text
stringlengths
0
11.4k
በቤተሰብ ስምምነት በሚፈፀመው ሕጋዊ ጋብቻ ወቅት ተጋቢዎች በተጋቡ በሶስተኛው ቀን የሙሽራው ወላጆችና ቤተዘመድ በወንዱ ቤት ተሰባስበው የጉርሻ /ጊጫ/ ሥነ ሥርዓት በማከናወን ለሙሽሪት የተለያዩ ስጦታዎችን የሚሰጥበት ሥርዓት አለ። በዚህን ዕለት የሙሽራው ዘመድ አዝማድ በተገኘበት ሙሽራዎች /ወንዱ በስተቀኝ ሴቷ በስተግራ በመሆን/ ከተሰብሳቢዎች ፊት ለፊት ቁጢጥ ብለው የሚከናወነውን የጉርሻ /የስጦታ/ ሥነ ሥርዓት ለመፈፀም ይጠባበቃሉ። ጉርሻው /ስጦታው/ የሚጀመረው ከሙሽራው አባት ወይንም አባት ከሌለ ከተሰብሳቢዎች መካከል አንጋፋ ከሆነው ሰው ስለሆነ ሙሽሪት ቀደም ብላ በተዘጋጀችበት መሠረት ጉርሻውን /ስጦታውን/ ለመቀበል ወደ አባት ወይንም አንጋፋው ሰው ተጠርታ ትሄዳለች። በዚህ ሥነ ሥርዓት ወቅት ሙሽሪት ከወንዱ ቤተሰብ የምትፈልገውንና የምትጠብቀውን ስጦታ እስከምታገኝ ድረስ የሚሰጣትን ጉርሻ አትቀበልም። ስለዚህ በጥሪው መሠረት የልጁ አባት ወይንም አንጋፋው ቤተዘመድ አጉራሽ " ይህን ያህል ብር ሰጠሁሽ ይላታል። " እሷም " አይበቃኝም" ትላለች። በመቀጠል " ይህን ያህል መሬት ሰጠሁሽ" ይላል። አሁንም መልሳ “አይበቃኝም” ትላለች። ከዚያም "ይህንን ያህል ከብት ሰጠሁሽ" ሲላት አይበቃኝም አይበቃኝም " እያለች ከቆየች በኋላ ከአጉራሹ /ከስጦታ ሰጪ/ ዘንድ የምትፈልገውን ያህል ስጦታ ስታገኝ ጉርሻውን ትቀበላለች። በዚህ መልኩ የተሰበሰበውን ቤተ ዘመድ በሙሉ በማዳረስ ለጎጆ መውጫ የሚሆናትን በቂ ሀብትና ንብረት ታገኛለች።
በጌዴኦ ብሔረሰብ ቤት የአንድን ግለሰብ ወይም ቤተሰብ ማህበራዊ ደረጃ መገለጫ ስለሆነ ትልቅ ግምትና ክብር አለው። በብሔረሰቡ ባህል መሠረት አንድ ልጅ ካገባ በኋላ እስከ አንድ ዓመት ድረስ በአባቱ ወይም ወላጆቹ ቤት መቆየት ይችላል። ከአንድ አመት በኋላ ግን ደረጃውን የሚያስጠብቅ ቤት ሠርቶ መውጣት የግድ ነው። ጌዴኦዎች ቤት የሚሠሩት በአንድ አካባቢ ተሰባስቦ በመንደር መልክ ነው። በጌዴአዎች የተለያዩ የቤት ዓይነቶች ያሉ ሲሆን ዓይነታቸው የሚወሰነው ፡- በቅርፅ፣ በግንባታ፣ ቁሳቁስ፣ በክዳን ዓይነትና በሚሰጠው አገልግሎት ነው።
ዶጐዶ ለአጭር ጊዜ ለሚቆይ ዝግጅት የሚሆን ጊዜያዊ ቤት ነው። አገልግሉቱ ለጫጉላ ቤት፣ እህል ለመጠበቅ ባህላዊ በዓላት ለማክበር እና እንሰት ለመፋቅ ነው። ቅርፁ ክብ ሆኖ ከ4 ካሬ ሜትር የማይበልጥ ስፋትና ከ2 ሜትር የማይበልጥ ቁመት ያለው ነው። ከቀጫጭን ጭራሮ እንጨት፣ ከወፊቾ ገመድና በእንሰት ቅጠል ሊሠራ ይችላል።
የዚህን ዓይነት ቤት የሚሠሩት ሰዎች በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ፣ አዲስ ጐጆ ወጪዎች እና ከዋናው ቤት በተጨማሪ ለከብት ማደሪያነት የሚጠቀሙ ናቸው። ቤቱ ከቀርቀሃ፣ ከሸምበቆ ከወፎፊቾና ከሰምበሌጥ ሊሠራ ይችላል። የቤቱ የውስጥ አደረጃጀት በአብዛኛው ሁለት ክፍል ያለው ሲሆን በር ኖሮት መስኮት አይኖረውም።
የዚህ ቤት ዓይነት ረጅም ጊዜ ዝግጅት የሚጠይቅ ነው። ዝግጅቱ የመሥሪያ ቁሣቁስ በጥንቃቄ ይዘጋጃል፣ ለቤት ሠሪዎች ምግብ፣ እና በተለይ ከቁሳቁስ የምሰሶ መረጣ ትልቁን ጊዜ የሚወስዱ ተግባራት ናቸው። የዚህ ቤት የውስጥ አደረጃጀት ሲታይ ከሁለት በላይ ክፍሎች ሊኖሩት ይችላሉ፣ መስኮትና የጓሮ በር ይኖረዋል። የአዲች ሚኔ ቤት ሥራ ልዩ ባለሙያ ለምሰሶ መረጣ፣ ለሣር ክዳን ሥራ፣ የመሥሪያ ቦታ ማዘጋጀትና የምሰሶ ቅርፅ ማውጣት እንዲሁም ጣራ ማዋቀር የተለየ ባለሙያ ይፈልጋል።
ሌላው አራተኛ ዓይነት ቤት ሸካ (የቀርከሃ ቤት) ነው። የቤቱ ዓይነትና አሠራር ከዲቻ ማኔ ሆኖ ልዩነቱ ከቀርቀሃ ልባስ (ጳሻ) እና ከቀርከሃ የሚሠራ በመሆኑ ብቻ ነው። ቤቱ የሚታወቀው የደገኞች ቤት በመባል ነው። የቤቱ መዝጊያም ጭምር ቀርከሃ ሲሆን ከፍተኛ የቀርከሃ ጥበብ የሚታይበት ነው።
የብሔረሰቡ ዋነኛ ባህላዊ ምግብ «ቆÝ» ወይንም በብሔረሰቡ አጠራር «ዋሳ» ሲሆን ከዕለታዊ ምግብነቱ በተጨማሪ ለደስታም ሆነ ለሀዘን በተለያየ ዓይነት እየተዘጋጀ ከሌሎች የማባያ ዓይነቶች ጋር ይበላል። በስምንት የተለያዩ ባህላዊ አዘገጃጀት የሚዘጋጀው ቆÝ ከሚቆይበት ጊዜ አንፃር ፣ ከማበያው ዓይነት፣ እና ከሚጠቀመው ሰው አኳያ እንደሁኔታው እየታየ ይዘጋጃል። ከባህላዊ የቆÝ ምግብ ዓይነቶች አንዱ «ወእረሞ» የሚባል ሲሆን ብዙውን ጊዜ በኳስ ቅርጽ ተድበልብሎ ከገብስ ወይም ከበቆሎ ዱቄት ጋር በመደባለቅ የሚዘጋጅ፣ ለማንኛውም ዓይነት ዝግጅት የሚውል ከጐመን ወይንም ከስጋ ጋር የሚበላ ጣፋጭ ምግብ ነው።
ሌላው ተወዳጅ ምግብ «ኮፎ» በመባል የሚታወቅ ሲሆን አዘገጃጀቱ እንደ ዱቄት ሆኖ የተዘጋጀ ቆÝ ከገብስ ዱቄት ጋር በመደባለቅ የሚነኮር፣ በቅቤ እና ሌሎች ቅባት ነክ ነገሮች እንዲለሰልስ ተደርጐ የሚዘጋጅና፣ የተለየ ክብር ለሚሰጠው እንግዳ ወይንም ትላልቅ ሰዎች የሚቀርብ ነው። አንዳንዴም ይህን ምግብ ከአደንጓሬ ጋርም በመደባለቅ አዘጋጀተው ይጠቀሙታል። «ጣልታ» እና «ኬቦ» የተሰኙት የቆÝ ምግብ ዓይነቶች የመጠን ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ጠፍጠፍ ወይንም ሞልሞል ተደርገው በቀላሉ በአምባሻ መልክ የሚዘጋጁ ናቸው። «ሆጨቆ» ቆÝ ብቻውን በማድበልበል በመጠን አነስ ተደርጐ የሚዘጋጅ ከጐመን ጋር የሚቀቀል ጣፋጭ ምግብ ነው። «ቁንጭሣ» ደግሞ የቆÝ ዱቄት በምጣድ ላይ ተደርጐ ሲበስል እንደእንጀራ እየተቆረሰ የሚበላ ብዙ ማገዶ የማይፈጅ የዘወትር ባህላዊ ምግብ ነው። ኦጣ ርሞጦ የሚባለው ደግሞ ለረጅም ጊዜ ሳይበላሽ እንዲያገለግል በተለይም ለረጅም ጉዞና በጦርነት ወቅት ስንቅ እንዲሆን ታስቦ የሚዘጋጅ እንደ ድፎ ዳቦ ዓይነት ነው። ኮሣ /ጉንጃ/ በማድበልበል ጠቅለል ተደርጎ በእሣት ፍም ወይንም ትኩስ ረመጥ ላይ ተደርጎ ሲበስል የሚበላ ተዘውታሪ ምግብ ነው። በአጠቃላይ የቆÝ ምግብ በዓይነቱና በአቀራረቡ የተለያየ ቢሆንም ማባያዎቹም በዋናነት ጎመን፣ ወተትና ሥጋ ናቸው።
በጌዴኦ ብሔረሰብ ሰው ሲሞት ለየት ያለ ባህላዊ የለቅሶ ሥርዓት ይካሄዳል። በተለይ በተለይ ወጣት ወይንም አዛውንት የሆነ ሰው ሲሞት «ዘመድ አዝማድ ሣይሰበሰብ ከተቀበረ ጥሩ አይደለም» ተብሎ ስለሚታመን እስከ ሁለት ሶስት ቀናት ድረስ አስከሬን ሣይቀበር ሊቆይ ይችላል። ሕፃናት ሲሞቱ ግን አስከሬን በዕለቱ ይቀበራል፤ ሀዘኑም የዚያኑ ዕለት እንዲያበቃ ሽማግሌዎች ቤተሰቡን ይመክራሉ፤ የሐዘን ዳርቻ እንዲያደርግላቸውም ይመርቃሉ። የዕድሜ ባለፀጋ የሆነ ሰው ሲሞት የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ከተፈፀመበት እለት ጀምሮ የሚፈፀሙ የተለያዩ ባህላዊ የለቅሶ ሥርዓቶች አሉ። ሁሉም የየራሳቸው የአከባበር ሥርዓት አላቸው። ከነዚህ መካከል አንዱና የመጀመሪያው በብሔረሰቡ ቋንቋ «ዊልኢሻ» ይባላል። በዚህ የሐዘን መግለጫ ሥርዓት ሟች ከተቀበረበት ዕለት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የሟች ማንነትና ያከናወናቸው ሥራዎች፣ ለሕዝቡ የፈፀመው መልካም ተግባር፣ ለጋሽነቱ፣ ሀብቱ፣ የልጆች አባትነቱ፣ ርህሩህነቱ፣ ጀግና ከሆነ ጀግንነቱ እየተገለፀ፣ በግጥም እየተገጠመ፣ እየተጨፈረ ይለቀሳል። ዊልኢሻ ከአራት እስከ ስምንት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ማታ ማታ «ጋዳ» የተባለ የሀዘን ማስረሻ ዘፈን እና ጭፈራ ሐዘንተኞች ወይንም የሟች ቤተሰቦች እንዲሁም የአካባቢው ሕብረተሰብ ተሰባስበው ይጨፍራሉ። ጋዳ በሀዘን የተቆራመዱትን የሟች ዘመዶችና ቤተሰቦችን ከሀዘን ድባብ ለማውጣትና ለማጽናናት ማታ ማታ የሚከናወን ድራማዊ ጭፈራ ነው።
ከዚህም "በዊልኢሻ" የመጨረሻ ቀን ማታ ጀምሮ ልዩ ልዩ የተዝካር ዓይነቶች ይፈፀማሉ። የመጀመሪያው ተዝካር በብሔረሰቡ ቋንቋ /ሬንሽማ/ ሲከናወን የሚደረግ ዝግጅት ሲሆን «ሁጐ» የሚባለው ደግሞ የሟች ቤተሰብ ሙታንን የሚዘክሩበት፣ የሚያናግሩበት፣ የሟች እህት በባህል መሠረት የ«ኡማቶ» ሥርዓት በቀዳሚነት የምትፈፅምበት እንደሆነ ይነገራል። የመጀመሪያው የተዝካር ሥርዓት በተከናወነ ማግስት የቤትና የግቢ ፅዳት የሚደረግ ሲሆን ይህም «በዳኣ» ተብሎ ይጠራል። የመጨረሻው የተዝካር ዓይነት «አዋላ» በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህን ዕለት ከብት ታርዶ ከሟች የሥጋ ዘመድ በስተቀር ሌሎች የታረደውን ከብት ሥጋ በአካባቢው «ሀይቻ» አማካይነት የሚከፋፈሉበት ነው።
ከዊልኢሻ ቀጥሎ ያለው የለቅሶ ሥርዓት «ቡቺሣ» የሚባል ሲሆን በዚህ የለቅሶ ዓይነት ፆታን በመለየት የማስለቀስ ተግባር ይከናወናል። ሟች ሴት ከሆነች ውበቷን፣ የዋህነቷን፣ ለጋሽነቷን፣ ሙያዋን፣ እንግዳ ተቀባይነቷን ...ወዘተ እየጠቃቀሱ የለቅሶ ጭፈራ ይከናወናል። እንደዚሁም ሟች ወንድ ከሆነ ጀግንነቱን፣ ቤተሰባዊ አመጣጡን፣ ያከናወናቸውን ተግባራት /ክንውኖች/ ...ወዘተ የሚገልፁ ግጥሞችን በመደርደር ይለቀሣል፣ ይጨፈራል። ሟች ጀግና ከሆነ ለጀግንነቱ መለያ እንዲሆን «ዱፈኣ» ከተባለ ጥቁር እንጨት የሚዘጋጅ ረጅም ጊዜያዊ ሀውልት በመቃብሩ ላይ ተተክሎ በዊልአሻ ጊዜ ለጀግንነቱ መገለጫ ማቶት ተዘጋጅቶ የሰጎን ላባ ተሰክቶበት በመቃብሩ ላይ በተደረገው ጊዜያዊ ሀውልት ላይ ይንጠለጠላል። የሟችን «ሞቴ» የሚባል መቀመጫ እና «በራቴ» የሚባል የእንጨት ትራስ በመሰባበር እዚያው ሀውልት ስር በመታሰቢያነት በማስቀመጥ የሀዘን ፍፃሜ እንዲሆን ይደረጋል።
በጌዲኦ ብሔረሰብ ባህላዊ የለቅሶ ሥርዓት ደንብ መሠረት ለቅሶ የሚጠናቀቀው በአራተኛ ቀን ሲሆን ይህም ቀን ከሀጢያት የሚነፃበት ቀን ነው ተብሎ ይታመናል። በዚህን ዕለት የቤት ጠረጋ ሥርዓት ይከናወናል። በቤት ጠረጋው ቀን ከባልዋ ተጣልታ ወደ ወላጆቿ የመጣች ሴት ያለማንም አስታራቂ ከባሏ ጋር ተያይዛ ወደ ቤቷ ትሄዳለች። ከዚህ በተጨማሪ ዕለቱ የሟች ኑዛዜ ካለ በሕዝቡ ፊት ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቹ ተስማምተው እንዲኖሩ የሚመከሩበት የተጣላ ካለ የሚታረቅበት ዕለት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል።
ቅኔ፤ ግጥምና የተለያዩ ድርሰቶች ባጠቃላይ ሲጠሩ 'ሥነ ጽሑፍ' ይባላሉ። ሥነጽሑፍ የሚለው ሐረግ ጥሬ ትርጉም 'የጽሑፍ ውበት' ማለት ነው። ለሥነጽሑፍ ይህ ስያሜ የተሰጠበት አንዱ ምክንያት ድርሰቶች ሲጻፉ በቃል አመራረጥ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን፤ ሥነ ጽሑፍ መዋብ እንደሚገባው ለመግለጽ ጭምር ይመስለኛል።
ቃል፤ በተለይ ባገራችን አያሌ ቋንቋዎች ስላሉ፤ ባንዱ ቋንቋ አንድ ትርጉም ሲኖረው ይኸው ቃል በሌላው ቋንቋ ሌላ ትርጉም የሚይዝበት አጋጣሚ አለ። ያም ቃል ንባቡን እንዳያጠፋ በቃል አመራረጥ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
ለምሳሌ በቅኔ ቤት 'ወገረ' የሚለው የግዕዝ ቃል በትግርኛ ሌላ ትርጉም፤ ማለት ከሴት መገናኘትን ያመለክታል ስለሚባል ቃሉ በቅኔ ውስጥ ከገባ ጸያፍ ነው ይባል ነበር።
ሌላ ምሳሌ፤ 'በዳዳ' ለሚለው የኦሮምኛ ስም 'ደ' የሚለው ያማርኛ ሆሄ ድምፅ የኦሮምኛውን ድምፅ በትክክል እንደማያሰማ ይታወቃል። ነገር ግን ስለቸገረን ለተባለው ድምፅ ይህንኑ ሆሄ በመጠቀማችን ሌላ የቃል መመሳሰል አስከትሏል። ትክክለኛውን የኦሮምኛውን ድምጽ ካልን ግን የተባለው መመሳሰል አይኖርም።
እዚህ ላይ ለፊደሉ እንደ 'ቨ' ሌላ ሆሄ ከመቅረጽ ሌላ፤ ስም በሌላ አይተካም። ልክ 'በ'ን ወደ 'ቨ' እንደቀየሩ 'ደ' አናት ላይ ሰረዝ በማድረግ ለምን አዲስ ሆሄ በፊደላችን ላይ እንደማይጨምሩ አይገባኝም። ይህን ነገር በልጅነቴ ያየሁት ይመስለኛል። ለምን እስከ ዛሬ እንዳላዳበሩት ወይም ለተባለው ድምፅ ሌላ ሆሄ እንዳልተቀረጸለት አይገባኝም። ሰረዙ ከ'ደ' አናት ላይ ቢደረግ ከ'ጀ' ጋር ስለሚመሳሰል ከ'ደ' ግርጌም ቢያደርጉት ችግር ያለው አይመስለኝም። ለማንኛውም ነገሩ መደረግ ያለበት በጥናት ስለሆነ እግረ መንገዴን ለባለሙያዎች ጥቆማ ለማድረግ ነው።
በልጅነታችን 'ቁራ ቆላ ወረደ'፤ 'በቅል ጥሬ ኳኳ' የመሳሰሉትን ሐረጎች ቶሎ ቶሎ ደጋግማችሁ በሉ እየተባልን በሚያስከትለው ሌላ ትርጓሜ በታላላቆቻችን ይሳቅብን ነበር። እንዲህ ያለው የምድጃ ዳር ጨዋታ እንደ እንቆቅልሹና ተረት ተረቱ ሁሉ ማታ ማታ በጊዜ የሚመጣውን እንቅልፍ ስለሚያበርርልን እንወደው ነበር። ጨዋታው ግን ቃላት ሲከታተሉ ሌላ ትርጉም የሚያመጡበት ጊዜ ስላለ ጥንቃቄ እንድናደርግ ትምህርትም ይሰጣል።
ቃልና ቃል ሲናበቡም (ሲገናኙም) ሌላ ትርጉም ያስከትላሉ። አሁንም በቅኔ ቤት 'ልብ' የሚለው ቃል 'ዳዊት' ከሚለው ስም ጋር አይናበብም። በሌላ አነጋገር 'ልበ ዳዊት' (የዳዊት ልብ) አይባልም። ከተባለም ሌላ ትርጉም ያስከትላል።
በደርግ ጊዜ አንድ አቀንቃኝ (ስሟን ዘነጋሁት) ርዕሰ ብሔር መንግሥቱ ኃይለማርያምን ለማወደስ ይመስላል፤ '... ልበ ደንዳና' እያለች ስትዘፍን በሬዲዮና በቴሌቪዥን እንሰማ ነበር። በተለይ ወደ ዘፈኑ መጨረሻ ይህን ሐረግ ደጋግማ ስትዘፍነው እሷ ልብ ያላለችውን ቃል ስሰማ "ይቺ ሰው ሃይ የሚላትም የለ?" እል ነበር። ግጥሙን ያዘጋጀው ሌላ ሰው ከሆነም በዚህ በኩል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገው ነበር። የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎቹም አውቀው ይሁን ሳያውቁ ዝም ብለው ያዘፍኑት ነበር። ምናልባት አውቀው ከሆነም እገዳም ቢያደርጉ ውዳሴውን ከሚፈልጉት ወገኖች ጣጣ እንዳይመጣባቸው ፈርተው ይሆናል።
ከዚሁ ከቃል ማናበብ ሳንወጣ አሁንም በቅኔ ቤት 'እም' የሚለው የግዕዝ ቃል 'ፍጥረት' ከሚለው ቃል ጋር አይናበብም። በሌላ አነጋገር እምፍጥረት አይባልም። እንደዚህ ብሎ ከተቀኘም ቅኔው ላይ ንፍጡን ተናፈጠበት ተብሎ ቅኔው ይነቀፋል። በሌላ አነጋአገር 'እምፍ' ብሎ ተናፈጠበት ማለት ነው። አሁንም 'እም' የሚለው የግዕዝ ቃል ከ'ስ፣ ሥ' ሆሄያት ጋር አይናበብም። ለምሳሌ 'እም' የሚለው የግዕዝ ቃል ከ'ሥጋ' ጋር አይናበብም። በሌላ አነጋገር 'እም ሥጋ' አይባልም። ከተባለም ሌላ አነጋገር ወይም ቃል ብቅ ይላል። የዚህ ዓይነት ሌሎችም አሉ።
እንግዲህ የቀደሙ አባቶች (በተለይ የቅኔ መምህራን) በሥነጽሑፍ ባሕላቸው፤ ንባብን ለማሳመር ምን ያህል እንደሚጠነቀቁ አየን። ቅኔ የሚያስደስተው በይዘቱና በምስጢሩ ብቻ አይደለም። በቃላት አሰካኩም ጭምር እንጂ!
ባማርኛ አነጋገራችንም፤ ባህል ስለሚያስገድደን እነዚህን ከፆታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቃላት በግልጽ ላለመጥራት 'አባለ ዘር፤ ብልት፤ ሩካቤ ሥጋ፤ ፍትወተ ሥጋ፤ ተገናኘ፤ አወቀ፤ ወዘተ ...' በማለት አነጋገራችንን እናሳምራለን። እንደነ አቶ ሰሎሞን ዴሬሳ ያሉ ዘመናውያን ገጣሚዎች ደግሞ እነዚህን ድብቅ ቃላት በግልፅ እንድንጠራቸው ድፍረቱ እንዲኖረን በግጥማቸው ቃሉን እየጠሩ ያደፋፍራሉ። ተከታይ ካገኙ መልካም ነው። ነገር ግን ይህ አካሔድ በኛ ሕብረተሰብ ከባህል ያፈነገጠ ይመስለኛል። እንደእምነታችንም አዳምና ሔዋንም ራቁትነታቸውን ሲያውቁ ቶሎ ብለው በቅጠል የሸፈኑት እነዚህኑ አባለ ዘራቸውን ነው። ካልጠፋ ቃል ቃሉም በቃል ቢሸፈን ጥሩ ይመስለኛል።
ከላይ ባቀረቡት ጽሑፍዎ ላይ የኦሮምኛውን ቃል "በዳዳ" በግዕዝ/አማርኛ ፊደል መጻፍ ይቻላል። እርስዎ የጠቀሷት የኦሮምኛ ድምፅ በአብዛኞቹ ዩኒኮድ የኮምፒዩተር ፊደላት ውስጥ ተካታለች። ፊደሏም እርስዎ እንዳሰቧት በ'ደ' አናት ላይ ቅጥያ በመስራት የተፈጠረች ነች። ከተፈጠረች ረዘም ያሉ ዓመታትን አስቆጥራለች፤ ምናልባትም ከ12 ዓመታት በላይ አልፈዋል። ፊደሏና ዘርዎችዋም የሚከተሉት ናቸው፤ ዸ ዹ ዺ ዻ ዼ ዽ ዾ። ከላይ የጠቀሱትን ስም 'በዻዻ' ብሎ በመጻፉ ትክክለኛውን ድምፅ ማውጣት ይቻላል።
ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነ በቀለ ገርባ ክስ ላይ ተጠርተው ሳይገኙ በቀሩ ምስክሮች ላይ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ተበተነ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ አራተኛ የወንጀል ምድብ ችሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች በእነ አቶ በቀለ ገርባ መዝገብ ለተከሰሱ ታሳሪዎች ለምስክርነት ተጠርተው ባልቀረቡ ምስክሮች ላይ ትዕዛዝ ያስተላልፋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ለሌላ ጊዜ በቀጠሮ ተበተነ፡፡
ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ለተከሰሱ 22 ታሳሪዎች ምስክር እንዲሆኑ የተጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቢይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የለገዳዲ ከንቲባ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒንና የዕድሜ ልክ እስር ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት የቀድሞ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር የነበሩት አቶ አንዷለም አራጌ ምስክርነት ለመስማት ከታህሳስ 17 ቀን 2010 ዓ.ም. እስከ ታሀሳስ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዞ ነበር፡፡
ነገር ግን ከትናንት ወዲያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ለፍርድ ቤቱ በአክብሮት በላከው ደብዳቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥራ መደራረብ ምክንያት ለምስክርነት መቅረብ እንዳልቻሉ ጠቅሶ ተለዋጭ ቀን ጠይቆ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በተመሳሳይ የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ከኦሮሚያ ክልል ለምስክርነት የተጠሩ የሥራ ኃላፊዎች በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እያደረጉ በመሆኑ መገኘት ስለማይችሉ ተለዋጭ ቀን እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን በአክብሮት ጠይቀው ነበር፡፡ አቶ አንዷለምም መቅረብ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ለምስክርነት የተጠሩት የሥራ ኃላፊዎች የተቀጠሩበት ቀን እስከዛሬ ታህሳስ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ስለሆነ ቀኑ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ጠብቆ ትዕዛዝ እንደሚያሳልፍ ገልጾ ነበር፡፡ ይህ ቀን ዛሬ ላይ ቢጠናቀቅም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ለመስጠት ለታህሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ ተበትኗል፡፡
ኣብ ውሽጢ ስርዓት ርክብ ህዝብን መንግስትን ቅድመ ግንባር ብምዃን፣ ኣብ መንጎ መንግስትን ህዝብን ቕልጡፍን ውፅኢታውን ኮሙኒኬሽን ክህሉ ብምግባር ኣብ ክልላውን ሃገራውን ቀንዲ ጉዳያት ብሄራዊ ምርድዳእ ብምፍጣር ኣብ ምህናፅ ሰናይ ምስሊ እዛ ሃገር መተካእታ ዘይብሉ እጃም ምፍፃም፡፡
ኣብዚ ክልል ቅልጡፍ፣ ውፅኢታውን ክብፃሕ ዝኽእል ስርዓት ርክብ ህዝቢ (ኮሙኒኬሽን) ብምህናፅ መንግስትን ህዝብን ብሓበሬታ ተረባሕቲ ብምግባር ሓደ ፖለቲካዊን ኢኮኖምያዊን ማሕበረሰብ ንምህናፅ ኣብ ዝግበር ፃዕሪ ዝጉልህ ኣስተዋፅኦ ምውፋይ
“አሁን የምሰራበት…ከአንድ ሰዓት ተኩል የመኪና ጉዞ በኃላ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ነው። እ..እ.. እ..ና “እዚያ ሆስፒታል ውስጥ ለግዜው የምሰራው በሽተኞች ሲመጡ ተራ ማስያዝ ነው። በቃ ማለት ማሰለፍ።”
መጋቢት ፳፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፹፱ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፷፩ ቀናት ይቀራሉ።
፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ፣ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተብለው በንጉሠ ነገሥት ዙፋን ተቀመጡ፡፡
፲፱፻፵ ዓ.ም - የእንስሳት ሕክምና ባለሙያውና የግዕዝ ፊደላትን በኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲቻል ያደረጉት ምሁር ዶ/ር ኣበራ ሞላ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
፲፱፻፳፪ ዓ/ም - ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በነገሡ በአሥራ ሦሥት ዓመት ተኩል በ፶፬ ዓመት ዕድሜያቸው ዐረፉ። የሞታቸው ዜና እንደተሰማም በከተማው የሐዘን ጥላ አጠላበት። አባታቸው ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በተቀበሩበት በታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
1437ኛው የኢድ አል አድኻ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲከበር ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፤ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከተፈረደባቸው የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል ስድስቱ በቅርቡ የተለቀቁት በእነርሱ ጥያቄና ጥረት እንደሆነ፤ ጥያቄአቸው ምላሽ በማግኘቱና ጥረታቸው በመሳካቱ መደሰታቸውን ገልጸው፤ ለመንግሥት ምሥጋና ማቅረባቸውን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ከስፍራው ባስተላላፈው ዘገባ አሰምቶናል። ወያኔ ግዜና ወቅት እየጠበቀ የሚጠቀምባት የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ የይቅርታ ካርድ በሌላ መንገድና መልክ ተመዘዘች ማለት ነው።
ይቅርታ መጠየቃቸው ተሰምቶ ሳይፈቱ ዓመታት ያስቆጠሩ፤ በአንጻሩ ይቅርታ መጠየቅ ቀርቶ በፍርድ ቤቱ እምነት የለንም በማለት የፍርድ ማቅለያ አስተያየት አናቀርብም ያሉ ይቅርታ ጠየቁ ተብሎ ሲፈቱ፤ እንዲሁም ወራት በፈጀ የሽምግልና ጥረት የተፈቱ ፖለቲከኞች ወያኔ የጭንቁን ግዜ ሲያልፍ ክዶ፤ ሽምግልና ብሎ ነገር የለም በሕግና በሕግ ብቻ ነው የተፈቱት፤ … ወዘተ እያለ በይቅርታ ፖለቲካ ሲቆመር አይተናል ሰምተናል።
ወያኔዎች ይህን የሚፈጽሙት የይቅርታ ሥነ ሥርዓት አዋጁ ከጠረጴዛቸው ላይ ተቀምጦ ጻፋችሁኝ እንጂ አታውቁኝም፣ አወጃችሁኝ እንጂ አትተገብሩኝም እያለ እንዳያፌዝባቸው፣ ሌላውም ሰው አውቆትና ተረድቶ እንዳይጠይቅ መሳቢያ ውስጥ ቆልፈው ነው። በመሆኑም በየደረጃው በትንሽም በትልቅም ኃላፊነት ላይ ያሉ የሚሠሩት ሕጉን አውቀው ሳይሆን በአለቆቻቸው የሚታዘዙትን ነው። ከተቀዋሚውም በአብዛኛው የሚሰማው ጩኸትም ሆነ ተቃውሞ ወያኔ ከሚሠራውና ከሚናገረው በመነሳት እንጂ አዋጁን መሰረት ባደረገ አይደለም።
ይቅርታ ምንድን ነው? ማነው የሚጠይቀው የሚጠየቀውስ? መቼና እንዴትስ ነው የሚጠየቀው? የሚሉትን ጥያቄዎች ምላሽ ማወቅ ወያኔ ይቅርታን የፖለቲካ መቆመሪያ ካርታ አድርጎ እየሠራበት መሆኑን በበቂ ማረጋገጥ ያስችላል። እናም ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ የአዋጅ ቁጥር 395/1996 አንቀጾችን ለማሳየት እሞክራለሁ።
የይቅርታ ጥያቄ ማለት፤ ይህ ዐዋጅ ትርጓሜ በሚለው ክፍሉ አንቀጽ 4 “የይቅርታ ጥያቄ ማለት አንድ ፍርድ በሙሉ ወይንም በከፊል ቀሪ እንዲሆን ወይም የቅጣቱ አፈፃፀምና አይነት በቀላል ሁኔታ እንዲፈፀም የሚቀርብ ነው” በማለት ይተረጉማል። በአንቀጽ 2(3) ደግሞ “ፍርድ ማለት በወንጀል ጉዳይ በፍ/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ የተወሰነ ዋና ቅጣት፣ ተጨማሪ ቅጣት ወይንም የጥንቃቄና ጥበቃ ውሳኔ ነው” ይላል።
የይቅርታ ጥያቄ የሚቀርበው በማን ነው? ስለ ይቅርታ ጥያቄ አቀራረብ የሚገልፀው የዐዋጁ ክፍል፤ ስድስት ንዑሳን አንቀጾች ያሉት ሲሆን፣ ንዑስ አንቀጽ 1 “በወንጀል ጉዳይ በፍ/ቤት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ የተፈረደበት ማንኛውም ሰው፣ የተወሰነው ፍርድ በሕግ ይቅርታ የሚያስከለክል ካልሆነ በስተቀር የይቅርታ ጥያቄውን ራሱ ወይንም በባለቤቱ፣ በቅርብ ዘመዶቹ፣ በወኪሉ ወይም በጠበቃው አማካኝነት ማቅረብ ይችላል” ይላል።
ይህ አንቀጽ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮችን መያዙን ልብ ማለት ያሻል። ይሄውም አንደኛ የይቅርታ ጥያቄው መቅረብ የሚችለው ከመጨረሻ ፍርድ በኋላ መሆኑንና ሁለተኛ ጥያቄው በማን እንደሚቀርብ በግልፅ የሚያሳይ መሆኑን።
የዐዋጅ አንቀጽ 12(2) ደግሞ የፍትሕ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን፣ ይቅርታ ሊደረግላቸው የሚገባቸውን ሰዎች በመምረጥ የይቅርታ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ ይገልፃል።
ይቅርታ የሚጠየቀው መቼ ነው? የይቅርታ ጥያቄ መቼ እንደሚቀርብ ግልፅ የሚያደርገውና ይህንኑ ብቻ የሚገልፀው አንቀጽ 14(1) ፍርዱ ከተሰጠ በኋላ በማናቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል በማለት በማያሻማ ሁኔታ በግልፅ አስፍሯል።
የይቅርታ ጥያቄ የሚቀርበው ለማን ነው? የይቅርታ ጥያቄ የሚቀርበው የይቅርታ ቦርድ (ኮሚሽን) ተብሎ ለተሰየመው ተቋም ሲሆን፣ የሱ ተግባርም በአዋጁ አንቀጽ 4(1) የይቅርታ ጥያቄውን በመመርመር የውሳኔ ሃሳብ ለፕሬዝዳንቱ ማቅረብ እንደሆነ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል።
ይቅርታ የሚሰጠው ማነው? ይቅርታ መስጠትም ሆነ መንሳት ብሎም የተሰጠን ይቅርታ ማንሳት በአዋጅ ሳይሆን በሕገ መንግሥቱ ሥልጣን የተሰጠው ለፕሬዝዳንቱ ነው። የሕጎች ሁሉ የበላይ የሚባለው (የሚባለው ያልኩት በተግባር የሕጎች ሁሉ የበላይ መሆን ቀርቶ የባለሥልጣናትም የበ