Proverb
stringlengths 4
244
|
---|
ግፍ ሲቆም፤ ጸልት አያሻም። |
ግፍ ሲናኝ፥ ኩበት ሰጥሞ ድንጋይ ይዋኝ። ግፍ ሲናኝ፥ ኩበት ሲጠልቅ ድንጋይ ይዋኝ። ግፍ በአገር ሲሞላ፥ ርስ በርስ ያባላ። |
ግፍ በአገር ሲናኝ፥ ኩበት ይጠልቃል ድንጋይ ይዋኛል። ግፍ በአገር ሲናኝ፥ ኩበት ጠልቆ ድንጋይ ይዋኝ። |
ግፍ አይቀርም፤ ስም አይቀበርም። |
ግፍ አይፈሬ መሬት፥ እንክርዳድ ያበቅላል። ግፍ የላለበት ጠላ፥ ያለ ብቅል ይበስላል። ግፍ የተሠራብን በእኛ፤ ካሱ ይሉናል በዳኛ። |
ግፍስ በባሕር ይመላል፤ አሣ አሣውን ያበቅላል። (ያበቅላል ~ ይበላል) ጎልማሳ በሚስቱ፤ ንጉሥ በሠራዊቱ። |
ጎልማሳ ቢታጠቅ ከደረቱ፥ ሲሮጥ ከጉልበቱ። |
ጎልማሳ እበቀለበት ላም አይማረክም፥ ሽማግላ እበቀለበት ነገር አይሳሳትም። ጎልማሳ፥ እንደ በላ አንበሳ። |
ጎልማሳ ከአለበት ከብት አይሰረቅ፤ ሽማግላ ከዋለበት ነገር አይነጠቅ። ጎልማሳ ከአለበት ከብት አይነጠቅ፤ ሽማግላ ከዋለበት ነገር አይወድቅ። ጎመን ለአጡለት፥ ሀር ቀደደለት። |
ጎመን በጤና። |
ጎመን ባወጣው ነፍስ፥ ቂጥጥ አለች ገብስ። ጎመን ባወጣው ነፍስ፥ አትኩራ ገብስ። ጎመን ጠነዚ፥ ሴት ከበዚ። |
ጎረምሳ እንደበላህ፥ አንሣ። (አንሣ ~ አግሳ) ጎረቤት አያውቅ ነገር፤ ወንጠፍት አያጠራው አሰር። ጎረቤት የላለው፥ አንባሮ የለው። |
ጎረቤት ይሆናል ጠላት፥ ያችን ሴት አትንጊ በሎት። ጎረቤት ጤና ይደር፥ አንተ ጤና እንድታድር። ጎረቤትህን ሲያማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ። |
ጎረቤት፥ ይሆናል ጠላት። |
ጎራዳ ለወንበዳ፤ ሱቅ ለነጋዳ። ጎራዳህ ጎመዳም፤ ሚስትህ አመዳም። |
ጎራዳና ምስጥ፥ ውስጥ ለውስጥ። |
ጎርፍ ሲወስድ እያያሳሣቀ፥ ተንኮለኛ ሰው ሲጎዳ እየተራቀቀ ነው። ጎሽ ለልጇ (ስትል) ተወጋች። |
ጎሽ ለልጇ (ብላ) ትወጋ። |
ጎሽ ላይሉኝ ወሶ፥ ደርሼ ነበር እረጋ ለቅሶ። |
ጎሽ ጠመድኩ ይሆናል ብዬ፥ ፈትቼ ሰደድኩ አይሆንም ብዬ። (ይሆናል ~ ይሆነኛል) |
ጎበዝ ጎበዝ ቢሎት፥ የባሎን መጽሀፍ አጠበች። |
ጎበዝ:_ ፊት ሰማይ ሰማይ ያያል፥ ኋላ ምድር ምድር ያያል። ጎባጣን ሲቀብሩ፥ እንደ አመሉ። |
ጎበዝ፥ ስለ በለስ። |
ጎበዝ፥ አደባባይ አያንቧትርም፥ እበረሓም አይለቅም። ጎበዝ ዳኛ፥ ቆይቶ አራጋቢ ይሆናል። |
ጎባጣን ቀንና፥ ቅዝምዝምን አጎንብሰህ እሳልፈው። ጎባጣን እንዳት ይቀብሩ፥ ቢሉ እንዳመሉ። |
ጎባጣን ይቀብሩ፥ እንደ ምግባሩ። (ይቀብሩ ~ ይቅበሩ) ጎኑ ቀኜ፤ ቀኑ ለእኔ። |
ጎኑ የእኔ፤ ቀኑ ሠኔ። |
ጎንደሬ ሲናገር፥ እንን ሸዌ ጎጃሜም አይሰማው። ጎንደር ወጣህ፥ ምን ይህ መጣህ? |
ጎንደር ወጣሽ፥ ምን አመጣሽ? ጎንደር ወጣሽ፥ ምንድር አመጣሽ? ጎንደር ወጣ፥ ምን ይዝ መጣ? ጎንደርን በመከራ፤ ጎጃምን በከራ። ጎዳ ከብት፥ ከቀንዳም ይብሳል። ጎዳናና መንገድ፤ ጉንጉንና ገመድ። ጎዳው ፍየል፥ ቀንዳሙን ወጋው። ጎድል ነበር ሞላ፤ ሞልቶ ነበር ፈላ። ጎጃም ሲያምጥ፤ በጌምድርን በፍልጥ። ጎጃም በነበ፥ ሳይንት እህል ሆነ። ጎጆ ወጭ ሙሽራ፥ በገፍ ወጥ ትሠራ። |
ጐረሮ የሚውጠውን፥ እጅ ይመጥነዋል። ጉረኛ ዕውር ቴላቭዥን ይገዚል። |
ጠላ ሲሉት ሽምጥጥ፤ ኮሶ ሲሉት ስቅጥጥ። ጠላ በማቶቱ፤ እንጀራ በላማቱ። |
ጠላ ቢመላ ሦስት ነገር ያጠፋል። መጀመሪያ አፍ ያሞጠሙጣል፤ ኹለተኛ እርሱ ይፈሳል፤ ሦስተኛ ልብስ ያበላሻል። |
ጠላ ባለቤቱን አያውቅም። |
ጠላ ከማቶት፤ እንጀራ ከላማት። ጠላ ከአሰከረው፥ ወተት ያሰከረው። ጠላ ከአሥር፤ ነገር ከአገር። |
ጠላ የባዕድ፥ አሳላፊ መድ። |
ጠላ ያለ አተላ፤ ጠጅ ያለ አንቡላ። ጠላሽ መለኛ፤ ወወኛ። |
ጠላሽ በቀጠነ፤ ዳቦሽ ባረረ። |
ጠላቴን ሳማ፥ እኔ እጎዳለኹ እንጂ እሱ አይጎዳም። ጠላት ሲነሣብህ፥ የወዳጆችህን ቁጥር አበርክት። ጠላት ሳይነቀል፥ ሰብል አይለቀም። |
ጠላት በጥርስ ሲገኛ፥ (እባክህ) አታስጎምጀኛ። ጠላት በጥርስ ሲገኝ። |
ጠላት ቢያብሉት፥ ወዳጅ አይሆንም። (ቢያብሉት ~ ቢያባብሉት) ጠላት ባጭር ታጥቆ፤ ገር ነቅንቆ ። (ነቅንቆ ~ ነጥቆ) |
ጠላት ከውጭ አይመጣም። |
ጠላት የላለው፥ ወዳጅ አያሻውም። ጠላት ያማል፤ ወዳጅ ይወቅሳል። ጠላት ያነቃል፥ ያተጋል። |
ጠላት ይገፋል ዱቃላ፤ ረኃብ ይከላል ባቄላ፤ ቀን ያሳልፋል ነጠላ። ጠላት ይገፋል ዱቃላ፤ ወራት ይገፋል ባቄላ፤ ያግደረድራል ነጠላ። ጠላትህን ውሃ ሲወስደው፥ እንትፍ ብለህ ጨምርበት። |
ጠላት፥ ይቀባል፥ ጥላት። |
ጠላትን በጦር፤ አባትን መጦር። |
ጠላትህን የምትጠነቀቀው አንድ ጊዛ፤ ወዳጅህን የምትጠነቀቀው ኹል ጊዛ። ጠላትን ለማግኘት ሲጎረጉሩ፥ በወዳጅ ይጀምሩ። |
ጠላና ወጥ ያነሰው፥ ደረቅ። ጠላና ዝና ዕለቱን አይደርስም። |
ጠላና ጉተና፥ በአንድ ቀን አይደርስም። ጠላና ጉተና ዕለቱን አይደርስም። |
ጠላኝ ማለት ያስጠላል፤ ልግደል ማለት ያስገድላል። ጠላው ሳይገባ፥ ማቶቱ። |
ጠላው ሳይገባ ማቶቱ፤ ቀንደ ሳይገባ ጅራቱ። ጠላው አልበጀ፤ ቅራሪው ሰው ፈጀ። |
ጠላው የባዕድ፥ አሳላፊው መድ። ጠላዬ በቀጠነ፤ ቆልዬ ባረረ ማሩኝ። ጠልቶ ለጠላት፤ አስሮ ለእስራት። ጠመንጃ ራሱ ገድል፥ ራሱ ይጮሀል። |
ጠመንጃ ያለ ጥይት ደላ፤ ወንድ ያለ ሴት ቀውላላ። ጠመደና በሬና ዝኆን፥ መቸም እንዳይሆን። ጠማማ ሰው፥ ክፋትን ከዅሉ ያደርሳል። |
ጠማማ ዚፍ፥ በየጊዛው ከአልቀና አይስተካከልም። ጠረፍ ያለ ባላንጣ፥ ቤት ያለ ጣጣ። |
ጠሪታው፥ ወይ ባዩን አስቆጣው። ጠርሙስ በልታ። |
ጠርቦ ለደጁ፤ ፈርድ ለልጁ። |
ጠርጥር፥ በገንፎ ውስጥ እንዳለ ሥንጥር። ጠርጥር፥ ከምግቡ ውስጥ አለ ሥንጥር። ጠርጥር፥ ከገንፎም አለ ሥንጥር። |
ጠቋሚ ከእናሪያ ይመጣል፤ አጥፊ ከጉልበት ይወጣል። ጠቋሚ ጠቃሚ። |
ጠበቃ ታፈጀ፤ በርበሬ ታረጀ። |
ጠበቃና ቅል፥ ባጠገብ ይውላል። (ይውላል ~ ይውል) ጠበንጃ፥ ራሱ መቶ፥ ራሱ ይጮሀል። |
ጠቢብ፥ ይበላል በገል። |
ጠባ ለኪዳን፤ መሸ ለቁርባን። |
ጠባቂ ያላት በግ፥ ላቷን እደጅ ታሳድራለች። ጠባቂ ያላት በግ፥ ላቷ እደጅ ያድራል። ጠባብ አልጋ፥ የግድ ያስተቃቅፋል። |
ጠባብ አልጋ፥ ያለውድ ያስተቃቅፍ። ጠባብ የወፍ ቤት፥ በግድ ያስተቃቅፋል። |
ጠባዩ ያውሬ፤ መልኩ የበሬ። ጠባይ ሲደረጅ፥ ባሕርይ ይሆናል። ጠብ ያለሽ በዳቦ። |
ጠብ ባለበት ቤት፥ ድሮ (ከቆጥ) ትሞት። ጠብ ተጀመረ፤ አንበሳ ላምን ሰበረ። |
ጠብ ተጀመረ፤ ያ ልጅሽ አለ? ልጄ ሲል የነበረ። ጠብ ከአለበት ቤት፤ ድሮ ከጋጥ ትሞት። |
ጠብ የሻ መኮንን፥ አምጡ ይላል የድሮ ሻኛ። ጠብ ያለበት፤ ቤት ድሮ ትሞት። |
ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም። ጠንቋይ ለራሱ አያውቅ፥ ለአዋይ። |
ጠንቋይ ባያሳምን፥ ያጠራጥራል። (ያጠራጥራል ~ ያጠራጥር) ጠንቋይ ባያሳምንም፥ ያጠራጥራል። |
ጠንቋይ፥ አባይ ቤት ያስፈታል። ጠዋት ሽሮ፤ ማታ ድሮ። |
ጠዋት ከበላተኛ፤ ማታ ከአድመኛ። ጠዋት ከበላተኛ፤ ማታ ከጦመኛ። ጠዋት ከጀንበር፤ ማታ ከጨንገር። ጠዋት ከጾመኛ፤ ማታ ከአድመኛ። ጠዋት ጆሮ፤ ማታ ጆሮ። |
ጠያቂ ባይኖር፥ ዅሉ መምህር። |
ጠያቂ የለም እንጂ፥ ከድሀ ምክር ይገኛል። ጠይቆ ከማፈር፤ ወድቆ መሰበር። |
ጠይብ፥ በገል ይበላል። |
ጠጅ ለወረት፤ ወዳጅ ለችግር ዕለት። |
ጠጅ ለጨዋ ልጅ መጫወቻው፤ ለባለጌ ልጅ መማቻው። (ለባለጌ ~ ለድሀ) ጠጅ በብርላ፤ ነገር በምሳላ። |
ጠጅ በብርላ፤ ዛማ በሃላ። ጠጅ የላለበት አበጋዝነት። |
ጠጅ የወረት፤ ወዳጅ የበላ ዕለት። ጠጅ የጠጣ ከሰረ፤ ውሃ የጠጣ ከበረ። |
ጠጅ ይሻላል በመጠኑ፤ የጨዋ ልጅ ይበልጣል በቀጭኑ። ጠጅና መኮንን፤ ድሀና ጎመን። |
ጠገብኹ ያለውን ብላ አትበለው፤ ፈራኹ ያለውን ድፈር አትበለው። ጠጉረ ሉጫ፤ አይነ መጭማጫ። |
ጠጉራም ውሻ አለ፥ ሲሉት ይሞታል። ጠፍር መጫኛ፤ ቁርበት መገኛ። |
ጠፍር በሉታ ብትኼድ፥ ልም በሉታ መጣች። ጡት መጥባት፥ የእናት። |
ጡጥም ከፈስ ተቆጠረች። |
ጢም የላለው መምህር፤ አጸድ የላለው ደብር (አምሮም አያምር)። ጢምህን እጠላለኹ፤ መሳምህን እወዳለኹ። |
ጢሰኛ ሲቆይ፥ ባለርስት ይሆናል። ጣል በደጅ፤ እሰር በፍንጅ። |
ጣል በግድ፤ እሰር በግንድ። ጣመኝ ድገመኝ። |
ጣት ገማ ብል፥ ቆርጦ አይጣልም። ጣዝማ ሰርሳሪ፤ ዳኛ መርማሪ። |
ጣዝማ ይሰረስራል፤ ዳኛ ይመረምራል። ጣይ ብልጭ ሲል፤ ወፍ ጭጭ ሲል። ጣይ ያየውን፥ ሰው ሳያየው አይቀርም። ጣጣ ፈንጣጣ። |
ጣጣ ፈንጣጣ፤ ድንጋይ ፈለጣ። |
ጣፊያ ቢነሧት፥ ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች። ጣፋጭ ፍቅር ሲያረጅ፥ ፍቅረኞችን ያፋጅ። ጤና ከሀብት፤ ወፍጮ ከከብት አይቆጠርም። ጤፍ መፍሰስሽን ቢያይ፥ ገበሬ ባልራሽ። ጤፍ ቢሰኩ፤ ሰማይን ቢያኩ አይገኝም ልኩ። ጤፍ አይቆላ፤ የጨዋ ልጅ አይጠላ። |
ጤፍ አጎደለ፤ ቢለው ገብስ እንዳይሰማ አለው። ጤፍ ከአላረሙ አይለማ፤ ሥጋ ከአልሰነበተ አይገማ። ጤፍ ከአቅሙ፥ እንክርዳድ ከፈለ። |
ጤፍ ከመዶ፥ ጎታ ትሞላ። (ትሞላ ~ ትሞላለች) ጥለውት የመጡትን ደኛ፥ ዙረው አያዩትም። ጥላና ሸኝ ቤት አይገቡም። |
ጥል ያለሽ፥ በዳቦ። |
ጥል ያጠላላ፤ ኮሶ ለአፍ ይጠላ። ጥልቅ ብዬን፥ ውሃ ወሰዳት። |
ጥልቅ ጥብቅ ሀሳቡና ነገሩ፤ ጠባዩና ግብሩ። |
ጥምድ እንደ በሬ፤ ቅንት እንደ ገበሬ። |
ጥምጥም የላለው መምህር፤ አጸድ የላለው ደብር። |
ጥሩ መስል አተላ፤ ፍሬ መስል ገለባ። ጥሩ እንደ ብርላ፤ ቀይ እንደ በርበሬ። ጥሩ ከአደፍ። |
ጥሩ ወዳጅ፤ ጥሩ ጠላት፤ ጥሩ ጠላት፤ ጥሩ ወዳጅ ይሆናል። ጥሩ ድህነት፤ ጥሩ ነጻነት፤ ጥሩ ሀብት፤ መልካም ርስት። ጥሩ ጠላት፤ ጥኑ ወዳጅ ይሆናል። |
ጥሩ ወዳጅ፥ ጠላት ይሆናል። ጥሩ ወዳጅ፤ ጥሩ ጠላት ይሆናል። |
Subsets and Splits