Proverb
stringlengths 4
244
|
---|
መቀመጥ መቆመጥ። መቀመጥ በአልጋ፥ ታላቅ ደጋ። |
መቀመጥ ቦና ነው፤ መኼድ በልግ ነው። መቀመጫዬ ይብሳል አለ ዝንጀሮ። |
መቀመጫዬ ይቅደም አለች። ዝንጀሮ፥ በሰው ክምር ይዳዳር። ዝንጀሮ ቢሰበሰብ ውሻን አይመክትም። |
መቀናጆ የላለው በሬ፤ ለምድ የላለው ገበሬ። |
መቃ እንዱያ ሲያምር አያፈራ፤ ወርቅ ቢሞላ አይራ። መቃብሩ የተቆፈረለት፤ መግነዙ የተጋጀለት። |
መቃን ከመግጨት፥ ዝቅ ብል መግባት። መቃደን ታጥቆ፤ መቋሚያውን ነጥቆ። መቃጀትና መስከር፤ ላይመልሱ መበደር። መቅረቧን ሳታውቅ፥ እጇን ታጠበች። መቅደስ የገባ አይወጣ፤ ከል የገባ አይነጣ። |
መበለት በቄስ፤ ገበሬ በንጉሥ፤ ደብተራ በጳጳስ ቢቀኑ አይገናኙ። መብሉ እኩል፤ ሥራው ስንኩል። |
መብላት ከኹለት፤ መፍረድ በእውነት። (በእውነት ~ በእውነቱ) መብላት ከባዕድ፤ ምክርን ከመድ። |
መብላት ያስለመድከው ሰው፥ ሲያይህ ያዚጋል። |
መብላቷን ሳታውቅ፥ እጇን ታጠበች። (ሳታውቅ ~ አላወቀች) መብላቷን አላወቀች፥ እጇን ታጠበች። |
መብላን ሰንቆ፤ ምርኩዛ ሸንበቆ። መብላን ይዤ፤ ቅልውጤን ረሳኹት። መብል ያለ መጠጥ፤ እንጀራ ያለ ወጥ። መብልን ለቁራ፤ ጩኸትን ለአሞራ። መብልን ከሰው ቤት፤ መኝታን ከቤት። መብልን ከባዕድ፤ ኀንን ከመድ። መብልን ይዤ፤ ቅልውጤን ረሳኹት። |
መብረቅ ሲመታው፥ እሳት ይህ አባብለው። መብረቅ የመታውን፥ ወት አስተኛው። |
መብራት ለጨለማ፤ አፍንጫ መያዝ እንዳይገማ። መተው ነገሬን ከተተው። |
መታለል፥ ገደል መንከባለል። መታዝ፥ ከመሥዋዕት ይበልጣል። |
መታፈር በከንፈር። |
መታዝን ሳያውቁ ማዝ፥ ታላቅ መዝ። መታዝን የማያውቅ፥ ማዝን አይችልም። መታጠቂያዬን አጥብቁልኝ። |
መቶ ኹለት መቶ ሲያወጣ ፈረስ፥ በመቶ ተሸጠ የሰው አጋሰስ። መቸም ጨዋታ ነው፥ ውሽማሽ ማን ነው? አለ ያ ሰውየ። መቸር፥ እጅ ሲያጥር። |
መቼ መጣሽ ሙሽራ? መች ቆረጠምሽ ሽንብራ? ( መች ~ መቼ) መቼ ገባህ ፊት፤ ምን በላህ ፍትፍት። |
መቼም አላለልኝ፥ ከሬ ቁዪልኝ። መቼም አላማረበት፥ እሪበት። |
መች ተጽፎ ትችት፤ መች ተወግዝ ሙግት። |
መነኰሴ በቆቡ፤ ወንበር በክታቡ። (በክታቡ ~ በክታብ) መነኰሴ ቤት ሲሠራ፥ ሀረግ ትሸሸጋለች። |
መነኰሴ ከአልሞተ፤ ስንዳ ከአልሸተ አይታወቅም። መነኰሴ ከደብሩ፤ አንበሳ ከደሩ ወጥተው ከአደሩ። መነዚነዝ ያመጣል መዝ። |
መነገድ ለማትረፍ፤ መማር ለመጻፍ። መናኝ ለነፍሱ፤ አዳኝ ለጥርሱ (ይገሰግሱ)። |
መናኝ ዳዋ ለብሶ፤ ጤዚ ልሶ፤ ድንጋይ ተንተርሶ (ይኖራል)። መናከስ ከአልቻልክ፥ ጥርስህን አታሳይ። |
መናጆ የላለው በሬ፤ ደበል የላለው ገበሬ። (ደበል ~ ለምድ) መናገር መልካም ነው፥ ማዳመጥ ይበልጣል። |
መናገር ሳያስቡ፤ ምላጭ መሳብ ሳያልሙ። መናገር ብር ነው፤ ዝምታ ወርቅ ነው። |
መናገር የለመደ ምላስ፤ መታገም የለመደ ራስ። መናፍቅ ለትርሜ፤ ትንባሆ ለልምላሜ። መንቀጥቀጥ፥ እንደ ወላድ ምጥ። |
መንቻካ ሴት፥ አትሆንም ባለቤት። መንካት፥ ያደርሳል ከመነካት። |
መንዛ ራቱ በጊዛ፥ ምሳው ኹለት ጊዛ። |
መንዛ እንደሚለው፥ እስኪ ከቁርበቴ ልምከር። መንደር በልጆች፤ አገር በገበሬዎች። |
መንደር ከዋለ ንብ፤ አደባባይ የዋለ ዝንብ (ይሰለጥናል)። መንገደኛ ከሥንቁ፤ ነጋዳ ከወርቁ። |
መንገደ ቀቀኝ ቢለው፥ ሱሪህን ተንተራሰው ብል መለሰለት። መንገደ፥ የተልባ ወጥ ይኹንልህ። |
መንገድ ለቀደመ፤ ውሃ ለገደበ። መንገድ ሳለ በደር፤ በቅል ሳለ በእግር። መንገድ፥ በሀሳብ አይደረስም። |
መንገድ በወሬ፤ ጠላ በአቦሬ። መንገድ በጠዋት፤ ሚስት በልጅነት። |
መንገድ ከሀገር ልጅ፤ ምክር ከጨዋ ልጅ። መንገድ ከሀገር ልጅ፤ ስደት ከሹም ልጅ። መንገድ ከመንገድ ያደርሳል። |
መንገድ ወጭ፥ ከላባ ቤት አብሮ ይኑር። |
መንገድ የምታውቅ አይጥ፥ ከፈረስ የበለጠ ትሮጣለች። መንግሥቴን የነሡ፤ ክብሬን የወረሱ። |
መንገድ፥ ከሽንት ይቀራል። |
መንግሥት አልሰማ ሲል ዓመታት፤ ሕዝብ አልሰማ ሲል ዕለታት። መንፈሱ አልበጀ፤ ውቃቢው ሰው ፈጀ። |
መንፈራገጥ ለመላላጥ። መኖሪያዋን ትታ መዝሪያዋን። መኖሪያውን ትተው መናገሪያውን። መኖር ማለት ብርሃንና መሰንበት። መኖር ማለት ብርሃንና መስተዋት። መኖር በከንቱ፥ ሰው አለቤቱ። መኖር በከንቱ፥ ያለ ባለቤቱ። |
መከራ ያልፋል፥ እስኪያልፍ ግን ያለፋል። መከራና አፈር፥ ቢዝቁት አያልቅም። መከራና ዕዳ፤ እንግዳና ሞት በድንገት። መከራና ጉም እያደር ይቀላል። |
መከራን መሸፈን፥ እግዛርን ማመን። መከራን የቻለ አሸናፊ ነው። |
መከራው ያላለቀለት በሬ፥ ከሞተ በኋላ ቆዳው ለነጋሪት ይጠፈራል። መከር ከአልተከተተ፤ መነኰሴ ከአልሞተ። |
መከበር በከንፈር። |
መከፈንና መሸፈን፥ እግዛርን ማመን። |
መካሪ የላለው ንጉሥ፥ አንድ ዓመት አይነግሥ። መካር አይጥፋ። |
መካር የላለው ንጉሥ፥ ያላንድ ዓመት አይነግሥ። መክሮ ልብ አይደል፤ አሟጭቶ ጥርስ አይደል። መክዳትና መኮብለል፤ ወድቆ መንከባለል። |
መክፈልት ሲሹ፥ መቅሰፍት። (መቅሰፍት ~ መቅለፍት) መኮርተሚያን ያላገኘ፥ መርጊያን ተመኘ። መኮርኮሚያ(ን) ያላገኘ፥ መርጊያን ተመኘ። መወለድ ቋንቋ ነው። |
መኼድ መነሣት፤ መከተል መሸኘት። መኼድ በጋ ነው፤ መቀመጥ ክረምት ነው። |
መኼድ የለ ዚቻ ብቻ፤ መሥራት የለ ሀሳብ ብቻ። መኼድ የለመደ፥ ቢቀመጥ ታከተው። |
መኼድ ያማረው፥ እራቱን በጨረቃ ይበላል። መኼድና መምጣት፤ ማግኘትና ማጣት። መኼጃ የላለው፤ መውጫውን ያበስራል። |
መሆን በሆነ፤ ዳሩ ግን ምን ይሆናል፤ አገርህ ሩቅ ሆነ። መለመን የለመደ ምላስ፥ በሕልሙ አቁማዳ ይዋስ። መላ እንደ ሴት፤ ግርማ እንደ ላሉት። |
መወለድ ካለ፥ ማን አይገድም። መዋቀስ መራከስ። |
መዋዕል ለፍስሓ፤ ዕድሜ ለንስሓ። መዋጋት ከድርጅት፤ መብል ከጠቦት። መዋጋት ያብሳል። |
መውረድና ማፍረስ ይቀላል። |
መውደደንስ አንተን እወዳለኹ፤ ኋላ ወዳት እገባለኹ? መውጫህን ሳታይ አትግባ። |
መዝሙር በሃላ፤ ነገር በምሳላ፤ ጠጅ በብርላ። መዝገብ ቢጠፋ ባገር፤ ቤት ቢላላ በማገር። መዝጊያ የላለው ቤት፤ ሴሰኛ ሴት። |
መዥገር፥ ቁም ነገረኛ እንዱባል፥ ቁርበት ላይ ተጣብቆ ይሞታል። መድረሻ ያጣ ደቄት፥ ከነፋስ ይጠጋል። |
መጀመሪያ ስሕተት፤ የኋለኛው እብደት። መጀመሪያ የመቀመጫዬን አለች ዝንጀሮ። መገናኛ ድንበር፤ መሳሳሚያ ከንፈር። መገን አንቺን ይዝ፥ መቻ ነው ጉዝ። |
መገን ይህቺ ዓለም፥ የጀመራት እንጂ፥ የጨረሳት የለም። መገዝገዝ አያርድም። |
መጋኛና በኛ አርፎ አይተኛ። መግረፉን ግረፍ ግን ከባት አትለፍ። መግነዝ ፍቱልኝ፤ መቃብር ክፈቱልኝ። |
መግዚት ቢያምርህ ችላ፤ ጥጋብ ቢያምርህ ጥላ። መት ያከሳል። |
መጠራጠር፥ ያደርሳል ከቁም ነገር። መጠንቀቅ መጠበቅ። |
መጠንቀቅ ከመለጠቅ። መጠየቅ ያደርጋል ሉቅ። |
መጠጊያ ያጣ ደቄት፥ ከነፋስ ይጠጋል። መጠጥ ለጨዋታ፤ ወንድም ለግርግርታ። |
መጠጥ ከጨዋ ልጅ፤ ምክር ከአገር ልጅ። (ከአገር ~ ከድሀ) መጠጥ የጨዋ ልጅ መጫወቻ፥ የባለጌ ልጅ መማቻ። መጠጥና ሴቶች፥ መምህራንን ያስቷቸዋል። |
መጣ ዝም ብል፥ ኼደ ተናግሮ። መጣደፍ መቸኮል፤ መረዋና ደወል። መጣፍ ከመከረው፤ መከራ የመከረው። መጣፍና ተማሪ፤ ቀለበትና ድሪ። መጥረቢያው የተውሶ፥ ጠፋ ተመልሶ። መጥኖ የሚበላ፥ ሰውነቱ ጤና። |
መጥፊያው፥ መልሚያው መስል፥ ይታየዋል ለሰው። መጥፎ ሣር፥ ይለመልማል እንጂ፥ አይጠፋም። መጥፎ ሴት ያገባ፤ በሬው በሠኔ ገደል ገባ። |
መጥፎ ሥጋ ከጥርስ፤ መጥፎ ነገር ከከርስ። መጥፎ ቁራኛ፥ ያለመቃብር አይለቅም። መጥፎ ወሬ ይበራል፥ መልካሙ ይተኛል። መጥፎ ወጥ፥ በጥሩ እንጀራ ይበላል። መጨነቅ፥ የመጠበብ እናት። |
መጫር ያበዚች ድሮ፥ የመታረጃዋን ቢላዋ ታወጣለች። መጫኛና ስልቻ። |
መጭ መጭ፤ ከሚሉት በቅል መጫሚያ። መጭ ብል ቢመጣ፥ ብር ብል ቀደመው። መጽሀፍና ተማሪ፤ ቀለበትና ድሪ። መፍረሱ ላይቀረኝ፤ ለምን ፈጠረኝ። መፍራት ለመታማት። |
መፍታት ሳለ መሞት። |
መዙን ሳታይ፥ መልኩን አይታ። መዚወሪያ ትተህ ብላ። |
ሙሉ ክረምት የአገለገለ፤ በመከር ሰፌድ ያቀበለ። ሙልጭ እንደ ሥብቆ፤ እንጣጥ እንደ ፌቆ። |
ሙሽራ ሳይዙ፥ ሰርገኛ። ሙሽራ በሚዛ፤ ንስሓ በትካዛ። ሙሽራ በሚዛ፤ ንስሓ በኑዚዛ። |
ሙሽራዋስ እኔ ድሮዋን ማን በላት ካለእኔ። |
ሙሽሮች ሲተዋወቁ፥ ምነው ሰርገኛው ልብ መውለቁ። ሙቅ በገንፎ ተደግፎ። |
ሙቅ ውሃና፥ የሰው ገንብ አይጠቅምም። ሙት ለሙት፥ ያለቅሳል። |
ሙት መውቀስ፤ ድንጋይ መንከስ። ሙት ማንሣት፤ ዕውር ማብራት። ሙት፥ ምሥጢር አያወጣም። ሙት አይሰማም፥ አይለማም። ሙት፥ ወደ ሙት ይኼዳል። ሙት ይዝ ይሞታል። |
ሙት፥ ደረቅ አይበላም። |
ሙክት ሲሰባ ካራ ይታከካል፥ ባለጌ ሲከብር ያፎከፉካል። (ካራ ~ ከካራ፥ ያፎከፉካል ~ ይፎከፉካል) |
ሙዙን ሳላይ፥ መዙን። |
ሙዝ ላጥ፥ ዋጥ። (ሙዝ ~ ሙዙን) ሙያ በልብ። |
ሙግት ለአፈኛ፤ አቢቹ ለጌኛ። |
ሙግት ያውቃል ይለቃል። (ይለቃል ~ ይላቀቃል ~ ይልቋል) ሚስቱ ትሻል፥ ብይኗ ያመሻል። |
ሚስቱ ክፉ፥ ባቄላ እራቱ፥ ብሳና ዕንጨቱ፥ ኀን ነው እቤቱ። ሚስቱ ደግ፥ ስንዳ እራቱ፥ ወይራ ዕንጨቱ፥ ደስታ ነው እቤቱ። ሚስቱን ገድል፥ አማቱ ቤት ተሸሸገ። |
ሚስቱን ገድል፥ አማቱ ቤት ተደበቀ። ሚስቱን ጠልቶ ከአማቱ፤ ልጁን ከሶ ከአባቱ። ሚስቱን ጠልቶ፥ ከአማቱ ቤት ተሸሸገ። ሚስቱን ፈትቶ፥ ከአማቱ ቤት ተደበቀ። |
ሚስቴ እንደምትመኝልኝ እንጂ፥ እናቴ እንደምትመኝብኝ አትስጠኝ። ሚስት ሳታገባ ሀብት አፍራ፤ ልጅ ሳትወልድ ብላ። |
ሚስት በወቅቱ ከአልተገባ፥ አፈር አላባሽ እንጂ፥ ውሃ አጣጪ አትሆንም። ሚስት ባታብል፥ ባሎን ትወልዳለች። |
ሚስት ከፈቷት ባዳ፥ ማሽላ ከተቆረጠ አገዳ። |
ሚስት ፈትቶ፥ ከአማት መቀለብ፥ በእንፉቅቅ መኼድ። ሚስትህ አመዳም፤ ጎራዳህ ጎመዳም። |
ሚስትህ አረገች ወይ ቢለው፥ ማንን ወንድ ብላ አለው። ሚስትህን ስደድ፤ በሬህን እረድ ይላል የባለጌ መድ። ሚስትና ዳዊት ከብብት። |
ሚስጥርህን ለባዕድ ለምን አዋየኸው፤ ወንፊት ውሃ ይዝ የት ሲደርስ አየኸው። |
ሚካኤል አትቀየመኝ፥ መጭውን ስቀበል ኺያጁን ስሸኝ። ሚዛ ቢከተል፥ አሽከር ይመስላል። |
ሚያ ባለ፥ ፍየል ከፈለ። ሚያ ባልኩ፥ ፍየል ከፈልኩ። |
ሚያዙያ ከተበላ፥ እናትና ልጅ ተባላ። |
ሚዳቋ ቀስ ብላ ስትኼድ፥ የተያች ትመስላለች። ሚዳቋ፥ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተሰንጥቃ ሞተች። ሚዳቋ፥ ላ ላ ከመሬት። (ከመሬት ~ ከምድር) ማሕላት በግርግርታ፤ ዳዊት በቀስታ። |
ማለዳ የምትለቅምን ድሮ፥ ጭልፊት አትጠልፋትም። ማልደው ቢነሡ፥ እኩለ ቀን አይደርሱ። |
ማማት የለመደ አፍ፥ ሲያለግ ያድራል። (ሲያለግ ~ ሲድልት) ማማው ሞረት፤ ማሽላው ቅንቢቢት። |
ማማው ከጉልበት፤ ማሽላው ከዕንብርት። ማምሻም ዕድሜ ነው። |
Subsets and Splits