|
proverb,Description
|
|
ለለአሐዱ በከመ ምግባሩ።,ለእያንዳንዱ እንደሥራው፡፡
|
|
ለሰብእ ጸሩ ሰብአ ቤቱ፡፡,የሰው ጠላቱ፣ ቤተሰቡ
|
|
ለዘቦ ይሁብዎ፤ ወይዌስክዎ፤ ወለዘለ አልቦ አለሂ ቦ የህይድዎ፡፡,ላለው ይለጡታል፣ ይጨምሩለታልም፡፡ የሌለውን ግን ያለውንም እንኳን ይነጥቁታል፡፡
|
|
አኮ በሲበት አላ በአእምሮ,በሽበት አይደለም፤ በማስተዋል ነው እንጅ።
|
|
መጥወኒ እመጥወ,ስጠኝ እስጥህለሁ
|
|
ምዉት የሀውር ሀበ ምዉት,ሙት ወደ ሙት ይሄዳል
|
|
ወእመ ሖርከ ብሔረ ባዕድ ኩን ከማሆሙ,ሌላ አገር ብትሔድ፤ እንደነሱው ሁን
|
|
ዘበልዐ በአቅም የሀድር በሰላም,በልኩ የበላ ስላማዊ ዕንቅልፍ ይተኛል
|
|
ሀቡ ዘነጋሚ ለነጋሚ፤ ወዘእግዚአብሔር ለእግዜአብሔር,የቂሳርን ለቁሳር፤ የእግኢአብሔርን ለአግዚአብሔር ስጡ
|
|
ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለክ,ለለመነህ ሁሉ ስጥ
|
|
ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር,መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥ
|
|
ሃይማኖት እንተ አልባቲ ምግባረ ሠናይ ምውት ይእቲ,በጎ ሥራ ያልተሠራባት ፃይማኖት የሞተች ናት
|
|
ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ,በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተተኩልሽ
|
|
ለልላነ አጓለእመሕያውሰ አልቦ ዘይክል አግርሮታ,ምላስ ይተባል፤ ጥርስ ይወጋል
|
|
ለሰሚዕ እጹብ,ለሰሚው አስደናቂ
|
|
ለስሒት መኑ ይሴብዋ,ስህተትን ማን ያስተውላታል
|
|
ለእመ ረክብከ ሰብአ በፍኖት ኢትጻባሕ፤ ወለእመ ተጻብሐክ ኢታውስኦ,በመንገድ ካገኘኸው ጋራ አትጣላ እሱ ነገር ቢፈልግህም አትመልስለት
|
|
ለአመ ብከ ህብ ወለእመ አልብከ ኀሊ,ካለህ ስጥ ከሌለህ እዘን
|
|
ለእመ ብከ ጥበብ ጸሐፍ,ዕውቀት ካለህ ጻፍ
|
|
ለወሀቤ ዝናም ማየ ከልእዎም,ለዝናብ ጌታ ውሃ ነሱት
|
|
ለውሂብ ኢትጉጔእ ወውሂበከ ኢትናፍቅ,ለመስጠት አትቸኩል፤ ሰጥተህም አትጸጸት
|
|
ለዘመጽአ በለላም በዝ አባርኮ ወለዘመጽአ በኀኬት በዝ እዘተርኮ,በለላም የመጣውን በዚህ እባርከዋለሁ፤ በክፋት የመጣውን በዚህ እዘተርከዋለሁ
|
|
ዘመጽአ ኀቤየ ኢይሰድዶ፤ ወኢያወጽኦ አፍአ,ወደኔ የመጣውን ወደ ውጭ አላወጣውም
|
|
ዘቦ ይሁብዎ፤ ወይዌስክዎ፤ ወለዘለ አልቦ አለሂ ቦ የህይድዎ፡,ላለው ይለጡታል፣ ይጨምሩለታልም፡፡ የሌለውን ግን ያለውንም እንኳን ይነጥቁታል
|
|
ለዘኢይሰቲ ወይነ ምንት ውእቱ ሕይወቱ,ወይን የማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አሰው?
|
|
ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል,ለሚያምን ሁሉ ይቻላል
|
|
ለጠቢብሰ አሃቲ ቃል ትበቁእ,ላሰተዋይ ሰው አንድ ቃል ይበቃዋል
|
|
ልሳነ እጓለ እመህያው ሐጽ ወኩናት,የሰው አፍ እንደ ተሳለ ጦር ነው
|
|
ልደትሰ በኩሉ ልደት ጸውኡኒ በካልእ ዕለት,የልደት ድግስ በሁሉም ነው፤ ሌላ ቀን ጥሩኝ
|
|
ሎቱ ስብሐት,ምስጋና ለርሱ ይሁን
|
|
ሐለሙ ሕልመ ወአልቦ ዘረከቡ,ሕልም አለሙ፣ ያገኙት ነገር ግን የለም
|
|
ሐንካስ በአግረ ዕውር ሖረ! ዕውርኒ በዐይነ ሐነካስ ነጸረ ወበክልዔሆሙ ወይንየ ተመዝበረ,አንካሳ በዕውሩ አግር ሄደ፤ ዕውሩም በአንካሳው ዐይን አየ፤ በሁለቱም አታከልቴ ተመዘበረ
|
|
ሕሙማን ይፈቅድዎ ለዐቃቤ ሥራይ ወአኮ ጥዑያን,ባለመድኃኒቱን በሽተኞች ይፈልጉታል ጤነኞች አይሹትም፡
|
|
ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ,ያይን በሽታዋ፣ ጠላትን ማየቷ
|
|
ሕንጻ ወውሉድ ያዐብዩ ስመ,ግንብና (ሕንጻ) ልጅ፤ ስምን ያስጠራሉ
|
|
ሕያዋን ይስእሉ ለሙታን፤ ሙታን ይስአሉ ለሕያዋን,ያሉት ለሞቱት ይጸልያሉ፤ የሞቱት ያሉትን ያስባሉ፡፡
|
|
ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን,ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ
|
|
መምህራነ ኮኑ በበደወሉ፤ ፊደላተ በሆለቆ ኩሉ,ፊደል የቆጠሩ ሁሉ፤ በያካባቢው አስተማሪዎች ሆኑ
|
|
መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ,ፊት አይቶ የማያዳላ መምርና መካሪ
|
|
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ,የሕይወት መሠረትና የድኅነት መገኛ ማርያም ናት
|
|
መስዋዕቱ ለእግቢአቢሔር መንፈስ የዋህ,የእግዚአብሔር መስዋዕቱ ቅን መንፈስ ነው
|
|
መስገርትስ ተቀጥቀጠት ወንህነስ ድኅነ,ወጥመድ ተሠበረች፤ እኛ ግን አመለጥን
|
|
መኑ ከመ አምላከነ?,እንደ እግዚአብሕር ያላ ማን አለ?
|
|
መኑ ዘደመሮ ለብርሃን ምስለ ጽልመት?,ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
|
|
መኑ የአቁር እሳተ ውስተ ኅጽኑ?,እሳትን በጭኑ ማን ይሸከማል?
|
|
መንግሥት እንተ ትትናፈቅ በበይናቲሃ ኢተጸንእ,እርስ በርሷ የምትለያይ መንግሥት አትጸናም
|
|
መዐር ኢይጥዕሞ ለአድግ,ለአህያ ማር አይጥማትም
|
|
መዓተ ንጉሥ ከመ መልአክ ሞት,የንጉሥ ቁጣ፣፤ የመልአከ ሞት ያህል ያሰፈራል
|
|
መጋቢ እንበለ ሊሳይ፤ ጸባቲ እንበለ ማይ,ያለ ምግብ መጋቢ የለ ውሃ ዋናተኛ
|
|
መጠኑ ለረድእ በከመ ሊቁ፡፡,የተማሪ ደረጃው (ከብሩ) እንደ መምሩ ነው፡፡
|
|
መጥወኒ አመጥወከ፡፡,ስጠኝ አለጥህለሁ
|
|
ማኅቶቱ ለሥጋክ ዐይንክ ውእቱ,የሥጋህ መብራት ዐይንህ ነው።
|
|
ማዕረሩ ብዙኅ ወገባሩ ህዳጥ,መኸሩ ብዙ ሠራተኛው ጥቂት፡፡
|
|
ማይ ብዙኅ ኢይክል አጥፍአታ ለፊቅር፡፡,ብዙ ውሃ ፍቅርን አያጠፋትም
|
|
ምሉዕ በኩለሄ,በሁሉ የተሟላ
|
|
ምሕረተ እፈቅድ ወአኮ መስዋዕተ,ምሕረትን እወዳለሁ፤ መስዋዕትን አይደለም።
|
|
ምንት ብክ ዘኢነሳእከ እም ካልዕከ?,ከስው ያልወስድከው ምን አለህ?
|
|
ምንዳቤያትሰ ኢኮና ርሁቃተ እምኔከ፤ አላ ይነቅአ እምታህተ እገሪከ፡,ችግሮችህ ሩቆች አይደሉም፤ ከአንተው ከራስህ ይመነጫሉ አእንጅ።፡
|
|
ምክር ሠናይት ለኩሉ ዘይገብራ።,ለሚተገብራት፤ ምከር መልካም ናት
|
|
ሞቱ ሰኃጥኣ ጸዋግ,የኃጢአተኛ አሟሟት የከፋ ነው
|
|
ሞታ ለነፍስ ርቅ እም አግዚብሔር፡፡,የነፍስ ሞቷ፤ ከእግዚአብሔር መራቋ
|
|
ምውት የሐውር ኀበ ምውት፡,ሙት፣ ወደ ሙት ይሄዳል፡፡
|
|
ምኩራብ አነመት ፀምረ፤ ወቤተ ክርሰቲያን ተአጽፈቶ፡፡,ምኩራብ ግምጃ ፈተለች፤ ቤተክርስቲያን ለበሰችው፡፡
|
|
ሠናይ ለብእሲ መቅበርቱ ለእመ ኮነ በውስተ ርስቱ፡፡,የሰው መቃብሩ፣፤ በአገሩ ቢሆን መልካም ነው፡
|
|
ሠናይ ብእሲ ያወጽኣ ለሠናይት፣ እም ሠናይት መዝገበ ልቡ፡፡,በጎ ሰው ከበጎ ልቡ በጎ ነገርን ያወጣል፡
|
|
ሠናይ እገሪሆሙ ለአለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡,መልካም ዚና የሚነግሩ አብሣሪዎች፣ እግሮቻቸው ያማሩ ናቸው፡፡
|
|
ሣህል ወርትዕ ተራከባ፤ ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ።,ቅንነትና ይቅርታ ተገናኙ እውነትና ሰላም ተሰማሙ
|
|
ሥርዉ ለኩሉ እኩይ፣፤ አፍቅሮ ንዋይ፡,የክፉ ተግባር ሁሉ ሥሩ የገንዘብ ፍቅር ነው፡፡
|
|
ሥጋ ትሄይላ ለነፍስ፤ በከዊነ ማኅደር፡፡,ማደሪያ በመሆኗ፤ ሥጋ ነፍስን ትጨቁናታለች
|
|
ርቱዕ አበው ይዝግቡ ለውሉዶሙ፤ ወአኮ ውሉድ ለአዝማዲሆሙ,ወላጆች ለልጆች እንጅ፤ ልጆች ለወላጆች ሀብት ሊያከማቹ አይችሉም
|
|
ርኅቀተ ሀገር፤ ኢይከልኣ ለፍቅር፡፡,የሀገር ርቀት፣ ፍቅርን አያስቀራት
|
|
ሰላም ለላም ለሰራቄ ቅኔ ናሁዳ፤ ዳር ዳሩን ኮርኩሞ፣ መሀሉን ሳይጎዳ፡,ቀነጣጥቦ ለሚሰርቅ የቅኔ ሌባ ሰላም ይሁን
|
|
ሰብአ ቤቱ ይጻረሮ ለለብእ,ሰውን የገንዛ ቤተሰቡ ይቃወመዋል፡፡
|
|
ሰብአሰ ገጸ ይሬኢ፤ ወእግዚአብሔርሰ ልበ ይሬኢ፡፡,ሰው ፊትን እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፡፡
|
|
ሰብእ አልብየ,ለው የለኝም፡፡
|
|
ሰብእ ወጣኒ፤ እግዚአብሔር ፈጻሚ,ሰው ይጀምራል፣ እግዚአብሔር ይፈጽማል፡
|
|
ሰብእ ይሠምር በዘይጌይሶ ለሥጋሁ።,ሰው ሰሥጋው የሚጠቅመውን ይወዳል፡፡
|
|
ሰብእ ይቄድሶ ሰመካን፤ መካን ይቄድሶ ለሰብእ፡፡,ሰው ቦታን ያሰከብረዋል፤ ቦታም ሰውን ያሰከብረዋል፡፡
|
|
ሰብእ ይከብር በእንተ ልብሱ፡፡,ሰው በልብሉ ይከበራል፡፡
|
|
ሰንበት ተዐቢ እምኩሉ ዕለት፤ ወሰብእ ይከብር እም ዙሉ ፍጥረት፡፡,ሰንበት ከዕሰታት፣ ሰው ከፍጥረታት፣ ሁሉ ይበልጣሉ፡
|
|
ሰአሉ ወይትወህበክሙ፤ ኅሥሠ ወትረክቡ፤ ጐድኮጐዱ ወያርህዉ ለክሙ፡፡,ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ እንኳኩ ይከፈትላችቷል፡፡
|
|
ሰይፍ ዘክልዔ አፉሁ፡,ሁሰት አፍ፤ ያለው ሠይፍ፡፡
|
|
ሲሲታ ስነፍስ ቃሰ እግዚአብሔር፡፡,የነፍስ ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
|
|
ስማዕ ወልድየ ሕገ አቡከ,ልጄ ሆይ! ያባትህን ትእዛዝ ስማ፡
|
|
ስብሐት ለእግዚአብሔር!,እግዚአብሔር ይመስገን!
|
|
ስብዓ ይወድቅ ጻድቅ ወይትነሣአእ፡,ጻድቅ ሰባት ጌዜ ቢወድቅ ሰባት ጌዜ ይነሣል፡፡
|
|
ሰታይ ወአንስት ያስሕታሆሙ ለመምህራን፡፡,መጠጥና ሴቶች መምህራንን ያስቷቸዋል፡፡
|
|
ሶበ ተሐውር ምስስ ፅድውከ ኅበ መልአክ ተዐረቅ በፍኖት,ወደ ዳኛ በምትሄድበት ገዜ፣ በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ታረቅ
|
|
ሶበ ትረክቦ ኃጢአቱ ይጸልኣ፡,ጥፋቱን ሲያውቃት ይሰቀቃታል፡፡
|
|
ሶበ ኢያሥራሕክምዋ ሰእጐልትየ እም ኢረከብክምዋ ሰአምሳልየ፡፡,በጥጃዬ ባላረሳችሁ፤ የእንቁቅልሼን ፍች ባላወቃችሁ፡
|
|
ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ አግዚአብሔር,የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡
|
|
ቀዳሜ ሕይወቱ ሰሰብእ እክል ወማይ፣፤ ወይን ወሥርናይ,እህልና ውሃ ወይንና ስንዴ ለሰው ሕይወት፣ መሠረት ናቸው፡፡
|
|
ቀጥቅጥ መዝራዕቶ ሰኃጥእ ወሰእኩይ፡፡,ክፉና ተንኮለኛን ሰው ድቅቅ ስብርብር ማድረግ ነው፡፡
|
|
ቃለ መዋቲ ጽንዕት ይኣቲ፡፡,የሙት ቃል አይሻርም፡፡
|
|
ቅኑተ ይኩን ሃቁየክሙ ወኅትወ መኀትዊክሙ።፡,ትጥቃችሁ የጠበቀ መብራታችሁ የበራ ይሁን።
|
|
ቅድመ አውጽእ ሠርዌ እም ዐይንክ,በመጀመሪያ ባንተ ዐይን ያለውን ግንድ አውጣ፡፡
|
|
ቅድመ ይባኡ ውስተ ኅርየት ይምሃርዎሙ ቃለ ሃይማኖት፡,ከመሾማቸው በፊት የሃይማኖትን ቃል ያስተምሯቸው
|
|
በስሐቅ ወበስላቅ ይበውእ ጸላኤ ሠናያት፡፡,ክፉ መንፈስ በሳቅ በስላቅ ይገባል
|
|
በሳምናዊት ዘመን ትሴኮስ ፍቅር፡፡,በስምንተኛው ሽህ ፍቅር ትቀዘቅዛለች፡፡
|
|
በስምዐ ክልዔቱ ወሠለስቱ ይቀውም ኩሉ ነገር፡፡,ነገር ሁሉ በሁለትና በሦስት ምሥክሮች ይጸናል።፡
|
|
በቀዳሚ ጉየይ፤ ወበካልዕ ጉየይ፤ ወበሳልስ ተንሥእ ወተቃተል፡፡,በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሽሽ፣ በሶስተኛው ግን ተነስተህ ተፋለም
|
|
በብዙኅ ጻማ ሀሰወነ ንባእ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር፡፡,ወደ እግዚአብሔር መንግሥት፣ በብዙ ድካም እንገባለን
|
|
በትዕግስትክሙ ታጠርይዋ ለነፍስክሙ፡፡,በመታገሳችሁ ነፍሳችሁን ታድናላችሁ፡፡
|
|
በአርምሞ ይመስል ጠቢብ፡፡,ዝም በማለቱ ብልህ ይመስላል፡፡
|
|
በአይቴ ኀሊፈኪ ድጓ ተምሂረኪ?,በየት አልፈሽ ድጓ ተማርሽ?
|
|
በከንቱ ዘነሳእክሙ ሀቡ በከንቱ፡፡,ያለ ዋጋ የተቀበላችሁትን ያስ ዋጋ ስጡ፡
|
|
በዘሠፈርክሙ ሎሙ ይሠፍሩ ለክሙ፡፡,በሰጣችኋቸው ልክ ይስጧችኋል።
|
|
በዝ ግብርኪ፣ ተገደፍኪ፡፡,በዚህ ሥራሽ፤ ወጥተሽ ወደቅሽ፡፡
|
|
በጽባሕ ዘተናገረ ኢይደግም በሠርክ፡፡,ጧት የተናገረውን ማታ አያስታውሰውም፡
|
|
በሞተ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ፡፡,በርሱ ሞት እኛ ተፈወስን፡፡
|
|
ቢጽ ለቢጹ ይትራድዖ፡,ጓደኛ ጓደኛውን ይረዳዋል
|
|
ቢጽ ምስለ ቢጹ።,ጓደኛ ከጓደኛው፡፡
|
|
ባኡ እንተ ጸባብ አንቀጽ፡፡,በጠበበው በር ግቡ፡፡
|
|
ቤዛ ነፍሉ ለሰብእ ጥሪተ ብዕሉ,ሃብት ለሰው ቤዛው ነው
|
|
ብላዕ በሐፈ ገጽከ,ጥረህ ግረህ ብላ
|
|
ብእሲ ማእምር ኀዘን ለነፍሱ,አስተዋይ ሰው ያዝንበት እያጣም
|
|
ብአሲት አዛል (አዚዝ) አክሊል ለምታ,መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት
|
|
ብእሲ እኩይ የኃብል አእርክተ,ክፉ.ሰው በነገር ሥራ ወዳጆችን ይለያያል
|
|
ብእሲ ወብእሲት እሐዱ አካል እሙንቱ,ባልና ሚስት አንድ ከካል ናቸው
|
|
ብእሲ ጠዋይ ይልዕክ እከየ,ጠማማ ለው ክፋትን ከሁሉ ያደርሳል
|
|
ብዙኃን መኳንንት እለ ወድቁ ውስተ ምድር ወቦ ባሕታዊ ዘተቄጸለ አክሊለ,በዚህ ዓለም በመከራ የወደቁ ባለሥልጣኖች ብዙ ናቸው! ዘውድ የተቀዳጀ ባሕታዊም አለ
|
|
ብዙኃን አለ ወድቁ በሐጺን ወአኮ ከመ እለ ወድቁ በልሳን,በጦር ተደብድበው የወደቁ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን በነገረ ሠሪ አንደበት እንደጠፉት አይሆኑም
|
|
ብዙኃን ይመውኡ,ብዙዎች ያሸንፋሉ
|
|
ብዙኃን ጽዉኣን፤ ወኅዳጣን ኅሩያን,የተጠሩ ብዙዎች፤ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው።፡
|
|
ብየ ሥልጣን ላዕለ ኩሉ ዘኮነ ወአኮ ዙሉ ዘይበቁዓኒ,ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም
|
|
ብፁዓት መካናት ዘኢወለዳ,ያልወለዱ ብፁዓት ናቸው
|
|
ብፁዓን ገባርያነ ሰሳም,የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው
|
|
ብፁፅ ዘይሁብ አም ዘይነስእ,ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ በፁዕ ነው
|
|
ብፁዕ ዘይደበድባ ለከርሱ,ሰውነቱን የሚንከባከባት ብፁዕ ነው
|
|
ቦ እለ ተሐርዩ እምከርሠ እሞሙ፡,ከናታቸው ማህጸን ጀምሮ የተመረጡ አሉ
|
|
ቦ ጊዜ ለዙሉ,ለሁሉም ጊዜ አለው
|
|
ተልዒልየ ተትህትኩ፤ ወተመነንኩ፡,ተከብሬ ሳበቃ ተዋረድኩ
|
|
ተሰአሎ ለአቡከ ይነግረከ፤ ወለሊቃውንቲከ ይዜንዉከ,አባትህን ጠይቀው ይነግርሃል
|
|
ተበአስ በአንተ ጽድቅ እስክ ለሞት,ለአውነት እስከ ሞት ድረስ ተጋደል
|
|
ተንተንኩ ለወዲቅ፤ ወእግዚአብሔር አንሥአኒ,ልወድቅ ተንገዳገድኩ፤ እግዚአብሔር ግን አነሣኝ
|
|
ተአምሑ በበይናቲከሙ በአምሐ ቅድሳት,በተቀደሰ ስላምታ እጅ ተነሳሱ
|
|
ተዓቀብ አምጸላእትከ አሐደ ጊዜ ወተኣቀብ እም ፍቁርክ ፲፻ ጊዜያተ,ከጠላትህ አንድ ጊዜ፣ ከወዳጅህ ሽህ ጊዜ ተጠንቀቅ
|
|
ተዘከሩ መኳንንቲክሙ፣ ዘነገሩከሙ ቃለ እግዚአብሔር,የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን፤ አስተማሪዎቻችሁን አስታውሱ
|
|
ተገሃሥ እም እኩይ፤ ወግበር ሠናየ,ከክፋት ራቅ፤ መልካምንም አድርግ
|
|
ተፋቀሩ በበይናቲከሙ,እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ
|
|
ተፋቅሮሰ ፍጹም ሕግ,ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው
|
|
ትበልዒ ወኢትጸግቢ,ትበያለሽ ግን አትጠግቢም
|
|
ትንቢት ይቀድሞ ለነገር,ድርጊትን ትንቢት ይቀድመዋል
|
|
ትእቢትሰ ጸሩ ስሰክርስቶስ,ትቢተኛ የክርስቶሰ ጠሳት ነው
|
|
ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ,የደጋግ ሰዎች ልጆች ይባረካሉ
|
|
ኅላፊ ንብረት፣ ክመ ጽላሎት,ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው
|
|
ኀበ ሀሎ መዝገብክሙ ሀየ ይሄሉ ልብክሙ,ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛል
|
|
ኀበ ሀሎ ገደላ ሀየ ይትጋብኡ አንሰርት,ጥንብ ባስበት አሞሮች ይሰበሰባሉ
|
|
ሃዘን ለአብዳን፤ ወፍስሐ ለጠቢባን,ሀዘን ለሰነፎች፣ ደስታ ለብልሆች
|
|
ኀጺን ለነጺን ይትባልሁ,ብረት ብረትን ይስስዋል
|
|
ኃይሉ ስስብእ በአምጣነ ቆሙ,የስው ኃይሉ በቁመቱ ልክ
|
|
ኅዳጣን ይትጌበሩ፤ ወብዙኃን የዐርሩ,ጥቂቶች ይሠራሉ፤ ብዙዎች ይስበስባሉ
|
|
ኅድጉ አበሳ ቢጽክሙ,የወንድማችሁን በደል ተዉለት
|
|
ኅድጋ ለመዓት ወግድፋ ለቁጥዓ,ብስጭትን ተዋት፤ ቁጣንም ጣላት
|
|
ኅድግዎሙ ለሕጻናት ይምጽኡ ኀቤየ,ሕጻናትን ተዉአቸው ወደኔ ይምጡ
|
|
ኀድግዎሙጮ ለምጢዉታን፤ ይቅብሩ ምዉታኒሆሙ,ሙታንን ተዉአቸው፤ ሙታኖቻቸውን ይቅበሩ
|
|
ነባህነ ነባህነ ከመ ዘኢነባህነ ኮነ,ጮህን ጮህን አንዳልጮህን ሆን
|
|
ነገሥት ያፈቅሩ ጽልሕዋነ ወመደልዋነ,ገዥዎች ግብዞችንና ሸንጋዮችን ይወዳሉ።
|
|
ነገረ አማጽያን ኃየለነ,የነገረኞች ወሬ በጠበጠን
|
|
ነገረ ዘርቅ,ተራ ወሬ አሉባልታ
|
|
ነፍስ ርኅብት መሪርኒ ጥዑመ ያስተርእያ,የተራበች ነፍስ መራራው ሁሉ ጣፋጭ ይመሰላታል።
|
|
ነፍስየ ትጻእ ምስለ ኢሎፍላውያን፡,ከኢሎፍኣውያን ጋር ነፍሴ ትውጣ
|
|
ነፍስ ጽግብት ጸቃውዓ መዓር ትሜንን,የጠገበች ነፍስ የማር ወለሳ ትረግጣስች
|
|
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይፄልዉ አኃው ኅቡረ,እነሆ ወንድሞች ተባብረው ሲኖሩ መልካም ነው
|
|
ንሕነ ነአምር ግብሮን ለቆራብት,የቆራቢዎችን ተግባር እኛ እናውቃለን
|
|
ንሥኣ ወብልዓ ለአእንታከቲ መጽሐፍ,አንካ ይችን መጽሐፍ ብላት
|
|
ንቃህ መዋቲ,የተኛህ ንቃ
|
|
ንባብ ይቀትል፤ ወትርጓሜ ያሐዩ፡,ንባብ ይገላል፤ ትርጓሜ ያድናል
|
|
ንነግርሂ ወኢንዘብጥ,እንናገራለን እንጅ እንማታም።
|
|
ንዋይ ከመ እግዜኡ,ገንዘብ እንደጌታው ነው
|
|
ንዋይከ በቅድሜከ፡፡,ገንዘብህን ከፊትህ አትለይ፡፡
|
|
ንግባአኬ ኀበ ጥንተ ነገር፡፡,ወደ ቀደመው ነገር አንመለሰ፡፡
|
|
አልቦ በቁዔት በከሲተ ኅሊናየ,የልቤን ብናገር ጥቅም የለውም፡፡
|
|
አልቦ ክዱን ዞኢይትከለት፤ ወአልቦ ኅቡእዕ ዘኢያስተርኢ,የማይገለጥ ሽሸግ የማይታይ ሥውር የለም፡፡
|
|
አልቦ ዘያበርህ ማኅቶተ ከመ ያንብራ ታህተ ከፈር፡፡,መብራት አብርቶ እንቅብ የሚደፋባት የለም፡፡
|
|
አልቦ ዘይእህዝ እርፈ ወየሐርስ ድኅሪተ፡፡,እርፍ ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም:
|
|
አልቦ ገብር ዘየዐቢ እም እግዚኡ፤ ወአልቦ ረድእ ዘየዐቢ እም ሊቁ፡,ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ፤ ከመምሩ የሚበልጥ ተማሪ የለም፡፡
|
|
አልቦ ገብር ዘይክል ተቀንዮ ለከልዔ አጋአእዝት፡፡,ለሁለት ጌቶች ሊገዛ የሚችል አገልጋይ የለም፡፡
|
|
አሐቲ ይእቲ ለእማ ።,ለእናቷ አንዲት ናት።
|
|
አሐደ ቀለመ ዘነገረከ ይኩን ከመ አቡከ፤ ክልዔተ ቀለመ ዘነገረከ ይኩን ከመ ፈጣሪከ፡፡,አንድ ቀለም የነገረህ እንደ አባትህ፣ ሁለት ቀለም የነገረህ እንደ ፈጣሪህ ይሁንልህ፡፡
|
|
አሐደ ይኩን ቃልክሙ፤ እመኒ እወ አወ ወእመኒ አልቦ አልቦ፡፡,ቃላችሁ አንድ ይሁን፤ አዎ ከሆነ አዎ አይደለም ከሆነም አይደለም በሉ፡፡
|
|
አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ፣ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ,እሳትና ውፃ አቀረብኩልህ፤ እጅህን ወደምትሻው ስደድ፡፡.
|
|
አቅድሙ ስንቀከሙ፡፡,ስንቃችሁን አስቀድሙ።
|
|
አበውኒ ኢታስተቆጥዑ ውሉደክሙ፡፡,አባቶች ልጆቻችሁን አታስቆጡ
|
|
አብዝኖ መጻሕፍት ያዘነግእ ልበ,መጻሕፍትን በብዛት ማንበብ ዝንጉነትን ያመጣል፡፡
|
|
አብድ ይነውም በጊዜ ማአኣረር፡,ሰነፍ በአዝመራ (በሥራ) ጊዜ ይተኛል፡፡
|
|
አነ አዐብዮ ሰአቡየ ዕዝን፣ ደኃራዊ ዘበቁልኩ ቀርን።,በኋላ የበቀልኩ ቀንድ አባቴን ጆሮን እበልጠዋለሁ፡፡
|
|
አነ ዘጳውሎሰ፣ ወአነ ዘአጵሎስ፣ ወአነ ዘኬፋ፡፡,ኦኔ የጳውሎስ፣ አኔ የአጵሎሰ፣ አኔ የኬፋ።
|
|
አንብብዋ ለመልእክት፤ አም ጥንታ እስከ ተፍጻሜታ፡፡,መልአክቲቱን ከመጀመሪያዋ እሰከ መጨረሻዋ አንብቧት፡፡
|
|
አንተ ኮኩህ!,አንተ መሠረት ነህ!
|
|
አንትሙስ ኅሱ እንተ አፍኣ ወእንተ ውሰጡስ የአምር አግዚአብሔር፡፡,እናንተ የላዩን መርምሩ፤ የውስጡን እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡
|
|
አንትሙ ተሐውሩ ግድመ ግድመ፤ አነኒ አሐውር ግድመ ግድመ፡፡፥,እናንተ ግራ ግራውን ትሄደሳችሁ፤ እኔም ግራ ግራውን እሄዳለሁ፡፡
|
|
አንፄዋ ለኅልፈታ አንፈ ፄሴሜት ታጹኑ።,አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች፡፡
|
|
አክብር አባክ ወአመክከ፡,አባትና እናትህን አክብር፡፡
|
|
አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ፡፡,በሮጠ አይደለም በቀደመ እንጅ፡፡
|
|
አኮ በሲበት አላ በአአምሮ።,በሽበት አይደለም፤ በማስተዋል እንጅ፡፡
|
|
አኩቴቶሙ ዕረፍቶሙ፤ ዕረፍቶሙ አኩቴቶሙ።፡,እረፍታችው ማመስገናቸው፤ ማመስገናቸው አረፍታቸው ነው፡፡
|
|
አድኅን ርእስከ፡፡,ራስህን አድን።፡
|
|
አጽንእ ዘብከ ከመ አልቦ ዘይነሥእ አክሊሰከ፡፡,ጸጋህን ማንም እንዳይወስድብህ፣ ያለህን አጥብቀህ ያዝ፡፡
|
|
አፉሁ ለጻድቅ ይትሜህር ጥበብ፡፡,የደግ ሰው አፍ ጥበብን ይማራል፡፡
|
|
አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስክ፡፡,ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡
|
|
አፍትን ርእሰከ ለካህን፡፡,ራስህን ለካህን አሳይ፡
|
|
አፍኒ ወልብኒ ኅቡረ ይእመኑ።,አፍም ልብም በአንድነት ይመኑ፡፡
|
|
አፍ ይጸውአ ለሞት፡፡,አፍ ሞትን ይጠራል፡፡
|
|
ኢተህቡ ፍኖተ ለሠይጣን፡,ለሠይጣን በር አትስጡት፡፡
|
|
ኢታልምድዎ ወኢትክልእዎ፡፡,አታስለምዱት፤ አትከልክሉት፡፡
|
|
ኢታትህት ርአስክ ለብእሲ አብድ,ለሰነፍ ለው ራስከን ዝቅ አታድርግ፡፡
|
|
ኢታንሥእ ዘኢያንበርከ፡፡,ያላስቀመጥከውን አታንሣ፡፡
|
|
ኢታንክር ዘንተ ዘይብእስ ሀሎ፡፡,የባስ አለና ይህን አታድንቅ፡
|
|
ኢታድልዉ ለገጸ ሰብአ፡፡,የሰው ፊት አይታችሁ አታዳሉ፡፡
|
|
ኢታፍቅሩ ወርቀ ወኢብሩረ፡፡,ብርና ወርቅን አትውደዱ፡፡
|
|
ኢትህሚ ሰብአ ውስተ ቤትከ፤ አስመ ዖፈ ሰማይ ያወጽኦ ለነገርከ፡፡,ቤትህ ውስጥ እንኳ ቢሆን ሰውን አትማ፤ ነገርህን የሰማይ ወፍ ያወጣብህልና፡፡
|
|
ኢትልበሱ ልብሰ ሐራ።,የማይገባችሁን ልብስ አትልበሱ።
|
|
ኢትማዖ ሰአኩይ በእኩይ፤ አላ በገቢረ ሠናይ፡፡,ክፉን በክፉ አታሸንፈው መልካም በመሥራት እንጅ፡፡
|
|
ኢትርአይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ፡፡,የኢያልያብን ግርማ ሞገስ አትይ፡፡
|
|
ኢትርፍቅ ውስተ ርእስ ምርፋቅ፡፡,ከላይኛው መቀመጫ አትቀመጥ።
|
|
ኢትስርቁ ትብል ወለሊከ ትሰርቅ፡፡,አትስረቁ ትላለህ፤ አንተ ግን ትዘርፋሰህ፡፡
|
|
ኢትስተይ ማይ እራቆ፤ አላ ቶስህ ወይን በአንተ ህማመ ከብድከ፡፡,ውሃ ብቻ አትጠጣ፤ ስለሆድህ ህመም ትንሽ ወይን ጨምር እንጅ
|
|
ኢትቁም አራቀክ ቅድመ ነቢየ አግዚአብሔር፤,በእግዚአብሔር ሰው ፊት ባዶ እጅህን አትቅረብ፡፡
|
|
ኢትቅናዕ ላዕለ አኩያን፡፡,በክፉዎች አትቅና፡፡
|
|
ኢትኅድግ ዐርከክ ዘትካት፤ እስመ ኢይከውነክ ከማሁ ዐርከ ግብት፡፡,ድንገተኛ ወዳጅ እንደሱ አይሆንልህምና የቀድሞ ወዳጅህን አትተው
|
|
ኢትንአዶ ሰለብእ ዘእንበሰ ትርዐይ ተፍጻሜቶ፡።፡,ሰውን መጨረሻውን ሳታይ አታመስግነው፡
|
|
ኢትኩኑ ከመ መደልዋን፡፡,እንደግብዞች አትሁኑ፡፡
|
|
ኢትኩን ጻድቀ ፈድፋደ፤ ወኢትጠበብ ፈድፋደ፡፡,እጅግ ጻድቅ እጅግም ጠቢብ አትሁን፡፡
|
|
ኢትክሉ ተቀንዮ ለአግዚአብሔር ወለንዋይ፡፡,ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም፡፡
|
|
ኢትክሉ ተቀንዮ ለክልዔ አጋእዝት፡,ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም፡፡
|
|
ኢትክል ተከብቶ ሀገር፤ እንተ ተሐንጸት መልእልተ ደብር,በተራራ ላይ የተሠራች ህገር መሠወር አትችልም፡፡
|
|
ኢትዛለፍ በማእከለ ሊቃውንት፡፡,በሊቃውንቱ መካከል አትጥቀስ፡፡
|
|
ኢትግሥሠ መሲሃንየ ወኢታህስሙ ዲበ ነቢያትየ፡፡,መልእክተኞቼን አታስጨንቁ፤ በነቢያቶቼም ላይ ከፉ አታድርጉ
|
|
ኢትፍርህዎ ለሞት ፍርህዋ ለኃጢአት,ሞትን አትፍሩት፤ ኃጢአትን እንጀ፡፡
|
|
ኢትፍጽሞ ለብዕራይክከ ሶበ ታከይድ እክለክ፡፡,እህልክን ስትወቃ የሚያበራየውን በሬ አፍ አትለጉመው፡፡
|
|
ኢየኃድጋ ለሀገር ዘእንበለ አሐዱ ሔር፡፡,ሀገርን ያለ አንድ ቸር ለው አይተዋትም፡፡
|
|
ኢየአርሩ በለለ እም አስዋክ፤ ወኢይቀስሙ አስካለ እም አሜከላ፡፡,ከአሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንደርም ወይንን አይቆርጠም፡፡
|
|
ኢያስህትከ ላህያ ለብእሲት፡፡,የሴት ውበቷ አያታልህ፡፡
|
|
ኢይመውያ ሰሚዕ ለርእይ፡፤,መስማት ማየትን አያሸንፍም፡፡
|
|
ኢይትፈቀድ ምክንያት ለኢአሚን፤ ዳዕሙ ይትፈቀድ ለአሚን,ለማመን እንጅ ላለማመን ምክንያት አያሻም፡፡
|
|
ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ፡፡,ነቢይ በሀገሩ አይከበርም፡፡
|
|
ኢይድህን ንጉሥ በዝኀ ሠራዊቱ፡፡,ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፡፡
|
|
ኢይጥዕሞ መዓር ለአድግ ዘእንበለ እጉስታር፡፡,ላህያ ገለባ እንጅ ማር እይጥማትም፡፡
|
|
ኢይፈቅድ ይንግርዎ ግኦእዞ ለሰብእ,የሰውን ማንነቱን አንዲነግሩት አይሻም፡፡
|
|
ኤፍሬም ይበልዖ ለምናሴ፤ ወምናሴ ይበልዖ ለኤፍሬም፡,ወንድም ወንድሙን ያጠፋዋል፡፡
|
|
እለ መጥባሕተ ያነሥኡ በመጥባሕት ይመውቱ፡፡,በሾተል የገደሉ፣ በሾተል ይሞታሉ፡፡
|
|
እለ ትነብሩ ተንሥኡ፡፡,የተቀመጣቸችሁ ተነው፡፡
|
|
እለ ከርሦሙ አምላኮሙ።፡,ሆድ አምላኩዎች፡፡
|
|
እለ ጻጹተ ትነጥፋ ወእለ ገመለ ትውህጡ።,ግመልን የምትውጡ፣ ትንኝን የምታጠሩ፡፡
|
|
እመሰ ይትከሃለክሙ ምስለ ዙሉ ሰብእ ተእኅዉ፡፡,ቢቻላችሁስ ከሰዉ ሁሉ ጋር ተወዳጁ፡፡
|
|
እመሰ ጼው ለስሐ በምንት እንከ ይቄስምዎ?,ጨው አልጫ ቢሆን በምን ያጣፍጡታል?
|
|
አመ ተናገርኩ ጽድቀ ሰብእ ዛቲ ዓለም ይጸልኡኒ፤ ወከመ ኢይንብብ ሀሰተ ኩነኔ ዚእከ ያፈርሃኒ፤ ወእም ኩሉሰ አርምሞ ይቴይስ ወይሜኒ፡፡,እውነት እንዳልናገር የዚህ ዓለም ሰዎች ይጠሉኛል፤ ሀሰትም እንዳልናገር ፍርድህ ያስፈራኛል፡፡ ከሁሉም ዝምታ ይሻለኛል፡፡
|
|
እመ ወሀበ ብእሲ ኩሎ ንብረቶ ለፍቅር መንኖ አይሜንንዎ፡፡,ስው ስለፍቅር ንብረቱን ሁሉ ቢሰጥ ፈጽሞ አይንቁትም፡፡
|
|
እመ ይሰድዱክሙ እም አሐቲ ሀገር ጉዩ ኀበ ካልዕታ፡,ካንዱ አገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌካው ሽሹ
|
|
እም ተናግሮ ይሄይስ አርምሞ፡,ከመናገር ዝም ማለት ይሻሳል፡፡
|
|
እምነ መንግሥት የዐቢ ክህነት,ከቤተ መንግሥት ቤተ ክህነት ይበልጣል፡
|
|
እምነ ረፃብ የሄይስ ኩይናት፡፡,ከረሀብ ጦርነት ይሻሳል፡፡
|
|
እም ንጉሥ እቡድ ይቴይስ ገብር ጠቢብ፡፡,ከሰነፍ ንጉሥ ብልሀ አገልጋይ ይሻካል።፡
|
|
እም አሐዱ አፍ ይወጽኡ ቡራኬ ወመርገም፡,እርግማንና ምርቃት ከእንድ አፍ ይወጣሉ፡፡
|
|
እም እፈ በላዒ ወጽአ መብልዕ፤ ወእም አፈ ኃያል ተረክበ ጥዑም፡፡,ከበላተኛ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ፡፡
|
|
እም ከመ ተፈስሐ ልብ ይበርሀ ገጽ፡፡,ልብ ሲደስት ፊት ይበራል፡፡
|
|
እም ከመ ኀዘነ ልብ ይዴምን ገጽ፡,ልብ ሲያዝን ፊት ይጠቁራል።፡
|
|
እም ድኅረ ሞቱ ለስብእ አልቦቱ ንስሐ፡፡,ስው ከሞተ ንስሐ የሰውም፡
|
|
እም ዙሉ ምግባረ ጽድቅ የዓጽብ ጽሙና፣ ወእም ኩሉ መዓርግ ይትሌዓል ብሕትውና።,ከጽድቅ ሥራ ሁሉ ጭምተኝነት፣ ከማዕረግም ሁሉ ምንኩስና ይበልጣሉ፡፡
|
|
እስመ ሰውዳሴኒ ክንቱ ይልዕካ ዝሙት፡፡,ውዳሴ ከንቱን ዝሙት ይልካታል፡፡
|
|
እስመ ልብሱ ለሥጋ ሞገሱ,ልብስ ለሰውነት ክብሩ ነው፡፡
|
|
እስመ መብልዕ ወመስቴ ያስተፋቅር፡፡,ምግብና መጠጥ ያዋድዳል፡፡
|
|
እስመ ስሙ ይመረሖ ኅበ ግብሩ፡፡,ስሙ ወደ ሥራው ይመራዋል፡፡
|
|
እስመ በብዝኃ ጥበብ ብዙኅ ኀዘን፡፡,በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛል፡፡
|
|
እስመ በትህትና ረከበ ልዕልና፡፡,በትህትና ክብርን አገኘ፡
|
|
እስመ በአሐዱ ፍቁር ይስሀብ ካልኡ፡፡,በአንዱ ፍቅር ሌላው ይሳባል፡
|
|
እስመ ተፋቅሮ ይደፍኖን ለኩሎን ኃጣውአ፡፡,ፍቅር በደልን ሁሉ ይፍቃል፡፡
|
|
እስመ ነፍስ ተሐድር በደም፡፡,ነፍስ በደም ታድራለች፡፡
|
|
እስመ ነፍስ ተዓጽብ እምሲሲት፤ ወሥጋ የዓጽብ እም ዓራዝ፡፡,ሥጋ (ስውነት) ከልብስ ነፍስም ከምግብ ይበልጣሉ፡፡
|
|
እስመ አልቦ ነገር ዘይስአኖ ሰእግዚአብሔር፡፡,ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የሰም፡፡
|
|
እስመ እም ቃልከ ትጸድቅ ወእም ቃልከ ትትኳነን፡፡,በአነጋገርሀ ይፈረድብሀል፤ ወይም ይፈረድልሀል፡፡
|
|
እስመ እምተረፈ ልብ ይነበብ አፍ።፡,ከልብ ሞልቶ የተረፈውን እፍ ይናገራል፡፡
|
|
እስመ ዘአፍቀረ ይጌሥጽ እግዚአብሔር፡፡,እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻል።፡
|
|
እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት ።,ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት፡፡
|
|
እስመ ኩሉ ለቤቱ ይሄሊ።,ሁሉም ለቤቱ ያስባል፡፡
|
|
እስመ ኩሉ ጾሮ ይጸውር፡፡,ሁሉም እዳውን ይሸከማል፡፡
|
|
እስመ ቁር ወረሃብ ያረስዕ ጸሎተ፡,ብርድና ረሃብ ጸሎትን ያስረሳል፡፡
|
|
እስከ ማዕዜኑ ተሐነከሱ በክልዔሆን ጌጋያቲክሙ?,በሁለት ሃሳብ እለከ መቸ ታነከሳሳችሁ?
|
|
አቀትሎ ለኖላዊ ወይዘረዉ አባግዒሁ።፡,እረኛውን እገድለዋለሁ፤ በጎቹም ይበተናሉ፡፡
|
|
እንበለ መከራ፤ ኢይትረከብ ጸጋ፡፡,ያሰመከራ ጸጋ፤ ያለ ድካም ዋጋ አይገኝም፡፡
|
|
እንበለ ዝናም ደመና፤ እንበለ ንጽህ ምንኩስና:,ያለዝናብ ደመና፤ ያሰንጽህና መንኩስና፡፡
|
|
እንተ ኢትልህቅ ጣዕዋ ትመርሕ እማ፡፡,የማታድግ ጥጃ እናቷን ትመራለች፡፡
|
|
እንዘ ቦ ልሂቅ ኢይትናገር ደቂቅ፡፡,አዋቂ ሽማግሌ እያለ ልጅ አይናገርም፡፡
|
|
እንዘ ቦ ርሁብ ውስተ ቤትከ አታውጽእ አፍእ፡፡,ከቤትህ ራብተኛ እያለ ውጭ አውጥተህ አትስጥ።
|
|
እኩይ ብእሲ ያወጽኣ ለእኪት እም እኪት መዝገበ ልቡ።,ክፉ ስው ከክፉ ልቡ ክፋቱን ያወጣታል
|
|
እክል ያጸንእ ኃይለ ሰብእ።,እህል (ምግብ) የለውን ኃይል ያጠነክራል፡፡
|
|
እድ ጽኑእ ብእሴ ያብዕል፡፡,የትጉህ እጅ ታበለጽገዋለች፡፡
|
|
እግዚአብሔር ወኀበ ወአግዚአእብሔር ነሥአ፡፡,እግዚአብሔር ለጠ፤ እግዚአብሔር ነሳ፡፡
|
|
እጽብሰ እጹብ ውእቱ፤ እሰመ ለእጹብ ትርጓሜ እልቦቱ፡፡,እጹብ እጹብ ነው ለእጹብ ትርጉም የለውም፡፡
|
|
ኦሆ በሀሊ፡፡,አሽ ባይ።
|
|
ከመዝ ንግሩ፤ ወከመ ዝ ግበሩ፡፡,እንዲህ ንገሩ፤ እንዲህ ሥሩ።
|
|
ከንቱ ውዳሴ፡፡,የማይገባ ምስጋና
|
|
ኩኑ ቅዱሳነ፤ እሰመ አነሂ ቅዱስ አነ።,እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሶች ሁኑ፡፡
|
|
ኩኑ ከመ ይእዜ እለ ተወልዱ ሕጻናት,ዛሬ እንደ ተወለዱ ሕጻናት ሁኑ።
|
|
ኩኑ ጠቢባነ ከመ እርእዌ ምድር፤ ወየዋሃነ ከመ ርግብ፡፡,እንደ እባብ ብልህ፤ እንደ ርግብ የዋህ ሁኑ።
|
|
ኩን መሃይምነ እስከ ለሞት፡።,እለከሞት ድረስ የታመንከ ሁን፡፡
|
|
ኩን ጠቢበ ለእድውከ,ለባለንጋራህ ብልህ ሁንበት፡።
|
|
ካህናቲከ ይለብሉ ጽድቀ።፡,ካህናቶችህ ጽድቅን የጎናጸፋሉ።
|
|
ካህን ይነብር በየማነ ንጉሥ፡፡,ካሀን በንጉሥ ቀኝ ይቀመጣል፡፡
|
|
ከቡር ሞቱ ለጻድቅ፡፡,የደግ ሰው ሞት የከበረ ነው፡፡
|
|
ከቡር እውስቦ በኩለሄ ወለምስካቡኒ አልቦቱ ስእበት፡፡,መጋባት በሁሉም ዘንድ ከቡር፤ መኝታውም ቅፃዱስ ነው፡፡
|
|
ኮከብ እም ኮከብ ይሄይስ ክብሩ,በክብሩ ኮከብ ከኮከብ ይበልጣል፡፡
|
|
ወለሊሁ ሠይጣን ይትሜሰል ከመ መልአከ ብርሃን፡፡,ሳይጣን ራሱ የብርፃን መልእከን እስኪመሰል ይለወጣል፡፡
|
|
ወለእመ ሖርከ ብሔረ ባዕድ ኩን ከማሆሙ።፡,ሌላ አገር ብትሄድ እንደ እነሱው ሁን
|
|
ወለእመ ይለድድዱክሙ እም አሐቲ ሀገር ጉዩ ኅበ ካልዕታ፡፡,ካንዱ ሀገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌላው ሽሹ።፡
|
|
ወለደቂቀ መንግሥትሰ ያወጽእዎሙ አፍኣ፡፡,የመንግሥትንም ልጆች ወደ ውጭ ይጥሏቸዋል፡፡
|
|
አግዚእ አእምሮ በጠጅ፣ እነወለቡ በደጅ፡፡,ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፡፡
|
|
ወሙጻኡ ለቅስት የሃልቅ በመሐላ፡፡,ከርክር በመሐላ ይዘጋል፡፡
|
|
ወቀላለ ኮነት ዘመንየ ከመ ነገረ ከየአንም፡፡,ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይቸኩላል፡፡
|
|
ወቀደምትኒ ይከውኑ ድኅረ፡፡,ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ፡፡
|
|
ወትወርድ አመጻሁ ዲበ ድማሁ፡፡,ክፋቱ በራሉ ላይ ትደርሳለች፡፡
|
|
ወነገረ ቢጽ ኢይጥዕሞ ስሰቢጹ፡፡,የባልንጀራው ሃሰብ ለባልንጀራው አይጥመውም፡፡
|
|
ወነገርከ ያዔውቀከ፡፡,አነጋገርህ ማንነትህን ይገልጽብሃል፡፡
|
|
ወኢይጻእ ዐቢይ ነገር እም አፉክሙ፡፡,ክፉ ነገር ካፋችሁ አይውጣ፡፡
|
|
ወእምኩሉ የዐቢ ተፋቅሮ፡፡,ከሁሉም ፍቅር ይበልጣል
|
|
ወክልዔቴ ይስድድዎሙ ለእልፍ፡፡,ሁሰቱ ሺህዎቹን ያሳድዷቸዋል፡፡
|
|
ወዘአዝለፊ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን፡፡,ትዕግሥትን ያዘወተረ እርሱ ይድናል፡፡
|
|
ወያገብእ እሁ እኅዋሁ ለሞት፡,ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል
|
|
ወይን ወማኅሌት ያስተፌስሁ አልባበ፡፡,ወይንና ማኅሌት ልብን ያስደስታሉ፡፡
|
|
ወይን ያስተፌስሕ ልበ ለብእ፡፡,ወይን ጠጅ የሰውን ልብ ያስደስታል፡፡
|
|
ወድሶ ለለብእ በዘይደሉ፡፡,ስውን በሚገባው አመስግነው፡፡
|
|
ወኩሉ ዘተጽሕፈ ሰተግሣጸ ዚእነ ተጽሕፈ፡፡,የተጻፈው ሁሉ እኛ አድንመከርበት ተጻፈ።
|
|
ውሂብሰ እም ልማድ ውእቱ፡፡,መስጠት ከመልመድ ይመጣል፡፡
|
|
ውሂብሰ እም ረኪብ ውእቱ፡፡,መስጠት ከማግኘት ይመጣል፡፡
|
|
ውሂብ እም ድኅረ ስኢል እስረተ እድ ውእቱ፤ ወውሂብስ ቅድመ ስኢል ፈቲሐ እድ ውእቱ።,ከተለመኑ በኋሳ መስጠት እጅ መታሠር፤ ሳይለመኑ መስጠት ልግስና ነው፡፡
|
|
ዐቃቤ ሥራይ ፈውስ ርእሰከ፡፡,ባለ መድኃኒት ሆይ! ራስህን ፈውስ፡፡
|
|
ዓስምስ ያፈቅር እሊእሁ፡፡,ዓለም የራሱ የሆኑትን ይወዳል፡፡
|
|
ዕብን ዘመነንዋ ነደቅት፤ ወይእቲ ኮነት ውስተ ርእስ ማዕዘንት፡፡,አናጢዎች የናቋት ድንጋይ እርሷ የማዕዘን ራስ ሆነች፡፡
|
|
ዕውር ለዕውር ይትማርሑ ወይወድቁ ውስተ ግብ፡፡,ዕውር ዕውርን ቢመራ ተያይዞ ገደል፡፡
|
|
ዕውር ኢይባእ ውለተ ዝማሜ ወመሳጣ አይሠራዕ ጋሜ፡፡,ዕውር አይዘም፣ መላጣ ጋሜ አይሠራ፡፡
|
|
ዘላዕለ ነፍሱ ይኤብስ ለመኑ ኄረ ይከውን?,ራሉን የሚነፍግ ለማን ቸር ይሆናል?
|
|
ዘልህቀ በውስቴታ፤ የአምር ሥርዓታ፡፡,በውስጧ ያደገ ሥርዓቷን ያውቃል፡፡
|
|
በመሀሩክሙ ዕቀቡ ወዘከመ ምግባሮሙሰ ኢትግበሩ።,ያስተማሯችሁን ተግብሩ፤ የሚሠሩትን ግን አትሥሩ፡፡
|
|
ዘምር በመጠንከ,በልክ ዘምር!
|
|
ዘምስለ ጠዋይ ተጠዊ፤ ወምስለ ኅሩይ ኅሩየ ትከውን፡,ከጠማማ ጋር ጠማማ ከቀና ጋር ቀና ትሆናለህ፡፡
|
|
ዘረከበ ብአሲተ ሄርተ ረከበ ሞገስ፡፡,ቸር ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፡፡
|
|
ዘሰ በዐቅሙ ይበልዕ ጥዑይ ነፍሱ፡፡,መጥኖ የሚበላ፣ ጤውነቱ ጤና፡፡
|
|
ዘበውሁድ ምዕመን በብዙኅኒ ምዕመን፡፡,በትንሹ የታመነ በብዙዉም ይታመናል።
|
|
ዘቦ ብዙኅ ኢያትረፈ፤ ወዘቦ ውጉድ ኢያኅጸጸ።,ብዙ ያለው አልተረፈውም፤ ትንሽ ያለውም አልጎደለበትም፡፡
|
|
ዘተወክፈ ጻድቀ በስመ ጻድቅ፣ ዐስበ ጻድቅ ወእሴተ ጻድቅ ይረክብ፡፡,ጻድቁን በጻድቁ ስም የተቀበለ የጻድቁን ዋጋ ያገኛል፡፡
|
|
ዘኀሠሠ ክልዔ ኢይረክብ አሐደ፡፡,ሁለት የሻ አንድም አያገኝ
|
|
ዘኒ ትፈቅዱ ይግበሩ ለክሙ ሰብእ አንትሙኒ ግበሩ ሎሙ፤ ወዘኒ ኢትፈቅዱ ይግበሩ ብክሙ ኢትግበሩ ቦሙ,ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትሹትን አድርጉላቸው፤ ቢያደርጉባችሁ የምትጠሱትንም አታድርጉባቸው፡፡
|
|
ዘንስቲት ባቲ፤ ዕረፍት አልባቲ,ትንሽ ያላት፣፤ ዕንቅልፍ የላት፡፡
|
|
ዘአሀዙ ወርቀ ወዘኢአህዙ፣ ክልዓሆሙ ኅቡረ ተከዙ።፡,ወርቅ የያዙትም ሆኑ ያልያዙት በአንድነት አዘኑ።፡
|
|
ዘአልቦ ብእሲት ምንዱብ ውእቱ፡፡,ሚስት የሌለው የተበደለ ነው፡፡
|
|
ዘአልቦ ኃጢአት ለይገራ፡፡,ኃጢአት የሌለበት ይውገራት፡፡
|
|
ዘአልቦ ጽልቱጉት፡፡,ማስመስል የሌለበት፡፡
|
|
ዘአልዐለ ርእሶ የኃስር፤ ወዘአትሀተ ርአሶ ይከብር,ራሱን ከፍ ከፍ ያደረገ ይዋረዳል፤
|
|
ከኢተሰምዐ ተሰምዐ፤ ዘኢተገብረ ተገብረ፡፡,ያልተለማ ተለማ፤ ያልተደረገ ተደረገ፡፡
|
|
ዘኢተገብረ ለመላአክት ተገብረ ለካህናት፡፡,ለመላእክት ያልተደረገው ለካህናት ተደረገ
|
|
ዘኢኮነ ዕድውክሙ ቢጽክሙ ውአቱ፡፡,የማይቃወመን እርሱ ከኛ ጋር ነው፡፡
|
|
ዘኢይክል ሠሪዐ ቤቱ እፎ ያስተሐምም ቤተ አግዚአብሔር?,የራሱን ቤት በሥርዓት ያላደራጀ ቤተ አግዚአብሔርን እንዴት ያስተዳድራል?
|
|
ዘኢይፈቅድ ይትጌበር ኢይሴሰይ፡፡,ሊሠራ የማይወድ አይብላ፡፡
|
|
ዘእም ተረፈ ልብ ይነብብ አፍ፡፡,ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል፡፡
|
|
ዘአግዚአብሔር አስተጻመረ ኢይፍልጥ ሰብእ፡፡,አግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው አይለየው፡፡
|
|
ዘከዐወ ደመ ሰብኣ ይትከዐው ደሙ፡፡,የሰው ደም ያፈሰሰ ደሙ ይፈሳል።፡
|
|
ዘክልዔ ልቡ ህዉክ ውአቱ።፡,መንታ ልብ ያሰው የታወከ ነው፡፡
|
|
ዘወጠነ ይፌጽም፡።,የጀመረ ይፈጽም፡፡
|
|
ዘዐቀበ አስኪቶ የዐቅብ ህይወቶ፡፡,ህፍረተ ሥጋውን የጠበቀ፣ ህይወቱን ጠበቀ፡፡
|
|
ዘዘገኑ ወርቀ ወዘኢዘገኑ፤ ክሌዔሆሙ ኅቡረ ኀዘኑ።፡,ወርቅ ያገኙም አዘኑ፤ ያላገኙም አዘኑ፡
|
|
ዘየሐውር መርድአ የኀሥሥ ምክንያተ፡፡,የሚሄድ ተማሪ ምክንያት ይሻል
|
|
ዘየዓቅብ አፋሁ ይትመሐፀን ነፍሶ፡፡,አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፡፡
|
|
ዘያፈቅር ቢጾ ውስተ ብርሃን ይነብር ።,ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል።
|
|
ዘይትናገር ዘኢይደልዎ ይሰምዕ ዘይጸልኦ።፡,የማይገባውን የሚናገር የማይወደውን ይሰማል፡፡
|
|
ዘይከሪ ግበ ለቢጹ ይወድቅ ውስቴቱ፡፡,ለጓደኛው ጉድጓድ የሚቆፍር ራሉ ይወድቅበታል፡፡
|
|
ዘይወጽእ እም አፉሁ ለሰብእ ውእቱ ያረኩሶ።፡,ካፉ የሚወጣው ስውን ያረክሰዋል፡፡
|
|
በድኅረ መጽአ ዐይነ አውጽአ፡፡,ከኋላ የመጣ ዐይን አወጣ፡፡
|
|
ዘጸንአ ዴዴሃ ይበልዕ ፍሬሃ,ደጅ የጠና ፍሬውን ይበላል፡፡
|
|
ዘጻመወ በዓለም የሐዩ ለዝሉፉ፡,በዚህ ዓለም የደከመ ለዘላለም ህያው ይሆናል፡፡
|
|
ዚአከ ለዚአየ፤ ዚአየ ለዚአከ፡፡,አንተ ለኔ እኔ ላንተ፡፡
|
|
ዛቲ ተግሣጽ ትኩነኒ እምዮም፡፡,ከዛሬ ጀምሮ ይች ተግሣጽ ትዝ ትበለኝ፡፡
|
|
ዝልፎ ለጠቢብ ከመ ይዌስክ ጥበበ፤ ኢትዝልፎ ለአብድ ከመ ኢይጽላእከ፡፡,ብልህን ገሥጸው ጥበብን ይጨምራል፤ ሞኝን አትገሥጸው አንተኑ ይጠላሃል፡
|
|
ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ።,የደግ ሰው ሥራ ለዘላስም ይኖራል
|
|
ዝ ኩሉ ሥርጋዌ በአንተ አሐዱ ነገር፡፡,ይህ ሁሉ መሽሞንሞን ለላንድ ጉዳይ ነው፡፡
|
|
የሀጉል ርአሶ ዘኀልያነ ይነሥአ፡፡,መማለጃን የሚጠላ በሕይወት ይኖራል፡፡
|
|
የአምነከ ሰብአ ሶበ ታሴኒ ሎቱ፡።,ሰው ስትውልለት እምነት ይጥልብሃል፡፡
|
|
ያኃሥረከ በአኅደርኮ፤ ወይዘረክየከ ዘለቃሕኮ፡፡,ያሳደርከው ያዋርድሀል፤ ያበደርከው ይሰድብሀል፡፡
|
|
ያዕቆብሃ አፍቀርኩ፤ ወኤሳውዛ ጸላእኩ,ያዕቆብን ወደድኩ፤ ኤሳውን ግን ጠላሁ፡፡
|
|
ይቤ አጋግ «ከመ ዝኑ ሞት መሪር»,«በውነት ሞት አንዲህ መራር ነውን» አጋግ፡፡
|
|
ይብሉ «ሰላም ሰሳም!» ወአልቦ ስላም፡፡,«ሰላም ስላም!» ይሳሱ ሰላም ግን የላቸውም፡፡
|
|
ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር,ሰነፍ በልቡ አምላከ የለም ይላል፡፡
|
|
ይብእስከ ረጊጽ ውስተ ቀኖት በሊህ።፡,የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተው ይብስብሃል፡
|
|
ይትወለወል ሰብእ እም ገዜ ልደቱ እስከ ጊዜ ሞቱ፡፡,ሰው አሰኪሞት ድረሰ ሲያመነታ ይኖራል፡፡
|
|
ይሄይስ ህዳጥ ዘበጽድቅ አምብዙኅ ብዕለ ኃጥአን,በዓመፅ ከተሰበሰበው ከብዙው፤ በሥራ የተገኘው ትንሹ ይበቃል፡
|
|
ይሄይስ ብሂም እምነቢበ ሀሰት፡።,ውሸት ከመናገር ዲዳነት ይሻላል።፡
|
|
ይሄይስ ብእሲ ዕጉስ እም ኃያል,ከኃይለኛ፤ ይሻላል ትዕግሥተኛ፡፡
|
|
ይሄይስ ነዳይ ጥዑይ ሥጋሁ ወፍቱሕ ነፍሱ፤ እምነ ባዕል ዘድውይ ሥጋሁ ወእሱር ነፍሱ፡,ሰውነቱ ከታመመና ሆዱ ከታሰረ ባለጸጋ ሰውነቱ ጤነኛ የሆነና ሆዱ የተከፈተ ደሀ ይሻላል
|
|
ይሄይሰ አሐዱ እም ፲ ፻፤ ወይሄይስ መዊት ዘእንበሰ ውሉድ እም ወሊድ ወልደ እኩየ፡፡,ከሺዎች ይልቅ እንድ አዋቂ ልጅ ይሻላል፤ ከፉ ከመውለድም ሳይወልዱ መሞት ይሻላል፡፡
|
|
ይሄይስ አርክ ቅሩብ እም እሁ ዘርቀ የኀድር።,ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት፡፡
|
|
ይሄይስ ፍተ ሐምል ፍቅር ዘቦቱ አመግዝዕ ዘአልህምት፡፡,የጎመን ወጥ በፍቅር መብላት ጥል ባበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል፡፡
|
|
ይኩን ኩሉ ብእሲ ፍጡነ ለሰሚዕ፤ ወጉንዱየ ለነቢብ ወለመዓት፡፡,ለው ሁሉ ለማዳመጥ ፈጣን፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየ ይሁን፡
|
|
ይወድስከ አፈ ነኪር ወአኮ አፈ ዚአከ,ራስክን አታወድስ! ሌላው ያመስግንህ እንጂ
|
|
ይደልዎ ለዘያነብብ ይዝክር ስሞ ለበዓሰ መጽሐፍ,አንባቢ የባለ መጸሐፉን ስም ሊያስታውስ ይገባዋል፡፡
|
|
ይደልዎ አስቡ ለዘይትቀነይ።፡,ለሠራተኛ ደመወዙ የገባዋል፡፡
|
|
ይጹም ዐይን፤ ይጹም ልሳን፤ ዕዚንኒ ይጹም።፡,ዐይን ይጹም፤ አፍ ይጹም፤ ጆሮም ይጹም፡፡
|
|
ድልዋኒክሙ ንበሩ!,ተዘጋጅታችሁ ኑሩ!
|
|
ድክምት ቃል ትሰብር አጽመ,የተለሳለስች ቃል እጥንት ትለብራለች፡፡
|
|
ገብአተኒ ወርቅየ፡፡,ገንዘቤን አገኘኋት፡፡
|
|
ጊዜሁ ለመብልዕ ረሃብ ወለስትይ ጽምእ፡,የመመገቢያ ጊዜው መራብ፣ የመጠጫም ጊዜው መጠማት ነው፡፡
|
|
ጊዜ ሰአልኩከ ጸግወኒ ፍታ፤ እስመ ኢየአምር ስብእ ዘትወልድ ሳኒታ፡፡,የስው ልጅ ነገ የሚሆነውን አያውቅምና በለመንኩህ ጊዜ የዕለት እንጀራየን ስጠኘኝ፡
|
|
ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡፡,እግዚአብሔር የሥራ ጌዜ አለው፡፡
|
|
ጌሰምሰ ትሄሊ ለርእላ፡፡,ነገ ሰለ ራሷ ታስባለች፡
|
|
ግብር ዘአልቦ ምጣኔ ገዐር ውዕቱ፡፡,ልክ የሌለው ሥራ ብክነት ነው፡
|
|
ጠቢብ ገብር ይሜብል እግዚኡ፡,ጥበበኛ ባሪያ ጌታውን ይገዛል፡፡
|
|
ጥበብ ትትበደር እምወርቅ፡፡,ከገንዘብ ጥበብ ትመረጣለች፡፡
|
|
ጥበብ ትሄይስ እመኩሉ መዛግብት፡፡,ከሀብት ሁሉ ጥበብ ትበልጣለች፡፡
|
|
ጸላእተከሙ አፍቅሩ።,ጠላቶቻችሁን ውደዱ።፡
|
|
ጸሎቱ ለመስተቀይም ኢውክፍት ቅድመ እግዚአብሔር፡,የቂመኛ ጸሎት በአግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የለውም
|
|
ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመ ዘርዕ ዘወድቀ ማዕከስ አስዋክ፡፡,የቂመኛ ጸሎት ከእሾህ ላይ እነደ ወደቀው ዘር ነወ
|
|
ጸጋ በዲበ ጸጋ፡፡,በጸጋ ላይ ጸጋ፡፡
|
|
ጻማ ከናፍር፡፡ ,ጉንጭ አልፋ፡፡
|
|
ጻድቅስ ይምሕር ወይሁብ፡,ደግ ይራራል፤ ይሰጣልም፡፡
|
|
ጽጋብ ያመጽእ ግብረ ቅንጻዌ! ወቅንጻዌ ያፈደፍድ ደዌ,ጥጋብ ያዘልላል፤ ዝላይም ለከፋ ሕመም ያጋልጣል፡፡
|
|
ፀሩ ለከርሥ አፍ፡፡,የሆድ ጠላቱ አፍ ነው፡
|
|
ፈታሒ በጽድቅ ኩናኒ በርትዕ፡፡,እውነት ፈራጅ ቅን ገዥ፡፡
|
|
ፍሬ ከናፍር።,የንግግር ፍሬ ቃል፡፡
|
|
ፍዳ ለኃጥአን ዕሴት ለጻድቃን፡፡,ለኃጥእን ቅጣት፤ ለጻድቃን ሽልማት፡፡
|
|
ፓፓ ዘኢይስሕት፡፡,ፓፓዉ አይሳቱም፡፡
|
|
ኩሉ ማእምር፣ ይገብር በምክር፡፡,ዐዋቂዎች ሁሉ ተማክረው ይሠራሉ፡፡
|
|
ኩሉ ቡሩክ፡፡,ሁሉ መልካም፡፡
|
|
ዙሉ ነፍስ ይሴብሖ ለእግዚአብሔር።,ነፍስ ሁሉ እግዚእብሔርን ያመሰግናል፡፡
|
|
ኩሉ ንጹሕ ለንጹሓን፡፡,ለንጹሖች ሁሉም ንጹሕ ነው፡
|
|
ኩሉ ከንቱ፡፡,ሁሉም ከንቱ ነው፡፡
|
|
ኩሉ ዐረየ ወኅቡረ አለወ,ሁሉም ተባበሮ ከፋ፡፡
|
|
ዙሉ ዕፅ ዘኢይፈሪ ፍሬ ሠናየ ይትገዘም፤ ወውስተ እላት ይትወደይ፡፡,መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል፡
|
|
ኩሉ ዘነፍስ፤ ይበሊ ከመ ልብስ፡፡,ሰው ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃል፡፡
|
|
ኩሉ ዘገብራ ለሠናይት ይረከብ ሠናየ፡,መልካም የሠራ መልካም ነገር ያገኛል፡፡
|
|
ኩሉ ይሴኒ ሰአመ ንሴኒ ንህነ,እኛ ጥሩ ከሆን ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል፡፡
|
|
ኩሉ ይሄሊ ትካዘ ርእሱ፡፡,ሁሉም የራሱን ጭንቅ ያሰባል፡፡
|
|
ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱፅ፡፡,መልካም ጊዜ ሁሉም ደግ ይሆናል፡፡
|
|
ኩሎ አመክሩ ወዘሠናየ አጽንኡ,ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ።
|
|
ጐንዱየ እብጽሕ እገሪከ ኀበ እርከከ፤ ከመ ኢይጽገብከ፤ ወኢይጽላእክ፡፡,እንዳይሰለችህ፣ እንዳይጠላህም የባልንጀራህን ቤት አታዘውትር፡፡
|
|
ጉየያ ለፍትወተ ውርዙትከ፡፡,የወጣትነት ፍላጎትህን ሽሻት፡፡ |