Dataset Viewer
query_id
stringlengths 32
32
| passage_id
stringlengths 32
32
| query
stringlengths 1
300
| passage
stringlengths 78
13.7k
| category
stringclasses 7
values | link
stringlengths 28
740
⌀ | source_dataset
stringclasses 3
values |
---|---|---|---|---|---|---|
460e6bed89ae74e77469682001948a3a | c903306280bbc6d6cb8a2675f424191c | ማንም አልተረፈም | በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተመዘገበው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት 149 መንገደኞችንና ስምንት የበረራ ቡድን አባላትን አሳፍሮ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ የተነሣው ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከ38 ደቂቃ ላይ ሲሆን መሬት ከለቀቀ ከስድስት ደቂቃ በኋላ ከምድር መቆጣጠሪያው ጋር የነበረው ግንኙነት መቋረጡ ተገልጿል።ከተሣፋሪዎቹ መካከል ሰላሣ ሁለት ኬንያዊያን፣ ስምንት ካናዳዊያን፣ ስምንቱን የበረራ ቡድኑን አባላት ሳይጨምር ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያንና ስምንት አሜሪካዊያን መንገደኞች ይገኙበት እንደነበረ ታውቋል።ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት አዲስና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰው ባለፈው ኅዳር ሲሆን የዛሬው አደጋ ከመድረሱ በፊት አብራሪው የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው አሳውቆ ወደ ቦሌ ለመመለስ ፍቃድ እንዲሰጠው ጠይቆ እንደነበር በአደጋው ሥፍራ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለጋዜጠኞች መናገራቸው ተዘግቧል።አይሮፕላኑን ያበርሩ የነበሩት ካፕቴን የረዥም ጊዜ ልምድ የነበራቸው መሆኑን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ አቶ አሥራት በጋሻው ለቪኦኤ ተናግረው መንስዔውና የአደጋው ዓይነት እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል።አይሮፕላኑ ባለፈው ዕሁድ ከጆሃንስበርግ መንገደኞችን አሳፍሮ አዲስ አበባ አርፏል።የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት በመንግሥቱና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ለተጎዱ ቤተሰቦች ጥልቅ ኀዘኑን በትዊተር ባሠራጨው መልዕክት አሳውቋል።ቦይንግ ኩባንያ ዛሬ ባወጣው ባለአንድ አረፍተ-ነገር መግለጫ ስለአደጋው ሪፖርት የደረሰው መሆኑንና ሁኔታውን በቅርብ እንደሚከታተል አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለጋዜጠኞች የሰጡትን መግለጫ ከሥር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ። /እንግሊዝኛ/የሪፖርተሮቻችንን ተጨማሪ ዘገባዎችና ቃለ-ምልልሶችን በፌስ ቡክ ገፃችን @voaamharic ላይ ያገኛሉ። ሁኔታውን እየተከታተልን ማውጣት እንቀጥላለን።የኢቲ-302 ተሣፋሪዎች ቁጥርና ሃገሮቻቸው | ሀገር አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/ethiopian-airlines-flight-et-302-boeing-737-max-8-crash-at-bishofu/4822249.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
13a9425dbd451b702e4ce4383f7c705e | 0402e2304c04df9f64318c84f9fc1812 | ጦማሪያኑ ከተመሠረተባቸው የሽብርተኝነት ድርጊት ወንጀል ክስ በነፃ ተሰናበቱ | ከሚያዝያ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 18 ወራት በእስር ላይ የነበሩት ጦማሪያን፣ ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. የተመሠረተባቸውን የሽብር ድርጊት ወንጀል ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ፡፡ከታሰሩ ጀምሮ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ በነፃ እንዲሰናበቱና በዕለቱ እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠው ጦማሪያን አቤል ዋበላ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በሌለችበት የተከሰሰችው ሶሊያና ሽመልስ ናቸው፡፡ ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ የተከሰሰበት የወንጀል ሕግ ተቀይሮ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን እንደገለጸው፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ያቀረባቸው የሰውም ሆኑ የሰነድ፣ የኦዲዮና ቪዲዮ ማስረጃዎች እንደ ክሱ የሚያስረዱ ሆነው አልተገኙም፡፡ ወይም ምንም ዓይነት ቅርርብ የላቸውም፡፡ በመሆኑም መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ግን ለፖሊስ በሰጠው የተከሳሽነት ቃል፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት (ኢሕአዴግ) በምርጫ ወይም በሰላማዊ ትግል የሚወገድ ስላልሆነ፣ በሁከትና በሕዝባዊ አመፅ መወገድ አለበት፡፡ አምኜ እንደ ግብፅ ሁከትና ብጥብጥ በኢትዮጵያም እንዲከሰት ቀስቃሽ ጽሑፎችን ጽፌያለሁ፤›› ብሎ የእምነት ቃል መስጠቱን ፍርድ ቤቱ በንባብ አሰምቷል፡፡ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የሚያስረዱ ከኢንተርኔት ያቀረባቸው ጽሑፎችም፣ ተከሳሹ ለፖሊስ ከሰጠው ቃል ጋር ተያያዥነት እንዳላቸውና የሚደግፉ መሆናቸውን በመግለጽ እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ ብይን ከሰማ በኋላ የተከሳሾች ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ፣ ተከላከል የተባለው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ይከላከል የተባለበት የሕግ አንቀጽ ዋስትና ስለማይከለክለው፣ አቅሙን ያገናዘበ ዋስ እንዲፈቀድለት ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም በዋስትና ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ለማሳወቅ ለጥቅምት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ዓቃቤ ሕግ በብይኑ ላይ ይግባኝ ስለማለቱ ተጠይቆ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ብይን እርስ በርሱ እንደሚጋጭ በመጠቆምና የተሰጠው ብይን የቀረበውን ማስረጃ ያላገናዘበና በአግባቡ ያልተመዘነ መሆኑን በመግለጽ፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለቱን አስታውቋል፡፡ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን በሚመለከት አስተያየታቸውን የሰጡት ጠበቃ አመሐ መኮንን ‹‹ብይኑ ከግለሰብ ችሎታ አንፃር ከታየ በበለጠ በተሻለ ሁኔታ መተንተን ይቻል ነበር፡፡ ከፍርድ ቤቱ አቅም አንፃር ግን ብይኑ ሚዛናዊ ነው፡፡ መረጃዎቹን ከሕጉ ጋር በደንብ አገናዝበው ሠርተውታል፡፡ በአጠቃላይ ጥሩ ብይን ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ሥጋት እንዳላቸው የተናገሩት አቶ አመሐ፣ ሥጋታቸው ደግሞ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲሰናበቱ የሰጠውን ትዕዛዝ፣ ቀደም ብሎ በሌሎች ደንበኞቻቸው (እነ ሀብታሙ አያሌው) ላይ የተፈጸመው ዓይነት ድርጊት ይፈጸማል የሚለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዕለቱ እንዲፈቱ ካዘዘ በኋላ፣ የማረሚያ ቤት ኦፊሰር የማስፈቻ ትዕዛዝ ወስዶ ለሚመለከታት የማረሚያ ቤቱ ሠራተኛ መስጠቱን መረጃ እንዳላቸው የተናገሩት አቶ አመሐ፣ የማረሚያ ቤቱ ሠራተኛ በተደጋጋሚ ስትጠየቅ ‹‹አልደረሰኝም›› ማለቷንም መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡በመሆኑም በፍርድ ቤት የተገኘውን መብት እንደገና የሚነፈግበት ወይም ሊነጠቅ የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደማይገባም አቶ አመሐ አስረድተዋል፡፡ ከአራትና ከአምስት ለማይበልጡ ጉዳዮች የፍትሕ ሥርዓቱን በጠረባ እየመቱ መጣል ለማንም እንደማይጠቅምም አክለዋል፡፡ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ሌሊት ድረስ ጦማሪያኑ አለመፈታታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ | ፖለቲካ | https://www.ethiopianreporter.com/article/9121 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
32daab06f86c9030e3b3d599aa7ff1c8 | b11ebba52646ed81eba8c39ddf84e395 | የቻይና መንግሥት በድርቅ ለተጋለጡ ሶማሊያውያን የ1 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ሠጠ | የቻይና መንግስት በድርቅ ለሚሰቃዩና ለተፈናቀሉ የሶማሊያ የህብረተሰብ ክፍሎች በእርዳታ የሚሰጥ የ 1 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠች።ጎረቤት ሃገር ሶማሊያ በየጊዜው የሚያጋጥማት የድርቅና የረሃብ ችግር ለመላቀቅ የአለም ሃገራት እርዳታ ስትሻ ቆታለች፡፡አሁን ካለችበት የድህነት አዘቅት ለመውጣትና ገፅታዋን ለመቀየርም እየጣረች እንደሆነ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሲዘግቡ እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡ አሁንም ግን ከድርቅ መላቀቅ አልቻለችም፡፡ቻይና በሶማሊያ ለተፈናቀሉ እና ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኩል የሚሰጥ የ 1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገረገች፡፡ቻይና ወደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) የላከችው ገንዘብ ኤጀንሲው የስደት ቀውሱን እንዲያስተካክል እና በሶማሊያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች መጠለያ እንዲሆን ይረዳል፡፡ በሶማሊያ የደረሰው ድርቅ እስካሁን ድረስ የቀጠለ ሲሆን ድርቅን ለመግታት ደግሞ ከሶማሊያ መንግስትና ከአለም አቀፍ ጋሮች ጋር ተባብረው በመስራት ላይ መሆናቸው ሽንዋ ዘግቧል፡፡የሶማሊያ መንግስት በበኩሉ ቻይና ድርቁን ለመታደግ ላደረገችው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናውና ገልጿል፡፡የተፈጥሮ አደጋ ቁጥጥር እና የሰብአዊ እርዳታ ሚኒስትር ዋና ፀሃፊ ሞሃመድ ሟይላም እንደተናደሩት ቻይና ለሶማሊያ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሃገራት መካከል መሪ ናት፡፡ቻይና አሁን ባደረገችው እርዳታም ለ 2500 ቤተሰቦች ና ሞቃዲሾ የሚገኙ በረሃብ፣ በድርቅና በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ከ ግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን ነው አክለው የገለፁት፡፡በሶማሊያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት ኪን ጂያን በበኩላቸው የሃገራቸው መንግስት ሶማሊያን ለመደገፍና በሁለቱ ሃገራት ያለው ወዳጅነት ለማጎልበት በመስራት ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ ቻይና በሶማሊያ የቤናዲር ሆስፒታልና የሞቃዲሾ ስቴዲየምን እንደገና ለመገንባት ከሃገሪቱ መንግስት ጋር የተስማማች ሲሆን ከዚህ በፊትም 89 ፕሮጀክቶችን በሶማሊያ አከናውናለች፡፡ ( ምንጭ: ዠንዋ) | ሀገር አቀፍ ዜና | https://waltainfo.com/am/33369/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
6c3fa2cdf9e00b80488963c173f095e1 | ac7f14d105040e73b3133472a70dd4f2 | ለውጡና ውህደቱ በቀድሞ የኢህዴን ታጋዮች አንደበት | ስለ ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ሲነሳ ለቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ /ኢህዴን / ታጋዮች ያበረከተው አስተዋጽኦ ይወሳል። ትግሉን የተቀላቀለው ብቻ ሳይሆን፣ በቀዬው ሆኖ ስንቅ በማቀበልና ልጁን ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል ያደረገው ነዋሪ ሚና አይዘነጋም።
ተራራዎቹም ባለታሪክ ናቸው። የያኔዎቹ ታጋዮች የአሁኖቹ ጡረተኞች ታጋይ ሰለሞን መሐመድ፣ ታዘበ ከፍያለው እና ከበደ
ተገኝ ትግሉን በተቀላቀሉበትና ተወልደው ባደጉበት አካባቢ ማህበር መስርተው ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር በእንቅስቃሴ
ላይ ይገኛሉ። ያለፈውን የትግል ትውስታቸውንና ሁለተኛ ዓመቱን ስለያዘው ለውጥ ሀሳባቸውን አካፍለውናል።
በሰቆጣ ከተማ ያገኘኋቸው የቀድሞ ታጋዮች እንዳጫወቱኝ በወጣትነት እድሜያቸው ነበር በ1970ዎቹ ኢህዴንን
የተቀላቀሉት። ትግሉን የተቀላቀሉት በወቅቱ የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብት በማፈን፣ ሰብዓዊ መብትን በመጣስ፣ በማሰር፣
በመደብደብ፣ በመረሸን ህዝብን ለስቃይና እንግልት ይዳርግ የነበረውን ጨቋኝ ሥርዓት ለመጣል ነው። ትግሉም ግቡን
መቷል ይላሉ። በጨቋኙ መንግሥት ቦታ በህዝብ የተመረጠ መሪ መቀመጡንም ያስረዳሉ። እንደታሰበው
የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበና ህዝብን ከድህነት ያላቀቀ የላቀ ውጤት ባይመዘገብም በልማቱና በፖለቲካው ሰፊ
ሥራ መሰራቱን ይናገራሉ። ይሁን እንጂ በሂደት የታገሉለት ዓላማ ወደ ኋላ መመለሱን ካለው ነባራዊ ሁኔታ
መገንዘባቸውንም ይገልጻሉ። ከህዝብ ጥቅም ይልቅ እራስን ማስቀደም እየሰፋ መምጣቱ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና
ሌሎችም በህዝብ የሚቀርቡ ቅሬታዎች እየበዙ መምጣታቸው ‹‹ለዚህ ነበር እንዴ የታገልነው›› እንዲሉ አድርጓቸዋል።
አሁን የመጣው ለውጥም የዚሁ ውጤት እንደሆነ ይገልጻሉ። ታጋዮቹ ከሁለት ዓመት በፊት ሀገሪቷ ውስጥ
የመጣውን ለውጥ ይደግፋሉ። የቀድሞ ታጋዮች ራስ አገዝ ማህበርን በአስተባባሪነት የሚመሩት ታጋይ ሰለሞን መሐመድ
በሰጡት አስተያየት ለውጡን ቢደግፉም ሁለት ነገሮችን እንዲገነዘቡ አድርጓቸዋል። በአንድ በኩል የመረረው
ህዝብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ስልጣን የሚፈልግ አካል መኖሩ ይሰማቸዋል። ከዚህ ቀደም የሚያውቁት ኢህአዴግ
የተፈጠረውን ችግር ይገመግማል። ጥፋተኛውንም ያስተካክላል። ያም ሆነ ይህ ‹‹ኢህአዴግ ጎዳን በደለን የሚል የህዝብ ቅሬታ በማየሉ›› ለውጡ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተውታል። የመስተካከል ዋና መርሁ ለውጥ እንደሆነና ህዝባዊ የሆኑ አሰራሮችን ማስፈን ጭምር ነው ይላሉ።
የኢህአዴግ ስልጣን ላይ መቆየትም ዘላለማዊ መሆን እንደሌለበትና ስልጣን ማሸጋገር እንደሚጠበቅበት ይገልጻሉ።
በለውጡ የታዩት የእርስበርስ ግጭቶችና ዜጎችንም ከአካባቢያቸው እስከማፈናቀል መድረሱ አሳዝኗቸዋል።
የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) አባል እና አጋር ድርጅቶች ውህደትን ታጋይ ሰለሞን
ከኢትዮጵያ ሰላም፣ ከህዝቦች መረጋጋትና ፍቅር እንዲሁም ከኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጥቅም አንጻር
እንደሚያዩት ይናገራሉ። በዓላማ የሚተሳሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተዋህደው መንቀሳቀሳቸው ለኢትዮጵያ አማራጭና እፎይታ
እንደሆነ ባይተዋርነትንም እንደሚያስቀር ገልጸዋል። ታጋይ ታዘበ እንዳሉት ታጋዩ ብቻ ሳይሆን፣
የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ነዋሪ በአጠቃላይ ለውጡን በድጋፍ ሰልፍ እንደተቀበለው በማስታወስ፣ ሰላማዊ
ሰልፉ የድጋፍ መግለጫ እንደሆነም አስምረውበታል። ውህደቱንም በተመለከተ ለኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት፣ ማዕከላዊ መንግሥቱ እንዲጠናከር ለማድረግ፣ ሀገርንም በልማት ለማበልጸግና ዴሞክራሲን ለማስፈን ውህደቱ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ያስረዳሉ።
በድርጅት ደረጃም አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለውጡን ተቀብሎ መንቀሳቀሱ ማሳያ እንደሆነና ታጋዮችም
ከድርጅቱ የሚለዩ አለመሆናቸውን ይገልጻሉ። ከመነጣጠል በአንድ ሆኖ ሀገርን መምራት እንደሚጠቅም ተናግረዋል።
ታጋይ ከበደ ተገኝ በበኩላቸው የለውጡን አስፈላጊነት ይደግፋሉ። ለውጡ ያስገኛቸውንም መካድ አይገባም ይላሉ። ነገር
ግን ለውጥ ሰሞነኛ መሆን እንደሌለበት ያምናሉ። እርሳቸው እንዳሉት የደርግ ሥርዓት የተገረሰሰው ለውጥ በማስፈለጉ
ነው። አሁንም የመጣው ለውጥ ይሄን የሚደግም እንዳይሆን ከሥር ከስር ማየት ይገባል። ችግሮች የማይደገሙበትና ወደ ህዝብ ጠብ የሚል ነገር ሲኖር ለውጡ ላይ እምነት መጣል ይቻላል ይላሉ። ውህደቱንም በተመለከተ ዘግይቷል ይላሉ። በተለይ አጋር ድርጅቶች እስከ መቼ በአጋርነት ይቀጥላሉ ለሚለው ምላሽ የሰጠም እንደሆነ ይገልጻሉ። መስማማት ለውጤት ያበቃል ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 2/2012 ለምለም መንግሥቱ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.press.et/Ama/?p=24247 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
a13c722888f9cd48e89946f903f0a1a2 | db1a9dde73735836a9394a4be9eec9d3 | ኢትዮጵያ በብዝሃ ሕይወት ሃብት ከበለጸጉ አገራት ተርታ መሰለፏ ልዩ ድጋፍ ያስገኝላታል | ኢትዮጵያ ከሳምንታት በፊት ሜክሲኮ በተካሄደው የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የብዝሃ ሕይወት ጉባኤ ላይ በብዝሃ ህይወት ከበለፀጉ አገራት ተርታ እንድትሰለፍ መደረጉ ልዩ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያስገኝላት የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አስታወቀ ። የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚንስትር ዶክተር ገመዶ ዳሌ ዛሬ በሠጡት መግለጫ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በዓለም በብዝሃ ህይወት እውቅና ከተሠጣቸው አገራት መካከል በ19ኛነት መመዝገቧና እውቅና ማግኘቷ የብዝሃ ህይወት ሃብቷን ይበልጥ ለማልማት የሚያግዝ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ እንድታገኝ ያስችላታል ። ኢትዮጵያ የተለየ የብዝሃ ሕይወት ክምችት ባለቤት በመሆኗ የያዘችው እምቅ ሃብት እንዳይጠፋ ልዩ ቴክኒካዊና የፋይናንስ ድጋፍ የማግኘት መብት የሚሠጣት ከመሆኑ በተጨማሪ ለአገሪቱ ገጽታ ግንባታና በዘርፉ ያላትን ተሰሚነት የሚያሳድግ መሆኑን ዶክተር ገመዶ ዳሌ አመልክተዋል ። በሜክሲኮ ጉባኤ የኢትዮጵያ መብትና ጥቅም ከማስከበር አኳያ በአገር ደረጃ ከጉባኤው ጎን ለጎን የተለያዩ ድርድሮች መካሄዳቸውን የገለጹት ዶክተር ገመዶ ኢትዮጵያ በብዝሃ ህይወት ያላት ምርጥ ተሞክሮ በምሳሌነት ለሌሎች አገራት አቅርባለች ።ኢትዮጵያ 6ሺ 500 የእጽዋት ሃብት ፣ 320 የእጥቢ እንስሳትና 926 የአዕዋፋት ሃብት ባለቤት በመሆኗ በብዝሃ ህይወት ከበለጸጉ አገራት መካከል አንዷ እንድትሆን ትልቅ ማሳመኛ ምክንያት መሆኑን ዶክተር ገመዶ አብራርተዋል ።ማህበረሰብ ዓቀፍ የሆኑ የብዝሃ ህይወት ማከማቻ ባንኮችና ማዕከላት በተለያዩ አገሪቱ አካባቢዎች መቋቋማቸውን ሌላው በጉባኤውን ቀልብ የሳበና ኢትዮጵያም በብዝሃ ህይወት ከበለጸጉ አንዷ እንድትሆን እውቅና ያሠጣት ተግባር መሆኑን ዶክተር ገመዶ አያይዘው ገልጸዋል ።ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት በምታደርገው ጥረት የተጎዱ አካባቢዎችን በብዝሃ ህይወት ማበልጸግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት በመግለጫው ተመልክቷል ።በቅርቡ በሜክሲኮ ካንኩን በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የብዝሃ ህይወት የሚኒስትሮች ጉባኤ “ ብዝሃነትን ማካተት ለሁሉም ድህንነት ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን 37 ውሳኔዎች መተላላፉን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ። | ቢዝነስ | https://waltainfo.com/am/22944/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
3edfa2fea86d5e0309aeef28648a8f9f | b5824201f1cc74afb01fe4e7d1134725 | የአማራ ክልል መንግስት ፍንዳታው በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል | የፌደራል መንግስት ህወሓት በትናንትናው እለት በባህርዳርና ጎንደር ሮኬት መተኮሱንና በአውሮፕላን ማረፊያዎች አካባቢ ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል፡፡
ህወሓት “በእጁ ያሉትን የመጨረሻ መሳሪያዎች ጠጋግኖ” መሞከሩን የገለጸው መንግስት “ከመሞቱ በፊት የመጨረሻውን ዐቅሙን እየሞከረ መሆኑን ያመለክታል” ብሏል፡፡
የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ እያጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአማራ ክልል መንግስት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ በጎደርና በባህርዳር ፍንዳታ መከሰቱን አረጋግጦ፣ ሁኔታው በጸጥታ ሀይሎች በቀጥጥር ስር መዋሉን አስታውቆ ነበር፡፡
ህወሓት የፌደራል መንግስት በአየር ጥቃት የሚፈጽም ከሆነ አውሮፕላኖቹ በሚነሱባቸው አየርማረፊያዎች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝር ገልጾ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጥቅምት 24 ምሽት ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረሱን ከገለጹ በኃላ በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የነበረው የቆየ አለመግባባት ተባብሶ ወደ ጦርነት አምርቷል፡፡
ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ የትግራይን ክልል የሚመራው ህወሓት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲኖር ፍላጎቱን ቢገልጽም የፌደራል መንግስት “የህገወጡ የህወሓት” ቡድን ህግ ፊት ሳይቀርቡ ድርድር እንደማይኖር ገልጿል፡፡
የተወካዮች ምክርቤት የክልሉን መሪ ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ብረሚካኤልን ጨምሮ የ39 የምክርቤት አባላትን ያለመከሰሰ መብት አንስቷል፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በህወሓት መሪዎች ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ አውጥቶባቸዋል፡፡
በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል ያለው አለመግባባት የጀመረው ኢትዮጵያን ለ27 አመታት ሲመራ የነበረው ኢህአዴግ ፈርሶ ብልጽግና ፓርቲ ሲመሰረት፣ ከመስራቾቹ አንዱ የነበረው ህወሓት የውህደቱ አካል አልሆንም ባለበት ወቅት ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ የፌደራል እና የክልል የጸጥታ ሃይሎች የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት እንዲጠብቁና ሰብአዊ መብትን እንዳይጥሱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
| ፖለቲካ | https://am.al-ain.com/article/government-says-rocket-cause-damage-in-gondar-and-bahir-dar | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
6087940ba4d1c58722a8eb01f416f2b9 | 009658535179802a350c793c818b911f | በሽብር የተዘጋው የናይጀሪያው ዳፕቺ ትምህርት ቤት ተከፈተ | ናይጀሪያ ውስጥ ላለፉት ሦስት ወራት ተዘግቶ የቆየ አሸባሪዎች ጥቃት ያደረሱበትና 109 ተማሪዎች የተጠለፉበት ትምህርት ቤት ተከፈተ።ከተጠለፉት የሚበዙት ሴት ተማሪዎች ለቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ቢሆንም ወደ ዳፕቺ ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን ለመላክ የደህንነታቸው ጉዳይ እያሳሰባቸው መሆኑን ወላጆች እየተናገሩ ነው። | ዓለም አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/nigerua-dapchi-girls-5-21-2018/4403292.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
3f94eb536e699a276d0dd000189b92f8 | 7e6bac0d2718b15992b54d842888d060 | ዶናልድ ትራምፕ - ስለ ጆን ሉዊስ | ኮንግሬስ ማን ሉዊስ “ወሬ ብቻ እንጂ እርምጃ መውሰድ ወይም ውጤት ማስመዝገብ አይሆንላቸውም” ሲሉም ትራምፕ ተችተዋል።እንደራሴ ጆን ሉዊስ “ወንጀል የበዛበትንና እየተፈረካከሰ ያለውን ወረዳቸውን ማስተካከል ሲገባቸው ስለ ምርጫው ውጤት በሀሰት ምሬት ያሰማሉ” በማለትም ወርፈዋቸዋል።ውዝግቡ ከተፈጠረ ወዲህ በተመራጩ ፕሬዚዳንት የቃለ መሃላ ስነ ሥርዓት ላይ እንደማይገኙ የሚገልፅ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከ50 በላይ ደርሰዋል።ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
| ዓለም አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/democracy-in-action-1-18-2016/3681840.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
674b08f5ca6ba039837887c8abd628bb | a4e80bdf5c51d1597e11a9b6d6e0fd5a | የተጓዡ የሰላም ጥሪ | የሀገሪቱ አበይት ጉዳዮች መስተናገጃ፤ የመዲናይቱ ሁነቶች ማሳለጫ የሆነው መስቀል አደባባይ፤ ማለዳ ወደተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጓዦችን ጭነው ለማድረስ የተዘጋጁ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች ይሰባሰቡበታል። ሆዳቸው በሰው እስኪሞላ በራቸውን ክፍት አድርገው፤ የደንበኞቻቸውን ጓዝ ሸክፈው ፀሀይ ከመውጣትዋ በፊት ቦታውን ይለቅቃሉ። የበልግ ፀሀይ ከምስራቃዊ የመዲናዋ ክፍል ስትፈነጥቅ ሰርክ ሰዎችን የማያጣው አደባባይ ልዩ ፍካት ይጎናፀፋል። ከወትሮው በተለየ
መልኩ
ትልቅ
ሀገራዊ
ጉዳይ
ያነገበ፤
የሀገሪቱ
ወቅታዊ
ሁናቴ
ያሳሰበውና
“የበኩሌን
አስተዋፅዖ
ላበርክት”
ያለ፤
ሀገራዊ
ሃላፊነቴን
ልወጣ
ብሎ
ያሰበ
አንድ
ቤተሰብ
አምባሳደሩን
ወደተለያዩ
የሀገሪቱ
ክፍሎች
ሊሸኝ
ተሰባስቦበታል።
ይህ
ቤተሰብ
ስለ
ሰላም
ሊሰብክ፤
ስለ
ፍቅር
ሊመክር
ያዘጋጀውን
አባሉን
“አላማህ
ይሰካ”
ብሎ
ሊሰናበት
እዚያ
ቦታ
ተገኝቷል።
የሰላም ምልክት የሆነው የእርግብ ምስል በሙሉ ነጭ ባንዲራ ላይ ጎልቶ ይታያል። በመኪናው አራቱም ጎን ጠርዝ ላይ አርማው በአጫጭር ዘንጎች ተሰቅሎ ይውለበለባል። በመኪናው የተለያየ ጎኑ ስለ ሰላም የሚነግሩ መልዕክቶች ተለጥፈውበታል። ከፊት ለፊት የመኪናው አካል (ኮፈኑ) ላይ “እኔ ስለ ሰላም እጓዛለሁ! እናንተስ?” የሚልና የተመለከተውን ሁሉ ጠያቂ ጥቅስ በጉልህ ተፅፎ ተለጥፏል። በመኪናው ላይ በተሰቀለ የድምፅ ማጉያ የስመ ጥሩ አርቲስት ማህሙድ አህመድ “ሰላም በዓለም ዙሪያ ሁሉ…” የሚለው ዜማ ከተጓዡ የሰላም መልዕክቶች ጋር ተቀነባብሮ ይደመጣል። ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ ነው። አቶ አዳሙ አምባቸው፤ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታየው የሰላም እጦት አሳስቧቸው በመላው ኢትዮጵያ በመዞር ስለ ሰላም አስፈላጊነት ለመስበክና መልዕክት ለማስተላለፍ ማክሰኞ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በግል መኪናቸው የሰላም ጉዞ ጀምረዋል። “ለሀገሬ ሰላም የድርሻዬን እወጣለሁ” በሚል መርህ ሀገር አቀፍ የሰላም ጉዞ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን የሚገልፁት በጎ ፈቃደኛውና የሰላም ተጓዡ አቶ አዳሙ አምባቸው፤ በቀጣይ ለአምስት ተከታታይ ሳምንታት ለሚያደርጉት የሰላም ጉዞ መኪናቸውንና ሙሉ ወጪያቸውን በግል በመሸፈን “አገራዊ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የበኩሌን አስተዋፅዖ ማበርከት አለብኝ” በሚል ዓላማ እንደተነሱ አስረድተዋል። አቶ አዳሙ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋለው የእርስ በእርስ ግጭትና አለመግባባት ማህበረሰቡን የሰላም ስጋት ውስጥ ጥሎታል። በመሆኑም እኔ ስለ ሰላም ጠቀሜታ መልዕክት በማስተላለፍና ስለ ፍቅር በመንገር ሃላፊነቴን ለመወጣት እጥራለሁ በማለት የያዙትን ዓላማ ያስረዳሉ። “ስለ ሰላም በጉዞዬ የሚገጥመኝን ሁሉ ለመጋፈጥና መስዋዕትነት ቢሆንም ለመክፈል እራሴን አዘጋጅቻለሁ” የሚሉት አቶ አዳሙ፤ ሰላም ለሰው ልጅ ህይወት እና ደህንነት የሚያስፈልግ፤ ሁሉም ሊጠብቀው የሚገባ መሆኑን ይናገራሉ። በተለያዩ የክልል ከተሞች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የገበያ ቦታዎች፣ ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አደባባዮችና መድረኮች ስለ ሰላም በመናገር መልዕክት በማስተላለፍ የሰላም ጠቀሜታ ለማስረዳት ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ይገልፃሉ። የአቶ አዳሙ ባለቤት ወይዘሮ የምስራች ፍቅሩ፤ ሰላም ለሀገር ህልውና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አስታውሰው፤ ባለቤታቸው የሰላም ጉዞ ማድረግ ከፈለጉበት ጊዜ ጀምሮ ለጉዞው ስኬት ድጋፍ ማድረጋቸውን ይገልፃሉ። “ለሰላም መስፈን ሁሉም በጋራ ሊሰራ ይገባል” ያሉት ወይዘሮ የምስራች፤ ለሁለንተናዊ ለውጥና እድገት ሰላም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ለህብረተሰቡ የሰላምን ጠቀሜታ መንገር፤ ሰላም እንዲሰፍን መጣር ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑንም አክለዋል። የሰላም ተጓዡ የአቶ አዳሙ ቤተሰብና ወንድም የሆኑት አቶ ግርማ ሸዋፈራው “ስለ ሰላም መረጋገጥ ሁሉም የራሱን ሚና ሊጫወት ይገባል” ይላሉ። “ከግጭት የሚገኘው እልቂትና መለያየት በመሆኑ ቀድሞ የነበረውን አብሮነት ማስቀጠል ተገቢ ነው፤ ለመጪው ትውልድ ሰላሟ የተረጋገጠች ኢትዮጵያን ማውረስ ይገባል” በማለት ምክረ ሃሳባቸውን ይለግሳሉ። ሁሉም ህብረተሰብ የሰላምን አስፈላጊነት በመረዳት ነገሮችን በሰከነ መንገድ በውይይት ሊፈታ እንደሚገባውም ይመክራሉ። የሰላም ተጓዡ አቶ አዳሙ ሰላም ካለ የማይፈታ ችግር አለመኖሩን ተረድተው ፖለቲከኞች ከፖለቲካዊ ፍላጎታቸው በፊት ህዝብንና ሀገርን ሊያስቡ እንደሚገባም ይናገራሉ። “እኔ ለሀገሬ የሰላም መስፈን የድርሻዬን ለመወጣጥ ዝግጁ ነኝ። ሰላም ህይወት ነውና ለህይወት መረጋገጥ እተጋለሁ” በማለት ለሰላም ሊያደርጉት ያሰቡትን የግል ጥረትና ዝግጅት ያስረዳሉ። ከዚህ ቀደም በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ሲሳተፉ መቆየታቸውን የሚናገሩት አቶ አዳሙ የሰላም ጥሪ ለማድረግ በሚያደርጉት ጉዞ መላ ኢትዮጵያውያን ስለ ሰላም በማሰብና የሰላምን ጠቀሜታ በመገንዘብ ቀና ትብብርና አድማጭ የሆነ ጆሮ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።አዲስ ዘመን የካቲት 18/2012ተገኝ ብሩ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.press.et/Ama/?p=27881 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
78384839099da7b17fa966a55ee3916f | 6479c0a2308ac7189b5975118b44a447 | የኢንተርኔት ማቆም፣ መዝጋትና መረጃን አጣርቶ መልቀቅ የሚያስችል ህግ ሊወጣ ነው | አዲስ አበባ፡- የኢንተርኔት ማቆም፣ መረጃን አጣርቶ ማውጣትና መዝጋት በተመለከተ በአገር ደረጃ የወጣ ህግ ባለመኖሩ ተገቢው መረጃ ለተገቢው አካል እንዳይደርስ ሆኗል። በዚህም ይህንን ለማረም በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ ለማካተት ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑን የብሔራዊ ህግና ፍትህ አማካሪ ምክርቤት አስታወቀ።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህርና በጠቅላይ አቃቤ ህግ የተቋቋመው የህግና ፍትህ አማካሪ ምክርቤት አባል ረዳት ፕሮፌሰር መሰንበት አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ መንግስት ኢንተርኔትን በማቆም፣ በመዝጋትና መረጃ አጣርቶ በማውጣቱ ዙሪያ ሊከተላቸው የሚገቡ ህጎች በአገር ደረጃ አልተቀመጡም። በዚህም በተለያየ መንገድ እነዚህ ክዋኔዎች ተግባራዊ እየሆኑ መጥተዋል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚዎችንም ሆነ ህዝቡን መረጃ በትክክል እንዳያገኝ አድርጎታል። በሚዲያ የመረጃ ነጻነትና
በኮምፒውተር ወንጀሎች ረቂቅ
አዋጅ ዙሪያ አሁን
ባለው ደረጃ ምክር
ቤቱ ከባለድርሻ አካላት
ጋር በመወያየት ህግ
ለማውጣት እየሰራ እንደሆነ
የሚገልጹት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤
የህጉ መውጣት በህግ
አግባብ የተቃኘ መረጃ
ለህዝብ እንዲደርስ እድል
ይሰጣል ብለዋል። የኢንተርኔት
አጠቃቀም ሁኔታውም ሥርዓት
እንዲኖረው ያደርጋል። ከዚያ
ባሻገር መንግስት ምን
ምን አስገዳጅ ሁኔታ
ሲገጥመው ኢንተርኔትን ማቆም፣
መዝጋትና ትክክለኛ መረጃ
አውጥቶ ማሰራጨት እንዳለበትም ያመላክታል። ከዚያ ውጪ ከተሰራ ደግሞ ተጠያቂነት እንዲኖርበት ያደርጋል። በተመሳሳይ ተጠቃሚ አካላትም የህግ አግባብን ተከትለው አቤቱታቸውን እንዲያቀርቡ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የመገናኛ ብዙሃን ህግ መምህርና በኔቶርክ ፎር ዲጅታል ራይት አባል ዮሐንስ እንየው በበኩላቸው፤ አገሪቱ በተለያየ መልኩ በቴክኖሎጂ እያደገች ከመምጣቷ ጋር ተያይዞ ብዙ ወንጀሎች ይፈጸማሉ። በዚህም ይህ ህግ አለመኖሩ ወንጀሉ እንዲበራከት ያደርጋልና ህጉ እንዲወጣ መታሰቡ የመረጃ ትክክለኛነትን ከማረጋገጥ አኳያ የማይተካ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ ውስጥ ተካቶ ተጠያቂነት እንዲኖር መደረጉ ግን አጠያያቂ እንደሆነ የሚጠቅሱት መምህር ዮሐንስ፤ ኢንተርኔት ከለውጥ በፊትም ሆነ በኋላ እየተዘጋ ነው። አሁንም ዝግ የሆነባቸው ቦታዎች አሉ። ስለሆነም ለምን ተዘጋ የሚለውን በደንብ ግልጽ ማድረግና ከኮምፒውተር ወንጀል አዋጁ ጋር ማገናኘት ያስፈልጋል ብለዋል። ተፈጻሚነቱንም ማፋጠን እንደሚገባ አሳስበዋል። ምክንያታቸውም በቅርብ በወጣው የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ 22 ነጥብ 74 ሚሊዮን ህዝብ ኢንተርኔት ይጠቀማል። በዚህ አዋጅ ውስጥ የሚካተቱ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ጥርት ባለ መልኩ መጻፍና መተግበር እንዳለባቸው የሚናገሩት መምህር ዮሐንስ፤ ሁኔታው በፍጥነት ተጠናቆ በህግና መመሪያ ታስሮ ወደ ትግበራ መግባት እንዳለበት አስረድተዋል።አዲስ ዘመን ጥር 24/2012ጽጌረዳ ጫንያለው | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.press.et/Ama/?p=26518 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
9fa8548b4c0f8c2f8dccf9c20a32cb1b | 3e85aae8839d691fc26a90946c5b8084 | በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለኮቪድ መከላከያ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ | አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለኮቪድ መከላከያ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ድጋፉ በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢፌዲሪ ሚሲዮኖች ኮቪድ 19 ለመከላከል የተደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መረጃ አስታውቋል። ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰራተኞች ለወረርሽኙ መከላከል የ4 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውም ተገልጿል።ድጋፉ በብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ስር የተቋቋመው የውጭ ድጋፍ አሰባሰቢ ንኡስ ኮሚቴ አስተባባሪነት መሰብሰቡም ነው የተገለጸው።በዚህም በምስራቅ አውስትራሊያ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያደረገችውን የገንዘብ ድጋፍ በመወከል የማዕከላዊ እና የምዕራበ ጎንደር ሊቀ ዻዻስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ዮሀንስ፣ አገር ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ዳያስፖራ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱላዚዝ ኢብራሂም እንዲሁም የዩኤስ ኮሌጅ ባለቤት አቶ ቶላ ገዳ ተገኝተው ለንኡስ ኮሚቴው ድጋፋቸውን በቼክ አስረክበዋል።ኮሚቴው ባለፉት ሳምንታት ከተለያዩ ሃገራት ሃብት የማሰባሰብ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።በተለያዩ የዓለም አገራት የተቋቋሙ 60 የኢፌዲሪ ሚሲዮኖች የኮሚቴውን እቅድ መነሻ በማድረግ በልዩ ልዩ ደረጃዎች ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙም ነው የተገልጸው።በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ሚኒስትሮች በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጀች እና ዲፕሎማቶች ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በመጠበቅ ለወገን እያደረጉ ላለው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።የኮሮና ቫይረስ የደቀነውን ስጋት መቋቀም የሚቻለው ሁሉም አካል በሚችለው አቅሙ ሲረዳዳ እና ሲተባበር በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ሚኒስትሮቹ ጥሪ አቅርበዋል። | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8b%8d%e1%8c%ad-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8a%96%e1%88%a9-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%89%b5%e1%8b%8d%e1%88%8d%e1%8b%b0-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
ca3eeb1657d36c7daa6927eafc3cd62c | b8bd363f0ebf6459c1ba9ff26cc2cbbb | ሪፖርት | መቐለ ከሜዳው ውጪ ጣፋጭ ሙሉ ነጥብ ጨበጠ | በአራተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲዳማ ቡና በመጀመሪያው አጋማሽ በተቆጠሩበት ግቦች በመቐለ 70 እንደርታ 2-1 ተሸንፏል፡፡ባለሜዳው ሲዳማ ቡና ባሳለፍነው ሳምንት ጅማ አባ ጅፋርን ሲረታ ከተጠቀመው የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ዮሴፍ ዮሃንስን በአበባየው ዮሃንስ የለወጠ ሲሆን በተመሳሳይ መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር 1-1 በተለያየበት ጨዋታ የተሰለፈው አስናቀ ሞገስን በአምበሉ አንተነህ ገብረክርስቶስ ተክቶ የዛሬውን ጨዋታ ጀምሯል፡፡ፌዴራል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ በመሩት በዚህ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተመሳሳይ የአጨዋወት መንገድን ይዘው የገቡ ቢሆንም አዋጪ የማጥቃት ኃይላቸውን ግን በግልፅ መመልከት ያልቻልበት ነበር። ይሁንና ሲዳማ ቡና እንደ ወትሮው በዳዊት ተፈራ ይመራ የነበረው የአማካይ ክፍሉ ያለመረጋጋት ይታይበት የነበረ በመሆኑ በመልሶ ማጥቃት ወደ አማኑኤል ገብረሚካኤል እና ኦኪኪ አፎላቢ ላዘነበለው ምዓም አናብስት በቀላሉ ተጋላጭ ሆኗል፡፡ አጀማመራቸው በእንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ ያመረላቸው ሲዳማ ቡናዎች በቀኝ በኩል ሀብታሙ ገዛኸኝ በ7ኛው እና 10ኛው ደቂቃ በፈጣን ሽግግር የተገኙ ሁለት አጋጣሚዎችን ሞክሮ ግብ ጠባቂው ፊሊፕ ኦቮኖ አዳነበት እንጂ በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች መሪ ለመሆን ተቃርበው ነበር።የጨዋታው ደቂቃ እየገፋ ሲመጣ የሲዳማን የአጨዋወት መንገድ በሚገባ የተረዱት መቐለዎች 20ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥረዋል፡፡ በመሀል ሜዳ የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች ኳስ በሚቀባበሉበት ወቅት ኦኪኪ አፎላቢ በፍጥነት ከኃላ ደርሶ የነጠቃትን ኳስ በግራ አቅጣጫ አመቺ ቦታ ላይ የሲዳማ ቡና ተከላካዮችን የአቋቋም ስህተት በመጠቀም ለአማኑኤል ገብረሚካኤል አሳልፎለት አጥቂው በሚታወቅበት የማስቆጠር ብቃት ኳሷን እየነዳ ወደ ሳጥን በመግባት ግብ አድርጓታል፡፡ግብ ካገቡ በኃላ አሁንም ሌላ ግብ ፍለጋ አፋጣኝ የመልሶ ማጥቃት አደረጃጀትን ለመጠቀም ያሰቡትን መቐለ 70 እንደርታዎች በድጋሚ የሲዳማ ቡናን ስህተት ተጠቅመዋል፡፡ 44ኛው ደቂቃ ያሬድ ከበደ መሀል ሜዳው ጨረር ላይ ከሀብታሙ ገዛኸኝ ላይ ኳስን ነጥቆ ጥቂት ከገፋት በኋላ ለአማኑኤል ሰጥቶት አማኑኤል የሲዳማን የተከላካይ መስመር መዘናጋት ተመልክቶ በድጋሚ ነፃ ቦታ ላይ ለቆመው ያሬድ አሳልፎለት ያሬድም ወደ ግብነት ለውጧት በሁለት ግቦች ልዩነት የመቐለን መሪነት አስተማማኝ አድርጓል፡፡ሁለት ግብ በራሳቸው ግልፅ ስህተት ለማስተናገድ የተገደዱት ሲዳማ ቡናዎች የዕረፍት መውጫ ጭማሪ ደቂቃዎች ላይ በከፈቱት ማጥቃት በግራ የመቐለ የግብ ክልል ወደ ኃላ በተጠጋ ቦታ ላይ አንተነህ ገብረክርስቶስ በሀብታሙ ገዛኸኝ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን ቅጣት ምት ዳዊት ተፈራ በረጅሙ ሲያሻማ አበባየው ዮሐንስ በግንባሩ ጨረፍ አድርጎ ግብ በማስቆጠር ሲዳማን ወደ ጨዋታው መመለስ የቻለች ግብ አግብቶ 2-1 በሆነ ውጤት መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡በእረፍት ሰዓት የቡድኖቹ አባላት ወደ መልበሻ ክፍል በሚያመሩበት ወቅት የመቐለ 70 እንደርታ የአሰልጣኞች ቡድን አባላት ከእለቱ ዳኞች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ የገቡ ሲሆን የቃላት ምልልሶችንም አስተውለናል።ከዕረፍት ሲመለሱ እየተመሩ ከሜዳ የወጡት ሲዳማ ቡናዎች የተጫዋቾቻቸውን የጨዋታ ቦታ ከመለወጥ ባለፈ ቅያሪዎችንም አድርገው ገብተዋል፡፡ ተከላካዩ ሰንደይ ሙቱኩን አውጥተው በመሀል ሜዳ የነበረባቸውን ክፍተት ለመድፈን ብርሀኑ አሻሞን በማስገባት በተከላካይ አማካይ ቦታ ላይ ሲጫወት የነበረው ግርማ በቀለን ወደ መሀል ተከላካይነት መልሰዋል፡፡ በአንፃሩ መቐለ 70 እንደርታዎች በመከላከሉ ቀዝቀዝ ብሎ የታየውን ቢያድግልኝ ኤልያስን አስወጥተው ጋናዊውን ተከላካይ ላውረንስ ኢድዋርድን ወደ ሜዳ ማስገባታቸው እና የመከላከል ቁጥራቸውን ከአማካይ ክፍሉ አሚኑ ነስሩን ወደ ኃላ በማስጠጋት ከፍ ማድረጋቸው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ውጤቱን አስጠብቀው ለመውጣት ማቀዳቸውን የሚያሳይ ነበር። የሲዳማ ቡና የበላይነት አመዝኖ በታየበት በዚሁ አጋማሽ የብርሀኑ አሻሞን መግባት ተከትሎ በረጅሙ ወደ አዲስ እና ሀብታሙ የሚጣሉ ኳሶች በተደጋጋሚ ይታዩ ነበር።የመቐለ 70 እንደርታ አጥቂዎች እጅጉን ቀዝቅዘው በታዩበት ሁለተኛው አጋማሽ ኦኪኪ አፎላቢ በግል ጥረቱ አግኝቶ መጠቀም ካልቻለባት አንድ አጋጣሚ ውጪ አብዛኞቹ ተጫዋቾች አፈግፍገው በመጫወት እና ሰዓት ለማባከን በተደጋጋሚ በመውደቅ አሳልፈዋል። በተቃራኒው ተደጋጋሚ የግብ ዕድሎችን የፈጠሩት ሲዳማዎች ደግሞ ኳስ እና መረብን ማገናኘት ቸግሯቸዋል።ከነዚህም ውስጥ በ59ኛው ደቂቃ አዲስ ግደይ በቀኝ በኩል በረጅሙ የጣለለትን ይገዙ ቦጋለ በግንባር መትቶ ኦቮኖ የያዘበት የሚጠቀስ ሲሆን ግብ ጠባቂው በዳዊት ተፈራ ተቀይሮ ከገባ በኃላ ኳስን ለመያዝ ጥረት ሲያደርግ የነበረው ሚካኤል ሀሲሳ ክፍተቶችን እየጠበቀ ከርቀት ያደረጋቸው ሦስት ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችንም አምክኗል። በተጨማሪም 69ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ በኩል ከቅጣት ምት አዲስ ግደይ መትቶት ፊሊፕ ኦቮኖ እንደምንም ያወጣበት ኳስ ሲዳማ ቡናን አቻ ለማድረግ የተቃረበ ነበር፡፡በቀሪዎቹ ደቂቃዎች ሲዳማ ቡና ፍፁም ብልጫን ወስዶ ቢጫወትም ጥቅጥቅ ብሎ መከላከልን አማራጩ ያደረገው የገብረመድህን ኃይሌ ቡድን 2ለ1 በማሸነፍ ከሜዳው ውጪ ወሳኝ ሙሉ ነጥብን ይዞ ወጥቷል፡፡ | ስፖርት | https://soccerethiopia.net/football/53212 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
8409fb7b34c69c671cbefa2e81787d75 | 44bdb55b3f790c85c7f487d2439a470e | የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላልወሰነ ጊዜ ተቋረጠ | አራተኛ ሳምንት ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላልወሰነ ጊዜ እንደሚቋርጥ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።የፌዴሬሽኑ መረጃ ይህንን ይመስላል፡-የኢትዮጵያ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድኖች በቀጣይ ከዩጋንዳ እና ከቡሩንዲ አቻዎቻቸው ባለባቸው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መደረጉን የሴቶች እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ዛሬ ታህሳስ 21 ባካሄደው ሳምንታዊ ስብሰባ አሳወቀ፡፡ውድድሩ ለመራዘሙ ምክንያት በመሆን የቀረበው በርካታ ተጫዋቾች ለብሄራዊ ቡድኑ በየእድሜ ደረጃው በመመረጣቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ ታህሳስ 18/2012ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ውድድር ጨዋታዎች ለ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ሴት ብሄራዊ ቡድን 6ተጫዋቾችን ካስመረጠው የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቡድን በስተቀር ውድድሮቹ በተያዘላቸው የጨዋታ ፕሮግራም መሰረት እንዲካሄዱ ተወስኗል፡፡ | ስፖርት | https://soccerethiopia.net/football/53355 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
6a6d2d3eda1b5298c91dbf1822c27300 | 5bbb1aa7bf3820a6f614597d0efc858f | ባንግላዲሽ፡ ፆታዊ ትንኮሳ ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት | ኑስራት ጃሃን የ19 ዓመት ወጣት ነበረች። ባንግላዴሽ ውስጥ ፌኒ በምትሰኝ አነስተኛ ከተማ ውስጥ የእስልምና ትምህርት ቤት ውስጥ ትምህርቷን ስትከታተል ቆይታለች።
መጋቢት 18 2011 ዓ.ም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ኑስራትን ወደ ቢሮው ያስጠራታል። ከዚያም ኑስራት እንደምትለው ርዕሰ መምህሩ ባልተገባ ሁኔታ ይነካካት ጀመረ። ከዚያም ከቢሮው ሮጣ አመለጠች።
የባንግላዴሽ ሴቶች ከማህብረሰቡ እና ከቤተሰቦቻቸው የሚደርስባቸውን መገለል እና ሃፍረት በመፍራት የሚፈፀምባቸውን ፆታዊ ትንኮሳዎች አይናገሩም። ኑስራት ግን ርዕሰ መምህሩ የፈፀመባትን መናገር ብቻ ሳይሆን በቤተሰቦቿ እርዳታ ጉዳዩን ፖሊስ ጋር ወሰደችው።
ፖሊስ ግን ቃሏን ተቀብሎ ጉዳዩን እያጣራ ከለላ ማድረግ ሲገባው ኑስራትን ማብጠልጠል ጀመረ። በዕለቱ ተረኛ የነበረው ፖሊስ ኑስራት ቃሏን ስትሰጥ ቪዲዮ እየቀረፃት ነበር። ኑስራት ቃሏን እየሰጠች በፖሊሱ መቀረፅ አላስደሰታትም። በተቀረፀው ቪዲዮ በግልፅ እንደሚታየው ኑስራት በእጇ ፊቷን ለመሸፈን ጥረት ታደርግ ነበር።
በተንቀሳቃሽ ምስሉም ፖሊሱ የኑስራትን ቅሬታ ''ይህ ትልቅ ጉዳይ'' አይደለም እያለ ሲያጣጥል ይሰማል። ይህ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል።
ኑስራት ላይ የተፈፀመው አስከፊ ተግባር በርካቶችን አስቆጥቷል።
ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄዳ ቃሏን ከሰጠች በኋላ፤ ርዕሰ መምህሩ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ተደረገ። ይህ ግን ለኑስራት ችግርት ፈጠረ። በቡድን የተደራጁ ወንዶች ርዕሰ መምህሩ ከእስር እንዲለቀቁ ሰልፍ ማድረግ ጀመሩ። ተቃውሞ ሰልፉን ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል ኑስራት የምትማርበት ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ሁለት ወንዶች ይገኙበታል። የአከባቢው ፖለቲከኞችም የተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊ ሆነዋል።
በርካቶች ለርዕሰ መምህሩ መታሰር ኑስራትን ተጠያቂ ማድረግ ጀመሩ። ወላጆቿም የልጃቸው ደህንነት ያሰጋቸው ጀመር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ለፖሊስ ቃሏን ከሰጠች ከ11 ቀናት በኋላ ኑስራት ማጠቃለያ ፈተና ለመፈተን ወደ ትምህርት ቤቷ ሄደች።
''ደህንነቷ ስላሰጋን ትምህርት ቤት ድረስ ይዣት ሄድኩ። ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳልገባ ግን ተከለከልኩ።'' ይላል የኑስራት ወንድም መሃሙዱል ሃሰን ኖማን። "እንዳልገባ ባይከለክሉኝ ኖሮ፤ ይህን መሰል ተግባር በእህቴ ላይ አይፈፅሙም ነበር'' ሲል ጨምሮ ይናገራል።
የኑስራት ወንድም መሃሙዱል ሃሰን ኖማን በኑስራት የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ሃዘኑን ሲገልጽ።
ኑስራት በሰጠችው ቃል መሠረት አንድ የክፍል ጓደኛዋ፣ ጓደኛቸው እየተደበደበች እንደሆነ በመንገር ኑስራትን የትምህርት ቤቱ ሕንፃ ጣሪያ ላይ ይዛት ትወጣለች። ጣሪያው ላይ የጠበቃት ግን ሴት ለመምሰል ዓይነ እርግብ የለበሱ (ዓይናቸው ብቻ የሚያሳይ ሂጃብ) አምስት የሚሆኑ ወንዶች ነበሩ።
ከዚያም ኑስራትን በመክበብ በርዕሰ መምህሩ ላይ ያቀረበችውን ክስ እንድታነሳ ያስፈራሯታል። ኑስራት ግን እንደማታደርገው ትናገራለች። ከዚያም ነዳጅ አርከፍክፈውባት እሳት ለኩሰው አቃጠሏት።
የመርማሪ ፖሊሶች ኃላፊ ባንድ ኩማር ማጁመደር እንዳሉት ተጠርጣሪዎቹ ''ኑስራት እራሷን ያጠፋች ለማስመሰል አስበው ነበር'' ሃሳባቸው ሳይሳካ የቀረው ተጠርጣሪዎቹ ኑስራት ሕይወቷ ያለፈ መስሏቸው አካባቢውን ጥለው ከሄዱ በኋላ ኑስራት እስተንፋሷ ሳይወጣ ቃሏን በመስጠቷ ነው።
''አንደኛው ተጠርጣሪ የኑስራትን ጭንቅላት በእጆቹ ወጥሮ ከመሬት አጣብቆ ይዞ ስለነበረና ጭነቅላቷ ላይ ነዳጅ ስላላፈሰሱ ከአንገቷ በላይ አልተቃጠለችም። በዚህም ሕይወቷ ሊቆይ ችሏል'' ሲሉ የፖሊስ አዛዡ ለቢቢሲ ቤንጋሊ ቋንቋ አገልግሎት ተናግረዋል።
ኑስራት አካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል ስትወሰድ 80 በመቶ... | UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
b3b7e503de6b8a3181fedd8a7d763e49 | 1704e3762144be620a3eea43c615a07e | ዛሬ በመቀሌ ሊካሄድ የነበረ ሠላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ | ይህ ሠላማዊ ሰልፍ የተጠራው የትግራይ ክልል የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ተማሪዎች ችግር ያጋጥማቸዋል ወደተባሉ ቦታዎች እንዲሄዱ እንዳይደረግ በክልሉ መንግሥት ላይ ግፊት ለማድረግ እንደነበረ ተነግሯል።
ሠላማዊ ሰልፉን የጠራው ማህበር ሊቀ መንበር መሃሪ ዮሐንስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ስለሰልፉ ለማሳወቅ ለመቀሌ ከተማ ከንቲባ ጸሐፊ ደብዳቤ ማስገባታቸውንና ግልባጩንም ለዞኑ ፖሊስ ለማስገባት ሙከራ ባደረጉበት ወቅት አንቀበልም መባላቸውን ተናግረዋል።
• በመቀሌ ከተማ ፆታዊ ጥቃትን በመቃወም ሊደረግ የነበረው ሰልፍ ተከለከለ
• የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አንደማይልክ አስታወቀ
ሊቀ መንበሩ በተጨማሪ ሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ማሳወቅ እንጂ የመፍቀድና የመከልከል ህጋዊ መብት የለውም ብለዋል።
ዛሬ ጠዋት ሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ሮማናት ተብሎ በሚጠራው የመቀሌ ከተማ አደባባይ መሰባሰብ በጀመሩበት ጊዜ ፖሊሶች ወደ ስፍራው መጥተው ሰልፉ ህጋዊ ስላልሆነ በመግለጽ እንዲያስቆሙ መታዘዛቸውን በመግለጽ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ ማድረጋቸውን የሰልፉ አስተባባሪዎች ተናግረዋል።
አስተባባሪዎቹም ከፖሊስ ጋር ግብግብ መፍጠር ተገቢ ባለመሆኑ ሰልፉን ለማካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ለፖሊስ የማሳወቂያ ደብዳቤ እንደሚያስገቡ ተናግረዋል።
• "ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ
• ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ብቻ ነው መማር የሚችሉት- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
የመቀሌ ከተማ ምክትል ከንቲባ ስለተከለከለው ሠላማዊ ሰልፍ ተጠይቀው "ሰልፉ ሊከለከል አይገባም። ቢሆንም የጸጥታውን ሥራ በተመለከተ ማን ተጠይቆ ምን መልስ ተሰጠ? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይገባል" ብለዋል።
የሠላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤውን ተቀብሎ ወደሚመለከተው አካል ያላቀረበ ግለሰብ ካለ እንቀጣለን" ያሉት አቶ አቶ ብርሐነ፤ ለፖሊስ ቀርቦ ነበር የሚለው ቅሬታን ተከትሎ ፖሊስ የመከልከል መብት ስለሌለው ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል።
ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተጠይቆ ሲከለከል በዚህ ሳምንት ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከቀናት በፊት በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃትን ለማውገዝ በተመሳሳይ መቀሌ ውስጥ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቀርቦ እንደተከለከለ መዘገባችን ይታወሳል።
| UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
7fe3b2689ab2d3a28a75a8db9ce0c74c | b7ca9f7eb563d479961f2c974e921262 | ፊንላንድ ለአባቶች የእናቶችን ያህል የሥራ ፈቃድ ልትሰጥ ነው | የጾታ እኩልነትንና ደህንነትን ለማበረታታት በሚል የሚሰጥው እረፍ ክፍያንም እንደሚጨምር ታውቋል።
የፊንላንድ ጎረቤረት የሆነችው ስዊድን ወላጆች ልጅ ከወለዱ በኋላ ለእያንዳንዳቸው 240 የወላጆች የእረፍት ፈቃድን በመስጠት በአውሮፓ ውስጥ ለጋስ የሆነ የተደነቀ ሥርዓትን በመዘርጋት ትታወቃለች።
የፊንላንድ የጤናና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አይኖ-ካይሳ ፔኮነን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከመጀመሪያው አንስቶ የወላጆችን ግንኙነት ለማጠናከር ባለመ ሁኔታ "ቤተሰቦች በሚያገኙት ጥቅማጥቅሞች ላይ መሰረታዊ ለውጥ" ተደርጓል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ፊንላንድ ለወለዱ እናቶች ከአራት ወራት በላይ የወሊድ ፈቃድ የምትሰጥ ሲሆን ለአባቶች ደግሞ ከሁለት ወር በላይ ፈቃድ ይሰጣል። ነገር ግን በአማካይ ከአራት ወንዶች አንዱ ብቻ ነው የተሰጠውን ፈቃድ የሚጠቀምበት። አሁን የታቀደው የፈቃድ አይነት የወላጆች ፈቃድን ብቻ የሚመለከት ነው ተብሏል።
ወላጆች ከሚሰጣቸው ፈቃድ ውስጥ 69 ቀኑን ወደ ሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ይችላሉ፤ በተጨማሪም ነፍሰጡር እናቶች አንድ የወር ደሞዝን ያህል ክፍያን ያገኛሉ ተብሏል።
የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪና ባለፈው ወር እንዳሉት አገራቸው የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚቀሯት ሥራዎች እንዳሉና ልጆቻቸው ታዳጊ እያሉ አብረዋቸው ጊዜ የሚያሳልፉ አባቶች ቁጥር በጣም ውስን ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
በኦስሎ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሊሲ ኢሊንግሳትር ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፊንላንድ የምትገኝበት የኖርዲክ አካባቢ አገራት ወደ እናቶች የማይዘዋወር የወላጅነት የሥራ ፈቃድ በመስጠት በኩል ቀዳሚ ሆነው ቆይተዋል።
የአውሮፓ ኅብረትም ተመሳሳይ ውሳኔን እየተከተለ ሲሆን ባለፈው የፈረንጆች ዓመት አባል አገራት ለእያንዳንዱ ወላጅ የአራት ወር ፍቃድ እንዲሰጡና ከዚህም ውስጥ ሁለቱ ወር ወደ ሌላ ጊዜ የማይተላለፍ እንዲሆን የሚያስገድድ ነው።
ፖርቱጋል የትኛውንም ጾታ የማይለይ ሁሉን አቀፍ ሥርዓት ያላት አገር ናት። በዚህም ለሁለቱም ወላጆች የአራት የሥራ ፈቃድና ሙሉ ደሞዝ እንዲሁም የሚፈልጉ ከሆነ ተጨማሪ አንድ ወር ፈቃድና የደሞዛቸውን 80 በመቶ እንዲያገኙ ይፈቀዳል።
ከታኅሳስ ወር ጀምሮ ፊንላንድ በአራት ፓርቲዎች ጥምረት እየተመራች ሲሆን እያንዳንዱን ፓርቲም የሚመሩት ሴቶች ናቸው።
ለወላጆች በሚሰጠው የሥራ ፈቃድ ላይ የሚደረገው ለውጥ የፊንላንድ መንግሥትን ተጨማሪ 110 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣው ተገምቷል።
ስዊዲን፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ኢስቶኒያና ፖርቱጋል ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ፖሊሲ በማውጣት ባለፈው ዓመት በዩኒሴፍ አድናቆትን አግኝተዋል።
| UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
f77747d1f84381569bee5eac76449590 | 0e0c3db9aabdf2ded4e7cad800579b3e | በምዕራብ ኦሮሚያ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ በምዕራቡ ክፍል የሚገኘው የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ለቢቢሲ ተናገረ። | ኩምሳ ዲሪባ (መሮ)፡ የኦነግ ጦር መሪ በትግላችን እንቀጥላለን አለ\nየምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር መሪ መሮ (ግራ) እና የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ (ቀኝ)።
መንግሥትን እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴ ትናንት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት መድረክ ላይ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአሁን በኋላ ኦነግ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ የጦር ኃይል አይኖረውም ማለታቸውን ተከትሎ ነው የጦሩ መሪ ይህን የተናገረው።
• በምዕራብ ኦሮሚያ ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ
በምዕራብ ኦሮሚያ የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ ''የተለወጠ ነገር የለም'' በማለት ከኦነግ ሊቀ መንበር በተለየ መልኩ የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ለቢቢሲ ተናግሯል።
መሮ መከላከያው፣ ፖሊስ እና የደህንነት አካሉ ሙሉ በሙሉ የፓርቲ ወገንተኝነቱን አቁሞ የሕዝብ ወገንተኝነቱን እስካላረጋገጠ ድረስ የመንግሥትን ጥሪ አንቀበልም ብሏል።
''እኛ ለፓርቲ ወግኖ ሕዝብን የሚጎዳ የመከላከያ አካል መሆን አንሻም'' ሲል ከዚህ በፊት ከመንግሥት ጋር በተደረሰው ስምምነት የግንባሩ ታጣቂዎች ከመንግሥት የጸጥታና የመከላከያ ኃይል ጋር ለማካተት የቀረበውን ሃሳብ መሮ ውድቅ አድርጎታል።
• በጦላይ የኦነግ ሠራዊት አባላት ላይ የተከሰተው ምንድን ነው ?
ጨምሮም ''ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ በንግግር ተሸፋፍኖ የሚያልፍ ነገር አያዛልቅም። ነገ እሳት መነሳቱ አይቀርም። ዘላቂ መፍትሄ በሚሰጡ ምክክሮች ላይ ለመወያየት ግን ዝግጁ ነን'' በማለት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል።
መንግሥትን እና ኦነግን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት መሣሪያ አንገበው ጫካ ገብተው የነበሩ የኦነግ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ወይም ወደሚዘጋጅላቸው ስፍራ ለስልጠና እንዲገቡ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሷል።
ኮሚቴው የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነው ሪፖርቱን ያቀረበው።
• «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር)
ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ፤ ኦነግ ከአሁን በኋላ ጦር አንግቦ የሚንቀሳቀስ ሠራዊት አይኖረውም፤ መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚወስደውን እርምጃም እንደግፋለን ብለዋል።
የኮሚቴው ሪፖርት ቁልፍ ነጥቦች
የአስታራቂ ኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረቡት አቶ በቀለ ገርባ ሲሆኑ፤ ባቀረቡት ሪፖርት ውስጥ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል።
ኦነግ ከአሁን በኋላ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ጦር ስለማይኖረው ኮሚቴው የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካቱን ጠቅሰው፤ ኮሚቴው በኦነግ እና በመንግሥት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ታስረው የነበሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል።
• ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር
በተጨማሪውም ኮሚቴው ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካዊ ትግሉን ለመቀጠል በሚያደርገው እንቅስቃሴ የመንግሥት ድጋፍ እንዳይለይ እና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ የገቡ የኦነግ ጦር አባላት ቃል የተገባላቸው ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ኮሚቴው ጠይቋል።
| UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
3229af0f7bddbac561380a46b16e67e9 | a9776eb5efd212efd630e0cd578a2ec8 | በችግር ላይ የሚገኙ የወረገኑ ተፈናቃዮች የስደተኞችን ያህል ዕርዳታ እንዲፈቀድላቸው ጠየቁ | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ባካሄደው ሕገወጥ ያላቸውን ቤቶች የማፍረስ ዘመቻ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የወረገኑ አካባቢ ነዋሪዎች፣ ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ስደተኞች እንደሚደረገው ሁሉ ለእነሱም ዕርዳታ የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻች ጠየቁ፡፡ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉት እነዚህ ወገኖች ባቋቋሙት ኮሚቴ አማካይነት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ጎዳና ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል፡፡‹‹የምንኖረው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ነው፡፡ በድንገት ቤታችን በመፍረሱ ጭራሹኑ የኑሮ መሠረታችን ተናግቷል፤›› በማለት ለከተማው ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ የገለጹት እነዚህ ተፈናቃዮች፣ ‹‹ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ከልጆቻችን ጋር ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገናል፤›› ሲሉም መንግሥት እንዲደርስላቸው ተማፅነዋል፡፡እነዚህ ተፈናቃይ ወገኖች በጻፉት መማፀኛ ደብዳቤ ሌሎች አማራጮች ባይኖሩ እንኳን፣ ቢያንስ መንግሥት ችግራቸውን ተረድቶ ለደቡብ ሱዳን፣ ለሶማሊያና ለኤርትራ ስደተኞች እንዳደረገው ላስቲክ ወጥረው የሚኖሩበትን መንገድ እንዲያመቻች ጠይቀዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ያስከተለባቸው የከፋ ችግር ባለበት ወቅት ቀጣዩ የትምህርት ዘመን እየቀረበ በመሆኑ፣ ልጆቻቸውን በቋሚነት ለማስተማር ለመወሰንም እንደተቸገሩ ተፈናቃዮቹ በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ዶ/ር ታቦር ገብረ መድኅን የተፈናቃዮቹን ጥያቄ ከተመለከቱ በኋላ፣ ሊደረግ የሚችል ድጋፍ ካለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲመለከተው ጠይቀዋል፡፡‹‹የከተማው አስተዳደር ምንም መጠለያ ለሌላቸው መፍትሔ ለመሻት ባለው ዕቅድ መሠረት የሚሰጥ ምላሽ ካለ እንዲመለከተው›› በማለት ዶ/ር ታቦር ተፈናቃይ ወገኖች የጻፉትን መማፀኛ ደብዳቤ አባሪ በማድረግ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መርተዋል፡፡ነገር ግን ተፈናቃይ ወገኖች ያቋቋሙት ኮሚቴ አባላት በተደጋጋሚ ወደተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ቢመላለሱም መፍትሔ ማጣታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከዚህ የባሰ ችግር የለም፤›› ያሉት ስማቸውን ቢገልፁ ሌላ ያልጠበቁት ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል የሰጉ የኮሚቴው አባላት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ‹‹መንግሥት ባለበት አገር እንዲህ ዓይነት ስቃይ ሊገጥመን አይገባም፡፡ ቢያንስ ላስቲክ ወጥረን የዕለት ኑሯችንን የምንገፋበት መንገድ ይመቻች፤›› በማለትም ተማፅነዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚያዝያ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረገኑና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሃና ማርያም አካባቢዎች ሕገወጥ ያላቸውን ግንባታዎች ማፍረሱ ይታወሳል፡፡በወረገኑ አካባቢ 4,800 ቤቶች ፈርሰዋል፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ ቤቶች በመፍረሳቸው ከአምስት ሺሕ በላይ የሚቆጠሩ ዜጎች እንደተፈናቀሉ የኮሚቴ አባላቱ ይናገራሉ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1988 እስከ 1997 ዓ.ም. ድረስ ከተገነቡት በስተቀር፣ የተቀሩት በተለይ ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ የተገነቡት ‹‹ሕገወጥ›› በመሆናቸው መፍረስ እንደሚኖርባቸው ይገልጻል፡፡የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታምራት አስናቀ እንደሚሉት፣ እስከ 1997 ዓ.ም. ከተገነባው ‹‹ሕገወጥ›› ግንባታ በስተቀር አግባብ ባልሆነ መንገድ የተያዘን መሬት መንግሥት ሕጋዊ አያደርግም፡፡ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ግን የፈረሱባቸውን ቤቶች ሲገዙም ሆነ ሲገነቡ መንግሥት ያውቅ ነበር፡፡ በኮብልስቶን፣ በድልድይ ግንባታ፣ በኮሙዩኒቲ ፖሊሲንግ፣ እንዲሁም በአካባቢው በተካሄዱ የልማት ሥራዎች ከገንዘብ መዋጮ ጀምሮ ተሳታፊ እንደነበሩ ያስታውሳሉ፡፡‹‹ይህ ሁሉ ቀርቶ አሁን የምንፈልገው የላስቲክ መጠለያ ነው፤›› በማለት የኮሚቴ አባላቱ በተለይ የመጠለያ ችግር የተፈናቃዮችን ሕይወት እያናጋ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ተማፅነዋል፡፡ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%89%A0%E1%89%BD%E1%8C%8D%E1%88%AD-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8C%88%E1%8A%99-%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%88%A8%E1%8C%88%E1%8A%91-%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8A%93%E1%89%83%E1%8B%AE%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%88%B5%E1%8B%B0%E1%89%B0%E1%8A%9E%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%8B%AB%E1%88%85%E1%88%8D-%E1%8B%95%E1%88%AD%E1%8B%B3%E1%89%B3-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%8D%88%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%8B%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%8C%A0%E1%8B%A8%E1%89%81 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
f216913f849de6138461f4bf002aede6 | 42547809e4b5ed7f701ad67abb73054f | የብሔር ጥቃት የሚፈፅሙ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ | በሃገሪቱ ማንነትን መሠረት አድርገው የሚፈፀሙ ኢ-ሠብአዊ ድርጊቶችና መፈናቀሎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ያሳሰበው ሠማያዊ ፓርቲ፤ መንግስት ኃላፊነቱንም እንዲወስድ የጠየቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ፤ ከቤኒሻንጉል ተፈናቅለው ለወራት በባህርዳር ተጠልለው የሚገኙ ዜጎችን ሁኔታ እመረምራለሁ ብሏል፡፡ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም ከ30 ዓመታት በላይ ከኖሩበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለጋንፎ ወረዳ የሠው ህይወት በጠፋበት ሁኔታ በሃይል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው ሠማያዊ ፓርቲ፤ ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም በደል በአስቸኳይ እንዲቆም ለመንግስት ጥሪ አቅርቧል፡፡ በህዝቡ ላይ በደል ያደረሱ፣ ግድያ የፈፀሙና ያስፈፀሙ አካላትም ተጣርተው ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ የጠየቀው ፓርቲው፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈፀመው መፈናቀል በመንግስት ባለስልጣናት ትዕዛዝ ነው የሚል ጥርጣሬ እንዳለውና መንግስት በባለስልጣናት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡ በመንግስት ሃላፊዎች ትዕዛዝ በተደጋጋሚ ማንነትን መሠረት አድርጎ የሚፈፀም ጥቃት አሣሣቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው ፓርቲው፤ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየተፈፀመባቸው ያሉ ማህበረሠቦችን አስፈላጊውን ከለላ በመስጠት መንግስት ከጥቃት የመከላከል ሃላፊነት አለበት ብሏል፡፡ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=21843:%E1%8B%A8%E1%89%A5%E1%88%94%E1%88%AD-%E1%8C%A5%E1%89%83%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8D%88%E1%8D%85%E1%88%99-%E1%89%A3%E1%88%88%E1%88%B5%E1%88%8D%E1%8C%A3%E1%8A%93%E1%89%B5-%E1%88%88%E1%8D%8D%E1%88%AD%E1%8B%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%89%80%E1%88%AD%E1%89%A1-%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%8B%A8%E1%89%80&Itemid=180 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
3bddf0eac5527066c820513d3635385a | 47cc888c1d94b58b09b61390f54c8224 | ካንበራ | ካንቤራ የአውስትራሊያ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 339,900 ሆኖ ይገመታል። በዚህም በሀገሪቱ ካሉት የየብስ ከተሞች ትልቁ ሲሆን በአጠቃላይ ደግሞ ፰ኛው ከፍተኛ የህዝብ ብዛት የሚገኝበት ከተማ ነው። ካምቤራ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ነጮች መጀመርያ የሠፈሩበት በ1818 ዓ.ም. ገደማ ነው።
ዋና ከተሞች
የአውስትራልያ ከተሞች | UNK | null | https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia |
2520d489819f4487aa3a8793f152b1c6 | bb57e6a79cab6576e3afb645bd10a0bc | በአንዋር መስጊድ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በርካታ መደብሮች ወደሙ | የንብረት ግምት ገና እየተጣራ ነው ተብሏል መርካቶ በአንዋር መስጊድ በከለላቸው የንግድ መደብሮች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት መውደሙን የንብረቶቹ ባለቤቶች ገለጹ፡፡ የአንዋር መስጊድ አስተዳደር ካከራያቸው 300 ያህል መደብሮች ውስጥ 50 ያህሉ መቃጠላቸውን የተገለጸ ቢሆንም፣ ንብረቶቻቸው የእሳቱ ሰለባ የሆኑባቸው ባለንብረቶች ግን የሱቆቹ ብዛት ከ163 በላይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አቶ ከድር መሐመድ የተባሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መሸጫ መደብር ባለቤት እንደተናገሩት፣ መርካቶ ውስጥ ሦስት በአራት የሆነ ክፍል ሰባትና ስምንት ሱቆችን አካቶ እንደሚይዝ ገልጸው፣ የእሳቸው ሱቅ በውስጡ ከ200 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ነበረው ብለዋል፡፡ ስፋቱ ግን ሁለት በሁለት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ሃምሳም ይሁኑ መቶ መደብሮችን የመስጊዱ አስተዳደር ማከራየቱን ቢገልጽም፣ በነፍስ ወከፍ ተይዘው ይሠራባቸው የነበሩ ሱቆች ግን ሁለት መቶ ሊደርሱ እንደሚችሉ አቶ መሐመድ ጠቁመዋል፡፡ ረቡዕ ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ እሳቱ መነሳቱን የገለጹት ባለመደብሮቹ፣ በወቅቱ ሁሉም መደብሮች ዝግ ነበሩ ብለዋል፡፡ የተወሰነ እንኳን ማትረፍ እንዳይችሉ ተደውሎላቸው የደረሱት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓትና ከዚያ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ምንም ዓይነት ንብረት ማትረፍ አለመቻሉን፣ አንዳንዶቹ አዳዲስ ግዥ ፈጽመው መደብሮቻቸውን የሞሉ በመሆናቸው ማካካሻ እንኳን እንደሌላቸው አስረድተዋል፡፡ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠር ባለሥልጣን ተደውሎለት ከሌሊቱ 7፡30 ሰዓት በቦታው መገኘቱን፣ ከ15 በላይ የአደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎችና 112 ሠራተኞቹን በማሠማራት እሳቱ ወደ ሌላ እንዳይዛመት ባለበት ለመቆጣጠር መቻሉን አስታውቋል፡፡ የባለሥልጣኑ የኮሙዩኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሰለሞን መኮንን ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በመስጊዱ አስተዳደር መረጃ መሠረት የተቃጠሉት 50 መደብሮች ናቸው፡፡ መደብሮቹ በተቀጣጣይ ሸቀጣ ሸቀጦች የተሞሉ በመሆናቸው እሳቱ በቀላሉ ስለሚዛመት፣ ወደ ሌላ እንዳይስፋፋ በመከላከል እዚያው እንዲቀር ተደርጓል፡፡ በሕዝቡ ትብብር እስከ ንጋት ድረስ በተደረገው ርብርብ እሳቱ ሳይዛመት ለመቆጣጠር ቢቻልም፣ መደብሮቹን ማዳን አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማወቅ ባለሥልጣኑ ከፖሊስ ጋር በመተባበር እየሠራ በመሆኑ፣ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ መግለጽ እንደማይቻልም ተናግረዋል፡፡ የእሳቱ መንስዔም ምን እንደሆነ ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ አቶ ሰለሞን አክለዋል፡፡ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.ethiopianreporter.com/article/11575 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
d510f0a33881dec680a6af2c61e6c2b3 | d2dbbf004e0e605c9c6ccda6b83ce802 | ሃያ ሺ የሚጠጉ አባወራዎች ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ተጠቃሚ መሆናቸው ተጠቆመ | አዲስ አበባ፡- በ2011 በጀት ዓመት 19 ሺ 739 አባወራዎች ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ቅጥያ ተሰርቶላቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም 12 ሺ 201 አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አመልክቷል፡፡የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን የሥራ ሂደት መሪ ወይዘሮ ሰርካለም ጌታቸው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከሚሰራቸው ሥራዎች መካከል ፍሳሾችን ከህብረተሰቡ ሰብስቦ በማጣራት መልሶ የመጠቀም ሥራ አንዱ ነው፡፡ በዚህም በ2011 ዓ.ም ላይ 19 ሺ 739 አባወራዎች ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ቅጥያ ተሰርቶላቸው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ እንደ ወይዘሮ ሰርካለም ገለፃ፤ ህብረተሰቡ የቤት ለቤት ቅጥያ በስፋት ያለመሳተፍ ችግር ቢኖርም በተያዘው በጀት ዓመት በዋነኝነት ትኩረት በማድረግ 12 ሺ 201 አባ ወራዎችን የቅጥያ ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል፡፡ ባለፉት አራት ወራትም የክረምት ወቅት በመሆኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን ነበር:: በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ውስጥ 689 አባወራዎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በቀጣይ በመካኒሳ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶና በአዲስ ከተማ ቅርንጫፎች ሰፊ ሥራ ለመስራት እቅድ መያዙን የጠቆሙት ወይዘሮ ሰርካለም፤ ከዚህ ቀደም ሶስት ሺ 460 ተሰርቶ ህብረተሰቡ ደጃፍ ላይ ቢደርስም ቅጥያ ያልተሰራላቸውን ማጠናቀቅ እንዲሁም በፕሮጀክት ጽህፈት ቤቶች እየተሰሩ የሚገኙ አምስት ሺ 526 ቅጥዎች ለማጠናቀቅ ይሰራል ብለዋል፡፡ ህብረተሰቡ ሴፍቲ ታንከሩን ላለማፍረስ የፍሳሽ ማስወገጃ ቅጥያ ደጃፋቸው ደርሶ የማይጠቀሙበት ሁኔታ መኖር፣ የመስመር ክዳን ስርቆት፣ በመስመሮች ውስጥ የፕላስቲክ ጠርሙሶች እና የጫት ገረባና ቆሻሻዎችን መክተት እንዲሁም በህገወጥ መንገድ የፍሳሽ ማስወገጃ ቅጥያ የሚያደርጉ ግለሰቦች ለሥራው ተግዳሮት መሆናቸውን የገለፁት ወይዘሮ ሰርካለም ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ወጪ ቆጣቢ በመሆኑ ህብረተሰቡ በአግባቡ መጠቀም እንዳበትም አሳስበዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 22/2012 መርድ ክፍሉ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.press.et/Ama/?p=23454 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
c8500c38a9d9b3bf759725be0d65727e | dbb917ac36cb75ef848fd91968bd6f58 | ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቆም ዘመቻ ተጀመረ | በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ለሚከሰቱ 1.2 ሚሊዮን አደጋዎች አምስት ምክንያቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በተለይ ሁለቱ በፍጥነት ማሽከርከርና ጠጥቶ ማሽከርከር ናቸው፡፡ እነዚህም በተጠናቀቀው 2008 ዓ.ም. በመላ አገሪቱ ለ4,358 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን በሚቀጥሉት ሳምንታት ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቆም ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ባለፈው ዓርብ መስከረም 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠጥቶ ማሽከርከር ለማስቆም ዘመቻ ለመጀመር ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ በመግለጫው ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰሎሞን ኪዳኔ፣ በአጋርነት የሚሠራው የቫይታል ስትራቴጂ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማስተር ሆዙ ሉዋ ካስትሮን ጨምሮ በርካታ የባለድርሻ አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8C%A0%E1%8C%A5%E1%89%B6-%E1%88%9B%E1%88%BD%E1%8A%A8%E1%88%AD%E1%8A%A8%E1%88%AD%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%89%86%E1%88%9D-%E1%8B%98%E1%88%98%E1%89%BB-%E1%89%B0%E1%8C%80%E1%88%98%E1%88%A8 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
24dd8b5e4b76f4146900d6ecbe18f74b | b6c311197a51bb87c1777fb774d322c6 | ሲዳማ ቡና በረከት አዲሱን ለሁለት አመት አገደ | ሶከር ኢትዮጵያ ባረጋገጠችው መረጃ መሰረት በረከት አዲሱ ለሌሎች የክለቡ ተጨዋቾች አርአያ የማይሆን የክለቡን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር ሲፈፅም ደርሼበታለው በማለት ለሁለት አመት ምንም አይነት ግልጋሎት እንዳይሰጥ የዲሲፒሊን ቅጣት አስተላልፎበታል፡፡ከእግር ኳስ ህይወቱ በስተጀርባ ከባድ ጉዳቶች እና ውዝግቦች የማያጡት የቀድሞው የንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ከተማ አጥቂ ባለፈው የውድድር ዘመንም ከአሰልጣኙ ጋር በተፈጠረ ልዩነት ለክለቡ እምብዛም ግልጋሎት መስጠት አልቻለም ነበር፡፡ | ስፖርት | https://soccerethiopia.net/football/22121 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
9a8d5064bfd25ad07950e629381f8e3f | 7cb3bce30691349b73e4687b7229e1c2 | ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ በ2017 | የመጀመሪያው የአዲሱ ብሔራዊ ጦር ልምምድ ተጠናቆ የፊታችን ጥር ወር ሥራውን ይጀምራል፤ የአውሮፓ ሕብረት ወታደራዊ አሰልጣኞች በቀጣዩቹ ሁለት ዓመት ውስጥ እስከ 2ሺሕ ወታደሮችን አሰልጥነው ያወጣሉ ተብሎም ይጠበቃል። የማዕከላዊ አፍሪካ ሠራዊት፣ በማካሄድ ላይ ባለው የነፍስ-አድን ልምምድ፤ የተራቀቀ ትርዒት በማሳየት ላይ ይገኛል።ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ | ዓለም አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/car-eu-army-12-27-2016/3653023.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
e0bc551a236af24b8bc89df9249d8c7c | 8d46cd29e49ff07603a65f2c8682b34b | የሰው ልጅ ከሚበላቸው ምግቦች መካከል እጅግ ፍጹም የሆነውን ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል፤ እንቁላል ግን ለፍጹምነት የቀረበ የምግብ አይነት እንደሆነ ይነገርለታል። | ለሰው ልጅ ምርጡ ምግብ እንቁላል ይሆን?\nእንቁላል በቀላሉ መገኘት ይችላል፣ በቀላሉ መብሰል ይችላል፣ ዋጋውም ርካሽ የሚባል ሲሆን ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ፕሮቲንንም በብዛት ይዟል።
በዩኒቨርሲቲ ኦፈ ከነቲከት የሥነ ምግብ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ክሪስቶፈር ብሌሶ እንደሚሉት እንቁላል ሁሉም አይነት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ያሉት ሲሆን፤ አንድን ፍጥረት በተገቢው ሁኔታ ለማሳደግ ብቻውን በቂ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ።
• ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?
ከዚህ በተጨማሪ እንቁላልን ከሌሎች ምግቦች ጋር ቀላቅሎ መመገብ ሰውነታችን ቫይታሚኖችን በቀላሉ ለመሰብሰብ ያስችለዋል። ለምሳሌ አንድ ጥናት እንደጠቆመው እንቁላልን ከአትክልት ጋር መመገብ በአትክልቱ ውስጥ ያለውን ቫይታሚን ኢ የመሰብሰብ ሥራን ቀላል ያደርገዋል።
ነገር ግን በእንቁላል ውስጥ ያለው የኮሌስትሮል መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ለብዙ ዓመታት መከራከሪያ ሆኖ ቆይቷል። ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ደግሞ ለልብ በሽታዎች ያጋልጣል።
በእንቁላል ውስጥ የሚገኘው አስኳል እስከ 185 ሚሊግራም የሚደርስ ኮሌስትሮል በውስጡ ይይዛል።
ይህ ማለት እንቁላል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ማለት ነው?
ኮሌስትሮል በጉበታችንና በጨጓራችን ውስጥ የሚመረት ቢጫ ቀለም ያለው 'ፋት' (ጮማ) ሲሆን በእያንዳንዱ የሰውነታችን ሴሎች ውስጥ ይገኛል። ብዙዎቻችን መጥፎ ነገር እንደሆነ እናስባለን። ነገር ግን ኮሌስትሮል ሴሎቻችንን ሸፍኖ ከተለያዩ ነገሮች ይጠብቃቸዋል። ከዚህ ባለፈም ቫይታሚን ዲ ለማምረትና እንደ ቴስቴስትሮን እና ኦስትሮጅን ያሉ ሆርሞኖችን ለማማንጨት ይረዳል።
ምንም እንኳን ሰውነታችን ኮሌስትሮልን በራሱ ማማረት ቢችልም ከተለያዩ የእንስሳት ምርቶችም ሊያገኝ ይችላል። ለምሳሌ የበሬ ሥጋ፣ እንቁላል፣ አይብ እና ቅቤን መጥቀስ ይቻላል።
• ምግብ ወሲብን የተሻለ ያደርጋል?
መርሳት የሌለብን እንደ ልብ በሽታ ላሉ ከፍተኛ የጤና እክሎች የሚያጋልጠን ኮሌስትሮል በተፈጥሯዊ መንገድ የሚመረተው ሳይሆን፤ ሰው ሰራሽ የሆነው በተጠበሱ ምግቦች፣ ኬኮችና ሌሎችም ውስጥ የሚገኙት ናቸው።
በእንቁላል ውስጥ የሚገኘው የኮሌስትሮል መጠን ከተለያዩ የእንስሳት ምርቶች የበለጠ ቢሆንም የስብ (ፋት) ክምችቱ ግን በጣም አነስተኛ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ደግሞ ይህ የስብ ክምችት የደም ቧንቧችንን በመድፈን ለልብ በሽታ ሊያጋልጠን ይችላል።
በቦስተን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ኤሊዛቤት ጆንሰን እና ባልደረቦቻቸው በሰሩት ጥናት መሰረት ከቀጥተኛ የእንስሳት ተዋጽኦ የምናገኘው ኮሌስትሮል ለልብ ህመም እንደሚያጋልጥ ማረጋገጫ ማግኘት አልተቻለም።
ሰውነታችን ኮሌስትሮልን እንደ እንቁላል ካሉ ምግቦች ማግኘት ከቻለ በራሱ የሚያመርተውን መጠን መቀነስ ይችላል። ይህ ማለት ደግሞ ተፈጥሯዊው ኮሌስትሮል መቼም ቢሆን በሰውነታችን ውስጥ መኖር ካለበት መጠን አያልፍም ማለት ነው።
• እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? የምርምርና ስርፀት ሥራዎች በኢትዮጵያ
የዘርፉ ባለሙያዎች በቅርቡ በሰሩት ጥናት እንቁላል ምንም አይነት የጤና እክል እንደማያስከትል አረጋግጠናል እያሉ ነው። ተመራማሪዎቹ ባለፉት 17 ዓመታት 30 ሺህ ሰዎች ስለተመገቧቸው ምግቦች የሚያትቱ መረጃዎችን ሲያሰባስቡ ነበር።
በጥናቱም መሰረት በየቀኑ እንቁላል የሚመገቡ ሰዎች በተለያዩ የልብ በሽታዎች የመሞት እድላቸው 18 በመቶ የቀነሰ መሆኑን የደረሱበት ሲሆን በደም ግፊት የመያዝ እድል ደግሞ እንቁላል ከማይመገቡት ጋር ሲነጻጸር 28 በመቶ የቀነሰ ነው።
ምንም አንኳን እርግጠኛ ሆኖ መደምደም ባይቻልም እንቁላል ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚጎላ መገመት ቀላል ነው። በእንቁላል ውስጥ የሚገኘው ኮላይን የተባለው ንጥረ... | UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
8a7181e288a3f72a4ab97db2a901f8ab | e646ff0e6fde77ced2c9c53bf6448cd8 | ጃፓን ለምግብ እርዳታና ሌሎች ለኢትዮጵያ የ30 ሚሊዮን እርዳታ ሰጠች | የዓለም ምግብ ፕሮግራም በበኩሉ የሚፈለገዉ እርዳታ ካልደረሰ አስከፊ ችግር ሊከሰት ይችላል አለ የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱና ለሌሎችም ምላሽ የሚሆን የ 30 ሚሊዮን እርዳታ ዛሬ ይፋ አድርጓል።የምግብ እስርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ዜጎችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስፈልገዉ የገንዘብ መጠን በአስቸኩዋይ ካልደረሰ አስከፊ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታዉቋል።የድምጽ ፋይሉን በመጫን የእስክንድር ፍሬዉን ዘገባ ያድምጡ። | ዓለም አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/japan-food-aid-to-ethiopia-due-to-drought/3261906.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
96cffe7025da574a58c487052e874c45 | 0582cb850cd400216914d5dcbaf313df | ኢንጂነር ይልቃል ሰማያዊ ፓርቲን በድጋሚ ለመምራት ይወዳደራሉ | ሰማያዊ ፓርቲን ከምሥረታው ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ፓርቲውን ዳግም ለመምራት ራሳቸውን ዕጩ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡ፓርቲው ከተመሠረተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባዔ በመጪው ነሐሴ 16 እና 17 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን፣ በወቅቱ በሚካሄደው የአዳዲስ አመራር ምርጫ ላይም በአሁኑ ጊዜ ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት እያገለገሉ የሚገኙት ኢንጂነር ይልቃል፣ ፓርቲውን ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በመሪነት ለማገልገል በዕጩነት እንደሚቀርቡ አረጋግጠዋል፡፡በሰማያዊ ፓርቲ መተዳደርያ ደንብ መሠረት አንድ አባል ፓርቲውን ለመምራት ሁለት ጊዜ እንዲወዳደር ይፈቅዳል፡፡ ኢንጂነር ይልቃልም በዚህ ደንብ መሠረት ዳግም ፓርቲውን ለማገልገል እንደሚወዳደሩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ስለሚኖረው ውድድርና እነማን ተፎካካሪዎቻቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹እስካሁን ድረስ በግልጽ ራሱን ለፕሬዚዳንትነት ዕጩ አድርጐ ያቀረበ ተወዳዳሪ አባል የለም፡፡ እኔ ግን ለምክር ቤቱም ሆነ ለሚመለከታቸው አካላት ለፕሬዚዳንትነት እንደምወዳደር ይፋ አድርጌያለሁ፡፡ ተወዳዳሪዎች እንደሚኖሩ ጥርጥር የለውም፡፡ እስካሁን ይፋ ያደረገ ግን የለም፤›› ብለዋል፡፡በፓርቲው መተዳደርያ ደንብ ላይ ጠቅላላ ጉባዔ በየአንድ ዓመቱ እንደሚሰበሰብ ይደነግጋል፡፡ ይሁንና እስካሁን ድረስ ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ አያውቅም፡፡ ያልጠራችሁት ለምንድነው ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹በየዓመቱ የሚለው እንደ ሁኔታው ነው የሚወሰነው፡፡ ፓርቲው በራሱ አስፈላጊ ነገሮች ሲኖሩና ጉባዔው ቢያያቸው ጥሩ ነው በሚል እሳቤ በየዓመቱ ጠቅላላ ጉባዔ ሊያካሂድ ይችላል እንጂ፣ በአስገዳጅነት በየዓመቱ መካሄድ አለበት የሚል ነገር የለም፡፡ በአስገዳጅነት መካሄድ አለበት የሚለው የሦስት ዓመቱ ነው፤›› ብለዋል፡፡‹‹የጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣን ትልቅ ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን በተግባር ደረጃ ሲታይ ግን በሦስት ዓመት አንዴ ነው የሚሰበሰበው፡፡ ያንን ለምን አንቀይረውም በማለት በዚያ መሠረት ነው ደንባችን ውስጥ ያካተትነው እንጂ፣ የጠቅላላ ጉባዔው የሥልጣን ዘመን ለሦስት ዓመት ጊዜ ነው፤›› በማለት ጨምረው አስረድተዋል፡፡የፓርቲው መተዳደርያ ደንብ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር በሚመለከት የሚደነግገው አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 13፣ ‹‹የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በድጋሚ ካልተመረጡ በስተቀር የሥራ ጊዜያቸው ሦስት ዓመት ይሆናል፡፡ በሊቀመንበርነት የኃላፊነት ቦታ ማገልገል የሚቻለው ለሁለት ተከታታይ ዙሮች ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ከአንድ የሥራ ዘመን ዕረፍት በኋላ ተመልሶ ለዚያው ቦታ ሊመረጥ ይችላል፤›› ይላል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላላ ጉባዔው መደበኛ ጉባዔውን በዓመት አንድ ጊዜ ማካሄድ እንዳለበት ደንቡ በአንቀጽ 24 ላይ ይደነግጋል፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ቢያጋጥምም ማራዘም የሚቻለው ለሦስት ወራት ብቻ እንደሆነ ያሰፍራል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ያሉት አስገዳጅ የሆነ የጉባዔው ስብሰባ በየሦስት ዓመቱ እንደሆነ የሚገልጽ አንቀጽ ግን የለም፡፡የፊታችን ቅዳሜና እሑድ በሚካሄደው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ በአጠቃላይ የነበረውን የፓርቲውን ጉዞ እንደሚገመገም የተገለጸ ሲሆን፣ በተጨማሪም ፓርቲው አሁን ካለበት ተነስቶ ምን ማድረግ አለበት የሚሉትን ጉዳዮች፣ እንዲሁም አጠቃላይ የአገሪቱንና የቀጣናውን የፖለቲካ ሁኔታ በመዳሰስ አቋም እንደሚወሰድ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡በጠቅላላ ጉባዔው ለመሳተፍ ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ 250 ያህል የፓርቲው አባላት እንደሚወከሉ ገልጸው፣ ‹‹ጠቅላላ ጉባዔውም ጠንካራ የትግል መንፈስ ለመፍጠርና ፓርቲው የነበሩትን ጠንካራና ደካማ ጐኖችን ገምግሞ፣ በጠንካራዎቹ ላይ የበለጠ ለመሥራት፣ ደካማ ጐኖችን ደግሞ እየቀረፈ በመሄድ ተጠናክሮ ለመሥራት አቅጣጫ ይቀመጣል፤›› በማለት ኢንጂነር ይልቃል የጠቅላላ ጉባዔው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ በይፋ መመሥረቱን ያወጀው ታኅሳስ 2004 ዓ.ም. ላይ የነበረ ቢሆንም፣ በምሥረታው ወቅት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡ፓርቲውንና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን አወዛግቦ የነበረው ጉዳይ ደግሞ ፓርቲው ያቀርበው የነበረ የሕግ አግባብ ነው፡፡ ይህም አንድ ፓርቲ የምሥረታ ጥያቄውን ለምርጫ ቦርድ ባቀረበ ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ካልተሰጠው ዕውቅና እንደተሰጠው ይቆጠራል የሚለው ነው፡፡ በዚህም መሠረት ፓርቲው በታኅሳስ 2004 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ መመሥረቱን ይፋ ሲያደርግ፣ ከምርጫ ቦርድ ዕውቅና አግኝቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ግን ከሐምሌ 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡ | ፖለቲካ | https://www.ethiopianreporter.com/article/8404 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
1ace737574924851bdee90f05c5f39e5 | 6f25bfd8796fda2ea66336238251826f | የ40/60 ቤቶችን ብረት በመዝረፍ የተጠረጠሩ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው | የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ እየገነባቸው ለሚገኙት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የተገዙ ብረቶችን በመዝረፍ ለግል ጥቅማቸው በማዋል ተጠርጥረው በታሰሩ ሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ፣ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀናት ጊዜ ተጠየቀባቸው፡፡ተጠርጣሪዎቹ የኢንተርፕራይዙ የንብረት አስተዳደር ሠራተኛ መብራቱ ካሳሁን፣ የንብረት ክፍል ሠራተኛ ሔኖክ ነጋሳ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ሥራ አስኪያጅ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር፣ ነጋዴዎች ታከለ ግርማ፣ ይስሀቅ ለማ፣ ጌታቸው ዩሱፍና የገልባጭ ተሽከርካሪ ሾፌር ዕቁባይ ገብረ ጊዮርጊስ መሆናቸውን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መርማሪ ፖሊስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አስረድቷል፡፡ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለውን ባለስድትና ባለ ስምንት ስታፋ ብረቶች ከመጋዘን በሐሰተኛ ሰነድ ዘርፈው መውሰዳቸውንና በተለያዩ ቦታዎች በመበታተን፣ በመሸጥና በመሸሸግ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ምርመራ የተለያዩ ሰነዶችን መሰብሰቡን ገልጾ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን፣ የጣት አሻራ መወሰድ እንደሚቀረውና የተወሰኑ ብረቶችን ማስመለስ እንደሚቀረው በማስረዳት፣ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ተከሳሾቹ የተጠረጠሩበት ጉዳይ ዋስትና እንደማያስከለክል አስረድተው ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡ነገር ግን መርማሪ ፖሊስ ጥያቄውን በመቃወም በዋስ ቢለቀቁ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ሊያስጠፉ እንደሚችሉ፣ ሥልጣን ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች በመሆናቸው ሰነዶችን ሊያጠፉ እንደሚችሉ አስረድቶ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ለመርማሪው የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ሰጥቶ የዋስትና ጥያቄውን በማለፍ፣ ለታኅሳስ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8B%A84060-%E1%89%A4%E1%89%B6%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%88%A8%E1%8D%8D-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%88%A8%E1%8C%A0%E1%88%A9-%E1%89%B0%E1%8C%A8%E1%88%9B%E1%88%AA-%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%88%98%E1%88%AB-%E1%8C%8A%E1%8B%9C-%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%89%A3%E1%89%B8%E1%8B%8D | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
41f642ab30376bab5e96da540d7788ed | 5ac262c14313da8274724eb2022a9e70 | በግጭት የተሳተፉ አመራሮች ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ | በአገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በአገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ የፈጠሩ ኃይሎችንና አመራሮችን በሕግ መጠየቅ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ አብዛኞቹ የግጭት ፈጣሪዎች በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ሥር የዋሉ መሆኑንና ቀሪዎቹን በዚህ ሳምንት ውስጥ በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ አረጋግጠዋል፡፡ ከፀረ ሰላምና አሸባሪ ኃይሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በቅርቡ በአገሪቷ የተከሰተውን አለመረጋጋት ለራሳቸው የፖለቲካ ፍላጎት በመጠቀም እየሠሩ የነበሩና የሚገኙ አመራሮች ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት የኪራይ ሰብሳቢዎችና የኢሕአዴግ አመራሮች ተሳትፎ እንደነበረበት ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በአወዳይ ላይ ዜጎች መቀላታቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ፈጥኖ ባይደርስ ኖሮ እልቂቱ የከፋ ነበር ብለዋል፡፡ ‹‹የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ንፁህ ፖሊስ ነው፤ ሕዝባዊም ነው፤›› ሲሉ አወድሰዋል፡፡ | ፖለቲካ | https://www.ethiopianreporter.com/article/2712 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
02d5980b1d59aab9c8bab857fea39533 | ca6a82752dbf21da5639127483d9baa8 | በኡጋንዳ 30 ባለስልጣናት በመፈንቅለ መንግስት ሴራ መታሰራቸው ውጥረት ፈጥሯል | የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮሪ ሙሴቬኒ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣኔን ለመቀማት ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለሁ ያሏቸውን 30 ያህል የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መሪዎችና ባለስልጣናት ማሳሰራቸውን ተከትሎ በአገሪቱ ውጥረት መንገሱ ተዘገበ፡፡ከአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመጣል አሲረዋል የተባሉት የጦር መሪዎችና ባለስልጣናቱ፣ ባለፈው ሳምንት መታሰራቸውን ያስታወሰው አሶሼትድ ፕሬስ፤ ይህን ተከትሎም ድርጊቱን የተቃወሙ ታጣቂዎች በመንግስት ፖሊሶች ላይ ተኩስ መክፈታቸውንና ውጥረት መንገሱን ገልጧል፡፡የአገሪቱ ፖሊስ ከመፈንቅለ መንግስት ሴራው ጋር ንክኪ አላቸው ያላቸውን በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና ደጋፊዎችን ማሰር መቀጠሉን የጠቀሰው ዘገባው፤ 12 ያህል የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ ታጣቂዎች፣ ኡጋንዳ ፒዩፕልስ ኮንግረስ የተባለው ፓርቲ አባል የሆኑትንና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉትን ዳን ኦላ ኦዲያ የተባሉ ግለሰብ ለማስለቀቅ፣ባለፈው እሁድ በፖሊስ ላይ ተኩስ በመክፈት ብጥብጥ መፍጠራቸውን ጠቁሟል፡፡ ባለፈው የካቲት ወር በተካሄደው የአገሪቱ ምርጫ የሙሴቬኒ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡትና የምርጫውን ውጤት በመቃወም ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል ወደ ወህኒ የተወረወሩት ፎረም ፎር ቼንጅ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ኪዛ ቢሲጂ፤ባለፈው ረቡዕ በአገር ክህደት ተከሰው በናካዋ ከተማ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት፣ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ እንደነበር ዘገባው አመልክቷል፡፡ መፈንቅለ መንግስቱን የጠነሰሱት ኪዛ ቢሲጄ የተባሉ የአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር እንደሆኑ መነገሩን የጠቆመው ዘገባው፣ ግለሰቡ በአገር ክህደት ከተከሰሱት ቢሲጂ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ገልጾ፣ ቢሲጂ በመንፈንቅለ መንግስቱ ሴራ እጃቸው ሊኖርበት እንደሚችል መጠርጠሩን አስታውቋል፡፡ቪኦኤ በበኩሉ፤ የአገሪቱ መንግስት ባለስልጣናቱን በመፈንቅለ መንግስት ሴራ ጠርጥሮ ማሰሩ በቀጣይም ከፍተኛ ብጥብጥ ሊፈጥርና አገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ ሊከታት እንደሚችል እየተነገረ እንደሚገኝ ዘግቧል፡፡ | ዓለም አቀፍ ዜና | https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=18385:%E1%89%A0%E1%8A%A1%E1%8C%8B%E1%8A%95%E1%8B%B3-30-%E1%89%A3%E1%88%88%E1%88%B5%E1%88%8D%E1%8C%A3%E1%8A%93%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%88%98%E1%8D%88%E1%8A%95%E1%89%85%E1%88%88-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%88%B4%E1%88%AB-%E1%88%98%E1%89%B3%E1%88%B0%E1%88%AB%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%8B%8D%E1%8C%A5%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%8D%88%E1%8C%A5%E1%88%AF%E1%88%8D&Itemid=212 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
f733ada59b037dc0071da0cf52db94fd | c56a445992ccb830fb5712a2f1493ca0 | በባሕር ዳር ከተማ በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ | የአማራ ክልል አድማ ብተና 2ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል ምክትል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ዳኛ ለአብመድ እንደተናሩት፤ በ20 ጆንያዎች የተቋጠረ 497 ሽጉጥ እና ወደ 46 ሺህ የሚገመት ጥይት በባሕር ዳር ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነትና ከኅብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ከነዳጅ ጋር ተቀላቅሎ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በገባ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ውስጥ ሲጓጓዝ ነው ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተደረገ ክትትል ነው ባሕር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡አሽከርካሪው ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ያስታወቁት ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ነዳጁ ከባሕር ዳር አልፎ የሚሄድ እንደነበርና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያውን ከቦቴው ለማውጣት የሚያገለግል ብረት ከተሽከርካሪው መገኘቱን አመልክተዋል፡፡ | ፖለቲካ | https://waltainfo.com/am/31352/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
beddd20d92ba7652a1d49b684b99db0b | eb18a57edcb010752485d227ad86b8f8 | ባሕር ዳር በጣና ላይ የጀልባ ትርኢትና በሌሎች መሰናዶዎች እንግዶችን ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች፡፡ | ባሕር ዳር ጥር 7/2012ዓ.ም (አብመድ) ሆቴሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች ለጥምቀት በዓል የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል፡፡ለእንግዶች አቀባበል ያደረጉትን ዝግጅት በተመለከተ አብመድ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳድር የሚገኙ የሆቴል ሥራ አስኪያጅ እና አስጎብኚ ድርጅቶችን አነጋግሯል፡፡ የዩኒሰን ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ አክሊሉ ባለፈው የልደት በዓል ጥሩ ዝግጅት እና አፈጻጸም እንደነበራቸው ተናግረዋል፡፡ ለጥምቀትም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሃገር ለሚመጡ እንግዶች እንደየ ባህላቸው አገልግሎት ለመስጠት ሆቴሉ በቂ ዝግጅት አድርጓል ነው ያሉት፡፡የባሕር ዳር ከተማ የአስጎብኚዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ማስተዋል ዘለቀ ደግሞ ለጥምቀት በዓል የበጎ ፈቃድ አግልግሎት የሚሰጡ 28 ወጣቶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ የጎንደርን የጥምቀት በዓል ለመታደም የሚመጡ እንግዶች በባሕር ዳር የሚኖራቸውን ቆይታ ያማረ እና አይረሴ ለማድረግ ማኅበሩ መዘጋጀቱንም ነው የተናገሩት፡፡ ከዝግጅቶች መካከልም ጥር 14/2012 ዓ.ም በጣና ሐይቅ ላይ የሚካሄደው የጀልባ ትዕይንት ይጠቀሳል፡፡ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.amharaweb.com/%e1%89%a3%e1%88%95%e1%88%ad-%e1%8b%b3%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%8c%a3%e1%8a%93-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%8d%e1%89%a3-%e1%89%b5%e1%88%ad%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%88%8c/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
516ba357e3695520a652c2b3725371f8 | afd67eb9614d258a9386d57081f69c9e | ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 225 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል | አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 225 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ቫይረሱ የተገኘባቸው 5 ወንድ እና 6 ሴት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ17 እስከ 45 አመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ 6 ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ፣አንድ ሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ለይቶ ማቆያ ናቸው፡፡ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ ሰባቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው እንዲሁም አንደኛው ንክኪም ሆነ የውጭ ሃገር ጉዞ የሌለው ነው ብለዋል።በዚህም አሁን ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 317 ደርሷል፡፡እስካሁን 113 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት 197 ሰዎች ደግሞ በህክምና ላይ ይገኛል።የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ። | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.fanabc.com/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-24-%e1%88%b0%e1%8a%a0%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%88%884-%e1%88%ba%e1%88%85-225-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%88%8b%e1%89%a6%e1%88%ab%e1%89%b6%e1%88%aa/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
f785875b8b9a38373c834c49d11b36d1 | 9b895abb338607b96935805ce73b361d | በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ሊፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ | በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ሊፈፅሙ በዝግጅት ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ ።በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ብጥብጥና የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሶስት የባጃጅ አሽከርካሪዎች እና በመድሃኒዓለም ክፍለ ከተማ ደግሞ ለአድማ የሚያነሳሳ መልዕክት የያዘ ወረቀት ሲበትኑ የነበሩ አምስት የፀረ ሠላም ኃይሎች ናቸው የተያዙት።ግለሰቦቹ በከተማዋ ነዎሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተመልክቷል። በተጨማሪም ከሶስት ቀን በፊት በከተማዋ ላይ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የፀረ ሠላም ሀይሎች ከያዙት ቦምብ ጋር በፀጥታ ሀይሎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢሮው አስታውሷል።በሌላ በኩል ነሃሴ 6 2009 ምሽት 1 ሰአት ከ50 በባህር ዳር ሰፈነ ሰላም ክፍለ ከተማ አካባቢ ቦምብ በመወርወር ለሁለት ሰዎች መቁሰል ምክንያት ሆነዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ አምቦ ቀበሌ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል(ኤፍ.ቢ.ሲ) ። | ፖለቲካ | https://waltainfo.com/am/29306/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
4acd70377521db08843aa6de4cccd4ff | 01daa25af9657e855e41766969e5368e | የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም ለቆመችለት መርህ ያላትን ታማኝነት ያረጋገጠ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር | አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም ለቆመችለት መርህ ያላትን ታማኝነት ያረጋገጠ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በህዳሴ ግድብና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡በመግለጫቸውም የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም ለቆመችለት መርህ ያላትን ታማኝነት ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያውያን ያቀዱትን የሚያሳኩ ሀዝቦች መሆናቸውን ለዓለም ያስመሰከሩበት መሆኑንም አውስተዋል፡፡በህዳሴ ግድብ ላይ እየተካሄደ ያለው የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት መመራቱ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑንም አስረድተዋል።በመግለጫው የውሃ ሙሌቱ በድል መጠናቀቁ ኢትዮጵያውያንን በዓለም መድረክ ከፍ አድርጓልም ነው ያሉት።በሌላ በኩል በባህር ማዶ በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተም ከዓለም አቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡እስካሁንም ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኩዌት፣ ቤሩት እና ከሌሎች ሃገራት 30 ሺህ 87 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ከዚህ ባለፈም ወደ ሃገር ቤት የሚመለሱትን ዜጎች የማቋቋም ስራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡በሌላ በኩል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኮቪድ19 ሳቢያ ችግር ውስጥ ለገቡ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡በምስክር ስናፍቅ እና ስላባት ማናዬ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8b%b3%e1%88%b4-%e1%8c%8d%e1%8b%b5%e1%89%a5-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%aa%e1%8b%ab-%e1%8b%99%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8b%8d%e1%88%83-%e1%88%99%e1%88%8c%e1%89%b5-2/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
e896557d4200fe016b437761f05f6739 | 5219b0a1422ea8c6be13e00f1e4eaffc | የሰላም ኮንፈረንስ በይርጋለም ከተማ | የአገር ሸማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ በይርጋለም ከተማ ተካሂዷል፡፡ወጣቶች ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ የሲዳማ "ሃላሌ" ባህላዊ ስርዓት ተከትለው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠይቁ የሲዳማ አገር ሸማግሌዎች አሳስበዋል፡፡"ኤጄቶዎች" ወይም የሲዳማ ወጣቶችና አገር ሸማግሌዎች የጋራ የሰላም ኮንፈረንስ ማካሄድ ከጀመሩ በኋላ ለውጥ መታየቱን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ አስታውቋል፡፡"ኤጄቶዎች" የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የሚረጋገጥበትን ህዝበ ውሣኔ እንዲያስፈፅም የክልሉ ምክር ቤት ለምርጫ ኮሚሽን ቢስታውቅም ዘግይቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ | ሀገር አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/yergalem-peace-conference-1-30-2019/4765690.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
41fca0cb804a9b7883787d6f4463dd42 | 8703949006519fc8763580785a0eb18e | የጋዜጠኛ መሃመድ ስራጅ አጭር የህይወት ታሪክ | • ሙሉ ስም ከነአያት፡___መሃመድ ስራጅ ዋበላ
• እምነት፡- ሙስሊም
• ዕድሜ፡__38
• ጾታ፡__ወንድ
• ዜግነት፡- ኢትዮጵያዊ
• አሁን የሚሰራው ሥራ (መስሪያ ቤት)፡- የማስታወቂያ ባለሙያ፤ደራሲ፤የማህበረሰብ አንቂና ጋዜጠኛ ሲሆን በአዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ በዋና ስራ አስኪያጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡
የት/ ደረጃ፡-
የመጀመሪያ ድግሪ በቋንቋና ስነ-ጽሁፍ ፤በሁለተኛ ድግሪ በማህበረሰብ ጥናት (Sociology) በአሁን ሰአት ደግሞ በሚችጋን ዩኒቨርሲቲ Leadership and Management (Leading People and Teams Specialization) Masters Program From University of Michigan.
የስራ ልምድ፡_
ከ19/97 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁኗ ሰአት ድረስ 18 አመት በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ከባለሙያ እስከ ከፍተኛ ሃላፊነት፤በግል ስራ ድርጅት አስተዳደር፤በጋዜጠኝነትና በማህበረሰብ አንቂነት እየሰራ ሲሆን በአሁን ሰአትም በአለም አቀፍ ተደማጭነት ባለው ተወዳጅና ተመራጭ የራዲዮ ጣቢያ አዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ራዲዮ በስራ አስኪያጅነት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በአመራሩም በሃገራችን ካሉ ሚዲያዎች በዚሁ አመት በኢትጵ ብዙሃን መገናኛ ተሸላሚ እንዲሆን አድርጓል፡፡
• ጋዜጠኛ መሃመድ ስራጅ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ሃገሩን በተሰማራባቸው ዘርፎች በታማኝነት፤በቅንነትና ያለ አድሎ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ በጋዜጠኝነትና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ከ18 አመታት በላይ ያገለገለ ሲሆን በዋናነት ከሰራባቸው የሚደያ ተቋማቶች መካከል የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን፤በፋና፤ በዋልታ፤በኢ.ቢ.ኤስ፤በኤፍ.ኤም.አዲስ 97.1፤በአሐዱ ኤፍ.ኤም.94.3፤በአሁኑ ሰአት ደግሞ በአዋሽ 90.7 ኤፍ.ኤም በስራ አስኪያጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡
• ጋዜጠኛ መሃመድ ሃገሩን በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በተለያዩ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ሰርቷል፤በማህበረሰብ አንቂነት፤በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች፤ከግለሰብ አስከ ክልልና ብሔሮች መካከል በእርቅና በሰላም፤በባህልና በቱሪዝም፤በሐይማኖት አብሮነት፤በዲሞክራሲና ኢኮኖሚ ግንባታ፤በስራ ባህል መዳበር፤
• የኢትዮጵያ ኩላሊት ህሙማን እጥበት ማህበርን በመመስረት፤ገንዘብ በማሰባሰብና በመደገፍ፣ የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎትን በመደገፍና ደም በማሰባሰብ፣ በጎዳና ላይ ህጻናቶች በበርካታ የህብረተሰባዊ ድጋፍ አገልግሎቶች ላይ ተሳትፎ በማድረግ እና በማህበራዊ ጉዳዮች በመንቀሳቀስ አመርቂ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተለይ የህጻናት ማሳደጊያዎችን ገቢ በማሰባሰብ፤በመደገፍና በማስተባበር የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመመገብና ከሱሰኝነት እንዲላቀቁ በማድረግ፤ በትምህርት፣ በጤና፣ በጋብቻ እና በኢንተርፕርነሮች ዘርፎች ባለሞያዎችን በማስተባበር በነጻ ስልጠና ለተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች እየሰጠም እያሰጠም ይገኛል፡፡
• ጋዜጠኛና ደራሲ መሃመድ ስራጅ በተለያየ ጊዜያት ከ500,000 ሰው በላይ ጊዜያዊ የስራ እድል ፈጠራ፤በአወንታዊና ሀገራዊ አስተሳሰብ፤በተለያዩ ሃገር በቀል ፕሮጀክቶች፤በሀገርና በስብእና ገጽታ ግንባታ፤በህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰብ፤በ6ተኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ፤በሰሜኑ አካባቢ በተከሰተው ጦርነት ከገቢ ማሰባሰብ እስከ የጦር ዘገባ፤
• ለተከታታይ 10 አመታት በተለያዩ በክልልና በማህበረሰብ ራዲዮ፤በሚኒ-ሚዲያና በተለያዩ ክበባት በተግባቦት፤በመሰራዊ ጋዜጠኝነት፤በራስ ማሰተዳደር እና በሌሎች የህይወትና የስራ ክህሎቶች ከ1,5000 ሰው በላይ በነጻ ስልጠና በመስጠት፤በኮቪድ-19 የግንዛቤ ፈጠራና ገቢ ማሰባሰብ፤የየክልል ልማት ማህበሮች ገቢ ማሰባሰብ፤በህገ-ወጥ ስደት፤በአረንጓዴ አሻራ፤በዲፕሎማሲ፤በአዳዲስ ፈጠራና በቴክኖሎጂ፤በሃገራዊ መግባባትና የተለያዩ የአስተሳሰብ ከፍታን የሚያሳዩ ሃገር የሚያሻግሩ በራሱ ወጪ ስድስት(6)ታትመው ለንባብ የበቁ መጽሐፎች ‹‹ከሰማይ ውስጥ››፤‹‹ከፍታ››፤ ‹‹ጋብቻና ፍቅር››፤‹‹መሪ››፤‹‹ይመለከተኛል ኢትዮጵያ›› የተሰኙ መጽሃፎችን ለሃገሩ አንባቢዎች ያበረከተና ሌሎች በአሁን ሰአት ለህትመት የተዘጋጁ ከስምንት (8) በላይ እጅግ ትውልድን የሚቀይሩ አወንታዊ አስተሳሰብን፤የስራ ባህልን፤የቁጠባ ባህልን፤የንባብ ባህልንና የአብሮነት እሴትን የሚያዳብሩና ለጥናትና ምርምር መነሻ የሚሆኑ ዝግጅትና አርትኦት ስራቸው ጥንቅቅ ያሉ አእምሮን የሚለሙ መጽሃፎቶች በእጁ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለነዚህም ስራዎቹ ምስክርነት መንግታዊና መንግታዊ ካልሆኑ ተቋማት ከመቶ ሰማንያ (180) በላይ የምስጋናና የምስክር ወረቀቶች በማህደሩ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ500,000 (ከአምስት መቶ ሺ) በላይ ተከታይ ባለው የግል ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም አነቃቂና ሃገራዊ ሃሳቦችን በማንሳት ማህበረሰቡን በሃገር ፍቅር፤በመልካም ስነ ምግባር በማሳወቅ፤በመቀስቀስና ተአማኝ መረጃ በመስጠት ሃገሩ በፈለገችው ቦታዎች ሁሉ በፍትሃዊነት፤በታማኝነትና በልማታዊ አስተሳሰብ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ሃገሩን በቁርጠኝነት እያገለገለ ይገኛል፡፡
• ጋዜጠኛና ደራሲ መሃመድ ስራጅ በአሁን ሰአትም በአዋሽ 90.7 ኤፍ.ኤም ከስራ አስኪያጅነት በተጨማሪ ተወዳጅና ትውልድ ገንቢ የሆኑ ‹‹ከአባይ ጓዳ››፤ ‹‹ይመለከተኛል ኢትዮጵያ››፤ ‹‹አዋሽ ስፔሻል›› ፤ “አዋሽ ወቅታዊ”ና ሌሎችንም ፕሮግራሞችን በዋና አዘጋጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡ | UNK | null | https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia |
a1e289c3d18e2f8acae5f4c85ef5cc79 | 5be0f5a37a03c78cfb5a8e3cf943f928 | አራት ሜክሲኳውያን ተማሪዎች ከጾታዊ ጥቃት የሚከላከል ካፖርት ፈልስፈዋል። የካፖርቱ እጀታ የተሰራው ከሚነዝር ኤሌክትሪክ ሲሆን፤ ጥቃት የሚሰነዝር ሰው ካፖርቱን የለበሰን ሰው ክንድ ሲይዝ እንዲነዝረው ያደርጋል። | የሜክሲኮ ተማሪዎች ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ፈለሰፉ\nየካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነው
ተማሪዎቹ ካፖርቱን የፈለሰፉት ሀገራቸው ውስጥ የተንሰራፋውን ወሲባዊ ትንኮሳ ለመከላከል ሲሆን፤ "ውሜን ዌረብል"ወይም "እንስቶች የሚለብሱት" የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቶታል።
• ሴቶች እንዲደፈሩ ያበረታታው ግብጻዊ የህግ ባለሙያ ተፈረደበት
• ካይሮ፡ ለሴቶች በጣም አደገኛ ከሆኑ ከተሞች አንዷ
ከአራቱ ተማሪዎች ሁለቱ አናይድ ፓራ ኮሬዝ እና ኤስቴላ ጎሜዝ የሜካትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ናቸው። የሮቦቲክስ ተማሪዋ ግዌን ፓርክ እንዲሁም የህግ ተማሪ ጉዋዱልፔ ማርቲኔዝም ተሳትፈዋል።
አራቱ የካፖርቱ ፈልሳፊዎች
ፈልሳፊዎቹ የፈጠራ ኃሳቡ ብልጭ ያለላቸው ለአንድ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ፕሮጀክት ሲያውጠነጥኑ ነበር። አናይድ ፓራ "ብዙ ሴት ጓደኞቻችን የሀይል ጥቃት ይደርስባቸዋል። ጾታን መሰረት ስላደረገ ጥቃት ጥናት ከሰራን በኃላ ካፖርቱን ለመስራት ወሰንን" ትላለች።
በሚኖሩበት የሜክሲኮዋ ፑቤላ ግዛት በየቀኑ ወሲባዊ ትንኮሳ ይደርሳል።
ካፖርቱ የተሰራው ከጥጥ ሲሆን፤ ዘጠኝ ቮልት የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጭ ባትሪ ውስጡ ተቀብሯል። የኤሌክትሪክ ገመዱ በካፖርቱ ውስጥ ለውስጥ ይዘዋወራል። ካፖርቱ ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ መዝጊያው (ዚፕ) ላይ ማብሪያና ማጥፊያ ተገጥሞለታል።
ካፖርቱ የሚሰራው ቀልፉን በመጫን ነው
አንድ ሰው ካፓርቱን የለበሰ ሰውን ለማጥቃት አስቦ የተጠቂውን ክንድ ቢይዝ የኤሌክትሪክ ንዝረት ይከተላል። አጥቂው በኤሌክትሪክ ንዝረቱ ሲንዘፈዘፍ ተጠቂው ከአካባቢው ርቆ ለመሸሽ ጊዜ ያገኛል።
የህግ ተማሪው ጉዋዱልፔ ማርቲኔዝ፤ ካፖርቱን ጥቅም ላይ ማዋል የህግ ጥያቄ እንደማያስነሳ ሲያስረግጥ "አላማው ራስን መከላከል ብቻ ነው" በማለት ነው።
ካፖርቱ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ንዝረት ለህይወት ስለማያሰጋ እንደ መሳሪያ ሊቆጠር እንደማይቻልም ያስረዳል።
• ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ
• ቢል ኮዝቢና ፖላንስኪ ከኦስካር አካዳሚ ተባረሩ
የካፖርቱን ንድፈ ሀሳብ የሚያሳይ የሙከታ ስራ (ፕሮቶታይፕ) ለማጠናቀቅ ሶስት ወር ወስዶባቸወሰል። በቀጣይ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ከካፖርቱ እጀታ በዘለለ በሌሎች የካፖርቱ ክፍሎችም የመግጠም እቅድ አላቸው።
ተማሪዎቹ ተመሳሳይ መንገድ በመጠቀም ነዛሪ ካናቴራ፣ ቀሚስና ሱሪም ለመስራት አስበዋል። ካፖርቱ ገበያ ላይ ከዋለ 50 ዶላር የሚሸጥ ይሆናል።
| UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
3277fc6d984bc7a4f40c4d8700ba6534 | e8448e3362bf4c1a7797852c4f299444 | ሰርከም ሚኒራል በአፋር ፖታሽ እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጠው | ሰርከም ሚኒራል የተባለው የእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያ፣ የፖታሽ ማዕድን በአፋር ለማውጣት የሚያስችለውን ስምምነት ከማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ጋር ተፈራረመ፡፡ስምምነቱን ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳና የሰርከም ሚኒራል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብራድ ሚልስ በሚኒስቴሩ ቅጥር ግቢ ዓርብ መጋቢት 29 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ተፈራርመዋል፡፡ከፊርማው ሥነ ሥርዓት በኋላ ኩባንያው ሥራውን በሁለት ወራት ውስጥ ይጀምራል ተብሏል፡፡ ለኩባንያው የተሰጠው የከፍተኛ ደረጃ የማዕድን የማውጣት ፈቃድ ለሃያ ዓመት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን፣ በባለፈቃዱ ጥያቄ መሠረት የፈቃድ ዕድሳት ጊዜ ከአሥር ዓመታት ላልበለጠ ጊዜ ሊታደስ ይችላል፡፡ይህ የማዕድን የማውጣት ፈቃድ ኩባንያው በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ በ365 ኪሎ ሜትር ካሬ ውስጥ የሚገኝ 4.9 ቢሊዮን ቶን የፖታሽ ማዕድን ላይ መብት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ከፖታሽ ማዕድን ጋር በተያያዘ ሰርከም ሚኒራል ማዕድኑን የማውጣት ፈቃድ ያገኘ ሁለተኛው ኩባንያ ሆኗል፡፡ ከአሁን ቀደም አላና ፖታሽ የተባለው የካናዳ ኩባንያ ፈቃዱን አግኝቶ ነበር፡፡ በቅርቡም ያራ የተባለው ዓለም አቀፍ ኩባንያ የፖታሽ ማዕድን ለማውጣት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ጥያቄውም በመንግሥት እየታየ እንደሆን ተገልጿል፡፡ ያራ ኢትዮጵያ ወደ አገር ውስጥ የምታስገባቸውን ማዳበሪያዎች ለብዙ ዓመታት ሲያቀርብ እንደነበር ይታወሳል፡፡በፖታሽ ላይ የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በዳሎል ብቻ 12 ቢሊዮን እስከ 14 ቢሊዮን ቶን የሚጠጋ የፖታሽ ማዕድን አለ፡፡ሰርከም ሚኒራል ከዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በፖታሽ ፍለጋ ላይ ነበረ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በዳሎል ጥናት እንዲያደርግ ፈቃድ አግኝቷል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በአካባቢው ላይ ማዕድኑን ማግኝት እንዳቻለ አሳውቆ ነበር፡፡እስካሁን ባለው ቆይታ ኩባንያው ወደ 65 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉ ታውቋል፡፡ ከአሁን በኋላ በአምስት ዓመት ውስጥ ፖታሽ ማምረት ይጀምራል ተብሏል፡፡በአጠቃላይ ወደ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያወጣ ተገልጿል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየተነጋገረ እንደሆነ ኩባንያው ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ሰርከም ሚኒራል በዓመት 2.75 ሚሊዮን ቶን ፖታሽ እንደሚያመርት፣ ከዚህ ውስጥ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋው ፖታሽ እንደሆነና ቀሪውን ፖታሽየም ሰልፌት ዳሎል ከሚገኘው ፕሮጀክቱ ያመርታል ተብሏል፡፡ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ የፖታሽ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ መቀነሱ ይታወሳል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት 570 ዶላር በቶን ሲሸጥ የነበረው በአሁኑ ጊዜ ወደ 214 ዶላር ወርዷል፡፡ሰርከም ሚኒራል የሚያከናውነው ፕሮጀክት ከታጁራ ወደብ በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ይገኛል፡፡ ከፕሮጀክቱ እስከ ወደቡ የሚያገናኙ መንገዶችን ለመገንባት መንግሥት እየሠራበት አንደሆነ፣ በፊርማው ላይ የተገኙት የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቴዎድሮስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግረዋል፡፡ከፕሮጀክቱ ጋራ የሚያገናኙ መንገዶችን ለመገንባት በቅርቡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የግንባታ ውል እንደተፈራረመ ይታወሳል፡፡በዋናነት ኩባንያው የውጭ ገበያ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ በአገር ውስጥ ሊገነቡ ለታቀዱ የማዳበሪያ ፋብሪካዎችም ፖታሽ ማቅረብ እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡በቅርቡ የሞሮኮ መንግሥት በኢትዮጵያ የማደበሪያ ፋብሪካ በ3.7 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያቋቁም መግለጹ ይታወሳል፡፡ ፋብሪካው ሲጠናቀቅ በዓመት 3.7 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በተጨማሪም ያዩ የተባለው የማዳበሪያ ፋብሪካ በብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሥር በግል ኩባንያዎች እየተገነባ ነው፡፡ ይህ ፋብሪካ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 300 ሺሕ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ወደ አገር ውስጥ ተገዝተው በሚገቡ ማዳበሪያዎች ጥገኛ ለሆነው የኢትዮጵያ ገበያ፣ በመንግሥት በሺዎች ቶን መጠን ይቀርብለታል፡፡ | ቢዝነስ | https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%A8%E1%88%9D-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%AB%E1%88%8D-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8D%8B%E1%88%AD-%E1%8D%96%E1%89%B3%E1%88%BD-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%8B%AB%E1%8B%88%E1%8C%A3-%E1%8D%88%E1%89%83%E1%8B%B5-%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%8C%A0%E1%8B%8D | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
8027a1fd917d94f6787d9b11bda25a8d | 28afc57ca782158a223abb5b84bc0307 | ግዙፉ ኤሌክትሮኒክስ አምራቹ ፎክስኮን ኮሮናቫይረሰን ለመከላከል ወይም በቀዶ ህክምና ወቅት ሊደረግ የሚችል የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ወይም ጭምብል ሊያመርት መሆኑ ተነግሯል። | የአይፎን ስልክ አምራቹ ኩባንያ ኮሮናቫይረስ መከላከያ ጭምብል ማምረት ሊጀምር ነው\nየአይፎን ስልክ አምራች ጭምር የሆነው ኩባንያው በኮሮናቫይረስ ምክንያት በቻይና ለመዝጋት የተገደደውን ማምረቻ ጣቢያዎቹን ለመክፍት ጥረት እያደረገ ይገኛል።
የኮሮናቫይረስ መከሰት በመላው ዓለም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ 'ማስክ' እጥረት እንዲያጋጥም አድርጓል።
ፎክስኮን በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በቀን ሁለት ሚሊዮን የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎችን ለማምረት ማቀዱን አስታውቋል።
"ይህን ወረርሽኝ ስንዋጋ እያንዳንዷ ሰከንድ ትርጉም አላት" ሲል ኩባንያው 'ዊቻት' በተሰኘው ማህብራዊ ሚዲያ ላይ አስፍሯል።
"የመከላከል እርምጃ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ያስችላል። የሰዎችን ህይወት መታደግ መቻል ማለት በፍጥነት ቫይረሱን ማሸነፍ ማለት ነው" ብሏል አይፎን አምራቹ ኩባንያ።
ይህ ኩባንያ የዓለማችን ግዙፉ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ሲሆን፤ ከአይፎን በተጨማሪ፣ አይፓድ፣ የአማዞን ኪንድል እና ፕለይስቴሽኖችን ያመርታል።
ኩባንያው በቅድሚያ የሚያመርታቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ምርቶች ለሠራተኞቹ እንደሚያድል ከዚያ በኋላ ምርቶቹን ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
| UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
4536cf379e0915b2d4495d3ea9c493f0 | 3d6165bd9a3dfbab25c33de4c8dec1f1 | በዘንድሮ ዓመት አገሪቱ ካለፈው አመት ጋር ተመሳሳይ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዝግባለች- ብሔራዊ ባንክ | በተያዘው ዓመት አገሪቱ ካለፈው የበጀት ዓመት ከተመዘገበው የ7ነጥብ7 በመቶ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተቀራራቢነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ታስመዘግባለች ተብሎ እንደሚጠበቅ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ ከ1996 – 2007 ዓ.ም ባሉት ዓመታት በአማካይ 10 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቧን ያስታወሱት ዶክተር ይናገር ከ2008 ዓም አንስቶ እድገቱ መቀዛቀዙን አስረድተዋል፡፡ለዚህ ደግሞ የወጪ ንግድ መቀነስ፤ በሃገሪቱ የነበረው የፖለቲካ ሁኔታ፤ የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት፤ የዓለም ኢኮኖሚ በተለይም የቻይና መቀዛቀዝ በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ ገልጸዋል፡፡በተለይ የወጪ ንግዱ መቀዛቀዝ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲከሰት በማድረጉ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል፡፡የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ የወጭ ንግዱን ማሳደግና ኮንትሮባንድን መቆጣጠር እንደሚገባ ዶክተር ይናገር ገልጸዋል፡፡የኮንትሮባንድ ንግዱን ለመቆጣጠር የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይገባልም ብለዋል፡፡የውጭ ብድርን በተመለከተ ሃገሪቱ 26 ቢሊዬን ዶላር እዳ እንዳለባት ዶክተር ይናገር ጠቁመው ከዚህም ውስጥ 85 በመቶ የሚሆነው የቻይና እንደሆነ ተናግረዋል፡፡23 ሚሊዮን ሰዎች ከድህነት ወለል በታች ሲሆኑ 8 ሚሊዮኑ ደግሞ ከመንግስት የምግብ ድጋፍ የሚጠብቁ መሆናቸውን የብሄራዊ ባንክ ገዢ ተናግረዋል፡፡ | ቢዝነስ | https://waltainfo.com/am/23724/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
674569196d8be6f73eb4d2edecefe6c9 | 78387e74002fab6840d3331083544a5a | የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ – ሜክሲኮ ድንበር ግንብ መገንባት ጀመሩ | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች አሜሪካ እና ሜክሲኮን ድንበር የሚለያየውን ግንብ ባገኙት የገንዘብ ድጋፍ መገንባት መጀመራቸውን አስታውቀዋል።የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋም የቀድሞ አባል ብሬን ኮልፋጅ በኒው ሜክሲኮ ግዛት የተጀመረውን ግንባታ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ያጋሩ ሲሆን፣ የግንባታውን መሠረት የያዙት ብረቶች የቆሙት በእርዳታ በተገኘ 22 ሚሊየን ዶላር እንደሆነና ገንዘቡን በበይነመረብ አማካኝነት ባካሄዱት ዘመቻ እንደሰበሰቡት ተናግረዋል።ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግንቡን ለመገንባት ያቀረቡትን ሃሳብ ምክር ቤቱ ውድቅ ካደረገባቸው በኋላ ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራውን እንደጀመሩ ገልፀዋል።ባለፈው እሁድ የቀድሞው የአየር ኃይል አባል ኮልፋግ አዲስ እየተገነባ ያለውን ግንብ ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶግራፍ በትዊተር ገፃቸው ላይ ለቀውታል ነው የተባለው።"ታሪክ ሰርተናል! በመጀመሪያው የተሰበሰበው ገንዘብ ዓለም አቀፉን ድንበር ለመገንባት ውሏል" ሲሉ ኮልፋግ በትዊተር ገፃቸው ላይ ደስታቸውን ገልፀዋል።ግንቡ የሚሰራው 'ዊ ቢዩልድ ዘ ዎል ኢንክ' በተሰኘ ለትርፍ ባልተቋቋመው ድርጅታቸው ሲሆን ድርጅቱ የተመሰረተው ከገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻው በኋላ ነው።የቀድሞ የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን ስቴቭ ባነን የዚህ ድርጅት አማካሪ ቦርድ ኃላፊ ናቸውም ተብሏል።የቦርዱ ኃላፊ ባነን ለሲ ኤን ኤን እንደተናገሩት አዲስ እየተገነባ ያለው 21 ማይል ርዝመት ካላቸው ሁለት ግንቦች ጋር የሚያያዝ ነው ብለዋል።የቀድሞ ካንሳስ ሃገረ ገዢ የነበሩትና በአሁኑ ሰዓት የድርጅቱ አማካሪ ክሪስ ኮባች በበኩላቸው ግንባታው 8 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ እንደሚፈጅ ገልፀዋል።ግንባታውን እያካሄዱ ያሉት ቡድኖች በሰሜን ዳኮታ ግዛት የዓሳ አምራቾች ተቀጥረው የሚሰሩ ተቋራጮች ሲሆኑ ፕሬዚደንት ትራምፕ ግንባታውን እንዲያካሂዱ አሳስበዋቸው ነበር።ከትራምፕ ደጋፊዎች አንዱ የሆነው የ56 ዓመቱ ጄፍ አለን ግንቡ የተገነባው በሰን ላንድ ፓርክ በኒው ሜክሲኮ ግዛት ሲሆን ከሜክሲኮ ሲዩዳድ ጁዋሬዝ በተቃራኒው አቅጣጫ የሚገኝ ነው።ጄፍ አለን እንዳለው ግማሽ ማይል የሚሆነው የግንቡ ክፍል በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይጠናቀቃል ተብሏል።"ግንቡን ራሳችን እንገነባዋለን፤ ይህ አውሮፓ አይደለም፤ ይህ አሜሪካ ነው፤ ድንበራችችንን ራሳችን እንጠብቃለን" ሲልም ለኤ ኤፍ ፒ ተናግሯል።ይሁን እንጂ ይህንን የሚያደርጉት ስደተኞችን በመጥላት እንዳልሆነ በመናገር ሚስቱ ሜክሲኳዊት ስትሆን ሴት ልጁም የተወለደችው ሲዩዳድ ጁዋሬዝ ውስጥ መሆኑን ጠቅሷል።ውሳኔው ላይ የደረሰው ዘረኛ ስለሆነ ሳይሆን ራሱንና አሜሪካን ለመጠበቅ ደህንነቱ የተረጋገጠ ድንበር እንዲኖራት ስለሚፈልግ እንደሆነም አክሏል።"ሰዎች አገራቸውን ትተው ለመሰደድ ካሰቡም በቀጥታ በመሄድ ማመልከት ይችላሉ" ብሏል ጄፍ አለን።በመጨረሻም ግንባታውን እያካሄደ ያለው ድርጅት "ይህ ጅምር ነው፤ በአሜሪካ ደቡባዊ ክፍል ያለውን ድንበር መጠበቅ ዓላማችን ነው"ሲል አስታውቋል።ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ግንቡን ለመስራት ያቀረበውን የገንዘብ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | ፖለቲካ | https://waltainfo.com/am/33940/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
40f7c404c3925890db033fd5b07d80a6 | 282e54e8400f259eaef39b0edfcd8196 | በደቡብ ክልል፤ ከፋ ዞን፤ ቦንጋ ከተማ ሠርግ አስደግሶ "የሙሽራዬ ቤት ጠፋኝ" ያለው ግለሰብ ከእስር መለቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክፍሌ ተካ ለቢቢሲ ገለፁ።
ነገሩ እንዲህ ነው. . . | ከፋ ዞን፡ በቦንጋ ሠርግ አስደግሶ "የሙሽራዬ ቤት ጠፋኝ" ያለው ግለሰብ የእስር ጊዜውን አጠናቀቀ\nግለሰቡ በቦንጋ ከተማ ቤት ተከራይቶ ይኖር ነበር። ዕድሜው አሁን ወደ 30 ይጠጋል። የኑሮ ሁኔታውም ዝቅተኛ ደረጃ የሚባል ዓይነት ነው ይላሉ የሚያውቁት።
ታዲያ አንድ ቀን ለሠፈሩ ሰዎች "ላገባ ነው" ሲል ያበስራቸዋል። መቼም አንድ ሰው በሕይወቱ ወደ መልካም ምዕራፍ ሲሸጋገር ደስ ያሰኛልና እነርሱም ደስታቸውን ይገልፃሉ። "አበጀህ የእኛ ልጅ" ይሉታል።
• 'ወንድ ያገቡት' ኡጋንዳዊ ኢማም ከኃላፊነታቸው ታገዱ
• የቴክሳስ ፖሊስ ልማደኛዋን ድንኳን ሰባሪ እየፈለገ ነው
ሁሉም ባቅሙ እያዋጣ እርሱም ካመጣው ጋር እየተጨማመረ ድግሱ በትብብር ተዘጋጀ።
የሠርጉ ቀን ሲደርስም ሸራ ተወጥሮ፣ ወንበር ተሰባስቦ ለእንግዶች ተሰናዳ። ዳሱም በአበባ እና በዘንባባ ተጌጠ። ጎረቤቱም እንደ ባህሉ ተሰባስቦ በአቅማቸው ድግሱን ሲያስተናብሩ ዋሉ።
ሁሉም ተሰናድቶ ካለቀ በኋላ ሙሽራው ከአጃቢዎቹ ጋር [6 ወንድ እና ሁለት ሴት] እየጨፈሩ፣ እየዘፈኑ ሙሽሪትን ለማምጣት ዴቻ ወረዳ፤ ሻፓ ወደ የሚባል ቀበሌ አመሩ።
ሻፓ በእግር ቢያንስ 1 ሰዓት ይወስዳል። ሚዜዎቹና አጃቢዎቹ "ደስታህ ደስታችን ነው" ብለው ይህንን ሁሉ ርቀት ተጉዘው ሥፍራው ደረሱ።
ይሁን እንጂ ሙሽራው አንዳች ነገር እንደጠፋው ሁሉ መንደሩን መዟዟር ጀመረ። በድካም የዛሉት ሚዜዎቹ "ቤቱ አንደርስም ወይ? ሙሽራዋ የታለች?" ብለው መጠየቃቸው አልቀረም። ግን መዳረሻው አልታወቅ አለ። በአካባቢው የሚታይም ሆነ የሚሰማ የሠርግ ሁናቴ የለም።
ግራ የተጋቡት አጃቢዎች "የታለች?" ሲሉ ሙሽራውን ወጥረው ይይዙታል።
"ልጅቷ ያለችበት ቤት ጠፋብኝ " ይላቸዋል። 'ሙሽራዋ ጠፋች'።
በነገሩ ግራ የተጋቡት አጃቢዎቹ የሚያደርጉት መላ ቅጡ ጠፋቸው። ዳስ ውስጥ ሆነው እየዘፈኑ ሙሽራዋን የሚጠባበቁት ሠርገኞች ፊት እንዴት ባዶ እጃቸውን እንደሚገቡ ጭንቅ ያዛቸው።
በዚህ መሃል አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላቸው። ከአጃቢዎቹ አንዱን ጫማው እንዲያወልቅ አድርገው በነጠላ በመሸፋፈን ሙሽራ አስመስለው እየዘፈኑ፣ እየጨፈሩ ይዘው መግባት። በሃሳቡ ተስማሙ፤ እንዳሰቡት አደረጉ።
ቤቱ እንደደረሱም "በእግሯ ረዥም ሰዓት ስለተጓዘች በጣም ደክሟታል።" ብለው ወደ ጫጉላው ቤት አዝለው ያስገቧታል። የሆነውን ማንም የገመተ የለም።
ትንሽ ቆይቶ "ሙሽራዋ ትውጣና ራት ይበላ" ሲሉ ደጋሽ ጎረቤቶች ይጠይቃሉ። ምላሹ አሁንም "ደክሟታል" የሚል ነበር።
አቶ ሙሉጌታ ገ/ሚካኤል ሠርግ ተጠርተው ከተገኙት ጎረቤቶች መካከል አንዱ ነበሩ።
"ከሌላ ቦታ መጥቶ እኛ ሠፈር ቤት ተከራይቶ ይኖር ነበር። 'ላገባ ነው' ብሎ የተወሰኑ ጎረቤቶቹን ሠርግ ጠራ። እኔም ተጠርቼ ስለነበር ሠርጉ ላይ ተገኘሁ። ሙሽራዋን እንቀባለለን ብለን ሽር ጉድ ስንል ዋልን። በ'ጂ ፓስ' የሠርግ ሙዚቃ ተከፍቶ እየተጠባበቅን ነበር።
በኋላ ላይ አምሽተው መጡ። ነገር ግን ብንጠብቅ ብንጠብቅ ሙሽራዋ አትመጣም። ወሬ አይቀርምና ሴት አስመስለው ይዘው የገቡት ወንድ ነው ተባለ። እንግዶችም ድግሱን ሳይቀምሱ ወዲያው ነበር በብስጭትና በእፍረት የተበታተኑት" ሲሉ አጋጣሚውን ያስታውሱታል።
ሚስጢሩ ከጫጉላ ቤቱ ወጥቶ ወደ ዳሱ ሲዛመት ግን አፍታም አልቆየ። "ሴት አይደለም ወንድ ነው" የሚል። 'ጉድ' ተባለ። የሆነውን ባለማመን እያጉመተመቱ ወደየመጡበት የሄዱ እንዳሉ ሁሉ ጉዳዩን ለሕግ አካል ለማሳወቅም ያሰቡ አልጠፉም።
ለፖሊስ ጥቆማ ተሰጠ። ፖሊስም በሥፍራው ተገኝቶ 'ሙሽራውን' በቁጥጥር ሥር አዋለ።
" እኔ እንዲህ ዓይነት ነገር ሰምቼም አላውቅም።" የሚሉት አቶ ሙሉጌታ፤ በአካባቢው ባህል መሠረት በሠርግ ወቅት ገንዘብ ስለሚሰጥ ግለሰቡ ይህን ያደረገው ገንዘብ ለማግኘት መሆኑን የተረዳነው በኋላ ነው ይላሉ።
ቆይተው... | UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
f1a6b31bea5ada9d52d3cf135c5ccc34 | 2f055e82b5e4485b0a7c6697c31cb997 | “ጠላት” የነበሩ ሴቶች ዳግም ዕውቅና ማግኘት የሴቶቹ ሹመት ሕዝባዊ ፋይዳ | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመጡ ወዲህ በታየው የለውጥ ሒደት ውስጥ በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ ሴቶችን የማስቀመጥ ጅምሩ ጉልሕ ድርሻ ካላቸው ለውጦች አንዱ ነው። ይህንን በማስመልከት ቤተልሔም ነጋሽ ፋይዳውን ይነግሩናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዛሬ ሰባት ወራት ገደማ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፣ ያንን ተከትሎ የመጀመሪያውን አነቃቂና ተስፋ ሰጪ የተባለ ንግግራቸውን ፓርላማው ፊት ሲያደርጉ፣ በሴቶች መብቶች ዙሪያ ያገባናል ለምንል ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ታይቶን ነበር። ይኸውም መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያ ሴቶች ትንሽም ቢሆን የተሻለ ይሆናል የሚል ነበር። እንደ እኔ ቢያንስ ያለፉትን ዐሥርት ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶችን ጉዳይ ጉዳዬ ብሎ የተከታተለ ሰው እንደሚረዳው፣ ቢያንስ በመንግሥት ደረጃ ገዢው ኢሕአዴግ ‹የሴቶች ጥያቄ ተመልሷል› ብሎ ያምን ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን ሽረው ከከፈሉት መስዋዕትነትና በአገሪቱ እያደረጉት ካሉት ከፍተኛ አስተዋፅዖበተቃራኒ የኢትዮጵያ ሴቶች ዕውቅና ተነፍገው መክረማቸውን ጠቀሱ።በግላቸው የባለቤታቸውንና የወላጅ እናታቸውን አስተዋጽኦ ተናግረው በይፋ አመሰገኑ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደሥልጣን ከመጡ በኋላ ቃል የገቡትን የለውጥ እርምጃ ተከትሎ በተለያዩ አካላት “ይህን ቢያደርጉ” ተብለው ከሚሰነዘሩ የፖሊሲና ተያያዥ ለውጥ ሐሳቦች መካከል የሴቶችን ጉዳይ የሚመለከቱ ሐሳቦችም ነበሩበት። በሴቶች መብት ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚሠሩ ተቋማት በጋራ ለጽ/ቤቱ ካስገቡት ይፋዊ ደብዳቤ ሌላ በግለሰብም ደረጃ የሚሰነዘሩ፣ ይህ ቢደረግ በሴቶች ሕይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ይመጣል የሚባሉ አስተያየትና ጥቆማዎችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ስንሰማ ነበር።
የሴቶች እኩልነት ላይ በሚሠሩ ተቋማትና በግላቸውም አቀንቃኝ በሆኑት ሰዊት ኃይለስላሴ እና ቢልለኔ ሥዩም (በአሁኑ ሰዓት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሪታሪ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት) የጻፉትና በተለያዩ ድረ-ገጾች ያጋሩት “ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ” የሚለው የጥያቄዎች ስብስብ ምናልባትም በዚህ ዘርፍ ከቀረቡት ሐሳቦች መካከል በድረ ገፆች በመታተምና በተለይ አንደኛዋ ጸሐፊ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ በመዘዋወር ተጠቃሽ ነው። በደብዳቤው ላይ በግልጽ ከተቀመጡት ጥያቄዎች መካከል በካቢኔ የሴቶች ቁጥር ጨምሮ ሃምሳ-ሃምሳ የፆታ ተዋፅዖ እንዲኖር በተጨማሪም የወንዶች ግዛት ተደርገው ሚወሰዱት እንደ ንግድ፣ መከላከያ፣ ፋይናንስ እና ኢንዱስትሪ በሴቶች ቢያዙ የሚል ነበር።
ጥቅምት 6፣ 2011 ጠቅላይ ሚኒስትሩ 20 አባላት ያሉት አዲሱን ካቢኔያቸውን ሲያስተዋውቁ የሆነው ግን ከተስፋውና ከጥያቄው ጋር ቢሔድም በፍፁም ያልተጠበቀ ነበር። በመጨረሻ የኢትዮጵያ ሴቶች ጊዜ መጣ እስኪባል ደስታ ሆኖ ነበር።
በሳምንቱ የቀድሞዋ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣ ቀጥላ ታዋቂዋ የሴቶች መብት ተሟጋችና ሴቶች ላይ አድልዎ ያደረጉ በርካታ ሕጎች እንዲቀየሩ ምክንት የሆነው የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መሥራች መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆና ስትሾም እንደ ካቢኔው የፆታ ተዋፅዖ መመጣጠን ዜና ሁሉ አገራችን በዓለም በአዎንታዊ መልኩ ሥሟ ተነሳ።
ለዘመናት ትርጉም ያለው የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ መብት እንዲረጋገጥ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ፣ የሴቶች ውክልና ሊረጋገጥ ይገባል ብለው ባገኙት መድረክ ሲሟገቱ የከረሙ ጥረታቸው ፍሬ አፈራ።
ለእኔ በተለይ በሴቶች መብቶች ዙሪያ ድምፃችንን ለምናሰማና በዚህ ጥላሥር ለተሰባሰብን ድሉን የበለጠ ጣፋጭ የሚያደርገው የሴቶችን መብቶች ጥየቃ መንግሥትን አላግባብ ተዳፈራችሁ ተብለው ድርጅታቸው የተዘጋው እነ መዓዛ አሸናፊ ይገባችኋል ተብለው ለቁልፍ ሥራ መታጨታቸው ነው። አሸባሪ ተብለው በእስር ቤት መከራ ከማየት እስከመሰደድ የደረሱት እነ ብርቱካን ሚደቅሳ መብታቸውን የነሳቸው ተቋም ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ነው። በብዙ የሴቶች መብት መሸራረፍ ዘልማድ ሆኖ እንዲቀጥል ፈላጊዎች እንደ ፅንፈኛ የሚታየውን ፌሚኒዝም በይፋ የሚያቀነቅኑ ሌሎች እንደ ፕሬስ ሴክሪታሪዋ ያሉ ፖለቲከኛ ያልሆኑ ዋነኛ የሴት መብት ተሟጋቾች በመንግሥት ከፍተኛ ቦታዎች መግባታቸው ነው።
ያሁኑን ውጤት ጣፋጭ የሚያደርገው በመንግሥት ሳይቀር የነበረውን አሠራር በመገዳደራቸው ድርጅቶቻቸው እስኪዘጉ ‹ጠላት› ተደርገው የተቆጠሩ ዕውቅና ሲሰጣቸው ብቻ ሳይሆን ‹ታውቃላችሁ፣ ትችላላችሁ፣ ኑ ምሩ!› ሲባሉ ማየቱ ነው። ለዚህም ነው ይህ እውን እንዲሆን በአገራችን የመጀመሪያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቡድን (ሴቶች) የከፍተኛውን ሥልጣን ግማሹን እንዲይዙ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ብቻ ሳይሆን እንደ መዓዛ ያሉ ከእሷ ጋር የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርን የመሠረቱ፣ ያለምንም ማወላወል የተጋፈጡ ለቆሙለት ዓላማ “ትዳር አፋቺ” እና ሌላ ሥያሜ ተለጥፎባቸው ቢጠሉም ወደኋላ ያላሉ፣ በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሴቶች መከታ የሆኑ በፍርድ ቤት በነፃ እየቆሙ አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሔዱ ያደረጉ ዛሬ ለመጣው ለውጥ ለከፈሉት ዋጋ የምናመሰግናቸው።የሹመቱ ፋይዳ
የሴቶች ወደ ሥልጣን መውጣት ለምን ያስፈልጋል የሚለውን ተመልክቼ ጽሁፌን ልቋጭ። ግሎሪያ ስቴነም ባለፈው ሰሞን የአሜሪካ ‹የሚድ ተርም› ምርጫን አስመልክቶ በርካታ ሴቶች በእጩነት ስለመቅረባቸው ስትጠየቅ ለሲኤንኤንዋ ክርስቲያን አማንፑር እንደተናገረችው ‹የመጀመሪያው በዲሞክራሲ መርሖ መሠረት ሥልጣን ላይ የሚወጡት ሰዎች በፆታም፣ በዘርም፣ በሃይማኖትም በአመለካከትም አጠቃላዩን ሕዝብ የሚመስሉ መሆን አለባቸው› ብላለች።
በስፋት ተቀባይነት ካገኙ የዲሞክራሲ ፅንሰ ሐሳቦች መካከል አንዱ የፖለቲካ እኩልነት ሲሆን ሁሉም ዜጎች እኩል የፖለቲካ ተሳትፎ መብት አላቸው የሚለው ሐሳብ የዲሞክራሲ ዋና መሠረት ነው። ይህ የዜጎች እኩል ተሳትፎ መረጋገጥ የሚለው ብቻ በቂ ላለመሆኑ ግን ከጥቂቶች በስተቀር በብዙ የዓለም አገራት የሴቶች ውክልና አናሳ መሆን ምስክር ነው። ለዚህም ነው የአውሮፓ አገራትን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ባሉ ፓርላማዎች ጥናት ያደረጉ ምሁራን ከእኩል ውክልና (Equal representation) ይልቅ ገላጭ ውክልና(Descriptive Representation)ተገቢ የዲሞክራሲ ማረጋገጫ መንገድ መሆን አለበት ሲሉ የሚከራከሩት።ገላጭ ውክልና ማለት በፓርላማና በሌላውም የፖለቲካ ሥልጣን ላይ የሚሆነው አካል የሕዝቡን ብዝኃነት ያካተተ ሲሆን ማለት ነው።
ሕዝቡ በትክክል ተወከልኩ የሚለው እያንዳንዱ እሱን የሚመስል ሰው በፓርላማም በቀበሌም በሚኒስትር ደረጃም ሥልጣን ይዞ ማየት ሲችል፣ ድምፁ በሚመስሉትና ኑሮን እሱ በሚያየውና በሚያልፍበት መንገድ ያለፉ ሰዎችን ማየት ሲችል ነው። ይህ በምላሹ ፖለቲካ የተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት ወይም ርስት ሳይሆን ብቃትና ዕውቀት ያላቸው ሰዎች በፍላጎት ተነሳስተው የሚገቡበት እንዲሆን ያበረታታል።፡
ከሁሉም በላይ የሴቶች ወደከፍተኛው የሥልጣን እርከን መምጣት ዋጋ የሚኖረው ደግሞ በተለይ ለሴት ሕፃናት ነው። እነሱን የሚመስሉ ሴቶችን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲመለከቱ ወደፊት በፖለቲካ ለመሳተፍ፣ እነኛን ቦታዎች ለመያዝ የማለም ዕድል ይኖራቸዋል።
ከዚህ ሌላ ሴቶች ለፓርላማውም ይሁን ከታች ጀምሮ እስከላይኛው የሥልጣን እርከን ሲመጡ ይዘው የሚመጡት የተለየ እይታ አለ። ሴቶች ከዕለት ተዕለት ኑሮ ፣ ወደ ፖለቲካ ከመግባት አንስቶ ሥልጣን ላይ እስከመውጣት ባለው ሂደት የሚያልፏቸው ተግዳሮቶች ከወንዶች የተለዩ ናቸው። ይህን ነገሮችን በተለየ መነፅር የመመልከት ይህንና የተለየ የህይወት ልምዳቸውን ለአመራር ዘይቤያቸው ሲጠቀሙ አመራሩና ሂደቱ የተሟላ እይታና ልምድ የሚጠቀም እንዲሆን ይረዳል።
በተጨማሪም ፖለቲከኞች የወከሉትን ብቻ ሳይሆን የወጡበትን ማኅበረሰብ ችግር የመፍታት አዝማሚያ አላቸው። ሴት ባለሥልጣናት ሲበዙ ፖሊሲዎች ሲወጡ የሴቶች ድምፅ እንዲካተት ያደርጋሉ የሚል ነው እሳቤው።
ደግሞም የፕሬዚዳንትነትም ሆነ የግማሽ ካቢኔው እንዲሁም አሁንም በሌሎች ቦታዎች እስከ ቀበሌ ድረስ ይቀጥላል ብለን በምናምነው ሹመት የሚካተቱ ሴቶች በችሮታ የተሰጣቸው ሳይሆን በመብታቸውም፣ በትግላቸው ያገኙትም ጭምር ነው።
በመጨረሻም“አሁንማ መከላከያ ሚኒስቴር ሆናችሁ፤ ከዚህ በላይ ምን ትፈልጋላችሁ?” የሚል አስተያየት ለሚሰነዝሩ የሚከተለውን መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ። ሕገ መንግሥቱን ጨምሮ ለሴቶች መብቶችን የሚያጎናፅፉ መልካም የሕግ ማዕቀፎች ቢኖሩም፣ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት እየጨመረ መጥቷል። ታዳጊ ሕፃናትና ወጣት ሴቶች ሊጠብቋቸው፣ ከለላ ሊያደርጉላቸው በሚገባ የቅርብ በሚሏቸው ሰዎች ሳይቀር ይደፈራሉ። ትምህርት ቤቶች ለሴቶች አመቺ አይደሉም። ሴቶች ዕለት ተዕለት ኑሯቸውአሁንም በሥጋት የተሞላ ነው። ለብዙ ሴቶች በሠላም ወጥቶ መግባት አሁንም ምኞት ነው። በሥራ ቦታዎች ሴቶች አሁንም ሴት በመሆናቸው ብቻ አድልዎና በደል ይፈፀምባቸዋል። ዛሬም “ፈልጌሻለሁ” ያለ ወንድ እንቢ በማለታቸው አሲድ የሚደፋባቸው ሴቶች አሉ። የድህነት ከባድ ጫና ዋነኛ ተሸካሚ ሴቶች ናቸው።
ተስፋችን ይህ ይቀየራል የሚል ነው። የሴቶች ቁጥር በዛ ብሎ በውሳኔ ሰጪነት ላይ መሳተፍ ትርጉም ኖሮት፣ በየዘርፉ ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ አይቶ ሆን ብሎ ያንን ለመቀየር የሚሠራ መንግሥት እንዲኖረን ያደርጋል የሚል ነው።ቤተልሔም ነጋሽ የፖለቲካ ተግባቦት ባለሙያ ናቸው። በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ሊገኙ ይችላሉ። | ፖለቲካ | https://addismaleda.com/archives/2043 | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
5c975fe8ddd874f5595e76d4edcaa501 | a10f8d4b2d57cb29119f43024c86731d | እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ላይ ነጻ ሆነን የመታየት መብታችንን የሚቃረን አስተያየት በመስጠታቸው ፍርድ ቤቱ እንዲጠይቅላቸው አቤቱታ አቀረቡ። | ጃዋር መሐመድ፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተጠየቀ\nአቶ በቀለ ገርባና ጀዋር መሐመድ የጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት በመገኘት ለጋዜጠኞች የሰጡት መግለጫ ነጻ ሆኖ የመታየት መብታቸውን የሚጻረር መሆኑን እና ለህይወታቸው አስጊ እንደሆነ ዛሬ ለተሰየመው ፍርድ ቤቱ ገልፀዋል።
"እኛ ላይ ምስክሮች እንኳ ሳይሰሙ፣ የፖለቲካ ባለስልጣናት፣ በተለይም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ፍርድ ቤቱ እኛ ላይ ውሳኔ እንዳስተላለፈ አድርገው ነበር የተናገሩት" ያሉት አቶ ጃዋር መሐመድ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መግለጫ ለህይወታቸው አስጊ መሆኑን ተናግረዋል።
"ጽንፈኞች ተብለናል፤ እንዲሁም ግርግር እንደፈጠርን እና ሰው እንደገደልን ወስነዋል" በማለት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲጠየቁ አቤቱታቸውን አሰምተዋል።
አቶ በቀለ ገርባም " ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ እኛ መከላከል በማንችልበት ሁኔታ ለውጪ አገር ሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል። ይህም የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገለልተኛ መሆን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው" በማለት ዶ/ር ጌዲዮን ፍርድ ቤት ቀርበው መጠየቅ አለባቸው ሲሉ ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም በበኩሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚቀጥለው ቀጠሮ ላይ በጽሑፍ ምላሽ እንዲሰጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
የዛሬ ችሎት ውሎ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በ24 ሰዎች ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የከፈተውን ክስ ለተከሳሾች አንብቧል።
ፍርድ ቤቱም ከተራ ቁጥር 1 እስከ 15 ድረስ ያሉ ተከሳሾችን ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ ሁከት በመፍጠር በአዲስ አበባ ከተማ የ13፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ 167 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ 360 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እና 4.6 ቢሊዮን ብር በላይ የተገመተ ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን አንብቧል።
ከዚህም ውጪ ያለፈቃድ የጦር መሳሪያዎችን ይዘው በመገኘትና የቴሌኮም ማጭበርበርን መፈፀም የሚሉ ጉዳዮች ክሱ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮች ናቸው።
18ኛ ፣ 21ኛ፣ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ፣20፣7ኛ ተከሳሾች አማርኛ የማይሰሙ መሆናቸው ተገልጾ እነርሱ ላይ የቀረበውን ክስ አለመረዳታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።
ጠበቆቻቸው ደግሞ በደንበኞቻቸው ላይ የተከፈተውን ክስ ማረሚያ ቤት በመገኘት ማሳወቅ እንደሚችሉ ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል።
ፍርድ ቤቱም የተከሳሽ ጠበቆችን ሁሉንም በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ አግኝተዋቸው እንዲወያዩ ማረሚያ ቤት ሁኔታውን እንዲያመቻች ትዕዛዝ ሰትቷል።
አቤቱታና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ
በዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው እንዲሁም ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤት በማቅረብ ፍርድ ቤቱም ትዕዛዝ ሰጥቶባቸዋል።
ተከሳሾች እጃቸው በካቴና ታስሮ ረዥም ሰዓት መቆየታቸውንና እንዲፈታ ጠይቀው እምቢ መባላቸውን፤ እንዲሁም ጠዋት ቁርስ ሳይበሉ ወደ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን በመግለጽ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ለምን በካቴና እንደታሰሩ ማረሚያ ቤቱ በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ተከሳሾች ማለዳ ወደ ፍርድ ቤት ሲወሰዱ እስር ቤቱ ቁርስ እንዲያቀርበላቸው ፍርድ ቤቱ አዟል።
የተከሳሽ ጠበቆች ሸምሰዲን ጠሃ የኢሬቻ በዓል ላይ እንዲገኝ ያቀረበውን ጥያቄ ትዕዛዝ ይሰጥልን በማለት ጠይቀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሾች የባህል ልብስ እንዲገባላቸውና የኢሬቻን በዓል እስር ቤት በጋራ እንድናከብር ይፈቀድልን ሲሉ ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም ሸምሰዲን ጠሃ ኢሬቻ ላይ ተገኝቶ በዓሉን እንዲያከብር ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተከሳሾች ግን የባህል ልብስ ገብቶላቸው ከዚህ በፊት የተለያዩ የእምነት በዓላት ሲከበሩ እንደቆየው እንዲያከብሩ ሁኔታዎች እንዲመቻችላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በተጨማሪም ባህር ማዶ ቤተሰብ... | UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
761e877e874553633a7d31ad21c9c034 | 2b464374c357fa2e0311f20fa9c79baf | ባለፉት 24 ሰዓታት 890 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 3 ሰዎች ህይወት አልፏል | አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 916 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 890 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 76 ሺህ 988 ደርሷል።በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 3 ሰዎች ህይወት አልፏል።በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 208 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።በ24 ሰዓታት ውስጥ 247 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 31 ሺህ 677 ደርሷል።እንዲሁም 296 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል። | ሀገር አቀፍ ዜና | https://www.fanabc.com/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-24-%e1%88%b0%e1%8b%93%e1%89%b3%e1%89%b5-890-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%88%b2/ | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
054cd0177bc68a0ba1981ca6e5b15a83 | 3899ca19ab42c77d93f35d142ca79538 | የኦሎምፒክ ችቦ ዘንድሮ ውድድሮቹን ወደ ምታስተናግደው ወደ ሪዮ ዲ ጃኔሮ የብራዚል ከተማ ጉዞ ጀምሯል | የኦሎምፒክ ችቦ ዘንድሮ ውድድሮቹን ወደ ምታስተናግደው ወደ ሪዮ ዲ ጃኔሮ (Rio De Janero) የብራዚል ከተማ ጉዞ ጀምሯል። ችብው ትናንት አጠር ያላ የማብራት ሥነ ሥርዓት ተደርጎለት ጉዞውን የጀመረው የኦሎምፒክ ውድድሮች ከተጀመሩባት ከግሪክ ከተማ ከኦሎምፒያ (Olympia) ነው። ችቦውን በርካታ የግሪክ ከተሞችን ለስድስት ቀናት አቋርጦ በሚያልፍበት ወቅት አንድ የዚያችን ሃገር ጥገኝነት የጠየቀውን ሦሪያዊ ስደተኛ ጨምሮ፥ 450 ሰዎች ይቀባበሉታል። በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ አስተናጋጇ ብራዚል ከገባ በሁዋላም፥ በ 83 ትላልቅና በ 500 አነስተኛ ከተሞቿ ሲያልፍ 12 ሺህ ሰዎች ይቀባበሉታል። የመጨረሻው ሰው በኦሎምፒክ መክፈቻው እለት በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ ችቦውን ማራካና (Maracana) ስታዲየም በተዘጋጀለት ልዩ ሥፍራ ላይ ያኖራል።በነገራችን ላይ ኦሊምፒክ በአንድ የላቲን አሜሪካ ሃገር ውስጥ ሲዘጋጅ የ 2016ቱ በታሪክ የመጀመሪያው ነው። | ዓለም አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/the-olympic-in-rio-de-janero-started-on-thursday-in-olympia/3298531.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
043833e6a0b94cb363dde1e9324b20ed | b09ccd2c0b349000c1bd2dd386c29ba5 | ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የግልግል ዳኝነቶችን በግዛቷ ከማስፈጸም ምን ታተርፋለች? | በውጭ ሀገራት የሚሰጡ የግልግል ዳኝነቶችን ዕውቅና መስጠት እና ማስፈጸምን በተመለከተ የተደረሰው ስምምነት ይፋ ከተደረገ 60 ዓመታት አልፈዋል።በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የራሷን አሰራር ከመዘርጋት ውጪ የስምምነቱ ፈራሚ ሆና አልታየችም ነበር።አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ በውጭ ሀገራት የተሰጡ የግልግል ዳኝነቶችን በሀገር ውስጥ ያለ ተጨማሪ ስነ-ስርዓት እና ቅድመ -ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችላትን ሰነድ ለማጽደቅ እየተዘጋጀች ስለመሆኑ ተሰምቷል። የተሰኘው ይሄንን ሰነድ ለመቀበል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወሰነ ሲሆን ፣ገዥነቱን ለማጽደቅ ደግሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጠሮ እንደያዘለት ተሰምቷል።ለመሆኑ የሰነዱ ዓላማ ምንድነው? ኢትዮጵያ ሰነዱን በመፈረሟ የምትጠቀማቸው እና የምትጎዳባቸው ጎኖች አሉ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስቶ ሀብታሙ ስዩም ከባህርዳር ዩኒቨርሰቲው የግብር እና ኢንቨስትመንት ህግ መምህር ምስጋናው ጋሻው ጋር አጨር ቆይታ አድርጓል። አቶ ምስጋናው የሰነዱን ምንነት እና ይዘት በማስረዳት ይጀምራሉ።
| ሀገር አቀፍ ዜና | https://amharic.voanews.com//a/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%A0%E1%89%80%E1%8D%8D-%E1%8B%A8%E1%8C%8D%E1%88%8D%E1%8C%8D%E1%88%8D-%E1%8B%B3%E1%8A%9D%E1%8A%90%E1%89%B6%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%8C%8D%E1%8B%9B%E1%89%B7-%E1%88%88%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%8C%B8%E1%88%9D-%E1%8A%A5%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%8A%93%E1%8B%B3%E1%89%BD-%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%8A%A8%E1%8B%9A%E1%88%85-%E1%8A%A5%E1%88%AD%E1%88%9D%E1%8C%83-%E1%88%9D%E1%8A%95-%E1%89%B5%E1%8C%A0%E1%89%80%E1%88%9B%E1%88%88%E1%89%BD-/5217061.html | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification |
330bf35c55443c58f49c5604c9d28fb5 | 1db0f3f26cdbc17b162d23030687f2ea | በቅማንት አካባቢ ግጭቱ እንደገና ያገረሸው ባለፈው ዓመት ጳጉሜ 3/2011 ዓ.ም እንደሆነ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑት መምህር መካሻው ለቢቢሲ ተናግረዋል። | "ታጣቂዎች ሰላማዊ ዜጎች መኪና አስቁመው ተገድለዋል" አቶ አገኘሁ - "ሰላማዊ ሰዎች በአማራ ልዩ ኃይል ጥቃት ደርሶባቸዋል" የአካባቢው ነዋሪ\nየነዋሪውን ሀሳብ የሚያጠናክሩት የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ይከበርልኝ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ከፍአለ ማሞ በበኩላቸው ከጳጉሜ 3 ጀምሮ በአካባቢው ጦር መዝመቱን የይናገራሉ።
የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው የክልሉ ልዩ ኃይል ሕግ ለማስከበር ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ከጳጉሜ 3 ጀምሮ የክልሉ የፀጥታ ኃይል ወደ አካባቢው አንቀሳቅሶ ወደ ቀበሌዎች በመግባት፣ ሰላማዊ መንደርን ከብቦ ጥቃት ማድረሱን የተናገሩት መምህር መካሻው የፀጥታ ኃይሉ ለተኩሱ ምክንያት የሰጠው በአካባቢው ሽፍታ አለ የሚል መሆኑን ያስረዳሉ።
• የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች
• የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ
• ቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ የተመሰረተበትን 70ኛ አመት እያከበረች ነው
መምህር መካሻው በስፍራው ሽፍታ እንደሌለና፣ ሰላማዊ ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ በልዩ ኃይሉ ጥቃት እንደተፈጸመ ይናገራሉ።
"በሕዝብ ይሁንታ የቅማንት የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄን ለማስተባበር የተቋቋመው ኮሚቴ አባላትን ለመያዝ ሆን ብሎ የተደረገ ነው" የሚሉት መምህር መካሻው ሕዝቡ ኮሚቴዎቻችንን አትንኩ እያለ ስለሆነ "ሽፍታ ልንይዝ ነው" በሚል ሰበብ መጥተዋል ሲሉም ያስረዳሉ።
አቶ ከፍአለ ማሞ በበኩላቸው በ2012 ዓ.ም ከመስከረም 10 ጀምሮ በአካባቢው የልዩ ኃይል ጥቃት እያደረሰ ነው ሲሉም ይከስሳሉ። መስከረም 11 ወደ መንደር ገብተው ወጣቶች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ከዚያም ገበሬውም ላይ መተኮስ መጀመሩን ያስረዳሉ።
በአሁኑ ሰዓት ወደ ስፍራው ከፍተኛ ጦር እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ይናገራሉ።
መምህር መካሻው መስከረም 11 የልዩ ኃይል አባላት በድጋሚ መጥተው መንደሩን ማሰሳቸውን፣ የደረሰውን ሰብልም ሲያጠፉ ውለዋል ሲሉ ምሬታቸውን ይገልፃሉ።
"የፀጥታ ኃይሉ በእግሩ የደረሰውን ሰብል ሲረመርም ገበሬዎች ተኩስ መጀመራቸውን" የሚናገሩት መምህር መካሻው "በጥቃቱ ምክንያት ንብረት ወድሟል፣ ሰዎች ከቀያቸውና ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል" ሲሉም ያለውን ሁኔታ ያስረዳሉ።
ከዚህ በኋላም ከመስከረም 16 ጀምሮ ባሉ ተከታታይ ቀናት ጥቃት እየደረሰባቸው እንዳለ የተናገሩት ግለሰቡ በዚህም የተነሳ አንድ ሰው ጨንቾ አካባቢ መሞቱን ተናግረዋል።
አይከል ከተማ አካባቢም የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ግለሰቡ በወና ከተማ ሰው መገደሉን በመግለፅ በቁጥር በርከት ያሉ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ያብራራሉ።
አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የቅማንት የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄ በአግባቡ እንዲፈታ ክልሉ ውሳኔዎችን ማሳለፉን በማስታወስ "የአማራ ክልል ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ እንዳይፈጠር የሚፈልጉ ኃይሎች" ያሏቸውን ለተፈጠረው ግጭት ተጠያቂ ያደርጋሉ።
እነዚህን ኃይሎችን በስም ባይጠቅሱም፤ የግጭቱ ዓላማ ነው ያሉትን ሲያስረዱም "በአካባቢው አለመረጋጋት እንዲኖር፣ ወደ መተማ የሚሄደውን መንገድ መዝጋት፣ በዚህም የተነሳ የአማራ አርሶ አደርና ባለ ሀብት ምርቱን እንዳይሰበስብ ሆን ተብሎ፣ ታቅዶ እየተሰራ ያለ ሥራ ነው" ይላሉ።
• ከልጁ ስድስት ልጆች የወለደው አባት
በአካባቢው በታጣቂዎች ደረሰ ያሉትን ጥቃት ሲዘረዝሩም "ሰላማዊ ዜጎች በመኪና ሲንቀሳቀሱ መኪናውን አስቁመው በማንነታቸው ብቻ ተገድለዋል፤ ከዚህ በተጨማሪም የሚኒባስ ሾፌር ተገድሏል" የሚሉት ኃላፊው የነዳጅ ቦቴ ሾፌሮች መታገታቸውንና ቦቴውን ማቃጠላቸውንም ጨምረው አስረድተዋል።
የሰሞኑ ግጭት የተቀሰቀሰው የፀጥታ አካላት አንድ በወንጀል የሚጠረጠር ግለሰብ ይዘው ከአንድ ቀበሌ ወደ ሌላ ቀበሌ ሲንቀሳቀሱ... | UNK | null | https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization |
End of preview. Expand
in Data Studio
This dataset can be used directly with Sentence Transformers to train Amharic embedding models.
Source Datasets:
- Downloads last month
- 66