊዜ አስፈላጊው ጥንቃቄና ድጋፍ ስለማይደረግላቸው ለጉዳት እየተደረጉ ነው።", "የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀትና የልብ ህመም ተጋላጭ ናቸው ተባለ አንድ የጥናት ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀት ይጋለጣሉ፤ የሚደግፉት ቡድን ሲሸነፍ የሚሰማቸው ስሜትም ለልብ ህመም ያጋልጣቸዋል ተባለ። በምሳሌነት ደግሞ በ 2014 ቱ የዓለም ዋንጫ ብራዚል በጀርመን 7 ለ 1 በተሸነፈችበት ወቅት በርካታ ብራዚላውያን ለከባድ የጤና እክሎች መጋለጣቸውን ጥናቱ ጠቅሷል። ጥናቱ እንደጠቆመው በወቅቱ የብራዚል ደጋፊዎች ብሄራዊ ቡድናቸው በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፉን ተከትሎ ለጭንቀት የሚያጋልጡ ሰውነት የሚያመርታቸው ሆርሞኖች መጠን መጨመር ታይቶባቸዋል። • አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ፡ \"የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው\" • ከኮከብ እግር ኳስ ተጫዋችነት - ፖለቲካ - ወደ ታክሲ ሹፌርነት ይህ ደግሞ አደጋ አለው ይላሉ ተመራማሪዎቹ፤ የደም ግፊታቸው ጨምሯል፤ እንዲሁም ልባቸው ተጨንቃ ልትፈነዳ ደርሳም ነበር ብለዋል። ምንም እንኳን በርካቶች ወንዶች ለእግር ኳስ የበለጠ ፍቅር ስላለቸው ለበለጠ ጭንቀት ይጋለጣሉ ብለው ቢያስቡም፤ ተመራማሪዎቹ አገኘነው ባሉት መረጃ መሰረት ግን በሴትና በወንድ እግር ኳስ ደጋፊዎች የጭንቀት መጠን ላይ ልዩነት አልተገኘም። ''ለረጅም ዓመታት ድጋፋቸውን ለአንድ ቡድን ብቻ አድርገው እግር ኳስን የሚመለከቱ የኳስ አፍቃሪዎች ደግሞ ለበለጠ አካላዊ መዛልና ጭንቀት የተጋለጡ ናቸው'' ይላሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የጥናቱ ተሳታፊ ዶክተር ማርታ ኒውሰን። እሳቸው እንደሚሉት አልፎ አልፎ ቡድናቸውን ለመደገፍ እግር ኳስን የሚመለከቱ ሰዎች ጭንቀት ቢያጋጥማቸውም እንደ ቋሚ ደጋፊዎቹ ከፍተኛ አይደለም። ለረጅምና ተከታታይ ጭንቀት የሚጋለጡ ሰዎች ተከታዩቹ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፡ ከባድ የእግር ኳስ ፍቅር ያለባቸው ደጋፊዎች ቡድናቸው ሲሸነፍ ወይም ግብ ሲቆጠርበት የሚያጋጥሙ የልብ ድካም በሽታዎች ከጊዜ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውንም ጥናቱ ጠቁሟል። • \"በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር ታሪክ መስራቴ አስደስቶኛል\" ሎዛ አበራ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ለማስረጃነት እንዲጠቅማቸው በእግር ኳስ ፍቅር ያበዱ 40 ሰዎችን ከመረጡ በኋላ ከዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች በፊትና በኋላ ምራቃቸውን በመውሰድ መርምረዋል። ባገኙት መረጃ መሰረትም በተለይ ደግሞ ከግማሽ ፍጻሜ በኋላ የደጋፊዎቹ የጭንቀት መጠን በእጅጉ ከፍ ብሏል።", "እግር ኳስ፡ ቀጣይ መድረሻው ያልታወቀው የሊዮኔል ሜሲ ጉዳይ የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ክለቡ ባርሴሎናን ሊለቅ እንደሚችልና ሌላ አገር ሄዶ መጫወት እንደሚፈልግ በተናገረ ጊዜ በርካቶች ዜናውን በእንባ ነበር የተቀበሉት። ቤሰቦቹን ጨምሮ። ነገር ግን መጨረሻ ላይ ሜሲ ያሰበው ነገር ሳይሆን ቀረና በዘንድሮው የላሊጋ የውድድር ዓመት በባርሴሎና ለመቆየት ተገዷል። ሜሲ ከባርሴሎና ጋር የገባው ውል የሚያበቃው በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት 2021 ነው። ከዚያ በፊት ተጫዋቹን መግዛት የፈለገ ክለብ ደግሞ 700 ሚሊዮን ዩሮ ማውጣት ይኖርበታል። ሜሲ ግን ከባርሴሎና ጋር በተፈራረመው ውል ላይ \"'ከፈለኩ በነፃ እንድሰናበት' የሚል አንቀፅ አለ፤ እሱን ተግባራዊ ማድረግ እፈልጋለሁ\" ብሎ ነበር። ሊዮኔል ሜሲ ባርሴሎናን የተቀላቀለው የ12 ዓመት ታዳጊ እያለ ነበር። 10 የላ ሊጋ ዋንጫ ጨምሮ 34 ዋንጫዎችን ከቡድን አጋሮቹ ጋር ማንሳት ችሏል። ከዓመታት በኋላ ግን የ33 ዓመቱ ሜሲ ጫማውን የሚሰቅለው በየትኛው ክለብ ነው የሚለውን መወሰን ይጠበቅበታል። ምንም እንኳን ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች ባርሴሎናን ለመልቀቅ ፍላጎት አሳይቶ የነበረ ቢሆንም እንደአሁኑ ግን ክለቡን ለመቀልቀቅ የተቃረበበት አጋጣሚ አልነበረም። የዚያን ጊዜ ወደ አርጀንቲና መመልስን ችላ በማለት ስፔን ውስጥ ከአባቱ ጋር ለመሆን መወሰኑ በርካታ የቤተሰቡ አባላትን ልብ ሰብሮ ነበር። ውሳኔው ህይወቱን የመቀየር ኃይል ነበረው። መጨረሻው ያልታወቀውን የሜሲ ጉዳይ በድጋሚ ትኩረት እንዲያገኝ ያደረገው ደግሞ ባርሴሎና በዚህ ሳምንት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከፈረንሳዩ ፒኤስጂ ጋር ያለበት ጨዋታ ነው። ፒኤስጂዎች ከጅምሩ የሊዮኔል ሜሲ አድናቂ መሆናቸውንና ክለቡን እንዲቀላቀል እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ጨዋታው በተቃረበ ቁጥር ደግሞ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሃን ስለ ሜሲ የተለያዩ መረጃዎችን ይዘው መውጣት ጀምረዋል። አንድ ጋዜጣ ደግሞ ሊዮኔል ሜሲ የፒኤስጂን ማልያ ለብሶ የሚያሳይ ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ተጫዋቹ ፒኤስጂን ሊቀላቀል የሚችልባቸው ሁኔታዎችንም በዝርዝር አስነብቧል። የፒኤስጂው ኮከብና የቀድሞ የባርሴሎና ተጫዋች ኔይማርም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት ሰጥቷል። ባለፈው የፈረንጆቹ ታኅሣስ ላይ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድን ካሸነፉ በኋላ ኔይማር \"ከዚህ በኋላ ከምንም በላይ የምፈልገው ከሜሲ ጋር በድጋሚ መጫወት ነው፤ ከእሱ ጋር በሜዳ ላይ ሆኜ እግር ኳስን ማጣጣም እፈልጋለሁ\" ብሎ ነበር። \"ከፈለገ እኔ በምጫወትበት ቦታ ሊጫወት ይችላል፤ ምንም ችግር አይኖረውም። እርግጠኛ ነኝ። እሱ ብቻ ፒኤስጂን ይቀላቀል እንጂ ሌላው አሳሳቢ አይደለም። ከእሱ ጋር በድጋሚ መጫወት ትልቁ ህልሜ ነው። በሚቀጥለው የውድድር ዓመት ይህ እንደሚሆን ደግሞ እርግጠኛ ነኝ\" ሲል አስተያቱን ሰጥቶም ነበር። ሌሎቹ የፒኤስጂ ተጫዋቾች ዲ ማሪያ እና ቬራቲ እንዲሁም የፒኤስጂ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሊአንድሮ ፓሬዴዝ ሊዮኔል ሜሲ ባርሴሎና መጫወት ካልፈለገ ቡድናቸውን እንዲቀላቀል እንደሚፈልጉ በግልጽ ተናግረዋል። ሜሲ ከዚህ ሁሉ ድራማ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን ባስተላለፈው መልዕክት ሰዎች በእሱ ጉዳይ ላይ እየሰጡ ባለው አስተያየት ደስተኛ እንዳልሆነና የቅርብ ወዳጆች የሚላቸው ጭምር ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ጫና በማሳደራቸው መገረሙን ገልጾ ነበር። ነገሮችን ይበልጥ ውስብስብ የሚያደርገው ደግሞ ኔይማር ወደ ባርሴሎና የመመለስ ሀሳቡን በመተው በፒኤስጂ ለመቆየት መወሰኑና ኪሊያን ምባፔም የመሄድ ሐሳቡን በመተው ከክለቡ ጋር ድርድር መጀመሩ ነው። እነዚህ የእግር ኳስ ክዋክብት በፒኤስጂ የሚቆዩ ከሆነ ሜሲም ሊቀላቀላቸው እንደሚችል ይገመታል። በሌላ በኩል ደግሞ ሜሲ ባርሴሎናን እንደሚለቅ ባስታወቀ ጊዜ መዳረሻው በቀድሞው የባርሴሎና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ ሊሆን እንደሚችል በስፋት ሲገለጽ ነበር። እንደውም በሐሳብ ደረጃ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሎም ነበር። የአሁኑ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከ2008 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 2012 ድረስ ለአራት ዓመታት ያህል ሜሲን አሰልጥኖታል። በአራት ዓመት ጊዜውም ሦስት የላሊጋና ሁለት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በአንድ ወቅትም \"እኔ በጣም እድለኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ቢያንስ የዓለማችንን ምርጡን ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲን አሰልጥኜዋለሁ\" በማለት ጋርዲዮላ ለሜሲ ያለውን አድናቆት ገልጿል። ይህ ወደጅነታቸውም አሁን እንደገና ሊያገናኛቸው ይችላል የሚለውን ግምት በበርካቶች ዘንድ አሳድሯል። ነገር ግን ጋርዲዮላ የማይታሰብ ነው ብሏል። \"እዚያው [ባርሴሎና] ይቆያል፤ የእኔ ፍላጎትም ይህ ነው\" በማለት። የባርሴሎናው የምንጊዜም ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ በመሆን የምድራችን ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን በባርሳ ቆይታው 10 የላሊጋና አራት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፏል። እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ በባርሳ የሚያቆየው ኮንትራትም አለው። የሜሲ ወደ ማንቸስተር ሲቲ የመምጣት ጉዳይ ደግሞ እንደ ኬቨን ደብራይነ ያሉ የክለቡ ኮከብ ተጫዋቾችን ምቾት የነሳ ሆኗል። ምክንያቱም ደብራይነ ከክለቡ ጋር የሚያቆየውን ኮንትራት ለመፈራረም እያመነታ ነው። ክለቡ ለተጫዋቹ ያቀረበው ገንዘብ ደብራይነ ከሚያስበውና ከሚፈልገው በእጅጉ ያነሰ ነው። አንዳንዶ ደግሞ ማንቸስተር ሲቲ ገንዘብ እየቆጠበ ያለው ምናልባት ሜሲ ከመጣ ለእሱ የሚሆን ክፍያ እንዲኖረው ይላሉ። ወጣም ወረደ ግን በመጪው መጋቢት ወር ባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ የሚያደርገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የክለቡን ውሳኔም ሆነ የሊዮኔል ሜሲን መዳረሻ ፍንጭ የሚሰጥ ይሆናል። ሊዮኔል ሜሲ 644ኛ ጎሉን ለክለቡ ባርሴሎና በማስቆጠር የፔሌን ክብረ ወሰን የሰበረው ታኅሣስ ወር ላይ ነበር። ሜሲ የከፍተኛውን ግብ ክብረ ወሰን በእጁ ለማስገባት የቻለው ቡድኑ ባርሴሎና ከሪያል ቫላዶሊድ ጋር በነበረው ግጥሚያ ከመረብ ባገናኘው ጎል ነው። በዚህም ሜሲ ለአንድ ክለብ ብዙ ጎሎች በማስቆጠር የብራዚላዊውን እግር ኳሰኛ ፔሌ ክብረ ወሰን ሰብሯል። የ33 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ባርሴሎና ሪያል ቫላዶሊድን ባሸነፈበት ጨዋታ ከክለብ አጋሩ ፔድሪ የተቀበላትን የቅንጦት ኳስ ወደ ጎል ቀይሮ ነው ክብረ ወሰኑን የጨበጠው። ብራዚላዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ፔሌ ለሳንቶስ ክለብ ከ1956 እስከ 1974 ተጫውቷል። ለ19 የውድድር ዘመኖች ለአገሩ ክለብ የተጫወተው ፔሌ 643 ጎሎች ከመረብ ማገናኘት ችሏል። በቀጣይ ምን እንጠብቅ? ሜሲ በባርሴሎና ቆይታው ከፒኤስጂ ጋር ባደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች አራት ጊዜ ኳስን ከመረብ ማገናኘት ችሏል። በአሁኑ ጊዜ መወሰን የቻለው ብቸኛው ነገር ደግሞ የዘንድሮው የውድድር ዓመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ባርሴሎናን አለመልቀቅ ነው። በዋነኛነት የሚጠብቀው ነገር ደግሞ መጋቢት ላይ የሚካሄደውን የክለቡ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነው። እንደሚያሸንፉ በስፋት እየተነገረላቸው የሚገኘው የቀድሞው ፕሬዝደንት ሁዋን ላፖርታ ሲሆኑ እኚሁ ሰው የሚያሸንፉ ከሆነ ሜሲ በባርሴሎና የመቆየቱ ነገር የተረጋገጠ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው የቅርብ ሰዎች ነን የሚሉ ተንታኞች። እኚህ ሰው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው የሚያሸንፉ ከሆነ ከዕቅዳቸው ውስጥ አራቱን ፈረንሳያውያን በመሸጥ እስከ 200 ሚሊየን ዩሮ መሰብሰብ የመጀመሪያው ነው። የሚሸጡት ተጫዋቾች አንትዋን ግሪዝማን፣ ኦስማን ዴምቤሌ፣ ክሌመንት ሎንግሌ እና ሳሙኤል ኡምቲቲ ናቸው። ከእነዚህ ተጫዋቾች ሽያጭ በሚገኘው ገንዘብ ደግሞ እንደ ዴቪድ አላባ፣ ኤሪካ ጋርሺያ እና ኤርሊንግ ሃላንድን የመሳሰሉ ክዋክብትን መሸመት ነው። አሁን ዋናው ጥያቄ ኮሮናቫይረስ እግር ኳስን ጨምሮ በርካታ እንቅስቃሴዎች ባሽመደመደበት ወቅት ይህን ያክል ገንዘብ (200 ሚሊየን ዩሮ) አውጥቶ ተጫዋቾችን የሚገዛው ማነው? የሚለው ነው። ሜሲ ወደ አሜሪካ የመሄድ ፍላጎትም እንዳለው አልደበቀም። ባለቤቱ አንቶኔላ ከቀድሞው የክለብ ጓደኛው ሴስክ ፋብሬጋስ ባለቤት ጋር ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት መስርታለች። ፋብሬጋስ እና ባለቤቱ ደግሞ ሜሲና ባለቤቱ ወደ አሜሪካ መጥተው የመጨረሻዎቹን የእግር ኳስ ዓመታት እዚያ እንዲያሳልፉ ይፈልጋሉ። በተደጋጋሚም ወደ አሜሪካ እንዲመጡ ለማሳመን ሲጥሩ ነበር። ከአውሮፓውያኑ 2019 ጀምሮ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድንም ሆነ አትሌቲኮ ማድሪድን እንዲሁም ሲቪያን አሸንፎ አያውቅም። ድል ለሚጠማው ሜሲ ደግሞ ይህ ትልቅ ቁጭት ነው። ባርሴሎና በቶሎ እነዚህን ክለቦች ማሸነፍ እንደሚችል ማሳየት ካልቻለ ሜሲ ምናልባትም እስከወዲያኛው ባርሴሎናን ለቅቆ ሊሄድ ይችላል።", "የዓለም ዋንጫ ለሜሲ ወይስ ለምባፔ? የእርስዎ ግምት ወዴት ያደላል? ቦታ፡ የባሕረ ሰላጤዋ ሃገር ካታር ቀንና ሰዓት፡ እሑድ ታኅሣሥ 09/2015 ዓ.ም. ተጋጣሚዎች፡ የሜሲ አርጀንቲና ከኪሊያን ምባፔ ፈረንሳይ ከ1400 ቀናት በላይ አስጠብቆን የመጣው የዓለም ዋንጫ እነሆ ነገ ሰንበት ፍፃሜውን ያገኛል፤ አርጀንቲና እና ፈረንሳይም ታሪክ ለመፃፍ ቋምጠዋል። ቀጣዩ የዓለም ዋንጫ 1270 ቀናት ይቀሩታል። አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ያስተናግዱታል። የዘንድሮውን የኳታር የዓለም ዋንጫን የኮመኮሙ “ይህን የመሰለ የዓለም ዋንጫ ተመልክተንም አናውቅ” እያሉ ነው። “ኳታር የዓለም ዋንጫን ታዘጋጃለች” ተብሎ ሲታወጅ የአገሪቱን ዜጎችን ጨምሮ የዓለም ሕዝብ ያልጠበቁት ስለነበረ መደነቅና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር። በርካቶች የዓለም ዋንጫ ወደ በረሃማዋ ዶሃ ማቅናቱ ተገቢ አይደለም ሲሉ አጉረመረሙ፣ ኳታር ለሰብዓዊ መብቶች ግድ የላትም ሲሉ ከሰሱ፣ ጨዋታው በወርሃ ታኅሣሥ ሊሆን አይገባም ሲሉም ተቃውሟቸውን አሰሙ። የጠላት ወሬ አልሰማም ያለችው ዶሃ የደመቀ የዓለም ዋንጫ ለማዘጋጀት ለአስር ዓመታት ደፋ ቀና ማለቷን ቀጠለች። ቀኑ ደርሶ የዓለም ሕዝብ ወደ ዶሃ ተመመ። የሚሊዮኖች ዐይን የቴሌቪዥን መስኮት ላይ ተተከለ። የኳታር የዓለም ዋንጫ ብዙዎችን አጀብ ያሰኙ ክስተቶች የተስተዋሉበት ነበር። የመጀመሪያዋ የዚህ ክስተት ተጠቂ ደግሞ የዋንጫ ተፋላሚዋ አርጀንቲና። አርጀንቲና ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ልትጫወት ቀጠሮ ያዘች። ሳዑዲዎች ቡድናቸውን ሊደግፉ ድንበር አቋርጠው ወደ ዶሃ ፈለሱ። ጉዟቸው መና አልቀረም። በርካቶች “እንዲህ ዓይነት እግር ኳሰኛ ዓይተንም አናውቅ” የሚሉለት ባለ ግራ እግሩ ተዓምረኛ ሜሲ የመጀመሪያዋን ጎል በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጠረ። የሳዑዲዎች ቀፎ ተነካ። እንደ ንብ ተመው የመጀመሪያዋን ጎል አስቆጠሩ። ደጋፊው አበደ። ሁለተኛ ደገሙ። ምድር ተናጋች። የአርጀንቲና ሽንፈት አስደንቆን ሳያበቃ ጃፓን ጀርመንን አርበድብዳ ጉድ አሰኘች። ደቡብ ኮሪያ ደግሞ ስፔንን አንገት አስደፍታ እንካችሁ ተዓምራት አለች። እግር ኳስ ሁሉን አስረሳ። የኳታር ነቃፊዎች አፍ ተዘጋ። ሁሉም ትኩረቱን ወደ ሃያ ሁለቱ ተጫዋቾች እና ወደ ወደ ኳሷ አዞረ። የኳታር የዓለም ዋንጫ ክስተት፤ የአህጉረ አፍሪካ ኩራት፤ የአረቡ ዓለም ትሩፋት፤ ሞሮኮ። ሞሮኮ፤ ስፔንን ከርክማ፣ ፖርቹጋልን አጋድማ፣ ለግማሽ ፍፃሜ በቅታ ፈረንሳይን ነብስ ውጭ ነብስ ግቢ ታሰኛታለች ብሎ የገመተ ካለ እጅ ያውጣ - ከሳሙዔል ኤቶ በቀር። ካለፈው የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ክሮሺያ እና ከወቅቱ የዓለም እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኖች ቁንጮ ቤልጂዬም ጋር የተመደበችው  ሞሮኮ ኃያላኑን ገነዳድሳ ነው ለዚህ የበቃችው። አሠልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከተረከቡ መንፈቅ እንኳ ባይደፍኑም የተከላካይ መስመሩ የሚያስፈራ ቡድን መሥራት ችለዋል። ሞሮኮ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ከክሮሺያ አቻ፤ በሁለተኛው ቤልጂየምን 2 ለምንም ረመረመች። በሦስተኛው ካናዳን 2 ለ 1 ረታች። በዙር 16 ስፔንን በፍፁም ቅጣት አሰናብታ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ቀጠሮ ያዘች። በርካቶች ሞሮኮ ሩጫሽ መልካም ነበር፤ ነገር ግን የሮናልዶን ቡድንማ አትረችም ብለው ቢያሟርቱም የአትላስ አናብስቱ ፖርቹጋልን አሸንፈው ወደ ግማሽ ፍፃሜው በማለፍ ከአፍሪካ እና ከአረቡ ዓለም ቡድኖች የመጀመሪያው ሆኑ። በሺዎች የሚቆጠሩ የሞሮኮ ደጋፊዎች ለቡድናቸው ከለላ ለመሆን ወደ ዶሃ በረሩ። አህጉረ አፍሪካ ተቁነጠነጠ፤ የአረቡ ዓለም የሚይዝ የሚጨብጠውን ሳያውቅ በጉጉት የጨዋታዋን ሰዓት ጠበቀ። ቢሆንም ሞሮኮ ለፍፃሜው ለማለፍ የነበራት ሕልም በኪሊያን ምባፔ ቡድን ከሰመ። በተጋጣሚ ቡድን ጎል ከተቆጠረባት ዘመናት ያየችው ሞሮኮ [ከካናዳ ጋር በነበረው ጨዋታ የተቆጠረው በራስ መረብ ላይ ነው] በፈረንሳይ 2 ለምንም ተረታች። እነሆ አንድ ምድብ ውስጥ ተደልድለው የነበሩት ሞሮኮ እና ክሮሺያ ዛሬ ቅዳሜ አመሻሹን የሦስተኛነት ክብር ለማግኘት ይፋለማሉ። ሁለቱ “አሳዛኝ ተሸናፊዎች” የብዙዎችን ግምት አክሽፈው ለዚህ በመብቃታቸው “ኩራት ሊሳማቸው ይገባል” የሚሉ ብዙዎች ናቸው። በበርካታ መገናኛ ብዙኃን የእሑዱን ፍልሚያ ሊዮኔል ሜሲ ከከሊያን ምባፔ የሚል የዳቦ ስም ሰጥተውታል። ለፈረንሳዩ ፒኤስጂ የሚጫወቱት ሁለቱ የአንድ ክለብ አጋሮች በዓለም ዋንጫው ባላንጣ ሆነው ተገናኝተዋል። የ23 ዓመቱ ፈረንሳዊ የእግር ኳስ ኮከብ ሁለተኛ የዓለም ዋንጫውን ሊያነሳ ተሰናድቷል። በ12 ዓመት የሚበልጠው የኳስ ፈርጥ ደግሞ ለመጀመሪያ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ለመጨበጥ ጓጉቷል። የዓለም ዋንጫን ለመጨረሻ ጊዜ በተከታታይ ያነሳችው ብራዚል ናት። ጊዜው ደግሞ በፈረንጆቹ 1958 እና 62። ፈረንሳይ በ2018 ክሮሺያን 4 ለ 2 በመርታት ዋንጫ ስታነሳ ጎል ካስቆጠሩ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ኪሊያን ምባፔ ነው። የወንዶች ዓለም ዋንጫን ሦስት ጊዜ ያነሳው ብቸኛው የዓለማችን ተጫዋች ብራዚላዊው ፔሌ ነው። ፔሌን ጨምሮ 21 ወንድ ተጫዋቾች ብቻ ናቸው የዓለም ዋንጫን ከአንድ ጊዜ በላይ የማንሳት ዕድል ያገኙት። ኪሊያን ምባፔ ገና በለጋ ዕድሜው ይህን ታሪክ ይቋደስ ይሆን? ወደ ሊዮኔል እንምጣ። ሜሲ ጫማ ወደ መስቀያ ዕድሜው እየተቃረበ ነው። በእግር ኳስ ዓለም ያሉ ዋንጫዎችን ሁሉ አጋብሷል - ከዓለም ዋንጫ በቀር። ሜሲ በፈረንጆቹ 2014 ለፍፃሜ ደርሶ ዋንጫውን አጨብጭቦ ለጀርመን አስረክቦ መመለሱ ይታወሳል። ሊዮኔል ሜሲ የእሑዱ ግጥሚያ የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ ጨዋታው እንደሆነ ተናግሯል። አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ጠቢብ እሑድ ምሽት የዓለም ዋንጫን ካነሳ በእግር ኳስ ደጋፊዎች ዘንድ የምንም ጊዜ ምርጡ የተሰኘውን የክብር ስም ይቆናጠጣል። ለዚህ ነው የእሑዱ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አጓጊነቱ፤ ልብ አንጠልጣይነቱ ከፍ ያለው። የኳታር የዓለም ዋንጫ አንድ ነገር አስተምሮናል። ማንም ከማንም ይጫወት ዘንድሮ እከሌ ይረታል ብሎ መገመት ከባድ ነው። ቢሆንም እርስዎ ከመገመት ወደኋላ እንዳይሉ እናበረታታለን። ዋንጫውን ማን ያነሳል? ሜሴ ወይስ ምባፔ? የእሑድ ሰው ይበለን።", "በዶሃ የሴቶች ማራቶን 28 ሯጮች አቋርጠው ወጡ ትናንት እኩለ ለሊት በኳታር፣ ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካሄደው የማራቶን ሩጫ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ማቋረጣቸው ተሰማ። ሩጫውን በበላይነት ኬኒያዊቷ ሩት ቼፔንጌቲች ያሸነፈች ሲሆን፤ ከ68 ተወዳዳሪዎች 28ቱ በሙቀቱ ከባድነት ምክንያት አቋርጠው መውጣታቸው ተዘግቧል። እኩለ ለሊት ላይ የተደረገውን ይህ የሴቶች የማራቶን ውድድር ካቋረጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ አንዷ ነች። የውድድሩ አዘጋጆች ከዋናው ውድድር ቀድመው የማራቶን ውድድሩ እንዲካሄድ ያደረጉት የአየር ጠባዩ ለማራቶን ምቹ ላይሆን ይችላል በሚል እንደሆነ ተነግሯል። • በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ • ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ስለአባይ አጠቃቀም ምላሽ ሰጡ • ፌስቡክ 'የላይክ' ቁጥርን ማሳየት ሊያቆም ነው የሴቶች ማራቶን ሲካሄድ፤ የሙቀት መጠኑ 32 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ወበቁ ደግሞ ከ70 በመቶ በላይ ነበር ተብሏል። የኢትዮጵያ ማራቶን አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ ሮባ፤ የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊዋ ሩቲ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተወዳዳሪዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል። \"በአገራችን ማራቶንን በዚህ የአየር ጠባይ መሮጥ የሚታሰብ አይደለም\" ካሉ በኋላ \"ምን ያህሎቹ እንደሚጨርሱ ለማየት ጓጉቻለሁ\" ብለዋል። የ23 ዓመቷ ቼፔንጌቲች ሩጫውን በ2 ሰዓት ከ32 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ በማጠናቀቅ ወርቅ ስታገኝ፤ የባህሬን ዜግነት ያላት ሯጭ ሁለተኛ፣ ናሚቢያዊቷ ሯጭ ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል። ቼፔንጌቲች፤ \"በእንዲህ አይነት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አሸንፋለሁ ብዬ አልጠበቅኩም\" በማለት ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ተናግራለች። የብሪታኒያ ፈጣን የማራቶን ሯጭ ቻርሎቴ ፑርዱኤ እና ሌሎች ታዋቂ ሯጮችም አቋርጠው ከወጡት መካከል ናቸው።", "ኢቢሲ ያልተፈቀዱለትን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች በማስተላለፉ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቀው ፊፋ አስታወቀ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በኳታር ዶሃ እየተካሄደ የሚገኛውን የዓለም ዋንጫ በቀጥታ እንዲያስተላለፍ ከተፈቀዱለት ጨዋታዎች ውጪ በመቅረቡ ቅጣት እንደሚጠብቀው ፊፋ ለቢቢሲ ገለጸ። ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢቢሲ ሁለት ሳምንት የሆነውን በኳታር እየተካሄደ የሚገኘውን የዓለም ዋንጫ ውድድር ሁሉንም ጨዋታዎች ለተመልካቾቹ እንደሚያቀርብ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል። ነገር ግን ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል ፊፋ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደገለጹት የቴሌቪዥን ጣቢያው ለተመልካቾቹ እንዲያቀርብ የተፈቀደለት የተወሰኑ ጨዋታዎችን ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጪ ውድድሮችን አስተላለፏል ብሏል። ይህም ኢቢሲ እንዲያስተላለፍ መብት ከተሰጠው ጨዋታዎች ውጪ ነጻ በሆነ ስርጭት ማስተላለፉ በኢቲቪ በኩል ለተመልካች በማቅረቡ ከፊፋ ጋር የገባውን ውል በግለጽ የሚጥስ ነው ሲል ቅሬታውን ገልጿል። በዚህም ሳቢያ የዓለም ዋንጫን ለተመልካቹ እንዲያቀርብ ፊፋ ከኢቢሲ ጋር የገባው ስምምነት መቋረጡን ገልጾ፣ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ “ጠንካራ” ያለውን እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ነገር ግን ከዚህ ጋር ተያይዞ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በኢቢሲ ላይ እወስዳለው ስላለው እርምጃ ምንነት ከመግለጽ ተቆጥቧል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ የበላይ አካል ጋር የገባው ውል በመቋረጡ ተቋሙ በኳታር እየተካሄዱ ያሉትን ቀሪ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ማስተላለፍ አልተፈቀደለትም። ፊፋ ይህንን ቢልም ኢቢሲ የኳታር ዓለም ዋንጫ አንዳንድ ጨዋታዎችን እያስተላለፈ እንደሚገኝ ቢቢሲ ለመረዳት ችሏል። ፊፋ ለቢቢሲ እንደገለጸው የዓለም እግር ኳስ ውድድርን ለማስተላለፍ ከተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር ከስምምነት ደርሶ ፈቃድ የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ አይቻልም። ስለዚህም የፊፋ ፈቃድ ሳይኖር “በየትኛውም አይነት የሥርጭት ዘዴ፣ በመስመር ቴሌቪዥን ወይም በዲጂታል መድረኮች አማካይነት የሚደረጉ የሥርጭት ስርቆቶችን” አጥብቆ እንደሚከታተል እና እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል። ይህንንም ለመከላከል ፊፋ ከፍተኛ ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግ በመላው ዓለም ከትትል ከማድረጉ በተጨማሪ ከብሮድካስተሮች፣ ከዲጂታል ሚዲያ መድረኮች እና ከማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ጋር በጋራ ይሰራል። በተጨማሪም የሥርጭት የቴክኒክ አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም የብሮድካስት ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት በመተባበር “በውድድሮች ሥርጭት ላይ የሚፈጸሙ ማንኛውንም አይነት የተዘረፋ ስርጭቶችን ለመለየት እና ለማቆም ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል” በማለት የፊፋ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናገረዋል። ከኢቢኢ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር እንዳለው “በቴሊቪዥንም ይሁን በሌሎች ዲጂታል አማራጮች የሚደረጉ “ስርቆቶችን” በቸልታ አልመለከትም” ያለ ሲሆን፣ ለዚህም ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ክትትል እና እርምጃ ይወስዳል ብሏል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፊፋ ስለሰጠው ማስጠንቀቂያም ሆነ ቅጣቱን አስመልክቶ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም። በባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር እየተካሄደ ያለው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን በዓለም ዙሪያ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተሉት ነው። አስካሁን ባለው ግምት መሠረት የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ በተለያዩ የሥርጫት መንገዶች አመካይነት አስከ አምስት ቢሊዮን የሚደርስ ሕዝብ እንደሚመለከተው ተነግሯል።", "ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ለብሔራዊ ቡድኑ የማይጠሩት ለምንድን ነው? ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የተመለሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ ማለፍ ባለመቻሉ በጊዜ ወደ አገሩ ተመልሷል። በወጣት ተጫዋቾች የተዋቀረው የዋሊያዎቹ ስብስብ ሁለት ከኢትዮጵያ ውጪ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ቢያካትትም ሁለቱም ተጫዋቾች ይህ ነው የሚባል ሚና አልነበራቸው። ለግብፁ ክለብ ኤል ጉናን የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ በጉዳት ምክንያት፤ ለአልጄሪያው ጄኤስ ካቢሌ የሚጫወተው ሙጂብ ቃሲም ደግሞ የአሠልጣኙ የመጀመሪያ ምርጫ ባለመሆኑ ሜዳ ላይ አልታዩም። በአፍሪካ ዋንጫ ከተሳተፉ 24 ቡድኖች መካከል አንድም ከአፍሪካ ውጪ የሚጫወት እግር ኳሰኛ ያላካተተችው ኢትዮጵያ ብቻ ነበረች። ለምሳሌ ወደ ዙር 16 ተሻጋግራ ከካሜሩን ጋር እህል አስጨራሽ ፍልሚያ አድርጋ የወደቀችው ኮሞሮስ የመጀመሪያ ምርጫ የሆኑ 11 ተጫዋቾች በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ናቸው። በሌላ በኩል ከአልጄሪያና ኮትዲቯር ጋር ተደልድላ ከምድብ ከማለፍ አልፋ ማሊን በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜ የተሸጋገረችው ኢኳቶሪያል ጊኒ ስፔንና ጣልያን ባሉ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲቪዚዮን የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ነው የያዘችው። በሩብ ፍፃሜ ከካሜሩን ጋር የተፋለመችው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያዋ የሆነውና በቀድሞው የዋሊያዎቹ አሠልጣኝ ቶም ሴንትፊት የምትመራው ጋምቢያም እንዲሁ ከአገር ውጪ በመጡ ተጫዋቾች የታጀበች ናት። ለመሆኑ ዋሊያዎቹ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋቾችን ማካተት ለምን አልቻሉም? በአውሮፓ የሚጫወት ተጫዋች ስለሌለን? ወይስ ሌላ? 'የፓስፖርት ጉዳይ' ከምድቡ አንድ ነጥብ ይዞ ከአህጉሪቱ ትልቁ ውድድር የተሰናበተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ \"ተሳትፏችን መልካም ነበር\" ብለዋል። በሌላ በኩል የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ ባሕሩ ጥላሁን ደግሞ የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣታችን \"የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን\" ሲሉ ተደምጠዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸውን ዋና ፀሐፊው እንደዋነኛ ምክንያት የጠቀሱት የፓስፖርት ጉዳይ ነው። \"ኢትዮጵያ ጥምር ዜግነት ስለማትፈቅድ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በቡድኑ ውስጥ ማከተት አልቻንም\" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም ለብሔራዊ ቡድኑ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቡና የተጫወተው ትውልደ ጀርመናዊው ዴቪድ በሻህ ግን ይህ ምክንያት ሊሆን አይገባም ይላል። \"እርግጥ ነው ከኔም ልምድ በመነሳት የሌላ አገር ዜግነት ካለህ ለኢትዮጵያ መጫወት አትችልም። አሊያም ደግሞ የያዝከውን ዜግነት አሳልፈህ መስጠት አለብህ።\" ዴቪድ ከአፍሪካ ዋንጫ በፊት ለኢትዮጵያ ለመጫወት ፈቃደኛ የሆኑ መቀመጫቸው አውሮፓ የሆነ ዘጠኝ ተጫዋቾችን ስም ዝርዝር ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ለአሠልጣኙ አቅርቦ ነበር። \"ጊዜው አጭር ነበር። እኔ ተጫዋቾቹን መመልመል የጀመርኩት መስከረም ወር መጨረሻ ነበረ። ነገር ግን ጥሩ አቋም ላይ ያሉ ወጣት ተጫዋቾችን ለአሠልጣኙ ባቀርብም አሠልጣኙ በተጫዋቾቹ ብቃት ደስተኛ እንዳልሆነ ነበር የነገረኝ።\" ዴቪድ ተጫዋቾቹን ለአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት የነበረው ጊዜ እጅግ አጭር እንደነበር ቢስማማም አንዳንዶቹ ተጫዋቾች ለትላልቅ ቡድኖች የሚጫወቱና ጥሩ አቋም ያላቸው ናቸው ይላል። \"በተለይ ወደፊት በመገስገስ የሚያጠቁ ተጫዋቾችን ነበር ለብሔራዊ ቡድኑ የመለመልኩት። አንድ ኖርዌይ የሚጫወት ወጣት ግብ ጠባቂም መርጬ ነበር። ቢያንስ አሠልጣኙ ተጫዋቾቹን ጠርቶ በልምምድ ሜዳ ብቃታቸውን ቢፈትሽ መልካም ነበር። በተሰጠኝ ምላሽ ደስተኛ አይደለሁም\" ይላል። ትውልደ ጀርመናዊው ዴቪድ \"ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ተሰጥዖ አውቃለሁ። እኔም ለስድስት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ተጫውቻለሁ\" ይላል። \"ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ያላቸውን ብቃት አሟጠው እንደሚጫወቱ አውቃለሁ። ነገር ግን ያለን መሠረተ ልማት ጠንካራ አይደለም። እነ ጋምቢያ፣ ኬፕ ቬርድ፣ ሴራ ሊዬን እንዲሁም ሌሎች ብሔራዊ ቡድኖችን ብትመለከት ውጭ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን አካተዋል\" በማለት ያሳዩትን ብቃት በዋቢነት ጠቅሷል። ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አመለካከት \"አውሮፓ የሚገኙ ተጫዋቾች እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አሊያም ላሊጋ ወይም ቡንደስሊጋ ካልተጫወቱ የተጫዋቾቹን ብቃት የሚፈትሹበት መንገድ የላቸውም\" ይላል። \"ለምሳሌ ከመለመልኳቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ በጀርመን ሦስተኛው ሊግ የሚጫወት ነው። አንድም የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ቡድን ይህንን ሊግ እንደማይቋቋመው አውቃለሁ።\" አሠልጣኙ \"ተጫዋቾቹን እዚህ አምጥቼ አቋማቸውን ብፈትሽ ችግር አልነበረውም ነገር ግን የፖስፖርት ጉዳይ ያግደኛል\" የሚለው ዴቪድ፣ የፓስፖርት ጉዳይ አፋጣኝ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንደሚሻ ይናገራል። 'ጉዳዩ የፓስፖርት አይደለም' በፈረንጆቹ ከ2011 ጀምሮ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾችን ለብሔራዊ ቡድኑ በመመልመል የሚታወቁት ፋርሃን ሞሐመድ ጉዳዩ የፓስፖርት አይደለም ይላሉ። \"እመነኝ ጉዳዩ የፓስፖርት አይደለም። እንደዚያ ከሆነ ዴቪድ በሻህ አውሮፓ ሄዶ ተጫዋቾችን እንዲመለምል ለምን ላኩት? የተጫዋቾቹን ስም ዝርዝር ይዞ ሲመጣ አሠልጣኙም የሰጡት ምላሽ ብቃታቸው ጥሩ አይደለም የሚል ነው።\" ፋርሃን ችግሩ ያለው አሠልጣኞች ጋር ነው ሲሉ ይሞግታሉ። \"ከአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ጊዜ ጀምሮ ተጫዋቾችን ለመመልመል ሞክሪያለሁ። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን አሠልጣኞች ፈቃደኛ አይደሉም። ማሪያኖ ባሬቶ ብቻ ነው ፈቃደኛነቱን ያሳየኝ። ፌዴሬሽኑ ተጫዋቾችን ከውጭ እንዲያመጣ ግፊት በማድረጉ በእሱ ጊዜ እነዩሱፍ ሳልህ፣ ዋሊ ዳታና አሚን አስካር መጥተው ነበር።\" በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስለትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በመፃፍ የሚታወቀው አዶናይ ኤርሚያስም ይህ ምክንያት ሊሆን አይገባም ሲል ይላል። \"እኔ ባገኘሁት መረጃ አውሮፓ ውስጥ ብቻ 35 ገደማ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች አሉ\" በማለት ከመካከላቸው የተወሰኑትን ይጠቅሳል። በዚህም ኖርዌይ ዳንኤል፣ ከጀርመን የሊቨርፑሉ መልካሙ ወንድም መለሰ ፍራውንዶርፍን እንዲሁም ለአትላንታ የሚጫወተው አንዋር ሜዴሮን በማንሳት፣ በእስራኤል የመጀመሪያው ዲቪዚዮንም እንዲሁ ሦስት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች አሉ ይላል። አዶናይ የጠቀሳቸውን ተጫዋቾች ጨምሮ ስዊትዘርላንድ የሚጫወተው ማረን ኃይለ ሥላሴንና አሚን አስካር ለዋሊያዎቹ አስፈላጊ ናቸው ይላል። \"ዩሱፍ ሳላህ፣ ዋሊ ዳታ እና አሚን አስካር ለኢትዮጵያ እንዲጫወቱ የተጠሩት በአሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ጊዜ ይመስለኛል። ኢትዮጵያውያን አሠልጣኞች ከሚያውቁት ተጫዋች ጋር መሥራት እንጂ ከውጭ የሚመጡ ተጫዋቾችን ማከተት ይፈልጋሉ ብዬ አላስብም።\" ዴቪድ በሻህም በዚህ ሐሳብ ይስማማል። በተለይ ባለፉት ጊዜያት አሠልጣኞች ብዙም ፍላጎት እንደሌላቸው ይናገራል። አዶናይ የፓስፖርት ምክንያት ውሃ የሚያነሳ አይደለም ይላል። \"ፊፋ 2014 ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት አንድ ተጫዋች በእናቱና በአባቱ አሊያም በአያቶቹ ኢትዮጵያዊ ከሆነና ላደገበት አገር ዋና ብሔራዊ ቡድን ካልተጫወተ ለኢትዮጵያ የመጫወት መብት አለው። አሁን አሁን ፌዴሬሽኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እየሠራ ያለ ይመስለኛል።\" 'የማጣሪያ ጊዜ ለምን አይመጡም?' ዴቪድና አዶናይ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ አሊያም ለሌላ ውድድር ስታልፍ ብቻ ነው የሚመጡት በሚለው ሐሳብ አይስማሙም። \"የውጭ ተጫዋቾች ምልመላን የጀመርኩት መስከረም ላይ ነው። ከዚያ በፊት ማን ጠርቷቸው ያውቃል? ማን ኑና ተሳተፉ ብሏቸው ያውቃል? ማንም። ነገር ግን ተጫዋቾቹ ጥሪ ብቻ ነው የሚጠብቁት። አሁን ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፍን በኋላ የምልመላ ሥራውን ስለሰጡኝና ጊዜው ስለተገጣጠመ እንዲህ ማለት አይቻልም\" ይላል ዴቪድ። \"ተጫዋቾቹ በማንኛውም ጊዜ ለኢትዮጵያ ለመጫወት ዝግጁ ናቸው። ነገር ግን ማንም ጠርቷቸው አያውቁም። ካልተጠሩ እንዴት ነው የሚመጡት?\" አዶናይ በበኩሉ ይህ ምክንያት የተጫዋቾችን ሞራል የሚነካ ነው ሲል ይከራከራል። ለዚህ ነው አንዳንድ ተጫዋቾች ለኢትዮጵያ የመጫወት ፍላጎታቸው እየቀነሰ የመጣው ይላል። ፋርሃን 'ለዋንጫ ስናልፍ ብቻ ነው የሚመጡት' የሚለው ምክንያት ትርጉም አልባ ነው ይላሉ። \"የማጣሪያ ጨዋታ በሚደረግበት ወቅት ለአሠልጣኙ ሳይቀር እነዚህን ተጫዋቾች ተመልከቷቸው ብዬ መልዕክት ልኬ ነበር። ነገር ግን ከምንም ምላሽ አላገኘሁም።\" \"ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾችን መጥራት ቀላል ነው። በግሌ ማኅበራዊ ሚድያን ጨምሮ በተለያየ መንገድ ያገኘኋቸውን ተጫዋቾች እንኳ ሊቀበሉ አልፈለጉም። አንዳንዴ ለአውሮፕላን ትኬት መክፈል አንችልም ይሉኛል። ተጫዋቾቹ ራሳቸው የትኬት ወጪያቸውን ይሸፍኑ ያሉኝ ጊዜም ነበር።\" 'የስፖርት ቪዛ' ዴቪድ ይህ የጥምር ዜግነት ጉዳይ ለሌሎችም አገራት ደንቃራ የነበረ ጉዳይ ነው ይላል። ነገር ግን አብኞቹ አገራት ይህንን ችግር እንደቀረፉ ይጠቅሳል። ዴቪድ እንደምሳሌ ሱሪናም የተሰኘችውን ደቡብ አሜሪካዊት አገር ይጠቅሳል። \"99 በመቶ የሚሆኑት የኔዘርላንድስ ጥቁር ተጫዋቾች ከዚያ ነው የመጡት። ቫን ዳይክ ብትል፣ ክሎይቨርት፣ ሲዶርፍና ሌሎችም ከሱሪናም ናቸው። ነገር ግን ከሁለት ወይም ሦስት ዓመታት በፊት ይህን ችግር ለመቅረፍ 'ስፖርት ፓስ' አዘጋጁ። ይህ ፓስፖርት ለስፖርተኖች ብቻ የሚሰጥ ነው። \"ለምሳሌ ለቼልሲ የተጫወተው ሃስልባንክ ወንድም ልጅ በዚህ ፓስፖርት ምክንያት ሱሪናምን የወከለ የመጀመሪያው ተጫዋች ነው። ሌሎች ተጫዋቾችም ይህን ተከትለው መጥተው ሱሪናም ባለፈው ዓመት በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኮንካፍ ጎልድ ዋንጫ ማለፍ ችላለች።\" ዴቪድ ለዚህ ነው ይህ ጉዳይ ከታሰበበት መፍትሔ ማበጀት ቀላል ነው የምለው ይላል። \"ለምሳሌ እኔ ለብሔራዊ ቡድኑ በተጫወትኩበት ወቅት ፓስፖርት ያስፈልጋችኋል ብለው አምጥተው ሰጡን። በወቅቱ በኦፊሴላዊ መንገድ ላይሆን ይችላል ያደረጉት። አሁን ግን ይህ ችግር ፖለቲካዊ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ነው የምለው።\" ይህ ሁኔታ ጊዜ እንደሚወስድ የሚገነዘበው ዴቪድ ሂደቱን ማፋጠን ይገባል ይላል። \"ኢትዮጵያ ይህን መመሪያ የምታራምድ የመጨረሻ አገር ሳትሆን አትቀርም። እጄ ላይ ለምሳሌ 150 ተጫዋቾች አሉኝ። አብዛኞቹ በአካል ባላውቃቸውም በጊዜ ሂደት ማወቄና መመልመሌ አይቀርም።\" ዴቪድ በሻህ የውጭ ተጫዋቾች ይምጡ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጫወቱት ይቀመጡ ማለት አይደለም ሲል ያሰምራል። \"እኔ ዓላማዬ ብሔራዊ ቡድኑን በትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሙላት አይደለም። በፍፁም። እኔ ማየት የምሻው ብሔራዊ ቡድኑ የድንቅ ተጫዋቾች ስብስብ ሆኖ ውጤት እንዲያመጣ ነው።\" ዴቪድ አክሎ ምንም እንኳ ኃላፊነቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቢሰጠውም ወጪውን ራሱ እየሸፈነ ተጫዋቾችን እንደሚመለምልና ከፌዴሬሽኑ ጋር በዚህ ጉዳይ ለመነጋገር እንዳቀደም ይናገራል። \"እኔ ተጫዋቾችን መመልመል እቀጥላለሁ። ትኩረቴን ወጣቶች ላይ ነው የማደርገው። ያሉበት ድረስ ሄጄ እገመግማለሁ። ማን ያውቃል የወቅቱ አሠልጣኝ ባይጠራቸው ቀጣዩ አሠልጣኝ ይጠራቸው ይሆናል. . . \"", "በኢትዮጵያ የበላይነት የተጠናቀቀው 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመጋቢት 9 እስከ 11/2014 ዓ.ም. በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ በተካሄደው 18ኛው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ የበላይነትን ይዛ ያጠናቀቀችው በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብር እና በሁለት ነሐስ በድምሩ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ነው። በውድድሩ ከ2008 እስከ 2018 በነበሩት ተከታታይ ውድድሮች ሰንጠረዥ በአንደኝነት ስትመራው የነበረችው አሜሪካ ስትሆን፣ ዘንድሮ ይህንን የበላይነት በኢትዮጵያ ተነጥቃለች። በውድድሩ ታሪክም በሰንጠረዡ አናት በመቀመጥ ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የአፍሪካ አገር ነች። በዘንድሮ የቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮና አሜሪካ፣ ቤልጂየም፣ ሲዊትዘርላንድ እና ስዊዲን ኢትዮጵያን ተከትለው በውድድሩ ሰንጠረዥ ከሁለት እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኢትዮጵያ የዘወትር ተፎካካሪ የሆነችው ኬንያ 1 ብር እና 1 ነሐስ በማግኘት በረጃ ሰንጠረዡ ውስጥ መካተት ከቻሉት 29 አገራት በ22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሌላኛው አፍሪካዊት አገር ኡጋንዳ ደግሞ አንድ ነሐስ ማግኘት ችላለች። 680 አትሌቶች [308ቱ ሴቶች] የተወደደሩበት የዘንድሮ 18ኛው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 136 አገራት ተሳትፈውበታል። ከተለያዩ አገራት የተወጣጡ ስድተኞችን የያዘው ቡድንም የውድድሩ ተሳታፊ ነበር። ኢትዮጵያ ለውድድሩ ከ800 እስከ 3 ሺህ ሜትር ሩጫ ላይ የሚሳተፉ 5 ወንድ እና 9 ሴት አትሌቶችን የላከች ሲሆን በወንዶች 2 ወርቅ እና 1 ብር ስታገኝ የተቀረው 6 ሜዳሊያ በሴቶች የተመዘገበ ነው። ጉዳፍ ጸጋዬ እና ሳሙኤል ተፈራ በ1 ሺህ 500 ሜትር ለሀገራቸው ወርቅ ያመጡ ሲሆን፤ ሰለሞን ባረጋ እና ለምለም ሃይሉ ደግሞ በ3 ሺህ ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያውን አጥልቀዋል። ሳሙኤል ተፈራ በርቀቱ የውድድሩን ክበረወሰን አሻሽሏል። ሰለሞን ባረጋ 1ኛ በወጣበት 3ሺህ ሜትር ለሜቻ ግርማ 2ኛ መሆን የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። የተቀረውን የብር ሜዳሊያ ደግሞ ፍሬወይኒ ሃይሉ በ800 ሜትር እና አክሱማይት እምባዬ በ1 ሺህ 500 ሜትር ያስመዘገቡበት ነው። ሒሩት መሸሻ በ1 ሺህ አምስት መቶ ሜትር እና እጅግአየሁ ታዬ 3 ሺህ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል። በሶስት ሺህ ሜትር የሴቶች አትሌቲክስ ውድድር ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለው ደረጃ ኢትዮጵያውያኑ የተቆጠጠሩት ሲሆን አንደኛ የወጣችው ለምለም ሃይሉ በርቀቱ የውድድሩን ሪከርድ ሰብራለች። ኢትዮጵያ በ18ኛው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳታፊዎች ብዛት: 14 [5 ወንድ እና 9 ሴት] የተወዳደሩባቸው ርቀቶች: 800፣ 1 ሺህ 500 እና 3 ሺህ ሜትር የሜዳሊያ ብዛት: 9 [4 ወርቅ፣ 3 ብርና 2 ነሃስ] የሜዳሊያ ብዛት በጾታ: 6 በሴቶች [2 ወርቅ፣ 2 ብር እና 2 ነሐስ] 3 በወንዶች [2 ወርቅ፣ 1 ብር] የሜዳሊያ ብዛት በርቀት: 2 ወርቅ በ3 ሺህ ሜትር፣ 2 ወርቅ በ1 ሺህ 500 ሜትር፣ 1 ብር በ800 ሜትር፣ 1 ብር በ1 ሺህ 500 እና 1 ብር በ3000 ሜትር እንዲሁም 1 ነሃስ፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር እና 1 ነሃስ በ3000 ሜትር ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች ወርቅ ብር ነሐስ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደ አውሮፓውያኑ በ1985 የቤት ውስጥ ጨዋታዎች በሚል በፈረንሳይ ፓሪስ የተጀመረ ሲሆን በ1987 የመጀመሪያው ስያሜ ተቀይሮ አሁን ያለውን መጠሪያ ይዟል። ውድድሩ በየሁለት ዓመቱ ይካሄዳል።", "የሳዑዲው ኩባንያ የእንግሊዙ ኒውካስትል እግር ኳስ ክለብን ገዛ የሳዑዲ አራቢያ የኩባንያዎች ጥምረት የእንግሊዙን ኒውካስትል ዩናይትድ በ305 ሚሊዮን ፓውንድ መግዛቱ ተገለጸ። ፕሪሚዬር ሊጉ ኒውካስትል ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ ተላለፎ እንዲሰጥ የወሰነው የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በጉዳዩ ጣልቃ እንደማይገባ ከስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ ነው። ፐብሊክ ኢንቨስትመንት ፈንድ የተሰኘው ጥምረት 80 በመቶ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከመንግሥት ጋር ሳይነካካ በራሱ ነው የሚንቀሳቀሰው ተብሏል። ነገር ግን የሳዑዲ አራቢያው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን የፐብሊክ ኢንቨስትመንት ፈንድ አለቃ ናቸው። ኒውካስትል የዚህ ጥምረት ንብረት የሆነው የግዢው ስምምነት በፕሪሚዬር ሊጉ ባለንብረቶችና ዳይሬክተሮች ምርመራ ከተደረገ በኋላ ነው። ላለፉት 14 ዓመታት ኒውካስትል ዩናይትድን የግል ንብረታቸው አድርገው ሲቆጣጠሩ የነበሩት ማይክ አሽሊ ከቡድኑ ጋር ተለያይተዋል። ከዜናው በኋላ የቡድኑ ደጋፊዎች በሴይንት ጄምስ ፓርክ ስታድዬም ዙሪያ ደስታቸውን ሲገልፁ ተስተውለዋል። ፐብሊክ ኢንቨስትመንት ፈንድ 250 ቢሊዮን ፓውንድ የሚገመት ሃብት ያለው ሲሆን ኒውካስትልም ከዓለማችን ውድ ክለቦች አንዱ መሆን ችሏል። ጥምረቱን አናግረው ግዢውን እውን ያደረጉት የፋይናንስ ባለሙያው አማንዳ ስታቭሊ አዲሶቹ የክለቡ ባለቤቶች የረዥም ጊዜ ዕቅድ ያላቸው ሲሆን ኒውካስትልን የዋንጫ ባለቤት ለማድረግ አልመዋል ይላሉ። ኒውካስትል ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫ ያነሳው በፈረንጆቹ 1995 በተካሄደው የኤፍ ኤ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ነበር። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ባወጣው መግለጫ ፈንዱ ኒውካስትልን ለመግዛት አጋጥሞት የነበረውን አነጋጋሪ ጉዳይ ፈቷል ብሏል። አነጋጋሪ የነበረው ጉዳይ ክለቡ ከተሸጠ በኋላ ባለቤትነቱ የማን ይሆናል የሚለው ሲሆን አሁን በተደረሰው ስምምነት መሠረት ፈንዱ ኒውካስትልን በተመለከተ ከሳዑዲ መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ አይኖረውም ይላል የፕሪሚዬር ሊጉ መግለጫ። የኒውካስትል ደጋፊዎች \"እኛ የምንሻው ክለባችን እንዲያሸንፍ ሳይሆን ቢያንስ እንዲሞክር ነው\" የሚል መፈክር አንግበው ስታድየማቸው አካባቢ ታይተዋል። ኒውካስትል በማይክ አሽሊ ዘመን አንድ ጊዜ ብቻ ነው ለአህጉር አቀፍ ውድድር ማለፍ የቻለው። ክለቡና ፈንዱ ባለፈው ዓመት ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ፕሪሚዬር ሊጉ ክለቡን ማን ነው የሚገዛው በሚል ጉዳይ ስምምነት ላይ መድረስ ያስፈልጋል በማለቱ ምክንያት ተቋርጦ ነበር። የቢቢሲ ስፖርት ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት የፕሪሚዬር ሊጉ አስተዳዳሪዎችና ጥምረቱ ዜናው ይፋ ከሆነበር ዕለተ ረቡዕ አስቀድመው ከስምምነት ደርሰው ነበር። የሳዑዲ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደርሳል የሚሉ ወቀሳዎች በተደጋጋሚ ስለሚበሱበት ነው ፕሪሚዬር ሊጉ መንግሥት በስምምነቱ ጣልቃ እንዲገባ ያልፈለገው። ምዕራባዊያን የስለላ ድርጅቶች የሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን ጋዜጠኛ ጃምል ኻሾግጂ እንዲገደል አዘዋል ሲሉ ይወቅሳሉ። ልዑሉ ደግሞ እጄ የለበትም ይላሉ። አንዳንድ ለሰብዓዊ መብት ክብር ቆመናል የሚሉ ድርጅቶች ኒውካስትል የሳዑዲ አራቢያ ኩባንያዎች ጥምረት ንብረት መሆኑን ተቃውመውታል። ከእነዚህ መካከል የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የዩናይት ኪንግደም ቅርንጫፍ አንዱ ነው። ኒውካስትል በያዝነው የውድድር ዘመን ሰባት ጨዋታዎችን አድርጎ አንድም ጨዋታ ሳያሸንፍ በሰንጠረዡ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አሠልጣኝ ስቲቭ ብሩስ ሊባረሩ ይችላሉ የሚሉ ዜናዎች በስፋት እየተሰራጩ ነው።", "የኢትዮጵያዊው የአምቡላንስ ሹፌር ትዝብት የኮሮናቫይረስ ሕሙማንና ሕክምና ላይ ታሪኩ አትረጋ እባላለሁ። የአምቡላንስ ሹፌር ነኝ። የአምቡላንስ ሹፌር ከሆንኩ አጭር ጊዜው ነው። ገና ሦስት ወራት። ለሹፌርነት ግን አዲስ አይደለሁም። በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ሹፌር ሆኜ አገልግያለሁ። ለከተማው አዲስ አምቡላንስ ተሰጠ። አዲስ ሥራዬን በአዲስ መኪና ጀመረኩኝ። መጀመሪያ ወደ ሃገር የሚገቡ ሰዎችን ወደ ኳራንቲን ማዕከላት ማመላለስ ነበር ሥራዬ። ኢትዮጵያዊያኑ በተለያየ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ ይገባሉ። አድራሻቸው እና ሙቀታቸው ተለክቶ ወደ ለይቶ ማቆያ ይገባሉ። ኮኪት፣ ገንደ ውሃ ወይም ወደ ሌሎች የለይቶ ማቆያ ማዕከላት። እነዚህ ተጠርጣሪዎች ናቸው። አምቡላንስ ቢሆንም የማሽከረክረው አንድ ላይ የመጡትን እስከ ስድስት ሰባት ሰው ነው የምጭነው። ወደ ለይቶ ማቆያ የምወስዳቸው በተለያየ ቡድን በመክፈል ነው። ከተለያየ ቦታ የመጡትን ለየብቻ እንለያቸዋለን። ከበረሃ የመጡትን ለብቻ። ከካርቱም የመጡት ለብቻ. . . ንክኪ ይኖራል በሚል የተደረገ ነው። ለሁለት ሳምንት በለይቶ ማቆያ ከቆዩ በኋላ ናሙና ይወሰድላቸውና ይመረመራሉ። • «የሕዳሴው ግድብ ለግብፅና ሱዳንም ይጠቅማል» ጥቁር አሜሪካውያን ፖለቲከኞች • ኮቪድ-19 ያስተጓጎለው የኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና • \"ልባችንም ቤታችንም ጨልሟል\" የጀነራል ሰዓረ እና ሜ/ጀነራል ገዛኢ ቤተሰቦች ከዚያ በኋላ ነው ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ወደ ህክምና ማዕከል ማመላለስ የጀመርኩት። ብዙ ጊዜ ኮሮና እንዳለባቸው የተረጋገጠባቸውን ሰዎች አመላልሻለሁ። በቁጥር ብዙ ነው። ባህር ዳር 2 ጊዜ ወስጃለሁ። ጎንደር ደግሞ ወደ 12 ወይም 13 ጊዜ ወስጃለሁ። ከሳምንታት በፊት ዞኑ የተቀበላቸውን አዳዲስ አምቡላንሶች በመጨመር 4 ወይም 5 አምቡላንስ ተመድቦ ነበር ይዘን የምንሄደው። ከመተማ ጎንደር 190 ኪሜ ይርቃል። ከጎንደር ባህር ዳር ደግሞ 180 ኪሜ ነው። ስለዚህ ከመተማ ባህር ዳር 370 ኪሜ ይርቃል ማለት ነው። ኮቪድ-19 ባለሙያዎች አንኳን ገና ተጠንቶ ያላለቀ የሚሉት ቫይረስ ነው። ህብረተሰቡም መጀመሪያ ላይ ወዲያው ይገላል የሚል እምነት ነበረው። በዚህ ወቅት ነው በአካባቢው ሁለት ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የታወቀው። ምልክት አልነበረባቸውም። አንዱ ሱዳን በረሃ የዕለት ሠራተኛ ሌላው ደግሞ የካርቱም ነዋሪ። እነዚህን ነው ከጤና ባለሙያ እና ከጸጥታ ሃይል ጋር በመሆን ወደ ጤና ተቋማት መጀመሪያ የወሰድኳቸው እኔ ነኝ። ከካርቱም የመጣው ግለሰብ '[ቫይረሱ] ቢኖርብኝም ማገገም እችላለሁ። ግን የለብኝም። ምንም ዓይነት ምልከት ሳይኖረኝ እንዴት አለብህ ትሉኛላችሁ? ይሄ ስህተት ነው። ወደ ቤተሰቦቼ እንዳልሄድ እያደረገቻሁኝ ነው' በሚል ቅሬታ አሰምቷል። ወደ አምቡላንሱ እንዲገባም የጤና ባለሙያ ምክር አስፈለጎ ነበር። ጥንቃቄን በተመለከተ አምቡላንሶቹ ከኋላ ሙሉ ዝግ ናቸው። አቀማመጣቸውም የተወሰነ [ከእኛ] ርቀት አለው። ቫይረሱ አለባችሁ ሲባሉ የሚረብሹ ስላሉ። የግንዛቤ ማስጨበጫ እንሰጣቸዋለን። [ቫይረሱ] አለባችሁ ሲባሉ 'የለብንም ስህተት ነው። ውሸት ነው' ብለው የሚረብሹ፤ መስኮት ለመክፈትም ሆነ ለመስበርም የሚታገል አለ። 'አልሄድም' ብሎ የሚገላገልም አለ። • ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ? • ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው እኛ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እና የእጅ ጓንት እንጠቀማለን። ባህር ዳር የሚገኘው የህክምና ማዕከል ስንደርስ ጸረ-ተዋሲያን ርጭት ያደርጋሉ። ጎንደር ላይ ግን ለማድረግ ራሱ ዝግጁ ሆነው አይጠብቁም። ባህር ዳር ይዤ ስሄድ በአግባቡ መድኃኒት ይረጫል። እኔ ራሱ መሬት ላይ አልወርድም። ጎንደር ግን 'ተቀበሉን አንቀበልም' በሚል አንደ ሰዓትም ብዙ ጊዜ 30 ደቂቃ እቆማለሁ። ሕሙማንና የተለየየ ባህሪያቸው አንዳንዴ ኬዝ [ቫይረሱ ያለበት ሰው] ጭነን ስንቆም 'በግድ ነው ያመጣችሁን። እነሱ ራሱ አንፈልጋችሁም እያሉን ነው ይሄን ያህል ያቆሙን። የት ነው የምትወስዱን?' እያሉ ብዙ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት አሰጣ አገባዎች አሉ። የመተማ ልጅ ስለሆንኩ የአካባቢውን ህብረተሰብ ባህሪ ስለምረዳ ሳናግራቸው ይረዳሉ። ቁጣ ምናምን ከቀላቀልክ አይሆንም። በኋላ በኋላ ከኳራንቲን ቫይረሱ አለባችሁ ተብለው ወደ ህክምና ማዕከላት የሚሄዱ ሰዎች [የሚሄዱበትን ማዕከል] ማማረጥ ጀመሩ። በህክምና ማዕከላት እና በለይቶ ማቆያ ያሉት ስልክ ተደዋውለው መረጃ ይለዋወጣሉ። [ባህር ዳር የተሻለ ነው ስለሚሏቸው] ቫይረሱ ተገኘባችሁ ሲባሉ 'ባህር ዳር ከሆነ ውሰዱን ጎንደር ግን አንሄድም' የሚል ባህሪ እያመጡ ነው። የመጀመሪያ ሁለት ኬዝ ይዤ ስሄድ አንዱ የሲጋራ ሱስ አለበት። ለካ ሲጋራ ይዞ ነበር። ልክ ጎንደር እንደገባን 'ሲጋራ ልለኩስ ነው' አለ። ሲገባ ፍተሻ ስላልተደረገበት ሲጋራ ይዟል። 'ልለኩስ?' ሲል ለሁላችንም መጥፎ ነው እንዳትለኩስ አልነው። ቆይቶ 'እሺ በቃ ሽንቴን ልሸና ነው በቃ አውርዱኝ' አለ። በወቅቱ ቫይረሱ አዲስ እና በእኛም አይታወቅም ነበር። አንዴ ጉዞ ከጀመራችሁ በኋላ ባህር ዳር ነው የምትቆሙት ተብለናል። መንገድ ላይ ማውረድ አንችልም ማለት ነው። እንደተባለው አደረግን። ባህር ዳር ማታ አካባቢ ነበር የገባነው። ወደ 4 ሰዓት ገደማ ነበር የገባነው። ልክ ከተማ ከገባን በኋላ 'አልቻልኩም ከፈለጋችሁ አውርዳችሁ ግደሉኝ እንጂ' ብሎ ሲጋራውን አውጥቶ ለኮሰ። አብሮኝ ጋቢና ያለው የህክምና ባለሙያ ነው። የጸጥታ አባሉ በሌላ መኪና ነበር። አይዞህ እያልን እያበረታታን ሲጋራውን አስጥለን ወደ ህክምና ማዕከል አስገባነው። አንድ ጊዜ ደግሞ ስምንት ኬዝ ተገኘ። ለህክምና ጎንደር ነበር የሚሄዱት። • ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ? • \"የቻይናና የአሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ከኮሮናቫይረስ በላይ ለዓለም ያሰጋል\" • \"ልባችንም ቤታችንም ጨልሟል\" የጀነራል ሰዓረ እና ሜ/ጀነራል ገዛኢ ቤተሰቦች ከህክምና ማዕከሎች ጋር መተዋወቅ ሲመጣ እየደወሉ አምጣ ሲሉኝ በቀጥታ ይዤ እሄዳለሁ። በወቅቱ ከሱዳን ወደ ሃገር ውስጥ በጫካ በኩል አዲስ የሚመጡትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እና የሙቀት ልኬታ ስላለ የጸጥታ መዋቅሩም ሥራ በዝቶበት ነበር። ስምንቱን ይዤ እንድሄድ የጸጥታ አካል አብሮኝ መሳፈር ያስፈልግ ነበር። ከጤና ባለሙያ ወደ ህክምና ማዕከል የማስገባበት ወረቀት ተሰጥቶኛል። የቀረው የጸጥታ መዋቅር አባሉ ከእኔ ጋር ጋቢና ሆኖ ማድረስ ነው። ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች አምቡላንሱ ውስጥ ጫንኩኝ። አባሉ ወጥቻለሁ ቢለንም ስንጠብቀው የለም። ዝም ብዬ ነዳሁት። ግማሽ መንገድ ከደረስን በኋላ 'ሽንታችን ስለመጣ አውርደን' አሉ። 'እንዴት አደርጋለሁ?' የሚል ጭንቀት ያዘኝ። 'ችግር የለም ግን ከተማ ላይ ማቆም አይቻልም። ጫካም ለእናንተ [ደህንነት] ጥሩ ስላልሆነ ከተማ ላይ አንድ የጤና ማዕከል ገብተን ሸንታችሁ ተጣጥባችሁ ትሄዳላችሁ' አልኳቸው። አሁን አሁን እያልኩ እያዋራሁ እያሳሳቅኩኝ ጎንደር ከተማ ገባን። መንገድ ላይ እንደፈለጉ መሆን ይፈልጋሉ፤ ሲጋራ ማጨስ ሽንታቸውን በተለያየ ሰዓት መሽናት ይፈልጋሉ። ከዚያ ውጭ ብዙም ችግር የለባቸውም። አብዛኛዎቹ በሚዲያ የሚተላለፈውን ይሰማሉ። 'ለምን አንድ በአንድ አትወስዱንም?' ሲሉ ይጠይቃሉ። 'መቼም በሃገሪቱ ሁኔታ ለስምንት ሰው ስምንት አምቡላንስ አይመደብም' እንላቸዋለን። 'አንድ ላይ የተገኛችሁ ስለሆናችሁ አንድ ላይ ትሄዳላችሁ። አንድ ሰው ከተገኘበት ለብቻው ነው የሚሄደው ነው' የምላቸው። [ለይቶ ማቆያ ያሉት] ተደጋጋሚ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸውን እንደማመላልስ ሰለሚያውቁ ናሙና ሰጥተው ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ወደ ህክምና ማዕከል ለመውሰድ ስጭናቸው 'ታሬ ታሬ የት ነው የምትወስደን? ባህር ዳር ነው ጎንደር?' ይሉኛል። \"እናንተ እንደምርጫችሁ ባህር ዳር ያለ ባህር ዳር፤ ጎንደር ያለ ጎንደር እላለሁ።\" ምክንያቱም እንዲህ ካልካቸው ነው ተስማምተህ ልትነዳ የምትችለው። እንዲህ ካላልካቸው አትስማማም። እኛ ጎንደር እና ባህር ዳር የህክምና ማዕከላት ይዘን እንሄድ ስለነበር ሁሌም ያጠናሉ። 'የተሻለ ምግብ የሚያቀርቡልን የት ነው ጎንደር ነው ወይስ ባህር ዳር ነው?' ይላሉ። የምትፈልጉት ማዕከል አስገባችኋለሁ እላለሁ። ያው እኔ የጤና ባለሙያው በሚለኝ ነው የምሄደው። ጎንደር ካለኝ ጎንደር እሄዳለሁ። ግን የምትፈልጉት ቦታ እወስዳችኋለሁ ስላቸው 'ባህር ዳር፣ ባህር ዳር' ይሉኛል። በኮቪድ ጉዳይ ጥቂቶች ናቸው በሽታው ስለመኖሩን የሚያውቁት። ከዚያ ውጭ ግን እንደ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ብራዚል፣ ስፔን እና ጣሊያን ሞት ካላየ የማያምን ህብረተሰብ ነው ያለው እኛ አካባቢ። እኛ አካባቢ ውሸት ነው የተባለበት ጊዜም አለ። ምክንያቱም 'አላሳለኝ፣ ሙቀት አልተሰማኝ፣ ሙቀቴ አልጨመረ። ጤነኛ ሰው ነኝ። እንዴት አለብህ ትሉኛላችሁ?' ይላሉ። ብዙዎች አለባችሁ የሚባሉትም አልተዋጠላቸውም። በትክክል ተገኝቶብኛል ብሎ ራሱን ያሳመነ አካል የለም። ቫይረሱ ያለባቸውን እና ተጠርጣሪዎችን ሳመላልስ ሙሉ ከተማው ይጠቋቆምብኝ ነበር። ምክንያቱም ኮኪትም ገንደ ውሃ [ከተሞች] ላይ ሳልፍ በጣም እሯሯጥ ነበር። 'ኮቪድ የሚያመላለስው ማነው?' ሲባል 'የመተማው ሹፌር- የመተማው ሹፌር ታሪኩ የሚባል ነው' ይላሉ። እኔ ራሱ ቫይረሱ ያለባቸውን ባህር ዳር ወስጄ ስመለስ ሌላ ቦታ ወርጄ ሻይ መጠጣት ተሳቀቅኩኝ። ሻይ መጠጣት እፈልጋለሁ ግን ተሳቀቅኩኝ። ማህበረሰቡ 'ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የሚሠራ ሰው ራሱን አግልሎ ማግለያ ውስጥ መቀመጥ አለበት ነው' የሚለው። • ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊያንሰራራ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል እኔ ሹፌር ሆኜ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ስሠራ ጀምሮ ከቤተሰብ ጋር ከሚስቴ ጋር መቀላቀል የለበኝም። ተመቻችቶ ለብቻዬ ኳራንቲን ሆኜ ከማህበረሰቡ፣ ከእናቴ እና ከባለቤቴ ጋር መቀላቀል አልነበረብኝም። አድርሼ ስመለስ ጓደኞቼ አትቀላቀልም በሚል ከአንገት በላይ ነበር ሠላም የሚሉኝ። አሁን ግን ለውጥ አለው። 'ችግር የለም ሰላም በለን' የሚልም አለ። አሁን ተለምዷል። መጀመሪያ ግን 'መተማ ላይ [ቫይረሱ] ከገባ እሱ ነው የሚያስገባብን' በሚል እኔ ላይ ያነጣጠረ ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ ነው የነበረው። ከጊዜ ወደ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ስለጨመረ ከአምቡላንስ አቅም በላይ ሆነ። ጎንደር ዩኒቨርሰቲ አውቶብስ ስለሰጠን እሱን እየተጠቀምን ነው። አንዴ ኬዝ ሲመጣ ከ20 በላይ ስለሚሆን አምቡላንስ ስለማይበቃ ዩኒቨርሲቲው በሰጠን አውቶብስ እየተመላላሱ ነው። አሁን ከጸጥታ እና ህክምና ባለሙያዎች ጋር በመሆን በጫካ በኩል ወደ ማህበረሰቡ የገቡ ስለሚኖሩ እነሱን እየሄድኩ ከጸጥታ መዋቅር ጋር ወደ ገንደ ውሃ እና መተማ ኳራንቲን ነው የማስገባው። ቫይረሱ ያለባቸውን ወደ ህክምና ማዕከል አላመላልስም። በመተማ ድንበር የሚመጡ የበረሃ ሠራተኞች የተለያየ የሱስ ሁኔታዎች ያለባቸው አሉ። ሲጋራ፣ ሺሻም ጫትም ሱስ ያለባቸው አሉ። ለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ ሁሉን ያጣሉ። ለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ 'የምንበላው አይመቸንም' በማለት የሚጠፉ አሉ። ለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ ሁለት ሳምንት ሞልቷቸውም 12 ወይም 13 ቀን የቆየ ሌላ ሰው ናሙናው ሲወሰድ እኛ 14 ቀን ሞልቶን ለምን አይወሰድልንም በሚል 14 ወይም 15 ቀን ሞልቷቸዋው ለሊት ላይ ከፀጥታ መዋቅሩ በመሸሸግ ከተለያዩ ማዕከላት ያመልጣሉ። በህዝብ ክትትል እና ጥቆማ ይያዛሉ። መጀመሪያ ከቢቢሲ ሲደወልልኝ '14 ቀን ሞልቶኛል። ናሙና መወሰድ ነበረበት። ካልተወሰደ ለምን እቀመጣለሁ?' በማለት ወደ መንደር 7 ከተማ የጠፋ ግለሰብ ለመያዝ እያቀናሁ ነበር። እንደጠፋ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ መንደር ሰባት ላይ ተያዘ። ከቦታው ድረስ ሄጄ አምጥተነው ናሙና እንዲሰጥ አድርገናል። እስካሁን ባለው ሁኔታ ምንም ዓይነት ስሜት የለኝም። መሥራት ከጀመርኩ ራሴንም አሞኝ አያውቅም። ሙሉ ጤነኛ ነኝ። ግን ስጋት ነበረኝ። ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ሳይ ምንም ምልክት የለባቸውም። በወቅቱ ሳመላልሳቸው ንጹህ ሰዎች ናቸው። አንዱን አውርጄ ሌላ ለመጫን መኪናውን ጸረ-ተዋህሲያን የሚረጨው ጠፍቶ ለመርጨት የምገደደበት ጊዜ አለ። ሥራው የህሊና ሥራ ስለሆነ ራሴ በጸረ-ተህዋሲያን መኪናውን አጸዳለሁ። አጣዳፊ ሲሆን የእጅ ጓንትም ሲያልቀብኝ አልኮል ያለው ማጽጃ (ሳንታይዘር) እጄን ረጭቼ በር እከፍት ነበር። ራሴን እጠራጠር ነበር። ከሳምንት በፊት ተመረመርኩኝ። ነጻ ሆኜ ተገኘሁ። ከዚህ በኋላ ግን በደንብ እንደምጠነቀቅ ነው የተማርኩበት። ኢትዮጵያ ውስጥ ኮቪድ አስጊ ከሆነባቸው ቦታዎች አንዱ ምዕራብ ጎንደር ነው። ከሱዳኖች ጋር ፊት ለፊት እየተያየን እየተጨባበጥን ነው የምንኖረው። የ10 ሜትር ልዩነት ናት። ዋናው ቦታ ደግሞ መተማ ዮሃንስ ላይ ነው። ኬላውን ሲከፍቱ ምናምን እንተያያለን። እንደሃገር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ አይደለም። ብዙ በሮች እና ፍሰት ያለበት ቦታ ነው። የሱዳን ኬዝ ሲጨምር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ፍልሰት ይጨመራል። በረሃ ውስጥ ከሚሠሩት በተጨማሪ ከተማ ላይ የሚኖሩም እየመጡ ነው። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት። ባለው የበጀት ምክንያት ጸረ-ተዋህሲያን በአግባቡ አያመጡልንም። የእጅ ጓንት እና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አይመጣልንም። በነበረው ነው የምንጠቀመው። ከኮሮና ኬዝ በኋላ የገባልን ነገር የለም። ኮታው እየጨመረ ነው። ግን የደረሰ ነገር የለም። የጸጥታ መዋቅሩም ንክኪ አለው ማለት ይቻላል። እየተጋለጠ ነው። [ተጠርጣሪዎችም ሆኑ ቫይረሱ ያለባቸው] አንሄድም ሲሉ ገፍተው ያስገቧቸዋል። ለምርመራ ጎንደር እና ባህር ዳር መኬድ የለበትም። ለምን ገንደ ውሃ አይሆንም። በሽታው እንደ ሃገር እየተስፋፋ ነው። እየተከላከለን አይደለም። ብቻ ያስቡበት።", "ተክሌ አበራ፡ ዓይነ ስውሩ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የዘመናት ደጋፊ ካምቦሎጆና እና ተክሌ ከተዋወቁ አስርት ዓመታት ነጉደዋል። ከ1968 ጀምሮ የካምቦሎጆን መግቢያ መውጫውን አብጠርጥሮ ያውቀዋል። \"ያኔ በደርግ ዘመን 68 አካባቢ ነው። 50 ክለቦች ነበሩ። ሁሉንም ክለቦች እመለከት ነበር። የራሴ የሆነ የማውቀው ቡድን አልነበረኝም። ከኤርትራም የሚመጡ ቡድኖች ነበሩ። አዲስ አበባ በሚጫወቱበት ወቅት እመለከት ነበር\" ሲል ያስታውሳል። ያኔ 'ቡንዬ' አልነበረም። ከፍተኛ ዲቪዚዮን ውስጥ \"እነ ጥጥ የድሬዎቹ፣ አዱሊስ የአሥመራዎቹ እነ አብዮት ፍሬ፣ ትግል ፍሬ በደርግ ዘመነ መንግሥት ናቸው የነበሩት\" እንጂ ቡና የዚያን ጊዜ አልነበረም። \"ቡና በ19 77 ነው የተቀላቀለው። ማንም አያውቀውም የሠራተኛ ማኅበር ነው የነበረው።\" በወቅቱ የ50 ክለቦች ውድድር ይካሄድ ነበር። ቡና እና ተክሌ አበራም የተዋወቁት የዚያን ጊዜ ነው። አጋጣሚውን ተክሌ አይረሳውም። \"ቡና ከአደይ አበባ ጋር ሲጫወት ተመለከትኩት። ውድድሩ በጣም ከባድ ነበር። [ቡና] የላቀ ቡድን ሆነብኝ። ምክንያቱም በጣም በራሱ የሚተማመን በሳል አሰልጣኝ ነበረው። ከነበሩት ቡድኖች የማረከኝ ቡና ብቻ ሆነ። በዚህ መልኩ ነው ቡናን የተዋወቅኩት\" ይላል። የእግር ኳስ ፍቅር ከቡና ጋር ተጀመረ። በሠላማዊው ውጊያ በፍልሚያው ስፍራ የቡና ፍቅር ስንቱን \"ብዙ ሊገለጽ የማይችል\" የሚለውን አጋጣሚ አጋፈጠው። \"የታሰርኩበት ጊዜ አለ። ብዙ መከራ እና ውጣ ውረድ የገመኝ ጊዜ አለ። ከስታዲም የታገድኩበትም ጊዜ ነበረ። ብዙ የራሴ የሆነ ነገር ያጣሁበት ጊዜ አለ። ቡናን በማየቴ የሥራ ዘመኔን ያባከንኩበት ጊዜ አለ። ብዙ የገጠሙኝ ነገሮች አሉ ሊቆጠሩ የማይችሉ መሰናክሎች አጋጥመውኛል\" ይላል የኋሊት እያስታወሰ። ስታዲም እንዳይገባ ከተደረገበት እንጀምር በወቅቱ ወፖ (ወታደራዊ ፖሊስ) የሚባሉ ወታደሮች ነበሩ በስታዲየሙ ጨዋታ ሲኖር የሚጠብቁት። ተደባዳቢ ነው በሚል ወደ ስታዲየም ዝር እንዳትል ተባልኩ። 'በቡና የተነሳ ከሰው ጋር ይደባደባል ብለው ነው' ላለማስጋባት የወሰኑት። \"ቡናን ስለምወድ በማስጨፍረበት ሰዓት ይቃወሙኝ ነበር\" ይላል። አንድ ቀን ወፖዎች ይዘውት ወደ ለገሃር አቀኑ። ለገሃር የማይሠሩ አሮጌ ባቡሮች ነበሩ። አንዱ ውስጥ የቆልፈውበት ይሄዳሉ። ረሱት። ከቤትም የት ገባ? የት ጠፋ? የሚለው አጥቶ የት እንዳለ ሳይታወቅ ቆየ። ከእስሩ በላይ ረሃቡን አልቻለውም። \"በጣም ርቦኝ ስጮህ በመኪና የሚያልፉ ሰዎች መጥተው አስወጥተውኛል\" ይላል። ከእስር ቢወጣም ስታዲየም እንዳይገባ የተጣለበት እገዳ ግን አልተነሳም። ይህም ግን ኳስ ከመመልከት አላገደውም። ሌላ ዘዴ ይዞ ብቅ አለ። \"እነሱ አግደውኛል እንጂ እኔ በኤሌክትሪክ ገመድ ተስቤ ተደብቄም እግባ ነበር። በባሕር ዛፍ ላይ ተንጠላጥዬም፣ በገመድም ተስቤ እገባ ነበር\" የሚለው ተክሌ በዚህ ምክንያት \"ጨዋታ አያመልጠኝም ነበር\" ይላል። በድጋሚ ደግሞ አሁንም ታሰረ። ይኼኛው ደግሞ በሌላ ምክንያት ነው። \"አንድ ጓደኛ አለኝ። አብደላ አህመድ ይባላል። ካታንጋ ሆነን ስንጨፍር የምድር ጦር ደጋፊዎች ዝም ብለው መጡ እና ሁለታችን ላይ ሽጉጥ አወጡ። ሽጉጥ ሲያወጡ አብሮኝ የነበረው በጣም ደንግጧል እና እንዳልነበረ ሆነ። እኔ ደሞ 'ምንድነው? በሰላም አገር ላይ ሽጉጥ ምን ያስፈልጋል መብታችን እኮ ነው። የማንንም መብት አልነካንም። ተኩስ ተኩስ' አልኩንና ሳፈጥበት ይዘውኝ ሄዱ እና ቆለፉብኝ\" ይላል አጋጣሚውን እያስታወሰ። \"ሦስት ቀናትን በእስር አሳለፍኩ። ከፍተኛ ዱላም ቀምሻለሁ። እዚያ ካስገቡን በኋላ በጣም ጎድተውኛል።\" የቡና ደጋፊ ሆኖ ብዙ አሳልፏል። \"በበኩሌ ሊቆጠር የማይችል ብዙ እንግልት ነው የደሰረሰብኝ\" የሚለውም በምክንያት ነው። ለቡና የነበረው ፍቅር ግን እያበበ ሄደ። በዚህ መልኩ የተክሌ እና የቡና ፍቅር ዘለቀ። የቡና ውጤት ከፍም ዝቅም ሲል ተክሌ አለ። ቡና በዚህ ሁሉ አልፎ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ ሲያነሳ እማኝ ለመሆንም በቅቷል። ለውብ ጨዋታ ቡና ለኳስ እርካታ ቡና ኢትዮጵያ ቡና የኛ የኛ . . . በ2005 ተክሌ ህይወት እስከ ወዲያኛው ተቀየረ። የመኪና አደጋ አጋጠመው። \"2005 ላይ የመኪና አደጋ አጋጠመኝ። በቅርብ ነው 10 ዓመት አልሞላኝም። ዘጠኝ ዓመት ከምናምን ነው። የመኪና አደጋ አጋጥሞኝ የዓይን ብርሃኔን አጣሁ።\" ከደረሰበት አደጋ ለመዳን ሙከራ ቢያደርግም የሚሳካ አልሆነም። \"በወቅቱ እድናለሁ ብዬ ምኒልክ [ሆስፒታል] ሄድኩኝ። ሐኪሞቹ የሁለቱም የዓይኖቼ ብሌኖች እንደሌሉ ተናገሩ።\" አንድ አውራ ጣቱም በአደጋው ስብራት ደረሰበት። \"ከዚያ በኋላ ደግሞ ማገገም አልቻሉኩም\" የሚለው ተክሌ \". . . አቅም አልነበረኝም። ይህን አደጋ መቋቋም አልቻልኩም። ተጎዳሁ፣ ብርሃኔን አጣሁ፣ አልጋ ያዝኩኝ\" ሲል ሁኔታውን ይገልጻል። አስፈላጊውን ህክምና ተከታትሎ አጠናቀቀ። ማየት ባይችልም ድጋሚ ጉዞ ወደ ካምቦሎጆ ተጀመረ። አደጋው ደርሶበት ህክምናውን ከተከታተለ በኋላ ምንም ጨዋታ እንዳላመለጠው በተደጋጋሚ ይናገራል። \"እኔ አደጋው ከደረሰብኝ በኋላም አቋርጬ አላውቅም። [ስታዲየም] እሄዳለሁ\" ይላል ተክሌ። ዋናው ጥያቄ ይሄኔ ይነሳል። እንዴት ጨዋታውን ይከታተላል? የሚለው። \"ጨዋታውን አነበዋለሁ። እንቅስቃሴውን በደንብ አውቀዋለሁ። ምክንያቱም በማጥቃት ከኋላ ጀምሬ የቡድኑን እንቅስቃሴ በደንብ አውቀዋለሁ። አካሄዱን በደንብ እረዳዋለሁ። በማጥቃት በኳሱ ፍጥነት አውቀዋለሁ።\" በደንብ እንዲያስረዳን ድጋሚ ጨዋታውን እንዴት እንደሚከታተል እና ስለ ጨዋታው ሂደት የሚነግረው ሰው ስለመኖሩ ጠየቅነው። \"እኔ ከሰው ጋር [ስታዲየም] አልገባም። አንድ ህጻን ልጅ አለኝ አልፎ አልፎ ትምህርት ከሌለው እሱን ይዤው እገባለሁ። እሱም ኳስ ይወዳል። በጣም በጣም የቡና ደጋፊ ነው። እኔ በራሴ እመለከታለሁ። ልጄ አጠገቤ ካለ ልጄ ይረዳኛል። ልጄም [ስለ ኳስ] ያውቃል። እሱም ከእኔ የበለጠ ስሜታዊ ነው። 14 ዓመቱ ነው። እንደ ልጅነቱም ሳይሆን ጨዋታ በደንብ ገምግሞ ያውቃል።\" ብዙ አገራት ለአካል ጉዳተኛ ደጋፊዎች የሚመቹ ስታዲየሞችን እና አሠራሮችን ዘርግተዋል። ሰዎችም ተባባሪ ናቸው። በኢትዮጵያ ግን ከዚህ እንደሚለይ ተክሌ ይገልጻል። \"ካምቦሎጆ በምትገባበት ጊዜ አንዳንዶች ሊረዱህ ቀርቶ በመግባትህ የሚገረሙ አሉ። አሁን ኑሮ ውድ ነው። [የስታዲየም] መግቢያ ውድ ነው። አንድ ብር ሳይከፍልልህ መግባትህ የሚደንቀው ሰው አለ። ለወሬ የሚሞት ሰው አለ\" ይላል ተክሌ። ይህ ግን የሁሉም መገለጫ አይደለም። በቅርቡ እንኳን የዓመት ቲኬት ገዝተው የሰጡት ሰዎች መኖራቸውን ይናገራል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የገጠመውን እንደሚከተለው አጫውቶናል። አንድ ጊዜ የዓመት ቲኬት ይዞ ከልጁ ጋር ካምቦሎጆ ይደርሳል። ስታዲየም ሊገባ ሲል አንዱ ደጋፊ ፖሊሱን 'ለምን ታስገባዋለህ? ለምን ታስገባዋለህ? መልሰው' ይለዋል። ተክሌ ቢሰማውም እሱን አልመሰለውም ነበር። ፖሊስ፡ ተክሌ፣ ተክሌ ተክሌ፡ አቤት ፖሊስ፡ ስላንተ ነው የሚያወሩኝ ግን ሂድ ግባ። ተክሌ ሊገባ ሲል በድጋሚ ፖሊሱ 'አሁንም መልሰው እያሉኝ ነው' ይላል። ተክሌ፡ ለምን? ምን አድርጌው ነው የሚመልሰኝ? ይከፍልልኛል? ለመንኩት? ልመና ወጣሁ? ጉዳዩ ምንድነው? ፖሊስ፡ 'ዱላ ይዞ ስለሚገባ ሰው ሊጎዳ ይችላል' በሚል ነው አለ። 'በዱላ ስለሚሄድ ወይ ዱላውን ውሰድበት ወይ ደግሞ መልሰው' እያለ ነው። ይህን ሲሰማ ተክሌ በጣም አዘነ። ወደ አንድ ጥግ ፖሊሱን ጠርቶ 'ይህንን ያለህን ሰውዬ ሃሳብ ትጠቀምበታለህ እንዴ?' ሲል ጠየቀው። ፖሊሱም 'ሂድ ግባ አልኩህ እኮ። ለምን እንደዚህ አይነት ጥያቄ ትጠይቀኛለህ። ሂድ ግባ ማንም አይከለክለውም ብዬዋለሁ' ብሎ መለሰለት። ተክሌ ጨዋታውን ሊከታተል ሜዳ ሲገባ ፖሊሱም ወደ ሥራው አቀና። እንደዚህ የሚያስቸግር አጋጣሚ ካለ በራዲዮ ወይም በቲቪ መከታተል አይሻልም? እነዚህ ለተክሌ ጥሩ ምርጫዎች አይደሉም። መልሱ ደግሞ ግልጽ ነው \"ይለያያል\" የሚል። \"ይለያያል። . . .አንተ ያየኸውን፣ የነበርክበትንና ሰው የሚነግርህን እኩል አታራምደውም። ኖረህ እንቅስቃሴውን፣ ፍጥነቱን በማጥቃቱም በጎሉም በምኑም ያየኸውን የነበረክበትንና ሰው የሚነግርህ ልዩነት አለው\" ይላል። ለዚህም ነው በአካል ተገኝቶ ጨዋታዎቸን መመልከትን የሚያስቀድመው። በዚህም ቡድኑ በሚለማመድበትም ሆነ ግጥሚያ ሲኖረው ቦታው ድረስ እየሄደ ይከታተላል። ወደ ፊትም ጨዋታዎችን መከታተሉ ይቀጥላል። \"ሁሌም ስታዲየም እሄዳለሁ። ለምን ጠንካራ እና ደካማ ጎኑን ለመገምገም እና እንቅስቃሴውን ለማንበብ ነው። እኔ የቡድኑን አቋም ለማወቅ እና እንቅስቃሴውን ለማየት ነው የምሄደው። ምክንያቱም አንተ ያላማረህን ነገር አትበላም አይደል? አሰልጣኙን ለመንቀፍም ሆነ በልጆቹ ለማዘን የቡድኑን አቋም ውጤቱንም ለማወቅ በሚዲያ መስማት ይቻላል። ስለዚህ እንቅስቃሴውን ለማንበብ በቦታው መገኘት ይበልጣል።\" ተክሌ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ብዙም አይከታተልም። \"ከአገሬ እኩል አላይም። እኔ ከእነሱ [እግር ኳስ] የአገሬን ነው የማስቀድመው\" ይላል። ቢሆንም የባሕር ማዶ ጨዋታዎችን አልፎ አልፎም ቢሆን እንደሚከታተል ይጠቅሳል። የእንግሊዙ አርሴናል ደግሞ የሚመርጠው ቡድን ነው። \"የእንግሊዙ አርሴናል በሚጫወትበት ጊዜ ከእኔ ክለብ ጋር እንቅስቃሴያቸው ተመሳሳይ ነው። አርሴናል ከምወደው ቡድን [ቡናን ማለቱ ነው] ጋር እንቅስቃሴው ተመሳሳይ ነው። ሁለቱም ኳሱን ይዘው መጫወትን ይመርጣሉ። እና አልፎ አልፎ እሱን እከታተላሁ\" ይላል። ዛሬስ ልዩ ናቸው ባርሳም ቢመጣ አይችላቸው። ለዓመታት ካምቦሎጆ የተመላለሰው ተክሌን የትኛው ተጫዋች ቀልቡን ይይዘዋል? ማንን ያስበልጣል? \"እንደዚያ አይደለማ\" ሲል ምላሹን መስጠት ይጀምራል። \"እንደዚያ አይደለም፤ ልጅ ከውደድክ ከነምናምኑ ነው የሚባል የሃበሻ ተረት አለ። ቡድኑ ሙሉ ለሙሉ የራሴ ነው። ክለቤ ነው። ያደኩበት ክለቤ ነው። እዚህ የደረስኩበት ክለብ ነው። ከጀርባዬ የቆመ ክለብ ነው። በእግር ኳስ ደግሞ ውጣ ውረድ አለ። አንዳንዴ ባልጠበከው መንገድ ታገኘዋለህ። አንዳንዴ መሰናክሎች ይኖራሉ። \"ገና ገና ብዙ መንገድ ይራመዳል ብዬ ነው የምጠብቀው። ምክንያቱም የራሴ ፍላጎት ከራሴ ጋር ነው ያለው። ለምሳሌ ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ እንዲወዳደር እመኝ ነበር። ደርሶ አይቼዋለሁ ተወዳድሯል። ሁለተኛ በሊጉ አንደኛ እንዲሆን እመኝ ነበር ሆኖ አይቸዋለሁ። ዘንድሮም ገና ጅምር ነው እንጂ አላለቀም። ከአንድ እስከ ሦስት ባለው ደረጃ ውስጥ ይገባል ብዬ እገምታለሁ\" ሲል ምላሹን ያጠናቅቃል። ተክሌ ባለትዳር ነው። አራት ልጆች አሉት-ሁለት ወንድ ሁለት ሴት። ሥራ የለውም። 'የሰው እጅ ከማየት ብሎ' ከሰል ቸርችሮ በመሸጥ ነው ኑሮውን የሚገፋው። የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማኅበር አባል ነው። \"ደጋፊ ማኅበር ማለት እንደ አቅምህ የተለየያ ከፍለህ ነው የምትገባው። እኔ ድሮ ከጤናዬ ጀምሮ አባል ነኝ።\" ማኅበሩ በተለይ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ድጋፍ አድርጎለታል። \"እኔን በደንብ ያውቁኛል። ብዙዎች ያውቁኛል ምክንያቱም ብርሃን ባጣሁ ጊዜ በጣም ረድተውኛል። በታመምኩ ጊዜ ለእኔም ለልጆቼም በተለያየ ጊዜ በጣም ረድተውኛል\" ብሏል። ተክሌ ኳስ ተመልካች ብቻ አይደለም የዓይን ብርሃኑን ከማጣቱ በፊት ይጫወትም ነበር። ሆኖም \"የዓይን ብርሃኔን ካጣሁ በኋላ ሁሉንም ነገር ተውኩት\" ይላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓይነ ስውራን የሚሳተፉበት ውድድር አለ። እንዴት ለመጫወት አልሞከርክም ብለን ገፋ አድርገን ጠየቅነው። \"አሁንማ እንዴት አድርጌ ብርሃን የለኝም ዱላ ይዤ፣ በዚያ ላይ ደግሞ ልጆች አሉ። መብራት፣ የቤት ኪራይ፣ ውሃ እና ምግብ አለ። ይሄ ሁሉ ጭንቀት እና መከራ እያለ እንዴት አድርጌ እጫወታለሁ። ለልጆቼም ዳቦ እንኳን ለመግዛት በምታገልበት ሰዓት እንዴት እጫወታለሁ?\" ይላል። ወደ ቡና ቡድኖች እንመለስ። ደጋፊዎች በተለያዩ ወቅቶች ከነበሩ የቡና ስብስብ መካከል የራሳቸውን ምርጥ ቡድን ሲሰይሙ ይታያል። ይኼኛው ቡድን ምርጥ ነበር፤ ይኼኛው ይሻለኛል እያሉ። የተክሌስ ምርጡ ቡድን የቱ ነው ? \"ከ1983 አስከ 1989፣ በ1994 እንደገና በ1995 እንዲሁም በ2003 ዓመታት የነበሩት ቡድኖች ለእኔ በጣም በጣም ምርጥ የቡና ስብስቦች ነበሩ\" ሲል በአጭሩ ይመልሳል። ተክሌ ከሰሞኑ አንኳን ቡናን ሃዋሳ ድረስ ተጉዞ ሲከታተል በቴሌቭዥን መስኮት ታይቷል። የዘንድሮውን ቡድን በተመለከተ ሃሳቡን ሰጥቶን ቆይታችንን አጠናቀቅን። \"ቡና ሁሌም ጣፋጭ ነው። ሁሌም ልዩነት የለውም። በእግር ኳስ ዓለም ውጣ ውረድ ያለ ነው። አንድ ቡድን አንዴ ይጠነክራል አንዴ ዝቅ ይላል። ውጤት ይቀንሳል እንጂ ሁሌም ቡና ጥሩ ነው።\"", "አራት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ሲሞን ከቶኪዮ የፍፃሜ ውድድር ራሷን አገለለች አሜሪካዊቷ የጂምናስቲክ አትሌትና አራት ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ሲሞን ባይልስ በቶኪዮ በነገው ዕለት ከሚደረገው የጂምናስቲክ የፍፃሜ ውድድር ራሷን ማግለሏን አስታውቃለች። በአለም በጂምናስቲክ ስፖርት ዘርፍ የምንጊዜውም ምርጥ የሚል ስም ማትረፍን የቻለችው አትሌቷ ከሴቶች ቡድን የፍፃሜ ውድድር ራሷን ያገለለችው በአዕምሮ ጤንነቷ ላይ ማተኮር ስላለባት መሆኑንም ተናግራለች። የአሜሪካ ኦሊምፒክ ቡድን መሪ እና አትሌቶችም ሲሞን ለአእምሮ ጤንነቷ ቅድሚያ ለመስጠት መወሰናቸውን አድንቀዋል። የ 24 ዓመቷ አትሌት በቶኪዮ አምስቱን የግለሰብ የጂምናስቲክ ዘርፍ ፍፃሜዎች ደርሳለች። በመጪው ሃሙስ 'ኦል አራውንድ' በተባለው ውድድር የቀደመ አሸናፊነቷን ለማስጠበቅ መሳተፍ ነበረባት። ከዚያ በኋላም በመጪው እሁድ፣ ሰኞና ማክሰኞም ሌሎች በጂምናስቲኩ ዘርፍ ባሉ ውድድሮችም መሳተፍ አለባት። የአሜሪካ ጂምናስቲክስ እንዳለው \"ሲሞን በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄዱት የግለሰብ የፍፃሜ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ወይም ላለመሳተፍ መቻሏንም በተመለከተ በየቀኑ ትገመገማለች\" ብሏል። \"እኛ የሲሞንን ውሳኔ በሙሉ ልብ እንደግፋለን እናም ለጤንነቷ ቅድሚያ በመስጠት ድፍረቷን እናደንቃለን ። ድፍረቷ አሁንም ለምን ለብዙዎች አርአያ እንደምትሆን አሳይ ነው\" ብሏል። ሲሞን ከቡድኑ የፍፃሜ ውድድር ራሷን ከማግለሏ በፊት በአንደኛው የጂምናስቲክ ውድድር አይነት ዝቅተኛውን ነጥብ አስመዝግባለች ተብሏል። ምንም እንኳን ከውድድሩ መድረክ ብትወጣም የኦሎምፒክ ቡድኗን ለመደገፍ ተመልሳ መምጣቷ ተገልጿል። የኦሎምፒክ ቡድኗ ሩሲያን ተከትሎ የብር ሜዳልያ ማግኘት ችሏል። ለሲሞን ይሄኛው ስድስተኛው የኦሎምፒክ ሜዳልያዋ ሲሆን 30 የአለም ሻምፒዮና ሜዳልያም ማግኘት የቻለች አትሌት ናት። ከውድድሩም በኋላ \" ከውድድሬ በኋላ መቀጠል አልፈለግኩም። በአዕምሮ ጤንነቴ ላይ ማተኮር አለብኝ። በአሁኑ ወቅት የአዕምሮ ጤንነት ሁኔታ በስፖርት ውስጥ በጣም የተስፋፋ ይመስለኛል። \" ብላለች። \"ዓለም የሚፈልገውን ብቻ ማድረግ የለብንም። ሰውነታችንና የአዕምሮ ጤንነታችንን ልንጠብቅ ይገባል\" በማለትም መልዕክቷን አስተላልፋለች። \"ከእንግዲህ በራሴ ላይ እምነት የለኝም። ምናልባት በዕድሜ እየተለቅኩ ስለሆነ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ሰው ስለኔ ትዊት በሚያደርግባቸው የተወሰኑ ቀናት የዓለምን ሸክም ሁሉ የተሸከምኩ ይመስለኝ ነበር\" \"እኛ አትሌቶች ብቻ አይደለንም። በቀኑ መጨረሻ እኛም እንደሌላው ብዙ ስሜት የሚሰማን ሰዎች ነን እናም አንዳንድ ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለንም ልናይ ይገባል\" በማለትም መልዕክቷን አስተላልፋለች።", "በባዕድ አገር እንግዳ ሆኖ እንግዶቹን 'ለማስተናገድ' የተገደደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ የፊፋን መመዘኛ የሚያሟሉ የሚባሉ ስታዲየሞች በአገሪቱ አራቱም አቅጣጫዎች ተገነቡ፣ እየተገነቡ ነው ሲባል ተደጋግሞ ተሰምቷል። ስታዲየሞች በባሕርዳር፣ ነቀምቴ፣ ወልዲያ፣ አዲስ አበባ፣ ሐዋሳ እና ሌሎች አካባቢዎችም ባለፉት ዓመታት ተገንብተዋል። እየተገነቡም ነው። ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተጠናቀቀው የወልዲያው ሼህ መሐመድ አሊ አላሙዲን ስታዲየም ነው። አንዳንዶቹ ጨዋታ ማስተናገድ ቢጀምሩም በተለያየ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ። አዲስ አበባ ስታዲየም ከሰባት አስርታት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል። ስታዲየሙ በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጥቅምት 23 ቀን 1940 ዓ.ም የመሠረተ ድንጋይ የተጣለለትና እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ \"ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታዲየም\" ይባል ነበር። ከደርግ መንግሥት መምጣት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም ተቀይሯል። የስታዲየሙ ግንባታ በመዘግየቱ ምክንያት በ1953 ሊደረግ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ በአንድ ዓመት ለመራዘሙ አንድ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። ዕድሜ ጠገቡ ስታዲየም ሦስት የአፍሪካ ዋንጫዎችን (3ኛ፣ 6ኛ እና 10ኛውን) ጨምሮ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን አስተናገዷል። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባስተናገደችው ሦስኛው የአፍሪካ ዋንጫ ስታዲየሙ ያለ መብራት የአህጉሪቱን ትልቁን የፍጻሜ ጨዋታ ተከናውኖበታል። ለምሽት ጨዋታዎች የሚያገለግለው መብራት የተተከለለት በ1959 ዓ.ም ነው። በነገራችን ላይ የሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኢትዮጵያ ነበረች። ብቸኛው የውድድሩ ዋንጫዋም ነው። ከዚህ በብቸኝነት ስፖርታዊ ውድድሮች በተጨማሪ ሐይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እና የሙዚቃ ድግሶችን ሲያስተናግድ ከቆየው ስታዲየም በኋላ ሌሎችም መገንባት ቀጠሉ። አዳዲሶቹ ስታዲየሞች ምን ገጠማቸው? በተለይ በቅርብ ዓመታት የሚሠሩት ሲጀመሩ 'የፊፋን እና/ወይም የካፍን መመዘኛ የሚያሟሉ' ተብለው ነው። የኋላ ኋላ ግን እንቅፋት እየገጠማቸው ነው። በተባለላቸው ጊዜ አይጠናቀቁም። ሲጠናቀቁም አነስተኛውን መመዘኛ አያሟሉም ይባላል። ቀጥሎ ውድድር እንዳያዘጋጁ ከካፍ እና ከፊፋ እገዳ ይጣልባቸዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተገንብተው 'የካፍ መመዘኛ የሚያሟሉ' ተባሉትን ስታዲየሞች በመተማመን የቻን 2020 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባ ዕድሉ ተሰጥቷት ነበር። ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማስተናገድ ስትመረጥ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን (ኢእፌ) ውድድሩን አዘጋጅበታለሁ ብሎ አምስት ስታዲሞችን መርጦ ነበር። ነገር ግን ካፍ ገምጋሚ ቡድን በመላክ የአዲስ አበባ፣ የመቀለ፣ የሐዋሳ፣ የባሕር ዳር እና የድሬዳዋ ስታዲየሞቹን ከተመለከቱ በኋላ ውድድሩን ለማዘጋጀት ብቁ አይደሉም ብሎ በመወሰኑ፣ ጨዋታው ከኢትዮጵያ ተነጥቆ ካሜሮን እንድታዘጋጀው ተወሰነ። አንዳንድ ሁኔታዎችን በማጤን ውድድሮች እንዲካሄዱበት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረውን የአዲስ አበባ ስታዲምም በተመሳሳይ እገዳ ተጥሎበታል። የአዲስ አበባ ስታዲየም ሙሉ እድሳት ካልተደረገለት ምንም ዓይነት የካፍ ጨዋታዋችን እንዳያስተናግድ ነው የተባለው። ከእገዳው በተጨማሪ መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች በአስቸኳይ የማይሻሻሉ ከሆነ በካፍ የተመዘገቡ ሁሉም ጨዋታዎች ወደ ጎረቤት አገር እንደሚዘዋወሩም አስታውቆ ነበር። ማስጠንቀቂያውን ተከትሎ የስታዲየሞቹን ደረጃ የማሻሻል ሥራዎችን ተጀመሩ። በዚህም የባሕርዳርና የመቀለ ስታዲየሞችን ቀሪ ሥራም መከናወን ቀጠለ። በተለያዩ ጊዜያት ካፍ ከሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ጎን ለጎን ጊዜያዊ ፈቃድ በመስጠት የባሕር ዳር እና መቀለ ስታዲየሞች እንዲሠሩ ፈቀደ። ፈቃዱም በተለያየ ጊዜ ሲታደስ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በአህጉር ደረጃ የሚወዳደሩ የአገሪቱ ክለቦች በእነዚህ ሜዳዎች ላይ ጨዋታዎችን ሲያደርጉ ነበር። በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት በእግር ኳሱም ላይ ጥላውን አሳርፎ፣ የትግራይ ክልል ክለቦች ከሊጉ ውድድር ውጭ ሆኑ። ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኒጀር ጋር ኅዳር 2013 የመልስ ጨዋታ ባሕር ዳር እንደሚካሄድ ተወስኖ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ላይ ነበር። በወቅቱ የባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ ለተወሰኑ ቀናት ሥራ በማቆሙ ጨዋታው የሚደረግበት ስታዲየም እንዲቀየር ሆነ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጠየቀው መሠረት ካፍ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ እንዲካሄድ ወሰነ። ይህም ጨዋታ ከረዥም ጊዜ በኋላ በአዲስ አበባ የተካሄደ የመጀመሪያው የካፍ ጨዋታ ለመሆን በቃ። አውሮፕላን ማረፊያው ሥራ ሲጀምር ሁሉም ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የክለቦች እና የብሔራዊ ቡድን ውድድሮች በባሕር ዳር ስታዲየም መካሄዳቸው ቀጠሉ። ባሕር ዳር ስታዲየምም ብዙ አልተጓዘም። የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር የባሕር ዳር ስታዲየም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ በማገዱ አገሪቱ መሰል ውድድሮችን ማስተናገድ እንደማትችል ተረጋገጠ። የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባሕር ዳር ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮና ውድድሮች እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ ያስታወቀው ሰኞ ነው። የባሕር ዳር ስታዲየም የጨዋታ ሜዳው እና ለጨዋታ ሜዳው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ባለማማላቱ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የቡድኖች እና የጨዋታ አመራሮች ማረፊያ ክፍሎች ስለሌሉት እና የህክምና ክፍሉ የተሟላ ባለመሆኑ እግድ ተጥሎበታል። በተጨማሪም የተመልካቾች መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ፣ የክብር እንግዶች መቀመጫ እና የመስተንግዶ አካባቢ በበቂ ደረጃ ባለመዘጋጀቱ፣ በስታዲየሙ ደረጃውን የጠበቀ የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል አለመኖር እንዲሁም የልምምድ ሜዳው በዝቅተኛ ደረጃ በመያዙ ለመታገድ እንዳበቃው ተጠቅሷል። ክልሉ ምን አለ? በአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባንተ አምላክ ሙላት ክልሉ በተቻለው አቅም ለሦስት ዓመት ከተለያዩ በጀቶች በመቀነስ ስታዲየሙን ሲያሟላ መቆየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአጭር ጊዜ ማሟላት የሚችለውን አሟልተው ጨዋታዎች መካሄድ መጀመራቸውንም ጠቅሰዋል። \"በ2013 በጀት ዓመት ክልሉ ያለበት ይታወቃል። ከአንድ ሚሊየን በላይ ሕዝብ የተፈናቀለበት እና የህልውና ዘመቻ ውስጥ በመሆናችን በጀቱ ወደዚያ በመመደቡ ክልሉ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ ገብቶ በጀት ይመደበልን ብሏል\" ሲሉ ተናግረዋል። ካለው የበጀት እጥረት በተጨማሪ አቶ ባንተ አምላክ በካፍ ግምገማ አካሄድ ላይም ደስተኛ አይመስሉም። \"የካፍ ኢንስፔክሽን ቡድን ከጉብኝቱ በኋላ የሰጡን ሃሳብ እና አገራቸው ሆነው የላኩት አስተያት የተለያዩ ናቸው። በእኛ በኩል የካፍ እና ፊፋ ዝቅተኛ መመዘኛ መሟላት አለበት የሚለውን እናምናለን። አሁን የቀረበው ግን ከዚህ በፊት ያልተካተቱ ሃሳቦችን የያዘ ነው\" ብለዋል። ለዚህም እንደማሳያ ቀደም ሲል ሙሉ መልበሻ አራት ክፍሎች አዘጋጁ ተብሎ ቢዘጋጅም አሁን እሱን ጭምር ቀይሩ መባሉን ጠቅሰዋል። የመኪና መቆሚያን በተመለከተም \"ስታዲየሙ ሲጠናቀቅ ጀምሮ አብሮ የተጠናቀቀ እና በሺህዎች የሚቆጠሩ መኪናዎቸው የሚያቆም በቂ ቦታ አለው። ይህ አስተያት ትክክል አይደለም። አንቀብልም\" ብለዋል። \"የስታዲየሙ ሁለት መለማመጃ እና ዋናው ሳር ከዚህ በፊት ምንም አስተያየት አልተሰጠውም። ያ ማለት ጥሩ ሳር ነው ማለት ነው። ይህን የሚከታተል ድርጅትም ውል ይዞ ይከታተለዋል። እዚህ ሜዳ ላይ ብዙ ውድድር መካሄዱ አይካድም። በዚህ ምክንያት ሳሩ የተወሰ መጎዳት እንጂ የሚያስቀይረው አይደለም\" ሲሉ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። በገምጋሚ ቡድኑ ቀደም ሲል የተሰጠው አስተያየት ሳሩ መጎዳት እንጂ እንዲቀየር የሚል እንዳልሆነ አቶ ባንተአምላክ አስታውሰው \"ሙሉ ለሙሉ የአውሮፓ ዘር አምጥታቸውሁ ትከሉ ነው ያሉት። በአገር ደረጃ ይህ ሊሆን አይችልም። ከዚህ ውጭ ያሉት በተባለው ጊዜ አልተሟላም። ይህም በበጀት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ነው\" ሲሉ ገልጸዋል። እንደዚህም ሆኖ ከዚህ በፊት የተሰጡ አስተያቶች ላይ ምላሽ ለመስጠት እየሠሩ መሆኑን ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ባንተ አምላክ ጠቁመዋል። \"በዚህም መሠረት ካፍ ከሰጠን የማሟላት ሥራዎች ከ70 በመቶ በላይ ሥራ ተጀምሯል እስከ በአራት ወር ውስጥ ይጠናቀቃል። የተጎዱት ሳሮችም ተከላ ተምሯል። ሳሩን በአደዲስ የማስተካከል ሥራ እየተሠራ ነው። በእኛ አቅም መሠራት ያለበትን ሥራ እንሠራለን\" ያሉት ዳይሬክተሩ ሌሎች ሥራዎችም ደግሞ የስታዲየሙ የጣሪያው ሥራ ሲሠራ አብሮ የሚሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህንን ጨምሮ ሁሉንም ሥራዎች ለማጠናቀቅ ከፌደራል መንግሥት የተጠየቀው ሁለት ቢሊዮን ብር ከተገኘ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ብለዋል። \"በካፍ አስተያት መሰጠቱ መልካም ነው። ጦርነት እና ኮቪድ ባለበት እና ሌሎች አሸዋ ላይ እየተጫወቱ ስታዲየሙ መታገዱ ተገቢ አይደለም። የተለያየ የአስተያየት መስጠትም ተገቢ አይደለም\" ብለው መንግሥትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲይደርግም ጠይቀዋል። ፌደሬሽኑስ ምን አለ? ካፍን ውሳኔ ብዙ ጊዜ ሲፈሩት የነበረው መሆኑን ጠቅሰው \"እንደማይቀር የምናውቀው ውሳኔ ነው የተወሰነው\" ያሉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና ጸሐፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ናቸው። ፌደሬሽኑ ስታዲየም እንደማይሠራ እና እንደማያስተዳደር ያስታወቁት አቶ ባሕሩ ጥላሁን ፌደሬሽኑ በተለያየ ጊዜ ስለ ስታዲየሞቹ ከካፍ የሚደርሱትን መረጃዎች ለሚመለከታቸው አካላት ሲያስተላልፍ መቆየቱን አስታውቀዋል። \"ጫናዎችን በተለያየ መንገድ ለማድረግ ሞክረናል። . . . ፌደሬሽኑ ከዚህ በላይ ማድረግ አይችልም። የራሱ ሜዳ ስለሌለው ማሳወቅ የሚገባንን አሳውቀናል። ከካፍ ጋር ደግሞ አንገት ለአንገት ተናንቀን ከዚህ በፊት እንዳንቀጣ ለማድረግ ብዙ ጊዜ ሞክረናል አሁን ግን ጠንከር አድርጎ በመሄዱ ተወስኗል\" ብለዋል። ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎችም በካፍ በኩል ስለመነሳታቸው የተጠየቁት አቶ ባሕሩ የባሕር ዳር ስታዲየም መልበሻ ክፍል የተሟላ ቢሆንም \"ካፍ የሚጠይቀው የተሟላ ብቻ ሳይሆን ምችቾት ያላቸው የመልበሻ ክፍሎችን ነው። እንደዚህ አይነት ጥያቄ የሚጠይቅ ቢሆንም አብዛኛውን ሃሳብ እንቀበላለን። ስታዲየሙ ላይ ያሉ ክፍተቶች ናቸው ብለን እንወስዳለን\" ይላሉ። የካፍን ደረጃ የሚያሟላ ስታዲየም እንዲኖር በሚሰጠው ትኩረት እና በጀት ላይ ይወሰናል ያሉት ዋና ጸሐፊው በዚህ ረገድ ከተሠራ \"ከሰባት እስከ ስምንት ወሮች\" ባለው ጊዜ ማጠናቀቅ ይቻላል ሲሉም ገልጸዋል። \"አደይ አበባ ስታዲየም ካፍን ደረጃ የሚያሟላ ነው። አደይ አበባ ስታዲም ሁለት እና ሦስት ዓመት ይፈልጋል። አዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት ላይ ነው። በቶሎ የሚጠናቀቅ ከሆነ ትልቅ ዕድል ይሆናል።\" ለዚህ ደግሞ የክልሎችን ጨምሮ የፌደራል መንግሥት ጋራ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል። እስከዚያ ግን የወንዶች ብሔራዊ ቡድን እና በአህጉር አቀፍ ደረጃ የሚካፈሉ ቡድኖች በሌላ አገር የሚጫወቱ ይሆናል። በቀጣይ ብሔራዊ ቡድኑ የት ይጫወታል ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ለኬንያ፣ ለዚምባብዌ እና ለደቡብ አፍሪካ ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል። ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ፈቃድ ሰጥተዋል። ቢዘገይም በተመሳሳይ ዚምባብዌ ጥያቄውን ተቀብላለች። \"ፌደሬሽኑ ሌላ ገቢ የለውም። ከአገር ውጪ መጫወቱም ሌላ ወጪ እንዲያወጣ ያደርገዋል። በካፍ እና በፊፋ ድጋፍ ላለ ፌደሬሽን እና ለቡድኑ ሥነልቦናም ጥሩ አይደለም። እንደ አገርም ስታዲም የለንም ብለን ወደ ሌላ አገር መሄድም የራሱ ተጽእኖ ይኖረዋል\" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ 7 ተደልድሎ ነበር። የማጣሪያ ጨዋታዎቹ ባይጠናቀቁም ቡድኑ ከወዲሁ ለዓለም ዋንጫው እንደማያልፍ ተረጋግጧል። በቀጣይ ከጋና እና ከዚምባቡዌ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ቀሪዎቹን የምድብ ጨዋታዎች ያከናውናል። በዚህም ፌደሬሽኑ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኦርላንዶ ስታዲየም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ እንደያስተናግድ መርጦታል። እንደ ፌደሬሽኑ ከሆነ ደቡብ አፍሪካ የተመረጠችው የመጨረሻ ጨዋታው ዚምባቡዌ ሐራሬ ላይ ስለሆነ የጉዞ እና ተያያዥ ወጪዎችን ለመቀነስ ነው።", "እግር ኳስ፡የቀድሞው የጋና እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚደንት የታጣለባቸው የሕይወት ዘመን እግድ ተቀነሰላቸው የቀድሞው የጋና እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚደንት ክዌሲ ንያንታኪ የተጣለባቸው የሕይወት ዘመን እገዳ ወደ 15 ዓመት ዝቅ እንደተደረገላቸው ተገለፀ። ይህ የሆነው በስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም [ካስ] ይግባኝ ከጠየቁ በኋላ ነው። ይህንንም ተከትሎም \" ክዌሴ ንያንታኪ በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍም ደረጃ ከእግር ኳስ ጋር ከተገናኙ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ከጥቅምት 29/ 2018 ጀምሮ ለ15 ዓመታት ታግደዋል\" ሲል የግልግል ተቋሙ ለቢቢሲ አስታውቋል። የቀድሞው የእግር ኳስ ፌደሬሽን ምክር ቤት አባል እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚደንት ክዌሴ፤ ጉቦ በመቀበልና በሙስና ቅሌት ሳቢያ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን (ፊፋ) ለሕይወት ዘመን የታገዱት እአአ.ጥቅምት 2018 ነበር። ካስ ሚያዚያ ወር ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎም የስዊዝ ፍርድ ቤት ጋናዊው ላይ መጀመሪያ ላይ ጥሎት የነበረው የ550 ሺህ ዶላር ቅጣትም ወደ 110 ሺህ ዝቅ ተደርጎላቸዋል። የፊፋ የሥነምግባር ኮሚቴ ውሳኔ ካሰለፈባቸው ከቀናት በኋላ ስማቸውን እንደገና ለማደስ ፍላጎት እንዳላቸው የገለፁት ክዌሴ፤ ታህሳስ 2018 ላይ ለግልግል ተቋሙ (ካስ) ይግባኝ ብለው ነበር። ክዌሲ ራሱን በደበቀ የምርመራ ጋዜጠኛ 65 ሺህ ዶላር ጉቦ ሲቀበሉ በድብቅ ተቀርፀው ነበር። 65 ሺህ ዶላር ጉቦ ሲቀበሉ የሚያሳየው ፊልም በጋና የምርመራ ጋዜጠኛ አናስ አረሜያው ነበር የተቀረፀው። ፊልሙ ክዌሴ በጋና እግር ኳስ ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ የፈለገ ባለሃብት መስሎ ከቀረባቸው ጋዜጠኛ ገንዘቡን ተቀብለው ፌስታል ውስጥ ሲከቱት ያሳያል። ከዚያም በኋላ ሚሊየን ዶላሮችን ሊያስገኝ ይችል የነበረና እአአ. ከ2005 ጀምሮ ለመሩት ለጋና እግር ኳስ ማህበር የተወሰነ ድጋፍ ( ስፖንሰርሽፕ) ወደ ራሳቸው ድርጅቶች እንዲዛወሩ ስምምነት አድርገዋል። የቢቢሲ የምርመራ ክፍል 'አፍሪካ አይ' ፊልሙን አስተላልፎት ነበር። ይህ በምዕራብ አፍሪካ እና ኬንያ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የእግር ኳስ ኃላፊዎች ከጨዋታ በፊት ገንዘብ ሲቀበሉ የሚያሳየው የምርመራ ዘገባ በቢቢሲ ከተላለፈ በኋላም ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ዘገባው የአፍሪካ እግር ኳስ ማነቆዎችን በግልጽ ያሳየ ነውም ተብሏል። ሁለት አመት የፈጀው እና ለብዙ ሰአታት የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል የእግር ኳስ ዳኞች እና ኃላፊዎች ጨዋታዎች ከመካሄዳቸው በፊት ገንዘብ ሲቀበሉ ያሳያል። ክዌሲ በወቅቱ ፊልሙ እርሳቸውን በሃሰት ለመወንጀል የተሰራ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር ። ፊልሙ በዚያው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ለሕዝብ ዕይታ ከበቃ በኋላ በአፍሪካ እግር ኳስ ሁለተኛው ተፅእኖ ፈጣሪ ሰው ከጋና እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚደንትነት ለቀዋል።", "ሱፐር ሊግ፡ የአውሮፓ ትልልቅ ክለቦች ለምን የራሳቸውን ሊግ መመስረት ፈለጉ? የአውሮፓ ትልልቅ የሚባሉት ክለቦች በአዲስ መልክ የሚቋቋመውን የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ለመቀላለቀል ተስማምተዋል። ይህ ውድድር ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና በአጠቃላይ ትልልቆቹ የዓለም እግር ኳስ ውድድሮችን የሚገዳደር ይሆናል። ለዚህ ውድድር ትልቁ መነሻ ገንዘብ ይመስላል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደሚለው ውድድሩ ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ ይሆናል። የሚሳተፉት ቡድኖችም ቢሆኑ ጠቀም ያለ ትርፍ እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች ቀላል የማይባል ጫና ደርሶባቸዋል። ለቡድኖቹ የሚጫወቱት ታላላቅ ተጫዋቾችም ቢሆኑ የሚከፈላቸው ገንዘብ ከፍተኛ ነው። ''አሁን ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የአውሮፓ እግር ኳስ አካሄድ በወረርሽኙ ምክንያት ክፉኛ መጎዳቱን ተከትሎ ነው ይህ አዲስ ሊግ የመመስረቱ ሀሳብ ወደፊት የመጣው'' ብለዋል 12ቱ መስራች ክለቦች ዕሁድ ዕለት ባወጡት የጋራ መግለጫ። ''አዲሱ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ውድድር ለክለቦች ከፍተኛ የሆነ የገቢ ምንጭ ከማስገኘቱ በተጨማሪ በረጅም ጊዜ ለአውሮፓ እግር ኳስ እድገትም ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ ይኖረዋል'' ሲል አክሏል መግለጫው። አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም በአውሮፓ ሱፐር ሊግ ለመሳተፍ የተስማሙ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቡድኖች ናቸው። ከጣልያን ኤሲ ሚላን፣ ኢንተር ሚላን እና ጁቬንቱስ ለመቀላለቀል ወስነዋል። ከስፔን ደግሞ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይቀላቀላሉ። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደገለጸው መስራች ቡድኖቹ የሳምንቱ ግማሽ ላይ ጨዋታዎቹን ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን የአገራቸው ሊግ ጨዋታ ላይ ግን መሳተፋቸውን አያቆሙም። አክሎም ''የመጀመሪያው የውድድር ዓመት እቅዱ ተግባራዊ መደረግ ሲችል ወዲያውኑ ይጀመራል። ሶስት ተጨማሪ ቡድኖች ደግሞ ሊጉን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል'' ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የወንዶቹ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ውድድር ከተጀመረ በኋላ የሴቶች ሱፐር ሊግም እንደሚጀመር ተገልጿል። እሁድ ዕለት የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ዜና መሰማቱን ተከትሎ የዩናይትግ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውሳኔውን አውግዘውታል። የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪው ፊፋ በበኩሉ ቀደም ብሎ ለመሰል ውድድሮች እውቅና እንደማይሰጥና በውድድሩ የሚሳተፉ ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫ ላይ ላይሳተፉ እንደሚችሉ አስታውቋል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ዜና ከተሰማ በኋላ ፊፋ እንደማይቀበለው አስታውቋል። ''ለእግር ኳስ ሲባል በዚህ ውሳኔ ላይ የተሳተፉት አካላት በሙል የተረጋጋ፣ ጠቃሚና ሁሉንም የሚጠቅም ውይይት ሊያደርጉ ይገባል'' ብሏል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ደግሞ በመግለጫው ''ወደፊት መስራች ክለቦቹ ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና ፊፋ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ'' ብሏል። ሊጉ 20 ተሳታፊ ብድኖችን የሚያካትት ሲሆን 12ቱ መስራች ክለቦች እና እስካሁን ስማቸው ያልተጠቀሰው ሶስት ክለቦች በፍጥነት ይቀላቀላሉ። ከአገር ውስጥ የሊግ ውድድሮች ደግሞ አምስት ቡድኖች ተወዳድረው የአውሮፓ ሱፐር ሊግን ይቀላሉ። በእቅዱ መሰረት የአውሮፓ ሱፐር ሊግ በየዓመቱ ነሀሴ ወር ላይ የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታዎቹም የሳምንቱ አጋማሽ ላይ ይደረጋሉ። ተሳታፊዎቹ 20 ቡድኖችም በሁለት ምድቦች ተከፍለው በደርሶ መልስ ጨዋታ ይፋለማሉ። በዚህ ውድድር የሚሳተፉ ክለቦች አሁን በሚሳተፉባቸው ውድድሮች ከሚያገኙት ገቢ አንጻር ይሄኛው በእጅጉ የተሻለ ገቢ እንደሚያስገኝላቸው ተገልጿል። በመጀመሪያዎቹ የውድድሩ ወራትም እስከ 10 ቢሊየን ዩሮ ድረስ ሊያስገኝ ይችላል። እንደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና የጣልያን ሴሪ አ ያሉ የአውሮፓ ሊጎች በመላው ዓለም ከፍተኛ ተከታታይ አላቸው። አዲሱ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ደግሞ የእነዚህን ሊጎች ተወዳጅነትና ገቢ እንዳይቀንሰው ተፈርቷል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርም ቢሆን እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ በአውሮፓ ሱፐር ሊግ የሚሳተፉ ተጫዋቾች ከሁሉም የአገር ውስጥ ውድድሮች ሊታገዱ እንደሚችሉ ያስታወቀ ሲሆን በአውሮፓም ሆነ በዓለም መድረክ ከብሄራዊ ቡድን ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጿል። ነገር ግን በዚህ ውድድር ለመሳተፍ የተስማሙት ክለቦች የቀረበላቸው ከፍተኛ የገቢ አማራጭ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽን ጋር ተደምሮ የማይተዉት አማራጭ አድርጎባቸዋል። መስራቾቹ ክለቦች በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት ለደረሰባቸው ኪሳራና ያላቸውን መሰረተ ልማት ለማሳደግ ከአውሮፓ ሱፐር ሊግ 3.5 ቢሊየን ዩሮ ያገኛሉ። ''12ቱ ክለቦች በዚህ ወሳኝ ሰአት አንድ ላይ የመጡት የአውሮፓ እግር ኳስን ለማዘመንና ለመቀየር ነው። የምንወደውን እግር ኳስ ቀጣይነት እንዲኖረውም ለማድረግ ነው'' ብለዋል የጣልያኑ ጁቬንቱስ እግር ኳስ ክለብ ኃላፊና የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ምክትል ሊቀመንበር አንድሪያ አግኔሊ። ምንም እንኳን የእንግሊዝ፣ ጣልያን እና የስፔን ትልልቅ ክለቦች በአውሮፓ ሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ቢስማሙም የፈረንሳይ እና የጀርመን ክለቦች ግን እስካሁን ምንም አላሉም። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በአዲስ መልክ 36 ክለቦችን የሚያሳትፍ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድርን ዛሬ ይፋ እንደሚያደርግ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን አዲሱን ሊግ የመሰረቱት 12ቱ ክለቦችን ግን በተጀመረው የለውጥ ሂደትና ፍጥነቱ ደስተኞች አይደሉም። የስፔኑ ሪያል ማድሪድ ፕሬዝደንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ የመጀመሪያው የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ኃላፊ ሲሆኑ ''በሁሉም ደረጃ እግር ኳስን እንደግፋለን'' ብለዋል። ''እግር ኳስ በዓለማችን ላይ ከ4 ቢሊየን በላይ አፍቃሪዎቹ ያሉት የስፖርት ውድድር ነው። የዚህ ስፖርት አድናቂዎችን ፍላጎትና ምኞች ማሳካት ደግሞ የእና የትልልቆቹ ክለቦች ኃላፊነት ነው።'' የጁቬንቱሱ ኃላፊ አንድሪያ አግኔሊ ደግሞ ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት እራሳቸውን ያገለሉ ሲሆን አሁን ደግሞ የአውሮፓ ሱፕ ሊግ ምክትል ሆነዋል። የማንቸስተር ዩናይትዱ ጆዌል ግሌዘር በበኩሉ '' የዓለማችንን ታላላቅ ክለቦች አንድ ላይ ማምጣትና በአንድ ሊግ ላይ እንዲወዳደሩ ማድረግ ለአውሮፓ እግር ኳስ አዲስ በር የሚከፍት ነው። በዚህ ውድድር ላይ ክለቦች የተሻለ የእግር ኳስ መሰረተ ልማት ያገኛሉ፤ መጨረሻ ላይ የሚያገኙተ ገቢም ቢሆን ጠቀም ያለ ነው'' ብለዋል። አዲሱን የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደሚቀላቀሉ የሚጠበቁት የጀርመኑ ታላቅ ክለብ ባየርን ሙኒክ እና የፈረንሳዩ ፒኤስጂ በበኩላቸው እሁድ ዕለት የአውሮፓ ክለቦች ማህበር የጠራውን ድንገተኛ ስብሰባ ተሳትፈዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአገራቸው ክለቦች እስካሁን ምንም አለማለታቸውን በጥሩ ጎን እንደሚመለከቱትና እንደሚደግፏቸው ገልጸዋል። የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰንም ቢሆኑ በዚህ ውድድር ሀሳብ እንደማይስማሙና እግር ኳስን እንደማይጠቅም አስታውቀዋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር፣ የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር፣ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ የስፔን እግር ኳስ ፌደሬሽን፣ ላ ሊጋ፣ የጣልያን እግር ኳስ ፌደሬሽን እና የጣልያን ሴሪ አ ሁሉም በአንድ ድምጽ አዲሱን ውድድር ለማስቆም በህብረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። የሊቨርፑልና የቶተንሀም የቀድሞ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የነበረው ዳኒ መርፊ ከቢቢሲ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ በአውሮፓ ሱፐር ሊግ ሀሳብ ደስተኛ አለመሆኑን ገልጿል። የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ አምበል ጋሪ ኔቪል በበኩሉ በውሳኔው ''በጣም ተበሳጭቻቸለው'' ብሏል። ሌላኛው የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ ደግሞ ውሳኔው በይበልጥ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን እንደሚጎዳ ገልጿል። የበርካታ የእንግሊዝ ክለቦች ደጋፊዎች ማህበራትም ቢሆን በውሳኔው ደስተኞች እንዳልሆኑና ቡድኖቹ ቆም ብለው እንዲያስቡበት እየጠየቁ ይገኛሉ። አሁን ላይ ግን 12ቱ መስራች ክለቦች ከዚህ በኋላ ወደኋላ የሚሉ አይመስልም። እንደውም እርስ በርሳቸው እየተደጋገፉና በቶሎ ውድድሩን ለማስጀመር ደፋ ቀና እያሉ ነው። በአሁኑ ሰአት በርካታ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርና የአገር ውስጥ ሊጎች የሚያደርሱባቸውን ጫና እና ተቃውሞ ተቋቁመው ይቀጥሉበት ይሆን? ቀሪዎቹ ሶስት ክለቦች እንማን ናቸው? ባየርን ቡኒክ እና ፒኤስጂ አዲሱን የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ይቀላቀሉ ይሆን? የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ በጉጉት የሚጠበቅ ጉዳይ ነው። ነገር ግን አሁን ላይ በአውሮፓ ሱፐር ሊግ ለመሳተፍ የተስማሙት 12ቱ ክለቦች ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ግንኙነት ስራ ይጠበቅባቸዋል። ምክንያቱም ከጅምሩ የታየው ምላሽ ተስፋ ሰጪ የሚባል አይደለምና።", "የመጀመሪያው በገመድ ላይ መረማመድ የዓለም ሻምፒዮና ተካሄደ በስዊትዘርላንድ የአልፕስ ተራራ ላይ ከመላው ዓለም የተወጣጡ ተወዳዳሪዎች ተሰባስበው የመጀመሪያውን በገመድ ላይ መረማመድ ሻምፒዮና አካሂደዋል። ከባሕር ወለል በላይ 2252 ሜትር ከፍታ ባለው የተወጠረ ገመድ ላይ በመረማመድ 31 ተወዳዳሪዎች ችሎታቸውን አሳይተዋል። በእዚህ ውድድርም በዓለም የመጀመሪያው ሻምፒዮና ለመሆን በፍጥነት መራመድን እና ትርኢት ማሳየትን ጨምሮ አስደናቂ ክንውኖች ተካሂደውበታል።", "ሴኔጋል ለእያንዳንዱ ተጫዋች ከ87 ሺህ ዶላር በላይና መሬት ሸለመች ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫን ላመጡት የብሄራዊ ቡድኗ እያንዳንዱ ተጫዋች የገንዘብና የመሬት ሽልማት ሸለመች። በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት በተካሄደው ስነ ስርዓትም እያንዳንዱ ተጫዋች ከ87 ሺህ ዶላር በላይ ሽልማትና በዋና ከተማዋ ዳካር እና በአጎራባቿ ዲያምኒያዲዮ ከተማ ውስጥ መሬት እንዲሰጣቸው ተደርጓል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ለቡድኑ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሚባለውን የክብር ሽልማት (ኦርደር ኦፍ ዘ ላየን) የሰጧቸው ሲሆን በርካታ ደጋፊዎቻቸውም ከቤተ መንግሥቱ ውጭ በደስታ ጩኸታቸውን እያሰሙ ነበር። ፕሬዚዳንቱ ቀደም ሲል ቡድኑን የአፍሪካ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረስ እና \"ለአገሪቱም ክብር እና ኩራት በማስገኘት የህዝቡን ታላቅነት አስመስክረዋል\" በሚልም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። እንዲሁም የቡድኑን አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴንም አወድሰዋል። አሊዩ ሲሴ \"ጠንክረህና ጸንተህ ከሠራህ የምትፈልገውን እንደምታገኝ ያሳያል\" ሲሉ ድሉን ገልጸውታል። \"በጣም ስሜታዊ ሆኛለሁ ምክንያቱም የሴኔጋል ህዝብ ይህን ዋንጫ ለ60 ዓመታት ናፍቋል\" ብለዋል አሰልጣኙ። ሴኔጋል በፍጻሜው ጨዋታ ግብፅን 4 ለ2 በመለያ ምት አሸንፋ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች። ጨዋታው በሁለቱ የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ እና መሐመድ ሳላህ መካከል የተደረገ ፍልሚያ ተብሎ በብዙዎች በከፍተኛ ጉጉት የተጠበቀ ነበር። ጨዋታው ያለምንም ጎል በመጠናቀቁ ነበር ወደ መለያ ምት የተሸጋገረው። ሴኔጋል ከዚህ ቀደም በሁለት የፍጻሜ ጨዋታዎች ከተሸነፈች በኋላ በመጨረሻም የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች።", "ሮሜሉ ሉካኩ፡ ቼልሲ ቤልጂየማዊውን አጥቂ ሪከርድ በሆነ በ97.5 ሚሊዮን ፓውንድ ከኢንተር ሚላን አስፈረመ ቼልሲ አጥቂውን ሮሜሉ ሉካኩን ከኢንተር ሚላን በ97.5 ሚሊዮን ፓውንድ ከኢንተር ሚላን በድጋሚ አስፈረመ። የ28 ዓመቱ ቤልጅየማዊ ከለንደኑ ክለብ እአአ በ2014 በ28 ሚሊዮን ፓውንድ ኤቨርተንን ቢቀላቀልም በድጋሚ በአምስት ዓመት ውል ስታምፎርድ ብሪጅ ደርሷል። ክፍያው ማንችስተር ሲቲ ለጃክ ግሪሊሽ ከከፈለው የ100 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ክብረወሰን በጥቂቱ ያነሰ ነው። ሉካኩ \"ብዙ የመማር ችሎታ ያለው ልጅ ሆኜ መጥቼ ነበር። አሁን ብዙ ተሞክሮ እና በበለጠ ብስለት ተመልሻለሁ\" ብሏል። \"ቼልሲን በልጅነቴ ደግፌያለሁ። አሁን ተመልሼ ብዙ ዋንጫዎችን እንዲያሸንፉ ለመርዳት መሞከር አስደናቂ ስሜት አለው።\" ብሏል ሉካኩ። ክለቦች ለሉካኩ የዝውውር ክፍያ 290 ሚሊዮን ፓውንድ ያህል በመክፈል በታሪክ ውስጥ ከማንኛውም ተጫዋች የበለጠ ብዙ ገንዘብ በአጥቂው ላይ አውጥተዋል። በብሪታንያ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ለአንድ ተጫዋች ከተከፈሉት አምስት ከፍተኛ ክፍያዎች መካከል ሁለቱ የሉካኩ ሆነዋል። የቤልጂየም የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው በሴሪአ ክለብ የተሸጠ በጣም ውድ ተጫዋች ሲሆን በ2019 ከማንችስተር ዩናይትድ በ74 ሚሊዮን ፓውንድ፤ ጣሊያን የደረሰበት ዋጋ ደግሞ በሊጉ ሦስተኛው ከፍተኛ ዋጋ የወጣበት ተጫዋች ሆኗል። በሊጉ የሚገኙ ክለቦች ከሌሎች ተጫዋቾች ጋርም ስማቸው እየተነሳ ይገኛል። ማንቸስተር ሲቲ የ28 ዓመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ ሃሪ ኬንን ከቶተንሃም ለማስፈረም 150 ሚሊየን ዩሮ ለመክፈል ተዘጋጅተዋል። አጥቂው ፕሪሚየር ሊግ ጉዞው ከተጀመረ በኋላ የወደፊት ቡድኑ የበለጠ ግልፅ እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋል። ሪያል ማድሪድ የ22 ዓመቱን ፈረንሳዊ አጥቂ ኪሊያን ምባፔን በ2022 ሲያስፈርም ፓሪስ ሴንት ዠርሜን በበኩሉ ከጁቬንቱስ የ36 ዓመቱን ፖርቹጋላዊ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶን በማስፈረም ለመተካት ይፈልጋል። ብራዚላዊው አማካይ ፊሊፔ ኩቲንሆ ከባርሴሎና ወደ ሊቨርፑል ይመለሳል ተብሎ ተጠብቋል። ብራዚላዊው ከመርሲሳይዱ ክለብ 142 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ስፔን ካመራ በኋላ ስሙ ከኤቨርተን፣ ማንቸስተር ዩናትድ፣ ቶተንሃም እና ሌስተር ጋር ሲነሳ ቆይቷል። ሊቨርፑሎች ቤልጄማዊውን አጥቂ ጄረሚ ዶኩን ከሬኔስ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል። የ19 ዓመቱ አጥቂ 38 ሚሊዮን ፓውንድ ሊጠይቅ ይችላል። የቀዮቹ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ግን ክለቡ \"ብዙ ተጫዋቾችን አይፈልግም\" ብለዋል። ሪያል ማድሪድ እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የመሃል ተከላካዩ አንቶኒዮ ሩዲገር በቸልሲ ያለውን ሁኔታ እየተከታተሉ ሲሆን የቅድመ ኮንትራት ስምምነት በጥር ወር ከ28 ዓመቱ ጋር ሊፈራረሙ እንደሚችሉም ይታወቃል። ቶተንሃሞች የቪያላሪያሉን የ24 ዓመት ስፔናዊ ተከላካይ ፓው ቶሬስን ሊያዘዋውሩ ይችላሉ። ክሪስታል ፓላስ የሃድስፊልድ ታውንን እንግሊዛዊ አማካይ ሉዊስ ኦብራይን ለማስፈረም ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ለመፎካከር ተዘጋጅቷል። የሳውዛምፕተን አሰልጣኝ ራልፍ ሃሰንሃትል በአስቶን ቪላ እና በቶተንሃም የሚፈለገውን የ26 ዓመቱን እንግሊዛዊ አማካይ ጀምስ ዋርድ-ፕሮስን ለማቆየት ቆርጠዋል። ማንችስተር ዩናይትድ የአይቮሪኮስቱን አጥቂ አማድ ዲያሎን በውሰት ሊለቅ ነው። ጁቬንቱስ አርሰናል በጥብቅ ሲፈልገው የነበረውን የ23 ዓመቱን አማካይ ማኑዌል ሎካቴሊን ከሳሱሎ ለማስፈረም ተዘጋጅቷል። ዌስትሃም ለሞሮኮው ተከላካይ ናየፍ አጉየር ያቀረበው 17 ሚሊዮን ፓውንድ በሬንስ ውድቅ ተደርጎበታል። ሊድስ ዩናይትድ የ24 ዓመቱን እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጫዋች ራያን ኬንትን ከሬጀርስ ለማስፈረም አዲስ ጥረት ሊያደርግ ይችላል። የአርሰናሉ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ የዝውውር ቀነ -ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ተጨማሪ ተጫዋች የማስፈረም ተስፋ አላቸው። የ32 ዓመቱ ስፔናዊ አጥቂ ዲዬጎ ኮስታ በታህሳስ ወር ከአትሌቲኮ ማድሪድ ከወጣ በኋላ አለመጫወቱን ተከትሎ ከአትሌቲኮ ሚኔሮ ጋር በብራዚል ሕይወቱን ሊጀምር እየተነጋገረ ነው። የባርሴሎና የ32 ዓመቱ ብራዚላዊ ግብ ጠባቂ ኔቶ በዚህ ክረምት ወደ አርሰናል በቋሚነት ሊዛወር ይችላል። የውሰት ውልም ሊኖር ይቻላል ተብሏል።", "ሊዮኔል ሜሲ የኢንስታግራም ልጥፍ እና ሌሎች የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ክብረ ወሰኖችን ሰበረ ሊዮኔል ሜሲ የአርጀንቲና ቡድን የዓለም ዋንጫን ካሸነፈ በኋላ ያጋራቸው የፎቶ ስብስቦች በኢንስታግራም ታሪክ ከፍተኛውን መወደድን [ላይክ] ያገኘ ሆኖ ተመዘገበ። የአገሩን ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ክብር ያበቃው የ36 ዓመቱ ሜሲ ያጋራቸው የኢንስታግራም የፎቶግራፍ ስብስቦች ከ60 ሚሊዮን ከሚልቁ ሰዎች መወደድን አግኝተዋል። ድንቅ በተባለው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲና ፈረንሳይን በመለያ ምቶች በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳቷ ይታወሳል። ይህ የሜሲ የኢንስታግራም ልጥፍ ከዚህ በፊት ከፍተኛውን የመወደድ ምላሽ በማግኘት ክብረወሰን ይዞ ከነበረው የእንቁላል ምስል ከአንድ ሚሊዮን በላይ በልጧል። ከሜሲ በፊት በኢንስታግራም ላይ በመወደድ ክብረወሰኑን የያዘው እንቁላል ምንም የተለየ ነገር ያልነበረው ሲሆን፣ በወቅቱ ክብረወሰኑን የያዘችውን ካይሊ ጀነርን ለመብለጥ ሰዎች ቅስቀሳ ያደረጉበት ምስል ነው። በመዋቢያ እቃ ምርቶችን የነጠጠች ሀብታም የሆነችው ጀነር ክብረ ወሰኑን ይዛ የነበረው ከአራት ዓመት በፊት ኢንስታግራም ላይ የለጠፈችው የልጇ ፎቶ ነበር። በወቅቱ ፎቶው 18 ሚሊዮን ላይኮችን አግኝቶ ነበር። በተጨማሪም ካይሊ ጀነር በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ 300 ሚሊዮን ተከታዮችን በማግኘት የመጀመሪያዋ ሴት ስትሆን፣ ሜሲም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸውን ተከታዮች አፍርቷል። ከጀነር በመቀጠል ክብረ ወሰኑን ይዞ የቆየው የእንቁላል ምስልን በኢንስታግራም ላይ በማውጣት ዝነኛ ያደረገው ማን እንደሆነ እና በፍጥነት ያን ያህል ተወዳጅነትን እንዴት ለማግኘት እንደቻለ ከግምት በስተቀር የሚታወቅ ነገር የለም። አንዳንዶች በርካታ ተከታዮችን ለማግኘት በአንድ ድርጅት የተደረገ የገበያ ማማለያ ነው ሲሉ፣ ብሪታኒያዊው የግብይት ባለሙያ ክሪስ ጎድፍሬይ ከሌሎች ጋር በመሆን የፈጠሩት እንደሆነ ይናገራል። ዋነኛ ዓላማውም የተቻለውን ያህል ላይክ እንዲያገኝ ማድረግ ነበር። በዚህ ወቅት የእንቁላሉ ምስል በአጠቃላይ 56 ሚሊዮን መወደድን በማግኘት የጀነርን ክብረወሰን ሰብሮ ይዞት ቆይቷል። አሁን ግን የዓለም ዋንጫን ድል ተከትሎ ክብረወሰኑ በሜሲ እጅ ገብቷል። ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማብቃት በኋላ የዓለም የክብረ ወሰን መዝገብ የሆነው ጊነስ በባለድሉ ሊዮኔል ሜሲ የተሰበሩ ክብረ ወሰኖችን መመዝገቡን ይፋ አድርጓል። በዚህም በጀርመኑ ሉተር ማቲያስ ተይዞ የነበረውን በበርካታ የዓለም ግጥሚያዎች በመሳተፍ ክብረ ወሰን ሜሲ ተረክቦታል። በተጨማሪም በበርካታ የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች የጨዋታዎች ኮከብ በመሆን፣ በአምበልነት በበርካታ የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች በመጫወት እና በሌሎችም ክብረወሰን እንደያዘ ተመዝግቧል።", "ድሮግባ ለአይቮሪኮስት እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ሳይመረጥ ቀረ ዕውቁ የእግር ኳስ ተጫዋች ዲዲየር ድሮግባ ለአይቮሪኮስት እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ቢወዳደርም አልተሳካለትም፡፡ ቅዳሜ ዕለት ከብዙ መዘግየት በኋላ በተደረገው ምርጫ ያሲን ኢድሪስ ዲያሎ አሸናፊ ሆኗል፡፡የቀድሞው የቸልሲ አጥቂ ድሮግባ በዚህ ውድድር ተሸናፊ የሆነው ገና በመጀመርያው የማጣሪያ ምርጫ ነው፡፡ የድምጽ ሰጪዎችን አንድ አምስተኛ እንኳ ድምጽ ማግኘት አለመቻሉ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በሁለተኛው ዙር ድምጽ አሰጣጥ የቀድሞው የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የንግድ ሰው የሆነው ዲያሎ የቀድሞ የፌዴሬሽኑን ምክትል ፕሬዝዳንት ሶሪ ዲያያባቲን 63 ለ61 በሆነ ጠባብ ልዩነት አሸንፏል፡፡ ቅዳሜ የተደረገው ምርጫ ከ2020 ዓ/ም ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲራዘም የቆየ ነበር፡፡ ይህም የሆነው የአንዳንድ እጩዎች ተገቢነት ጉዳይ ላይ ጥያቄ በመነሳቱ ነበር፡፡ ከነዚህ የተገቢነት ጥያቄ ከተነሳባቸው መካከል ዲዲየር ድሮግባ አንዱ ነው፡፡ከብዙ አለመግባባት በኋላ ፊፋ በገላጋይ ዳኝነት ገብቶ ጉዳዩን መልክ ከሰጠው በኋላና ድሮግባም ተገቢ እጩ ስለመሆኑ ካረጋገጠ በኋላ ምርጫው እንዲደረግ ሆኗል፡፡ ድሮግባ ለዝሆኖቹ ከመቶ ጊዜ በላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ይህም በ2006 እና በ2010 የተደረጉትን የዓለም ዋንጫዎች ይጨምራል፡፡ ነገር ግን በነሐሴ 2020 ድሮግባ ለፕሬዝዳንትነት እጩ መሆን እንደማይችል ተነግሮት ነበር፡፡ፊፋ በጉዳዩ ጣልቃ የገባውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ የ44 ዓመቱ ድሮግባ 4 የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎችን እና 4 የኤፍ ኤ ዋንጫ እንዲሁም ሻምፒዮንስ ሊግን ያነሳ ሥመ ጥር አጥቂ ነው፡፡ይሁንና ይህ የእግር ኳስ ጀግና ለአገሩ ፌዴሬሽን በፕሬዝዳንትነት ሲወዳደር ገና በመጀመርያው ዙር 21 ድምጽ ብቻ በማግኘት ይሰናበታል ያለ አልነበረም፡፡ ተቀናቃኞቹ ዲያሎ 59 ድምጽ ዲያባቴ 50 ድምጽ አግኝተው ነበር በማጣሪያው ምርጫ፡፡ድሮግባ ለአገሩ እግር ኳስ ማበብ ሰፋፊ መርሐግብሮችን ነድፎ በማቅረቡ ዝናው ከፍ ብሎ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ገና በአንደኛው ዙር መሸነፉ በርካታ የአገሬውን ዜጎች ሳያስቆጣ አልቀረም፡፡ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በርካታ ሰዎች ይህን ቁጣቸውን ሲገልጹም ነበር፡፡ ‹የአይቮሪኮስት እግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንቶች ድሮግባን ከዱት፤ የአገሪቱን ተስፋም አጨለሙ፡፡› ሲሉ የጻፉ ሰዎች ነበሩ፡፡አሁን በፕሬዝዳንትነት የተመረጠው ኢድሪስ ዲያሎ ለአራት ዓመታት ያገለግላል፡፡ አይቮሪኮስት ከዚህ ቀደም ለሁለት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን የበላች ሲሆን በ2023 የአፍሪካ ዋንጫን ታዘጋጃለች፡", "ብራዚል በተጫዋቿ ላይ የተፈጸመውን የዘረኝነት ጥቃት አወዘገች ከቱኒዝያ ጋር በነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ተመልካቾች አጥቂው ሪቻርለሰን ላይ ሙዝ እና ሌሎች ነገሮችን በመወርወር የዘረኝነት ጥቃት መድረሱን ብራዚል አወገዘች። ፓሪስ ላይ ለቱኒዚያ ጋር በተካሄደው ጨዋታ ብራዚል 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። የቶተንሃሙ አጥቂ የጨዋታውን ሁለተኛ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ድርጊቱ መፈጸሙ ታውቋል። ከጨዋታው በኋላ የብራዚል እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ሲቢኤፍ) ባወጣው መግለጫ “ዘረኝነትን ለመዋጋት አቋሙን እንደሚያጠናክር እና የትኛውንም ጭፍን ጥላቻ እንደማይታገስ” አስታውቋል። ከጨዋታው መጀመር በፊት ብራዚል ተጫዋቾች ዘረኝነት የሚያወግዝ መልዕክት ይዘው ነበር። የቡድኑ አባላት “ካለጥቁር ተጫዋቾቻችን ማሊያችን ላይ ያሉትን ኮከቦች አናሳካም ነበር” የሚል መልዕክት አስተላለፈዋል። የሲቢኤፍ ፕሬዝዳንት ኤድናልዶ ሮድሪጌዝ በበኩላቸው “ሜዳ ውስጥም ሆነ ከሜዳ ውጪ እንዲህ ያሉ ባህሪያት ተቀባይነት የላቸውም” ብለዋል። በጨዋታው ብራዚል በራፊንሃ ጎል ቀዳሚ ለመሆን በቅታለች። ቱኒዝያ በሞንታሳር ታልቢ ጎል አቻ በመሆን ወደ ጨዋታው መመለስ ብትችልም ሪቻርልሰን በድጋሚ ብራዚል ቀዳሚ አድርጓል። ኔይማር በፍጹም ቅጣት ምት ቡድኑ 3 ለ 1 እንዲመራ ያስቻለችውን ጎል አስቆጥሯል። ራፊንሃ ለቡድኑ አራተኛውን ለራሱ ደግሞ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሯል። 65 በመቶ የኳስ ቁጥጥር የነበራት ብራዚል አምስተኛውን ጎል በፔድሮ አማካይነት አግኝታለች። በሁለቱ አገራት መካከል ፈረንሳይ ውስጥ የተካሄደው ይህ የወዳጅነት ጨዋታ በመጪው ኅዳር ወር ኳታር ውስጥ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ዝግጀት የተደረገ ነበር። ብራዚል ከደቡብ አሜሪካ ቱኒዚያ ደግሞ ከአፍሪካ በዚህ የዓለም ዋንጫ ከሚሳተፉ ቡድኖች መካከል የሚገኙ ናቸው።", "በአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ቡድኖች የራስዎን ኮከብ ተጫዋቾች በማካተት ምርጥ ቡድን ያዋቅሩ ጥር 01/2014 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ መካሄድ የጀመረው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በርካታ ኮከብ ተጫዋቾችን ያሳተፈ ነው። ተሳታፊ አገራት በታላላቅ ሊጎች የሚጫወቱ ኮከብ ተጫዋቾችን ባሰለፉበት በዚህ ውድድር ላይ ከሚሳተፉ ተጫዋቾች መካከል የእራስዎን ኮከብ ተጫዋቾችን በማካተት ምርጥ የሚሉትን ቡድን እዚህ ይፍጠሩ። ለምርጫዎ ከሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች ተጫዎቾች የቀረቡ ሲሆን ኢትዮጵያውያንም ይገኙበታል። እስኪ የራስዎን የኮከቦች ስብስብ ቡድን ከተለያዩ አገራት ያዋቅሩ።", "የኳታር ዓለም ዋንጫ፡ የትኞቹ አገራት አለፉ? እነማንስ የማለፍ እድል አላቸው? በአውሮፓውያኑ 2022 በኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ውድድሮች ባለፈው ሳምንት ሲካሄዱ ነበር። ጥቂት የማይባሉ አገራት ከወዲሁ በዓለም ዋንጫው መሳተፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በሚቀጥሉት ወራት በሚደረጉ ጨዋታዎች ይለያሉ። የአፍሪካ አገራት በ10 ምድቦች ተደልድለው በደርሶ መልስ ጨዋታቸውን ሲያከናውኑ ነበር። እንደ ሴኔጋል ያሉ አገራት ቀድመው ማለፋቸውን ማረጋገጥ ቢችሉም ከየምድባቸው ያለፉት 10 አገራት ትናንት ምሽት በተደረጉ ጨዋታዎች እንዲሁም ዛሬና ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይለያሉ። እነዚህ ከየምድቦቹ የሚያልፉት 10 አገራት በመጪዎቹ ወራት በሚያደርጓቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አምስቱ በቀጥታ ወደ ኳታር የዓለም ዋንጫ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ። ከምድብ አንድ አልጄሪያ በ13 ነጥብ አንደኛ ስትሆን ቡርኪና ፋሶ በ11 ነጥብ ትከተላታለች። በዚህ ምድብ ነገ አልጄሪያ ከቡርኪና ፋሶ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ በጉጉት ተጠባቂ ሆኗል። አሸናፊው አገር በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ ይገባል ማለት ነው። በምድብ ሁለት ቱኒዚያና ኢኳቶሪያል ጊኒ በአምስት ጨዋታ በተመሳሳይ 10 ነጥብ አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ተቀምጠዋል። ነገ ምሽት ቱኒዚያ ከዛምቢያ እንዲሁም ኢኳቶሪያል ጊኒ ከሞሪታኒያ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ሁለቱም የማለፍ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። በምድብ ሦስት ደግሞ ናይጄሪያ ከ5 ጨዋታ 12 ነጥቦችን በመሰብሰብ አንደኛ ስትሆን ኬፕ ቬርዴ በ10 ነጥብ ትከተላታለች። ነገ ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ ሁለቱ አገራት የሚገናኙ ሲሆን አሸናፊው በቀጥታ ያልፋል። አቻ የሚወጡ ከሆነ ደግሞ ናይጄሪያ ማለፏን ታረጋግጣለች። አይቮሪ ኮስትና ካሜሩን የሚገኙበት ምድብ አራት እስከ መጨረሻው ጨዋታ ድረስ አጓጊ ነው። ምድቡን አይቮሪ ኮስት በ13 ነጥብ ስትመራ ካሜሩን ደግሞ በ12 ትከተላታለች። ነገ ምሽት አራት ሰዓት ላይ እነኚህ በአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ ስም ያላቸው አገራት ይፋለማሉ። አቻ መውጣት ለአይቮሪ ኮስት በቂዋ ሲሆን ካሜሩን ግን የግድ ማሸነፍ አለባት። በምድብ አምስት ደግሞ ማሊ ከስድስት ጨዋታ 16 ነጥብ በመሰብሰብ ወደ ጥሎ ማለፉ መቀላቀሏን ያረጋገጠች ሲሆን፤ በምድብ ስድስትም ቢሆን ግብፅ በተመሳሳይ ከ5 ጨዋታ 11 ነጥብ በመሰብሰብ ወደ ቀጣዩ ጥሎ ማለፍ ገብታለች። ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ ሰባት ጋና እና ደቡብ አፍሪካ እስከ መጨረሻው ተናንቀው የቆዩ ቢሆንም፤ ትናንት ምሽት ባደረጉት ጨዋታ ጋና አንድ ለባዶ አሸነፋለች። በዚህም ጋና ጥሎ ማለፉን መቀላቀል ችላለች። ምድብ ስምንትን ሴኔጋል በበላይነት ጨርሳለች። ከስድስት ጨዋታ 16 ነጥቦችን በመሰብሰብ በአስገራሚ አቋም የምድቡን ድልድል አሸንፋለች። በምድብ ዘጠኝም ቢሆን ሞሮኮ ከአምስት ጨዋታ 15 ነጥብ በመሰብሰብ አንድ ጨዋታ እየቀራት በበላይነት መጨረሷን አረጋግጣለች። በምድብ አስር ደግሞ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ከስድስት ጨዋታ 11 ነጥብ በመሰብሰብ በአንደኛነት አጠናቃለች። ከአውሮፓ ምድብ ሰባት አገራት ከወዲሁ በኳታር ዓለም ዋንጫ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። አገራቱም ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሰርቢያ እና ስፔን ናቸው። በዚህ ምድብ 13 አገራት ወደ ዓለም ዋንጫው የሚያልፉ ሲሆን ቀሪዎቹ አገራት ዛሬና ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች እንዲሁም በደርሶ መልስ ጨዋታዎች የሚታወቁ ይሆናል። ዛሬ ምሽት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል በምድብ ሦስት ስዊዘርላንድ ከቡልጋሪያ እንዲሁም ጣልያን ከሰሜን አየርላንድ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቁ ናቸው። ምድቡን ጣልያን በ15 ነጥብ ስትመራ ስዊዘርላንድም በተመሳሳይ 15 ነጥብ ሁለተኛ ላይ ትገኛለች። ሁለቱም አገራት የማለፍ ዕድል ያላቸው ሲሆን የዛሬ ምሽቱ ጨዋታ የመጨረሻውና ወሳኙ ነው። በምድብ ሰባት ደግሞ ኔዘርላንድስ፣ ቱርክ እና ኖርዌይ ተፋጠዋል። ኔዘርላንድስ በ20 ነጥብ አንደኛ፣ ቱርክ በ18 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ኖርዌይ በተመሳሳይ 18 ነጥብ ሦስተኛ ላይ ናቸው። ነገ በሚደረጉት የዚህ ምድብ የመጨረሻ ዙር ጨዋታዎች ኔዘርላንድስ ከኖርዌይ እንዲሁም ቱርክ ከሞንቴኔግሮ ይገናኛሉ። በምድብ ዘጠኝ እንግሊዝ እና ፖላንድ እስከመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ድረስ አንገት ለአንገት ተያይዘው ቀጥለዋል። እንግሊዝ 23 ነጥብ ያላት ሲሆን ፖላንድ በ20 ትከተላለች። ዛሬ ምሽት ፖላንድ ከሀንጋሪ እንዲሁም እንግሊዝ ከሳን ማሪኖ የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ከደቡብ አሜሪካ ማለፍ የሚችሉት አራት ወይም አምስት አገራት ሲሆኑ ከወዲሁ ማለፏን ያረጋገጠችው ግን ብራዚል ብቻ ናት። የማለፍ ተስፋ ካላቸው አገራት መካከል አርጀንቲና፣ ኢኳዶር፣ ቺሊ፣ ኡራጓይ እና ኮሎምቢያ ተጠቃሽ ናቸው። ከሰሜን እና ማዕከላዊ አሜሪካ እንዲሁም ካሪቢያን አገራት ሦስት ወይም አራት ማለፍ የሚችሉ ሲሆን እስካሁን ግን የትኛውም አገር ማለፉን አላረጋገጠም። ነገር ግን ምድቡን አሜሪካ በ14 ነጥብ እየመራች ሲሆን ሜክሲኮ በተመሳሳይ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጣ ሁለተኛ ላይ ትገኛለች። ካናዳ እና ፓናማም ቢሆኑ የማለፍ እድል አላቸው። በእስያ ምድብ አምስት ወይም ስድስት አገራት ለኳታሩ ዓለም ዋንጫ እንደሚያልፉ ይጠበቃል። ነገር ግን በዚህ ምድብ እስካሁን ከአዘጋጇ ኳታር በስተቀር ተሳትፎውን ማረጋገጥ የቻለ አገር የለም። ኢራን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሊባኖስ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ አውስትራሊያ እና ጃፓን ሁሉም የማለፍ እድል አላቸው።", "የዓለም አትሌቲክስ የለተሰንበት ጊደይን ክብረ ወሰን አጸደቀ ከአንድ ወር በፊት በሁለት ቀናት ልዩነት ውስጥ ከ15 ሰከንዶች በላይ ተሻሽሎ በኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ጊደይ እጅ የገባው የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ጸደቀ። የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል ታላቁ የኦሊምፒክ ውድድር በቶኪዮ ከተጀመረ ከቀናት በኋላ እንዳሳወቀው፤ ከአራት ዓመት በፊት በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ በኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና ተይዞ የነበረው የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በሁለት አትሌቶች በተከታታይ መሰበሩን አጽድቋል። የውድድሩ ክብረ ወሰን በቀዳሚነት በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ ዜጋ ሲፋን ሐሰን፤ ሄንግሎ ላይ ሰኔ 29/2013 ዓ. ም 29:06.82 በመሮጥ ከቀድሞው ሰዓት ላይ 10 ሰከንዶችን ያህል በማሻሻል ክብረ ወሰኑን በእጇ አስገብታ ነበር። ነገር ግን የሲፋን ክብረ ወሰን ከሁለት ቀናት በላይ ሳይቆይ ለተሰንበት ጊደይ እዚያው ሄንግሎ ውስጥ 29:01.03 በመሮጥ በአምስት ሰከንዶች አሻሽላው ክብረ ወሰኑን ተቆጣጥራዋለች። የዓለም አትሌቲክስ ተቋምም የሁለቱን ተከታታይ ክብረ ወሰኖች በይፋ ሳያጸድቀው ቆይቶ አሁን የርቀቱ ክብረ ወሰን ሆኖ መጽደቁን ዛሬ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። ለተሰንበት ባለፈው ዓመት ላይ 14:06.62 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ የዓለም የ5000 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰንን የሰበረች ሲሆን፤ በቀጣይም ሰዓቱን ከዚህም በላይ ለማሻሻል እንደምትሞክር ተናግራ ነበር። ለተሰንበትና ሲፋን ጃፓን ላይ እየተካሄደ ባለው ኦሊምፒክ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፤ በ10,000 ሜትር ውድድርም የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለማጥለቅ እንዲሁም ክብረ ወሰኑን ለማሻሻል ይፋለማሉ። ለተሰንበት በቶኪዮው ኦሊምፒክ ላይ በ10,000 ሜትር የምትወዳደር ሲሆን ሲፋን ግን ከ10,000 ሜትር በተጨማሪ በ1,500 እና 5,000 ሜትር ትወዳደራለች። የዓለም አትሌቲክስ ከለተሰንበት እና ከሲፋን ክብረ ወሰኖች በተጨማሪ በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ክብረ ወሰን ያሻሻሉትን የኬሊ ሆጅኪንሰንን፣ የግራንት ሆሎዌይን እና የካርስቲን ዋርሆልምን ክብረወሰኖች ማጽደቁን ይፋ አድርጓል።", "ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ ጂሮ ዲኢታሊያ ውድድርን በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ኤርትራዊው የብስክሌት ተወዳዳሪ ቢንያም ግርማይ ጂሮ ዲኢታሊያ የተሰኘውን ትልቅ ስም ያለው ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ዙር በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሆን ችሏል። ቢንያም ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ በሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ባጋጠመው አደጋ ምክንያት ሆስፒታል መግባቱም ተሰምቷል። የ22 ዓመቱ ኤርትራዊ ብስክሌተኛ፤ ማቲው ቫን ደር ፖል የተሰኘውን ተወዳዳሪ የመጨረሻው መስመር አካባቢ በመንደርደር ቀድሞ ነው የ10ኛውን ዙር ውድድር አሸናፊ መሆን የቻለው። ነገር ግን ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ደስታውን ሲገልጽ በሻምፓኝ መክደኛ ግራ አይኑን መመታቱን ተከትሎ መጨረሻ ላይ የተካሄደውን ጋዜጣዊ መግለጫ መታደም አልቻለም። የቡድን አጋሮቹ ግን ከሆስፒታል መልስ ደስታቸውን አብረው እንደገለጹ ተናግረዋል። ኢንተርማርቼ- ዋንቲ- ጎበርት ለተሰኘው ቡድን የሚወዳደረው ቢንያም በዚህ ዓለም አቀፍ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያ ጊዜው ነው። ውድድሩን ለማሸነፍ እስከ የመጨረሻዋ መስመር ድረስ ቢንያምን ሲፎካከረው የነበረው ሆላንዳዊው ቫን ደር ፖል መሸነፉን በማመን በእጁ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክቱን ገልጾለታል። ''ለማመን የሚከብድ ነው። እያንዳንዱ ቀን አስገራሚ ታሪኮችን ይዞ ይመጣል። ስለዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ'' ብሏል ቢኒያም ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ። ''ከውድድሩ ጅማሮ አንስቶ ምድቡን በደንብ ተቆጣጥረነው ነበር። የቡድን አጋሮቼ ያደረጉትን ነገር ሁሉ እንዴት አድርጌ እንደምገልጸው አላውቅም'' ቢንያም ባሳለፍነው ወር በቤልጂየም የተካሄደውን የጌንት-ዌል የብስክሌት የዕለት ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ከሆነ በኋላ በጂሮ ዲኢታሊያም ከባድ ተፎካካሪ እንደሚሆን ተገምቶ ነበር። ቢንያም የጌንት-ዌል የብስክሌት ውድድር የዕለት አሸናፊ በመሆን ታሪክ ከሰራ በኋላ በሰጠው ቃለ ምልልስ \"የማይታመንና የሚገርም ነው። ይህን አልጠበቅኩም ነበር\" ብሎ ነበር። አክሎም ''የመጣነው ለጥሩ ውጤት ነው። ውድድሩ አስደናቂና የማይታመን ነው\" ብሏል ቢንያም። በትናንቱ የጂሮ ዲኢታሊ ውድድር ቢንያም ለማሸነፍ ስድስት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩት በተሳሳተ መንገድ ለመሄድ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ወዲያው በመመለስ ግን ሆላንዳዊው ተወዳዳሪ ላይ መድረስ ችሏል። ''ውድድሩን ስንጀምረው የማሸነፍ ዕድል እንዳለን እናውቅ ነበር። ስለዚህ የስኬታችን ሚስጥሩ የሁሉም የቡድን አባል ጥረት፣ የቤተሰቦቼ እንዲሁም የሁሉም ነው'' ሲል ተደምጧል። ውድድሩን 2019 ላይ ያሸነፈው ሪቻርድ ካራፔዝ ባጋጠመው አደጋ ምክንያት ወደኋላ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም እስከመጨረሻው ድረስ በመታገል የመጀመሪያ አምስት ተወዳዳሪዎች ውስጥ መሆን ችሏል። ''መጨረሻ ላይ የነበረው ትንቅንቅ በጣም አስገራሚ ነበር። ይህ ድል ለቢንያም በጣም ትልቅ ነው። ምክንያቱም ያሸነፈው በዓለማችን አሉ ከሚባሉት ትልልቅ የብስክሌት ተወዳዳሪዎች መካከል አንደኛውን ነው'' ብለዋል የኢንተርማርቼ- ዋንቲ- ጎበርት ስፖርት ዳይሬክተሩ ቫሌሮ ፒቫ። ''ከጥቂት ቀናት በፊት የማሸነፍ ዕድሉ እንዳለን ተገንዝበን ነበር። ስለዚህ በዛሬው ውድድር ብስክሌተኞቹን ለማነቃቃትና ለማደፋፈር ሞክረን ነበር። በቢንያም ዙሪያ የነበረው ቡድን በታጣ አስገራሚ ነው'' አክለውም ''ይህ ትልቅ ትርጉም አለው። በብስክሌት ውድድር አሸናፊዎች ዝርዝር ውስጥ ሌላ አህጉር መጨመሩ በጣም ጠቃሚ ነው'' ብለዋል። 203 ኪሎ ሜትሮች የሚሸፍነው የውድድሩ 11ኛ ዙር ዛሬ ረቡዕ ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።", "ባራክ ኦባማ የእንግሊዙ እና የማንቸስተር ዩናይትዱን አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድን አወደሱ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ በጸረ ድህነት ዘመቻው ከባራክ ኦባማ አድናቆት ተቸረው። በዙም አማካይነት በኢንተርኔት በተካሄደው ውይይት ላይ ራሽፎርድን \"እኔ በእሱ ዕድሜ ከነበርኩበት ቀድሞ የሄደ\" ሲሉ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት አወድሰውታል። ማንቸስተር ከሚገኘው መኖሪያው ማዕድ ቤት ሆኖ በውይይቱ የተካፈለው የ23 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ከኦባማ ጋር መነጋገሩን \"የማይታመን\" ነው ብሏል። ኦባማ እንደ ራሽፎርድ ያሉና \"በማኅበረሰባቸው አዎንታዊ ተጽዕኖ ፈጣሪ\" የሆኑ ወጣቶችን ደግፈዋል። ፔንግዊን በተባለው አሳታሚ በተዘጋጀው ውይይት ላይ በቀድሞው ፕሬዝዳንት 'ማስታወሻ' ላይ በመወያየት፤ በእናት እጅ ብቻ ስለማደግ እና በማኅበረሰብ ፕሮጀክቶች ውስጥ ስለመሳተፍ ያሉት ልምዶች ተነስተዋል። 'መከራ እና እንቅፋቶች' \"በአነስተኛ ደረጃ አዎንታዊ ነገር ብታደርጉ እንኳ ለውጥ እያመጣ ነው። ከጊዜ በኋላም አዎንታዊ ነገሮችን የሚያደርጉ ሰዎች መጨመር ካለፈው ትውልድ ትንሽ እንድንሻል ያደርገናል\" ብለዋል ኦባማ። በተጨማሪም ወጣት በነበሩበት ጊዜ ፕሬዝዳንት የመሆን ተስፋ እንዳልነበራቸው ተናግረዋል። \"የበለጠ ችሎታ ቢኖረኝ ኖሮ እንደ ማርከስ ስፖርተኛ መሆን እመርጥ ነበር\" ብለዋል ኦባማ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለማርከስ ራሽፎርድ \"ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ብዙውን ጊዜ የሚጀምሩት በወጣቶች ነው\" ሲሉ ነግረውታል። የእግር ኳስ ተጫዋቹ ግን ብዙውን ጊዜ \"ድምጻቸው ምን ያህል ኃይል እንዳለው አይረዱም\" ብሏል። የህጻናትን ረሃብ ለመከላከል ከፍተኛ ዘመቻ የሚያካሂደው የማንችስተር ዩናይትዱ አጥቂ \"ፕሬዝዳንት ኦባማ ሲናገሩ ማድረግ የምትፈልገው ማዳመጥ ብቻ ነው\" ሲል ተናግሯል። \"ማለቴ ማንቸስተር ውስጥ በሚገኘው ማዕድ ቤቴ ተቀምጬ ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር እየተነጋገርኩ ነው። ግን ወዲያውኑ እንድረጋጋ አደረገኝ። በጣም የማይታመን ነው አይደል?\" ብሏል። \"ለአሁኑ ማንነታችን መፈጠር ልጆች እያለን ያጋጠሙንን ልምዶች ምን ያህል እንደሚመሳሰሉ የተረዳሁት ብዙም ሳይቆይ ነበር\" ሲል ገልጿል። የምግብ ድህነት በዚህ ሳምንት ቡድኑ ማንቸስተር ዩናይትድ በዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ መሸነፉን ተከትሎ ራሽፎርድ \"የዘረኝነት ጥቃቶች\" በማኅበራዊ የትስስር ገጾች እንደገጠሙት ሲገልጽ ቡድኑ ደግሞ \"አሳፋሪ የዘረኝነት ጥቃት\" ብሎታል። ሁለቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች በመጽሐፍትን እና በንባብ አስፈላጊነት ዙሪያ ተወያይተዋል። እናታቸው \"የንባብ ፍቅር እንደዘሩባቸው\" የተናገሩት ባራክ ኦባማ ሲሆኑ ራሽፎርድ በበኩሉ መጻሕፍት የራሱን ሃሳብ የመከተል ነፃነት እንደሰጠው ተናግሯል። \"ሰው ይህን አድርግ ያንን አድርግ ከሚለኝ ይልቅ መጽሐፍት በራሴ መንገድ እንድፈጽም ረድቶኛል\" ብሏል ራሽፎርድ። ችግረኛ ወጣቶችን የንባብ ችሎታን ለማሻሻል የእግር ኳስ ተጫዋቹ ባለፈው ዓመት የራሱን የልጆች መጽሐፍ ክበብ አቋቁሟል። ራሽፎርድ ከቴሌቪዥን የምግብ አብሳዩ ቶም ኬሪጅዝ ጋር በመሆን የምግብ ድህነትን የዘመቻው አካል በማድረግ የተመጣጠነ እና በቀላሉ የሚገኝ ጤናማ ምግቦች አዘገጃጀት ዙሪያ ምክሮችንም ይሰጣል። ራሽፎርድ በልጅነቱ ስለመራብ እና በልጅነት በነጻ የትምህርት ቤት ምገባ ላይ ጥገኛ ስለመሆን ተናግሯል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ትምህርት ቤቶች በነጻ ምግባቸው እንዲቀጥሉ ሃሳብ በማቅረብ ከመንግሥት ጋር የተሳካ ጥረት አድርጓል። የቀድሞው የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ዶሚኒክ ኩሚንግስ ለተመረጡት የፓርላማ አባላት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ \"ከራሽፎርድ ጋር ጠብ አትምረጡ\" የሚል ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።", "የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች፡ ከአሠልጣኝ እስከ ወኪል ‘የሚቀራመቱት’ የተጫዋቾች ደመወዝ አምና የቡድኑ ማገርና ምሰሶ ሆኖ ደረቱ ላይ የተለጠፈውን አርማ እየሳመ ያያችሁት ተጨዋች ዘንድሮ የተቀናቃኝ ክለቡ አምበል ሆኖ ቢያዩት ሊገርምዎት አይገባም። ምክንያቱም ይህ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ነው። በአንድ መስኮት 11 ተጫዋች ማስፈረም ከመለመድ አልፎ 17 ተጫዋቾችን ማስኮብለል አዲስ ባሕል ሆኗል። ኳስ እየተመለከቱ የጨዋታው ተንታኞች [ኮሜንታተር] ሃያ ሁለቱንም ተጫዋቾች የቀድሞ ክለባቸውን እየገጠሙ ይገኛሉ ቢልዎ አያስደንቅም። ምክንያቱም ይህ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ነው። ባለፈው ዓመት ዋንጫ ያነሳ አሊያም ሁለተኛና ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ቡድን 8 እና 9 ተጫዋቾች ሲያስፈርም፤ የክለቡ አከርካሪ የሆነውን ተጫዋች ሲሸጥ ቢያሰተውሉ ግራ እንዳይጋቡ። ምክንያቱም. . . ለዚህ አንደኛውና ዋነኛው መንስዔ ሶልዲ ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት የተጫዋቾች ደመወዝ 50 ሺህ ገባ ሲባል ብዙዎች ‘ይህ ሁላ ገንዘብ. . .’ ብለው ተደንቀዋል። ዘንድሮ 50 ሺህ ከጨዋታ በኋላ ለኪስ ተብሎ የሚሰጥ የላብ ገንዘብ መሆኑን እየሰማን ነው። የአንድ ተጫዋች ዋጋ 7 ሚሊዮን ብር ደርሷል፤ 10 ሚሊዮን ብር ያወጡም አሉ። ለመሆኑ የፕሪሚዬር ሊጉ ክለቦች ከካዝናቸው እየመዠለጡ ሚሊዮኖች የሚያፈሱት ከየት አምጥተው ነው? ተጫዋቾችስ ይህ ገንዘብ ኪሳቸው ይገባልን? በተጠናቀቀው የዝውውር መስኮት ክለቦች በርከት ያሉ ተጫዋቾች አስፈርመዋል፤ ውል አድሰዋል፤ ከታችኛው ሊግም አስመጥተዋል። ከተስፋና ከታዳጊ ቡድን ያደጉ ተጫዋቾችንም እየተመለከትን ነው። ከውጭ ሃገራት በተለይ ደግሞ ከምዕራብ አፍሪካ ሃገራት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ቁጥርም ከፍ ብሏል። በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ሊደረስበት ያልቻለው ወልቂጤ ከተማ ነው። ወልቂጤ 17 ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። ዝቅተኛው ደግሞ  [ሶስት ተጨዋቾች] ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። በቀድሞ ስሙ መከላከያ በዘንድሮው ስሙ መቻል፤ ከነዓን ማርክነህን ጨምሮ 16 ተጨዋቾችን አስፈርሟል። ይህ ሁሉ ተጫዋቾች በአንድ መስኮት አስፈርሞ እንዴት ነው ዘላቂ የሆነ ቡድን መመሥረት የሚቻለው የሚለውን ለጊዜው ወደጎን እንተውውና የተጨዋቾች ዝውውር ዋጋና ደመወዝ ላይ እናተኩር። \"ተጫዋቾቹ የሚዘዋወሩበት መንገድ ምንም ግልፅ አይደለም። የክፍያው ሁኔታ ትክክለኛ ነው ብለህ ለመገመት ትቸገራለህ\" ይላል የስፖርት ጋዜጠኛው አብረሃም ተክለማርያም ። \"አንዳንዱ የምትሰማው ክፍያ ጆሮህን ያስይዝሃል። አንድ ተጫዋች ለሁለት ዓመት 10 ሚሊዮን ብር እንደተከፈለው ሰምቻለሁ።\" በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዝቅተኛው የተጫዋች ዝውውር ቆይታ አንድ ዓመት ነው፤ ከፍተኛው ደግሞ አምስት ዓመት። ነገር ግን አንድ ተጫዋች ከዚህ በላይ በሆነ ዋጋ ሊፈርም አይችልም አሊያም ደመወዙ ከዚህ ሊያንስ ወይም ሊበልጥ አይገባም የሚል ሕግ የለም። እርግጥ ይህ አብዛኛው ዓለም የሚመራበት ሕግ ነው። ነገር ግን እግር ኳስ ተመንድጓል በሚባልበት የዓለም ክፍል ‘ፋይናንሻል ፌር ፕለይ’ የተሰኘ መመሪያ አለ። ይህ መመሪያ ዋነኛ ዓላማው ክለቦች ስኬትን ሽጠው ከገበያቸው በላይ ወጪ እንዳያደርጉ የሚያግድ ነው። ይህ ሕግ ክለቦች የፋይናንስ አዘቅት ውስጥ እንዳይገቡ የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የክለቦችን የገቢ ምንጭና ወጪ የሚቆጣጠርበት መመሪያ ይኖረው እንደሆን ግልጽ አይደለም። የተጫዋቾች ዝውውርን በተመለከተ አስተያየት እንዲሰጡን የደውልንላቸው የሊጉ አክሲዮን ማሕበር ሥራ አስኪያጅ ክፍሌ ሰይፈ \"ይህ የፌዴሬሽኑ ጉዳይ ነው\" የሚል ምላሽ ነው የሰጡን። ነገር ግን የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ‘ፋይናንሻል ፌር ፕለይ’ አሊያም የክለቦች ፍትሐዊ ወጪና ገቢን የሚቆጣጠርበት ኦፊሴላዊ መመሪያ እንደሌለው አብረሃም ይናገራል። \"ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ፋይናንሻል ፌር ፕሌይ’ በመባል የምናውቀው ሕግ የለም። ነገር ግን ለምሳሌ ‘ሳለሪ ካፕ’ የሚባል የዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ የወጣ ሕግ ነበር። ይህ ሕግ የደመወዝ ጣራ 50 ሺህ ብር እንዲሆን ወስኖ ነበር። ቅጥ ያጣ የዝውውር ገንዘብን ለመግታት በሚል ነበር ይህ ሕግ የወጣው።\" አብርሃም፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የስፖርት ኮሚሽን ባሠራው ጥናት መሠረት የኢትዮጵያ ክለቦች አጠቃላይ ዓመታዊ ወጪ ከ2 ቢሊዮን ብር እንደነበር ያስታውሳል። ጥያቄው እግር ኳስ የወጪውን ግማሽ ያህል እንኳ ገቢ እያደረገ ነው ወይ? ነው። አብርሃም ‘አይመስልኝም’ ይላል። \"ለምሳሌ በአምናው [2014] የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ተሳታፊ ከነበሩ ክለቦች ከሶስት ወይም አራት ክለቦች በቀር ሁሉም የደመወዝ ክፍያ ችግር ነበረባቸው።\" ፌዴሬሽኑ በክለቦችና በተጫዋቾች መካከል መቃቃር ሲፈጠር ከማደራደር በቀር ሌላ ምንም ሥልጣን እንደሌለው አብረሃም ይናገራል። ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን ፌዴሬሽኑንም ሆነ ፕሪሚዬር ሊጉን ጠንቅቀው ከሚያውቁ ሰዎች አንዱ በዚህ ይስማማል። የተጫዋቾች ደመወዝ 50 ሺህ ብር በነበረበት ወቅት \"ትላልቅ የሚባሉ ተጫዋቾችን ጨምሮ ብዙዎች በጎን ተጨማሪ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር\" ይላል። \"50 ሺህ ብሩን ፌዴሬሽኑ ያፀድቅልሃል። ለምሳሌ ይህን ያህል ጎል ካስቆጠርኩ ይህን ያህል ይከፈለኛል የሚል ካለም ፌዴሬሽኑ ያፀድቃል። ነገር ግን ተጨዋቹና ክለቡ ከዚህ ውጭ ሌላ ድርድር ያደርጋሉ። 200 እና 300 ሺህ የሚበሉ ነበሩ።\" በክለቡና ተጫዋቹ መካከል አለመግባባት ሲኖር ግን ፌዴሬሽኑ ከማደራደር ውጭ ምንም ማድረግ እንደማይችል ይናገራል። ለዚህም ነው አንዳንድ አለመግባባቶች ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት የሚሄዱት ሲል ያስረዳል። በቀደመው ግዜ፤ ማለትም የተጫዋቾች ደመወዝ 50 ሺህ ብር በነበረበት ወቅት አንዳንድ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው ብድር ይሰጡ እንደነበር ይህ ውስጥ አዋቂ ይናገራል። \"ለምሳሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፊርማው ገንዘብ የተወሰነውን በብድር መልክ ይሰጥ ነበር።\" ዘንድሮስ? የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ  አሁን አሁን ግን አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ሙሉውን ገንዘብ ቀድመው ይቀበላሉ። ከዚያ በየወሩ የሚደርሳቸው ድጎማ [ኢንሴንቲቭ] ነው።\" ‘ከፌዴሬሽኑ ጋር ተጋጭቼ ክለቤ እንዲጎዳ አልፈልግም’ ብለው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን የክለብ ሥራ አስኪያጅ \"አሠራሩ [ከፍተኛ ክፍያው] ትክክል አለመሆኑን ሁሉም ሰው ያውቀዋል\" ይላሉ። \"የፕሪሚዬር ሊግ አክሲዮን ማሕበሩ በጠራው ስብሰባ ላይ ይህን ሐሳብ አንስተናል። ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁ ዓመቱ ሲጀምር ገንዘባቸውን ያገኛሉ። እኛ ደግሞ በየወሩ ለተጫዋቾች ደመወዛቸውን እንከፍላለን።\" አብርሃም፤ ከታችኛው ሊግ ወደ ፕሪሚዬር ሊግ የሚመጡ ተጫዋቾች እንዲሁም ከተስፋና ታዳጊ ቡድን የሚያድጉ ተጫዋቾች የሚያገኙት ደመወዝ አነስተኛ ነው ይላል። ይህን ለማጣራት በቅርቡ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ካደጉ መካከል ወደ አንዱ ክለብ ሥራ አስኪያጅ ስልክ ደወልን። ስማቸው ይፋ እንዳይሆን የጠየቁን ሥራ አስኪያጁ \"አዎ እውነት ነው\" ይላሉ። \"በጣም ዝቅተኛ ደመወዝ ከሚከፍሉት መካከል ነው የኛ ክለብ። ግን ምን ማድረግ እንችላለን\" ሲሉ ሥራ አስኪያጁ ምሬታቸውን ያሰማሉ። \"የሌሎቹ ክፍያ ከፍ ማለቱ ይጎዳናል? አዎ ይጎዳናል። 300 እና 500 ሺህ ለጠየቀ ሁሉ ከፍለን የማይሆን ነገር ውስጥ መግባት አንፈልግም። እኛ የማንቀበለው፤ የማንጓዝበት ራሱን የቻለ ሚስጥር አለው ይህ ክፍያ። እንጂ ተጫዋቹ ያን ሁሉ ገንዘብ ያገኘዋል ብለህ አትጠብቅ።\" ተጫዋቹ ሙሉውን ገንዘብ ካላገኘው ማነው ተጠቃሚ? በተጫዋችነት ዘመኑ ለኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ለብሔራዊ ቡድኑ የተሰለፈው ኤፍሬም ወንድወሰን አሁን የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማሕበር ምክትል ፕሬዝደንት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። \"እግር ኳሱ እያደገ በመምጣቱ የገንዘብ መጠኑም ከፍ ብሏል\" ይላል ኤፍሬም። \"እግር ኳስ እንደ በፊቱ በሳምንት ሁለትና ሶስት ቀን የሚሠራ ሳይሆን የሙሉ ጊዜ ሥራ ሆኗል። እግር ኳሱ በዚህ ደረጃ አድጓል አላደገም ሌላ ጥያቄ ነው።\" የተወሰኑ የክለብ አመራሮች፣ የተወሰኑ አሠልጣኞች እና በመሃል ባሉ ሰዎች ምክንያት ተጫዋቾች የሚገባቸውን ገንዘብ እያገኙ እንዳልሆነ ተጫዋቾቹ ይነግሩናል ይላል ኤፍሬም። \"ማስረጃ አምጡልን፤ የሕግ ባለሙያ ስላለን ድጋፍ እናደርጋለን ስንላቸው ግን ፈቃደኛ አይሆኑም። ፈሪ ሆነህ እንድትጫወት ነው የሚፈለገው።\" ኤፍሬም ተጫዋቾቹ ጉዳዩን ቢያጋልጡ ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ ይላል። \"ከአንድ ክለብ አሠልጣኝ ጋር ካልተስማማህ ወደሌላ ክለብ እንዳትሄድ ትደረጋለህ። ብትጎዳም ቤተሰብ አለብኝ፣ ቤት ኪራይ ደርሶብኛል ብለህ አንገትህን ደፍተህ እንድትጫወት ትደረጋለህ። ምክንያቱም ክለቦችና አሠልጣኞች እንዲሁም በመሃል ያሉ ሰዎች ይተባበሩብሃል።ተጫዋቾች የሚገባቸውን ገንዘብ አለማግኘታቸው ልናጠራው ያልቻልነው እንቆቅልሽ ሆኖብናል።\" አብርሃምም በጋዜጠኝነት ዘመኑ እንዲሁ ተጫዋቾች በደል ደርሶብናል ብለው ነግረውት ነገር ግን ጉዳዩን አደባባይ ለማውጣት ሳይችሉ እንደቀሩ ያስታውሳል። \"እከሌ የሚባል አሠልጣኝ ይህን ያህል ገንዘብ ተቀብሏል፤ እከሌ ለሚባል ሥራ አስኪያጅ ይህን ያክል ገንዘብ ሰጥተነዋል ይሉናል። ይህ መረጃ ነው። ማስረጃ ለምሳሌ ባንክ ያስገቡበት ደረሰኝ ስትላቸው ያንን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም። እኔ እንኳ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ቴሌቪዥንም ራድዮም ላይ ላቀርባቸው ተቀጣጥረን የጠፉብኝ አሉ።\" ውስጥ አዋቂ ምንጫችንም በአንድ ስብሰብ ላይ የተጫዋቾች ማሕበር ፕሬዝደንት [ዮሃንስ ሳሕሌ] \"ተጫዋቾቹ ገንዘቡን አያገኙትም ሲሉ ሰምቻለሁ\" ይላል። \"ይታወቃል እኮ\" ይላል ምንጫችን። \"አንድ ተጫዋች ሲሰጥ ነው የሚሳካለት። ለአሠልጣኙ ደመወዙን ሰጥቶ ነው የሚገባው። ከአንድ አሠልጣኝ ጋር ክለብ የሚቀያይሩ ብዙ ተጫዋቾች የምታየው ለዚህ ነው። ብቃቱ ጥሩም ይሁን፤ አይሁን ተጨዋቹ አብሮት ይዞራል። አሠልጣኝ፤ የቡድን አመራር. . . ሁሉም ተነካክቷል።\" የተጫዋቾች ማሕበር ምክትል ፕሬዝደንት ኤፍሬምም ይህ እውነት ነው ይላል። \"ይህን ያህል ለአሠልጣኝ፤ ይህን ያህል ደግሞ ለኔ ትሰጠኛለህ ተብሎ ቅድመ ክፍያ ሁሉ ይፈፀማል። ነገር ግን ቀጥታ ሳይሆን በወኪሎች አማካኝነት ነው የሚነግረው።\" ፌዴሬሽኑ ይህን ለመግታት ከጥቂት ጊዜ በፊት ፈቃድ ላላቸው ወኪሎች ብቻ ፈተና አዘጋጅቶ እንደነበር ውስጥ አዋቂው ለቢቢሲ ይናገራሉ። አልፎም እያንዳንዱ ተጫዋች ወኪል እንዲኖረው የሚል መመሪያ አውጥቶ እንደነበር ያስታውሳል። ይህ የፊፋ መመሪያ እንደሆነም ይጠቁማል። \"ፌዴሬሽኑ ሕግ ለማውጣት ጎበዝ ነው። ነገር ግን የሚቆጣጠርበት መንገድ የለውም። ለምሳሌ በቅርቡ በተዘጋው የዝውውር መስኮት ወቅት የወኪሎች ፈተና አልነበረም።\" አብረሃም፤ በተለይ የከነማ/ከተማ አስተዳደር ክለቦች ከገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ብዙ ጊዜ ስማቸው እንደሚነሳ ይናገራል። በቅርቡ ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ያደገው ክለብ ሥራ አስኪያጅም ይህን ይላሉ። \"በደመወዝ አከፋፈል ከከተማ ቡድኖች ጋር መወዳደር የማይታሰብ ነው።\" \"እስከ ዓመቱ መጨረሻ መክፈል ይችላሉ ወይ? እሱ ሌላ ጥያቄ ነው። 3 እና 5 ሚሊዮን ብር እየከፈልክ ውጤት ማምጣት ትችላለህ። እኛ ግን በዚህ እንመራም።\" አብረሃም እንደሚለው የከተማ አስተዳደር ክለብ የቦርድ አባላት የሚታሙበት ሌላኛው ጉዳይ የሚፈልጉት ተጫዋች እንዲመጣ የሚያሳድሩት ጫና ነው። \"አንዳንድ ጊዜ የማይጠቅማቸው ተጫዋች በ6 እና 7 ሚሊዮን ብር ወደ ክለባቸው ይመጣና እነሱ በመሃል ገንዘብ ያገኛሉ\" ይላል። \"ይህንን የሚያሳልጡት እነማን ናቸው ካልከኝ አንደኛው የተጫዋቹ ‘ኤጀንት’ [ወኪል] ነው፤ ቀጥሎ ደግሞ ወኪሉንና ክለቡን የሚያገናኝ ደላላ አለ። አሠልጣኝ አሊያም የቴክኒክ ዳይሬክተር፣ የክለብ ሥራ አስኪያጅ ወይም ደግሞ የክለቡ የበላይ ጠባቂ ሊሆን ይችላል።\" ለመሆኑ እነዚህ ክለቦች የገንዘብ ምንጫቸው ምንድን ነው? ገቢና ወጪያቸውን የሚቆጣጠረውስ ማን ነው? \"ገቢህን እኮ የምታውቀው አንድ ነገር ወደ ገበያ ይዘህ ስትወጣ ነው\" ይላል አብራሃም። አብረሃምም ሆነ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን ምንጫችን እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች በውል የሚታወቅ ገቢ ከዲኤስቲቪ የቴሌቪዥን መብት ሽያጭ የሚያገኙት ገቢ ነው። \"የዲኤስቲቪ ገቢ ከ9 ሚሊዮን ጀምሮ እንደየደረጃቸው የሚከፋፈል ነው። ከዚያ በተረፈ ግን እንኳን የከተማ አስተዳደርና የከነማ ቡድኖች ይቅርና ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና እንኳ በጀታቸው አይታወቅም\" ይላል አብረሃም ተክለማርያም። እንደምሳሌ ኢትዮጵያ ቡናን ያነሳል። ክለቡ ከስፖንሰሮች እንዲሁም ከሌሎች ምንጮች በገንዘብና በዓይነት በሚያገኘው ገቢ ብቻ እንደማይመራ ግልጽ ነው ይላል። \"ለምሳሌ የተጫዋቾች ክፍያን ተመልከት። በዚህኛው የዝውውር መስኮት 12 ገደማ ተጫዋቾች ናቸው የፈረሙት። ደመወዛቸውን ብትደምረው በጣም ብዙ ነው። የኦፕሬሽን ወጪ አለ፤ የጉዞ ወጪ አለ፤ የሚያርፉበት ቦታ ክፍያ አለ፤ ድጎማ አለ። ይህ ወጪ ከስፖንሰርና ከቡና ላኪዎች ብቻ በሚገኝ ገቢ የሚሸፈን አይደለም።\" ስሙን የማንጠቅሰው ምንጫችንም እንዲሁ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሲዳማ ቡናና ወላይታ ድቻን የመሳሰሉ ቡድኖች የገቢ ምንጫቸው ቢታወቅም ወጪያቸው ግን የትየለሌ እንደሆነ ይናገራል። \"በቅርቡ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ የመጣው ወልቂጤ የከተማ አስተዳደሩ እኔ አልችልም በማለቱ ድጋፍ የሚደረግለት በፕሬዝደንቱ ነው። ፕሬዝደንቱ ገንዘብ ስላላቸው ክለቡ ውጥንቅጥ ውስጥ ሲገባ ከኪሳቸው እያወጡ ብዙ ጊዜ ከፍለዋል።\" ወልቂጤ በቅርቡ በተገባደደው የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት አንጋፋው አሥራት መገርሣን ጨምሮ 17 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። \"ክለቦች እንደምናስበው ወረቀት ላይ ያለው ‘ፋይናንሻል ስትራክቸር’ የላቸውም። የከተማ አስተዳደር ክለቦች ሲቸግራቸው ክልሉን ይጠይቃሉ።\" አብረሃም የክልል ክለቦች መሠረታዊ ገበያ ከከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች የሚያገኙት ገንዘብ እንደሆነ ይጠቁማል። ድሬዳዋ፣ ፋሲል፣ አርባ ምንጭ. . . ከከተማ ነዋሪዎችና ከደጋፊዎች የተወሰነ ገንዘብ እንደሚያገኙ ይናገራል። \"ምን ያክል ሰብስበው በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ አውለዋል? አይታወቅም። የኛ ሃገር ክለቦች ስካፍርና ‘ሬፕሊካ’ ማሊያ ነው እንጂ ሌላ ለገበያ ይዘው የሚወጡት ነገር የላቸውም።\" የመንግሥት ቡድን የሆኑት እነ ኢትዮ ኤሌክትሪክና መድህን በጀታቸውን የሚያገኙት ከመንግሥት ካዝና እንደሆነ ይታወቃል። ምንጫችን እንደሚለው ከዲኤስቲቪ ከሚገኘው ገቢ 85 በመቶው ለክለቦች የሚከፋፈል ነው። 50 በመቶውን እኩል ይከፋፈሉትና የቀረው ደግሞ እንደወጡበት ደረጃ የሚሰጣቸው ይሆናል። የዳኛ፣ የጨዋታ አመራር. . . የመሳሰሉትን ወጪዎች የሚሸፍኑት ከዚህ ገቢያቸው እንደሆነ የሚናገረው ምንጫችን አንድ ዳኛ በጨዋታ 3 ሺህ፣ የቀን አበል 2 ሺህ፤ በጠቅላላ 5 ሺህ ብር እንደሚያገኝ ነግሮናል። ምንጫችን አክሎ ፌዴሬሽኑ ክለቦች ገቢና ወጪያቸውን በኦዲተር አስመዝግበው እንዲያመጡ መመሪያ ቢያስቀምጥም አብዛኛዎቹ ክለቦች ይህን ማድረግ አልቻሉም ይላል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን የክለብ ሥራ አስኪያጅ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የራሱን ቁጥጥር ማድረግ አለበት ይላሉ። የተጫዋቾች ማሕበር ምክትል ፕሬዝደንቱ ኤፍሬም፤ \"አብዛኛዎቹ ክለቦች በልምድ እንጂ በዕውቀት ስለማይመሩ ነው ይህ ችግር የተባባሰው\" ይላል። አብረሃም ደግሞ ፌዴሬሽኑ፣ ክለቦች፣ ደጋፊዎች. . . ሁሉም ይመለከተዋል ባይ ነው።", "''ለ 12 ዓመታት ባልተደፈረው ቦክስ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ መወከል እፈልጋለሁ'' ተመስገን ምትኩ ተመስገን ምትኩ ይባላል። ባሳለፍነው ዓመት የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን ባዘጋጀው የቦክስ ክለቦች ሻምፒዮና በ75 ኪሎ ግራም አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን የዓመቱ ምርጥ ቦክሰኛ ተብሎም ተመርጧል። ገና የ22 ዓመት ወጣት ነው። በቅርቡ ሃገሩን ወክሎ ኦሎምፒክ ላይ እንደሚሳተፍ ተስፋ ተጥሎበታል። 2005 ዓ.ም. ክረምት ላይ በታላቅ ወንድሙ ገፋፊነት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ወጣቶች ማዕከል ቦክስ የጀመረው ተመስገን ከቦክስ ይልቅ ለቴኳንዶ ፍቅር እንደነበረው ይገልጻል። • የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? • “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር ''ሰፈር ውስጥ አስቸጋሪ ልጅ ስለነበርኩ ወንድሜ ቦክሱንም እየሰራሁ ስነምግባሬም እንዲስተካካል በማሰብ ቦክስ ወስዶ አስመዘገበኝ።'' ክረምቱ መጨረሻ ላይ የውድድር ዕድል አግኝቶ አሰልጣኙ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳለው ሲጠይቁት በደስታ ነበር የተቀበለው፤ ተመስገን። ''ድፍረትና ከነበሩት ልጆች የተሻለ ጉልበት ስለነበረኝ ለግጥሚያው ተስማማሁ። ነገር ግን ብዙም ልምድ ስላልነበረኝ በዝረራ ተሸንፌ ወጣሁ። በጣም እልህ ይዞኝ ስለነበር ያሸነፈኝን ልጅ መልሼ ለማግኘት ስል በቦክሱ በርትቼ ቀጠልኩበት።'' ምንም እንኳን በዝረራ ያሸነፈውን ቦክሰኛ ለመግጠም ብሎ በቦክሱ ቢቀጥልም ጭራሽ ክረምቱ ሲያበቃ ሁለቱም በተመሳሳይ ክለብ ውስጥ ተቀጠሩ። በወቅቱ በ57 ኪሎ ይወዳደር የነበረ ሲሆን በ60 እንዲሁም በ 63 ኪሎም ጭምር ተወዳድሯል። የቀድሞው ኒያላ የአሁኑ ማራቶን ክለብ ተወዳዳሪው ተመስገን በ 2006 ዓ.ም. የክፍለ ከተማዎች ውድድር አሸናፊ በመሆን አዲስ አበባን ወክሎ አዳማ ላይ በተካሄደው የሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶች ውድድር ተካፈለ። በውድድሩም በ 63 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ተመስገን የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያውን ማግኘት ችሏል። በ2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው 'ሴሚ ፕሮፌሽናል' (የከፊል ፕሮፌሽናል) ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው ተመስገን በ 64 ኪሎ ግራም ወርቅ ሜዳሊያ አገኘ። በተመሳሳይ ውድድር 2010 ዓ.ም. ደግሞ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ። የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን በዓመት አራት ጊዜ የሚያዘጋጀው ብሄራዊ የክለቦች ሻምፒዮና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ይካሄዳሉ። በ2011 ዓ.ም ድሬዳዋ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ዙር ውድድርም ተመስገን በ63 ኪሎ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነበር። ሁለተኛው ዙር ወላይታ ላይ ተካሂዶ እዛም ተመሳሳይ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘ ሲሆን በደሴ በተካሄደው ሶስተኛው ዙርም አሸናፊ በመሆን ጨርሷል። የዓመቱ የመጨረሻውና አራተኛው የአዲስ አበባ ክለቦች አቋም መለኪያ ላይ ደግሞ አሁንም የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት ያለመሸነፍ ጉዞውን ቀጠለ። በሀገር ውስጥ ውድድሮች ሁሉንም በሚባል ደረጃ አብዛኛውን በድል ማጠናቀቅ የቻለው ተመስገን በአፍሪካና በዓለም ደረጃ ሃገሩን የመወከል እድሎችንም አግኝቷል። 2010 ዓ.ም. ላይ በአፍሪካ ምድብ ሞሮኮ በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ሀገሩን ወክሎ በመሳተፍ ሶስተኛ ወጥቶ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚም ነበር። በዚሁም ሃንጋሪ ለሚካሄደው የዓለም ወጣቶች ውድድር አለፈ። ነገር ግን ከውድድሩ በኋላ አንድ ያልጠበቀው ነገር ተፈጠረ። የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን በወቅቱ በጀት የለኝም በማለት ተመስገን ወደ ሀንጋሪ እንደማይሄድ ተነገረው። '' ሀገሬን ወክዬ ውጤት እንደማመጣ እርግጠኛ ነበርኩ፤ የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር እሱን ማሳካት አለመቻሌ ነው። እርግጠኛ የሆንኩበት ምክንያት በሞሮኮው ውድድር በትንንሽ ስህተቶች ነበር የተሸነፍኩት። ከአብዛኛዎቹ ተወዳዳሪዎች የተሻልኩ ነበርኩኝ፤ ነገር ግን ሀገር ውስጥ ብቻ ካገኘሁት ስልጠና አንጻር ብዙ የዓለማቀፍ ህጎችን ስለማላውቅ አንደኛ መውጣት አልቻልኩም።'' ላለፉት 12 ተከታታይ ዓመታት ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ በቦክስ የሚወክላት አላገኘችም። ተመስገን ምትኩ ግን ያሉበትን ማጣሪያዎች በድል አጠናቅቆ ሀገሩን በቦክስ ወደ ኦሎምፒክ መድረክ መመለስ እንደሚፈልግ ይናገራል። እስከዛሬ በሄደባቸው ውድደሮችና ስልጠናዎች በሙሉ ብዙ ታዳጊ ልጆች ከፍተኛ የሆነ ተፈጥሮአዊ አቅም ቢኖራቸውም የሚያገኙት ስልጠና ግን ከልምድ የመጣ ብቻ እንደሆነ ተመስገን ያስረዳል። ''በተፈጥሮ ያገኙት አካላዊ ብቃት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መዳበር ሲገባው እንደነገሩ ስለሆነ ስልጠና የሚሰጣቸው፤ በዓለማቀፍ ደረጃ መፎካከርም ሆነ ብቃታቸውን ማሳደግ አይችሉም።'' ይላል ከዚህ በተጨማሪም በጣም ከባድ ስልጠናዎችን ከሰሩ በኋላ የሚያገኙት ምግብ ለሰውነት ግንባታ የማይጠቅምና የላብ መተኪያ እንኳን አለመሆኑ ችግር እንደፈጠረባቸው ያስረዳል። በአሁኑ ሰአት ለብሄራዊ ቡድን ሲመረጡ በቀን ሶስት ጊዜ ስልጠና የሚሰሩ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ስልጠና ሶስት ሰአት የሚፈጅ ሲሆን ከሌሊቱ 11 ሰአት፣ ጠዋት ሶስት ሰአት እና ከሰአት በኋላ ዘጠኝ ሰአት ላይ ስልጠናቸውን ይሰራሉ። ''ነገር ግን ከስልጠና በኋላ እዚህ ግባ እንኳን የማይባል ወጥ ነው የሚቀርብልን። ያው ሁሌም በጀት የለንም ነው የምንባለው። እንደዚህ ደክመን ሰልጥነን ተገቢውን ምግብ ካላገኘን እንዴት ነው ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር መፎካካር የምንችለው?'' በማለት ይጠይቃል። ከዚህም በተጨማሪ በብሄራዊ ቡድን ደረጃም ሆነ በክለብ ስልጠና የሚሰሩበት ቦታ አዳራሽ ብቻ እንጂ ተገቢው የስልጠና መሳሪያዎች እንኳን ያልተሟሉለት እንደሆነም ተመስገን ይናገራል። ''ሌላው ቀርቶ ፌደሬሽኑ ለስልጠና ጓንት ብቻ ነው የሚያቀርብልን። እንደ ቁምጣ እና ሌሎች ትጥቆችን የምናሟላው በራሳችን ነው። አንዳንዴም ባለን ልብስ ስልጠና እንሰራለን።'' በማለት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ይናገራል። • በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ ተመስገን ሌላው በኢትዮጵያ ያለውን የቦክስ ስፖርት ወደኋላ እየጎተተው ያለው የዳኝነት ችግር እና ከክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንደሆኑ ያስባል። ''ዳኞች ተገቢውን ዓለማቀፍ ስልጠና አያገኙም፤ ከዚህ በተጨማሪም የማዳላት ነገር ይስተዋላል። በሌላ በኩል አድካሚ ስልጠና ለሚሰሩ ቦክሰኞች የሚቀርበው ክፍያ በጣም ትንሽ ነው።'' ይላል። በብሄራዊ ቡድን ደረጃ እንኳን ምንም አይነት ክፍያ እንኳን እንደሌለ የሚገልጸው ተመስገን ሃገር ወክለው በውጪ ሃገራት የሚሳተፉ ቦክሰኞች ምናልባት እስከ 5 ሺ ብር የሚደርስ ለተሳትፎ እንደሚሰጣቸው ያስታውሳል። ተመስገን በ 2020 በጃፓን አዘጋጅነት ለሚካሄደው ኦሎምፒክ ሀገሩን ወክሎ ለመሳተፍ በደቡብ አፍሪካና በካሜሩን የኦሎምፒክ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ይጠብቁታል። ተጋጣሚዎቹን በማሸነፍ በቦክስ ውድድር ሀገሩን በኦሎምፒክ ለመወከል ተስፋ ሰንቆ በአሁኑ ሰአት ስልጠናውን እያከናወነ ይገኛል።", "ራልፍ ራንኚክ፡ አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ ጊዜያዊ አሠልጣኝ ማናቸው? የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ራልፍ ራንኚክን በጊዜያዊ አሠልጣኝነት ሊቀጥር ከጫፍ ደርሷል። የ63 ዓመቱ ጀርመናዊ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቡድኑን ማሰልጠን የሚያስችላቸውን ውል ለመያዝ ከጫፍ ደርሰዋል። ራልፍ ቀጣይ እሑድ ዩናይትድ ከቼልሲ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በሥራ ፈቃድ ምክንያት መታደም ባይችሉም ከሚቀጥለው ጨዋታ በኋላ ኃላፊነት ይወስዳሉ። ዩናይትድ ከራልፍ ጋር ስምምነት ቢደርስም አሁን በስፖርትና ዕድገት ኃላፊነት ከሚሠሩበት ሎኮሞቲቭ ሞስኮው ጋር መስማማት ይቀረዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ለሶስት ዓመታት ያክል ቡድኑን አሠልጥኖ ውጤት ማምጣት ካልቻለው ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ጋር ከተለያየ በኋላ ነው ራልፍ ለመቀጥር የተስማማው። ራንኚክ ከሻልከ ጋር በፈረንጆቹ 2011 የጀርመን ዋንጫ ያነሱ ሲሆን አርቢ ሊፕዚክን ደግሞ ከሁለት ዓመት በፊት ለፍፃሜ አድርሰዋል። ጀርመናዊው አሠልጣኝ በ2010/11 የእግር ኳስ ዘመን ሻልከን ይዘው ለቻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ቢደርሱም ከዩናይትድ ጋር በነበራቸው የደርሶ መልስ ጨዋታ 6-1 ተሸንፈው መውደቃቸው አይዘነጋም። ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው ፕሪሚዬር ሊግ ሰንጠረዥ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በ1999 ቻምፒዬንስ ሊግ ፍፃሜ ለዩናይትድ ዋንጫ ያስገኘች ጎል ያስቆጠረው ሶልሻዬር ከአሠልጣኝነቱ የተሰናበተው በዋትፈርድ 4-1 ከተሸነፈ በኋላ ነው። የክለቡ የቀድሞ አማካይና የኦሌ ረዳት አሠልጣኝ የነበረው ማይክል ካሪክ ቡድኑን በጊዜያዊነት እየመራ ይገኛል። በማይክል ካሪክ የተመራው ዩናይትድ በቻምፒዬንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ቪላሪያን 2-0 በመርታት የምድቡ አንደኛ ሆኖ ማለፉን አረጋግጧል። ራንኚክ፤ ስቱትጋርት፣ ሃኖቨር፣ ሆፈንሃይም፣ ሻልከና ሊፕዚክን አሠልጠናዋል። በዚህ በጀርመን እግር ኳስ ስማቸው ተደጋግሞ ይነሳል። ከዩናይትድ ጋር በሳምንቱ መባቻ ንግግር ያደረጉት ራንኚክ ከቡድኑ ጋር የስድስት ወራት የጊዜያዊ አሠልጣኝነት ውል የሚገቡ ሲሆን ቡድኑ ቋሚ አሠልጣኝ ከቀጠረ በኋላም በቴክኒካል አባልነት ሊቆዩ ይችላሉ። የእግር ኳስ ተንታኞች ዩናይትድ ሰውዬውን ማምጣቱ ተገቢ ነው፤ ቋሚ አሠልጣኝ ፈልጎ ለመቅጠርም ዕድል ይሰጣል ይላሉ። ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ የዩናይትድ ቀዳሚ የአሠልጣኝ ምርጫ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ነገር ግን ከፒኤስጂ ጋር ያልተቋጨ ውል ያለው ፖች ወዲያውኑ ላይገኝ ይችላል የሚል ስጋት አለ። ዩናይትድ እሑድ አመሻሹን ከቼልሲ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በማይክል ካሪክ እየተመራ እንደሚፋለም ታውቋል። ራንኚክ ከአሁኑ የቼልሲ አሠልጣኝ ቱኽል ጋር አብረው የሠሩ ሲሆን የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕም የሳቸው የጨዋታ ፍልስፍና ውጤት ናቸው ይባላል።", "የዝነኛው ቅርጫት ኳስ ተጨዋች ማይክል ጆርዳን ጫማ 1.47 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን አድርጎት የተጫወተበት ጥንድ ጫማ በጨረታ በ1.47 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠ ሲሆን ይህም ታይቶ በማይታወቅ ዋጋ የተሸጠ የስፖርት ጫማ አድርጎታል። ማይክል ጆርዳን ይህንን ጫማ እንደ አውሮፓውያኑ በ1984 ከቺካጎ ቡልስ ጋር በነበረው የመጀመሪያ ግጥሚያ ወቅት ተጫምቶት የነበረ ሲሆን ቀይ እና ነጭ ቀለም ያለው፣ የናይኪ ምርት የሆነና 'ኤር ሺፒንግ' የሚል ስያሜ ያለው ነው። ያ ዓመት ማይክል የናይኪን የአልባሳት እና የጫማ ምርት ለመጠቀም ከኩባንያው ጋር የተፈራረመበት ወቅት ነበር። ታዲያ ያ ጫማ አሁን ለጨረታ ቀርቦ የተሸጠበት ዋጋ በማንኛውም ስፖርት ከተሸጡ ጫማዎች ክብረ ወሰንን የሰበረ ነው ተብሏል። በቅርጫት ኳስ ውድድር ውስጥ የገዘፈ ስም ያለው ማይክል፤ በ2003 ጡረታ የወጣ ሲሆን በአሜሪካ የቅርጫ ኳስ ሊግ ውስጥ የመጀመሪያው ቢሊየነርም ነው። የጫማው በዚህ ዋጋ መሸጥ የማይክልን በቅርጫት ኳስ ውስጥ ያለውን ቦታ የሚያሳይ ነው ተብሏል። ጫማውን በጨረታ አሸንፎ የገዛው ኒክ ፊዮሬላ የተባለ የተለያዩ ቁሶችን ገዝቶ በማሰባሰብ የሚታወቅ ሰው ነው። ጨረታው ከመካሄዱ በፊት ጫማው ከ1 ሚሊዮን እስከ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ እንደሚችል ተገምቶ ነበር። ይህ ጫማ በስፓርቱ ዘርፍ በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠ ጫማ ይሁን እንጂ ከስፓርት ውጪ ከዚህም በላቀ ዋጋ የተሸጡ ጫማዎች አሉ። በዓለም በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠው ጫማ የናይኪ 'ኤር ዬዚ 1' የተባለው የሙከራ ምርት (ፕሮቶታይፕ) ሲሆን፤ ራፐር ካንዬ ዌስት በ1.8 ሚሊዮን ዶላር ገዝቶታል።", "እግር ኳስ፡ ሃሪ ኬን ቶተንሀምን ሊለቅ ይሆን? እንግሊዛዊው የቶተንሀም ግብ አዳኝ ሃሪ ኬንን ለማስፈረም ከቼልሲና ከማንቸስተር ሲቲ በተሻለ መልኩ ማንቸስተር ዩናይትዶች እድል እንዳላቸው ፉትቦል ኢንሳይደር አስነብቧል። የ27 ዓመቱ ሃሪ ኬን በአሁኑ ሰዓት ከአገሩ እንግሊዝ ጋር በመሆን በአውሮፓ ዋንጫ እሑድ ለሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ መድረስ የቻለ ሲሆን ቡድኑን በአምበልነት እየመራ እስካሁን በውድድሩ አራት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ፉትቦል ኢንሳይደር ከታማኝ ምንጮቼ አገኘሁት ብሎ ይዞት በወጣም መረጃ መሠረት፤ ቶተንሀሞች ለኮከብ ተጫዋቻቸው 100 ሚሊዮን ፓውንድ እና ሁለት የማንቸስተር ዩናይትድ ዋናው ቡድን ተጫዋቾችን በምትኩ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል። ማንቸስተር ዩናይትዶች በዘንድሮው የክረምት የዝውውር መስኮት እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ጄዳን ሳንቾን በ70 ሚሊየን ፓውንድ ያስፈረሙ ሲሆን በመቀጠል ተከላካይና አጥቂ መግዛት እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። በሌላ የዝውውር ጭምጭምታ ሌላኛው የማንቸስተር ክለብ ሲቲ ፈረንሳያዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጫዋች አንትዋን ግሪዬዝማንን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንዳደረገ ተዘግቧል። የ30 ዓመቱ ግሪዬዝማን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ወደ ባርሴሎና ሲያቀና በርካቶች ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል ገምተው የነበረ ቢሆንም፤ የባርሴሎና ቆይታው ግን ብዙም አስደሳች አልነበረም። ለዚህም ነው ተጫዋቹ አዲስ ክለብ እየፈለገ እንደሆነ የተገለጸው። ሁለቱ ታላላቅ የጣልያን ክለቦች ኢንተርና ሚላን እንዲሁም የእንግሊዙ ሌስተር ሲቲ ብራዚላዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጫዋች ፊሊፔ ኩቲንዮን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል። የቀድሞው የሊቨርፑል ኳስ አቀጣጣይ ኩቲንዮ 29 ዓመቱ ሲሆን በጉልበት ቀዶ ሕክምና ምክንያት ያለፈውን የውድድር ዓመት ሁለተኛ ግማሽ ኳስ አልተጫወተም። ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ድሮ አቋሙ እየተመለሰ መሆኑን ተከትሎ በርካታ ክለቦች ተጫዋቹን የግላቸው ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ስለዚህም ክለቡ ባርሴሎና ለተጫዋቹ እስከ 20 ሚሊዮን ፓውንድ የሚከፍል ከመጣ ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።", "የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ካሜሩን በሶስተኛነት አጠናቀቀች የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ካሜሩን በትናንትናው ዕለት ጥር 28፣ 2014 ዓ.ም በተካሄደው ጨዋታ በፍፁም ቅጣት ምት ቡርኪናፋሶን በመርታት ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች። ካሜሩን በቡርኪናፋሶ 3ለ0 እየተመራች የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን 3 ጎል በማስቆጠር እኩል በመሆናቸው ጨዋታው በፍፁም ቅጣት እንዲጠናቀቅ ሆኗል። በዚህም ካሜሩን አሸናፊ ሆናለች። ቡርኪናፋሶ በስቲቭ ያጎ፣ የካሜሩኑ አንድሬ ኦናና በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ እንዲሁም በጅብሪል ኦታራ ጎሎች 3 ለ0 እየመራች ነበር። ነገር ግን በደጋፊዎቻቸው ፊት የተጫወቱት ካሜሮኖች በስቴፋን ባሆከንና በቪንሰንት አቡበከር ሁለት ጎሎች ወደ መጨረሻው ሰዓት እኩል መሆን ችለዋል። የጨዋታው 90 ደቂቃ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጨማሪ ጊዜ ሳይጨመር ቡድኖቹ በፍፁም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ተደርጓል። ለ49 ደቂቃዎች ያህል ጨዋታውን ተቆጣጥረውት ለነበረው ቡርኪናፋሶዎች ውጤቱ አሳዛኝ ሆኗል። በተቃራኒው አምስት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ካሜሩን አምስቱንም የቅጣት ምቶች ወደ ጎል በመቀየር ግሩም በሆነ መልኩ በሶስተኛነት አጠናቃለች። በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የሚጠናቀቅ ሲሆን የሰባት ጊዜ ሻምፒዮናዋና ክብረ ወሰንን የጨበጠችው ግብፅ የፍፃሜ ጨዋታዋን ከሴኔጋል ጋር ታደርጋለች።" ]
[ 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5, 5 ]