Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet
doc_id
stringlengths
1
5
text
stringlengths
42
393k
1
በትግራይ ደቡባዊ ዞን ጫት በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ። በትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያና አዘቦ ወረዳ በመስኖ በሚለማ የእርሻ መሬት የጫት ተክል በአሳሳቢ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ መሆኑን የራያ ሸለቆ የተቀናጀ እርሻ ልማት እህፈት ቤትና የወረዳው ፖሊስ አስታወቁ ። የእህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ተስፋይ ኪዳኔ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጹት ከ5 አመት በፊት አርሶ አደሮች በመስኖ ውሃ ሰብልና ፍራፍሬዎችን ያለሙበት የነበረው መሬት በአሁኑ ወቅት በጫት ተክል እየተሸፈነ ነው ። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አቶ ገብረህይወት ሀጎስ በበኩላቸው ጫት ጋ ተያይዘው በወረዳው የሚፈጠሩ ወንጀሎችን ለመከላከል በተካሄደው ትናት ከአምስት አመታት በፊት በአርሶ አደሩ ዘንድ እምብዛም የማይታወቀው የጫት ተክል በአሁኑ ሰአት በ54 ሄክታር መሬት ላይ መስፋፋቱ ተረጋግጧል ብለዋል ። በወረዳው በጫት ምርት የተሳተፉ ከአንድ ሺ በላይ አርሶ አደሮችም በአመት እስከ 10ሺ ብር የሚደርስ ገቢ እያስገኘላቸው በመሆኑ ምርቱን የማስፋፋት አዝማሚያ ጎልቶ እየታየ መሆኑን አዛዡ ገልጸዋል ። የፖሊስ የጥናት ውጤት እንዳመለከተውም በራያና አዘቦ ወረዳ ብቻ ከ12ሺ በላይ ቻት ቃሚዎች የሚገኙ ሲሆን ከቃሚዎች ቁጥር መጨመር ተያየዞ የወንጀል ድርጊቶችም በአሳሳቢ ሁኔታ መበራከቱን አዛዡ ገልጸዋል ። ከማይጨው ማዘጋጃ ቤት የቀረጥ ሰራተኞች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከቀረጥ ለማምለጥ በህገወጥ መንገድ የሚያልፈውን ሳይጨምር በየቀኑ እስከ 20 ኩንታል ቻት ወደ ማይጨው ፣ መቀሌና ሌሎች የክልሉ ከተሞች እየተላከ ነው ።
10
የጫት ንግድና አጠቃቀምን ህግ ሊወጣ ነው 2015 0 262 197 5 አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11 2007 ዋኢማ የጫት ንግድና አጠቃቀምን ስርአት ለማስያዝ የሚያስችል ረቂቅ ህግ እየተጠናቀቀ መሆኑን የምግብ፣መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ ። በህገወጥ የምግብ፣መድሃኒትና ጤና አገልግሎት ቁጥጥር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰሞኑን በሎግያ ከተማ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ እንዳስታወቁት ወጣቱ ትውልድ ስትራቴጂካዊ ሀይል በመሆኑ ከጫት፣ሲጋራና አልኮል ሱስ ነፃ የሆነ ልማታዊ ትዉልድ ማፍራት ይገባል። በተለይ ከፍተኛ አመራሩ፣የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶች ራሳቸዉን ከዚህ ሱስ ነፃ በማድረግ ህብረተሰቡን በማስተማር የመሪነት ሚና መጫወት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ጫት ያለው ንጥረ ነገር በሰዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ጠቁመው፤እንደካንስር፣ጉበት፣የመርሳት ችግር፣ስንፈተወሲብና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮችን እያስከተለ እንደሚገኝ አስረድተዋል ። መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት በማስገባት ከ2003 ጀምሮ የጫት ንግድና አጠቃቀምን ስርአት ለማስያዝ የሚየስችል ህግ ለማዉጣት ረቂቁ ተጠናቆ በቅርቡ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል ። ሲጋራም ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ማጨስን የሚከለክል አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ካለፈዉ 2006 ጀምሮ የሀገሪቱ ህግ አካል ሆኖ በፓርላማ የፀደቀ በመሆኑ፤ በሂደት አቅርቦቱን መቀነስ የሚያስችል እርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን መግላቸውን
11
በጫት ምርት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ሊጣል ነው 2012 0 228 170 5 አዲስ አበባ ሰኔ 292004ዋኢማ በጫት ምርት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ለመጣል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምርት ቤት ቀርቦ ውይይት ተካሂደበት። ቀደም ሲል የምርቱ ሽያጭ ይካሔድ የነበረው መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመሆኑና አብዛኞቹ ነጋዴዎችም በቋሚነት የሚታወቁበት ስፍራ ስለሌላቸው በቀረጥ አሰባሰቡ ላይ ችግር ፈጥሯል። ሁኔታውን ለማረምም ቀደም ሲል የነበረውን የጫት ግብር በኤክሳይዝ ታክስ እንዲተካ ለማድረግ የሚያስችለው ይኸው ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ ለበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል። በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢንቨስትመንት ረቂቅ አዋጅን ለማሻሻልና የወጪ ንግድ የቀረጥ ማሰባሰቢያ ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ወደሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።
12
የባሕር ዳር አርሶ አደሮች ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 302011ዓም አብመድ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጎርደማ አካባቢ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲያለሙት የነበረውን ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ አርሶ አደሮቹ ጫት እያስከተለ ያለውን ማኅበራዊ ጉዳት በመረዳት ነው ከማሳቸው በማስወገድ በሌላ ጠቃሚ ሰብልና የጓሮ አትክልት ለመተካት እንቅስቃሴ የጀመሩት፡፡ ዛሬ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጫት ማስወገድ የጀመሩት አቶ ሙስጦፋ ታደሰ የተባሉ የጎርደማ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፤ ሌሎችም የእርሳቸውን አርዓያነት እንደሚከተሉ ይጠበቃል፡፡ ጫት በባሕር ዳር አካባቢ ማኅበራዊ ችግር እየሆነ መምጣቱን በመጥቀስ በርካቶች መፍትሔ እንዲሰጠው ሲጠይቁ መኖራቸውን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
13
ጫት ጫት ወይንም በርጫ፡ በርጫ በምስራቅ አፍሪካና በየመን የተለመደ ቅጠል ነው። የጫትን ቅጠል በማኘክ ምርቃና የሚባል ቃሚዎቹ ተወዳጅ ስሜት ነው የሚሉት ላይ መድረስ ይቻላል። ይህ የሚሆነው ጫት ውስጥ ያሉት ንጥረ ነግሮች ኣንጎል ላይ በሚፈጥሩት ለውጥ ሲሆን የጫት ወይም ጅማ የስነ ፍጥረት ስሙ በእንግሊዝኛ Catha edulis ነው። ጫት የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ይባላል። የጫት ዝርያዎች በኤትዮጵያ ወስጥ በተለያዪ ክፍለ ሃገራት ይገኛል። እንደየአገሩም የጫት የተክሉ ዓይነት እና በወስጡ ያለው ንጥረ ነገር ጥንካሬ የምርቃና ሃይል ይለያያል። በሃረር እና በአካባቢው የሚገኝ የጫት ዓይነት ዓወዳይ የሚባል ሲሆን ቅርንጫፎቹ ረጃጅም ቅጠሉ ደግሞ ሰፋ ያለ ከሌሎች የጫት ዓይነቶች ጋር ሲተያይ በወንዶ ገነት አካባቢ የሚገኘው ደግሞ ወንዶ ገነት የሚባል ሲሆን የማስከር የምርቃና ሃይሉ ከዓወዳይ እንደሚበልጥ ይነገራል። የተክሉ ዓይነት፡ ቅርንጫፎቹ ቀጫጭን እና አጫጭር፣ ቅጠሉም ቀጠን ብሎ ዓወዳይን ያህል ወዝ የሌለው። ጫት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልላት በተለያየ አይነት መልኩ በመቃም ላይ ይገኛል። ለአብነትም በአማራ ክልል ውስጥ በጎንደር ባህርዳርና አካባቢዎቹ የጫት አቃቃምም ሆነ አሰፋፈሩ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በፍፁም ይለያል ይኅውም በሌላው የሀገራችን ክፍል ጫት ከነ ገረባው ወይም እንጨቱ በአነስተኛ ፕላስቲክ ተደርጎ ሲሸጥ በጎንደር ባህርዳርና አካባቢዎቹ ግን የጫቱ ቅጠል ሊቃም ከሚችል የጫቱ ለስላሳ የግንድ ክፍል ጋር ተቀንጥሶ በሚዛን ከ25 ግራም ጀምሮ እስከ ብዙ ኪሎዎች ይሸጣል። ብዙ ጊዜ ጫት መቃም ከጥቅሙ ጉዳቱ ቢብስም አንዳንድ ጥናቶች ግን ጫት ልክ እንደመድሀኒትም ያገለግላል ይላሉ። ጫት አትኩሮትን ሙሉ በሙሉ ሰርቆ ትውስታን በመንጠቅ ህይወትን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚከታት Attention Deflict Disorder ከተባለው በሽታ ነፃ እንደሚያወጣ ይነገራል።
2
የባሕር ዳር ዙሪያ አርሶአደሮች ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጎርደማ አካባቢ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲያለሙት የነበረውን ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ አርሶ አደሮቹ ጫት እያስከተለ ያለውን ማኅበራዊ ጉዳት በመረዳት ነው ከማሳቸው በማስወገድ በሌላ ጠቃሚ ሰብልና የጓሮ አትክልት ለመተካት እንቅስቃሴ የጀመሩት፡፡ ዛሬ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጫት ማስወገድ የጀመሩት አቶ ምስጦፋ ታደሰ የተባሉ የጎርደማ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፤ ሌሎችም የእርሳቸውን አርዓያነት እንደሚከተሉ ይጠበቃል፡፡ ጫት በባሕር ዳር አካባቢ ማኅበራዊ ችግር እየሆነ መምጣቱን በመጥቀስ በርካቶች መፍትሔ እንዲሰጠው ሲጠይቁ መኖራቸውን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
3
ጫት እንዴት ሊጠፋ ይችላል ጫት በማምረት የሚተዳደሩ እጅግ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ጫትን በማምረት ልጆቻቸዉን ያስተምራሉ፤ቤተሰባቸዉን ያስተዳድራሉ እንዲሁም ህይዎታቸዉን ይመራሉ፡፡ በተለይ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ እጅግ ቁጥሩ ብዙ ገበሬዎች ሌሎች ሰብሎችን ከማምረት ይልቅ ጫትን በቀላሉ በማምረት ተጠቃሚ ናቸዉ፡፡በዚህ ወረዳ የሚኖሩ ወጣቶች ሀብት ንብረት አፍርተዉበታል፡፡እንደሚታወቀዉ ይሄ ወረዳ ለከተማዉ ቅርብ በመሆኑ በተለምዶ ቦታዉን በመሸጥ ወደ ተለያየ ቦታ ይፈልሳሉ፡፡ አስቡት የአበባበ ምርት ምርት ሲመረት መሬቱ ከዛ በኋላ ምንም አይነት አዝርዕርት ማብቀል አይችልም፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም የከርሰምድር ዉሃን ሳይቀር እንደሚበክል በጥናት ተረጋግጧል፡፡ ነገር ግን የአበባ ምርት በሳይንሳዊ መንገድ ይመረታል፡፡ የአበባ ምርት ህጋዊ ምንዛሬ የሚያስገኝ ሰለሆነ ችግሩ አይወራም፡፡ ነገር ግን ብዙ ገበሬዎችን ያፈናቅላል፡፡ ጫት በራሳቸዉ በገበሬዎች ስለሚመረት የማፈናቀል ጉዳይ የለም፡፡ ጫት ይዉደም ስንል ለነዚህ ገበሬዎች ምን ታስቦ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ህግ ጫትን በአደገኛ እፅ ደረጃ አልፈረጀዉም፡፡ በህግ ደረጃ ጫትን ማጥፋት አይቻልም፡፡መጀመሪያ ህግ መከለስ አለበት፡፡ በተደረጉ ጥናቶች ጫት አምራች ገበሬዎች ጫትን ለማነቃቃት ወይም ለሌላ ጉዳይ አይጠቀሙም፡፡ገበሬ ጫትን ኮትኩቶ ቅጠሉ ለጥቅም ሲደርስ ቆርጦ ወይም ማሳዉ ላይ ለጫት ነጋዴ አሳልፎ ይሸጣል፡፡የሚገርመዉ ጫትን መከልከል ቢጀመር እጅግ አደገኛ እፆች መቸብቸባዉ የማይቀር ነዉ፤ ይሄን መቀሌ ላይ ማየት ይቻላል፡፡ ከአንድ አመት በፊት በ2ተኛ ዲግሪ ምርምር ተደርጎ ነበር፡፡ ጫት እንዲጠፋ የሚፈለግበት ምክንያት 1 ጫት በግብራ ባለሙያ ድጋፍ እና ክትትል ባለመደረጉ 2 የጫት ማሳ በዘፈቀደ ስለሚመረጥ 3 ጫትን ከተለያዩ በሽታዎች ለመከላከል ተብሎ የሚረጨዉ አደገኛ መርዝ 4 አብዛኛዉ አምራች ገበሬ አዝርዕትን ከማምረት ይልቅ ወደ ጫት ማዘንበላቸዉ 5 ጫት በግብርና ሚኒስቴር በኩል በአትክልትና ፍራፍሬ ስም አለመመዝገቡ 6 የሚረጨዉ መድሀኒት በባለሙያ ስለማይታገዝ 7 የሚረጨዉ መድሀኒት ከአፈሩ ጋር ኮንታሚኔት ስለሚያደርግ 8 የሚረጨዉ መድሃኒት የተለያዩ እንስሳትን በቀላሉ ስለሚገድልልክ እንደ ዲዲት ለትንኝ ማጥፊያ ተብሎ በአለም ደረጃ በተሳሳተ መንገድ ሲረጭ እንነበረዉ 9 በአካባቢዉ ስለሚመረት ወጣቱ በቀላሉ ስለሚያገኘዉ 10 ወጣቱ ተሯሩጦ ከመስራት ይልቅ ከአንድ ቦታ ቁጭ ብሎ መዋልን ስላስከተለ 11 ወጣቱን ለስራ አጥ ስለሚጋብዝ 12 አላስፈላጊ ሱሰኝነትን ስለሚገብዝ
4
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ብዙ በልተኸው ርቦህ ትነሳለህ። ሳይቀቀል እና ሳይጠበስ ከነቆሻሻው በታሸገ ውኃ ትቅመዋለህ፤ ከታጠበ አያመረቅንም ተብሎ ይገመታል። በዲዲቲ ምክንያት ትል ያለውን ወይም ትል የበላውን ፈልገህ ትቅማለህ፣ ምክንያቱም ትል ከሌለው መድኃኒት የተረጨበት ነው ተብሎ ይታመናል። ዋነኛ የጫት መቃሚያ ሰዓት ማለት ዋነኛ የሥራ ሰዓት ነው። ሰው ሥራ ጠግቦ ሲመለስ አንተ ብው ብለህ ለሥራ ትወጣለህ። የአንጎልህ እሽክርክሪት በብዙ እጥፍ ይጨምራል። ቩቩቩቩቩኡኡኡኡኡ ዘወትር ለእብደት ሩብ ጉዳይ ጋር ደርሰህ ትመለሳለህ። ያለኮማንድ ፖስት ትእዛዝ ረጭ ብለህ ከመሬት ጋር ተሰፍተህ ትቀመጣለህ። አፍህ ውስጥ ምንም ነገር ሳይኖር ታኝካለህ። በሰፈርህ የተከበርከው ሰውዬ የሳጠራ ቤት ውስጥ ወይም እንደ ዶሮ ቆጥ ላይ ወይም እንደ ቤት እንስሳት ቆጥ ስር ወይም እንደ ቸኮለ ሰው ዱካ ላይ ቁጢጥ ብለህ ልትቅም ትችላለህ። ስትቅም ጉዳይህ ሁሉ የተሳካ ይመስልሀል፤ ምርቃናው ሲበርድ ግን ከመወሳሰቡ የተነሳ አልቅስ አልቅስ ይልሀል። ሰውነትህ በጣም ከመጋሉ የተነሳ የዘር ፈሳሽህ በተቀመጥክበት ሊወጣ ይችላል። በቃ ጫት ማለት መኪናህን ዜሮ ማርሽ ላይ አድርገህ ነዳጅ በኃይለኛው መስጠት ወይም ሁሉንም ጎማ በጋራጅ ክሪክ ሰቅለኸው አየር ላይ መንዳት ማለት ነው።
5
የባሕር ዳር አርሶ አደሮች ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጎርደማ አካባቢ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲያለሙት የነበረውን ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ አርሶ አደሮቹ ጫት እያስከተለ ያለውን ማኅበራዊ ጉዳት በመረዳት ነው ከማሳቸው በማስወገድ በሌላ ጠቃሚ ሰብልና የጓሮ አትክልት ለመተካት እንቅስቃሴ የጀመሩት፡ ዛሬ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጫት ማስወገድ የጀመሩት አቶ ሙስጦፋ ታደሰ የተባሉ የጎርደማ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፤ ሌሎችም የእርሳቸውን አርዓያነት እንደሚከተሉ ይጠበቃል፡፡ ጫት በባሕር ዳር አካባቢ ማኅበራዊ ችግር እየሆነ መምጣቱን በመጥቀስ በርካቶች መፍትሔ እንዲሰጠው ሲጠይቁ መኖራቸውን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገቡን ያስታወሰው አብመድ ነው፡፡
6
ጫት መቃም ለማቆም የሚያግዙ 5 ምክንያቶች ጫት መቃም ለአፍ ቁስለት፣ ለአፍ ካንሰርና ለጥርስ መቦርቦር ይበልጥ ያጋልጣል። 2 ጫት መቃም ለእንቅልፍ ማጣት፣ ለስሜት መሸበርና ለድካም ይዳርጋል። 3 ጫት መቃም ለተጓዳኝ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። 4 ጫት የጸረኤችአይቪ መድሀኒቶችን ውጤታማነት ይቀንሳል። 5 ጫት መቃም የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳል።
7
ዜጎችን ከጫት ጉዳት ለመታደግ መንግስት ፈጣን እርምጃ መውሰድ አለበት ምሁራን በዜጎችና በሃገር ላይ ጉዳት እየደረሰ ያለውን ጫት በዘላቂነት ለመከላከል መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ምሁራን አመለከቱ። በጫት ሱስ ምክንያት የሚመጡ የጤና፣የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በነቃ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንከላከል በሚል መሪ ሃሳብ ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሄዷል። በዚህ ወቅት የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ታምራት ዘላለም ጫት በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና እያሳደረ መሆኑን ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ገልጸዋል አቶ ታምራት በሃገሪቱ አሁን ላይ 27 ነጥብ 6 በመቶ ወንዶችና 11 በመቶ ደግሞ ሴቶች ጫት በመቃም ሱስ ውስጥ መውደቃቸውም ባካሄዱት ጥናት አረጋግጠዋል። በጫት ሱስ የሚጠቁ ወጣቶችም በውስጡ ባለው እፅ ምክንያት ለከፍተኛ ድብርት፣ ለብቸኝነት፣ ለእብደትና በመጨረሻም እራስን እስከማጥፈት የሚደርስ ጉዳት ያደርሳል ብለዋል። ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና በሱሱ የሚጠቁ ሰዎች እየጨመረ በመሄዱ መንግስት ለጉዳዩ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ አመልክተዋል። ለዚህም ማምረትም ሆነ መጠቀምን የሚከለክል ጠንካራና የማይሸራረፍ ህግ ሊወጣና ተግበራዊ ሊደረግ እንደሚገባው አቶ ታምራት በጥናታቸው ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጡት ዶክተር የራስወርቅ አድማሴ በበኩላቸው አንዳንድ ወጣቶች ለአደንዛዝ እፅ ተገዥ እየሆኑ ማህበራዊ ህይወታቸው እየተመሰቃቀለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለሰብል ልማት ይውሉ የነበሩ የእርሻ መሬቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለጫት ልማት እየዋሉ ነው ያሉት ምሁሩ የወጣቶችን ደህንነት አጥብቆ ለመጠበቅ የጫት ተክል ልማትና ንግድ ላይ ወሳኝ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባው ገበየሁ የክልሉ መንግስት የችግሩን ስፋትና ጥልቀት በመለየት በጉዳዩ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ከጤና ቢሮ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ህግና መመሪያ ለማዘጋጀት እየሰራ እንደሆነም አብራርተዋል። ጫት የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከርዕሰ መስተዳደር ጀምሮ የትኩረት አጀንዳ ሆኖ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ናቸው። የሱስ ማገገሚያ ማህበራዊ አገልግሎት ተቋም ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ካላዩ እራሳቸው እንደቀልድ በጓደኛ ተገፋፍተው የጀመሩት የጫት መቃም ለ13 ዓመታት በችግር ውስጥ እንደኖሩ ተናግረዋል፡፡ በማገገሚያ ማዕከል ገብተው በተደረገላቸው ህክምናና ምክር ጤንነታቸው መመለሱን ጠቁመው ከዚህ በመማር በተመሳሳይ ሱስ የተጠቁ ዜጎችን ለመታዳግ ማገገሚያ ተቋም አደራጅተው እየሰራ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የጫትን ጉዳት ለመከላከል መንግስት በፍጥነት ወደ እርምጃ ሊገባ ይገባል ብለዋል የሱስ ማገገሚያ ማህበራዊ አገልግሎት ተቋም ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ካላዩ ። በባህር ዳር ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የምክክር መድረክ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
8
ዜጎችን ከጫት ጉዳት ለመታደግ መንግስት ፈጣን እርምጃ መውሰድ አለበት ምሁራን በዜጎችና በሃገር ላይ ጉዳት እየደረሰ ያለውን ጫት በዘላቂነት ለመከላከል መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ምሁራን አመለከቱ። በጫት ሱስ ምክንያት የሚመጡ የጤና፣የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በነቃ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንከላከል በሚል መሪ ሃሳብ ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሄዷል። በዚህ ወቅት የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ታምራት ዘላለምጫት በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና እያሳደረ መሆኑን ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ገልጸዋል በሃገሪቱ አሁን ላይ 27 ነጥብ 6 በመቶ ወንዶችና 11 በመቶ ደግሞ ሴቶች ጫት በመቃም ሱስ ውስጥ መውደቃቸውም ባካሄዱት ጥናት አረጋግጠዋል። በጫት ሱስ የሚጠቁ ወጣቶችም በውስጡ ባለው እፅ ምክንያት ለከፍተኛ ድብርት፣ ለብቸኝነት ፣ ለእብደትና በመጨረሻም እራስን እስከማጥፋት የሚደርስ ጉዳት ያደርሳል ብለዋል። ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና በሱሱ የሚጠቁ ሰዎች እየጨመረ በመሄዱ መንግስት ለጉዳዩ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ አመልክተዋል። ለዚህም ማምረትም ሆነ መጠቀምን የሚከለክል ጠንካራና የማይሸራረፍ ህግ ሊወጣና ተግበራዊ ሊደረግ እንደሚገባው አቶ ታምራት በጥናታቸው ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጡት ዶክተር የራስወርቅ አድማሴ በበኩላቸው አንዳንድ ወጣቶች ለአደንዛዝ እፅ ተገዥ እየሆኑ ማህበራዊ ህይወታቸው እየተመሰቃቀለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለሰብል ልማት ይውሉ የነበሩ የእርሻ መሬቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለጫት ልማት እየዋሉ ነው ያሉት ምሁሩ የወጣቶችን ደህንነት አጥብቆ ለመጠበቅ የጫት ተክል ልማትና ንግድ ላይ ወሳኝ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባው ገበየሁ የክልሉ መንግስት የችግሩን ስፋትና ጥልቀት በመለየት በጉዳዩ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ከጤና ቢሮ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ህግና መመሪያ ለማዘጋጀት እየሰራ እንደሆነም አብራርተዋል። ጫት የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከርዕሰ መስተዳደር ጀምሮ የትኩረት አጀንዳ ሆኖ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ናቸው። የሱስ ማገገሚያ ማህበራዊ አገልግሎት ተቋም ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ካላዩ እራሳቸው እንደቀልድ በጓደኛ ተገፋፍተው የጀመሩት የጫት መቃም ለ13 ዓመታት በችግር ውስጥ እንደኖሩ ተናግረዋል፡፡ በማገገሚያ ማዕከል ገብተው በተደረገላቸው ህክምናና ምክር ጤንነታቸው መመለሱን ጠቁመው ከዚህ በመማር በተመሳሳይ ሱስ የተጠቁ ዜጎችን ለመታዳግ ማገገሚያ ተቋም አደራጅተው እየሰራ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የጫትን ጉዳት ለመከላከል መንግስት በፍጥነት ወደ እርምጃ ሊገባ ይገባል ብለዋል።
9
በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በጫት ምርት ላይ ከነገ ሚያዚያ 172010ዓም ጀምሮ ቀረጥ ሊጣል መሆኑ ተገለፀ፡፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ በጫት ምርት ላይ ከነገ ጀምሮ በተደራጁ ማህበራት አማካኝነት የቀረጥ ስራ ይጀመራል፡፡ በዋናነት ቀረጥ ማስቀመጥ ያስፈለገበትን ምክንያትም ሲገልፁ፤ በጫት ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የገዥን አቅም ማዳከምና ጫት የሚቅም ወጣትን ለመታደግ የታሰበ ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩልም ለከተማው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡ እንደ ኃላፊው ገለፃ በቅርቡ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ወደ ባህር ዳር ከተማ በቀን ብቻ ከ5ሺህ ኪግ በላይ የጫት ምርት ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት ለባህር ዳር አካባቢ ከ1 ኪግ ጫት ላይ 5 ብር ቀረጥ የተቀመጠ ሲሆን ከባህር ዳር ውጭ በሚጫኑ የጫት ምርቶች ላይ ከ1 ኪግ የጫት ምርት ላይ 30 ብር የተቀመጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
14
በምስራቅ ሀረርጌ 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ግሪሳ ወፍ ተከሰተ የአይሮፕላን ድጋፍ አስፈልጓል ። በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሶስት ወረዳዎች 7 ነጥብ 4 ሚሊየን የግሪሳ ወፍ መንጋ መከሰቱን የዞኑ ግብርና ልማት መምሪያ አስታወቀ ፤ 30 ኪሎ ሜትር በመብረር ጉዳት እንደሚያደርስም ገለጸ ። በመምሪያው አዝርእት ትበቃ ቡድን መሪ አቶ ሞገስ ሂርመጂ ዛሬ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንዳስታወቁት የግሪሳ ወፍ መንጋው የተከሰተው ካለፈው መስከረም አጋማሽ ጀምሮ ነው ። ወፉ በባቢሌ ፣ ፈዲስ እና ጉርሱም ወረዳዎች በሚገኙ እብዳ ፣ ለገፈጣን ፣ ጎላጀ ፣ በከካ እና ጉበሌ ሸለቆዎች አካባቢ በ50 ሄክታር ላይ እንደተከሰተ መረጋገጡንና ብዛቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚሄድ እንደሚጠበቅ ተቁመዋል ። እስከ 30 ኪሎ ሜትር ድረስ በመብረር ሰብል ማጥቃት የሚችል መሆኑን ያመለከቱት ቡድን መሪው ፤ የግብርና ባለሙያዎች ካለፈው መስከረም ወር መግቢያ አንስቶ አሰሳ በማካሄድ ወፎቹ አንድ ላይ በሚሰበሰቡበት ወቅት ኬሚካል ለመርጨት ሲጠብቁ መቆየቱን አስረድተዋል ። ባለፉት 10 ቀናትም የድሬ ቲያራ አይሮፕላን ማረፊያ በ11ሺ ብር ተጠግኖ የሚረጭ ኬሚካል መዘጋጀቱን የተናገሩት አቶ ሞገስ ፤ እስካሁን በሰብል ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አመልክተዋል ። ይሁንና አስቀድሞ ለመከላከል ከክልሉ ግብርና ቢሮ አይሮፕላን እንዲመጣ መጠየቁንና በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ርጭቱ እንደሚጀመር አስታውቀዋል ። አንዷ የግሪሳ ወፍ በቀን 3 ግራም በመመገብ እስከ 50 ግራም የማሽላ ሰብል ታጠፋለች ተብሎ ይገመታል ።
15
7 ነጥብ 4 ሚሊየን ግሪሳ ለመከላከል በአይሮፕላን ኬሚካል መርጨት ተጀመረ ። በምስራቅ እትዮጵያ የተከሰተውን 7 ነጥብ 4 ሚሊየን የግሪሳ ወፍ መንጋን ለመከላከል በአይሮፕላን ትናንት የኬሚካል ርጭት መጀመሩን የሀረር አዝርእት ትበቃ ክሊኒክ አስታወቀ ። የክሊኒኩ ሃላፊ አቶ ሰይፉ ወልደኪዳን ዛሬ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንዳስታወቁት ርጭቱ የተጀመረው ከክልል ፣ ከዞንና ከወረዳ ግብርና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ለአንድ ወር ያህል በተካሄደው አሰሳ በተገኙት የተለያዩ 64 ሄክታር የወፎቹ መራቢያና ማደሪያ ስፍራዎች ነው ። በግብርና ሚኒስቴር እና በምስራቅ አፍሪካ የአንበጣ መከላከያ ድርጅት አማካኝነት ወደ ስፍራው የተላከው አውሮፕላን ከባቢሌ ጊዜያዊ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ርጭቱን እያካሄደ ያለው በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ዞን ፋፈም በተባለ ሸለቆ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል ። በመጪዎቹ 10 ቀናት የድሬ ቲያራን አውሮፕላን ማረፊያ ችምር በመጠቀም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ፣ ፈዲስና ጉርሱም በተገኙ የወፎቹ ማደሪያ ላይ ርጭት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ። የወፍ መንጋው ከተከሰተባቸው ሁለት ክልሎች ውጭ ወደ ሃረሪ ክልልና ድሬዳዋ አስተዳደር ካውንስል በመንቀሳቀስ የማሽላ ሰብል ሊያጠፋ ይችላል ያሉት አቶ ሰይፉ ጉዳቱን ለመከላከል ርጭቱ ወቅቱን ተብቆ ተጀምሯል ብለዋል ።
16
9 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚገመት የግሪሳ ወፍ ተወገደ ። በምስራቅ እትዮጵያ ባለፈው መስከረም መጨረሻ የተከሰተውን 9ነጥብ6ሚሊየን የሚገመት የግሪሳ ወፍ መንጋ ለማስወገድ መቻሉን የሀረር አዝርእት ትበቃ ክሊኒክ አስታወቀ ። በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ፣ ፈዲስና ጉርሱም ወረዳዎች ፤ በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ዞንና በሀረሪ ክልል የተከሰተውን ግሪሳ ወፍ ለመከላከል የተቻለው ባለፉት 12 ቀናት በአውሮፕላን በተካሄደው የመድሃኒት ርጭት መሆኑን የክሊኒኩ ሃላፊ አቶ ሰይፉ ወልደኪዳን ገልጸዋል ። በዚሁ የመድሃኒት ርጭት ወፎቹ በሚያድሩባቸው 297 ሄክታር የግራር ዛፍ በበዛበትና ሸለቆማ ቦታዎች 595 ሊትር ጸረወፍ መርዝ በመረጨቱ 93 በመቶ የሚበልጠው መንጋ እንደተወገደ መረጋገጡን ሃላፊው አስረድተዋል ። የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር በጀት ፣ ኬሚካልና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎችን በመመደብ ፣ የምስራቅ አፍሪካ አንበጣ መከላከያ ድርጅት አውሮፕላን ከነ አብራሪው በማቅረብ እንዲሁም የክልል ግብርና ቢሮዎችና መምሪያዎች አሳሽ ባለሙያዎችን በማሰማራት ቅንጅታዊ ስራ በመሰራቱ ውጤቱ መግኘቱን ተናግረዋል ። መንጋውን በወቅቱ መቆጣጠር ባይቻል ኖሮ በአካባቢው በስፋት የሚመረተውን የማሽላ ሰብል በቀን በግምት እስከ 960 ኩንታል ምርት ያወድም እንደነበር ሃላፊው መግለጻቸውን ዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል ።
17
በዝዋይ ግብርና ልማት ማእከል ፤ማረሚያ ቤቶችና በአካባቢዉ በሚገኙ ገበሬዎች ማሳ ላይ ተከስቶ የነበረዉ የግሪሳ ወፍ መንጋ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ለመቆጣጠር መቻሉ ተገለጠ ። የዝዋይ ሰብል ጥበቃ ክሊኒክ ኤክስፐርት አቶ ዘብዲዎስ ሰላቶ እንደገለጡት ከፍተኛ ቁጥር ያለዉን የግሪሳ ወፍ መንጋ ለመቆጣጠር የተቻለዉ በአካባቢዉ በአዉሮፕላን የኬሚካል ርጭትና በባህላዊ ዘዴ የተጠናከረ የመከላከል ስራ በመካሄዱ ነዉ ። የግሪሳ ወፎች የደረሰዉን የበቆሎ ፍሬ በመብላትና ሽፋኑን በመላጥ ለዝናብ እንዲጋለጥ በማድረግ ሰብሉን ለጉዳት እንደሚዳርጉ አስረድተዋል ።
18
በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ በየጊዜው የሚከሰተውን የግሪሳ ወፍ መንጋ ለመከላከል በአምስት ሚሊዮን ብር የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ገለጸ፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ታዲ ዋቆ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት የፌዴራሉ መንግስት በመደበው በጀት ግንባታው በመከናወን ላይ ያለው ጣቢያ 100 ሜትር ስፋትና ሁለት ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ የጣቢያው ግንባታ ሲጠናቀቅ መንጋው በሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል እንደሚረዳና ከዚህ ቀደም ከጎረቤት አገር በመነሳት የሚያደርሰውን ከፍተኛ ጉዳት ማስቀረት እንደሚያስችልም አመልክተዋል፡፡ በመንገድ ችግር ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችና ሌሎች ችግሮች ሲያጋጥሙ የቅርብ እገዛ ለማድረግ ጠቀሜታ እንዳለውም አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡ የፌዴራሉ መንግስት የአርብቶ አደሩን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን ለማቃለል እየወሰደ ያለው እርምጃ አበረታች በመሆኑ ሊጠናከር እንደሚገባውም አቶ ታዲ አሳስበዋል፡፡
19
በምስራቅ ሽዋ ዞን ስምጥ ሸለቆ አከባቢ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ተከስቶ የነበረውን ከ3ነጥብ8 ሚሊዮን በላይ የግሪሳ ወፍ በሰብል ላይ ጥፋት ሳያደርስ ለማስወገድ መቻሉን የባቱ እፅዋት ክሊኒክ ፅሀፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የፅሀፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ተሾመ ቡርቃ ለኢትዮጰያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በስመጥ ሸለቆ በሚገኙት የአዳሚ ቱሉ ጅዶ፣ ዱግዳ ቦራና ዝዋይ ወረዳዎች ተከስቶ የነበረውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ የተቻለው በአውሮፕላን በመታገዝ በተካሄደ የኬሚካል ርጭት ነው፡፡ በዚሁ ዘመቻ ወፎቹ የሚያርፉበትና የሚራቡበት 175 ሄክታር መሬት ላይ 350 ሊትር ኬሚካል በመርጨት እንዲወገዱ በመደረጉ ከ2ሚሊዮን600ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ሊሰጥ የሚችል የስንዴ፣ የማሽላና ጤፍ ሰብል ከውድመት ለመከላከል እንደተቻለም አስረድተዋል፡፡ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴርና የኦሮሚያ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ፣ ከምስራቅ አፍሪካ የአንበጣ መከላከያ ድርጅት ጋር በመተባበር ባካሄዱት የአሰሳና የኬሚካል ርጭት ስራ የግሪሳ ወፉን ለማስወገድ እንደተቻለ አቶ ተሾመ ጨምረው ገልጠዋል፡፡
20
የግሪሳ ወፍ በማሽላ ሰብላችን ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው – የሰሜን ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች ደብረ ብርሃን ጥቅምት 82011 በማሽላ ሰብላችን ላይ የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ በባህላዊ መንገድ ለመከላከል ጥረት ብናደርግም ከአቅማችን በላይ በመሆኑ ተቸግረናል ሲሉ በአማራ ክልል የሰሜን ሽዋ ዞን አርሶ አደሮች ገለፁ። ከ280 ሺህ በላይ የሚገመተውን ሰብል አውዳሚ የግሪሳ ወፍ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአውሮፕላን በታገዘ መንገድ ርጭት ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል። በቀወት ወረዳ የየለን ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ተፈራ ደስታ ከግማሽ ሄክታር ማሳ በላይ በዘሩት የማሽላ ሰብል የግሪስ ወፍ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡ ችግሩን ከጅምሩ ለግብርና ባለሙያዎች ከማሳወቅ ባለፈ ጉዳት እንዳያደርስ ማማ ሰርተው ወፎችን በባህላዊ መንገድ የመከላከል ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ የግሪሳ ወፉ በመንጋ ስለሚንቀሳቀስና ቁጥሩ በርካታ በመሆኑ በባህላዊ መንገድ የሚያደርጉትን መከላከል አዳጋች እንዳደረገባቸው አስታውቀዋል። በዚህም በማሳቸው ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ የምርት ቅናሽ ያደርሳል የሚል ስጋት አንዳደረባቸው አመልክተዋል፡፡ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የወፍ መንጋዉን ሊያጠፋልን ይገባልም ሲሉም ጠይቀዋል። ሌላው አርሶ አደር ወርቁ ሞላ በበኩላቸው በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ በዘሩት ማሽላ የግሪስ ወፍ መከሰት መጀመሩ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። ”ለግብርና ባለሙያዎች በማሳወቅ የመከላከል ሥራ ብጀምርም የወፎች ቁጥር በመጨመሩ በሰብሉ ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው” ብለዋል። በግማሽ ሄክታር ማሳ ላይ የዘሩት ማሽላ በግሪስ ወፍ መጠቃቱን የገለፁት ደግሞ በኤፍራታና ግድም ወረዳ የነጌሶ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አወቀ በላቸው ናቸው፡፡ አስተያየት ሰጪው እንዳሉት ማማ ሰርተው በባህላዊ መንገድ ለመካላከል ቢሞክሩም ውጤታማ አልሆኑም። ”ለመሰብሰብ ያቀድነውን ምርት አጥተን ለችግር እንዳንጋለጥ የግሪሳ ወፎች የሚያድሩበት ቦታ ኬሚካል በመርጨት የማጥፋት ስራ መንግስት ሊሰራልን ይገባል” ብለዋል፡፡ በሰሜን ሽዋ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ገበየሁ ሽፈራ በበኩላቸው በዞኑ ማሽላ አብቃይ በሆኑ ቀወትና አፍራታ ግድም ወረዳዎች የግሪሳ ወፍ መከሰቱን ገልጸዋል፡ በመንጋ ወፉ የደረሰው የጉዳት መጠን በውል ባይታወቅም የግሪስ ወፎች በሁለቱ ወረዳዎች የሚገኝ የማሽላ ሰብልን እያወደሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንድ ወፍ በአማካኝ በቀን ከ30 እስከ 50 ግራም ማሽላ የመብላት አቅም እንዳለዉ የተናገሩት አቶ ገበየሁ ችግሩ በፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ አርሶ አደሩ ማሳውን በማሰስ በባህላዊ መንገድ የመከላከሉን ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል መክረዋል፡፡ በሁለቱ ወረዳ የተከሰተውን የወፍ መንጋ ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር በሚቀጥለው ሳምንት በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ በሽዋሮቢት ከተማ የአውሮፕላን ማረፊያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ወቅቱ ማሽላ የሚያፈራበት በመሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወፎች በአፋር ክልል በኩል ወደ ዞኑ ይገባሉ ተብሎ ስለሚጠበቅ በባህላዊና ዘመናዊ መንገድ የመከላከሉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡ በዞኑ 88 ሺህ 700 ሄክታር ማሳ ላይ ከተዘራው የማሽላ ሰብል ከ3 ሚሊዮን 400 ሺህ ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል፡፡
21
ሰሜን ሸዋ ውስጥ በማሽላ ሰብል ላይ የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መከላከል ተቻለ 1285 Share ደብረ ብርሀን ጥቅምት 202011 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት እና ኤፍራታ ግድም ወረዳዎች በማሽላ ሰብል ላይ ተከስቶ የነበረ ከሁለት ሚሊዮን 500ሺህ በላይ የግሪሳ ወፍ በማስወገድ መከላከል ተቻለ፡፡ የዞኑ ግብርና መምሪያ እንዳስታወቀው በወረዳዎቹ የለን እና ነጌሶ በተባሉት ቀበሌዎች በለማ የማሽላ ሰብል ከሁለት ሳምንታት በፊት ተከስቶ የነበረውን የግሪሳ ወፉን መከላከል የተቻለው በአውሮፕላን በተካሄደ የኬሚካል ርጭት ነው፡፡ በፌዴራል መንግስት ድጋፍ ከጥቅምት 162011ዓም ጀምሮ ለሶስት ቀናት ምሽት ላይ የግሪሳ ወፉ ማደሪያ ውስጥ በተደረገ የኬሚካል ርጭት ማስወገድ ተችሏል፡፡ ለዚህም 145 ሊትር ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉን በመምሪያው የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ገበየሁ ሺፈራ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ ” ኬሚካል ከተረጨ በኋላ ለ72 ሰዓታት አርሶ አደሩ እንሰሳትና ልጆችን ወደ አካባቢው እንዳይልክም መጠንቀቅ አለበት” ብለዋል፡፡ ወፉ ሰፋ ያለ ስፍራን ተዘዋውሮ የመብላት አቅም ያለው በመሆኑ አርሶ አደሩ ዘወትር ማሳውን በማሰስ በባህላዊ መንገድ ከመከላከል በተጓዳኝ ከተከሰተም ለአካባቢው ግብርና ባለሙያ መጠቆም እንዳለበትም ተመልክቷል። በሌሎች አካባቢዎችም የወፎችን ማደሪያ በማጥናት በኬሚካል ለማጥፋት የዘመቻ ስራው እንደቀጠለ ነው ተብሏል። በኤፍራታና ግድም ወረዳ የነጌሶ ቀበሌ አርሶ አደር ክንዴ ሽመልስ በሰጡት አስተያየት በግማሽ ሄክታር ማሳቸው ላይ የዘሩት ማሽላ በግሪሳ ወፍ እንዳይጠቃባቸው በባህላዊ መንገድና መንግስት በአውሮፕላን ባካሄደው ርጭት መከላከል እንደቻሉ ተናግረዋል። በግማሽ ሄክታር ማሳ በዘሩት ማሽላ ሰብል ላይ ተከስቶ የነበረው ግሪሳ ወፍ ሰሞኑን በተካሄደ ርጭት መከላከል በመቻላቸው እፎይታ ማግኘታቸውን የገለጹት ደግሞ በቀወት ወረዳ የየለን ቀበሌ አርሶ አደር ተፈራ ደስታ ናቸው፡፡ በሰሜን ዞን በማሽላ ሰብል ከለማው 88 ሺህ ሄክታር ማሳ ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም ታውቋል። ባለፈው ዓመትም በአካባቢው 10ሚሊዮን የሚገመት የግሪሳ ወፍ በሰብል ላይ ተከሰቶ በተመሳሳይ መከላከል መቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አመላክቷል፡፡ Related Posts
22
የግሪሳ ወፍ በኅዳር ወር 2006 ዓም የግሪሳ ወፍ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች Eና ሕዝቦች በኮንሶ Eና Aማሮ ልዩ ወረዳዎች፤ ከOሮሚያ በዝዋይ ዱግዳ፣ ተለተሌ፣ Aዳሚ ቱሉ Eና ሊበን Eንዲሁም ከAማራ ክልል በቀወት፣ ኤፍራታ፣ ጂሌ ጥሙጋ፣ ዳዋ ጨፌ Eና ቃሉ ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን ወፎቹ ወደ Eህል ማሳ ሳይዛመቱ በተካሄደዉ ተገቢ Eና Aፋጣኝ የኬሚካል ርጭት Eርምጃ በቁጥጥር ሥር ሊዉል Eንደቻለ በግብርና ሚኒስቴር ከAዝርEት ጥበቃ ክፍል የተገኘዉ መረጃ ይጠቁማል። የአዕዋፍ ዝርያዎች ማሽላን የሚያጠቁ ቢሆንም አብኛውን ጉዳት የሚያደርሰው ግን ግሪሳ ነው፡፡ የግሪሳ ወፍ በመንጋ በመንቀሳቀስ ከፍተኛ የምርት ውድመት ያደርሳል፡፡ ግሪሳ በብዛት የሚራባው ግራር በሚበዛበት እና ውሃ በሚተኛበት አካባቢየስምጥ ሸለቆ አካባቢ ሆኖ ጥቃቱን ግን የሚያደርሰው ብዙ ኪሎ ሜትሮች በመጓዝ ነው፡፡ ወፍ መጠበቅና ወፍን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን መጠቀም የተሻለ የመከላከያ ዘዴ ሲሆን በተጨማሪም ከ14 ኪሎ ግራም በሄክታር ሚቲዮካርብ የተባለ ፀረወፍ መድሃኒት በውሃ በጥብጦ በመራቢያው ቦታ ላይ በመርጨት ለመቆጣጠር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ኬሚካል በሚረጭበት ጊዜ ሌሎች ዐፅዋትንና ነፍሳትንም ሊገድል ስሚችል የመጨረሻ አማራጭ ተደርጎ ቢወሰድ ይመረጣል፡
23
ባሳለፍነው ነሐሴ ወር የተዛማች ፀረ ሰብል ተባዮች የበረሐ አንበጣ፣ ተምችና ግሪሳ ወፍ ክስተት በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ አለመኖሩን ከክትትል መረጃዎች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የግሳ ወፎች በነሐሴ ወር የግሪሳ ወፍ ክስተት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያልነበረ ቢሆንም ባለንበት መስከረም ወር በመካከለኛ፣ ስምጥ ሸለቆና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ክስተቱ ሊኖር ስለሚችል በየአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮችና የልማት ሠራተኞች አስፈላጊውን አሰሳ በማድረግ ወረርሽኙ ከተከሰተ ለሚመለከተው ክፍል በፍጥነት ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
24
‹‹በአማራው ላይ የተሰራው የህዝብ ቆጠራ ስህተት እንዳይደገም ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡›› የክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ባሕር ዳር፡ የካቲት 262011 ዓምአብመድ የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች እየተሰጠ ነዉ። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን ፀሀፊ አቶ ተስፋ ተገኝ እንደተናገሩት በስልጠናው ከሰሜን፣ ከማዕከላዊ፣ ከምዕራብ እና ከደቡብ ጎንደር ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች እና ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የአይሲቲ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው፡፡ የቆጠራ ማዕከል ይሆናሉ ከተባሉ 11 ጣቢያዎች እና ከተሞች የተመረጡ መምህራን እንዲሁም የግብርና እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችም እየተሳተፉ መሆናቸው ታውቋል፡፡ የስልጠናው ዋና ዓላማ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን በማጎልበት የዘንድሮውን የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከስህተት የጸዳ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል፡፡ ቆጠራው በቴክኖሎጂ ታግዞ የሚሰራ በመሆኑ ስልጠናውም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ፀጋ ጥበቡ እንደተናገሩት በ1987 እና በ1999 ዓም በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ብዙ የአማራ ሕዝብ ቁጥር በትክክል ባለመቆጠሩ ክልሉ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። በተለይም የ1999 ዓም ቆጠራ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ቅነሳ የተደረገበት በመሆኑ ምክንያት ክልሉ ከፌደራል መንግስት ማግኘት የነበረበትን በቢሊዮን የሚቆጠር በጀት አጥቷል ነው ያሉት፡፡ የክልሉ ህዝብ ትክክለኛ አሃዛዊ መረጃም እንዳይታወቅ አድርጎታል። የቁጥሩ መሳሳት ለፖሊሲ እና ለጥናትና ምርምር የሚገኘውን መረጃም አዛብቶታል። ይህ የሆነው በቆጠራው ወቅት በተሰራ ቸልተኝነት በመሆኑ በቆጠራዉ የሚሳተፉ ባለሙያዎች በጥንቃቄ መስራት እንዳለባቸው ዶክተሩ መክረዋል። ችግሩ በዘንድሮው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ እንዳይደገም የክልሉ መንግስት ኃላፊነት ወስዶ በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች የቆጠራ ኮሚሽን አዋቅሮ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በኃላፊነት የሚሰሩ ቆጣሪ እና ተቆጣጣሪዎች መመልመላቸውም ተገልጧል፡፡ የስልጠናው ታሳታፊዎችም በቂ እውቀት እንደሚያገኙ እምነታቸውን ነግረውናል። ቆጠራውንም ያለምንም ስህተት ለመስራት ዝግጅት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ስልጠናው ከየካቲት 26 እስከ መጋቢት 82011 ዓም ይቆያል፡፡ በአማራ ክልል ባሕር ዳር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች ላይም በሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለሚሳተፉ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡
25
የህዝብና ቤት ቆጠራው እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳብ መቅረቡ ተገቢ አይደለምየትግራይ ክልላዊ መንግስት ኢፕድ የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብርሀም ተከስተ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት የቆጠራ ስራው በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። የቆጠራ ስራው እንዲራዘም ያጋጠመ የተለየ ችግር የለም ያሉት ኃላፊው አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ እንዲራዘም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የመንግስትን የአመራር ግልጽነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ብለዋል። ውሳኔው ከህገመንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር እንደማይጣጣም ገልጸው ችግሮች ቢያጋጥሙ እንኳ ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ስራውን ማስቀጠል ይገባ እንደነበር ተናግረዋል። ኢዜአ እንደዘገበው የኢትዮጵያና የዓለም ህዝብ ቆጠራውን እየጠበቀ ባለበት ሁኔታ መራዘሙ ሀገሪቱ የሚኖራትን አመኔታ ሊያሳጣት እንደሚችል ጠቁመዋል። በክልሉ ለቆጠራው ስኬታማ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ተናግረዋል። የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓም ባካሔደው ስብሰባ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው የመመለሱ ስራ በበቂ ሁኔታ ባለመሰራቱ ቆጠራው እንዲራዘም የውሳኔ ሀሳብ ማቅረቡ ይታወሳል።
26
የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2011 ባካሄደው ስብሰባ አራተኛዉን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሄድ የተደረገዉን ዝግጅት በመገምገም የዉሳኔ ሃሳቦች ኣሳልፏል በዚህም መሠረት • የሕዝብና ቤት ቆጠራው እንዲቀጥል በቴክኒክ ደረጃ በቂ ዝጅግት የተደረገ መሆኑንና ኮሚሽኑና ማእከላዊ እስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሰፊ ስራ የሰሩ መሆኑን፤ • የካርታ እና ተያያዥ ስራዎች እየተገባደዱ መሆኑን፤ • ሌሎች ዝግጅቶችም እየተደረጉ መሆኑን ግንዛቤ ወስዶ የቆጠራውን አላማና ግብ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችሉ ተግባራት የተሟሉ ባለመሆናቸው ማለትም በየአካባቢው ለስራው መሳካት በተገቢው ሁኔታ መጠናቀቅ የሚገባቸው ተግባራት ባለመጠናቀቃቸው እና ተጨማሪ ግዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ፤ • ምንም አንኳን ለቆጠራ የቀሩን ቀናት ጥቂት ቢሆንም በተለያዩ ገጭቶች ምክንያት የትፈናቀሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወገኖች ወደነበሩበት ቀዬ የመመለሱ ስራ በበቂ ሁኔታ ባለመሰራቱ አሁንም በርካታ ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህ ወገኖች ትርጉም ባለው ደረጃ ወደ ነበሩበት ቦታ እስኪመለሱ ድረስ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ ቆጠራው እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳቡን ለተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች እንዲቀርብ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።
27
‹‹የሕዝብና ቤት ቆጠራው ከመንግሥት በላይ ለሃይማኖት ተቋማት አስፈላጊ በመሆኑ ከስህተት የጸዳ ቆጠራ እንዲካሄድ እየሠራን ነው፡፡›› የሃይማኖት አባቶች ባሕር ዳር፡ የካቲት 272011 ዓምአብመድ ከ12 ዓመታት በኋላ የሚካሄደው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ መጋቢት 29 ቀን 2011ዓም ሊጀመር ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡ ዓመታትን አስቆጥሮ የመጣውን ይህን የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ በውጤት እንዲጠናቀቅ የሃይማኖት አባቶች ድርሻቸው ከፍተኛ እንደሆነ የሃይማኖት አባቶች ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የትምህርትና ዳእዋ ዘርፍ ኃላፊ ሼህ አህመድ ዘይን እንደተናሩት የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለሃይማኖትም ሆነ ለዓለማዊው አስተዳደር ጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም ለምዕመኖቻቸው የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው መልዕክት እያስተላለፉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሙስሊሙ አለሁ ብሎ መቆጠር አለበት›› የሚል አቋም እንዳላቸውም አስታውቀዋል፡፡ ሙስሊሙ መስጂድ ለመገንባት ‹‹መሬት ይሰጠን›› ከማለት ጀምሮ መብቱን እንዲጠይቅ መቆጠሩ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው ነው ያስረዱት፡፡ ‹‹ልጅን ማስቆጠር ማስገምገም ነው›› የሚሉ አባባሎችና ከኅብረተሰቡ ልማድ ጋር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ላለመቆጠር ወይም ላለማስቆጠር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት እንደሌላቸውም አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ከአላስፈላጊ አምልኮ ጋር የተያያዙ አስተሳሰቦች ናቸው›› ሲሉም ያለማስቆጠር ዝንባሌን አውግዘዋል፡፡ ‹‹የሃይማኖት አባቶች ስህተት እየተፈፀመ እየተመለከትን በዝምታ የምናልፍ ከሆነ ሀገርን ከመሸጥ አይተናነስም›› ሲሉም በቆጠራው ወቅት ስህተቶችን አይቶ ማለፍ እንዳይኖር አሳስበዋል፡፡ ቆጣሪዎች ‹‹ቆጥረናል›› ቢሉ እንኳ የሃይማኖት አባቶች እውነታነቱን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡ ምዕመኑም በዓይኑ ዓይቶ ማረጋገጥ ይገባዋል፤ ምክንያቱም ለሀገር የሚሠራ እንዳለ ሁሉ ‹የእኔ ይቅደም፤ የኔ ይብለጥ› ሽኩቻዎች ስለሚኖሩ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡ የባሕር ዳር ወንጌላዊ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ዋና ጸሐፊ መጋቢ ደሳለኝ አባተ ደግሞ ሕዝብና ቤት ቆጠራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ይህን ምዕመኑም ያውቀዋል፤ ቆጠራ ከተካሄደ መንግሥት በጀት ለመመደብ፣ ለአስተዳደራዊ ክንውኖችና ለሌሎች የሀገር ዕድገቶች ወሳኝ ነው›› ብለዋል፡፡ መጋቢ ደሳለኝ አባተ እንዳሉት በጎ ባሕል እንዳለው ሁሉ ጎጂ ልማድም አለ፤ በተለይ አካል ጉዳተኛ የሆኑ ልጆችን የመደበቅ ልማድ መኖሩን ነው ያብራሩት፡፡ ነገር ግን ‹‹የእኛ እምነት ሁሉም ሰብዓዊ የሆነ ፍጡር መቆጠር አለበት የሚል ነው፡፡ ባለመቆጠር እንጎዳ እንደሆነ ነው እንጂ ሌላ አናተርፍም›› ነው ያሉት፡፡ የተለዬ ተጠቃሚ እሆናለሁ በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ ሰዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባና ተጽእኖው ከፍተኛ እንደሚሆንም መጋቢ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡ ‹‹መቆጠር መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው፡፡ አልቆጠርም የሚል አስተሳሰብ እንዲቀርም የበኩላችንን እየተወጣን ነው›› ብለዋል፡፡ መጋቢ ደሳለኝ በሰጡን መረጃ መሠረትም ከአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከጤና ጥበቃ ቢሮና ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመሆን ኅብረተሰቡን በኅብረት የማነቃቃት ሥራ እንዲከናወን መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ሰው ቤቱን እንዳይዘጋ፤ ከቤተሰብ አባላት የሚያውቁ ግለሰቦች በየሰፈሩ ቆጠራ በሚጀመርበት ቀን እንዲገኙ እና በአግባቡ ለሚጠየቁት ነገር ምላሽ እንዲሰጡ ለማድረግ የግንዛቤ ሥራ መጀመሩንም ነግረውናል፡፡ በ1999 ዓም የሕዝብና ቤት ቆጠራ የአማራ ሕዝብ አንሷል በሚል ውዝግብ መነሳቱን ያስታወሱት መጋቢ ኤፍሬም ‹‹አሁንም ስህተቶች እንዳይሰሩ ጥንቃቄ ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡ በቴክኖሎጂ ሥርዓት በመታገዝ የሚካሄደው ቆጠራ ተቆጣሪው ትክክለኛውን መረጃ እስከሰጠ ድረስ ስጋቶችን ለመቀነስ ይረዳል የሚል እምነት አለኝ›› ሲሉም አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሕዝቡ እንዲቆጠር ማንኛውም ሰው የቤተሰቡን አባላት እንዲያስቆጥር የተላለፈውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ወንጌል ሰባኪዎች፣ ካህናትና ሌሎችን በመሰብሰብ ስልጠና ተሰጥቷል ያሉት የክልሉ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ መልአከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም ናቸው፡፡ ‹‹ቆጠራው መንግሥት ሕዝቡ ምን ያህል ነው የሚለውን አውቆ ምን ያስፈልገዋል፤ ይበጀዋል በሚለው ጉዳይ ላይ ለመሥራት ይጠቅመዋል፡፡ ሕዝብ ማለት የመንግሥት አካል የሆነ ቤተሰብ ነው፡፡ መንግሥትም የሕዝብ ቤተሰብ ነው›› ሲሉ ገልፀውታል፡፡ ሃይማኖት ሲጠየቅ ምዕመኑ ‹ኦርቶዶክስ ተዋሕ› ብሎ እስከመመለስ ድረስና ለሌሎች ጥያቄዎችም ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥ የቅስቀሳ ክንውን እየተገበሩ መሆናቸውን ነው መልአከ ሰላም ኤፍሬም ያስታወቁት፡፡ በአፍሪካ ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያና ግብፅ በሕዝብ ብዛት በቅደም ተከተል የመሪነቱን ስፍራ ይዘው ይገኛሉ፡፡ በአፍሪካ ደረጃ ውጤታማ የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ በማካሄድ ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ነች፡፡
28
ቆጠራው ህልውናን የሚፈታተን በመሆኑ በቀጣዩ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አብን አሳሰበ። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄአብን በደብረታቦር ከተማ ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር ተወያይቷል። ወቅታዊ ጉዳዮችንና የሕዝብና ቤቶች ቆጠራን አስመልክቶ ነው ውይይቱን ያዘጋጀው። ለውይይት መነሻም ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል። በፅሁፉም የአንድን ሃገር የሕዝብ ቁጥር ያላገናዘበ ምንም ዓይነት ልማት እንደማይሰራ ተብራርቷል። የሥራ አጥ ቁጥርን፣ የኑሮ ሁኔታን፣ የህብረተሠቡን የፍልሰት ሁኔታ፣ የግብር ከፋይ ቁጥርን እና ሌሎችንም መሠረታዊ መረጃዎች ለማግኘት ቆጠራው ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ተመላክቷል። የሕዝብን መሠረታዊ ፍላጎት ለሟላት እና ፖሊስ ለመቅረፅ የህዝብ ቆጠራ ማድረግ ወሳኝ መሆኑም በውይይቱ ተብራርቷል። ከአሁን በፊት በተደረጉ የህዝብና ቤቶች ቆጠራዎች በአማራው ላይ የተሠሩ ስህተቶች ህዝብን ዋጋ ማስከፈላቸውና ጥቅሙንም ማሳጣታቸው ታውቆ በቀጣዩ ቆጠራ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ነው አብን ያሳሰበው። ቆጠራው የመኖር እና ያለመኖር ህልውናን የሚፈታተን በመሆኑ ሁሉም ህዝብ በጥንቃቄ ሊከታተለው እንደሚገባም ንቅናቄው አሳስቧል። የደቡብ ጎንደር ዞን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የምክር ቤት አባል አቶ ከፍያለው ጎላ ወጣቶች በተረጋጋ መልኩ ማህበረሠቡን በማነቃቃት ለቆጠራው ስኬትና ለአካባቢያቸው ፀጥታ እንዲሰሩ ጠይቀዋል። በሌላ በኩል በምዕራብና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በነበረው የፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች የአብን አባላት ከደመወዛቸው 10 በመቶውን ድጋፍ ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል። የደንቢያ ወረዳ የአብን ጽህፈት ቤትም ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2መቶ ሺህ ብር በላይ እርዳታ መስጠቱ ታውቋል። ለተጎጅዎች ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አብን አስታውቋል።
29
እኛ አማራዎች የህዝብና ቤት ቆጠራው እንዲራዘም የምንፈልግበት ምክንያቶች፦ 1የፖለቲካ መተማመን ስለሌለ 2በሀገሪቱ አብዛኛው አካባቢ የፀጥታ ስጋት ስላለ ለቆጣሪዎች 3ዜጎች ራሳቸውን በማንነታቸው ቢገልፁ ብሄራቸውን Identify ቢያደርጉ የጥቃት ሰለባ ሊሆኑ ስለሚችሉ በነገራችን ላይ አሜሪካም በትራምፕ አስተዳደር ጥቃት ይደርስብናል ያሉ ጥቁሮች ቅሬታ ስላቀረቡ ህዝብና ቤት ቆጠራው እያወዛገበ ነው 4የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማከናወን ብቁ እና ተዓማኒ ተቋም፣ ባለሙያና ቴክኖሎች ባለመኖሩ 5የህዝብና ቤት ቆጠራው በባለሙያ ሳይሆን በካቢኔ ስር በመሆኑ 6የከዚህ በፊቱ ቆጠራ በተለይ በፓርላማ ጭምር ውዝግብ ያለበት የ 2007 ቆጠራ ውድቅ መደረግ ስላለበት 7ለህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ቅሬታ ቢነሳ ማስተናገድ የሚችል የህግ ማዕቀፍና ተቋም ባለመኖሩ 8ከቆጠራው በፊት የ2007ቱን የተሳሳተ መረጄ መነሻ በማረግ የተሰራው ፕሮጀክሽንትንበያ ውድቅ መደረግ ስላለበት 9ዜጎች ራሳቸውን እንዲገልፁ የተዘረዘሩ መስፈርቶች አንዳንዶቹ የጠሩ እና ከቀናነት የተዘረዘሩ ባለመሆናቸው እና ቅድሚያ መሻሻል ያለባቸው በመሆኑ ለምሳሌ ድብልቅ ማንነት፣ ብሄር የለኝም፣ወዘተ 10የህዝብና ቤት ቆጠራ ባለሙያዎች በክልሎች ስለሚካሄድ ቆጣሪዎችና በአንዳንድ ክልሎች የሚኖሩ ዜጎች በቋንቋ ካለመግባባትም በላይ ቆጣሪዎች ተዓማኒ ሊሆኑ ስለማይችሉ ሌላ ስልት መፈለግ ስለሚገባ 11ቆጠራውን በዚህ በአጣብቂኝ ወቅት ማካሄድ ግዴታ ስላልሆነ እና መነሻውም ከጤነኝነት የመነጨ ስላልሆነ 12በኢትዮጵያ ፖለቲካ የበለጠ የግጭት ምንጭ ሊሆን ስለሚችል 13በተለይ በአማራ ክልል ከህዝብና ቤት ቆጠራና ከክትባት ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት የተሰሩ ግልፅ ሸፍጦችና በደሎች ስለነበሩ ህዝቡ ቂም ስለያዘ ቆጣሪዎች ላይ ርምጃ ሊወስድ ስለሚችል በእነዚህና ተያያዥ ምክንያቶች የህዝብና ቤት ቆጠራውን ማካሄድ ተገቢ አይደለም።ይህ ሆኖ እያለ ህዝብና ቤት ቆጠራው ቢካሄድ በአማራ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አይኖረዉም። ለአማራ ህዝብ እንታገላለን፣እንቆረቆራለን የሚል ማንኛውም አካል ይህ የህዝብና ቤት ቆጣራ ቆጠራ እንዲራዘም እንዲጠይቅ፣ እንዲሁም እምቢ ብለው ቆጠራ ካካሄዱ ደግሞ ውጤቱ ተቀባይነት እንደሌለው ቀድሞ አቋም እንዲይዝ እንመክራለን።
30
‹‹ያጣነውን ታማኝነት በአራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጣራ መመለስ አለብን፡፡›› ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን ባሕር ዳር፡ መጋቢት 022011ዓም አብመድ በአራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ከዚህ በፊት በአማራ ክልል ሕዝብ የተሰሩት ስህተቶች እንዳይደገሙ ሁሉም የክልሉ ሕዝብ በጥንቃቄ መሥራት እንዳለበት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡ መጋቢት 29 ቀን 2011ዓም ለሚደረገው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ እስካሁን ክልሉ የሄደበት ደረጃ እና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተወያይተዋል፡፡ በ4ኛው የሕዝብ እና የቤቶች ቆጠራ በአማራ ክልል ሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ዳኘው እስካሁን ያሉትን ሂደቶች ለከፍተኛ አመራሮች ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በሪፖርታቸውም ቆጣራውን ለማስኬድ የሚያስችሉ ሥራዎችን በተደራጀ መልኩ እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጅ በማዕከላዊ ጎንደር ላይ አርማጭሆ፣ ጭልጋ ቁጥር1 እና አይከል ከተማ ቆጠራውን ለማስኬድ ስጋቶች እንዳሉ በሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡ የአደርጃጀት ለውጥ ያደረጉ ቦታዎች መኖር፣ ‹ሥራ የሌላቸው ወጣቶች እያሉ ለምን የመንግሥት ሠራተኞች ይቆጥራሉ› የሚሉ ጥያቄዎች መነሳት፣ አንዳንድ አካባቢዎች ነፍሰጡሮችን ለቆጠራ መመልመል፣ ተፈናቃዮች አካበቢ የተደረጀ መረጃ አለመያዝ እና በአይ ሲ ቲ ክህሎት የሌላቸውን ባለሙያዎች መመልመል ችግሮች መሆናቸውን አቶ አማረ ለክልሉ አመራሮች አስረድተዋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ‹‹በሥስተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ያጣነውን ታማኝነት በአራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጣራ መመለስ አለብን›› ነው ያሉት፡፡ ቆጠራው ቅድመ ቆጠራ፣ ቆጠራ እና ድኅር ቆጠራ ያለው በመሆኑ በቅድመ ቆጠራ ቆጣሪ እና ተቆጣጣሪ በቂ ዝግጅት አድርገው ታሪክ የማይዘነጋውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸውም አቶ ደመቀ አሳስበዋል፡፡ ‹‹በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ወገኖችም ወደ ቦታቸው እስኪመለሱ በአሉበት ሆነው ይቆጠራሉ›› ነው ያሉት አቶ ደመቀ፡፡ የክልሉ የዞን እና የወረዳ አመራሮች ክልሉ የሚያገኘውን ጥቅም እንዳያጣ ደግሞ ችግሮችን በየጊዜው በመወያየት መፍታት እንዳለባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ መመሪያ ስጥተዋል፡፡
31
በመጋቢት ወር መጨረሻ 4ኛውን ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራን ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተደረገ መሆኑን፣ ቆጠራውን የሚያካሂደው ማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል። የዚህ ቆጠራ ሂደት ዋነኛው ፈተና ብሄርን ከማስመዝገብ ጋር የተያያዘ ነው። በቆጠራ ቅጹ ላይ ዜጎች ማንነታቸውን እንዲገልጹ የሚገደዱት በብሄራቸው እንጅ በዜግነታቸው ወይም በኢትዮጵያዊነታቸው አለመሆኑን የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማሃኝ አስረስ ይናገራሉ። በቅጹ ላይ ኢትዮጵያዊነት እንደ አንድ መስፈርት አለመቀመጡ፣ ማንኛውም ዜጋ የፈለገለውን የማንነት መገለጫ እንዲጠቀም የሚያስችለውን በህገ መንግስትና እና በተለያዩ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች የተቀመጠለትን መብት የሚጥስ ነው። “አንድ ሰው በብሄር ማንነቴ አልመዘገብም፣ መገለጫዬ ኢትዮጵያዊ ነው” ካለ፣ “የለም፣ ብሄርህን እንጅ ኢትዮጵያዊ ማንነትህ አንቀበልም” ማለት “ለአንተ እኔ አውቅልሃለሁ” እንደማለት የሚቆጠር ትልቅ የመብት ጥሰትን የሚያስከትል አካሄድ ነው። ማንም ሰው ማንነቱን በመፈለገው መንገድ ሊገልጽ ሲገባው፣ የግድ በብሄር ቋት ካልተመዘገብክ ተብሎ ከተገደደ፣ ራሱን የመገልጽ ነጻነቱን እንደተገፈፈ የሚቆጠር ነው። አንድ ሰው “በኢትዮጵያዊነቴ እንጅ በብሄሬ አልመዘገብም” ቢል፣ ያ ሰው ይመዘገባል ወይስ ሳይመዘገብ ይቀራል የሚለውም ሌላ ጥያቄ ነው… ከዚህ ቀደም የነበሩ አሰራሮች እንደሚያሳዩት ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ብለው የሚገልጹ ሰዎች፣ የአባታቸውን ስም እንዲናገሩ ከተጠየቁ በሁዋላ፣ መታወቂያቸው ወይም ሌሎች ማህደሮቻቸው ላይ ያባታቸውን ብሄር እንዲጻፍ ሲደረግ እንደነበር አይተናል። ወንድአፍራሽ ወርዶፋ የተባለ ሰው በኢትዮጵያዊነት መዘግቡኝ ቢል፣ ወርዶፋ ኦሮምኛ ስለሆነ፣ አንተ ኦሮሞ ነህ ተብሎ ይመዘባል እንጅ ኢትዮጵያዊነቱ አይመዘገብለትም ነበር። ይህ አሰራር የእናትነትን መብት የሚጥስ አደሎአዊ አሰራር ነው። አንድ ሰው የእናትና አባት ውህድ ሆኖ እያለ ማንነት ብዙውን ጊዜ የሚዛመደው ከአባት ጋር ነው… አንድ ሰው በእናቱ አማራ በአባቱ ኦሮሞ ቢሆን የአባቱን ብሄር ከእናቱ ብሄር የሚያስቀድምበት ምንም አይነት ሳይንሳዊ ምክንያት የለም። በብዙ መስፈርቶች ከታዬ፣ የእናት ማንነት ከአባት ማንነት የተሻለ የሰዎች መገለጫ ሊሆን ይችላል እንጅ ከአባት ማንነት የሚያንስበት ነገር የለም… የብሄር ማንነት በደም ከተቆጠረ ከየት ነው የሚጀምረው፣ ከአያቱ ፣ ከቅድመ አያቱ ወይስ ከዚያ በፊት ካለው ትውልድ ይህን የሚወስነውስ ማን ነው የሰውየውን ብሄር ለመወሰንስ ምን ስልጣን አለው የሚሉትም ጥያቄዎች ሌላ ውዝግብ የሚፈጥሩ ናቸው ሌላው መነሳት ያለበት ከተለያዩ ብሄሮች የተወለደ ሰው “ በተቀመጠው መስፈረት መሰረት” ራሱን ከተለያዩ ብሄሮች እንደተወለደ አድርጎ ቅጹ ላይ ቢሞላ፣ እንዲህ ብለው ለሞሉት ሰዎች የፓርላማ ወንበር ውክልና ያገኛሉ ኢኮኖሚያዊ መብቶቻቸው ይረጋጡላቸዋል…
32
የህዝብና ቤቶች ቆጠራውን ማስተላለፍ ለስኬታማ ውጤት የተሻለ አማራጭ ነው አበራ ውሂብ ዶር እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ 1984 በተደረገው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤቶች ቆጠራ ላይ የማከላዊ እስታቲስቲክስ ጽቤት ሰራተኛ ሆኜ ገና ከኮሌጅ በወጣሁ በሁለት አመት የተሳተፍኩበትና ለሃገሪቱም የመጀመሪያው ስለነበር በብዛት ትዝ የሚለኝና የማረሳው ግዜ ነበር። ወቅቱ የደርግ ጊዜ ነበርና በሲዳሞ ክፍለ ሃገር በያቤሎ አውራጃ የቴክኒክ ሃላፊ ሆኜ ለሶስት ወራት ያህል በመስክ ላይ ስለነበርኩ በመሬት ላይ የነበረውን ሁኔታ በደንብ አስታውሳለሁ። በዚያን አስርተ አመታት 1975 1984 95 በመቶ የሚሆነው የአለም ህዝብ የተቆጠረበት ጊዜ መሆኑን አንድ በተባበሩት መንግስታት የእስታቲስቲክስ ኮሚሽን በወቅቱ የወጣ ሪፖርት ያመላክታል። ያም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ፣ በኤርትራ እና በኦጋዴን የገጠር አካካቢ በወቅቱ በነበረው የበጸጥታ ችግር ቆጠራው አለመካሄዱ የሚታወቅ ሃቅ ነበር። ያኔም እንዳሁኑ ቆጠራውን በበላይነት እንዲመራ በአዋጅ የቆጠራ ኮሚሽን ተቋቁሞ ነበር። አለመታደል ሆኖ ግን እኔ እስከማውቀው ድረስ የህዝብና የቤቶች ቆጠራን በበላይነት የሚመራው የማከላዊ እስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ከመንግስት ተጽእኖ እና ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ ስራውን በትክክል የሰራበትን ጊዜ ግን ትዝ ኣይለኝም። እኔ የመስሪያ ቤቱ አባል በነበርኩበት የደርግ ዘመነ መንግስት እንኳ የአወቃቀር ተጽእኖ በአጀንሲው ላይ እንደነበረ ቢታወቅም ተጽእኖው ግን ከህዝብ ቆጠራው ይልቅ በሌላው የአጀንሲው መደበኛ የስታቲስቲክስ ስራ ላይ ነበር። በግብርና እና በሌሎች የምርት ውጤት ጥናቶች ላይ ጫና ነበር ማለት ይቻላል መረጃዎች በሙያው እውቅት የሌላቸው የበላይ ባለስልጣናት ካላጸደቁት ለተጠቃሚዎች አይለቀቅም ነበር። አሁን ሚን ያህል እንደሆን ባላውቅም ያን ጊዜ መንግስት ያልተስማማባቸው የጥናት ውጤቶች ይፋ አይሆኑም ነበር። ያም ሆኖ ግን ለደርግ የህዝቡን ብዛት ማወቅ ያለው ፋይዳ አሁን ከሚኖረው በጣም ይለያል፤ ክፍልሃገራት የህዝብ ብዛት ፉክክር ስላልነበራቸው ወይም የህዝብ ቁጥር መብዛት ለክፍለሃገራት የሚያስገኘው ልዩ የፖለቲካ ጥቅም ስላልነበረ በአቆጣጠሩ ላይ ብዙም የከፋ ጫና አልታየም። የህዝቡን ቁጥር ማወቁ ግፋ ቢል አስፈላጊ የምግብና ሌሎች ፍጆታዎችን ለመገመት ካልሆነ፣ ወይም ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ የአለም ህዝብ አካል ስለነበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሚያደርገው ትጽእኖ ካልሆነ በስተቀር ሌላ የፖለቲካ ፋይዳው ይህን ያህል አልነበረም ማለት ይቻላል። ብቻ ያኔ የነበረው የፖለቲካ ድባብ አሁን ካለው ፍጹም የተለየ ነበር ብሎ ለመገመት የተለየ አዋቂ ሰው መሆን አያስፈልግም እንደኔ አይነቱም ሰው ይህንን በቀላሉ መገንዘብ ይችላል ብዬ አስባለሁ። ታዲያ የፖለቲካው ሁኔታና የጸጥታ ሁኔታ ለቆጥራ ፍጹም ነው በማይባልበት ጊዜ፤ እንዲያውም የሃገሪቱ አለመረጋጋት ከፖለቲካው ጋር ቁርኝቱ ከፍ ባለበት ሁኔታና ጽንፈኝነት በነገሰበት በዚህ በአሁኑ ሰአት ቆጠራውን እንዴት በትክክል ማስኬድ ይቻላል ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ ማለት ህዝቡን ባለበት ቦታ በተወሰነ የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ በትክክል መቁጠር ማለት ሲሆን ይህንን ለማካሄድ የማአከላዊ እስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን ማድረግ መቻል ያለበት ይመስለኛል። ይህም ቆጠራውን በመመሪያው መሰረት የሚመዘግብ ሰራተኛ ማዘጋጀት፤ በተባለው የጊዜ ሰሌዳ የሚቆጠረው ህዝብጋ ደርሶ ምዝገባውን ማካሄድ፤ እና ከዚያም መረጃውን ሰብስቦ እና አጠናቅሮ የቆጠራውን ውጤት ለህዝብ ማሳወቅ ናቸው። ታዲአ እነዚህን ለማድረግ ከፖለቲካ ጫና ውጪ የሆነ የቆጠራ ሰራተኛ በየቆጠራው አካባቢ ለማግኘትና በተባለው ሰአት ህዝቡጋ ደርሶ ቆጠራውን ለማካሄድ የየአካባቢው ሁኔታ አመቺ መሆን እንዳለበት ግልፅ ነው። እንደእውነቱ ከሆነ በየደረጃው ያሉ የመንግስት ተቋማት ከላይ የጠቀስኳችውን የኤጀንሲው ማድረግ ያለበትን ነገሮችን ለማሳካት ከመርዳትና ከመተባበር ውጭ ሌላ ተጽእኖ መፍጠር የለባቸውም። ሌላው የቆጠራ ጉዳይ መተው ያለበት ለቆጣሪው መቤት ብቻ ነው። የማአከላዊ እስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በቆጠራው ጉዳይ ላይ ፍጹም ነጻ መሆን ይገባዋል። ያለበለዚያ የቆጠራው ውጤት በተወሳሰበው የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ አንድ ተጨማሪ እራስ ምታት እንዳይሆን እሰጋለሁ። ለሃገራችን ፖለቲከኞች አይታያቸው ይሆናል እንጂ የማአከላዊ እስታቲስቲክስ ኤጀንሲ እንደምርጫ ኮሚሽንና እንድ ፍርድ ቤቶች ፍጹም ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ተቋም መሆን አለበት። በተጨማሪ የተቋሙ ቀዳሚ ስራ ደግሞ የሃገሪቱን መረጃዎች በሚገባና ሳይንሳዊ ዘዴን በተከተለ ሁኔታ ሰብስቦ ያለምንም አድሎና ተጽእኖ መረጃ ስጪዊችን ባላጋለጠ ሁኔታ ለተገልጋዮች ወይም ለተጠቃሚዎች ማቅረብ መሆን አለበት። የህዝብ ቆጠራው አካሄድና ውጤትም ከዚህ የተለየ ሊሆን አይገባውም። ታዲያ አሁን ያለንበት ሁኔታ ለምርጫ አመቺ ካልሆነ እንዴት ለቆጠራ አመቺ ይሆናል ተብሎ ተገመተ በርግጥ ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ ከምርጫው በፊት መሆን ቢገባውም የምርጫውን ያህል ጸጥታና መረጋጋት ስልሚፈልግ እንዴት ያንን መንግስት ማየት እንዳልቻለ ለኔ ግልጽ አይደለም። በመሬት ላይ ያለው ጉዳይ የዛሬ 35 አመት እኔ ከነበርኩበት ጊዜ የተለየ ቢሆንም ዋናው ቆጥራ የሚደረገው በታችኛው የመንግስት መዋቅር ማለትም በቀበሌ ወይም በገበሬ ማህበር መሆኑ በአሁኑ ቆጠራ የሚቀየር ጉዳይ አይመስለኝም። ከበጀትና ሌሎች ክልላዊ ድልድሎች ውጭ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ማወቅ ብዙ አዎንታዊ ፋይዳዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። መንግስት ወቅታዊ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፕላን ለማዘጋጀት የህዝቡን ቁጥር በብሄራዊና በክልል ደረጃ ብሎም ወረድ ባሉ የአስተዳደር ደረጃዎች ማወቅ ቢችል ጠቃሚነቱ አያጠያይቅም። እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ የአለም ህዝብ አካል እንደመሆኑ ሁሉ ቆጠራው የአለም ህዝብን በትክክል ለመቁጠር አንድ እርምጃ ተደርጎ ሊገመት ይችላል። ለኤጀንሲው ደግሞ ወደፊት ሌላ የህዝብ ቆጠራ እስከሚካሄድ ድረስ አመታዊ የህዝብን ግምታዊ ቁጥር ለመተንበይ population projection እና ለሌሎች የኤጀንሲው ቀጣይ ጥናቶች ናሙናዊ ማእቀፍ sampling frame ለማዘጋጀት ዋናው ቁልፍ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። እኔ እስከማውቀው ድረስ አመታዊ የግብርና ናሙናዊ ጥናቶችም ሆኑ ሌሎች የእኮኖሚ ጥናቶች ለሚቀጥሉት በርካታ አመታት መሰረታቸው የሚሆነው ይኸው ያሁኑ ጠቅላላ የህዝብ ቆጠራ ውጤት ነውና በትክክል የመሰራቱን አስፈላጊነት ላሰምርበት እፈልጋለሁ። የፖለቲካ ምርጫ በትክክል ወይም ባልተጋነነ ሥህተት መካኼድ እንዳለበት ካመንን የሕዝብ ቆጠራን በትክክል ወይም ባልተጋነነ ሥህተት መካኼድ እንዳለበት መቀበል ግድ ይላል፤ የምርጫን ውስብስብነት ከተቀበልን የሕዝብ ቆጠራን የባሰ ውስብስብነት መገንዘብ ይኖርብናል ብዬ አምናለሁ። ምርጫ በምርጫ ጣቢያ ብዙ ታዛቢዎች ባሉበት ባብዛኛው የሚከናወን ሲሆን ከምርጫ ጣቢያ ደረጃ ሳይወርድ ሊጠናቀቃል፣ በጣቢያ ደረጃ ስለሆነም የብዙ ሰው አይንም ሁኔታውን በቅርብ ሊከታተለው ይችላል፤ ያም ሆኖ ግን በየጊዜው የሚከሰተውን የምርጫ ችግር የሚያውቅ ያውቀዋል። ህዝብ ቆጠራ ላይ ግን የቆጠራው ጣቢያ እኔ እስከማውቀው ድረስ የሚሸፈነው በአንድ ቆጣሪ ነው፤ የሚከናወነውም በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት ነው። ተመራጭ ባይሆንም አንዳንድ ቦታዎች ላይ የአካካቢው የጸጥታ ሰዎች የቆጣሪውን ስራ ለማሳካት ሊያጅቡት ይችሉ ይሆናል። ሆኖም በጸጥታ ጠባቂዎች እገዛ ላይ ተመርኩዞ የሚደረግ ቆጠራ ለመረጃ ብክነት ከመጋለጥም ባሻገር ሰዎች በሚሰጡት መረጃ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው መገመት ተገቢ ነው። ስለዚህ በባለስልጣናት አጀባ የሚካሄድ ቆጠራ ውጤት ላይ ጥያቄ እንደሚጋብዝ ቢታወቅም ከመደበኛ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ ውጪ በመሆኑም የመረጃ ጥራት ጉድለት ሊኖረው ይችላል። ታዲያ አሁን ባለው ሁኔታ ይኼ ጉዳይ ፍጹም ሆኖ ሊከናወን ይችላል ወይ በየቤቱ እየዞረ ቆጣሪው የሚያከናውነው ሰራተኛ በቆጠራ መመሪያው መሰረት መስራት ቢፈልግስ ምን ያህል ይሳካለታል የአካካቢው ሰው እንደመሆኑ መጠን ቆጣሪው ሕሊናውን ነጻ አድርጎ ለመስራትስ አሁን ያለው ሁኔታ ያስችለዋል ወይ እነዚህ ችግሮች ያሉት በአንዳንድ አልፎ አልፎ በሚገኙ ኪስ አካባቢዎች ቢሆን እንኳን ልዩ የግመታ ዘዴዎችን inferential method በመከተል ቆጠራውን ማስተካከል ይቻል ብሎ አማራጭ መፍትሄ ማቅረብ ይቻል ነበር፤ የችግሩ ጀረጃ ግን አልፎ አልፎ በሚገኙ ኪስ አካባቢዎች ላይ ብቻ የተወሰነ አይመስለኝም። ካልተሳሳትኩ በስተቀር በአሁኑ ጊዜ ያለው የሃገሪቱ አጠቃላይ ገጽታ በተሻለ መረጋጋት የመረጋጋት ሁኔታ ላይ መሆን ይገባዋል ብዬ አስባለሁ። ሁኔታው ለቆጠሪዎች የተመቻቸ፣ በየአካባቢው የፖለቲካ ተጽእኖ የማይታይበት፣ የማእከላዊ እስታቲስቲክስ አኤጀንሲም የቆጠራ ተልኮውን ያለ እኔ አውቅልሃለሁ የፖለቲካዊ ጉትጎታ ማጠናቀቅ መቻል አለበት። ይህንን መሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ ረዘም ያለ ጊዜ ይፈጃል የሚል ሃሳብ አለኝ። ይህንን ያህል በርካታ ሃብት አፍስሶ በቆጥራውን ዘግይቶም ቢሆን በትክክለኛ ውጤት ማጠናቀቁ ይሻላል እንጂ አሁኑኑ ብዙ ክፍተቶች ባሉበት ሁኔታ እናድርገው ማለቱ ጉዳቱ ያመዝናል ብዬ አምናለሁ። መንግስት ለምርጫው የወደፊት ተአማኒነት ጥረት እንደሚአደርገው ሁሉ ለህዝብ ቆጠራውም የወደፊት ተአማኒነት የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት ብዬ አስባለሁ። የህዝብ ቆጠራ ውጤት ሁሉንም ፖለቲከኛ ያስደስታል ብሎ ማመን ይችግራል። እንኳን እንደኢትዮጵያ ባለው ታዳጊ ሃገር ይቅርና በአደጉትም ሃገሮችህ የህዝብ ቆጠራ አጨቃጫቂ የፖለቲካ መስመር መፍጠሪያ መንገድ መሆኑን እናያለን። ታድያ በበለጸጉት ሃገሮች ጭቅጭቁ እነማን ይቆጠሩ በሚለው ላይ ሊሆን ይችላል እንጂ በቆጠራው ውጤት ላይ ግን ሲሆን እምብዛም አይስተዋልም። ምክንያቱም ቆጠራው የሚከናወነው እና የሚመራው ኤጀንሲ የሙያው ክህኖት ባላቸው አዋቂ ኤክስፐርቶች እንጂ በፖለቲካ ተሳትፎአቸው በሚመደቡ የፖለቲከኞች ስላልሆነ የቆጠራው ውጤትም ሆነ የኤጀንሲው ተአማኒ መሆን አከራካሪ አይሆንም። ፖለቲከኞችም በቆጠራ ጉዳይ ባጀት ከመመደብ በላይ ጣልቃ ለመግባት አይደፍሩም። ይህ ግን በኛ ሃገር የህዝብ ቆጠራ ታሪክ ሆኖ ባያውቅም አሁን ሃገሪቱን የሚመራው መንግስት ኤጀንሲውን ከፖለቲካ ነጻ ማድረግ አይፈልግም ብዬ መገመት ፍጹም ይቸግረግናል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የለውጡ ሃይል ሌሎች ሃገሪቱ አይታ የማታውቀውንና ለየዲሞክራሲ መሰረታዊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ሲያመቻች በአይናችን አይተናል። የሃገሪቱን ህዝብ በሚገባ ማወቅ በተለይም ለፌደራላዊ ዲሞክራሲ በጣም አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅምና መንግስትም የህዝቡን ቁጥር በትክክል ማወቅ ያለውን ጠቀሜታ በሚገባ ተገንዝቦ፣ ቆጠራውን የሚመራው መንግስታዊ ድርጅት ከማንምና ከምንም የፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ መሆኑን ከቆጠራው በፊት ማረጋገጥ ዪኖርበታል ብዬ አምናለሁ። ስለዚህም በመጀመሪያ የማእከላዊ እስታቲስቲክስ አኤጀንሲ እራሱን ከፖለቲካ ነጻ በሆነ መንገድና በበቂ ሙያተኞች መገንባቱ ግድ ይሆናል። ኤጀንሲው ከፈለገ ሊረዱ የሚችሉ ባለሙያዎችን ማግኘት የሚቸግረው አይመስለኝም። በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተናገሩትን ማስታወስ ይበቃል፤ “ሃገራችንን የተማረ ሰው ድህነት የለባትም” ብለው ነበር። በርግጥም ኤጀንሲውን በዚህ የሙያ መስክ ሊረዱ የሚችሉ በቂ ኤክስተርቶች በአለም ዙሪያ አሉን ብዬ እገምታለሁ። እነዚህን የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸውንና ሃገራቸውን ሊረዱ የሚፈልጉ ሙያተኞች ከሃገር ውስጥም ይሁን ከውጭ ለዚህ ስራ እንዲረዱ ኤጀንሲው ምን ያህል ጥረት እንዳደረገ ባላውቅም ብዙ እንደማይሆን ግን እገምታለሁ። ዋናው ጉዳይ ግን ቆጠራው በሙያተኖች በተሞላ እና በሙያተኛ ብቻ በሚመራ ድርጅት ያለ ምንም መንግስታዊ ተጽእኖ መከናወኑ ስለሆነ ይህ መሟላቱን መንግስት ከቆጠራው በፊት ማረጋገጥ ይኖርበታል። ቆጠራው በዋናነት መሚካኼድባቸው ወረዳና ቀበሌዎች ያሉ ባለስልጣናት የሕዝብ ቁጥር የአስተዳደር ጫና ፈጣሪ እዳ እና የመልካም አስተዳደር መንገድ የወደፊት አመላካች መረጃ እንጂ የፖለቲካ ትርፍ ማካበቻ ዘዴ አድርገው እንዳያዩት በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። እንደዚህ ያለ የተንጋደደ ግንዛቤ በአሁኑ ወቅት በዞንም ሆነ በክልል ደረጃ አይኖርም ብዬ ለመገመት እቸገራለሁ፤ ስለዚህ የህዝብ ቁጥርን ውጤት በትክክል ማወቅ ያለውን ጠቀሜታ በየደረጃው ላሉ ባለስልጣናት ማስገንዘብ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ፤ ታዲያ ይህንን በሚገባ ለማከናወን ኤጀንሲው በቂ ጊዜ ሊኖረው ይገባል ብዬ አምናለሁ። የህዝብ ቁጥርን ውጤት መቀየር ወይም ሆን ብሎ ማሳሳት ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ለህዝቡ በተለይም ለወጣቱ መሚገባ ማስተማር ይገባል። አሁን የሚሰራ ስህተት የሚያምጣውን ችግር የሚረከው ያሁኑ ወጣት ነው፤ ይህንን ደግሞ አዲሱ የሃገሪቱ የለውጥ ሃይል በሚገባ እየሰራበት ስለሆነ የኤጀንሲውን ስራም ያቀለዋል ብዬ እገምታለሁ ሆኖም እታች ወጣቱጋ እስከሚደርስ ጊዜ መውሰዱ ግን አይቀሬ ነው። የግድ አሁኑኑ ይደረግ ብሎ ከማሰብ አላስፈላጊ የጊዜ ገደብ ከመጫን ይልቅ የህዝብ ቆጠራውን የተሳካ ማድረጉ ላይ ቢሰራ ጠቃሚ ይመስለኛል። ያን ያውራ የነበረ ነውና ለቆጠራው መሳካት የተረጋጋና ፀጥታው የተረጋገጠ ሃገራዊ ሁኔታን ማመቻቸት ከሁሉ በላይ ቀዳሚ ጉዳይ መሆን አለበት፤ በተጨማሪ ቆጠራውን አስመልክቶ የህዝቡ ግንዛቤ እንዲያድግ በቂ ትምህርትና ቅስቀሳ ከቆጠራው በፊት መደረግ ይኖርበታል ብዬ አስባለሁ። ቆጠራውን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ትምህርት በየአካባቢው ላሉ የክልል፣ የዞን የወረዳ የገበሬ እና የከተማ ቀበሌ ባለስልጣናትና ሊሰጥ ይገባዋል፤ በርግጠኝነት ለመናገር ያብዛኛዎቹ የቆጠራ ግንዛቤ ከፖለቲካ የተያያዘ ነው ቢሎ መናገር ይቻላል፤ ይህ የተሳሳተ ግንዛቤ በበቂ ትምህርትና ስልጠና መቀየር አለበት። በመጨረሻም ቆጠራውን የሚመራው ኤጀንሲ ለቆጠራው መዘጋጀቱ አስፈላጊ ነው። በአደረጃጀቱም ሆኖ በሰው ሃይል ክምችቱ ከፖለቲካ የራቀ መሆን አለበት። መስሪያ ቤቱ እንደ ፍርድ ቤትና እንደ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ተጽእኖ የማይደረግበትና በራሱ የሙያው ብቃት ባላቸው ሰራተኞቹ ሃላፊነት ሥራውን በሚገባ መስራት የሚችል መሆን አለበት። አሁን ባለንበት ሁኔታ ግን ኤጀንሲው በዚህ ደረጃ ላይ ነው ብሎ መናገር ይቸግራል። መንግስትም ኤጀንሲውን ከፖለቲካ ነጻ በሆነ አደረጃጀት መስሪያ ቤቱን ማደራጀቱ ላይ በማተኮር የህዝብ ቆጠራውን ለተሻለና ለተረጋጋ ጊዜ ማስተላለፉ ተገቢ ነው። ቆጠራው ቢተላለፍ ለስራው የተመደበውን ሃብት ለሌላ አሁን ሊሰራ ለሚችል ተግባር ማዋል ይቻላል ማለት ነው። የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ በእትዮጵያ በማእከላዊ የእስታቲስቲክስ አጀንሲ ውስጥ ለስድስት ዓመት ተኩል እንደ አውሮጳ አቆጣጠር ከ1982 ጀምሮ የሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ በሚገኝ አንድ ፈደራል መስሪያ ቤት ከፍተኛ የእስታቲስቲክስ ባለሙያ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል። በተጨማሪ የፁሁፉ ይዘት የፀሓፊውን የግል ሃሳብ እንጂ በምንም መልኩ የሚሰራበትን መስሪያ ቤት በመወከል አለመሆኑ በቅድሚያ እንዲታወቅ ፀሃፊው ያሳስባል።
33
በዚህ ዓመት በአማራ ክልል የሚከናወነው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ የጠፉ ዜጎችን የማፈላለግ ጉዳይ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ባለፉት 12 ዓመታት ከ2 ነጥብ 5 እስከ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ የአማራ ክልል ነዋሪዎች መጥፋታቸውንና የጠፉት ነዋሪዎች ከአንድ ትልቅ ዞን ሕዝብ ቁጥር በላይ ይሆናሉ እንደሚሆኑ የአማራ ክልል ፕላን ኮሚሽን ባለሙያ ተናገሩ፡፡ ባሕር ዳር፡ የካቲት 262011 ዓምአብመድ ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት ለሦስት ጊዜ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ሥራዎችን አካሂዳለች፡፡ ከአከናወነቻቸው የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች በ1976 ዓም እና በ1987 ዓም የተደረጉት ሁለት ቆጠራዎች እስከ ችግራቸውም ቢሆን ዓለማቀፋዊ ሕጉን የተከተሉ ነበሩ፡፡ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላን ኮሚሽን የሥነሕዝብ ጥናት እና መረጃ ባለሙያ አቶ ታደለ አሳቤ ‹‹ኢትዮጵያ ካደረገቻቸው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራዎች መካከል የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ የተሻሉ ነበሩ›› ብለዋል፡፡ በ1999ዓም የተደረገው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ‹‹ፖለቲካዊ ይዘት የነበረው፤ ለግላዊ ጥቅም እንጅ ያለውን አጠቃላይ ጠቀሜታ ታሳቢ ያላደረገ ነበር›› ብለውታል፡፡ አቶ ታደለ እንዳሉት በአማራ ክልል በቀበሌዎች እና ወረዳዎች በሚሰጠው የጤና እና የሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶች ምዝገባ መሠረት ሲታይ ከ2 ነጥብ 5 እስከ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ጠፍተዋል፡፡ የነበረው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራም የት እንደገቡ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ለመጥፋታቸው ምክንያት የሚሆን በጥናት የተረጋገጠ መረጃም የለም፡፡ አቶ ታደለ በዓለፉት 12 ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከፖሊሲ እና ከበጀት ውጭ እንደነበሩም አመላክተዋል፤ ‹‹የጠፉት ዜጎችም ከአንድ ትልቅ ዞን ሕዝብ በላይ ይሆናሉ›› ብለዋል፡፡ በ1999 ዓም በተደረገ ቆጠራ መሠረት አማራ ክልል ከሌሎች ክልሎች አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ የሆነ የውልደት እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት መጠን እንዲኖረው ተደርጓል ነው ያሉት፡፡ በዚህ ዓመት በሚካሄደው 4ኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ የሥነሕዝብ ባለሙያዎችን የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ እንዳላካተታቸው የተናገሩት አቶ ታደለ ቆጠራው አሁንም ከአድሎ እና ከፖለቲካ ትርክት ካልወጣ ችግሩ ሊደገም እንደሚችል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ አቶ ታደለ በዘንድሮው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ይተገበራል የተባለው ቴክኖሎጂ መልካም የሚባል ቢሆንም ቆጣሪዎቹ ቴክኖሎጂውን በሚገባ ሊያውቁት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ኅብረተሰቡም የልጆቹን እና የንብረቱን መቆጠር ዓላማ እና ጥቅም በውል ማወቅ መቻል እንደሚኖርበት አስገንዝበዋ፡፡ በአማራ ክልል በየጊዜው የሚከናወነው የአስተዳደር ለውጥ ለቆጠራው መዛባት ምክንያት እንደሆነም መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ተናግረዋል፡፡ በየጊዜው የሚፈጠሩት ቀበሌዎች፣ወረዳዎች ወይም ከሌላ ቀበሌ እና ወረዳዎች ላይ የሚቀላቀሉ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ለቆጠራው አስቸጋሪ እንደሚሆኑ ባለሙያው አብራርተዋል፡፡ በአንዳንድ የመንግሥት አካላት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚነሳው የቆጠራ ይዘግይ ጥያቄ አግባብነት እንደሌለው ያነሱት አቶ ታደለ ቆጠራው መካሄዱ በተለየ ሁኔታ ለአማራ ክልል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አስምረውበታል፡፡ ‹‹ቆጠራው መካሄዱም ባለፉት 12 ዓመታት ከበጀት እና ከፖሊሲ ውጭ የነበሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ዜጎች በፖሊሲ እና በበጀት እንዲካተቱ ያደርጋል›› ነው ያሉት፡፡ በ4ኛው የሕዝብ እና የቤቶች ቆጠራ በአማራ ክልል ሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ዳኘው በበኩላቸው ከአሁን በፊት በነበሩት የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ሕዝብ እንዲቀንስ የሆነባቸው ምክንያቶች የቆጣሪዎች ዕውቀት እና ክህሎት ማነስ፣ ቸልተኝነት፣ ማኅበረሰቡ ለማስቆጠር የነበረውው አመለካከት የተዛባ መሆን፣ ቴክኖሎጂዎችን ያለመጠቀም፣ በወቅቱ የነበሩ አመራሮች ትኩረት ማነስ፣ አድሏዊነት መታየት እና የመረጃ አያያዙ እና አተናተኑ ላይ ችግር መፈጠር መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ አቶ አማረ ‹‹የሥነሕዝብ ባለሙያዎች በአስተባባሪነት እንዲሰሩ ተደርጓል፤ በቆጣሪ እና በተቆጣጣሪ ግን መንግሥት ካወጣቸው ዕቅዶች ውጭ ስለሆኑ አይሳተፉም›› ብለዋል፡፡ አቶ አማረ በአለፉት ጊዜያት በተደረጉ የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ የተፈጸሙ ስህተቶች እንዳይፈጠሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በትኩረት እየሰሩ እንደሆነና ከወትሮው በተለየ መልኩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እንደሚውል አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ዓመቱ ቆጠራ ቀደም ብሎ ቀበሌዎች እና መንደሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሠረት በመረጃ ስለተያዙ ችግሮች እንደማይኖሩም አስታውቀዋል፡፡ ከአዲሱ ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘም ቆጠራውን ለሚያካሂዱ ሰዎች ለ13 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እንደሚሰጥና ቴክኖሎጂውም ከዚህ ቀደም የተስተዋሉትን ችግሮች የሚያስቀር መሆኑን አብራርተዋል፡፡ አቶ አማረ በ1999ዓም የተደረገው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት አሁን ላይ ሊኖር እንደማይችል እና ስር የሰደዱ ስህተቶች እንደማይኖሩ ነው የተናገሩት፡፡ ማኅበረሰቡ አሁንም በአለፉት ዓመታት የተፈጠሩት ስህተቶች እንዳይደገሙ መረጃውን በትክክለኛው መንገድ እንዲያደርስም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
34
የህዝብና ቤት ቆጠራ የለም። ☆☆☆☆☆ የህዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት በቀጣይ አመታት በሀገሪቷ ላይ ለሚደረጉ ማንኛውም የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዉሳኔዎች መሰረት ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት 292011 ዓም ሊያካሄድ ያሰበዉ የህዝብና ቤት ቆጠራ ሀ በአገሪቷ ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ለ የአማራ ህዝብ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች እልባት ሳያገኙ ሐ የአማራ ህዝብ በየአቅጣጫው እየተፈናቀለ ባለበት ሁኔታ መ በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ዙሪያ የአብይ አህመድ ፓርቲ ኦዴፓ በለማ መገርሳና ታከለ ኡማ አስፈፃሚነት የዲሞግራፊክ ለዉጥ ለማምጣት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኦሮሞችን በቦታዉ ማስፈር፣ መታወቂያ ማደልና ነባር ነዋሪዎችን የማፈናቀል እኩይ ተግባር እየተፈጸመ ባለበት ሁኔታ ሠ በአማራ ክልል በኦሮሞ ልዩ አስተዳደር የቆጣሪዎች ምልመላ ብሔር ተኮር መሆኑና አማራን ያገለለ በመሆኑ ረ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የጌዲኦ ብሔር ተወላጆች ዘርን መሰረት ባደረገ ጥቃት ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለውና እርዳታ እንዳያገኙ ተከልክለው እጅግ አስከፊ በሆነ ርሀብና ችግር እየረገፋ፣ እየተሰቃዩ ባሉበት ሁኔታ የህዝብና ቤት ቆጠራ አይኖርም።
35
‹‹ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያለ በጀት እየኖረ ነው፡፡ ስለዚህም 4ኛው ዙር የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ለአማራ ሕዝብ ልዩ ጥቅም አለው፡፡›› ፕላን ኮሚሽን ባሕር ዳር፡ መጋቢት 062011ዓም አብመድ አራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መካሄዱ ለአማራ ክልል ሕዝብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በአማራ ፕላን ኮሚሽን የሥነ ሕዝብ ባለሙያ አቶ ታደለ አሳቤ ተናግረዋል፡፡ አቶ ታደለ እንደሚሉት በሀገራችን በ1976፣ 87 እና 99 ዓመተ ምሕረቶች ለሦስት ጊዜያት ቆጠራዎች ተካሂደዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ቆጠራዎች በአንጻራዊነት የጎላ ችግር ያልተስተዋለባቸው ነበሩ፡፡ ይሁንና በ1999 ዓም የተካሄደው ምርጫ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የተደረገበት እንደነበር ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ ችግሮች እንደተስተዋሉበትም አስታውቀዋል፡፡ በኅብረተሰቡ በኩል መረጃን በአግባቡ ያለመስጠት፣ በቆጣሪዎች ደግሞ ሥነምግባርን የተከተለ ቆጠራ እና መረጃ አያያዝ አለመኖርን በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹አመራሩ የቅስቀሳ እና የቁጥጥር ሥራውን በተገቢው መንገድ አለመወጣቱ፣ ከቆጠራ በኋላ መረጃውን በመተንተን ሂደቱ ላይም ችግር መኖሩ ተጠቃሽ ጉድለቶች ናቸው›› ብለዋል፡፡ እንደ አቶ ታደለ ገለጻ የአማራ ሕዝብ ቁጥር አስቀድሞ ከተተነበየው በሦስት ሚሊዮን አካባቢ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ ይህ ማለት በሦስተኛው ዙር ቆጠራ 20 ሚሊዮን ይደርሳል የተባለው 17 ሚሊዮን አካባቢ ሆኖ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ ይህም ከክልሉ የውልደት መጠን አንጻር ትክክለኛ እንዳልነበረና፣ ፓርላማ ድርስም ጉዳዩ ቀርቦ መወያያ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ በአንድ ሀገር ፖሊሲ፣ ዕቅድ፣ ፕሮግራም፣ ስትራቴጂ ለመንደፍ እና መሠረተ ልማት ግንባታ ለማካሄድ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ ትክክለኛ መረጃ ዕቅዶችን በአግባቡ ለማውጣት እና ለማስፈጸም እንዲሁም ትክክለኛ በጀት ለመመደብ ያስፈልጋል፡፡ እንደ ባለሙያው የአማራ ክልል ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ማለትም የአንድ ዞን ነዋሪ የሚሆን ሕዝብ ለ10 ዓመታት ያክል ያለበጀት እንደኖረ ጠቁመው አራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ያለበጀት የኖረው ሕዝብ በበጀቱ እንዲካተት እና የተስተጓሉ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲካሄዱ ያስችላል፡፡ በዚህም ሕዝባችን ተጠቃሚ ይሆናል ነው ያሉት አቶ ታደለ፡፡ ‹‹የሕዝብና ቤት ቆጠራው ከተካሄደ በኋላ ቁጥሩ አንሶም ጨምሮም መምጣት የለበትም›› ሲሉ አቶ ታደለ ተናግረዋል፡፡ የኔ ብሔር ወይም ሃይማኖት ቁጥር ይበልጣል በሚል አጋኖ መገመት እና ማስቀመጥ ከሥነምግባርም ሆነ ከሳይንስ አንጻር ተገቢ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ የአማራ ክልል የውልደት መጠን ከሌሎች ጎረቤት ክልሎች ተቀራራቢ ስለሆነ ‹‹ሰፊ የሕዝብ ቁጥር ልዩነት ይኖራል›› ብለው እንደማያምኑ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ለፖለቲካ ፍጆታ ያልተገቡ ሥራዎች መሠራታቸውንም ተናግረዋል፡፡ በአራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ የአማራ ክልል ሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ዳኘው በበኩላቸው ‹‹ቆጠራው ለአማራ ሕዝብ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ በፊት የተፈጸሙ ችግሮች ይልቅ ማስተካከያው ላይ ማተኮር ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡ በቀጣዩ ቆጠራ ‹‹የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም›› ያሉት አቶ አማረ መረጃው ተሰብስቦ የሚተነተነው ፌደራል ላይ ቢሆንም የክልሉ መንግሥት ሙሉ መረጃውን ይዞ እንደሚከታተል ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ትክክለኛ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ቆጠራ ለማካሄድ ያስችል ዘንድ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም ቆጠራው በአግባቡ እንዲካሄድ በር ይከፍታል ብለዋል፡፡ የቆጠራው ትክክለኛ መረጃ ለራሱ ለመንግሥት ጠቃሚ በመሆኑ ያለፉት ስህተቶች እንደማይደገሙ ያላቸውን እምነት አቶ አማረ ገልጸዋል፡፡
36
የሕዝብና ቤት ቆጠራው ወቅታዊ ሁኔታ ሀ የደቡብ ክልል አሁን ባለው ሁኔታ ለማስቆጠር አቅም የለኝም ብሏል። አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማጓጓዝም ሆነ ቆጣሪዎቹን ማሰልጠን አልቻልኩም ማለቱም ተሰምቷል። ለ የሶማሊ ክልል አክቲቪስቶች ሕዝብና ቤት ቆጠራ መካሄድ የለበትም የሚል አቋም ይዘው ሕዝቡን እያስተባበሩ ነው። ባለፈው የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወሳል። ሐ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። ስብሰባው የተጠራበት ዋና ምክኒያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ አካባቢዎች ቆጠራውን በታቀደለት ጊዜ ለማካሄድ አመች ሁኔታ አለመኖሩን በመገንዘብ ነው። መ አዴፓብአዴን በመረጃ የተደገፉት የአማራ አክቲቪስቶች እያደረጉ ያሉት ዘመቻ ጫና ውስጥ ከቶታል። በየአካባቢው የተበተኑ በራሪ ወረቀቶች ከፍተኛ ጫና መፍጠራቸው ታውቋል። አብዛኛው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ቆጠራው መራዘም አለበት የሚል አቋም ይዘዋል። ይሁን እንጅ አቋማቸውን ቴክኒካል ነገር በማንሳትና ሌሎቹን አሳምኖ በጋራ በማስቆም ላይ ትኩረት አድርገዋል። ሠ የግብርና ልማት ሠራተኞች፣ መምህራንና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች የሕዝብና ቤት ቆጠራውን የመወያያ አጀንዳ አድርገውት ሰንብተዋል። ሕዝባችን የሚጎዳ ምንም ዓይነት ነገር አናደርግም እስከዛሬው የደረሰበት በደል ይበቃዋል እያሉ ነው። ረ አብን በጠንካራ አቋሙ ገፍቶበታል። የፊታችን ማክሰኞ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚያወጣ አስታውቋል። የሕዝብና ቤት ቆጠራ መራዘም አለበት
37
4ተኛው ዙር የህዝብ ቤት ቆጠራ ባሕር ዳር፡ጥር 232011 ዓምአብመድ 1 የህዝብ ቤት ቆጠራ ትርጉም የህዝብ ቤት ቆጠራ በተወሰነ ወቅት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወይም በሀገር ውስጥ በተወሰነ የአስተዳደር ክልል ስለአለው የህዝብ ብዛት እና የስነ ህዝብ ባህሪያት፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ወይም በተወሰነ የአስተዳደር ክልል ስለሚገኙ ቤቶች ብዛት ፣ስለ ቤቶች ሁኔታ የሚገልፁ ስታስቲካዊ ሁኔታ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፣የማጠናቀር፣የመተንተን፣ትክክለኛነቱንም በመገምገም የትንተና ሪፖርት ማዘጋጀት እና የተገኘውን ውጤት ለተጠቃሚዎች የማሰራጨት ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡ የህዝብ እና የቤት ቆጠራ ውጤት ከአነስተኛ የአስተዳደር ክልል ማለትም ከገጠር እና ከተማ ቀበሌ አስተዳደር እሰከ ብሄራዊ ክልል እና በሀገር አቀፍ ደረጃ መረጃዎችን ያስገኛል፡፡ 2 የአራተኛው ዙር ቤት ቆጠራ አስፈላጊነት በሀገራችን እስካሁን ድረስ ሶስት ጊዜ አገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራዎች የተካሄዱ ሲሆን የመጀመሪያው 1976ዓም እና ሁለተኛው በ1987ዓም ሶስተኛው ደግሞ 1999ዓም ተካሂዷል፡፡ በነዚህ ዓመታት ውስጥ በሀገሪቱ የህዝብ ብዛት እና ስርጭት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ሁኔታ ለውጦች ተከስተዋል፡፡ ስለዚህ ከ1999 ዓም የህዝብ እና ቤት ቆጠራ የተገኙትን መረጃዎች ወቅታዊ ለማድረግ፣የተከሰቱትን ለውጦች ለመገምገም ፣አዳዲስ መረጃዎችን በጥራት ለመሰብሰብ እንዲሁም የህዝቡን የወደፊት የስነ ባህሪያት ፣የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አስተማማኝ እና ወቅታዊ ከሆኑ መረጃዎች በመነሳት ለመተንበይ በመጋቢት 292011 ዓም የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ አስፈላጊ ነው፡፡ 3 የአራተኛው ዙር የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ዓላማ የህዝብ ቆጠራው ዋነኛ አላማ ለዕቅድ ዝግጅት፣፤ለፖሊሲ ቀረፃ፣ለአገልግሎት አሰጣጥና የስነ ህዝብ ፖሊሲ አፈፃጸምን ለመገምገም የሚያስችሉ ወቅታዊ እና አስተማማኝ የስነ ህዝብ ማህበራዊ መረጃዎችን በማግኘት የኢትዮጵያውያንን የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል ማድረግ 4 ከአራተኛው ዙር ህዝብ እና ቤት ቆጠራ የሚገኙ መረጃዎች ያላቸው ጠቀሜታ፡፡ የትምህርት ዘርፉን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል በየጊዜው ለሚዘጋጁ እቅዶች እና ፖሊሲዎች የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ እና ጥራትን ለማሻሻል ለሚዘጋጁት እቅዶች እና ፖሊሲዎች፡፡ ለዜጎች በቂ የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል እቅድ ለማዘጋጀት እና ተግባራዊነቱንም ለመከታተል እና ለመገምገም፡፡ የሀገሪቱ ህዝብ ግማሽ ክፍል የሆኑትን ሴቶች በማህበራዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሚዘጋጁ እቅዶች እና ፖሊሲዎች፡፡ የተለያዩ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በተለይም የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ድርቅ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ በዘለቄታዊነት ለማቋቋም የሚያስችል እቅዶዶች እና ፖሊሲዎች ለማዘጋጀት የህዝብ እድገት ከተፈጥሮ ሀብት እና ከባቢ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማድረግ ለሚዘጋጁ እቅዶች እና ፖሊሲዎች፡፡ የዜጎች የመሰረተ ልማት ፍላጎትንጹህ ውሃ፣መብራት፣ቴሌኮምኒኬሽን፣መንገድ ፣የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና ለመሳሰሉትተደራሽነትን እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፡፡ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና በእድሜያቸው ምክንያት ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በሀገሪቱ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ውስጥ እኩል ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ ለሚቀረጹ ፖሊሲዎች ፡፡ ለንግድ ኢንቨስትመንት እና ኢንደስትሪ ልማት አገልግሎትን ለማስፋፋት ለሚነደፉ አስትራቴጅዎች ለእነዚህ እና ለመሳሰሉት ከህዝብ እና ቤት ቆጠራ የሚገኙ መረጃዎች ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ 5 የአራተኛ ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ መቼና እንዴት ይካሄዳል • ቆጣሪዎች በተመደቡበት አካባቢ በተዘጋጀላቸው የቆጠራ ቦታ ካርታ እየታገዙ ከመጋቢት 27 – 29 ከቤት ወደ ቤት በመሄድ በመጀመሪያ በቆጠራ ቦታው ውስጥ የተካለሉ ቤቶችን፣ ቤተሰቦችንና ድርጅቶችን ይመዘግባሉ፡፡ • ቆጠራው በመላ ሀገሪቱ በገጠርና በከተማ በአንድ ተመሳሳይ ቀን መጋቢት 292011ዓም የሚካሄድ ሲሆን ለቆጠራው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ምዝገባው በተከናወነበት ሁኔታ ከመጋቢት 29 ሚያዝያ 20፣ 2011ዓም ከቤት ወደ ቤት በመሄድ ዝርዝር መረጃ ይሰበሰባል፡፡ 6 በአራተኛ ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሚሰበሰቡ መረጃዎች ይዘትና ዝርዝር ሀ ሕዝብን በተመለከተ የሚሰበሰቡ መረጃዎች • ጾታ፣ ዕድሜ፣ ሃይማኖት፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ የብሔር ብሔረሰብ • የትምህርት፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ የጋብቻና የሥራ ሁኔታዎች • ሴት የቤተሰብ አባላት ሲሆኑ የወለዱ ከሆነ ስለልጆቻቸው ብዛት • ወላጆቻቸውን ስላጡ ሕጻናትና ወጣቶች፣ • ስለፍልሰት፣ • በቤተሰቡ ውስጥ ስለተከሰተ ሞት የሚመለከቱ … ወዘተ መረጃዎች ይሰበሰባሉ፡፡ ለ ቤቶችን በተመለከተ የሚሰበሰቡ መረጃዎች • የቤቱ ዓይነት፣ የቤቱ ዕድሜ • የቤቱ ግድግዳ፣ ጣሪያ፣ ኮርኒስና ወለል በአብዛኛው ከምን እንደተሠራ፣ • ቤቱ ያሉት ክፍሎች ብዛት፣ • ቤቱ ያለው የመጸዳጃና የማዕድ ቤት ዓይነት፣ • ቤተሰቡ በምን ዓይነት ማገዶና መብራት እንደሚጠቀም፣ • ቤተሰቡ የመጠጥ ውኃ ከየት እንደሚያገኝ፣ • በቤቱ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና መደበኛ ስልክ ስለመኖሩ ወዘተ መረጃዎች ይሰበሰባሉ፡፡ 7 በቆጠራው የሚካተቱት እነማን ናቸው • በመደበኛ ቤታቸው የሚኖሩ ሰዎች • በሆቴል፣በሆስፒታል እና በሌሎች የጋር እዮሽ መኖሪያዎች ማለትም በአዳሪ ትምህርት ቤቶች፣በህጻናት ማሳደጊያዎች፣በሰራተኛ ካምፖች፣በእስር ቤቶች፣በገዳሞች ወዘተ የሚኖሩ ሰዎች፡፡ • መጠለያ ቤት የሌላቸውየጎደና ተዳዳሪዎች፣ቤተክርስቲያን ፣መስጊዶች፣በመቃብር ቤቶች እና በመሳሰሉት ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች • በአጠቃላይ ጨቅላ ህጻናት፣ታመው አልጋ ላይ ያሉ ሰዎች፣አካል ጉዳተኞች፣ወጣት ወንዶች እና ሴቶች፣የውጭ ሀገር ዜጎች ሁሉም በቆጠራው ይካተታሉ፡፡ 8 በቆጠራው መተግበር ያለባቸው መርሆዎች • ማንኛውም ሰው መቆጠር አለበት • እያንዳንዱ ሰው መቆጠር ያለበት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ 9 በቆጠራው ወቅት ቆጣሪዎችን እና ተቆጣጣሪዎችን እንዴት እንለያቸው፡፡ ቆጣሪዎች ሆኑ ተቆጣጣሪዎች የቆጠራው ሰራተኞች ስለመሆናቸው የሚገልጽ የቆጠራ ባጅ እና ደብዳቤ ይኖራቸዋል፡፡በተጨማሪም ለስራው የሚለብሱት ኮፍያ እና የሚይዟቸው ቦርሳ እንዲሁም የቆጠራ መጠይቆች እና ቅጾች የቆጠራ ኮሚሽን አርማ ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህን ማረጋገጫዎች ያልያዘ ቆጣሪ ወይም ተቆጣጣሪ የሚል ሰው የቆጠራው ሰራተና ባለመሆኑ ሁኔታውን ወዲያውኑ ጉዳዩ ለሚመለከተው ህጋዊ አካል ማሳወቅ ይገባል፡፡ 10ለቆጣሪው ስኬታማት ከህብረተሰቡ የሚጠበቅ ትብብር፡፡ • ቆጣሪዎች ወደየቤቱ በሚሄዱበት ጊዜ ቤት በመገኘት ለሚጠይቁት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን፡፡ • ለሚጠይቁት ጥያቄ የሚሰጡት ምላሽ ለአገር ግንባታ ለሚታቀዱ የልማት ዕቅዶችና ፖሊሲዎች መሰረታዊ ግብዓት የሆኑ መረጃዎችን የሚያስገኝ መሆኑን በመረዳት ትክክለኛ ምላሽ መስጠት፡፡ • በሚገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለቆጠራው ዓላማ እና ጠቀሜታ ለጎረቤቶቻችን በተለይ ላልተማሩ ወገኖች ቆጠራውን አስመልክቶ በተለያየ መንገድ የሚተላላፉ መልዕክቶችን ይዘት በማብራራት በቂ ግንዛቤ እንዲፈጥር በማድረግ ድርሻውን መወጣት አለብን፡፡
38
የሕዝብ እና የቤት ቆጠራን አስመልክቶ፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄአብን የተሰጠ የአቋም መግለጫ በ19989 ዓም የተደረገውን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ተከትሎ፣ መንግሥት ባወጣው ይፋዊ የቆጠራ ውጤት፣ 25 ሚሊየን የሆነ የአማራ ሕዝብ ጠፍቷል ተብሎ ለአገራችን ፓርላማ ሪፖርት መደረጉ ይታወቃል፡፡ በመንግሥት የታመነው እና ጠፋ የተባለው የአማራ ሕዝብ ብዛት 25 ሚሊየን ቢሆንም፣ እኤአ የ1984፣ የ1994 እና የ2007ን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ያጠኑ ምሁራን፣ የታዳጊ አገሮችን የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ፣ የሌሎች ኢትዮጵያውያን ብሔረሰቦች የዕድገት ምጣኔ እና አስቀድሞ የነበረውን የአማራ ሕዝብ ቁጥር መሰረት አድርገው በሰሩት ትንታኔ፣ እኤአ 2007 ዓም በ19989 ዓም በተደረገው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ መኖራቸው የተካደው ወይም እንዲጠፉ የተደረጉት አማሮች ቁጥር እስከ 62 ሚሊየን ሕዝብ እንደሚደርስ አረጋግጠዋል፡፡ በ1998 ዓም በተደረገው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ በአማራ ሕዝብ ላይ ከተፈፀመው የቁጥር እልቂት numerical genocide በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ እና በጉራጌ ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ የቁጥር እልቂት የተፈፀመ ሲሆን፣ የቅማንትን ሕዝብ ኅልውና በመካድ በአገራችን ከተከናወኑ የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ታሪክ አስነዋሪ ወንጀል የተፈፀመበት መሆኑን፣ የመስኩ ምሁራን በጥናት አረጋግጠዋል። የአንድ ሕዝብ የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ የሚሰላው እና በመሬት ላይ የሚከናወነው ቆጠራ እውነተኛነት የሚመሳከረው፣ መሬት ላይ በሚደረግ ቆጠራ ብቻ ሳይሆን፣ አስቀድሞ ተለይቶ ታውቋል ከሚባል የሕዝብ ቁጥር እና የዕድገት ምጣኔ ጋር ተሰናስሎ ተመሳክሮ በመሆኑ፣ በአንድ የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ወቅት የተሰራ ጥፋት የዘላለም ጥፋት ሆኖ እንደሚቀር ይታወቃል። በመሆኑም በዚህ ዓመት የሚከናወነው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ፣ ከአድልዎ እና ከሸፍጥ ነፃ ይሆናል ቢባል እንኳን፣ ቆጠራው አስቀድሞ በተከናወነው የሕዝብና የቤት ቆጠራ የተፈፀመው የቁጥር እልቂት ጥገኛ መሆኑ የታመነ ነው። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄአብን ባለፉት የሕዝብ እና የቤት ቆጠራዎች ሆን ተብሎ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውን የቁጥር እልቂት፣ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እና ወንጀሉ ከፊታችን በሚደረገው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ላይ እንዳይደገም ለማድረግ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መክሮበታል። ይሁንና በችግሩ ላይ ይኼ ነው የሚባል መፍትሔ ሳይገኝ፣ መንግሥት የሕዝብ እና የቤት ቆጠራውን ለማከናወን ውሳኔ ላይ መድረሱ፣ ንቅናቄያችንን በእጅጉ አሳስቦታል። ስለሆነም አብን ለመንግሥት የሚከተለውን ጥሪ ያደርጋል፡ ፩ መንግሥት የሕዝብ እና የቤት ቆጠራውን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝመው እና ባለፈው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ በአማራ ሕዝብ፣ በአዲስ አበባ ሕዝብ፣ በጉራጌ ሕዝብ እና በቅማንት ሕዝብ ላይ የተፈፀመው የቁጥር እልቂት numerical genocide፣ በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲጣራ። ፪ የ19989 ዓም የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ውጤት ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ እና ከፊታችን የሚከናወነው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ ስሌት projection ከ19989 ዓም በፊት የተደረጉ የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ውጤቶችን ብቻ መሰረት አድርጎ እንዲከናወን። ፫ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን የተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 44997 እንዲከለስ፤ በተለይም የአዋጁ አንቀጽ 6 ላይ የተመለከተው የኮሚሽኑ አባላት ስብጥር፣ ተመጣጣኝ እና ሚዛናዊ ውክልና ኖሮት፣ ከመንግሥት ባለሥልጣናት በተጨማሪ በሕዝብ እና በመንግሥት እምነት የሚጣልባቸው ኢትዮጵያውን ምሁራን ተካተው ኮሚሽኑ እንደገና እንዲቋቋም፡፡ ፬ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለሥልጣን የተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 44297 እንደገና እንዲከለስ እና የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆኑ ባለሙያ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲደራጅ፡፡ ፭ አስር ሺህ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለማከፋፈል እምነት ያልተጣለበት የኢትዮጵያ መረብ ደኅንነት ኤጁንሲ INSA ያዘጋጀው የመረጃ ማሰባሰቢያና ማደራጃ ሶፍትዌር፣ ከመቶ ሚሊየን በላይ ሕዝብ ለመቁጠር እምነት ሊጣልበት ስለማይችል፣ በኢንሳ የተመረተው የኮምፒውተር ሶፍትዌር ውድቅ እንዲደረግ እና ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሕዝብ ቆጠራ መረጃ መሰብሰቢያና ማደራጃ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እንዲውል። ፮ በ19989 ዓም በተደረገው ቆጠራ በኃላፊነት የተሳተፉ ግለሰቦች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱና እንዲጠየቁ። ፯ በወልቃይት እና በራያ ቆጠራው ከመከናወኑ በፊት፣ አካባቢዎቹ በፌዴራል መንግሥቱ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ እየጠየቅን፤ መንግሥት ጥያቄዎቻችንን ተቀብሎ ለሚወስዳቸው የማስተካከያ እርምጃዎች፣ ንቅናቄያችን አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ከወዲሁ እናስታውቃለን። መንግሥት ንቅናቄያችን ያቀረባቸውን የመፍትሔ ሐሳቦች የማይቀበል ቢሆን እና ከላይ የተጠቀሱት የሕግ፣ የተቋማት እና የቴክኖሎጂ ማሻሻያ እርምጃዎች ሳይወሰዱ፣ ቆጠራውን የሚያከናውን ቢሆን፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብና የቤት ቆጠራ ውጤቱን የማይቀበለው መሆኑን በአፅንዖት እየገለፅን፣ የአማራን ሕዝብ የፍትኅ እና የእኩልነት ጥያቄዎች ባለመቀበሉ ምክንያት በሕዝብና በቤት ቆጠራ ሂደቱ እና ውጤቱ ላይ ለሚደርሰው ኪሳራ መንግሥት ኃላፊነት የሚወስድ መሆኑን፣ ከወዲሁ እናስታውቃለን።
39
4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማከናወን መምህራንን ጨምሮ 180 ሺህ ሰራተኞች ይሰማራሉ ተባለ On Feb 6 2019 1235 አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2011 ኤፍቢሲ አራተኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማከናወን መምህራን፣ የግብርናና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 180 ሺህ የመንግስት ሰራተኞች እንደሚሰማሩ ተገለጸ። የማዕከላዊ ስታቲስትክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ቆጠራው ከስህተት የጸዳ ለማድረግ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይልና በአሰራር ስርዓት ልዩ ዝግጅት ስለመደረጉ ተናግረዋል። አቶ ቢራቱ የተጋነነ የቁጥር መቀነስና መጨመር እንዳያጋጥም አስቀድሞ በመላው ሀገሪቱ 150 ሺህ የቆጠራ ካርታ በማዘጋጀት የእያንዳንዱን የቤተሰብ ዝርዝር ቅድመ መረጃ መያዙን ገልጸዋል። እንዲሁም ከ37 ሺ በላይ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን በመክፈት ባለሙያዎች በመላው ሀገሪቱ እንዲሰማሩ ይደረጋልም ብለዋል አቶ ቢራቱ። በተጨማሪም ቆጠራውን በአጭር ጊዜና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናውን የሚያስችል ቴክኖሎጂ በተያዘው ዓመት ወደ ስራ እንደሚገባም ተገልጿል። ቆጠራ የሚደረግባቸው ታብሌት ኮምፒዩተሮች ከቆጠራ ካርታ የቆጠራ የአሰራር ስርዓቶች ጋር በዳታ ቤዝ እንዲገናኙም ተደርጓል። በአሁኑ ወቅት በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የቦታ ይገባኛል ጥያቄዎችን በምን መልኩ ለማስተናገድ አቅዷል ተብለው የተጠየቁት አቶ ቢራቱ፥ የቆጠራ ካርታውን ከሚያዘጋጅበት ጊዜ ጀምሮ ኤጀንሲው እክል ገጥሞት እንደነበር አንስተዋል። በሚነሱ አለመግባበቶች ካርታ ያልተሰራላቸው ከአምስት የማይበልጡ አካባቢዎች እንዳሉም ጠቅሰዋል። ሆኖም ጉዳዩ ከህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ቀርቦ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ቆጠራው በአካባቢዎቹ እንደሚደረግ ጠቅሰው፥ ውጤቱ ይገባኛል በሚሉት ወረዳ፤ ዞንም ይሁን ክልሎች አይካተትም ብለዋል። መጋቢት 29 የሚጀመረው የህዝብና ቤት ቆጠራ በቴክኖሎጂ መታገዙ ካለማወቅ የሚፈጠሩ ችግሮችን በቅርበት ለማረምና ሆን ብለው ስህተት እንዲፈጠር የሚሰሩት ቆጣሪዎች ካሉም ለይቶ በህግ ፊት ተጠያቂ ለማድረግ ያስችላልም ብለዋል አቶ ቢራቱ።
40
በህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ የመረጃ ደህንነትና የሳይበር ጥቃት እንዳይኖር ዝግጅት ተደርጓል አዲስ አበባ ጥር 232011 በአራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ የመረጃ ደህንነትና የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ቆጠራው ተዓማኒ የሆነ ውጤት እንዲኖረው ለማስቻል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋቱም ተጠቁሟል። ኤጀንሲው የቆጠራውን ቀንና የዝግጅት ስራዎችን ዛሬ ይፋ ሲያደርግ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቢራቱ ይገዙ እንደተናገሩት ፤ የዘንድሮውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ወቅታዊ፣ ጥራት ያለው፣ ተአማኒና ተቀባይነት ያለው ለማድረግ የአሰራር ማሻሻያዎች ተደርገዋል። ከዚህ ቀደም በወረቀት ይካሄድ የነበረው የመረጃ አሰባሰብ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲካሄድ፣ በአንድ ቋንቋ ይደረግ የነበረውን የቆጠራ አሰራር በአምስት ቋንቋዎች እንዲካሄድና የመረጃ ደህንነትና የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሰርቷል። ለቆጠራው 152 ሺህ ካርታዎችና ከ37 ሺህ የመቆጣጠሪያ ቦታ ካርታዎች በዲጂታል የተዘጋጁ ሲሆን ዋናው የቆጠራ መረጃ በ’ታብሌት’ አማካኝነት እንደሚካሄድ ገልጸዋል። የቆጠራው ስራ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በተመሳሳይ ወቅት እንዲካሄድ መደረጉ የመረጃውን ተአማኒነትና ፍጥነት እንደሚያግዝ ተገልጿል። የቆጠራውን መጠይቆች ግልጽ ለማድረግና በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ በአፋርኛና በሶማሊኛ እንዲዘጋጁ መደረጉን ኤጀንሲው ገልጿል። ከዚህ ቀደም የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጣ የአማካሪ ምክር ቤት ተቋቁሞ የቆጠራውን ተአማኒነት ለመጨመር መሰራቱን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ቆጠራው ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 20 ቀን 2011 ዓም ድረስ የሚከናወን እንደሚሆን ታውቋል። የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በበኩላቸው የህዝብና ቤት ቆጠራ ለልማት የዕቅድ ዝግጅት፣ ለፖሊሲ ቀረጻ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም። የህዝብና ቤት ቆጠራው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የሲቪክና የሙያ ማህበራት፣ ሕዝባዊ አደረጃጀቶች የኃይማኖት ተቋማት ህዝቡን በማስተማርና በመቀስቀስ ለቆጠራው መሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። በቆጠራው የጤና፣ የትምህርት፣ የቤት፣ የቴክኖሎጂ አጠቀቀምና የፖለቲካ ጉዳዮች ተካተው መረጃ የማሰባሰብ ተግባር እንደሚከናወን ሚኒስትሯ አመልክተዋል። ”በተዘረጋው ዘመናዊ አሰራር ከዚህ ቀደም የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚያገኙ ይታመናል” በማለት ገልጸው ለቆጠራው መላው ህብረተሰብ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል። በኢትዮጵያ ሶስት ጊዜ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የተካሄደ ሲሆን አራተኛው በጸጥታ ችግር የተነሳ መራዘሙ ይታወቃል።
41
አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ ታግዞ እንደሚከናወን ተገለጸ Wed Feb 20 2019በአድማሱ አራጋውአካሉ ጰጥሮስ የሀገር ዉስጥ ዜና በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከፖለቲካና ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ ታግዞ እንደሚሰራ የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ገልጿል፡፡ በዘንድሮ የህዝብና ቤት ቆጠራ በተለያዩ ምክንያቶች ከአከባቢያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችንም መቁጠር የሚያስችል ቴክኒክ መዘጋጀቱን የኮሚሽኑ ፀሓፊ አቶ ቢራቱ ገዙ ለዋልታ ቴሌቭዥን ገልፀዋል፡፡ በዘንድሮ ቆጠራ የኮሚሽኑ የአስተዳደር ሠራተኞችን ጨምሮ ከ1 መቶ 85 ሺህ በላይ ቆጣሪዎች የተዘጋጁ ሲሆን ከፖለቲካ ወገንተኝነት እንዲሁም ከዘር በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ ቆጠራው በተሳካ መልኩ እንዲካሄድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሣትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለመጡ 1200 የምርጫ ኮሚሽን ኃላፊዎች ለስድስት ቀናት የሚቆይ የአሠልጣኞች ሥልጠና በአዲስ አበባ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በሥልጠናው የተሣተፉ ኃላፊዎችም በቀጣይ በየአካባቢው ለሚገኙ ተሣታፊች ሥልጠና ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 20 ድረስ ይካሄዳል፡፡
42
የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ መጋቢት 29 ሊካሄድ ነው፡፡ ፡፡ ባሕር ዳር፡ጥር 232011 ዓምአብመድ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ ፕላን ኮሚሽን ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ 4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ በሚቀጥለው መጋቢት 292011 ዓም ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ በ1979፣1987 እና 1990 ዓም ላይ ለሶስት ጊዜ ሲካሄድ በርካታ ቅሬታዎች ይነሱበት ነበር፡፡በተለይም በአማራ ክልል ህዝብ ቁጥር ላይ ትክክለኛ መረጃ ሪፖርት አልተደረገም የሚል ቅሬታ ተነስቷል፡፡ ስለሆነም በ4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ከወረቀት አሰራር ወጥቶ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ስለሚካሄድ ቅሬታዎችን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ በሀገሪቱ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት መራዘሙ ይታወሳል፡፡
43
4ኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ተራዘመ፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 092011ዓም አብመድ መጋቢት 29 ቀን 2011ዓም እንደሚካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው 4ኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በድጋሜ ተራዘመ፡፡ ከዓመት በፊት ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በተወሰኑ ክልሎች በነበረ የፀጥታ ችግር መራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡ የፀጥታ ችግሮች ተቀርፈው በዚህ ዓመት እንደሚካሄድ ተጠብቆ የነበረና ሰፊ ቅድመ ዝግጅት የተደረገ ቢሆንም ዋልታ እንደዘገበው የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ አብመድ ከሰሞኑ በሕዝብና ቤቶች ቆጠራው መካሄድ ዙሪያ በማኅበራዊ ገጹ የሕዝብ አስተያዬት ጠይቆ የነበረ ሲሆን ብዙዎቹ አስተያዬት ሰጭዎች ‹‹ባለው ነባራዊ ሁኔታ መካሄድ የለበትም›› የሚል ሐሳብ ሰጥተው ነበር፡፡ ምንጮቻችን እንደነገሩን ደግሞ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽኑ የቆጠራው ይራዘም ውሳኔ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል።
44
የሕዝብ አለመቆጠር ክልሉን ጥቅም እንደሚያሳጣው ፟፟መገንዘብ እንደሚገባ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አሰማኸኝ አሳሰቡ ባሕር ዳር፡ ጥር 292011 ዓም አብመድ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ እንደሚከናወን አቶ አሰማኸኝ አስረስ ተናገሩ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በየ10 ዓመቱ የሚደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ መጋቢት 29 ይጀመራል፡፡ ለአራተኛ ጊዜ ነው ቆጠራው የሚከናወነው፡፡ ለህዝብ እና ቤት ቆጠራው የሚያግዙ 180 ሺህ የሚጠጉ ታብሌት ኮምፒውተሮች ተገዝተዋል፤ መተግበሪያም ተጭኖላቸዋል፡፡ የሀይል እጥረት ችግር እንዳይኖርም 26 ሺህ የሀይል ባንክ ግዥ ተፈጽሟል፡፡ ቆጠራው ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ይከናወናል ነው የተባለው፡፡ ወደ እያንዳንዱ ቤት ተቆጣጣሪና አረጋጋጮችን የያዙ ሶስት ሰዎች ለምዝገባው ያመራሉ፡፡152 ሺህ የቆጠራ ካርታዎችም ተሰናድተዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ በአማራ ክልል 37 ሺህ 1 መቶ 96 የቆጠራ ካርታዎች ናቸው የተዘጋጁት፡፡ በ2009 ዓም ሊካሄድ የታሰበው ቆጠራው በሀገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት በሁለት አመታት ዘግይቷል፡፡ ለሥራው መሳካትም በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ላቀ አያሌው የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽንም ተመስርቷል፡፡ በመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽቤት የሚመራ ነው፡፡ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ አካላትን ያቀፈ ነው፡፡ በወረዳ ደረጃም በመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የሚመራ ኮሚቴው ተቋቁሟል፡፡ ከክልሉ ውጭ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ኑሯቸውን የመሰረቱ የአማራ ብሔር ተወላጆች የሚቆጠሩት ባሉበት ክልል ነው፡፡ ኦሮሚያ ክልል ይህን ያህል ህዝብ አለው ሲባል የአማራውን ጨምሮ ነው፡፡ በአንፃሩ አማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጅ ሰዎችም በተመሳሳይ፡፡ ነገር ግን ብሔራቸው ይመዘገባል፡፡ ይህም በተናጠል ይህን ያህል አማራ፣ ኦሮሞ ወይም ሌሎች ብሔሮች በዚህ ክልል ውስጥ አሉ ብሎ ለመናገር ያግዛል፡፡ እንዲመዘገቡ እና በምዝገባው ወቅትም አንዳይደናገሩ በድሬደዋ፣ ሀረሪ፣ ጎባ፣ ጅማ የአማራ ተወላጆችን ሰብስቦ የማስገንዘብ ስራ ይከናወናል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አሰማኸኘ፡፡ በተረፈ ግን ማንኛውም ቆጣሪ እንዲህ ሁን፣ የዚህ ብሔር ሁን ብሎ መደራደርና ማዘዝ አይችልም ብለዋል፡፡ ‹‹ይህ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ አማራ በብዛት ምን ያህል እንደሆነ የምናውቅበት ነው፤ ያለፉትን ስህተቶች መርሳት ያስፈልጋል፤የፈሰሰ ውሃ አይታፈስምና›› ብለዋል አቶ አሰማኸኝ፡፡ የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራው የህልውና ጉዳይ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ ሌላ ክልል ውስጥ ሆነው የማንነት ጥያቄ ያነሱ ሰዎች ባሉበት ክልል ይቆጠራሉ፤ብሔራቸውን ሲጠየቁም ይመዘገባል፡፡ በትግራይ እና በአማራ መካከል ያለውን የራያና የወልቃይት የማንነት ጥያቄ በዋቢነት አቅርበዋል፡፡ በግጭቶች መንስኤነት ተፈናቅለው በክልሉ በመጠለያዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ይቆጠራሉ፡፡ ከየት አካባቢ እንደተፈናቀሉ፡ በዚህ ዓመት ከህዝብና ቤቶች ቆጠራ በላይ ትኩረት ሰጥተን የምናከናውነው ስራ የለም ያሉት አቶ አሰማኸኝ አስረስ መቆጠር መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታ ከመሆኑ ባለፈ አለመቆጠር ክልሉ ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም እንደሚያሳጣው መገንዘብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ዘጋቢ፡ኪሩቤል ተሾመ
45
ግጭት ያለባቸውን አካባቢዎችና የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ መጋቢት 29 በሚጀመረው የህዝብና ቤት ቆጠራ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችና የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ ዜጎችን ጉዳይ በተመለከተ እያንዳንዱ ክልል ከለውጡ በኋላ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሁለት ወራት በፊት ስብሰባ ተደርጎ መገምገሙን በኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነትና መረጃ አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ሁሉም ክልል የየራሱን ሪፖርት ካቀረበ በኋላ፣ የቆጠራ ኮሚሽኑ መሰረታዊ ነጥቦች ላይ በሰፊው ውይይት አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡ በዚህም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የህዝብና ቤት ቆጠራውን ለማካሄድ እንደ አማራጭ ክልሎች በአስቸካይ ተነጋግረው ችግሮችን በፈቱባቸው አካባቢዎች የቆጠራ ካርታ መሰራቱንም ገልጸዋል፡፡ አቶ ሳፊ እንደሚሉት ክልሎች ችግሩን መፍታት ባልቻሉባቸውና የቆጠራ ካርታ ባልተሰራባቸው አካባቢዎች ‘’ልዩ የቆጠራ ቦታ’’ ‘’Special Enumiration area’’ ተብሎ ተይዞ ቆጠራው ይካሄዳል፡፡ በግጭቱ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ በተመሳሳይ ውይይት ተደርጎ የተፈናቃዮች ብዛትና ያሉበት ሁኔታ መለየቱም ተመልክቷል፡፡ በዚህም የግጭቱን መንስኤ በመለየት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ተመልሰዋል፡፡ ወደ ቀያቸው ያልተመለሱ ዜጎችን ለመመለስ ክልሎች ከፌዴራል መንግስት ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል፡፡ የማንነት ጥያቄን በተመለከተ የህዝብና ቤት ቆጠራ ከማንነት ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነም ኤጀንሲው ገልጿል፡፡ በዚህም ማንኛውም ሰው ወይም አካል የማንነት ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረብ እንደሚችልና ከመቆጠር የማያግድ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
46
‹‹ባለፈው የሕዝብና ቤት ቆጠራ የአማራ ክልል ሕዝብ ቅሬታ ነበረው፤ አሁን ይህን ቅሬታ ለመፍታት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል፡፡›› የአማራ ክልል ፕላን ኮሚሽን ባሕር ዳር፡ የካቲት 262011 ዓምአብመድ በአማራ ክልል ባለፉት ጊዜያት የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ሲካሄድ የተሠሩ ስህተቶች ከዕውቀት ማነስ የመነጩ እንደነበሩና ስህተቶችን ለማረም መንግሥት በስፋት ሊያስተምር እንደሚገባ አብመድ ያነጋገራቸው አስተያዬት ሰጭዎች ተናገሩ፡፡ አራተኛውን የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ በተመለከተ ለአብመድ አስተያዬት የሰጡት በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች ‹‹ባለፉት ጊዜያት ቆጠራ ሲካሄድ የሠራናቸው ስህተቶች ከዕውቀት ማነስ የመነጩ ነበሩ፤ ያለንን ቤተሰቦች ሁሉንም አላስመዘገብንም፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ልጆችን ማስቆጠር ትክከል አይደለም የሚል የተሳሳተ እምነት ስለነበረንና የማስቆጠሩን ጥቅም ስለማናውቅ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ስለጥቅሙ ለሕዝቡ ትምህርት ሊሰጥ ይገባል›› ብለዋል፡፡ ኅብረተሰቡ የሕዝብና ቤት ቆጠራው በማኅበራዊ፤ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ዘርፎች ያለዉን ፋይዳና ጉዳቱን ተረድቶ በቆጠራው ዕለት በነቂስ እንዲሳተፍ አስቀድሞ ትምህርት መሰጠት እንዳለበት ነው አስተያዬት ሰጭዎች የተናገሩት፡፡ ከዚህ በፊት በነበረው የሕዝብና ቤት ቆጠራ የተሳተፉ የቆጠራ ባለሙያዎች ደግሞ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራን በተመለከተ በአመለካከት ላይ የተሠራ ግንዛቤ በቂ ባለመሆኑ አንዳንድ ቦታዎች ሰዎች የቤታሰብ ቁጥራቸውን ቀንሰው ሲያስመዘግቡ መታዘባቸውንና ባለሙያዎችም ያለውን ድካም በመፍራት አንድ ቦታ ላይ ሆነው በግምት ሞልተው ይመለሱ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ጉዳዩ የሕዝብን ጥቅም የሚያሳጣ በመሆኑ በዚህ ቆጠራ ላይ ይህን ላለመድገም መሠራት እንዳለበትም አስያዬት ሰጥተዋል፡፡ በየ10 ዓመቱ የሚደረገዉ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ለምርጫ፣ ለዕቅድ ዝግጅት፣ ለክትትልና ግምገማ እንዲሁም ለምርምር የሚጠቅሙ ሕዝብን የሚመለከቱ መረጃዎችን በቆጠራ መሰብሰብ፣ ማጠናከር፣ መገምገምና ማሰራጨት በመሆኑ በአራተኛዉ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ፍትሐዊና ትክክለኛ መረጃ ለማሰባሰብ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በድሉ ድንገቱ ተናግረዋል፡፡ አቶ በድሉ እንደገለጹት የአንድን ሀገር የልማት እንቅስቃሴ ለመምራት የሕዝቡን ቁጥር ማወቅ ትልቅ ፋይዳ አለዉ፡፡ እንደ ሀገር እና እንደ ክልል የሚወጡ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ሕዝቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ከተፈለገ የሕዝብን ቁጥር ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ሕዝቡን ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በነብስ ወከፍ ደረጃ ተቆጥሮ በትክክል መታወቅ ይኖርበታልም ነው ያሉት፡፡ የሚሰበሰቡ የሕዝብና ቤት ቆጠራ መረጃዎች ትክክለኛ ካልሆኑ ሕዝቡን በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ ፍትሐዊ ተጠቃሚነቱን እንደሚያሳጡት ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል፡፡ ኢኮኖሚዉ የሚያመነጨዉን ሀብት በፍትሐዊነት ተጠቃሚ ለማድረግ ትክክለኛው የሕዝብ ብዛት መታወቅ አለበት፡፡ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና አገልግሎት እና የንጹህ መጠጥ ዉኃ ለመዘርጋት በአንድ አካባቢ የሚኖርን ሕዝብ ብዛት መታወቅ አለበት፡፡ የሕዝቡ ብዛት በትክክል ካልታወቃ ሕዝቡ ከሀገሪቷ ሀብት በፍትሐዊነት እንዳይጠቀም ያደርጋልም ነው ያሉት፡፡ የሕዝብ ቁጥርን በፖሊቲካዊ ጥቅሞቹ ሲታይ ለአብነት በምርጫ ውክልና የሚሰጠው በሕዝብ ብዛት ነዉ፤ ስለሆነም የሕዝቡ ቁጥር ካልታወቀ ሕዝቡ በብዛቱ ልክ ማግኘት ያለበትን ዉክልና ሳያገኝ ይቀራል ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ አካል ተዋቅሮ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የትምህርትና ቅስቀሳ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአማራ ክልል 37 ሺህ 196 የሚጠጉ የቆጠራ ቦታዎች ተለይተዋል፡፡ በገጠር የቆጠራ ቦታ ከ100 እስከ 150 ቤተሰብ ሲይዝ በከተማ ደግሞ ከ150 እስከ 2መቶ ቤተሰብ ታሳቢ ያደረገ ነዉ፡፡ ቆጠራውን ለማከናወንም 34 ሺህ 351 ቆጣሪዎች ተመልምለዋል፡፡ 8ሺህ 760 ቆጠራውን የሚከታታሉ ባለሙያዎች ሱፐርቫዘሮች ይሳተፋሉ፡፡ መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም የሚጀመረዉ የዚህ ዓመት የሕዝብና ቤት ቆጠራ ልዩ የሚያደርገው በቴክኖሎጂ የተደገፈ መሆኑ ነዉ፡፡ ሥራው በ‹ጅፒኤስ ቴክኖሎጅና ሶፍትዌር› የሚታገዝ መሆኑም ታውቋል፡፡ ለቴክኖሎጂው መሳካት በቅርበት የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ የሚችሉ 188 የኢንፎርሜሽንና ኮምፒዉተር ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እየተመለመሉ መሆኑም ታውቋል፡፡ እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ ከሆነ በአማራ ክልል የቴክኖሎጂውን ውጤታማነት ለመፈተሸ 10 ቦታዎች ተመርጠዉ የሙከራ ቆጠራዎች ተካሄደዉ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡ ቴክኖሎጂዉ መሠረታዊ ችግር እንዳይኖርበት በባለቤትነት ይዞ የሚሠራዉ የፌዴራል ማዕከላዊ ስታስትክስ ኤጀንሲ ነዉ፡፡ በ1999 ዓም በተደረገዉ የቤትና የሕዝብና ቤት ቆጠራ መሠረታዊ ክፍተት በመኖሩ የአማራ ክልል ሕዝብ ቅሬታ ያለዉ መሆኑን አቶ በድሉ አስታውሰው ዘንድሮ ስህተቱ እንዳይደገም ሁሉም በነቃና በባለቤትነት መሳተፍ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በየደረጃዉ ያለዉ የመንግሥት መዋቅር ትኩረት ሰጥቶ በትክክል ተፈፃሚ እንዲሆን መሥራት አለበት፡፡ የሃይመኖት አባቶች፣ በመንግሥት እና በተለያዩ ድርጅቶች ዉስጥ ያሉ ሠራተኞች ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በመሥራት የበኩላቸዉን እንዲወጡ ኮሚሽነር በድሉ ድንገቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
47
ስለሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ግንዛቤው እንደሌላቸው አብመድ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ገለጹ ባሕር ዳር፡ የካቲት 302011 ዓምአብመድ አርሶ አደሮች ስለሕዝብ እና ቤት ቆጠራው ዕውቅና እንዲኖራቸው እየሠራ መሆኑን ደግሞ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም ይጀመራል፡፡ ለሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ከወዲሁ ሰፊ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረገ መሆኑንም በመንግሥት በኩል እየተገለጸ ነው፡፡ ከዝግጅቶች መካከል ኅብረተሰቡ ቤቶችንና ልጆቹን እንዴት ማስቆጠር እንደሚገባው የግንዛቤ ፈጠራ መሥራት አንዱ ነው፡፡ በከተሞች አካባቢ ያለው ሕዝብ ስለቆጠራው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አማራጮች የተሻለ ግንዛቤ እንደሚያገኝ ይገመታል፡፡ ነገር ግን ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የአማራ ክልል ሕዝብ በገጠር የሚኖር በመሆኑ በቂ የሚዲያ አማራች እንዳለው ለመግለጽ አያስደፍርም፡፡ አብመድ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ስለቆጠራው የሰጡት አስተያዬት በቂ ግንዛቤ ላለመፈጠሩ ማሳያ ናቸው፡፡ ከአነጋገርናቸው ውስጥ አቶ ይታየው በዓለም እና ወይዘሮ ይታጠቁ ጥላሁን ስለሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ‹‹መንግሥት የሚያመጣው ማንኛውም ነገር አይጎዳንም፤ ሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ግን ለማን ለምን እንደሚጠቅም ብዙም ዕውቀቱ የለንም›› ብለዋል፡፡ የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ በአግባቡ ካልተካሄደ ደግሞ በአርሶ አደሮች አካባቢ ማዳበሪያ ለማዳረስ፣ የጤና ተቋማትን ለመሥራት፣ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲደርሱ ድጋፍ ለማድረግ እና በጀት ለመመደብ አስቸጋሪ እንደሚሆን የሥነሕዝብ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ለአርሶ አደሮች ተገቢ የሆነ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ተሰርቶ የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ በአግባቡ እንዲመራ ከዞኖች ጀምሮ እስከ ወረዳ አስታዳደር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤቶች ሥራውን በአግባቡ እንዲያስኬዱ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው እየሠሩ ነው፡፡ አርሶ አደሮች በየአደረጃጀት እና በየእምነት ተቋማት ግንዛቤ እንዲፈጠር ሥራ እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የሚዲያ ይዘት ማበልፀግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተረ አቶ ጋርዳቸው አንሙት ናቸው፡፡ አቶ ጋርዳቸው እንደገለጹት በክልል ደረጃ ግንዛቤ ለመፍጠር ተልዕኮ ከተሰጣቸው የዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጋር በየቀኑ በሪፖርት እየተገናኙ ነው፡፡ ከወረዳዎች ጋር ግን ክልሉ በቀጥታ ስማይገናኝ ኃላፊነቱን ዞን መስጠቱንም አስታውቀዋል፡፡ ‹‹በሥራው ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን እየለየን፣ እየገመገምን እናርማለን›› ብለዋል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ በአግባቡ እንዲካሄድ ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላትም ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ ሥራዎችን እንዲሠሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
48
የ3ኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት እንዲሰረዝ አብን ጠየቀ። ባሕር ዳር፡ መጋቢት 102011ዓም አብመድ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን በ1999 ዓም የተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት እንዲሰረዝ ጠይቋል። ንቅናቄው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በቆጠራው የተሳተፉ ባለሙያዎችና ባለስልጣናት ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸውም አቋሙን አሳውቋል። በቆጠራው ለተፈጠረው ስህተትም መንግስት ካሳ መክፈል እንዳለበት ነው አብን የጠየቀው። በአዲስ አበባ እና አካባቢው ስለታማ ነገሮችን በመያዝ ከህግ አግባብ ውጭ እተንቀሳቀሱ እና ህዝብን እያሸበሩ ባሉ አካላት ላይ የኦሮሞ ፖለቲካ ኃይሎች ዝምታ ተገቢ አለመሆኑንም አብን በመግለጫው አስታውቋል። የንቅናቄው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መልካሙ ሹምዬ እና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በሰጡት መግለጫ መንግስት የህግ የበላይነትን ማስከበር ባለመቻሉ የዜጎች ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተጣሰ ለእንግልትና ለስደት እየተዳረጉ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች በፍትሃዊነት ያሳተፈ እና ተጠቃሚ ያደረገ ባለመሆኑ እንዲቀየር አብን ጥረት እንደሚያደረግም አስታውቀዋል። ፍትህ እንዲሰፍን እና የዜጎችን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች መንግስት እልባት እንዲሰጣቸው አብን ጠይቋል፡፡ ንቅናቄው በ1999 ዓም በተካሄደው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ በተፈፀመው ጥፋት ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈል፤ ቆጠራውም እንዲሰረዝ እና ጥፋተኞች በህግ እንዲጠየቁ መንግስትን ጠይቋል፡፡ ላልተወሰነ ጊዜ በተራዘመው 4ኛው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ተዓማኒነት የተሞላባቸው አሰራሮች እንዲካሄዱ እና ከአሁን በፊት የተፈፀሙ ስህተቶች እንዳይደገሙ ትግል እንደሚያደርግ ንቅናቄው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
49
የሕዝብና ቤት ቆጠራ መራዘም ጉዳይ የፌደራል መንግሥት ከኦሮሞ ኤሊቶችና ኦነግ ውጭ በሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ለአንዳቸውም መልስ ሲሰጡ አይታይም፤ ይህ አንድም ንቀት አሊያም ምን ታመጣላችሁ ነው፡፡ በንቀት እየተሔደበት ያለው አንደኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራው ነው፡፡ አጀንዳ በአጀንዳ ላይ እየደራረቡ የሕዝብና ቤት ቆጠራው የሚጀመርበት ቀን ላይ መድረስን ነው እንደመፍትሔ ያደረጉት፡፡ ይህ አካሔድ አደገኛ እንደሆነ እንዲረዱን እንፈልጋለን፡፡ ምናልባትም በጅምር የቀረው አቢዮት መጨረሻ ሊሆን ይችላል፡፡ በትንሹ ሊቆጥሩ የሚመጡ ባለሙያዎች በአካባቢያችን ዝር እንዳይሉ ማድረግ ቀላል ነው፡፡ ስምምነት የሌለበት ፕሮጀክት ሁሌም አይሳካም፡፡ በአጪሩ በአማራው አካባቢ በዚህ ዓመት የቤት ቆጠራ የለም፤ ቤት እቆጥራለሁ ብሎ የሚመጣ ባለሙያ ሪስክ እንዳይወስድ እንመክራለን፡፡ ሚሊዮን ዜጎች ማደሪያቸው ጎዳና ሆኖ ሚሊዮን ቤቶች ፈርሰው የሚቆጠረው የትኛው ነው የተቃጠለ ባድማ ይቆጠራል በቡልዶዘር የፈረሰ ቤት ይቆጠራል በጫካ መድረሻ ያጡ መጻጉ ዜጎችን የት አግኝተን ነው የምንቆጥራቸው በመጀመሪያ የተረጋጋ ሰላም ይፈጠር ቅድሚያ ለዜጎች መኖር ዋስትና እንስጣቸው ከዚያ ቤትና ሕዝብ ቆጠራ አሊያም ምርጫ ይምጣ
50
ባለፋት ሶስት ጊዚያት በኢትዮጵያ በተካሄዱት የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች የተሰሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አሳሰበ፡፡ ባሕር ዳር፡ የካቲት 082011 ዓምአብመድ ባለፋት ሶስት ጊዚያት የተካሄዱትን የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች መነሻ በማድረግ ቀጣይ በሚካሔደው ቆጠራ ስጋቶች እና መደረግ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ በአዲስ አበባ ውይይት እያካሄደ ነው። ባለፋት የቆጠራ ጊዚያት የተሠሩት ስህተቶች መጋቢት 29 2011 ዓም በሚካሄደው 4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤቶች ቆጠራ እንዳይደገሙ ሁሉም የአማራ ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍ ንቅናቄው ጠይቋል፡፡ በተለይም ምሁራን ህዝቡን በማንቃት እና ቆጠራው በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ነው ንቅናቄው የጠየቀው፡፡ የአብን ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ‹‹ባለፋት ቆጠራዎች የአማራ ህዝብ ቁጥር ‹‹ሆን ተብሎ›› እንዲቀንስ ተደርጓል፤ በዚህም ክልሉ በብዙ ዘርፎች ተጎድቷል›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ የሚካሔደውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤታማ በማድረግ የክልሉ ህዝብ ማግኘት ያለበትን ማህበራዊ እና ኢኮኖማያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥነ ህዝብ እና ዲሞግራፊ መምህር ዶክተር ሲሳይ ምስጋናው በኢትዮጵያ ባለፉት ጊዚያት የተካሄዱት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራዎች ችግሮችና የ2011 ዓም ቆጠራ ስጋቶችን መሠረት የደረገ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጥናታዊ ጽሁፋቸው እንዳመላከቱትም ባለፋት ቆጠራዎች የአማራ ክልል ህዘብ ቁጥር በ1987 ዓም ከነበረው በ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቀንሷል፡፡ በሶስቱ ቆጠራዎች ደግሞ 6 ሚሊዮን የሚሆን የአማራ ክልል ህዝብ አለመቆጠሩን ተናግረዋል። የህግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት በበኩላቸው ‹‹የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ህግ ማዕቀፍ›› በሚል ርዕስ የሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮዎች እያጣቀሡ አቅርበዋል፡፡ በጽሁፋቸውም ቆጠራውን ያካሔደው ተቋም ገለልተኛ እና ነጻ አለመሆን ከአሁን በፊት በተካሔዱት ቆጠራዎች ለተፈጠሩት ስህተቶች ምክንያት ነበር ብለዋል፡፡ አደረጃጀቱ አለመቀየሩም ለአሁኑ ቆጠራ ስጋት እንደሚሆን ነው ያቀረቡት፡፡
51
የቆጠራ ካርታ ባልተዘጋጀላቸው አካባቢዎች የህዝብ እና ቤት ቆጠራው በልዩ ሁኔታ ይካሄዳል On Feb 25 2019 810 አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2011 ኤፍ ቢ ሲ የቆጠራ ካርታ ባልተዘጋጀላቸው የተወሰኑ አካባቢዎች የህዝብ እና ቤት ቆጠራው በልዩ ሁኔታ እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ባለፈው አመት መካሄድ የነበረበት 4ኛው ብሄራዊ የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ መጋቢት 29 ቀን ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው። ለቆጠራው የሚያስፈልጉ የግብዓት ስርጭት እና የቆጠራ ተቆጣጣሪዎች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ስልጠናም እየተካሄደ ይገኛል። ይሁን እንጅ ከቆጠራው አስቀድሞ የቆጠራ ካርታ ያልተሰራላቸው ቦታዎች እንዴት ሊቆጠሩ ነው በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ከቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌና ሃረሪ ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተወያዩበት ወቅት ጥያቄዎች ተነስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በምላሻቸው የህዝብና ቤት ቆጠራው ዋነኛ አላማ ትክክለኛ የኢትዮጵያን ህዝብ ቁጥር ማወቅ መሆኑን ጠቅሰው፥ ብዙ ቁጥር ለመያዝ የሚደረግ ሽሚያ ካለ መቆም እንዳለበት ተናግረዋል። የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በበኩሉ በክልሎች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች መካከል የቦታ ይገባኛል ጥያቄዎች ሲነሱ መቆየታቸውን ይገልጻል። ለቆጠራው በመላ ሀገሪቱ ከ152 ሺህ በላይ ካርታ ሲዘጋጅም በእነዚህ አካባቢዎች ጥንቃቄ ተደርጓል ነው ያለው። ካርታው ከተዘጋጀ በኋላም የይገባኛል ጥያቄ ተነስቶባቸው ጉዳዩ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ባለፉት ሁለት አመታት ጥረት ተደርጎ ስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸው ጥቂት አካባቢዎች መኖራቸውን በኤጀንሲው የካርቶግራፊ እና ጂ አይ ኤስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ጉታ ይናገራሉ። ከኤርትራ ጋር ቀደም ብሎ በነበረው ችግር ሳቢያም 16 የአፋር ክልል ቀበሌዎች እንዲሁም ሞያሌ ከተማ የቆጠራ ካርታ አለመዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል። የቆጠራ ካርታዎቹ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍና በእግር በመንቀሳቀስ የተዘጋጁ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም ቆጠራው በሚካሄድባቸው ታብሌቶች ላይ እየተጫኑ ይገኛሉ። ካርታ ያልተዘጋጀላቸው አካባቢዎች ላይም ኤጀንሲው በሚከተለው ልዩ የቆጠራ ዘዴ መሰረት ቆጠራው ይካሄዳል ነው ያሉት። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙም በ4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ የማይቆጠር ሰው እና ቤት አለመኖሩን ጠቅሰው፥ የቆጠራ ካርታ ባልተዘጋጀላቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች እና ቤቶች በልዩ ሁኔታ ይቆጠራሉ ብለዋል። የአፋር ክልል 16 ቀበሌዎች የቆጠራ ካርታ ባይዘጋጅላቸውም ከሌላ ወገን የሚነሳ ቅሬታ ስለሌለባቸው ቆጠራው ሲሰራ ለአፋር የሚደመር ይሆናል። የሞያሌው ግን በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች መካከል ስምምነት እስካልተደረሰ ድረስ ቆጠራው ሲከናወን ለሁለቱም ክልሎች ሳይደመር ቁጥሩ በብሄራዊ ደረጃ እንደ ግብዓት ይውላል ተብሏል። ኤጀንሲው የይገባኛል ጥያቄዎችን የመመለስ ስልጣን እንደሌለውና ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ጭምር ቆጠራው እንደሚካሄድ ጠቅሶ፥ ጥያቄው ምላሽ ሲያገኝ የቆጠራው ውጤት ወደተወሰነለት አካል ይደመራል ብሏል። 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ያለምንም ሳንካ እንዲካሄድም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራውና የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች የሚሳተፉበት የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን በበላይነት እያስተባበረ ይገኛል።
52
አዲስ አበባ መጋቢት 62011 በተያዘው ወር መጨረሻ የሚጀመረው 4ኛው ዙር አገር አቀፍ ሕዝብና ቤት ቆጠራ ዝግጅት መጠናቀቁን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት አበራሽ ታሪኩ ከሌሎች የኤጀንሲው የስራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም በይፋ የሚጀመረው 4ኛው ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ የካርታ ስራ፣ የመረጃ ቋት ማሳደግ፣ የሰው ኃይል ማሟላት፣ ሎጂስቲክስና ስልጠና ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። ”ለ1 ሺህ 600 የአሰልጣኝ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው፤ ከየካቲት 26 ጀምሮ እስከ መጋቢት 8 የሚቆይ የቆጣሪና ተቆጣጣሪ ስልጠናዎች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 25 ቅርንጫፎች ለ8 ሺህ 600 ባለሙያዎች በመሰጠት ላይ ነው” ብለዋል። በቆጠራው በአጠቃላይ 180 ሺህ የሰው ሃይል እንደሚሰማራ ገልጸው፤ የዘንድሮ ቆጠራ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሶስት ቆጠራዎች በተለየ የመረጃ አሰባሰብ በዲጅታል ወይም በታብሌት ኮምፒተሮች እንደሚደረግ ተናግረዋል። ለቆጠራው የተመለመሉ ሰዎች መምህራን፣ የጤናና የግብርና ባለሙያዎች ሲሆኑ አካላዊ ብቃት፣ ስነ ምግባርና ሌሎች መስፈርቶች እንዳሉበት ጠቁመዋል። ለመረጃ ስብሰባ ከሚሰራጩ 180 ሺህ ታብሌቶች መካከል 90 በመቶዎቹ የመረጃ መሰብሰቢያ መተግበሪያ እንደተጫነላቸው ገልጸው፤ ቀሪዎቹም በጥቂት ቀናት ውስጥ ሶፍትዌሩ ተጭኖላችው እንደሚሰራጩ ገልጸዋል። የቆጠራ መረጃዎችን የያዙት መተግበሪያዎች በኤጀንሲው ከፍተኛ የአይሲቲ ባለሙያዎች የተዘጋጁና በልዩ ልዩ መረጃ መሰብሰቢያ ሲያገለገሉ የቆዩ ቢሆንም ከአሁኑ ቆጠራ ግዙፍነት አንጻር ከአሜሪካ የቆጠራ ቢሮ የባለሙያ ድጋፍ መገኘቱን ጠቁመዋል። በሶፍትዌር ዝግጅቱ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኢንሳ እንዳለበት የሚገለፀው ጉዳይ ከእውነት የራቀ መሆኑን ገልጸው፤ ኢንሳ በመረጃው ቋት ደህንነት ጥበቃ እንጂ በሌሎች ቴክኒካል ጉዳዮች ኃላፊነት እንደሌለው አብራርተዋል። ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ለቆጠራ ስራ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት እንደነበረው የገለጹት ወይዘሪት አበራሽ፤ አሁን ላይ ለሚደረጉ ስራዎች በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በኩል 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለክልሎች መከፋፈሉን ገልጸዋል። በወቅቱ ግምት ውስጥ ያልገቡ ስራዎችን ለማከናወን ደግሞ ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን በማመልከት በጀቱ በቅርብ እንደሚለቀቅ እምነታችውን ገልጸዋል። የሚሰበሰበውን መረጃ ተዓማኒነት በተመለከተም ከፌዴራል እስከ ወረዳ የራሱ የቆጣሪ ተቆጣጣሪዎች እንዳሉት በመጠቆም፣ መረጃው ከተሰበሰበ በኋላ ቆጣሪው የሞላውን መረጃ ከታብሌት ኮምፒተሮች የሚያሳይበትና ከተቆጣሪ ጋር የሚፈራረምበት ወረቀት መዘጋጀቱን አመልክተዋል። ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበርም የተሰበሰበው መረጃ ከተቆጠረበት ታብሌት በቀጥታ ወደ ማዕከል የመረጃ ቋት የሚገባበት ስርዓት ተዘጋጅቷል። በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ባለው አለመረጋጋትና የዜጎች መፈናቀል ባለበት ስፍራ ቆጠራውን ለማካሄድ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። የተፈናቀሉ ዜጎች ወደነበሩበት ቦታ ከተመለሱ በቋሚ መኖሪያቸው፣ ካልተመለሱም ባሉበት አካባቢ ስለመፈናቀላችው የሚያሳይ አስፈላጊው መረጃ ተሞልቶ በተጠለሉበት ስፍራ እንደሚቆጠሩ አመልክተዋል። ብሔርና ሃይማኖትን በተመለከተም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ማንኛውም ብሄር ብሔረሰብ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት በተወስደ ዝርዝር መሰረት በተሰጣቸው ኮድ እንደሚቆጠሩ ተናግረዋል። ”ተቆጣሪው ከሁለት ብሄር በመወለድም ሆነ በሌላ ምክንያት ‘ብሔሩን’ ለመመለስ ከተቸገረ ዘር፣ ትውልድ፣ ነገድና ጎሳውን በማብራራት በተቀመጡ ኮዶች እንዲካተት ይደረጋል” ብለዋል። የጥያቄው ዓላማ የብሄር ስብጥር መረጃ ለመሰብሰብ በመሆኑና ‘ኢትዮጵያዊ’ የሚለው የዜግነትን እንጂ የብሔር ማንነት ስለማይገልጽ ‘ኢትዮጵያዊ’ በሚል የቆጠራ ኮድ አልተዘጋጀም ብለዋል። ኃይማኖትን በተመለከተም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኃይማኖቶች ተለይተው ኮድ መሰጠቱን፤ ከ18 ዓመት በታች ከሆኑት በስተቀር የቤተሰቡ አባላት ግላዊ ሃይማኖታቸውን በማሳወቅ እንዲሞላ ለቆጣሪዎች ስልጠና መሰጠቱን ተመልክቷል። 4ኛው ዙር ቆጠራ ከመጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ለ20 ቀናት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። በቆጠራው የሚገኘውን ውጤት፣ ሌሎች የመረጃ ግብዓቶችን በመጠቀም የሕዝብ ብዛት ትንበያ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።
53
4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ የብሄራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽን አራተኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታወቀ። የህዝብና ቤት ቆጠራውን አስመልክቶ በዛሬው እለት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ መግለጫ ተሰጥተዋል። ኮሚሽነሯ በመግለጫቸውም መጋቢት 29 ቀን 2011 የሚጀመረውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ግልጽና ተዓማኒ በሆነ መልኩ ለማካሄድ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል። እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅሬታዎች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ነው ዶክተር ፍጹም የገለፁት። የህዝብና ቤት ቆጠራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ ሲሆን፥ አዳዲስ አሰራሮች ተግባራዊ ይደረጉበታልም ነው የተባለው። በዚህም በርካታ ታብሌቶች፣ ጂፒኤስና ሌሎች መሰል ግብዓቶች መዘጋጀታቸውም ተገልጿል። የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በበኩላቸው፥ ቆጠራውን ለማካሄድ ከዚህ በፊት ወረቀት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ሲሆን፥ አሁን ላይ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድ አሰራሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል መቀየሩን ተናግረዋል። በቆጠራ ሂደት ችግሮች ቢከሰቱ እንኳን ቶሎ ለማስተካከል የሚያስችል የበይነ መረብ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ የሚደርግ ሲሆን፥ ቆጠራው በትክክል ስለመካሄዱም ማረጋጋጫ የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን አስገንዝበዋል። በቋንቋ አጠቃቅም ዙሪያ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍም መጠይቆች በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አፋርኛ፣ ሶማሌኛና ትግርኛ መዘጋጀታቸውን ነው ያስረዱት። ቆጠራው የአርብቶ አደር አካባቢዎችን ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ወቅት እንደሚከናወን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በተመሳሳይ ጊዜ ቆጠራው መካሄዱ ከዚህ ቀደም የታዩ ስህተቶችን ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል። ቆጠራውን የሚከታተል የሂሳብ ባለሙያዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የተካተቱበት አማካሪ ምክር ቤት መቋቋሙም ነው የተገለጸው። ባለፉት ጊዜያት ሶስት የህዝብና ቤት ቆጠራዎች መካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን፥ ሶስተኛው ቆጠራ በርካታ ቅሬታዎች የተነሱበት ነበርም ተብሏል። የፊታችን መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም ለመጀመር የታቀደው የህዝብና ቤት ቆጠራ ፕሮግራም በ2010 ዓም ሊካሄድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፥ በሀገሪቱ በተከሰቱ አለመረጋጋቶችና ጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ መራዘሙ ይታወሳል።
54
አዲስ አበባ መጋቢት 102011 በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወገኖች ወደ ነበሩበት ቀዬ የመመለሱ ስራ በበቂ ሁኔታ ባለመሰራቱ 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ እንዲራዘም የዉሳኔ ሀሳብ ቀረበ። የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ባካሄደው ስብሰባ አራተኛዉን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሄድ የተደረገዉን ዝግጅት በመገምገም የውሳኔ ሃሳቦች አሳልፏል። በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ትርጉም ባለው ደረጃ ወደ ነበሩበት ቦታ እስኪመለሱ ድረስ ቆጠራውን ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳቡ ቀርቧል። የውሳኔ ሃሳቡን ኮሚሽኑ ለተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች እንዲቀርብ በአብላጫ ድምፅ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ ያሳያል። የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል። • የሕዝብና ቤት ቆጠራው እንዲቀጥል በቴክኒክ ደረጃ በቂ ዝጅግት የተደረገ መሆኑንና ኮሚሽኑና ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሰፊ ስራ የሰሩ መሆኑን፣ • የካርታ እና ተያያዥ ስራዎች እየተገባደዱ መሆኑን፣ • ሌሎች ዝግጅቶችም እየተደረጉ መሆኑን ግንዛቤ ወስዶ የቆጠራውን አላማና ግብ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችሉ ተግባራት የተሟሉ ባለመሆናቸው ማለትም በየአካባቢው ለስራው መሳካት በተገቢው ሁኔታ መጠናቀቅ የሚገባቸው ተግባራት ባለመጠናቀቃቸው እና ተጨማሪ ግዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ • ምንም እንኳን ለቆጠራ የቀሩን ቀናት ጥቂት ቢሆንም በተለያዩ ገጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወገኖች ወደ ነበሩበት ቀዬ የመመለሱ ስራ በበቂ ሁኔታ ባለመሰራቱ አሁንም በርካታ ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህ ወገኖች ትርጉም ባለው ደረጃ ወደ ነበሩበት ቦታ እስኪመለሱ ድረስ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ ቆጠራው እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳቡን ለተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች እንዲቀርብ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።
55
አዲስ አበባ ሰኔ 32011 የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የሕዝብና ቤት ቆጠራ መራዘምን አስመልክቶ በቀረቡ የተለያዩ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ክርክር በማድረግ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ወስነዋል። የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ ባደረጉት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ የጋራ ስብሰባ የ2011 ዓም የሕዝብና ቤት ቆጠራ ይራዘም እና አይራዘም በሚሉት ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። የምክር ቤቶቹ አባላት ቆጠራው ይራዘም፣ አይራዘም፣ የሚራዘምበት የጊዜ ገደብ ላልተወሰነ ጊዜ ይባልና ለስድስት ወር ተብሎ ገደብ ይበጅለት የሚሉ የመከራከሪያ ሃሳቦችን አንስተዋል። አገሪቱ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ቆጠራውን ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ የለም ያሉት አብዛኞቹ አባላት ናቸው። በአገሪቱ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያቶች በርካታ ዜጎች በተፈናቀሉበትና የጸጥታ ስጋት እየተፈጠረ ባለበት ሁኔታ ቆጠራውን ማካሄድ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ስለማያስችል መራዘም አለበት፤ ለቆጠራው የተመረጠው ጊዜ አርሶ አደሩ በእርሻ ስራ ሳቢያ ቤቱ የማይገኝበት፣ተፈናቃዮች ከቀዬአቸው የሌሉበት እንዲሁም ዜጎች በስነ ልቦናና ሞራል ያልተረጋጉበት በመሆኑ መካሄዱ የሚፈለገውን መረጃ ለማግኘት ያዳግታል ነው ያሉት። በሌላ በኩል ቆጠራው መራዘሙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ ከማሳደሩ ባለፈ ግዙፍ አገራዊ አጀንዳዎችን ለማከናወን እንቅፋት ስለሚፈጥር መራዘም የለበትም ያሉም ነበሩ። መንግስት ቆጣራውን ለማካሄድ በቂ ዝግጅት ያደረገና በርካታ ወጪ ያወጣ በመሆኑ ቆጠራው ቢራዘም ኢኮኖሚው ይጎዳል በማለት የመከራከሪያ ሃሳብ አቅርበዋል። እነዚህ አባላት በችግር ውስጥ ሆኖ ቆጠራውን ማካሄድ አገሪቱ በቀጣይ ለምታካሂደው አገራዊ አጀንዳና ምርጫ ጠቀሜታ ይኖረዋል ባይ ናቸው። ቆጠራው ይራዘም የሚለውን ሃሳብ የደገፉት ደግሞ አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ የጊዜ ገደብ አስቀምጦ በዚህ ቀን ይካሄድ ለማለት አስቻይ ሁኔታ ስለሌለ ላልተወሰነ ጊዜ ይራዘም ሲሉ፣ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ሃላፊነት ተሰጥቶት የጊዜ ገደቡን ያስቀምጥ ያሉም ነበሩ። ቆጠራው ከሚሰጠው አገራዊ ጠቀሜታ አንጻር ጊዜ መስጠት ግድ ይሆናል ነው ያሉት። አገሪቱ በለውጥ ጉዞ ላይ እንደመሆኗ ሰላምን ለማረጋገጥና የህዝቡን ስነ ልቦና መረጋጋት የማምጣቱ ስራ ሊተኮርበትና ጊዜ ሊሰጠው ስለሚገባ ላልተወሰነ ጊዜ የሚለው ሃሰብ እንዲጸናም ጠይቀዋል። ቆጠራውን ለአንድ ዓመት ማራዘም ይበዛል ያሉት ደግሞ አሁን ያለው ተስፋ ሰጪ ሰላም በቅርብ ጊዜ ይረጋገጣል፤ የተጀመረው ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ አመላካች ሁኔታዎች ስላሉም ስድስት ወር በቂ ነው ሲሉ ተከራክረዋል። የቆጠራውን መራዘም ምክር ቤቱ ማጽደቅ ያለበት አሁን አይደለም፤ ለመራዘሙም የሚመለከታቸው አካላት የአገርን ሰላም የማስጠበቅ ሚናቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ነው የሚል አስተያየትም ተሰንዝሯል። የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለቀረቡ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ምላሽ ሲሰጡ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለአገር የሚኖረውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ሰፊ መሆኑን አውስተዋል። የልማት እቅዶች፣ ፕሮግራሞችና ፖሊሲዎች ለመንደፍና ሀብትን በፍትሃዊነት መድቦ ለማስተዳዳር የቆጠራው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በመጥቀስ። ያም ሆኖ አሁን በአገሪቱ ቆጠራውን ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታዎች ባለመኖራቸው በተረጋጋና ምቹ አካባቢያዊ ሁኔታ እንዲሁም ጊዜ ማካሄድ ‘አማራጭ የሌለው ነው’ ብለዋል። የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን በ2011 የሚካሄደው ቆጠራ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን አሳውቆ ለፌዴራል ምክር ቤቶች የአንድ ዓመት የማራዘሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል። በመጨረሻም ምክር ቤቶቹ ቆጠራው ለአንድ ዓመት ይራዘም የሚለውን የውሳኔ ሃሳብ በ30 ተቃውሞና በሶስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቀውታል። ምክር ቤቶቹ ከጋራ ስብሰባቸው ቀደም ብሎ በተናጠል ባካሄዱት ውይይትም የህዝብና ቤት ቆጠራው እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፈው ነበር። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህዝብና ቤት ቆጠራው ይራዘም የሚለውን የውሳኔ ሃሳብ በ8 ተቃውሞና በአራት ድምፀ ተአቅቦ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደግሞ በ24 ተቃውሞና በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነበር ያሳለፉት።
End of preview. Expand in Data Studio
README.md exists but content is empty.
Downloads last month
3