Proverb
stringlengths
4
244
ፀሓይ ያየውን፥ ሰው ሳያየው አይቀርም። ፀሓይና ንጉሥ ሳለ፥ ዅሉም አለ። ፀሓይና ጣውንት መልክ ያጠፋል። ፀሓይን በእጅ መከለል።
ፈላ ገነፈለ፤ ተሞላ ጎደለ።
ፈረሰኛ የወሰደው(ን)፥ እግረኛ አይመልሰው(ም) ፈረሰኛ ሲሮጥ፥ እግረኛን ምን አቆመው? ፈረሰኛ ሲሸሽ፥ እግረኛን ምን አመጣው? ፈረሰኛ ሲሸሽ፥ እግረኛ ምን ይቆማል?
ፈረሱም ይኸው፤ ሜዳውም ይኸው። ፈረስ ለጦርነነት፤ በቅል ለጌትነት።
ፈረስ መውጣት፥ የማያውቅ እጥፍ ይ዗ላል። ፈረስ ሲያጠብቅ፥ ል጑ም አይለቀቅ።
ፈረስ በራሪ፤ በቅል ሰጋሪ። ፈረስ ቢያነክስ፤ አህያ ታጉዝ።
ፈረስ ቢጠፋው፥ ኮርቻውን ገልቦ አየ። ፈረስ አውቃለኹ፤ ስገታ እወድቃለኹ። ፈረስ የጠፋው፥ ኮርቻ ገልብጦ አየ። ፈረስ ያደርሳል እንጂ፥ አይዋጋም።
ፈረስ ጥል ይደነግጣል፤ በቅል ጥል ይረግጣል። ፈረስና ገብስ ያጣላል።
ፈረንጆች እንደመርፌ ይገቡ፥ እንደ ዋርካ ይሰፉ። ፈሩ ፈሩ፥ ማጀት አሩ።
ፈሪ ለሀገሩ። ፈሪ ለእናቱ።
ፈሪ ለእናቱ ይገባል።
ፈሪ ለእናቱ፤ ጀግና ለጀግንነቱ።
ፈሪ ቢሸፍት፥ እስከ ጑ሮ።
ፈሪ እንዳይሉኝ አንድ ገደልኹ፥ ጀግናም እንዳይሉኝ አልደገምኹ። ፈሪ፥ ከላይ ቢል፥ እኔ አለኹ አለ።
ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢኛ፥ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ። (ቢኛ ~ ቢተኛ) ፈሪና ንፉግ እያደር ይቆጨዋል።
ፈሪ፥ ለ዗መቻ መጣስ? ቀረስ? ( ምን ያጎድላል)። ፈሪ፥ በገዚ ጠቡ፥ ገላጋይ ይሆናል።
ፈሪ፥ ከአልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል። ፈሪ፥ ከአልጋ ላይ ይወድቃል። ፈሪ፥ ከውሃ ውስጥ ያልበዋል። ፈሪ፥ ውሃ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል።
ፈሪ፥ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል። ፈሪ፥ የእናቱ ልጅ ነው።
ፈሪን ከውሃ ውስጥ ያልበዋል። (ከውሃ ~ ውሃ) ፈሪን የገዚ ጥላው ያሯሩጠዋል።
ፈርተው ድንጋይ ሲጥሉ፥ ጅብ ወጣ ከደሩ። (ሲጥሉ ~ ቢወረውሩ ~ ቢጥሉ) ፈርቶ ድንጋይ ቢጥሉ፥ ጅብ ወጣ ከደር።
ፈስ በወረንጦ እየተለቀመ ነው። ፈስ ያለበት ቂጥ፥ ዝላይ አይችልም። ፈስ ያለበት፥ ዝላይ አይችልም። ፈስቶ፥ ቂጥን መያዝ።
ፈሷን ፈስታ፥ ቂጧን ጨበጠች።
ፈቅደሽ ከተደፋሽ፥ ቢረግጡሽ አይክፋሽ።
ፈትል ሲረዳዳ፥ አንበሳ ያስራል። (ያስራል ~ ያስቀራል) ፈትል ቢያብር፥ አንበሳ ያስር። (ያሥር ~ ያስራል) ፈንድሻ፥ ሲቆሉት ድምፅ፥ ሲበሉት ድምፅ።
ፈክሮ መሸሽ፥ ታሪክ ያበላሻል። ፈዚዚ፥ እያንቀላፋ ይገባል ፈፋ።
ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ፥ እስኪበርድ ይራበኝ። ፈገግታ፥ የልብ አለኝታ።
ፈጣሪን የሚያህል ጌታ፥ ርስትን ያህል ቦታ። (ርስትን ~ ገነትን) ፈጥነው የገመደት፥ ፈጥኖ ይበጠሳል።
ፈጥኖ መስጠት፥ ቶል ለመጸጸት። ፈጭታ የነበረች፥ ላመልማል ኮራች። ፉት ቢሉ፥ ጭልጥ።
ፈጥኖ መስጠት፥ ኋላ ለመጸጸት። (ለመጸጸት ~ ለማጣት) ፈጥኖ መስጠት፥ በኋላ መጸጸት።
ፊተኛው ወዳጅህን፥ በምን ቀበርከው? በሻሽ፥ ኋለኛው እንዳይሸሽ። ፊት፥ በላህ ፍትፍት።
ፊት ከወጣ ጆሮ፥ ኋላ የበቀለ ቀንድ በለጠ።
ፊት ወዳጅህን በምን ቀበርከው? በሻሽ፥ የኋለኛው እንዳይሸሽ። ፊት የበሰለውን ወፍ ይበላው፤ ቀድሞ የተናገረውን ሰው ይጠላው። ፊት የተናገረን ሰው ይጠላው፤ ፊት የደረሰን ወፍ ይበላው።
ፊት የወጣን ጆሮ፥ ኋላ የበቀለ ቀንድ በለጠው።
ፊት የደረሰን ወፍ ይበላው፤ ፊት የተናገረን ሰው ይጠላው። ፊት ያልፈጁት፥ ነገር ያፋጃል።
ፊት ያሞጠሙጧል፥ ኋላ ይስሟል። (ይስሟል ~ ይፏጯል) ፊት ጆሮ ይፈጠራል፥ ኋላ ቀንድ ይበቅላል።
ፊት፥ አንቺ አንቺ፥ ኋላ እንቺ እንቺ። ፊት አይቶ የማያዳላ፥ መምህርና መካሪ።
ፊደልን የአወቀ፥ ዅሉን አስለቀቀ። ፋሲል ሲፈርስ፥ ጎንደር ይታረስ።
ፋሲካ የላለው ጦም፤ ደስታ የላለው አለም። ፋሲካን ሉያገኙ፥ ሐዳዳን ይመኙ።
ፋቂ ቁርበቱን፤ አናጢ ዕንጨቱን። ፋኖ ቢሰማራ፥ ከጠላት ሉበላ። ፌቆ ስት዗ል፥ አትፈራ ገደል።
ፌንጣ ብትቆጣ፥ (አንድ) እግሯን ታጣ። ፌንጣ ብትቆጣ፥ እግሯን ጥላ ኼደች። ፌንጣ፥ አቅሟን አታውቅ ትንጣጣ። ፍላጎት አይረግፍም፥ ካልከሰሙ እንደፍም። ፍልፈል ሳትጠረጥር፥ አጥር አትመነጥር። ፍረድ ለነፍስህ፤ ብላ ለከርስህ።
ፍሪክና ጻድቅ አይቀጣጠርም። ፍሬ ለመብል፤ ሥንቅ ባገልግል።
ፍሬ በመስጠቱ ባልታወቀ ሾላ፥ የወፎች ዝማሬ ቀደመ አሉ። ፍሬ ፍሬ ላይ ቆሞ፥ ጎተራ ይሞላል።
ፍርሀቴ ለእናቴ አለች ጫጩት። ፍርሀት ሲመጣ፥ ዚቢያ ቆረጣ። ፍርሀት የናላ ነው፥ ከቁም ይጥላል። ፍርደ ገምዳይ፤ እውነት አጉዳይ።
ፍርድ ለልጅ፤ ጥራቢ ለደጅ። (ጥራቢ ~ ጥራጊ) ፍርድ ለተቀማጭ፤ ወጥ ለቀላዋጭ።
ፍርድ ልበስ የእኔ ጌታ፥ አሽከር አስነሣኝ ከገበታ። ፍርድ ሲ጑ደል፥ ድሀ ሲበደል።
ፍርድ እንደ አሉላ፤ ጽድቅ እንደ ላሉበላ።
ፍርድ ጎደለ፥ ድሀ ተበደለ የሚል ንጉሥ አይታጣ። ፍርድና ፍትፍት በየፊት። (በየፊት ~ ወደፊት)
ፍቅር መያዣ የላለውን የሰውን ልብ ማሰሪያ ገመድ ነው። ፍቅር ሲጠና፥ ቆል ያ጑ርሣል።
ፍቅር በደልን ዅሉ ይፍቃል። ፍቅር እንደሞት፥ ጽኑ ናት። ፍቅር ካለ፥ ቡጢ ራት ነው።
ፍቅር ካለ፥ ዗ጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል። ፍቅር ካለ፥ የቁንጫ ቆዳ ለሦስት ሰው ይበቃል። ፍቅር ያመናቅር።
ፍቅር ያሰከረው፥ ነግቶም ያገረሻል።
ፍቅር ያስራል፤ ዕውቀት ያስከብራል፤ ጥበብ ያኮራል። ፍቅር ያስራል፤ ዕውቀት ያኮራል፤ ጥበብ ያስከብራል። ፍቅር ይታወቃል፥ በእግር።
ፍቅር ፍቅር ሲሉ፥ ድሀ ሆነው ቀሩ።
ፍቅርና ጉርሻ ከአላስጨነቀ አያምርም። ፍቅርና ጦር ይጥላል ከአጥር።
ፍቅርን የአገኘ፥ ስምምነትን፥ ስምምነትን የአገኘ ድልን። ፍትፍቱን አሳይቶ፥ እበቱን አጎረሠኝ።
ፍቅርህን የፈለገ ልጅህን፥ ጥልህን የፈለገ የላም ልጅህን። ፍቅርና ድን኱ን፥ የትም ይተከላል።
ፍትፍት ለልጅ፤ ጥራጊ ለደጅ።
ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ።
ፍንጥር ፍንጥር እንደ ሽንብራ፥ ያባ ምን ይዋብ ፉከራ። ፍየል ኹለት ወልዳ፥ አንደ ለመጽሀፍ፥ አንደ ለወናፍ። ፍየል ለአምስት፤ ድሮ ለባልና ለሚስት።
ፍየል ልጅ እወልዳለኹ ብላ፥ ባል የሚሆናትን ወለደች። ፍየል መሀል ግመል።
ፍየል መንታ ትወልድ፥ አንደ ለወናፍ፥ አንደ ለመጽሀፍ። ፍየል መንታ ወልዳ፥ አንደ ለመጽሀፍ፥ አንደ ለወናፍ። ፍየል ሲሰባ፥ ሾተል ይልሳል።
ፍየል ሲቀናጣ፥ እናቱን ይሰርራል።
ፍየል በልታ፥ በበግ አሳበበች። (አሳበበች ~ አበሰች) ፍየል በግርግር፥ እናቱን ይሰርር። (ይሰርር ~ ይሰርራል) ፍየል ብትመነኩስም፥ መቀነጣጠሷን አትተውም። ፍየል ከመድረሷ፥ ቅጠል መበጠሷ።
ፍየል ከቀ዗ነ፤ ዱያቆን ከ዗ፈነ፥ አይድንም ይሞታል እየመነመነ። ፍየል ወዱህ፥ ቅዝምዝም ወዱያ።
ፍየል ከቀ዗ነ፤ ዱያቆን ከ዗ፈነ።
ፍየል የለኝ፥ ከነብር አልጣላ።
ፍየል ፈጁን አውሬ፥ ፍየል አርደህ ያ዗ው። ፍየል(ም) የለኝ፥ ከነብር ምን አጣላኝ። ፍየልና ምን እየረገሙት ይረባል።
ፍየልና ቀበሮ፤ ምጥማጥና ድሮ።
ፍየልና የከተማ ሰው፥ ዝናብና ጭቃ አይወድም። ፍየሎን እንደበግ።
ፍዳ ለኀጥአን፤ እሴት ለጻድቃን።
ፍጥም አያናግር፤ የጎርፍ ሙላት አያሻግር። ፍጥም አፍራሽ፤ ቤተክርስቲያን ተ኱ሽ። ፍጥም ያቆማል፤ እርቅ ይጠቀልላል። ፍጥም ያዋውላል፤ አቧራ ያስላል።
ፎክሮ መሸሽ፥ ታሪክ ያበላሽ። (ያበላሽ ~ ያበላሻል)
ፖለቲካ በደቦ፤ ክብር በአግቦ። ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ።
኱ስ ለራስሽ ስትይ ጎል ግቢ፥ አለዙያ ፎሪ ብለው ይጠልዙሻል።
኱ደሬ በንጉሥ፤ መበለት በቄስ መቅናት አይችልም።
ዘላለም ከመፍሳት፥ አንዳ መቅ዗ን።
ዘመነ ግርምቢጥ:_ ውሻ ወደ ሰርድ፥ አህያ ወደ ሉጥ።
዗መናይ ቅል ድንጋይ ይሰብራል።
዗መኔ፥ ከሸማኔ መወርወሪያ ይቸኩላል።
዗መን ሲበላሽ፥ አይጥ መጥረቢያ ይቆረጥማል።
዗መን እንደ ንጉሡ፤ አውድማ እንደ ንፋሱ።
዗መን የሚወልደውን፤ ንጉሥ የሚፈርደውን የሚያውቅ የለም።
዗መን የሚወልደውን፤ ንጉሥ የሚፈርደውን።
ዘመን የሰጠው ቅል፥ ድንጋይ ይሰብራል።
ዘመን የወለደው፤ ንጉሥ የወደደው።
ዘመን ያነሣው ቅል፥ ድንጋይ ይሰብራል።
ዘመን ያነሣው ታላቅ ዛማ፥ ዕንቅርት ያፈርጣል።
዗መደ ብዙ፥ ጠላሽ ቀጭን ነው።
ዘመደ ብዙ፥ ጠላው ቀጭን ነው።
዗መደን የሚያማ፥ ገማ።
዗መደን ያማ፤ (ለ)ራሱ ገማ።
዗መደን ያማ፥ ገማ።
዗መድ ሲፈራ፤ ላሉበላ ሲኮራ።
዗መድ በየወንዙ ይርባ።
዗መድ በ዗መደ አይጨክንም ሆደ።
዗መድ ቢረዳዳ፥ ምን ችጋር ሉጎዳ?
዗መድ ቢረዳዳ፥ ችግርም ባልጎዳ። (ባልጎዳ ~ አይጎዳ)
዗መድ ከ዗መደ፤ አህያ ከአመደ።
዗መድ የላለው፥ ቁስል ይገድለዋል።
዗መድ ያረጀ፥ በልቶ ያፈጀ።