text
stringlengths
0
2.31k
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ዳግማዊ እንኳን አብሮ ደስ አለን! በጣም አስደናቂ አትሌት ናት:: በሳል ታክቲክ ነው የተጠቀመችው:: ጉልበቷንና ፍጥነቷን በሚዛን ተጠቅማ ለራሷና ለአገሯ አኩሪ ድል አገኘች:: በየቦታው ባንዲራ እያውለበለቡ ሲያበረታቷት የነበሩ ኢትዮጵያዊያንም አስተዋጽዋቸው ቀላል አልነበረም:: ውብ ነች! አኮራችን::
ጌታ እና ቀደምት...በድጋሚ እንኳን አብሮ ደስ አለን :!:
አሁን ግን ነገር ሆዴ ገባ........ምን መሰላችሁ......ውድድሩን እከታተል የነበረው መጠጥ እየተጎነጨሁኝ በኤንቢሲ ቀጥታ ስርጭት ነበር.....እና ጀግናዋ ጢቂ ገላና ውድድሩን በድል ከጨረሰች በኻል የኢትዮጵያን ባንዲራ አንግባ ስትሮጥ እኔም በደስታ እየጨፈርኩኝ እያለ የኮሜንታተሩ ንግግር ጆሮዬ ውስጥ ጥልቅ አለ....ባልሳሳት ያለው "There is a soviet style training camp in Addis Ababa" ነው.....ያዳመጣችሁ ካላችሁ ወይ አረጋግጡልኝ ወይም አርሙኝ :?
ግን አስቡት.....ይሔኔ ውድድሩን ያሸነፈችው አሜሪካዊት ብትሆን ኖሮ ይሉት የነበረውን ታውቃላችሁ....."ተአምረኛ"; "ልዩ ፍጡር"; "እድሜ ልኳን ለፍታ"; "ወደር የለሽ"; "ጀግና" ወዘተ ነው.......ነገር ግን አሸናፊዋ ጀግና ኢትዮጵያዊት ስለሆነች እርሷን እንደማድነቅ ፈንታ ጠንክሮ ልምምድ መስራት ሀጢያት ይመስል "There is a soviet style training camp in Addis Ababa" ሲል ለአሜሪካውያን የቴሌቪዥን ተመልካቾች የሚያስተላልፈውን መልእክት ልብ በሉ :roll: በጣም ያሳዝናል.....ያናድዳል :evil: :evil: :evil:
ዌካም ቱ ዘ ሪል ወርልድ ! እና ምን ሊሉ ጠበቅክ ? ሴት ያደረጉልን ሂወት አለ... ከዛ ከወጣህ ንዴታቸውን መቆጣጠሪያ ጊዜ ራሱ የላቸውም... ማለቱን አልሰማሁም ምክኒያቱም ውድድር መኖሩን አለሰማሁም :? አይልም ብዬ ግን አላምንም ..
ነገር ከአረቄ ጋር ጥሩ አይደለም አመዶ :lol:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote: ጌታ እና ቀደምት...በድጋሚ እንኳን አብሮ ደስ አለን :!:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
rechoዬ...ድሮም አንቺን አልሰማም ብዬ አጉል ግትር ስሆን እውነታውን ከአረቄ ጋር ሳልወድ በግድ አጋቱኝ :lol: :lol: :lol: ከምር በጣም አናደዱኝ.....ለካ እውነትም ወደው አይስቁም :lol:
"ማሪኝ ብዬሻለሁ" የሚለውን ዘፈን ጋብዤሻለሁ :lol:
recho wrote: ዌካም ቱ ዘ ሪል ወርልድ ! እና ምን ሊሉ ጠበቅክ ? ሴት ያደረጉልን ሂወት አለ... ከዛ ከወጣህ ንዴታቸውን መቆጣጠሪያ ጊዜ ራሱ የላቸውም... ማለቱን አልሰማሁም ምክኒያቱም ውድድር መኖሩን አለሰማሁም :? አይልም ብዬ ግን አላምንም ..
ዳግማዊ መቼም የነጮችን ዘረኛነት ማንም አፍሪካዊ በሚገባ የሚያውቀው ነው:: እስካሁን አላጋጠመህ ከሆነ ብዙም አትበሳጭ:: እኔም ምንጊዜም የማልረሳው ታሪክ አለ:: ያኔ ፋጡማ ሮባ ኦሎምፒክ ላይ ስታሸንፍ እያየን አይናችንን ማመን አቅቶን በደስታ የእምባ ሲቃ ውስጥ ነበርን:: አንድ የፈረንሳይ ቻነል ላይ ነበር ውድድሩን የምንከታተለው:: ሁለት ሆነው ከሚያስተላልፉት ጋዜጠኞች አንደኛው ፋጡማ ወደ ፍጻሜው ብቻዋን እየተቃረበች ስትመጣ ምን አለ መሰለህ: ''እነዚህ ኢትዮጵያዊያን በችጋር የሚሰቃዩ ናቸው: ከእንግዲህ የምግብ ችግሯን ታቃልላለች'' አለ:: በጣም ነው የደነገጥኩትና ያዘንኩት:: የነበረኝን የደስታ ስሜት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሚጻረር አንድ ስሜት ወረረኝ:: አብሮት የነበረው አስተላላፊ ግን ገሰጽ አርጎ ''ይኽ ስፖርት ነው: ልጅቷ ያገኘችው ታላቅ ድል ነው:: ስለ ስፖርቱ ብናወራ ይሻላል'' አለው:: እኛ ተፍጨርጭረን መውጣት አለብን እንጂ የነጮቹ ነገር መቼም ብዙ ነው::
አያ እኔ እንኩዋን ሰውየው እንዳለ ከንፈርም ለማድረግ ነው::
ዶሜክስ አሁን ስለ እንዳለ ከንፈር ማን አነሳ? :) :)
የምንወደውን ብንጠላ የምንጠላውን ብንወድ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ ለውጥ አመጣን ማለት ነው!
ጥሩነሽ በ5ሺ ላይም እንደምትካፈል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ አመራር አረጋገጠ:: ስለሆነም ዝነኛዋ አትሌት ድጋሚ በማሸነፍ ልዩ ታሪኳን እንደምትጨምርበት: የኛንም ደስታ እጥፍ ድርብ እንደምታደርገው ተስፋ አለኝ:: በሌላ በኩል በ800 ሜትር ተስፋ ተጥሎባት የነበረችው ፋንቱ በልምምድ ወቅት በደረሰባት ጉዳት ለመካፈል አለመቻሏ ያሳዝናል::
ቀደምት wrote: ጥሩነሽ በ5ሺ ላይም እንደምትካፈል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ አመራር አረጋገጠ:: ስለሆነም ዝነኛዋ አትሌት ድጋሚ በማሸነፍ ልዩ ታሪኳን እንደምትጨምርበት: የኛንም ደስታ እጥፍ ድርብ እንደምታደርገው ተስፋ አለኝ:: በሌላ በኩል በ800 ሜትር ተስፋ ተጥሎባት የነበረችው ፋንቱ በልምምድ ወቅት በደረሰባት ጉዳት ለመካፈል አለመቻሏ ያሳዝናል::
የፋንቱ መጎዳት ያሳዝናል......ይበልጥ ደግሞ ጥሩነሽ በገነት ቦታ እንድትሮጥ መደረጉም ያሳዝናል....አስቀድሞ በወጣው መስፈርት መሰረት መሮጥ የነበረባት ገነት ያለው ነበረች.....ገና ለገና ለሜዳልያ ጉጉት ተብሎ መርህን መጣስና ለታዳጊዎች እድል አለመስጠት በጣም ስህተት ነው :!: የሚገርመው ደግሞ ተተኪ ታዳጊዎችን መኮትኮት ያስፈልጋል እያሉ የሚያላዝኑ ሁሉ አሁን ጥሩነሽ መሮጥ አለባት እያሉ መጮሀቸው ነው :wink:
የፋንቱ መጎዳት ያሳዝናል......ይበልጥ ደግሞ ጥሩነሽ በገነት ቦታ እንድትሮጥ መደረጉም ያሳዝናል....አስቀድሞ በወጣው መስፈርት መሰረት መሮጥ የነበረባት ገነት ያለው ነበረች.....ገና ለገና ለሜዳልያ ጉጉት ተብሎ መርህን መጣስና ለታዳጊዎች እድል አለመስጠት በጣም ስህተት ነው :!: የሚገርመው ደግሞ ተተኪ ታዳጊዎችን መኮትኮት ያስፈልጋል እያሉ የሚያላዝኑ ሁሉ አሁን ጥሩነሽ መሮጥ
መሀይም ---- ውስጥ ለውስጥ የተሰገስጉት ኮሚቴወች እነማን ሆኑ እና ነው...አሁን አንተ አሳቢ የሆንከው ያንተ ፍጥጥ ያለው ድድብናህ ይህው ባደባባይ ሲገለጽ
አንደኛ....ሀሳብህን በግልፅ ማስረዳት ልመድ....ቀጥሎ ደግሞ ጥሩነሽ በገነት ቦታ መወዳደሯን አትደግፍም ማለት ነው :?: :wink:
ሰንበት 14 ጥሪ 2018 – ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ
ቀዳም 13 ጥሪ 2018 – ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ
ዓርቢ 12 ጥሪ 2018 – ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ
ሓሙስ 11 ጥሪ 2018 – ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ
ዓርቢ 5 ጥሪ 2018 – ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ
ሓሙስ 4 ጥሪ 2018 – ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ
ሰሉስ 2 ጥሪ 2018 – ፕሮግራም ሬድዮ መድረኽ
 WARKA ዋርካ • View topic - ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!
እያለ ይዘፍን ነበር ገልቹ ኃይሉሸምቦ... ነፍሱን ይማረውና... በጊታሩ!...
እንደምን አላቹ የወዩ ልጆች....
አንዴ የሰማሁት ነው..... የቅዳሜ ገበያ አልቆ... ጉጆቹ ጠጅ እየጠጡ ነበር.... ሰፈሩንና ነገሩን አልጥቀሰውና.. ብቻ አንዱ ጉጂ ጩኸቱን አቀለጠው... በር ላይ ወጥቶ.... ፖሊስ መጥቶ ምን እንደሆነ ሲጠይቀው ምን እንዳለ ታቃላቹ....
ቁመቱ እንዴት እንደደረሰለት ጌታ ይወቅ... ለነገሩ ልምድ ነበረው አሉኝ.... አሁን የት ይሆን ያለውውውውውውው...
በተረፈ... እስኪ ትንሽ ፋታ ሳገኝ ብዙ ብዙ ትዝታዎች አሉኝ.. እዛች አገር ውስጥ.... እንዲሁ እንዲሁ እየተጨዋወትን ያንን ያልኳችሁን የመፃፉን ጉዳይም እንድንነጋገርበት እወዳለሁ....
የጌታ ፍቃድ ከሆነ በኦክቶበር አሜሪካ ሄጄ በማርች ወደ አዶላ ላቀና አስቤአለሁ.... የሚጠረቃቀም ነገር ካለ... መፃፍ መፃፍ መፃፍ... እስኪ ሁላችንም በያለንበት እንዘጋጅ... ከልብ .. በየዋህነት....
ማትሪክ ስፈተን አንዲትም መፃፍ ለማንበብ አልታደልኩም ነበር.... ጌታ ምስክሬ ነው.... ታናናሽ ወንድሞቻችንና ወገኖቻችን እኛ ያጣነውን ባያጡ... መልካም ምኞቴ ነውና...
አደራ በምድር በሰማይ...
ያንፈራራው ሀጂ-ገሪገሪ የቢሉው ሼ-አሊፋሪስ... የ01ዱ ስላሴ የ04 ሚካኤል ከነደባሉ... መድሀኒአለምና ማርያም ይታዘቡኛል ... ብዋሽ...
ወይ ጉድ ወሬኛ ሆንኩ"ኮ
እስኪ ቸር ይግጠመን
ይቅርታ አድርጉልኝ ግን ሳልጠራ በመግባቴ:: ውይ ደስስስ ስትሉ እንዴት እንደምታስቀኑ!!! እግዚአብሄር ሀሳባችሁን ይሙላላችሁ:: በሉ እንግዲህ ለቁም ነገር አብቁት መሰባሰባችሁን::
እኔም አንድ ቀን የትውልድ መንደራችሁን ለማየት ያብቃኝ::
ትህትናዬ ስለአድናቆትሽ አመስግንሻለው :!: ሲዳሞ ማለት በጣም የሚናፈቅ አገር ነው::እንደው በዝና ከሆነ የምታውቂው አንድ ቀን እንጋብዝሻለን መቼም ወረድ አላልሽ ይሆናል እንጂ ላንጋኖን ወንዶገነትን የምታውቂው ይመስለኛል::በዚያው መስመር ነው ይቺ ትንሽ ከተማችን የአዋራዋ ትዝታ ከፊት አይጠፋም::ስውም በጣም ሰለሚዋደድ ነው መሰለኝ ::
እኔ የራሴን ሳወራ ግዜ አጠፋሁ ወገኖቼ እንዴት ከረማችሁ! ተበራክታሁ የለም እንዴ:: (ትናንት ከሻለቃ ደስታ ጋር ነው ያደርኩት"ቢያስ......ንም ጮማ ይሻላል" አለች ብርሀኔ)ጊዜዬን ከናንተጋ ባጠፋ ና ሁሉም ቢቀርስ::የቀድሞ ክ/መንግስትን ሳስታውስ በተለይ አራዳ .አዲሴ-ሌቴ-ሲዴ-ጸጋዬ ሳንታ ሌሎችም በጣም ትዝ ይሉኛል::ጻዲቄ እና በጠሶቀጠሶንማ ሁኔታቸው ሁሉ አይረሳኝም::
በእውነቱ ስለ አዶላ(ክ/መ)በማንሳታችሁ በጣም ደስ ብሎኛል::የቦሬ ልጅ ብሆንም ክ/መን ከቦሬ ባልተናነሰ እወዳታለሁ: ራስ ብሩም በአንድ ወቅት 7ና8 ን ዉብሸት ምንድጌ የሚባል ዳይሪክተር በነበረበት ጊዜ ተምሬአለሁ::በጣም ብዙ ትዝታ አለኝ ሚ/ር ባክስቸር (አሜሪካዊ)አስተማሪ;ያሽልንግዬ ያሽልንግዬ ጉጂን ጉጂ ጂቤ ገብሬ መላጥዬ: --የሚለው መዝሙር;በዚያን ጊዜ የነበረ ኳስ (የመሰንጠቂያና ሌሎች ክለቦች) ወንድሙ ሳንታ;ሲሳይ ሳንታ;የወቅቱ አርቲስት አህመድ ሺፋ;እፍሬም ጎርፉ:ትዝ ይሉኛል::በተለይ 3ኛው ዙር መሰረተ ትምህርት ዘመቻ ሬጂ እብሮኝ ዘማች የነበረው ጓደኛዬ ወንደሰን ገድሌ ሁሌም አስታውሰዋለሁ::በተረፈ በርቱ እኔም ት/ቤቴን ለመርዳት ዝግጁ ነኝ::እዚህ በምኖርበት እንግሊዝ ብዙ ልጆች እንዳሉ አውቃለሁ::ለማስተባበር በጀምጀም ወዩ ስም ቃል
አንተ ወቤጃሎ እንዴት ከረምክ ጃል!አደቆርሳ ያቺን አዮ ቦሬ ከገብሱ እሸት መሀል አገኘሁአት ሲል አምጣ የኔ ናት ለማለት ብቅ አልክ ብዬ........ ነበር:ዳሩ አንተም የራስብሩ ሆነህ በመምጣትህ ደስ ብሎናል::
ገሚሻ አሁንም ያው ነው:ደራርቱ የዘመዶቹን እርጎ እየጠጣ ነው::ከጠቀስካቸው ውስጥ ኤፍሬም ጎርፌና ወንድሙ ሳንታ አሁን በህይወት የሉም::በነገራችን ላይ የኢሀፓ እልቂት ሲጀመር በዚያው በጨምቤ በኩል እግሬ አውጪኝ ያሉ የወዩ ልጆች አሁን የት እንዳሉ የሚያውቅ አለ ???ተከስተ ሀብቴ ከረዥም ግዜ በሁዋላ ተመልሶ አሁን ያለው ክ/መ.ነው.እነ ሳህሉና ሀብቱ ኪዳኔ:ስለሺ ተስፋዬ.ከዚያ ደሞ እነ ተስፋዬ ሀ/ጊዮርጊስ(ጨጎና),አስቴር በተላ,የት ይሆኑ?እስቲ የሚያውቅ ካለ እጁን ያውጣ::
ሠላም ቅሩንፉድ በጽሁፍሽ የነስመኝ አለማየሁን ሻይቤት ስታስታውሽን ወይኔ....እረፍት ሆኖ እዚያ ለመሄድ.......በጣም እጅግ በጣም ትልቅ የልጅነት ትዝታ ቀሰቀስሽ አቦ !!!!! ወፉን በሚገባ አስታውሰዋለሁ እንጂ ....እንደውም ወፉን በጣም የሚወዱት ጋሽ ርዕሶም እና ጋሽ ከድሮ ስይድ ነበሩ::ጋሽ ከድሮ ሱቅ ሄዶ ያቺን ልብስ..?ብሎ ወፉ ከጠየቀው ያቺንው ነበር አውርዶ የሚሰጠው::ግን ከዚያች ቀን በላይ ወፉላይ የለችም::ጋሽ ርዕሶምም አንዳንዴ አመት በዓል ወይም (specialdays)ሲሆን ቂቅ አድርጎ አልብሶት እጁን ይዞ ወደከተማ ይወጣ ነበር::ወፉግን በአጠቃላይ ልብስ መልበስ አይወድም::""ያም ትመጣለህ""የሚለው የዘወትር አባባሉም አይረሳኝም:: መላጣውስ ?
ሌላው ቁምቢ ሮቢ እና ቢሆኔም ትዝ ይሉኛል::እነ ሀና ሀብቴ በረንዳ የሚያድረው አደፍርስም የኛ ሰፈር የካምቦ ልጅ ነበር::ስለ ወፉ ጨምራለሁ ባልሽው ላይ ሌላም ጨማምረሽ በትዝታ አዝናኚና አቦ !!
ወንድሜ ቀለቤለጌ በጣም የሚገርመው ትናንት የጻፍኩት በድንገት ነበር:ሆኖም ማታ ተኝቼ ሁሉም ነገር ፊቴ ላይ ተደቀነ:ዘሜ አሊን በታሪክ አልረሳትም ድንቅ ዳንሰኛ ነበረች:: ዛሬ ላነሳት ስል ቀደምከኝ::ሌላው,የሱማሌው የጃማ ሻይ ቤትእና ቆጪ አጠገብ ያለው ትልቅ ቤት የነበረ ሳምቡሳ ና ብስኩት ትዝ ይሉኛል::በአንድ ወቅት ገበያ ክፍል ኬላው አጠገብ ያለው ሀምሌ 19 (የግራዝማች ደመቀ) ሆቴል ነበር ባልሳሳት:የቦሬ ልጆች አልቤርጎዉን ተካራይተው (ለትምህርት መጥተው)ይኖሩ ነበር: አንድቀን እኔም ነበርኩ ከድር ከማል የተባለ ልጅ ወደጓሮ ሄዶ የተጣለች አሮጌ መኪና ስር የተኛች ትልቅ ሚዳቋ አይቶ ጠርቶን ይዘናት በማታ ከጆቫኒ መሰንጠቂያ ፊትለፊት ካለው ትልቅ ቤት ለሚኖረው አሜሪካዊ አስተማሪ ሚ/ር ባክስቸር በ14 ብር ሸጠን ያደረግነው ሰርግና ምላሽ አይረሳኝም::ሌላው የልጅነት ትዝታዬ ስለሆነ ና ያለፈ ታሪክም ስለሆነ ለምን ስለ <ሀዳ ፉሪ ቤት>አናወራም መቼም በዚያን ወቅት መዝናኛችን,መለማመጃችን ---ላኪ አቦ ----ኢጆሌ ቦሬ ነኝ ቸር ይግጠመን::
Truth-based articles, analysis, and commentary on wide spectrum of contemporary issues, Politics, social, Religion, Human Rights and Current Events from Theological Perspective. No Spin! ሣልሳይ ወያነ፥ በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል አዘጋጅነት የሚቀርብ ድረ – ገጽ ሲሆን በዚህ የመወያያና የመመካከሪያ መድረክ ኃይማኖታዊ፣ ሀገራዊ፣ ማህበራዊና ወቅታዊ እንዲሁም ሰብአዊ መብት ነክ ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የሚዳስስ፤ የድረ ገጹ አዘጋጅ ከሥነ መለኮት ዕይታ ወንጌላዊ፣ ምሁራዊና ሙያዊ ትንተናና ሐተታ የሚሰጡበት ገጽ ነው። ሣልሳይ ወያነ፡ “ደጋፊ” አልያም “ተቃዋሚ” የሚል መታወቂያ የሌለው ዜጎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ግላዊ አመለካከታቸው የሚያንጸባርቁበት የዜጎች ነጻ ሃሳብ የሚንሸራሸርበት ለሕዝብ የቆመ ሕዝባዊ ገጽ ነው።
የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው!
ለመንደርደሪያ ይህን ያህል ካልኩ ዘንዳ ወደ ፍሬ ነገሬ ስመለስ መቼም ሰው በተለያዩ መንገዶችና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከቀድሞ መንገዱ መመለሱ ወይም ከስህተቱ መማሩ የማይቀር ነው። [“መንገዶች” የሚለውን አንድም በፈሊጥ አልያም በፍልጥ ለማለት ተፈልጎ ሲሆን “በልዩ ልዩ ምክንያቶች” የሚለውን አገላለጽ ደግሞ አንድም በውዴታ አንድም በግዴታ ማለትም ሌላ አማራጭ ስሌለው ተገዶ ይማራል ለማለት ተፈልጎ ነው።]
ኢሳት እነዚህ ዘመቻዎች ብቻ አይደለም ሊያሳየን ያልወደደው። ከእነዚህ ዝግጅቶች ቀደም ሲል እ.አ.አ መስከረም 19/2013 ዓ/ም በእስራኤል ያዘጋጃው አዝማሪ ታማኝ በየነ አንድ ጊዜ ብቻም አይደለም ሁለቴና ሦስት ጊዜያት በትግራይ ሕዝብ ላይ ያለውን ፍጥጥ ያለ ጥላቻና በቀል ያሳየበትና አሳፋሪ በሆነ መልኩ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያለውን መራራ ጥላቻ የገለጸበት ዝግጅትም ቢሆን በሌሎች ድረ ገጾች ቀድሞ አምልጦ ስለ ተሰራጨና ከኢሳት ቁጥጥር ውጭ ስለሆነ እንጅ ኢሳት በራሱ ድረ ገጽ አለጠፈውም። የኢሳት የዝርፍያ ዝግጅት በእስራኤል ምን ይመስል እንደነበረ ለማንበብ ሊንኩን (አዝማሪውም አለ …! http://wp.me/p3MQOW-75) በመጫን ለማንበብ ይችላሉ።
በነገራችን ላይ ታማኝ በየነ ራሱ “አዝማሪ ነኝ፣ የማልረባ ትቢያ ነኝ፣ አፈር ነኝ፣ ትል ነኝ፣ ተራ ነኝ፣ ዶማ ነኝ፣ አካፋ ነኝ፣ ሸክላ ነኝ፣ ድስት ነኝ፣ ምጣድ ነኝ … ወዘተ እያለ በአጉል ትህትና ራሱን ለማቅረብ ስለሚከጅለውና ራሱን በዚህ መልኩ ስለሚጠራ ነው እንጅ በግሌ “አዝማሪ ታማኝ በየነ” ብዬ የመጥራትም ሆነ ግለሰቡን “የመዘንጠል” ፍላጎት ሆነ ዝንባሌ የለኝም። በግሌ “አዝማሪነት” ሞያ እንጅ ስድብ ነው ብዬ ባላምንም ብዙዎች በዚህ መልኩ ላያዩት ስለሚችሉ ግን ራሴን ግልጽ ማድረግ ግድ ብሎኛል። ወንድም ታማኝ እንደው አርፎ ስለማይቀመጥ ነው እንጅ እኔም እንደሆንኩ እጄን አከብድበት ዘንድ አልወድም። ማለትም በዙሪያው የመጻፍ ፍላጎቱ የለኝም። ወንድም ታማኝ ቆሞም ሆነ ተቀምጦ (ብቻ እንደሚያመቸው ሆኖ) እንግዶቹን ቢያስተናግድና ሳክስፎኑን ቢነፋ በእውነቱ ነገር ችግር የለኝም።
ለማንኛውም ግን ኢሳት በየስፍራው እየዞረ የሚደርጋቸው የዝርፍያ ዝግጅቶች ውሎ ለአየር አላበቃም ማለት ግን ኢሳት በትግራይ ሕዝብ ላይ ያለውን ሥር የሰደደ ጥላቻና ተሸክሞት የሚዞረው የህግደፍ የጦርነት ዘመቻ አጀንዳ አቆመ ማለት አይደለም። በዚህ አጋጣሚ እያንዳንዱ ዜጋ ሊያውቀውና ሊረዳው የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ግን ኢሳት ማለት ሌላ ማንም ማለት ሳይሆን ኢሳት ማለት የትግራይ ሕዝብ ጠላት፣ ዘሩን ለማጥፋት ከሚቋምጡ የውስጥም የውጭም የሞት ጥላ ናፋቂ ኃይሎች ድምጽና ደመኛ ተቋም ለመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ ልያሰምርበትና ልብ ሊለው የሚጋባ ተጨማሪ ማስረጃ የማስፈልገው ሐቅ ነው።
ሌላ “ለሺህ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ” እንደሚባለው የኢሳት የውሸትና የቅጥፈት እንቅስቃሴ ባለበት ለማምከንና ከምንጩ ለማድረቅ ምንም ዓይነት ጋጋታም ሆነ የሰራዊት ብዛት አንደማያስፈልገው ይህ በቂ ትምህርት ሊሆን ይገባል። አንድ ሰው በብዙ የመንግሥታት እጆች የቆመ ድርጅት እንደዚህ ማሽመድመድና ማጥመልመል ከቻለ እያንዳንዱ ዜጋ ባለበት ኃላፊነት ተሰምቶት ለአመጻ እንቢ! በማለት ለእውነት ቢቆምና ከእውነት ጋር ሕብረት ቢፈጥር ምንኛ አገር ትቀና እንደነበርም ከዚህ ለመማር እንችላለን።
ሰው ከፈራ ውሸት፣ ቅጥፈትንና ሌብነትን ነው መፍራት ያለበት እንጅ እውነት ካለውና/ከያዘ ከእውነት ጋር ከተጣበቀ አንዳች የሚስፈራው ነገር ሊኖር አይገባም። ገፋ ቢል እውነት የገባችበት ስፍራ ይገባል። እውነት ጉድጓድ ወይም ሲዖል ውስጥ ገብታ ሰምጣ አልቀረችም እንጅ። ታድያ የሐሰት አባት የዙፋኑ መቀመጫ ኢሳት ፊት ለፊት በግልጽ መቃወምና መገሰጽ የሚያስፈራንና የሚያሽቆተቁጠን ምንድ ነው?
ኢሳት ጤና ቢኖረው ኖሮ በገንዘቤም በእውቀቴም ኢሳትን በሁለት እግሩ ለማቆም ማንም አይቀድመኝም ነበር። ዳሩ ግን ኢሳት ራሱን በአመጽ ስለ ገለጠ እኔም ከአመጸኛ መዓድ ጋር የምካፈልበት ምንም ዓይነት ምክንያት ስለ ሌለኝ ለሞቱም እንዲሁ መቅረዜን በዘይት ሞልቼ ከፊቱ ላይ ቆሜለሁ። ፈጽሞ እስከሚወድቅ ድረስ ደግሞ እገዘግዘዋለሁ። ይህ ደግሞ መንፈሳዊ ዜግነታዊም ግዴታዬ ነው።
በተረፈ የአብነት ተማሪ “ስለእመብርሃን ስለ ወላዲተ አምላክ” ብሎ የዕለት እንጀራውን እንደሚያገኝ ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለኢሳት የመለመኛ ቅላጼው ነው። ኢሳት የትግራይ ሕዝብ ስም ሳያጎድፍ፣ የጥላሸት ሳይቀባ፣ ሳይቦጭቅ፣ ሳይዘባበት፣ ሳያቃልል፣ ሳይሳደብ፣ ሳይዘረጥጥ፣ ሳይኮንን፣ ሳይራገም፣ ሳያጣጥል፣ ሳያማ፣ ሳይዘልፍ፣ ሳያሽሟጥጥና ሳያዋርድ የሚሰበስባት ዜሮ አምስት ሳንቲም የለችም። ታድያ ይህ የኢሳት የተበላ ቁብ እንቅስቃሴ ለትግራይ ወጣቶች በአጠቃላይ ለትግራይ ሕዝብ የሚያስተላልፈፍ መልዕክት አይኖርም ብሎ ማመንም ሆነ መገመት በራስ ላይ እንደመሽናት ነው የሚቆጠረው።
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
አጽናኝ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእናንተ ጋር ይሁን
ሰባኪው እውነት ተናግሯል – ኢሳት ቅዠት ውስጥ ነው!
በዳያስፖራ ማህበረሰብ ዘንድ “ተቃዋሚ” ተብሎ ለመጠራት ሆነ ለመወደስ፡ መመዘኛው
የየመን ባንዴራ ማቃጠል ምን ዋጋ አለው? ካቃጠሉ አይቀር የእንግሊዝ ነው እንጅ!
የመቼው አንዳርጋቸው ጽጌ ኖት፡ የድሮ ወይስ የዘንድሮ?
አንድዬን ያሳረፈ ማን ይሆን፡ ህ.ግ.ደ.ፍ ወይስ ግንቦት 7?
አንዳርጋቸው ጽጌ፥ ከባህር የወጣ ሙት አሳ!
“ኢትዮጵያዊነት” እና “አንድነት” ከሚለው ዘፈን ጀርባ ያለው ጸረ እኩልነት የነፍጥ ፖለቲካ ሲፈታ፡
ይድረስ ለኤልያስ ክፍሌ፥ … ስለ ምን ትመታኛለህ?
መዋቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ “NSA” የዒላማ መዝገብ ስማቸው ተገኘ
“ኢትዮጵያዊነት” ማንነት ሳይሆን ዜጎች በህግ የሚጎናጸፉት ማሊያ ነው!
HRW፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወይስ የኃያላን መንግሥታት መልዕክተኛ?
የሒሳብ አያያዝ ባለሞያ የለም ወይ ባገሩ? (በለንደን ለምትገኝ ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላት)
ዘንድሮ ሼባዎቹ ምን ነካቸው?
ወዳጄ ሆይ! የሚሾመውና የሚከብረው ሌላ ሆኖ ሳለ አንተ ለምን ትሞታለህ?
ሲሳይ አጌና፡ እውን ሲሳይ ወይስ መርገም?
የመገንጠል ጥያቄ ያለው ሕዝብ – ይቀንጠስ!
ኢሳት፡ አማርኛ ተናጋሪ የሻዕቢያ ቡችላ!
መራሕቲ “ህወሓት” ኣብ ታሪኽ ንሕዝቢ ትግራይ ደው ዝበልሉ ዕለት የለን! (ትግርኛ)
ለምን አድዋን ቆርጣችሁ ወደ ኤርትራ አትቀጥልዋትም!?
ሰላማዊ ትግል ኢትዮጵያ ውስጥ ተነበበ እንጅ አልተተረጎመም!
“አንድ ነን” እየተባለ እርስ በርስ እየተነካከስን ከምንጠፋፋ ተለያይተን ብንለማ አይሻልም ወይ?
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ “ከኢትዮጵያ ጋር መታረቅ ስለሚባለው ባልሰማውና ባላስበው እመርጣለሁ” አላሉም!
የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል ድረስ!
አሜሪካ ገፋ ቢል ማድረግ የምትችለው ነገር ቢኖር ግንቦት 7 አስታጥቃ የኢትዮጵያ ከተሞች ባግዳድ ማድረግ ብቻ ነው!
ኢሳት፡ በሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባበት! ክፍል ፪
ኢሳት፡ በሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባበት! ክፍል ፩
“ኢሳት የእኔ ነው!” በማለት ለሚንጣጣና ለሚንቀለቀል ዜጋ መድኃኒቱ: የትግራይ ሕዝብ ማንቃት፣ ማደራጀትና ማስታጠቅ ነው!
ኢትዮጵያዊ ማንነት ሆነ ኢትዮጵያዊነት ብሎ ደም የለም!
የቀን ቅዠት ያበላሸው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ከማንዴላ ምን ይማራል፡
ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ! (ክፍል አንድ)
አጉል ተስፈኞች አንሁን፤ ተመጻዳቂዎች ከመሆን ህይወትም እንውጣ! (ክፍል አራት)
የኤርትራ ጉዳይ፡ አንድ ነበርን ማለት ነን ማለት አይደለም!
ኢሳት የእኔ ሊሆን አይችልም!