text
stringlengths 0
11.4k
|
---|
የወታደሮች መዝሙር የሚባሉት አስራ ሁለት በጥንቱ አማርኛ የተጻፉ ግጥሞችን ነው። ከነዚህ ግጥሞች አራቱ በ1300ወቹ በአጼአምደ ጽዮን ዘመን የተጻፉ ሲሆን ምናልባትም በጣም ቀደመትና እስካሁን ካልጠፉ የአማርኛ ጽሁፎች መካከል ናቸው። [1]እኒህ አራቱ ግጥሞች በኤድዋርድ ኡልንድሮፍ የበለጠ ተጠንተዋል[2]። የመጀመሪያዎቹ ግጥሞች ስለ 15ኛው ክፍለ ዘመን ንጉስ፣ ስለ ቀዳማዊ አፄ ይስሐቅ የተገጠሙ ሲሆን ጣሊያናዊው ታሪክ ተማሪ ሴሩሊ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ፈርጥ ካላቸው ወገን ናቸው። ቀሪዎቹ ግጥሞች ለዓፄ ዘርአ ያዕቆብና በኋላም ለዓፄ ገላውዲወስ የተገጠሙ ነበሩ።
|
ከዚህ ጎን በ1881 በጣሊያን አገር ታትሞ ከወጣው የጥናት መጽሄት ሙሉው ፲፪ቱ ግጥሞች ቀርበዋል። የቃላቶቹ አጻጻፍ፣ አልፎ አልፎ አደናጋሪና በ1686ዓ..ም ለታተመው የአማርኛ መጽሐፍ መጽሐፈ፡ትምህርት፡ዘልሳን፡አምኅራ። የቀረቡ ናቸው።
|
እንዴት ታስደነግፅ
|
ደንጊያ በቁልቁለት ስሮጽ
|
እርሱ በእርሱ ሲፋለጽ
|
እንዴት ያስደነግጽ
|
እንዴት ታስደነግፅ
|
ኮከብ ትመስል ዣን በጽሩ ሰማይ ሲሮጽ
|
ወደ ምዕራብ ሲሠርፅ
|
ገጽኹ እንዴት ያስደነግፅ
|
ሲሬ ሠራዌ የመስል ዣን
|
ሐምበል አልብሶ ረመጽ
|
ጎድን በሪም ሲፈጸፍጽ
|
ሐንገት በሰይፍ ሲቆርጽ
|
ገጽኹ እንዴት ያስደነግፅ
|
ዣን ይስሐቄ ገጽ
|
ምላት የመስል ዣን
|
ሳፍ ለሳፍ ካንፈርዓጽ
|
ወርካ ከስሩ ነቅሎ ሲያሮጽ።
|
እንዴት ያስደነግፅ
|
ገጽኹ የዣን ይስሐቄ እንዴት ያስደነግጽ
|
ዣን ይስሐቄ ገጽ።
|
ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ (ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፮ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.)[1] ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኃይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ እና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ።
|
ቴዎድሮስ ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን ተዳሩ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በኒህ ተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ፫ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሥ ካሳ - ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ።
|
ሥርዓተ ንግሡ የዘመነ መሳፍንት መቃብር በመሆን የዘመናዊ ኢትዮጵያን ታሪክ "ሀ" በማለት ጀመረ። ዓፄ ኃይለ ስላሴ እስከ ፈጸሙት ድረስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ሥራም በዚሁ ወቅት ተጀመረ። ዓፄ ቴዎድሮስ ሰሜናዊ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አንድ ለማድረግ የሞከሩት፣ አጠቃላይ በታሪክ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ክፍል ነበር - ለዚህም ዋቢ ወደ ወሎና ወደ ሸዋ ያደረጓቸው ዘመቻወች ይጠቀሳሉ።
|
በዘመነ ንግሣቸው ዓፄ ቴዎድሮስ አገሪቱን የሚያሻሽሉ ሥርዓቶችን ለአገራቸው አስተዋውቀዋል። ከነዚህም ውስጥ፡ ባርነትን የሚያግድ አዋጅ፣ የመጀመሪያው መንገድ ግንባታ፣ የሥርዓተ ንዋይና የፖለቲካ ሥርዓቱን በማዕከላዊ መንገድ ማዋቀር፣ የባላባት የተከፋፈለ "ሁሉ-በሁሉ-ጦርነት ሥርዓት"ን በማስቀረት ብሔራዊ ውትድርናን ማስተዋወቅ ይጠቀሳሉ። በዘመነ መሳፍንት እንደልባቸው ይፈልጡ ይቆርጡ በነበሩ ባላባቶች ዘንድ እኒህ ለውጦች እጅግ የተጠሉ ሆኑ። በ፲፰፻፶ ዓ.ም. ብዙወቹ ባላባቶች አመጽ ማነሳሳት ጀመሩ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርስት የነበረውን መሬት ለገበሬወች በማከፋፈላቸው ከሃይማኖት መሪወች ጋር ተጣሉ። ይህን ተከተሎ በየቦታው አመጽ በሚነሳበት መካከል አውሮፓውያን ሚሲዮኖችም ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በተነሳሳ አለመግባባት ምክንያት በዓፄው ታሰሩ።
|
በመጋቢት ወር ፲፰፻፷ ዓ.ም ላይ የእንግሊዝ መንግሥት በሮበርት ናፒየር የሚመራ፣ በጊዜው እጅግ ግዙፍ የተባለ ኃይልን አሰናድቶ አውሮፓውያን እስረኞችን ለማስፈታት ጦር ላከ። መጋቢት ፭ ቀን ፲፰፻፷ ዓ.ም ይህ ጦር በመቅደላ ምሽግ ላይ በሚገኘው፣ በአመጽ በተዳከመ የንጉሱ ጦር ላይ ጥቃት አደረሰ። በውጊያው መሃል ንጉሠ ነገሥቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁ እስከመጨረሻው አሻፈረኝ በማለት በሽጉጣቸው እራሳቸውን ገድለው በጀግንነት አለፉ። ዓፄ ቴዎድሮስ ያሰቡትን ለውጦች በሙሉ በተግባር ቢፈጽሙ ኖሮ በእርግጥም ታላቅና የሰለጠነ ሀገር መሪ ሊሆኑ ይችሉ እንደነበር ታሪክ ተመራማሪወች ይስማማሉ። ዕቅዳቸው በዚህ መልኩ ቢሰናከልም፣ እጅግ ድንቅ መሪ፣ የተዋጣላቸው ወታደርና የተባበረች ዘመናዊ አገር ራዕይ አብሳሪ እንደነበሩ ያሰሯቸው አውሮጳውያን ሳይቀር ሳይመሰክሩ አላለፉም።
|
የዙፋን ስማቸው «ቴዎድሮስ»ን የወሰዱት ከፍካሬ ኢየሱስ ከተገኘ ትንቢት ነበረ። በዚያው ትንቢት በኩል፣ በዓለም መጨረሻው ክፍለ ዘመን፣ ተወዳጁ፣ የጥንቱ ዘመን ንጉስ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ እንደገና ተነስቶ አገሪቱን ለ፵ ዓመታት ይገዛል የሚል ነበር። "ቴዎድሮስ" የሚለው ስም ከግሪክ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም «ጤዎስ ዶሮስ»፣ 'የአምላክ ስጦታ' ማለት ነው።
|
ዘመነ መሳፍንት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከ፲፰ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ እስከ ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የተከሰተ ጊዜ ሲሆን፣ በወቅቱ የየአካባቢው መሳፍንት ኃይል የገነነበትና እርስ በርሳቸው የሚዋጉበት እንዲሁም ዋናው ንጉስ ሥልጣኑ ከመዳከሙ የተነሳ ከጎንደር ከተማ ውጭ እምብዛም ተሰሚነት ያልነበርበት ወቅት ነበር። ከነበረው አለመረጋጋትተነሳ ከጎንደር ከተማ ተነስቶ እየተስፋፋ የነበረው ስልጣኔ የኮሰመነበት፣ እንዲሁም ህብረተሰቡና ባህሉ ወደፊት አንድ እርምጃ መራመድ አቅቶት እየበሰበሰ የነበርበት ወቅት ነው። ከትውፊት አንጻር የዚህ ዘመን ጅማሬ የሚቆጠረው ራስ ሚካኤል ስሑል ዳግማዊ ዓፄ ኢዮአስን ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፲፯፻፷፩ ዓ.ም. ሲያስገድለው ሲሆን በተቃራኒው የዘመኑ ፍጻሜ ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ የካቲት ፬ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሠ ነገሥት ሆነው ስል፧ቾጣን ላይ ሲወጡ ነው።
|
ዳግማዊ ኢያሱ (ጥቅምት 21፣ 1723 እ.ኤ.አ - ሐምሌ 27፣ 1755) በዙፋን ስማቸው ዓለም ሰገድ ከመስከረም 19፣ 1730 ጀምሮ እስከ እለተ ህልፈታቸው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ሲሆን አባታቸው አጼ በካፋ ሲሆኑ እናታቸው እቴጌ ምንትዋብ (የክርስትና ስም - ወለተ ጊዮርጊስ) ነበሩ።[1]
|
የወደፊቱ ዳግማዊ እያሱ ወደ ስልጣን በወጣበት ጊዜ ገና ህጻን ስለነበር እናቱ እቴጌ ምንትዋብ የልጁ እንደራሴ ሆና ተሾመች። ነገር ግን የልጁን መንገስ የሚፎካከሩ አካሎች የፋሲል ግቢን በመክበብ ጥቃት ማድረስ ጀመሩ። ስለሆነም ከጎጃም 30፣000 ሰራዊት ተነስቶ ጎንደር ስለገባ የስልጣን ተፎካካሪወች የፋሲልን ግቢ ጥሰው ውስጥ ሳይደርሱ ተሸነፉ.[2]። በዚህ ግርግር ምክንያት እቴጌ ምንትዋብ በእንደራሴነት ሳትወሰን እራሷ ላይ ዘውድ በመጫን ከልጇ ጋር እኩል ስልጣን እንዳላት አወጀች። በዚህ ሁኔታ የንግስትነት ማዕረግን ስትይዝ እቴጌ ምንትዋብ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ለመሆን በቃች።
|
የዳግማዊ ኢያሱ አስተዳደር
|
ዳግማዊ ኢያሱ በ8 አመቱ ስልጣን ላይ የወጣ ሲሆን እንደ ታሪክ አጥኝው ፓውል ሄንዝ አባባል ከእናቱ ብዙ ምክርን ቢያገኝም እርሱ ግን ብዙ ጊዜውን አደን በማደንና የጎንደር ከተማን በተለያዩ ጌጣጌጦች በማስዋብ፣ ለውጭ አገር እጀ ጠቢባን ብዙ ገንዘብ በመክፈል፣ ከአውሮጳ የተለያዩ የቅንጦት እቃወችንና ትላልቅ መስታውቶችን በማስመጣት የአገሪቱን ጥሪት በማሟጠጡ በብዙወች ዘንድ ይነቀፍ ነበር[3] ። ሆኖም ግን በዚያው ዘመን ከአሁኑ ቼክ ሪፐብሊክ ተጉዞ በጎንደር ለ፩ ዓመት ቆይቶ የነበረው ሃኪም ሬሜደስ ፑትኪ በጊዜው እንዳስተዋለ በኢያሱ ዘመን ተከስቶ ለነበረው የንዋይ እጥረት ልጇን ሳይሆን እናቱን እቴጌ ምንትዋብን ተጠያቂ ያደርጋል። በፑትኪ አገላለጽ፣ ኢያሱ ገና ህጻን እያለ ንግስት እናቱ «"የአገሪቱን ግዛቶች ከፋፍላ ለተለያዩ ገዥወች ስለሰጠች ልጁ በዚህ ወቅት ለራሱ ተራ ወጭ የሚሆን በቂ ንዋይ እንኳ እንዳይኖረው ሆኗል"»። ፑትኪ በመቀጠል ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት፣ ኢትዮጵያ በነበረበት በ1752ዓ.ም.፣ ንግሱ ከእህቱ ጋር ከጎጃም በሚመጣ ገቢ ምክንያት እየተጣሉ እንደነበር ዘግቧል [4]።
|
ከዚህ በተረፈ፣ ወጣቱ ንጉስ ፣ በ16 አመቱ፣ ከህዝቡ ዘንድ ከበሬታን ለማግኘት ሲል በሰናር መንግስት ላይ ዘመቻ አድርጎ በ1738ዓ.ም. በድንዳር ወንዝ ጦርነት ላይ በስናሮች የቆረጠ ራሱ ምስልና ግማደ መስቀሉ ተማረከ። ለኒህ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ቅርሶች ማስመለሻ 8000 ትሮይ ኦንስ ወርቅ እንዲከፍል ተገደደ[5]። እንደ ታሪክ አጥኝው ዶናልድ ሌቪን አስተያየት ምንም እንኳ ለብዙ ዘመናት አመጽ የሚካሄድበትን ላስታን ዳግማዊ ኢያሱ በጦርነት ቢያረጋግም፣ በአጥባራ ወዝን አካባቢ በሚኖሩ ነገዶች ላይ ድልን ቢቀዳጅም ፣በድንዳር ወንዝ ጦርነት የገጠመውን ሽንፈት ሊያስተሰርይ አልቻለም [6]።
|
በዚሁ ንጉስ ዘመን በተነሳ የአንበጣ መንጋና በኋላም በተነሳ ተላላፊ በሽታ በሺህ የሚቆጠሩ ሰወች አለቁ። አቡነ ክሬስቶዶሎስ ሲያርፉ ሌላ አዲስ አቡን ከግብጽ ለማስመጣት በቂ ነዋይ ታጣ። ከዚህ አንጻር በጎንደር የሚኖሩት ነገስታት ሃይል መዳከም ጀመረ። በላስታና በሸዋ እንዲሁም በትግሬ (የራስስሁል ሚካኤል መነሳት) ጠንካራም ባይሆን በለሆሳስ ራስ ገዝነት የመጀመረው በዚህ ንጉስ ጌዜ ነበር። የንጉሱ የቀደመ ሙሉ ሃይል በጎንደርና ጎጃም ተወስኖ ነበር[7]።
|
እቴጌ ምንትዋብ ከአማቷ፣ ሮማነወርቅ( የአጼ በካፋ እህት) ፣ ልጅ ምልማል እያሱ ጋር የምታደርገውም ግንኙነት ዳግማዊ እያሱን እጅግ ያስቆጣ ነበር። እቴጌ ምንትዋብ ከዚህ ከምልምል እያሱ ዘንድ 3 ልጆን ሴት ልጆችን ስታፈራ ከነዚህ ውስጥ አንዷ ወይዘሮ አስቴር ኢያሱ በመባል በቁንጅናዋ በታሪክ የምትታወቀው ነበረች። የእቴጌ ምንትዋብ ከአማቷ ልጅ ጋር መማገጥ በዘመኑ እጅግ ትልቅ ነውር የነበር ቢሆንም ንጉሱ ግማሽ እህቶቹን ይንከባከብ ነበር። አባታቸውን ግን ከመጥላቱ የተነሳ በ1742 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ከጣና ሃይቅ ዳርቻ ካለ ገደል ተወርውሮ እንዲሞት እንዳደረገ ይታመናል.[8] ።
|
ሞት
|
ዳግማዊ እያሱ ግንቦት 1755 ላይ በጸና ታመው በሚቀጥለው ወር ሞቱ። የምልማል እያሱ እህት በወንድሟ ሞት ንዴት መርዝ ሰጥታው እንደገደለቸው በጊዜው የታመነ ጉዳይ ነበር። እቴጌ ምንትዋብም ልጇን ለማስቀበር ከግምጃ ቤት ንዋይ ብትፈልግ ከጥቂት ዲናሮች በስተቀር ካዝናው ባዶ ሆኖ ተገኘ። በዚህ ያዘነቸው ምንትዋብ ሁሉን ትታ በቁስቋም ወዳሰራችው ቤተመንግስቷ ሄዳ ከጎንደር ለመራቅ ዛተች። ሆኖም ግን ጥቂት መኳንንት የልጅ ልጇ ኢዮአስ እንደራሴ ሆና እንድትቀጥል አሳመኗት።[9]
|
የምንትዋብ መዋኛ ወይም የምንትዋብ መታጠቢያበእቴጌ ምንትዋብ የተሰራ በፋሲል ግቢ ውስጥ ከምንትዋብ ግምብ አጠገብ የሚገኝ ቱርክ መታጠቢያ (ሐማም) ነበር። ስለሆነም ከህንጻው ስር ምድጃ ሲኖር፣ ውሃ በቱቦ ይገባለትና እንፋሎት እያተነነ የተለያዩ የሚሸቱ ቅጠሎች በላዩ ላይ እየተደረጉ ለህመም ፈውስ የሚገኝበት ክፍል ነበር። በዚህ መታጠቢያ ቤት የመጀመሪያው ክፍል እራቁትን ሆኖ ሰውነትን ለማሞቅ የሚያገለግል ሲሆን፣ ሁለተኛ የበለጠ ሰውነትን በማጋል ላብ የሚያስወጣ ነበር። ከዚህ ቀጥሎ በቅዝቃዛ ውሃ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መታጠብ ሂደቱን ያጠናቅቃል።
|
ምንትዋብ ግምብ በእቴጌ ምንትዋብ የተሰራ ሲሆን በፋሲል ግቢ ይገኛል።
|
ስዕል ቤት በደብረ ፀሐይ ቁስቋም የሚገኝ ክብ ህንጻ ሲሆን በዙሪያው አስራ ሁለት ክፍተቶች ነበሩት።
|
ሴቶች በወር አበባቸው ጊዜ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ መታገዳቸውን በማስመልከት እቴጌ ምንትዋብ (ብርሃን ሞገስ)፣ በየሰዓቱ (ለ12 ሰዓታት) እየሄደች ትጸልይበት ዘንድ አሰራችው። በሱዳን ደርቡሾች እስከተቃጠለ ጊዜ ድረስ፣ ህንጻው እጅግ ባማሩ ስዕሎችና ልዩ ልዩ የወርቅና የብር ጌጦች እንዲሁም በግምጃና ህብረ ቀለማዊ አልባሳት ያሸበረቀ ነበር። በዚህ ቦታ ከነበሩት ልዩ የዕደ ጥበብ ውጤቶችና አይን የሚስቡ ስዕላት አንጻር፣ ቤተ ስዕል ወይም ስዕል ቤት ተባለ። በ1879 የሱዳን ደርቡሾች አቃጠሉትና ሊፈርስ በቃ።
|
ደብረ ፀሐይ ቍስቋም ማርያም ከጎንደር ከተማ በስተ ስሜን ምዕራብ ወጣ ብሎ በሚገኘው በደብረ ፀሐይ ቁስቋም የተሰራ ቤተክርስቲያን ነው። ደብረ ፀሓይ ቁስቋም በእቴጌ ምንትዋብ፣ ከ1725 ዓ.ም. እስከ በ1738ዓ.ም. ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በጊዜው 360 መስታዎቶች የነበሩት፣ በቀይና ሰማያዊ ሃር አልባሳት ያሸበረቀ፣ እንደ ደብረ ብርሃን ስላሴ በጥሩ ኪነት የተዘጋጀ፣ ከወርቅና ከብር የተሰሩ የቤተ ክርስቲያን ማገልገያወች የነበሩት፣ በጊዜው የተደነቀ ቤተ ክርስቲያን ነበር። ደብረ ፀሐይ በተመሰረተበት ዘመን የራሱ ጉልት የነበረው ሲሆን ይኼውም በእብናት፣ በለሳ እና አርማጭሆ ተሰባጥሮ ይገኝ ነበር፤ ስለሆነም 260 ቀሳውስትን በስሩ ያስተዳድር ነበር፡፡ ከህንጻ ይዘቱ አንጻር በዚሁ ዘመን በምንትዋብ ከተገነባው ናርጋ ስላሴ ጋር ይመሳስል እንደንበር ግንዛቤ አለ።
|
የቁስቋም ግቢ ሦስት ጊዜ ጉዳት ደርሶበታል። በመጀመሪያ በ1858፣ ዓፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ሊያሰሩት ላሰቡት ቤተ ክርስቲያን ከቤተክርስቲያኑ የተለያዩ ንዋያትን መውሰዳቸው ነበር። ሁለተኛው ጉዳት የደረሰው በ1870ወች፣ ደርቡሾች ግቢውን በእሳት በማጋየት ያደረሱት ዋናው ጉዳት ነበር። በዚህ ቃጠሎ ቁስቋም ማርያም ሊፈርስ ችሏል። ቤተክርስቲያኑ አሁን የያዘውን ቅርጽ ያገኘው በጣሊያኖች ጊዜ ሲሆን ያሁኑ መልኩ ከድሮው እጅግ ይለያል። የእቴጌ ምንትዋብ፣ የልጇ ዳግማዊ እያሱ እና ልጅ ልጇ እዮዋስ አጥንቶች በመስታዎት ሳጥን ሆነው በዚህ ቤተክርስቲያን ይገኛሉ። ከእሳት የተረፉ የእቴጌ ምንትዋብ መገልገያዎች አሁን ድረስ በቤተክርስቲያኑ ይገኛሉ።
|
ታሪክ ወንግሥት፡ ብርሃን፡ ሞገሳ ፣ ታሪክ፡ ዘንጉሠ፡ ነገሥት፡ አድያም፡ ሰገድ በዘመናቸው በነበረው ፀሐፊ [[]] በግዕዝ እንደተጻፈና በኢኛትሲዮ ግዊዲ በ1895 ፣ በጣሊያን አገር እንደታተመ ከጎን ቀርቧል። ይህ የንግሥት ምንትዋብና የልጇን ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱን ዜና ውሎ ይተርካል። በተጨማሪ የዓፄ ኢያሱን ልጅ የዓፄ ኢዮአስን ዜና መዋዕል በተከታዩ ገጽኦች አካቶ ይዟል።
|
ናርጋ ስላሴ ከጣና ሐይቅ ደሴቶች በስፋቱ አንደኛ ከሆነው ደቅ ደሴት ላይ በምዕራባዊ ክፍሉ የሚገኝ ቤ/ክርስቲያን ነው።
|
ቤተክርስቲያን በእቴጌ ምንትዋብ 1700ወቹ መጨረሻ ላይ የተገነባ ሲሆን፣ እበሩ ላይ የሚታይቱት ስዕሎች የእቴጌ ምንትዋብና እንዲሁም ኢትዮጵያን በዚያው ዘመን ጎብኝቷት የነበረው የስኮትላንድ ተጓዥ ጄምስ ብሩስ (ሃኪም ይጋቤ) ናቸው።
|
እቴጌ ምንትዋብ በዙፋን ስሟ ብርሃን ሞገስ በ1698 ዓ.ም. ከአባቷ ደጅአዝማች መንበር እና እናቷ ልዕልት እንኮይ በቋራ፣ ጎንደር ስትወለድ የክርስትና ስሟ ወለተ ጊዮርጊስ ነበር። እናቷ ልዕልት እንኮይ ከዓፄ ሚናስ ዘር የምትወለድ እንደነበረች ይጠቀሳል[1]። ምንትዋብ በ18ኛው ክፍልዘመን ኢትዮጵያ ላይ ብዙ አሻራ ትታ የለፈች ንቁ፣ ሃይለኛና ተራማጅ መሪ ነበረች። ከባሏ ዓፄ በካፋ ዘመን ጀምሮ እስከ ልጇ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ እና ልጅ ልጇ ዓፄ እዮዋስ ዘመን ድረስ ለ40 አመታት የአገሪቱ እኩል መሪ የነበረች ናት። በዚህች መሪ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ የህንጻዎች ግንባታና የቤተክርስቲያን ድረሰት፣ እንዲሁም ስነ ጥበብ እድገት ታይቷል። በፋሲል ግቢ የመጨረሻውን ግንብ ያስገነባችው ምንትዋብ ነበረች። ከልጆቿ የእድሜ አናሳነትና እራሷም በሰራቻቸው አንድ አንድ ስህተቶች ምክንያት በስልጣን በነበረችበት ዘመን የነበረው እድገትና ሰላም እርሷ ስታልፍ አብሮ አለፏል። እንግዴህ አገሪቱ ወደ ዘመነ መሳፍንት የተሻገረችው ልክ እርሷ እንዳለፈች ነበር።
|
ዐፄ በካፋ
|
ከዐፄ በካፋ ጋር ስለመገናኘቷ
|
ዐፄ በካፋ በህዝብ ዘንድ ክብርን ካስገኘለት ስራው አንዱ ብዙ ጊዜውን በመሰዋት፣ እራሱን ደብቆ በግዛቱ ሁሉ እየተዘዋወረ ስህተት የተሰራውን ማቃናቱ ነበር። [2] በዚህ ሁኔታ አንድ ቀን ተደብቆ ከጣና ሃይቅ በስተ ምዕራብ ሲጓዝ ቋራ ላይ ወባ ታመመና ከአንድ ገበሬ ቤት አረፈ። የስኮትላንዱ ተጓዥ ሐኪም ይጋቤ ሲተርክ "ወጣቷ ምንትዋብ ከመጠን በላይ ቆንጆ፣ ተግባቢና ልዝብ" [3]የነበረች ሲሆን በካፋ ታሞ ያረፈበት ቤት ባለቤት ልጅ ነበረች[4]። ምንትዋብ ታማሚውን ንጉሥ ተንክባክባ ለጤንነት ስላበቃችው ጳጉሜ5፣ 1716 (እ.ኤ.አ) ላይ ወደ ጎንደር ከተማእንዳስመጣትና እንዳገባት ይዘግባል። በ1717 ዳግማዊ አጼ ኢያሱን ወለደች። ከዚህ በኋላ ለ2 አመት ጎንደር ከተማ ተቀምጣ በመካከሉ በ1718 ወደ ወልቃይት እንድትሄድ ተደረገ። ምንም እንኳ ከሁለት ወር በኋላ ብትመለስም ልጇ ግን ወደ ሰሜን ሽሬ፣ ትግሬ ተልኮ በዚያ እስከ 1730 መኖር ቀጠለ[5]።
|
የአጼ በካፋ መሞትና የምንትዋብ መንገሥ
|
አጼ በካፋ በ1722 ዓ.ም. ሲሞት የከተማው ህዝብ ሞቱን ሊቀበል አልቻለም። ለዚህ ምክንያቱ ከአሁን በፊት ንጉሱ ሳይሞት የሞተ በማስመሰል ህዝቡ ላይ ሽብር በመፍጠሩ ነበር። ምንትዋብም ባሏ ሲሞት የህዝቡን ጥርጣሬ በመጠቀም ውስጥ በማስገባትና ከቋራ አምስት ወንድሞቿ መጥተው የቤተመንግስት ስልጣን እስኪጨብጡና እስኪያረጋጉ ድረስ የንጉሱን ሞት ደብቃ ቆየች[6]። ከወንድሞቿ መምጣት በኋላ እርሷና ዘመዶቿ ሆነው የ 7 አመት ልጇን ኢያሱን ለማንገስ ቻሉ። ከ2 ወር በኋላ ታህሳስ 15፣ 1722 ላይ የልጇን ህጻን መሆን በማስታከክ እራሷ ላይ ዘውድ በመጫን በንግሥት ሥልጣን እንደራሴነቷን አሳወጀች[7]። ለሚቀጥሉት 40 አመታት እርሷና ወንድሟ ወልደ ልዑል ከንጉሥ ልጇና ልጅ ልጇ ጋር እኩል ተሰሚነት ኑሯቸው አገሪቱን ለማስተዳደር በቁ፡፡ አንዳንዶች ይህ በዝምድና የተተበተበ አመራርና ያስከተለው የዘር ፉክክር አገሪቱን ለዘመነ መሳፍንት ያበቃ ተግባር ነበር ሲሉ ይታዘባሉ[8]።
|
የምንትዋብ አስተዳደር
|
ምንትዋብና ልጇ ይከተሉት የነበረው ፖሊሲ ፊት ለፊት መጋፈጥ ሳይሆን እርቅንና መስማማትን ነበር። ለዚህ ተግባር እንዲረዳት፣ በጣም ቆንጆ የሚባሉ ሶስት ሴት ልጆቿን (ከበካፋ ሞት በኋላ ካገባችው ምልምል ኢያሱ የተወለዱ) በዘመኑ ኃይለኛ ለተባሉ የጎጥ መሪወች በመዳር (ወለተ እስራኤልን ለጎጃም ጦረኛ ደጃች ዮሴዴቅ ወልደ ሃቢብ (1751)፣ ወይዘሮ አልጣሽን ለሰሜን ባላባት ወልደ ሃዋርያት (የራስ Michael Sehul ልጅ)1747 እና ወይዘሮ አስቴርን ለትግሬ መሪ ራስማርያም ባሪያው1761) በመዳር በግዛቷ ስላም አስፍና ነበር[9]። ንግስቲቱ በማዕከላዊው መንግስት ሹም ሽረት ብታደርግም ራቅ ብለው የሚገኙት ክፍሎች ግን በራሳቸው እንዲተዳደሩ አድርጋ ነበር። የኦሮሞ ቡድኖች ወደ ሰሜን የሚያረጉትን ዘመቻ ስላቋረጡ በደቡብ በኩል መረጋጋት ተከስቶ ነበር። በሌላ ጎን፣ በደቡብ የተወሰዱ መሬቶችን ለማስመለስ ምንም አይነት ዘመቻ በዚህ ዘመን አልተካሄደም። ስለሆነም ከጊዜ ወደጊዜ ራቅ ያሉ ስፍራወች ኢ-ጥገኝነታቸው እየጎላ ሄደ። ከነበረው አጠቃላይ ሰላም አንጻር ልጇ እያሱ ወደ ሰሜን የሚያደርገው ዘመቻ የፖለቲካ ሳይሆን ለአደንና መሰል ክንውኖች ነበር[10]።
|
ምንትዋብና ያከናወነቻቸው ስራዎቿ
|
በልጇና በልጅ ልጇ ዘመናት ለ40 ዓመት ስትነግስ ያከናወናቸቻው ስራወች ብዙ ነበሩ። ምንትዋብ በባህሪዋ ተራማጅና ንቁ ነበረች። በቤተክርስቲያን ተነስቶ በነበረው የቅባት እና ተዋህዶ ክርክር ለማስታረቅ ያደረገችው ጥረት የተሳካ ነበር። ስለሆነም ከሞላ ጎደል በአስተዳደሯ ወቅት ሃይማኖታዊ ስላም ነግሶ ነበር።[11] ከሌሎች መንፈሳዊ ስራዎቿ ውስጥ ብዙ አብያተ-ክርስቲያናትንና ግንቦችን በማነጽ እንዲሁም በግሏ እየተከታተለች ድርሰቶችን በማስደረስ ስሟ ይጠቀሳል።
|
ቁስቋምን በደብረ ፀሐይ ስለመመስረቷ
|
እቴጌ ምንትዋብ በተለያዩ ምክንያቶች እራሷን ከጎንደር ከተማ ለማራቅ ጥረት አድርጋለች። የዚህ ጥረት ውጤት ከጎንደር ከተማ 3 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘውደብረ ፀሐይ (ቁስቋም) ያሰራቻቸው ህንጻወች ናቸው። የስኮትላንድ ተጓዥጄምስ ብሩስ (ሃኪም ይጋቤ) በኒህ ህንጻወች አንድ ክፍል ተሰጥቶት ይኖር ነበርና ስለቁስቋም ሲጽፍ 3 ፎቅ የሆነ ቤተመንግስት፣ ክብ የሆነ ቤተክርስቲያንና ብዙ የተለያዩ የሰራተኞችና ዘበኞች ቤቶች እንዲሁም ግብዣ ቤት በአንድ ማይል ዙርያ በታጠረ ግቢ ይኖር እንደነበር አስፍሯል[12]። እነዚህን ቤተመንግስቶችና ቤተክርስቲያኖች ከ1723 ጀምራ በማሰራት በ1732 ነበር ያስመረቀቻቸው[13]።
|
በግቢው ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን፣ ደብረ ፀሐይ ማርያም ይባላል። በጄምስ ብሩስ ግምት፣ ኢትዮጵያ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሃብታም የነበረና ብዙ ምርጥ ምስላትንና በወርቅና በብር የተሰሩ የቤተክርስቲያን መገልገያ ዕቃወችን የተመላ ነበር[14]። የተገነባውም በአናጢዎችመሪ በጅሮንድ ኢሳያስ እና አዛዥ ማሞ፣ አዛዥ ህርያቆሳና አዛዥ ናቡተ መሪነት ነበር። ቤተክርስቲያኑ በቀይ ሃር አሸብርቆ በዙሪያው 380 መስታውቶች ተተክለውት ብርቅርቅታው ጎንደር ከተማ ድረስ ይታይ ነበር[15]። ነገር ግን ቤተክርስቲያኑና ሌሎች በግቢው የነበሩ ህንጻወች በሱዳን ወራሪ መሃዲስቶች፣ በ1880 ተቃጠሉ። አሁን በጊቢው የሚገኘው ቤተክርስቲያን በዚህ ፍርስራሽ ላይ የተሰራ ነው።
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.